አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም “እጮኻለሁ ተይው አትጎትችው ይምጣ ይደብድበኝ የኔ የአዳሙ ጩኸት እንዳይመስልሽ እንቅልፍ የነሳው! የራሱ ኅሊና ነው፣የራሱ ኅሊና አፍ ቢዘጋ ኅሊና ዝም እይልም የጅብ አገር ሕግ ባይምር፣ እንዴት ጓደኛ ጓደኛውን እይምርም? እንዴት ነው የሚኖረው እዚች ምድር ላይ? .…ድንበር መለካት ብቻ አደደለም መሐንዲስነት፣ ለራሳችን ስግብግብነትም…»
#ልትመጪ_ነው_መሰል

ዓለም ቢሰወረኝ ፥ ሔደሽ ስትቀሪ
ተስፋ እንደ ሎተሪ
ቆርጬልሽ ነበር
ጨለማዬን ስፍቅ ፥ ደረሰችኝ ጀምበር።
እንዴት ሊሆን ቻለ?
እንዴት ሊኖር ቻለ?
ቀን እና ጨለማ ፥ ምሽት እና ንጋት
ይህ ዓለም ያላንቺ ፥ እንዴት ቻለ መርጋት?

መዓዛሽ ያሸገው
ለመኖር ጠረንሽን ፥ እንደ አየር ሚምገው
የአፍንጫዬን በር ፥ ምን ተዓምር ከፈተው?
ምንድን ነው ሚያውደኝ ፣ ምንድን ነው ሚሽተው?

ያንቺ ምስል ብቻ ፥ የሚመለከተው
ዐይኔን ምን ከፈተው
ገለጠው ምን ተዓምር ?
ይህ ዓለም ያላንቺ
እንዴት ሊኖር ቻለ ፥ ትዕንግርት ነው የምር !

ያንቺን ድምፅ ብቻ ፥ ሲያቃጭል የኖረ
የቆለፍሽው ጆሮ ፥ በምን ተሰበረ?
ይኸው ብዙ ድምፆች
ከየትም እየመጡ ፥ ይሰሙኝ ጀመረ።
የዘጋሽው ልቤ !
የቆለፍሽው ልቤ !







እንዴት ሰው አማረው?
...
አንቺን ተከትሎ
ጓዞቹን ጠቅልሎ
ወዳ'ንቺ ኮብልሎ
የጠፋ ዓለሜን
የጠፋ ቀለሜን
የጠፋ ሰላሜን
የተሰወረ ሕልሜን
ዳግም የፈጠረ
የምን ጉድ ነው ኧረ?

ልረሳሽ ነው መሰል ፥ ወይ ደግሞ ልትመጪ
ይሰማኝ ጀመረ
ያውደኝ ጀመረ
ይታየኝ ጀመረ ፥ ዓለም ካንቺ ውጪ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#አልጋ_ወራሽ

ከዘሬ ንግስና
አልታደልኩምና
እንደ ሀገሩ ልማድ ፥ አልሆነም ልማዴ
የኋሊት ቢቆጠር...
ከንጉስ አይደርስም ፥ ሴት ናት የዘር ግንዱ

ስለዚህም ብዬ
ከዙፋን የላቀ ለሴት አደላለሁ
ወንበርና አልጋን አላመሳስልም
ከተቀማጭ በላይ ተኚን እመርጣለሁ ።

ለቃል ያለኝ ትርጉም
እንደ ሀገር ትርጉም ፥ አይደለም በጭራሽ
አንቺ ስትሔጂ
የምትመጣ ሴት ናት ፥ የ'ኔ አልጋ ወራሽ ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የሞት_ጥቁር_ወተት

"ሰው አምላክ ቢሆንስ?በሐሳብ መቅደሱ
ፈጣሪስ ሰው ቢሆን?ሥጋን በመልበሱ
ድንቅ ነው! ረቂቅ ! ፣ ካምላክ መወዳደር
ከምድር ላይ ቆሞ፣ሰማይ ላይ መንደርደር።
ከጥቁር ገጽ ሥር.. .
በቃል ኅይለ ብእር ፣ ብርሃንን መልበስ፣
በሕያው ነፍስ ላይ...
የሞት ጥቁር ወተት፣ለዘላለም መቅመስ።

🔘ተስፋኹን ከበደ🔘
የኤፍ ኤም "ጠቅላላ ዕውቀት” ፕሮግራም

በኤፍ ኤም ሬድዮ ጣብያ አንድ አድማጭ አየር ላይ ነው።

“እሺ... ጥያቄ አንድ! ጥያቄ አንድ! አዲስ አበባን የቆረቆራት ማነው?”

“እ... አላውቀውም ። ሌላ ጥያቄ?

“ሌላ ጥያቄ… ሌላ ጥያቄ...”

“እ... የአድዋ ጦርነት መቼ ተካሄደ? ”

"እ... ይለፈኝ!”

“የመጨረሻ ዕድል...”

“በአንደኛው የአለም ጦርነት ከተዋጉ ሀገራት ሦስቱን ጥቀስ? ”

“በእናትህ ስጋ ስፖርት የለህም? ስፖርት ጠይቀኝ ።"

“አይሆንም ።ለሌላ አድማጭ ዕድል እሰጣለሁ ።

ሌላ አድማጭ መሥመር ላይ ፤

“እሺ... የአድዋ ጦርነት መቼ ተካሄዶ ?"

“አይ የስፖርቱን ለመመለስ ነበር..."

“የቱን...?”

"ማድሪድ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ለፈረንሳዩ ክለብ PSG በስንት እሸጣለሁ ነው ያለው
የሚለውን..."

"እሺ.."

"135 ሚሊዮን ፓው፣ድ ነው!"

"ትክክክ! በጣም ትክክክ!"

"ከዚህ በፊት አቅርበው የነበረውን ፤ ዋጋ ልጨምር.…?”

“አይ ግዴለም ፣ ወደ ሌላ ጥያቄ እንለፍ... አዲስ አበባን......"

"አይ ሌላ ስፖርት ካለ ጠይቀኝ….."

ሌላ አድማጭ ፣

"ሃሎ"

“የቫን ፐርሲን ለመመለስ ነበር..."

ይቺ ናት ጠቅላላ ውድቀት!!!

ቻናላችንን ሼር ያድርጉ

ሌለኛውን የፍቅር ቻናል ይቀላቀሉ

🔘በሕይወት እምሻው🔘
ፍፃሜው ካልሆነ

ፍፃሜው ካልሆነ የዓለም ድንቁርና
ጅማሬው ካልሆነ ማሰቂያው ጉስቁልና
በሽታ ካልጠፋ ካልሰፈነ ጤና
በእኩል ካልስመረ የዓለም ብልፅግና
የእምነት ብርሐን ከስሞ ፍርን ካጠፋ
ጽልመት ከተስፋፋ
ከመከነ ተስፋ
ከበጎ እኩይ ልቆ ምድር ላይ ከከፋ

አፍኖ መግዛትም ተኩሶ መግደልም
በጥይት መሞትም በግፍ መበደልም
በዓለም ላይ ካልቀረ
በሐሳብ ማመጹ
መፃፉ መግለጹ
እግር ተወርች ካስያዘ በግፍ ካሳሰረ
እንደ እንስሳ በረት ጋጣ ካሳጎረ
የእልፍ አዕላፍ ጀግና ደም እንደጅረት ፈሶ
የእልፍ አዕላፍ ፈሪ አጥንት በትግል ተከስክሶ

እልፍ አዕላፍ ታጋይ ሕይወቱን ሰውቶ
እልፍ አዕላፍ ሙታን የሞት ሞቱን ሞቶ
የባርነት የግንብ አጥር ካልቀረ ፈራርሶ
ካልኖረ የሰው ልጅ ነፃ አየር ተንፍሶ ፤
ልክ እንደብሒሉ
“የደንቆሮ ልቅሶ፧ መልሶ መላልሶ፡፡”

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘

አዘጋጅ፦አቢ ፍቅር

👇
ሌላኛውን የፍቅር ቻናል ይቀላቀሉ
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

እስከ ሐሙስ ከቆየህ፣ ለምን ራስህ አታያትም እውነቴን ነው ማረሚያ ቤት መሄጃ ጋ ካሉት ካፌዎች አንዱ በረንዳ ላይ ተቀምጠህ ስትገባ ማየት ትችላለህ”

እኔ ምን ትሰራልኛለች፤ ነገሩ ገርሞኝ ነው እንጂ”

"እሱማ እኔም በውስጤ ለብቻዬ ስገረም ነበር"

የዚያን ቀን እንዲቹ እንደፈጠጥኩ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ሌሊቱን አጋመስኩት፡፡ ለሮሐ አልነገርኳትም፡፡ ልጃችንን ይዛ ቤተሰቦቿ ቤት ነበረች፡፡ እንኳን ለሷ ልነግራት ለራሴም በማመንና ባለማመን መሀል እየወላወልኩ ነበር፡፡ሳሌም እንዴት የደፈራትን መሐሪን ያውም በየሳምንቱ ለዓመታት እየሄደች ትጠይቀዋለች…? ያውም ያንን በደል ይቅር ብላ? እኔ የዓመታት ጓደኝነቴን በዚያች አጋጣሚ አሽቀንጥሬ ጥዬ ይኼው ዓይኑን ካየሁት አስራ
ሦስት ዓመቴ፡፡ ምን እሱን ብቻ እንደ እናት ያሳደገችኝን ማሚን እንኳን እንዴት ነሽ
ብያት አላውቅም፡፡ ወደ ወቀሳ በሚቀርብ ግርምት ስገረም አደርኩ፡፡ መጨረሻ ላይ
የራሷ ጉዳይ ነው … እኔ መነኩሴ አይደለሁም” ብዬ ራሴን አጽናናሁ፡፡
የሳሌምን ዕድሜ በውስጤ አሰላሁት ሃያ አምስት፣ ሲበዛ ሃያ ስድስት ቢሆናት ነው፡፡

ጧት ከእንቅልፌ ስነቃ፣ ድንገት ሳሌምን የማግኘት ሐሳብ ከውስጤ ገንፍሎ ወጣ፡፡በቀጣዩ ቀን ለሮሐ ጉዳዩን ሳልነግራት፣ እንዲሁ እስከ ቅዳሜ እንድንቆይ ነገርኳት፡፡ሐሙስ ነበር ወደ አዲስ አበባ ልንመለስ ያሰብነው፡፡

ችግር የለውም፣ ቤቢቾ ተመችቶታል፡፡ ዘና ብለህ የምትሠራውን ጨርስ” አለችኝ፡፡
ለምን? እንዴት? እንኳን አላለችኝም፡፡ እንዲህ ናት በቃ፡፡ የነፍሴ ምቾት ሮሐ፡፡ ጨረቃን አውርጄ ልከሰክሳት ነው ብላት፣ ቆይ መሰላል ልያዝልህ ከማለት አትመለስም፡፡

ሐሙስ ቀደም ብዬ ወጥቼ፣ ልክ ተስፍሽ ፔሌ እንደነገረኝ፣ በማረሚያ ቤቱ ዋና በር
በኩል ካሉት ካፍቴሪያዎች አንዱ በረንዳ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ልቤ እንደጉድ ይመታ ነበር፡፡ምን አስፈራኝ…? ምንም ወንጀል አልሠራሁም እያልኩ ለራሴ! ከተቀመጥኩበት ቦታ ሦስት መቶ ሜትር ርቀት ላይ፣ ለአስራሦስት ዓመት ዓይኑን ያላየሁት መሐሪ የሚባል ልጅ አለ፡፡ እንደማግኔት ሞገድ ወደ ውስጥ ሳበኝ ይሰማኛል፡፡ ማን ያውቃል፣ በዚች
ቅጽበት ትከሻውን እየከበደው ይሆናል፡፡ ድንገት ሃሃሃሃ የሚል ሳቅ ሰምቼ ስዞር

ተስፍሽ "ፔሌ" አጠገቤ እንደጅብራ ተገትሯል፡፡ መላ ሰውነቴን እፍረት አጥለቅልቆ፣እፍረት የቀላቀለ ሳቅ አብሬው ሳቅሁ፡፡

እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ” እለ።

"እንዴት አውቅህ ባክህ?”

