አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD)

በመጨረሻም ተስማማች፣ እኔ ጋር
አደረች፡፡ በተከፈተልኝ በር ወስኜ መግባት እንዳልከበደኝ፣ አለባበሷና የወይኑ ስሜት ተደማምሮ፣ በድንገት ሰተት ብዬ ገባሁ፡፡ የመጀመሪያ ቀን አይቻት ስደነግጥ እንዲህ በቀላሉ ማገኛት፣ እኔ ላይ እንዲህ ፍላጎት አሳይታ እሺ ምትላኝ አልመሰለኝም ነበር፡፡ በጥዋት ወደ ቤት ሳደርሳት እንደዚህ ያለ ነገር ውስጥ፣ ስራ ቦታዬ ላለመግባት ወስኜ እንደነበር፣
ነገር ግን፣ የእርሷ ውበት ከምቆጣጠረው በላይ እንደሆነብኝና የሆነው ድንገት እንደሆነ ነገርኳት፡፡ ስራችን ላይ ተፅዕኖ እንዳይኖር፣ ሰው እንዳያውቅ ጠየኳት፣፥ ግቢ ውስጥ እንድንጠነቀቅ አሳሰብኳት፡፡ እርሷም እንደዛ እንደማትፈልግና እንደምትጠነቀቅ አረጋገጠችልኝ፡፡
ህይወት ቀና ሆነችልኝ፡፡ በጣም ደስተኛ ሆንኩ፡፡ ስራዎችን በሚገባ አቅዳለሁ! አፈፃፀማቸውን እከታተላለሁ! ለአለቃዬ ሁሉንም በግዜው ሪፖርት አደርጋለሁ፡፡ ሁሉም በስራዬ ደስተኛ ሆኑ፡፡ በተለይ
አለቃዬ ያበረታቱኛል። በውስጤ ብዙ እምቅ አቅም እንዳለ ይነግሩኛል፡፡
ስለ ስራ ልምዳቸው፣ ከፍተኛ ትምህርት ውጪ ሃገር ሄደው ስለመከታተላቸው፣ እኔም እንደዚህ ጠንክሬ ከሰራሁ ትልቅ ደረጃ እንደምደርስ በተገናኘን ቁጥር ይነግሩኛል፡፡ ብዙ ስራተኛ ይፈራቸዋል፡፡
ቁጡና ሃይለኛ ናቸው ይላሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ድርጅቱ የዘመዳቸው ስለሆነ፣ ፈላጭ ቆራጭ ናቸው ይላሉ፡፡ በዚህም፣ ሰራተኛው እንዳሻው ብሎ የቅፅል ስም አውጥቶላቸዋል፡፡ እኔ ግን ነገሮችን በፍጥነት የመረዳት አቅማቸው፣ ልምዳቸውን ለማካፈልና ሰውን ለማሳደግ ያላቸው ቀናነትን ስመለከት እያደር በጣም እንዳደንቃቸው አድርገውኛል፡፡

ዛሬ ቅዳሜ ነው፡፡ ቅዳሜ ብዙ ስራ የለም፡፡ ስራተኞች እንደገቡ ካረጋገጥኩና ምርት በሚጠበቀው እየተመረተ እንደሆነ ካየሁ በኋላ፣ሰዓት እስኪደርስልኝ በየቢሮው እየተንቀሳቀስኩ ምልከታ አደርጋለሁ፡፡
ጨርሼ ቢሮዬ እንደተቀመጥኩ፣ ማሂ እንደተለመደው መጥታ ሸኘኝ አለችኝ፡፡ ለመውጣት እየተዘጋጀን፣ ሳሚ በሩን ከፍቶ ገባ፡፡ ሳሚ የሂሳብ ክፍል ሃላፊ ነው፡፡ ረጅምና ግዙፍ ተክለ ሰውነት ያለው ሲሆን፣ በባህሪው ሳቂታና ብቻውን መሆን ሚከብደው አይነት ሰው፡፡ ሰላምታ
ከተለዋወጥን በኋላ፣

“ዛሬ ትልቅ ደስታ አለኝ፡፡ ምን እንደሆነ አልናገርም፡፡ ግን የደስደ

ሱን ልጋብዛችሁ ፍቃደኛ ነኝ፡፡ ፈቃደኛ ናችሁ?” ፈገግ ብሎ
ቁልቁል እየተመለከተ ጠየቀን፡፡

ተገኝቶ ነው?፣ ያውም በደስታ ነዋ!” አልኩት፡፡

በሉ እንውጣ!”

“እንዴ ቆይ እኔንም ጠብቁኛ፣ ቢሮ ዘግቼ ልምጣ?” ማሂ መልስ ሳትጠብቅ ወጥታ ሄደች፡፡ ቢሮ ቆልፈን፣ ማሂን ለመጠበቅ ቀስ ብለን እየተራመድን፣ ከነጩ
ህንፃ በር ላይ. ግርማና ቤቲ ቆመው አየናቸው፡፡ ቤቲ ሂሳብ ክፍል ምትሰራ የግቢያችን አንዷ ቆንጆ ነች፡፡ ለሴት ረጅም የሚባል ቁመና ያላት፣ ቀይ፣ ተግባቢና ደፋር ልጅ ናት፡፡ ትውልዷም እድገቷም አዳማ ነው፡፡ አሁንም ከቤተሰቧ ጋር ትኖራለች፡፡ ጥርሷ እንዳብዛኛው ያገሩ ሰው፣ የበዛ ባይሆንም፣ ለፈገግታዋ ውበት የሆነ ትንሽ ብልዝ አለባት፡፡በግሩፓችን፣ ወርቃማው ፈገግታ ጎልደን ስማይል እንላታለን፡፡ ማታ ላይ በስልክ አልፎ አልፎ አወራታለሁ፡፡ መስሪያ ቤት ግን ከስራ ውጪ ብዙም አላዋራትም፡፡ እርሷ ግን፣ ስትፈልግ ቢሮዬ ድረስ ሰተት ብላ
ትመጣለች፡፡ ከሳሚ ጋር አንድ ቢሮ ናቸው፡፡ ክፍላቸው ብዙ ሰራተኛ
ስላለና ስለማይመቸው፣ እኔ ቢሮ ሲያገኛት እወድሻለሁ፣ ካልሳምኩሽ
እያለ ይላፋታል፡፡ ከስራ በኋላ ካልጋበዝኩሽ ብሎ ደጋግሞ ሲጠይቃትም ሰምቻለሁ፡፡ እሺ አትለውም፡፡ እኔ ደግሞ፣ እንከኗ ይሄ ነው ባልልም፣ ስምጥ ብላ አልገባችልኝም፡፡ የሆነ ሚጎረብጥ ነገር እንዳላት ይሰማኛል፡፡ ዛሬ ቤቲ አብራን ከወጣች የሳሚ የደስ ደስ እርሷ ናት፤ ብዬ አሰብኩ፡፡
“እንውጣ፣ ኮተት እንዳይበዛ፡፡” አለ ሳሚ ወደ መኪናዋ እየሄደ የመኪናውን የሪሞት ቁልፍ ተጭኖት፡ የግቢው መኪና ማቆሚያ ውስጥ ተደርድረው ከቆሙት መኪኖች ጥቁሯ ቪታራ፣ ዋይ ዋይ ማለት
ጅመረች፡፡

“አንድ ሰው ካንተ ጋር ይሁና?” አለኝ ሳሚ፣ የከፈተውን የጋቢናውን በር ተደግፎ፡፡

“እሺ!”

ወዲያው ማሂ መጥታ መኪናዬ ውስጥ ገባች፡፡ የተለመደው ስጋ ቤት ስደርስ፣ ሳሚ እያቆመ ነው፡፡ አጠገቡ ሄጄ አቆምኩ፡፡ ስጋ ቤቱ እንደተለመደው ደርቷል፡፡ ባለቤቱ ገና እንዳየን ሚያብለጨልጭ መላጣውን እያሻሽ ወደ ጓሮ ይዞን ገባ፡፡

“ማነህ፣ ና እስቲ! እዚህ ጋር ሁለት ወንበር ጨምርላቸው፡፡”ጮኸ፡፡ ሳሚ ለቤቲ ከጎኑ ወንበር አስተካክሎ፣ ጎንበስ ብሎ እንድትቀመጥ ጋበዛት፡፡ ተቀመጠች፡፡ ግርማ ከቤቲ ጎን ተቀመጠ፡፡ ማሂ ቀጠለች፣ እኔ ክቡን ለመሙላት በማሂና በሳሚ መሃከል ወንበር አስተካክዬ
ተቀመጥኩ፡፡

“ጠፍታችኋል፣ በሰላም ነው?” ባለቤቱ የግሩፑን መሪ ሳሚን ጠየቀው፡፡ ሳሚ ጭር ሲል ማይወድ፣ ነገር ቶሎ ሚረብሽውና ነገርን እንደጦር ሚሸሽ ነው፡፡ ወሬ ሚያቋርጠውን ሰው አይወድም፡፡እንደሚፈልገው ስለምሆንለት፣ ከኔ ጋር መሆን የበለጠ ነፃነት ይሰጠዋል፡፡ ጨዋታ ደምቆ ደስ ካለው ደግሞ፣ ድንገት ተነስቶ ጋባዥ
ነኝ ማለት ይወዳል።

“ምን እንጠፋለን፣ ቅዳሜ መጥተን አልነበር?”
“እሺ ስንት ልዘዝላችሁ? ሁለት
ላድርገው...?”

“አድርገው፡፡”

“የሚጠጣ፣ ያ የተለመደውን?”

“እሺ፡፡ ደግሞ ከረሜላ ላክልን፤ አሪፍ ይሁን ሳሚ የተለመደውን ትዕዛዙን አስከተለ፡፡

ሰውዬው እንደሄደ፣ ጫጫታው
መድረኩን ተረከቡት፡፡ የጀማው ድርሻ የነሱ ሃሳብ ላይ መጨመር፣ አስተያየት መስጠት ወይም መሳቅ ብቻ ነው፡፡ ሚያስቁ ትዝታቸውን፣ ቀልዶችን እያወሩ ይበሻሽቃሉ፤ ያስቁናል፡፡ ከረሜላው ከአዋሽ ተከሽኖ ጋር መጣ፡፡ ጥብሱ ተከተለ፡፡ መጠጡ በፍጥነት ያልቃል፡፡ ከሁለተኛው በኋላ፣ ማን እንደሚያዝ እንኳ አይታወቅም፡፡ ቦታው ሰወር ያለ
በመሆኑ፣ እንደፈለግን ለመንጫጫት ተመችቶናል፡፡ አንዱ ወሬ ሲያልቅ
ሌላ ይቀየራል፡፡ ያኛውስ፣ እንትን” እያሉ ሳሚና ማሂ ይሽቀዳደማሉ።አንዳንዴ አልደማመጥ ሲሉ፣ ማሂ ወደኔ ትዞራለች፡፡ ሳሚ አጠገቡ ላለችው ቤቲ ያወራል። መልሰው በጋራ አንድ ወሬ ይጀምራሉ፡፡ አሁን የቤቲም የግርማም ድምፅ ጎልቶ መሰማት ጀምሯል፡፡

“ሳሚ፣ ሳሚ፣ አንተ...” ማሂ ጮኸች፡፡
“ወይዬ፣ቆንጆ”

ነገ ሶደሬ እንሂድ?”

“ዛሬ ካልደከምን፣ አይተን እንደሙዳችን።”
“እንሂድ በናትህ ... ኪ.ኪ.ኪ...”

“ምንድን ነው? መረጫጨት ነው እንዴ?”

“እንደፈራሁት አይደለም ናፍቆኛል...፡፡ ኪ.ኪ.ኪ...” ማውራት እስኪያቅታት ትስቅ ጀመር፡፡ እሱም አብሯት መንከትከት
ጀመረ።

“እንዴ ንገሩን እና እኛም አብረን እንሳቅ እንጂ..ሃይ!” በመሃል ገባሁ፡፡

“ይኸውልህ ያቡ፣ ባለፈው ከስራ ስንወጣ ሶደሬ ካልሄድን ብሎኝ ሄድን፡፡ ከዛ ካልዋኘሁ ብሎ ተከፍሎ ሚዋኝበት ስንሄድ፣ ስው ሚባል የለም፡፡ እዋኛለሁ ብሎ ገባ፡፡ ከዛ ወዲያው ብቅ ጥልቅ መጫወት አይጀምርም...፡፡ ኪ.ኪ.ኪ..
ደንግጬ እጄን ብሰጠው፣ ብጠራው
ሊሰማኝ ነው...፡፡ ከዛ ኡ...ኡታዬን አስነካሁታ፡፡ ኪ.ኪ.ኪ...ሁላችንም ተከትለናት እንስቃለን፣ እሱም አብሮን ይስቃል...።

“በናትሽ ከዛስ?”

“ከዛማ የሆኑ ሰዎች መጥተው አወጡት፡፡ ኪ.ኪ.ኪ...። አቤት ያስመለሰው ውሃ ብዛቱ... ኪ...ኪ...ኪ... ከመቼው ያን ሁላ ውሃ እንደጠጣ... ኪ.ኪ.ኪ...፣ ደግሞኮ ሲገባ፣ ገንዳው ቆሽሿል ምናምን ሲለኝ፣ ሊጠጣ እንደሚገባ እኔ መች ገባኝ... ኪ.ኪ.ኪ...” ማውራት እሰኪያቅታት ትስቃለች፡፡ ሳሚም ይስቃል፣ እኛም ተከትለን
👍6👏2🔥1
እንስቃለን፡፡ወሬውን ሊያስቀይራት ቢልም፣ አላቆም ስትለው አስተናጋጁን ድንገት፣

“ና እስቲ ሚጠጣ ጨምርልን!” አለው፡፡

“ደግሞኮ፣ በጣም ያሳቀኝ፣ስንመለስ መኪና ውስጥ፣
ኪ......ኪ....ኪ...... እንዴት ነህ?' ስለው፣ “እንደፈራሁት አይደለም አይለኝም... ኪ.ኪ...ኪ...”

