አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ርምጃ

ሰው
ካለበት ቦታ ተነስቶ
ሩቅ ለመሄድ ቢመኝ
ሩቅ ለመጓዝ ቢያምረው፤

ያንን የተስፋ ርምጃውን
አንድ ብሎ ነው የሚጀምረው

አንድ አልኩ....
#ራሴን_በላሁት

ገብቼ ሱባኤ
ከብቻ ጉባኤ፣
ላያሌ አመታት
በእኔነት ማሳ ተመላልሼበት፣
ወጥቼ ወርጄበት፣
አዝመራ ባጣበት፥
ራሴን በላሁት
እየመነዘርኩት፣
እያመናዘርኩት።

🔘ደበበ ሰይፉ🔘
​​#ልጩህበት!!


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በጥላሁን

ምኑን ከምኑ ነው እምመርጠው?
"ወይ ኤደንን እኔ ሄጄ እንዳናግራት መፍቀድ ካልሆነ ከልጅቷ ጋር ፍቅር ጀምረህ ኤደንን መርሳት!"
ጆሲ አምርሯል ግራ ገባኝ ። ኤዱን እንዲያናግራት በጭራሽ እንደማልፈልግ አውቃለሁ ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ ጡጫ ሆነብኝ ቢሆንም•••
ውስጤ እንደማይሆን እያወቀው ከዳኒ ጭቅጭቅ ለመገላገል ስል •እሺ አልኩት
በቃ እሺ!
"በቃ እሺ ምን በየትኛው ሀሳብ?"
"በቃ ካልካት ልጅ ጋር እንቀራረባለና!"
አዋ ዳንዬ አንዳንዴ እንኳን እንደዚህ እሺ በለኝ እስቲ ዳንዬ ዋናው መቀራረባችሁ ነው ከዛ ቡሀላ ሌላው ይከተላል ኤዱንስ ቢሆን ሳትቀርባት አላፈቀርካት!"
እሺ አልኩህ እኮ በቃ አልኩት። ከዛች ሰአት ጀምሮ ጆሲ ስራውን ጀመረ ።
ልጅቷን እቤት ያመጣትና መጣሁ ብሎ በመውጣት ጥሎን ይጠፋል።
መቀራረብ ብንጀምርም እውነቱን ለመናገር እሷን ለብቻዋ ከማገኛት ይልቅ ኤዱን ከልጁ ጋር ሆና ባገኛት እመርጥ ነበር።

ለሶስት ወር ልጅቷ እና ጆሲ ስራ አደረጉኝ የተቀየረ ስሜት አልነበረም በመሀል ድንገት ለተከታታይ ቀናት ጥፍት አለች።
ለስድስት ቀን ያህል ድምጿንም ስልኳንም አጥፍታ ከተሰወረች ቡሀላ በሰባተኛው ቀን እኔና ጆሲ ሰፈር ውስጥ ቁጭ ባልንበት እራሷ ጆሲ ስልክ ላይ ደወለች።
ስልኩን ለሁለታችንም እንዲሰማ አደረገና •••
" ምን ሆነሽ ነው የጠፋሽው?" የጆሲ ጥያቄ ነበር
" ምን ላድርግ ጓደኛህ ኤደን የምትባል ሰይጣን አጠናፍራዋለች መሰለኝ በተገናኘን ቁጥር ወሬው ሁሉ ከሷ አያልፍም እንዴ እኔ ልጅቷን ሳላውቃት ሁላ እንድጠላት ነው ያደርገኝ በጣም ነው የተጎዳሁት ጆሲ ከቻልክ ጓደኛህን ወይ አሳክመው ወይ ፀበል ውሰደው " ብላው እርፍ አለች ።

ጆሲ ዘወር ብሎ ሲያፈጥምኝ ተነስቼ ካጠገቡ ሄድኩ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ከጆሲ ጋር ስለምንም ነገር ሳናወራ የኤዱ ምርቃት ሰባት ቀን( ሳምንት) ቀረው ።
ስድስት ቀን ሲቀረው ደውላ ቤተሰቦቿ ለምርቃቷ ከሁለት ቀን ቡሀላ እንደሚመጡ እና ከምርቃቷ ቡሀላ አብራቸው ወደ አዲስ አበባ እንደምትሄድ ነገረችኝ ።
ይህ ንግግሯ መብረቅ በሉት ለኔ ።ጨነቀኝ ።
ያን ቀን ጠጥቼ ብገባም እንቅልፍ እንቢ አለኝ እኩለ ለሊት ላይ አንድ ሀሰብ መጣልኝ።
ተነስቼ ለኤዱ ደብዳቤ መፃፍ ጀመርኩ•••
••••• ለኤደን
ኤዱዬ ህይወትን መራራም ጣፋጭም እንድትሆን ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?
እኛ ሰዎች ስላለፈው እና ስለ አሁኑ እንጂ ነገ ምን እንደሚፈጠር እለማወቃችን ነው ።
ነገን አለማወቅ የራሱ የሆነ ብዙ ጥሩም መጥፎም ገፅታዎች አሉት።
ነገ የሚከሰተውን መጥፎ ነገር ቀድመን ስናውቅ እና ነገ የሚከሰተውን ጥሩ ነገር ቀድመን ስናውቅ የሚሰሙን ሁለት ተቃራኒ ስሜቶች ናቸው።
እንዲህ ያልኩሽ አሁን የሆንኩትን ነገር ያኔ በዛ በብርድ እዛ ሆቴል በር ላይ ቆመሽ ባየሁሽ ሰአት ቀድሜ ባውቀው ምን እወስን ነበር ብዬ ሁሌም እራሴን ስለምጠይቀው ነው
"አሁን ምን ሆንክ? ትይ ይሆኖል። ምንም አታውቂምና ጥያቄሽ ልክ ነው የኔ ስስት ያኔ ካሁን ቡሀላ ወንድምሽ ነኝ ስልሽ አንቺም ተቀብለሽ የእውነት ወንድም አድርገሽኛልና ምን ሆንክ ብትይኝ ባንቺ አይፈረድም እኔ ግን ብዙ ሆኛለሁ አንቺን በማፍቀሬ እንኳን አንቺ እኔ እንኳን የማላውቀው ሌላ ዳኒ እንደሆኑኩ አውቃለሁ።
ኤዱዬ አፈቅርሻለሁ!
ይህን ስታነቢ ምን ትይኝ ይሆን?
በቃሌ የማልገኝ እራስ ወዳድ ነኝ አደል ኤዱዬ?
በጣም ይቅርታ።
ከግዜ ቡሀላ ለኔም ባልገባኝ መንገድ ውስጤ ተቀያይሮ ካቅሜ በላይ ሆኖብኝ እንጂ ያኔ ወንድም እሆንሻለሁ ከጎንሽ ነኝ እንደወንድምሽ እይኝ ያልኩሽ ግን ከልቤ ነበር!።
ሁሌም ቃሌን ያጠፍኩ መስሎ ይሰማኛል ላንቺ ስላልነገርኩሽ ምንም ባትይኝም ብታውቅ ምን ትለኛለች እያልኩ ከመሸማቀቅ አልዳንኩም።
ፍቅር የሻቱትን ማግኘት ብቻ አይደለምና የኔ እንደማትሆኚ እያሰብኩም አፈቅርሻለሁ።
ከምንም ነገር በላይ አንቺን በእውኔም በህልሜም ማየት፣ ስላንቺ ማሰብ ፣ ስላንቺ ማውራት ያስደስተኛል ። ካንቺ ውጪ ሁሉ ነገር አልጥምህ ካለኝ ወራቶች ተቆጥረዋል።
"ታድያ በነበረን ግዜ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ከነበርክ እንዴት አልነገርከኝም?
ወይም እንዴት ከፊትህ መረዳት አልቻልኩም? " ትይኝ ይሆናል
በፍቅር ንዳድ ከመለብለብ በላይ በልብ ውስጥ ያለውን የፍቅር እሳት አውጥቶ ላፈቀሩት ሰው ንዳዱን ማሳየት ለብዙ አፍቃሪዎች ከባድ ነው።
እኔን ግን አውጥቶ ከመናገሩም በላይ ከባድ የሆነብኝ ብነግርሽ የሚሰማሽን ስሜት ማሰብ ነው።
ፍቅረኛሽ ሆኜ ቢሆን አሁን ወንድምሽ በመሆኔ የተደሰትሽውን ያክል እምትደሰቺ መስሎ አይታየኝም ።
ካፌ ሻይ ቡና እያልን ፊት ለፊቴ ቁጭ ብለሽ ከናት ካባቴ ባትወለድም አንተን የመሰለ ወንድም በስጦታ ስለሰጠኝ እያልሽ ፈጣሪን ስታመሰግኚ ስሰማ እንኳን ልነግርሽ ማፍቀሬን የምታውቂብኝ እየመሰለኝ ምክንያት ፈጥሬ ካጠገብሽ እሽሻለሁ ።
ጆሲ ጓደኛዬ ምን እንደሚለኝ ታውቂያለሽ ኤዱዬ?
••••" አንተኮ መፍታት ያቃተህ መጀመሪያ ላይ እራስህ አጥብቀህ ያሰርከውን ቋጠሮ ነው አልፈታ ባለህ ቁጥር ደግሞ በንዴት ለመበጠስ እየሞከርክ የበለጠ ታጠብቀዋለህ!" ይለኛል
እውነቱን ነው ትዝ ይልሻል እዱዬ?
ስለመሲ ስናወራ አንድ ሰው ውለታ ውሎልሽ ውለታውን በመንተራስ ከፍላጎትሽ ውጪ የሚጫንሽ ከሆነ ውለታ ሳያስቀድም ተመሳሳይ ጥያቄ ከሚጠይቅሽ ሰው በላይ እርኩስ ነው ብዬሽ ነበር ።
እኔም የፍቅር ጥያቄዬ ካደረኩልሽ ትንሽ ውለታ ጋር እንዳይያያዝብኝ ፈራሁ።
አንቺንም እኔን ወንድም እንጂ ፍቅረኛ የማድረግ ፍላጎት ውስጥሽ ሳይኖር የምጫንሽ ጥያቄዬን ባለመቀበልና እኔን ባለማስከፋት መሀል ሆነሽ የምትጨነቂ መስሎ ታየኝ ።
በዚህ መሀል እናንተ ባታዩኝም ከልጁ ጋር ሆኖችሁ ብዙ ቦታዎች ታጋጥሙኝ ጀመር።
ያኔ በሱም ባንቺም ሳይሆን በራሴ ይበልጥ መናደድ ጀመርኩ ።
ህመምህ መድሀኒት የለውም አትድንም እንደተባለ በሽተኛ የፍቅር ህመሜ ፈውስ የሆንሽውን አንቺን የኔ እንደማላደርግሽ ተረዳሁ ።
ኤዱዬ በመመረቅሽ እንኳን ደስ አለሽ!
በመመረቅሽ የተሰማሽን ደስታ ትንሽ ሳታጣጥሚውና ከድሬ ሳትወጪ አንብበሽው ሌላ ስሜት ውስጥ እንድትገቢ ስላልፈለኩ ነው ይህን ደብዳቤ በእጅሽ ሳልሰጥሽ ከምርቃቷ ቡሀላ ወደ አዲስ አባባ ስሸኛት ሳታየኝ የልብስ ሻንጣዋ ውስጥ አስቀምጥላታለሁ ባየችው ግዜ ትየው ብዬ የወሰንኩት።
በነበረን ስሜት ወንድምሽ ሆኜ ልሸኝሽ ቀናቶች ቀርተዋል ለዛም ተዘጋጅቻለሁ ።
የኔ ኤደን ዛሬም ቢሆን ስላወኩሽ ደስተኛ ነኝ።
የማንም ሁኚ እኔ ግን አፈቅርሻለሁ። መቼም ቢሆን አረሳሽም። ዝምምምም ብዬ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ።
ሰላም ሁኚ!
ዳኒ ነኝ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3
#ልጩህበት!!


