#ማምሻ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
አብሮ አደጌ ሎዛ እና ዳግም(ዳግማዊ ነው ሙሉ ስሙ ሊጋቡ ሽር ጉድ ሲባል፤ ለሁቱም የቅርብ ጓደኛ ስለነበርኩ አብሬ ላይ ታች ማለት ጀመርኩ። ከዳግም ጋር ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ ጓደኞች ነን። በመሃል አቋርጦ ቤተሰቦቹ ጋር አውሮፓ ሄደ እንጂ ዩኒቨርስቲ የገባነውም አብረን ነበር። ታዲያ ስንት ዓመት ሙሉ እዚህ አጠገቤ ሆኖ ያልነገረኝን፣ አውሮፓን በረገጠ በወሩ በጻፈው ደብዳቤ “ከሎዛ ጋር 'ርሌሽን ሽፕ
ጀምረናል!" አለኝ እስቲ ምን አሰደበቃቸው!? እሱስ እሽ የሷ መደበቅ ምን ይባላል?ጭራሽ በኋላ ስሰማ፣ የፍቅር ግንኙነት ከጀመሩ ሁለት ዓመት አልፏቸው ነበር፡፡ ዳግም ስንትና ስንት ቀን አበሳጭቶኝ “ይኼ ከርፋፋ ብጉራም” ብዩ ለሎዛ አምቼዋለሁ፡፡ የአውሮፓ ኑሮ እንዲህ የተወለወለ መስተዋት ሳያስመስለው በፊት፣ ያኔ እንደ ጧት ጤዛ ያበጡ ብጉሮች የወረሩት አሰቃቂ ፊት ነበረው፡፡ የሆነ ሆኖ ከዓመታት በኋላ ሊጋቡ፡
ይኼው ለዳግም ሚዜ እሆን ዘንድ ጠየቁኝ፡፡ እንቢ አይባል ነገር።
ሰርግም ይሁን ሌላ “ማኅበራዊ ጉዳይ" በሚል የዳቦ ስም የተጠቀለለ ግርግር ባልወድም፡
የዚያን ሰሞን ግን ከነሎዛ ቤት አልጠፋ አልኩኝ ሰበቡ “የሎዛን ቤተሰብ እንደቅርብ ሰውነቴ ሥራ ማገዝ አለብኝ የሚል ቢሆንም እውነቱን ለመናገር ግን ምንም የሚታገዝ ሥራ አልነበረም፡፡ ልክ ከሥራዬ እንደወጣሁ ወደነሎዛ ቤት መሮጤ ምስጢሩ ወዲህ ነው፡፡ ሰርጉ ሁለት ሳምንት ሲቀረው፡ በየቀኑ ማታ ማታ በርከት ያልን የቅርብና የሩቅ ጓደኞች ተሰብስበን ያሳለፍነውን እያነሳን መሳሳቅ ከሩቅና ከቅርብ ከተሰበሰቡ የሎዛ እና
የእህቶቿ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሴት ጓደኞች ጋር ሲሳሳቁና ሲያወሩ ማምሸት፣ ደስ የሚል ስሜት ነበረው፡፡ እነሎዛ እነዚህን ሁሉ ሴቶች ምን ቀን እንዳወቋቸው እንጃ፡ለነገሩ እንኳንም አወቋቸው፡፡ ደግሞ ተመራርጠው የተወዳጁ ይመስል ሁሉም
ቆንጆዎች፣ በውድና በቆንጆ ልብሶች የተሽቀረቀሩ ፣ የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች መዓዛ አየሩን ሞልቶ የሚናኝ፡ ሁሉም ጨዋታ አዋቂዎች፡ እግዜር ድግስ እንዲያደምቁ የፈጠራቸው የሚመሳስሉ ውብ እና ወጣት ሴቶች እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ቆነጃጅት
ከብዙ ሳቅና መሽኮርመም ጋር እዚያ ቤት ያመሻሉ ቢባል፣ እንኳን የእኔ ቢጤው ወጣት፣
እንደ ዶሮ በጊዜ አልጋው ላይ የሰፈረ ሽማግሌም ቢሆን እስቲ ምርኩዜን አቀብሉኝ ብሎ ወደነ ሎዛ ቤት ማዝገሙ አይቀርም፡፡
አንድ ቀን ታዲያ እንደልማዴ ከሥራ ስመለስ፣ ቶሎ ልብስ ቀይሬ ወደነሎዛ ቤት ተጣደፍኩ:: እቤት ስደርስ ሎዛ ፊቷ በርበሬ መስሎ፣ ስስ ነጭ መጋረጃ የመስቀያ ብረት ላይ ትሰገሰጋለች፡፡ ሁሉንም ሰላም ካልኩ በኋላ “ሙሽሪት?” ብዬ ለመቀለድ ሞከርኩ፡፡
ሁልጊዜ ስታኮርፍ እንደምትሆነው ዓይኔን ሳታይ እ” ብላ ጉንጨን ጉንጨን በጉንጫ
ነካ አድርጋ ወደ መጋረጃዋ ተመለሰች የምቀመጥበት ስፈልግ “ና እዚህ ጋ አብርሽ
አለችኝ ፍኖት፤ በተቀመጠችበት ረዥም ሶፋ ላይ ጠጋ ብላ ቦታ እያመቻቸችልኝ፡፡ የሎዛ እህት ነች፡፡ እሷም ፊቷ ልክ አይደለም፡፡ አብሮ ከማደግ ባገኘሁት ልምድ፣ የቤተሰቡን ፊት እንደ መጽሐፍ በማንበብ ተክኛለሁ፡፡ ይኼን ፊት አውቀዋለሁ፡፡ከሎዛ ጋር ሲጣሉ ዓይኗ ሁልጊዜ በቁጣ ይጉረጠረጣል፡፡ አንድም ቀን ተስማምተው አያውቁም:: እናታቸው ሁልጊዜ “እናንተ ልጆች ምን እንደ ጣውንት ያናጫችኋል?” ይላሉ:: በውስጤ ነገር አለ እያልኩ ሂጄ አጠገቧ ተቀመጥኩ፡፡ ፍኖት ከወደታች ስፋ ስለምትል ቦታው ጠበበኝ፡፡
ከተቀመጥኩ በኋላ ጉልበቷን ቸብ አድርጊያት ሰላም ነው?» አልኳት፡፡
“ምን ሰላም አለ! ይች ክሬዚ እያለች” አለችኝ፡፡ እንዲህ ናት ፍኖት ነገር ከያዘች ቶሎ ማፍረጥ ነው፡፡
“ምን አደረገች ደግሞ? ሙሽራኮ ቀልብ የለውም”
አንተ ምናለብህ! ስሰላም ሥራህ ውለህ ትመጣለህ… ቤቱ ሲታመስ ነው የዋለው:: ማሚ
በብስጭት እራሷን አሟት ተኝታለች”
“ምንድነው? ባል ይቀየርልኝ አለች እንዴ? እሷኮ አታደርግም አይባልም” በቀልዱ ከመሳቅ ይልቅ በእልህ ወደ ሎዛ እያየች “ባክህ አትቀልድ! ይኼ ነገር ሲሪየስ' ነው አለችኝ ከረር ባለ ድምፅ።
እኮ ምንድነው? ችግር አለ?”
እሷ ካለች ሁልጊዜም ችግር አይጠፋም፡፡ እስከዛሬ ማን እንደሆነች አልናገርም ብላ
የደበቀቻት ሚዜ ታውቀች እለችኝ፡፡
ከወራት በፊት ተናግራ፣ የአንዷን ማንነት ግን “ሰርጉ ካልደረስ አልናገርም ብላ ሰለነበር፣
አረ ባክሽ!…ማን ሆነች?” በጣም ነበር ለማወቅ የጓጓሁት ሎዛ ሁሉንም ሚዜዎቿን ሰው ሁሉ በድብብቆሹ ግራ ተጋብቶ ነበር። እስቲ አሁን ሚዜ ምን ይደበቃል?እየተባለ፡፡ ነገሩ ይበልጥ ያጓጓኝ ደግሞ፣ እኔንም በቀጥታ ስለሚመለከተኝ ነበር፡፡
ስድስት የወንድ ሚዜዎች ተመርጠን፣ አምስት የሴት ሚዜዎች ብቻ በመታወቃቸው፣
ከእኔ ውጭ አምስቱም ሚዜዎች ከሴቶቹ ጋር ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ የኔዋ እየተጠበቀች
ነበር፡፡ ሚስትም እንዲህ በጉጉት አይጠበቅ” እስኪባል፡፡ መቸም በሰርግ ላይ ከባልና
ሚስት ቀጥሎ የሚዜዎች ጥምረት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር ነው፡፡ አንዳንዴም ሚዜዎች እጩ ሙሽራ የሚሆነበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ ማን ያውቃል? አምስቱ የወንድ ሚዜዎች፣ እነዚያን ሽንጣቸው እንደ ነብር ሸንጥ የሚመዘዝ፣ ጸጉራቸው ወገባቸው ላይ የሚዘናፈል፣ እንደ ወንዝ ዳር ቄጤማ ነፋስ የሚያወዛውዛቸው
የሚመሳስሉ ሴቶችን አቅፈው ዳንስ ሲለማመዱ፣ ሁለት ሁለት እየሆኑ ከወዲያ ወዲህ ሲሉ፧ ሚዜ ሳይሆኑ አብረው የሚዳሩ አምስት ሙሽሮች ይመስሉ ነበር፡፡
ቤተሰቡም ሆነ ሚዜዎቹ ባያምኑኝም፣ ሎዛ ለእኔም የተደበቀችዋን ሚዜ ማንነት
አልነገረችኝም ነበር፡፡ እውነቴን ነበር አልነገረችኝም። ሁሉንም ነገር የምትነግረኝ ንስሐ
አባቷ እደረጉኝ እንዴ? ከገዛ ጓደኛዬ ጋር ሁለት ዓመት፣ ያውም አፍንጫዬ ሥር በፍቅር
ዓለሟን ስትቀጭ ራሱ መች ነገረችኝ? ሁሉም ያሰቡት እኔና ሎዛ ሚስጢረኞች ስለሆንን፡
የእኔዋን ልዕልት መጨረሻ ላይ የምታመጣት አድርገው ነበር፡፡ ከትንሽ አድሎ ጋር ቆንጆዋን ካለሽሚያ ልታሳቅፈኝ፡፡ ለነገሩ ጉራ ሳይሆን፣ ከወንዶቹ ሚዜዎች፣ በመልክም ይሁን በአቋም፣ እኔ እንደማምር በአለፍ ገደም ነግረውኝ፣ ኩራት ቢጤና የተሻለችው ሚዜ ትገባኛለች የሚል ትንሽ ትዕቢት ልቤ ውስጥ ነበር፡፡
ፍኖት ታዲያ የሚዜዋን ማንነት ስጠይቃት፣ ከግርምትና ከብስጭት "ሆሆ ጋር የተቀላቀለ ሳቅ ስቃ፣ አንገቷን እየሰበቀች፣
“የማታውቅ ለመምሰል ነው?” አለችኝ
እግዚአብሔርን ፍኖት! ለምንድነው የማታምኚኝን ታውቂያት የለ እንዴ ሎዛን? ችክ ካለች አለች ነው፡፡ ምንም አልነገረችኝም
እንግዲያስ ጉድህን ስማ! ማምሻ የምትባለውን ሴትዮ ሚዜ አደርጋለሁ እያለች ነው አለችኝና እጅ በደረት አድርጋ ፍጥጥ ብላ አየችኝ፡፡
“ማምሻ? ማምሻ? ይቺማምሻ?” አልኩ በጣቴ ወደነማምሻ ቤት አቅጣጫ እየጠቆምኩ :
“አወና አለችኝና ትክ ብላ እየችኝ፡፡ ዓይን ለዓይን ተፋጠን ለሰኮንዶች እንደቆየን፡
“ካላመንክ ራሷን ጠይቃት!"አለች፣ በአገጯ ወደ ሎዛ እየጠቆመች፡፡ ሳቅሁኝ መጀመሪያ ቀልድ ነበር የመሰለኝ፡፡ ፍኖት ኮስተር ስትል ግን፣ ነገሩ የምር መሆኑ ገባኝና፣ እንደገና መሳቅ ጀመርኩ፡፡
“ሳቅ፡ አንተ ምናለብህ? አልደገስክ ሰው አልጠራህ! ውርደቱ የኛ” ብላኝ ተነስታ
እየተቆናጠረች ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ፊቴ ላይ ለይቶለት ያልፈነዳ ሳቅ እያንዣበበ
ባለማመን ወደ ሎዛ ስመለከት፣ ዓይን ለዓይን ተገጣጠምን፡፡ ኮስተር ብላ በከንፈር
እንቅስቃሴ ብቻ “ዋት?” አለችኝ፡፡ መስማቴን አውቃለች:: ሳላስበው ንጥሻ የሚመስል
ሳቅ ከውስጤ ወጣ:: ትከሻዬ

👍1
እኩል ከሳቁ ጋር ወደላይ ተናጠ፤ ፈጣን እስክስታ
የሚመስል መናጥ።
“ማምሻ ሚዜ!?” አልኩ ለራሴ: የሎዛ ነገር ሁልጊዜ ግራ ቢሆንም፣ ይኼንኛው ግን ባሰ።
ይቺ ልጅ በዚህ ውዝግብ ወዳድነቷ እንዴት ነው ይኼ ትዳር…? ሐሳቤን ሳልጨርስ ተውኩት፡፡ ለምን በሰው ትዳር አሟርታለሁ? ብዬ፡፡ ፍኖት ተመልሳ ብቅ አለችና፣ ሎዛ እንድትሰማ በሚመስል ዘረኛ ድምፅ፣ አብርሽ ማሚ ትፈልግሃለች" ብላ ጮኸች፡፡
ተነስቼ ወደ ውስጥ ስገባ፤ሎዛ ከምኔው እንደደረሰች እንጃ እየተቆናጠረች ኮሪደሩ ላይ
ገፍታኝ አለፈችና፣ እናቷ ያሉበትን ክፍል በርግዳ ቀድማኝ ገባች::.......
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#MUTE ያደረጋቹ ደሞ ምርጥ ምርጥ ድርሰት አምልጧቹሀል ቶሎ ብላቹ #UNMUTE አድርጉ

#የሀገሬ_ሰው
“እንደምን አድርጎ እንዴት ነው የሚኖረው?
የጽልመቱን ዘመን
በብሩህ ብርሐን ማነው 'ሚቀይረው?
“ለምንድን ነው?” አለ “ማነው ሚመልስው?”
