አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዞር_በል

ህመሜን ካልታመምክ
ችግሬ ካልገባክ
ውስጤን ካልተረዳህ
ዐይኔን ካላነበብክ
ኀዘን ደስተዬን አብረክ ካልተካፈልክ
ካልገባክ ችግሬ
እኔው ለኔ ልኑር
ዞር በል ከስሬ።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ምልክት

ያሁሉ ሽንገላ
የቃላት ድርድርህ
ውዳሴ ከምርህ
ከወዴት ተነነ
ከመቼ አለቀብህ ?
ከምን ደረሰብህ ?
ንገረኝ አንተ ሰው እስኪ ልጠይቅህ ?
ምን አገኘህና ጠፋብህ ተረቱ ?
ውዴ፣ ሆዴ አንጀቴ ሕይወቴ ማለቱ
በሁሉ መማረር ማንነትን መርሳት
በዋሉበት ማደር በብዙ መሳሳት
ደርሶ ቱግ ማለት በትንሽ ትልቁ
ምልክት ነው እንዴ የፍቅርህ ማለቁ ?
#እማማ_ዣ


#ክፍል_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

#ትንሽ_ወሰድ
ይኼን ሁሉ ውጣ ውረድ አሳልፌ ለእማማ ዣ የገዛሁትን ኦሞ “ይኼው” ስላቸው፣

“ምኑ!?” ይሉኛል ...ኦሞ ግዛ ብለው መላካቸውን ረስተውታል፡፡ አንዳንዴ እንዲ
“ልባቸውን ወሰድ የሚያደርገው ነገር አለ” እያለ የሰፈሩ ሰው ያማቸዋል፡፡ በእርግጥ
የመንደሩ ሰው እንደሚያወራው አይጋነን እንጂ አልፎ አልፎ ነገር ይረሳሉ። ይኼ ደግሞ ማንም ሰው ሊያጋጥመው የሚችል ነገር ነው። እኔ ራሴ ብዙ ነገር እረሳ የለ እንዴ?! ስንት ጊዜ ነው እናቴ የተጣደ ነገር ጠብቅ ብላኝ የረሳሁት? እዚያው እንደ አሻሮ ከስሎ፣ ቤቱ በጭስ ከታፈነ በኋላ አይደል እንዴ፣ ትዝ የሚለኝ?! …ማንም ሰው ይረሳል …ምን ሰው ብቻ …የሰፈራችን ትልልቅ ሰዎች ራሳቸው በሬዲዮ የድርቅና የወረርሽኝ ምናምን ዜና በሰሙ ቁጥር፣ ስንት ጊዜ ነው “ምነው እግዚሐር ኢትዮጵያን ረሰሃት!?” የሚሉት?! እንግዲህ እግዚሐርም ቢረሳ ይሆናላ፤ ያውም ስንት ሚሊየን ሕዝብ በየቀኑ ቤተክርስቲያን እየሄደ አትርሳኝ እያለው፤ ጎረቤቱ እማማ ዣ ላይ ለምን እንደሚያጋንነው
አይገባኝም! እማማ ዣ ሽቅርቅር! ባል ነበራቸው እየተባለ ይወራል፡፡ (ሽቅርቅር ቃሉ ስለሚገርመኝ አልረሳውም!) ታዲያ ያ ባላቸው ይኼን ሆንኩ ሳይል ድንገት ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ፡፡ መጀመሪያ አንዱ ዘራፊ ገድሎ ጥሎት ይሆናል ብለው ያላመለከቱበት ፖሊስ
ጣቢያ አልነበረም አሉ፡፡ ጎረቤቶቻችን ሲያወሩ ነው እንግዲህ የሰማሁት:: ብዙ ቀን ስለ እማማ ዣ ሲያወሩ ሰምቻቸዋለሁ የኛ ሰፈር ሰው ከሥጋ ቅርጫ ቀጥሎ የሚወደው ነገር፣ እማማ ን ማማት ይመስለኛል።
እናቴ እራሷ ታወራለች! በእርግጥ እናቴ ያወራችው እማማ ዣን ለማማት አልነበረም አልፎ አልፎ እቤታችን የምትመጣውን የአክስቴን ልጅ ስትመክር እንደ ምሳሌ ነው ያነሳቻቸው።የአክስቴ ልጅ ሔለን (ሳይሞቅ ፈላ ነው እናቴ የምትላት) አንድ ቅዳሜ ቀን እኛ ቤት አደርኩ ብላ፣ ሌላ ቦታ ማደሯ ታወቀ:: ከማን ጋር እንዳደረች ባላውቅም፣
ከእናቴ አወራር ግን፣ ከሆነ ወንድ ጋር አድራ መምጣቷን ጠርጥሪያለሁ.……. የዚያን ቀን እናቴ እማማ ዣን ምሳሌ አድርጋ ስትመክራት እንዲህ አለች “ይችን የኛን ጎረቤት ያንዣብን ታውቂያቸው የለም ?…. ይኼውልሽ እሳቸው እንዲህ ነካ አድርጓቸው የቀሩት በወንድ ነው…” ካለች በኋላ፣ እማማ ዣ ለባላቸው ያደረጉለትን ውለታ…ከአመድ አንስተው ሰው እንዳደረጉት፣ በሕልሙ እንኳን አይቶት የማያውቀውን ኑሮ እንዳሳዩት
ብዙ ብዙ ነገር እንዳደረጉለት አውርታ በቁጭት እንዲህ አለች…

“ያን ሁሉ አርገውለት፣ አፈር አይንካህ ብለውት አፈር ያስበላውና! ..ሌላ ሴት በላያቸው ላይ ወዶ፣ ባዶ ቤት አስታቅፏቸው ሄደ። የጠፋ ሰሞን ...እሳቸው ምን ሆነብኝ ብለው
ፊታቸውን እየነጩ በየፖሊስ ጣቢያው፣ በየሆስፒታሉ ሲዞሩ ከረሙ …ምን መዞር ብቻ፣ በየሜዳው ሞቶ የተገኘውን ዘመድ ያጣ የስንት ቀን ሬሳ እያገላበጡ ሲያዩ ከርመው በኋላ ባልሽ ተገኝቷል' ሲባሉ ከቤታቸው የጀመሩ እልልል… እያሉ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ! የምስራች ሰምተው በደስታ ፖሊስ ጣቢያ የደረሱት ሴትዮ፣ ሌላ መርዶ ጠበቃቸዋ!”

“ምን ሆነ? ሞተ?” አለች የአክስቴ ልጅ፡፡

“በምን ዕድሉ! …ባለጌ ይሞታል እንዴ?! …ፖሊሶቹ አርፈሽ ተቀመጭ! እሱ አንዲት ሴት ወዶ ጠቅልሎ ገብቶልሻል
አሏቸው እንጂ! እንግዲህ ያኔ እዛ ፖሊስ ጣቢያ ሲደነግጡ ያግኛቸው፣ አልያ የማንንም ሬሳ ሲያገላብጡ ሰይጣን ይስፈርባቸው እንጃ .. ይኼው ስንት ዘመን አይምሯቸው ተቃውሶባቸው ቀሩ!”
“ሚስኪን! ታዲያ ምናደረጉ?” አለች የአክስቴ ልጅ ማስቲካ እያላመጠች ስትናገር እንደ መሞላቀቅ ያደርጋታል!
“…ምን ያደርጋሉ ... እየፈነጠዙ የሄዱት ሴትዮ፣ የመንደሩን ዓይን ለማየት ተሸማቀው ጥፍር አክለው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፤ ቤታቸውን ዘግተው ከርመው በስንተኛው የባላቸውን ልብስ ነሽ፣ ፎቶ ነሽ፤ ሁልጊዜ የሚቀመጥበትን ሶፋ ሳይቀር፣ ከሌላው ሶፋ ነጥለው ግቢያቸው ውስጥ ከመሩና እሳት
ለቀቁበት ... ቤታቸውን ታውቂው የለም? …እሳቱ ያንን ረዥም ግንብ አልፎ ሲንቀለቀል ደመራ መሰለ ...

