#ሰው_መሆን_ምንድን_ነው???
..እናልሽ ቆንጅቴ
የሆነ ዕለት ማታ
ገና አይኗ ያልበራ - የውሻ ቡችላ
ከእናቷ ተነጥቃ - መንገድ ዳር ተጥላ፣
ያውም በክረምቱ
ያውም በምሽቱ፣
እናቴን፣
ሙቀቴን፣
ህይወቴን እያለች
ቱቦ ስር ተኝታ - ታለቃቅሳለች፡፡
ምናልባት ሌሊቱን
ዝናብ ከዘነበ - ጎርፉ ይወስዳታል
ጎርፍ ካልወሰዳት
ራቱን ፍለጋ የወጣ ቀበሮ - ራት ያደርጋታል፡፡
ይህንን ስታይ - መኖር ይገርምሻል
ህይወት ግን ምንድን ነች?- ያፈላስፍሻል፡፡
ደግሞ በሌላ ቀን
አያቴ 'ሚሆኑ - እድሜ ጠገብ ባልቴት
በጠራራ ፀሐይ - ጥላ በሌለበት፣
ከአካላቸው ሚገዝፍ - የእንጨት ክምር አዝለው
ገዢ ይመኛሉ - ገንዘብ ተስፋ አድርገው፡፡
አንዲት ወጣት መጥታ - እየተቻኮለች
እንጨቱን ለመግዛት - ባልቴቷን ጠየቀች፤
“ስንት ነው?” ጠየቀች ወጣቷ
“ሃያ ብር” መለሱ አሮጊቷ፣
“ቀንሱልኝ ማዘር?”
“አስራ ስምንት አርጊው”
“አስራ አምስት ልውሰደው?”
“አላነሰም ልጄ?”
“ይህንም ማደርገው- ከምዞር ብዬ ነው!”
“በ...ይ እሽ ውሰጅው”::
ይታይሽ እንግዲህ
ሌሊቱን በሙሉ - የተጓዙበትን
መቼም ላይቃኑ - የጎበጡበትን፣
ከአራዊት ጋር ታግለው - ያመጡትን እንጨት
በአንድ ቢራ ዋጋ - አስራ አምስት ብር ሽጡት፡፡
አስራ አምስት ብር ብቻ!!!
አየሽ ያቺ ወጣት የ'ሷ ድካም እንጅ የባልቴቷ ኑሮ
አላስጨነቃትም
የምታወጣቸው አምስት ብሮች እንጅ - የአሮጊቷ ድካም
አላሳሰባትም፡፡
ይህንን ስታይ እንባ ያስወጣሻል
“መተዛዘን የታል?” ግራ ያጋባሻል፡፡
ትላንትና ደግሞ
በአንድ ቴሌቪዥን - ሰበር ዜና አይቼ
ሲያስታውከኝ አደርኩ - ከእንቅልፍ ተፋትቼ፤
ምን አየሁ መሰለሽ :-
አንድ የሰዎች ቡድን - ሰዎችን አግቶ
ሁሉንም በአንድ ላይ - ጠባብ ቤት ውስጥ ዘግቶ፣
እንደ በቆሎ እሸት - እያንከባለለ
ከነህይወታቸው - በእሳት አቃጠለ፡፡
በስመ አ..........ብ!!!
ይህንን ስታይ ህይወት ያስጠላሻል
የሰው ልጅ ምንድን ነው?' ያወዛግብሻል::
ታዲያ ግን አለሜ፤
ስንቱን ጉድ አይቼ፣
ስንቱን ጉድ ሰምቼ፣
በብዙ ቆስዬ፣
በብዙ ነድጄ፣
ነድጄ
ነድጄ........
አንቺን እንዳገኘሁ
ያስከፋኝን ሁሉ በአንዴ ረሳውና-
«ይህች ዓለም ጣፋጭ ነች - ቆንጆ ነች!› እላለሁ፡፡
እውነቴን ነው ምልሽ
አንቺን እንዳገኘሁ፡-
ባገባኋትና - አይኔን በአይኔ አይቼ
እስከፍፃሜየ - በኖርኩ ተደስቼ!
እያልኩ አመኛለሁ፡፡
ታዲያ ይህ ምኞቴ - ለኔም ይገርመኛል
'ሰው መሆን ምንድን ነው?” - ውስጤ ይጠይቀኛል፡፡
ምስኪኗን ቡችላ - በቆፈኑ ክረምት - ቱቦ ስር የጣሏት
ደካማዋን ባልቴት - ከእንጨት አሳንስው - ጣል ጣል ያረጓት፣
ስውን ሚያህል ፍጡር- ከነህይወታቸው - በእሳት ያጋዩዋቸው
እውነት ሰዎች ናቸው?
እኔ ራሴስ ብሆን?
ይህን ሁሉ ህመም - እያየሁ ያስቻለኝ
በምችለው መጠን - ርዳታ ፈላጊን - መርዳት የተሳነኝ
ጭራሽ ከአንቺ ጋራ - ሁሉን ረስቼ - መቦረቅ የሚያምረኝ
እውን እኔ ሰው ነኝ ??
ልጠይቅሽ እስኪ፡-
የምስኪኗን ጩኸት፣
የባልቴቷን ብሶት፣
የንፁሃንን ሞት፣
የሰውን ልጅ እክል፣
የምድርን ምስቅልቅል፣
አንቺ ካስረሳሺኝ
ጠቀምሽኝ?
ጎዳሽኝ?
ገደልሽኝ?
አዳንሽኝ?
መልስ እፈልጋለሁ
ሰው መሆን ምንድን ነው???
🔘መሉቀን ሰለሞን🔘
..እናልሽ ቆንጅቴ
የሆነ ዕለት ማታ
ገና አይኗ ያልበራ - የውሻ ቡችላ
ከእናቷ ተነጥቃ - መንገድ ዳር ተጥላ፣
ያውም በክረምቱ
ያውም በምሽቱ፣
እናቴን፣
ሙቀቴን፣
ህይወቴን እያለች
ቱቦ ስር ተኝታ - ታለቃቅሳለች፡፡
ምናልባት ሌሊቱን
ዝናብ ከዘነበ - ጎርፉ ይወስዳታል
ጎርፍ ካልወሰዳት
ራቱን ፍለጋ የወጣ ቀበሮ - ራት ያደርጋታል፡፡
ይህንን ስታይ - መኖር ይገርምሻል
ህይወት ግን ምንድን ነች?- ያፈላስፍሻል፡፡
ደግሞ በሌላ ቀን
አያቴ 'ሚሆኑ - እድሜ ጠገብ ባልቴት
በጠራራ ፀሐይ - ጥላ በሌለበት፣
ከአካላቸው ሚገዝፍ - የእንጨት ክምር አዝለው
ገዢ ይመኛሉ - ገንዘብ ተስፋ አድርገው፡፡
አንዲት ወጣት መጥታ - እየተቻኮለች
እንጨቱን ለመግዛት - ባልቴቷን ጠየቀች፤
“ስንት ነው?” ጠየቀች ወጣቷ
“ሃያ ብር” መለሱ አሮጊቷ፣
“ቀንሱልኝ ማዘር?”
“አስራ ስምንት አርጊው”
“አስራ አምስት ልውሰደው?”
“አላነሰም ልጄ?”
“ይህንም ማደርገው- ከምዞር ብዬ ነው!”
“በ...ይ እሽ ውሰጅው”::
ይታይሽ እንግዲህ
ሌሊቱን በሙሉ - የተጓዙበትን
መቼም ላይቃኑ - የጎበጡበትን፣
ከአራዊት ጋር ታግለው - ያመጡትን እንጨት
በአንድ ቢራ ዋጋ - አስራ አምስት ብር ሽጡት፡፡
አስራ አምስት ብር ብቻ!!!
አየሽ ያቺ ወጣት የ'ሷ ድካም እንጅ የባልቴቷ ኑሮ
አላስጨነቃትም
የምታወጣቸው አምስት ብሮች እንጅ - የአሮጊቷ ድካም
አላሳሰባትም፡፡
ይህንን ስታይ እንባ ያስወጣሻል
“መተዛዘን የታል?” ግራ ያጋባሻል፡፡
ትላንትና ደግሞ
በአንድ ቴሌቪዥን - ሰበር ዜና አይቼ
ሲያስታውከኝ አደርኩ - ከእንቅልፍ ተፋትቼ፤
ምን አየሁ መሰለሽ :-
አንድ የሰዎች ቡድን - ሰዎችን አግቶ
ሁሉንም በአንድ ላይ - ጠባብ ቤት ውስጥ ዘግቶ፣
እንደ በቆሎ እሸት - እያንከባለለ
ከነህይወታቸው - በእሳት አቃጠለ፡፡
በስመ አ..........ብ!!!