#ክፍል_ሀያ_አራት(የመጨረሻው ክፍል)


#ድርሰት_በጥላሁን

ሌላ ስሜት ውስጥ እንድትገቢ ስላልፈለኩ ነው ይህን ደብዳቤ በእጅሽ ሳልሰጥሽ ከምርቃቷ ቡሀላ ወደ አዲስ አባባ ስሸኛት ሳታየኝ የልብስ ሻንጣዋ ውስጥ አስቀምጥላታለሁ ባየችው ግዜ ትየው ብዬ የወሰንኩት።

በነበረን ስሜት ወንድምሽ ሆኜ ልሸኝሽ ቀናቶች ቀርተዋል ለዛም ተዘጋጅቻለሁ ።
የኔ ኤደን ዛሬም ቢሆን ስላወኩሽ ደስተኛ ነኝ።
የማንም ሁኚ እኔ ግን አፈቅርሻለሁ። መቼም ቢሆን አረሳሽም። ዝምምምም ብዬ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ።
ሰላም ሁኚ!
ዳኒ ነኝ።
ደብዳቤውን ፅፌ እንደጨረስኩ ለመውረድ ተጨማሪ ሀይል እየጠበቀ ያቀረረውን እንባዬን ከአይኖቼ ላይ ጠራረኩና ተጠቅልዬ ተኛሁ።

የውስጤን በትንሹም ቢሆን አውጥቼ ስልፃፍኩት ነው መሰለኝ ቅልል ያለኝ መስሎ ተሰማኝ ። እንቃልፍ ይዞኝ ከመሄዱ በፊት ፈጣሪዬ አንተ ያልከው ብቻ ይሁን! አልኩ ። እንቅልፍ ወሰደኝ።
ጥዋት ከንቅልፌ ስነቃ ጆሲ እክፍላችን ውስጥ መሀል ግድግዳ ላይ በሰቀላት ክብ መስታወት እየተመለከተ እርጥብ ፀጉሩን ያደራርቃል ።
በኔ ተናዶ ስለምንም ጉዳይ ከኔ ጋር ማውራት ካቆመ ቢቆይም ላወራው ፈለኩ•••
ጆሲ ለኤደን እኮ ደብዳቤ ፃፍኩላት !
"ተው ባክህ! ምነው ቁልቁል?"
ምንድነው ቁልቁል?
"በቴክኖሎጂ ተሽቀንጥሮ የተጣለውን የፍቅር ደብዳቤ መፃፃፍ ኬት ፈልገህ አገኘከው ብዬ ነዋ!"
የመረጥኩት መንገድ እሱን ስለሆነ ከወደቀበት አነሳሁት!
"ምርጫህ ከሆነ ይሁን ግን ምነው ፈጠንክ ገና ከመተዋወቃችሁ!"
እያላገጥክ ነው ጂሲ?
"እያላገጥክ ያለኸው እማ አንተ ነህ ዳንዬ እሄን ሁሉ ግዜ በፍቅሯ ፍዳህን ስታይ ቆይተህ
አንተስ ወደህ ነው ባንተ እንደዛ መሆን እኔንም ቤተሰቦችህንም በጭንቀት ስትንጠን ከርመክ አሁን ልጅቷ ትምህርቷን ጨርሳ አንተንም ሀገሩንም ጥላ ልትሄድ ቀናቶች ሲቀሯት ምን ብለህ ልትፅፍላት ነው ?
እባክሽ ጥለሽኝ አትሂጂ ወይ ተያይዘን እንሂድ ልትላት ነው?
ቆይ በዚህ ሰአት ምን ልትላት ነው!?
አፈቅርሻለሁ ነው አፈቅርሽ ነበር ?"
ጆሲ በቃህ እንግዲህ አታናደኝ !
ከተረዳኸኝ እኔ ለሷ ያለኝ ፍቅር እሷን በማግኘትና በማጣት የሚወሰን አይደለም !
የትም ትሁን የማንም ትሁን አፈቅራታለሁ!
ደሞም ደብዳቤውን የፃፍኩት አሁን ልሰጣት አይደለም!
"ምን ማለት ነው ? ከሄደች ቡሀላ በፖስታ ቤት ልትልክላት ባልሆነ!"
ለምን አይሆንም ?ቢሆንስ?
" እንዴ ታድያ ለምን መፃፉ አስፈለገህ ዝም ብልህ እንዲሁ ፍቅር ዲዳ ያረገህ ይመስል ትንፍሽ ሳትል እንደተለጎምክ ለምን አትሸኛትም?
አዋ እንደተለጎምኩ እሸኛታለሁ ከልጁ ጋር ፍቅር እንደጀመሩ እርግጠኛ ነኝ የኔ ላትሆን ላስጨንቃት አልፈልግም !
"ታድያ እንደዛ ካሰብክ ተዋታ ! እርሳታ በቃ ደብዳቤውን እዛ ደርሳስ ቢሆን ስትልክላት ማንበባቧ ይቀራል እንዴ ያኔስ አትጨነቅም ነው የድሬዳዋ እና ያዲስ አበባ ጭንቀት ይለያያል!"
ጭንቀቱ ላይለያይ ይችላል ያንን የማደርገው በሁለት ምክንያት ነው
አንድ አሁን በመመረቋ የተሰማትን ደስታ ላለመረበሽ
ሁለተኛው እና ዋናው ምክንያቴ ደግሞ ተመርቃ ከሄደች ከኔ ምንም ነገር በማትፈልግበት ሁኔታ ውስጥ ስትሆን ለመወሰን ነፃ ትሆናለች
"አየህ አሁንም ዙረህ ዙረህ ቋጠሮው ጋር ሄድክ ዳንዬ እሄን ቋጠሮ መፍታት ወይ መተው ካልቻልክ በሷ ጉዳይ ከኔ ጋር መቼም አንግባባም "
ብሎኝ ጥሎኝ ወጣ። እሱ ባይሰማኝም
እንኳን ካንተ ጋር ከራሴም መግባባት አልቻልኩም ጓደኛዬ ይቅርታ ስላስጨነኩህ አልኩ ለራሴ።

የኤዱ ቤተሰቦች ድሬ ዳዋ ከመድረሳቸው ከሰአታት በፊት ያ ከመደብደብ ያተረፈኝ ጥበቃ ወደ ሚሰራበት ሆቴል ሄድኩና አልጋ ያዝኩላቸው ስገባ አለነበረም ስወጣ ገና ከሩቅ ሲያየኝ መሳቅ ጀመረ አጠገቡ ስደርስም•••
" ካካካካ ስማ እኔ እኮ እነዛን ልጆች አውቃቸዋለሁ ያን ቀን የባጥ የቋጡን ቀባጥሬ ባላስመልጥህ ለቀብር እሚሆንም እንኳን አያስቀሩልህም ነበር
የት እንደማውቃቸው ታውቃለህ•••"
ብሎ ሊቀጥል ሲል እኔም ፈገግ እያልኩ አቦ ሌላ ግዜ በሰፊው እናወራለን እሺ ከአዲስ አበባ የሚመጣ እንግዳ ልቀበል ነው ደርሰዋል ብየው የሻሂ ሰጠሁትና ሄድኩ።
ከኤዱ ጋር ሆነን ቤተሰቦቿን እየጠበቅን ያ ልጅ በየደቂቃው ይደውል ነበር ስታናግረውም ከኔ ፈንጠር እያለች ነበር ቤተሰቦቿ ደርሰው በኔው ባጃጅ ወደ ያዝኩላቸው ማረፊያ ሄድን ።
እንደደረስን •••
"እማ ዳኒ ማለት እኮ እሱ ነው " አለች እናትና አባቷን በየተራ ልብ በሚሰውረው ፈገግታዋ እያቻቸው።
አቤት ምርቃት እናትና አቧቷ እየተቀባበሉ የመረቁኝ ምርቃት ሰምቸው ሁላ አላውቅም ካሁን ቡሀላ በሂወት ዘመኔ ማንም እኔ ነኝ ያለ ተራጋሚ የፈለገውን አይነት እርግማን ቢረግመኝ እራሱ እሄን ምርቃት አሸንፎት እንደማይደርስብኝ እርግጠኛ ነኝ።
ኤዱ በተመረቀችበት እለት መሄዷን እያሰብኩ ውስጤ ሀዘን ቢሰማውም መመረቋ በሷና በቤተሰቦቿ ፊት ላይ የማየው የደስታ ጥግ ግን ሀዘኔን ለግዜውም ቢሆን አክሽፎት ደስታቸውን ለመጋራት ተገደድኩ።

እንዳትደርስ የፈራኋት የመጨረሻዋ ሰአት ደረሰች።
እኔና ኤዱ በኔ ባጃጅ ወደ ግቢ ሄድንና ከግቢ ያመጣቻቸውን ሻንጣዋን ጨምሮ ሌሎች የግል እቃዎቿን ባጃጇ ውስጥ አስገብታ•••
"ዳኒዬ መጣሁ እሺ ጓደኛቼን ልሰናበታቸው" ብላኝ ሄደች።
ደብዳቤውን ከውሃላ ኪሴ አወጣሁና የልብስ ሻንጣዋን ከፍቼ ልብሶቿ መሀል አርቄ ቀበርኩት።
ሀሙስ ከለሊቱ 10:30 ድሬ ዳዋ የድሮ ባቡር ጣብያ ፊት ለፊት ባጃጄን ተደግፌ ቆሚያለሁ
ከኔ ፊት ለፊት እነ ኤዱን ይዞ ወደ አዲስ አበቧ የሚነጉደው ዘመናዊ አውቶብስ የተሳፋሪዎቹን እቃ ከታች ሆዱ ውስጥ ተሳፋሪዎቹን ደግሞ ከላይ ጭኖ ለመምዘግዘግ መዘጋጀቱን በሚያጓራው ድምፁ ያውጃል።
ኤዱ አንዴ ከኛ ራቅ ብለው የያዙትን እቃ ወደሚያስመዝኑት ቤተሰቦቿ አንዴ ውስጤ ትርምስምስ እንዳለ ባጃጄን ተደግፌ ወደ ቆምኩት ወደኔ ሄድ መለስ ትላለች ።
ግራ ግብት! ጭንቅ !እንዳላት ታስታውቃለች ።
ያን ስሜት የፈጠረባት የኔ ሁኔታ ሳይሆን አይቀርም ።
ምንም ማውራት ሳንችል በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ካቅማችን በላይ ሆነና መላቀስ ጀመርን በቃ ተላቀስን እሷን እያባበልኩ እኔ አለቀስኩ።
እኔን እያባብለች እሷም አለቀሰች ።
ተለያየን ሄዱ ።
በሄደች በአራተኛው ቀን ስልኬ ላይ በማላውቀው ቁጥር ተደወለ አነሳሁት ••• ኤዱ ነች•••
"ዳንዬ ቆይ ለምን ለምን ለምን " ብቻ ብላ ማልቀስ ጀመረች ደብዳቤውን አግኝታ አንብባው እንደሆነ ገባኝ ።
በስልክም ከመላቀስ ውጩ ብዙ ማውራት አልቻልንም ነገር ግን በሷ ምክንያት በመጎዳቴ እጅግ ማዘኗንና ከልጁ ጋር በፍቅር አብራ መሆኗን ነገረችኝ ለኔ አዲስ አልነበረም በነበርኩበት ከባድ የድብርት ሂወት ቀጠልኩ።
ይህ ከሆነ አንድ አመት ከሁለት ወር እንደሆነው
እንደሁልግዜው ማታ በስካር ጥንብዝ ብዬ ገብቼ ተኝቻለሁ እዛው እንደተኛሁ ከቀኑ አምስት ሰአት አከባቢ ከተኛሁበት በሀይል ተቀሰቀስኩ ብንን ስል ጆሲ ጓደኛዬ እና የኔዋ ኤደን አጠገብ ላጠገብ ቆመዋል።
ወይ መቃዥት አልኩና አይኔን እየጠራረኩ ከተኛሁበት ብድግ ብዬ ቆምኩ አሁንም ፊት ለፊቴ ጎን ለጎን ቆመዋል።ግን ዝም ብለው ያዩኛል እንጂ ትንፍሽ አይሉም።
ያበድኩ የለየልኝ መሰለኝ።ወደ ጆሲ ተጠጋሁና ነካ አደረኩት ።ያኔ ባሰብኝ።ለራሴ አዘንኩ እንባዬ በሁለቱም አይኖቼ ግጥም አለ። የጆሲንም እንባ ያየሁት መሰለኝ።
ጆስዬ በናትህ ተንፍስ!?
ጆሲ እባክህ እውነት ነው እየቃዥህ አይደለም በለኝ ።
ህልም ነው እንዳትለኝ እሺ ጆሲ?
አጠገቤ የቆመችው ያንተዋ ኤደን ነች በለኝ
ተወርውራ አንገቴ ላይ
👍2
​​ተጠመጠመች !።
"አዎ ዳንዬ ያንተዋ ኤደን ነኝ ሁሉንም ነገር ትቼ ወዳንተው መጥቻለሁ ።
እጠብቅሻለሁ ብለከኝ የለ ዳንዬ አረሳከኝም አደል? ዛሬም ታፈቅረኛለህ አይደል ዳንዬ?"
አፏን አፍኜ አቋረጥኳትና እንባዋን እየጠራረኩ ወደ ጆሮዋ በመጠጋት አንድ ጥያቄ ብቻ ልጠይቅሽ ኤዱዬ አልኳት።
እሺ አለችኝ አፋን ስላፈንኳት ጭንቅላቷን እያወዛወዘች ።
አንዴ ልጩህ በናትሽ?????