ካ..ካ..ካ... ከዛ በላይ፣ ምን ነበር የፈራው...?” እኔም መሃል ገባሁ፡፡

“እንደዛ የተንቀለቀለው፣ ውሃ ጠምቶት ነው ለካ ኪ.ኪ.ኪ. እንደዚህ እየተጫወትን ቤት ሳንቀይር መሸ፡፡ ሰዓቴ ከምሽቱ
ሶስት ሰዓት ይላል፡፡ ሁሉም ሞቅ ያለው ይመስላል፡፡ የሳሚ ግንባሩ ደም ስር ተወጣጥሯል፡፡ ፊቱ ወዝቷል፡፡ እንደዛ አየተሳሳቅን ድንገት ግርማና ቤቲ ይጨቃጨቃሉ። ሳሚ ጨዋታውን አቁሞ ሊያግባባቸው መሃል ገባ፡፡ ነገሩ ጭራሽ ጦዘ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD) በመጨረሻም ተስማማች፣ እኔ ጋር አደረች፡፡ በተከፈተልኝ በር ወስኜ መግባት እንዳልከበደኝ፣ አለባበሷና የወይኑ ስሜት ተደማምሮ፣ በድንገት ሰተት ብዬ ገባሁ፡፡ የመጀመሪያ ቀን አይቻት ስደነግጥ እንዲህ በቀላሉ ማገኛት፣ እኔ ላይ እንዲህ ፍላጎት አሳይታ እሺ ምትላኝ አልመሰለኝም ነበር፡፡ በጥዋት ወደ ቤት ሳደርሳት እንደዚህ ያለ…»
#ሰመመን


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

የፍልስፍናወኑ መምህር ዮናታን እጅጉ የተማሪዎቻቸውን ወረቀት በማረም ላይ ሳሉ አንድ በግዴለሽነት የተሰራ የጥናት ጽሑፍ ገጠማቸው ። ጽሑፉ የአቤል ሙሉዬ መሆኑን ማመን ስላቃታቸው እቢሯቸው ድረስ አስጠርተው ጠየቁት ።

“ እቤል ይህ የጥናት ጽሑፍ ያንተ ነውን ?
አዎ ! የኔ ነው ። ”
“ ስትሰራው ተቻኩለህ ነበር መሰለኝ ? ”

አቤል ስለ ተደናገጠ ዝም አለ። ቶሎ መልስ አልሰጣቸውም ። ዮናታንም ድንጋጤውን ከገጽታን ላይ ስላነበቡ አነጋገራቸውን ለማቅለል ሞከሩ።

“ማለቴ ለዝግጅቱ የሰጠኋችሁ ጊዜ አንሶአችሁም ሊሆን ይችላል ።”

አሁንም አቤል መልስ አልሰጠም ። የይድረስ ይድረስ ሥራ መሥራቱን ልቡ ያውቃል ። ጊዜ አንሶትም አልነበረም ። እንዲያውኑም ከተሰጠው ጊዜ አንድ ሳምንት ቀድም ነው ያስረከበው ።
በመሰረቱ መምህሩ በሰጡት የጊዜ
ገደብ ውስጥ የጥናት ጽሁፍ ተሰርቶ መቅረብ አለበት ።ከዚያ በኋላ የመምህሩ ድርሻ እንደ ሥራው ጥራትና ይዘት ውጤት መስጠት ነው ። አስተዋዩ ዮናታን ግን ፥ በተበላሸው የአቤል ወረቀት ላይ ሳያመዛዝኑ ርምጃ መውሰነድ አልፈለጉም ዐይናቸውን ወረቀት ላይ ተክለው በሐሳባቸው የአቤልን ለውጥ ለማጥናት ተገደዱ ።

በአዲስ አበባው ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል የዓመቱ ተመራቂዎች ሰባት ናቸው ። ከሰባቱ መሐል አንዱ አቤል ሙሉዬ ነው ። መምህር ከማናቸውም ይልቅ በአቤል ላይ ያላቸው እምነት ላቅ ያለ ነው ። የሶስቱን ዓመት
የዩኒቨርስቲ ትምህርት እያጠናቀቀ የመጣው ከፍ ባለ ውጤት ነው።
ከዚህም በላይ በክፍል ውስጥም ሆነ በውጭ በግል የሚያቀርበው ጥልቅ ዲያሎግ በዮናታን ልብ ውስጥ ትልቅ
ቦታ ነበረው ። የዮናታን ምኞት አቤል በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቆ የበለጠ ከፍተኛ ትምህርት እንዲከታተል ነው ።
...ታዲያ ይህ የአፋፍ ላይ እንቅፋት ምን ይሆን ? ” ሲሉ ዮናታን ራሳቸውን ጠየቁ ።

ካቀረቀሩበት ወረቀት ቀና ብለው መነጽራቸውን በጣታቸው ሽቅብ ገፋ እያደረጉ ፡ ለአቤል ድንገተኛ ጥያቄ
አቀረቡለት ።

“ ዕድሜህ ስንት ነው ? ”

“ ሃያ አንድ ። ”

“ ገና ወጣት ነህ ” አሉት የደረሰበትን የትምህርት ደረጃ ከዕድሜው ጋር በማነጻጸር ።

“ በአንደኛና በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ ሦስት ያህል ክፍሎች በእጥፍ ነበር ያለፍኩት፤
ለዚህ ነው በጊዜ ዩኒቨርስቲ የገባሁት ” አላቸው መግረማቸዉን በማየት።

ወላጆችህ በቅርብ ናቸው ? ”

ይህ ድንገተኛ ጥያቄ አቤልን ቢያስደነግጠውም ከጥናት ጽሁፉ ጉዳይ ወጣ ያለ አርዕስት በመሆኑ ወዶታል ። ይሁንና በተዘዋዋሪም ቢሆን ለዚህ ጥያቄ መንሥኤው የጥናት መበላሸት መሆኑን ሳይገምት አልቀረም ።

“ በቅርብ እንኳ የሉም ። ጎንደር ክፍለ ሀገር ናቸው ።ሲል መለሰ ።

የኑሮ ደረጃቸው እንዴት ነው? ”

“ መቼም ጎርሰው ያድራሉ ። ቋሚ የገቢ ምንጭ ግን የላቸውም ” ካለ በኋላ ' ድንገት ግልፍ ብሎት ፥ “ ያው እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያውያን ወላጆች የእኔኑ እጅ ተጠባባቂዎች ናቸው ” ሲል አከለበት

ይህ ከጥያቄአቸው ውጭ ቢሆንም አንድ አቤል የተቸገረበት ጉዳይ መሆኑን ከአነጋገሩ ለመረዳት ዮናታን ብዙ ጊዜ አልወሰደባቸውም ። ሆኖም የእሳቸው መንደርደሪያ በአቤል ውስጥ በቅርብ የደረሰ አደጋ ወይም አጋጣሚ እንዳላ
ለመረዳት ነበር ። በዚህ ረገድ ቀጥተኛ መልስ ባያገኙም ጥርጣሬአቸውን ለማስወገድ ችለዋል ።

ታዲያ... ብለው ዮናታን መናገር ያሰቡትን
ሳይጨርሱ አጠገባቸው ያለው ስልክ አቃጨለ ። የስልክ ጥሪው የማን መሆኑን በልባቸው ገመቱ ።

“ ሁሉ ... ሊብሊንግ ” አሉ አንዳች ነገር እንደሚጠብቁ ሁሉ ፊታቸው ላይ ጉጉት እየተነበበ ።

የደወለችው ሚስታቸው ሞኒካ ነበረች ። ንግግራቸው በጀርመንኛ ስለሆነ አቤል ከዮናታን አፍ ምንም ነገር ሊረዳ አልቻለም ነገር ግን የዮናታን ሚስት ጀርመናይት መሆኗን በዩኒቨርስቲው አካባቢ ሲወራ ይሰማ ስለ ነበር ፥ ዮናታን አሁን የሚነጋገሩት ከሷ ጋር መሆኑን ገመተ።

ሰሞኑን በርሊን ውስጥ የሚገኘው የሞኒካ ወንድም በጠና ታሞ ከባድ ቀዶ ሕክምና እንዲደረግለት እየተጠባበቀ ነበር ።
ዮናታንና ሚስታቸውም ይህንኑ ጉዳይ በቴሌፎን በመከታተል አብረው ሲጨነቁ ነው የከረሙት ። የተጠቀሰው ዕለት
ደርሶ ሦስት ሰዓት ያህል የፈጀ ቀዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ ወንድሟ በሰላማዊ ሁኔታ እንደሚገኝ ዘመዶቿ ከበርሊን ደውለው ለሞኒካ ይነግሯታል ። ሞኒካም ወደ ዮናታን የደወለችው ይህንኑ ልታበሥራቸው ነበር ።

ዮናታን ቴሌፎኑን ከዘጉ በኋላ በደስታ ስሜት ፊታቸው ፈካ ። ከአቤል ጋር ጀምረውት የነበረውን አርዕስት
በዜናው ጣልቃ ገብነት ለማሳጠር ተገደዱ ።

“...እስቲ ለማንኛውም እንደገና እየው” አሉት ፥ በሚያባብል ድምፅ ።

አቤል በእሽታ ራሱን ናጠ ።
“ ሐሳብ ውስጥ ገብተህ ወይም ተቻኩለህ ይሆናል እንጂ አንተ እንዲህ ዓይነት ሥራ እንደማትሠራ እተማመናለሁ” እያሉ ለአቤል ወረቀቱን መልሰው ሰጡት
ወረቀቱን ሲቀበላቸው ፊቱ ላይ አንድ ስሜት አነበቡ ።ሰሜቱ የገባቸው ይመስል “ አይዞህ የሦስት ሳምንት ጊዜ ሰጥቼሃለሁ ። ረጋ ብለህ ሥራው » አሉት
አቤል ሲወጣ ከእንድ እሱነቱ ውስጥ ሁለት ስሜት እየተጓተቱ ነበር ።
ስማ አቤል ! አሁን ወረቀቱን መልስህ የተቀበልካቸው ምን ልትጨምርበት ነው ? የተቻለህን ያህል ሠርተሃል ፡ ይልቅ ፡ የማውቀው ይህን ያህል ነው በቃ ” በልና
መልስላቸው ፤ ያሻቸውን ውጤት ይስጡህ ይላል አንዱ ስሜቱ ።

ይህን ማመንታትህን ትተህ እንደ ገና በደንብ አጥርተህ ለመሥራት ሞክር : ተፍጨርጨር። የመጨረሻ ዓመትህ መሆኑን አትርሳ ። ወላጆችህም በተስፋ የአንተኑ እጅ ጠባቂዎች መሆናቸውን አትርሳ ። የሚወዱህን መምህርም
አታስቀይማቸው ...” ይላል ሌሳው ስሜቱ

የወላጆችህም ችግር ሆነ የመምህርህ ፍቅር ከችሎታህ ህና ከአቅምህ በላይ ሊያደርግህ አይችልም ። የምትችለው
ያንን ያህል ነው ፥ በቃ !... ”

እስቲ ለማንኛውም እንደ ገና እየው
እንዲህ ስሜቶቹ እየተሟገቱ ከመኝታ ክፍሉ ደረሰ ።
ሶስቱም የመኝታ ክፍል ጓደኞቹ እዚአው ውስጥ ነበሩ ።
አቤል ምንም ሳይነግራቸው በቀጥታ ወደ አልጋው ሔዶ በአንድ ጎኑ ዐረፍ አለ ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አቤል ለመኝታ ክፍል ጓደኞቹ ወሬ ማካፈል ቀርቶ ፥ አብረውት መሆናቸውም እያስጠላው ነበር ።
ብቸኝነት እያጠቃው ስለ መጣ ብቸኛ ክፍል ወስጥ ቢሆን ምንኛ በወደደ !... ከራሱ ጋር በመጣላቱ የፈጠረው ጥላቻ እንጂ ፥ ከአንዳቸው ጓደኞቹ ጋር ግጭት አልነበረውም ።

እስክንድር ማንደፍሮ አቤልን ተደራራቢ አልጋ የሚጋራው የመኝታ ክፍል ጓደኛው ነው ። በዩኒቪርስቲው ውስጥ
ሦስት ዓመት አብረው ቆይተዋል ። ከመኝታ ክፍል ጓደኝነታቸወም ሌላ ፥ ሁለቱም የፍልስፍና ተማሪዎች ናቸው ። እስክንድር ከአቤል በዕድሜ ላቅ ያለ ሲሆን ፥ በአቤል የትምህርት ጉብዝና ሳይ ጤናማ የሆነ ቅናት አለው ።

ሰሎቹ ሁለቱ የመኝታ ክፍል ጓደኞቹ ሳምሶን ከልሌ እና አስራት ጣሰው ናቸው ሁለቱም በግቢው ውስጥ የሚታወቁት በቅጽል ስማቸወ ነው " ሳምሶን ከስሙ ጋር ጉልቤው ” የሚል ቅጥያ ስም ወጣለት ማንኛውም ተማሪ ሲጠራው ሳምሶን ጉልቤውን ? እያሉ ነው ። አሥራት
ደግሞ የሚታወቀው “ ድብርት ” በሚል ቅጽል ስም ነው በተማሪው ዘንድ ትክክለኛ ስሙ ጭራሽ ተረስቷል
ማለት ይቻላል ።

ሳምሶን ጉልቤው ” እነ አቤል መኝታ ክፍል የመጣው በዚ ዓመት ነው ። እስክድር ጋር የአንድ ሰፈር ልጆች ስለሆኑ አንድ የፍልስፍና ተማሪ ፈተና
👍2
ወድቆ ከወጣ በኋላ ክፍላቸው ውስጥ ትርፍ መኝታ መኖሩን አይቶ ነው የመጣው ። የሁለተኛ ዓመት የምጣኔ ሀብት ተማሪ ነው ።በአንደኛ ዓመት ትምህር ፡ ባገኘው ዝቅተኛ ውጤት "ማስጠንቀቂያ ” ውስጥ "ቢገባም ስፖርቱን አላቋረጠም ። ስፖርትና ምግብ በጣም ይወዳል ። የዚያኑ ያህልም ሰውነቱን ስላዳበረ ። አፍላነቱ ይፈታተነዋል ። ለዚህ ነው “ጉልቤው” የሚል ቅጥያ የወጣለት ። በዚህ ዓለም ላይ ማንም ሰው የሚያሸንፈው አይመስለውም ። እንኳን እሱን ቀርቶ ጓደኞቹን የሚደፍር ከመጣ ፡ ማነው እሱ ? እናቱን ፤ ” ብሎ ማፍጠጥ
ነው ። “ ጥርሱን ነው የማመልቀው ! ” ሴትም ከሆነች “ጥርሷን ነው የማወልቀው ! ” የጡንቻ መፈክሮች
ናቸው ። ሁሌ ሁሉን ሰው እንዳንቀጠቀጠ
ነወ።አንድ ቀን ብቻ በአንድ የግቢው ወጣት ተደፍሮአል።

ስምሶኦን የምግብ እዳራሽ ሰልፍ አይወድም ሁሌ ጥሶ ነው የሚገባው
አንድ ቀን እንደ ለመደዉ ሰልፍ ጥሶ ሊገባ
ሲል ከፊት የነበረ በዕድሜው በሰል ያለ ወጣት በአድራጎቱ በሽቆ ጭንቅላት እያለህ ለምን በጡንቻህ ታስባለህ ? በጡንቻው የሚያስብ አህያ ብቻ ነው ” አለው• ። ሳምሶን ጉልቤው ” ይህን ሰውና ቃላቱን እስከ መቼውም አይረሳውም
ካልተደባደኩ ብላ ለጊዜው ቢጋበዝም
ከዚያ በኋላ ባላቸው ግኑኝነት ለራሱም በማይገባው ስሜት ወጣቱን ያከብረው ነበር ።

አሥራት ፍጹም ዝምተኛ ነው ብሶትም አለበት እዛው ለዚያው ያልጎመጎማል እንጂ በወጉ አይናገርም ጣእም የሌለው
ዝምታው በጣም ያስጠላል መሃበርያዊ ኑሮ ውስጥ ያለ አይመስልም።“ድብርት ” የሚል ቅጽል ያወጡለትም ለዚህ ነው።

💥 ይቀጥላል 💥
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

...ሳሚ ጨዋታውን አቁሞ ሊያግባባቸው መሃል ገባ፡፡ ነገሩ ጭራሽ ጦዘ፡፡

“አንተ ለሷ መደረብህ ነው? ምን አገባህ! ምታመዛዝን ትልቅ ሰው ትመስለኝ ነበር! እንደዚህ የወረድክ መሆንህን ባውቅማ፣ ወይኔ...!” ግርማ እየጮኸ ያወራል፡፡ ነገሩ አላምርህ ሲለኝ አስተናጋጅ ጠርቼ ሂሳብ
አምጣልን አልኩት።

“ተረጋጋ! ቀስ ብለኸ አውራ! ” ሳሚ ሊያረጋጋው ሞከረ፡፡

“አንተ ስለእርሷ ምን አገባህ?!” ግርማ ነገሩን በጣም አከረረው፡፡ከደቂቃዎች በፊት ሳቅና ጨዋታ የነበረው ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ተለወጠ፡፡

“በቃ ተነሱ፤ ሂሳብ ተከፍሏል እንሂድ” ሳሚ ተነስቶ ወጣ፣ተከተልነው፡፡

“አንተ ምን ስለሆንክ ነው ምትከፍለው?! ሂሳቡን አሳየኝ የራሴን እከፍላለሁ!” ግርማ ሳሚን እየተከተለው፣ ተጨቃጭቀው፡፡ ሳሚ ሪሲቱን አሳየው፡፡ ግርማ የሆነ ብር ሰጠውና ተለያዩ፡፡

