አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ፍላት የማይመስላት ሴት አይደለችም፡፡ አዎ! እንዲያልፍላት የግድ ወንድ በእግሮቿ መሃል ማለፍ የለበትም ጠንካራ ሰውነት ነው ያላት፡፡አንተን ጨምሮ እዚህ ሰፈር ያላችሁ ወንዶች፡ አብራችኋት መተኛት ይቅርና፣ አብራችኋት ፎቶ መነሳትን እንኳን እንደትልቅ ውለታ ልትቆጥሩት
ቆንጆ አይደለችም! ሲኒማ ጋብዛችኋት ታውቃላችሁ? አታውቁም፡ ምክንያቱም ቆንጆ
ትፈልጋላችሁ፡፡ የፍቅር ደብዳቤ ጽፋችሁላት ታውቃላችሁ?አታውቁም! ምክንያቱም ቆንጆ
ኣይደለችም! ሌላው ይቅር፣ አንድ ቀን እንኳን የለበሰችውን ልብስ አምሮብሻል ብላችኋት
ታውቃላችሁ? ያው ሚዜ ሆነህ አየሁህኮ፣ ለእኔ ቤተሰቦች ምከንያቱ ምንም ይሁን፣
ለአንተና ለመሰሎችህ ግን፣ ጕዳዩ የፎቶም የእኔ ሰርግ መድመቅና አለመድመቅም አይደለም፣ ወሲብ ነበር! ዋናው ፉከተር ወሲብ ነው! ብትችሉ አንሶላ ለመጋፈፍ፣ካልተሳካም በየትኛውም አጋጣሚ የምታገኟትን አብራችሁ የምትቆም ቆንጆ ሴት… ጡትና እግር እያያችሁ፣ በሽተኛ ምኞታችሁን ታስታምማላችሁ! ማምሻን በተለሳለሰ ብልግና ገፍተህ፤ ከእዚያች ነርስ ጋር ጨዋ ጨዋ ስትጫወት፣ በገባች በወጣች ቁጥር ዘመናዊ ለመሳል ወንበር ስትጎትት አበሳጭተኸኛል እሷም ስትገለፍጥልህ ነበር፡፡ ምናልባትም አብረኻት ተኝተህ ይሆናል። ሁለታችሁም ገደል ግቡ…” ይውጣላት ብየ ዝም አልኳት፡፡

“ማምሻ ተገፍቶ ተገፍቶ ግድግዳ ጋ የተጣጋ፣ ልሽሽ ብትልም መሸሻ በሌለው የመገፋት
ጥግ ላይ ነው ያለችው::ማኅበረሰቡ ግን አሁንም መግፋቱን አላቆመም፣ ያላት አማራጭ፣
ወይ በገፊ ማኅበረሰብና በማትገፋው የእድል ግድግዳዋ መሃል ተጨፍልቃ መሞት
አልያም በእነዚህ ብርቱ እጆቿ መልሳ የገፋትን የድሀነት እጅ መግፋትና እንደገና
መንገዷን መጀመር ነው፡፡ እኔ፣ አንተ፣ ሁላችንም ከምናየው ማንም በስለታም ምላሱ ከሚያርደውና ከሚሸልተው የበግ ቆዳዋ ሥር ያለውን የአንበሳ ቆዳ ለማውጣት ቢያምም፣ ራሷ ቆዳዋን ለመግፈፍ ወስናለች፡፡ የመጀመሪያው ጉዳይ የተቀመጠልህን የባርነትና የአትችልም መስመር በአእምሮህ ማለፍ ነው፡፡

ለአካላዊ ጥንካሬውማ ዕድሜዋን ሙሉ በጉልበት ሥራ ስትደከም የፈረጠመ ክንድ አዳብራለች፣ ያውም ወንድን የሚያስንቅ…”

አባባን ማታ ቢራ ጋብዤ ቁጭ እድርጌ ነገርኩት መንገር ከማለት ለመንኩት ብል ይሻላል) ሥራው ለሴት አይከብድም ብለሽ ነው? አለኝ፡፡ “ሞከራት ለእኔ ስትል ሞከራት ብዬ ለመንኩት፡፡ ተስማምቷል፡፡ዛሬ ትጀምራለች፡፡ አባባን እሱ ለሠራተኞቹ የሚከፍለውን፣ እኔ እንደምከፍላት ስነግረው ሳቀብኝ፤ ችግር የለም፣ እኔ እሰጣታለሁ
አለኝ፡፡ እስካሁንም ለሰራችበት እንደሚከፍላት ሳይሆን እንደሚመጸውታት ነው የሚያስበው፡፡ አውቃለሁ፣ እሷን ተማምኖባት አይደለም፤ ለእኔ ሲል ነው፡፡ ዋት ኤቨር ከትንሽ ወራት በኋላ፣ ለእኔ ሲል ሳይሆን ለራሱ ሲል ይከፍላታል፡፡ ምክንያቱም በሥጋም በመንፈስም እዚያ ከሚሠሩት ብትሻል እንጂ አታንስም! ጠንካራ ናት! በማንም ተራ የወንድ አድናቆት የተገነባ የሴትነት ሞራል ሳይሆን፤ መገፋትን ተቋቁሞ በቆመ ብርቱ መንፈስ ትክክለኛ ማንነቷን የተረዳች ልጅ ናት።ዞሮ ዞሮ አባባም ወንድ ያሳደገው ወንድ ነው ይሄንን አትርሳ።

"ማክያቶ ልዘዝልሽ?ሳትጠጪው ቀዘቀዘ"አልኳት!

"አብርሽ..."

"እ.."

"እናትክን! አንተም ሁላችሁም እናታችሁን!..ይሄ ድንጋይ ወንድነትህ ያልኩትን ሁሉ አንጥሮ ሲመልሰውና ፣ ወሬዬን ሁሉ ተራ "የፌሚኒዚም" ልፍለፋ አድርጎ ሲመለከተው ፤ አይንህ ላይ እያየሁት ነው።በእኔ ቦታ ሆነህ ብትመለከተው እኮ፣ እናንተ ወንዶች እንዴት እንድምትደክሙ? ብላኝ ቦርሳዋን አንስጣ ወጣች።አውቃለሁ ነገ በሌላ የንዝንዝ ርዕስ እንደምንገናኝ።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#ማምሻ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ....አገሩ የበጎች ነው፤ ግን የበጎች ታሪክ ቦታ የለውም! በጎች ራሳቸው የሚተርኩት የአንበሶችን የጀግንነት ጀብዱ ነው፡፡ ምናልባት ታሪኩ የበጎችን ስም ካነሳ፣ በጎች በአንበሶች እንዴት እንደተበሉ ከመተረክ አያልፍም፡፡ የበግ ቆዳ የለበሱ አንበሶች፣ ጠላታቸው የለበሰው ቆዳቸው ነው፤ ስለዚህ ይህን ቆዳ እንዲገፉትና ታሪካቸው እንዲጻፍ ትንሽ መርዳት…»
በአንድ ሰሞን፣ ያነበብኩት “የታሪክ መጽሐፍ” መሳጭ ልብወለድ ነው : :

መቼም በዘመናችን የታሪክ “ደራሲያን" በዝተዋል ሃይ ባይ እስከሌለ ድረስ ማስርጃና ማጣቀሻ የሌላቸው ፣ “የታሪክ ልቧለዶች” በገፍ እየታተሙ
ነው።

አንድ የማላስታውሰው ወዳጄ እንዳው በአብዮቱ ጊዜ በቤተ መንግሥት ወጥ ወጥዋጭ የነበረ ሰው ሳይቀር ፣ “ረጅሙና እልህ አስጨራሹ
የቤተመንግስት ሕይወቴ እና ድብልቅልቁ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሂደት" እያለ የሚፅፍበት ጊዜ ላይ እንገኛለን : :

ተቆጪ በሌለበት ዘመን ሁሉም የሆነውን ያሻውን እውነት በወገንተኛ አርትዖት እየከረከመ ፣
ጋሻውን፤ እውነት በትልቅ እመጫት እያስገባ ፣
የቆረቆረውን፣ እየሰረዘ የፈለገውን ይፅፋል ታሪክን ይደርሳል።

ይህ ነገር የሚከተለውን፣ የኤዞፕን ተረት አስታወሰኝ ።

አንበሳና ሰው ከባድ ክርክር ላይ ናቸው : :

“አንበሳው ከሰው ጉልበት የአንበሳ ጉልበት ይበልጣል" ሲል ፤ ሰውየው ደግሞ ፣ “የለም ፤ የሰው ልጅ ከአንበሳ እጅግ ያይላል” ይላል።

በዚህ ሁኔታ ክርክሩ ከቀጠለ በኋካ ሰውየው ፣ “ቆይ እንደውም ሰው አንበሳን፣ በጉልበት እንደሚያስከነዳ የሚያሳይ መረጃ ላሳይህ መLካሳ ይ” ይልና አንበሳውን አንድ ሐውልት ከቆመበት ቦታ ይወስደዋል ።

ሐውልቱ አንድ ሰው እጅግ ግዙፍ የሆነን አንበሳን ጉሮሮ እንቅ አድርጎ ይዞ ያሳያል ሐውልቱን ሲያይ የቆየው አንበሳም ፣ ይህ ሐውልት የሰው ልጅ ከአንበሳ የሚበልጥ ጉልበት እንዳለው ሊያሳምን አይችልም” ይላል።

ሰውየውም ፣ “እንዴ ... እያየኸው ምን ማለትህ ነው?” ብሎ ሲጠይቅ ፤ አንበሳው ቀበል አደረገና ፣ “ማየቱንስ አየሁት ... ግን ሐውልቱን ያነጸው ማን ሆነና? ” ብሎ መለሰለት አሉ።

እኛም ከእንግዲህ እንደዚህ ዓይነቶቹን፣ መጽሐፍት ስናነብ "ዝም ብለን" በማመን ፈንታ ፣ “የጻፈው ማን ሆነና” በማለት ሚዛን ላይ ማስቀመጥ ብንለምድ አይከፋም : :

🔘ሕይወት እምሻው🔘
#በትንሳኤ_ማግስት

ጾም ስግደቱ ሲቆም ጸሎቱም ተረሣ
እኛ መሞት ጀመርን አንተ ስትነሣ።

🔘 ዲያቆን ሄኖክ ኅይሌ🔘
#የበላይ

አየሽው አለሜ
ማንም ሰው የሰውን ፥ ህይወት ቢቀለጥም፤
ስሜት ቢያሰክረው ነው ፤ የበላይነት ጥም!