💫ተፈፀመ💫

በአጨራረሱ ዙርያ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት በ @atronosebot በኩል እጠብቃለሁ።
አትሮኖስ pinned «#ልጩህበት!! ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አራት(የመጨረሻው ክፍል) ፡ ፡ #ድርሰት_በጥላሁን ሌላ ስሜት ውስጥ እንድትገቢ ስላልፈለኩ ነው ይህን ደብዳቤ በእጅሽ ሳልሰጥሽ ከምርቃቷ ቡሀላ ወደ አዲስ አባባ ስሸኛት ሳታየኝ የልብስ ሻንጣዋ ውስጥ አስቀምጥላታለሁ ባየችው ግዜ ትየው ብዬ የወሰንኩት። በነበረን ስሜት ወንድምሽ ሆኜ ልሸኝሽ ቀናቶች ቀርተዋል ለዛም ተዘጋጅቻለሁ ። የኔ ኤደን ዛሬም ቢሆን ስላወኩሽ ደስተኛ…»
#ኤጭ_ወድያ

እንዲህ ከሆነ እኔ
ይቅርብኝ መሠልጠን ማወቅ መዘመኔ
መጫጫስ መታጠን ጉንጭ መወገሩ
ፏ ብትን ማለቱ በሺሻ በጫቱ
መስከር መንገዳገድ በዬ ስራ ስሩ
መጓተት መጋደም ቀየምናምኑ
ራስን ሳይሆኑ
ይህማ ከሆነ የዝማኔ ጣጣ
ባፍንጫዬ ይውጣ
አልወቅ ግዴለም
ይሁን ፋርነቴ አይግባኝ ዘላለም።

🔘በሰላም ዘውዴ🔘
🥰2
#ወለምታ

የቃላት ጦርህን ወርውረህ ስትወጋ
ውስጥን ስታሳምም ልብን ስታደማ
አጥንት ስታናጋ፣
አሁን ምንተገኘ ይሆን እሺ እሚያስበል
አልገባህም እንዴ የምላስ ወለምታ
በእሺታ እንደማይድን።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ሽንቁር


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

እያፈርኩ ለሰው አላወራውም እንጂ፣ ረዥም የትዝታ እጁን እየላከ፣ የዛሬ ኑሮዬን
የሚፈተፍትና ከአእምሮዬ የማይጠፋ አንድ ጉዳይ አለ፡፡ በየቀኑ በምክንያትም
ካለምክንያትም ውልብ እያለ ትዝ ሳይለኝ ውሎ አያውቅም፡፡ ቆይቷል ከዚያ ወዲህ ስንትና ስንት ነገር በዕድሜዬ ማገርና ቋሚ ላይ እንደ ጭቃ ተለስኖ፣ እንደ አሸዋና ስሚንቶ ተገርፎ፣ ደንዳና ወጣት ሆኛለሁ፡፡ ግን ያ ትዝታ ዛሬም ድረስ ከነትኩስነቱ፣ልቤን እንደ ቃልቻ ድቤ ከሚያስደልቃት ፍርሀት ከቀላቀለ ጉጉቱ ጋር በውስጤ ተዝናንቶ ተቀምጧል፡፡ ለማንም አላወራሁትም፤ እንኳንስ ለሌሎች ላወራው፣ ለራሴም እንደ ፎቶ
ካሜራ ብርሃን ብልጭ ከሚል ቅጽበት አልፎ በውስጤ ቃል ሆኖ እንዳይወለድ ፊት ነስቼው ነው የኖርኩት፡፡

ትምህርት ቤት የተዘጋበት የክረምት ወቅት ነበር፡፡ ያ ክረምት ከዚያ በፊት
እንዳሳለፍኳቸው የተለመዱ ዓይነት የክረምት ወቅቶች አልነበረም - ለእኔ፡፡ የሆነ ነገሬ ላይመለስ የተቀየረበት ክረምት ነበር፡፡ ከሰፈር ልጆች ጋር ተሰባስበን ጭቃውን ከሰማይ
እንደ ወረደ መና በጉጉት እያድበለበልን የምንወራወርበት ክረምት አልነበረም፣ በጭቃ እና በውሃ የላቆጠ ኳስ እየጠለዝን የምንጨዋወትበት ክረምት አልነበረም፡፡ በዚያ ክረምት የስምንተኛ ክፍል “ሚኒስትሪ” ፈተና ወስደን፣ ወደ ዘጠነኛ ክፍል የመሸጋገሪያ ወቅታችን ላይ ነበርን፡፡ በየክረምቱ የምናቋቁመውና በየዓመቱ እየፈረሰ እንደገና የምንመሠርተውን የእግር ኳስ ቡድን እንደገና ለመመሥረት ቸል ያልንበት ክረምት ነበር፡

ይልቅ ኳስ ተከትለው የሚቃብዙ፣ በድንጋይ መትተን የምናባርራቸውን ወፎች አንጋጠው በየዛፉና በየቤት ጣሪያ ላይ የሚፈልጉ፣ ዓይኖቻችን፤ ተልከው በሚያልፉና እኮዮቻችን በሚሆኑ ልጃገረዶች ላይ የሚንከራተቱበት፣ ከፍ ባሉና በደረሱ ሴቶች ላይ
የሚንከባለሉበት ልዩ ክረምት ነበር፡፡

እንዴት ነው ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ቀናት ይኼን ሁሉ ለውጥ ያመጡብን!?
እንዲያውም ብዙዎቻችን በቁመትም በክብደትም ቅንጣት ታህል ጭማሬ ሳናሳይ፣ምናችን ነው እንዲህ ከውስጣችን ተቀይሮ አዲስ ዐመል ያሸከመን!? ዛሬም ድረስ የጉርምስናችን ቅኔ ለምን በዚያች ክረምት እንደተቀኜ፣ ባወጣ ባወርድ አልተገለጠልኝም ብቻ ስንጎረምስ ትዝ ይለኛል በዚያ ክረምት ነበር የጎረመስነው፡፡ ልክ ሰው ቁመቱ
ያደገባትን ቀን፣ ሰዓትና ደቂቃ ሂደቱን ሳይሆን ቅጽበቱን፣ እንደ ሬዲዮ አንቴና ድንገት ቁመቴ የተመዘዘባትን ቅጽበት አስታውሳታለሁ ቢል እንደሚገርመው፤ የጎረመስንባትን ጧት ማስታወሴ ይገርመኛል፡፡ እንግዲህ ተመልሼ ሳሰላው አሥራ ስድስት ዓመት ገደማ ሆነው ፡፡

አንድ ጧት፣ ፈተና እንደ ትላንት ጨርሰን እንደ ዛሬ፣ አባ ኃይሉ በረንዳ (አባ ኃይሉ፣
ሸገኔ ሱቅ የምትባለው ባለቤት ናቸው ... ከሱቋ ግራና ቀኝ ረዥም የግንብ ውሃ ልክ
ያላት፣ አንዳንዴ ሰው እንዳይቀመጥበት የተቃጠለ ጥቁር ነዳጅ የሚፈስበት ድድ ማስጫ ነገር) አምስት የምንሆን የሰፈር ልጆች (አዲስ ምልምል ጎረምሶች) ተቀምጠናል፡፡ አላፊ አግዳሚውን እየቃኘን ነበር፡፡ የዚያኑ ቀን ገና ዓይናችን በተአምር የበራልን ይመስል፣ሁሉን ነገር፣በተለይ ግን ሁሉን ሴት፣በተለይ ሁሉን ወጣት ሴት በጉጉት እንመለከታለን፡፡
እኛ ትምህርት ቤት ታጉረን ስንውል፣ ምን መድኃኒት ሲረጩባቸው ነው ሴቶቹ ሁሉ
እንዲህ ያማሩት!? ሳንል አልቀረንም! ... በሦስት መቶ ስልሳ አምስት ቀናት ምን የሚሉት ኬሚስትሪ በሰውነታቸው ውስጥ ቢቀናበር ነው፣ ቅልቦሽ ሲጫዎቱ የነበሩ የሰፈራችን ሴቶች እንዲህ ሙሉ ሴት ሆነው አረማመዳቸው ተቀይሮ ሽንጣቸው የሚመዘዘው?!..
ጡቶቻቸው ከፊት ቀድመው እየተንሳፈፉ አየር የሚያነፈነፉት? ለምንስ ነው የቡሄ ዳቦ ሲናጠቁን፣ ማስቲካና ከረሜላ እንድናካፍላቸው ሲለማመጡን እንዳልነበር ዓይናችንን
ማየት አፍረው በመሽኮርመም አየት የሚያደርጉንና ሳያናግሩን የሚያልፉት? በዚያ የዘነበው ዝናብ ምን ተአምር ተበጥብጦበት ነበር? ..
ያኔ ነው በማየት ሱስ ተለከፈን በበረንዳዋ ፍቅር የወደቅነው፡፡ ሕይወት ጦርነት ነው፣
አነሰም በዛም እኛም ወታደሮች፤ያች በረንዳ የወላጅና የበላዮቻችንን “አትንኩ!
አትቅመሱ!” ትእዛዝ በዓይንም ቢሆን ልንጥስ የከተምንባት ምሽጋችን ነበረች፡፡ ፀሐይ ገብታ ቀኑ ሊመሻሽ ሲል፣ ተሰባስበን በረንዳዋ ላይ እንኮለኮላለን (ኮልኮሌ ሁሉ! ይሉናል የበረንዳዋ ባለቤት አባ ሃይሌ)