ይህንን ስታይ ህይወት ያስጠላሻል
የሰው ልጅ ምንድን ነው?' ያወዛግብሻል::
ታዲያ ግን አለሜ፤
ስንቱን ጉድ አይቼ፣
ስንቱን ጉድ ሰምቼ፣
በብዙ ቆስዬ፣
በብዙ ነድጄ፣
ነድጄ
ነድጄ........
አንቺን እንዳገኘሁ
ያስከፋኝን ሁሉ በአንዴ ረሳውና-
«ይህች ዓለም ጣፋጭ ነች - ቆንጆ ነች!› እላለሁ፡፡
እውነቴን ነው ምልሽ
አንቺን እንዳገኘሁ፡-
ባገባኋትና - አይኔን በአይኔ አይቼ
እስከፍፃሜየ - በኖርኩ ተደስቼ!
እያልኩ አመኛለሁ፡፡
ታዲያ ይህ ምኞቴ - ለኔም ይገርመኛል
'ሰው መሆን ምንድን ነው?” - ውስጤ ይጠይቀኛል፡፡
ምስኪኗን ቡችላ - በቆፈኑ ክረምት - ቱቦ ስር የጣሏት
ደካማዋን ባልቴት - ከእንጨት አሳንስው - ጣል ጣል ያረጓት፣
ስውን ሚያህል ፍጡር- ከነህይወታቸው - በእሳት ያጋዩዋቸው
እውነት ሰዎች ናቸው?
እኔ ራሴስ ብሆን?
ይህን ሁሉ ህመም - እያየሁ ያስቻለኝ
በምችለው መጠን - ርዳታ ፈላጊን - መርዳት የተሳነኝ
ጭራሽ ከአንቺ ጋራ - ሁሉን ረስቼ - መቦረቅ የሚያምረኝ
እውን እኔ ሰው ነኝ ??
ልጠይቅሽ እስኪ፡-
የምስኪኗን ጩኸት፣
የባልቴቷን ብሶት፣
የንፁሃንን ሞት፣
የሰውን ልጅ እክል፣
የምድርን ምስቅልቅል፣
አንቺ ካስረሳሺኝ
ጠቀምሽኝ?
ጎዳሽኝ?
ገደልሽኝ?
አዳንሽኝ?
መልስ እፈልጋለሁ
ሰው መሆን ምንድን ነው???
🔘መሉቀን ሰለሞን🔘
#አላምንም
ጓደኞቼ ቢያውቁ
እኔ እንደምወድሽ፣
አንቺ እንደማትጠይኝ
ግን እንደማትሆኚኝ
ላንቺ መንሰፍሰፌን
እንድተው መክነፌን፣
ሊያስረዱኝ ፈልገው
አዋዝተው ቀባብተው፡-
“ስማ የኛ ችኮ!
እሷ ማለት እኮ
አንተን ትወዳለች
ሌላም ትወዳለች
ሌላም ትወዳለች
ሌ ላ ም ትወዳለች........
ስለማትኖር ታምና
አትሆንህምና
ትቅርብህ!!” ቢሉኝም
ሰው ምቀኛ ነው - ሰዎችን አላምንም፡፡
(አቤት ሰው! አቤት ሰ.......ው
የሷን ወሬ ለኔ - መቶ ሚያላልሰው
ምን እንዳደርግ ነው?
ምንም ሳላኮርፋት
ምናለ ብወዳት
ምናለ ባፈቅራት?)
ነገሩን አልኩ እንጅ
ከሰዎች አብልጦ አይኔም ጠቁሞኛል
ስራሽን ነግሮኛል፡፡
ቢሆንም
ቢሆንም
“መጣሁ ጠብቅ” ብለሽ
ቶሎ ልትመለሽ፣
ልብሽ ከኔ ርቆ
ከሌላ ተዋውቆ፣
ሆነሽ የእምነት ደሐ - የፍቅር መሃይም
ባይኔ በብረቱ - ስትሳሚ ባይም፣
አይኔ ምቀኛ ነው - አይኔንም አላምንም፡፡
(አይኔን መች አጣሁት፡-
ሴቶችን ሁሉ - በአንች እያስመሰለ
የሌሎችን ኃጢያት - ለአንቺ እያሸከመ፣
ሌላው በተሳመ - በአንቺ እያላከከ
መጥፎ ምስል ልኮ - ልቤን እያወከ......
ሊያጣላኝ መሆኑን - አይኔን መች አጣሁት
አላምነውም ተውኩት፡፡)
እውነቱን ልንገርሽ ?
ስላንቺ ከሆነ
ጆሮየን አላምንም፣
አይኔንም አላምንም፣
ሰውንም አላምንም
ማንንም አላምንም፣
አላምንም፡፡
አላምንም።
አውነትን መጨፍለቅ - ከፍቅርሽ አይከብድም።
🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
ጓደኞቼ ቢያውቁ
እኔ እንደምወድሽ፣
አንቺ እንደማትጠይኝ
ግን እንደማትሆኚኝ
ላንቺ መንሰፍሰፌን
እንድተው መክነፌን፣
ሊያስረዱኝ ፈልገው
አዋዝተው ቀባብተው፡-
“ስማ የኛ ችኮ!
እሷ ማለት እኮ
አንተን ትወዳለች
ሌላም ትወዳለች
ሌላም ትወዳለች
ሌ ላ ም ትወዳለች........
ስለማትኖር ታምና
አትሆንህምና
ትቅርብህ!!” ቢሉኝም
ሰው ምቀኛ ነው - ሰዎችን አላምንም፡፡
(አቤት ሰው! አቤት ሰ.......ው
የሷን ወሬ ለኔ - መቶ ሚያላልሰው
ምን እንዳደርግ ነው?
ምንም ሳላኮርፋት
ምናለ ብወዳት
ምናለ ባፈቅራት?)
ነገሩን አልኩ እንጅ
ከሰዎች አብልጦ አይኔም ጠቁሞኛል
ስራሽን ነግሮኛል፡፡
ቢሆንም
ቢሆንም
“መጣሁ ጠብቅ” ብለሽ
ቶሎ ልትመለሽ፣
ልብሽ ከኔ ርቆ
ከሌላ ተዋውቆ፣
ሆነሽ የእምነት ደሐ - የፍቅር መሃይም
ባይኔ በብረቱ - ስትሳሚ ባይም፣
አይኔ ምቀኛ ነው - አይኔንም አላምንም፡፡
(አይኔን መች አጣሁት፡-
ሴቶችን ሁሉ - በአንች እያስመሰለ
የሌሎችን ኃጢያት - ለአንቺ እያሸከመ፣
ሌላው በተሳመ - በአንቺ እያላከከ
መጥፎ ምስል ልኮ - ልቤን እያወከ......
ሊያጣላኝ መሆኑን - አይኔን መች አጣሁት
አላምነውም ተውኩት፡፡)
እውነቱን ልንገርሽ ?
ስላንቺ ከሆነ
ጆሮየን አላምንም፣
አይኔንም አላምንም፣
ሰውንም አላምንም
ማንንም አላምንም፣
አላምንም፡፡
አላምንም።
አውነትን መጨፍለቅ - ከፍቅርሽ አይከብድም።
🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
#ምኗን_እንደወደድኩት?
አረማመዷ እንቅልፍ ነስቶኝ - ሌሊቱን ሙሉ እያለምኩት
ሐር መሳይ ጥቁር ጸጉሯ - ጠልፎ ሲጥለኝ እያየሁት
ምኗን እንደወደድኩት!?
እንደ በረዶ በነፁ - ጥርሶቿ እያሳሳችኝ
በአይኗ ጨረር እንዳልወጋ - አንገቴን እያስደፋችኝ
እንዴት ደስ እንዳለችኝ!?
አንገቷን ፣
የረዘመውን - ብስመው እንደሚያዞረኝ
ጡቶቿን፣
የሚዋጉትን - ብነካቸው እንደሚነዝረኝ
ገዳይ መሆኗን እያወኳት
እንዴት እንዳፈቀርኳት!?
ችቦ ማይሞላው ወገቧ - በልቶ ማያድር የመሰለ
ወ...ረ..ድ ሲሉ ዳሌዋ - ራስ ዳሽንን እያከለ
ምኗን እንደወደድኩት!?