እልፍ አዕላፍ ጥያቄ ጠየቀ የሀገሬ ሰው::
በገዛ ሀገሩ ላይ
በሐሳብ መግባባት መስማማት ሲጠፋ
ቂም በቀል ጥላቻ
ሥቃይና በደል ግድያው ሲከፋ
እሥራት እንግልት ስደቱ ሲስፋፋ
ሰላም ተናግቶበት
ፍቅርም መክኖበት ሲቀር ያለ ተስፋ
ጣዕሟ ቢጠፋበት ሕይወት ብትመረው
ዘመኑን በአግባቡ በቅጡ ያልኖረው
ምስኪኑ የሀገሬ ሰው መኖር ቢቸግረው
ለፈጣሪው አለው
“አኗኗሬን ሳይሆን.ሞቴን አሳምረው!”
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
“እንደምን አድርጎ እንዴት ነው የሚኖረው?
የጽልመቱን ዘመን
በብሩህ ብርሐን ማነው 'ሚቀይረው?
“ለምንድን ነው?” አለ “ማነው ሚመልስው?”
እልፍ አዕላፍ ጥያቄ ጠየቀ የሀገሬ ሰው::
በገዛ ሀገሩ ላይ
በሐሳብ መግባባት መስማማት ሲጠፋ
ቂም በቀል ጥላቻ
ሥቃይና በደል ግድያው ሲከፋ
እሥራት እንግልት ስደቱ ሲስፋፋ
ሰላም ተናግቶበት
ፍቅርም መክኖበት ሲቀር ያለ ተስፋ
ጣዕሟ ቢጠፋበት ሕይወት ብትመረው
ዘመኑን በአግባቡ በቅጡ ያልኖረው
ምስኪኑ የሀገሬ ሰው መኖር ቢቸግረው
ለፈጣሪው አለው
“አኗኗሬን ሳይሆን.ሞቴን አሳምረው!”
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
👍1
#ዘይገርም_ነገር
ችግሩን ከምንጩ ከሥሩ አድራቂ
የሀገር ሽማግሌ ሳለ መላ አዋቂ
ገላጋይ ሳይጠፋ አራቂ አስታራቂ
የሀገር ልጅ በዋዛ
ውድ ሕይወቱን ሲያጣ
ፍትሕ የለሽ ሆኖ
በእሥራት ሲቀጣ
መኖሩ ሳያንሰው
ለሀገር ልጅ ለሀገር ሰው
አስለቃሽ ጭስ ሳይቀር
ከውጭ እሚመጣ
እርግማን ነው መሰል
የፈጣሪ ቁጣ፡፡
ዘይገርም ነገር በዓለም አስደናቂ
እንደሳቅ ተወዶ ሆኖ ተናፋቂ
ሞግዚት ተሰየመ ለዕንባ ዕንባ ጠባቂ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
ችግሩን ከምንጩ ከሥሩ አድራቂ
የሀገር ሽማግሌ ሳለ መላ አዋቂ
ገላጋይ ሳይጠፋ አራቂ አስታራቂ
የሀገር ልጅ በዋዛ
ውድ ሕይወቱን ሲያጣ
ፍትሕ የለሽ ሆኖ
በእሥራት ሲቀጣ
መኖሩ ሳያንሰው
ለሀገር ልጅ ለሀገር ሰው
አስለቃሽ ጭስ ሳይቀር
ከውጭ እሚመጣ
እርግማን ነው መሰል
የፈጣሪ ቁጣ፡፡
ዘይገርም ነገር በዓለም አስደናቂ
እንደሳቅ ተወዶ ሆኖ ተናፋቂ
ሞግዚት ተሰየመ ለዕንባ ዕንባ ጠባቂ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#የማይሞተው_ሞተ
ንፁህ ሆነህ ሳለ
አዛኝ ሆኖ ልብህ
ሞትህን ፈልገው
አይሁድ መከሩብህ
አወቀህ እንዳላወቅህ
ምክራቸው ሲፀና
የሞትህን ፅዋ ተጎነጨህና
በጠላቶችክ ፊት
ቆምክ በትህትና
በአንደበትህ ሀሰት
ባይገኝም ቅሉ
የልባቸው ክፋት ለከቱን አጣና
ሁሉም ፈረዱብህ ይሰቀል እያሉ
ጲላጦስም ገፋህ ሄሮድስም አልራራ
አሰለፈው ሰጡህ አንተን ለመከራ
አንገላቱህ በግፍ ገረፋህ አብዝተው
አዳኝነትህን ክብርህን ዘንግተው
ተዘባበቱብህ አፋቸውን ከፍተው
ልባቸውን ዘግተው
አጥንትህ ሲቆጠር
ስጋህ ተበጣጥሶ
መላ ሰውነትህ ደም አቯራ ለብሶ
ንጉስ ሆይ እያሉ ይሳለቁበሀል
አንተ የኔ ቤዛ
መስቀል ተሸክመህ ስቃይ በዝቶብሀል
ምድረ ጎለጎታ መከራህ በረታ
በሾህ አክሊል ስለት እራስህ ተመታ
እጅህን በሚስማር
እግርህን በሚስማር
ልብህ ደረትህም በሚስማር ተወጋ
ሰጋህ ተቆረሰ
አጥንትህ ደቀቀ
የአለሙ ጌታ አልፋና ኦሜጋ
ከወንበዴዎች ጋር አቆሙህ በመስቀል
ቀኑ ደረሰና
የአዳም እርግማኑ በሞትህ ሊነቀል
ተጠማሁ ብትልም
የጭካኔን ፅዋ ቀድመው ስለዋጡት
ሀሞት ሰጡህና ጥምህን ቆረጡት
አለቀሰች ድንግል አዘነች አብዝታ
ተሰቅለህ በመስቀል
በግፈኞች በትር መከራህን አይታ
እሚያደርጉትን ሁሉ እያቁትምና
አባት ሆይ ማራቸው በማለትም ፀለይክ
የምህረትህ ነገር ጥግ የለውምና
ላደረገው ሁሉ በአይሁዶች እይታ
መሞት ሆነ ዋጋህ
ትንቢት ይፈፀም ዘንድ
በፈቃድህ ለየህ ነፍስህን ከስጋህ
ምድር ተናወጠች ጨርቃም ደም ለብሳ
ከዋክብት ረገፉ መቃብር ተከፍቶ ሙታኑም ተነሳ
ቃሉም ተፈፀም አዳም ነፃ ወጣ
እንጦረጦስ ገባ ሰይጣን ሀይሉን አጣ
የሚሆነው ሆኖ የማይሞተው ሞተ
የሂወት በራችን
በደሙ ማሀተም ዳግም ተከፈተ
ይሄን የአምላክ ፍቅር
የማዳኑን መንገድ መግለፅ ይከብደኛል
ምትን በምት ሽሮ
ሂወትን የሚሰጥ ከ ወዴት ይገኛል
የማይሞተው ሞተ
🔘በሳሙኤል አዳነ🔘
@sam2127
💘❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️💘
ንፁህ ሆነህ ሳለ
አዛኝ ሆኖ ልብህ
ሞትህን ፈልገው
አይሁድ መከሩብህ
አወቀህ እንዳላወቅህ
ምክራቸው ሲፀና
የሞትህን ፅዋ ተጎነጨህና
በጠላቶችክ ፊት
ቆምክ በትህትና
በአንደበትህ ሀሰት
ባይገኝም ቅሉ
የልባቸው ክፋት ለከቱን አጣና
ሁሉም ፈረዱብህ ይሰቀል እያሉ
ጲላጦስም ገፋህ ሄሮድስም አልራራ
አሰለፈው ሰጡህ አንተን ለመከራ
አንገላቱህ በግፍ ገረፋህ አብዝተው
አዳኝነትህን ክብርህን ዘንግተው
ተዘባበቱብህ አፋቸውን ከፍተው
ልባቸውን ዘግተው
አጥንትህ ሲቆጠር
ስጋህ ተበጣጥሶ
መላ ሰውነትህ ደም አቯራ ለብሶ
ንጉስ ሆይ እያሉ ይሳለቁበሀል
አንተ የኔ ቤዛ
መስቀል ተሸክመህ ስቃይ በዝቶብሀል
ምድረ ጎለጎታ መከራህ በረታ
በሾህ አክሊል ስለት እራስህ ተመታ
እጅህን በሚስማር
እግርህን በሚስማር
ልብህ ደረትህም በሚስማር ተወጋ
ሰጋህ ተቆረሰ
አጥንትህ ደቀቀ
የአለሙ ጌታ አልፋና ኦሜጋ
ከወንበዴዎች ጋር አቆሙህ በመስቀል
ቀኑ ደረሰና
የአዳም እርግማኑ በሞትህ ሊነቀል
ተጠማሁ ብትልም
የጭካኔን ፅዋ ቀድመው ስለዋጡት
ሀሞት ሰጡህና ጥምህን ቆረጡት
አለቀሰች ድንግል አዘነች አብዝታ
ተሰቅለህ በመስቀል
በግፈኞች በትር መከራህን አይታ
እሚያደርጉትን ሁሉ እያቁትምና
አባት ሆይ ማራቸው በማለትም ፀለይክ
የምህረትህ ነገር ጥግ የለውምና
ላደረገው ሁሉ በአይሁዶች እይታ
መሞት ሆነ ዋጋህ
ትንቢት ይፈፀም ዘንድ
በፈቃድህ ለየህ ነፍስህን ከስጋህ
ምድር ተናወጠች ጨርቃም ደም ለብሳ
ከዋክብት ረገፉ መቃብር ተከፍቶ ሙታኑም ተነሳ
ቃሉም ተፈፀም አዳም ነፃ ወጣ
እንጦረጦስ ገባ ሰይጣን ሀይሉን አጣ
የሚሆነው ሆኖ የማይሞተው ሞተ
የሂወት በራችን
በደሙ ማሀተም ዳግም ተከፈተ
ይሄን የአምላክ ፍቅር
የማዳኑን መንገድ መግለፅ ይከብደኛል
ምትን በምት ሽሮ
ሂወትን የሚሰጥ ከ ወዴት ይገኛል
የማይሞተው ሞተ
🔘በሳሙኤል አዳነ🔘
@sam2127
💘❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️💘
#ማምሻ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ተነስቼ ወደ ውስጥ ስገባ፤ሎዛ ከምኔው እንደደረሰች እንጃ እየተቆናጠረች ኮሪደሩ ላይ
ገፍታኝ አለፈችና፣ እናቷ ያሉበትን ክፍል በርግዳ ቀድማኝ ገባች::
አንችን ማን ጠራሽ? እንዲያው አታውሩ እትተንፍሱ ነው እንዴ? አሉ እናቷ ግልፍ ብለው።
ለመጣው ለሄደው ሁሉ ስሞታ፤ ቆይ እናንተ ምናችሁ ተነካ ፡ አምባረቀች፡፡
"ምናችን እንደተነካ እኛ ነን የምናውቀው፡፡ አሁን አትቅለብለቢብኝ ላውራበት አሉ፤ በቁጣ: ግራ ገብቶኝ ቁልጭ ቁልጭ ስል፣
አብርሽ! ይኼው ሞልቶ ለሚንጋጋ ጓደኛ…እኔን ካላዋረድኩ…የአገር መሳቂያ መሳለቂያ
ካላደረኩ፣ ሙቼ እገኛለሁ እያለች ነው፡፡ እንግዲህ አንተም አብረህ ተዋረጅ መሳቂያ ሁኚ ካልክ ደህና! ካልሆነ ይችን እብድ እንደጓደኝነትህ ምከር ዝከር ነገ ቤተሰብ የላትም ወይ መካሪ ጓደኛ የላትም ወይ? ነው የሚባለው"
ኦ ማይ ጋድ! …ማሚ፣ ማምሻ ሚዜ ስለሆነች ምንድነው የምትዋረዱት? ምንድነው አገር የሚስቀው! ኧረ እግዚኣብሔራችሁን ፍሩ፤ ሰውስ ሲሰማችሁ ምን ይላል? እንደ እናንተው ሰው ናትኮ! ሰውሰው!” ብላ ጮኸች፡፡ ስትቆጣ ከንፈሯም እጇም ይንቀጠቀጣል…እልኸኛ ናት፡፡ ከልጅነታችን አንስቶ ያለችው ካልሆነ፡ አገር ነው
የሚታመሰው፡፡
ወዲያ አትፈላሰፊብኝ…ሰው ሲታጣ ይመለመላል ጎሰጣ አሉ…ታዲያ ሰው የሆነች እንደሆነስ? እግዜር ሲፈጥረን መቼም ቦታ ቦታ አዘጋጅቶ ነው፡፡ እኔ መልኳን አልሠራሁ ምንድነው ሰው ለማስኮነን ሩጫ!? ሚዜ ለዓይን የሚያምር፡ ቀልጠፍ ያለ፣ እኩያሽ ሲሆን፤ ለተመልካችም፣ ለደጋሽም፣ ለፎቶም፣ ለቪዲዮም ደስ ያሰኛል ፎቶውም ታይቶ
አይጠገብም፡፡ እኔ ማምሻ ለሚዜነት አትሆንም አልኩ እንጂ፣ ሰው አይደለችም ወጣኝ…ምናለ ክፉ ባታስብዪኝ፣ ከጎረቤት ባታነካኪኝ ከፈለግሽ ከሰርጉ በኋላ በአንቀልባ አዝለሻት ዙሪ” ፍኖት ከኋላዬ በሩን ተደግፋ እንደ ቆመች ቡፍ ብላ ሳቀች፡፡ሎዛ ፊቷ ተቀያየረ፡፡ ወደ እህቷ ዙራ ፓ 'ዲያና' ብላ፣ አሽሟጠጠቻትና እናቷን
ቆፍጠን ባለ ንግግር፣ “ከሰርጉ በኋላ ሚዜ አያስፈልገኝም፡፡ ማምሻ አንደኛ ሚዜዬ
ትሆናለች! አለቻቸው፡፡
ዋ..ት..?” አለት ፍኖት፡፡
አይ! ተይው፣ ተይው እናቴ እኔ ጤነኛ መስለሽኝ ነው… ጭራሽ አንደኛ ሚዜነት እንግዲህ እኔ ሙቼ ከሆነ እናያለን!” አሉ እናቷ ጉልበታቸው ላይ ያስቀመጡትን ትራስ አንስተው፣ በቁጣ ወደጎናቸው እየወረወሩ፡፡
“ቆይ ይኼ ሁሉ ማካበድ ምንድነው?…ሰርግ አይደል እንዴ? የሆነ ሌላ ተአምር
እስመሰላችሁትኮ?”