“አሁን እንዴት ነው የምንሄደው? እኔ ቤቲን አደርሳታለሁ ፤አንተ ሁለቱን ታደርሳቸዋለህ” አለኝ ሳሚ መኪናውን እየከፈተ፤

“እሺ! ችግር የለም አደርሳቸዋለሁ።”

“ኖ!..ኖ! እኔ በባጃጅ ሄዳለሁ፤ አልፈልግም!” ብሎ ግርማ ጥሎን
ሊሄድ ሲል፣ ተከሻውን ያዝ አደረኩና አረጋግቼ ከማሂ ጋር መኪና ውስጥ አስገብቼ ልሽኛቸው ወደ ዋናው መንገድ መንዳት ጀመርኩ፡፡

“ማሂላ መጀመሪያ ግርምሽን እናድርሰው አይደል?” ማሂ አጠገቤ ብትሆንም ግርማ እንዲሰማ ጮክ ብዬ ጠየኳት፡፡ ስንመለስ ብቻችንን እንድንገናኝ እንደምትፈልግ አውቃለሁ፡፡ ማሂ ቆንጆ ብቻ ሳትሆን ፈጣንና ተግባቢ ናት፡፡ ከጠበኩት በላይ በፍጥነት ነው ተግባብተን ግንኙነት የጀመርነው፡፡ ስንመለስ አብረን እንድናድር እንደፈለኩ
ገብቷታል፡፡

“በፍፁም አይሆንም! መጀመሪያ ለሴት ነው። ቢመሽም እኔ ወንድ ነኝ፣ እርሷን እናስቀድም፤” አለ ግርማ፡፡
“አይ ችግር የለውም ግርምሽ፡፡ የኔ ቤት መንገድ ዳር ስለሆነ እሱም ሲመለስ እንዳይቸገር፣ መጀመሪያ አንተ ቅደም፡፡ ስላስቀደምከኝ ግን በጣም አመሰግናለሁ!” ብላ ከመጨረሷ፣ ቀበል አድርጌ፧

“የት ሰፈር ነህ ግርምሽ?” አልኩት ሌላ ክርክር እንዳያመጣ፡፡

ቀበሌ አስራ አንድ፡፡ ፖስታ ቤት ጀርባ፡፡ ግን አስቸገርኩህ፣በባጃጅ መሄድ እችላለሁኮ...”
“እረ ችግር የለውም! ደግሞ አብረን ወጥተን ተለያይቶ መግባት ደስ አይልም፡፡”

“እሺ ካላቹ፤” ብሎ ስለቤቲና ሳሚ እያማረረ እቤቱ አደረስነው፡፡ስንመለስ፣ ወደ መብራት ሃይል እየነዳሁ ፤
“መቼም በቅዳሜ፣ በዚህ ሰዓት እንግባ እትዪኝም፡፡”

“ደስ ወዳለህ ንዳው፣ እኔም መዝናናት ፈልጌያለሁ፡፡”

ጭፈራ ቤት እየቀያየርን፣ ቢራና ውሲኪ እያፈራረቅን ጠጣን፣በደስታና በመጠጥ ሰክረን ጨፈርን፡፡ የሚያቀን ሰው ቢያየንስ ሳንል፣ በየመሃሉ እንሳሳማለን፡፡ ያለልጓም እስኪወጣልን ተዝናናን፡፡ ሲደክመን
ወደቤት ለመሄድ ወጣን፡፡ ማሂም እንደኔው በግንኙነታችን ደስተኛ የሆነች ትመስላለች፡፡ በየምክንያቱ እኔ ጋር ማደር ልማድ ሆኗል፡፡ ዛሬ ደግሞ እቤት እስክንደርስም አላስቻላትም፡፡ እየነዳሁ ትስመኛለች፡፡ ስንደረስ፣ ማላቃት እስኪመስለኝ፣ የፍቅርና የእልህ በሚመስል መልኩ፣ ዝለን እንቅልፍ እስኪወስደን ድረስ ግንኙነት አደረግን፡፡ ጥዋት አንድ ሰዓት ሲሆን እንደተለመደው እቤቷ አደረስኳት፡፡

####

ባልጠበኩት መልኩ ጥሩ ስራና ቆንጅዬ ልጅ በአንዴ አግኝቼ፣አንድ ቀን ሳይከፋኝ አንድ አመት አለፈኝ፡፡ በሁሉም ነገር ደስተኛ ነኝ፡፡ከማሂ ጋር በጀመርኩት ግንኙነትም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል፡፡ይሁን እንጂ፣ አሁንም ከማሂ ጋር ያለኝ ግንኙነት በሚስጥር እንዲቀጥል
እፈልጋለሁ፡፡ አሁንም ልቤ ሜሪ ጋር ነው፡፡ በስልክ ምናደርገውን ግንኙነት አላቋረጥኩም፡፡ ግን ሽማግሌ ሳይላክ ምንም አይነት ግንኙነት መጀመር እንደማትችል ነግራኛለች፡፡ እዚህ መስሪያ ቤት ከገባሁ በኋላ፣ ህይወት ብርሀን፣ ፍካት፣ ጣፋጭ እና አጓጊ ሆናልኛለች፡፡ ተስፈኛ ሰው ነኝ! ዛሬም እንደተለመደው በሙሉ ሱፍ ነኝ፡፡ ሱፍ ያምርብሃል
ቢሉኝም፣ እኔ ሱፍ ማዘወትረው የስራ ዩኒፎረሜ ስለሚመስለኝ ነው::ካለሱፍ ስሄድ እረፍት ላይ ያለሁ ይመስለኛል፡፡

ከሆነ ግዜ ጀምሮ ግን አለቃዬ ባህሪያቸው እየተቀየረብኝ መጥቷል። እንደዛ እንዳላከበሩኝና በስራዬ እንዳልኮሩብኝ፣ ከስራዬ እንከን
እየፈለጉ ይዘልፉኝ ጀምረዋል፡፡ በአሽሙር እኔን መቅጠራቸው ትልቅ ስህተት እንደሆነ በሰዎች መሃል ይናገራሉ፡፡ እንዳልገባኝ እሆናለሁ።ቢሯቸው ለጉዳይ ከሄድኩ፣ ስራ እንደያዙ በምልክት እያሳዩ
እንድወጣላቸው ያደርጋሉ፡፡ ስንዝናና እንኳ፣ እኔ ካለሁ ምክንያት ፈጥረው ይሄዳሉ፡፡ ቅሬታቸው ለሰዎች እስኪገለጥ በገሃድ አደረጉት።ለኔ ግን ምን እንዳጠፋሁ እንኳ አልነገሩኝም፡፡ ሲደጋገምብኝ፣ ቢሯቸው ሄጄ ጋሼ ብዬ፣ ምን አጥፍቼ እንዲህ እንደተለወጡብኝ እንዲነግሩኝ ጠየኳቸው፡፡ ከስራ ውጪ ሚያገናኘን እንደሌለና ሁለተኛ እንደዚህ
አይነት ጥያቄ እንደማይፈልጉ፣ እንደውም ስራ እንደረበሽኳቸው ነግረውኝ፣ ከቢሯቸው እንድወጣ አደረጉኝ፡፡ ባህሪያቸው ይሆናል ብዬ ወደስራዬ አተኩሬ መስራቴን ቀጠልኩ፡፡ውስጤ ግን ማብሰልሰል ጀመረ።

“ምነው በጥዋት በሃሳብ ሄድክ፣ ና ተነስ ቡና ልጋብዝህ!” ማሂ ናት፡፡ አሁን አሁን ሰው እስኪጠረጥር ቢሮዬ መመላለስ አብዝታለች፡፡በሻይ ሰዓት ደጋግማ እየመጣች ከእርሷ ጋር አብረን እንድንወጣ ታደርጋለች፡፡ እሺ ብያት ስንወጣ፣ ከፊታችን ግርማን አየነው፡፡

“ቀስ በል፣ ይሄ ማቶ እንዳያየን፤” አለች ወደ ግርማ በአገጯ እየጠቆመች።

“እንዴ! ቢያየንስ፣ ምን ችግር አለው?”

“ኧረ ባክህ? በዚህ ጥዋት ማን የሱን ዝብዘባ ይሰማል፡፡ ምኑን ከምን እንደሚያገናኘውኮ? በዛ ላይ ሲያወራ
ነን ስቶፕ፡፡”

“ማለት?”

“እንጃ ግርማ የሆነ ትንሽ የላላ ነገር አለው፡፡ ከፈሱ የተጣላ ነው፡፡” ከካፍቴሪያ ጀርባ ተቀምጠን ቡና አዘዝን፡፡

“ከፈሱ የተጣላ ማለት?”

“በጣም ተጠራጣሪ ነዋ፡፡ ባለፈው ማታ ከቤቲ ጋር የተጣሉት ቢራ ብርጭቆዬን ቀየርሽብኝ ብሎ አይደል እንዴ.. ሆ..:: እዚህ ግቢ ከሰው ጋር ሁሉ ተናክሶ ጨርሷል፡፡ ሰው ሁሉ እሱን ሚሰልለው
ይመስለዋል፡፡ ወሬው ሁሉ እከሌ እንዲህ አስወርቶብኝ፣ እንዲህ አስደርጎኝ.. ምናምን ነው፡፡ በተለይ ይቺን እንዲህ ብታደርጋት፤ ብለህ አስተያየት ከሰጠኸው...፣ አለቀልህ፡፡”

“ማለት?”

“አንተ እረስተኸው ሁላ፣ ያለህበትን በእግር በፈረስ አፈላልጎ ይመጣና፣ አንተ ግን ቅድም ምን አስበህ ነው እንደዚህ ያልከኝ?፣ ማን ነው እንደዛ በል ያለክ?፣ ምናምን እያለ አይፋታህም፡፡ አዛ ያደርግሃል።

በዚህ ባህሪው ከብዙ እስታፍ ጋር ተጣልቷል፡፡ ለማንኛውም ተጠንቀቅ፡፡

‹‹እሺ፡፡ እጠነቀቃለሁ፡፡››

ቡናችንን ጠጥተን፣ እያወራን እኔ ቢሮ ድረስ ሽኘችኝ፡፡ ከቢሮ ልትወጣ ስትል፣ ሳሚ ሳታስበው ገብቶ ከኋላዋ አቀፋት፣

“እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?”

“ያቡን ምን ጎደለህ ልለው...”

“እርሱ ምን ስለሆነ...? እኔን መጥተሽ መች እንደ ትይኛለሽ...?” እየሳቀ ጉንጫን ለመሳም ይታገላታል። ሳሚ ልማዱ
ነው፡፡ ሴቶቹን አየዞረ ጉንጫቸውን መሳም አመል ሆኖበታል፡፡ አብዛኞቹ ይተባበሩታል፡፡

“አንተስ ከመቼ ጀምሮ ነው፣ ፋይናንስና አድሚንን እኩል ያደረከው...?፡፡" ከእቅፉ ሾልካ አመለጠችው፡፡

“ደግሞ እንዲህም መከፋፈል ጀመራችሁ? እኛም ከአድሚን
ስራተኛ ጋር አንድ መሆን አንፈልግም...!” እያላት ከላይ እስከታች ተመለከታት፣

“አቤት... ዛሬ ደግሞ፣ ውበትሽን ገልጠሽዋል፡፡ ደግሞ ማንን
ልታጠምጂ ይሆን..?”
👍3
ሌላስ? እኔማ ሁሌም ውብ ነኝ! ታውቃለህ!”

“እሱን አምናለሁ፡፡ የዛሬው ግን፣ ወጥመድ ይመስላል፡፡”
ካካካ... የተለመደ ካንገት በላይ ሳቁን፣

“አንተ ሳሚ የማኔጅመንት ስብሰባው ሰዓት ደርሷል፣ ወሬውን አቁምና እንሂድ፤” አልኩት በመሃል አቋርጬው፡፡

“ወይኔ ጉዴ...!” ብላ ማሂ እየሮጠች ወጣች፡፡

“እኔም የመጣሁት እንሂድ ልልህ ነበር እኮ፡፡ እቺ ሸቃባ ልቤን አጠፋችብኝ፡፡ ደግሞ እዚህ ቢሮ እግር አብዝታለች። ጠንቀቅ በል፤” ብሉኝ ተያይዘን ወደ ስብሰባው አዳራሽ ሄድን፡፡

የስብሰባው አዳራሽ ስንደርስ፣ አብዛኞች ተሰብሳቢ ቀድሞን ተገኝቷል፡፡ እንደገባን ስብሰባው ተጀመረ፡፡ የስብሰባው ዋና አጀንዳ በአቶ ኤፍሬም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ለመነጋገር ነው፡፡ የአቶ ኤፍሬም የክስ ደብዳቤ በሰብሳቢው በአለቃዬ ተነብሶ፣ ለውይይት ቀረበ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) ...ሳሚ ጨዋታውን አቁሞ ሊያግባባቸው መሃል ገባ፡፡ ነገሩ ጭራሽ ጦዘ፡፡ “አንተ ለሷ መደረብህ ነው? ምን አገባህ! ምታመዛዝን ትልቅ ሰው ትመስለኝ ነበር! እንደዚህ የወረድክ መሆንህን ባውቅማ፣ ወይኔ...!” ግርማ እየጮኸ ያወራል፡፡ ነገሩ አላምርህ ሲለኝ አስተናጋጅ ጠርቼ ሂሳብ አምጣልን አልኩት። “ተረጋጋ! ቀስ ብለኸ…»
#ሰመመን


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ከሳምሶን ጋር ተደራራቢ አልጋ ቢጋሩም” ቅሉ አይስማሙም። ሳምሶን ንጋት ላይ እየተነሣ የሚሠራው ስፖርት ድምፅ ስለሚፈጥር ፡ “ድብርትን” ያናድደዋል ። አልጋው ላይ የሚያደርገው መወራጨት ያበሽቀዋል ። ከሁሉም በላይ ድብርትን ” የሚያናድደው ደግሞ የሳምሶን ፈስ ነው በየጊዜው ቁልቁል ሲያቦንበት ፡ አፍንጫውን ይዞ ከማነፋነፍ ሌላ ምርጫ አልነበረውም ።

አሥራት "ድብርት ” ሌላ በጣም የሚጠላው ነገር ቢኖር መኝታውን ማንጠፍ ነው ። እንዲሁ እንዳድበሰበሰ
የየትምህርት ወራቱን ይጨርሳታል እንጂ አንሶላውን አራግፎ በቅጡ አያነጥፍም ። ካልሲውን ማጠብም አይወድም ።
ከእነእስክንድር የሚጣላው በዚህ ነው ትምህርትም ከሌሉች በጋራ ማጥናት ወይም መወያየት አይሆንለትም ።
አድፍጦ ከርሞ ፈተና ላይ መሟሟት ነው፥ የእሱ ችሎታ ።

ጓደኞቹ ዝቅ አርገው የሚገምቱት ዕውቀቱና ፈተና ላይ የሚያመጣው ከፍ ያለ ውጤት ያለመጣጣም ብዙዎቹን
ያስገርማቸዋል ...

