አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጊዜን_ሽግግር

ትናንትን መውቀሱ
ትናንትን መክሰሱ
ዛሬን ማወደሱ
ዛሬን ማሞገሱ
ነገን ማጨለሙ
ነገን መራገሙ
ምንድ ነው ጥቅሙ?!?
የጊዜ ምንነት ምሬቱና ጣዕሙ
ፋይዳ 'ሚኖረው የሕይወት ትርጉሙ
ሲያብሩ ብቻ ነው ባንድነት ሲቆመ::
የዛሬ መሠረት
ነበር ትናንትና
የነገም ውሃ ልክ
ቀድሞ ሚቀመጠው
በዛሬ ነውና
የትናንቱም ዕለት
የዛሬውም ዕለት
የነገውም ዕለት
ቁርኝት አላቸው ልክ እንደሠንሠለት፡፡
ምንም ጊዜ የለም እንደአምድ የፀና
ቀጥ ብሎ የቆመ በእራሱ ሕልውና፡፡
ካቻምና በአምና አምና በዘንድሮ
በቀጣዩ ዓመት
ዘንድሮ እንደገና
ወሩ ተራው ደርሶ ዓመት ሙሉ ኖሮ
ጊዜውን ጨርሶ በስም ተቀይሮ
አምና ተብሎ ይጠራል
ካቻምናም ይሆናል
ሕያው ሆኖ ነግሶ ድሮም ተብሎ ይኖራል፡፡
እያንዳንዱ ጊዜ በጊዜ ያስፈራል
በጊዜ ሚዛን ላይ ይወጣል ይለካል
እንደገና ይወርዳል “ሌላ ጊዜ” ይመጣል፡፡
ዘይገርም ነገር
ጊዜ ከዘረ ሰው በጣሙን ይረቃል
በእጅጉ ይልቃል
ሥልጣነ ጊዜውን በጊዜ ይለቃል
በፍቅር ይለቃል
በሰላም በፍቅር ጊዜ ይፈራረቃል
ያለአንዳች ኮሽታ
ያለአንዳች ሁካታ
እርስ በርሱ ይተካል ሁሌም እግር በእግር፤
ሒደቱ ቀጣይ ነው
ጊዜም አይገታውም የጊዜን ሽግግር፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
1
አትሮኖስ pinned «#ማምሻ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ሎዛ ከዓመት በኋላ ባሏ ጋ ጠቅልላ አውሮፓ ገባች፡፡ ያው እዚህ እንደነበረው ቶሎ ቶሎ ባንገናኝም አልፎ አልፎ ትደውልና ተጨቃጭቀን፣ ተሰዳድበን፣ አኩርፋ ጆሮዬ ላይ ዘግታብኝ፤ ከሆነ ጊዜ በኋላ መልሳ ደውላ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ እናወራለን፡፡ በመሃል ሰፈራችን ከላይ እስከታች ፈራርሶ ጎረቤቱ ሁሉ ተበታተነ፡፡ ሰፈራችን ሲፈርስ…»
#አፍሪካ_አንድም_ኀምሳ_አራትም

አክራ ባሕር ዳር ተቀምጠህ ፣ በጋና ችክችካ ሙዚቃ ስልት እስክስታ ስትወርድ የአፍሪካ አንድነት ይታይሃል ።

ካምፓላ መንገድ ላይ ተቀምጠው ባህላዊ ጌጣጌጥ Pሚሸጡ ነጋዴዎቹ ፣ የላሊበላን መስቀል ሲሸጡ ስታይ ፣ የአፍሪካ ኅብረት ይሰማሃል : :

ዝነኛው የናይጄርያው ፣ “ሳዋ ሳዋ ሳዋሌ” ዘፈ፣ ምቱን ሳይለቅ በአማርኛ ተሠርቶ አዲስ አበባ የምሽት ክለብ ኢትዮጵያውያንን ያለ እረፍተሸ
ሲያስጨፍር ስታይ ፤ የአፍሪካ መመሳሰል ይታወቅሃል : :

ፕሪቶርያ ምሽት ክበብ ቁጭ ብለህ ፣ የጃሉድን የመሰለ የ"ጫካ ድምፅ" ያለው ሙዚቀኛ ፣ሬጌ ዜማ እየሰማህ ቢራህን ስትጎነጭ ፣ አፍሪካ አንድ
መሆኗ ነጋሪ እንደማያሻው ትረዳህ : :

ናይሮቢ ሰማይ ላይ ተንጠልጥሎ የታየ ደመና ፣ አስመራ መሬት ላይ ዝናብ ሆኖ ሲወርድ ፤ “አፍሪካ አድ ሀገር ናት” ያሰኝሃል።

ዕድሜውን፣ ሙኩ ሀገሪቷን እየዞር ፣ የአፍሪካን ሕፃናት በፎቶ ሲሰበስብ የኖረ ፈረንጅ ያሳተመውን ፎቶዎች መጽሐፍ ከጫፍ ጫፍ ባገላበጥህ
ጊዜ ፤ የፈገግታቸውን መመሳሰል ባየህ ጊዜ ፤ ሁላችንም የምንነቃው የጠራ አፍሪካ ሰማይ ሥር መሆኑ ይሰማሃል።

🔘ሕይወት እምሻው🔘
#በጣም_ታምሪ_ነበር

ሠው ሰራሹ መልክሽ..
እፍጥጦ ባይወጣ
በጅንስ ታፍኖ..
ዳሌሽ ባይቀጣ
ጡትሽ ቤቱ ቢኖር...
ልታይ ሳያበዛ
ፀጉርሽ ያንቺዉ ቢሆን..
ከሱቅ ባይገዛ
ጊዜ ሳይቀይርሽ...
በቃልሽ ብታድሪ
ሀሊናሽ ቢገዛሽ
በሥጋሽ ባትኮሪ
የሴትነት ክብሩ ...
ቢገባሽ በልኩ
ሲጠሩሽ ባ'ሮጭ....
በርሽን ሲያኳኩ
አስተዋይ ብትሆኝ.…....
ምግባርሽ ቢከበር
ሔዋኔ ልንገርሽ...
በጣም ታምሪ ነበር፡፡

🔘አለ ታምራት🔘
🔥1
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


በታላቋ አሜሪካ፣ በግዙፍ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ሥር ሳልፍ፣ በውብ መናፈሻዎች ራስጌና ግርጌ ስመላለስ፣ ሰፋፊ መንገዶች እንኳን በእግር ሄደውባቸው በዓይን አይተው በማያካልሏቸው ትላልቅ የገበያ አዳራሾት መኻል ወዲህ ወዲያ ስል፣ ነፍሴ መደበቂያ የሚሆን አንዳች ሽርኩቻ ፍለጋ ትራወጣለች: አፍንጫዬ ሁልጊዜ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት አየር፣ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ የሚሸት ሰው ፍለጋ ይቀሰራል፡፡ በርገር እና ፒዛ
ቤት ገብቼ የዶሮ ወጥ ሽታ አነፈንፋለሁ፡፡ እግሬ የአሜሪካን ምድር ከረገጠበት ቀን ጀምሮ እየተነፈስኩ እታፈናለሁ፣ እያወራሁ እታፈናለሁ። ናፍቆት አይደለም፤አለመመቼትም አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት በሚስኪን ነፍስ ውስጥ የታሰረ ግዙፍ መንፈስ ነው ይኼ መንፈስ አሜሪካ ይጠብበዋል፣ ዓለም ይጠብበዋል:: ለአንድ
ኢትዮጵያዊ፣ እንደ ጫማ እና እንደ ልብስ ተለክታ የተሠራች ብቸኛ የመንፈሱ ጓዳ፣በሚጠብበው ዓለም ውስጥ ያለችው ሰፊዋ ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ ሌላው ሁሉ ይጠብባኛል፡፡

ለዚህም ሳይሆን አይቀርም፣ ባለችኝ ትንሽ ትርፍ ጊዜ ሁሉ ልክ እንደ እናት ማሕፀን የምትሞቅ፣ ከቤቴ ወደ ሃያ ደቂቃ መንገድ የምትርቅ፣ ጠባብ የሐበሻ ሱቅ ውስጥ የማልጠፋው፡፡ የአብሮ አደጌ የፋሲል ሱቅ ናት፡፡ ፋሲል አስማተኛም፣ አርበኛም
ይመስለኛል፡፡ ሚኒሊክ ፣አሉላ አባነጋ፣ በላይ ዘለቀም ይመስለኛል። አገሬን ከወራሪ ሰላቶ
ማስጣል ብቻ ሳይሆን፤ ተሸክሞ አምጥቶ ነጮች ምድር ያውም መሀል ከተማቸው ላይ በክብር ያስቀመጠ አርበኛ ይመስለኛል። አንድ ሐበሻ አስቁሞ “የኢትዮጵያ ኤምባሲ' የት ነው” ቢለኝ፣ የፋሲልን ሱቅ የምጠቁም እስኪመስለኝ ለእኔ ይህች ሱቅ በወርድም በቁመትም ትንሽ ኢትዮጵያ ነበረች፡፡