“ሰርግኮ የአንድ ቀን የባርቲ ቤት ጭፈራ አይደልም፡፡ ታሪክ ነው፡፡ ታሪክ በፎቶ በቪዲዮ
እያንዳንዱ ነገር ተመዝግቦ ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ይገባሻል!?…ተይው፣ ጥፋቱ የአባትሽ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ዩኒበርስቲ ገብቶ ሐኪም፣ መሐንዲስ ሲሆን፣ አንቺ እብደት ልማር ስትይ፣ ይለይልሽ ብሎ ፈቀደ፣ ይኼው …ልብስ መጣል ነው የቀረሽ! (ሰው ሁሉ የሚሉት የሎዛንን ታላላቆች ነው) ..እንግዲህ አሻፈረኝ፣ ከኔ በላይ ሰው ካልሽ፣ …እዛው አባትሽ እንደሚያደርግ ያድርግ” ሎዛ ፍልስፍና ነው ያጠናችው፡፡ ያኔም ፍልስፍና ልማር ስትል፣ እንዲሁ ቤቱ ታምሶ ነበር፡፡ የሎዛ አባት “የወደደችውን ትማር” ብለው ፈቀዱ፡፡ ተመርቃ ካለሥራ ሁለት ዓመት በመቀመጧ፣ በተለይ እናቷ “ብዬ ነበር እያሉ ባላቸውን ይወቅሳሉ፡፡ ደግነቱ
አባትዬው ለወቀሳም ለምስጋናም ግድ ያላቸው ሰው አልነበሩም፡፡ ሎዛ የአባቷ ነገር ሞቷ ነው፡፡ ከሕፃንነቷ ጀምሮ ከአባቷ ሥር አትጠፋም፡፡ ሰፈራችን ውስጥ ወዳለው ግሮሰሪ ሳይቀር ተከትላቸው እየሄደች፣ ባለጌ ወንበር ላይ እግሯን አንጠልጥላ፣ እሳቸው ከጓደኞቻቸው ጋር ዘና ሲሉ፣ እሷ ለስላሳዋን ይዛ ቁጭ ትል ነበር፡፡
የሎዛ ኣባት የተለዩ ሰው ናቸው:: በከተማው የታወቀ ጣውላ ቤት አላቸው። ሲበዛ
ዝምተኛና የሥራ ሰው ነበሩ፡፡ ሚስታቸውን ጨምሮ፣ ወንዶቺም ሴቶቹም ልጆቻቸው
ለከተማው የታወቁ ዘናጮች ቢሆኑም፣ ሰውዬው ከሰኞ እስከ ሰኞ ቱታቸውን ለብሰውና፡
አፉቸው ላይ ከቀንድ የተሠራች ጥቁር ፒፓቸውን ሰከተው ሥራ ላይ ናቸው፡፡ ሁለት ወንድ ልጆቻቸው ሐኪሞች ናቸው፡፡ አንዷ ሴት ልጃቸው፣ ለከፍተኛ ትምህርት ውጭ አገር ነው ያለችው። አርክቴክት ናት፡፡ የሎዛ ታላቅ ፍኖትም በምሕንድስና ነው
የተመረቀችው፡፡ ከቤቱ ልጆች ተለይታ ፍልስፍና ያጠናቸው ሎዛ ነበረች፡፡ ያውም በከፍተኛ ውጤት ዩኒቨርስቲ ገብታ ሥራዬ ብላ መርጣ፡፡ ሎዛ ከልጅነቷም መሬት ከፍ ሰማይ ዝቅ ቢል፣ ካመነችበት ነገር ወደ ኋላ የማትል ልጅ ናት፡፡ እንደዚያም ሆኖ ታዲያ፣ የጓደኞቿ ብዛት ለጉድ ነበር፡፡ እኔ ጋር በአሥር ጉዳዮች ላይ ብናወራ፣ በዘጠኝ ተኩሱ እንስማማም፤ ግን እንዴት እንደሆነ አይገባኝ ሩጨ እሷ ጋር ነኝ ፣እሷም ከአጠገቤ
አትጠፋም፡፡ አሁን ከምታገባው ከዳግም ጋር ራሱ፣ አስር ጉዳዮች ቢያወሩ፣ በአስሩም
እይስማሙም፤ ግን ይኼው ሊጋቡ ነው፡፡ የሎዛ ነገር እንዲህ ነው፡፡ ጭቅጭቋ እንደ ፍቅር
ቃል ሱስ የሚሆን፡፡ በምድር ላይ የሎዛንን ሐሳብ የሚያስቀይር አንድ ሰው ብቻ ነው አባቷ! ይኼው ማምሻ የምትባለውን የሰፈራችንን ልጅ ሚዜ አደርጋለሁ በማለቷ የተነሳው ጭቅጭቅ፣ ለሰርጓ ከየአገሩ በመጡ እህትና ወንድሞቿ፣ በምንቀርባትም ጓደኞቿ እልባት ባለመገኘቱ ጕዳዩ ለውሳኔ ወደ እባቷ ተላከ፡፡ አባት ምንም ይበሉ፣
በውሳኔያቸው ላይ ይግባኝ የለም፡፡
።።።።።።።።።።።።።።
“ማምሻ” ብለው ስም ያወጡላት አባቷ ጋሽ ቢሆነኝ ናቸው። “ማምሻ ቢሆነኝ” (የአባትና
ልጅ ስም እንዲህም ገጥሞ አያውቅ፤ ይላሉ የሰሙ ሁሉ) እሳቸው እንኳን ለክፋት
አልነበረም፤ ወንድ ልጅ ክፉኛ ይፈልጉ በነበረበት ሰሞን፣ የመጀመሪያ ልጃቸው ሴት ሆነች ያውም እናቷን ወይዘሮ ዓምድነሸን የምታስከነዳ መልከ ጥፉ! ጎረቤቱ ቁርጥ እናቷን” እያለ በሰላሙ ጊዜ ለመናገር የማይደፍረውን የወይዘሮ ዓምድነሸን መልክ ጥፉነት፣ በአራስ ጥየቃ ሰበብ ተነፈሰው ቆንጆ ልጅ!ገና ምን አይታችሁ? ከፍ ስትል
መልኳዋ ይወጣል” አሉ አንዳንዶች፡፡ የአራስ ጥየቃ ውጉ ነው ብለው: ማምሻ ከፍ ስትል
ግን ጭራሽ ድንቡሸ የልጅነት ሥጋ ደብቆት የነበረ መልከጥፉነቷ ቁልጭ ብሎ ወጣና፣
ድንገት ሲመለከቷት እንደ ልጅ ስመው ሳይሆን፣ እንደተከሰተ ጋኔል አማትበው የሚያልፉት ልጅ ሆና አረፈች፡፡ እንዲያው ለወላጆቿ ይሉኝታ ሲል ማምሻን ለመሳም የሚገደድ ጎረቤት ዓይኑን መጨፈን ግድ ይሆንበት ነበር። የሆነ ሆኖ ወንድ ልጅ እስኪወለድ መቆያ ትሆናለች ሲሉ፣ አባት “ማምሻ አሏት፡
ይኼን የማምሻ ገድል በመሀላችን እየኖረች፣ ግን በሆነ ሩቅ ዘመን እንደኖረች ጕድ፡ እንደተረት የነገሩን ታላላቆቻችን ነበሩ፤ ያውም በብዙ ሳቅና ፌዝ አጅበው
ይኼ ፌዝና ሳቅ ያጀበው ታሪክ እንዲህ እያሉ ሲያሙሽ፣ ለምን አላችኋት ብዬ ተጣላሁ
በሚል መጠቅለያ፤ ተቆርቋሪ ነን ሲሉ በሚዳዳቸው ነገር አድራሾች፣ ለማምሻ ለራሷ
ይደርሳታል: በዚህ ዓይነት ፌዝ ነበር እኩል ከእኩዮቿ ጋር የመቆም መብቷን በየቀኑ ሰነጣጥረን፣ አንዲት ግፋችን ከብዷት ገና በልጅነቷ የጎበጠች ወጣት የፈጠርነው፡፡
ፌዛችን አንገት ማስደፋቱ፣ ለደፊዋ እንድናዝን ሳይሆን፣ በፌዛትችን ጥንካሬ እንድንደመም
እድርጎን፣ ስየቀኑ አዲስ ቀልድና ስላቅ መፈብረክና የግፍ ምርታችንን በጎበጠ ጀርባዋ ላይ ጭነን መሳቅ ቀጠልን:: እናቶችም ለማጉበጡ አልሰነፉ፤ሕፃናት ልጆቻቸው ሲረብሹ
ለማስፈራራት ምን ይሉ ነበር?… “ማምሻን እንዳልጠራት!” ልጆቹ ወደኋላ ተገላምጠው
በፍርሃት ይርዳሉ: መንደሩ ከእናት ጡት በላይ የማምሻን ማስፈራሪያነት እየተጋተ ባደገ
ሕፃን የተሞላ

👍3
ነበር፡፡ እማኝ መጥቀስ ካስፈለገ፣ ዱዱሻ የምትባለው ሕፃን የሥዕል ደብተሯ ላይ በአረንጓዴ እርሳስ ቀለም ከሳለችው ሰው ፊት ለፊት፣ በጥቁር ቀለም የተንጨፈረረ ጸጉር ያለው ፍጥረት ሥላ “ማምሻ ሕፃኑን ልትበላው ሲያለቅስ!” በማለቷ ያ ሥዕሏ፣ ከፒካሶ ሥዕል በላይ ቅርስ ሆኖ፣ በየመንደሩ ሰው እጅ እየዞረ ሲታይና ሳቅ ሲፈጥር ከርሞ ነበር፡፡
“ስምን መልአክ ያወጣዋል” ይሉት ብሂል፣ በስም ሰበብ በምንለጥፈው ሟርት ሰውን ለመግፋት ለራሳችን የምንስጠው ፈቃድ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ላሟረትንበት ሰው ያስመርነውን የግፍ መስመር በዘወርዋራ ተረትና ምሳሌ ስንጠቁም፣ ድንበርህ እዚያ ነው፡እንዳትቀላቀለን ዓይነት የማይታይ እስር ቤት:: ማምሻ ስታድግ፣ በስም ተጭኖ ከኋላ
የሚያዘግም ሟርት ፈጥኖ ተከተላት:: የተመኙትን ወንድ ልጅ ይቅርና፣ ጭራሽ ልጅ የሚባል ነገር ማግኘት ያልቻሉት አባቷ ጋሽ ቢሆነኝ፣ በዘጠኝ ዓመቷ ማምሻንና እናቷን እባዶ ቤት ጥለዋቸው አገራቸው ገቡ አሉ…(አገራቸው የት እንደሆን እንጃ! …እንደዛ ነው የሚለው ጎረቤቱ ) ቆይቶ በወሬ ወሬ…“እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛልያ ከሚል ማጀቢያ ተረት ጋር፣ ገጠር አንዲት 'ምን የመሰለች ቆንጆ ልጃገረድ አግብተው ወንድ ልጅ ለላይ
በላዩ ወለዱ ተባለ፤ ከዚያ በኋላ ወሬያቸውም የለ፡፡ የሰው አወራር፣ ጋሽ ቢሆነኝ ትዳራቸውን ሜዳ ላይ በትነው በመሄዳቸው፣ የመውቀስ ሳይሆን ከእስር ቤት ጀብድ ሠርቶ እንዳመለጠ የግፍ እስረኛ፣ በአድናቆትና እንኳን ተሳካላቸው የሚል ስሜት የተሞላ ነበር፡፡

👍2
#ጠያቂ_እና_አማኝ
“ጭራሽ ሰው አታዪም?
ለበርካታ ጊዜያት ቆሜ አይቼሻለሁ
መንገድ ላይ ብቻሽን ምን እያረግሽ ነው? ”
“ሰው እጠብቃለሁ።”
“እንዴት ዓይነቱን ሰው!?!”
“በፍቅሩ በሳቁ ልብን የሚያፈርሰው።”
“ምን ያደርግልሻል?..
ስለምን ያሻሻል?.."
“ልቡ ይፈልግኛል
ልቤም እሱን ይሻል፡፡”
“በርግጥ ይወድሻል?”
ካንጀቱ ያፈቅረኛል፡፡”
“ታዲያ
አውላላ ሜዳ ላይ እንዴት ይተውሻል?
ለምን ይዋሽሻል? ”
ካልመጣ ይነግረኛል
ለምን ይዋሸኛል!?!”
“እቀራለሁ ብሎ እንዴት ይነግርሻል?
አንቺን ላለማጣት ቢያውቀውም ይዋሻል፡፡”
“ጠንቅቄ ሐሳቡን
አውቀዋለሁ ልቡን ፧
ከልቤ አምነዋለሁ
እናፍቀዋለሁ
እጠብቀዋለሁ፡፡”
“በ ጣ ም ትገርሚያለሽ!
እስከመቼ ድረስ ትጠብቂዋለሽ?”
“እስከመጨረሻ
እስከ ዝንተ ዓለሜ
እስከ ሕይወት ፍፃሜ።”
“ምኒቱ ፍጡር ነሽ!”
መኖር ወይ መሞቱን በምን ታውቂዋለሽ?”
“ቃሉን አክባሪ ነው ውዴ አያውቅም ዋሽቶ
ድንገት በአጋጣሚ
ነፍሱ ከሥጋው ጋር ቢቀር ተለያይቶ
ለእኔ አይደብቀኝም ይነግረኛል መጥቶ፡፡
ፈንቅሎ መቃብር
ይነሳል በክብር
እጠብቀዋለሁ ውዴ አይቀርም ሞቶ
ሞትን አሽንፎ ይመጣል ድል ነስቶ፡፡”
ፋሲል ተካልኝ
አዘጋጅ፦ አትሮኖስ..m
“ጭራሽ ሰው አታዪም?
ለበርካታ ጊዜያት ቆሜ አይቼሻለሁ
መንገድ ላይ ብቻሽን ምን እያረግሽ ነው? ”
“ሰው እጠብቃለሁ።”
“እንዴት ዓይነቱን ሰው!?!”
“በፍቅሩ በሳቁ ልብን የሚያፈርሰው።”
“ምን ያደርግልሻል?..
ስለምን ያሻሻል?.."
“ልቡ ይፈልግኛል
ልቤም እሱን ይሻል፡፡”
“በርግጥ ይወድሻል?”
ካንጀቱ ያፈቅረኛል፡፡”
“ታዲያ
አውላላ ሜዳ ላይ እንዴት ይተውሻል?
ለምን ይዋሽሻል? ”
ካልመጣ ይነግረኛል
ለምን ይዋሸኛል!?!”
“እቀራለሁ ብሎ እንዴት ይነግርሻል?