ፖሊስ እይደለሁ?… ፊትህ ላይ አነበብኩት ወንበር ስቦ መንገዱ እንዲታየው አመቻችቶ እጠገቤ ተቀመጠና ሰዓቱን አየት አድርጎ በሹክሹከታ “አሁን ትመጣለች” ብሎኝ ፈገግ አለ፡፡

እንዲሁ ገርሞኝ ነው …አለ አይደል” አፍሬ ነበር፡፡

“ይገባኛል አብርሽ፣ ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፤ እኔም እንዳንተው ነው የተሰማኝ፡፡እንዲያውም እንኳን መጣህ አብሮኝ የሚገረም ሰው አገኘሁ” ብሎ ትከሻዬን በወዳጅነት ቸብ አደረገኝ፡፡

ቡና አዘን እየጠጣን፣ እስረኛ ለመጠየቅ የሚገቡትን፣ ሰዎች ታሪክ ያወጋኝ ጀመር፡፡ “ይች ሴትዮ ባሏ የደርግ ባለሥልጣን ነበር ዕድሜ ልክ ፍርደኛ ነው… ያች በሷ ምክንያት በጩቤ ሰው የገደለ ቦይ ፍሬንዷን ነው የምትጠይቀው፣ ይኼ ባለባርኔጣው ሰውዬ " እያለ የጠያቂ ታሪክ ሲያሸመድደኝ ቆየንና፣ ድንገት በሹክሹክታ “መጣችልህ” አለኝ፡፡
ቢያንስ ከእኛ መቶ ሜትር እርቀት ላይ ረዥም ጥቁር ቀሚስ የለበሰች፣ ራስ ላይ
የሚጠለቅ ነጭ የጸጉር መሸፈኛ ሻሽ ያደረገች ረዘም ባለ ሰንሰለት አንገቷ ላይ የጣውላ መስቀል ያንጠለጠለች ወጣት መነኩሲት በፈጣን ርምጃ በእጄ ከበድ ያለ የጨርቅ ከረጢት አንጠልጥላ ስትመጣ አየሁ፡፡ እየቀረበች ስትመጣ ለአንዴ ነበር የለየኋት፡፡ ፊቷ ትንሽ ውፍረት ጨምሯል፡፡ ቀጥ ብሎ ወርዶ ጫፉ ወደላይ የሚቀሰር አፍንጫዋና ቀይ ፊቷ ግን ጩኾ ሳሌም ነኝ ይላል፡፡ ታጥፋ ወደ ማረሚያ ቤቱ የሚያስገባውን መንገድ ተከትላ ስትሄድ ከኋላዋ ፈዝዠ እያየኋት ነበር፡፡ ውስጤ ርብሽብሽ አለ፡፡ የዚያች ቀን ምሽት፣ እኔ እዚህ የተቀመጥኩት ሰውዬ ጓደኛዬ መሐሪን መጠጥ እንዳይጠጣ
ብከለክለው፣ ያችን ውስኪ ከሮሐ እጅ ሊቀበል ሲያቅማማ “ተው” ብለው፣ ይች ልጅ እንደዚህ ትሆን ነበር ወይ? ሰው መነኩሴም ይሁን ዓለማዊ፣ ምርጫው ከሆነ ችግር አይደለም፡፡ ሌሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ገፍተው ለዚህ ሲያበቁት ግን ያሳዝናል፡፡ እዚህ ጥቁር ቀሚስ ሥር ያለ ቁስለኛ ልብ ላይ የእኔም ስም የተመዘገበበት የጥላቻ መዝገብ ይኖር እንደሆንስ ማን ያውቃል?፡፡ እነሱ አሳስተውኝ ነው፣ ይቅር በይኝ ብሏት ቢሆንስ?፡፡ እኛን ጭዳ አድርጎ በእኛ ስም እጁን ታጥቦ ቢሆን፡
እህ …ዋሸሁ ” አለኝ ተስፍሽ፡፡

"እሷ ነች አይደለችም?"

“ይገርማል! ራሷ ነች …”

ነገርኩህ …ምንስ ፎር ፖይንት አምጥተን ዩኒቨርስቲ ባንገባ፣ ይች ይችማ አታቅተንም እኔ የምልህ ተስፍሽ፣ ማናገር ብፈልግ ክልክል ይሆን እንዴ? ማለቴ በእምነታቸው ከወንድ ጋር አያወሩም..?

ኦ! ልታወራት ፈለክ …?

“ያው ታውቃለህ እህቴ ማለት ነበረች፡፡ እጃችን ላይ ነው ያደገችው:: ዩ ኖው ቁም
ነገር ባይሆንም እንዲሁ ባናግራት ደስ ይለኛል፡፡ ሰላም ብላት ምናምን፣ እኔጃ፣ ምን ይመስልሃል ችግር አለው?”

እኔጃ!

ስልኳን ማግኘት ግን እችላልሁ መዝገብ ላይ ስለሚመዘገብ ከፈለክ አመጣልሃለሁ

እባክህ ተቸገርልኝ "

ግን ሕጋዊ አይደለም ብሎ ሳቀ፡፡ ማታ እቤት መጣና ቁራጭ ወረቀት እያቀበለኝ
በሹክሹክታ “ሲስተር ሳሌም ማለት አትርሳ” ብሎኝ እየሳቀ ሄደ፡፡

በቀጣዩ ቀን ጧት ወደአራት ሰዓት አካባቢ ደወልኩ፡፡ ስልኩ ይጠራል አይነሳም፡፡
ሁለተ ሞከርኩ፡፡ አይነሳም፡፡ ወደምሳ ሰዓት አካባቢ መልሶ ተደወለልኝ፡፡ በረዥሙ ተንፍሽ አነሳሁና። ሔሎ አልኩ…
“ጤና ይስጥልኝ፣ በዚህ ስልክ ከሁለት ሰዓት በፊት ተደውሎልኝ፣ ሥራ ላይ ስለነበርኩ አላነሳሁም ይቅርታ፣ ማን ልበል?” አለችኝ ረጋ ባላ ጨዋ ድምፅ፡፡ ልቤ ተመንጥቃ ልትወጣ ደርሳ ነበር፡፡

“ አዎ! አዎ! ኢሲስተር ሳሌምን ፈልጌ ነበር” አልኩ እኔም ረጋ ብዬ፡፡

“ ሲስተር ሳሌም ነኝ… ማን ልበል እርስዎን” አንቱ ልበላት እንቺ ልበላት፣ ግራ ገባኝ…

“እኔ እኔ አብርሃም እባላለሁ፡፡ በጣም ቆየ እንጂ እንተዋወቃለን፡፡ እኔጃ እንዴት
መግለፅ እንዳለብኝ …ብቻ የመሐሪ ጓደኛ ነበርኩ፡፡ እንችም ልጅ ሁነሽ ታውቂኝ ነበር፡፡ እንጃ ታስታውሽኝ እንደሆን …” ኤፌ ተሳሰረብኝ፡፡

“አብርሃም ?እንዴት ነህ? እንዴ በሚገባ አስታውስሃለሁ እንጂ! የት ሄደ እያልኩ
ስጠይቅ ነበር? እንዴት ስልኬን አገኘኸው ኡፍፍፍ ቀለል አለኝ፡፡

“ታሪኩ ረዥም ነው …የምኖረው አዲስ አበባ ነው፡፡ አሁን ለሰዓል ከባለቤቴና ከልጄ ጋር መጥቸ ነው፡፡” አልኩ፡፡ ማግባትና መውለዴን የቀባጠርኩት እንድትረጋጋ ብዬ ነበር፡፡

“ እግዚእብሔር ይመሰገን …”ብላ ዝም አለች፡፡

“እንዲያው እንዴት መጠየቅ እንዳለብኝ አላውቅም፣ ግን ከቅዳሜ በፊት በአካል ባገኝሽና አይቸሽ ብመለስ ደስ ይለኝ ነበር፣ ይቻል ይሆን?”

በሚገባ ይቻላል… የምትመጣበትን ቀን ከነገርከኝ ጥበቃዎቹ ጋ የመግቢያ ካርድ
እተውልሃለሁ”

ኦ …ዛሬ ሰዓት ካለሽ፣ ከሰዓት መምጣት እችላለሁ?

አዎ ትችላለህ… እባከህ ና! ከስምንት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዐስር ሰዓት ባለው መምጣት ትችላለህ፣ ስትደርስ ስምህንና ከእኔ ጋር ቀጠሮ እንዳለህ ንገራቸው ውስጤ በደስታ፣በስጋት እና በማላውቀው ስሜት ተናወጠ፡፡ እንዲህ ይቀላል ብዬ አላሰብኩም
👍31
ነበር፡፡ኧረ ለመሆኑ ምንድነው የምላት? “ምን ልታዘዝ? ብትለኝ ምን እላለሁ? በቃ እንዲሁ ላይሽ ነው የመጣሁት እላለኋ፡፡ በፍጥነት ሮሐ ጋ ደርሼ አብረን ምሳ በልተን ወደ ቤት ተመለስኩ፡፡ ያረፈችው ቤተሰቦቿ ጋር ነበር፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
ትምህርትና_ዕውቀት

የተቀደደ ሱሪ ጣጥፈን ለብሰን፣

ያአባታችንን ያለቀ ካልሲ ወርሰን ፣

በዱቤ ዱቄት የላስቲክ ቦርሳ ፤ እርሳስና እስኪቢርቶ ፣ ደብተር ፣ 1 ከ 5
የተሰጠንን መጽሐፍ ይዘን...