ሰባተኛ ክፍል ሦስት ጊዜ ደግማ፣ “የማታ ትምርት” ቢሻላት ተብሎ የማታ ተማሪ
የሆነችው ህሊና የምትባለው የሰፈራችን ልጅ፣ አንዲት ደብተር በቄንጥ አንጠልጥላ ፣አቋሙ ከሚያምር ልጅ ጋር ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ አይተናል፡፡ ደግሞ ሲመሻሽ፣ሲራመድ ጎበጥ-ጎበጥ ከሚልና፣ በቁመት ከሚያንሳት ልጅ ጋር ከትምህርት ቤት ስትመለስ፣ ቀይ ብርሃን እየተፉ መንገዱን በቀይ ወጋገን በሚያጨቀዩት የመንገድ ዳር
መብራቶች የበለጠ አምራ አይተናል፡፡ በየቀኑ የሚወስዳት ሌላ፣ የሚመልሳት ሌላ ወንድ ሲንጋጋ ታዝበን “በትምህርቷ የሰነፈችው ከወንዶች ጋር እየተንዘላዘለች ነው” የሚባለውን የሰፈራችንን ሐሜት እውነት ነው ብለን አምነናል ደግሞ ሰሎሜ የምትባል ቆንጆ ቀይ ሴትዮ (ከሰፈራችን ነዋሪ ሁሉ ብቸኛ የመንግሥት ሥራ ያላትና ጉልበቷ ላይ የሚቆም
ጉርድ ቀሚስ የምትለብስ ባለትዳር ሴት) ከባሏ አስታጥቄ ጋር ከሥራ ሲመለሱ የዕለት ትዕይንታችን የዘወትር ግብአት ነበሩ! ሁልጊዜ በፌስታል የሆነ ነገር አንጠልጥለው ነበር ወደቤት የሚገቡት፡፡
ፍቅረኛሞች ከባለትዳሮች የሚለዩት፣ ወደ ቤት ሲገቡ አንዳች ነገር
በማንጠልጠል ሳይሆን አይቀርም!
ለእኔ ግን የዘወትር የዓይኖቼ ርሃብ አንዲት ሴት ነበረች፤ ፖሊስ ናት፡፡ ኢንስፔክተር
መንበረ የምትባል፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ ያች ሴት ስታልፍ ካላየሁ፣ ቋጥኝ የሚያህል ድብርት ተጭኖኝ ነበር ወደ ቤቴ የምገባው፡፡ ደግነቱ ከሰፈራችን በላይ ከነበረው አራተኛ
ፖሊስ ጣቢያ፣ ልክ 1፡30 ሲሆን ወጥታ፣ በፈጣን እርምጃ በመንገዱ ማለፉ አይቀርም፡፡ የእግሮቿ ፍጥነት፣ ፊቷ ላይ
ሁልጊዜ የማይጠፋው ኮስታራነት እና፣ ሁልጊዜም ከሩቅ፣ዓይኔ ውስጥ ከምትገባበት ርቀት ጀምሮ፣ አልፋን ከዓይኔ እስከምትጠፋበት መታጠፊያ
ድረስ፣ የመንገዱን ግራ ይዛ ቀጥ ያለ መስመር ተከትላ መራመዷ፣ ተራማጅ ቅርፅ እንጂ ሰው መሆኗን ያጠራጥረኛል፣ሁልጊዜ መስመሯን አለመቀየሯ ይገርመኛል፡፡ አንዳንድ
ለሕዝብ ተብሎ በተሠራው መንገድ ላይ፣ ለሷ ብቻ ተብሎ ለሌሎች በማይታይ ሥውር ቀለም የተሰመረ የሐሳብ ሐዲድ ያለ እስኪመስለኝ እርምጃዋ ዝንፍ አይልም ሰዎች ሰላም ሲሏት(ሁልጊዜ ሰላም የሚሏት ሰዎች ይሽቆጠቆጣሉ) የእርምጃዋን ፍጥነት፣የፊቷንም ገጽታ ሳትቀይር፣ እጇን ብቻ በፍጥነት ከፍ አድርጋ እና አንገቷን ሰበር አድርጋ
ታልፋለች፡፡ ታዲያ ይህች ሴት እንደ ሰው እቤቷ ሄዳ አድራ የምትመጣ ሳይሆን፣
እንዲሁ በዚሁ እርምጃ ይህችኑ መስመር ተከትላ፣ ዓለም ጥግ ድረስ እየተራመደች፣ ዙራ ጧት በዚሁ የምትመለስ ዑደት ነገር ትመስለኝ ነበር፡፡

ኢንስፔክተር መንበረ ከብዙዎቹ ከማውቃቸው ሴቶች ረዘም ያለች፣ የፖሊስ ጉርድ ካኪ ቀሚስ፣ አንዳንዴም ሱሪ የምትለብስ፣ ሁለቱም የሚያምርባት፣ ቀጭን ወገቧ ላይ ሰፊ ብርማ የብረት ዘለበት ያለው የሸራ ቀበቶ የምትታጠቅ ቀበቶው ላይ በግራ በኩል( ሽጉጥ ከነማኅደሩ የሚንጠለጠልበት) ፀጉሯን ጠቅልላ ጀልባ የመሰለች የፖሊስ ኮፍያ
ጣል የምታደርግ፣ ዕድሜዋ ቢበዛ በሃያዎቹ መጨረሻ አልያም ሠላሳ የሚሆናት ሴት ነበረች መርማሪ ናት ይላሉ ለምን እንደሆነ
👍1
እንጃ፣ የእግሮቿን ጥርት ያለ ጠይምነት እና፣ የፖሊስ ዩኒፎርሟን ንጽሕና ስመለከት፣ ያውም ከነማዕረጓና ከነሽጉጧ፣ የፖሊስ
ልብስ መልበሷን እያየሁ እንኳን፣ ለእኔ ግን ነርስ ትመስለኛለች፤ የምትመረምረው
በሽተኞችን ይመስለኛል፡፡ እሷን ማየት ነበር ሱሴ፡፡
የሁላችንም ቤተሰቦች እዚያች በረንዳ ላይ መሰብሰባችንን አይወዱትም፡፡ ሂዱና የአባ
ኃይሌን በረንዳ አሙቁ” እያሉ ይነጫነጩብናል! በተለይ የእኔ እናት “ተጎርምሶ ተሞተ!
የማንም ዱርዬና ሌባ መሰብሰቢያ በረንዳ ላይ መሄድህን ተው ብያለሁ፣ ኋላ አንዲት ነገር እሰማና፣ ውርድ ከራሴ!” ትለኛለች፡፡ መልስ አልሰጣትም፡፡ ሲመሻሽ ከጓደኞቼ ጋር እዚያው ነኝ፡፡ የሱቁ ባለቤት አባ ኃይሌ አጭር፣ ክብ የቴክሳስ ኮፍያ የሚደፉና ባለቀጭን ጥለት ነጠላ የማይለያቸው ኮስታራ ሽማግሌ ናቸው፡፡ ኮስታራ ብቻ አይደሉም፣ ነጭናጫም ጭምር ናቸው፡፡ ወርቃማ እጄታ ያላትን የምታምር ከዘራቸውን ክንዳቸው ላይ አንጠልጥለው (ሁልጊዜ አይመረኮዙባትም) የሱቋን ዙሪያ ይቃኛሉ፡፡
በተለይ ከጎረቤት ጋር የምታወስነዋን ድንበር በጥንቃቄ ነው የሚመረመሯት፡፡ በዚሁ ድንበር ብዙ ዓመት ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል፡፡ (ጉቦ ሰጥተው ነው ያሸነፉት እንጂ ሱቁ የተሠራበት ግማሽ ቦታ ጭምር የቅመም ሻጩ ጎረቤታቸው የጋሽ ውበቱ ድንበር ነበር
እየተባለ ይታማል)

ኧረ በሕግ አምላክ ወዲያ ሂዱልኝ እናንተ ልጆች!…በሩ ላይ ተኮልኩላችሁ ገበየተኛው በየት በኩል አልፎ ይገበያይ"?ይላሉ:: ድምፃቸው ከዚያች አጭር ሰውነት የሚወጣ አይመስልም፣ አስገምጋሚ ነው፡፡ ለዓይናቸው አይወዱንም፡፡ ወዲያው ከፊታቸው ዞር
እንልና በቀጣዩ ቀን ግን እዚያው ነን፡፡ በረንዳቸው ላይ መቀመጣችንን እንደማይወዱት እናውቃለን፡፡ እንዲያውም በየጊዜው የተቃጠለ ነዳጅ ከጋራዥ እያስመጡ ግንቡ ላይ ያስፈስሱበታል፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው፣ መቀመጡ ይቀራል እንጂ እዛው ቁመን የዕለት
ሱሳችንን ማድረሳችን አይቀርም፡፡ ዛሬም ድረስ ሱቁ ፈርሶ ትልቅ ሕንጻ ተሠርቶበት፣
ከሕንጻው መስተዋቶችና መግቢያው ላይ ከሚኮለኮሉት የሀብታም መኪኖች ይልቅ፣ ያች ጉርምስናችን ተወልዳ እትብቷ የተቀበረበት፣ ነዳጅ ያጠቆራት በረንዳ ገዝፋ ትታወሰኛለች፡፡ ዛሬ ወደ ሕንጻው ጎራ ከሚሉ በመዋቢያና በውድ ልብሶች ከተሸቀረቀ ሀብታምና ውብ ሴቶች ይልቅ፣ ያኔ የሻይ ቅጠልና ቡና ሊገዙ ከመንደሮቹ ውስጥ ወደ ሸገኔ ሱቅ ብቅ የሚሉ የተፈጥሮ ለዛቸው ከዕድሜ ትኩሳታቸው ጋር ከሩቅ የሚጣራ ወጣት ሴቶች ትዝ ይሉኛል፡፡መቼስ ለትዝታ ሩቅ የሚባል ..ላለመድረስ ከፈለጉም
ቅርብ የሚባል ቦታ የለም፡፡

አንድ ምሽት እንደ ልማዳችን አባ ኃይሌ በረንዳ ላይ ተኮልኩለን የባጥ የቆጡን
እናወራለን፡፡ እያወራን፣ የሌሎቹን እንጃ፣ እኔ ግን በዓይኔ ኢንስፔክተር መንበረን
እጠብቃለሁ፡፡ ቀኑን ሙሉ የክረምት የማይመስል ኃይለኛ ፀሐይ ወጥቶ ስለነበር፣ የተቀመጥንበት ግንብ እንደወትሮው አይቀዘቅዝም፡፡ የበረንዳው ውሃ ልክ ከሰዓት በኋላ የማታ ፀሐይ ሲቀጠቅጠው ስለሚውል ሁልጊዜም ለሰስ ያለ ሙቀት ነበረው፡፡ እሱም
ይሆናል አንዱ ምቾታችን፡፡ የምናወራውን እንጃ ብቻ የሞቀ ወሬ ላይ ነበርን፡፡ ድንገት
እዚያው አጠገባችን የአንዲት ሴት ኡኡታ አካባቢውን አደበላለቀው፡፡ “ኡኡኡኡ
ተዘረፍኩ! ጉድ ሆንኩ! ሌባ ሌባ ሌባ …” የባህል ቀሚስ የለበሱ ወፍራም ሴት ነበሩ፡፡ከዛ ወፍራም ሰውነት እንደዛ ጆሮ የሚወጋ ቀጭን ድምፅ መውጣቱ ይገርማል፡፡ ደግሞ እሪታቸው መርዘሙ እልልታ ነበር የሚመስለው፡፡ ሰው የሚጮሁትን ሴትዮ ከበው በጥያቄ ያጣድፏቸው ገባ