አንቺን ላለማጣት ቢያውቀውም ይዋሻል፡፡”
“ጠንቅቄ ሐሳቡን
አውቀዋለሁ ልቡን ፧
ከልቤ አምነዋለሁ
እናፍቀዋለሁ
እጠብቀዋለሁ፡፡”
“በ ጣ ም ትገርሚያለሽ!
እስከመቼ ድረስ ትጠብቂዋለሽ?”
“እስከመጨረሻ
እስከ ዝንተ ዓለሜ
እስከ ሕይወት ፍፃሜ።”
“ምኒቱ ፍጡር ነሽ!”
መኖር ወይ መሞቱን በምን ታውቂዋለሽ?”
“ቃሉን አክባሪ ነው ውዴ አያውቅም ዋሽቶ
ድንገት በአጋጣሚ
ነፍሱ ከሥጋው ጋር ቢቀር ተለያይቶ
ለእኔ አይደብቀኝም ይነግረኛል መጥቶ፡፡
ፈንቅሎ መቃብር
ይነሳል በክብር
እጠብቀዋለሁ ውዴ አይቀርም ሞቶ
ሞትን አሽንፎ ይመጣል ድል ነስቶ፡፡”
ፋሲል ተካልኝ
አዘጋጅ፦ አትሮኖስ..m
👍1
#ልቅሶ
ከሐይቁ ዳርቻ
ካለው ድንጋይ ተመቻችተሽ ተቀምጠሽ
ደረትሽ ላይ እጆችሽን አስቀምጠሽ
ስትነፍሺ ስትተነፍሺ በሐዘን ድባብ ተውጠሽ
ደሞ ፈጠን ብለሽ ስትተነፈሺ ድምፅ ስታወጪ
ለአፍታ ስታደምጪ ትንፋሽ ስታምጪ
እንደብላቴና ስትንሰቀሰቂ
ፋታ ሳትሰጪ ስትነፋረቂ
እንደጠይብ ሆኜ ቀርቤ እንደአዋቂ
ብዬሽ ነበር ኮ “ባክሽ አታልቅሺ
ስሜትሽን አምቂ ዕንባሽን አብሺ
ልቅሶሽን አፍኚ ሐዘንሽን እርሺ፡፡”
ምክሬ የማይረባኝ
መሆኑ መች ገባኝ?!?
ጭንቀት ጉዳትን ማርገቢያ
የድረሱልኝ ጥሪ ማቅረቢያ
የተፈጥሮ ቋንቋ መግባቢያ
ሐሳብ ለሐሳብ መገናኛ
የተሰበረ ልብ መጠገኛ
የአዕምሮ እርካታ ማግኛ
የውስጥ ሥቃይን ማስረሻ
መርዛማ ሕመምን ማርከሻ
ከጥልቅ አዘቅት መውጫ
አቋራጭ መንገድ ማምለጫ
እምቅ ስሜትን መግለጫ
ልቅሶ ፧ ልቅሶ፣ ልቅሶ፡፡
ልቅሶ እንደሆነ እኔ መች አውቄ ?!
ተለያይተን ቀርተን ካንቺ ዘንድ እርቄ
በትዝታሽ ውስጥ ተዘፍቄ
ዓይንሽን ማየት ናፍቄ
በሐሳብ ተብሰልስዬ በሐዘን ተጨንቂ
ጤናዬን አጥቼ ከስቼ ደቅቄ
እንዳልጠፋ ከዓለም እንዳልሞት ጨርሶ
በድንገት መንጭቶ እንደጠበል ፈሶ
ሞቃቱ ዕንባዬ አልፎ ገደብ ጥሶ
ዓይኔንም ቆጥቁጦ
ስሜቴን ለውጦ መንፈሴን አድሶ
“ብቁ ሰው” አርጉኛል ሕመሜን ፈውሶ
ልቅሶ ፤ልቅሶ ፤ ልቅሶ ፧ ልቅሶ፡፡
የጉዳትሽን መጠን
የጭንቀትሽን ልክ ሳየው በኔ ደርሶ
የዛን ጊዜ ገባኝ ትርጉሙ የልቅሶ::
ፍቱን መድኃኒቱን አግኝቼ ፈልጌ
መልሼ ቀብሬ ከእይታሽ ሸሽጌ
አንቺን አላስቀርም ሕመምተኛ አርጌ፡፡
ይኸውልሽ
ይኸውልሽ
መንፈስሽ ይታደስ ሕመምሽ ይወገድ
ማልቀስ ነው መፍትሔው እውነተኛው መንገድ፡፡
ከውስጥ መንጭቶ ነፅቶ የሚያጠራ
ከአዘቅት የሚያወጣ ከጭንቅ ከመከራ
ተፈጥሯዊ ቅመም በዕንባ የተሠራ
ማልቀስ ማትረፍ እንጂ አይደለም ኪሣራ፡፡
ስለዚህ ባክሽን
ውስጣዊ ስሜትሽን ጭንቀትን እርሺ
ጤነኛ ለመሆን አምርረሽ አልቅሺ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
ከሐይቁ ዳርቻ
ካለው ድንጋይ ተመቻችተሽ ተቀምጠሽ
ደረትሽ ላይ እጆችሽን አስቀምጠሽ
ስትነፍሺ ስትተነፍሺ በሐዘን ድባብ ተውጠሽ
ደሞ ፈጠን ብለሽ ስትተነፈሺ ድምፅ ስታወጪ
ለአፍታ ስታደምጪ ትንፋሽ ስታምጪ
እንደብላቴና ስትንሰቀሰቂ
ፋታ ሳትሰጪ ስትነፋረቂ
እንደጠይብ ሆኜ ቀርቤ እንደአዋቂ
ብዬሽ ነበር ኮ “ባክሽ አታልቅሺ
ስሜትሽን አምቂ ዕንባሽን አብሺ
ልቅሶሽን አፍኚ ሐዘንሽን እርሺ፡፡”
ምክሬ የማይረባኝ
መሆኑ መች ገባኝ?!?
ጭንቀት ጉዳትን ማርገቢያ
የድረሱልኝ ጥሪ ማቅረቢያ
የተፈጥሮ ቋንቋ መግባቢያ
ሐሳብ ለሐሳብ መገናኛ
የተሰበረ ልብ መጠገኛ
የአዕምሮ እርካታ ማግኛ
የውስጥ ሥቃይን ማስረሻ
መርዛማ ሕመምን ማርከሻ
ከጥልቅ አዘቅት መውጫ
አቋራጭ መንገድ ማምለጫ
እምቅ ስሜትን መግለጫ
ልቅሶ ፧ ልቅሶ፣ ልቅሶ፡፡
ልቅሶ እንደሆነ እኔ መች አውቄ ?!
ተለያይተን ቀርተን ካንቺ ዘንድ እርቄ
በትዝታሽ ውስጥ ተዘፍቄ
ዓይንሽን ማየት ናፍቄ
በሐሳብ ተብሰልስዬ በሐዘን ተጨንቂ
ጤናዬን አጥቼ ከስቼ ደቅቄ
እንዳልጠፋ ከዓለም እንዳልሞት ጨርሶ
በድንገት መንጭቶ እንደጠበል ፈሶ
ሞቃቱ ዕንባዬ አልፎ ገደብ ጥሶ
ዓይኔንም ቆጥቁጦ
ስሜቴን ለውጦ መንፈሴን አድሶ
“ብቁ ሰው” አርጉኛል ሕመሜን ፈውሶ
ልቅሶ ፤ልቅሶ ፤ ልቅሶ ፧ ልቅሶ፡፡
የጉዳትሽን መጠን
የጭንቀትሽን ልክ ሳየው በኔ ደርሶ
የዛን ጊዜ ገባኝ ትርጉሙ የልቅሶ::
ፍቱን መድኃኒቱን አግኝቼ ፈልጌ
መልሼ ቀብሬ ከእይታሽ ሸሽጌ
አንቺን አላስቀርም ሕመምተኛ አርጌ፡፡
ይኸውልሽ
ይኸውልሽ
መንፈስሽ ይታደስ ሕመምሽ ይወገድ
ማልቀስ ነው መፍትሔው እውነተኛው መንገድ፡፡
ከውስጥ መንጭቶ ነፅቶ የሚያጠራ
ከአዘቅት የሚያወጣ ከጭንቅ ከመከራ
ተፈጥሯዊ ቅመም በዕንባ የተሠራ
ማልቀስ ማትረፍ እንጂ አይደለም ኪሣራ፡፡
ስለዚህ ባክሽን
ውስጣዊ ስሜትሽን ጭንቀትን እርሺ
ጤነኛ ለመሆን አምርረሽ አልቅሺ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ዕለተ_ቅዳሜ_ፒያሳና_ቦሌ
ቀጭን ወገቧ ላይ
ከእንብርቷ በላይ ልብሷ ተንጠልጥሏል
የወርቅ መስቀሏ
ጡቶቿ መካከል ዘንበል ብሎ ወድቋል
መንገድ ላይ ያየኋት
የማላውቃት ሴት ናት።
ወዴት እንደምትሄድ ባሳቤ ገመትኩኝ
አንድ የቀጠራትን ወንደላጤ አሰብኩኝ
ሠባት እንቁላሎች
ግማሽ ኪሎ ሥጋ ... (ገዝቶ)
ከርሷ ጋር ካልሆነ
ቡና አልጠጣም ብሎ አሥሬ እያዛጋ
መጽሐፉን ከፍቶ
በሩን ክፍት ትቶ
መልሶ መላልሶ ሠዓቱን እያየ
የሚጠብቃት ሠው
ሐሳቤ ውል አለው
ምክንያቱም ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
-
እርሷ አለፍ እንዳለች
መሐሙድ ፊት ለፊት
አራዳ ሬሰቶራንት
አራት ጎረምሶች ሰባት ምግብ አዘው
ለመመገብ ሳይሆን
ምግቡን ለመጨረስ እጅጉን ተጣድፈው
በቆየ ጋዜጣ
የተጠቀለለ ምናምን አስቀምጠው
ፊት ለፊቴ አሉ
ምግቡን ሳያኝኩት ቶሎ መጉረሳቸው
አራት ሆነው ሳሉ ዝም ማለታቸው
ገባኝ ሁኔታቸው
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
እግሬን ለማፍታታት እየተራመድኩኝ
ወደ ሆነ መንደር በድንገት ገባሁኝ
የሆነ በራፍ ላይ
ውስጥ ልብስ ያረገች
ልብስ አጠባ ውላ ትንሽ የደከመች
ፀጉሯን ልትሰራ
ጓደኛዋ ጭን ስር ሽጉጥ ልጥፍ ያለች
እግሯ ከፈት ያለ
ጡቷ ወፈር ዯያለ
የአንድ እጇን መዳፍ
በስተግራ በኩል የፀጉሯ ክፋል ላይ
የአንድ እጇን መዳፍ
ክፍት እግሮቿ መሃል
አንገቷ ወደላይ
ረፍት የሚመስል ሰማዩ ላይ ወድቋል
አይኗ ከሩቅ አልፏል
እፎይ . . . የሚል ፊደል ገላዋን በሞላ
እንደ ልጅ አቅፎታል
የዚህ ሁሉ ነገር
የዚህ ሁሉ ዉበት ምክንያቱ ምንድን ነው
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
-
እዚህ መንደር ጫፍ ላይ
አንድ ያቧራ ሜዳ ከሩቅ ይታየኛል
እንደ መዝሙር ሆኖ
የሕፃናት ጩኸት ወደኔ ይመጣል
ከሜዳው መሃል ላይ አቧራው ይበናል
ሕፃናት ነበሩ አበቦች ነበሩ
ምሳቸውን ትተው
በጨዋታ ምሳ ጠግበው የሰከሩ
ምክንያቱ ምንድን ነው
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
-
Oslo በረንዳው ላይ
አንድ ጥቁር ቡና ከተቆራጭ ጋራ
በቀኙ ጋዜጣ
ግራ እጁ ጣት መሃል ሮዝማን ሲጋራ
ቀልቡን ጋዜጣው ላይ
የሲጋራውን ጢስ ከጋዜጣው በላይ
ቡናውን ሲጎነጭ ንባቡን ሲያቆም ዐይኖቹ ውብ ሴት ላይ
እያቀያየረ
በልቡ ባሳቡ እያመነዘረ
Oslo በረንዳው ላይ ተቀምጦ ያለ
አንድ ጎልማሳ አለ።
ምሑር የሚመስል እንደዚህ ያለ ጎበዝ
ከኬክ ቤት በራፍ ላይ ሊቀመጥ የቻለው
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
-
የሆነች ሕፃን ልጅ
የቅዳሜ ጠዋት ፀሐይ የሚመስል
ጉንጯ ላይ ፈገግታ በደማቁ ፅፋ ባጠገቤ አለፈች
ሠላሣ ማለቂያ
አርባ መጀመሪያ . . . አካባቢ ያለች
የተጠቀለለ የታሸገ ነገር በጇ ላይ የያዘች
የሕፃኗን መንገድ እየተከተለች
ጠይም ሴት አለፈች።
ለቅድሟ ሕፃን እናቷ ነች መሰል
(ይመስለኛል መሰል)
የሴቷ ባለቤት
የልጅቷ አባት
ትንሽ አመም አርጎት ሆሰፒታል ተኝቷል
ወይም . . .
የተጠቀለለው የታሸገው ነገር
የወይን የውስኪ ጠርሙስ ግን ከሆነ
ጠይም ቆንጆዋ ሴት
አንድ የተፋታችው አንድ የምትፈልገው
የሆነ ሰው አለ . . .
ትንሿን ሕፃን ልጅ የምታስተዋውቀው
እና . . .
የ’ርጅና ፍርሃቷን አብራ ምትጋራው።
አያገባኝ ነገር
ያገባኛል ብዬ ይህን ያሰብኩበት ምክንያቴ ምንድ ነው?
ያ ቀን #ቅዳሜ ነው።
-
ይህንና ያንን
የግራ የቀኙን
ከፒያሳ መሐል እስከ ጣልያን ሠፈር . . .
አንዱን እያነሳሁ
አንዱን እየጣልኩኝ
በሐሳብ ሕንፃ ላይ አንዱ እየተሰራ አንዱ እየፈረሰ
ከልጅቷ ጋራ
የተቃጠርኩበት ሠዓቱ ደረሰ
መጣች ተገናኘን
ዮኧምያ ምሳ ቶምካ ቡናችን
የደንቡን አደረስን።
ልብሷን ሳታወልቀው ራቁቷን ሳልኳት
ዘወትር አንድ ቤት
ደንብ አይደለም ብዬ ቦሌ እንሂድ አልኳት
የተስተካከለ
ጥሩ አልጋ ያለው የማውቀው ቤት አለ።
ፒያሳን ለቀቅን . . .