ተምረን.........ተምረን

የPኢኮኖሚ ዋልታ ቡና ቡና ን ስንሰማ የልጅ ልባችን በ "ረፈደ" ፍራቻ እየመታ፤ በወፍ እግራችን በርረን፣

የዘበበኛ ጥፊ ቀምሰን ገብተን ፣
በአርፋጅ ቅጣት ውሳኔ እጅ በጆሮ ይዘን፣

በማስመሪያ ተገርፈን ፣

በተጣበቁ ትንንሽ ጣቶቻችን መሀል እስኪብርቶ ገብቶ አልቅሰን፣

ተምረን........ተምረን

ሽንት ለመሽናት አስፈቅደን ፣
ውሃ ለመጠጣት ለምነን ፣

ትምህርት ቤት የጓሮ አትክልት አልምተን፣

ለአስተማሪዎች 3፤ ተልከን ተላልከን፣

ተምረን.......ተምረን

“ጉልቤዎች” ያለችንን ቀምተውን፣
ጎርምሶች፣ “ወደድኩሽ” ብለው ጠፍጥፈውን፣
ወላጆቻችን በትምህርት ቤት ክፍያ ተማረውብን፣
የክረምት ትምህርት መማሪያ ገንዘብ አጥተን ቀርተን፣

ተምረን.......ተምረን

ውድ የልጅነት እንቅልፋችንን፣
እግራችንን ውሃ ውስጥ እየዘፈዘፍን አባርረን፣

ይህንንም ያንንም ሸምድደን፣

በመዳፋችኝ “አጤሬራ” ጽፈን

“ማትሪክ” ሲቃረብ ያለፈ አመታት “ሺቶችን፣ አገላብጠ፣

የማትሪክ ዕለት “ሸርተቴ” ይዞን ፣

ማትሪክ ወጣ ሲባል የወጣትነት ወኔያችን ክዶን ፣

ተምረን......ተምረን

ደግሞ በዩኒቨርሲቲ....
ወላጆቻቸንን በሬ አሽጠን ፣ መጽሐፍ ሳሙና ፣ ቅባትና ሞዴስ ለመግዛት
አባት እናታችንን በአውቶብስ አስኪደን ፣
በ “ኤ” ናፍቆት ተነገላተን ፣ በ“ኤፍ” ፍራቻ ተንቀጥቅጠን ፣
“የገና ማዕበል” እንዳይወስዶን ለስንቱ ታቦት ተስለን፣

የካፌ ምግብ እያቃረን በልተን ፣

ፕሮክተሮችን ሸሽተን፣

አስተማሪን እንደ እግዜር ፈርተን ፣

ተምረን........ተምረን

ሥራ ገባንና ፤

ቢሮ ገባና

"ይህን ሥሩ" ሲሉን ፣

ስንማር የኖርነው እኛ

የ"ቲዎሪ" ንጉሶች እኛ

ዕውቀት እንደ ቁምጣ አጠረን

🔘በሕይወት እምሻው🔘


ሼር እያደረጋቹ ቤተሰቦች ሼር...ሼር

አዘጋጅ፦ አቢ ፍቅር
‹‹አባይ ወንዝ አይደለም!›› አለ!

አባይ !
አልሰማም
አላይም
ባይ።
የጀግንነት የእምቢታ ምስክር
አባይ ሽፍታው ፣
አባይ ፋኖው ፣
አባይ ቆላው ፣
አባይ ደጋው ፣
አባይ ሜዳው አባይ ዱሩ ፤
ባደገበት ባይተዋሩ፤
አይቀመር የእድሜህ ሰገግ ፣
አይደበዝዝ የዘሩ ሀረግ፤
አይነጥፍ
አይታጠፍ፡ . . . ቃልኪዳኑ ፤
የነፍስ ኩራት . ሰመመኑ
ሰመመን ፤ .
ምታት- ደዌ - ሰቀቀኑ፡፡

አባይ ግገዝፈት - አይፈተን !
አባይ ወረት - አይዘገን ፤
አባይ የእምቢታ፣ የጀግንነት ማሰሪያ
አባይ የብቸኝነት፣ የመነጠል መጠሪያ!
የሀብታምነት ጣሪያ፣
የንፉግነት መስፈሪያ፤
መፎከሪያ ፤
መቆዘሚያ፡፡

አባይ ችኩል ተጓዥ፧
አባይ ነቃይ አጋዥ ፧
ከወለደው - ካደገበት፣ ማርፈደሸ ቢያምረው ፧
ባዶ ሆዱን ለዘፈነለት፣ ከወለደው - ካሳደገው
ደርቆ ልሳን ሳያጥረው፣ ውቅያኖስ ሳይሰለቅጠው ፤
ከዘመናት ግርጌ ላይ፣ በወገኖቹ ሸንጎ ቢታደም፣ በጉማ ልታረቅ ባለ፤
በሄድሮስ ‹‹የአባይ ስጦታ፦ ብሂል፣ ርእዩን የሰነከለ፤
በኤሊያድና ኦዲሴይ፣ በሆሜር የምናብ ማሳ፣ ህልሙን
ዘርቶ ያበቀለ፤
አባይ ወንዝ አይደለም አለ!

አባይ አይጨበጥ - መንፈስ ወረት፣
አባይ ግጥም- አባይ ተረት፤
አባይ ጨኸት
አባይ ቅዥት
አባይ ደራሽ
አባይ ገስጋሽ
አባይ ገንቢ
አባይ አፍራሽ፤
አባይ ተካይ፣
አባይ ነቃይ፡፡

የአፍሪካ የጥቁር መሬት ወንዞች አባት አይደክም፤
አያታክት ብርቱ ፤
ታሪክ - አይደለዝ ፍስቱ፤
ሀቅ - አይታክት ጩኸቱ ፤
ወላድ አምካኝ ስስቱ፤
በረሀ አልሚ ትሩፋቱ፡፡

አመት ቆጥሮ በክረምት ዶፍ፣ እንደመነቸከ ሸማ፣ ሀገር
እየዘፈዘፈ፧
ተራራና ሸንተረሩን፣ አሽቶ እያለቀስ፣ ጨምቆ እያራገፈ ፣
የሀገሬን ድንግል አፈር፣ ሰሀራ ላይ ቢያሰጣለት፤
እንደ ዱር ወፍ፣ ያለሐሳብ - ያስጭንቁ ቢመግበው ፧
ስስቱ የሰነከለው ፤
ያ ያልታደለ፤
አባይ ወንዝ አይደለም አለ!

አባይ -
ያጨለምኩትን ላብራ፣ የነቀልኩትን ላጽድቅ ባለ ፤
በሄረዶስ "አባይ ስጦታ"ብሂል ወደፊቱን የደለለ
በኢልያድ ኦዲሴይ ተረት፣ ርእዩ የማለለ ፤
አባይ ወንዝ አይደለም አለ!

አባይ የምናውቅህ የምታውቀን፤
ያሳደግንህ - የማትጦረን ፣
አባይ አብሮ አደጋችን . . .
የልጅነት - ተረታችን
የወጣትነት - ግጥማችን
የጉልምስናችን ፉከራ - የበስተርጅናችን ጸጸት፣
አይጨበጥ አይደርስ ስለት፡፡

አባይ የሰሀራ በረሀ፣ ስለት በረከት፤
የፈርኦን ተአምር፣ ከየት መጣ ምታት፣
የአልሲሲ የእንቅልፍ ልብ፣ ጭራቅ - ቅዠት፡፡

ወንድሜ ‹‹ወንዝ አይደለም›› ያልከው ፤
ከቀን ቅዠትህ ተፋትተህ፣ እስቲ አባይን ጠይቀው!
ማን አምጦ እንደወለደው ፤
ማን መግቦ ቅስም እንደሆነው፤
አባይ ይንገርኸ ጠይቀው፡፡

አዛውንትነቱን አይደለም፣ አስተዳደጉን ጠይቀው፤
እሱ ነው እውነቱ ያነቀህ ፣ እሱን ነው የዘነጋኸው ፤ ጠይቀው!
የወፌ ቆመች ጊዜውን፣ ዳዴ ያለበትን ደጃፍ፣
ማማ! ባባ!›› ያለበትን ፣ የተኮላተፈበትን አፍ ፤
አባይ የምናውቅህ የምታውቀን፤
ከቤትህ ውሉ ሳያድር፣ አረብኛ ሳታስለምደው፤
ቋንቋው ምን እንደነበር፣ አባይ እራሱን ጠይቀው።

ይነግርሀል . . .
የደንቢ መስክ የዶፍ ምጡ፣ ከጣና ማህጸን ገላግሎት፧
ከጎጃም እስከ ቤንሻንጉል፣ በለስ ግራውን ደግፎት፤
ከሻንቦ እስከ ጊንቢ፣ ባንኮ እስከ ነቀምት፣
ከቱሉ ወሊ እስከ አሶሳ፤
አልቦ እያጠባው ዲዴሳ ፤

የሱሉልታ - ገብረ ጉራቻ ፧
የንፋስ መውጫ - ቤተሆር፣
የመርጦ ለማርያም - የአርባ ፈሪ ተራራ፣ የቢሻሉ አይደርቅ
እምባ፤
የአልዲያ ተራራ ወዝ፣
የቦረንቲ ዙሪያ፣ የቦስ ቀርሳ፣ ተልተሌና ቀራሴ ጥንስስ፤
ከሁሉቃ እስከ ደቢስ.....
አይጻፍ አባይ ድርሳኑ፤
አይቀመር እድሜው ዘመነ፡፡
ድርሳኑ ከቋንቋ ይሰፋል፣
እድሜው ከዘመን ይተርፋል፡፡
ወንዝ ሆኖ አይታስር፣
ውሀ ሆኖ አይሰፈር ፤

አባይ ሀገር ነዉ መስፈሪያው፣ ነጻነት አቻ ትርጉሙ ፤
ከሰንደቅ ጋር ህመuው::

አባይ የሴም፣ የኩሽ የካም ህዝቦች ሙሾ፣ የእድሜ ሙሉ
ጸጸቱን፤
ለበደለው ለነቀለው፣ ቆንጥሮ ቢሰጥ ወረቱን፤
እድሜ ሙሉ የታወረ አይኑ በርቶ፣ ከወለዱ ካሳደገው - ካሳደገው፣
ልታረቅ ባለ፤
ለበደለው - ለነቀለው፣ ጸጸት - እምባውን ባካፈለ፤
ከወለደው - ካደገበት ማርፍድ ቢያምረው፤
ባዶ ሆዱን ለዘፈነለት፣ ደርቆ ልሳን ሳያጥረው፣
ውቅያኖስ ሳይሰለቅጠው፤
ከዘመናት ግርጌ ላይ፣ በወገኖቹ ሸንጎ ቢታደም፣ በጉማ
ልታረቅ ባለ፣
በሄድሮስ, የአባይ ስጦታ» ብሃል፣ ወደፊቱን የደለለ፣
በኤልያድ ኦዲሴይ ተረት፣ ርእዩ የማለለ፤
አባይ ወንዝ አይደለም አለ!