አቤል ከዮናታን ቢሮ ከተመለሰ በኋላ ፡ ለአንዳቸውም ነገሩን ሳየያነሳ ቢቆይም የገጽታውን መለዋወጥ በማየት እስክንድር መወትወቱ አልቀረም ።

ምነው ? ሀገር ሰላም አይደለም እንዴ ? ”
ምን እባክህ ፡ እነ ዮናታን ረበሹኝ ” አለ አቤል ስሜቱን አክፍቶ ።

“ ኦ ! ኣባታችን ምን አርግ አሉህ ? ” ፍቅሩን ለመግለጽ የሚጠቀምበት የአነጋገር ስልት ነበር ።

“ ሰሞኑን የሰጠኋቸውን የጥናት ጽሑፍ እንደ ገና እንድሠራው ኣዘዙኝ ።

“ ምን ታረገዋለህ ! መበርታት ነው ። አይዞህ ስድስት ወር እኮ ነች የቀረችን ።

በሱ ቤት ስድስት ወሩን የስድስት ሰዓት ያህል አቅልሎ መናገሩ ነው። ለአቤል ግን ስድስት ወሩ ስድስት ዓመት
ሆኖ ነበር የተሰማው
።።።።።።
የዓመቱ ትምህርት ከተጀመረ ሁለት ወር እንኳ ባይሞላም ፡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በጥናት ተዋክበዋል " አብዛኛው ተማሪ ፡ ፊቱን ወደ ቀለም መልሶአል ። አንዳንዱ ደግሞ የሌላው ኣጠናን ተስፋ አስቆርጦት ፡ የትምህርት
አሰጣጡ ክብደት ወይም ደግሞ አንድ የሙከራ ፈተና አስበርግጎት የመሰናበቻ ጊዜውን ብቻ በመጠባበቅ አሥራ ስድ
ስት ሰዓት ይተኛል ።አይብዛ እንጂ አቤል የገጠመው ዓይነት ችግር ውስጥ ገብቶ የሚዋዥቅም አይጠፋም ።

የሁለተኛና የሦስተኛ ዓመት ተማሪዎች መጠነኛ መረጋጋት ይታይባቸዋል ። ጥናቱ በመጀመሪያና በመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች ላይ ያይላል በተለይ በርካታ ተማሪ የሚያረግፈው የመጀመሪያ ዓመት አጋማሽ ፈተና እንደ ጦር ስለሚፈራ ተማሪዎቹ ፥ “ የገና ማዕበል” የሚል ስም አውጥተውለታል ።

የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ለትምህርቱ ብቻ ሳይሆን ለግቢውም እንግዳ ስለሚሆኑ፥ መቻኮልና መረበሽ ይታይባቸዋል ። በዚሁ ምክንያት ፡ “ፍሪሽ ጦጣው ” የሚል ስያሜ ወጥቶላቸዋል ።

ትግላቸው ፈተና ለማለፍ ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የመቆየት ህልውናቸውን አስከብረው ይህን ስያሜ ለማስፋቅም ጭምር ነው ።

ትፅግሥት ፈረደ ከማዕበሉ ግፊት ለመዳን ከሚፍጨረጨሩት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች አንዷ ናት ። አብዛኛ
ውን ጊዜ የምታጠናው ከዋናዉ ቤተ መጻሕፍት ጀርባ የሚገኝ ዋርካ ሥር ነው ጓደኛዋ ማርታ ደመቀ ፡ ይህን ቦታ
እምብዛም ባትወደውም ፡ በትምህርቱ ረገድ የትዕግሥትን ርዳታ ስለምትፈልግ ብዙ ጊዜ አብራት ታጠናለች ።

ሰሞኑን የመጀመሪያ ዓመት አጋማሽ የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ትምህርት ፈተና አለ ስለተባለ ሁሉም የሜያጠኑት

ይሄንኑ ነው። አብዛኛው ተማሪ የአጠናን ስልት የለውም ወደናገጥ ይበዛበታል ። የአንድ ትምህርት ፈተና አለ ከተባለ ፥ ተማሪው ሁሉ ኃይሉን እዚያ ትምህርት ላይ ያውላል ።

የተቀሩት ትምህርቶች ሳይታዩ ይከርማሉ ሌላ ፈተና ሰመጣ ደግሞ ወደ ሌላው ይዘመትበታል ። ትምህርትን በአእምሮ ውስጥ ከሚቀርፅ የአጠናን ዘዴ ይልቅ ፥ በሽምደዳ ለጊዜው ያህል አውቆ መሰናክሉን የማለፍ ልምድ እዮዳበረ መጥቷል ።

ትዕግሥትና ማርታ ከዋርካው ሥር ተቋምጠው ይህንንኑ ትምህርት በማጥናት ላይ ሳሉ " አንድ ወጣት በአካባቢያቸው ውልብ ሲል ታያቸው ። ቀድማ ያየችው ትዕግሥት ነበረች።
ሆኖም ቶሎ ብላ ዐይኗን ሰበረች ።

ማርታ ወጣቱን እንዳየች ከአፉ አምልጧት
“ ያውልሽ ! ” አለቻት ።
“ ምን? ” አለችና ትዕግሥት የማርታን ሐሳብ ለማዳና ቶሎ ብላ ፥ “ በይ ይልቅ ልጠይቅሽ ” አለቻት ።

ምን ? ” አለች ማርታም ትእግስት የማርታን ሃሳብ ለማደናገር ቶሎ ብላ "በይ
ይልቅ ልጠይቅሽ" አለቻተሸ።

ምን አለቻት ማርታም ድንገት ባመለጣት ቃል ተደናግጣ ።

ከምናጠናው ትምህርት ውስጥ ነዋ !

እሺ ፥ ጠይቂኝ” አለች ማርታ ለአፏ ያህል ልቧ ግን ወደ አለፈው ጉዳይ ቀርቶ ነበር

ለምንድነው የምትደብቀኝ ? ” ስትል አሰበች ። እኔ እንደሆንኩ ነቅቼባታለሁ ። ሞኝት ! በእሷ ቤት ማንም አላወቀብኝም ብላ እኮ ይሆናል ። ያበጠው ይፈንዳ እንጂ ፥ ዛሬ አውጣጣታለሁ ብላ በልቧ ፎከረች ።

"ግን ዋና ነሽ ትዕግሥት ሙች ! ”

ምነው ? ምን አረኩሽ ? ” አለች ትዕግስት
ነገሩ ቢገባትም እንዳላወቀች ሆና በመቅረብ ።

“ ስለ እሱ ሳነሳብሽ ለምን ትዘጊኛለሽ ? ” አለቻት !

ድርቅ ብላ ጉዳዩን ግልጽ በማውጣት ።


ትዕግሥት ምንም አልመለሰችም ። ክው አለች ። ወደ ኋላዋ አስታወሰች ። በእርግጥም ስለ አቤል ስታነሣባት ብዙ
ጊዜ ዘግታታለች ...

አንድ ጊዜ ማርታ አቤልን ከሩቅ ስታየው ፥ ከትዕግሥት ጋር ጨዋታ ለመክፈት ብላ ፥ “ ትዕግሥትዬ ! ይሄ ልጅ በትምህርቱም በጣም ጎበዝ ነው አሉ። በሦስተኛ ዓመት አጋማሽ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት ትምህርት “ B ” አግኝቶ ካልታነቅኩ ብሎ አስቸግሮ ነበር ይባላል ” አለቻት ።

“ ለምን ? ” አለች ትዕግሥት ፡ ለጨዋታው ብዙም ስሜቷን ያልሰጠች በመምሰል ።

“ ጂፒኤው ትንሽ ዝቅ ስላለበት ነዋ ! ከአራት ነጥብ ወርዶ አያውቅም ይላሉ ” አለች ማርታ የትዕግሥትን ስሜት የሳበች መስሏት ፥ ክፉኛ የተገረመች ያህል ራሷን
እየነቀነቀች ።

“ ኧረ ? ” አለችና ትዕግሥት ቶሎ ብላ ወደ ሌላ አርዕሰ ጉዳይ ዞረች ማርታም በሆዷ በሽቃ ነገሩን ተወችው።

ሌላ ጊዜ ደግሞ ፥ በመኝታ ክፍላቸው ውስጥ ከሌሎቹ ሁለት ልጃገረዶች ጋር ሆነው ስለ ትምህርት መስክ መረጣ
ጉዳይ ሲጨዋወቱ፡ በማርታ ሐሳብ ውስጥ አቤል ብቅ አለባትና

“ እኔ እንዳንድ ልጆች ጥሩ ጭንቅላት ኖሮአቸው ለምን የማይሆን መስክ እንደሚመርጡ ይገርመኛል ” አለች ።

እንዴት ? ” አለች ትዕግሥት ።

አሁን ዘንድሮ ፍልስፍና ትምህርት ከሚመረቁት ተማሪዎች መሐል አንድ ልጅ አለ ። ብታዬው እኮ........
“ የቱ ነው ? ” ሲሉ ሁለቱ ልጃገረዶች ጠየቁ ። ትዕግሥት የአቤል ጉዳይ መነሣቱ ስለ ገባት ፡ እንገቷን አቀርቅራ
ከጥፍሯ ወስጥ ቆሻሻ ታወጣ ጀመር

ማርታ ነቃችባት « ግን ጨዋታዋን አላቋረጠችም በጣም ጎበዝ ነው የሚባለው ” እያለች ለሁለቱ ልግረዶች
ለማስረዳት ሞከረች ፣ ስሙንም ታውቀዋለች » ሆኖም በትዕግሥት ፊት መጥራቱ የሚያስደነግጣት ወይም ሌላ ጥርጣሬ የሚያሳድርባት ስለ መሰላት ስሙን አልጠራችም ።

ሁለቱ ልጃገረዶች የአቤል ምስል ዐይኔ ኅሊናቸው ውስጥ ሊመጣላቸው ስላልቻለ “ እሺ ብቻ ጨዋታውንቀጥዪ ” አሏት ።

“ እኔ እሱን ብሆን ” አለች ማርታ ፡ “ እንደሱ ጭን ቅላት ቢኖረኝ ፡ ሜዲሲን ወይም ኢንጂነሪንግ ነበር የምመ
ርጠው ።

“እንደሱ ማለት እንኳ አትችዪም ” አለች አንደኛዋ ልጃገረድ ። “ ሰው እንደ ፍላጎቱ ነው ። አንቺ የምትዪው ልጅ የፍልስፍ
👍1😢1
ና ጥማትና ፍላጎት ይኖረው ይሆናል ። ደግሞስ የከበደና የከበረ ትምህርት ሜዲስን ብቻ ነው ያለው ማነው
እሱ ? ! በእኔ ግምት ማንኛውም የትምህርት ዐይነት የተከበረና ዋጋ ያለው ነው ። ዋናው ነገር እንደ ባለቤቱ ፍላጎትና
አያያዝ ነው

ትዕግሥት ልቧቅቤ ጠጣ ። ደስታዋ የልጃገረዷ አነጋገር አቤልን ስለሚደግፍ ሳይሆን የራሷም እምነት ስለሆነ ነበር።
በትዕግሥት አመለካከት የ ፍላጎትና ትክክለኛ ስሜት በገንዘብ መለወጥ የለበትም ። የመስክ መረጣው ጉዳይ በአብዛኛው ተማሪ ዘንድ ፥ “ ስሜቱ የትኛውን ይከተላል ? ”መሆኑ ቀርቶ፡ “የትኛው ብዙ ገንዘብና ዕድገት ያስገኛል?”የሚለው ሆኖኣል ፡ ቢገኝም ቅሉ ያለስሜትና ፍላጎት የሚሠራ ሥራ ብኩንነን ግዴለሽነትንና ራስን መጣልን
እንደሚያስከትል አርቆ የሚያስበው እምብዛም አልተገኘም ።

ለማንኛውም ፡ መነሾው የአቤል ጉዳይ በመሆኑ ትዕግሥት ጨዋታውን ተካፍላ ይህን አስተያየት ለመስጠት አልቻለችም ስሜቷን አፍና ዝም አለች ።

ማርታም የአቤልን አርዕስት ያነሣችው የትዕግሥትን ስሜት ለማጥናት ነበር እንጂ ለክርክሩ ብዙም ደንታ አልነበራትም ስለዚህ ያን ዕለትም በሽቃ አሳለፈችው
ትዕግሥት ይህንና የመሳሰሉትን አስታወሰች በኋላ በእርግጥም ስለ አቤል ስታነሣብኝ ብዙ ጊዜ ዘግቻታለሁ” ብላ አሰበች።

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

የክሱ ዋና ፍሬ ሃሳብ፣ የምርትና ሽያጭ ሃላፊ ሆኖ እየሰራ የነበረው አቶ ኤፍሬም፣ በተደጋጋሚ ከሰራተኞችና ከደንበኞች ቅሬታና ክስ ቀርቦባቸው እንዲያሻሽሉ፣ የቃልና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም፣ምንም አይነት የባህሪ ማሻሻል ካለማሳየታቸውም በተጨማሪ፣ በቅርቡ ከፍተኛ የምርታችን ተረካቢ የሆነን የውጪ ዜጋና የድርጅቱን ዋንኛ
ደንበኛን አፀያፊ ስድብ በመስደብ፣ ማስፈራሪያ ዛቻ በመፈፀም፣የድርጅቱን ስም፣ ዝናና ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ስለጎዱ በአፋጣኝ ከድርጅቱ እንዲሰናበቱ የመስሪያ ቤቱ የማኔጅመንት ኮሚቴ ተወያይቶ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ፤ አለቃዬ አጀንዳውን አቅርበው አባላቱን ተወያይተው ውሳኔ እንዲያሳልፉ ጋበዙ፡፡

በእድሜ ጠና ያሉት የመዝገብ ቤት ሃላፊ፣ እርጅና የተጫነውን ድምፃቸውን ለመክፈት፣ ሁለቴ ጉሮሯቸውን ከጠራረጉ ቦኋላ፣ “እኔ እሱ ሰውዬ ጤነኛ አይደለም ብያለሁ፣ ቀውስ ነው ካልኩ ቆየሁ፡፡ ሚሰማኝ ጠፍቶ እንጂ ይኼን ያክል ድርጅቱን ጉዳት ላይ እስኪጥል መጠበቅ
አልነበረበትም፡፡ ሰራተኛውን ከአፉ አውጥቶ ሚሳደባቸውን ስድቦች፣
አይደለም እዚህ ለመናገር መልሶ ለማሰብም ይቀፋሉ። ለነገሩ፣ እዚህ
ማን ያልሰማው ሰው ኖሮ ነው መድገም ሚያስፈልገው፡፡ እርሱኮ መባረር
የነበረበት፣ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በተፃፈለት ማግስት መዝገብ ቤት ድረስ መጥቶ ከመዝገቤ ውስጥ ይሄን ደብዳቤ አውጣ ብሎ የደበደበኝ እለት ነበር፡፡ እኔ በበኩሌ ምንም አይነት ውይይት ሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ በድርጅቱ ደንብ መሰረት ማሰናበት ነው !” አሉ ንዴትና ቁጭት ባዘለ ድምፅ፡፡

አብዛኛው የማኔጀመንት አባላትም ተመሳሳይ ሃሳብ ስጡ፡፡ስውዬው ብስጩ፣ ግልፍተኛ፣ እኔ ካልኩት ውጪ የሚል ጥጋበኛ እንደሆነ አብራሩ። ሜሪ የምርትና ሽያጭ ምክትል ሃላፊ ናት፤ እርሱ
ከማኔጅመንት ከታገደ በኋላ፣ እርሱን ተክታ ነው አባል የሆነችው፡ምንም ሃሳብ አልሰጠችም፡፡ ሳሚና እኔም ሃሳብ አልሰጠንም፡ አለቃዬ ሰሞኑን እኔ ምለው ሁሉ ስለሚያበሳጫቸው ብዬ አስተያየት ከመስጠት ተቆጠብኩ፡፡ በመጨረሻም በመመሪያው መሰረት እንዲሰናበት የሚል
ውሳኔ ተላለፈ፡፡

ከስብሰባው በኋላ ደበተኝ፡፡ ኤፍሬም አሳዝኖኛል፡፡ ሲያወራ ይፈጥናል፡፡ ቶሎ መገንፈሉን፣ ስሜቱን መቆጣጠር ቢችልና የተወሰነ መረጋጋት ቢችል፣ ኤፍሬም ትልቅ አቅም ያለው ልጅ ነው፣ ብዙ መስራት እንደሚችል በተለያዩ አጋጣሚዎች ታዝቢያለሁ፡፡ በራሪ ሃሳቦችንም ያበዛል፡፡ እንዴት አሰራራችንን ማዘመን እንዳለብን፣ ብዙ አይነት ጥናቶችን እንዳነበበ፣ ጥናት እየስራ እንደሆነ ያወራል፡፡ አንዱን
ሳይጨርስ ሌላ ይጀምራል፡፡ በራሱ ከመጠን ያለፈ መተማመን አለው፡፡
ቱርክ ያለ ፋብሪካ ልቀጠር ነው ይልና፣ መልሶ የራሴን ድርጅት እየከፈትኩ ነው ይላል፡፡