የጤፍ እንጀራ የሚቸረቸርባት… መቸርቸር ብቻ አይደለም ስለ እንጀራ ኬሚስትሪ የሚወራበት አብሲቱ በሙቅ ውሃ ተቀይጦ… የእንጀራው ዓይን እንዲህና እንደዛ ሆኖ ሰርገኛ ጤፍ ነጭ ጤፍ የሚባልባት፣ የሐበሻ ቡና የሚሸጥባት፣ የእሳት አደጋ ማስጠንቀቂያ ላይጮኸ እጣን በጊርጊራ የሚቦለቀለቅባት፣ የጀበና ቡና በጤናዳም
የሚጠጣባት፣ ጥሬ ሥጋ በፓውንድ የሚሸጥባት፣ ካለፈቃድ የሴት ልብስ መንካት ዘብጥያ በሚያስጥልባት አሜሪካ ባህሩ ቃኘ “ያዝ እጇን የሚባልባት ሱቅ፣ ጥላሁን ገሠሠ
"ጸልጌ አስፈልጌ፣ አስቴር አወቀ እሹሩሩ ፍቅር” የሚሉባት ሱቅ

የማነብበው ነገር ካለ እያነበብኩ፣ እጽፍም እንደሆነ ላፕቶፕ ኮምፒውተሬን ከፍቼ
ወጪና ሂያጁን ሐበሻ እየቃኘሁ፣ በዕረፍት ቀኔ ከፋሲል ጋር እውላለሁ! ሐበሻ ይመጣል፣
ዶላር ወደ አገር ቤት ይልካል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣እንጀራ ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ ቡና
ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ የወጥ ቅመም ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ የሚከራይ ቤት
ያለው ሰው ይጠይቃል፣ ሐበሻ ይመጣል፣ ፖለቲካ ያወራል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት ተሸክሞ “አገሩ አሜሪካ ከሽብርተኛ ጋር እዚያ መካከለኛው ምሥራቅ እየተፋለመችና በሚከፍለው ግብር ያመረተችውን ብዙ ቶን ቦንብ እያራገፈች መሆኑን የሚያሳይ ዜና ፊት ለፊቱ ባለ ቴሌቪዥን እየተላለፈ፣ በወረቀት በተሰናበታት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖትራክ መኪና ስለገጨው የመንገድ አጥር እየተብሰለሰለ በስሜት ያወራል፡፡ ሐበሻ
ነዋ! አንዱ ይመጣል፣ ሱቋ ውስጥ የተለጠፈውን የሚኒሊክን ፎቶ እየገላመጠ እንጀራ ገዝቶ ይሄዳል፡፡ ሌላው ይመጣል፣ በወዲያ በኩል የተለጠፈውን የመለስ ዜናዊን ፎቶ እየረገመ፣ እንጀራ ገዝቶ ይሄዳል፡፡ ሱቋ ውስጥ የሌለ የአገር መሪ ፎቶ የለም- ጥቁረቱም ከንፈሩም መንግሥቱ ኃይለማሪያምን የሚያስንቅ ሐበሻ መጥቶ፣ “ይኼን ሌንጨጫም ባሪያ ምን ይሁን ብላችሁ ለጠፋችሁት ደግሞ!?” ብሎ…ሁለት ፓውንድ ሥጋ አስቆርጦ በላዩ ላይ አሥር እንጀራውን አንጠልጥሎ ይሄዳል፡፡ ሐበሻ … በጤፍ እንጀራ ቀጭን ክር ላይ በሰልፍ የተሰካ የመቁጠሪያ ጠጠር ይመስለኛል፡፡ የተለያየ ግን የተሳሰረ።

ከተማረውና ከፍ ያለ ቦታ ካለው ሐበሻ ጀምሮ፣ እስከ ቀን ሠራተኛውና የታክሲ ሾፌሩ ድረስ ወደ ፋሲል ሱቅ የማይመጣ ሐበሻ የለም፡፡ መናኸሪያ ነበረች፡፡ ወሬ፣ ሐሜትና ፖለቲካው ይጦፋል፡፡ መረጃው ይጎርፋል፣ የሴራ ትንታኔው እየተነሳ ይጣላል፡የእድርና እቁብ ብር ይሰበሰባል፡፡ ፋሲል ሱቅ ስቀመጥ፣ አገሬን ትቼ የሄድኩ ሳይሆን፣ አገሬ ራሷ ውስጧ እንደተቀመጥኩ፣ እንደ አውሮፕላን ይዛኝ በርራ እዚያ ያሳረፈችኝ ይመስለኛል፣
አብረን ያረፍን፡፡ እንዲያውም ከስቋ ስወጣና የፈረንጅ መዓት ወዲያ ወዲህ ሲል፣የተወረርን ነው የሚመስለኝ::

የኑሮን ጎምዛዛ ጣዕም አገር ቤት ጣጥዬው መጣሁ ያልኩ እኔ ፣የሕይዎትን እውነተኛ ገጽ
ያየሁት፣ እንደመስኮት ሁሉን በጨረፍታ በምታስቃኘው በዚች ሱቅ ነበር፡፡ ደግሞ
ምሬቱ፡፡ ዕድል ፈግ ካላለች በስተቀር ምድሩ ወጥመድ ነው! ሥጋ እየደለለ ነፍስ ዐጽሟ
የሚቀርበት ምድር!

የሚመጣው ሁሉ የከሸፈ ታሪክ ልቡ ውስጥ አለ፡፡ የከሸፈ ኳስ ተጫዋች፣ የከሸፈ ሀኪም የከሸፈ ኢንጅነር፣ የከሸፈ ከያኒ፡ የከሸፈ ባለስልጣን ፣የከሸፈች ቆንጆ ሁሉም 'ነበርኩ' የሚለው ትዝታ አለው፡፡ ታዲያ ድፍን ሐበሻ አሜሪካ ላይ ወገቡ እስኪቆረጥ ሰርቶ በሰዓት የሚከፈለውን ድርጎ፣ የላቡ ዋጋ ሳይሆን እዛ አገር ቤት ትቶት ለመጣው፣ ለከሸፈ ትላንቱ የሚከፈል ካሳ ይመስለኛል፡፡

እንድ ቀን አንድ መላጣ ሰውዬ መጣ ዕድሜው ሃምሳዎቹን ያለፈ፤ ቢበዛ አራት ዓመት
የሚሆነው በምቾት ብዛት የተላጠ ብርቱካን የመሰለ ሕፃን ልጅ አቅፏል፡፡ ያስታውቃል
ያቀፈው ልጁ ከብዶታል፡፡ በኋላ ሰውዬው ራሱ "ልጄ ነው አለ እንጂ የልጅ ልጁ ነበር
የመሰለኝ፡፡ ሰውየው ከፋሲል ጋር የቆየ ትውውቅ ስለነበራቸው አረፍ ብሎ ወሬ ጀመረ፡፡ ያማርራል፤ ከፉኛ ያማርራል፡፡ በከንቱ የተበላ ዕድሜውን ከቡና እና ከቅመማ ቅመም ጋር ተደርድሮ ያገኘው ይመስል፣ ዓይኖቹ የሱቋ መደርደሪያ ላይ እየተንከራተቱ ያማርራል፡፡ የተኮሳተረ ጠይም ፊቱ ላይ እርካታ ያጣ ሕይዎቱ ከነሙሉ ሥርዓተ ነጥቡ
ተጽፎ ይነበባል: ከመደርደሪያው ኋላ ከተቀበሩት ድምፅ ማጉያዎች ፣ ኮለል ያላ የጥላሁን
ዘፈን ይፈስሳል፡፡ ሰውዬው ፊቱን ከስክሶና ወዲያ ወዲህ የሚል ልጁ ላይ ዓይኑን ተክሎ
ዘፈኑን እንደ ሙሾ ያደምጣል። በየመሀሉ “ምን የዛሬ ዘፋኞች! እያለ የዘመኑን ዘፋኞት
ያማርራል፤ ድንገት ወደ እኔ ዞሮ፣

አዲስ ህ?” አለኝ::

“ዓመት አለፈኝ

ሥራ ጀመርክ ወይስ ክላስ ምናምን?”

እየተማርኩ ነው

የምትማረውን ተምረህ ወዳገርህ ተመለስ! …ይኼ ቆሻሻ አገር እንደ ሸንኮራ አላምጦ ነው የሚተፋህ
እንዳታገባ፣ እንዳትወልድ፣ወዳገርህ ሰውዬው ኮስተር ብሎ ነው የሚያወራው የምመልሰው ግራ ገቦቶኝ ዝም እንዳልኩ፣ እጅህን ተመልከተው፣ እንደ ሴት እጅ የለሰለሰ ቆንጆ እጅ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ከስክርቢቶ ውጭ ምንም ጨብጦ አየውቅም፡፡ እኔም ስመጣ እንዳንተ ነበር እጄ፤ ለማስታወሻ ፎቶው አለኝ…ተመልከት አሁን” አለና እጁን ዘረጋ የተፍረከረከ የደህና አርሶ አደር እጅ ይመስላል፡፡ “የማንንም ሽንት ቤትና ወለል የፈገፈኩበት ነው፡፡ እንኳን ልስላሴው አሻራውም ጠፍቷል፡፡ አሁን
ይሄ አሜሪካ ውስጥ የሚኖር ሰው እጅ ይመስላል?” ብሎ የራሱን እጅ እያገላበጠ
ተመለከተና "ሃሃሃሃ” ብሎ ሳቀ፡፡ ሳቁ ያስፈራል::

ሰውዬው ፋሲል የጋበዘውን ቡና የመጨሻ ጠብታ አጣጥሞ፣ የገዛውን እንጀራ አንጠልጥሎ ልጁን እያቃሰተ አቀፈና ተሰናብቶን ወጣ፡፡ ዓይኔ ሳሩ ላይ መተከሉን አይቶ ፋሲል “የዚያች ልጅ ባልኮ ነው” አለኝ፡፡

የየቷ?”