አባይ ሰንደቅ - አይታጠፍ፤
አባይ ጽናት - አይዛነፍ፣
አባይ የሀገር ህይወት - ታሪካችን፣
ይፈሳል፤
አይገሰስ ነጻነታችን፣
ይጸናል፡፡
አባይ ወረት፤
አባይ ኩራት፤
አባይ አፈር፣
አባይ ሀገር፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘


ሼሬ እያደረጋቹ ሼር -ሼር
👍3
#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

ኧረ ለመሆኑ ምንድነው የምላት? “ምን ልታዘዝ? ብትለኝ ምን እላለሁ? በቃ እንዲሁ ላይሽ ነው የመጣሁት እላለኋ፡፡ በፍጥነት ሮሐ ጋ ደርሼ አብረን ምሳ በልተን ወደ ቤት ተመለስኩ፡፡ ያረፈችው ቤተሰቦቿ ጋር ነበር፡፡

የቀጠሮዬ ሰዓት ሲደርስ ለባብሼ ወጣሁ፡፡ እዚያው ሰፈራችን ያለው የፈረንጆች ግቢ” በዋናው በር ዙሬ በትንሽ የመስተዋት መስኮት በኩል ለተቀመጠው የጥበቃ ሠራተኛ ስሜንና ቀጠሮ እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ የተወሰኑ ካርዶች ካገላበጠ በኋላ፣ ፈገግ ብሎ በሩን ከፈተልኝ፡፡ ግቢው እጅግ ሰፊና ውብ ነው፡፡ አትክልቶቹ ያስደምማሉ፡፡ ፀጥታው ሌላ
ሩቅ አገር እንጂ ተወልጄ ያደኩበት ሰፈር አልመስልህ አለኝ፡፡ ሰፈሬ ውስጥ የታጠረ
ገነት፡፡ ጥበቃው አንድ ልጅ እግር ሰራተኛ ጠርቶ “ወደ ሲስተር ሳሌም ቢሮ ውሰዳቸው አለው፡፡ ልጁ እየመራ ወደ አንድ የሚያምር የድሮ ሕንጻ ወሰደኝና፣ የሳሌምን በር ጠቆመኝ፡፡ በሩ ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ “ሲስተር ሳሌም የሚል ወርቃማ ጽሑፍ ተለጥፎበታል፡፡ አንኳኩቼ ስገባ ሳሌምና አንዲት በዕድሜ የገፉ ፈረንጅ መነኩሴ በፈገግታ ተቀበሉኝ፡፡ እርስ በእርሳቸው በማላውቀው ቋንቋ አውሩና፣ ሴትዮዋ ሰላምታ ሰጥተውን እየሳቁ ወጡ፡፡

አብርሃም!” አለች እየሳቀች፡፡ እጂን መጨበጥ እችላለሁ ወይስ እምነታቸው ይከለክል ይሆን? ተንደርድሬ ማቀፍና እንደ ልጅነቷ ወደ ላይ ማንሳት እችላለሁ ወይስ ነው ነው? እያልኩ ግራ ስጋባ እጇን ለሰላምታ ዘረጋችልኝ፡፡

“ሳሌም ይቅርታ ሲስተር ሳ…

ችግር የለውም ሳሌም በለኝ፡፡ እንዴት ነህ? ሎንግ ታይም' ኡ” አለችኝ ትክ ብላ
አየችኝ፡፡ ምን እንደምናገር ግራ ገብቶኝ እኔም አየኋት፡፡ ከዕድሜዋ በላይ ትልቅ ሰው መስላለች፡፡ የደፋችው የራስ መሸፈኛም እንደሆነ እንደዚያ እንድትመስል ያደረጋት እንጃ፡፡ እንድቀመጥ ጋበዘችኝ፡፡

ምቹው የእንግዳ መቀበያ ወንበር ላይ አረፍ አልኩ፡፡ ቢሮው ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ ነው:: ፊት ለፊቴ ተቀምጣ አንገቷን ሰበር እደረገችና

“ዩኒቨርስቲ መግባትህን ሰምቻለሁ ..ምን ተማርክ?” አለችኝ አወራሯ ረጋ ያለና እጅግ ትሕትና የተሞላበት ነበር፡፡

“ኢንጅነሪግ“

እግዚአብሔር ይመስገን አሁን እየሠራህ ያለኸው በዛው ዙሪያ ነው”

አዎ… አንድ የግል ድርጅት ውስጥ እየሠራሁ ነው፡፡ ይቅርታ እርሰዎ ነው የሚባለው አንች … ድፍረት እንዳይሆንብኝ አላወኩም” ፈገግ አለችና ችግር የለም፣ ዝም ብለህ አውራኝ…ለስላሳ፣ ውሃ አለ፤ ምን ትፈልጋለህ?”

“ውሃ ይሁንልኝ!” ጥግ ላይ ከቆመ ማቀዝቀዣ ለራሷም ለእኔም የታሸገ ውሃ አመጣች

ውሃዩን ተጎነጨሁና “ሁልጊዜ አስብሻለሁ
ወደ ውጭ አገር ሄዳለች የሚባል ነገር ሰምቼ ነበር.....

“እውነት ነው! አምስት ዓመት አካባቢ ጀርመን ነበርኩ” ምን እንደተማረች መጠየቅ ፈለግሁ፣ ግን ፈራሁ፡፡ እንደው ይኼ አስራ ሦስት ዓመት እንዴት አለፈ? እስቲ ንገሪኝ ማለት ፈለግሁ …ብቻ ብዙና የማያቋርጥ ነገር ልጠይቃት ፈልጌ ሁሉንም ነገር ተውኩትና፣ ለቅጽበት ዝም ተባብለን ቆየን፡፡ እንደምንም ራሴን እደፋፍሬ በቀጥታ እንዲህ እልኳት…
“ሳሌም! ምንም ነገር ተመልሼ ላስታውስሽ አልፈልግም ግን ሁልጊዜ እራሴን እንደወቀስኩና እንደተጸጸትኩ ነው፡፡ መቼም ስለኔና መሐሪ ታውቂያለሽ፣ ወንድሜ ማለት ነበር፤ የተፈጠረው ነገር ከተፈጠረ በኋላ፣ ለአሥራ ሦስት ዓመት ዓይኑን አላየሁትም፡፡ አፈርኩ፣ ዓይኑን ለማየት ተሳቀቅሁ! በየቀኑ ሳላስበው ውዬ አላውቅም፡፡ ግን በቃ፣ እንዴት ልበልሽ፣ የዛሬ አሥራ ሦስት ዓመት እንደታሰረ አካባቢ፣ እኔና ሮሐ ልናየው ሂደን የተፈጠረው ነገር ትንሽ የሚያሳፍር ነገር ነበር፣ መሐሪ እኔንም ሮሐንም ለሆነው ነገር ወቀሰን፡፡ የዚያን ቀን ምሽት ሮሐ መጠጥ ይዛ ነበር የመጣችው፣ እኔም
አትጠጣ አላልኩትም

“አውቃለሁ አብርሃም፣ አትጨነቅ፣ ሁሉም ነገር ይገባኛል”

“ታንኪው! ትንሽም ቢሆን ለተፈጠረው ነገር የእኔ ስህተት እለበት ብዬ ነው የማስበው፡፡የዚያን ምሽት እንዳይጠጣ ብከለከለው ኑሮ ወይም አብሬው ባድር ኖሮ ብቻ ብዙ ነገር ያሳቅቀኛል፡፡ ከዚያ በኋላም ብዙ ነገር እጠፋሁ፡፡ ቤተሰቦቹን ሄጄ ኤልጠየኳቸውም ጋሼ ሲያርፍ እንኳን ለቅሶ አልደረስኩም፡፡ በዚያ ላይ ስለ ሮሐ ልነግራት አስቤ አፌ ላይ አድርሼ ተውኩት፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ንስሐ አባቱ ፊት እንደቀረበ ሰው መናዘዝ
ጀመርኩ፡፡ ዝም ብላ ስታዳምጠኝ ቆይታ፣

ራስህን አትውቀስ፣ ማንም ሰው የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ ሕይወት መቼም ያለፈውን ለመቀየር ዕድል አትስጠንም፣ ወደፊት በተስፋ መጓዝ ብቻ ነው፡፡ መሐሪን በየሳምቱ ማረሚያ ቤት እየሄድኩ እጠይቀዋለሁ

ኧረ? እንዳላወቀ ሰው ለመሆን ሞከርኩ፤ ድራማው ተሳክቶልኝም እንደሆን እንጃ!

ዓዎ! በአንዳንድ ምክንያት ሰዎች እንደምጠይቀው እንዲያውቁ አልፈለኩም፡፡ ያው ይገባሃል መቼም፡፡ሁልጊዜ ስለ አንተ ያነሳልኛል፤መሐሪ ኤልተቀየመህም፤ እንደውም የእውነት ናፍቆሃል፣ ቢያይህ ደስ ይለዋል”

እውነት!?”

አንቺ በእምነትሽም ምክንያት ይሁን በተፈጥሮ፣ ነገሮችን የምትቋቋሚ ሆነሽ ይቅር አልሺው፣ ጋሽ ዝናቡ በተከበረበት አገር ተዋርዶ፣ እዝኖ፣ ራሱን ያጠፋው በማን ምክንያት ነው?..በመሐሪ ምክንያት ነው! ..አባቴ ማለት ነበር፣ አብሮ አሳድጎናል ድምጼ እየጨመረና እንባ እየተናነቀኝ ነበር፡፡

ሳሌም ዝም ብላ ስትመለከተኝ ቆዬች “መሐሪን ይቅር አላልኩትም፣ እንጃ ለዚያም የሚበቃ ልብ ያለኝ አይመስለኝም፡፡ መሐሪን የምጠይቀው፣ ከጎኑ የሆንኩት፣ ሌላው ይቅርና በራሴ ምርጫ እዚህ ለመሥራት መርጨ የተመለስኩትና በየቀኑ ከማስታውሰው
ሕመም ጋር እየታገልኩ የምኖረው ደግ ስለሆንኩ ይመስልሃል? ከአንተም ከሮሐም የተለየ መንፈሳዊ ከፍታ ላይ ስላለሁ ይመስልሃልን አይደለም! እውነታው መሐሪ ምንም ወንጀል የሌለበት ንጹህ ልጅ ስለሆነ …ካለ ሥራው ዕድሜ ልኩን በእስር ስለሟቀቀ ነው

“ተይ እንጂ! ምንም ወንጀል የለበትም?” አጉል ሃይማኖተኝነት መሰለኝ ተበሳጨሁ!