አሁን ኤፍሬም ከስራው ተሰናበተ፡፡ ሰራተኛው ጤነኛ አይደለም፡፡ቀውስ፣ ወፈፌ ነው ይለዋል፡፡ እሱ ጤነኛ ነኝ፣ ሲሰርቁ አላሰርቅ ስላልኳቸው፣ አላሰራ ብለውኝ፣ ሆን ብለው እኔን ለማባረር አሲረውብኝ ነው ይላል፡፡ እንደሚለው እንኳ ያልታመመ ቢሆንም ከስራው እንዲለቅ ተደርጓል፡፡ በርግጥ፣ ሰው ወገቡን ሲያመው፣ አዕምሮው ወገብህን
አሞሃል ሃኪም ጋር ሂድ ይለዋል፡፡አዕምሮው ግን ሲታመም እንዴት
እራሱን ታምሜያለሁ ይላል? በእርግጥስ
የታመመ እዕምሮ፣እንደታመመ ያውቃል? ካወቀስ ምኑን ታመመ? 'ጭንቅላትህ አይክዳህ የሚለው ጓደኛዬ ትዝ አለኝ፡፡ ለኤፍሬም አዘንኩ፡፡ እግዚአብሄር ይሁንህ!
ሰዓት ሲደርስ፣ ከድባቴዬ ለመሸሽ ማሂ ጋር ደውዬ ተያይዘን ወጣን፡፡

#####

ሰሞኑን ውስጤ የነበረው ደስታና ተስፈኝነት በድንገት እየደበዘዘ ነው፡፡ ከእንቅልፌ ስነሳ ድካም ይሰማኛል፡፡ ስራ የምሄደው፤ መሄድ ግዴታዬ ስለሆነ እንጂ፣ ፍላጎቴና ተነሳሽነቴ እንደቀድሞ አይደለም፡፡ ካለቃዬ ጋር ያለው አለመግባባት ይህን ያህል ተፅዕኖ ሊያደርግብኝ እንደማይገባኝ አስባለሁ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ምክንያቱን ባላውቀውም
ጭንቅላቴ ሚያላምጠው ሚያመነዠከው መጥፎ መጥፎውን እየመረጠ ሆኗል፡፡ ላስቆመው አልቻልኩም፡፡ ሊነሳብኝ ነው መሰል፡፡ መስሪያ ቤት ሲያስጠላኝ ሲል፣ ልለቅ ስል እንዲህ ነው ሚያደርገኝ፡፡ የተበደለ ጠበቃ ካዘነ ጋር አዛኝ እሆናለሁ፡አሁን ግን በጭራሽ ልፈቅድለት አይገባም
ከዚህ ስሜት ለመውጣት፣ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ፡፡ ማን ይፈዛል?! አዎ፣ መዋኘት ጥሩ መፍትሄ ነው፡፡ ሶደሬ እንድንሄድ ማስተባበር ጀመርኩ። ቀድሜ ለማሂ ነገርኳት፣ ቤቲን እንድታሳምን፡፡ ቤቲ እሺ ካለች፣ የሳሚ እዳው ገብስ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ እቅዴ ሰምሮ፣ እኔና ማሂ፣ ሳሚ ከቤቲ ጋር፣ እየተከታተልን ሄድን፡፡ የዋና ልብሶቻችንን ቀይረን ስንወጣ፣ የዋና ገንዳው በሰዎች እንደጉንዳን ተከቧል፡፡

“ወይኔ የሰው ብዛት...!” ቤቲ ተገርማ ጮኸች፡፡

“ድሮም በቅዳሜ ሶደሬ ብላቹ፣” ሳሚ ተነጫነጨ፡፡ ወደ መታጠቢያው እየወረድኩ፣ የሚደረገው ትዕይንትን እመለከታለሁ፡፡ ከከፍታ ቦታ ላይ ዘሎ መግባት፣ የዋና አይነቶች፣ ውድድሮች፣ የተለያዩ የሰውነት ቅርፆች፣ የለማጆች ፍርሃትና ጩኸት፣ በዋና ልብሰ
የሚያማምሩ ሴቶች፣ ሁሉም ጥሩ ስሜት ይፈጥራሉ፡፡ ውስጤን ትንሽ ለቀቅ ሲያደርገኝ ተሰማኝ፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰድኩት፡፡ ወደ ዋናው ከመግባታችን በፊት ሻወር እየወሰድን፣

“ግን ለምንድን ነው፣ ሁሉም ሴቶች በዋና ልብስ የሚያምሩት?“ አልኩኝ፡፡

“ምነው ሁሉንም ወደድካቸው፣ አማሩህ...?“ ማሂ ከአፌ ተቀበለችኝ፡፡

“የምሬንኮ ነው፡፡ ሳሚ እኔ ብቻ ነኝ፣ የአዳም ሁሉ ችግር ነው?”

“ሆ ...፣ እረ እኔ ቤቲ ናት ሁሉንም ልብስ ቆንጆ ምታደርግብኝ እንጂ፣ ልብስ ሴትን ቆንጆ አያደርግብኝም፡፡” ሳሚ የቤቲ ጉዳይን ገና አልጨረሰም፡፡ እኔን አስበልቶ ነጥብ ሊያስቆጥር ሞከረ፡፡ አናደደኝ፡፡

“እረ መጎዝጎዝ...!” አለች ቤቲ፡፡

“ቀላል መጎዝጎዝ! አጉል ልወደድ ባይ! በቃ ሄደን እንዋኝ!”

“ምን..?! እንዋኝ ይላል እንዴ፣ አስለምድሻለው ብለህ ነው ያመጣኸኝ፤ በስነስርዐት አስለምደኝ” አለች ማሂ፡፡ ሰሞኑን ነጭናጫ ሆናለች፡፡ የወደቀ ዛፍ...

“እኮ አስለምድሻለዋ፡፡ ውሃ ገንዳ ውስጥ ሳንገባ ታዲያ እንዴት..፧” ንዴቴን ተቆጣጥሬ መለስኩ፡፡

“ቤቲዬ አንቺ ትችያለሽ ?” :

“እኔም አልችልም ያቡ፤” ፈገግ ብላ፡፡

“በቃ ሳሚ ደግሞ እሷን አስለምዳት”

“ችግር የለውም፤” አለ ሳሚ ፈገግ ብሎ፡፡

“ምን? አንተ ችግር የለውም ትላለህ እንዴ? ልትገለኝ ነው? ለእራሱም አይችልም እኮ፡፡ ያቡ አንተ ነህ ምታስለምደኝ፡፡”

«እረ አታካብዱት ዋና ቀላል ነገር ነው፡፡ የምን እንዲህ መፍራት ነው፡፡ ዋናው ፍላጎት ብቻ ነው፡፡››

“ኧረ... በፍላጎት ቢሆንማ ኖሮ እንደኔ ሚፈልግ አልነበረም፤” አለች ቤቲ፡፡

“የምሬን ነው፡፡ ፍላጎት ያለው አሁን አሜን ይበል፣ በቃ አሁን ለምዶ ይሄዳል፡፡”

“አሜን ማንኦፍ ጋድ፧” አላ ሳሚ፡፡ ተሳሳቁ፡፡ ስሜቱ በአንዴ ወደ ጨዋታ ተቀየረ፡፡ የመዋኛው ገንዳ ጫፍ ጋር ቆምን፡፡

ድንገት ሳይዘጋጁ ዘልዬ ውሃው ውስት ገባሁ፣ ደንግጠው “ዋይ!” ብለው ሲጮሁ ተሰማኝ፡፡ በውስጥ እየቀዘፍኩኝ በሌላኛው ጫፍ ወጣሁ።በመገረም እዛው ጋር ቆመው እያዩኝ ነው፡፡ ወዲያው፣ ውሃው ላይ በጀርባዬ ተኛሁበትና፣ እንደ እንቁራሪት በእግሮቼ እየቀዘፍኩ ተመልሼ ወደነሱ ሄድኩኝ፡፡ በመደነቅ ፈገግታ እየተመለከቱኝ ነው፡፡ ለማስታወቂያ ያደረኩት ነገር በደንብ ሰርቷል፡፡ በደንብ እንደምችል እርግጠኛ ሆነዋል፡፡አሁን ይተማመኑብኛል፡፡ የምላቸውን ተቀብለው ለመተግበር ድፍረት
👍1🔥1
ያገኛሉ በመሰላሉ ላይ ወርደው እንዲገቡ እጄን ዘረጋሁላቸው፡፡ ማሂ ቆይ ቆይ እራሴ እወርዳለሁ አለች፡፡ በየተራ በመሰላሉ እየተንፏቀቁ ወረደው ገቡ፡፡ በአንድ እጃቸው ብረቱን እንደያዙ ቆሙ፡፡

አሜን ያለ በደንብ ይስማኝ፡፡ ዋና ለመልመድ ሶስት ነገሮችን ማወቅና መተግበር ብቻ ነው ሚያስፈገው፡፡ እነሱን ያመነና የተገበረ፣ አሁኑኑ ይችላል።”

“ምንድናቸው እነርሱ?” አለች ቤቲ ለመስማት ጓጉታ፡፡
“በጣም ጥሩ ጥያቄ፣ 1ኛ ውሃውን አትፍሪው፤ 2ኛ ውሃውን እመኚው፤ 3ኛ ውሃውን ምቺው፡፡ ከዛ፣ አለቀ መዋኘት ቻልሽ ማለት ነው፡፡”

“ኧረ ባክህ? ኪ.ኪ.ኪ.. ምን ማለት ነው ውሃውን አትፍሪው፣ እመኚው፣ ምቺው ማለት?” ማሂ ጠየቀች። ሳሚ እየተንቦጫረቀ፣ መሃል ላይ ቆሞ ያዳምጣል፡፡

“አትፍሪው ማለት፣ ለምሳሌ አሁን ያለንበት ውሃ ጥልቀት የት ድረስ እንደሆነ እዩት፤ ሁለታችሁንም አያሰምጥም፡፡ አሁን በእግር ቆመን ነው ያለነው፡፡ ለኔ ደረቴ አካባቢ ነው፡፡ እናንተ ደግሞ ትከሻችሁ
ጋር፡፡ እዩኝ...፤” እንዲያምኑኝ ሁለት እጆቼን አውጥጬ ወደፊት በእግሬ እየሄድኩ አሳየኋቸው፡፡ “አያችሁ አያሰምጠንም፡፡ እንዴት መቆም
እንዳለብን ካወቅን ለምን እንፈራዋለን? ኑ! በእግር እየሄዳችሁ ሞክሩት፡፡” በእጄ ጎተትኳቸው፡፡ እየፈሩ፣ ዋይ እያሉ፣ ሞከሩት።መልሰው ብረታቸው ጋር ሲመለሱ ፈገግ አሉ፡፡ “ስለዚህ፣ ስትዋኙ
ሲያቅታችሁ፣ ቢደክማችሁ፣ ትቆማላችሁ እንጂ አትሰምጡም፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD)

...ደግሞ፣ እኔ አለሁ፤ ስለዚህ እመኑት፣ አትፍሩት። ግልጽ ነው?”በአዎንታ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁልኝ፡፡“በጣም ጥሩ፡፡

አሁን ደግሞ እመኚው ማለት ምን ማለት
እንደሆነ ላስረዳ፡፡ ውሃ ውስጥ ጠፍጣፋ ነገር ይሰምጣል?”

“አይ፣ አያሰምጥም፡፡”

“እንደማይሰምጥ ከልብ ታምናላችሁ?”

“አዎ፣አናምናለን፡፡”

“ስለዚህ እንዳንሰምጥ ሚጠበቅብን ሰውነታችንን እንደጣውላ ጠፍጣፋ ማድረግ ነው፡፡ አይደል?”

“አዎ።”

“ቬሪ ጉድ!”

“አሁን እዩኝ! እጆቼንና እግሮቼን እንደሚንጠራራ ሰው በደንብ ውጥርጥር፣ ግትር ሳደርጋቸው፣ ሰውነታችን እንደጣውላ ይሆናል፡፡ አንሰምጥም፡፡” እንዳልኩት፣ እጆቼን ወጥሬ ዘርጋሁና ወደ
ኋላ ውሃው ላይ ተንሳፍፌ ተኛሁበት፡፡ አላሰመጠኝም፡፡ እንደ ቅጠል ተንሳፈፍኩኝ። በአድናቆትና በአግራሞት ተመለከቱኝ፡፡ልብ በሉ፣እጆቼም እግሮቼም ምንም እያደረጉ አይደሉም፡፡ ውሃውን አምነዋለሁ፡፡አናንተም እንዲህ ውሃውን ማመን አለባችሁ፡፡››
“ኧረ በጣም ያስፈራል ያቡዬ፣” ማሂ እየሳቀች ነው::

“ምን ያስፈራል፡፡ እኔ አለሁ አይደል። የመጨረሻውን ልንገራችሁና እኔ ይዣችሁ ትለማመዳላችሁ፡፡ የመጨረሻው ህግ
ውሃውን ምቺው ነው፡፡ ምን ማለት መሰላችሁ፣ ዋና መንሳፈፍ ብቻ
አይደለም፡፡ በውሀው ላይ መሄድም ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመሄድ
ደግሞ፣ ውሀውን በእግሮቻችንና በእጆቻችን መምታት ወይም መቅዘፍ
ያስፈልጋል፤ ለምሳሌ፣” ብዬ፣ በጀርባዬ ተንሳፍፌ፣ እነሱን እያየኋቸው በእግሮቼና በእጆቼ ውሃውን እየገፋሁት ካጠገባቸው እየራኳቸው አሳየኋቸው፡፡ ለመቻል ባለ ጉጉት ውስጥ አትኩረው ይመለከቱኛል፡፡ ዋና ለመልመድ ጥሩ ፍላጎት እንዳላቸው አረጋገጥኩኝ፡፡ ወዲያው ተመለስኩና፣

“አሁን በተራ በተራ ብረቱን ትለቁትና፣ እኔ እጆች ላይ ተኝታችሁ፣ እንደነገርኳችሁ ትዋኛላችሁ፤” አልኳቸው፡፡ እንዳልኳቸው
አደረጉ፡፡ ከሶስትና አራት ሙከራዎች በኋላ ጥቂት መንሳፈፍ ቻሉ፡፡
“ኧረ ፍጥነት!” እያልኩ አበረታታኋቸው፡፡ ለቅቄያቸው ወደኔ እንዲመጡ
ጋበዝኳቸው፡፡ እያምቦጫረቁ እኔ ጋር ሲቀርቡ፣ ትንሽ እንዲሞክሩ ቀስ ብዬ እሸሻለሁ፡፡ ተንጠራርተው እላዬ ላይ ይለጠፋሉ፡፡ ዞረው እየዋኙ የመጡትን ሲያዩ፣ በደስታ ይፈነድቃሉ፡፡ ፍርሃቱ ለቋቸዋል፡፡ ቤቲ ደፋር ስለሆነች የተሻለ ቶሎ ለመደች፡፡ መላልሰው በደስታ ብዙ ሙከራዎችን አደረጉ፡፡ ሳሚ ለብቻው ሚችለውን ያህል ሲሞካክር ቆየ፡፡ ሳናስበው በጣም ደስ የሚል ቀን አሳለፍን፡፡

“እንዴት ቀላል እንደሆነ አያችሁት?”