ከዚያ ወዲህ ወንድ የሚባል ነገር አታንሱብኝ አሉ፣ በቃ… ማንም አጠገባቸው ስለሌ ትንፍሽ ብሎ አያውቅም:: ይኼው ስንት ዘመናቸው እንደ ባህታዊ ቤታቸውን ዘግተው
ልብስ ሲለኩና ሲያወልቁ ...በየቀኑ ኦሞ እየገዙ ምኝታ ቤታቸውን ሲያጥቡ ይውላሉ...አንድ ቀን ምኝታ ቤታቸውን በኦሞ ሳያጥቡ ውለው አያውቁም!! እና ምን ልልሽ ነው
….ወንድ አምነሽ እማይሆን ነገር ውስጥ እንዲች ብለሽ እንዳትገቢ… እንኳን ባዶ እጅሽን እየተወዘወሽ ቤታቸው ሂደሽ ቀርቶ፤ ወንዶች ከየትም አንስተው ወርቅ ላይ ቢያስተኟቸው፣ ልባቸው የማያርፍ ሰላቢዎች ናቸው ..” አለች።

የመጨረሻዋ ስድብ አባቴ ላይ ያነጣጠረች መሆኗን ከልምድ አውቃታለሁ..እናቴ “ሰላቢ” የሚል ቃል የምትጠቀመው፣ እኔን በወለደች በሁለት ዓመቷ የፈታትን አባቴን ስታነሳ ነው፡፡ ለፍቻቸው ዋናው መንሥኤ የአባቴ ቤተሰቦች “ልጁ ምኑም ምኑም አንተን
አይመስልም” ብለውት ነው አሉ፤ ታዲያ የአባቴን ፎቶ ባየሁ ቁጥር እንኳንም እሱን
ያልመሰልኩ እላለሁ፡፡ ..ሰው ልጄ እንደኔ መልከ ጥፉ ካልሆነ ብሎ እንዴት ሚስቱን
ይፈታል?!

ይህ የእማማ ዣ ታሪክ እኔን እንባዬ እስኪመጣ አሳዘነኝ እንጂ ላክስቴ ልጅ እንደሆነ ምንም አልጠቀማት፡፤ እንደ ቆንጆ የሬዲዮ ትረካ ማስቲካዋን እያላመጠች ይኼን ሁሉ የክህደት ታሪክ በኮመኮመች ልክ በአስራ አምስተኛው ቀን፣ ከአንድ ጉጉት ከመሰለ ልጅ
ጋር (እናቴ ናት ያለችው) ተያይዛ ጠፋች፡፡ እንዲያውም አብረው መኖር መጀመራቸውን ለእናቴ ደውላ ነገረቻት:: አክስቴ በሷ ምክንያት ታማ ስንት ወር ጠበል ለጠበል ዞራለች፡፡ በዓመቱ የአክስቴ ልጅ ሔለን ፊቷ አባብጦ፣ የግራ ክንዷ ተሰብሮ፣ ወደ ጤና ጣቢያ
የምትመጣ ይመስል እየተንከረፈፈች እቤታችን መጣች፡፡ “በትንሽ ትልቁ መቅናት ነው! መደብደብ! ..ነጋ ጠባ በጥፊ ጆሮ ግንዴን እየጠረቀመኝ፣ ይኼው የቀኝ ጆሮዬን ያዝ ያደርገኝ ጀምሯል ...” ብላ ተነፋረቀች፡፡

እናቴ ታዲያ እሱ እንኳ ድሮም ጆሮሽ ምክር አይሰማ! ዋናው ነገር እንኳን ነፍስሽ ተረፈ" ብላ ተቀበለቻት። ምስኪን የአክስቴ ልጅ! እንደማማ ዣ አቃጥላ እልኋን የምትወጣበት ልብስ እንኳን ሳይሰጣት፣ ተከትላው የሄደችው ወንድ ቀጥቅጦ ቀጥቅጦ መለመላዋን አባረራት፡፡ እናቴም ለወንዶች ባላት ጥላቻ ላይ፣ የአንድ ሰላቢ ወንድ ታሪክ ተጨመረላት። ታዲያ አንዳንዴ፣ ከአክስቴ ጋር እያወሩ እናቴ፣ “ያ! ሰላቢ…” ስትል
“የትኛው?” ትላታለች አክስቴ! አክስቴም ትንሽ ወሰድ ያደርጋታል!

#ከፈረሱ_አፍ
አንዳንዴ፣ “ይኼን የእማማ ዣ ታሪክ፣ እናቴ የአክስቴን ልጅ ለማስፈራራት የፈጠረችው ቢሆንስ!?” እያልኩ መጠራጠሬ አልቀረም! በእርግጥ የኦሞው ታሪክ እውነት ነበር፡፡በየቀኑ ከሱቅ የምገዛው እኔ ራሴ ስለነበርኩ ለዚህ ምስክር ነኝ፡፡ የተጠራጠርኩት
በባላቸው አጠፋፍ ላይ ነበር፤ምክንያቱም ከብዙ ጊዜ በኋላ ራሳቸው እማማ ዣ ፈፅሞ እናቴ ካወራችው የተለየ ታሪክ ሲያወሩ ስለሰማሁ ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮ እናቴም ሆነች እማማ ዣ፣ አልያም ጎረቤቱ የሚስማሙበት ነገር ሴትዮዋ ባላቸው ሄደ መጣ፣ ምንም ኤልጎደለባቸውም! እራሳቸውም “እኔ ያንዣቡ ምን ጎደለብኝ… ባቄላ አለቀ ..ምን ቀለለ አሉ!” እያሉ ከፍ ባለ ኩራት ይናገራሉ.ኩራትን መቸም እሳቸው ይኩሯት!

አንድ እሁድ ቀን ታዲያ እማማ ዣ ታጥቦ የተከመረ ልብስ እያዘጋጁ፣ እግረ መንገዳቸውን ብዙ ጊዜ ጀምረው
1
ያቋረጡትን የአባባ ጃንሆይን ታሪክ ያወሩልኛል፡፡እኔም ከሥር ከሥራቸው እየተከተልኩ አዳምጣለሁ፡፡ እያወሩ እየተከተልኳቸው፣ ኦሞ-ኦሞ ወደሚሸተው መኝታ ክፍላቸው ተከታትለን ገባን፡፡ በወሬው መሃል የታጠፈ ልብስ
ሊያስገቡ በልብስ ከተሞላው ትልቅ የድሮ ቁምሣጥናቸው ጋር ሲታገሉ፣ ድንገት
ከላይኛው መደርደሪያ፣ ከልብሶቹ መሃል የሆነ ነገር ዱብ ብሎ ወደቀ፡፡ በብርማ የብረት ክፈፍ የተከበበ፣ የእንቁላል ቅርጽ ያለው፣ ባለ ጥቁርና ነጭ ጉርድ ፎቶ ግራፍ ነበር፤ የሆነ ጎፈሬ ሰውዬ ፎቶ፡፡ እማማ ዣ ቤት ሥዕልም ይሁን ፎቶ የሚባል ነገር ለምልክት እንኳ ስላልነበረ፣ እንደ ተአምር ከሰማይ የወረደ ነበር የመሰለኝ፡፡የተሸከሙትን ልብስ አልጋቸው ላይ ወርውረው ፎቶውን ሊያነሱ ሲደነባበሩ፣ ቀድሚያቸው አፈፍ አድርጌ
እንዳነሳሁት፣ ከእጄ ነጥቀው ቁም ሣጥኑ ውስጥ፣ ልብስ መኻል ፈልፍለው ቀበሩና
ያጣጠፉትን ልብስ ሁሉ ሳያስገቡ ቁም ሣጥኑን ቆለፉት፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
አትሮኖስ pinned «#እማማ_ዣ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም #ትንሽ_ወሰድ ይኼን ሁሉ ውጣ ውረድ አሳልፌ ለእማማ ዣ የገዛሁትን ኦሞ “ይኼው” ስላቸው፣ “ምኑ!?” ይሉኛል ...ኦሞ ግዛ ብለው መላካቸውን ረስተውታል፡፡ አንዳንዴ እንዲ “ልባቸውን ወሰድ የሚያደርገው ነገር አለ” እያለ የሰፈሩ ሰው ያማቸዋል፡፡ በእርግጥ የመንደሩ ሰው እንደሚያወራው አይጋነን እንጂ አልፎ አልፎ ነገር ይረሳሉ። ይኼ ደግሞ ማንም…»
#ሌላ_ቀን

ሲከፋህ እልል በል
ስታዝን ተጽናና
ስትወድቅ ተፍጨርጨር
ለመነሳት ሞክር
ነገን በሌላ አስብ
ከራስህ ጋር ምከር
ይሄንን ሳታደርግ
ፋይል ዶሴ ከፍተህ
ለአለዎ ካስነበብካት
የቆምኩበት መንገድ
ፍጻሜ ነው ካልካት
ያን ጊዜ አበቃልህ
ደስታዋን አበስርካት
ዋጋ ቢስ መሆንክን
ራስህ ነገርካት
ይልቅስ ቀና ስል
ቀን አለ በልና
ወድቀው የተነሱትን
ፈርጦች አስብና
ያኔ ነው ዓለምን
ረግጠህ የምትጥላት
በራስህ ዛቢያ ሥር ምታሽከረክራት፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#እማማ_ዣ


#ክፍል_ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም

አልጋቸው ላይ ወርውረው ፎቶውን ሊያነሱ ሲደነባበሩ፣ ቀድሚያቸው አፈፍ እንዳነሳሁት፣ ከእጄ ነጥቀው ቁም ሣጥኑ ውስጥ፣ ልብስ መኻል ፈልፍለው ቀብሩና
ያጣጠፉትን ልብስ ሁሉ ሳያስገቡ ቁም ሣጥኑን ቆለፉት፡፡
“የማነው ፎቶ?” አልኳቸው፡፡

“የማነው ፎቶ?” አልኳቸው፡፡

“የቱ?”
ቁምሣጥኑ ውስጥ ያስገቡት ፎቶዎ

“እ…እሱማ የሞተው አጎቴ ነው” ብለው ኮስተር አሉ!