ምኗን እንዳፈቀርኩት!???
አረማመዷ እንቅልፍ ነስቶኝ - ሌሊቱን ሙሉ እያለምኩት
ሐር መሳይ ጥቁር ጸጉሯ - ጠልፎ ሲጥለኝ እያየሁት
ምኗን እንደወደድኩት!?
እንደ በረዶ በነፁ - ጥርሶቿ እያሳሳችኝ
በአይኗ ጨረር እንዳልወጋ - አንገቴን እያስደፋችኝ
እንዴት ደስ እንዳለችኝ!?
አንገቷን ፣
የረዘመውን - ብስመው እንደሚያዞረኝ
ጡቶቿን፣
የሚዋጉትን - ብነካቸው እንደሚነዝረኝ
ገዳይ መሆኗን እያወኳት
እንዴት እንዳፈቀርኳት!?
ችቦ ማይሞላው ወገቧ - በልቶ ማያድር የመሰለ
ወ...ረ..ድ ሲሉ ዳሌዋ - ራስ ዳሽንን እያከለ
ምኗን እንደወደድኩት!?
ምኗን እንዳፈቀርኩት!???
#የከብቶች_አገር
አንዲት መንደር አለች - እጅጉን ጩኸታም
እረኛ የሌላት - ግን የከብቶች ሐብታም፡፡
ወጣ ገባ ምድሯ - በእንስሳት ተሞልቶ
አንድ የሚያደርጋቸው - 'ሚያግባባቸው ጠፍቶ፣
በሁሉም አቅጣጫ - በአራቱም ማዕዘን
ሲበረቱ ጩኸት - ሲደክሙ ማላዘን
እምቧ ...... ይላሉ ከብቶች
ያናፋሉ አህዮች !
ቢኺኺኺ
ሚያው
ውውውውው......
በጎች
ወሻዎች
በመንደሯ ያሉት የቤት እንስሳዎች ፣
በሚችሉት መጠን - በራሳቸው ዓለም
ሁሉም ይጮሃሉ - ማንም ዝም አላለም
በዚያች የከብት አገር
መጫ
ጮህ ብቻ እንጂ - መደማመጥ የለም!!
🔘መሉቀን ሰለሞን🔘
አንዲት መንደር አለች - እጅጉን ጩኸታም
እረኛ የሌላት - ግን የከብቶች ሐብታም፡፡
ወጣ ገባ ምድሯ - በእንስሳት ተሞልቶ
አንድ የሚያደርጋቸው - 'ሚያግባባቸው ጠፍቶ፣
በሁሉም አቅጣጫ - በአራቱም ማዕዘን
ሲበረቱ ጩኸት - ሲደክሙ ማላዘን
እምቧ ...... ይላሉ ከብቶች
ያናፋሉ አህዮች !
ቢኺኺኺ
ሚያው
ውውውውው......
በጎች
ወሻዎች
በመንደሯ ያሉት የቤት እንስሳዎች ፣
በሚችሉት መጠን - በራሳቸው ዓለም
ሁሉም ይጮሃሉ - ማንም ዝም አላለም
በዚያች የከብት አገር
መጫ
ጮህ ብቻ እንጂ - መደማመጥ የለም!!
🔘መሉቀን ሰለሞን🔘
#የት_ነበርኩ?
ፍቅረኛዬን ጠበኩት። አልመጣም፡፡ ወደ መዝናኛው የሚገባውን ሰው ሁሉ አያለሁ። አንዲት ቀጭን ሴት ከአንድ ወጣት
ጋር ገባች።
ምን ብሎ እንዳስደሰታት እንጃ የኮቱን እጅጌ ወደታች ስትስበው ከአንገቱ ጎንበስ አለላትና፤ “የኔ ቆንጆ!” ብላ አንገቷን
አጠማዛ ከንፈሩ ላይ ሳመችው።
የአፍላነቴን ጊዜ አስታወስኩ። በጭለማ ሊያውም በአንሶላ ውስጥ ካልሆነ ባደባባይ ከንፈር ተስሞ አይታወቅም ነበር።የትውልዱ ለውጥ ገረመኝ፡፡
ክንዷን በወገቡ ዙሪያ ለማድረግ ሞክራለች፤ አልተሳካላትም፡፡የወገቡን ሩብ ያክል እንኳን አላቀፈችውም ልዩነታቸው ገረመኝ እሱ የተራራ ጉማጅ የሚያክል ግድንግድ፣ እሷ በመዳፍ ውስጥ
ያለች ትንሽ አሳ የመሰለች ደቃቃ፡፡ ፍቅር የሚባለውን ነገር አመሰገንኩት፤ መጠንን፣ ቀለምን እና ዘርን የማይመርጥ የማያዳላ
ክቡር ነገር፡፡
ልጅቱ ያለማቋረጥ ትስቃለች። ድምጿ ከቃጭል የቀጠነና ስቅጥጥ የሚያደርግ ነው፡፡ መድረክ ላይ ያለች ይመስል ለሰው ሁሉ እንዲሰማ አድርጋ እየተወራጨች ስታወራ በአካባቢዋ መደማመጥ
የሚፈልግ ሰው እንዳለ ልብ ያለች አትመስልም፡፡
እንደተቀመጡ አስተናጋጇ ወደነርሱ ቀረብ አለች ። “አንድ ቀይ ወጥና አንድ አልጫ!” ብላ ጮኸች። የቤቱን ሰው ሁሉ ያዘዘች ነው የምትመስለው።
ዐይኔም ጆሮዬም ቀልቤም እነሱው ላይ
የሚያስደስትም፣ የሚያስጠላም ነገር እኩል ቀልብ መሳቡ ሁልጊዜም
ይገርመኛል፡፡ ሴቲቱ ከመገልፈጧ የተነሳ ሳቅ ውድድር ላይ እያላች የደከማት ትመስላለች። የምታደርገው ነገር ሁሉ ወዝ የለውም።
ትኩረቴ ሁሉ ወደ ጥንዶቹ ሆኖና ልቤ ተንጠልጥሎ እጠብቀው የነበረውን ፍቅረኛዬን በጥቂቱም ቢሆን እንድረሳው
ምክንያት ሆኑኝ፡፡ በዚህ አመሰገንኳቸው፡፡ ምክንያቱም ሁልጊዜ ፍቅረኛዬን ስጠብቅ ልቤ በአፍንጫዬ እስክትወጣ ድረስ ትዘላለች።አንድ ቀን እሱን በጉጉት ስጠብቅ ልቤ ፍርጥ እንዳትል እሰጋለሁ።
ሳቋን አቋርጣ፣ “አይገርምክም ሆድዬ፣ ወደኔ ሲቀርብ እኮ አላየሁትም። ሆዷን ደግፋና አጎንብሳ እንባዋ እስኪንጠባጠብ ድረስ ሳቀች።
"ያጋጠመሽ እኮ እንደዚህ የሚያስቅ አልመሰለኝም"
“ሆድየ እንዴት ላብ በላብ እንደሆንኩ እኮ አትጠይቀኝ ታዲያ ይሄ አያስቅም በናትክ"
“ቀርቦ ያደረገውን ብቻ ንገሪኝ የኔ ውድ..ሃ...ሃ...ሃ" ሳቀ፡፡ሳቁ ጎርናና ነው።
“አይገርምም? መጀመሪያ የባሱን መደገፊያ በሁለት እጄ ይዤው ነበር፡፡ ከኋላዬ ክንዶቼን እንቅ አድርጎ ሲይዝ ተሰምቶኛል።
እኔ ደግሞ በቃ የሚይዘው ነገር ያጣ ነው የመሰለኝ፡፡”
“ብቻ አንቺ ላይ ሊንጠላጠል ፈልጎ እንዳይሆን?"