እንጂማ.....

የበላይነት ጥም
ስሜትን ቆንጥጦ፤እኛን ድል ባይነሳ፤
ቃዬን በአቤል ላይ፥ ድንጋይ ባላነሳ!

🔘በአብርሃም🔘
“ቀድመውኝ አይደለም፤ ዘግይቼም አይደለም።
ተቀድሜም አይደለም፤ ወይም እነሱ ዘግይተው።

ትክክለኛው ሰዓት ላይ ነኝ።” በል!
:
ምናልባት አንዱ በ20 ዓመቱ ያገባ ይሆናል፤ ለመውለድ አስር አመታትን ይወስዳል።

አንዱ በ30 ዓመቱ ያገባል፤ በዓመቱ ይወልዳል።

አንዷ በ22 ዓመቷ ታገባለች፤ ጥሩ ባል አይደለም።

ሌላኛዋ በ34 ዓመቷ ታገባለች፤ ደስተኛ ትዳርንም ትመራለች።

ከፊሉ በ22 ዓመቱ ይመረቃል፤ ስራ ለማግኘት 5 ዓመታ ይፈጅበታል።

ከፊሉ በ27 ዓመቱ ይመረቃል፤ ከመውጣቱ ስራን ያገኛል።

ሌላው በ25 ዓመቱ የድርጅት ስራ አስኪያጅ ይሆናል፤ በ40 ዓመቱ ይሞታል።

ሌላኛው በ50 ዓመቱ የድርጅት አስኪያጅ ይሆናል፤ በ90 ዓመቱ ይሞታል።
:

ጊዜህን ብቻ ተከተል።

የቀደሙህ ወይም የዘገየህ አድርገው ይስሉሀል።

አንተ ከማንም አልተቀደምክም፤ ከማንም አልዘገየህም።

ፈጣሪ በፈቀልህ ጊዜ ብቻ እየሄድክ ነው።

ይህንን እወቅ።

የአዕምሮ ረፍትና እርጋታህን ይዘህ ኑር።
:
ጊዜ በፈጣሪ እጅ ያለ መንገድ ነው። እንደፈለገ ያስኬደዋል። የፈለገውን ላንተ በፈለገልህ
ሰዓት ያደርግልሀል።
«ነገሩም ሁሉ በእርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው።»

"ትክክለኛው ሰዓት ላይ ነኝ በል።”

🔘ከ FB🔘
#ጥበቃ

ጐጆዬን ትቼ ወጥቼ አስጠልቶኝ ምቹ አልጋዬ
ከባቡሩ መንገድ ላይ እየታየሁ በጀርባዬ ተንጋልዬ
“ምን ሆነህ ነው?” የሚል አዝኖ እሚጠይቀኝ
አንድ ሰው አጥቼ አንድ ሰው ናፈቀኝ፡፡
የባቡሩ ሒዲድ ሥር የድንጋይ ጠጠሮች
ሐዲዱን ያሰሩት ትናንሽ ብሎኖች
ምቾት የሌላቸው እየቆረቆሩኝ የተኛሁባቸው
የጐረበጥኳቸው ያልተመቸዋቸው
ቁሳቁሶቹ እንኳን ባለቤት አላቸው፡፡
ከሐዲዱ ባሻገር የሚታየው ሻንጣ
ከራስጌዬ ኃላ
ያለውም ጃንጥላ
ትራሴ ሥር ያለው አሻንጉሊትና
ፊቴን የሸፈነው ትልቁ ባርኔጣ
ከሥሬ ያነጠፍኩት
ከላይ የለበስኩት ረዥም ካፖርታ
በጠራራው ፀሐይ አብሮኝ የተሰጣ
ከግርጌዬ ያለው ቀዩም ዕጌረዳ
ሁሉም የኔ አይደለም
የእኔ እምለው የለም፡፡
በሥጋዬ መሐል እምትኖረው ነፍሴ
እሷም የሌላ ነች አይደለች የራሴ፡፡
ነፍሴን ይዛዋለች
ነፍሴ ርቃኛለች፡፡
እንደ እሳት ቢፋጅም ቢግልም ሐዲዱ
ንቅንቅ አልላትም ከባቡር መንገዱ፡፡
ጥላኝ ብትሔድም ብትወኝም ንቃ
ከዕቃዎቿ መሐል ሆኜ የሰው ዕቃ
በብርድ ስጠበስ በፀሐይ ስንቃቃ
እኔ ውዬ አድራለሁ
እምትመጣበትን ባቡሩን ጥበቃ።
እንዴት ናፍቃኛለች?!!

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
👍1
#ማምሻ


#ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል)


#በአሌክስ_አብርሃም


ሎዛ ከዓመት በኋላ ባሏ ጋ ጠቅልላ አውሮፓ ገባች፡፡ ያው እዚህ እንደነበረው ቶሎ ቶሎ
ባንገናኝም አልፎ አልፎ ትደውልና ተጨቃጭቀን፣ ተሰዳድበን፣ አኩርፋ ጆሮዬ ላይ ዘግታብኝ፤ ከሆነ ጊዜ በኋላ መልሳ ደውላ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ እናወራለን፡፡ በመሃል ሰፈራችን ከላይ እስከታች ፈራርሶ ጎረቤቱ ሁሉ ተበታተነ፡፡ ሰፈራችን ሲፈርስ አብሮ ያልፈረሰ ነገራችን አልነበረም፡፡ ስንድህ፣ ዳዴ ስንለማመድ የትንንሽ መዳፎቻችን አሻራ
የታተመበት ደጅ ከታሪክ ገጽ ተሰረዘ፣ የተላለፍንባቸው መንገዶች ዳናችንን እንደያዙ
ጠፉ፣ የቆምንባቸው ጥጎች ላይመለሱ ከሰሙ፣ ከየት መጣችሁ? ቢሉን ዙረን የምነጠቁመው ነገር እስከናጣ ሰፈራችን… ትንሽ አገራችን ፈረሰች!! ማንም ሰው የመጀመሪያ አገሩ ሰፈሩ ነው፡፡ አገራችን ፈረሰች!! ከሎዛም ጋር እንዲሁ መደዋወላችን እየተቀዛቀዘ ሂዶ ሙሉ ለሙሉ ተጠፋፋን!! ጭራሽ እኔ የስልክ ቁጥሬን ከቀየርኩ በኋላ ፊት የሚያውቁኝ የሰፈር ልጆች ጋር ሁሉ ተጠፋፋሁ፡፡ ዓመታት ነጎዱ፡፡ ትላንታችን
ወደ ኋላ ሮጠ፡፡ አዲስ ሕይዎት አዳዲስ ጓደኞች ረብርበን ባለፉ ቀናቶች ላይ ከፍ ብለን ቆመን፡፡ በቆምንበት ከፍታ ትላንታችንን ረስተን ነገን ልናይ ተንጠራራን፡፡
።።።።።።።።።።።
ከሰባት ወይም ስምንት ዓመት በኋላ ይመስለኛል፣ የጓደኛችን እናት አርፈው፣ የአስከሬን ሣጥን ልንገዛ ሁለት ሁነን ወደ ፒያሳ ሄድን፡፡ ከተደረደሩት ሱቆች ከአንዱ ወደ ሌላው እያልን ዋጋ ስናወዳድር ቆይተን፣ ወደ እንዱ መሸጫ ጎራ አልን፤ ገና ከመግባታችን ሁለት ወጣት ልጆች አጣደፉን፡፡ እየተቀባባሉ ስለ አስክሬን ሣጥኑ ጥንካሬ፣ ስፋት፣ ምቾት ሳይቀር እየነገሩ አግለበለቡን፡፡ ዋጋ ቀንሱ አትቀንሱ ስንከራከር፣ ድንገት ከውስጥ
ቀንሱላቸው የሚል የሴት ድምፅ ሰምተን ዞር አልን፡፡ጠቆር ያለ አጭር ጋውን የለበሰች
ሴት፣ እጅና እጁን ጋውኑ ኪስ ከትታ ከኋላችን ከነበረ ከፍል ብቅ አለች፡፡ በግርምት ፈጥጨ ቀረሁ፡፡ ይሄን ፊት ማን ይረሳል …ማምሻ ነበረች፡፡