“ምንድነው?” “ሌባውን አይተሽዋል?” ሴትዮዋ ለቅሶ በተቀላቀለበት ድምፅ እየጮሁ፣ እኛ ወደተቀመጥንበት ጠቁመው፡፡

“ቦርሳዬን ቀምቶኝ ሮጠ አይቼዋለሁ፣ ተነሱ መኻል ነው ተነስቶ የመጣው አሉ፡፡
እግዚኦ!! የተሰበሰበው ሕዝብ እንዳለ ወደኛ ዞረ፡፡ እኔ እንደ በረዶ ገግሬ ከተቀመጥኩበት እንኳን መነቃነቅ አቃተኝ፡፡

አንድ ሽበታም ሰውዬ “ያዙዋቸው! ወመኔ ሁሉ!” ብለው ፉከራ በሚመስል ድምፅ
ሲጮሁ፣ ጓደኞቼ እንደ አንዳች ነገር ከጎኔ እየተስፈነጠሩ እግራቸው ወደ መራቸው
ተፈተለኩ፡፡ አንዱ ጓደኛችን፣ እንዲያውም መንገዱን አቋርጦ ሲሮጥ፣ እየተግለበለበ የሚያልፍ ታክሲ ሊገጨው ለጥቂት ተረፈ… ሲጢጢጢ! የሚል የመኪና ጎማ ድምፅ ከሰው ጫጫታ ጋር ተዳምሮ፣ አካባቢው ባንዴ በጩኸት ተደበላለቀ፡፡
በደነዘዝኩበት አንድ ጠንካራና የሚሞቅ እጅ፣ ከእጅጌ ጉርድ “ቲሸርቴ” ሥር ራቁት ክንዴን አፈፍ ሲያደርገኝ፣ ቀና ብዬ የያዘኝን ሰው ተመለከትኩ ..ኢንስፔክተር መንበረ ነበረች።መያዜም ሳይሆን፣ ጩኸቱም ሳይሆን፣ ኢንስፔክተር መንበረ ሐዲዷን ስታ እኔ አጠገብ መቆሟ ትንግርት ሆነብኝ ….ምድር ምህዋሯን ሳተች የተባልኩ ይመስል፡፡

ማመን አልቻልኩም፡፡ ከዚያች ቀን በፊት፣ እንኳን መታሰር፣ የታሰረ ሰው ለመጠየቅ
ፖሊስ ጣቢያ ደጅ ረግጨ አላውቅም ነበር፡፡ ኢንስፔክተር መንበረ ክንዴን አጥብቃ እንደያዘችኝ ከሰፈራችን አለፍ ብሎ ወደሚገኘው አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ስትወስደኝ፣ ዙሬ እንኳን ላያት ፈራሁ፡፡ አቀርቅሬ ተራ በተራ በፍጥነት በአስፋልት መንገዱ ላይ የሚያርፉትን ተወልውለው የሚያንጸባርቁ ጉርድ ጥቁር ቆዳ ጫማዎቿን እያየሁ፣ ከጎኗ
ሱክ ሱክ እላለሁ፡፡ በሰፋፊው ነው የምትራመደው፡፡ ፖሊስ ጣቢያው የተመሠረተው፣አንድ ሲያዩት የሚጨንቅ፣ ሙሉውን ከድንጋይና ከሰፋፊ ጣውላ የተሠራ የድሮ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ የአንድ ቀኝ አዝማች ይሁኑ ግራ አዝማች መኖሪያ ቤት የነበረና፣ በደርግ ዘመን የተወረሰ ነው ይባላል፡፡ ሰውዬው ይሄን ቤት ተወረስኩ ብለው፣ በደም ግፊት ይሁን በልብ ድካም እንደሞቱ ይነገራል፡፡ የልብ ምቴን ሳዳምጥ ይኼ ገፊ ቤት እኔንም እንደ ባለቤቱ ሊደፋኝ ይሆን ብዬ ሰጋሁ፡፡ ከእርጅናው ብዛት የተነሳ የወለሉ ንጣፍ..

💫ይቀጥላል💫
አትሮኖስ pinned «#ሽንቁር ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም እያፈርኩ ለሰው አላወራውም እንጂ፣ ረዥም የትዝታ እጁን እየላከ፣ የዛሬ ኑሮዬን የሚፈተፍትና ከአእምሮዬ የማይጠፋ አንድ ጉዳይ አለ፡፡ በየቀኑ በምክንያትም ካለምክንያትም ውልብ እያለ ትዝ ሳይለኝ ውሎ አያውቅም፡፡ ቆይቷል ከዚያ ወዲህ ስንትና ስንት ነገር በዕድሜዬ ማገርና ቋሚ ላይ እንደ ጭቃ ተለስኖ፣ እንደ አሸዋና ስሚንቶ ተገርፎ፣ ደንዳና ወጣት…»
#ጨለማ_እና_ብርሐን

ተፈጥራዊውን ሐቅ በውል ሳያስሰው
ውስብስቡን ምስጢር በወግ ሳይዳስሰው
የብርሃንን ሐይል ከፅልመት ሲያረክሰው
ፋይዳ ቢስ አርጉ ዋጋ ሲያሳንሰው
ማሾ ይዞ ወጣ ሰው የቸገረው ሰው።
እውነት በሌለበት
በገበያ ሥፍራ ከሚርመሰመሰው
ሳያገኝ ቀረና እንድ እውነተኛ ሰው
እውነት የጠፋበት
እውነቱን ፈላጊ ተቆጥሮእንደዘበት
ገብያተኛው ሁሉ በሳቅ አፌዘበት ።
ከሀቅ ያለያያል
እንደቂል ያሳያል ገበያ መሐል ላይ
የማሾ ብርሐን በጠራራ ፀሐይ።
ረቂቅ እውነቱ የብርሐን ውበት
ጎልቶ የሚወጣበት ደምቆ የሚታይበት
ነፍስ የሚዘራበት የሚሰጠው ሕይወት
ጨለማው እኮ ነው ድቅድቁ መስታወት።
1👍1
#ሽንቁር


#ክፍል_ሁለት(የመጨረሻ ክፍል)


#በአሌክስ_አብርሃም

...የወለሉ ንጣፍ ጣውላ ሲረግጡት፣ እሪታው ሌላ ሰፈር ድረስ የሚሰማ ይመስላል፡፡ ኢንስፔክተር መንበረ አንድም ቃል ሳትናገር፣ ክንዴን እንደያዘችኝ ነበር ከኋላ ከነ አጀበኝ የሕዝብ አጀብ ፖሊስ ጣቢያ የደረስነው፡፡ በሩ ላይ ስንደርስ፣ ቀጥ ብሎ ቆሞ ሰላምታ ለሰጣት
ፖሊስ “አስገባቸው” አለችው።

“እሺ! አስገባቸዋለሁ ኢንስፔክተር” አለ፡፡ ድምፁ ስልል ያለና አስፈሪ ነው “እሺ! ወደ ሲኤል እወረውራቸዋለሁ!” የሚል የሲኦል በር ጠባቂ ነበር የሚመስለው፡፡ እኔ ግን አስገባቸው?” ብዬ ዞር ስል፣ ለካስ ብቻዬን አልነበርኩም፤ እስካድማስ የሚባል የሰፈሬ ልጅም ተይዟል፡፡ ፖሊሱ ከኢንስፔክተር መንበረ ተቀብሎ፣ ከሷም በጠበቀ አያያዝ ክንዳችንን ጨምድዶ እያመናጨቀ፣ በሚንቋቋው አሮጌ የጣውላ ደረጃ ቁልቁል ወሰደና ከዋናው ቤት ሥር ያለ ሰፊ ክፍል ውስጥ ገፋ አድርጎ አስገብቶ ከውጭ ቆለፈብን፡፡ ይሄ ክፍል እኒያ በደም ግፊት የሞቱ ሰውዬ ሲያሠሩት ለአንዳንድ ዕቃ ማስቀመጫ ብለው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ጣሪያው በጣም ቅርብ ነው፡፡ እጄን ብዘረጋና ትንሽ ዘለል ብል እነካዋለሁ፡፡ እንግዲህ የታሰርንበት ክፍል ጣሪያ የዋናው ቤት የጣውላ ወለል ነው…ሰዎች ከበላያችን ሲረማመዱ የሚከነክን ልም አቧራ ይራገፍብናል፡፡ ከታሰርንበት ክፍል
በውጭ በኩል በር ላይ የተሰቀለው ፍሎረሰንት መብራት፣ ነጭ ብርሃን ከበሩ በላይባለው ክፍተት ገብቶ ቤቱን በለስላሳ ብርሃን በከፊል ሞልቶታል፡፡ ብርሃኑ ከበላያችን ባለው የጣውላ ክፍተት ሽቅብ አልፎ፣ ከላይ የሚረማመዱትን ሰዎች ያሳያል፡፡

ብዙም ሳይቆይ ከፖሊስ ጣቢያው ውጭ (በግምት በሩ አካባቢ ካለው መተላለፊያ
ይመስለኛል) የእናቴንና ተከትለዋት የመጡ ጎረቤቶቻችንን የተደበላለቀ ድምፅ ተሰማኝ፡፡
ነቃ አልኩ፡፡ “ይረጋጉ ማዘር ኢንስፔክተር
መንበረ ናት፡፡ እንዴት ነው የምረጋጋው
ልጄን እንደ ወንጀለኛ እያዳፋችሁ ስታመጡት፤ ከቤት ወቶ የማያቅ ልጅ በድንጋጤ ግጥም ብሎስ እንደሆን እንዴት ነው የምረጋጋው!? .…ልጄን! እኔ አፈር ልብላ” ትላለች
እናቴ፡፡ ሙቼ ከመቃብሬ ውስጥ ሆኜ የማዳምጣት መሰለኝ፡፡ እንደዚያ፣
እንግዲህ ንዝንዝ ጀመረችኝ!” ብዬ የምሸሸው ድምጿ ብዙ ዓመታት እንደተራራቀ ሰው ናፈቀኝ፡፡ከበላዬ ጣውላው በበርካታ ሰዎች እግር ሲረገጥ እና ሲንሲያጠጥ፣ያገር አቧራ እንደ
ዝናብ ሲዘንብ ይሰማኛል፡፡ የጣውላው ይኼን ያህል መንጓጓትና ሲጥሲጥታ የመንደሩ ሰው ከላይ የሚጨፍር ነበር ያስመስለው፡፡ “ችግር የለም ማዘር፣ ጉዳዩን አጣርተን እንለቃቸዋለን” ትላለች ኢንስፔክተር መንበረ፡፡ ይመስለኛል፣ ኢንስፔክተር መንበረ
እናቴን ጨምሮ ሁሉንም ሰዎች ወደውጭ እንዲወጡ አድርጋ፣ ተመልሳ ከአንድ ፖሊስ ጋር ዝቅ ባለ ድምፅ የሆነ ነገር ማውራት ጀመረች፡፡ የምትለውን መስማት አልቻልኩም፡፡ለማዳመጥ ጓጉቸ ከበላዬ ወዳለው የጣውላ ሽንቁር ጠጋ ብዬ ቆምኩና ሽቅብ በሽንቁ ዓይኔን ሰደድኩ፡፡