“ሞዛዛ!” አለችና በጥፊ አቃጠለችው፡፡ ዱላውን የለመደው ይመስላል። ምንም አልመሰለውም፡፡ ጥፊው ይደገም ይመስላል ፊቱን ቀበር እንደማድረግ ብሎ አድፍጦ ማዳመጡን ቀጠለ፡፡
“ፍቅር ካለ ለካስ ዱላም ይጣፍጣል?” አልኩ በሆዴ። አሁን በመዝናኛው ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ ጨዋታውን አቋርጦ እሷን
የሚያዳምጥ ይመስላል፡፡
“እላዬ ላይ ልጥፍ ሲል እኔ ደግሞ ያልተመቸው መስሎኝ ሳፈገፍግ የበለጠ ልጥፍ አለብኝ፡፡”
“ይለጥፍብሽ አንዳች! አልኩኝ በሆዴ፡፡
“እኔ የምለው... እና ሲለጠፍብሽ ዝም አልሽ?” አለ እሱም
እንደርሷ ባይሆንም ይጮኸል።
“እኔማ መጀመሪያ አልገባኝም፡፡ በኋላ ግን አንድ ነገር ከኋላዬ ሲላወስ የሰማሁ መሰለኝ፡፡ ገረመኝና እንዲህ ከወደታች የሚንቀሳቀስ ነገር ምን ሊኖር ይችላል ብዬ አሰብኩ፡፡ የሚንቀሳቀሰው ነገር
የሚቧጥጠኝ መሰለኝ”
"እስኪቧጥጥሽ ድረስ አንቺ ምን ትሰሪያለሽ?" አለና የቤቱን ሰው ሁሉ በጨረፍታ መልከት አድርጎ አጎነበሰ።
“ኧረ በጣም ትገርማለክ ታዲያ ምን ላድርገው? ወደፊት ለማፈግፈግ ሙከራ አደረኩኝ ግን ምንም መላወሻ አልነበረም::"
የእጇ መወራጨት እየጨመረ ነው፡፡
“አንቺ ግን ይሄ ለወንድ ይነገራል? መንገር ያለብሽና መንገር የሌለብሽን ለይተሸ አታውቂም?”
“ኧረ ባክክ! አሁን ይህን የመሰለ ታሪክ ሳልነግርክ ልቅር?” ሳቋ ከበፊቱ ጨምሯል። የተቀመጠችበትን ወንበር በተደጋጋሚ በመቁነጥነጥ ናጠችው፡፡
እንደልቤ መዞር አልቻልኩም፡፡ግን እዚያው ሆኜ ሳልንቀሳቀስ በምንክ ነው የምትወጋኝ?ምናለ ከኋላዬ ዞር ብትልልኝ አልኩት ።አረ ምንም መውጊያ የለኝም አለ እዛው እኔ ላይ እንደተለጠፈ። ሲያዩት ትልቅ ሰው ይመስላል። ደሞ ሊያውም የገጠር ሰው። ሽቅብ ሽቅብ እየተነፈሰ “እንዴት ብዬ ልላዎስ እሜትዬ ከኋላዬ ጠፍንገው ይዘውኝ አለ፡፡ ይህን
እየተነጋገርን እኮ የሚላወሰው ነገር ቀጥሏል!እ...ህህህህ! አለች። አሁን አሁን የሆነ ይመስል እንደመዘግነን እያላትና ከወደትከሻዋ በኩል ወደላይ ሳብ ብላ አንገቷን እየሰበቀች፡፡
ከዚያም “የሚጠጣ ነገር አላዘዝክልኝም
አለችና አጨበጨበች፡፡ አንድ ሰው ብቻ ያጨበጨበ አይመስልም፡፡ አራት
እጅ ነው እንዴ ያላት? እጆቿን አየሁ። ከእንቁላል መጠን ከሚያንስ
መዳፍዋ ያን ያህል ድምጽ ይወጣል ብሎ የሚወራረድ ማንም የለም፡፡
በስርአት ማጣቷና ሁላችንንም በመረበሿ የተበሳጨን ብዙዎች ብንሆንም ጆሯችንን ግን እንዳያዳምጥ አልከለከልነውም፡፡
ቀጠለች ወሬዋን፡፡
“በጣም ያሳቀኝ ነገር ሰውየው ማግኔት ነገር ያጣበቀው ነው የሚመስለው፤ ቀስቀስም እኮ አይል አይገርምክም? ከዚያ በኋላ ነው የበለጠ የገረመኝ! እንደመንቀሳቀስ ስል...አልተስማማሽም እቱ? አርፈሽ ተቀመጭ፡፡ ምን ያወራጭሻል! አይለኝ መስለህ! እንዲነችና! አልኩና ልዞር ስል መዞር አቃተኝ።"
“ምን ትዞሪያለሽ ጠርንፎ ይዞሽ፡፡”
“አንተ ደግሞ...”
"የነገርሽኝን ነው ያልኩት።"
አነስ ያለ ጥፊ ደግማ ሰነዘረች።
“ኧረ እንኳን አብሬ ያልነበርኩኝ ሆሆሆ!...” አለ፡፡
“ደሞ አንቆ ይዞ ምናምኑን እያንቀሳቀሰብኝ አትንቀሳቀሽ ማለቱ አይገርምክም!”
'ወቸ ጉድ!ዛሬ ደሞ ምኑን ያሰማኛል አልኩና ማዳመጤን ቀጠልኩ። አልፎ አልፎ ወደበሩ አያለሁ፡፡ ጓደኛዬ የውሃ
ሽታ ሆኗል፡፡አስናጋጇ የሚበሉትን አቅርባ ተመለሰች፡፡
“ኧረ በናትክ አጉርሰኝ፣ ከመቼ ወዲክ ነው ብቻክን የምትወጥቀው? ነው ሰውየው አበሳጨክ?” መልስ አልሰጣትም፡፡
ወዲያው አንድ ሰው ሲገባ አየችውና፣
“ደናነክ?” አለችው ትከሻዋን እየሰበቀች፡፡
“እስክስ!” አልኩ አሁንም በውስጤ፡፡
“ምነው ጠፋክ?” አለችና በተለፋደደ ድምጽ፡፡ ፊቷን ወደ ጓደኛዋ መልሳ ወሬዋን ቀጠለች።
“ምን እንዳለ ታውቃለህ “እንደሱ አርፈሽ ተቀመጭ፡፡
የራበሽን ያህል ነው የማጠግብሽ፡፡' ሲለኝ በጣም ገረመኝ፡፡”
"የራበሽን ያክል?... ተርቤያለሁ ብለሽው ነበር እንዴ"
"ብሽቅ! በጥፊ እንዳልልህ!... ደሞኮ ወደ ጆሮዬ ዝቅ ብሎ ነው የሚንሾካሾከው! እህ....” አለች በድካም ስሜት፡፡
አፏ ውስጥ ያለውን ምግብ አላምጣ ከጨረሰች በኋላ፣ “ከዛ የሚላወሰው ነገር ኋላዬን ውጥር አድርጎ ሲይዘኝ ቀስ ብዬ እጄን ሰደድ አደረግኩ።”
“እጅሽን ሰደድሽ ልትይዢው? አንቺ ደፋር!” አላት፡፡
“አኸ ወደክ ነው ይዤውማ ነው፡፡”
“ማን ፈቅዶልሽ ነው የሰው እቃ ለመያዝ...”
“ኧረ ባክክ ጨምላቆ....” ብላ ሳትጨርስ፣
“ያጨምልቅሽ!” አለና ከንፈሯን ቆነጠጣት፡፡
“ኡህ ካልጠፋ ቦታ ከንፈሬ ላይ ትቆናጠጣለክ...እንዴ?”
“ቢመቸኝ ምንሽጋ እንደምቆነጥጥሽ ታውቂያለሽ?”
“ኧረ ባክክ! ምናምንክን ቆንጥጥ እሺ?”
እርግጠኛ ነኝ ጤነኛ አትመስልም፡፡ ሁለቱም ሲያዩዋቸዉ ከአማኑኤል አምልጠው የመጡ... ይመስላሉ።
“ባገኘው ኖሮ ማጅር ግንዱን ብዬ ጣቢያ እቀለብ ነበር!” አለ፡፡
“እንዴ ምን አደረገ?"
“ከዚህ በላይ ምን ያድረገኝ? የሰራው
ነው.…እንዴ አንቺ ተስማምተሽበታል እንዴ?"
"ግን መጨረሻውን ሳትሰማ ለምን እንዲክ ትሆናለክ?"

👍3❤1
"መጨረሻውማ የበለጠ የሚያናድድ እንደሆነ ነው...”