“የምር ደስ ይላል፡፡ ሁለት ሳምንት ብንመጣ በቃ::”

“ስለዚህ አሜን አይደል፡፡”

“ኪ.ኪ.ኪ... ኧረ አሜን ነው፡፡ አሁንማ ከሳሚ አናንስም፡፡”እየተበሻሸቅን፣ እየተሳሳቅን ወደ አዳማ ተመለስን፡፡

#አልጓጓም

ዕሁድ እረፋዱ አምስት ሰዐት ነው፡፡ አዳማ ሳፋሪ ሎጅ፣ ጭር ብሏል፡፡ መዋኛ ገንዳው አጠግብ ያለ ወንበር አስተካክለን ተቀመጥን።እብድ ምሽትና አድካሚ ለሊት ነበር፡፡ የረጋውን ንፁህ የመዋኛ ገንዳ ውሃ እያየን፣ ማታ በመጠጥ የደረቀ አንጀታችንን ለማራስ፣ ለሊቱን በስሜት ልፊያ ያንጠፋጠፍነውን ሀይላችንን ለመተካት፣ ሁለታችንም ፓፓያ በማንጎ ጁስ እየጠጣን ነው፡፡ የመልካሙ ተበጀ ሙዚቃ በስሱ ተከፍቶ ይሰማል፡፡

አልጓጓም...
አልጓጓም.....
አ..ል....ጓ....ጓ...ም......አም..
አል-ጓጓ-ም........መኖር በአለም ላይ....

ጠረጴዛው ላይ ያለው የማሂ ስልክ፣
ጥዝ...ዝ...ዝ...ጥ...ዝ...ዝ..፣ እያለ ይንቀጠቀጥ ጀመር፡፡ ስልኩን ሳብ አድርጋ
የሚደውለውን ቁጥር ካየች በኋላ፣ ወደኔ ዞራ በሌባ ጣቷ አፏን ተጭና፣ዝም በል እንደማለት ምልከት ሰጥታኝ፣ ስልኩን አነሳችው፡፡

“ሄለው...” አለች በሚሞላቀቅ ድምፅ፡፡

“ደህና ነኝ፡፡”

ቁርስ እየበላሁ።”

“ደብረ ዘይት።”

“ከሰው ጋር፡፡”

“ማታውቀው ሰው፡፡”

“እንዴ ምነው የፖሊስ ጥያቄ አደረከው?” ድምፅ ሳላወጣ፣ አፌን እያንቀሳቀስኩ ማን እንደሆነ ለመጠየቅ ሞከርኩ፡፡ ጥያቄዬ ገብቷት፣ እርሷም እንደኔው በአፍ እንቅስቃሴ ብቻ፣ ማን እንደሆነ ነገረችኝ፡፡

“አሁን መምጣት አልችልም፡፡”

ማታ ወይም ነገ ነው ምመጣው፡፡” ዐይን ዐይኗን እያየሁ፣ምታወራውንና የፊቷን እንቅስቃሴ ማገናኝት እየሞከርኩ ነው፡፡ ማሂ ቆንጆ፣ ፊቷ በደስታ በርቶ በፈገግታ ነው ምታወራው፡፡

“የምመጣ አይመስለኝም፡፡”

“ነገርኩህ እኮ፣ ከሰው ጋር ነኝ፡፡” ስልኩን ላውድ ሰፒከር ላይ አደረገችው፡፡ የደዋዩ ድምፅ ይሰማኝ ጀመር፡፡

“ከያቤዝ ጋር ነሽ አይደል...?” የአለቃዬ ድምፅ...! በምልክት የነገረችኝ፣ እውነቷን ነበር፡፡ ከምፈራቸውና ከማከብራቸው አለቃዬ ጋር ነው የምታወራው፡፡ ግን፣ እንዴት ከእኔ ጋር እንደሆነች ሊገምቱ
ቻሉ...? ሰው ፈርቼ ባላውቅም፣ እርሳቸው ግን ይከብዱኛል።አከብራቸዋለሁ ሰሞኑን ባለን ሁኔታ ደግሞ የባሰ፡፡

“እንዴ...፣ እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ?” አሁን ድምፅ አውጥታ መሳቅ ጀመረች፡፡

“ንገሪኝ አትዋሺ! ትክክል ነኝ አይደል?”

“ያምሃል እንዴ ሃይሌ? ከማታውቀው ሰው ጋር ነኝ አልኩህ እኮ፡፡”

“እሺ፣ በጣም ደብሮኛል፡፡ ላገኝሽ እፈልጋለሁ።”

“የምመጣ አይመስለኝም፡፡ ሜሪን ካስተዋወኩህ በኋላ፣ እኔ እንዲህ አስፈልጌህ አላውቅም እኮ፡፡ ዛሬ በምን ትዝ አልኩህ?፣ የለችም እንዴ እርሷ?”

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ሰመመን


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ማርታ ወሬ ትወዳለች ። በተለይ የፍቅር ወሬ ከሆነ አነፍንፋ ነው የምትሰማው ። ልማድ ሆኖባት ነው እንጂ፥ በፍቅረኞች መሐል ገብታ ተንኮል ለመሥራት አይደለም። ከትዕግሥት ጋር በዩኒቨርስቲው የመኝታ ክፍል ውስጥ ተደራራቢ አልጋ ላይ ስለሚተኙና አብዛኛውን ጊዜ አብረው ስለሚያሳልፉ የአጭር ጊዜ ምስጢርም ቢሆን ሰርስራ ስለማወቅ ባለመቻሏ ከልቧ በሽቃለች ። ትዕግሥት ከአቤል ጋር የዐይን ፍቅር እንደጀመረች ከጠረጠረች እንኳ ወር ያህል ይሆነዋልው...

“ በእውነት ዋና ነሽ ” ስትል ደገመች ማርታ ፡ “ እኔ ጓደኛዬ ነሽ ብዬ የሆዴን ሁሉ አጫውትሻለሁ ። አንቺ ግን ልብሽ አይያዝም “ ”

ትዕግሥት ተረበሸች ። “ ልብሽ አይያዝም” የሚለው ቃል አስደነገጣት ።

“ እኔኮ ደብቄሽ አይደለም ። ”

“ ደብቀሽኝ ነው እንጂ ! እረ ታዘብኩሽ ዋና ነሽ ” አለች ማርታ አንጀት በሚበላ አነጋገር ።

« “ ማርታ ሙች መደበቄ አይደለም... አንዳንዴ መንገድ ላይ ስንገጣጠም ..ያየኛል በቃ ”

የማርታ የመሬ አንቴናዎች ከመቼውም በላይ ነቁ ። ሕዋሳቶቿ ከትዕግሥት አፍ ሲወጣ ለመስማት ሲጓጉ ለከረለት ነገር ተቁነጠነጡ ።

“ እንዴት ማየት ? ዝም ብሎ ማየት ? ” ስትል አፋጠጠቻት።

“አዎ በቃ...እንዴት ልበልሽ ?” አለች ትዕግሥት ሁኔታው ለገለጻ አስቸግሮአት ” ... ዝም ብሎ ያየኝና ዐይን ዐይን የተገጣጠምን እንደሆን ተሸማቆ ዐይኑን ይሰብራል ” አለች የራሷን ደብቃ ።

ማርታ በልቧ ቀች ። ሰሴሲ ች አብዛኛውን ጊዜ ተወደድን እንጂ ወደድን እንደማይሉ ታውቃለች። ልምዱ አላት ።ማርታና ትዕግሥትን አጋጣሚ በመኝታ ክፍል አገናኝቶአቸው ፥ የትዕግሥት የቀለም ትምህርት ጉብዝና አስተሳሰራቸው እንጂ ጓደኞች ሊሆኑ የሚችሉ አልነበሩም ። በአስተዳደግና በአኗኗር ሁኔታ ብዙ ይለያያሉ ።

ፍቅር ለደብረ ዘይቷ ትዕግሥት እንግዳ ነገር ነው። ፍቅር ተደጋግሞ በተጀመረ ቁጥር አዲስ መሆኑ ባይቀርም ቅሉ
ለመሃል አራዳ አደጓ ማርታ እንግዳ ነገር አልነበረም ።ቀን ከወንድ ጓደኛ ጋር መውጣት ማደር ፤ በተለያዩ የጨዋታ
ቦታዎች ላይ መገኘት ፥ ከማርታ አፍ የማይጠፉ ጨዋታዎች ናቸው ። ትዕግሥትም እኒህን መሳይ የማርታ ምስጢሮች” ስታዳምጥ በመክረሟ በዚህ ዕለት ልብሽ አይያዝም ”
ያለቻትን ለማስተባበል ስትል ፥ ደብቃ የቆየችውን የአቤልን ጉዳይ ለማውጣት ተገደደች።

« ለመሆኑ ስንት ጊዜ ሆነው ? ”” አለች ማርታ ለጥናት የገለጠችውን ደብቴር ጭራሹን ዘግታ።

ምኑ ? ”አለች ትእግስት “ጥያቄው ቢገባትም በአንዴ መመለሱ አስቸግሯአት

“ አአቤል ጋር በዐይን ... ከጀመራችሁ ነዋ ? ” አለቻት ድርቅ ብላ።

ትግሥት የአቤል ስም ሲነሣ የባሰ ድንግጥ አለች ደስታ የቀላቀለበት
ድንጋጤ "

በግምት ስድስት ሳምንት ይሆነዋል ” ካለች በኋላ ወድያውኑ እኔ እኮ እሱ ስለሚያየኝ ነው እንጂ...” አለችና በግዴቸሽነት ትከሻዋን ነቀነቀች።

“ እ ... ሺ? ” አለች ማርታ ጨዋታው በዚሁ እንዳያልቅ በመስጋት ። ትዕግሥት ትክ ብላ ከማየት በስተቀር ምንም አልተነፈሰችም ።

አሥራ አንደኛ ክፍል እያለሁ አንድ መምህር ምን አለ መሰለሽ?

ምን አለ? አለች ትዕግሥት ፡ ለመልሷ ብዙም ያልጓጓች በመምሰል ።

“ መጀመሪያ ለክፍሉ ጥያቄ አቀረበ ። ”
“ ምን የሚል ? ”
“ ፍቅር የሚጀመረው ከየት ነው ? ”
«« ከየት ነው አላችሁ ታዲያ ? ”
እኔ “ ከአካባቢ ወይም ከአቅራቢያ” ብዬ መለስኩ ።

ሌሎችም የመስላቸውን መለሱ " በመጨረጃ መምህሩ ራሱ " ፍቅር የሚጀምረው ከአይን ነው” ብሎ ገላግለን

ትዕግሥት ነገሩ ቢኮረኩራትም አልሣቀችም ። ማርታም አልረካችም ። ከትዕግሥት አፍ መስማት የፈለግችው ሁሉ ቀድማ የምታውቀው ሆኖ ስላገኘችው አዲስ ሚስጥር ለመሰርሰር ሰልተው የቆሙ የቆሙት ህዋሳቶቿ ሳይረዱ ቀሩ።

አይ አንቺ ! ” አለቻት ቆይታ ቆይታ ።
“ እንዴት ?
እንዲሁ ነው !
ትእግስት በመቅለስለስ ዐይነት ትከሻዋን ነቀነቀች።

አቤል ከፍልስፍና መምህሩ የተቀበለውን የጥናት ጽሑፍ ሲሸሸው ሰንብቶ፡በአራተኛው ቀን የግዱን አነሣው
አልጋው ላይ ጋደም እንዳለ ነበር ለማንበብ የፈለገው ። ኮሶ የሚጠጣ ይመስል ፊቱን አጨማዶ ገለጠው የመጀመሪያውን ገጽ ሳያነብ እያገላበጠ ከመሐል ደረሰ ። እንደገና ወደ ኋላ
ተመለሰ ። የራሱ የእጅ ጽሕፈት አስጠላው

• ኤጭ ! ” አለ ፡ በመሰላቸት ድምፅ ። “ አሁን ምኑን ነው የማሻሽለው ? የቻልኩትን ያህል ሠርቻለሁ ፡ በቃ ! ”

ገና ሳያነበው ፡ የሚሻሻል ነገር የለበትም ብሎ ወሰነ ።እጆቹ ሳይታዘዙ የጥናት ጽሑፉን ወረቀት ከደኑ ፡

“ምን ይመጣብኛል?” ሲል አሰበ። እንደ ገና ባልሠራው ተሰቀል የሚለኝ የለ " ያው ወድቆ መባረር ነው ። ይህ ደግሞ
በእኔ አልተጀመረ ለምን ራሴን አስጨንቀዋለሁ ?

ዮናታን በድንገት በሐሳቡ መጥተው ድቅን አሉበት ።ወረቀቱን ተቀብሏቸው ሲወጣ የተናገሩት ቃላት ታወሰው ።

ሐሳብ ውስጥ ገብተህ ወይም ተቻኩለህ ይሆናል እንጂ ፥ አንተ እንዲህ ዐይነት ሥራ እንደማትሠራ እተማመናለሁ

“ ዕዳ እኮ ነው” አለ በሐሳቡ። “እሳቸው ደግሞ ለምን የሰው ችግር አይገባቸውም ? ፍቅር ወጥመድ ውስጥ ለገባ ተማሪ ጥናትና ሥራ ምንኛ እንደሚያስጠሉት ለምን አይረዱልኝም ?...ያውም አቅፎ ወይም ስሞ ወይም ተዳርቶ ማስከን በማይቻል በዐይን ፍቅር ለተለከፈ ተማሪ ! ነገር የጠፋው ቀድሞ ነው ። ትምህርት አስቀምጦ ፍቅር የተጀመረ ዕለት !”

ማፍቀር በአንድ አጋጣሚ የሚከሠት የሕያውነት ነጸብራቅ ሳይሆን ራሱ ሥራዬ ብሎ ጎትቶ ያመጣው ይመስል ገና
የመጀመሪያ ዕለት ትዕግሥት ላይ ያረፉት በልቡ ረገማቸው እለቱ ፡ ያ የተረገመ ይሁን የተቀደሰ ያልገባው ዕለት ፥ በዐይነ ሕሊናው መጣበት ...

ጥቅምት 14 ቀን ፈጸሞ የማትረሳ ። በአቤል አዕምሮ የተቀረፀች እጅ ናት ። በዩኒቨርስቲዉ ውስጥ የመጀመሪያ
ዓመት ተማሪዎች የሚመዘገቡበት ዕለት ነበር ተመዝጋቢዎቹ ለዩኒቬርስቲው አዲስ በመሆናቸው ፥ በአዲስን ስሜት ፊታቸው
በርቶ ምዝገባው በሚካሄድበት መስኮት በኩል ሥርዓት ባጣ ሁኔታ ተሠልፈዋል ።

አቤል ለግል ጉዳዩ ምንባ ክፍል ደርሶ ሲመለስ ከተሰለፉት መሐል ከአንዲት ኮረዳ ጋር ዐይን ለዓይን ተገጣጠሙ
ሁለቱም በቅጽበት ዐይናቸውን ሰበሩ ። አያውቃትም ፤ አታውቀውም ። ለጊዜው ለማያውቃት ልጅ መደንገጡ አላስገረመውም ጥቂት መደፊቱ ከተራመደ በኋላ አስልቶ ዘወር ብሎ ተመለከታት

ጠይም» ናት ፤ ካውያ ያልነካው። ጸጉር ከማጅራቷም ባያልፍ ለማበጠር የሚያስቸግር ዐይነት አይደለም ። ቁመቷ
አጭር ነው ፤ አለባበሷ እንደነገሩ ይመስሳል ፤ ገና ሲያያት አጠገቧ ካሉት ልጃገረዶች ጋር በሆነ ጨዋታ ትሣሣቅ
ነበር ። ስትሥቅ ጉንጮቿ ስርጉድ ይላሉ ። በፈገግታ ጊዜ የሚሰረጉዱ ጉንጮች አቤል ከልጅነቱ ጀምሮ ይወዳል ።

ያያት ዕለት ፡ ያለ ምንም ሐሳብ ውሎ ማታ መኝታው ላይ ዐረፍ ሲል በሰመመን አጭር ወይም ልጅ የሚሰረጉዱ ጉንጮቿን እያሳየች ልታጫውተው ከተፍ አለች ።ያለምንም ማመንታት ተቀበላት ። ቀን ያየውን ቁመናዋንና አለባበሷን በልቡ ደግሞ አደነቀላት ። አንሶላውን ተከናንቦ ዐይኗን ስትጨፍን ስትሥቅ በሰመመን ተመለከታት ። “ እየሣቀች የጉንጮቿን መሰርጐድ በማሳየት ብታስከፍል ዐይኑን
የሚያሽ ያለ አይመስለኝም ።” ሲል በሐሳቡ ደመደመ ። ልቡ ውጥ ገብታ እንድትዝናና እንድትጫወት ። እንድትቦርቅ
እንድትተኛ እንድትነሣ ፥ እንደ ልቧ እንድትሆን ፈቀደላት ።

ንዕግሥት ከዚያን
👍1
ዕለት ጀምሮ በተፈቀደላት መሰረት ልቡ ውስጥ ገብታ ፥ እግሮቿን አኮራምታ ተቀመጠች ፤ ውላ
ስታድር ተንፈራጣ ተቀመጠች ። ስታሰልስ በጀርባዋ ጋደም አለች ። ስትከርምም ጭራሹን ሐሳብዋን ጠቅልላ ተኛች ።

መጀመሪያ በአቤል ልብ ወስጥ ትምህርቱና ትእግስት ጸብ ሲፈጥሩ አቤል ዳኛ ሆኖ " " ዕረፉና ተቀመጡ ለሁለታችሁም ይበቃል አላቸው ጠባቸው እየከረረ መጥቶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ አቤል በትምህርቱ ፈረደና
ትዕግሥትን አነገሣት . . .