“ማምሻ” አልኳት ፈገግ ብዬ፣

እንዴ! አብርሽ ባልሆንክ…ትልቅ ሰው! ትልቅ ሰው…” ጮኸች መጀመሪያ ለማጣራት
ብላም እንደሆን እንጃ፣ ግርምቷን ቆም አድርጋ፣
“ምነው? ማን ሙቶባችሁ ነው?” አለችኝ፡፡

“የጓደኛችን እናት ናቸው

የባጥ የቆጡን እያወራን፣ እንትና ደህና ነው? እነ አትናስ? እየተባባልን የአስከሬን ሣጥኑን ራሷ መረጠችልን፡፡ ልጆቹ ሳጥኑን እስኪያዘጋጁልንና እስኪጭኑት ድረስ፣ ወደ ውስጥ አስገብታን በግራና በቀኝ የአስክሬን ሣጥን በተከመረበት ሰፋ ያለ ቢሮዋ ውስጥ፡ ሻይ ጋበዘችን፡፡ በጣም ጎበዝ ጣውላ ሠራተኛ ከመሆን አልፋ፣ የራሷን ትንሽ ጣውላ ቤት ከፍታ ነበር፡፡ እዚህ ሥራ ላይ “ምን እግር ጣለሽ” አልኳት የከበቡንን የአስከሬን
ሣጥኖች እያየሁ፣

ሳቀችና እማማ ስታርፍ ራሴ ነኝ የአስክሬን ሣጥኗን የሠራሁላት….. አልጋ፣ ሶፋ፣ ቁም
ሳጥን እንሠራለን፡፡ ለምን እንደሆን እንጂ ከዚያ በኋላ የአስክሬን ሣጥን ስሠራ ደስ ነው
የሚለኝ፡፡ ወደድኩት! ሳጥኖቹን ስሠራ ሰላም ይሰጠኛል፡፡ ጨርቆቹ ላይ ያሉትን ጥልፎች የምሰራው ራሴ ነኝ፤ ሰዎች ሲሞቱ ከነሣጥናቸው ወደ እግዚአብሔር የሚያርጉ ይመስለኛል …" እግዚአብሔር ሣጥኖቹ ብቻ ሳይሆን በጥልፎቹም የሚደመም ይመስለኛል ብላ ሳቀችና “ይኼውልህ ይችን ሱቅ ተከራይቼ በዚሁ ሥራ ቀጠልኩ፡፡
ማምረቻትን ከኋላ በኩል ነው፡፡ ወይ አብርሽ ትልቅ ሰው ሆንክ ብላ በመደመም እጇን እፏ ላይ ስትጭን የጋብቻ ቀለበት ማድረጓን አየሁ፡፡ ግን ምንም አላልኩ፡፡

እማማ መቼ አረፉ” አልኳት፣

ትንሽ ዝም ብላ ቆየችና “አራት ዓመት ሆናት” አለችኝ፡፡

ሶሪ…" ዝም ተባብለን ቆየን! እንዲሁ ዝምታውን ለማስወገድ

የሰፈር ሰዎችን አግኝተሻቸው ታውቂያለሽ?» አልኳት፣

እዎ ተራ በተራ እየሞቱ ነው፣ ከዚሁ ነው ሣጥን የሚወስዱት፣ ደንበኛ ሁነናል…”አለችና
የአሽሙር የሚመስል ፈገግታ ፈገግ ብላ ከጠረጴዛዋ መሳቢያ ውስጥ ካርድ አውጥታ
ሰጠችኝ፡፡ “ማምሻ የጣውላ ሥራ አልጋ፣ ሶፋ፣ በሮች እንሠራለን እንዲሁም የተለያዩ
የአስከሬን ሣጥኖችን እናቀርባለን ይላል።

ሳጥኑ ተጭኖልን ስንወጣ፣ ማምሻ ፈገግ ብላ ጨበጠችኝና “ሎዛ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ መጥታ በእግር በፈረስ ብታስፈልግህ አጣችህ..ፖስታ ስጭው ብላ እኔ ጋር
አስቀምጣልህ ነበር፤ እቤት ነው ያለው፡፡ ያለህበትን ንገረኝና የሆነ ቀን አቀብልሃለሁ
ወይም መጥተህ ውሰድ አለችኝ፡፡ የእጇ ጥንካሬ እጄን የቆረጠመኝ እስኪመስለኝ አጥብቃ ጨበጠችኝ

ሰንመለስ፣ አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ “ማናት?” አለኝ፡፡

“ማምሻ ትባላለች የሰፈራችን አንደኛ አስቀያሚ ልጅ ነበረች…” ብዬ ከመጀመሬ፣

“አሁንም'ኮ በጣም አስቀያሚ ናት! ጭራሽ ይኼን መልክ በአስክሬን ሣጥን ተከቦ ማየት፣ አስበኸዋል!?” አለኝና በራሱ ቀለድ ከትከት ብሎ ሳቀ፡፡ እውነቱን ለመናገር የማምሻን መልክ ነገሬ ብዬ አላስተዋልኩትም ነበር፡፡

ከሳምንት በኋላ ለማምሻ ደወልኩላትና ሎዛ የተወችልኝን ፖስታ ልትሰጠኝ አንድ ካፌ
ተገናኘን፡፡ ቡና ጋብዣት እያወራን በወሬ ወሬ “አላገባህም?” ከሚል ጥያቄ ተነስቶ ነገሩ
ወደ እሷው ዞረና ማግባቷን ነገረችኝ ፤ ልጅ መውለዷንም ጭምር ፡፡ “እንኳን ደስ ያለሽ?
ከማለት ባለፈ ምንም ነገር ለመጠየቅ ፈራሁ፡፡ “ማንን አገባሽ” አልል ነገር “ማነው አንችን ያግባ!” ይመስልብኛል ብዬ …..ዝምታ ዓይኔን እዛና እዚህ ሳንከራትት ራሷ እግዚእብሔር ጥሩ ሰው ሰጠኝ …የሎዛ አባት ቤት ሶፋ የሚሰራ፣ ዳንኤል የሚባል ልጅ ታስታውሳለህ ? አለችኝ አላስታወስኩትም፡፡ የሎዛ መልክ ራሱ ደብዝዞብኛል፡፡

እሱ ጋር ተጋባን :-እጄን ይዞ ነው ጣውላ ስራ ያስተማረኝ፡፡እንጋባ ሲለኝ እየቀለደ ነበር
የመሰለኝ

ለምን?” አልኳት፡፡ የራሌ እንዳላወቀ መምሰል እያስጠላኝ::

ሳቀች እያወከው አብርሽ እኔን በዚህ መልኬ፣ እንኳን ማግባት አብሮኝ የሚቆም ወንድ አልነበረም ሃሃሃሃሃ ብላ ሳቀች፡፡

“ይሄን ያህልማ አታካብጅው አልኩ፣ ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ በሆነ ማጽናናት፡፡

ፈገግ ብላ ስንተዋወቅ” በሚል አስተያየት አየችኝ “እንደተሳቀስክሁ ነው የኖርኩት…ከሰው
እንደራቅሁ፡፡ ስወልድ እንኳን አስብ የነበረው እንደ እናት ስለ ልጄ ደህንነትም ሆነ ስለ ምጡ ስቃይ አልነበረም፡፡ ከምጡ በላይ ሐሳብ የሆነብኝ የልጄ መልክ ምን ይመስል ይሆን? የሚል ጭንቀት ነበር፡፡ አምጥተው ሲያሳቅፉኝ፣ገና ሳትታጠብ በፊት…ፍከት ባለ ቆዳዋ ከእኔ ዕጣ ማምለጧን ስመለከት በደስታ አለቀስኩ፡፡ ማንም ኤልገባውም! እናት መሆን ብቻውን ያስለቀሰኝ መስሏቸው ነበር፡፡

ዘጠኝ ወር ያረገዝኩት ጭንቀት እንደ መንታ በማሕጸኔ ከልጄ ጋር እያደገ ነበር፡፡
ተገላገልኩት፡፡ ልጄ ምኗም እኔን ባለመምሰሉ ፈጣሪን አመሰገንኩ፡፡ ሁልጊዜ የሚገርመኝ
ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ባለቤቴ አንቺን የምትመስል ልጅ ነው የምፈልገው ያለኝን
ነገር! እኔን ለማጽናናት ብሎ ይናገረውም አልያም ከልቡ ይሁን እንጃ! ብቻ ይሄ ንግግር ውስጤ ቀረ፡፡ ሰዎች “ቁርጥ አባቷን ሲሉ ነፍሴ ሐሤት ታደርጋለች አባቷ እኔን ከጥላቻ… ልጃችንንም እኔን ከመምሰል ሳያውቀው አድኖናል፡፡ በሄድኩበት ሁሉ ሎዛየንና ባለቤቴን ስማቸውን አንስቸ አልጠግብም፡፡ ነፍሴ ታከብራቸዋለች አሁንም ግን እንደገና ልጅ መውለድ እፈራለሁ፤ እኔን ብትመስልስ እያልኩ፡፡ አሁንም እሰጋለሁ… አንድ ቀን ባሌ እኔንም ልጄንም ጥሎን ቢሄድስ እያልኩ፡፡ እንጃ ከዚህ በሽታ እንዴት እንደምፈወስ!