“አብርሃም! የዚያን ቀን ምሽት መሐሪ አልደፈረኝም” ፍጥጥ ብዬ እየኋት፡፡

የደፈረኝ ጋሽ ዝናቡ ነው

“ምን? …ምንድነው የምታወሪው ሳሌም”
“እውነቱን ማወቅ ከፈለክ ይኼው ነው! … መሐሪ የደረሰው በደም ተጨማልቄ ሰውዬው አፌን አፍኖ እንዳልናገር ሲዝትብኝ ነበር፡፡ አቅፎኝ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ አብሮኝ ሲያለቅስ፣ እስከዛሬ ዓይኔ ላይ አለ፡፡ ወዴት ሊወስደኝ እንደነበር እንጃ ብቻ ይዞኝ ከዚያ
ክፍል ሲወጣ፣ ኮሪደሩ ላይ ከእናቴ ጋር ተገጣጠሙ፤ እናቴን ሳይ ጮህኩ ኡኡ አልኩ፡፡ ያን ለታ ማታ የለበስኩት ነጭ ቀሚስ ከፊትም ከኋላም በደም ተጨመላልቆ ነበር የሆነው ሆነ”

“እና…"

“እንድም ሰው መሐሪ ደፈረኝ አላልኩም፡፡ መሐሪ ራሱ ነበር ላገኘው ሰው ሁሉ
እንደደፈረኝ ሲያወራ የነበረው:: ለአንተና ሮሐ፡ ፍርድ ቤትም ጭምር አመነ፡፡ ማንም

ሰው አባቱን አልጠረጠረም፡፡ መሐሪ የዚያን ክፉ ሰውዬ ክብር ለመጠበቅ ሲል ከምንም በላይ እናቱ ተሳቅቃ እንዳትሞት፣ እንዳትሰማ፣ ራሱን መስዋዕት አደረገ፡፡ እኔም ተንፍሼ አላውቅም፡፡ ከእኔና ከመሐሪ ቀጥሎ አንተ መስማትህ ነው፡፡ ሰውዬው ሥራው አሳዶት ራሱን አጠፋ መሐሪም ውድ የወጣትነት ዘመኑን በእስር ቤት አሳለፈ፡፡ ከፍ ካልኩ በኋላ
የዚያን ወንጀለኛ ሰውዬ ድርጊት ለመደበቁ ለረዥም ጊዜ አዝኜበት ነበር፡፡ ግን ደግሞ
ማሚ፣ የእኔም እናት ናት፡፡ ውርደቷ ውርደቴ ነው፡፡ መሐሪ ዕድሜውን፣ እኔም የታፈነ በደሌን ለማሚ አዋጥተን ጐዳቷን ለመቀነስ ሞከርን፡፡
👍1
ያሰብነውን ያህል ባይሳካም፣ ቢያንስ በሕይወት አለች፡፡ ሰውዬው ራሱ ላይ ፈርዷል፡፡ ሕዝቡም ሴት መድፈር ምን ዋጋ እንደሚያስከፍል በመሐሪ አይቷል፡፡ ምንም ይሁን፣ እኔ ላይ ያረፈው የሕይወት ጠባሳ አብሮኝ እስከ መቃብር ይወርዳል፡፡ አንድ ንጹህ ነፍስ ግን፣ በእስር ቤት እየማቀቀ ነው፡፡ ወንድሜ ነው ከጎዳና ያነሳኝ ነው፡፡ አንተም እሱም! ወንድሞቼ ናችሁ፡፡ ነፍሱ
ትወደኛለች፣ ታከብረኛለች፡፡ ፍቅርን ያየሁት በመሐሪ ነው፡፡ ያንን ያህል በደል ይቅር
የምልበት የተለየ ልብ የለኝም፡፡ ምክንያቴ እውነት ብቻ ነው እውነቱ ደግሞ መሐሪ
ንጹሕ ነው፡፡ ይቅር እንድትለው አይደለም የምጠይቅህ፣ ሂድና በሕይወቱ የሚያምነው አንድ ሰው ንጹሕነቱን እንዳመነ ንገረው፡፡ ሕዝብ ሲገፋህ ሲያገልህ ዞር ስትል ይረሰሃል፡፡
ራስህ የማትረሳቸው ሰዎች ፍቅር ነው ምንጊዜም የሚከተልህ፡፡መሐሪ ንጹሕ ነው በእጇ እንባዋን ጠረገች ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
‹‹ሙሴ በለኝ› ማለትህ፣

««ሙሴን በለኝ ማለትህ ፤
ድፍረትህ!

ምን ህሊናህ ቢራቆት፣ ትቆነጥረው መላ ባይኖርህ ፤
ምንስ ድንቁርና፣ ጠምዶ ቢያርስብህ ፣

‹‹ሙሴ›› መባል ይመርህ?!

የወነጀለኝ ጣትህ፣ ሊመራኝ ዘንግ ሊጨብጥ? ..

ሲቋምጥ?
ይቅር ድርጊቱ ፣
መመኘቱ፣
አያጎብጥህም?

እኔ ምልህ!
ሙሴን መሆን ባይሆንልህ ፣
እንደ በትሩ፤
ሲጥልህ መሰሪ። እባብ ፤
ሲያነሳህ የጽድቅ እርካብ፤
መሆን ያማረህ!
አንተ ማነህ?
ማንስ አለህ?

ሙሴ እኮ የፈጣሪው ፣ የአልፋ ኦሜጋ፣ ቃል
ማሰሪያ፤
የበጎነቱ ፣
የተአምራቱ፡ . . . .መስፈርያ፤
የፈጣሪው ምድራዊ ጣት፣
ምድርን እንደብርቱካን፣
ሲያሻው ልጦ፣. . . . . 'ሚያስፈራራበት፧
ሲያሻው ገምጦ፣ .... 'ሚቀጣበት፤
ሲያሻው ንቆ፣ . . . 'ሚያበሰብስበት ፤
ሙሌ እኮ የእግዜር ጣት!
.
ሲያሻው እንደጠገበ ህጻን፣
አስገስቶ ፤
ሲያሻው እንደተጫነ ወደል፣
አስፈስቶ፤
ሲያሻው ኮርኩሮ እያሳቀ፤
ሲያሻው ፣
ደንቁሎ ማስለቀሻው፡፡
ሙሴ እኮ የእግዜር ጣቱ ነው፡፡
አንተ መሴ መሆን ያማረህ ፤
የማን ጣት ማነህ?

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

አዘጋጅ፦አቢ ፍቅር
ከዕለታት_ግማሽ_ቀን


ክፍል_ሀያ_ሦስት(የመጨረሻ ክፍል)


በአሌክስ_አብርሃም

ከሳሌም ጋር እንደወጣሁ፣ ሰማይ ምድሩ ጨላልሞብኝ መንገድ ዳር ቆምኩ፡፡ ከዚያ
ያደረግሁት ነገር ቢኖር፣ ዓይኔን በጨው አጥቤ ወደነመሐሪ ቤት መሄድ ነበር፡፡ እግሬን ወደ ፈለገበት እንዲሄድ ሊፈቅድለት፣ እራሱ የወለደኝ ይመስለኛል፡፡ ከአሥራ ሦስት ዓመት በኋላ፣ ለዚህ ሁሉ ዝብርቅርቅ መነሻ ከሆነው ግቢ በር ላይ ቆምኩ፡፡

ትልቁ የግቢ በር ዝገት ወርሶታል፡፡ በመንገዱ በኩል ሲያልፉ ግቢው ውስጥ ይታዩ የነበሩት ትልልቅ ዛፎች የሉም፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ግርማ ሞገሱ ተገፏል፡፡ አንድ ዕድሜው ዐሥር ዓመት የሚሆን ልጅ በሩን ከከፈተ በኋላ፣ ትክ ብሎ እያየኝ፣
“ማነው? አለኝ! ከፍቶ ካየኝ በኋላ ነው “ማነው ያለኝ፡፡ ገና በኮቲዬ የምታወቀው ሰውዬ እየታየሁ እንኳን ማንነቴ ሲጠየቅ፣ ከዓመታቶቹ በላይ የገዘፈ ርቀቴ ዘልቆ ተሰማኝ፡፡ማነው አለኝ? ያው ማነህ ነው! እቅፍ አድርጌው እዚያው በር ላይ ተቀምጨ፣ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ላወራው ተመኘሁ፡፡ አብርሃም ነኝ ብለው ምን ይገበዋል?! አንተን ሳክል የእዚህ ግቢ ባለቤት ነበርኩ፣ ብለው ምን ይገባዋል?! ይኼንን በር አንድ ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ አስራ ዘጠኝ ጊዜ ከፍቼ ዘግቼዋለሁ ብለው ምን ይገባዋል?! ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ በር እንደወጣሁ ከልቤ የገባሁበት ሌላ በር የለም ብለው ምን ይገበዋል?!

“ማሚ አለች? አልኩት

“ማሚ ማናት? አለኝ፡ በመጨረሻው ዘመን ማሚን የማያውቅ ትውልድ ይነሳል አልኩ
ለራሴ!

እንዲህ ስንባባል ከውስጥ የማሚን ድምፅ ሰማሁ፡፡

ማነው?

“አንድ ሰውዬ ነው አለ ልጁ በሩን እንደያዘ፡፡ እዚሁ በር ላይ እንደቆምኩ በአስማት ከሕፃንነት ወደ ሰውዩነት የተቀየርኩ መሰለኝ ያውም ወደ አንድ ሰውዬነት በሂደት ሳይሆን በድንገት!

“ታዲያ በሩን ልቀቃ! ሰው በየት ይለፍ” አለችው፡፡ ልጁ ወደጎን ዘወር ሲልልኝ ራመድ ብየ ገባሁ፡፡ ማሚ በረንዳው ላይ ቁማ ባለማመን ትክ ብላ አየችኝ ኧረ በሞትኩት! ወየው! ወየው!' ብላ በሁለት እጆቿ ራሷን ይዛ ማልቀስ ጀመረች፡፡
አለቃቀሷ ምርር ያለ እና ድምፅ ያለው ነበር፡፡ ያሳለፈቻቸው የሰቆቃ ዓመታት ይኼን አለቃቀስ አሰልጥነዋት
መሆን አለበት እንጂ፣ ማሚ እንባዋን ሰው እንዳያየው የምትደብቅ፣ ወደ ውስጧ የምታለቅስ ሴት ነበረች፡፡ ወደ እኔ ለመምጣት መንገድ ጀመረች አቃታት፤ ልክ የመውደቅ ያህል ደረጃው ላይ ዘጭ ብላ ተቀምጣ ማልቀሷን ቀጠለች!