“ምን ሁኖ ነው የሞተው?”

“አላርፍ ብሎ!……ምን የመሰለ የንጉሥ ፈረሱን እቤት አስሮ፣ አንዲት በቅሎ ሲጋልብ ይዛው ገደል ገባች ..በቅሎ ታቃለህ?!” ብለው ጠየቁኝና መልሴንም ሳይጠብቁ፣
“…ተያይዘው አመድ ሆኑ! አጥንታቸውም አልተገኘ፤ አመድ ነፋስ አበነናቸው…ብን…! ብለው በአራት ጣታቸው የታችኛውን ከንፈራቸውን ከታች ወደላይ መንጨር አደረጉት!
“አጥንታቸውና አመዳቸው ካልተገኘ …አጎትዎትና ፈረሳቸው መሞታቸውን በምን
አወቁ?”

“ፈረስ አላልኩም… እያጣራህ አእድምጥ ..በቅሎ .…”

“እኮ ...በቅሎ .……..

በረዥሙ ተንፍሰው ዝም አሉ:: የሚሠሩት ግራ እንደገባቸው ዓይነት፣ ፀጉራቸውን እንደ ማከክ እያደረጉ መኝታ ቤታቸውን ኮስተር ብለው ዙሪያውን ቃኙትና፣ በረዥሙ ተንፍሰው ከዚያ በፊት ሲያወሩኝ የነበረውን የአባባ ጃንሆይንም ወሬ ሳይጨርሱልኝ “አቡቹ .እራሴን አመም አርጎኛል ጋደም ልበል ሂድ” ብለው ወደ አልጋቸው ሄዱ፡፡

እኔም የጓጓሁለት ታሪክ በመቋረጡ ቅር እያለኝ ወደ ቤቴ አዘገምኩ። ሁለት ቀን ሙሉ ጠርተው ኦሞ ግዛ ሳይሉኝ፣ ጎረቤትም ቡና ሲጠራቸው ሳይሄዱ፣ ቤታቸውን ዘግተው ጠፉ “ተነሳባቸው” ተባለ፡፡በሦስተኛው ቀን ግን፣ በሐበሻ ቀሚስ ሽክ ብለው ዘንጠው፡ የወርቅ አምባርና ሐብላቸውን ከትልልቅ የጆሮ ጉትቻ ጋር እያንቦገቦጉ ብቅ አሉ፡፡ የሆነ
ቦታ ሊሄዱ መስሎኝ ነበር …ግን እንደዚያ ዘንጠው የትም አልሄዱ… ዝም ብለው
ይወጡና፡ የግቢውን የብረት በር ገርበብ አድርገው፣ ዙሪያውን ቃኝተው መልሰው
ይገባሉ፡፡ እሴታቸው ይገቡና ተመልሰው ይወጣሉ፡፡ በመጨረሻ ቀጥ ብለው እኛ ቤት መጡ፡፡ እናቴን ሰላምም ሳይሏት እስቲ ቆንጆ ቡና አፍሊ አቡቹ ናማ ቡና ግዛ” ብለው ከምታምር ቦርሳቸው ውስጥ ድፍን አምስት ብር አውጥተው ሰጡኝ:ወደ ዘመናይ ሱቅ በረርኩ፡፡

“አቡቹ ነፍሴ -ማታ የገባ የጅማ ቡና አለ - ብላ በዜማ አቦል ጀባ ብላ ቡናዎን
ብቀምሰው፣ እግሬ ወደ ጅማ ሱስ አመላለሰው ካካካካ” ስትዘፍን ድምጿ ያምራል፡፡

#ዳቦና\ሻይን_ተገን_በማድረግ
የእኔ ይለይ እንጂ፤ እማማ ያንዣቡን የመንደሩ ልጆች ሁሉ እንደ ነፍሳችን ነው
የምንወዳቸው፡፡ ቤታቸው ሻይ እይጠፋም፡፡ ልከውን ስንመለስ ዳቦ በሻይ የማይቀር ሐቃችን ነበር እስካሁንም ድረስ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 'ተላላኪ' የሚባሉ ሰዎች ደመወዛቸው ዳቦ በሻይ የሚመስለኝ ለዚያ ነው መሰል፡፡ ያኔ በሬዲዮ ተላላኪዎች አገር ለማፍረስ …ምናምን ሲባል ምናይነት አገር ናት በዳቦና በሻይ የምትፈርሰ እያልኩ አስብ
ነበር! እማማ ዣ ምንም እንኳን አፈ ታሪክ ከሚመስል ታሪካቸው ጋር በብቸኝነት ይኑሩ እንጂ፣ ኩራታቸው እና ለራሳቸው ያላቸው ከብር፡ በድፍን መንደሩ የታወቀላቸው ሴት ናቸው።

ሳውቃቸው ጀምሮ ቋሚ ሠራተኛ እንኳን ኖሯቸው አያውቅም። ከበድ ያለ ሥራ
ሲገጥማቸው፣ የቀን ሠራተኛ ቀጥረው ያሠራሉ፣ ዘመድ ጓደኛ የሚባል ነገር እቤታቸው ሲመጣ አላይም። እንደዚያም ሆኖ “ተነሰቶባቸዋልያ ከሚባሉባቸው እና ቤታቸውን ዘጋግተው ከሚቀመጡባቸው ቀናት ዉጭ ትልቁ የግቢያቸው በር ከጧት ጀምሮ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት እንዲሁ ከመዘጋት ውጭ ተቆልፎ አያውቅም፡፡ ብዙ ጊዜ እናቴ በራቸውን እንዲቆልፉ ትመክራቸዋለች…

እንዱ ይኼን ወርቅሁን ያየ ሌባ ዘሎ ይገባብኋል ያንዣብ” እያለች፡፡

አይ አንች…ሌባው ገብቶ ከወጣ ወዲያ…” ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርስ አንጠልጥለው ይተውታል

ሌላ ጊዜ መኝታ ቤታቸውን እያጠቡ ድክም ብሏቸው፣ እናቴ አገኘቻቸውና “ያንዣብ እንደው አንዲት ልጅ እግር የዘመድም ልጅ ብትሆን ለምን አታስመጡም? …ማነጋገሩም ቢሆን ቀላል ነው እንዴ!?” አለቻቸው፡፡

“ኤዲያ! ..እኔ ያንዣቡ የማንንም መገረናም አምጥቼ እሷን ላንዘፋዝፍ እንዴ? …ጥጋብ አይችሉም ልጄ ..ገና የተረከዛቸው ንቃቃት ሳይገጥም፣ አፋቸውን ይከፍታሉ ..ምን ዘመድ አለ? የጨዋው ልጅ ሁሉ አልቆ!” ብለው በማናናቅ እጃቸውን አወናጨፉት!

ሲያጥቡና ሲያስተካክሉ የሚውሉት ያበሻ ቀሚሳቸው ሲቆጠር አያልቅም፡፡ በወርቃማ ክር የተጠለፈ ጥቁር ካባ ሳይቀር ቁምሳጥናቸው ውስጥ አይቻለሁ፡፡ ሲለብሱት ግን አይቻቸው አላውቅም:: የአንገታቸው የወርቅ ሐብል ከነጉባጉቡ ልብ ያስደነግጣል፡፡
የጆሯቸውን ወርቅ አድርገውት ሲወጡ፣ ጆሮዋቸው ላይ የበቀለ የኮረዳ ጡት ነው
የሚያክለው! በተለይ ጉዳይ ኑሯቸው ወጣ ያሉ ቀን፣ ቀይ ገላቸው ላይ የወርቅ
ጌጣጌጣቸው ለጉድ ይንቦገቦጋል፡፡ ብዙ ጊዜ የሚወጡት የቤት ኪራይ ለመቀበል ነው፡፡አውቶብስ መናኸሪያው አካባቢ የሚከራይ አራት የግንብ ሱቅ አላቸው ይባላል።
መተዳደሪያቸው የሱቆቹ ኪራይ ሳይሆን አይቀርም።

ሀብታም ናቸው፤ ግን ያሳዝኑኛል:: ኩራታቸውና ሥነ-ሥርዓታቸው ቤተ-መንግሥት እንደምትኖር ልዕልት ዓይነት ነበር፡፡ ቢሆኑም ጎዳና ላይ እንደምትኖር አቅመ ቢስ እናት ውስጤ ይንሰፈሰፋል…የሚልስ የሚቀምሰው ያጣ ደሃ እንኳን እንደሳቸው አንጄቴን አይበላውም:: እናቴን ጨምሮ ጎረቤቱ ሁሉ ለዚያች ለሚሰጡኝ ሻይና ዳቦ ስል፣ ከሥር ከሥራቸው የምሮጥ ይመስላቸዋል፡፡ እንደማማ ዣ አይሁን እንጂ እኔም ኩሩ ነኝ፡፡
ማንም ቤት ብሞት ቁራሽ ቀምሸ አላውቅም! “የያንዣቡን ሞሰብ ለምዶ!” ይሉኛል፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
1
#ሠርጌ