እነሯ

ትቀልዳለህ?

እውነቴን ነው ማመን አልቻልኩም። አነሯ
👍5
የሚላት፣የሆነ ቀን ቡና ልትገዛ መጥታ
ያስደነበረችኝን ልጅ ነው፡፡ በጣም ወጣትና ቆንጆ ነች፡፡ አገር ቤት የመድረክ ቲያትር ስትሠራ፣ አውቃትም አደንቃትም ስለነበር፣ ከረዥም ጊዜ በኋላ ሳያት ደስ ብሉኝ፣ ፈገግ ብዬ ሰላም አልኳት! ኮስተር እንዳለች አንገቷን ብቻ ቀለስ እድርጋ ዝም አለች፡፡ “ይቅርታ አገር ቤት አውቅሻለሁ የእንባ ቀብድ የሚል ቲያትር ስትሠሪ…” ብዬ ከመጀመሬ፣ ፊቷ ተቀያይሮ “ይቅርታ! የኔ ወንድም ሥራ የለህም?” ብላ ኩም አደረገችኝ፡፡ ትንሽ ክብደት
ከመጨመሯ በቀር፣ አሁንም ቆንጆ ናት፡፡ ፊቷ ግን አስፈሪ ነበር፡፡ አሁን ገና የአባቷን ሞት ያረዷት ይመስል፣ ደህና ዋልሽ? ሲሏት የሚዘረገፍ የሚመስል እንባ ያረገዘ ሐዘንተኛ ፊት፣ ምን ስበብ አግኝቼ ባለቀስኩ የሚል ፊት፡፡ ብዙ አታወራም። ከዚያ ቀን በኋላም ብዙ ጊዜ ወደዚህ ሱቅ ስትመጣ፡ ኮስተር እንዳለች የምትፈልገውን ገዝታ ነው የምትሄደው።..........

አንብበው ጨርሰዋል አሁን ደሞ ከዚሁ ሳይወጡ #UNMUTE አድርገው ይውጡ አመሰግናለው

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የእንባ_ቀብድ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም በታላቋ አሜሪካ፣ በግዙፍ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ሥር ሳልፍ፣ በውብ መናፈሻዎች ራስጌና ግርጌ ስመላለስ፣ ሰፋፊ መንገዶች እንኳን በእግር ሄደውባቸው በዓይን አይተው በማያካልሏቸው ትላልቅ የገበያ አዳራሾት መኻል ወዲህ ወዲያ ስል፣ ነፍሴ መደበቂያ የሚሆን አንዳች ሽርኩቻ ፍለጋ ትራወጣለች: አፍንጫዬ ሁልጊዜ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት አየር፣…»
#የጋረዳት

ክቡር ስም ሰጥተናት
በተፈጥሯዊ ውበቷ ልዩ አርገን ስለናት
ከዓለም ለይተናት ከዓለም አጉልተናት
“የአሥራ ሦስት ወራት
የፀሐይ ብርሐን ሀገር ናት” ብለናት
ከሐቃችን ጋር ኖርን ለአያሌ ዘመናት፡፡
ለዓለም ያወጅነውን
ይፋ ያወጣነውን
የራሳችንን ሐቅ ቀድመን ብንዘነጋ
የእኛን ችላ ብለን
ከፍ ከፍ አድርገን የእነሱን የሐቅ ዋጋ
አምነን ተቀብለን
አንዳች ልዩ ተዓምር ይፈጠራል ብለን
ፀሐይዋ ተጋርዳ ጨለማ ሲውጠን
በዓይናችን ለማየት ጓጉተንና ቋምጠን
ከርቀት የሚያሳይ ባዕድ ቁስ አጥልቀን
እንደራቀ ወዳጅ ግርዶሽንም ናፍቀን
ሰማይ ላይ አንጋጠን ጠብቀን ጠብቀን
ሆኖም በሰማይ ላይ
አንዳች ተዓምር ስናይ
እንደወትሮው ሁሉ ፀሐይ እየሞቀን
በብርሐን ደምቀን
ብሩህ ሆኖ አለፈ ሳይገርመን ሳይደንቀን
ይጨልማል ያሉት ያ የጠበቅነው ቀን፡፡
ሐቃቸውን አምነን ሐቃችንን ጋርደን
ያጠፋነው እኛ ነን ወደንና ፈቅደን፡፡
ስለዚህ በቀኑ
በፀሐይዋ ብርሐን ከጥፋት ታርመን
ከገዛ ሐቃችን ጋር እንታረቅ ቀድመን፡፡
ወቅት 'ማይለውጠው ማይሽረው ዘመን
ይህ ነው ሐቃችን በጥብቅ የሚታመን፡፡
“ለአሥራ ሦስት ወራት
ፀሐይ ማይቸግራት
ምሥራቅ አፍሪካዊት
የፀሐይ መውጫ ሀገር
ተዓምር ያገነናት
ኢትዮጵያ ረቂቅ ናት፡፡”
ከዚህ ሐቅ የራቁ
ባለድንቅ አእምሮ በትምህርት የላቁ
በሙያ ክህሎት ለአንቱነት የበቁ
ዕውቀት የተካኑ
እኒያ አዋቀያኑ ፧
ቅድመ ትንበያቸው
“ለዛሬ አልተሳካም” ደግመው ይሞክሩ
የኢትዮጵያን ጉዳይ ጠልቀው ይመርምሩ
ሥረ መሠረቷን
ረቂቅ ምሥጢሯን ዘልቀው ይፈትሹ
እነሱ እንዳሉቱ
ጥላው ያጠላበት ፅልመት በትንሹ
የትአል የጋረዳት?!? የፀሐይ ግርዶሹ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

ከዚያ ቀን በኋላም ብዙ ጊዜ ወደዚህ ሱቅ ስትመጣ፡ ኮስተር እንዳለች የምትፈልገውን ገዝታ ነው የምትሄደው።

ፋሲል መደንገጤን አይቶ እየሳቀ “እስደነበረችህ አይደል?” አለ።

“ምን ሁና ነው እንደዚህ አነር የሆነችው በናትህ?”
“ሚስኪን ልጅ ነች …ባሏ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታክሲ ምናምን ነበር የሚሠራው፣ በሆን
እክሲደንት' እንዳይሠራ ታግዷል.አሁን እሷ ነች እየሠራች ቤተሰብ የምታስተዳድረው::
አሰበኸዋል? አዲስ አበባ መሬት አይንካኝ የምትል፣ በሕዝብ ጭብጨባና አድናቆት ታጅባ
የኖረች ልጅ፡ እዚህ ሞት የረሳቸው፣ እንደ ድንጋይ የሚከብዱ ባልቴቶችን፣ ስታነሳና ስታስተኛ መዋል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ? ከሥራው በላይ የሚጎዳው ግን ከአገር ቤት ይዘውት የሚመጡት አጉል ተስፋ ነው፡፡ መቼም በዕድሜ አባቷ የሚሆን ሰውዬ አፍቅራ አታገባም፡፡ የፈረደበት አሜሪካ ለመምጣት፣ ያገኙትን ያገባሉ በቃ! የማታፈቅረውን ስታገባ፣ ምንጊዜም ውስጥህ ተቀብሮ የሚያሰቃይህ፣ ረግጠኸው የመጣኸ ፍቅር ይኖር ይሆናል፣ ስቃዩ ቀላል አይደለም፡፡ የማታፈቅረውን ሰው አግብታ፣ በምድር ላይ ይኖራል ብላ እንኳ አስባው የማታውቀውን ከባድ ሥራ በቀን አሥር ሰዓት እየሠራች፣ አሜሪካ
አለ የተባለው ነገር ሁሉ አረፉ ሲሆን ህመሙ ቀላል አይደለም፡፡ መፍረድ አይቻልም፡፡በዚያ ላይ ሁለት ልጆች አሏት፡፡ እዚህ አገር ልጅ ማሳደግ ኢትዮጵያ ሁለት ሥራ ከመስራት እኩል ነው … ራሷን እንኳን መጠበቂያ ሰዓት የላትም፡፡ አንዳንዴ ሰላም ሆና ስታወራ ግን እንዴት ጥሩ ልጅ መሰለችህ!”