የሎዛን ፖስታ ስከፍተው
👍5
አንድ ባለቀለም ጉርድ ፎቶግራፍ ብቻ ነበር ውስጡ ያኘሁት፤አንዲት እድሜዋ ሦስት ዓመት የሚሆናት ቆንጅዬ ሕጻን ልጅ ፎቶ፡፡ከፎቶው ጀርባ
በእንግሊዝኛና አማርኛ ቅልቅል እንዲህ የሚል ጽሁፍ ተጽፏል የሎዛ የእጅ ጽሁፍ ነው፡፡
hello,uncle! guess what ...My name is "ማምሻ ዳግማዊ!!

ሟርት ነው አልኩ ለራሴ፡፡ ግን ደግም አይገርምም፣ ሎዛ እብድ ናት እብድ ቤተሰብ
መመስረትም ትችላለች፡፡ እናም ዓለም ፈውሷን ለመቀበል የሎዛ ዓይነት ብዙ እብዶች ሳያስፈልጓት አይቀም፡፡

ጨረስን

አረ ተዉ #MUTE ያደረጋቹ #UNMUTE አድርጉ ምንም አልሰማም አላችሁ እኮ😡 ምን ይሻለኛል ወይ እስቲ ስለድርሰቱ አስተያየት ስሰጡ #UNMUTE የማታደርጉበትን ምክንያት ምንድን ነው??? እባካችሁ ንገሩኝ..Post የሚደረጉትን ብዙ ሰው የማያነበው ከሆነ ማዘጋጀቱም ይደብራል..ሌላ ድርሰት ለመጀመር ወይም ለማቆም አስተያየታችሁን (ምክንያታችሁን) እፈልጋለው...በዛሬው ቀን ብቻ እንኳን #381 ሰው ቻናሉን #MUTE አድርጓል አስተያየት ይስጡ

@atronosebot ን ይጠቀሙ
#ስንቶች_ናቸው

ሰቅለው ሁለት ባላ
ሲሰበርባቸው አንዱ
በአንዱ 'ሚንጠለጠሉ
ነፍስና ሥጋቸው እየተጣላ
አልስማማው ሲላቸው
ወሰን ሲያልፍባቸው ሲጥስባቸው ኬላ
በስመ ፍቅር ከለላ ይዘው የነፍስ ምህላ
ዕለተ ልቡናቸውን አክብረው
ሽፍነው በትዕግሥት ጥላ
ሳይፈቀሩ አፍቅረው
ዘመናቸውን ሲፈጁ ኖረው ኖረው ኖረው
መግቢያ መውጫ ሲቸግራቸው
የፍቅረ ረቂቅ ኃይል ውስብስቡ ውጥንቅጡ
መስመራቸውን ሲያስታቸው ሲጠፋባቸው መላቅጡ
ሌላ አማራጭ ሲያጡ
በፅልመት ውስጥ ሲዋጡ ቶሎ ተስፋ ሲቆርጡ
ከራሳቸው ጋር ተጣልተው ከራሳቸው ጋር ሳይታረቁ
ጀንበራቸው አዘቅዝቀው የሰውን ፀሐይ እየጠበቁ
የሚሞቁ
ልባቸውን አቀዝቅዘው የሌላን ልብ እያሞቁ
መሪር ሐዘን ውጧቸው በሰው ደስታ እየቦረቁ
የራሳቸውን ጥርስ አኑረው በሰው ጥርስ እየሳቁ
“የእኔ” ከሚሉት በቀር ማፍቀር እንደማይችሉ እያወቁ
ያፈቀሩ መስለው ሳያፈቅሩ
አኗኗሪ ሆነው እሚኖሩ
የሚቆጠሩ እያሉ እንደሌሉ
በየቤቱ ስንቶች አሉ?!?
ከሚያፈቅሩት ሰው እየሸሹ ከሚያፈቅሩት ሰው እየራቁ
ለሚጠሏቸው እጅ የሰጡ በማይፈልጉት ሰው እጅ የወደቁ
ገና የቃልኪዳነን ቀለበት በጣታቸው ላይ ሲያጠልቁ
የሚያፈቅሩትን ሰው እየናፈቁ
ስንቶች ናቸው ፍቺያቸውን በጋብቻቸው ዕለት ያፀደቁ?!?
ስንቶች ናቸው
ተለይቶ ከራሳቸው
ተቦጭቆ ከገፃቸው የነፍስና ያካላቸው ግማሹ
ከሚያፈቅሩት ጋር እንደቀረ እያወቁ እየዋሹ
የሚያፈቅሩትን ሰው እያሰቡ
ከማይወዱት ጋር የሚቆርቡ
ላይፋቱ ያለፍቅር የሚጋቡ፡፡
ስንቶች ናቸው::
ራሳቸውን በራሳቸው የቀጡ
ራሳቸውን በራሳቸው የገደሉ
የፅድቅ መንገዳቸውን ያበላሹ
ፀዓዳ መንፈሳቸውን ያቆሽሹ
ከማያፈቅሩት ጋር እየኖሩ
የሚያፈቅሩትን ሰው እሚሹ፡፡
ስንቶች ናቸው?!?

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#የጊዜን_ሽግግር

ትናንትን መውቀሱ
ትናንትን መክሰሱ
ዛሬን ማወደሱ
ዛሬን ማሞገሱ
ነገን ማጨለሙ
ነገን መራገሙ
ምንድ ነው ጥቅሙ?!?
የጊዜ ምንነት ምሬቱና ጣዕሙ
ፋይዳ 'ሚኖረው የሕይወት ትርጉሙ
ሲያብሩ ብቻ ነው ባንድነት ሲቆመ::
የዛሬ መሠረት
ነበር ትናንትና
የነገም ውሃ ልክ
ቀድሞ ሚቀመጠው
በዛሬ ነውና
የትናንቱም ዕለት
የዛሬውም ዕለት
የነገውም ዕለት
ቁርኝት አላቸው ልክ እንደሠንሠለት፡፡
ምንም ጊዜ የለም እንደአምድ የፀና
ቀጥ ብሎ የቆመ በእራሱ ሕልውና፡፡
ካቻምና በአምና አምና በዘንድሮ
በቀጣዩ ዓመት
ዘንድሮ እንደገና
ወሩ ተራው ደርሶ ዓመት ሙሉ ኖሮ
ጊዜውን ጨርሶ በስም ተቀይሮ
አምና ተብሎ ይጠራል
ካቻምናም ይሆናል
ሕያው ሆኖ ነግሶ ድሮም ተብሎ ይኖራል፡፡
እያንዳንዱ ጊዜ በጊዜ ያስፈራል
በጊዜ ሚዛን ላይ ይወጣል ይለካል
እንደገና ይወርዳል “ሌላ ጊዜ” ይመጣል፡፡
ዘይገርም ነገር
ጊዜ ከዘረ ሰው በጣሙን ይረቃል
በእጅጉ ይልቃል
ሥልጣነ ጊዜውን በጊዜ ይለቃል
በፍቅር ይለቃል
በሰላም በፍቅር ጊዜ ይፈራረቃል
ያለአንዳች ኮሽታ
ያለአንዳች ሁካታ
እርስ በርሱ ይተካል ሁሌም እግር በእግር፤
ሒደቱ ቀጣይ ነው
ጊዜም አይገታውም የጊዜን ሽግግር፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
1
አትሮኖስ pinned «#ማምሻ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ሎዛ ከዓመት በኋላ ባሏ ጋ ጠቅልላ አውሮፓ ገባች፡፡ ያው እዚህ እንደነበረው ቶሎ ቶሎ ባንገናኝም አልፎ አልፎ ትደውልና ተጨቃጭቀን፣ ተሰዳድበን፣ አኩርፋ ጆሮዬ ላይ ዘግታብኝ፤ ከሆነ ጊዜ በኋላ መልሳ ደውላ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ እናወራለን፡፡ በመሃል ሰፈራችን ከላይ እስከታች ፈራርሶ ጎረቤቱ ሁሉ ተበታተነ፡፡ ሰፈራችን ሲፈርስ…»
#አፍሪካ_አንድም_ኀምሳ_አራትም

አክራ ባሕር ዳር ተቀምጠህ ፣ በጋና ችክችካ ሙዚቃ ስልት እስክስታ ስትወርድ የአፍሪካ አንድነት ይታይሃል ።

ካምፓላ መንገድ ላይ ተቀምጠው ባህላዊ ጌጣጌጥ Pሚሸጡ ነጋዴዎቹ ፣ የላሊበላን መስቀል ሲሸጡ ስታይ ፣ የአፍሪካ ኅብረት ይሰማሃል : :

ዝነኛው የናይጄርያው ፣ “ሳዋ ሳዋ ሳዋሌ” ዘፈ፣ ምቱን ሳይለቅ በአማርኛ ተሠርቶ አዲስ አበባ የምሽት ክለብ ኢትዮጵያውያንን ያለ እረፍተሸ
ሲያስጨፍር ስታይ ፤ የአፍሪካ መመሳሰል ይታወቅሃል : :

ፕሪቶርያ ምሽት ክበብ ቁጭ ብለህ ፣ የጃሉድን የመሰለ የ"ጫካ ድምፅ" ያለው ሙዚቀኛ ፣ሬጌ ዜማ እየሰማህ ቢራህን ስትጎነጭ ፣ አፍሪካ አንድ
መሆኗ ነጋሪ እንደማያሻው ትረዳህ : :