እምቢልታው ይነፋ ከበሮ ይመታ
ይጨፈር ዳንኪራ
ይድመቅ ቤቴ ይድራ
ይምጣ ዘመድ አዝማድ
ይሰብሰብ አጃቢ
በሉኝ ሙሽራዬ የወይን አበባዬ
ብሩህ አርጉት ቀኔን በእልልታ በሆታ
ያኔ ነው ሠርጌ
እኔ የሞትኩ ለታ፡፡
#የሴት_ልጅ

የሴት ልጅ ይለኛል ያዋረደኝ መስሎት
ስድብ እና ሙገሳ መለየት ተስኖት
አው የሴት ልጅ ነኝ ያውም የጀግናዋ
ጉንበስ ቀና ብላ ለልጅዋ ኗሪዋ
ዘጠኝ ወር ሳልከፍል በሆድዋ ተኝቼ
በጀርባዋ አዝላኝ እሰክሄድ በእግሮቼ
ተደፍታ ስታነድ ምግቡን ለማብሰል
እንጀራ ስትጋግር ፊትዋ መስሎ ከሰል
ሳጠፋ ገስፃ እንዳልኩራ መክራ
በርታ እያለችኝ ሁሌም እንዳልፈራ
አይዞህ አልከፋም ሴት ያሳደገኝ ነኝ
ስድብ ከመሰለህ ደጋግመህ ስደበኝ
አልቀየምህም በስምዋ ስትጠራኝ
እውነቱን ልንገርህ አዎ የሴት ልጅ ነኝ

"መታሰቢያነቱ እናቱን ለሚወድ በሙሉ።"

🔘ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን🔘
#የሴትነት_ክብር

ከእውነታው ድግስ በሀቅ እንዲታደም
ከሴቶች ቀን በፊት ሴትን ማክበር ይቅደም።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
#እማማ_ዣ


#ክፍል_አራት


#በአሌክስ_አብርሃም

ከእኛ ቀይ ወጥ የእማማ "ዣ" ሻይ እና ዳቦ በለጠበት ማለት መሸነፍ መስሏቸው ነው እንጂ፣ እማማ "ዣ" ቤት ከሻይ እና ዳቦ በስተቀር ሌላ ነገር ቀምሸ አላውቅም! ሻይ እና ዳቦ የሌለበት ቤት አለ? ከፈለግ እቤቴ ለማኅበርተኛ ጠላ በሚቀዳበት ማንቆርቆሪያ ሙሉ
አፍልቼ ስጠጣ መዋል እችላለሁ! እውነቴን ነው! እናቴ በሌላ ሌላው ነገር ነጭናጫ ትሁን እንጂ ለሚበላና ለሚጠጣ ነገር፣ እያፈስኩ ብበትነው ግድ የሚሰጣት ሴት አይደለችም። ሻይ በዳቦን ተገን ያደረገ ለራሴም የማይገባኝ ሐዘን ነብሴን በረዥም ክር አስሮ ወደዚያ ግቢ ይስባታል፡፡

እማማ ዣም ይኼን ባህሪዬን ሳያውቁት አይቀሩም፡፡ የሆነ ጊዜ ታመው ማታ አብሪያቸው አምሽቼ ወደ ቤቴ ተመለስኩና፣ በቀጣዩ ቀን በጧት እቤታቸው ሄድኩ …ተጨንቄ ነበር፡፡

“ቁርስ በልተሃል?” አሉኝ፡፡

"እዎ”

ሻይ ላፍላልህ?”

“አይ አልፈልግም…ልጠይቅሁ ነው
የመጣሁት” ትክ ብለው ሲያዩኝ ቆዩና “ይችን ዳቦ እና ሻይ ተገን አርገህ እየመጣህ ባታጫውተኝ ምናባቴ ይውጠኝ ነበር” ብለው ወደ ግቢያቸው አበቦች ዓይናቸውን በትካዜ ላኩ!

እማማ ዣ፣ ለኔ ነፍስ ያላቸው ተረት ነበሩ አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ፣
አልያም ተኝቼ ስነሳ ቤታቸውም እሳቸውም ብን ብለው ጠፍተው፣ ቤታቸው በነበረበት ቦታ ላይ ከበቀለ ጫካ መሃል፣ አንድ ባለነጭ ጢም ሽማግሌ ብቅ ብሎ “ተረት ነበሩ፣ ሲኖሩ ሲኖሩ… ሞቱ” የሚለኝ ይመስለኛል! ቆየት ብሏል እንጂ እንደዚያ ዓይነት ሕልም አይቻለሁ፡፡ በሰበብ አስባቡ ከቤታቸው አልጠፋም:: እቤት ሲደብረኝ አልያም የእናቴ ጭቅጭቅ ሲያማርረኝ፣ ደብተሬን ሰብስቤ በረንዳቸው ላይ ባለው የቀርቀሃ ወንበር ላይ፣የቤት ሥራየን ሥሰራ እውላለሁ እማማ ዣ አልፎ አልፎ ካልሆነ አያወሩም ብዙ ጊዜ
የሚያሳልፉት ወይ ልብስና ጌጣጌጦቻቸውን ሲያዘጋጁ፣ አልያም ቁጭ ብለው የግቢያቸውን ዙሪያ በመመልከት ነበር፡፡
እናቴ ታዲያ “አንተ ልጅ እዚች ሴትዮ ሥር ሥር እያልክ የተነሳባቸው ቀን፣ ሬሳህ ነው
ከዛ ግቢ የሚወጣው” ትለኛለች፡፡ ቀጠል አርጋ “ ደሞ እንዲህ አለችኝ በልና ከድሮ
ጎረቤቴ አጣላኝ…”

“ምኑ ነው የሚነሳባቸው?” እላታለሁ። ቢገባኝም ቢያንስ እብድ ናቸው መባሉን በመካድ የሰፈሩን ሰው ላለመተባበር! እናቴ ቆጣ ብላ፣

“ወሬ አትውደድ!” ትላለች: እናቴ ማውራት እንጂ ጥያቄ ስትጠየቅ አትወድም፤ በተለይ ጠያቂው እኔ ከሆንኩ።

“እስካሁን አልተነሳባቸውም?” ስላት ትበሳጫለች! ትክ ብላ ታየኝና

“ጅል” ብላኝ ወደ ሥራዋ ትዞራለች ታዲያ እንዲህ ትበል እንጂ እማማ ዣ ጋር ሽርክ
ናቸው እሷም በክፉ በደጉ ከሥራቸው አትጠፋም ሥራ በዝቶባት ሳታያቸው ከዋለች “ጉድ! ይችን ሴትዮ ቀኑን ሙሉ ሳላያቸው… እስቲ ሂድና አይተሃቸው ና!” ትለኛለች ገና ከአፉ ከመውጣቱ ምንጥቅ ብዬ ስነሳ፣

“ለዚህ ሲሉህማ ወፍ አይቀድምህም!” ትላለች: የእናቴ ባሕሪ ግራ ያጋባኛል፡፡ ትንሽ እናትነቷን የተሻሟት እየመሰላት ትቀናለች መሰል?!

#ኩርሲ
እናቴና እማማ ዣ ለአንድ ሳምንት ተኳርፈው፤ እናቴ ራሷ እግራቸው ሥር ወድቃ ይቅርታ ከጠየቀቻቸውና ከታረቁ በኋላ፣ በጥንቃቄ ነበር የምትይዛቸው የፀባቸው መነሻ እስካሁንም እናቴን እየገረማት “ልጅ እኮ ናቸው” ብትልም፣እኔ ግን ወደ እማማ ዣ ያደላ
“ግንኮ እውነት አላቸው” የሚል የማልናገረው ጥብቅና ውስጤ አለ፡፡ ከነገሩ ልክ መሆንና አለመሆን በላይ እማማ ዣ አለመሳሳታቸውን በመደገፍ ከእናቴ “ ልጅኮ ናቸው” ንግግር
ጀርባ ያለውን (ባትናገረውም) ለንክነታቸው እውቅና የሚሰጥ ፈገግታዋን ዋጋ ማሳጣት እፈልጋለሁ! ያን ፈገግታዋን አልወደውም! “የሆነ ቀንማ ልብሳቸውን ጥለው ማበዳቸው
አይቀርም” የሚል ሟርት ይመስለኛል፡፡
ፀቡ እኛ ቤት የመድኃኒያለም ዝክር የተደረገ ቀን ነበር የተፈጠረው፤ ከቅርብና ከሩቅ ያለ ዘመድና ማኅበርተኛ መጥቶ ስለነበር፣ ቤታችን ካፍ እስከገደፉ በሰው ተሞልቶ ነበር ...እማማ ዣ አዲስ የሐበሻ ቀሚሳቸውን ለብሰውና በወርቅ ተንቆጥቁጠው መጡ፡፡ ቤቱን የሞላው ሰው በሙሉ በአክብሮት ተነስቶ ቆመ፡፡ ሁሉም ወንበር ተይዞ ስለነበር እናቴ
ያኘቻትን ኩርሲ እበሩ አጠገብ እያመቻቸች “ እዚህ ያንዣብ.” አለቻቸው፡፡ እማማ "ዣ" አንዴ እናቴን አንዴ ኩርሲውን አየት አደጉና፣