ከዚህ ሁሉ አገር ሰላም ከሆነ እዛው ቢሰሩስ እንዲህ ብር የማያስታምመው የዕድሜ
ልክሸ ድብርት ተሸክሞ ከመኖር …” አልኩ።

ግው ከአገሩ የሚሰደደው ስላም ስላጣ ብቻ ይመስልሃል? አገሩ በጦርነት እየታመሰ፤
ምድሩን የሚገለባብጥ ቦምብ እየወረደብህ፣ አገሬን የሙጥኝ ልትል ትችላለህ!
ምክንያቱም ከምትወዳቸው ሰዎች ላለመለየት፡፡ የአምባገነን መንግስት እርግጫ ችለህ
እስርና እንግልቱን ተቋቁመህ ከነጠባሳህ ምድርህ ላይ መኖር ትችል ይሆናል. አየህ ሰውን ከአገሩ የሚያሳድደው ጦርነትና አምባገነን ሥርዓት ብቻ አይደለም! ድህነት ያስጨነቀው የእናትህ ፊት… ርሃብና መታረዝ ያጎሳቆላቸው ወንድምና እህቶችህ ፊት የማትጠግበው የእናትህ ፊት ከአንባገነን ስርዓት በላይ አስጨንቆ ወደስደት ሊገፋህ ባይናገሩትም ድረስልን ሲሉህ ሻንጣህን ይዘህ እንድትሰደድ ያስገድድሃል፡፡ አይተህ
ይችላል! ሂድና እርዳኝ የሚል ጎስቋላ ፊቷ ላይ እንባ እየጎረፈ በአንደበቷ 'አትሂድብኝ የምትልህ እናትህ ወደስደት ትገፈሃለች… አብሮ የሚበላ አብሮ የሚጠጣ' የምትለው ጎረቤት በተራ የዓውዳመት ድግስ ፉክክር፣ ለተራ የልብስና ጫማ ውድድር ወደ ስደት ሊገፋህ ይችላል. ህፃናት ወንድም እህቶቸ ጎረቤት የበዓል በግ ሲታረድ አይተው ተስማቸው ብለህ ነፍስህ ወደሚታረድበት ምድር ልትኮበልል ትችላለህ” ፋሲል ክርር ባለ ፊቱ መራር የራሱን ስደት እያስታወሰ ብሶቱን ዘረገፈው፡፡ የሁለተኛ ዓመት የህክምና ተማሪ እያለ ነበር አቋርጦ ወደ አሜሪካ የመጣው፡፡

ልጅቱ ልክ ፋሲል እንዳለው ቆይታ፣ ያውም መንገድ ላይ አውቶብስ ስጠብቅ፣ አዲስ
ቲዮታ ሃይላንደር መኪናዋን ድንገት እፊቴ አቁማ “ግባ ላድርስህ አለችኝ፡፡ ገባሁ።

በቀጥታ ይቅርታ! ባለፈው ትንሽ ባለጌ ሆንኩ፣ ልክ አልነበርኩም፡፡ ሥራ ቦታ አለመግባባት ምናምን ስለነበር እንደ ተበሳጨሁ ፊት ለፊቴ አግኝቼህ ጮኸኩብህ…ሶሪ ፈገግ አለች፤ ፈገግታዋ ያምራል፡፡

“ምንም አይደል?”

አዲስ ነህ መሰል?”

አዎ፣ ብዙ አልቆየሁም::”

እንኳን ደህና መጣህ! አሜሪካ ከተማርክ፣ ከጠነከርክ፣ ቆንጆ አገር ነት አለችኝ፡፡አመስግኜ እቤቴ በር ላይ ወረድኩ፡፡ መኪናውን በሚያስፈራራ ፍጥነት አዙራ እንደእብድ
ተፈተለከች፡፡ እዛ የብዙ ኢትዮጵያዊያን ህልም የሆነ ዘመናዊ መኪና ውስጥ የከሸፈ
ህልም ነበር፡፡

"አብርሽ!"

አቤት ዶክተር!

ሁነኛ፣ ቁመቷ ዘለግ ያለ፣ ቆንጆ፣ ለሚስትነት የምትሆን ልጅ አገር ቤት አታውቅም,,

"ልታገባ አስብክ እንዴ ዶክተር?”

አወቀ ብቸኝነት በቃኝ! ከአገር ቤት አንዲት ቆንጆ፡ጨዋ ሴት አግብቼ እርፍ ብዬ መኖር ነው የምፈልገው ትክ ብዬ አየሁት፡፡ ከሠላሳ ዓመት በላይ አሜሪካ ኗሯል፤ ብዙ ከመቆየቱ ብዛት፡
አሜሪካን ያገኛት እሱ ነው የሚመስለኝ:: ኢሕአፓ ጊዜ አሲምባ ወደሚባል ቦታ ዘምቶ፣ ጓደኞቹ ሲደመሰሉ እሱ ተርፎ አሜሪካ የገባ ሰው ነው። ከዚያ በኋላ ፖለቲካ የሚባል እርግፍ አድርጎ ትቶ፣ ፊቱን ወደ ትምህርት አዞረ: አንዳንዴ ግን እያገረሸት ፖለቲካ ማውራት ሲጀመር ማቆሚያ የለውም ፡፡ እዚያው ፋሲል ሱቅ ጓደኞቹ ጋ ሲመጣ ነው የተዋወቅነው:: ጥሩ ሰው ነው፡፡ ጨዋታ እና ሳቅ ይወዳል፡፡ ስለፈታት ሚስቱ ማውራት
ከጀመረ፣ ጥርስ እያስከድንም፡፡ እሱ እንደሚለው ከሆነ፣ ሚስቱ ቀናተኛ ነበረች፡፡“ተሳስቶ በቲቪ አንዲት ቀጭን ሴት ካደነቅሁ፣ ጧት ተነስታ መሮጥ ትጀምራለች፡፡አንዳንዴ በእልህ ረዥም ርቀት ሩጣ መመለስ ስለማትችል፣ ደውላ ና ወደ ቤት መልሰኝ ትላለች ይላል እየሳቀ፡፡ ሰው እንዴት መመለስ ወደማይችልበት ርቀት ይሮጣል?
ሃሃሃሃሃ

ታዲያ ስለ ፖለቲካ ሲያወራ በብስጭት ወደ እኔ እየተመለከተ “ፖለቲካ ሸርሙጣ ነው !ተመልከት፡ ከንጉሱ ጀምሮ የፖለቲካ እሳት ደሃውን እንጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ መሪዎችን አቃጥሎ አያውቅም፡፡ ካላመንክ አንድ በአንድ እያነሳን እንጫዎት… እዚህ አገር ተምሮ እና ተንደላቆ የሚኖረው ብዙኃኑ፣ ግፋ በለው! ሲል የኖረ ነው፡፡ መንግሥቱ ኃይለማርያም ያንን ሁሉ የደሃ ልጅ ማግዶ እሱ ዛሬ የት ነው? 'ዚንባቡዌ ተንደላቆ
ይኖራል፡፡ የኦነግ መሪዎችን ተመልከት፥ ወያኔዎችን ተመልከት ምን ሆኑ? ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርስ በእርስ ጦርነት ወጣቱ ነው የሚማገደው ሚስኪን ወጣቶች በፕሮፖጋዳ ያበደ አለማስተዋል ነው፡፡ ወጣት አልዋጋም ካለ፣ መሪዎች ሲጨባበጡ ነው የምታገኛቸው! እንዲህ ብለው ስንጥር አያነሱም፡፡ ምድረ ደም መጣጭ! ስንት ጓዶቻችን በርሃ ላይ ቀሩ! ስንት ጅኒየሶች! እንኳን ጦርነቱ፣ የፖለቲካ ወሬው ያደንዝሃል፡፡ ከዚህ ከብከተ እንቶፈንቶ ራቅ! ተማር! ተማር! አሁንም ተማር! ማንም መሀይም መተኮስ ይችላል! መግደል ጀብዱ አይደለም፤ ጅብም ሰው ይገድላል! ታይፎይድም፣ ወባም ሰው ይገድላሉ! ዓላማ የሌለው ሞት፣ አገር ሽርፎ ከመሸጥ እኩል
ነው ለምንድነው የምትሞተው?…ለምንድነው ወጣት የሚሞተው? ሊታረድ እንደሚነዳ
በሬ የማይረሳ ተስፋና ጥቅማጥቅም እንደ እርጥብ ሳር እያሸተቱ ወጣቱን ወደ ቄራ
ይወስዱታል፡፡ ወጣቱም ብልጥ የሆነ፣ ከሌላው የተለየ የገባው የረቀቀ፣ የመጠቀ አድርጎ
ራሱን ያያል ፤ሲሰተሙ ነዉ እንደዚያ የሚያደርግህ ከአንተ በላይ አዋቂ የሌለ መስሎ እንዲሰማህ እለፍ ብለህ እጅህን ስትዘረጋ አረፋ ነው ፡፡ ፖለቲካ እንኳን ይዘቱ ቅርፁ ለማንም ገብቶ አያውቅም ፤ፈሳሽ ውሃ ነው ፤ቅርፅ የለውም፡፡ አንተ ውስጥ ሲገባ አንተን ይመስላል፣ እኔ ውስጥ ሲገባ እኔን ሁላችንም ብርጭቆዎች ነን፡፡ በስልጣን ከፍ ያሉ
ያጋጩ ችርስ' የሚባባሉብን” በብስጭት ይናገራል፡፡ ሁልጊዜም እንዲህ ካወራ በኋላ
ሲጋራ ያጨሳል፡፡

ትምህርቱ በትክክል ለምን እንደሆነ እንጃለት፣ ብቻ በሆነ የባዮሎጂ ትምህርት ዶክትሬቱን ይዟል! አግብቶ ሁለት ልጆች ወልዶ፣ አድገው ዩኒቨርስቲ ገብተዋል፡፡ከሚስቱ ጋር የተፋቱት ከአራት ዓመት በፊት ነበር፡፡ ሰውዬው ታሪክ ብዙ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ አሁን ግን ዘለግ ያለ የሬሳ ሣጥን በመፈለጊያ
👍1
ዕድሜው፣ ዘለግ ያለች ሴት ይፈልጋል: ያውም ቆንጆ፣ ያውም ጨዋ፣ ያውም ልጅ እግር! መቼም ደግ ኑሮ ይዞት እንጂ ዕድሜው ስድሳን ሳይሻገር አይቀርም::