ናይሮቢ ሰማይ ላይ ተንጠልጥሎ የታየ ደመና ፣ አስመራ መሬት ላይ ዝናብ ሆኖ ሲወርድ ፤ “አፍሪካ አድ ሀገር ናት” ያሰኝሃል።

ዕድሜውን፣ ሙኩ ሀገሪቷን እየዞር ፣ የአፍሪካን ሕፃናት በፎቶ ሲሰበስብ የኖረ ፈረንጅ ያሳተመውን ፎቶዎች መጽሐፍ ከጫፍ ጫፍ ባገላበጥህ
ጊዜ ፤ የፈገግታቸውን መመሳሰል ባየህ ጊዜ ፤ ሁላችንም የምንነቃው የጠራ አፍሪካ ሰማይ ሥር መሆኑ ይሰማሃል።

🔘ሕይወት እምሻው🔘
#በጣም_ታምሪ_ነበር

ሠው ሰራሹ መልክሽ..
እፍጥጦ ባይወጣ
በጅንስ ታፍኖ..
ዳሌሽ ባይቀጣ
ጡትሽ ቤቱ ቢኖር...
ልታይ ሳያበዛ
ፀጉርሽ ያንቺዉ ቢሆን..
ከሱቅ ባይገዛ
ጊዜ ሳይቀይርሽ...
በቃልሽ ብታድሪ
ሀሊናሽ ቢገዛሽ
በሥጋሽ ባትኮሪ
የሴትነት ክብሩ ...
ቢገባሽ በልኩ
ሲጠሩሽ ባ'ሮጭ....
በርሽን ሲያኳኩ
አስተዋይ ብትሆኝ.…....
ምግባርሽ ቢከበር
ሔዋኔ ልንገርሽ...
በጣም ታምሪ ነበር፡፡

🔘አለ ታምራት🔘
🔥1
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


በታላቋ አሜሪካ፣ በግዙፍ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ሥር ሳልፍ፣ በውብ መናፈሻዎች ራስጌና ግርጌ ስመላለስ፣ ሰፋፊ መንገዶች እንኳን በእግር ሄደውባቸው በዓይን አይተው በማያካልሏቸው ትላልቅ የገበያ አዳራሾት መኻል ወዲህ ወዲያ ስል፣ ነፍሴ መደበቂያ የሚሆን አንዳች ሽርኩቻ ፍለጋ ትራወጣለች: አፍንጫዬ ሁልጊዜ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት አየር፣ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ የሚሸት ሰው ፍለጋ ይቀሰራል፡፡ በርገር እና ፒዛ
ቤት ገብቼ የዶሮ ወጥ ሽታ አነፈንፋለሁ፡፡ እግሬ የአሜሪካን ምድር ከረገጠበት ቀን ጀምሮ እየተነፈስኩ እታፈናለሁ፣ እያወራሁ እታፈናለሁ። ናፍቆት አይደለም፤አለመመቼትም አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት በሚስኪን ነፍስ ውስጥ የታሰረ ግዙፍ መንፈስ ነው ይኼ መንፈስ አሜሪካ ይጠብበዋል፣ ዓለም ይጠብበዋል:: ለአንድ
ኢትዮጵያዊ፣ እንደ ጫማ እና እንደ ልብስ ተለክታ የተሠራች ብቸኛ የመንፈሱ ጓዳ፣በሚጠብበው ዓለም ውስጥ ያለችው ሰፊዋ ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ ሌላው ሁሉ ይጠብባኛል፡፡

ለዚህም ሳይሆን አይቀርም፣ ባለችኝ ትንሽ ትርፍ ጊዜ ሁሉ ልክ እንደ እናት ማሕፀን የምትሞቅ፣ ከቤቴ ወደ ሃያ ደቂቃ መንገድ የምትርቅ፣ ጠባብ የሐበሻ ሱቅ ውስጥ የማልጠፋው፡፡ የአብሮ አደጌ የፋሲል ሱቅ ናት፡፡ ፋሲል አስማተኛም፣ አርበኛም
ይመስለኛል፡፡ ሚኒሊክ ፣አሉላ አባነጋ፣ በላይ ዘለቀም ይመስለኛል። አገሬን ከወራሪ ሰላቶ
ማስጣል ብቻ ሳይሆን፤ ተሸክሞ አምጥቶ ነጮች ምድር ያውም መሀል ከተማቸው ላይ በክብር ያስቀመጠ አርበኛ ይመስለኛል። አንድ ሐበሻ አስቁሞ “የኢትዮጵያ ኤምባሲ' የት ነው” ቢለኝ፣ የፋሲልን ሱቅ የምጠቁም እስኪመስለኝ ለእኔ ይህች ሱቅ በወርድም በቁመትም ትንሽ ኢትዮጵያ ነበረች፡፡

የጤፍ እንጀራ የሚቸረቸርባት… መቸርቸር ብቻ አይደለም ስለ እንጀራ ኬሚስትሪ የሚወራበት አብሲቱ በሙቅ ውሃ ተቀይጦ… የእንጀራው ዓይን እንዲህና እንደዛ ሆኖ ሰርገኛ ጤፍ ነጭ ጤፍ የሚባልባት፣ የሐበሻ ቡና የሚሸጥባት፣ የእሳት አደጋ ማስጠንቀቂያ ላይጮኸ እጣን በጊርጊራ የሚቦለቀለቅባት፣ የጀበና ቡና በጤናዳም
የሚጠጣባት፣ ጥሬ ሥጋ በፓውንድ የሚሸጥባት፣ ካለፈቃድ የሴት ልብስ መንካት ዘብጥያ በሚያስጥልባት አሜሪካ ባህሩ ቃኘ “ያዝ እጇን የሚባልባት ሱቅ፣ ጥላሁን ገሠሠ
"ጸልጌ አስፈልጌ፣ አስቴር አወቀ እሹሩሩ ፍቅር” የሚሉባት ሱቅ

የማነብበው ነገር ካለ እያነበብኩ፣ እጽፍም እንደሆነ ላፕቶፕ ኮምፒውተሬን ከፍቼ
ወጪና ሂያጁን ሐበሻ እየቃኘሁ፣ በዕረፍት ቀኔ ከፋሲል ጋር እውላለሁ! ሐበሻ ይመጣል፣
ዶላር ወደ አገር ቤት ይልካል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣እንጀራ ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ ቡና
ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ የወጥ ቅመም ይገዛል፡፡ ሐበሻ ይመጣል፣ የሚከራይ ቤት
ያለው ሰው ይጠይቃል፣ ሐበሻ ይመጣል፣ ፖለቲካ ያወራል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት ተሸክሞ “አገሩ አሜሪካ ከሽብርተኛ ጋር እዚያ መካከለኛው ምሥራቅ እየተፋለመችና በሚከፍለው ግብር ያመረተችውን ብዙ ቶን ቦንብ እያራገፈች መሆኑን የሚያሳይ ዜና ፊት ለፊቱ ባለ ቴሌቪዥን እየተላለፈ፣ በወረቀት በተሰናበታት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖትራክ መኪና ስለገጨው የመንገድ አጥር እየተብሰለሰለ በስሜት ያወራል፡፡ ሐበሻ
ነዋ! አንዱ ይመጣል፣ ሱቋ ውስጥ የተለጠፈውን የሚኒሊክን ፎቶ እየገላመጠ እንጀራ ገዝቶ ይሄዳል፡፡ ሌላው ይመጣል፣ በወዲያ በኩል የተለጠፈውን የመለስ ዜናዊን ፎቶ እየረገመ፣ እንጀራ ገዝቶ ይሄዳል፡፡ ሱቋ ውስጥ የሌለ የአገር መሪ ፎቶ የለም- ጥቁረቱም ከንፈሩም መንግሥቱ ኃይለማሪያምን የሚያስንቅ ሐበሻ መጥቶ፣ “ይኼን ሌንጨጫም ባሪያ ምን ይሁን ብላችሁ ለጠፋችሁት ደግሞ!?” ብሎ…ሁለት ፓውንድ ሥጋ አስቆርጦ በላዩ ላይ አሥር እንጀራውን አንጠልጥሎ ይሄዳል፡፡ ሐበሻ … በጤፍ እንጀራ ቀጭን ክር ላይ በሰልፍ የተሰካ የመቁጠሪያ ጠጠር ይመስለኛል፡፡ የተለያየ ግን የተሳሰረ።

ከተማረውና ከፍ ያለ ቦታ ካለው ሐበሻ ጀምሮ፣ እስከ ቀን ሠራተኛውና የታክሲ ሾፌሩ ድረስ ወደ ፋሲል ሱቅ የማይመጣ ሐበሻ የለም፡፡ መናኸሪያ ነበረች፡፡ ወሬ፣ ሐሜትና ፖለቲካው ይጦፋል፡፡ መረጃው ይጎርፋል፣ የሴራ ትንታኔው እየተነሳ ይጣላል፡የእድርና እቁብ ብር ይሰበሰባል፡፡ ፋሲል ሱቅ ስቀመጥ፣ አገሬን ትቼ የሄድኩ ሳይሆን፣ አገሬ ራሷ ውስጧ እንደተቀመጥኩ፣ እንደ አውሮፕላን ይዛኝ በርራ እዚያ ያሳረፈችኝ ይመስለኛል፣
አብረን ያረፍን፡፡ እንዲያውም ከስቋ ስወጣና የፈረንጅ መዓት ወዲያ ወዲህ ሲል፣የተወረርን ነው የሚመስለኝ::

የኑሮን ጎምዛዛ ጣዕም አገር ቤት ጣጥዬው መጣሁ ያልኩ እኔ ፣የሕይዎትን እውነተኛ ገጽ
ያየሁት፣ እንደመስኮት ሁሉን በጨረፍታ በምታስቃኘው በዚች ሱቅ ነበር፡፡ ደግሞ
ምሬቱ፡፡ ዕድል ፈግ ካላለች በስተቀር ምድሩ ወጥመድ ነው! ሥጋ እየደለለ ነፍስ ዐጽሟ
የሚቀርበት ምድር!