የለ! የለ! …ይንፈስብኝ እውጭ እሆናለሁ” ብለው ወጡ፡፡ እናቴ ዳቦና ጠላ ይዛ
ስትወጣ እማማ ዣ የሉም፡፡ ወደ ቤታቸው ሄደዋል:: ግራ ገብቷት ብቅ ብላ ወደ
ግቢያቸው ብታይ ጭር ብሏል፡፡

“አቡቹ ያንዣብ ወደየት ሄዱ”

“እኔጃ ወደ ቤታቸው ብል ማኅበርተኛው እብድ ሊላቸው አይደል

“ጅል! ….እዚሁ ተገትረህ እኔጃ ትላለህ?!” ብላ ከተነጫነጨች በኋላ ግራ እንደተጋባች ወደ ውስጥ ተመለሰች:: የዚያን ቀን እናቴ እንግዳ ስለበዛባት፣ እኔም ዕቃ ሳነሳሳና የመጣ የሄደው ናስቲ ሳመኝ? ሲለኝ ስለዋለ፣ መንገድ ላይ እያዩኝ የሚያልፉኝ ሁሉ እቤታችን
ድግስ ሲደገስ ካልሳምንህ የሚሉት ነገር ያበሳጨኛል) ...እማማ ዣን የዛን ቀን ሳናያቸው አድረን በነጋታው እቤታቸው ሄድን፡፡ ያው እናቴ ስትሄድ ከኋላ ኋላዋ ተከትያት እንጂ እንሂድ አላለችኝም:: እማማ ዣ በረንዳቸው ላይ ተቀምጠው፣ የጥርስ ብሩሽ ሳሙና እያስነኩ ጉልበታቸው ላይ ከዘረጉት የሐበሻ ቀሚስ ላይ ጠብ ያለ ነገር ሊያስለቅቁ ይፈገፍጋሉ

እናቴ እንደ ወትሮው “ያንዣብ እንዴት አደሩ?” ብትላቸው ጠርዘዝ ብለው፣

ይመስገነው!” አሉና፣ ተቀመጭም ሳይሏት ልብሱን መፈግፈጋቸውን ቀጠሉ: እናቴ ገብቷት ትንሽ ቆመችና፣ እንዴት አደርኩ ልበልሁ ብየ ነው፣ ወደኋላ ብቅ እላለሁ..ያደረ እንግዳ አለብኝ” ብላ ስትወጣ “ አትድከሚ! እንግዶችሽን ሸኝ” ብለው ኮስተር አሉ! እናቴ የግንባሯን ቆዳ ወደ ላይ ሰብሰብ አድርጋ ወደ ቤት ተመለሰች:: አውቃለሁ በውስጧ°ዛሬ ተነስቶባቸዋል" እንደምትል:: ከደቂቃዎች በኋላ አቀርቅረው ሲፈገፍጉ ከቆዩበት ድንገት ቀና ቢሉ፣ እፊታቸው ቆሚያለሁ “እያሱ ድረስ?” ብለው |
ጣሉት:: እኔም በድንጋጤ ደነበርኩ “አቡቹ! ምነው አለሁም አይባል እንዴ? በድንጋጤ ግጥም ብል ምን ትጠቀማለህ ልጄ?” ብለው ደጋግመው አማተቡና፣ ወዲያው ከት ብለው ሳቁ!….

“ና! ቁጭ በል እዚህ! ምን ይገትርሃል አለሁ ይባላል. ወይ ጉሮሮህን እህ እህ .
እንዲያ ነው ደንቡ ክስት ሰይጣን ይመሰል ..ሆሆ አጠገባቸው ሄጀ ረዥሙ
መደገፊያ የቀርቀሃ አግዳሚ ላይ እግሬን አንጠልጥዬ ተቀመጥኩ:: ትንሽ ዝም ብለው ወደ በሩ ሲመለከቱ ቆዩና፣ ልክ የሌላ ሰው እናት እንደሚያሙ ሁሉ፣ እናቴን ያሙልኝ ጀመር

“አየሃት ይችን እናትህን?…አወኩሽ ናኩሽ እኮ ነው…. እኔ ያንዣቡ ጠሪ አክባሪ ብዬ ሄድኩ እንጂ በእንተ ስመ ለማርያም…. ብዬ ቁራሽ ፍለጋ የሄድኩ መሰላት እንዴ. በተከበርኩ በታፈርኩበት መንደር፣ ኩርሲ አንከርፍፋ እንደውሻ በር ሥር ተቀመጭ _
የምትለኝ? ሆሆ (ወደው አይስቁ አሉ! …ጥንት ገረዶቼም ኩርሲ ላይ አልተቀመጡ
እንኳን እኔ ልጅት! ይበለኝ እኔው ነኝ ካለኩያየ ገጥሜ ራሴን ያሰደብኩ!”

ዝም ብዬ ሰማኋቸው… ሥራቸውንም ወሪያቸውንም ቆም አድርገው አየት አደረጉኝና…

“ምን ይለጉምሃል? ከናትህ ጋር አብረህ መስደብህ ነው?” ብለው ተቆጡ! ቁጣቸው ድንገተኛና ምርር ያለ ስለነበር በውስጤ ዛሬ የእናቴ ሟርት መድረሱ ነው!” አልኩ። ከዚህ ቤት ሬሳዬ …”

“ኧረ እኔ .…” ከማለቴ ሳያስጨርሱኝ ….

“ኤዲያ! የቅል ዘሩ አንድ ነው እኔ ያንዣቡ እንኳን አንድ ቋቁቻም፣ አገር ቢያኮርፍ
ምንተዳዬ…
👍3
ጃንሆይ ወደቁ፣ ዙፋኑ ተንኮታኮተ ብሎ፣ ባላባቱ ሁሉ የበላበትን ወጭት እየሰበረ፣ ከዛ መንግሥቱ ከሚባል ጥላቢስ ጋር አብሮ አንዴ ወዛደር አንዴ ላብ አደር እያለ ዘጭ ዘጭ ሲል.. እኔይቱ ልጅት ባደባባይ ደረቴን ነፍቼ “ኃይለሥላሴ ይሙት!” እያልኩ ስምል ነው የኖርኩት:: ብረት ያንጠለጠለ ምንደኛ አብዮት ጠባቂ፣ የጃንሆይን
ስም በሰማ ቁጥር በስመአብ እንዳሉበት ሰይጣን ሲበረግግና ዓይኑን ሲያጉረጠርጥብኝ እንኳ ተርበትብቸ አላቅም… ለምን!?… ጨዋ፣ የጨዋ ልጅ፤ በጨዋነት ያደኩ ነኛ! ጨዋ አይበረግግም

የሰው ልጅ፣ ሞቱ ታፈር መግባቱ አይደለም …. እሱንማ ደሃውም፣ ባሪያውም ቀጣፊውም… ሴት አውሉም ይሞተዋል …የጨዋ ልጅ ሞቱ ክብሩን እንካችሁ ብሎ ሲሰጥነው! ነው ይሁን ግዴለም እንኳን የኔ፣ የአገሪቱም ክብር
በማንም ብጣሻም ተንኮታኩቶ ወድቋል
ንጉሷን የበላች አገር ያንዣቡን ልትምር
ነበር ድሮስ?…. አይ አገር እቴ.…….
በሄደችበት እንደኔ ቢጤ ኩርሲ ላይ አስቀምጠው፣ ስንዴና ዘይት የሚወረውሩላት አዝነው መሰለህ?…ሰጭ ቁራሽ እህል እየሰጠ፣ ሙሉ ክብር ይወስዳል! በደጉ ንጉሥ ዘመንማ በሄዱበት ዙፋኑ ተዘፍኖ፣ ምንጣፉ ተነጥፎ መኳንንትና መሳፍንቱ ጎንበስ
ቀና ጠብ እርግፍ ብሎ ነበር የሚቀበላቸውን ያ ሁሉ ሽር ጉድ ለአንድ ተፈሪ እንዳይመስልህ፤ ተፈሪማ ምኑ? እንዲሁ እንደኔ ሥጋና ደም ነው…ላገር ነበር ክብሩ… ንጉሥ ራስ ነው ሁሉም በደረጃው በመዓረጉ ሲሆን ያምራል... ንፍሮ ነው ተቀላቅሎ የሚቀቀል የነፈረ ዘመን ! ብለው ለረዥም ጊዜ ዝም ብለው ቆዩና

“አቡቹ” አሉኝ።

“እ!”