ሁሉም ነገር አርጅቷል፡፡ እነዚያ ውብ የአበባ መደቦች የሉም፡፡ መዓት የወፍ ጎጆ
ይንጠለጠልባቸው የነበሩት ግዙፍ ዛፎች የሉም፡፡ በግቢው ዙሪያ አጥሩን ተጠግቶ
የሚከራዩ ቤቶች ተሠርተዋል፡፡ ብዙ ሕፃናት ግቢው ውስጥ ይንጫጫሉ፡፡ የጋሽ ዝናቡ ተወዛዋዥ ወንበር ይቀመጥበት በነበረው ቦታ ላይ፣ የቤት ፍርስራሽ የሚመስል እንጨት ተከምሮበት ቁሽሽ ብሏል፡፡ ማሚ ጸጉሯን ሽበት ወርሶታል፡፡ እርጅና እንዲህ በፍጥነት
ከንዱን ያበረታበት ሰው አይቼ አላውቅም፡፡

ሻይ አፈላችልኝ፡፡ ብዙ ብዙ አወራን፡፡ በየመኻሉ እያለቀሰችም እየሳቀችም ብዙ
አወራን፡፡ ስለማግባቴና መውለደ መስማቷን እንስታ፣ እንኳን ደስ አለህ እለቸኝ፡፡ ማንን እንዳገባሁ እንዳወቀች ባውቅም፣ ምንም አላለችም፡፡ ስለመሐሪ ብቻ ውስጧ እንስፍስፍ እያለ እንዲህ አለችኝ አሳድጌዋለሁ ይኼ ልቤ አለች ደረቷን ልክ እንደ አልቃሽ እየደቃች ደም አይደለም መሐሪ ነው የሚፈስስበት፡፡ የልጅነት ሳቁ ነው በደም ስሬ የሚፈሰስው፡፡ መረጃ አምጭ ቢሉኝ፣ እናትነት መረጃ አይሆንም እንጂ፣ነፍሴ
እስካሁንም መሐሪ ያንን ቆሻሻ ነገር አያደርገውም ነው የምትለኝ፡፡ መቼም አቀደች እንዴ ራሱ ያመነውን? ትለኛለህ፤ አውቃለሁ አገር እብድ ብሎኝ ጨርሷል፤ ግን ነፍሴ አላደረገውም ትለኛለች፣ በሄድኩ ቁጥር እጠይቀዋለሁ “እዎ! ተሳስቻለሁ ማሚ" ይለኛል፡፡ እየው እንግዲህ እናትነት እንዲህ ነው፡፡ ልጇን ራሱን ከራሱ በላይ የማውቀው ይመሰል አላምነውም!” አለችና እንባዋን ጠራረገች፡፡

ሰዓት ስመለከት ከምሽቱ ወደ አራት ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡ ተሰናብቻት ልወጣ ስነሳ ድንገት የሆነ ነገር ትዝ እንዳላት ሁሉ፣ “ቆይማ ቆዬኝ ብላ ወደ ውስጥ ገባችና ትንሽ፣ ቆይታ የተጣጠፈ ጋቢ እንደ ሕፃን አቅፋ ተመለሰች፡፡

“ስትመረቅ አላገኘሁህ፣ ስታገባ እንኳን ደስ ያለህ አላልኩ፣ አብርሽዬ እንግዲህ ሞኝ እንደሰማ ነው ይባላል፣ ይኼን ጋቢ ያዝ! መቼስ እንደ እናት በውጉ በማረጉ
አላስመረኩህ፣ አልዳርኩህ! ያዝ ይኼውልህ፣ እሺ በለኝ መሐሪ ራሱ የሠራው ነው፤እንዴት ያለ ባለሙያ ሆኗል መሰለህ፡፡ እዚያ እጅ ሥራ ያስተምሯቸዋል፡፤ ይኼው የኔም
የጓደኛህም ስጦታ፡፡ ድንገት መጣህብኝ፤ ምናባቴ ልስጥህ ጋቢውን አሳቀፈችኝና እቅፍ አድርጋ ጉንጩን አገላብጣ ሳመችኝ፡፡ የአሳሳሟ ጥንካሬ ለእኔ ሥጋ የተከለለ መሐሪን ለማግኘት ቆዳዩን የመሰርሰር ዓይነት ነበር፡፡

ከአፌ ላወጣ የቻልኩት ብቸኛ ቃል “ማሚ ይቅርታ?” የሚል ነበር፡፡ በእጆቿ ትከሻዬን
መታ መታ እያደረገች ሂድ አስመሽሁብህ …ሃድ” አለችኝ፡፡ ትከሻዬን መታ መታ
ስታደርገኝ፣ ያች ዓመታትን እየቆጠረች የኖረች፡ የማትሰራ የእጅ ሰዓቷ ያረጀ የብረት ማሰሪያዋ ተቅጨለጨለ፡፡

ጋቢዩን አቅፌ በጨለማው ውስጥ እግሬን እየጎተትኩ ወደ ቤቴ ሳዘግም፣ ጋሽ እዳሙ ጋር ተገጣጠምን፡፡ በጨለማው ውስጥ እየተወላገደ ይለፈልፋል …ትንሽ ይሄድና ይቆማል፡፡ሲቆም ይለፈልፋል፡፡ ልክ አልፌው ልሄድ ስል አዬኝ፡፡ ድንገት ልፍለፋውን አቆመና ትንሽ እንደሄድኩ ጮክ ብሎ

“ያምባሰል ማር ቆራጭ ይወጣል በገመድ ብሎ ሲጀምር፣ ከሱ በጎላና ምርር ባለ ድምፅ ጮኸ ብዩ፣

አደራ ቢሰጡት ይበላል ወይ ዘመድ?” ብዩ ጨረስኩለት፡፡ ድምጺ አዲስ ሆኖባቸው ነው መሰል፡ መንገዱ ዳር ያለ ግቢ ውስጥ የነበሩ ውሾች መጮኽ ጀመሩ፡፡

ጋሽ አዳሙ ከኋላዬ

“ውሾቹ ጮኹ አለ፡፡

አለቀ

በሌላ ድርሰት እንገናኛለን ለዛሬው ጨረስኩ አስተያየት ስጡ ተመቻቹ ወይስ ደበራቹ አስተያየታችሁን እፈልጋለው።

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍41
አትሮኖስ pinned «ከዕለታት_ግማሽ_ቀን ፡ ፡ ክፍል_ሀያ_ሦስት(የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ በአሌክስ_አብርሃም ከሳሌም ጋር እንደወጣሁ፣ ሰማይ ምድሩ ጨላልሞብኝ መንገድ ዳር ቆምኩ፡፡ ከዚያ ያደረግሁት ነገር ቢኖር፣ ዓይኔን በጨው አጥቤ ወደነመሐሪ ቤት መሄድ ነበር፡፡ እግሬን ወደ ፈለገበት እንዲሄድ ሊፈቅድለት፣ እራሱ የወለደኝ ይመስለኛል፡፡ ከአሥራ ሦስት ዓመት በኋላ፣ ለዚህ ሁሉ ዝብርቅርቅ መነሻ ከሆነው ግቢ በር ላይ ቆምኩ፡፡…»
ባዶ_ቤት

ጊዜ
አይከሰስ
አይወቀስ....አናጺ፤
ሞትን እንደሳንቃ፣
መውጫ ገበኔ ላይ፣
ገጥሞብኝ ሲየረበቃ፤
እኔና እራሴ፣
ቢጠፋብን መውጫ፣
ህይወት እንደቅርጫ፣
መድበን፣
ጊዜን እንደ ግንደ ቆርቁር፣
ፈልፍለን፤
ባዶ ቤት፣ ቁጭ ብለን፤
አለን።

ይኸው እባዶ ቤት ...
የደረቀ አንቀልባ፣
የአሻንጉሊት ክምር፤
አልጋው ላይ፤
አልጋው ስር፡፡
የህጻናት ፎቶ፣
ግርግዳውን ሞልቶ፤
የመነፈግ ማጥንት፣
ማፍራትን፣
ማጣትን፣
ናፍቆትን፣
ስቃይን፤
አጫጭሶ የሚያጥን፡፡
ይኸው እባዶ ቤት፡፡

ይኸው እባዶ ቤት . . .
መቅደስ ተሳልሜ፤
ለሰጠኝ፣
ለነሳኝ፣
እግዜሩን ረገሜ፡፡
ደግሞ ለምናልባት ፤
ምን ይቀርብኛል!
ቢኖርም፣
ባይኖርም፣
ሳይሻል አይቀርም፡፡
ገብቼ ንስሀ፣
ለወዲያኛው ስቃይ
ወይም ደግሞ ሲሳይ፤
ይኸው እባዶ ቤት፡፡

ይኸው እባዶ ቤት .
እድሬን አፍርሼ፣
ቀብሬን ተካፍዬ፣
ከፈን እንደድውር፣
ጣቴ ላይ ጠቅልዬ ፧
ኤሊ ሆኜ ኖሬ፣
ቀንዳውጣ አክዬ፡፡
ይኸው እባዶ ቤት፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

ሌላኛውን የፍቅር ቻናል ይቀላቀሉ
የሚሸሹትን_አያውቁምና.......