.. ያን ዕለት ነው ነገር የጠፋው አለ አቤል በልቡ ደጋግሞ በሃሳብ ወደ ኋላ ብዙ አተጓዘ በኋላ።

አንዳች ነገር የገፈተረው ይመስል ትስፈናጥሮ ከመኝታው ላይ ወረደ ። ወዴት እንደሚሔድ ሳያስብ ነበር የተነሳው ጫማውን አደረገና ክፍሉን ለቆ ወጣ ወዴትም ይሁን ሰው ወዳለበት ትእግስትን ሊያይ ወደሚችልበት የሚነዘንዝ ሕሊናውን ለማሸነፍ ትእግስትን ማየት አለበት ከዚያ ዕለት ጀምሮ ብቸኝነቱን መሸሽ እሚችለው ትእግስት
ላይ ዐይኑን በማሳረፍ ሆነ።

ከመኝታ ክፍሉ ወጥቶ ደረጃውን ሲወርድ እስክንድር ማንደፍሮን አገኘው።

“ ታዲያስ ኣቤል ፥ ወዴት ነው ምትሔደው ? ””
“ እስኪ መጻሕፍት ቤት ልድረስ ብዬ ነበር እሱን ሲያይ በቅጽበት የመጣለት ሐሳብ ነበር ። በመቀጠልም ያንን የጥናት ጽሑፍ መምህሩን ላለማስቀየም ብዬ እንደገና ልስራው ሞከርኩ ነገር ግን ገና ወረቀቱን ስገልጠው ያቅለሸልሸኛል አለው ።

“ በርታ እንደምንም መወጣት ነው” አለ እስክንድር ለማበረታታት ያህል ፡፡

“ እሱማ የት ይቀራል ! ” አለ አቤል ፡ የውስጥ ስሜቱን ለመግለጽ በሚሞክር የደከመ አነጋገር።

“ በል እንግዲህ ” ብሎት እስክንድር ሽቅብ ደረጃውን ወጣ ። አቤልም ቁልቁል እየወረደ የእስክንድርን አረማመድ ዘወር ብሎ ተመለከተ።ሁለት ሁለቱን ደረጃዎች ነበር በአንድ እርምጃ የሚመጣቸው ።

አቤል በማያስደንቀው ነገር በመደነቅ ትክ ብሎ ተመለከተው ።

💥ይቀጥላል💥
👍2
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

ሜሪ፣ ቆንጅዬ የማሂ ጓደኛና የመስሪያ ቤታችን ሰራተኛ ናት።በቁንጅና አይተናነሱም፡፡ ሜሪ ግን፣ በእድሜ ልጅ ነች። ገና እንቡጥ፡፡ልጅነቷ ተጨማሪ ውበት ሆኗታል። ማሂ አንዳንዴ፣ በአንድ ቤትማ ሁለት ንግስት አይኖርም እያለች ትቀልዳለች፡፡ እኔን ጨምሮ፣ ብዙ ወንዶች ዐይናችንን ሜሪ ላይ ጥለንባታል፡፡ አለቃዬን ግን በፍፁም አልጠረጠርኩም ነበር፡፡

“እሱን ማን ጠየቀሽ? አሁን አንቺን ነው ማግኘት የፈለኩት፡፡”አለቃዬ እንደመቆጣት አሉ፡፡

“ምነው አልሰጥም አለችህ እንዴ?” ብላ ክትክት ብላ ሳቀች፡፡

“ስነ ስርዐት! እንግዲህ አትጨማለቂ፡፡ ስንት ሰዓት ልምጣና ልውሰድሽ?”

“የአንተ መምጣት አያስፈልገኝም፡፡ በትራንስፖርት እመጣለሁ።ከመጣሁ እደውልልሃለው። ቻው።” መልስ ሳትጣብቅ ስልኩን ዘጋችው፡፡ፊቷ በደስታና በድል አድራጊነት በርቷል እኔ የምፈራቸውና ማከብራቸው አለቃዬን፣ ፀሃፊያቸው እንዴት እንዲህ ተዳፈረቻቸው...? ከስራ ውጪ ሌላ ግንኙነት አላቸው ማለት ነው? ስልኩን እንደዘጋች፣ ፋታ አልስጠኋትም፡፡ በጥያቄ አጣድፋት ጀመር፡፡
“አንቺ፣ ጋሽ ሃይሌን፣ አለቃችንን ነው እንዲህ እየተመናቀርሽ ምታዋሪያቸው..?” ዐይኗ ላይ አፍጥጬ ጠየኳት፡፡

“አዎ፡፡ ምን አጠፋሁ?”

ትንሽ እንኳ ክብር የለሽም...? አለቃሽ ናቸውኮ፡፡ ሌላው ቢቀር አባትሽ ይሆናሉ፡፡ እላያቸው ላይ እኮ ነው ስልኩን የዘጋችው። ሲጀመር እንዴት ደወሉልሽ፣ ትግባባላችሁ?”

“ታዲያ ባንግባባ ምን ያስደውለዋል?፡፡ የዛሬን አያድርገውና ከስራ አይጠፋም ነበር።”

“ምን ማለት ነው? እስቲ በደንብ አስረጂኝ፤ ምንድን ነው ማላውቀው ነገር?”

“ከኔ ስር አይጠፋም ነበራ...! ከኔ ጋር መሆን ኩራቱ ነበር።ከስራ ሲወጣ፣ ከተማውን ሚዞረው እኔን ይዞ ነበር :: ቅዳሜና እሁድ ደግሞ፣ ሶደሬ፣ ላንጋኖ፣”

“ትዳር የለውም እንዴ?” እኔም እንደሷ አንተ ማለት ጀመርኩ።

“ባለትዳር አይዝናናም?” እየሳቀች መልሳ ጠየቀችኝ፡፡ ይሄን አታውቅም ቂል ብላ፣ ምትስቅብኝ መሰለኝ፡፡

“አይ፣ በጣም ጀንትል ነው፣ እንደምታወሪው አይነት ሰው
አይመስልም፡፡”

“ኪ....ኪ...ኪ..!” እግሮቿን እያነሳች፣ በረጅሙ ሳቀችብኝ፡፡

“ምነው ሳቅሽ?”

“ሃይላን ነው፣ ጀንትል ያልከው፣ ሴት ካየ ሳይመርጥ ሚልከሰከስ፣ እዚህ ግቢ ያሉትን ሴቶች ሳያማርጥ ካልተኛሁሽ የሚል፣ስሜቱን መቆጣጠር ማይችል ዝርክርክ? እኔን ሚያናድዱኝና ሚያበሳጨኝ ሴቶቹ ናቸው። ጓደኛዋን እንደተኛት እያወቀች፣እግራቸውን ከፍተው አብራውት ሚተኙት፡፡”

“ማለት፣ ጋሽ ሃይሌ፣ ከስታፎች ጋር ይወጣል እያልሽኝ ነው?”

“እንዴ...፣ አገር ያወቀውን ፀሃይ የሞቀውን አንተ አላውቅም እያልከኝ ነው?”

“እውነቴን ነው፤ እኔ ምንም አላውቅም፡፡”

“ስም ልጥራልህ እንዴ...፣ ፌቨን፣ ሳራ፣ ቤቲ፣ አሁን ደግሞ ተረኛዋ ሜሪ ነች፡፡ አሁን ከእርሷ ጋር ከንፏል።” ብስጭት እያለች ነው፡፡

“ቆይ፣ ሚስቱን አይፈራም እንዴ?"

“ሚስትና ልጆቹ አዲስ አበባ ናቸው። ማን ያየኛል ብሉ እዚህ ይንዘላዘላል እንጂ፡፡”

“በስማም! ቢያንስ አይደብረውም...?”

“አይደብረውም አልከኝ...? አሁን ጭራሽ ሜሪን ሚስቴን ፈትቼ ካላገባሁሽ እያላት ነው፡፡ ደግሞ መጥታ ትነግረኛለች።”

“እና ሜሪ አመነችው...?”

“አዎና፡፡ የሆነች ጅል፣ ከርፋፋ፡፡ ቀላል አምናዋለች፡፡ ደሞ ድንግል ናት፡፡”

“እና ድንድልናዋን ሰጠችው...?

ወጣችለት...?” ምሰማው ሁሉ
ማመን አቅቶኛል፡፡

“እንጃባቷ...! ሰጥታው ነው ሚሆነው፡፡ የሆነች ነፈዝ፡፡” በጣም የልብ ጓደኛሞች ነበር ሚመስሉኝ፡፡ ከአነጋገሯ ግን ሌላ ነገር ተሰማኝ፡፡

“እኔ ምልሽ፣ አንችም ተነካክተሽ ነበር እንዴ? በጣም የቀናሽ ትመስያለሽኮ፡፡"

“ማ...? እኔ ማሂ ቆንጆ ከዚ ሼባ ጋር? በስማም አንተ!”

“አይ እንደምታወሪለት ከሆነ፣ ሰውየው የሆነ ያሰራው ነገርማ አለው፡፡”

“ብወደውማ፣ መጀመሪያውኑ እሷን አላሰተዋውቀውም ነበር፡፡”

“እሺ ግን እንዴት ከአንድ አንድ ከያቤዝ ጋር ነሽ' ብሎ ሊገምት ቻለ?”

“እኔንጃ፡፡ ምንአልባት፣ መጀመሪያ የመጣህ ሰሞን፣ “ለመጀመሪያ
ግዜ ደስ ሚል ወንድ ልጅ ቀጠራችሁ ብዬው ነበር መሰለኝ፡፡ አልፎ አልፎ፣ ያምራል ያልሽው ልጅ ተመቸሽ?' እያለ ይቀልድብኛል፡፡ ከዛ ተነስቶ ይመስለኛል።”

“አ.ሃ... ለዛ ነው? ሌላስ ምን ያውቃል? ሁሉንም ነገር ነግረሽዋላ?”

“ያምሃል እንዴ? ምን ብዬ ነው ምነግረው?” የተቆጣች ለመምሰል ሞከረች፡፡ ፊቷ ግን በፈገግታ እንደተሞላ ነው፡፡ ውስጤ በንዴት ሲጨስ እየተሰማኝ ነው፡፡ ቀልዳብኛለች! ሚስጥር ይሁን
ተባብለን ነበር፡፡ አሁን ምንድነው ሚሆነው? ምንድነው ማደርገው?
በሃሳብ ጭልጥ አልኩ፡፡

“ተጫወት እንጂ! በሃሳብ ነጎድክ።”

“ግን ቢያንስ ስለሰውየው ይሄን ሁሉ ነገር እንዴት አልነገርሺኝም...?” የሆነች ጨዋታ እንደተጫወተች እየተሰማኝ ነው፡፡
“ግቢው ውስጥ ሁሉም ሚያውቀው ስለሆነ፣ አንተም ምታውቅ መስሉኝ፡፡”

“እርግጠኛ ነሽ፣ ለዛ ብቻ ነው ያልነገርሺኝ?”

“እንዴ...! ሌላ ምን ምክንያት ይኖረኛል?”

“እሱንማ አንቺ ነሽ ምታውቂው፡፡”

ስልኬ መዝፈን ጀመረች፡፡ ከሱሪ ኪሴ ውስጥ አውጥቼ ተመለከትኩ፡፡ ሳምሶን ነው፡፡ ስልኩን አነሳሁት፡፡

“ጎረምሳው፣ ምነው በእሁዱ ድምፅህን አጠፍህ? ማታ ይዘህ . ነው እንዴ ያደርከው...?

“እንደውም ደብሮኝ ልደውልልህ ስል ነው የደወልከው፡፡”

“ምነው? ምን አጋጠመህ ወጣቱ...?”

“ዝም ብሎ ድብርት ቢጤ ነው፡፡ የት ነህ ልምጣ...?”

“እቤት ነኝ ና።”

“መጣሁ ጠብቀኝ፡፡” ስልኩን ዘጋሁት፡፡

“ምን መሆንህ ነው? ምን እያደረክ ነው?” አለችኝ ማሂ እንዳኮረፈች ሆና።

“መሄድ አለብኝ፡፡ የማላውቀው ነገር ውስጥ ገብቼ እየዋኘው እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ቢያንስ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማወቅ አለብኝ፡፡

ተነሺ እንሂድ፡፡”

የጠጣነውን ጁስ ሂሳብ አየሁት፡፡ ሰማንያ ስምንት ብር፡፡ መቶ ብር አስቀምጬ፣ መልስ ሳልጠብቅ ተነሳሁ። ማሂም ተከትላኝ ተነሳች፡፡

ከግቢው በር ላይ ካለው መኪና ማቆሚያ ጋር ሄድን የቆመችው ቪትስ መኪናዬ ውስጥ ገባን፡፡

“የት ላድርስሽ?”

“አንተ የት ነው ምትሄደው?”

“ሳወራ እየሰማሽኝ አልነበር? ሳምሶን ጋር ነዋ፡፡” ተነጫነጭኩ፡፡

“እኔም አብሬህ እሄዳለሁ።”

“አይሆንም!” አምባረኩባት፡፡

“ለምን?”

“ብቻዬን ላናግረው ፈልጋለሁ፡፡”

“ቆይ ምንድነው እንዲህ የቀያየረህ? ምንድነው ይሄን ያክል ያናደደህ?”

“ከዚህ በላይ ምን ታደርጊኛለሽ? ምን አስበሽ ነው ይሄን ሁሉ ሚስጥር እስካሁን የደበቅሽኝ?” መኪናዬን አስነስቼ ከግቢ እየወጣሁ።

“ሆን ብዬ አልደበኩህም፡፡ ምታውቅ ስለመሰለኝ ነው አልኩህ እኮ!”

“ሃ...ሃ...ሃ...! እረ ባክሽ? አንቺ ወሬ ደግመሽ የምታወሪ ልጅ፣ገና ለገና ሰምቶ ይሆናል ብለሽ፣ ይሄን ሁሉ ወሬ ዝም አልሽ?!. ጥሩ ቀልደኛ ሆነሻል ባክሽ፡፡ አሁን የት ላድርስሽ?”

“በታክሲ መሄድ እችላለሁ፡፡ እዚህ ጋር አውርደኝ፡፡”

“እሺ!”