“ባሪያ ይመስል ባፍንጫህ አታልጎምጉም… አቤት በል በወጉ!”

“አቤት”

እንደሱ ነው …ቁርስ በልተሃል?”

አይይይ ..” ቦርሳቸውን ያኖሩበት ጠፍቷቸው ዙሪያቸውን ሲፈልጉ ቆዩና፣ድንገት ትዝ ሲላቸው የቀሚሳቸውን አንገት ጎትተው ከጡታቸው መሃል ትንሿን የብር መያዣ ቦርሳ መዘው አወጡ…አዳዲስ ሁለት ብሮች ለይተው

ሂድ ዳቦ ገዝተህ ና” አሉኝ:: ወደ ዘመናይ ሱቅ በረርኩ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍3
አትሮኖስ pinned «#እማማ_ዣ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ከእኛ ቀይ ወጥ የእማማ "ዣ" ሻይ እና ዳቦ በለጠበት ማለት መሸነፍ መስሏቸው ነው እንጂ፣ እማማ "ዣ" ቤት ከሻይ እና ዳቦ በስተቀር ሌላ ነገር ቀምሸ አላውቅም! ሻይ እና ዳቦ የሌለበት ቤት አለ? ከፈለግ እቤቴ ለማኅበርተኛ ጠላ በሚቀዳበት ማንቆርቆሪያ ሙሉ አፍልቼ ስጠጣ መዋል እችላለሁ! እውነቴን ነው! እናቴ በሌላ ሌላው ነገር ነጭናጫ ትሁን…»
#ብዙ_ተባዙ

ሰውን በመፍጠሩ እግዜር ሚጠቀመው
ሰውም በመፈጠር ከእግዜር የሚያገኘው
አንዳች እውነት ባይኖር አንዳች ድብቅ ነገር
ምድሪቱን ለመሙላት ከብት ይበቃ ነበር።

🔘ኤፍሬም ስዩም🔘
#የሟች_ሃገር_እውነት

#ልጄ
"ሀገር ማለት ሰው ነው” ያሉህን ተቀበል፣
ሰው በሞተ ቁጥር ሀገሬ ሞተች” በል ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ለተመልካች_ሰማይ_ቅርቡ_ነው

ትውልድ ተበላሽ በሱስ ተጠመደ
ተስፋውን ለቀቅ ሄዶ ተሰደደ
ማንነቱን አጣ ህልውናወ ተናደ
የታመቀ ኃይሉ ትኩስ ማንነቱ በነነ ተነነ
እንደማይሆን ሆነ
ከንቱ የማይረባ ሲባል ሽክም ዜጋ
በተስፋ መቁረጠ በር አዕምሮውን ዘጋ
እንኳንስ ግዴታው ጠፋበት መብቱ
ፈሶ ወኔ አሞቱ
አስረካቢም ጠፋ እንኳን ተረካቢ
ከራሱ ያስፈ ለወገን አሳቢ
ግን ቢሆንም አይገርምም ይኼ ሁሉ ነገር
ከዛ ከዚህ ሆኖ ላይ ታች ብሎ
ቃሉን ተቀብሎ
እሱን ቤተሰቡን ህገሩን አስቦ
ሕልሙን አሰናድቶ አላማ ሰንቆ
ወደፊት ነጉደ አልሸነፍ ብሎ
ተማረ በረረ የልቡ ምኞቱ
ምርቃት ፍጻሜው ደስ አለው ሰዓቱ
እሱ መቼ ገባው በሀሳብስ መች መጣ
የእንዲህ ያለው ወጉ
ከመመረቅ ይልቅ ሕልም የሚያጨልመው
ሥራ መፈለጉ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#እማማ_ዣ


#ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል)


#በአሌክስ_አብርሃም

እቡቹ ቆንጆ እዲስ ባለሰሊጥ ዳቦ መጥቷልእንካ በነፃ ልጋብዝህ" ብላ በገዛሁት ዳቦ ላይ ልትመርቅልኝ በብረት መቆንጠጫ ትንቦክ የሚል ዳቦ አነሳች፡

አይ እልፈልግም” ብዬ የገዛሁትን ብቻ አንስቼ ሮጥኩ! ከኋላ ሳቋ ይሰማኛል… የዚህ ልጅ ኩራቱ … ካካካ !

#በፖሊስ
እማማ ዣ፣ ድሮ ድሮ ለግንቦት ልደታ በግ አሳርደውና ነጭ ልብስ ለብሰው ሰፈሩን ሁሉ ስለሚጋብዙት፣ ግንቦት ልደታ ራሳቸው እማማ ያንዣቡ ይመስሉኝ ነበር:: ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ከሆነ ዓመት በኋላ ግን መደገሱን እርግፍ አድርገው ተውት:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እንደበፊቱ መልበስና መዘነጡንም ተውት፤ አልፎ አልፎ ወጣ ሲሉም ቀለል ያለ የፈረንጅ ቀሚስ እንጂ እንደበፊቱ የሐበሻ ቀሚስ አይለብሱም ነበር! ጎረቤቱ ይኼንንም
አፈ-ታሪክ ከሚመስል ታሪካቸው ጋር አገናኘው። … ወሬው ብዙ ዓይነት ነው!

ታዲያ አንድ ቀን እቤታቸው ገብስ ሊወቅጥ ከመጣ ወዛደር ጋር እያወሩ(ወዛደሩን ጠርቼው ያመጣሁት እኔው ነኝ ሻይ እና ዳቦዬን ይዤ በረንዳው ላይ ተቀምጫለሁ፡፡
ወዛደሩ ገብሱን እንጨት ሙቀጫ ውስጥ እያስገባ በሚገርም ኃይል ይወቅጠዋል፡፡
የሙቀጫው ንዝረት በረንዳው ድረስ ዘልቆ፣ ስሚንቶው ወለል ላይ ያስቀመጥኩት ብርጭቆ ውስጥ የነበረውን ሻይ በቀስታ ያንቀሳቅሰው ነበር! ….ክንዱ ላይ ከጠቀለለው
ካኪ ሸሚዙ ሥር ብቅ ያለው ፈርጣማ ከንዱ የሚሰነዝረው ምት፣ የእማማ ዣን ዘመን ያስቆጠረ የቤት ምሰሶ ይነቀንቀዋል … እማማ ዣ በረንዳቸው ላይ ወገባቸውን ይዘው ቆመው፣ “እሰይ! እንዲህ ነው እንጂ የሥራ ስው እያሉ ያደንቁታል! በመኻል እናቴ ጠርታኝ እቤት ደርሼ ስመለስ፣ እማማ ዣ ለወዛደሩ ሻይ በዳቦ አቅርበውለት፣ ሞቅ ያለ ወሬ ይዘው አገኘኋቸው። የሙቍጫው ዘነዘና በከፊል የተፈተገ ገብስ የሞላውን ሙቀጫ ደገፍ ብሎ ቁሟል፡፡ እማማ ዣ በወሬ ተጠምደው መግባቴንም ያዩ አልመሰለኝም፡፡ አልያም ቢያዩኝም ወሬው በልጦባቸው ችላ ብለውኛል፡፡ በሁለት ነገሮች በጣም ተገረምኩ፡፡የመጀመሪያው ያስገረመኝ ነገር፣ የእማማ ዣ አቀማመጥ ነበር፡፡ በረንዳቸው ላይ ያለው ከፍ ያለ የቀርቀሃ ወንበር ላይ እንኳን ደጋግመው በጨርቅ ካላራገፉና “ይቀዘቅዘኛል” እያሉ ትራስ ቢጤ ጣል ካላደረጉ በቀር የማይቀመጡት ሴትዮ፣ እግር ሲረመርመው በሚውለው የበረንዳው ደረጃ ላይ፣ ያውም ምንም ነገር ሳያነጠፉ ወርደው ተቀምጠዋል:: ወዛደሩ ከሳቸው ዝቅ ብሎ ለአበባ መደብ መከለያ በተደረደረው ቀያይ ጡብ ላይ ነበር አረፍ ያለው፡፡ ታፋና ታፋው በቁምጣው ሙልት ብሎ ደህና ስፖርተኛ ይመስላል::
ሁለተኛው ግርምት፣ ለወዛደሩ ስለ ባላቸው እያወሩት ነበር፡፡ እዚህኛው ላይ ከመገረምም አልፌ ትንሽ ተበሳጨሁ፡፡ ከመጀመሪያው መስማት ባለመቻሌ፤ ወሬያቸው መኻል ላይ ደርሶ ነበር::

“…እኔ ልጅት አንዴ ከሰነዘርኩ
እንኳን ሰው ሰይጣንም አይመክተኝ ...ያንን ባል ተብዬ
ወተፋንም (የድሮ ባላቸውን ነው) “ አቤት ቁመና… አቤት መልክ .…” እያለች ምድረ
ኮማሪ ስታቀብጠው ጊዜ፣ እኔ ያንዣቡ ላይ ሊንቀባረር ከጄለዋ! አንድ ቀን ለባብሶ መቼም አለባበስ ከሱ ወዲያ ላሳር ነው…ደረቱን፣ ይኼን ትከሻና ትከሻውን ያየህ እንደሆነ፣ እንዲህ እንዳንተ ሳንቃ ነው…” ብለው ለወዛደሩ ዳቦ ከተከመረበት ሰሃን ላይ አንድ ዳቦ አንስተው ጨመሩለት፡፡
ወጋቸውን ቀጠሉ “አንድ ቀን እዚህ ነኝ እዛ ነኝ ሳይል፣ በዋለበት አድሮ አረፋፍዶ
ወደምሳ ሰዓት መጣ፡፡ ጭራሽ ይኼ ሲገርመኝ ..እልፍ ብሎ ገብቶ ተኝቶ ዋለና ...ወደ አመሻሹ ላይ ተነስቶ፣ ካሁን አሁን የት እንዳደረ ሊያወራኝ ነው ብዬ ስጠብቅ፣ ሙሉ ልብሱን ግጥም አርጎ ለባበሰና ሚኒስቴር መስሎ ..ደህና ዋይ እንኳን ሳይለኝ ውልቅ ብሎ ሊሄድ ...