ፈጽሞ ያላሰብኩት ነገር ነበር የጠበቀኝ፡፡ ኢንስፔክተር መንበረ ጥርት ያሉ ጠይም
እግሮች፣ እስከ ታፋዋ ጥግ ከበላዬ ቆሟል፡፡ ያንን የካኪ ቀሚስ በስሱ ባለፈው የፖሊስ ጣቢያው “ፍሎረሰንት” መብራት፣ ደግሞም ከታች እኛ ከታሰርንበት ሽቅብ ባለፈ ቀጭን ብርሃን ኪነታዊ ቅንብር፣ ጠይም እግሮቿ ከጉርድ ወታደራዊ ቆዳ ጫማዋ ጀምሮ
ጉልበቷን አልፎ ታፋዋ…ብሎም የውስጥ ሱሪዋ ድረስ ቁልጭ ብለው ይታያሉ፡፡ አንድ እግሯ ከጉልበቷ ትንሽ አጠፍ ብሏል፡፡ አንዳች የማላውቀው ንዝረት መላ ሰውነቴን ሲወረው ተሰማኝ፡፡ ሕልም ነበር የሚመስለው እስር ቤት ነኝ!..ያውም እንደ መቃብር በከበደ እና በሚቀዘቅዝ ምድር ቤት ውስጥ፡፡ እንዴት ነው እንዲህ የተቀናበረ በሚመስል ተአምር፣ እንደ የእጅ ባትሪ በቀጠነ የፍሎረሰንት ብርሃን፣ ያውም በሽንቁር ሽቅብ አልፎ እንዲህ ግራ የሚጋባ ነገር የሚታየው? የኢንስፔክተር መንበረ የውስጥ ሱሪ ቀይ ነው። ደማቅ ቀይ ..ቅላቱ እንግዳ ነበር! ሕይወት ያለው ቀለም፡፡ እግሮቿ ወደ ላይ ወደ ታፋዋ ቀላ ይላሉ... በተንቀሳቀሰች ቁጥር ብርሃኑ የሚያርፍበት የሰውነቷ ክፍል፣ በጥላና ብርሃን ፍርርቆሽ እየተጫወተ በመጠየምና በመጥቆር መካከል እየተቀያየረ ይታያኛል፡፡ እግሮቿን
ስትከድን ታፋዎቿ በስሱ ተነካኩ፡፡ ዓይኖቼ ከሽንቁሩ ሊነቀሉ አልቻሉም፡፡ የማይረሳ
አንዳች ትዕይንት ነበር ንዝረት የቀላቀለ፡፡
ዛሬ ላይ ሳስበው ታዲያ፣ የደቡብ አፍሪካው የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ፣ ሃያ ሰባት ዓመት በታሰሩበት ክፍል መስኮት ይሁን ፋካ፣ ተስፋቸውን የሚቀጥል ምን ነገር እያዩ እንደነበር ማን ያውቃል?! እላለሁ .…መቼስ እስር ቤትም ቢሆን ሽንቁር ይኖረዋል የሰው ልጅ ሁሉን ሽንቁር ደፍኖ አይችለውም፡፡ ሁሉም ነገር የሆነ ሽንቁር አለው ..ሕይወት
ድፍን አይደለችም፡፡ ሰው ራሱ ተስፋው በጨለማ ተከባ፣ ተጀብኖ እንደ ጥቢኛ እሳት መኻል ቢጣል፣ የከበበውን እሳት ይረሳ ዘንድ ሕይወት የተስፋ ውሃ የምታሳይበት አንዳች ሽንቁር አላት፡፡ እያጮለቅን እፎይታን ተስፋ እናደርግ ዘንድ፡፡ ይኼ ትዕይንት ካለፈ ደቂቃዎች በኋላ፣ አንድ ጥግ ቆሜ ትዕይንቱን ዕፍረት በጠላበት የውስጥ መደናገር
እየመላለስኩ ሳስብ።

አብሮኝ የታሰረው ጓደኛዬ እስካድማስ በተራው ወደ ሽንቁሩ አንጋጦ እየተመለከተ በፍርሃት በሚንቀጠቀጥ የሹክሹክታ ድምፅ “ሊያስሩን ነው መሰል ..ሊያስሩን ነው” አለ

እ?” አልኩት ከሐሳቤ ባንኜ … ከዚህ ወዲያ ምን መታሰር ሊመጣ ነው እያልኩ…

ወደ ሽንቁሩ እየጠቆመኝ “ና ና ተመልከት” አለ፡፡

ትከሻ ለትከሻ ገጥመን ወደላይ አንጋጠን ስንመለከት፣ አንድ የቆመ ፖሊስ በከፊል አንድ ጎኑ ብቻ ይታያል ... በሽንቁሩ ትክክል ሙሉ ለሙሉ የሚታየው
ግን ያንጠለጠለው የእጅ ካቴናው ነበር፡፡ ታፋውን በካቴናው መታ መታ እያደረገ፣ የሆነ ነገር የሚጠብቅ ይመስላል፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ አልፈራሁም! አንድ ከተማችን ውስጥ መንገድ ለመንገድ እየዞረ ወንጌል የሚሰብክ ጎልማሳ ነበር ድንገት ወደ አዕምሮዬ የመጣው፡፡
አንድ ቀን በመነበብ ብዛት የተጎሳቆለውን ባለጥቁር ሽፋን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ሂድ ወደዛ መናፍቅ? የሚሉት ሰዎች መኻል እንደቆመ….

ወገኖቼ ይኼ ቃል ሽንቁር ነው፣ መስኮት ነው፣ ነገ ይገለጥ ዘንድ ያለውን ዓለም
በከፊል የምናይበት ሽንቁር! ሲኦልንም ገነትንም በዚህ ሽንቁር ካልሆነ አታዩትም!
አትፍሩ… ወደ መስኮቱ ተጠጉ ዓይኖቻችሁንም ግለጡ .…” እያለ የጮኸው ነገር፡፡ የዛ ሰው ንግግር ድንገት ዛሬ እንዲህ በጨለማ የተገለጠልኝ ያህል፣ ደግሞም የማይታይ
በማየቴ ሽው ከሚልብኝ የመቀሰፍ ፍርሃት በላይ ቅዱስ የሆንኩ ዓይነት፣ ቅዱስ ሆኜ
እስር ቤት የተወረወርኩ ዓይነት፣ እንዲያው እዚህ ከጎኔ በፍርሀት ከሚርበደበደው ልጅ ጋር ጮኸ ብለን ብንዘምር የእስር ቤቱ በር በተአምር እንደሚከፈት ዓይነት፣ ውስጤን
አንዳች ንፁህ ደስታ ሲሞላው ይሰማኝ ነበር፡፡

የዚያን ቀን የተባለውን እንጃ፣ ብቻ በዚያው ምሽት ተፈተን ወደ ቤታችን ሄድን፡፡ተፈትቶ መመለስ” ይለዋል ጎረቤቱ ይኼን የሥጋ መንከላወስ፣ ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ቤት ማዝገም፡፡ ለእኔ ግን ጉዳዩ ሌላ ነበር፤ ታስሬ ነበር የተመለስኩት፡፡ የሴት ልጅ ሰውነት
በዚያ ልክ ተጋልጦ ሳይ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ ለስንት ዓመት ይሆን ከዚያ በኋላ
ኢንስፔክተር መንበረን ለማየት፣ አይቼም ከተሸፋፈነ እሷነቷ ሥር በድብቅ ትዕይንት
የተገለጠው ዓይኔ፣ የፖሊስ ዩኒፎርሟን ሰርስሮ እነዚያን እግሮች ሲያይ የኖረው
አላውቅም! ሱሪ ትልበስ ቀሚስ ብቻ ራቁት
👍2
እግሮቿን በአንዳች ተአምር ማየት እችል ነበር፡፡ከፖሊስ ጣቢያ ስንፈታ የመንደሩን ልጅ በሙሉ ዋስ ሆነው፣ የሴትዮዋን ጠፋ የተባለ ብር ከፍለው ያስለቀቁን አባ ኃይሌ ናቸው ሲባል ገረመኝ! ታዲያ በገደብ ነበር
ከዚያች ቀን ጀምሮ እዛች በረንዳ ድርሽ ላንል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶን፡፡ ሰውዬው
ፖለቲከኛ ነገር ናቸው፤ መሄጃቸው አይታወቅም፡፡ ተዘረፍኩ ካለችው ሴትዮ ጀምሮ አጠቃላይ ግርግሩ ከዛች የበረንዳ እርስታችን እኛን ለመንቀል፣ በራሳቸው የተቀናበረ ድራማ እንደሆነስ ምን ይታወቃል?! መቸስ በእያንዳንዱ የተንኮል ድራማ ውስጥ ለትውልድ የሚተርፍ ሽንቁር ይፈጠራል፡፡ ጦሱ ለእኔ ተረፈኝ፡፡

በረንዳው ከተከለከለ በኋላ ምን አደረግሁ? ፀሐይ ስታዘቀዝቅ ከቤቴ እወጣና “ወክ። ላድርግ” በሚል ሰበብ ለ“ወክ” በማይመቸው የሰፈራችን አስፋልት ላይ እየተራመድኩ
ኢንስፔክተር መንበረን እጠብቃታለሁ፡፡ ሸቀጡን አንስቶ ወደ ቤት በሚሮጠው ነጋዴ ከሥራ በሚመለሰው የቀን ሰራተኛ፣ ሙሉ ቀን ሲጓዝ ውሎ የጫነውን ሸቀጥና ሰው በሚያራግፈው እምክ እምክ በሚሸት መኪና መኻል እየተሹለከለኩ እጠብቃታለሁ የተከታተልኳት
እንዳይመስልብኝ (የምታውቅ እየመሰለኝ እፈራ ነበር) በምፈልገው ልክ ለማየት በማያስደስት ርቀት እየተከተልኳት፣ የከተማው ዋና አደባባይ ላይ ስትደርስ
እመለሳለሁ፡፡ አንዳንዴ ከአደባባዩ እጀምርና ከምትመጣበት ተቃራኒ አቅጣጫ፣ እኔ ብቻ በሚገባኝ ስሌት በተሰላ ግጥጥሞሽ፣ ፊት ለፊት እስክንተላለፍ የማግኘትና የማየት ዕድል
ገጥሞኛል፤ ግን ቀና ብዬ ላያት እፈራለሁ፡፡ ካለፈች በኋላም ወደኋላ ዞሬ አላያትም፡፡ ሳያት እሷም ዙራ “ምን ፈለክ?” የምትለኝ ይመስለኛል፡፡
ማን ያምናል፣ ወደ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ተከተልኳት ቢባል?! አረማመዷ ፈጣን ስለነበር አንዳንዴ ርቀቴን ለማስተካከል ሩጥ ሩጥ ይለኛል፡፡ መንገዱን የሞላው የራሴ ሰፈር ሰው ነው፤ ከጉልት ቸርቻሪው እስከ ባለ ሱቁ፣ ሁሉም ቢያንስ ዐዓይን ያውቀኛል። አንዱ በማያገባው ገብቶ “ምነው ትሮጣለህ?” ቢለኝ ምን እላለሁ? እያልኩ፣ ምናምን
ከተሸከመ ሰው…ወደቤቱ ከሚጣደፍም ሠራተኛ ጋር ላለመጋጨት እየተጠነቀቅሁ
ስከተላት ኖርኩ: አንዳንዴ ሆነ ብዬ ጠብቄ እሷ አጠገቤ ስትደርስ፣ የአንዱን ሚስኪን
ላብ አደር አፍንጫ ሰብሬ እንድታስረኝ የተመኜሁበት ጊዜም ነበር።ሱቅ ጠባቂ ብትሆን “ባለ ሱቅ ማስቲካ አለ?” በሚል ሰበብ…በየቀኑ በሚያስኬድ ደንበኝነት እየሄድኩ አያታለሁ፣…ፖሊስ ጣቢያ ምን ተብሎ ይኬዳል?!… ብዙ ብዙ ነገር እመኛለሁ ነገር የማያጡ ጎረቤቶቻችን መሰዳደብ ሲጀምሩ፣ ጠቡ ተባብሶ ፖሊስ ጣቢያ በሄዱ እያልኩ፣ መቼስ ጎረቤት ተከትሎ መሄድ ወግ ነው፤ ምናለ እኔስ የምስክርነት ወጉ ቢደርሰኝ?!
ደግሞ ለክፋቱ እንደዚያ በዶሮ ነሽ፣ በልጅ ነሽ፣ ከዱላ ቀረሽ ስድድብ እስከ መፈነካከት የሚደርሱት ጎረቤቶቻችን፣ ምን መልአክ አንደተጠጋቸው እንጃ በዚያ ዓመት ፍቅር በፍቅር ሆኑ