ታዲያ በዚያ ሰሞን ትልቅ መነጽሩን ይሰካና፣ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ላይ ሴት ሲያስስ ይውላል! አንድ የተረዳሁት ነገር፣ አሜሪካ ያሉ አንዳንድ ወንዶች፣ በተለይ ትንሽ ጥሩ ሥራና ገንዘብ ቢጤ ካላቸው፣ ድፍን የኢትዮጵያ ሴት አሜሪካ ያለ ወንድ ላግባሽ ካላት፣ ትዳር ቢኖራት እንኳ ጣጥላው የምትመጣ ይመስላቸዋል፡፡ ልከራከር ሞክሬ ነበር ገና አዲስ ነህ ዝም በል” ተባልኩ፡፡ ትዕቢት ያጠየመው በራስ መተማመናቸው የሚገርም ዓይነት ነው። እናም የዶክተር ጓደኞች (በእርሱ ዕድሜ የሚሆኑ) በየሳምንቱ

ቅዳሜ ከሰዓት ቁርጥ ሲበሉና ሲያወሩ ወደ ሱቋ ጎራ ሲሉ፣ ልክ እንደ ምግብ ቤት ሜኑ ኮራ ብለው በየስልኮቻቸው ሴት ይመርጣሉ፡፡ ቀፋፊ አስተያየት ሲሰጡ በግርምት እመለከታለሁ።

“ይቺ ጥሩ ናት ዶክተር” ይላል አንዱ፣ ፌስቡክ ላይ የአንዷን ፎቶ እያሳየ፡፡

"አይ!" ዛላዋ ከባድ ነው የግድ ይዛው ነው እንጂ አንድ ስትወልድ ዝርግፍግፍ ውድቅድቅ ነው የምትለው"
܀
“ይችኛይቱስ?"

“አይ! ይች ሥራዋ ፎቶ መለጠፍ ብቻ ነው እንደ ጉሊት ፌስቡከ ላይ ተሰጥታ የምትውል ላግባ እንዴ ደሞI?”

እሽ፣ ይች ምን ይወጣላታል? አፈር ስሆን ተመልከታት! ባላገባ ኑሮ አለቃትም ነበር
ሃሃሃሃሃ"

“ይች? እስቲ ከኋላዋ የሚያሳይ ፎቶ ካላት…ዋው ቢዩቲፉል! እስቲ እጇን ጠጋ አድርገው እስቲ እግሯ ….! ልቅም ያለች! እንዲህ ያለችዋን ነው ያልኩህ! የሳቀችበት ፎቶ የለም? ዋናው ፊት ነው ከፍትፍቱ ፊቱ ሃሃሃሃሃሃሃ..አቤት ጥርስ! አቤት ውበት
ምኑን ብትበላው ነው ባክህ? ይኼ ጤፍ እኮ ታምሩ ብዙ ነው! ሃሃሃ! እኔኮ የሚገርመኝ፣
ኢትዮጵያ አሥራ ሦስት ወር ሙሉ ፀሐይና አቧራ ሲከካቸው እየከረመ፣ እንዴት ነው ቆዳቸው እንዲህ የሚጠራው? ደሞ ቅላቷ! ማነው ስሟ? ፊደላዊት… ስሟ ራሱ ማማሩ እሷ ራሷ የግዜር የእጅ ጽሑፍ አይደል እንዴ የምትመስለው! ፓ! ስሟ አፍ ላይ መጣፈጡ ምራቁን ዋጠ ዶክተር፡፡ ትንሽ ስልኩን እየጎረጎረ ቆዬና “አይይይይይይ" አለ

"ምነው?"
ተይዛለች ኢን ርሌሽንሽፕ ይላል ስታተሷ…ወንዱ መች ተኝቶ ያድራል “

ሃሃ…ይችን ይችን ለኛ ተዋት… ዝም ብለህ ጻፍላት…” በየአፋቸው እየተንጫጩ አበረታቱት !ዶክተር ጻፈላት!.....



አንብበው ጨርሰዋል አሁን ደሞ ከዚሁ ሳይወጡ #UNMUTE አድርገው ይውጡ አመሰግናለው

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#አልጠግብሽም

ምነው ምን ነካቸው?
አይንና ጆሮዎቼ
ቅጥ ያጡት፣
እያዩሽም...
እየሰሙሽም...
ረሃብ የማያጡት፣
ያም አልበቃ ብሏቸው
አይኔን ብከድን
ላፍታ ሸለብታ፣
አንችኑ ያያሉ...
አንቺኑ ይሰማሉ...
በህልሜ ውልብታ፣
መች ይሆን...
ውበትሽን አይቼ
'ምጠግበው?
መቼስ ይሆን...
ድምፅሽን ሰምቼ
'ምሰለቸው?
ሁልጊዜ...
አንችኑ እራባለሁ...
ዘወትር...
አንቺኑ እጠማለሁ...
አጠገቤ እያለሽም...
አንቺን...አንቺን እላለሁ፣
ሆኖም...
መች እጠግብሻለሁ ? !!
አልጠግብሽም ስልሽ...

🔘ሃብታሙ ወዳጅ🔘
#ምትክ_የለሽ

አንቺን ያለው ልቤ
አንቺን ብቻ ፈቅዶ፣
በፍቅር ተገዶ...
አንቺን ብቻ ወዶ፣
መካሪ ነን ያሉ...
"እልፍ ቢሉ...
እልፍ ይገኛል" እያሉ፣
ቢመክሩኝም ቅሉ፣
እልፍን ላላገኘው
በድብቅ ተሸሽጎኝ፣
ይኸው ስንት ዘመን
ማለፍ ብቻ ተርፎኝ፣
እልፍ አእላፉ ሁሉ
በፍቅር ሲለካካ፣
አላገኘሁም ጭራሽ
አንቺን የምትተካ !!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_ሶስት(የመጨረሻ ክፍል)


#በአሌክስ_አብርሃም

ተይዛለች ኢንሪሌሽንሽፕ ይላል ስታተሷ…ወንዱ መች ተኝቶ ያድራል “

ሃሃ…ይችን ይችን ለኛ ተዋት… ዝም ብለህ ጻፍላት…” በየአፋቸው እየተንጫጩ
አበረታቱት !ዶከተር ጻፈላት!

1

2

3ቀን

መለሰች፡፡ መልሶ ጻፈላት

4..

5...

መለሰችለት፡፡ የጻፈውን ጮክ ብሎ ያነብልናል፡፡ የመለሰችውንም እንደዛው :: በግልጽ ፎቶዎችሽን አይቼ ደስ ስላሉኝ መተዋወቅ ፈለኩ፡፡ ብችልና ስልከሽን ብትሰጭኝ ደውዬ ብናወራ ደስ ይለኛል”ብሎ ጻፈላት ስልኳን ትልካለች፣ አትልከም፣ ውርርዱ ቀለጠ፡፡
ጭራሽ ከየዋሌታቸው የመዘዙትን የውርርድ ገንዘብ፣ እኔው ያዥ ሁኜ አረፍኩ፡፡ ትንሽ
ውስጤን ጸጸተኝ! አንዲት ነገር ዓለሙን የማታውቅ፣ በአዲሰ አበባ ብልጣብልጥነት፣
የሕይወትን ማሳለጫ የምታቋርጥ በመሰላት ሚስኪን የአገሬ ቆንጆ ላይ፣ ዕጣ ሲጣጣሉ
ማስጣሉ ሲቀር፣ የውርርድ ገንዘብ ያዥ መሆኔ፣ ውስጤን እንደ አንድ ነገር ሲያቃጥለው
ይሰማኛል፡፡ የወጋሪዎቹን ልብስ ጠባቂ ሆንኩ፡፡

7..8... 9 ስልኳን ላከችለት፡፡

የውርርዱ ገንዘብ ጥሬ ሥጋ ተቆረጠበት፡፡ ውስኪ ወረደበት፡፡

“አብርሃም ና እንጂ …”

“ጥሬ ሥጋ አልበላም

“ማነሽ ጥለሽለት”

“ያዝ ውስኪ

አልጠጣም

"ለስላሳ አምጭለት …”

11..12….13….14 ምን እንዳላት እንጃ…ምን እንዳወሩ እግዜር ይወቅ፣ ዶክተር በደፈናው
“ስለቁም ነገር እያወራን ነው” አለ፡፡ ከዛን ቀን ጀምሮ የዶክተር ጓደኞች ስለልጅቱ ሲያወሩ
ቆጠብ ማለት እንደጀመሩ አስተዋልኩ፡፡

15.. 16….17…18.…19..20 ቀናት አለፉ፡፡ ገርሞኝ የፊደላዊትን የፌስቡክ አካውት በዓይነቁራኛ እከታተላለሁ ትሰጥፈዋለች ይኼን ፎቶ! በምኞት የሰከረ ወንድ ከሚያጎርፈው ላይክ መኻል፣ ዓይኔ ዶክተርን ይፈልጋል፡፡ አገኘዋለሁ! “ላይክ ያደርጋል፡፡ ፈገግታዋ አንዳች የሚነዝር ውበት አለው፡፡ አንድ ወር..ሁለት ወር..ዓይኔ
ነው ወይስ ..እስከምል የፊደላዊት የፌስቡከ ስታተስ' ተቀይሮ አረፈው::
"relationship" የነበረው ወደ "open relationship" ተቀይሯል።

የሽማግሌዎቹ ባሕሪ ቁማር ነበር፡፡

“ተከፈተ! ሃሃሃሃ… አላልኩህም! ገና ሲንግል ትሆናለች” አለ አንዱ ሽማግሌ፡፡ ሌላው ይቀበላል…

"ሲንግል ምን አላት? ገና ድንግል ትሆናላች፡፡ አሜሪካኮ ነው 'ብራዘር …ሃሃሃሃሃ ኡሁ!
ኡሁ ሳል የቀላቀለ የሽማግሌዎች ሳቅ

ፋሲልን “ይችን ልጅ ማስጠንቀቅ አለብኝ” አልኩት፡፡

“አንተ ምን ቤት ነህ? አርፈህ ተቀመጥ!”