“ምን ሁነሃል!? …ወዴት እየሄድክ ነው ከመሸ …?” አልኩት… እንዲህ ወደ ማጀት አንዲት ደዘደዝ ሠራተኛ ስታጨማልቀው ምኗም አላምረኝ ብሎ ወዲያ ገፍቼ ራሴ ሊጥ እያቦካሁ እጄ ሁሉ ሊጥ ሁኗል ያመልጠኛል ብዬ ለቅለቅ እንኳን አላልኩትም፣ የትስ ብሄድ አንችን ማን ቦሊስ አረገሽ? ..አርፈሽ ጓዳሽ ግቢና ሊጥሽን አቡኪያ” ብሎኝ ጎምለል ጎምለል እያለ ውልቅ፡፡ እኔ ያንዣቡ እንኳን እንዲህ ከፍ ዝቅ ሊያረገኝ ቀርቶ፣ አፍንጫው መሬት እስኪነካ አሥራ ሁለተዜ ሰግዶ ነው ያገኘኝ.አሁን እጁ አስገባኝና፣ ቀን ከሌት የልቡን አድርሶ መናቁ ነዋ! ….ብልጭ አለብኝ! እንዲያው አንዳች ነገር ዓይኔ ጋረደኝ ..ሰማይ ልሁን መሬት አላውቀውም ንቀቱ ማጣጣሉ አይደለም፤ በዓኑ ያቀለለኝ ነገር ... አስተያየቱ አመመኝ! እዚህ ደጅ የተከመረ የቤት ጥራጊ እንኳን እንዲ አይታይም. እንደ ገረድ ጓዳ ለጓዳ ስንፏቀቅ፣ እውነትም ባሪያ መስዬው እንደሁ እንጃ
ደሞ አለ ... “ማን ቦሊስ አረገሽ?…ይኼ አንኮላ! ሴት ልጅ ለክብሯ ማንም ባይሾማትም ቦሊስ መሆኗ መች ገባው የማቦካና የምጠፈጥፈው ለሱ አልነበረም እንዴ? ... ሰው ካለ ነገሩ የት ትሄዳለህ ብሎ አይጠይቅምኮ፣ የኔ ብዬ ባከብረው ነበር፡፡ ማደሩ አንገብግቦኛል፣ ጭራሽ ይኼ ሲጨመር ደሜ ፈላ፣ ደርደር ብዬ ወጥቼ እዚህ ታዛው ላይ አዲስ ተፈልጦ ከተከመረው ፍልጥ አንዱን ላጥ አድርጌ አንድ ጊዜ ጀርባውን ባቦንነው የናቴ ልጅ .…የሰው ገላ እንደ ነጋሪት ሲኖጋ የዛን ቀን አየሁ!

“አላተረፍሽውም!” አለና፣ ወዛደሩ በግርምት ዳቦውን መብላቱን አቁሞ አፉን ከፈተ፡፡

“…ፍልጡ ሲያርፍበት እንደ ወንድ እንኳ ዘራፍ አላለም፡፡ ከዚህ ከኔ በር የበረረ፣ እዚህ ።አሁን ዘመናይ ሱቅ የተባለውጋ ቆመ፡፡ ልምረው ነው …ተከተልኩት ...ሰው አዬኝ . አላዬኝ ብሎ ዞር ዞር አለና፣ የሸሚዙን ኮሌታ አስተካክሎ “እብድ!” ብሎኝ እርፍ! .
አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው ኣሉ ካልክማ ብዬ አበድኳ! … አይሮጥ፣ ሰዎች አሉ፣ ኀፍረት ያዘው፣ ….አይቆም፣ ፍልጡን ፈራ፤ እንዲሁ ሲደናገር ደርደር ብዬ የበላሁ የጠጣሁትን አንቆራጠጥኩት! ሲብስብት እንደሴት እሪሪሪ ብሎ ሲጮህ ያየኸው እንደሆነ፣ ያ ጎምላላ፣ ያ ወንዳወንድ ነው ወይ ያስብላል ...

የአንድ እግሩን ጫማ አረጋሽ የምትባል እዚህ ታች አለች .እሷ በር ጥሎ እግሬ አውጭኝ ሊያመልጠኝ መሰለህ ... እንዳራስ ነብር ተወርውሬ ከረባቱን ጨመደድኩና (መቸስ አዙሮ አያይም እንጂ አንገቱ ለከረባት የሰጠ ነበር) እንደ በግ እየጎተትኩ አንጄቴ የጤሰውን ያህል፣ እስኪበቃኝ አበራየሁት! የሞት ሞቱን እየተውገረገረ ተነስቶ በረረ..ይኼው ስንት ዓመቱ ከዚያን ቀን ጀምሮ ይኑር ይሙት እንጃ፣ ጠፋ ጠፋ! አንዷ ኮማሪ
ጋር ጠቅልሎ ገብቶ የቢራ ብርጭቆ እያጠበ ይሆናል! ምናሻኝ ለምን እግር አያጥብም!
ያንዣቡ ምን እዳየ ..ከዛ ወዲያ አንድ ወንድ ንክች ሳያደርገኝ ይኼው ቅብርር ብዬ አለሁ” አሉ፣ ፉከራ በሚመስል ድምፅ ...አንገታቸውን በኩራት እየሰበቁ።
ኧረ አንችስ እሳት ነሽ የናቴ ልጅ!” አለ ወዛደሩ በስሜት ተውጦ! እንዴዴዴዴ...ቅድም ገብስ የሚወቅጥበትን ዋጋ ሲነጋገሩ …” አንቱ!” እያለ አልነበር ሲያናግራቸው የነበረው?
…ከምኔው “አንቺ!” አለ? ብዬ ገረመኝ!
እየገረመኝ ይኼን ሰምቼው የማላውቅ አዲስ ታሪካቸውን እያብሰለሰልኩ ማታ ሁሉ እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ አመሸ ።

#ዘጭ
በቀጣዩ ቀን፣ እማማ ያንዣቡ ሲጀምሩና ሲያቋርጡ የኖሩቱን የጃንሆይ ታሪክ፣ ድንገት አውሩልኝ ብዬ ሳልጠይቃቸው፣ ከመሬት ተነስተው ያወሩልኝ ጀመ፡ር …

አንድ ቀን አገር ሰላም ብዬ እዚህ እታች ባንኩ ቤት ደርሼ ስመለስ ብለው ሲጀምሩ ሌላ ወሬ መስሎኝ ነበር።
👍2
አንድ ዘባተሎ ድሪቶውን መንገድ ለመንገድ የሚጎትት እብድ ይሁን ለማኝ እንጃለት
… አንች! …ብሎ ጠራኝ …ሰው አንች ሲለኝ አልወድም።

'ምን ሆንከ? አልኩት፣ ለእብድ ፊት መስጠት ጥሩ አይደለም፡፡

“ጃንሆይ፣ ከዙፋኑ ዘጭ አለ!” ብሎ ከራማዬን ገፈፈው፡፡

ሂድ ወዲያ ዘላን ዘጭ የሚያደርግ ዘጭ ያርግህ እቴ!” ብዬ ተቆጣሁ፡፡ አባባ ጃንሆይን ሲናገሩብኝ አልወድም:: እርምጃዬን ፈጠን ፈጠን ባደርግ፣ ያ ዘባተሎ ሊተወኝ መሰለህ ከነተሸከመው ድሪቶ ከኋላዬ ጀፍ ጀፍ እያለ

ህህህህህ …ጃንሆይ ዘጭ! …ሽማግሌው! ..ዘጭ! …ጆሮውን ይዘው ዘጭ አደረጉት!
.ህህህህ ጭብጦ በምታህል መኪና እንደ ጤፍ ጭነው ወሰዱት ህህህህህ…”