ለአንድም ሰው ሳልተነፍስ ስከተላት ኖሬ አንድ ቀን (ሮብ ቀን ነበር ቀኑ) ኢንስፔክተር መንበረ በመንገዱ ላይ ሳታልፍ ቀረች ..ሁለት ጊዜ ፖሊስ ጣቢያው ድረስ እየደረስኩ ተመለስኩ፡፡ የለችም! ከዚያን ቀን ጀምሮ በቃ ጠፋች፡፡ በብዙ ሊሆኑም ላይሆኑም በሚችሉ 'ሊሆን ይችላሎች ራሴን አስታመምኩ ሥራ ቀይራ ኬኒያ ድንበር የኮንትሮባንድ
ንግድ እየተቆጣጠረች ሊሆን ይችላል፤
የፖሊስነት ስራዋን ትታ በግቢዋ አጥር በኩል ኪወስክ ከፍታ እየነገደች ሊሆን ይችላል፣ የሚከታተለኝ ሰው አለ ብላ መንገድ ቀይራ ሊሆን ይችላል
(ፊት ባልሰጠውም) አግብታ ሊሆንስ አይችልም?! የሚል ሐሳብም
ውልብ ብሎብኛል፡፡ ቢሆንም ፀሐይ ስታዘቀዝቅ አስቤም ይሁን በአጋጣሚ
መንገድ ላይ ከተገኘሁ፣ ዓይኔ ፍለጋውን አያቆምም ነበር፡፡

ከዓመታት በኋላ አደግሁ፣ በሰልኩ፣ ያለፈ ዘመኔን ድርጊት የሚመዝን አዋቂነት ላይ
ደረስኩ በሚል ዕምነት ኢንስፔክተር መንበረን ስከተል መኖሬን “ኪላቂልነት ነበር” ብዬ ደመደምኩ፡፡ ትልቁ እኔ ትንሹን እኔ ለሰራው የቂል ሥራ ገሰፅኩ፡፡ተራ የልጅነት ቂላቂልነት! ግን ቂላቂልነቴ ብልጣብልጥ ግሣጼ ውስጥ ተዳፍኖ በሕይወት እንደነበር የገባኝ ወዲያው ነበር፡፡ አንድ ቅዳሜ ቀን፣ እንጃ ወደ የት እየሄድኩ እንደነበር፣ (ብዙ ጊዜ ታክሲ የምጠቀመው አክስቴ ቤት ስሄድ ስለሆነ፣ ወደዚያው እየሄድኩ ሳይሆን አይቀርም) ከተሳፈርኩባት ታክሲ ውስጥ አንዲት ወጣት ልጅ ልትወርድ ባጎነበሰችባት ቅፅበት ከጠይም ገላዋ ጋር የተጣበቀ ቀይ የውስጥ ልብሷ ከፈፍ ውሃ ሰማያዊ ጅንስ ሱሪዋን አልፎ ብቅ አለና ጠፋ፡፡ ቅጽበት ነበር፡፡ ብልጭታ! ግን ሰማዩን እንደሞላ፣ወጋገኑም ምድርን እንዳጥለቀለቀ የመብረቅ ብልጭታ፡፡ ልጅቱን አውርዶ መንቀሳቀስ
የጀመረውን ታክሲ “ወራጅ” በሚል ችኩል ድምፅ አስቁሜ ከኋላዋ በሶምሶማ
ተከተልኳት፡፡ ልምድ ያለው ሴት አውል እንኳን በማይሞክረው ድፍረት፣ ከኋላዋ
ሰላም እልኳት፡፡ ትውውቃችን ፈጣን ነበር “የሆነ ቦታ አውቅሻለሁ” አልኳት፡፡
ፈጽሞ አላውቃትም ነበር!

“ታውቀኝ ይሆናል... እኔም በዓይን አውቅሃለሁ”

ኧረ ባክሽ ….የት?”

ቆየት ብሏል …”

“እኮ የት?”

“ብዙ ጊዜ ማታ ማታ ወደ አሥራ አንድ ተኩል ...አሥራ ሁለት ሰዓት አካባቢ፣ በሱቃች በር ስታልፍ አይህ ነበር ..ያ ልጅ አለፈ፣ ሱቅ እንዝጋ እንባባል ነበር፡፡ ሰዓታችን ነበርክ
…ሂሂሂሂ” ብላ በሳቅ ተፍለቀለቀች፡፡ አያለሁ ሲሉ መታየትም ነበር ለካ፡፡

“አሁን ግን ጠፍትሃል፣ አትታይም!”

ከበርካታ ወራት ቀጠሮዎች በአንዱ፣ ለዚያውም በስንት ፍርሃት የመጀመሪያ ወንድነቴ አጋኖ ያጠራቀመውን ምኞት ሊንድ በሚንጠራራበት አንድ ቀን፣
(የመጀመሪያዋ ይሁን አይሁን እንጃ ..አንድ ቅዳሜ ቀን ጓደኛዬ በተከራያት ባለ አንድ ክፍል ቤት ውስጥ
በተዘረጋ ፍራሽ ላይ፣ ይችው ልጅ የለበሰችውን ቀሚስ፣ በእኔው እርዳታ ያወለቀች ጊዜ
ምን አጋጠመኝ? …ነጭ የጡት ማስያዣና ነጭ የውስጥ ሱሪ ...በረዶ የመሰለ እና በረዶ ያደረገኝ.ድንገት ነበር የቀዘቀዝኩት፡፡ “ምን ሆንክ?” አለችኝ በአየር ላይ
የቀረ መንሰፍሰፌ ሲጠወልግ አይታ መሆን አለበት፡፡

“ሌላ ጊዜ እናድርገው” አልኩ በፍቅር እያየችኝ “ውይይይ …” ከሚል ፈገግታ ጋር ስሜታዊ አለመሆኔን አድንቃ አሞካሸችኝ! ይህም እንደጨዋነት ተቆጥሮልኝ፣በፈለክበት ቀን፣ እንኳን ሰውነቴ ነፍሴ የአንተ ነው በሚል ገራገር ፈቃድ፣ ያን ሌላ ጊዜ እንደ ምፅአት
ስትናፍቅ የውሃ ሽታ ሆንኩ! “ለሌላ ቀን ቀይ የውስጥ ሱሪ ለብሰሽ ተመለሽ!” አይባል ነገር
..ይባልም ከሆነ ጀማሪ እኔነቴ ልምድ አንሶት ይሆናል፡፡ ስሜታችንም ሙሉውን ሳይሆን፣ እንዲሁ በጨረፍታ እራሳችንን ቀንጭበን የምንሰጥበት ሽንቁር አለው፡፡ እንደዚያ ሳይሆን አይቀርም፣ ከዚያች ልጅ ጋር የጀመርነው ነገር፣ ሙሉ በሙሉ መሰጠት ሳይሆን በሽንቁር ነበር፡፡ በሽንቁር የሚገባ ንፋስ ምንነቱን እንኳን ሳናውቀው እንዲህ የለመለመ
አምሮትን ሲያደርቅ “ከመሬት ተነስቶ ተወኝ” የሚል ክስ እንደ ትልቅ በደል ይቆጠራል፡፡

ሌላ ቀን ሌላ ሴት፣ እንዲሁ በወጣትነት ሰላይ ዓይኖች ስመኛት እና ስከታተላት የኖርኩ፣በሰፈር ሠርግ ላይ ተገናኘን፡፡ ምን ለብሳ? ሙሉ ቀይ የእራት ልብስ! … ያንን በሽንቁር ያየሁትን ቅላት በአደባባይ ያራከሰችው መሰለኝ፡፡ ቅብጠት አይደለም፡፡ ቢሆንም ስሜታችን ሾልኮ እንደነገሩ ደርሶ የሚመለስበት ሽንቁር አለው፡፡ ይችኛይቱ ሽንቁሬን
አስፍታ በር ያደረገችው ጋ ደርሼ የተመለስኩት እንደዚያ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንዳች ልክፍት ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከቀይ የውስጥ ሱሪ ጋር የተቋጠረ
👍1👏1
አንዳች የልብ ምት ነገር አለ፡፡ አንዲት የመንደራችን አሮጊት፣ ለሴት ልጃቸው የተመኙት ወንደላጤ ተከራያቸው አንዲት የገጠር ሴት ሲያገባ ተበሳጭተው “ሙታንቲው ላይ አስደግማበት ነው አሉ” ይሉ ነበር፡፡ ያኔ ያስቀኝ ነበር አሁን ግን “ይች ኢንስፔክተር መንበረ የራሷ ሙታንቲ ላይ አስደግማበት ይሆን እንዴ” እስክል ግራ ይገባኛል .ግን ማን ሊያየው ብላ እዛ ላይ ታስደግማለች ካስደገመች አገር የሚያየው ትከሻዋ ላይ ያለ ማዕረግ ላይ፣ከወገቧ የሚሻጥ ሽጉጧ ላይ አይሻልም ነበር? ..እንዲህና እንዲያ አስባለሁ፡፡ ሳስባት ልቤ ይደልቃል ዘወትር እንደሚደልቀው ዓይነት የልብ ምት አይደለም፣ ስልት ያለው የልብ
ምት፡፡ ያንን ትንፋሽ የሚያሳጥር…. ያንን ንዝረት የሚለቅ ትዝታ፤ ስንት ቦታ፣ ስንት
እንስቶች ላይ ፈለግሁት፤ የለም አልነበረም!!