ደርሳ ምን እንዳስኮረፋት ሳይታወቅ አኮረፈች።
"በናትሽ መጨረሻውን ንገሪኝ አላት እየተለማመጠ፡፡ ኩርፊያዋን ትታ፣
“እህ እየነገርኩክ! በቃ መላወሱን አቁሞ እየገፋኝ ሲመጣ
እጄን እንደምንም አሾልኬ ተጠማዘዝኩና በእጄ ያለ የሌለ ሐይሌን
አሰባስቤ ጭምቅ ሳረገው ሚያው! ብሎ...” ሁለቱም ሳቁ፡፡ በእርግጥም የምታወራው ከጀርባዋ የነበረው ሰውዬ
በማዳበሪያ ይዞት ስለነበረው ትንሽ ድመት ነበር። እኛም ሳናስበው ሳቅን ::
“አይ ድመቱ! አይ ድመቱ! ለካ በፊስታል ይዞት ትንፋሽ አጥሮት ነው!” አለችና ቀስ ብላ ዙሪያዋን ቃኘች፤ እንደምናዳምጣት
እርግጠኛ ነበረች፡፡
💫አለቋል ደሞ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ

#የወንበር_ፍቅር
ቀይ ነኝ - አምራለሁ
ለውበቴ ደግሞ እጨናነቃለሁ ፤
ውበቴን ሳጎላ - ውበቴን ሳሳምር
የቀለም ምርጫየ
ጥቁር::
ፀጉሬን እንደ ቱ ፓክ- ልጭት አደርግና
ጥቁር ኮፍያየን
ጥቁር ካናቴራ
ጥቁር ጂንስ ሱሪ
ጥቁር ጫማ ሳደርግ
ፓ!
ቅላቴ ይጎላል
ውበቴ ይደምቃል፡፡
ግን ግን
አያርግብኝና!
አ ያ ር ግ ብ ኝ ና!
በጣም የምወዳት
ቅድመ አያቴ ብትሞት፣
ሃዘኔን ላስታውስ
ምንድን ነው የምለብስ?
ጥቁር ልብስ???
🔘በሙሉቀን🔘
ቀይ ነኝ - አምራለሁ
ለውበቴ ደግሞ እጨናነቃለሁ ፤
ውበቴን ሳጎላ - ውበቴን ሳሳምር
የቀለም ምርጫየ
ጥቁር::
ፀጉሬን እንደ ቱ ፓክ- ልጭት አደርግና
ጥቁር ኮፍያየን
ጥቁር ካናቴራ
ጥቁር ጂንስ ሱሪ
ጥቁር ጫማ ሳደርግ
ፓ!
ቅላቴ ይጎላል
ውበቴ ይደምቃል፡፡
ግን ግን
አያርግብኝና!
አ ያ ር ግ ብ ኝ ና!
በጣም የምወዳት
ቅድመ አያቴ ብትሞት፣
ሃዘኔን ላስታውስ
ምንድን ነው የምለብስ?
ጥቁር ልብስ???
🔘በሙሉቀን🔘
#የኖህ_ዘመን_ቁጣ
በጠራዉ ሰማይ ላይ ደመና መጣና
ያ ብርሐን ድንገት ጭጋግ ለበሰና
ሰማይ አለቀሰ፤
ሰውም አለቀሰ፤
ዛፉም አለቀሰ፤
ወነንዙም አለቀሰ፤
ፍጥረት አለቀሰ፤
የሐዘን ዶፍ ከላይ በምድር ፈሰሰ።
ዘሩን ብቻ አይጎዳም ዳር የለውም ጭራሽ
መዘዙ ብዙ ነው የሰው ልጅ ሲበላሽ።
በጠራዉ ሰማይ ላይ ደመና መጣና
ያ ብርሐን ድንገት ጭጋግ ለበሰና
ሰማይ አለቀሰ፤
ሰውም አለቀሰ፤
ዛፉም አለቀሰ፤
ወነንዙም አለቀሰ፤
ፍጥረት አለቀሰ፤
የሐዘን ዶፍ ከላይ በምድር ፈሰሰ።
ዘሩን ብቻ አይጎዳም ዳር የለውም ጭራሽ
መዘዙ ብዙ ነው የሰው ልጅ ሲበላሽ።
#የድንቄ_ኑዛዜ
አባ ምንተስኖት እና የሰፈር አዛውንቶች ለምን የጎረቤታችንን የድንቄን ኑዛዜ እንድንሰማ እንደፈለጉ ለጊዜው አልገባንም፡፡ ድንቄ አለኝ የምትለው ልጅ እስከ አሁን ብቅ አላለም፡፡ በሰፈሩ ውስጥም እሱን ያየ ወይም ስለሱ የሰማ የለም፡፡ የንስሐ አባቷ የሆኑት አባ
ምንተስኖት ድንቄ ለልጇ የሰጠችውን ኑዛዜ ሊያሳውቁን በቦታው እንድንገኝ ባደራ ጭምር አስጠንቅቀውናል።
አባ ምንተስኖትንና የማናውቀውን የድንቄን ብቸኛ ወራሽ ልጅ በጉጉት መጠበቅ ጀመርን፡፡ ሁሉም የራስ የራሱን ወሬ ይዟል፡፡እኔም አልፎ አልፎ እነሱ የሚያወሩትን እያዳመጥኩ በራሴው
ትዝታ እቆዝማለሁ፡፡
ድንቄ እንደ ጎረቤቷ ሳይሆን እንደ ልጇ ትወደኝና ትንከባከበኝ ነበር፡፡ እናቴም ድንቄ ለኔ ያላትን ታላቅ ፍቅር ስለምታውቅ ሁልጊዜም ብሄድ አትከለክለኝም፡ስትሞት
ልቆጣጠረው የማልችለው ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል፡፡ ድንቄ በዐይነ ህሊናዬ አዘውትራ ትመጣለች።
የሚያብረቀርቀው ወዟ በጥቁር መልኳ ላይ ሲታይ ፈጣሪ በጥሩ ቅባት ሲወለውላት አድሮ የዋለ ይመስላል፡፡ ዐይኗ የጥንታዊ ስዕሎችን ዐይን አይነት የነጻና ቦግ ያለ ነው። ከንፈሮቿ ሁሌም
ያስደንቁኛል፡፡ በላይኛው ከንፈሯ ብቻ መኸል ለመሀል አግዳ መስመር ቢሳልበት ራሱን የቻለ የአንድ ሰው ከንፈር ይወጣዋል ረጅምና ወፍራም ናት።
“አመድዬ አመዶ መርሻ! መርሻዬ የኔ መርሻ” የኔን ስም እያቆላመጠ ጮክ ብሎ በጎረነነ ድምጽ የሚጣራ ሰው ከድንብ
በስተቀር ማንም እንዳይደለ የታወቀ ነው፡፡
አቀበቱን ጨርሳ ዘቅዘቅ ያለውን የቡሐ መንገድ ስትጀምር እጇን እያጋጨችና ያለርህራሄ በኃይለኛ እርምጃ ቡሐ ድንጋዩን እየደቀደቀች ከመንደር ስትደርስ፣
“መርሻ! መርሻዬ የኔ መርሻ...” እያለች የኔን ድምጽ በጎረነነ ድምጿ ትጣራለች፡፡
ከሰፈር ውስጥ ካሉ ልጆች ሁሉ መርጣ እኔን እንዴት እንደ ወደደችኝ ከድንቄ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም። ምናልባት የራሴ የሆኑ ግምቶች አሉኝ፡፡ ድንቄ የሚያዳምጣትን የሚያጫውታትን
ትወዳለች፡፡ በተጨማሪም ደግሞ፣
“ሌሉቹ ልጆች በልተው ስለሚሄዱ አልፈልጋቸውም።
ለሆዱ ብቻ የማይቀርበኝ አመዶ ብቻ ነው::” ስትል ሰምቻታለሁ።እኔም ደግሞ የአቅሜን ለሷ ከማድረግ ቦዝኜ አላውቅም። ሳላያት ከዋልኩኝ ትናፍቀኛለች። ብርጉድ ብርጉድ የሚሸት ልብሷንና ገላዋን እወድላታለሁ፡፡
ሁልጊዜም እቤታችን ስትመጣ የምትለብሳትን ነጠላ ሳብ አድርጌ አሽትና፣ አንዳንዴም በነጭ ጨርቆች መጣፉ ስለሚገርመኝ፣
“በነጠላ ላይ ነጠላ ይጣጣፋል?” ስላት ወደኔ መቀመጫ በእጇ እያመለከተች "ያንተ ቂጥ ብቻ ነው የሚጣፍ አሐዶ ትለኛለች።"