ቦሌ ላይ ደረስን . . .
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመስልም
የቦሌ ቆንጆ ሕልም ከፒያሳ ቅዥት አይስተካከልም
የቦሌ ኮረዶች
በቀለማት ብዛት ውበታም ቢመስሉም
ጣልያን ሠፈር መሐል
ፀጉር እየተሰራች ያስተዋልኳት ሴት ላይ
ጥፍሯ ላይ አይደርሱም
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመስልም።
ቦሌን ታዘብኳትኝ
ቦሌን እርም አልኳትኝ
ቆንጆ አልጋ አለበት
ካልኩት መንገድ መሐል
አንድ የለቅሶ ድንኳን
ጎዳናውን ከድኗል።
ድንኳን ያ’ዘን ድንኳን
በ’ለተ ቅዳሜ በውበት በሕይወት ቀን
አብራኝ ያለችው ሴት
ተከተለኝ ብላ ወደ ኋላ ዞረች
እጆቿን ዘርግታ
አንድ ትንሽ ታክሲን ፒያሳ አዘዘች
ፒያሳ ደረስን
የቦሌውን ድንኳን እንዲያስረሳን ብለን
Sunshine ጎራ አልን . . .
ሙዚቃ
ሙዚቃ
ቢራ
ውስኪ
ቢራ . . .
ጫጫታ
ዳንኪራ
ዳንኪራ
ጫጫታ
ድንኳኑን ረሳን
ውበት ባህር ገባን
የዚህ ሁሉ ደስታ የዚህ ሁሉ ሐሴት . . .
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
ያውም የፒያሳ
እውነት ለመናገር . . .
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመሥልም
የቦሌም ቆንጆ ሕልም ከፒያሳ ቅዠት አይስተካከልም።
ያም ሆነ ይህ ግና
የዚህ ሁል ዉበት ምክንያቱ ምንድን ነው?
🔘ኤፈፍሬም ስዩም🔘
ቀጭን ወገቧ ላይ
ከእንብርቷ በላይ ልብሷ ተንጠልጥሏል
የወርቅ መስቀሏ
ጡቶቿ መካከል ዘንበል ብሎ ወድቋል
መንገድ ላይ ያየኋት
የማላውቃት ሴት ናት።
ወዴት እንደምትሄድ ባሳቤ ገመትኩኝ
አንድ የቀጠራትን ወንደላጤ አሰብኩኝ
ሠባት እንቁላሎች
ግማሽ ኪሎ ሥጋ ... (ገዝቶ)
ከርሷ ጋር ካልሆነ
ቡና አልጠጣም ብሎ አሥሬ እያዛጋ
መጽሐፉን ከፍቶ
በሩን ክፍት ትቶ
መልሶ መላልሶ ሠዓቱን እያየ
የሚጠብቃት ሠው
ሐሳቤ ውል አለው
ምክንያቱም ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
-
እርሷ አለፍ እንዳለች
መሐሙድ ፊት ለፊት
አራዳ ሬሰቶራንት
አራት ጎረምሶች ሰባት ምግብ አዘው
ለመመገብ ሳይሆን
ምግቡን ለመጨረስ እጅጉን ተጣድፈው
በቆየ ጋዜጣ
የተጠቀለለ ምናምን አስቀምጠው
ፊት ለፊቴ አሉ
ምግቡን ሳያኝኩት ቶሎ መጉረሳቸው
አራት ሆነው ሳሉ ዝም ማለታቸው
ገባኝ ሁኔታቸው
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
እግሬን ለማፍታታት እየተራመድኩኝ
ወደ ሆነ መንደር በድንገት ገባሁኝ
የሆነ በራፍ ላይ
ውስጥ ልብስ ያረገች
ልብስ አጠባ ውላ ትንሽ የደከመች
ፀጉሯን ልትሰራ
ጓደኛዋ ጭን ስር ሽጉጥ ልጥፍ ያለች
እግሯ ከፈት ያለ
ጡቷ ወፈር ዯያለ
የአንድ እጇን መዳፍ
በስተግራ በኩል የፀጉሯ ክፋል ላይ
የአንድ እጇን መዳፍ
ክፍት እግሮቿ መሃል
አንገቷ ወደላይ
ረፍት የሚመስል ሰማዩ ላይ ወድቋል
አይኗ ከሩቅ አልፏል
እፎይ . . . የሚል ፊደል ገላዋን በሞላ
እንደ ልጅ አቅፎታል
የዚህ ሁሉ ነገር
የዚህ ሁሉ ዉበት ምክንያቱ ምንድን ነው
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
-
እዚህ መንደር ጫፍ ላይ
አንድ ያቧራ ሜዳ ከሩቅ ይታየኛል
እንደ መዝሙር ሆኖ
የሕፃናት ጩኸት ወደኔ ይመጣል
ከሜዳው መሃል ላይ አቧራው ይበናል
ሕፃናት ነበሩ አበቦች ነበሩ
ምሳቸውን ትተው
በጨዋታ ምሳ ጠግበው የሰከሩ
ምክንያቱ ምንድን ነው
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
-
Oslo በረንዳው ላይ
አንድ ጥቁር ቡና ከተቆራጭ ጋራ
በቀኙ ጋዜጣ
ግራ እጁ ጣት መሃል ሮዝማን ሲጋራ
ቀልቡን ጋዜጣው ላይ
የሲጋራውን ጢስ ከጋዜጣው በላይ
ቡናውን ሲጎነጭ ንባቡን ሲያቆም ዐይኖቹ ውብ ሴት ላይ
እያቀያየረ
በልቡ ባሳቡ እያመነዘረ
Oslo በረንዳው ላይ ተቀምጦ ያለ
አንድ ጎልማሳ አለ።
ምሑር የሚመስል እንደዚህ ያለ ጎበዝ
ከኬክ ቤት በራፍ ላይ ሊቀመጥ የቻለው
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
-
የሆነች ሕፃን ልጅ
የቅዳሜ ጠዋት ፀሐይ የሚመስል
ጉንጯ ላይ ፈገግታ በደማቁ ፅፋ ባጠገቤ አለፈች
ሠላሣ ማለቂያ
አርባ መጀመሪያ . . . አካባቢ ያለች
የተጠቀለለ የታሸገ ነገር በጇ ላይ የያዘች
የሕፃኗን መንገድ እየተከተለች
ጠይም ሴት አለፈች።
ለቅድሟ ሕፃን እናቷ ነች መሰል
(ይመስለኛል መሰል)
የሴቷ ባለቤት
የልጅቷ አባት
ትንሽ አመም አርጎት ሆሰፒታል ተኝቷል
ወይም . . .
የተጠቀለለው የታሸገው ነገር
የወይን የውስኪ ጠርሙስ ግን ከሆነ
ጠይም ቆንጆዋ ሴት
አንድ የተፋታችው አንድ የምትፈልገው
የሆነ ሰው አለ . . .
ትንሿን ሕፃን ልጅ የምታስተዋውቀው
እና . . .
የ’ርጅና ፍርሃቷን አብራ ምትጋራው።
አያገባኝ ነገር
ያገባኛል ብዬ ይህን ያሰብኩበት ምክንያቴ ምንድ ነው?
ያ ቀን #ቅዳሜ ነው።
-
ይህንና ያንን
የግራ የቀኙን
ከፒያሳ መሐል እስከ ጣልያን ሠፈር . . .
አንዱን እያነሳሁ
አንዱን እየጣልኩኝ
በሐሳብ ሕንፃ ላይ አንዱ እየተሰራ አንዱ እየፈረሰ
ከልጅቷ ጋራ
የተቃጠርኩበት ሠዓቱ ደረሰ
መጣች ተገናኘን
ዮኧምያ ምሳ ቶምካ ቡናችን
የደንቡን አደረስን።
ልብሷን ሳታወልቀው ራቁቷን ሳልኳት
ዘወትር አንድ ቤት
ደንብ አይደለም ብዬ ቦሌ እንሂድ አልኳት
የተስተካከለ
ጥሩ አልጋ ያለው የማውቀው ቤት አለ።
ፒያሳን ለቀቅን . . .
ቦሌ ላይ ደረስን . . .
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመስልም
የቦሌ ቆንጆ ሕልም ከፒያሳ ቅዥት አይስተካከልም
የቦሌ ኮረዶች
በቀለማት ብዛት ውበታም ቢመስሉም
ጣልያን ሠፈር መሐል
ፀጉር እየተሰራች ያስተዋልኳት ሴት ላይ
ጥፍሯ ላይ አይደርሱም
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመስልም።
ቦሌን ታዘብኳትኝ
ቦሌን እርም አልኳትኝ
ቆንጆ አልጋ አለበት
ካልኩት መንገድ መሐል
አንድ የለቅሶ ድንኳን
ጎዳናውን ከድኗል።
ድንኳን ያ’ዘን ድንኳን
በ’ለተ ቅዳሜ በውበት በሕይወት ቀን
አብራኝ ያለችው ሴት
ተከተለኝ ብላ ወደ ኋላ ዞረች
እጆቿን ዘርግታ
አንድ ትንሽ ታክሲን ፒያሳ አዘዘች
ፒያሳ ደረስን
የቦሌውን ድንኳን እንዲያስረሳን ብለን
Sunshine ጎራ አልን . . .
ሙዚቃ
ሙዚቃ
ቢራ
ውስኪ
ቢራ . . .
ጫጫታ
ዳንኪራ
ዳንኪራ
ጫጫታ
ድንኳኑን ረሳን
ውበት ባህር ገባን
የዚህ ሁሉ ደስታ የዚህ ሁሉ ሐሴት . . .
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ #ቅዳሜ ነው።
ያውም የፒያሳ
እውነት ለመናገር . . .
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመሥልም
የቦሌም ቆንጆ ሕልም ከፒያሳ ቅዠት አይስተካከልም።
ያም ሆነ ይህ ግና
የዚህ ሁል ዉበት ምክንያቱ ምንድን ነው?
🔘ኤፈፍሬም ስዩም🔘
👍1
#ጥላቻ_እና_ፍቅር
ከጥላቻሽ ብዛት
አቃጥለሽ ብትገዪኝ አርከፍክፈሽ “ቤንዚን”
ይስ ይልሽ ነበረ ፤
ኖሮሽ መርዘሽኝ ብትገዪኝ በ"ራይዚን”
ደስ ይልሽ ነበረ፤
እሳተ ጐመራ በድንገት ፈንድቶ
ወዲያው ቢጠፋልሽ እኔን ብቻ አጥፍቶ
ደስ ይልሽ ነበረ፤
ሰማይ ቢያዝንብልሽ ቀላቅሉ በረዶ
ጐጆዬ እንዲገለኝ ላዬ ላይ ተንዶ
ምኞትሽ ነበረ
ደስታሽም ነበረ
በ “ነበረ” ቀረ፡፡
ወይ ነዶ!... ወይ ነዶ!... ይኸው እኖራለሁ
ወይ ወዶ!... ወይ ወዶ!... ውዴ አፈቅርሻለሁ::
ጥላቻሽን ፋቂው
እውነቱን እወቂው፡፡
ከፍቅሬ የተነሳ
ይጨንቃል ማሰቡ ኑሮዬን ያላንቺ
ከዚህ ዓለም ብጠፋ የኔ ውድ ብትሞቺ
ከፍቅሬ የተነሳ
አዕምሮዬ አምኖ እንዴት ይቀበላል?!?
እንዴት እሆናለሁ?!? ሞትሽ ከፍቶ ያይላል፡፡
ጨርቄን ያስጥለኛል እርቃን ያስቀረኛል
የኔ ውድ ብትሞቺ የማብድ ይመስለኛል፡፡
ሞትሽ ይቅርና
ካይዬ ሦር ሰሸትርቂ ላንዲት ቅፅበት እንኳን
ሐዘኔ ይከፋና
በፍጥነት ልቤ ውስጥ ይተከላል ድንኳን
ከፍቅሬ የተነሣ
ያለአንቺ አልኖርም ሕይወቴ ጣዕም ያጣል
ይኼውልሽ እንዲ ነው
ፍቅር ከጥላቻ ሺ ጊዜ ይበልጣል።
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
ከጥላቻሽ ብዛት
አቃጥለሽ ብትገዪኝ አርከፍክፈሽ “ቤንዚን”
ይስ ይልሽ ነበረ ፤
ኖሮሽ መርዘሽኝ ብትገዪኝ በ"ራይዚን”
ደስ ይልሽ ነበረ፤
እሳተ ጐመራ በድንገት ፈንድቶ
ወዲያው ቢጠፋልሽ እኔን ብቻ አጥፍቶ
ደስ ይልሽ ነበረ፤
ሰማይ ቢያዝንብልሽ ቀላቅሉ በረዶ
ጐጆዬ እንዲገለኝ ላዬ ላይ ተንዶ
ምኞትሽ ነበረ
ደስታሽም ነበረ
በ “ነበረ” ቀረ፡፡
ወይ ነዶ!... ወይ ነዶ!... ይኸው እኖራለሁ
ወይ ወዶ!... ወይ ወዶ!... ውዴ አፈቅርሻለሁ::
ጥላቻሽን ፋቂው
እውነቱን እወቂው፡፡
ከፍቅሬ የተነሳ
ይጨንቃል ማሰቡ ኑሮዬን ያላንቺ
ከዚህ ዓለም ብጠፋ የኔ ውድ ብትሞቺ
ከፍቅሬ የተነሳ
አዕምሮዬ አምኖ እንዴት ይቀበላል?!?