ስለ ፍቅር የሰበኩኝ
ስብከታቸው አልጥም ቢለኝ ፥ አደረጉኝ ጠላታቸው
አላማኝን እየጠሉ
ስለ ፍቅር በመለፈፍ ፥ ይፀድቁ እንደው እንጃላቸው።
የሚሰብኩትን አያውቁምና ፥ የጠሉኝን ይቅር በላቸው።

ከብርሃን ፍጥነት ቢፈጥን
ያሰተኞች በራሪ ክንፍ ፥ ያ'ስመሳዮች ተጓዥ ቅልጥም
እውነት እንደው ያነቅፋል !
ከራስ መሸሽ አይቻልም ፥ ሰው ከ'ሊናው አያመልጥም።

ሰው ኮንኖ ፥ ሰው ባይፀድቅም
የቆመን ሰው ሰው ይጥላል ፥ ሰው ያነሳል ሰው ቢወድቅም
ይህን እውነት ስለማምን ፥ አልመካም ባለኝ አቅም
ሁሉን እኩል አቀርባለሁ ፥ ሰው ነኝና ሰው አልንቅም
“እውነት ምንድነው” ብዬ ፥ ሀሰተኛን አልጠይቅም።
የሚጠይቁትን አያውቁምና ፥ ይቅር በላቸው ባንተ አቅም።

የማይኖሩትን ለሚያወሩ ፥ የሚኖሩትን ለማያውቁ
ከራሳቸው እየሸሹ ፥ ህሊናቸው ላይ ለሚወድቁ
በመራራ ምላሳቸው ፥ ጣዕሜን ቀምሰው ለሚንቁ
ምላሳቸው ሲመርራቸው
እኔን ይቅርታ የሚሉኝ ፥ ከራሳቸው ሳይታረቁ
ይቅርታቸውን አልሻም!
ይቅር ማለት ትልቅነት ፥ እንደሆነ ልቤ ሲያውቀው
ቅድሚያ ከራስ መታረቅ ነው ፥ ከሁሉ ጋር ሚያስታርቀው
ይቅርታ ሚሉትን አያውቁምና ፥ ይቅር በላቸው ምታውቀው

ለአቅመ መታመን ሳይበቁ
ስለመታመን ሲያወሩ ፥ ለሚኖሩ አስመሳዮች
ለቤት ሰጥቼ በቀረብኩ
ጀርባዬን ለማጥናት ብለው ፥ ለተጣበቁኝ ተባዮች
ሲበሉኝ ይኖራሉ እንጂ
ለነሱ እንኳንስ እጄን ፥ ማከኪያ ጥፍሬን አልሰጥም
እስከዛው ደሜን ይምጠጡት
እውነቴ ካልተጋረደ ፥ ውሸቱ አይጋለጥም፡፡
የሚሸሹትን ይቅር በላቸው ፣ ሰው ከህሊናው አያመልጥም

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘

አዘጋጅ፦ አቢ ፍቅር
አዲስ አበባን አረንጓዴ የማድረግ ፕሮጀክት

በአንዱ ቀን አሪፍ ምሳ ተጋብዤ ነበር። የጋበዘኝ ፣ “ አዲስ አበባን፣ አረንጓዴ የማድረግ ዘመቻ” የሚል ትልቅ ፕሮጀክት ቀርጾ ፣ ከፍተኛ
ገንዘብ ለማግኘት ከተለያዩ ኤን ጂ ዎች” ሰነዱን እየበተነ ያለ ጓደኛዬ ነበር ።

የምሳው አላማ ቀድም ብሎ የሰጠኝን እቅዱን አንብቤ የተሰማኝ፣እንድነግርው ነበር ።
የሰው ግብዣ እየበላ በትክክል የሚሰማውን የሚናገር ሰው መኖሩን እንጃ ፤ ግን እኔ ልሞክር ሄድኩ ።

ምሳው ቤቱ ነበር። ገብቼ የተዘጋጀልኝን ግሩም ምግብ በልቼ አስተያየቴን ከሰጠሁት በኋላ እንዲህ ብዬ ጠየቅኩት ፣ “ዞላ፣ ገንዘቡን
ምናምኑን ተወው ... እውነት ይሄ ልትሠራው የምትፈልገው ነገር ነው...? ማለቴ ሕልምህ ነው...? አዲስ አበባ አረንጓዴ ሆና ማየት?

“ኦፍ ኮርስ! ምን ማለትሽ ነው? ከልጅነቴ ሳስበው የኖርኩት ነገር ነው! ገንዘቡ እኮ ስራውን፤ ለመስራት ስለሚያስፈልግ ነው እንጂ ፣ ብቸል
እያነሸዳንዱ መንገድ ዳር ዶማ ይዤ እየቆፈርኩ ዛፍ ስተክል ብውልና ባድር ደስታዬን አልችለውም!”

“የ...ስ! ይሄን ያህል! ሕይወት ፣ ከተማው እኮ ተቃጠለ! ተቃጠልን! ልጆቻችን ምን ሊሆኑ ነው? ”

“እሱስ ልክ ነህ : : እኛ ካባቶቻችን ከተከሉት ዛፍ በተአምር በተርፈው ተጠለልን። የኛዎቹስ ምን ይሁኑ?”

“ታዲያስ!”

“አይ... እኔማ እንዲያውም የገንዘብ ማግኛ አድርገሃት እንዳይሆን ብዬ ነው ። አለ አይደል... ቢዝነስ ነገር?”

ተይ እንጂ...! ዛት ኢዝ ኖት ፊር! ኢንቫይሮመንተሸ“ ከድሮም ፓሽኔ ነው አልኩሽ እኮ... ”

ጓደኛዬን በጥያቄዬ ያስቀየምኩት መስሎኝ፤ አፈርኩና ወሬ ቀይሬ ትንሽ ከተጨዋወትን በኃላ ወደ ቢሮ ለመመለስ ተነሳሁ ።

ባለ ሰፊ ግቢ ትልቅ ቪላ ቤቱን ለቀን ልንወጣ ስንል ሰፊውን ሳሎን ቃኘት አደረኩ። ሰፊው ሳሎን ሰፊ ጠረጴዛ መሃል የተለያየ ቀለም ያላቸው
አበቦች ተቀምጠዋ።

ፕላስቲክ ናቸው ፡ ፡

ከፊሉ የሳሎነ ግድግዳ በሀረግ ተሸፍኗል ።

ፕስቲክ ነው ።

ሳሎኑን ለቀን ፤ ወደ ኮሪደሩ ስንደርስ አንድ ዘምባባ በፕላስቲክ ማስቀመጫ ውስጥ ተቀምጧል፡ ፡

ፕካስቲክ ነው ።

ከሳላኑ ስንወጣ ሰፊውን ግቢ ቃኘት አደረግኩ ፡ : መሬቱ፥ እንዲት ስንዝር ሳይቀር ከዳር እስከ ዳር በሲሚንቶ ሊሾ ሙልጭ ተደርጎ ተለስኗል ።

ደነቀኝ ።

ከዚህ በላይ የደነቀኝ ግን ይሄ ነው ፤ የራሱ ግቢ ውስጥ አዲት ተክል ያላፀደቀው ጓደኛዬ አዲስ አበባ፣ ያህል ከተማ አረንጓዴ ለማድርግ
የጻፈውን ፕሮጀክቱን ተሯሩጦ በአንዱ ኤን ጂ ኦ አጸደቀ ።

🔘በሕይወት እምሻው🔘

አዘጋጅ፦ በአበባ
1
የ“ኮንደም” ታሪካዊ አመጣጥ

ጤና ላይ ስለምሰራ ብዙ ያልተለመዱ ሥልጠናዎችን የመውሰድ ዕድል ነበረኝ።
ዛሬ ደግሞ የኮንዶም ታሪካዊ አመጣጥ እየተማርኩ ነው ።

አስተማሪው ደስ ይላሉ ።

“ኮንዶም መጠቀም መቼ እንደተጀመር ታውቃታችሁ?" ብለው ጀመሩ።

“ኤች አይ ቪ እና የአባላዘር በሽታ ሲባዛ” አhች አንዷ ።

“መቼ? ነው ያልኩት ... በዚህ ጊዜ በይኝ ፡ : ” አስተማሪው የያዙትን
የኮንዶም ካርቶን እያወዛወዙ ጠቅቁ ።

“እንጃ... በዐሥራ ዘጠኝ ሰባዎቹ…?"

“ስለዚህ በአንቺ አቆጣጠር ኮንዶም ገና ሰላሳ ምናምን ዓመቱ ነው ማለት ነው? ”

ልጅቱ ዝም አለች።

“ኮንዶም በትንሹ የሰባት መቶ ዓመት ታሪክ አለው። ለዚያውም የተጻፈ ብቻ” ሲሉ ሁላችንም ተደናገጥ።:
እንዲያውም ፣ ከዐሥራ ሦስት ሺህ ዓመት በፊት የተሳለ የዋሻ ስዕል ፣ ላይ አንዱ ሰውዬ ኮንዶም ሲጠቀም የሚ ያሳይ ምስል ሁሉ ተገኝቷል።

አረ... የዋሻ ሰው! የዋሻ ሰው ኋካ ቀር ሲመስል ለካ በጊዜ ነቅቶ ኖሯል! ” ብዬ አጠገቤ ላለችው ጓደኛዬ ሹክ አልኩ ።

“አንቺ እሱን ትያለሽ ... ከመጠቀማቸው ... ሳያፍሩ ግድግዳ ካጋ ሲጠቀሙ የሚያሳይ ስዕል መሳላቸው” ስትለኝ ሣቄን አፌ ውስጥ ማስቀመጥ አቃተኝ።

አባባሏ የእትዬ ጉአይ እና ባለቤታቸውን፣ ታሪክ አስታወሰኝ ።

አባባሏ የአስራ ሶስት ሺህ አመት ባከጸጋውን ኮንዶም ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሙን የሰማሁትበት፤ አጋጣሚ አስታወሰኝ ።

ጩጩ ነበርኩ ።

ውጪ ከጓደኞቼ ጋር “ፔፕሲ” ስራገጥ ሳለሁ ፤ በዛን ጊዜ ዕድሜው ወደ 12 የሚገመተው የጎረቤታችኝ እትይ ጉአይ ልጅ ፣ “ወይኔ እማዬ ..
ወየው እማዬ! አይለመደኝም!” እያለ ሲያለቅ፣ ሰማን ።

በበራቸው አጮልቀን አየን።

ልጃቸው ዳንኤል፣ እህል ውሃ በማያሰኘው የባለቤታቸው ቀበቶ እየገረፉት ነበር።የቀበቶው የብርት ዘለበት ባለበት በኩል ያለርህራሄ
ይለጠልጡታል።

ዳንኤል ፣ “ እማዬ...! እማዬ ....! አይለመደኝም!” እያለ ይጯሀል።

ይለጠልጡታል : :

“ዛሬ ደግሞ ምን አድርጎ ይሆን?” ብዬ አሰብኩ : :

“ ከቀት አባህ ወሰድከው? ተናገር አሁን!”

“መሬት ላይ አግኝቼው ነው!”

“አንተ ቀጣፊ..... ዕየው እውነቷን ካልተናገርክ ይሄ ቀበቶ አንተ ላይ ነው የሚያስቀው ዛሬ...!

“መሬት ላይ ነው ያገኘሁት እማዬ...! እንባው ፊቱም ፣ መሬቱም ላይ ይዘንባል።

“አንተ... ቀጣፊ...!”

እሱ "መሬት አገኘሁ” ሲል ፣ እሳቸው ፣ “አንተ ቀጣፊ ” እያሉ ያለማቋረጥ ሲገርፉት፥ ከቆዩ በኋላ ፤ ከቡፌው መሳቢያ ነው የወሰድኩት ብሎ አመነ ።

መናገሩ ላይቀር ይህን ሁሉ ስቃይ መቀበሉ ገርመኝ ።

እትዬ ጉአይ በቃው ብለው ሳይሆን ፣ ደክሟቸው ይመስለኛል ትተውት ወደ ጓዳ ሲገቡ እናባውን፤ እያባበሰ ፤ እጆቹን እያፋተገ ፤ እግሩን፣እየጎተተ፤ ግን ለቅሶውን፣ አቁሞ ወደ እኛ መጣ ።

“ ዳኒ ምን አርገህ ነው?”