የሚመጣው ሁሉ የከሸፈ ታሪክ ልቡ ውስጥ አለ፡፡ የከሸፈ ኳስ ተጫዋች፣ የከሸፈ ሀኪም የከሸፈ ኢንጅነር፣ የከሸፈ ከያኒ፡ የከሸፈ ባለስልጣን ፣የከሸፈች ቆንጆ ሁሉም 'ነበርኩ' የሚለው ትዝታ አለው፡፡ ታዲያ ድፍን ሐበሻ አሜሪካ ላይ ወገቡ እስኪቆረጥ ሰርቶ በሰዓት የሚከፈለውን ድርጎ፣ የላቡ ዋጋ ሳይሆን እዛ አገር ቤት ትቶት ለመጣው፣ ለከሸፈ ትላንቱ የሚከፈል ካሳ ይመስለኛል፡፡

እንድ ቀን አንድ መላጣ ሰውዬ መጣ ዕድሜው ሃምሳዎቹን ያለፈ፤ ቢበዛ አራት ዓመት
የሚሆነው በምቾት ብዛት የተላጠ ብርቱካን የመሰለ ሕፃን ልጅ አቅፏል፡፡ ያስታውቃል
ያቀፈው ልጁ ከብዶታል፡፡ በኋላ ሰውዬው ራሱ "ልጄ ነው አለ እንጂ የልጅ ልጁ ነበር
የመሰለኝ፡፡ ሰውየው ከፋሲል ጋር የቆየ ትውውቅ ስለነበራቸው አረፍ ብሎ ወሬ ጀመረ፡፡ ያማርራል፤ ከፉኛ ያማርራል፡፡ በከንቱ የተበላ ዕድሜውን ከቡና እና ከቅመማ ቅመም ጋር ተደርድሮ ያገኘው ይመስል፣ ዓይኖቹ የሱቋ መደርደሪያ ላይ እየተንከራተቱ ያማርራል፡፡ የተኮሳተረ ጠይም ፊቱ ላይ እርካታ ያጣ ሕይዎቱ ከነሙሉ ሥርዓተ ነጥቡ
ተጽፎ ይነበባል: ከመደርደሪያው ኋላ ከተቀበሩት ድምፅ ማጉያዎች ፣ ኮለል ያላ የጥላሁን
ዘፈን ይፈስሳል፡፡ ሰውዬው ፊቱን ከስክሶና ወዲያ ወዲህ የሚል ልጁ ላይ ዓይኑን ተክሎ
ዘፈኑን እንደ ሙሾ ያደምጣል። በየመሀሉ “ምን የዛሬ ዘፋኞች! እያለ የዘመኑን ዘፋኞት
ያማርራል፤ ድንገት ወደ እኔ ዞሮ፣

አዲስ ህ?” አለኝ::

“ዓመት አለፈኝ

ሥራ ጀመርክ ወይስ ክላስ ምናምን?”

እየተማርኩ ነው

የምትማረውን ተምረህ ወዳገርህ ተመለስ! …ይኼ ቆሻሻ አገር እንደ ሸንኮራ አላምጦ ነው የሚተፋህ
እንዳታገባ፣ እንዳትወልድ፣ወዳገርህ ሰውዬው ኮስተር ብሎ ነው የሚያወራው የምመልሰው ግራ ገቦቶኝ ዝም እንዳልኩ፣ እጅህን ተመልከተው፣ እንደ ሴት እጅ የለሰለሰ ቆንጆ እጅ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ከስክርቢቶ ውጭ ምንም ጨብጦ አየውቅም፡፡ እኔም ስመጣ እንዳንተ ነበር እጄ፤ ለማስታወሻ ፎቶው አለኝ…ተመልከት አሁን” አለና እጁን ዘረጋ የተፍረከረከ የደህና አርሶ አደር እጅ ይመስላል፡፡ “የማንንም ሽንት ቤትና ወለል የፈገፈኩበት ነው፡፡ እንኳን ልስላሴው አሻራውም ጠፍቷል፡፡ አሁን
ይሄ አሜሪካ ውስጥ የሚኖር ሰው እጅ ይመስላል?” ብሎ የራሱን እጅ እያገላበጠ
ተመለከተና "ሃሃሃሃ” ብሎ ሳቀ፡፡ ሳቁ ያስፈራል::

ሰውዬው ፋሲል የጋበዘውን ቡና የመጨሻ ጠብታ አጣጥሞ፣ የገዛውን እንጀራ አንጠልጥሎ ልጁን እያቃሰተ አቀፈና ተሰናብቶን ወጣ፡፡ ዓይኔ ሳሩ ላይ መተከሉን አይቶ ፋሲል “የዚያች ልጅ ባልኮ ነው” አለኝ፡፡

የየቷ?”

እነሯ

ትቀልዳለህ?

እውነቴን ነው ማመን አልቻልኩም። አነሯ
👍5
የሚላት፣የሆነ ቀን ቡና ልትገዛ መጥታ
ያስደነበረችኝን ልጅ ነው፡፡ በጣም ወጣትና ቆንጆ ነች፡፡ አገር ቤት የመድረክ ቲያትር ስትሠራ፣ አውቃትም አደንቃትም ስለነበር፣ ከረዥም ጊዜ በኋላ ሳያት ደስ ብሉኝ፣ ፈገግ ብዬ ሰላም አልኳት! ኮስተር እንዳለች አንገቷን ብቻ ቀለስ እድርጋ ዝም አለች፡፡ “ይቅርታ አገር ቤት አውቅሻለሁ የእንባ ቀብድ የሚል ቲያትር ስትሠሪ…” ብዬ ከመጀመሬ፣ ፊቷ ተቀያይሮ “ይቅርታ! የኔ ወንድም ሥራ የለህም?” ብላ ኩም አደረገችኝ፡፡ ትንሽ ክብደት
ከመጨመሯ በቀር፣ አሁንም ቆንጆ ናት፡፡ ፊቷ ግን አስፈሪ ነበር፡፡ አሁን ገና የአባቷን ሞት ያረዷት ይመስል፣ ደህና ዋልሽ? ሲሏት የሚዘረገፍ የሚመስል እንባ ያረገዘ ሐዘንተኛ ፊት፣ ምን ስበብ አግኝቼ ባለቀስኩ የሚል ፊት፡፡ ብዙ አታወራም። ከዚያ ቀን በኋላም ብዙ ጊዜ ወደዚህ ሱቅ ስትመጣ፡ ኮስተር እንዳለች የምትፈልገውን ገዝታ ነው የምትሄደው።..........

አንብበው ጨርሰዋል አሁን ደሞ ከዚሁ ሳይወጡ #UNMUTE አድርገው ይውጡ አመሰግናለው

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የእንባ_ቀብድ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም በታላቋ አሜሪካ፣ በግዙፍ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ሥር ሳልፍ፣ በውብ መናፈሻዎች ራስጌና ግርጌ ስመላለስ፣ ሰፋፊ መንገዶች እንኳን በእግር ሄደውባቸው በዓይን አይተው በማያካልሏቸው ትላልቅ የገበያ አዳራሾት መኻል ወዲህ ወዲያ ስል፣ ነፍሴ መደበቂያ የሚሆን አንዳች ሽርኩቻ ፍለጋ ትራወጣለች: አፍንጫዬ ሁልጊዜ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት አየር፣…»
#የጋረዳት