እንዴት እሆናለሁ?!? ሞትሽ ከፍቶ ያይላል፡፡
ጨርቄን ያስጥለኛል እርቃን ያስቀረኛል
የኔ ውድ ብትሞቺ የማብድ ይመስለኛል፡፡
ሞትሽ ይቅርና
ካይዬ ሦር ሰሸትርቂ ላንዲት ቅፅበት እንኳን
ሐዘኔ ይከፋና
በፍጥነት ልቤ ውስጥ ይተከላል ድንኳን
ከፍቅሬ የተነሣ
ያለአንቺ አልኖርም ሕይወቴ ጣዕም ያጣል
ይኼውልሽ እንዲ ነው
ፍቅር ከጥላቻ ሺ ጊዜ ይበልጣል።
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ማምሻ
፡
፡
#ክፍል_ሦስት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ጀብድ ሠርቶ እንዳመለጠ የግፍ እስረኛ፣ በአድናቆትና እንኳን ተሳካላቸው ሰሚል ስሜት
የተሞላ ነበር፡፡
እማማ ዓምድነሽ፣ ልጃቸውን ማምሻን አይገቡ ገብተው አሳደጓት: ሰው ቤት ልብስ እያጠቡ፣ ጉሊት እየቸረቸሩ ትምህርቷን ሊያስተምሯት ጣሩ፡፡ ማምሻ ግን ትምህርቱም ብዙ አልሆነላትም፡፡ የሰፈሩ ማንጓጠጥ ትምህርት ቤትም ተከትሏት ነበር፡፡ እየወደቀች እየተነሳች እንደምንም ዘጠነኛ ክፍል ደርሳ አቆመች:: የሻይ ቤት አስተናጋጅነት ሥራ እንዲያፈላልግላት ደላላውን በሽርን ብትጠይቀው፣ ያንን ጫት የተለሰነበት ጥርሱን
እየገለፈጠ “ማምሻ! በዚህ ፊት አስተናጋጅነት!?…”አላት አሉ፡፡ ይህም አንድ ሰሞን
ተሳቀበት…በኋላ በወር ሰማንያ ብር እየተካፈላት የሰፈራችን ቦኖ ውሀ አስቀጅ ሆነች::
ውሀ አታፍስሱ ያለቻቸው የመንደሩ ሴቶች ያንኑ ቁሰሏን በሽሙጥ ስንጥር እየነካኩ፣
በመልከጥፉነቷ እያሸሞሩ ቁጡ አደረጓት፡፡
“ቆጥባ መልከ ጥፉነቷን ልታጥብብት ነው?
እያሉ:: በነጋ በጠባ ጸብ ሆነ፡፡
አንድ ቀን ማምሻ አንዷን አሽሙረኛ እንደ ነብር ዘልላ ተከመረችባት፡፡ ማን ያላቅቃት?
የዘመናት ብሶቷን እዚያች ዕጣው እወደቀባት ሴት ላይ አራገፈችው፡፡ በትርምሱ የውሀ
መቅጃ እንስራም አልተረፈ፣ ተከለከከለ፡፡ ከዚያቹም ሥራ ተባረረች፡፡ ደግሞ የማባረሪያ
ምክንያቱ ግነት! “ሕዝብ እንድታገልገል በተቀመጠችበት ቦታ፣ ሥልጣኗን ተገን
በማድረግ፣ ተጠቃሚውን ኅብረተሰብ በመደብደብና ንብረት በማውደም ቦንብ ጣይ
አውሮፕላን እያበረረች አንድ ከተማ ሕዝብ የደበደበች ዓይነት! ኅብረተሰቡን
በመደብደብ እና ንብረት በማውደም!”
ተራ ፌዝና ስላቃችን አንገት ያስደፋት ማምሻ፣ ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ትታ፣ ባልቴት
እናቷ በየሰው ቤት ሠርተው በሚያመጧት ሳንቲም ኑሮዋን እየገፋች የወጣት ጡረተኛ ሆና እቤት ተቀመጠች፡፡ ይኼ መገፋት አጉብጧት እንዳቀረቀረች፤ እንጀራዋን እዚያው ባቀረቀረችበት አገኘችው፡፡ ልክ እንዲሰምጥ ወደ ባሕር የገፈተሩት ሰው የሚያስጎመዥ ዓሣ ይዞ የመውጣት ዓይነት ነበር ነገሩ፡፡ ማምሻ እንዳቀረቀረች ኪሮሽና ክር አነሳች፡፡እንዳቀረቀረች መርፌና ክር ታጥቃ በመራሩ ድህነት ላይ ዘመተች፡፡ በሰፊው የድህንትጥቁር ሸማ ላይ ውበትን ዘራችለት፡፡ ከዚያ የተገፋ ልብ፣ ያ ውበት እንዴት ወጣ?እላለሁ አንዳንዴ፡፡
ውበታቸው የመንደሩን ብቻ ሳይሆን፣ ከየትና የት ድረስ የሚመጡ የከተማውን ሴቶችን የሚያሻማ፣ ከምሶብ ዳንቴል እስከ ኤልጋ ልብስ፣ ከኩርሲ እስከሶፋ ልብስ፣ ከመጋረጃ እስከ ሐበሻ ቀሚስ ድረስ የጥልፍ ማጎተሟን አሳረፈች፡፡ ሰፈራችን በሙሉ በማምሻ የእጅ ሥራዎቿ ተጥለቀለቀ፡፡ የማምሻ ጥልፍ ያረፈባቸው መጋረጃወች በየመስኮቱ ተሰቅለው ሲታዩ፣ ማምሻ ገፊዎቿን በእጁ ጥበብ ድል ነስታ፣ ባንዲራዋን በድል
እድራጊነት በየቤቱ የሰቀለች ይመስል ነበር፡፡
በመቋጨት ይሁን በመጥለፍ፣ የማምሻ እጅ ያረፈበትን የባህል ቀሚስ ይሁን ነጠላ ለብሳ
ያልተውረገረገች፣ አንድ የመንደሩ ሴት ብትኖር፣ ማምሻ ራሷ ብቻ ነበረች። እንዲህ እያገባኝ ገብቼ የማምሻን የእጅ ሥራዎች ስመለከት፣ ከሌሎች ጥልፎች የተለዩ ይሆኑብኝ ነበር። ፍዝዝ ያለ ቀለም ባላቸው ክሮች፣ ደማቅ መደብ ላይ የምትጠልፋቸው አበቦች የራሷን ምስል የምትስል ሠዓሊ እስክትመስለኝ፣ አንዳች የሚያሳዝን ስሜት ውስጥ የሚያስገቡ ነበሩ:: በዚህም ሥራዋ እራሷን ባልቴት እናቷን በክር ጎትታ፣አንገታቸው
ከድህነት አዘቅት ብቅ እንዲል አደረገች፡፡ እናቷ በየሰው ቤት መንከራተት አቁመው እቤታቸው አረፉ፡፡ መንደርተኛውም ከማምሻ መልክ ይልቅ የእጅ ሥራዎቿ ዓይኖቹን ጋርደውት ከመዝለፍ ይልቅ ወደማድነቅ እና ማክበር የተሸጋገረ መሰለ፡፡ በእርግጥም ማምሻ መልከጥፉ ፊቷን በብርቱ እጆቿ ሽፍናው ነበር፡፡
ስም ውስጥ ሟርት አለ፡፡ ማምሻ እንደስሟ ማምሻ ሆነች: ሁሉም ነገር የተቀያየረው ድንገት ነበር፡፡ የእጅ ሥራዎቿን ሙሉ ለሙሉ ከገበያ ውጭ የሚያደርግ አጋጣሚ። ፈጣን እና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የጥልፍ መኪኖች በከተማው ውስጥ እንደ አሸን ፈሉ።
በአንድ ጀምበር ድፍን መንደር የሚያለብሱ፣ በደማቅ ከሮች ፎቶ የመሳሰሉ አበቦችን
የሚጠልፉ የ “ሲንጀር መኪኖች፡፡ የማምሻ ተስፋ ሟሸሽ! ጥበቧም ከምንም እስከ ሲንጀር መኪና ባለው ክፍተት መሀል ማምሻ መሸጋገሪያ ሆነ። በኑሮ አድማሷ ላይ ድንገት ብቅ ያለች ጀምበሯ፣ ሙቀትና ብርሃኗን በቅጡ ሳታጣጥማት ድርግም ብላ ጠፍታ፣ ዳግም የድህነትና የማንጓጠጥ ዝናብ ያዘለ ደመና በላይዋ ላይ ያንዣብብ
ጀመረ፡፡ ዳግም ወደ ማቀርቀር፣ ዳግም አንገት ወደ መድፋት ተመለሰች፡፡ ግና ምንም ያልተነኩ ቱባ ክሮችን ሰብስሳ ወስዳ ለባለሱቁ ከድሩ በርካሽ ሸጠችለት ተባለ፡፡ ያም የማምሻ የጥልፍ ሥራ ማብቂያ ሆኖ በጎረቤቱ ዘንድ ተወራ፡፡ በዚህም ተቀለደ፡፡ “ማምሻ ኪሮሽ ሰቀለችተባለ፡፡ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መጫወት ሲያቆሙ
ጫማ ስቀሉ” እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡ቀስ በቀስ እናቷ ወደ ሰው ቤት ሥራ ተመለሱ፣ ማምሻም እናቷን ለማገዝ እንጀራ መጋርና መሸጥ ጀመረች፡፡ ታዲያ በዚህ መሃል ትንሽ በጎነት ያሳየቻት ሴት ብትኖር፣ ሎዛ ነበረች፡፡ ከአባቷ ጣውላ ቤት የእንጀራ መጋገሪያ ሳጋቱራ በነፃ እንድትወስድ አስፈቅዳላት ነበር፡፡
ባልገባኝ ምክንያት የሎዛ ዓይኖች ሁልጊዜ ማምሻ ላይ ነበሩ፡፡ የሰፈሩ ሰው ርግፍ አድርጎ
በተዋቸው ሰዓት እንኳን የማምሻ እጅ ስራ የተጠለፈባቸው ልብሶችን ትለብስ የነበረች
ሴት ሎዛ ብቻ ነበረች፡፡ እንደውም ለእኔም ከማምሻ የገዛችውን አንድ የባህል ልብስ
ስጦታ ሰጥታኝ ነበር…ለብሸው ግን አላውቅም፡፡
።።።።።።።።።።።
ሎዛ ደውላ ሄይ አብርሽ… ከሥራ ስትወጣ እቤት እመጣለሁ፣ ጠብቀኝ አለችኝ፡፡
ከሥራ ስመለስ ቀድማኝ እኛ ቤት ደርሳ፣ የምትወደውን የጦስኝ ሻይ እየጠጣች ከእናቴ
ጋር ሲያወሩ ደረስኩ፡፡ እናቴ ፊት ብትስቅም ገና ሳያት እንዳኮረፈች ገብቶኝ ነበር፡፡
"ሙሽሪት” አልኩና በትከሻዬ ገፋ አድረጊያት ገባሁ፡፡ እናቴን ተሰናብታ ተያይዘን እንደወጣን፣ “ማምሻ ጋ አካሂደኝ አለችኝ፡፡
ለምን?
“ሚዜነቷ እንደቀረ ልነግራት!”
ቀረ እንዴ?” ዞር ብላ በብስጭት አይታኝ፣
“ደስ አለህ?” አለችኝ፡፡
“ለምን ደስ ይለኛል? …ግን አለ አይደል …”
በውስጤ ግን ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ በትዝብት አይታኝ፣
በቃ ቀርቷል፡፡ አባባ ተዪው አለኝ፡፡ ማሚ አሳምናው መሆን አለበት፡፡ማንም ሰው ከጎኔ
አልቆመም፣ ደከመኝ” አለች፡፡ ስልችት ያላት ትመስል ነበር፡፡ ተያይዘን እነማምሻ ቤት
ስንደርስ፣ ማምሻ የዘመመችው የጭቃ ቤታቸው ጋር ተያይዛ ከላስቲክ እና ከቆርቆሮ
ተሠራች ማድ ቤት ውስጥ ከጭስ ጋር እየታገለች እንጀራ ስትጋግር አገኘናት፡፡
ከማድ ቤቷ አጎንብሳ ስትወጣና አይታን ፈገግ ስትል ዓይኔን ማሳረፊያ ሌላ ቦታ ፈለግሁ፡፡
የማይለመድ መልከ ጥፉነት ነው ያላት፡፡ መልከ ጥፉ ብቻ አይደለችም… የሆነ በቀለኛ አጋንንት
ፊቷን በአጉሊ መነጽር እያየ ትንሽ ሰው ሊስብ ይችላል ያለውን ነገር ሁሉ እየለቀመ ያፈራረሰው ነበር የሚመስለው፡፡ እኔ ነኝ ያለ ደራሲ ይቅርና ፎቶ አንሺ እራሱ የማምሻን መልከ ጥፉነት በበቂ ሁኔታ አሳይቶ መጨረስ የሚችል እስከማይመስለኝ፣ ፊታ እንደ አዲስ አስገረመኝ፡፡ ምን ይሳነዋል ልሥራው ካለ ይሠረዋል፤ ላበላሸው ካለ ያበላሸዋል እላለሁ ለራሴ::
ወደ ቤታቸው እየመራች አስገባችን፣ የቤቷ ውስጥ ካሰብኩት በላይ እጅግ ንጹሕና በሥርዓት የተዘጋጀ ነበር የማምሻ ዘመን ያለፈባቸው ጥልፎች እንደሙዚየም ከአልጋ እስከ ኩርሲ በሥርዓት ለብሰው ተቀምጠዋል

እንደገባን “ትኩስ እንጀራ በበርበሬ ላቅርብላችሁ” አለችን፡፡ እኔ “አይ!” ስል ሎዛ ግን እሺ እንዲያውም ርቦኛል” አለች።
እንጀራ በበርበሬ እየበላን፣ በመሃል ሎዛ መብላቷን አቁማ ማምሻ ብላ ተጣራች፡
“የመጣሁት ሚዜነትሽ እንደቀረ ልነግርሽ ነው፤ እኔ እንኳን ሚዜዬ እንድትሆኚ ነበር የፈለከት፣ ግን ሁሉም ሰው አይሆንም አለ ሰርጉ የእኔ ቢሆንም የደገስኩት ግን እኔ አይደለሁም!… ሚዜ ሆንሽም አልሆንሽም እኔ እወድሻለሁ፣ ጓደኛዬ ነሽ” ብላ ተነስታ አቀፈቻትና እንባዋ ተዘረገፈ፡፡
ማምሻ ግን ፈገግ ለማለት እየሞከረች “ሎዛዬ አታልቅሽ የኔ ቆንጆ! ሙሽራ እያለቅስም
ነግሬሽ ነበርኮ…እኔ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የለመድኩት ነው፡፡ መቼም ሰርግሽ ላይ እትገኚ አይሉኝ እህቴ ስታገቢ መጥቼ አቀውጠዋለሁ” አለች፡፡ ሎዛ እንባዋን እየጠረገች በቅሬታ ፈገግ አለች፡፡ ግን እንደገና አቅፋት ማልቀስ ጀመረች …ለቅሶዋ ውስጥ እልህና መሸነፍ ነበር፡፡
ከነማምሻ ቤት ስንወጣ ሎዛን ለማጽናናት ክንዷን ያዝኳት፡፡ እጇን መንጭቃኝ ሂድ! አንዲት ቆንጆ ነርስ ሚዜ አምጥተውልሃል፤ እንዲያውም የአእምሮ ሐኪም ብትሆንልህ ይሻል ነበር፡፡ ሂድ አብረሃት ዳንስ ተለማመድያ ከተሳካልህም አብረሃት ተጋደም፡፡ እምቢ የምትል ዓይነት አይደለችም ብላኝ እዚያው የቆምኲባት ትታኝ ወደቤቷ ሄደች፡፡እንዴI እኔ ምን ላድርጋት ታዲያ? ይቺ ልጅማ ችግር አለባት፡፡ አሁን የሰርጓ ቀን ነው፤
ይለፍና እንነጋገራለን” ብዬ ወደ ቤቴ ለመመለስ ካሰብኩ በኋላ ሀሳቤን ቀይሬ
ተከተልከኳት የሆነ ሆኖ የማምሻም የሎዛም ነገር ከአእምሮዬ ወዲያው ወጥቶ የቆንጆዋ ነርስ ነገር አጓጓኝ፡፡ እቤት ስንደርስ ልብ ስንጥቅ የምታደርግ የጠይም ቆንጆ በፍኖት እየተመራች ወደእኔ መጥታ እየተሸኮረመመች ተዋወቀችኝ … “ፌበን" አለችኝ፡፡ ስትናገር አንገቷን ትሰብቃለች፡፡ ለስላሳና ውብ እጆቿን ጨብጨ አብርሃም” አልኩ! ተያየን፡፡
ዓይኖቿ ያምራሉ፡፡ ፈገግታዋ አዙሮ ይደፋል፡፡ የጎረስኩት የማምሻ እንጀራ በበርበሬ አፌ
ውስጥ ማቃጠሉ ይሰማኛል “ከፍትፍቱ ፊቱ” ብዬ ተረትኩ ለራሴ፡፡ ዞር ስል ከሎዛ እህት ከፍኖት ጋር ዓይን ለዓይን ተገጣጠምን እና ጠቀሰችኝ፡፡ ወደ ፌበን ዞሬ “ከዚህ በፊት ሚዜ ሆነሽ ታውቂያለሽ” አልኳት፣
የመጀመሪያዬ ነው…አንተስ?”