“ዳኒ ምን ሰርቀህ ነው?”

“ ዳኒ ምን በልተህ ነው?”

በጥያቄ አዋከብነው ።

”ኮንደም" ሰርቄ አለን።

ዳኒ “ኮንደም” ይበለው እንጂ ያኔ ነው “ኮንደም” የሚለውን፣ ቃል
ለመጀመርያ ጊዜ የሰማሁት ።

አጅሬ ፣ “ ኮንዶም ሰርቄ" ይበለን እንጂ የሰርቀው ነገር ምን እንደሆነ እናቱ ለአባቱ ፣ “ ኮንዶሙን ሰርቆ ሲጫወትበት አገኘሁት" ብለው ሲያወሩ
እስኪሰማ ድረስ አላወቀም ። እሱ የሰረቀ የመሰሀው አባቱና እናቱ ብቻ የሚመጫወቱበትን ፣ ሱቅ ፣ ለገና ለገና ዕለት ፤ ወይ ለልደት ለልደት
ዕለት የማይሽጥ ውድ ኛ መሆኑን ነበር የሚያውቀው

የተያዘው ኮንዶሙን እንደ ፊኛ ነፍቶ ከነ ዘርአይ ጋር ሲያባርር ነበር የያዘው እነ ዘርአይ ፣
“እንዴት የሚያምር ፊኛ ነው ... ” እያሉ
ሲቀኑበት ነበር : : እናቱ ጋማውን፣ ብለው እያክለበለቡ ቤት አስገብተው ልክ ያስገቡት ፤ የሰፈር ሕፃናት የዳኒን ግብዲያና አዲስ ፊኛ
ለመንካት መሰብሰብ ሲጀምሩ ነበር : :
ከዛ እናቱ ፣ “ኮንዶሙን፣ ከመሳቢያ ሰረቀ” ብለው ሲያወሩ ሰምቶ ፤ለሰፈሩ ልጆኝ በሙሉ፣ “እኛ ቤት ኮንደም አለ፡ : እኔም ሰርቄው ተገረፍኩ” እያለ ዜናውን፣ አሰራጨው ።

ሰፈሩ በ“ኮዳዶም” ወሬ በአንድ እግሩ ቆመ : :

እኛ ፣ “ ኮንደም ምንድነው?”

ከኛ ከፍ ያሉትና ፣ “ደረስን ደረስን" ፣ የሚሉት ልጆች ፣ እትዬ ጉአይና ጋሼ ለገሰ ኮንደም አላቸው”

የሰፈሩ አሽሟጣጭ ሴቶች ፣ “ጋሼ ለገሰ ሂያጅ ስለሆኑ ከሚስታቸው ጋር እንኳን ያለ ኮንዶም አያደርጉም... የሹፌር ነገር ይሄው ነው ፡ ፡
አይታመኑም እኮ”

የሰፈሩ ቄሶች ፣ አሁን እስቲ በባልና እና ሚስት መሃል ላስቲክ ጣልቃ ይገባል? አቤት! የመጨረሻው ዘመን እኮ ነው! ይሄው ... ምልክቱ ታየ!” እትዬ ጉአይ ፣ ልጃቸው ዳንኤል በጊዜው ብርቅና ሚስጥር የሆነውን ኮንደም ሰርቆ ፊኛ ብሎ ሲጫወትበት አግኝተው መግረፋቸው ፣
ከስርቆት ለማራቅ ነበር ።ግን ያላሰቡት ሌላ ጣጣ ተረፋቸው።

በዳኒ ወሬ መዛመት ፣ ስማቸው ከእትዬ ጉአይ ወደ “እትዬ ኮንደም” ተቀየረ

የቡና ቁርስ ሆኑ : :

እነሆ እኔና ጎደኞቼ ዛሬ ስለኳንደም ታሪካዊ አመጣጥ በብዙ ዶላር በተዘጋጀ ሴሚናር እንማራለን : :

አስተማሪው ቀጥለዋል : :

"ቅድም እንዳልኳችሁ ዛሬ የምናውቀው ኮንደም የድሮውን አይመስልም" የያዙትን የኮንዶም ካርቶን ፈትተው አንዱን አወጡና ጣታቸው ላይ እየለጠጡ ቀጠሉ : :

" እንግዲህ የጥንቶቹ ወንዶች የእንስሳት ቆዳን፣ እና ነጠላን መሰል ልብስ ደርብ አድርገው ወደ ስራ ይገቡ ነበር ፡ ፡

ሁላችንም ሳቅን።

“ ከዛ ደግሞ ከእንሰሳት ፊኛ እና አንጆት የሚሰራ ኮንዶም መጣ... እያለ እያለ ወደ 18ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ፣ ከጎማ የተሠሩ ኮንዶሞች እየተለመዱ መጡ ።
ሲሉ አጠገቤ የነበርው ልጅ ፣ “ ከጎማ...? እኮ ይሄ ጎማ ጎማ...? ከጎማ የተሰራ ኮንደም ተደርጎ... አይቆረፍድም ...? ማለት እንዴት... እንዴት ...
እዴት ይሆናል...?”

ሴቶቹ ለመሣቅም ፣ ለማፈርም መወሰን ሲያቅተን ፤ ወዳጆቹ እየጮሁ አጨበጨቡለት

ጭብጨባው ሳይበርድ አስተማሪያችን ፣ “ሰው ባለው ነው እንግዲህ በጊዜው የነበረው አማራጭ እሱ ነበር... ቢሆንም አንዳንዶቹ ፣
“አመመኝ ፣ አቆሰለኝ፣ ፣ 'የነገሩን ጣዕም አጠፋብኝ' ፣ 'በዚህስ ከማድረግ ባይደረግ ይቅር እያሉ የሚተውም ነበሩ ።ብለው መለሱ : :

ተምረን ስንጨርስ ፤ በመኪና ወደ ቢሮዬ እየተመለስኩ፣ ባለ ቡና ፣ ባለ ሙዝ ባለ ምናምን መዓዛ ኮንዶች” የሚለው፣ ቢልቦርድ አየሁና የዳኒን ታሪክ አሰብኩ ።

ኋላ ላይ ፣ “ለሕይወታቹሁ ዋጋ ስጡ” ተብሎ ኮንዶም ከሕፃናት ከረሜላ አጠገብ ተንጠልጥሎ በአደባባይ ሊቸረቸር ፤ በወግ አጥባቂ ማህበረሰብ መሀል በአዲስ ነገር ጀማሪነታቸው ዋጋ የከፈሉትን፤ ጎረቤቶቼን አሰብኩ ፡ ፡
ፋና ወጊነት በሚያስወጋበት ዘመን ፣ “ባከኮንዳም” የነበሩትን እትዬ ጉአይና ጋሽ ለገሰን አሰብኩ።

አለቀ

አዘጋጅ፦አቢ ፍቅር
ለአሟሟቴ_ድርሰት

አንበሳን ጥሎ ሚነሳ፣
የጥንት አቴና ግላዲያተር፤
እንደብስል መሀል ጥሬ አተር፣
በትውልድ አንዴ ነበር፡፡

የታሪክ ድርሳን ሲፈተሽ፣ ...
እንዳንቺ ሞቱን በፈገዝ የገደለ ፣
አንድም ስጋ ለባሽ የለ፡፡

ሞት በበረዶ ትንፋሹ፣ ካበደነው አካልሽ ላይ ፣
ከምርኮ አልጋሽ ሰማይ ፣
የጽናትሽ ጨረቃ ፣
በእጣ ሞቱ፡ ሲሳለቅ ፣ ድውያን ለፈውስ ሲያበቃ
ተአምራት አይቻለሁ፡፡
ድርሳኔ አደርግሻለሁ፡፡

ባንቺ ነው ፣ ሞትን ያወቅኩት ፤
ባንቺ ነው ፣ ሞትን የናቅኩት፣
የአሟሟቴ ድርሰት ነሽ፣ የመጨረሻው ተውኔቴ ፣
ከጨለማ ወደ ጭለማ፣ መሽጋገሪያ መስኮቱ፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

ታህሳስ 15፣ 2011 ፣ ሀዋሳ (ለሚሚ)


አዘገጅ፦አቢ ፍቅር

ሼሼሼር---እያደረጉ
እኔ እብድ ነኝ ?!?

ፀጉሬ ተቆጣጥሮ ተንጨባሮ
ገፄ ጠፍቶ መልኬ ጠቁሮ
ከሰውነት ተራ ወጥቼ ከስቼ
ተቀዳዳውና አድፈው ሸማዎቼ
ሲያዩኝ ቢያስተውሉኝ
ክብሬን ገፈው አቀለላኝ
እሾፉብኝ፤ እብድም ኣሉኝ፡፡
እኔ እብድ ነኝ ?!?
እብድ እምሰኝ፡፡
ፀጉሬ ቢንጨባረር
መች ኣቃተኝ ማበጠር?!
ተስተካክሉ ማሳጠር፡፡
እኔ ያጣሁት ማበጠሪያ
የሰው ስውነቱን ማንጠሪያ፡፡
ደግሞ እኮ ከሰውነት ተራ የወጣህ
እምበላው እምቀምሰው ስላጣሁ::
ያደፈም የተቀደደ መልበሴ መጫማቴ
ከእጄ በማጣቴ ብኩን ሆኜ በመቅረቴ፡፡
ዛዲያ
እኔ እብድ ነኝ?!?
እብድ እምሰኝ፡፡
በርግጥ ሥራ አልያዝኩም በመማሬ
ፍሬ አልባ ሆኗል ፊደልም መቁጠሬ፡፡
ያጋጣሚ ጉዳይ ተቸገርኩኝ ዛሬ፡፡
ዳሩ ግን የነገን ማን ያውቃል!?
ማጣትም ለማግኘት ቦታውን ይለቃል፡፡
ባይለቅም ግድ የለኝ
ለሚያየኝ እብድ ነኝ፡፡
ባገኝም ባላገኝ
ቢርበኝ ባይርበኝ
ቢቸረኝ ቢነፍገኝ
ወገን ግድ የለውም
ስም አይቸግረውም።
እብድ ነህ ይለኛል
እብድም ያሰኘኛል፡፡
እኔ እብድ ነኝ?!?
እብድ እምሰኝ፡፡
እብደቴ ሕመሜ
አንተነህ ወንድሜ
ሕመሜና እብደቴ
አንቺ ነሽ እህቴ፡፡
ሁላችሁም ናችሁ!!
ከመከራ ሳታወጡኝ ከሕመሜ ላትፈወሱኝ
ስሙን ስትሸልሙኝ ስሙን ስታውሱኝ
እርዳታ መስሏችሁ
እብድ ነህ አላችሁ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘

አዘጋጅ፦ አቢ ፍቅር