“ምንም አይሰማህም? ይች ልጅ ነገ መጥታ እንደ እነሯ የስቃይ ሕይዎት ውስጥ ብትገባስ?
እዚህ እንድ ሐሙስ የቀረው ሽማግሌ ጋር ምንድነው የምትሆነው?”

ለምን ግማሽ ሐሙስ አይቀረውም! …ሲጀመር ልጅቱ ራሷ ምቀኛ ነው የምትልህ፡፡ ወር እንኳን ሳይሞላት፣ በሯን ስትከፍት አይገባህም እንዴ? አዲስ ነህ! እንዲህ ዓይነት ነገር ውስጥ ጣልቃ አትግባ! እነዚህ በተንኮል ጥርሳቸውን የነቀሉ ሽማግሌዎች አንዴ ከጠመዱህ፣ጥሩ አይደለም. ወዲህም ገባያዬን እንዳትዘጋው… ሄደው አንዲት ቃል ቢተነፍሱ ሐበሻ እዚህ ሱቅ ዝር አይልም” ዝም አልኩ፡፡

ፊደላዊት ደወለች! ደወለች… ደወለች ቤቢ…… ደወለች…" ጎበጥ ጎበጥ እያለ ወደ ውጭ ይወጣል ዶከተር፡፡ አይመለስም! ለሰዓታት ስልክ ላይ ነው! ቀናት ሄዱ፣ ወራት ተከተሉ፣ ሁለት፣ ሦስት፣ አራት ወር፡፡

ምናገባኝ ብዬ መከታተሌን ትቸ ከርሜ አንድ ቀን ሳላየው የቆየሁትን የፊደላዊትን አካውንት ተመለከትኩ፡፡ ጭር ብሏል፡፡ የለጠፈቻቸውን ፎቶዎች ሁሉ አንስታቸው ነበር፡፡ ምን መጣ ብዬ መመልከቴን ቀጠልኩ፡፡ ከረዥም ቀናት መዘናጋት በኋላ ስመለስ፣ ስታተሏ ሲንግል” ሆኗል። ደነገጥኩ! ፍቅረኛዋ በአደጋ ሞቶ መሆን አለበት አልኩ ለራሴ፡፡ ዝግመተ ለውጥ እንዲህም ፈጥኖ አያውቅ:: አዎ ዝግመተ ለውጥ፡፡ እንዲህ ነበር ዝንጀሮ መሰል ፍጥረት ቀስ በቀስ ወደ ሰው ተቀየረ ያሉን፡፡ መሆን አለበት:: ቀን ከተለጠው፣ ዝንጀሮም ሰው፣ ሰውም ዝንጀሮ መሆን ሳይችል አይቀርም: ሰው የአገርህ ልጆች በረሃ አቋርጠው ተሰደዱ ሲባል ከንፈር ይመጣል፡፡ እግርማ በረሃን አቋርጦ ካለፈ እሰዬው ነው፡፡ እንዲህ ልቦቻችን ውስጥ ያቆጠቆጠውን ሰውነት፣ ፍቅር፣ እውነት፣
ጨፍጭፈን ዘላለም የማንሻገረውን በረሃ ልባችን ውስጥ ከመፍጠር የባስ፣ ከንፈርየሚያስመጥጥ ምን ሰቆቃ አለ?

አንድ ምሽት ድንገት ዶክተር ደወለና “ወደ አገር ቤት የምትልከው ቀለል ያለ ነገር ካለ፣ ነገ ይዘህ ና፣ መሄዴ ነው አለኝ

“የት?”

አገሬ ነዋ! ጕዳይ አለኝ” አልጠየኩም፣ ጉዳዩ እንዲሁ ይገባኛል!

ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ዶክተር ወደ ኢትዮጵያ ከሄደ ከሃያ ቀናት በኋላ የፊደላዊትን የፌስቡክ አካውንት” ተመለከትኩ፡፡

“ሰው ዝም ብሎ እግዚአብሔርን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው ከሚል ጥቅስ ጋር ረዥም ቬሎ ለብሳ ፣ብቻዋን የተነሳችው የሚያምር ፎቶ ተለጥፏል። ቬሎዋን ሳይ ያንን ትኩስ ሰውነት በበረዶ ያጀሎት ዓይነት ሰውነቴ ቅዝቅዝ ሲል ተሰማኝ፡፡ እጅግ በጣም ብዙ የእንኳን ደስ አለሽ አስተያየት ጎርፎላታል።

እግዚአብሔር የቅኖች አምላክ ነው?”

“ይገባሻል የኔ ቆንጆ?”

“የእብርሃም የሣራ....በሳምንቱ ከቤተሰቦቿ ጋር በወርቃማ ጥልፍ ያበደ ጥቁር ካባ ለብሳ፣ በሹሩባዋ ሳይ ወርቃማ አከሊል ደፍታ፣ የማላውቃትን ንግሥተ ሳባ መስላ
(ለምን እንደሆን እንጃ እንደዚያ መሰለችኝ) የተነሳችውን የምላሽ ፎቶ ለጠፈች፡፡ በጣም
ውብ ልጅ ነት፡፡ ያንለታውኑ ከአሥር በላይ የሚሆኑ ተደጋጋሚ የሰርግ ፎቶዎቿን
ለጠፌች፡፡ መንፈስ ያገባች ይመስል አንዱም ላይ የባሏ ፎቶ የለም።

ፋሲል እየሳቀ እና የአንድ ሽማግሌ ፎቶ፣ ባል ብላ ለጥፋ ሐበሻ ለብር ነው ለቪዛ ነው እያለ፣ አዛ ያድርጋት እንዴ? ዋናው ማግባቷ ነው፣ በቃ!” አለቀ፡፡ ከሠርግ የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፣የእኔ ባሉት ነገር እየታፈረ እንዴት ይኖራል?… እያልኩ ፎቶዎቹን እመለከታለሁ፡፡
ዓይኔ አንዱ ፎቶዋ ላይ አረፈ፡፡ ዓይኖቿ እንባ ሞልተው፣ በሚያማምሩ ጣቶቿ አፏን
እፍና፣ እናትና አባቷ ፊት ለስንብት ቆማለች፡፡ ፋሲልን አሳየሁት፡፡“ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ!” ብሎ እንደሚተርት እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ግን እንደዚያ አላለም፡፡ ቅሬታ ይሁን ሐዘን ባረበበት ፊት፣

“የእንባ ቀብድ! ብሎ ዝም አለ፡፡

የዶክተርን አካውት ተመለከትኩ፡፡ ጭር ባለው የፌስቡክ አካውንቱ ላይ፣ አንዲት ዐረፍተ ነገር በጎሉ እንግሊዝኛ ፊደላት ተለጥፋለች፡፡

love never gets old"

ፍቅር አያረጅምህ!


አንብበው ጨርሰዋል አሁን ደሞ ከዚሁ ሳይወጡ #UNMUTE አድርገው ይውጡ አመሰግናለው

ጨረስን

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍41
አትሮኖስ pinned «#የእንባ_ቀብድ ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት(የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ተይዛለች ኢንሪሌሽንሽፕ ይላል ስታተሷ…ወንዱ መች ተኝቶ ያድራል “ ሃሃ…ይችን ይችን ለኛ ተዋት… ዝም ብለህ ጻፍላት…” በየአፋቸው እየተንጫጩ አበረታቱት !ዶከተር ጻፈላት! 1 2 3ቀን መለሰች፡፡ መልሶ ጻፈላት 4.. 5... መለሰችለት፡፡ የጻፈውን ጮክ ብሎ ያነብልናል፡፡ የመለሰችውንም እንደዛው :: በግልጽ…»
#የዘመኑ_ተማሪ

“እ....ሺ ተማሪዎች” አሉ መምህሩ
በክፍለጊዜያቸው ተሜ'ን ሊያስተምሩ፡-

“እ....ሺ ተማሪዎች
ዛሬ ምንማረው
ስለ ድንቅነሽ ነው፡፡

ድንቅነሽ አፅም ናት እስትንፋስ የሌላት፤
ድንቅነሽ ህያው ናት ዘመን የማይገላት፤
ድንቅነሽ ታሪክ ናት ጥንትን የምትዘክር፤
ድንቅነሽ እውነት ናት ነገን ምትመሰክር፡፡

የኛዋን ድንቅነሽ ፈረንጆች ሲጠሯት
ሉሲ ነው የሚሏት፡፡
ሉሲ አሮጊት ነች ድሮን የምታሳይ ፤
ሉሲ ኮረዳ ነች የዘመኑ አማላይ ፤
ሉሲ የዓለም ነች የሰው ዘር ሁሉ እናት፧
ሉሲ የአገር ልጅ ነች የኢትዮጵያ ኩራት፡፡
ቅርስ ነች፣ ውርስ ነች የተፈላጊ ሐብታም፤
ውበት ነች፣ ቆንጆ ነች የአጥንት ደም ግባታም፡፡