እኔም እንዳንች ዓይነት ቆንጆ ሳይ የመጀመሪያዬ ነው”
“ወሬኛ” ብላ በወዳጅነት ትከሻዬን ቸብ አደረገችኝ፡፡ በኋላ ፍኖት፣ ስለዚህ “ቸብታ ሎዛ
እንዳትሰማ በሹክሹክታ ስትቀልድ እንዲህ አለች፣
ይኼ ቸብ ያረህ እጅ የማምሻ ቢሆን ኑሮ፣ መፍለጫ እንዳረፈበት ጕቶ ለሁለት
ተሰንጥቀህ ወለል ላይ ትበታተን ነበር፡፡ ዕድሜ ለኔም የታፈነ ሳቃችን ቀልዱን በሚስጥር አጀበው
የሎዛ ሰርግ ከሙሸራ እስከሚዜ ፣ከምግብ እስከ አዳራሽ እስደማሚ ሁኖ እለፈ፡፡ ማታ ሙሽሮች ሲወጡ፣ ታዳሚው ቆሞ እያጨበጨበ እትሸኟትም ወይ” ሲባል፣ ፌበንን ከጎኔ እድርጌ ከሙሽሮች ኋላ በዝግታ ስንጓዝ… ሎዛ ድንገት የመውጫውን በር ትታ ግራ በኩል ቬሎዋን እየጎተተች ሄደች፤ ባሏም ሚዜዎቹም ግራ ተጋብተን እንደቆምን፣ በውድ የሐበሻ ቀሚስና በወርቅ የተንቆጠቆጡትን አክስቶቿን አልፋ፣…እንደነገሩ የለበሱትና ትንሽ ነጠል ብለው የቆሙትን፣ ማምሻና እናቷ ቁመው ወደሚያጨበጭቡበት መቀመጫ ሄዳ
፣ ተራ በተራ አቀፈቻቸው፡፡ ማምሻ ከዘፈኑና ከጭብጨባው በላይ በሚሰማ ሳግ
በተቀቀለበት ድምፅ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ሎዛ ግን ፊቷ በእልህና በቁጣ ክርር እንዳለ፣ ሰላም ሊሏት የሚሻሙ እኮስቶቿን እንዳላየች አልፋ ተመልሳ መንዷን ቀጠለች። ዓይኔን ወደፌበን መለሰኩ፣ ያ ውብ ጥርሷ አንጀት በሚያርስ ፈገግታ ተቀበለኝ፡፡ በእውነት ይቺ ልጅ ቦታዋ ሚዜነት ብቻ አይደለም እስከምል በውስጤ፡፡

#እውነቱ
" የፍቅር ታሪኬ ደምቆ
ሳቢና ማራኪ ይሆናል
የኑሮዬ ገድል ልቆ
ከሰው ተለይቶ ይገናል”
ብዬ እንኳን ለሀገር
ለሰው ሁሉ ልናገር
ለአንዲቷም ቅፅበት
እንደዋዛ እንደዘበት
ለራሴው ተንፍሼ አላውቅም
ከነፍስሽ ይነጥለኝ!
መቼም ካንቺ አልደብቅም።
እውነት እውነት
መከራው ገዝፎ የታየ
ከስው ሁሉ የተለየ
ገድል አለኝ ብዬ ራሴን ከሰው ተራ አላርቅም
ታሪክ አለኝ ብዬ አልንቀባረርም አልመፃድቅም፡፡
ካንቺ ጋር ለዘላለም ምኖረው
እንደነፍሴ አንቺኑ ማፈቅረው
ታሪኬና ገድሌ
በሥመጥር ፀሐፍት እንዲፃፍ ለዓለም
በዕውቅ ሠዓሊያን እንዲሳል በቀለም
ፈልጌ እኮ አይደለም፡፡
አይደለም! አይደለም
ካንቺ ጋር ለዘላለም ምኖረው
እንደነፍሴ አንቺኑ ማፈቅረው
ከላይ ታች ምለው
ሠርክ ምባትለው ሠርክ ምባዝነው
ጀንበር ስትፈነጥቅ ስታዘቀዝቅም
ከጐንሽ ሳልጠፋ በሐዘን በደስታ አብሬሽ ምሆነው
ከአገር ሁሉ ከሰው ተለይቶ ስሜም የገነነው ፤
በሌላ እኮ አይደለም ይኸውልሽ እውነቱ ስለ ማፈቅርሽ ነው::
እያረፉ ይጣሉት እያረፉ ያንሱት እንዳሻቸው ስሜን
እኔ አፈቅርሻሁ ዕድሜ ዘላለሜን አሜን!
አሜን! አሜን!..
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
" የፍቅር ታሪኬ ደምቆ
ሳቢና ማራኪ ይሆናል
የኑሮዬ ገድል ልቆ
ከሰው ተለይቶ ይገናል”
ብዬ እንኳን ለሀገር
ለሰው ሁሉ ልናገር
ለአንዲቷም ቅፅበት
እንደዋዛ እንደዘበት
ለራሴው ተንፍሼ አላውቅም
ከነፍስሽ ይነጥለኝ!
መቼም ካንቺ አልደብቅም።
እውነት እውነት
መከራው ገዝፎ የታየ
ከስው ሁሉ የተለየ
ገድል አለኝ ብዬ ራሴን ከሰው ተራ አላርቅም
ታሪክ አለኝ ብዬ አልንቀባረርም አልመፃድቅም፡፡
ካንቺ ጋር ለዘላለም ምኖረው
እንደነፍሴ አንቺኑ ማፈቅረው
ታሪኬና ገድሌ
በሥመጥር ፀሐፍት እንዲፃፍ ለዓለም
በዕውቅ ሠዓሊያን እንዲሳል በቀለም
ፈልጌ እኮ አይደለም፡፡
አይደለም! አይደለም
ካንቺ ጋር ለዘላለም ምኖረው
እንደነፍሴ አንቺኑ ማፈቅረው
ከላይ ታች ምለው
ሠርክ ምባትለው ሠርክ ምባዝነው
ጀንበር ስትፈነጥቅ ስታዘቀዝቅም
ከጐንሽ ሳልጠፋ በሐዘን በደስታ አብሬሽ ምሆነው
ከአገር ሁሉ ከሰው ተለይቶ ስሜም የገነነው ፤
በሌላ እኮ አይደለም ይኸውልሽ እውነቱ ስለ ማፈቅርሽ ነው::
እያረፉ ይጣሉት እያረፉ ያንሱት እንዳሻቸው ስሜን
እኔ አፈቅርሻሁ ዕድሜ ዘላለሜን አሜን!
አሜን! አሜን!..
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ቸግሮኝ_እኮ_ነው
ቃልኪዳን አጉድዬ
እምነትን ገድዬ
ፍቅርንም በድዬ
ባሕል ልማድ ጥሼ
ሕግም ተላልፌ
በነፍሴ ቆርጬ
ሞገድ አሳብሬ
ፅልመቱን ገፍፌ
ይቅርታን አዝዬ
ምሕረትን ታቅፌ
እንደ ወፍ ከንፌ
እንደ ወፍ በርሬ
ትናንቱን ዘንግቼ
የመጣሁት ዛሬ
እህል ተቸግሬ
አጥቼ አይደለም
እልሰው እቀምሰው
ታርዤም አይደለም
አጥቼ እምለብሰው
ልሞላም አይደለም
ባዶ አቁማዳዬን
በእግዜር ስም ለምኜ
እደጅሽ ላይ ሆኜ
እምልከሰከሰው
ችግሮኝ እኮ ነው
እንዳንቺ ያለ ሰው።
ከቆዳሽ ውስጥ ዘልቆ
ከነፍስሽ ሥር ጠልቆ
ይስማሽ ችግሬ
ታውቂዋለሽና
ፍቅር ምን እንደሆን
ቀድሞውኑ ፍቅሬ፡፡
ፍቅር ይገባዋል
ልብሽ ለመረዳት መቸም አይሳነው
አይችሉትን ችዬ አይሆኑ ምሆነው ፧
ከቸገረኝ ሰው ውስጥ ፍቅርን ፍለጋ ነው።
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
ቃልኪዳን አጉድዬ
እምነትን ገድዬ
ፍቅርንም በድዬ
ባሕል ልማድ ጥሼ
ሕግም ተላልፌ
በነፍሴ ቆርጬ
ሞገድ አሳብሬ
ፅልመቱን ገፍፌ
ይቅርታን አዝዬ
ምሕረትን ታቅፌ
እንደ ወፍ ከንፌ
እንደ ወፍ በርሬ
ትናንቱን ዘንግቼ
የመጣሁት ዛሬ
እህል ተቸግሬ
አጥቼ አይደለም
እልሰው እቀምሰው
ታርዤም አይደለም
አጥቼ እምለብሰው
ልሞላም አይደለም
ባዶ አቁማዳዬን
በእግዜር ስም ለምኜ
እደጅሽ ላይ ሆኜ
እምልከሰከሰው
ችግሮኝ እኮ ነው
እንዳንቺ ያለ ሰው።
ከቆዳሽ ውስጥ ዘልቆ
ከነፍስሽ ሥር ጠልቆ
ይስማሽ ችግሬ
ታውቂዋለሽና
ፍቅር ምን እንደሆን
ቀድሞውኑ ፍቅሬ፡፡
ፍቅር ይገባዋል
ልብሽ ለመረዳት መቸም አይሳነው
አይችሉትን ችዬ አይሆኑ ምሆነው ፧
ከቸገረኝ ሰው ውስጥ ፍቅርን ፍለጋ ነው።
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ድምጽ_አልባ_ዝምታ
ድምጽ አልባ ዝምታ
ሲበየን ሲፈታ ምን ትርጉም ይሰጣል?
እንዴትስ ተደርጐ በቃል ይገለጣል?!?
ድምጽ አልባ ዝምታ
በትግል ሲፈታ
ከአመጽ ማህፀን
አይሎ ሲወጣ ልብን ያሸብራል
በእጅጉ ያስፈራል
የራሱን ዝምታ በጩኸት ይሰብራል
ጫጫታን ሁካታን በድንገት ይፈጥራል::
ድምጽ አልባ ዝምታ ቋንቋ አለው ያወራል!!
ድምጽ አልባ ቢሆንም ዝምታ ይናገራል
ለገባው ቋንቋ ነው
“ውሃ” ሲቀዘቅዝ “በረዶ” እኮ ይስራል::
ተራራ አክሎ ተከምሮ ኖሮ
ድንገት ሳይታሰብ በማመጽ አምርሮ
ድምጹ ይደመጣል
ጩኸቱ ያናውጣል
የበረዶ አለት
የፈራረሰ ዕለት!!
ሰምና ወርቅ ያለው
ቅኔው እንደሆነ ውሃ የተቀኘለት
ሁሉም ጫኺ ሆኖ
የቋዋንቋውን ፍቺ ማን ይተርጉምለት?!?
በማን ነው እሚፈታ?
በምን ነው እሚፈታ?
ድምጽ አልባ ዝምታ!!!
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
ድምጽ አልባ ዝምታ
ሲበየን ሲፈታ ምን ትርጉም ይሰጣል?
እንዴትስ ተደርጐ በቃል ይገለጣል?!?
ድምጽ አልባ ዝምታ
በትግል ሲፈታ
ከአመጽ ማህፀን
አይሎ ሲወጣ ልብን ያሸብራል
በእጅጉ ያስፈራል
የራሱን ዝምታ በጩኸት ይሰብራል
ጫጫታን ሁካታን በድንገት ይፈጥራል::
ድምጽ አልባ ዝምታ ቋንቋ አለው ያወራል!!
ድምጽ አልባ ቢሆንም ዝምታ ይናገራል
ለገባው ቋንቋ ነው
“ውሃ” ሲቀዘቅዝ “በረዶ” እኮ ይስራል::
ተራራ አክሎ ተከምሮ ኖሮ
ድንገት ሳይታሰብ በማመጽ አምርሮ
ድምጹ ይደመጣል
ጩኸቱ ያናውጣል
የበረዶ አለት
የፈራረሰ ዕለት!!
ሰምና ወርቅ ያለው
ቅኔው እንደሆነ ውሃ የተቀኘለት
ሁሉም ጫኺ ሆኖ
የቋዋንቋውን ፍቺ ማን ይተርጉምለት?!?
በማን ነው እሚፈታ?
በምን ነው እሚፈታ?
ድምጽ አልባ ዝምታ!!!
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
👍1
#Re_post
#ያመት_በአል_ማግስት_ትእይንቶች!!
- የተመጠጠ ቤት
የሞላ ሽንትቤት
ጭር ያለ ቤተሰብ
የተጠረገ ድስት -ድርቅ የመታው ሞሰብ!!