ክቡር ስም ሰጥተናት
በተፈጥሯዊ ውበቷ ልዩ አርገን ስለናት
ከዓለም ለይተናት ከዓለም አጉልተናት
“የአሥራ ሦስት ወራት
የፀሐይ ብርሐን ሀገር ናት” ብለናት
ከሐቃችን ጋር ኖርን ለአያሌ ዘመናት፡፡
ለዓለም ያወጅነውን
ይፋ ያወጣነውን
የራሳችንን ሐቅ ቀድመን ብንዘነጋ
የእኛን ችላ ብለን
ከፍ ከፍ አድርገን የእነሱን የሐቅ ዋጋ
አምነን ተቀብለን
አንዳች ልዩ ተዓምር ይፈጠራል ብለን
ፀሐይዋ ተጋርዳ ጨለማ ሲውጠን
በዓይናችን ለማየት ጓጉተንና ቋምጠን
ከርቀት የሚያሳይ ባዕድ ቁስ አጥልቀን
እንደራቀ ወዳጅ ግርዶሽንም ናፍቀን
ሰማይ ላይ አንጋጠን ጠብቀን ጠብቀን
ሆኖም በሰማይ ላይ
አንዳች ተዓምር ስናይ
እንደወትሮው ሁሉ ፀሐይ እየሞቀን
በብርሐን ደምቀን
ብሩህ ሆኖ አለፈ ሳይገርመን ሳይደንቀን
ይጨልማል ያሉት ያ የጠበቅነው ቀን፡፡
ሐቃቸውን አምነን ሐቃችንን ጋርደን
ያጠፋነው እኛ ነን ወደንና ፈቅደን፡፡
ስለዚህ በቀኑ
በፀሐይዋ ብርሐን ከጥፋት ታርመን
ከገዛ ሐቃችን ጋር እንታረቅ ቀድመን፡፡
ወቅት 'ማይለውጠው ማይሽረው ዘመን
ይህ ነው ሐቃችን በጥብቅ የሚታመን፡፡
“ለአሥራ ሦስት ወራት
ፀሐይ ማይቸግራት
ምሥራቅ አፍሪካዊት
የፀሐይ መውጫ ሀገር
ተዓምር ያገነናት
ኢትዮጵያ ረቂቅ ናት፡፡”
ከዚህ ሐቅ የራቁ
ባለድንቅ አእምሮ በትምህርት የላቁ
በሙያ ክህሎት ለአንቱነት የበቁ
ዕውቀት የተካኑ
እኒያ አዋቀያኑ ፧
ቅድመ ትንበያቸው
“ለዛሬ አልተሳካም” ደግመው ይሞክሩ
የኢትዮጵያን ጉዳይ ጠልቀው ይመርምሩ
ሥረ መሠረቷን
ረቂቅ ምሥጢሯን ዘልቀው ይፈትሹ
እነሱ እንዳሉቱ
ጥላው ያጠላበት ፅልመት በትንሹ
የትአል የጋረዳት?!? የፀሐይ ግርዶሹ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#የእንባ_ቀብድ


#ክፍል_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

ከዚያ ቀን በኋላም ብዙ ጊዜ ወደዚህ ሱቅ ስትመጣ፡ ኮስተር እንዳለች የምትፈልገውን ገዝታ ነው የምትሄደው።

ፋሲል መደንገጤን አይቶ እየሳቀ “እስደነበረችህ አይደል?” አለ።

“ምን ሁና ነው እንደዚህ አነር የሆነችው በናትህ?”
“ሚስኪን ልጅ ነች …ባሏ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታክሲ ምናምን ነበር የሚሠራው፣ በሆን
እክሲደንት' እንዳይሠራ ታግዷል.አሁን እሷ ነች እየሠራች ቤተሰብ የምታስተዳድረው::
አሰበኸዋል? አዲስ አበባ መሬት አይንካኝ የምትል፣ በሕዝብ ጭብጨባና አድናቆት ታጅባ
የኖረች ልጅ፡ እዚህ ሞት የረሳቸው፣ እንደ ድንጋይ የሚከብዱ ባልቴቶችን፣ ስታነሳና ስታስተኛ መዋል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ? ከሥራው በላይ የሚጎዳው ግን ከአገር ቤት ይዘውት የሚመጡት አጉል ተስፋ ነው፡፡ መቼም በዕድሜ አባቷ የሚሆን ሰውዬ አፍቅራ አታገባም፡፡ የፈረደበት አሜሪካ ለመምጣት፣ ያገኙትን ያገባሉ በቃ! የማታፈቅረውን ስታገባ፣ ምንጊዜም ውስጥህ ተቀብሮ የሚያሰቃይህ፣ ረግጠኸው የመጣኸ ፍቅር ይኖር ይሆናል፣ ስቃዩ ቀላል አይደለም፡፡ የማታፈቅረውን ሰው አግብታ፣ በምድር ላይ ይኖራል ብላ እንኳ አስባው የማታውቀውን ከባድ ሥራ በቀን አሥር ሰዓት እየሠራች፣ አሜሪካ
አለ የተባለው ነገር ሁሉ አረፉ ሲሆን ህመሙ ቀላል አይደለም፡፡ መፍረድ አይቻልም፡፡በዚያ ላይ ሁለት ልጆች አሏት፡፡ እዚህ አገር ልጅ ማሳደግ ኢትዮጵያ ሁለት ሥራ ከመስራት እኩል ነው … ራሷን እንኳን መጠበቂያ ሰዓት የላትም፡፡ አንዳንዴ ሰላም ሆና ስታወራ ግን እንዴት ጥሩ ልጅ መሰለችህ!”

ከዚህ ሁሉ አገር ሰላም ከሆነ እዛው ቢሰሩስ እንዲህ ብር የማያስታምመው የዕድሜ
ልክሸ ድብርት ተሸክሞ ከመኖር …” አልኩ።

ግው ከአገሩ የሚሰደደው ስላም ስላጣ ብቻ ይመስልሃል? አገሩ በጦርነት እየታመሰ፤
ምድሩን የሚገለባብጥ ቦምብ እየወረደብህ፣ አገሬን የሙጥኝ ልትል ትችላለህ!
ምክንያቱም ከምትወዳቸው ሰዎች ላለመለየት፡፡ የአምባገነን መንግስት እርግጫ ችለህ
እስርና እንግልቱን ተቋቁመህ ከነጠባሳህ ምድርህ ላይ መኖር ትችል ይሆናል. አየህ ሰውን ከአገሩ የሚያሳድደው ጦርነትና አምባገነን ሥርዓት ብቻ አይደለም! ድህነት ያስጨነቀው የእናትህ ፊት… ርሃብና መታረዝ ያጎሳቆላቸው ወንድምና እህቶችህ ፊት የማትጠግበው የእናትህ ፊት ከአንባገነን ስርዓት በላይ አስጨንቆ ወደስደት ሊገፋህ ባይናገሩትም ድረስልን ሲሉህ ሻንጣህን ይዘህ እንድትሰደድ ያስገድድሃል፡፡ አይተህ
ይችላል! ሂድና እርዳኝ የሚል ጎስቋላ ፊቷ ላይ እንባ እየጎረፈ በአንደበቷ 'አትሂድብኝ የምትልህ እናትህ ወደስደት ትገፈሃለች… አብሮ የሚበላ አብሮ የሚጠጣ' የምትለው ጎረቤት በተራ የዓውዳመት ድግስ ፉክክር፣ ለተራ የልብስና ጫማ ውድድር ወደ ስደት ሊገፋህ ይችላል. ህፃናት ወንድም እህቶቸ ጎረቤት የበዓል በግ ሲታረድ አይተው ተስማቸው ብለህ ነፍስህ ወደሚታረድበት ምድር ልትኮበልል ትችላለህ” ፋሲል ክርር ባለ ፊቱ መራር የራሱን ስደት እያስታወሰ ብሶቱን ዘረገፈው፡፡ የሁለተኛ ዓመት የህክምና ተማሪ እያለ ነበር አቋርጦ ወደ አሜሪካ የመጣው፡፡

ልጅቱ ልክ ፋሲል እንዳለው ቆይታ፣ ያውም መንገድ ላይ አውቶብስ ስጠብቅ፣ አዲስ
ቲዮታ ሃይላንደር መኪናዋን ድንገት እፊቴ አቁማ “ግባ ላድርስህ አለችኝ፡፡ ገባሁ።

በቀጥታ ይቅርታ! ባለፈው ትንሽ ባለጌ ሆንኩ፣ ልክ አልነበርኩም፡፡ ሥራ ቦታ አለመግባባት ምናምን ስለነበር እንደ ተበሳጨሁ ፊት ለፊቴ አግኝቼህ ጮኸኩብህ…ሶሪ ፈገግ አለች፤ ፈገግታዋ ያምራል፡፡

“ምንም አይደል?”

አዲስ ነህ መሰል?”

አዎ፣ ብዙ አልቆየሁም::”

እንኳን ደህና መጣህ! አሜሪካ ከተማርክ፣ ከጠነከርክ፣ ቆንጆ አገር ነት አለችኝ፡፡አመስግኜ እቤቴ በር ላይ ወረድኩ፡፡ መኪናውን በሚያስፈራራ ፍጥነት አዙራ እንደእብድ
ተፈተለከች፡፡ እዛ የብዙ ኢትዮጵያዊያን ህልም የሆነ ዘመናዊ መኪና ውስጥ የከሸፈ
ህልም ነበር፡፡

"አብርሽ!"

አቤት ዶክተር!

ሁነኛ፣ ቁመቷ ዘለግ ያለ፣ ቆንጆ፣ ለሚስትነት የምትሆን ልጅ አገር ቤት አታውቅም,,

"ልታገባ አስብክ እንዴ ዶክተር?”