በ'ርግጥ ተማሪዎች
ስለ ሉሲ ታሪክ ስለ ህያዋ አፅም
እንኳን በዚች ሰዓት በአርባ ደቂቃ አቅም
ዘመናትን ሙሉ

ቢነገር፣
ቢነገር፣
ቢነገር አያልቅም::
ምክንያቱም
በግልፅ እያየናት
ድንቅነሽ ሚስጥር ናት፤
በእጅ እየነካናት
ድንቅነሽ ሩቅ ናት፤
በአጭሩ
ድንቅነሽ ድንቅ ናት፡፡”

( ስለ ሉሲ ታሪክ - ስለ ሉሲ ጥቅም - ስለ ሉሲ ገላ
በሚችሉት መጠን - በአርባ ደቂቃ ውስጥ ካስረዱ በኋላ )

“መልካም ተማሪዎች
በዛሬው ገለፃ (በድንቅነሽ ዙሪያ) ግልፅ ያልሆነላችሁ
ከመውጣቴ በፊት ጥያቄ ካላችሁ?”
አሉ መምህሩ
ወደ ተማሪ እጆች በዓይን እያማተሩ፡፡

አንዱ እጁን አወጣ ጸጉሩን እያሻሸ
“እዛጋ!” አሉ ጋሼ

(ተማሪው ቀጠለ
ከርዳዳውን ፀጉሩን እየጠቀለለ)፡-

"ቴንኪው ቲቸርየ!
እውነት ለመናገር
የድንቅነሽ ታሪክ በጣም ፀድቶብኛል
የርስዎ ገለፃም
እንደተለመደው ግልፅ አድርጎልኛል፤
ግን ያልገባኝ ነገር
ይህች ተዓምረኛ ሉሲ 'ምትባለው
የአለምን ሳይንቲስት በሐሳብ ከፋፍላ ምታወዛግበው
የሰው ዘር ሁሉ እናት ፤
የኢትዮጵያ ኩራት፤
የአለም ልዩ ፍጡር፤
የእኛነት ምስክር ፤
ወዘተ ወዘተ......
ተብላ እየተጠራች የምትወደሰው
የኛዋ ድንቅነሽ
ብሔሯ ምንድን ነው???”

🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
#የሌለኝ

እኔስ አገር አለኝ - የተወለድኩበት
ውብ ሰፈርም አለኝ - ጭቃ ያቦካሁበት
የሌለኝ ገንዘብ ነው - ዳቦ ምገዛበት፡፡

እኔስ ጉልበት አለኝ - ምጠነቀቅለት
ሙሉ አካልም አለኝ - ምተማመንበት
የሌለኝ ወኔ ነው ስራ - ምሰራበት፡፡

ምን ጉልበት ቢጠጥር ቢለካ በፈረስ
ሙሉ አካል ታቅፈው - ቁጭ እስካሉ ድረስ፣ ፣
ሆድ እየተራበ - አረቄ ይጠጣል
የሚበላው አጥቶ - ጨጓራ ይላጣል
ሺህ ዳቦ ቤት ቢኖር -
ዳቦ ከየት ይመጣል???

🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
#የትዕዛዝ_ቅኔ

( 1 )
እዚህ በ'ኛ መንደር
እያደር እያደር
ያዛዥና ታዛዥ - መራራቁ ሰፋ
ያም 'አዞ' ፣ ያም አዞ - የሚታዘዝ ጠፋ፡፡

(2)
ያም አዞ ያም አዞ - መታዘዝ ከሞተ
አዳኙን' ይበላል - ህዝብ እየሸፈተ፡፡

🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
#የመመሳሰል_ፀብ

የእኔና አንቺ ችግር፡-
አይደለም ቋንቋችን - በመዘባረቁ፣
አይደለም ጎጇችን - በማጨናነቁ፣
አይደለም ባህላችን- ልዩነት መፍጠሩ፣
'መለያየታችን' - አይደለም ችግሩ፡፡

የኔና አንቺ ችግር፡-
በብዙ ነገሮች “መመሳሰላችን
መደመጥን እንጂ፣
ማዳመጥ የማንወድ ሰዎች መሆናችን፡፡

የኔና አንቺ ችግር፡-
በጸባይ በምግባር - አንድ መሆናችን
ነገር እየበላን - እህል መራባችን፡፡

ያው እንደምታውቂው-

ፍቅር እየተራበ - ነገር ተመጋቢ - እያደር ይከሳል
በምላስ የቆመ - ጆሮ የሌለው ቤት - በጩኸት ይፈርሳል፡፡

በቀላል መፍትሔ - የተናጋውን ቤት - ሲቻለን ለማደስ
በተራ ምክንያት - ፍቅራችን አክትሞ -ቅጥራችን እንዳይፈርስ፤
አንዴ እንነጋገር፣
አንዴ እንደማመጥ - ግዴለሽም ፍቅሬ
ምንድን ነው ችግርሽ!?
ምንድን ነው ችግሬ!???

🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
🥰1
#እድሜ

የሰው ህይወት አጥር
የቁጥር ስብጥር፣
አንድ
ሁለት
ሶስት
አራት
.
.
.
ጠብ
ጠብ
ጠብ
ይላል በቁጥር፤
ከሰው ወደ ምድር
ከምድር ወደ ሰው፣
የእስትንፋስን ድንበር
የእስትንፋስን አጥር
በአንድ ጊዜ ሊያፈርሰው፡፡
.
የቁጥር ገበታ
የቁጥር ጠብታ፣
በቁጥር ተሞልቶ
ቁጥርን አንጠባጥቦ
ቁጥርን ባዶ ሊያስቀር
ጠብ
ጠብ
ጠብ
ይላል በቁጥር፡፡

ሲንጠባጠብ ኖሮ
ይደፋል በሙሉ ከሰው ወደ ምድር
ተምሶ ሊቀበር፡፡

🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘
#ጨረሬን


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

እማማ ሞቱ !!

ትላንት ልክ ፀሐይ ስትጠልቅ፤ እማማ ይችን ዓለም ተሰናበቱ !

ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ከአልጋ ወርደው የማያውቁት ሚስኪን ሴት፣ የሰፈሩን ሰው ሁሉ እንዳኮረፉ ሞቱ። ዘጠኝ ዓመት አስታመን፣ እንደ እናት ተንከባክበን፣ ባለቀ ሰዓት ረግመውን ሞቱ” እያለ የሰፈሩ ሰው በሙሉ አዘነ: አፍ አውጥተው አይናገሩት እንጅ ያስረገምከን አንተ ነህ” የሚል ወቀሳቸውን ከእያንዳንዳቸው ዓይን ላይ እይቻለሁ፡፡እኔም ምነው በቀረብኝ ብዬ በውስጤ ስብሰለሰል ሳምንት አለፈኝ፡፡ የሆነ ሆኖ እማማ
ላይመለሱ ከነኩርፊያቸው አሸለቡ፡፡ ለነገሩ ኩርፊያ ይሁን ሐዘን ማንም አልገባውም:
በኩርፊያና በሐዘን መሃል ያለው ልዩነት ምንድነው? ምንስ ነው በቁጣና የኩርፊያ
መካከል ያለው መስመር? …መዝገበ ቃላት ቃላትን እንጅ ስሜትን አይፈታም፡፡ እማማ፡
በምናውቃቸው ቃላት የገለፅነው የማናውቀው ስሜት ውስጥ የነበሩ ይመስለኛል፡፡ የሕይወት ታሪካቸው ሲነበብ በደፈናው “የሁላችንም እናት ነበሩ” ከሚል የወል ምስጋና ውጭ እምብዛም የተዘረዘረ ነገር አልነበረም:: አስክሬናቸው በአራት የሰፈራችን ወንዶች ትስሻ ላይ ተቀምጦ በቀባሪው አጀብ በቀስታ ወደ መቃብር ቤቱ ጓሮ ሲጓዝ እእምሮዬ ወደትዝታው የኋሊት ነጎደ ፡፡

የዛሬን አያድርገውና ከሊቅ እስከ ደቂቅ መዋያችን እማማ ቤት ነበር፡፡ የእማማ ቤት እንደው ቤት ሆነ እንጅ ነገረስራው ድድ ማስጫ የሚሉት ዓይነት ነበር፣ ሕፃናቱ እማማ ቤት በር ላይ እቃቃቸውን ሲደረድሩና ሲያፈርሱ፣ የእቃቃ ሰርግ ሲደግሱና
ሲጋቡ፡ወጣቶቹ ተሰብስበን ካርታና ዳማ ስንጫዎት፡ ስለሴት ስናወራና ስናውካካ እንውላለን እሁድ እሁድ የሰፈሩ እድር ዳኞች እና የዕቁብ ገንዘብ ሰብሳቢዎች እዚያው እማማ ቤት ተሰብስበው ሲነታረኩ ያረፍዳሉ፤ ያ አንድ ክፍል የቀበሌ ቤት ሁል ጊዜ ከጧት እስከ ማታ በሩ ክፍት ነበር።