-ያደፈ ቄጤማ
በበግ በሰው እግር- የተደቀደቀ
ወዙ ባንድ ሌሊት -ተመጦ ያለቀ
መጥረጊያ ሚጠብቅ -ወድቆ ተበታትኖ
ትናንት ጌጥ የነበር- ዛሬ ጉድፍ ሆኖ!!
-የተወቀጠ ፊት -የነጋበት ድንገት
በዳንኪራ ብዛት-ወለም ያለው አንገት
የዞረበት ናላ -ጌሾ ያበከተው
እንኳንስ መገንዘብ -መጀዘብ ያቃተው
የወለቀ ወገብ -የዛለ ትከሻ
መኪና ይመስል -ብየዳ የሚሻ
-የጠጅና የጢስ- ድብልቅ እስትንፋስ
ከሆድ ሸለቆ ውስጥ -የታፈነ ነፋስ
ባንጀት የታሰረው
እንደተከበበ አመፀኛ ሽፍታ
መውጫ የቸገረው!
-የማይፈካ ሰማይ -የማይዘንብ ደመና
በላባና በፈርስ -ያደፈ ጎዳና
በበግ ራስ ምላስ -የተልከሰከሰ
የጠገበ ውሻ-
በመንፈቅ አንድ ጊዜ አጥንት የቀመሰ::
ሀንጎቨር ያዛገው-መሂና አሽከርካሪ
እግረኛ አስደንባሪ
በከፊል የነቃ -በከፊል የተኛ
ከሱ የማይሻል- የመኪና እረኛ
ካውራ ጎዳናው ዳር -ቁሞ ሚያንቀላፋ
ድብርትን ባናቱ -እንደ ቆብ የደፋ!!
The moral of the story :
የተድላ ማገዶ!!
ላጭር ጊዜ ነዶ
ላጭር ጊዜ ደምቆ
ላጭር ጊዜ ሙቆ
አመዱ ብዙ ነው: አያልቅም ተዝቆ!!
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ያመት_በአል_ማግስት_ትእይንቶች!!
- የተመጠጠ ቤት
የሞላ ሽንትቤት
ጭር ያለ ቤተሰብ
የተጠረገ ድስት -ድርቅ የመታው ሞሰብ!!
-ያደፈ ቄጤማ
በበግ በሰው እግር- የተደቀደቀ
ወዙ ባንድ ሌሊት -ተመጦ ያለቀ
መጥረጊያ ሚጠብቅ -ወድቆ ተበታትኖ
ትናንት ጌጥ የነበር- ዛሬ ጉድፍ ሆኖ!!
-የተወቀጠ ፊት -የነጋበት ድንገት
በዳንኪራ ብዛት-ወለም ያለው አንገት
የዞረበት ናላ -ጌሾ ያበከተው
እንኳንስ መገንዘብ -መጀዘብ ያቃተው
የወለቀ ወገብ -የዛለ ትከሻ
መኪና ይመስል -ብየዳ የሚሻ
-የጠጅና የጢስ- ድብልቅ እስትንፋስ
ከሆድ ሸለቆ ውስጥ -የታፈነ ነፋስ
ባንጀት የታሰረው
እንደተከበበ አመፀኛ ሽፍታ
መውጫ የቸገረው!
-የማይፈካ ሰማይ -የማይዘንብ ደመና
በላባና በፈርስ -ያደፈ ጎዳና
በበግ ራስ ምላስ -የተልከሰከሰ
የጠገበ ውሻ-
በመንፈቅ አንድ ጊዜ አጥንት የቀመሰ::
ሀንጎቨር ያዛገው-መሂና አሽከርካሪ
እግረኛ አስደንባሪ
በከፊል የነቃ -በከፊል የተኛ
ከሱ የማይሻል- የመኪና እረኛ
ካውራ ጎዳናው ዳር -ቁሞ ሚያንቀላፋ
ድብርትን ባናቱ -እንደ ቆብ የደፋ!!
The moral of the story :
የተድላ ማገዶ!!
ላጭር ጊዜ ነዶ
ላጭር ጊዜ ደምቆ
ላጭር ጊዜ ሙቆ
አመዱ ብዙ ነው: አያልቅም ተዝቆ!!
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
👍1
#በልጅነቴ_ይሄን_ተማርኩ
ልጅ ሆኜ...
የአባቴ ዘመዶች እማዬ በሌለችበት ሲመጡ ፤ እሷ ዘመዶቿ ሲመጡ እንደምታደርገው ቤት ውስጥ ያለውን፣ እንቁክ ሁኩ ጠብሼ ፣ በብዙ ዳቦ
አቀረብኩላቸው ።ማይዬ መጥታ የሆነውን፣ ስታውቅ ክፉኛ ገረፈችኝ።
ደግነት፥ ወገንተኝነት መሆኑን ያወኩት ያኔ ነው : :
ሁሌም ከኪሱ ብሮች የማይጠፋው ጓደኛኔ ጋር እየሄድን ነበር ፡ : አንድ ጉስቁልቁል ያለ ልጅ ፣
"ዳቦ ግዙልኝ” በርሃብ እያዛጋ ጠየቀኝ ።
ሁኔታውን ዐይቼ አላስችል ቢለኝ፤ ያለችኝን አንድ ብር ልሰጠው ከኪሴ ሳወጣ ፣ ጓደኛዬ እጄን ያዘና፣ “ለእሱ ከሰጠሽው ለአንቺ፣ አይኖርሽም”
አለኝ ።
ለጋስነት የድህነት መንስኤ መሆኑን፣ የተማርኩት ያኔ ነው ።
ሌላ ቀን ታላቅ እህቴ ፣ “እወደዋለሁ” እያለች፤ ከጋደኞቿ ጋር ቀን በቅን የምታነሳው ጎርምሳ ፣ ከታናሽ እህቱ ጋር ሰኞ ማክሰኞ ስጫወት መጣና
“እህትሽ ግን ለምንድነው የምትጠላኝ?” ሲለኝ፤ “አረ እንደውም እሷ በጣም ትወድሃለች ፤ ለጓደኞቿ ሁሌ እወደዋለሁ እንዳለች ነው” አልኩት። ብዙም ሳይቆይ ነገሩን የደረሰችበት እህቴ፣ በንዴት እሳት ጎርሳ በርበሬ አጠነችኝ።
ምስጢርን በመጠበቅ ሽፋን፣ ውሸት መናገርን የተማርኩት ያኔ ነው።
አምስተኛ ክፍል ሆኜ አስተማሪያችን ጥያቄ ጠይቆ፣ የሚመልስ ቢጠፋ እጄን አውጥቼ የመሰለኝን ተናገርኩ ፡ : መሳሳቴ፣ “አንቺ ደነዝ!”
ብሎ ሲነገረኝ የክፍሉ ተማሪ ሁሉ በአንድነት አውካካ።
ጥያቄን፤ መመለስ መሳለቅያ እንደሚያደረግ የተማርኩት ያኔ ነው : :
በኅብረተሰብ ክፍለ ጊዜ መምህራችን፣ “ሁላችሁም የአፍሪካ ካርታ ከመፀሀፍ ላይ እያያቹ
ደብተራችሁ ላይ ሳሉ" ብሎ አዘዘን ሁሉም ተማሪዎች ደብተራቸውን የጽሁፍ ስዕል ላይ አስደግፈው ፤የዋናውን ስዕል ጥላ እየተከተሉ ልክ እንደ መጽሐፉ አድርገው ስለው ሲመጡ ፤ እኔ ግን ፣ “እያያቹ ሳሉ” በተባለው መሰረት የመፅሐፉን ስዕል እያየሁ ሳላስደግፍ ደብተሬ ላይ ፣ “የኔን አፍሪካ” ስዬ መጣሁ : :
አስተማሪዬ አስደግፈው ለሳሉት ልጆች በሙሉ “እ...በ....ጥ...”እያሉ ፅፎ እኔ ጋር ሲደርስ ፣ እንደ ሌሎቹ ልጆች አስደግፈሽ ብትስይ ኖሮ እኝዲህ
አይጣመምብሽም ነበር ። ይሄ ምኑም አፍሪካን አይመስል!” ብሎ ዜሮ ከአስር ሰጠኝ : :
ቀድሞ የተሰራን ነገር፤ መቅዳት ሲያስሞግስ ፤ አዲስ ፈጠራና ሙከራ እንደሚያስቀጣ የተማርኩት ያኔ ነው : :
ደግሞ በሌላ አመት የህብረተሰብ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ስለ ዘጠኙ ፕላኔቶች ስንማር እጄን አወጣሁና ፣ “ቲቸር ፣ ለመሆኑ ከመሬታችን
ውጪ ሌሎች ፕላኔቶች ውስጥ ሰዎች ይኖራሉ?” ብዬ ጠየቅኩ : :
ቲቸር "ምን እዚህ...! ደብተራችሁን፣ እንኳን በቅጡ አታነቡም : :ስለ ሌላ ፕላኔት አስበን እንራቀቅ ትላላችሁ" በሚል ውረፋ ክፉኛ አሸማቀቀኝ።
አርቆ ማሰብና መመራመር እደሚያስኮንን የተማርኩት ያኔ ነው : :
አድጌ ፤ መስሪያ ቤቴ ያጸደቀው መሪ ዕቅድ ፣ ገንዘብ እደሚያባክን ሲገባኝ ፤ ቅዳሜና እሁዴን ሰውቼ አዲስ መሪ ዕቅድ አርቀቅኩና ሰኞ
ላይ ለአመራሩ አቀረብኩ : :
“የመስርያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ከስድስት ወር በላይ ፈጅተውና ለፍተው ያዘጋጁትን ዕቅድ በመናቅና ባስመታዘዝ” ጥርስ ተነክሶብኝ
ተገመገምኩ ። እሱን ተከትሎም የደረጃና የደሞዝ እድገት ታለፍኩ ፡ ፡
ቀናነት ከባድ ዋጋ እኝደሚያስከፍል የተረዳሁት ያኔ ነው : :
አሁን ታድያ በእድሜዬ ቶና ላይ ሆኜ ፤ ከጊዜና ኑሮ በተማርኩት መሠረት....
አዳልቼ ስሰጥ “ደግ ሰው” እየተባልኩ ፤
ከድሀ ነፍጌ ባስጠጋ እየሆንኩ፤
በአውራ ዋሾነቴ ሚስጥር ጠባቂ እየተባልኩ ፤
ጥያቄ ሳልመልስ “ምሁሯ” እየተባልኩ ፤
የተሰራን ገልብኩ “ፈጠረች” እየተባልኩ ፤
ቀና ባለመሆን ሽልማት እያፈስስ ፣
ደልቶኝ እኖራhሁ : :
🔘ጨረስኩ🔘

#የጥበብ_ፈተና
ለአንድ ነብስሽ እንኳ ለራስሽ ሳታቂ ለሌላ እመተርፊ
ሰው ሆነሽ ተፈጥረሽ ከሰው እምትልቂ ከሰው እምትገዝፊ
ሀ) በድምፅ ብትወከይ
ለ) ጆሮ ማያዳምጥሽ እማይለይ ውስጥሽ
ሐ)ቢቀርፁሽ ብትሳይ
መ)ለተመልካች ባዳ
ለእይታ እንግዳ
ሠ)በቃል ብትፃፊ
ረ)ለአንባቢ እማትገቢ።
እምትጋነኚ
እማትታመኚ
ከሰዓሊው እርቀሽ ከመስመር የወጣሽ ማየሸገልፅሽ ቀለም
ነፍስ ሚያለመልም ድምፅ አልባ ሙዚቃ ዜማ እንዳንቺ የለም
በመላው ምድረረ ዓለም።
ከገጣሚው ይልቅ አይረሴ ግጥም መንፈስ የሚያፀና
ከባለቅኔው ይበልጥ ተለይቶ ሚታይ የላቀ ልእልና
ከድርሰት በላይ ነሽ የደራሲ አሳር የጥበብ ፈተና።
አክሱም አይወክልሽ ላሊበላ አይሆንም ዕውነትሽን ማሳያ
ዘመን ተሻጋሪ ሕያው ለዝንታለም የሌለሽ አምሳያ
የሰማይ መቀነት ቀስተ ደመና ነው ሰንደቅሽ መታያ።
ሀገሬ ኢትዮጵያ ሆገሬ ኢትዮጵያ!
ስሜት ቢነ ቃቃ ስሜት ቢነሳሳ ሐሳብ ቢሰበሰብ
በረቀቀ ምናብ በጠሊቅ ልቡና ሺ ጊዜ ቢታሰብ
በቅርፅና ይዘት
መቼም አይፈጠር እንዳንቺ ገፀሀገር እንዳንቺ ገፀ ሰብ፡፡
ለአንድ ነብስሽ እንኳ ለራስሽ ሳታቂ ለሌላ እመተርፊ
ሰው ሆነሽ ተፈጥረሽ ከሰው እምትልቂ ከሰው እምትገዝፊ
ሀ) በድምፅ ብትወከይ
ለ) ጆሮ ማያዳምጥሽ እማይለይ ውስጥሽ
ሐ)ቢቀርፁሽ ብትሳይ
መ)ለተመልካች ባዳ
ለእይታ እንግዳ
ሠ)በቃል ብትፃፊ
ረ)ለአንባቢ እማትገቢ።
እምትጋነኚ
እማትታመኚ
ከሰዓሊው እርቀሽ ከመስመር የወጣሽ ማየሸገልፅሽ ቀለም
ነፍስ ሚያለመልም ድምፅ አልባ ሙዚቃ ዜማ እንዳንቺ የለም
በመላው ምድረረ ዓለም።
ከገጣሚው ይልቅ አይረሴ ግጥም መንፈስ የሚያፀና
ከባለቅኔው ይበልጥ ተለይቶ ሚታይ የላቀ ልእልና
ከድርሰት በላይ ነሽ የደራሲ አሳር የጥበብ ፈተና።
አክሱም አይወክልሽ ላሊበላ አይሆንም ዕውነትሽን ማሳያ
ዘመን ተሻጋሪ ሕያው ለዝንታለም የሌለሽ አምሳያ
የሰማይ መቀነት ቀስተ ደመና ነው ሰንደቅሽ መታያ።
ሀገሬ ኢትዮጵያ ሆገሬ ኢትዮጵያ!
ስሜት ቢነ ቃቃ ስሜት ቢነሳሳ ሐሳብ ቢሰበሰብ
በረቀቀ ምናብ በጠሊቅ ልቡና ሺ ጊዜ ቢታሰብ
በቅርፅና ይዘት
መቼም አይፈጠር እንዳንቺ ገፀሀገር እንዳንቺ ገፀ ሰብ፡፡
👍2