ድሮውንም እብድና ውሻ ዘሎ ሰው እንዳዋረደ ነው ብዬ ወደ ቤቴ ገባሁ! ..…ለካስ ያ ወፈፌ እውነቱን ኖሯል ራዲዮ
ነሺ… ቴሌቢጅን ነሽ፣ ጃንሆይ ተዙፋናቸው ወረዱ እያለ ከበሮ ይደልቃል፡፡ ይኼውልህ እኒያ ተሰማይ ተምድር የገዘፉ ንጉሥ በምድረ ኩታራ ከዙፋናቸው ወርደው አረፉት! ጊዜ ዝቅ ሲያደርግ መርዶህን እንኳን ደህና ሰው አያረዳልህም፡፡ እንዲህ ቤተ መንግሥትህን ማንም ይረግጠዋል ..ዙፋንህ ላይ ማነው
ቂጡን ያልጠረገ ግስንግስ ይወዘፍበታል ነገር ዓለሙ ዘጭ አለ! አገር ምድሩ ዘጭ
ለእግራችን የተጠየፍነውን በቂጣችን ተደላድለን ዘጭ አልንበት! አንድ ተፈሪን ያወረዱ መስሏቸው፣ እችን ልቃቂት አገር እራሷን ይዘው ሲጎትቱ ተዘክዝካ ውሏ ጠፋ በዚ ቢመዙ…. በዚህ ቢመዙ እንደ ፀጉር ተንጨፍርሮ ሁሉም ውል ነኝ አለ ..ቢጎትቱት ላይፍታታ፤ የጃንሆይ ነገር እንዲህ ሁኖ ቀረ እልሃለሁ… አቡቹ!” አሉና ተከዙ…. ትክ ብዬ አየኋቸው፡፡ ፀጉራቸው ገብስማ ሆኗል! ዓይናቸው ዙሪያውን ኩል ተኩሎ ነበር ከዚህ በፊት ተኩለው አይቻቸው አላውቅም።

“አቡቹ”

"እ"

ሂድ ዳቦ ገዝተህ ና” ብለው ድፍን አዲስ አሥር ብር ሰጡኝ፡፡ ቦርሳቸው
አልጠፋቸውም፤ በትክክል ሂደው ከተቀመጠበት ነበር ያነሱት፡፡ እየበረርኩ ሄጀ አፍታ " ሳልቆይ ባዶ እጄን ተመለስኩ

“ምነው ባዶህን መጣህ?” አሉ፣ አንዴ እኔን አንዴ መልሼ የዘረጋሁላቸውን ብር
እየተመለከቱ፡፡

“የዘመናይ ሱቅ ታሽጓል”

“ምነዋ?”

“ስሩ ላይ 'ግብርዎትን በወቅቱ ስላልከፈሉ ታሽጓል የሚል ወረቀት ተለጥፎበታል” አልኩ፡፡

“በል ብሩን ይዘህ ሂድና ከወደድከው ቦታ ብስኩትም ቢሆን ገዝተህ እቤትህ ቁጭ በልና ብላ…መልሱንም ስክርቢቶ ግዛበት” አሉኝ፡፡ ባለማመን አየኋቸው ..ከዛ በፊት በሕይዎት ዘመኔ ድፍን አሥር ብር ኖሮኝ አያውቅም፡፡የድፍን አዲስ አሥር ብር ጌታ! እቤቴ እስክደርስ ሦስት አራት ጊዜ ባለማመን ብሯን እያየሁ ተፈተለኩ፡፡

የዚያኑ ቀን ማታ ወደ ምሽቱ አንድ ሰዓት ይሆናል ...ሁልጊዜ እንደማደርገው ቤታችን በር ላይ ተቀምጬ እግሬን እታጠባለሁ፡፡ ታጥቤ እንኳን ጨርሻለዉ የታጠበ እግሬን ቆሻሻ እንዳይነካው አንፈራጥጬ ተቀምጬ እስኪደርቅ ቁጭ ብዬ ጥቁሩ ሰማይ ላይ የተዘሩትን ከዋክብት አያለሁ፡፡ ድንገት አንድ ሰው በጨለማው ውስጥ ከወደታች
መጥቶ፣ ወደ ማማ ዣ ቤት ሲጣደፍ ተመለከትኩ! በዓይኖቼ ጨለማውን እየሰረሰርኩ ማንነቱን ለመለየት ስታገል… ከአንድ ቤት መስኮት በመሹለክ የጨለማው ወሽመጥ መስላ መንገዱ ላይ የተጋደመች ብርሃን በእርምጃ ሲሻገር ባንዴ ለየሁት! ወዛደሩ ነበር!…ገብስ ወቃጩ ወዛደር! ...

በዚህ ምሽት ምን አመጣው…የእማማ ዣን የግቢ በር ከፍቶ ሲገባ፣ ባለቤት ነበር
የሚመስለው፡፡ እርምጃው ከሐሳቤ ይፈጥን ስለነበር፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ተጋብቼ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች በገባበት በር ላይ ዓይኔን ተከዬ ቆየሁ፡፡ ድንገት “ሰውዬው ሌባ ሲሆንስ!?” የሚል ሐሳብ ወደ አእምሮዬ መጣ፡፡እንደውም ሰተት ብሎ የገባው ሌባ ቢሆን ነው፤ ሌባ መቼም አንኳኩቶ አይገባ!! ትላንት ሲሰልላቸው ውሎ በጨለማ ሊዘርፋቸው ተመልሶ ቢሆንስ? ከሐሳቤ እኩል ሰውነቴም ከተቀመጠበት
ተስፈንጥሮ ተነሳ።

ግራ-ቀኝ ሰው መኖር አለመኖሩን እየተመለከትኩ ወደ ግቢው በር ሮጥኩ፡፡ መኻል መንገድ ላይ ስደርስ፣ ግቢው ከውስጥ ቊጭ ብሎ ሲቆለፍ ሰማሁ… ቆም አልኩ .. ትንሽ ጆሮዬን ቀስሬ አዳመጥኩና ወደ ግቢው በር ሄጄ ልከፍተው ብሞክር፣ በሩ በቁልፍ
ተዘግቷል. ይኼ በር በዚህ ሰዓት በጭራሽ ተዘግቶ አያውቅም ነበር፡፡ ቁልፉ እማማ ዣ አንገት ላይ ይንጠለጠልና ቁልቁል ወደ ጡቶቻቸው መሀል ይጠፋል! ማን ሌባ አስገብቶ በሩን ከውስጥ ይቆልፋል? ...ምናልባት ዓይኔ ይሆናል እንጂ የገባም ሰው ላይኖር ይችላል፡፡ ጆሮዬን በሩ ላይ ለጥፌ ሳዳምጥ፣ እማማ ዣ ለስለስ ባለ ድምፅ “ጠፋብህ እንዴ ቤቱ!” ሲሉ ሰማኋቸው! በቀስታ ዞሬ ወደ ቤቴ ተመለስኩ .. የታጠበ ርጥብ እግሬ
አፈር ቅሞ መቆሸሹ ትዝ ያለኝ፣ እቤት ስገባ ነበር፡፡ በባዶ እግሬ ነበር የሮጥኩት!

አንዱን የሰፈር ማቲ ጠርቼ እኪሴ በተቀመጠችው ድፍን አሥር ብር “ኦሞ ገዝተህ ና” ማለት አማረኝ ..ለእግሬ!!!

💫አለቀ💫
አትሮኖስ pinned «#እማማ_ዣ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም እቡቹ ቆንጆ እዲስ ባለሰሊጥ ዳቦ መጥቷልእንካ በነፃ ልጋብዝህ" ብላ በገዛሁት ዳቦ ላይ ልትመርቅልኝ በብረት መቆንጠጫ ትንቦክ የሚል ዳቦ አነሳች፡ አይ እልፈልግም” ብዬ የገዛሁትን ብቻ አንስቼ ሮጥኩ! ከኋላ ሳቋ ይሰማኛል… የዚህ ልጅ ኩራቱ … ካካካ ! #በፖሊስ… እማማ ዣ፣ ድሮ ድሮ ለግንቦት ልደታ በግ አሳርደውና ነጭ…»
#ፍራቻ

አብሬህ እያለሁ እምነት ካልጣልክብኝ
ያንተው ነኝ እያልኩህ ከተጠራጠርከኝ
እውነቴን እያየህ እፈራለሁ ካልከኝ
ፍሬ ቢስ ድርጊትህ ከልክ ከወጣ
እኔም ልፍራ መሰል ፍራቻህ ቅጥ አጣ።
#ያለ_እኔ

ዐይን ዐይኔን እያየ ቅልስልስ እያለ
በውብ ቃላቶቹ በዐይኑ እያባበለ
ሕይወቴ ባዶ ነው ያላንቺ አልኖር ቢለኝ
ያለ እኔ እማይኖሩት ብዛታቸው ገርሞኝ
አትኩሬ አስተዋልኩት
ላሁኑ ካለኔ ከማይኖር ከዛኛው ነኝ አልኩት።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