ደግሞ ሌላ ስራ እሰራለሁ። ከፊቷ ላይ ያለውን ወዝ ጥርግ አደርግና አመድ የመሰለውን እግሬን እባብሰዋለሁ
“አመዶ ተቀባ የኔ ወዝ እንኳን ላንተ ላስር አመዳም ይበቃል፡፡ እ...” ትለኝና ትስቃለች፡፡ ስትስቅ ደስ ትላለች። ጠቅላላ
ፊቷ ላይ ያለው ስጋ ተሰብስቦ ጉንጫ ላይ ይመጣና ይከመራል፡፡ ሳቋ ሳያልቅ የተጠራቀሙ ጉንጮቿን እይዛቸዋለሁ። እሷም ይህንን ስለምታውቅ እንደፈገገች ትቆያለች።
እሷን ከማጫወት ውጭ ሲደክማት የስሙኒ ቫዝሊን እገዛላትና እግሯን ከታጠበች በኃላ በትናንሽ እጆቼ እያሻሽሁ እሷን ማስደሰቴ አይቀርም፡፡
የድንቄ መሳቅና መጫወት ብቻ ለኔ በቂ ደስታ ነው፡፡ሁልጊዜ ድንቄ ስትጣራ ያለአንዳች ከልካይ እወጣለሁ። እሷም ያንን ለምዳዋለች፡ ሮጬ ካልወጣሁ ገስግሳ መጥታ፣ “አመድየ ምን ሆኖ
ነው?” ትላለች።
“እትዬ ድንቄ ምናለ አመዶ ባትይኝ?” እያልኩ ስወተውታት “ምን አይነት ስም ላውጣልህ አመድዬ?” ትልና እንደተለመደው ራሴን ታባብሳለች፡፡
አባ ምንተስኖትና በጉጉት የሚጠበቀው ልጅ አልመጡም፡፡
እናቴና ጎረቤቶቿ የማያቁትን የድንቄን ልጅ እያሽሟጠጡ ያወራሉ፡፡
“አበስኩ ገበርኩ እቴ! እስከዛሬ አይዞሽ ያላላት ልጅ ምን አይነት ይሆን?” አለች እናቴ፣ ሌላኛዋ ጎረቤታችን ቀጠሉ፡፡
“እኔ ብሆን ለማላውቀው ደሃ አወርሳለሁ እንጂ አንድም ቀን መጥቶ አይዞሽ ላላለኝ ልጅ...አላደርገውም።”
“እኛ የምናውቀው እሷንና ይሄን ቤት ያወረሷትን አክስቷን ብቻ ነው። እሷም እኮ የመጣችው እሳቸው ታመው ነው፡፡ እኔና
አክስቷ ይህን መሬት ከመመራታችን በፊት ሌላ አካባቢ አብረን ነበርን፤ ያኔም ቢሆን እሳቸውን ብቻ እንጂ ድንቄን አላውቅም፡፡
ድህነት ያዛትና ቤቱንም አስፋፍታ ሳትሰራ እሳቸው ያወረሷትን አንድ ክፍል ቤት ይዛ ኖረች፡፡ ግቢውን ከፍላ ሸጣ እንኳን ጥሩ ኑሮ ብትኖር ጥሩ ነበር።” አለችና እናቴ የጎረቤቶቿን ወሬ በተራዋ ማዳመጥ ጀመረች፡፡
ድንቄ የምትቀመጥበትን ሶስት እግር በርጩማ እናቴ ተቀምጣበታለች። ድንቄ ስትቀመጥበት መቀመጫዋ በሁለቱም ጎን ይተርፍና ሊወድቅ የተንጠለጠለ ይመስላል። ይህን ትርፍ መቀመጫዋን አልፎ አልፎ መዳበስ ትወዳለች።
አይኔን ሳዟዙር የድንቄን ምግብ ማቅረቢያ፣ በአለላ የተሰራ ስፌት አየሁና ምራቄን ዋጥኩኝ፡፡ ለምን የጨጓራ መረቅ
እንደማያንጠባጥብ ይገርመኝ ነበር፡፡ በልቼ እስከምጨርስ መረቁን ይዞ ይቆያል። ከዚያም ማወራረጃ ውሃ አያሥፈልገኝም።
ድንቄ ጠዋት ተነስታ መተዳደሪያዋ ወደ ሆነው ወደ ልብስ አጠባ ከመሄዷ በፊት የምታደርገው ነገር ቢኖር ገብሩ ስጋ ቤት
መሄድ ነው። ድንቄ የምትፈልገውን መናገር አያሥፈልጋትም፡፡ እንደደረሰች ገብሩ የምታወራውን በፈገግታ እያዳመጠ ጨጓራ በወረቀት መጠቅለል ይጀምራል ። ድንቄ ተቀብላ በእጇ እንደ መመዘን ታደርገዋለች።
“እኔኮ የራሴ ሚዛን እያለ የእጅሽ ሚዛንነት አይገባኝም?”ይላታል፤ አታዳምጠውም፡፡
✨ነገ ያልቃል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍3
#ዘመናይ_አፍቃሪ
እሙ
እንደምወድሽ እያወቅሽ አይንህን ላፈር ብለሻል
አንድ ነገር ልንገርሽ? :
ብታፈቅሪኝ ይሻልሻል!!!
ምን መሰለሽ
የፍቅር መዝገበ ቃላት መፅሃፉ እንደሚያስረዳው
ሰውን ከማፍቀር በላይ መፈቀር ነው የሚጎዳው።
"ለምን?”
ያፈቀረ አንዴ አፍቅሯል፤
ራሱን ለፍቅር ሰጥቷል፤
ክብሩን ለሰው ሰውቷል፡፡
ለስሙ አይጨነቅም፤
ለመከተል አይሳቀቅም፡፡
ለተፈቃሪ ነው እዳው፤
ተፈቃሪ ነው የሚጎዳው፡፡
"እንዴት?”
(እንዴት ማለት ጥሩ)
ለምሳሌ እኔ (አንቺን)
በምትገቢበት እየገባሁ፣
በምትወጭበት እየወጣሁ፣
ስትበይ እያየሁሽ፣
ስትጠጭም እያየሁሽ፣
መንፈስ ሆኜ ከማሳቅቅሽ፣
ሁሌም እንደምነግርሽ፣
ብትወጅኝ ነው የሚሻልሽ!!!
እ.ደ.ግ.መ.ዋ.ለ.ሁ!
ዳናሽን እየተከተልኩ፣
ስራሽን ሁሉ እየሰለልኩ፣
የምትበያቸውን ምግቦች፣
የምትለብሻቸውን ልብሶች፣
ያወራሻቸውን ሰዎች፤
በምን ሳሙና እንደታጠብሽ
ምን አይነት 'ፓንት እንዳደረግሽ..
እየነገርኩ ከማሳቅቅሽ
ለኔ ስትይ ሳይሆን ለራስሽ
ብትወጅኝ ነው የሚሻልሽ!!!
እህስ
ምን ታስቢያለሽ!!???😳
🔘በሙሉቀን🔘
እሙ
እንደምወድሽ እያወቅሽ አይንህን ላፈር ብለሻል
አንድ ነገር ልንገርሽ? :
ብታፈቅሪኝ ይሻልሻል!!!
ምን መሰለሽ
የፍቅር መዝገበ ቃላት መፅሃፉ እንደሚያስረዳው
ሰውን ከማፍቀር በላይ መፈቀር ነው የሚጎዳው።
"ለምን?”
ያፈቀረ አንዴ አፍቅሯል፤
ራሱን ለፍቅር ሰጥቷል፤
ክብሩን ለሰው ሰውቷል፡፡
ለስሙ አይጨነቅም፤
ለመከተል አይሳቀቅም፡፡
ለተፈቃሪ ነው እዳው፤
ተፈቃሪ ነው የሚጎዳው፡፡
"እንዴት?”
(እንዴት ማለት ጥሩ)
ለምሳሌ እኔ (አንቺን)
በምትገቢበት እየገባሁ፣
በምትወጭበት እየወጣሁ፣
ስትበይ እያየሁሽ፣
ስትጠጭም እያየሁሽ፣
መንፈስ ሆኜ ከማሳቅቅሽ፣
ሁሌም እንደምነግርሽ፣
ብትወጅኝ ነው የሚሻልሽ!!!
እ.ደ.ግ.መ.ዋ.ለ.ሁ!
ዳናሽን እየተከተልኩ፣
ስራሽን ሁሉ እየሰለልኩ፣
የምትበያቸውን ምግቦች፣
የምትለብሻቸውን ልብሶች፣
ያወራሻቸውን ሰዎች፤
በምን ሳሙና እንደታጠብሽ
ምን አይነት 'ፓንት እንዳደረግሽ..
እየነገርኩ ከማሳቅቅሽ
ለኔ ስትይ ሳይሆን ለራስሽ
ብትወጅኝ ነው የሚሻልሽ!!!