አወቀ ብቸኝነት በቃኝ! ከአገር ቤት አንዲት ቆንጆ፡ጨዋ ሴት አግብቼ እርፍ ብዬ መኖር ነው የምፈልገው ትክ ብዬ አየሁት፡፡ ከሠላሳ ዓመት በላይ አሜሪካ ኗሯል፤ ብዙ ከመቆየቱ ብዛት፡
አሜሪካን ያገኛት እሱ ነው የሚመስለኝ:: ኢሕአፓ ጊዜ አሲምባ ወደሚባል ቦታ ዘምቶ፣ ጓደኞቹ ሲደመሰሉ እሱ ተርፎ አሜሪካ የገባ ሰው ነው። ከዚያ በኋላ ፖለቲካ የሚባል እርግፍ አድርጎ ትቶ፣ ፊቱን ወደ ትምህርት አዞረ: አንዳንዴ ግን እያገረሸት ፖለቲካ ማውራት ሲጀመር ማቆሚያ የለውም ፡፡ እዚያው ፋሲል ሱቅ ጓደኞቹ ጋ ሲመጣ ነው የተዋወቅነው:: ጥሩ ሰው ነው፡፡ ጨዋታ እና ሳቅ ይወዳል፡፡ ስለፈታት ሚስቱ ማውራት
ከጀመረ፣ ጥርስ እያስከድንም፡፡ እሱ እንደሚለው ከሆነ፣ ሚስቱ ቀናተኛ ነበረች፡፡“ተሳስቶ በቲቪ አንዲት ቀጭን ሴት ካደነቅሁ፣ ጧት ተነስታ መሮጥ ትጀምራለች፡፡አንዳንዴ በእልህ ረዥም ርቀት ሩጣ መመለስ ስለማትችል፣ ደውላ ና ወደ ቤት መልሰኝ ትላለች ይላል እየሳቀ፡፡ ሰው እንዴት መመለስ ወደማይችልበት ርቀት ይሮጣል?
ሃሃሃሃሃ

ታዲያ ስለ ፖለቲካ ሲያወራ በብስጭት ወደ እኔ እየተመለከተ “ፖለቲካ ሸርሙጣ ነው !ተመልከት፡ ከንጉሱ ጀምሮ የፖለቲካ እሳት ደሃውን እንጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ መሪዎችን አቃጥሎ አያውቅም፡፡ ካላመንክ አንድ በአንድ እያነሳን እንጫዎት… እዚህ አገር ተምሮ እና ተንደላቆ የሚኖረው ብዙኃኑ፣ ግፋ በለው! ሲል የኖረ ነው፡፡ መንግሥቱ ኃይለማርያም ያንን ሁሉ የደሃ ልጅ ማግዶ እሱ ዛሬ የት ነው? 'ዚንባቡዌ ተንደላቆ
ይኖራል፡፡ የኦነግ መሪዎችን ተመልከት፥ ወያኔዎችን ተመልከት ምን ሆኑ? ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርስ በእርስ ጦርነት ወጣቱ ነው የሚማገደው ሚስኪን ወጣቶች በፕሮፖጋዳ ያበደ አለማስተዋል ነው፡፡ ወጣት አልዋጋም ካለ፣ መሪዎች ሲጨባበጡ ነው የምታገኛቸው! እንዲህ ብለው ስንጥር አያነሱም፡፡ ምድረ ደም መጣጭ! ስንት ጓዶቻችን በርሃ ላይ ቀሩ! ስንት ጅኒየሶች! እንኳን ጦርነቱ፣ የፖለቲካ ወሬው ያደንዝሃል፡፡ ከዚህ ከብከተ እንቶፈንቶ ራቅ! ተማር! ተማር! አሁንም ተማር! ማንም መሀይም መተኮስ ይችላል! መግደል ጀብዱ አይደለም፤ ጅብም ሰው ይገድላል! ታይፎይድም፣ ወባም ሰው ይገድላሉ! ዓላማ የሌለው ሞት፣ አገር ሽርፎ ከመሸጥ እኩል
ነው ለምንድነው የምትሞተው?…ለምንድነው ወጣት የሚሞተው? ሊታረድ እንደሚነዳ
በሬ የማይረሳ ተስፋና ጥቅማጥቅም እንደ እርጥብ ሳር እያሸተቱ ወጣቱን ወደ ቄራ
ይወስዱታል፡፡ ወጣቱም ብልጥ የሆነ፣ ከሌላው የተለየ የገባው የረቀቀ፣ የመጠቀ አድርጎ
ራሱን ያያል ፤ሲሰተሙ ነዉ እንደዚያ የሚያደርግህ ከአንተ በላይ አዋቂ የሌለ መስሎ እንዲሰማህ እለፍ ብለህ እጅህን ስትዘረጋ አረፋ ነው ፡፡ ፖለቲካ እንኳን ይዘቱ ቅርፁ ለማንም ገብቶ አያውቅም ፤ፈሳሽ ውሃ ነው ፤ቅርፅ የለውም፡፡ አንተ ውስጥ ሲገባ አንተን ይመስላል፣ እኔ ውስጥ ሲገባ እኔን ሁላችንም ብርጭቆዎች ነን፡፡ በስልጣን ከፍ ያሉ
ያጋጩ ችርስ' የሚባባሉብን” በብስጭት ይናገራል፡፡ ሁልጊዜም እንዲህ ካወራ በኋላ
ሲጋራ ያጨሳል፡፡

ትምህርቱ በትክክል ለምን እንደሆነ እንጃለት፣ ብቻ በሆነ የባዮሎጂ ትምህርት ዶክትሬቱን ይዟል! አግብቶ ሁለት ልጆች ወልዶ፣ አድገው ዩኒቨርስቲ ገብተዋል፡፡ከሚስቱ ጋር የተፋቱት ከአራት ዓመት በፊት ነበር፡፡ ሰውዬው ታሪክ ብዙ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ አሁን ግን ዘለግ ያለ የሬሳ ሣጥን በመፈለጊያ
👍1
ዕድሜው፣ ዘለግ ያለች ሴት ይፈልጋል: ያውም ቆንጆ፣ ያውም ጨዋ፣ ያውም ልጅ እግር! መቼም ደግ ኑሮ ይዞት እንጂ ዕድሜው ስድሳን ሳይሻገር አይቀርም::

ታዲያ በዚያ ሰሞን ትልቅ መነጽሩን ይሰካና፣ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ላይ ሴት ሲያስስ ይውላል! አንድ የተረዳሁት ነገር፣ አሜሪካ ያሉ አንዳንድ ወንዶች፣ በተለይ ትንሽ ጥሩ ሥራና ገንዘብ ቢጤ ካላቸው፣ ድፍን የኢትዮጵያ ሴት አሜሪካ ያለ ወንድ ላግባሽ ካላት፣ ትዳር ቢኖራት እንኳ ጣጥላው የምትመጣ ይመስላቸዋል፡፡ ልከራከር ሞክሬ ነበር ገና አዲስ ነህ ዝም በል” ተባልኩ፡፡ ትዕቢት ያጠየመው በራስ መተማመናቸው የሚገርም ዓይነት ነው። እናም የዶክተር ጓደኞች (በእርሱ ዕድሜ የሚሆኑ) በየሳምንቱ

ቅዳሜ ከሰዓት ቁርጥ ሲበሉና ሲያወሩ ወደ ሱቋ ጎራ ሲሉ፣ ልክ እንደ ምግብ ቤት ሜኑ ኮራ ብለው በየስልኮቻቸው ሴት ይመርጣሉ፡፡ ቀፋፊ አስተያየት ሲሰጡ በግርምት እመለከታለሁ።

“ይቺ ጥሩ ናት ዶክተር” ይላል አንዱ፣ ፌስቡክ ላይ የአንዷን ፎቶ እያሳየ፡፡

"አይ!" ዛላዋ ከባድ ነው የግድ ይዛው ነው እንጂ አንድ ስትወልድ ዝርግፍግፍ ውድቅድቅ ነው የምትለው"
܀
“ይችኛይቱስ?"

“አይ! ይች ሥራዋ ፎቶ መለጠፍ ብቻ ነው እንደ ጉሊት ፌስቡከ ላይ ተሰጥታ የምትውል ላግባ እንዴ ደሞI?”

እሽ፣ ይች ምን ይወጣላታል? አፈር ስሆን ተመልከታት! ባላገባ ኑሮ አለቃትም ነበር
ሃሃሃሃሃ"

“ይች? እስቲ ከኋላዋ የሚያሳይ ፎቶ ካላት…ዋው ቢዩቲፉል! እስቲ እጇን ጠጋ አድርገው እስቲ እግሯ ….! ልቅም ያለች! እንዲህ ያለችዋን ነው ያልኩህ! የሳቀችበት ፎቶ የለም? ዋናው ፊት ነው ከፍትፍቱ ፊቱ ሃሃሃሃሃሃሃ..አቤት ጥርስ! አቤት ውበት
ምኑን ብትበላው ነው ባክህ? ይኼ ጤፍ እኮ ታምሩ ብዙ ነው! ሃሃሃ! እኔኮ የሚገርመኝ፣
ኢትዮጵያ አሥራ ሦስት ወር ሙሉ ፀሐይና አቧራ ሲከካቸው እየከረመ፣ እንዴት ነው ቆዳቸው እንዲህ የሚጠራው? ደሞ ቅላቷ! ማነው ስሟ? ፊደላዊት… ስሟ ራሱ ማማሩ እሷ ራሷ የግዜር የእጅ ጽሑፍ አይደል እንዴ የምትመስለው! ፓ! ስሟ አፍ ላይ መጣፈጡ ምራቁን ዋጠ ዶክተር፡፡ ትንሽ ስልኩን እየጎረጎረ ቆዬና “አይይይይይይ" አለ

"ምነው?"
ተይዛለች ኢን ርሌሽንሽፕ ይላል ስታተሷ…ወንዱ መች ተኝቶ ያድራል “

ሃሃ…ይችን ይችን ለኛ ተዋት… ዝም ብለህ ጻፍላት…” በየአፋቸው እየተንጫጩ አበረታቱት !ዶክተር ጻፈላት!.....



አንብበው ጨርሰዋል አሁን ደሞ ከዚሁ ሳይወጡ #UNMUTE አድርገው ይውጡ አመሰግናለው

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