ንዴት በውስጤ እየፈላ ነው፡፡ ሳላንገራግር የመንገዱን ዳር ይዤ አቆምኩላት፡፡ ቦርሳዋን ከኋላ ወንበር አንስታ ተመናጭቃ ወረደች፡፡በቀጥታ ወደ ሳሚ ጋር ሄድኩና ተያይዘን ብቻችንን ስንሆን
የምናዘወትርበት ቤት ሄድን፡፡ ቢራ እየጠጣን ፑል መጫወት ጀመርን፡፡
ለወትሮው ስንጫወት በመበሻሸቅ እንሳሳቃለን፡፡ ዛሬ ቢቀልድብኝም
መልስ አልሰጠውም፡፡ ውስጤ ነገር ገብቷል፡፡ ማሂ የነገረችኝን ነገር
👍6
አኝካለሁ፡፡ ሶስት ጨዋታ እንደተጫወትን፣

“ምሳ እንብላ። እራበኝ፤” አልኩት፡፡

“ኦኬይ፤ ጨዋታው ብዙም አልጣመህም ነበር፡፡”

“እ.። ትንሽ ነገር ገብቶኝ እሱን እያመነዠኩ።”

“ምንድነው? ምን ተፈጠረ?”

“ምን ያልተፈጠረ ነገር አለ!” ብዬ ስለ አለቃችን ማሂ የነገረችኝን አወራሁለት፡፡ ምንም አዲስ ነገር እንዳልሰማ ዝም ብሎ አደመጠኝ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ስምንት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) ሜሪ፣ ቆንጅዬ የማሂ ጓደኛና የመስሪያ ቤታችን ሰራተኛ ናት።በቁንጅና አይተናነሱም፡፡ ሜሪ ግን፣ በእድሜ ልጅ ነች። ገና እንቡጥ፡፡ልጅነቷ ተጨማሪ ውበት ሆኗታል። ማሂ አንዳንዴ፣ በአንድ ቤትማ ሁለት ንግስት አይኖርም እያለች ትቀልዳለች፡፡ እኔን ጨምሮ፣ ብዙ ወንዶች ዐይናችንን ሜሪ ላይ ጥለንባታል፡፡ አለቃዬን ግን በፍፁም አልጠረጠርኩም…»
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

አልደነቀውም፡፡ጭራሽ፣ወሬ ሊያስቀይረኝ ይሞክራል። እርሷ ጋር ደውሎ፣ በስልክ ስለኔ ያወሩትን ነገር ነገርኩት፡፡

"ጠብቄው ነበር!”

“ምኑን?”

“ይሄንን ነዋ፡፡ ልጅቷ ነገሯ አላማረኝም ነበር፡፡”

እንዴት?”

“በቃ አለባበሷ፣ ቢሮህ መመላለሷ፣ ብቻ ነግሬህ ነበር፡፡”

“ምን ብለህ?”

“ቀስ በል! አትቸኩል፡፡ የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል!' ብዬ ነግሬህ ነበር፡፡”

“እና ማሂ ያለችው እውነት ነው፡፡ ሰውዬው እንዲህ ያደርጋል?”

“ወንድሜ፣ ሰውየው በተወለደበት ቀዳዳ ተለክፏል፡፡ መሞቻውም እዛው እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ ካ...ካ...ካ...፡፡ በዚህ እድሜ፣ሚስትና ልጆቹን አስቀምጦ ግቢ ውስጥ ያሉትን ሴቶች ሁሉ አትንኩብኝ ማለት...፣ እንደውም ደግ አደረክ! አንተ ወጣት ነህ፣ አላገበህም፣
መዝናናቱም፣ ሁሉም ባንተ ያምራል፡፡ እርሳው ባክህ፡፡ እንደውም ምሳችንን በልተን ሶደሬ እንሂድና ፈታ እንበል፡፡ ማሂንም ይዘናት እንሂድና ስትደጋግማት ታድራለህ፡፡ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም፡፡
ካ...ካ...ካ...”

“ትቀልዳለህ አንተ፡፡”

“የምሬን ነው፡፡” አሁን እኔም በአለቃዬ ድርጊት መናደድ ጀምሪያለሁ፡፡ እልህ እተሰማኝ ነው፡፡

“እሺ ደውልላት፡፡”

ለማሂ ደወለላት። አታነሳም፡፡ የኔን መኪና አቁመን በሱ መኪና ሶደሬ ሄድን፡፡ በፍልውሃ ታጠብን፣ እኔ ዋኘሁ፡፡ ሶደሬ ብቻችንን ስንመጣ እንደሚያደርገው፣ በሲጋራው ምትክ ሺሻ አጨስ፡፡ ወደ መዋኛው ገንዳ ተመልስን ዶሮ አሩስቶ አዘን በቢራ እያወራረድን በላን፡፡ ሰውዬው ለሰው ያለው ንቀትና ድርጊቶች አበሳጭተውኛል። የሳሚ አይዞህ
ሲጨመርበት፣ ውስጤ ተጋፈጠው ተጋፈጠው እያለኝ ነው፡፡ “ድርጅቱ
የቤተሰቡ ሀብት ቢሆን ሰራተኞቹንም የግል ንብረቱ አደረጋቸው እንዴ?፣
ቀጠራቸው እንጂ አላገባቸው...፣ ደግሞ አንዷ ብትበቃውስ፣ ሁሉን አትንኩብኝ፣ ጭራሽ የጣልኩትንም አታንሱ..? ቅሌታም! ደስ ያለኝን አማርጣለሁ፡፡ እንደውም፣ ማሂንም ጨምሬ እልሁን አስጨርሰዋለሁ።”ለራሴ አልኩኝ፡፡ ማታ እቤት ስገባ ምሽት ሶስት ሰአት አልፎ ነበር፡፡ደክሞኝ ስለነበር ወዲያው እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

የተፈጠረውን ነገር አዕምሮዬ ሊረሳው አልቻለም፡፡ የሆነ ድራማ እየተሰራብኝ እንደሆን አሰላስላለሁ፡፡ “የት ነሽ...? ከማን ጋር ነሽ...? ካልተገናኝን...?” ያለጥርጥር ከሰውየው ጋር ግንኙነት ነበራቸው፡፡ያለምክንያት እንደዛ አላንጓጠጠችውም፡፡ ሰውዬው ከእርሷ ጋር ከርሞ፣ እንደዘበት አሽቀንጥሮ በሜሪ ተክቶ አቃጥሏታል፡፡ ለዛ ነበረ ሜሪን ጅል፣
ነፈዝ እያለች ስታጣጥላት የነበረው፡፡ መጫወቻ ኳሷ አድርጋ፣ አለቃዬን
በኔ እያስቀናችና እያበሸቀችው ነበር፡፡ እኔ ጅሉ፣ እንደፈለገችው ተወንኩላት፡፡ ወይኔ ተኩቻው! አጠምዳታለሁ ብዬ ሄጄ፣ የእርሷ ወጥመድ ውስጥ ሰተት ብዬ ልግባላት? ፀባዩን የቀየረብኝ ይሄን አውቆ
ነበር ለካ..። ግን ቀንቶ ነው? ወይስ አሁንም ይፈልጋታል..? ወይኔ፣ ተኩቻው!! እቺ ብሽቅ እንዲህ ትጫወትብኝ፡፡

ስራ መሄድ ያስጠላኝ ጀምሯል። ግን እንደምንም እመላለሳለሁ፡፡ ተነሳሽነቴምና ትኩረቴም ከሞተ ቆይቷል። ከአለቃዬም ሆነ ከሌላ ሰራተኛ፣ ምንም ያየሁት አዲስ ነገር የለም፡፡ ውስጤ ግን እንደ ክረምት
ቀዝቅዟል፡፡ ተኮማትሯል፡፡ ሳሚ ቢሮ እየመጣ ሻይ እንድንጠጣ ይዞኝ
ይወጣል፡፡ እንደበፊቱ መሳቅ መጫወቴ ጠፍቷል። ውስጤ መጥፎና አስጨናቂ ሃሳቦችን እየመረጠ ያመነዥጋል፡፡ ስትስልልህ ነበር የከረመችው፤ ሰውየው ሊያጠቃህ አድፍጧል!' እያለ ጭንላቴ
ያስጨንቀኛል፡፡ አሁን፣ ለጨዋታዎች ስሜት አልባ ሆኛለሁ፡፡ ማሂም ማኩረፌን ስታይሉ ፣ ቢሮዬ ተመላልሳ፣ ይቅርታ ጠየቀችኝ፡፡ ሻይ እንድንጠጣ ጠየቀችኝ፡፡ አይሆንም አልኳዋት፡፡ እንደውም፣ ሁለተኛ
ቢሮዬ እንዳትመጣ፣ ላገኛት እንደማልፈልግ አምርሬ ነገርኳት፤ ቢሮዬ
መምጣት አቆመች፡፡

ከግዜ ወደግዜ ያለ በቂ ምክንያት መናደዴ፣ መበሳጨቴ እየተባባሰ መጣ፡፡ ስራ ስለመልቀቅ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ከዚህ በፊት ስራ በማቆሜ ምክንያት ያደረስኩትን ጉዳት በማስታወስ ውስጤን እንዲረጋጋ ታገልኩት። ስራዬ ግን እንደቀደመው አስደሳች አልሆን አለኝ፡፡ ከነ ሳሚ ጋር ወጥቼ መዝናናትን አቆምኩኝ፡፡ በምትኩ ደብረዘይት እየተመላለስኩ ጫት በመቃም ከድባቴዬ ለመሸሽ ሞክራለሁ፡፡ በተደጋጋሚ ምቅምበት ጫት ቤት አሌክስና ሃብታሙ ሚባሉ ጉደኛሞችን ተግባባሁ፡፡ አሌክስ
ሃብታሙን ዶክ እያለ ይጠራዋል። አሌክስ በጣም ፈጣን፣ ተጫዋችና ከሰው ጋር መግባባት ደስ ሚለው ሰው ነው፡፡ ቀልድ ሲያወራ አጠገቡ የተቀመጡ ሁሉ እንዲሰማው ጮክ ብሎ እንድናዳምጠው በዐይኑ እየጋበዘ ነው፡፡

“ትናንት ማታ የተዋወኳት ቺክ ውበት!፣ ወይኔ...!” ብሎ አሌክስ ለሁላችንም እንደሚያወራ በየተራ ተመለከተን፡፡

“ስንት ሰዓት? ትናንት እዚህ አብረን አልነበርን?” ሃብታሙ ጠየቀ፡፡

“ከዚህ እንደወጣን፣ ጨብሲ ሳንል ጥለኸኝ ላሽ አላልክም?”

“እ...፣ እሺ፡፡”

“የጨብሲ ስላልነበረኝ፣ በወክ ልሰብረው ብዬ ስዞር፣ የሆነች ልዕልት ምትመስል ቺክ አላገኝም፡፡ ወይኔ..፣ ወይኔ..፣ ወይኔ ዐይን! ስታያት በድንጋጤ ደንዝዘህ ትቀራለህ፡፡” ሲያወራ በመደነቅ ግንባሩን
ይዞ እያወዛወዘ ነው፡፡

“እሺ፡፡ ከዛስ ከምን አደረስካት ታዲያ?”

“በስማም ፣ ሞትኩባታ! ጭውቴው ደግሞ እንዴት ስክት ስክት እንዳለልኝ፡፡ ነገረ ስራዬ ለራሴ ገርሞኝ፣ እቤት ከገባሁ በኋላ ስስቅ ነበር።”

“ወሬ አታጣ ! ድሮስ ምላሳም አይደለህ? ምን ብለሃት ነው፣እንዲህ የተገረምከው?”

“ድንገት እጇ ላይ ተጠምጥሜ፣ 'የኔ ልዕልት መሳይ፣ በናትሽ ምሪኝ በናትሽ?” ብዬ ስለምናት፣ መጀመሪያ “ምን ሆንክ?” አለችኝ ደንግጣ፡፡ 'ይኼን ውብ ዐይንሽን ሳይ፣ የእኔ ዐይን አፍሮ ነው መሰል
አላይ አለኝ፣ ብዥ አለብኝ፡፡ ዐይኔን ልጨፍነውና፣ እባክሽን ምሪኝ?” ስላት በሳቅ ሞተች?!” ብሎ ሲስቅ፣ ሁላችንም በድርጊቱ አብረነው ሳቅን፡፡ አሳሳቁ ሰው ላይ ይጋባል፡፡ የዐይኖቹን ትንንሽነትና በራሱ ላይ መቀለዱ ደግሞ፣ የበለጠ እንድንስቅ አደረገን፡፡ ስግባባቸው፤ ሃብታሙ፣ የእንስሳት ሃኪም እንደሆነ አወኩ። አሌክስ ደግሞ የተገኘውን ተባራሪ ስራ ሚስራ አፈ ቀላጤ።

አንድ ቅዳሜ ምሽት፣ አሌክስ ወጥተን የጨብሲ አንድ ሁለት ካልጋበዝኩህ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ድርቅ አለብኝ፡፡ እሺ ብዬው አብረን ወጣን፡፡ እየጠጣን በአስቂኝ ጨዋታዎች የታጀበ ደስ ሚል ምሽት
አሳለፍኩ፡፡ እርሱ ልጋብዝህ ብሎ ይዞኝ ወጥቶ፣ ሂሳቡን ጓደኛው ሃብታሙ ከፈለ፡፡ ስልክ ተለዋወጥን፡፡ ጓደኛሞች ሆንን፡፡ አሌክስ በቀላሉ ጎትቶ ከነሱ ጋር ቀላቀለኝ፡ከነሱ ጋር ስሆን፣ ከአስጨናቂ ሃሳቦቼ
እረፍት ስለማገኝ እኔም ደስተኛ ሆንኩ፡፡ ቅዳሜና እሁድ ውሎና አዳሬ ቢሾፍቱ ሆነ፡፡ ገና ሰኞ ስራ ስገባ ቅዳሜ ትናፍቀኛለች፡፡ ከነማሂ ጋር ካሳለፍኩ፣ ስድስት ሳምንት አለፈኝ፡፡ ሳሚ በተደጋጋሚ በአካልም በስልክም ምነው ጠፋህ ሲለኝ፣ ቢሾፍቱ የራሴን ስራ ለመጀመር ስላሰብኩ፣ ቅዳሜና እሁድ ያን ለማመቻቸት እዛ እንደማሳልፍ ነገርኩት።
ምን ስራ ልትጀምር ነው?' ሲለኝ፣ ሲያልቅ ብታየው ይሻላል፤ አልኩት፡፡ እሺ ብሎ ተወኝ፡፡

ከእንቅልፌ ስነቃ ከንጋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ማታ ስጠጣ ያደርኩበት ጭንቅላቴን ይወቅረኛል፡፡ ከፍተኛ ድካምና ድባቴ እየተሰማኝ ነው፡፡ የሰውነቴ መዛል ከእንቅልፍ የተነሳሁ ሳይሆን፣ ሃያ አራት ሰዓት ካለረፍት ስስራ ያደርኩ ነው ሚመስለው፡፡ ስራ መሄድ እንዳለብኝ ሳስብ እንባዬ መጣ፡፡ የፈለገው ይምጣ ብዬ
👍41
ተመልሼ ተኛሁ፡፡እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን አልቻለም፡፡ 'መቅረት አብዝተሃል፣ ለጠላቶችህ ማጥቂያ መሳሪያ እራስህ እያቀበልካቸው ነው፤'፣ እያለ ጭንቅላቴ
ጠዘጠዘኝ፡፡ ቀርቼም ስላም ከሌለኝ ብዬ ቅዳሜና እሁድ በለበስኩት ልብስ
ስራ አርፍጄ ገባሁ፡፡ ላለባበሴ ትኩረት መስጠት አቁሚያለሁ። ትንሽ እንደተቀመጥኩ ማሂ ቢሮዬ ገባች፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) አልደነቀውም፡፡ጭራሽ፣ወሬ ሊያስቀይረኝ ይሞክራል። እርሷ ጋር ደውሎ፣ በስልክ ስለኔ ያወሩትን ነገር ነገርኩት፡፡ "ጠብቄው ነበር!” “ምኑን?” “ይሄንን ነዋ፡፡ ልጅቷ ነገሯ አላማረኝም ነበር፡፡” እንዴት?” “በቃ አለባበሷ፣ ቢሮህ መመላለሷ፣ ብቻ ነግሬህ ነበር፡፡” “ምን ብለህ?” “ቀስ በል! አትቸኩል፡፡ የጅብ ችኩል…»