እህስ
ምን ታስቢያለሽ!!???😳
🔘በሙሉቀን🔘
#የኔ_ነገር
የተሰበረ አጥንት የተከሰከሰ
መሬት ውስጥ ተቀብሮ አፈር የለበሰ፣
እቆጥራለሁ አጥንት
ዛሬ ላይ ቁጭ ብዬ እያሰብኩ እንደ ጥንት፡፡
አፈር ሆኖ ኖሮ ወደ አፈር የገባ
ደርቆ የሻገተ ሽታው ማያስጠጋ፣
እመትራለሁ ስጋ
ስለራሴ ሳላውቅ ስለ ሙት ሳወጋ፡፡
ወይ የደረቀ አጥንት ጋሻ ላይሰራልኝ
የሻገተ ስጋ ምግብ ላይሆንልኝ፣
ስጋየን ስመትር፣
አጥንቴን ስቆጥር፣
ተቆጠሩ አመታት ነጎዱ ዘመናት - ለራሴ ሳላድር ፤
በሙታን ሳቅራራ በሙታን ስፎክር፡፡
የተሰበረ አጥንት የተከሰከሰ
መሬት ውስጥ ተቀብሮ አፈር የለበሰ፣
እቆጥራለሁ አጥንት
ዛሬ ላይ ቁጭ ብዬ እያሰብኩ እንደ ጥንት፡፡
አፈር ሆኖ ኖሮ ወደ አፈር የገባ
ደርቆ የሻገተ ሽታው ማያስጠጋ፣
እመትራለሁ ስጋ
ስለራሴ ሳላውቅ ስለ ሙት ሳወጋ፡፡
ወይ የደረቀ አጥንት ጋሻ ላይሰራልኝ
የሻገተ ስጋ ምግብ ላይሆንልኝ፣
ስጋየን ስመትር፣
አጥንቴን ስቆጥር፣
ተቆጠሩ አመታት ነጎዱ ዘመናት - ለራሴ ሳላድር ፤
በሙታን ሳቅራራ በሙታን ስፎክር፡፡
#ተስፋ
ወቅቱ ክረምት ነው::
ዝናቡ ይዘንባል፣
በረዶ ይጥላል።
ቀኑ ብርዳማ ነው ፤
ሙቀት የናፈቀው::
በዚህ የቁር ዕለት
ሰው በማይወጣበት
ህይወት ያለው ፍጡር -
በአውራ ጎዳናው ላይ - በማይታይበት::
ቀዝቃዛ ቤቴ ውስጥ - ዱካክ ባናወዛት
የቆንጆ ሴት አምሮት - በሚወዘውዛት ፤
በበረደው ቤቴ - ትኩስ አካል ይዤ
በይሆናል ምኞት - በሃሳብ ናውዤ
በጠባብ መስኮቴ - አንገቴን መዝዤ...
ወደ ውጭ አያለሁ፡-
ምናልባት የኔ ውድ!
የእህል ውሐ ነገር
ምኑ ይታወቃል?
የፍቅር አምላክ ደጉ - ከዝናብ ሊያስጥልሽ
ወደ ተከፈተው - ወደ ባዶው ቤቴ
ያስገባሽ ይሆናል፡፡
ዝናቡ ከባድ ነው፣
ማንም የማይደፍረው፡፡
ወጨፎው ይነፍሳል፣
ውሐና በረዶ በበሬ እየገባ -ወለሌን ያርሳል፡፡
ግን መኖሪያ ቤቴ- መዋኛ ቢመስልም
ውስጤ ተስፋ አለና- በሬን አልዘጋሁም፡፡
“ምናልባት የኔ ውድ! -
የእህል ውሐ ነገር
ምኑ ይታመናል?
ወደ እኔ ስትመጭ-
በሩን ከዘጋሁት -
ሰው ያለበት መስሎሽ-
ትዘይኝ ይሆናል!
ብየ ስለማስብ
አለሁልሽ ውዴ፡-
ዝናብ እየመታኝ - ቤቴ እየበረደው
ትመጫለሽ ብዬ - ደጅ ደጁን እያየሁ፡፡
አለሁልሽ ውዴ....
🔘በሙሉቀን🔘
ወቅቱ ክረምት ነው::
ዝናቡ ይዘንባል፣
በረዶ ይጥላል።
ቀኑ ብርዳማ ነው ፤
ሙቀት የናፈቀው::
በዚህ የቁር ዕለት
ሰው በማይወጣበት
ህይወት ያለው ፍጡር -
በአውራ ጎዳናው ላይ - በማይታይበት::
ቀዝቃዛ ቤቴ ውስጥ - ዱካክ ባናወዛት
የቆንጆ ሴት አምሮት - በሚወዘውዛት ፤
በበረደው ቤቴ - ትኩስ አካል ይዤ
በይሆናል ምኞት - በሃሳብ ናውዤ
በጠባብ መስኮቴ - አንገቴን መዝዤ...
ወደ ውጭ አያለሁ፡-
ምናልባት የኔ ውድ!
የእህል ውሐ ነገር
ምኑ ይታወቃል?
የፍቅር አምላክ ደጉ - ከዝናብ ሊያስጥልሽ
ወደ ተከፈተው - ወደ ባዶው ቤቴ
ያስገባሽ ይሆናል፡፡
ዝናቡ ከባድ ነው፣
ማንም የማይደፍረው፡፡
ወጨፎው ይነፍሳል፣
ውሐና በረዶ በበሬ እየገባ -ወለሌን ያርሳል፡፡
ግን መኖሪያ ቤቴ- መዋኛ ቢመስልም
ውስጤ ተስፋ አለና- በሬን አልዘጋሁም፡፡
“ምናልባት የኔ ውድ! -
የእህል ውሐ ነገር
ምኑ ይታመናል?
ወደ እኔ ስትመጭ-
በሩን ከዘጋሁት -
ሰው ያለበት መስሎሽ-
ትዘይኝ ይሆናል!
ብየ ስለማስብ
አለሁልሽ ውዴ፡-
ዝናብ እየመታኝ - ቤቴ እየበረደው
ትመጫለሽ ብዬ - ደጅ ደጁን እያየሁ፡፡
አለሁልሽ ውዴ....