በዛ ዕድሜ እንደ እማማ ዓይነት ረዥም እና ቆንጆ ሴት አይቸ አላውቅም፤ በድህነት ተጎሳቁለው እንኳን ጥርት ያለ ጠይም ቆዳቸውና ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ፀጉራቸው አንዳች ሞገስ ነበረው ስለ ረዥም ቁመት ሲወራ ምሳሌ ነበሩ እንደ እማማ ዠርጋዳ ይባላል፡፡ ዠርጋዳ ነበሩ፤ ሲራመዱ የሚንሳፈፉ የሚመስሉ፡፡ በስተኋላ ዘመናቸው እርጅና ተጭኗቸው፣ ትንሽ ከወገባቸው ጎበጥ ብለው እንኳ በቁመት የሚስተካከላቸው
እልነበረም፡፡ ባልም ልጅም አልነበራቸውም፡፡ መተዳደሪያችው ሰርግና ድግስ ሲኖር ወጥ
በመስራት ነበር፤ ታዲያ ወጥ ሳይቀምሱ በሽታው የሚያውቁ ባለሙያ ናቸው ይባላል።
ሴት ልጅ የወጥ ማማስያ ከላሰች ምኑን ሴት ሆነች ኤዲያ !?” ይላሉ፤ውጥ ሲቀመስ ሲያዩ
እይወዱም:

እማማ ለምን ባል አያገቡም? ስንላችው፣

“በልኬ ወንድ አጣሁ፤ ጨርሶ ኩርፋድ አጎንብሸ ላግባ እንዴ…? ይሉና ይስቃሉ፤ ጨዋታ
እዋቂ ናቸው :

ታዲያ ዓመቱን ሙሉ ማድቤት ለማድቤት ከርመው ለጥምቀት ጽዓል ፀጉራቸውን ተሰርተው፣ሰፊ ባለባንዲራ፣ ጥለቱ ጉልበታቸው የሚደርስ ያበሻ ቀሚሳቸውን ይለብሱና፣ በወገባቸዉ ላይ ሶስት አራት ዙር ተጠምጥሞ ጫፉ ወደታች የሚንዘረፈፍ መቀነታቸውን ሸብ አድርገው፣ ክብ ሰርተው የሚጨፍሩ (እሳቸው “የአገሬ ሰዎች የሚሏቸው) ወንዶች መኻል ገብተው ምንጃርኛ የሚባል ዘፈን እያወራረዱ ጭፈራቸውን ያስነኩታል:እማማን ለማየት የማይመጣ ሰው የለም እማማ መጡ ክፈቱላቸውም ይባላል … ክቡ የሰው ቀለበት በመጡበት በኩል ተከፍቶ ይገባሉ… የታወቁ ናቸው !

ቸብ ቸብ ቸብ ሲዴረግ እማማ እጃቸውን ከፍ አድርገው …

“የምንጃር ልጅ …ሽቅርቅር ብለሺ ነይ ነይ ዙረሺ
ይላሉ፣

የከበበው ህዝብ ይቀበላቸዋል፤ ሕዝቡ ድንገት ለጥምቀት የተሰበሰበ ሳይሆን አብሮ ግጥምና ዜማ ሲያጠና የከረመ ነበር የሚመስለው!

ኢሄ የጀግናው አገር
.
እዛው ምንጃር …

ወረዶች ሸንኮራ …

ስንዴ ልትበላ፣

ወረደች ምንጃር ….

የጤፍ አገር፤

ተይ አብሪው ኩራዙን …

ሳትፈጅው ጎዙን፤

“ያዝ እንግዲህ!” ብለው በዛ ቁመት ድንገት ወደላይ እየዘለሉ ሲመለሱ በፀጉራቸው
የግዜርን ዘርፋፋ ቀሚስ ነክተው የሚመለሱ ነበር የሚመስሉት! ጭብጨባው፣ ጩኸቱ፣ሳቁ ይደምቃል ጎን ለጎን የተደረደሩ ጨፋሪዎች በከበበው ሰው ጭብጨባ ፊትም ልክ
በአንድ ላይ ሸብረክ ሸብረክ… ሸብረክ እያሉ ወደፊት ወደኋላ እተራመዱ ሲጨፍሩ
የተለየ ስሜት ነበረው፡፡

እዛ ማዶ፣

አሃ

ከተራራው!"

አሃ.!

ዓይኑ ነው ወይ፤

እሃ፣

የሚያበራው፧ - የሰሌን ባርኔጣ በቀኝ እጃቸው የያዙ ጨፋሪ ወንዶች በአንድ ላይ ባርኔጣቸውን ከፍና ዝቅ እያደረጉ ሲጨፍሩ አቧራው ይጨሳል …እማማ እንደዛ ነበሩ፡፡

በሰፈሩ ሰው ዘንድ እማማ የሚለው ቃል የወል ስምነቱ ቀርቶ የዚቹ ሴትዮ መጠሪያ ከሆነ ዘመን የለውም፡፡ ሰፈራችን ውስጥ የሚኖሩ ሰዕድሜ የገፉ ባልቴቶች ሁሉ እማማ ከሚለው ቀጥሎ ስማቸው ይጠራል፡፡ እማማ ተዋሱ ፡እማማ ዮሃና፣ እማማ ብርነሽ እማማ ግን እማማ ብቻ! የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ታዲያ ለማኅበር ድፎ ደፍተው ማድቤት ጉድ ጉድ ሲሉ ራሳቸውን ስተው እሳት ላይ ወደቁ፣ እሳቱ ግራ ክንዳቸውና በግራ
በኩል ያለ የራሳቸው ፀጉር ክፉኛ ተቃጠለ የግራ ጆሯቸውም በከፊል በእሳቱ ተጎድቶ ነበር፡፡ ያ የተረገመ አደገ የእማማ ጠይም ፊት ላይ በግራ በኩል ለማየት የሚያስፈራ የእሳት ጠባሳ ትቶባቸው አለፈ። ይሄም ባልከፋ ነበር፤ከአደጋው በኋላ ሁለት እግሮቻቸውና የቀኝ እጃቸው አልታዘዝ አላቸው… የግራ እጃቸው ብቻ ነበር የሚሰራው፡፡
በቃ እልጋ ላይ ዋሉ ሰው ደግፎ ካላነሳቸው በስተቀር ከአልጋቸውም መነሳት አይችሉም
ነበር፡፡

የሰፈሩ ሰው ደግ ነው እየተቀያየረ እማማን ለዘጠኝ ዓመታት አስታመመ፡፡ ቤታቸው
ሰው አይጠፋም፣ ከጧት እስከማታ የእማማ ቤት አደባባይ ነበር፤ መንደርተኛው ከልጅ እስከአዋቂ እማማን እየረዳ እግረመንገዱን ቤታቸውን መዋያ መቀጣጠሪያው አደረገው፡፡እማማ ትራሳቸውን ደገፍ ብለው ወጣቶቹ ሲጫወቱ እያዩ፣ አዋቂዎቹ ሲያጫውቷቸው እየተጫወቱ (እንደዛም ሆነው ጨዋታቸው ለጉድ ነበር ) ዘጠኝ ዓመታት አለፉ ።

እንድ ቅዳሜ ቀን ከሰዓት አምስት የምንሆን የሰፈር ልጆች ሰብሰብ ብለን እማማ ቤት ካርታ እንጫዎታለን ፡፡ ድንገት ዓይኔ እማማ ላይ ሲያርፍ የቤቱ ጣራ ላይ ባለች ሽንቁር የገባች ጨረር የብርሃን ዘነጓን ዘርግታ እማማ ጠይም ቆዳ ላይ የቀኝ ግማሽ ከንፈራቸውና የአፍንጫቸውን ጫፍ ያካለለች የብርሃን እንጎቻ ሰርታ ተመለከትኩ፡፡ አንዴ የጣራውን ሽንቁር አንዴ እማማ ፊት ላይ ያረፈውን ክብ ጨረር እያየሁ “ይሄ ሽንቁር ዝናብ ሲዘንብ

አልጋቸው ላይ ውሃ ያንጠባጥብባቸው ይሆን? ብዬ አሰብኩ፤ ጣራውን በሙሉ ስመለከተው ጥላሸት ሸፍኖታል፡፡ የጣራ ከዳኑ ቆርቆሮ እዚያና እዚህ ተበሳስቶ ጥቃቅን የብርሃን ነጠብጣቦቹ ጥቁር ሰማይ ላይ የተዘሩ ከዋከብት መስለዋል ።
ጓደኞቼ ጋር ተያይዘን ስንወጣ “ ለምን የእማማን ጣራ አናድሰላቸውም - አይታችሁታል? ጨረር ሁሉ ያስገባባቸዋልኮ” አልኳቸው… እኔም ሳስብ ነበር… እኔም… እያሉ በየአፋቸው ተንጫጩ፡፡ እንዲህ ነበር የተጀመረው፡፡ ለአንድ ሳምንት ቤት ለቤት እየዞርን ብር አሰባሰብን፤ ጎረቤቱ ሁሉ ደስ እያለው ካሰብነው በላይ ብር አዋጣ፡፡ እንደውም
አንዳንዶቹ ለራሳቸው ጉዳይ ገዝተውት ከተረፋቸው ማገርና ኣውራጅ እየቀነሱ ውሰዱ
አሉን ፡ ግርማቸው የሰፈራችን እናፂ ስራውን በነፃ ሊሰራ ቃል ገባልን ደግሞ ለማማ ብር ልቀበል እንዴ!?” ብሎ ::

በሳምንቱ እማማን ለማስደነቅ በማሰብ ሳንነግራቸው ቤታቸውን ለማደስ ወሰንንና አልፎ
አልፎ እንደምናደርገው አንድ ሁለት
👍1