🔘በሙሉቀን🔘
👍1
#የድንቄ_ኑዛዜ (መጨረሻው)
“እኔኮ የራሴ ሚዛን እያለ የእጅሽ ሚዛንነት አይገባኝም?”ይላታል፤ አታዳምጠውም፡፡
ቤቷ ገብታ እንደፊቷ ወዝ የጠገበች ማሰሮዋ ውስጥ ትጨምርና በላዩ ላይ ጨው በተን አድርጋ እሳት ትማግድበታለች።
ጠዋት ስራ ስትሄድ የጣደችው ጨጓራ በኩበትና በእንጨት ስትመጣ ገራም ሆኖ ይጠብቃታል፡፡ አሁን ጨጓራ የምትጥደው ለኔ ብቻ እስከሚመስለኝ ድረስ የምመገበው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ቁራጭ ጨጓራ ከበላች በአብዛኛው ለኔ
ትሰጠኛለች። በማሰሮ ውስጥ የሚቀራት ትንሽ ነው።
አናቴና ጎረቤቶቿ ከወሬ ወሬ እያፈራረቁ ስለድንቄ ንጽህና ማውራት ጀምረዋል። ንጽህናዋ ሰፈሩን ሁሉ ያስደነቀ ነው። ድንቄ እቤቷ ከሆነች የማታጥበው የማትጠርገው ነገር የለም፡፡ ብቻ ይህን
ለማድረግ በስካር ምክንያት አቅም አይነሳት እንጂ ስትጠርግ ውላ
ስትጠርግ ብታድር ደስተኛ ናት።
አዘውትራ “አምላክ ለደኸ ውሃ ባይሰጠው ጭቅቅቱም ይገለው ነበር!” ትላለች።
የእጇ አስተጣጠብ ስነ ስርአት ግዜውን ስለሚገድለው ያበሳጨኛል፡፡ መጀመሪያ በውሃ ትታጠባለች፡፡ ከዚያ ደግሞ ከቤቷ
ፊት ለፊት ወደ በቀለው ግራዋ ትሄድና ትል ያልበላውን ለምለም ቅጠል ስትበጥስ ትቆያለች። እየቀነጣጠበችና መሬት ላይ ከእጇ አምልጠው የወዳደቁ ቅጠሎች እየለቃቀመች አረፋ እስኪወጣ እጇ ላይ ትደፍቀዋለች፡፡ ውሃውን እጇ ላይ የማንቆርቆሩ ስራ ግን ለኔ ይተዋል። በሆዴ እረግማታለሁ፡፡ ምናለ ቶሎ ብላ ብትሰጠኝ እያልኩ መከረኛ ምራቄን ደጋግሜ እውጣለሁ።ጨጓራውን
ስትሰጠኝ እየተስገበገብኩ ስበላ አልፎ አልፎ፣ “አበስኩ ገበርኩ። ከነጋም ቁርስ አልሰጠችህም እናትህም ትላለች።
የአባ ምንተስኖት ድምጽ ከውጭ ሲሰማ ሁሉም ጨዋታውን አቆመ። እንደተባለው ወራሹን ልጅ ይዘው አልገቡም። ብቻቸውን
ነበሩ። ቁጭ እንዳሉ ወደዋናው ቁምነገር በቀጥታ አልገቡም፡፡ ትንሽ ሲያወሩ ከቆዩ በኋላ ከካፖርታቸው ውስጥ ወረቀት አውጥተው ጉሮሯቸውን ሲጠራርጉ አንድ ነገር ሊያነቡ እንደሆነ የገባት እናቴ፣
“ልጁ ሳይመጣ?” አለች።
አባ ምንተስኖት ሁላችንንም በፍቅር ዐይኖቻቸው ከተመለከቱ በኋላ ንግግራቸውን ጀመሩ።
“ልጆቼ! ድንቄ ይህን ኑዛዜ እናንተ ፊት እንዳነበው አስጠንቅቃ አዛኛለች። በእርግጥም ድንቄ ልጅ አላት። ልጇ ግን
እዚሁ ቅርባችን ነው ፤ እኛ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡
ሁላችንም በድንጋጤና በጉጉት ስናያቸው ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡
“ከመሞቷ በፊት አንድ ሳምንት ሲቀራት እኔና ሌሎች ሁለት ጓደኞቼን ጠራች። እኛም ያለችውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ
አሰፈርነው። ድንቄ ከዛሬ አስራ አምስት ዓመት በፊት ተቀጥራ ትሰራበት ከነበረበት ቤት ባለቤት አንድ ልጅ ወለደች፡፡”
አባ ምንተስኖት አልፎ አልፎ የሚያስላቸው ሳል የኑዛዜውን መጨረሻ በፍጥነት እንዳንሰማ ቢያደርገንም ሳላቸው አስኪያቆም ሁላችንም በያለንበት በጉጉት ጠበቅን፡፡
በመውለዷ የሚያስጠጋትና የሚረዳት ሰው ብታጣ ካለችበት ፍቼ ከተማ አክስቷ ወደ ሚኖሩበት መጣች። መውለዷ ሲነገራቸው ክፉኛ እንደተቆጡ ስትሰማ እንደማይቀበሏት ተረድታ ለረጅም ሰዓት
በለችበት ቆማ አለቀሰች፡፡ ከዚያም አክስቷ ቤት ልትደርስ ጥቂት ሲቀራት የቆመችበትን ቦታ አስተዋለች፡፡ ከአጠገቧ በግንብ የታጠረ ቤት አለ፡፡
ገርበብ ባለው አሮጌ የብረት በር ወደ ውስጥ ተመለከተች፡፡ በአካባቢውም ሆነ በግቢው አንድም ሰው አልነበረም፡፡
እንቅልፍ የወሰደውን የአንድ ወር ህጻን ከበሩ ላይ ቁጭ አድርጋው በፍጥነት ተሰወረች፡፡”
አባ ምንተስኖት ይህን እንደ ተናገሩ እናቴ እራሷን ይዛና ወደ መሬት አቀርቅራ እየየዋን አስነካችው። አባ ምንተስኖት እናቴ ለቅሶዋን እስክትጨርስ ይሁን አላውቅም ዝም ብለው አይዋት፡፡
ከእናቴ በቀር እንደዚያ ሆኖ ያለቀሰ አልነበረም፡፡
“ከዚያም...” ብለው ቀጠሉ አባ ምተስኖት... ከዚያም ያቺ ሴት መሐን ስለነበረችና ብቻዋን ስለምትኖር እግዜር ከሰማይ የላከላትን ልጅ በደስታ ተቀበለች፡፡ ይሄ የሆነው በፊት የድንቄ
አክስት ከሚኖሩበት ቦታ ነበር፡፡ ሰፈራቸው ፈርሶ ወደዚህ መጥተው ሲሰሩ ...”
እናቴ ለቅሶዋ እየጨመረ መጣ፡፡ አባ ምንተስኖት እናቴን በርህራሄ አይተው ጥቂት ዝም ካሉ በኋላ ። የዛሬው ሀብት ወራሽና
የድንቄ ልጅ፣ ተጥሎ የተገኘውና አሳዳጊዋ እናት ሆና ያሳደገችው
ልጅ መርሻ ነበር አሉ።”
ሁላችንም አለቀስን እኔም ሳትወልደኝ፣ እንደ እናት አድርጋ አንድም ሰው ልጂ አይደለም ብሎ ሳይጠረጥር ያሳደገችኝን እናቴን አቅፌ አለቀስኩ። እሷም እሩቅ ሀገር እንደሚሸኙት ሰው ጥብቅ
አድርጋ ይዛኝ ነበር፡፡
💫አልቋል💫

👍2
#እንዴት_ይሄን_አታውቂም!?
የሰው ልጅ ታሪክ ሲመረመር
እኩይና ጥሩ ሰው ነበር፡፡
እኩዮች አፈር ለብሰዋል
ጥሩዎች ሞት ድል ነስተዋል::
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
በቅርቡ እንኳን በቅርቡ - የታየ የተነገረ
በጎረቤታችን ምድር የሰው ደም ጎርፎ ነበረ፡፡
ወንድም በወንድሙ ላይ - ስለምን ሞት አነገሰ?
ለምን የንፁሃን ደም - በየጎዳናው ፈሰሰ?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
የባቢሎን ስልጣኔ - ባለመግባባት ፈራርሷል
ኢያሪኮን የመሰለ ግንብ - በጩኸት ተደረማምሷል
ብቻውን የቆመ አንበሳ - በጅቦች መንጋ ተበልቷል
የተባበሩ ጉንዳኖች - የመሬትን ሆድ ቀደዋል፡፡
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
ቂም በቀል ያረገዘች ልብ - ሰላምን ልታቅፍ አትችልም
ሰላምን ያላገኜች ነብስ - ፍቅርን አታስተምርም:
ፍቅር የራቃት ህይወት - የምትሰራው ቤት ጥላቻ
በጥላቻ የተሞላች ቤት - አማራጫ መፍረስ ብቻ::
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
ካወቅሽስ ምነው ችላ አልሽው?
ማፍረሱን ነው የናፈቅሽው?
መፍረሱን ነው የፈለግሽው?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እ.ን.ዴ.ት ይ.ዴ.ን ኢታ.ው.ቂ.ም!?
እንዴት!!???
🔘በሙሉቀን🔘
የሰው ልጅ ታሪክ ሲመረመር
እኩይና ጥሩ ሰው ነበር፡፡
እኩዮች አፈር ለብሰዋል
ጥሩዎች ሞት ድል ነስተዋል::
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
በቅርቡ እንኳን በቅርቡ - የታየ የተነገረ
በጎረቤታችን ምድር የሰው ደም ጎርፎ ነበረ፡፡
ወንድም በወንድሙ ላይ - ስለምን ሞት አነገሰ?
ለምን የንፁሃን ደም - በየጎዳናው ፈሰሰ?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
የባቢሎን ስልጣኔ - ባለመግባባት ፈራርሷል
ኢያሪኮን የመሰለ ግንብ - በጩኸት ተደረማምሷል
ብቻውን የቆመ አንበሳ - በጅቦች መንጋ ተበልቷል
የተባበሩ ጉንዳኖች - የመሬትን ሆድ ቀደዋል፡፡
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
ቂም በቀል ያረገዘች ልብ - ሰላምን ልታቅፍ አትችልም
ሰላምን ያላገኜች ነብስ - ፍቅርን አታስተምርም:
ፍቅር የራቃት ህይወት - የምትሰራው ቤት ጥላቻ
በጥላቻ የተሞላች ቤት - አማራጫ መፍረስ ብቻ::
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
ካወቅሽስ ምነው ችላ አልሽው?
ማፍረሱን ነው የናፈቅሽው?
መፍረሱን ነው የፈለግሽው?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እ.ን.ዴ.ት ይ.ዴ.ን ኢታ.ው.ቂ.ም!?
እንዴት!!???
🔘በሙሉቀን🔘