ኢንስፔክተር መንበረ ሂድ! ተፈተሃል” ብላ ወደ ሰፊው ዓለም በፖሊስ ጣቢያው ሽንቁር ስትልከኝ፣ አእምሮዬ ውስጥ ግን ኃይለኛ ብርሃንና ሙቀት የሚያሾልክ አንዳች ቀዳዳ ሳይፈጠርብኝ አልቀረም፡፡ እንግዲህ ነፃነት ምንድነው?! .…የነፍስን ሽንቁር መድፈን አይደለምን? የጎን አጥንት ሲባልስ የጎን ሽንቁር አይደለም ማን አለ?.…ከሁለተኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርስቲ፣ ደግሞም ሥራ በሚሉት ስንክሳር በሕይወት ጎዳና ግራ ቀኝ ሳልል፣
አንዲት ለሌሎች የማትታይ የሐሳብ ሐዲድ ተከትየ ፣እሷን ሳላዛንፍ እየተከተልኩ ሠላሳ ዓመት ሞላኝ፡፡ ሴቶቹ ብዙ፣ ወሬው ብዙ፣ መልኩ ብዙ፣ አጋጣሚው ብዙ፣ መገናኛው ብዙ መለያያው ግን ብዙ የሚመስል አንድ አእምሮዬ ውስጥ የተሰነቀረ ቀለም ነበር፤
ቀይ ቀለም!!

አሥራ ስድስቱን ዓመት እስረኛ ነበርሁ ….ብዙ ፋሽን መጣ፤ ብዙ ፋሽን ሄደ፤ አንዱም ላይ ግን የውስጥ ሱሪን የሚያሳይ ሽንቁር ያለው የሴት ልብስ እስካሁን አላየሁም፡፡
እንግዲህ መንገድ ዳር ቆሜ “እስቲ ቀሚሳችሁን አውልቁ፣ እንደእሳት ፍም የቀላ፣ቀይ የውስጥ ሱሪ የለበሰችው የአገሬ ሴት እሷ የጎን አጥንቴ ናት” አልል ነገር ... ካቀፉትም ገላ በላይ የትዝታ ገላ ሙቀቱ አይጣል ነው …ሌላው ይበርዳል …በሽንቁር እንደሚገባ ኃይለኛ ነፋስ በቀስታ ቅዝቃዜና መንሰፍሰፍ ወደ ነፍሴ የሚያስገባ ሽንቁር ዛሬም አለ፡፡
“ውይ! እሱ ያያት ሁሉ ታምረዋለች …ወረተኛ ነው” ይሉኛል፡፡ ሲያሻቸው ለበጣም ይመርቁበታል

አቀፈን… ታቀፍንለት፣ ሳመን…ተሳምንለት፤ ዓመል ነው እንጂ ከእኛ ምን አጣ?! ሽንቁር ያው ሽንቁር ነዉ!” እያሉ፡፡

💫አለቀ💫
#ቢሆንም

በል ውረድ እምባዬ ስቃዬን አጣጥበው
ሀዘኔን አባብሰው
ይውጣልኝ የውስጤ
ነዲድ ረመጤ
አንዳችም ባይፈይድ
ወጥቶ ለቀረው ሰው
ይሁን ፍሰስልኝ አንጀቴን አርሰው።

🔘በሰላም ዘውዴ🔘
#በአፍ_ብቻ

ይህን እልፍ መውደድህን
የቃላት ክምርህን
እልቆ ቢስ ፍቅርህን
በአፍ የምትለኝን እንቶ ፈንቶ ወሬ
ተግብረህ አሳየኝ እባክህን ፍቅሬ።

🔘በሰላም ዘውዴ🔘
#በስንቱ_እንጨነቅ

በሰልፍ በሁካታው
በኑሮ ጫጫታው
በስንቱ እንጨነቅ በስንቱ እንምታታ
በርሀብ በጥማት በስቃይ መብዛቱ
በሌለ ነፃነት በውስጠ ባርነት
በስንቱ እንብሰልሰል
በየቱ እንማሰል
በስልጣን ሽኩቻ በኔነት ዘመቻ
በአብይ ሌጋሲ በስም ዲሞክራሲ
በእርስ በእርስ ግጭት ውል በሌለው ፍጭት
በሃይማኖት ተገን
ፍቅር ሲያጣ ወገን
ብዙ በሆነበት አንድ የማያደርገን
በየቱ እንጨነቅ በስንቱ እንቃጠል
በመንገድ በቤቱ
በሥራ ማጣቱ
በሌለ ኢኮኖሚ ባጣንበት ሰሚ
ደግሞ ምን እናስብ
በስንቱ እንብሰልሰል
በየቱ እንማሰል?

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ማሙሼ


#ክፍል_አንድ


#በእየሩስአሌም_ነጋ

“ኤድያ እኔን ብሎ ንግሥት! አሁን ምኑ ታይቷቸው ነው ንግሥት ያሉኝ? ባዶ ምኞት!" አለችና ከአንደኛው መኖሪያ ቤት
ተጠራቅሞ የወጣውን ቆሻሻ ወደ ያዘችው ማዳበሪያ ገለበጠችው።

“አሁን አንቺ ንግሥት ለመባል ምን ያንስሻል? ዘውዱን እንደሁ ጭነሽዋል።” አለቻት ጓደኛዋ ጸአዳ ንግሥት ለፀሐይ
መከላከያ ራሷ ላይ የጠቀለለችውን ጨርቅ እያመለከተቻት፡፡ድምጻቸውን ጮክ አድርገው በሳቅ አወካኩ፡፡

“ምን ያንቺ ብቻ የኔንስ ስም አላስተዋልሽውም? ጸአዳ! አየ ጉድ! እንዴት ጸድቻለሁ እቴ! ጉድ!” አለች ራሷን ከእግሯ ጀምራ ወደ ላይ እየቃኘች በማሽሟጠጥ፡፡

“ይገርማልኮ! “መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንደ ሚሉት፤ ምናልባት የአሁኑ እጣ ፋንታችን ታይቷቸው ይሆናል” አለች
ንግሥት፡፡
“አይ እቴ እንደሱስ አይደለም። እንዲያው ጥሩ ነገር መመኘታቸው ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው ይኸው የሰው ቤት ቆሻሻ ገልባጭ ሆነን አረፍንላቸው!” አለችና በመታከት ከውስጧ የታመቀ የሚመስል ትንፋሽ ተነፈሰች።
ጸአዳ ማዳበሪያዋን እንደማስቀመጥ አድርጋ፣

“እኔ የምለው ይህን ስራ በመስራትሽ እግዚሐርን እንደማመስገን ታማርሬያለሽ?” አለቻትና ወገቧ ላይ ያሰረችውን መቀነት አጠበቀች።

“እ... ታዲያሳ አንቺስ ቅድም ምን ስትይ ነበር? ስታማርሪ አልነበረም?” አለቻት እርሷም እንደመቆም ብላ።

“እኔማ ልማድ ሆኖብኝ እንጂ ስራዬን መች ጠላሁ፡፡ እንዲያውም ጸአዳዬ ከዚህ ደግሞ ሻል ያለ ስራ ከሰሞኑ ሳናገኝ
አንቀርም።”

“ኧረ! እውነትሽን ነው?” አለች ጸአዳ በአግራሞት አፏን ከፍታ።

“እውነቴን ነው። ትንሽ ፍንጭ ቢጤ
አለ፣” አለች ንግሥት።

“ኤድያ! ገና ለገና ብለሽ ነው የምታጓጊኝ? እኔ ሌላ ስራ እስከማገኝ ዎሼ ቀንድ ታበቅላለች።”
“እንቺ ደግሞ ተስፋ የሚሉት ነገር ከግንባርሽም አልተጻፈም!” አለች ንግሥት።
“ኤድያ! ተስፋ ቢጋግሩት እንጎቻ አይሆን!” ጸአዳ ንግግሯ መረር ብሏል።

“ኧረ የኔውስ ተስፋ እንኳን እንጀራ ሌላም ይሆናል፡፡ ታያለሽ ያባቴ አምላክ ባያደርገው!” አለች የጣለችውን ማዳበሪያ
አንስታና በግንባሯ ላይ ኮለል ብሎ የወረደውን ላቧን ጠርጋ የጸአዳ ጥላ እንዲጋርዳት በጎን እየዞረች፡፡

“እስቲ በይ ተጠለይ! እኔን ጌታ ረጅም ባያረግልሽ ኖሮ በየትኛው ዛፍ ትጠለይ ነበር?” አለች እንደመኩራት እያለች፡፡
“አቤት! በዚችው ቁመትሽ እንዲህ የተመጻደቅሽ ሌላ ነገር ቢኖርሽ አለቅን!” አለችና ጸአዳን ወደ ኋላ ትታ በፍጥነት
ተራመደች፡ ወደ ሌላኛው ብረት በር ሲደርሱ በሩን አንኳኩ፡፡ በሩን በፍጥነት የከፈተ የለም፡፡

“እንዲያው ያንን የማሙሼን ነገር እንዴት አደረጋችሁለት?” አለች ጸአዳ በበሩ ቀዳዳ ወደ ውስጥ አጮልቃ እያየች።

“ውይ እንዲያውም እነግርሻለሁ እያልኩ ጸአዳዬ... የማሙሼ ነገርማ እያለቀለት ነው፡፡ ሁላችንም ቃላችንን ሰጥተናል።”

“እንዲያው ምን ብላችሁ ይሆን የመሰከራችሁት?”
“እናቱንና አባቱን ማጣቱን ድፍን የሚካኤል ሰፈር ሰው ያውቃል፡፡ ያው እውነቱን ነዋ የምንመሰክረው... ለማተባችን ስንል!” አለች ንግሥት ማተቧ ውስጥ ሌባ ጣቷን ከትታ ወደፊት ጎተት
እያደረገች፡፡

“ታዲያ አምነው ተቀበሏችሁ?”
“እንዴ... ለምን አያምኑንም?”
“እኛ እራሳችን መጤዎችና በሰው ማድቤት ተጠላልለን የምንኖር ነን፡፡ እንዳው አብረን ስላልኖርን...”

“እንዲህ ብሎ ነገርማ የለም፡፡ ትንሽ ጊዜም ቢሆን እኮ ከናቱ ጋር አብረን መአድ ቆርሰናል። ምስክርነት ደግሞ አብረው በኖሩ አይደለም፡፡”

“ስለዚህ አሳዳጊዎቹ ሊረከቡ ነው ማለት ነው?”
“ታዲያስ! ከሰሞኑ ሳይወስዱት አይቀሩም።”
“እስቲ ይለፍለት የኔ ከርታታ ገና በልጅነቱ አሳሩን አየ” አለች ጸአዳ፡፡
“አየ እንጂ፣ የሱ አሳር ደግሞ ይነገራል! ይቅር ብቻ!”
አሁንማ ለይቶለታል፡፡ የሚያዝንለትም ሰው ለአንዴ ሆይ! ሆይ! ብሎ ዝም አለ፡፡”
“ለዚያ ነው የገንዳ ምግብ የጀመረው?”
“ታዲያ ምን ያድርግ እራብ እንደው ክፉ ነው፡፡”
“ገንዳውንስ የሚያስጥለው ነገር ቢመጣ ጥሩ ነበር፡፡”
“ታዲያ ከኛ የቀረበ ማን ይመጣል? እኛ የምንበላውን ብናካፍለው...”

“እ... አሁን አስር ዓመቱ ሳይሆን ይቀራል ብለሽ ነው?" አለች ንግሥት የቆሙበት በር ሲከፈት ወደ ውስጥ እያየች፡፡

አንዲት ልጅ በማዳበሪ ውስጥ የተሞላውን ቆሻሻ እየጎተተች ወጣች፡፡ በግምት አባቷ የሚሆን ጎልማሳ
በፍጥነት መጥቶ ከእጇ ላይ እየተቀበለ “እናትሽ ይሄን ቆሻሻ አትንኪ ብላ ስንቴ አስጠንቅቃሽ ነበር!” አለና የቆሻሻውን ላስቲክ ንግሥት እግር ስር ወርውሮ
ተመልሶ ገባ፡፡ ንግሥት እስከ ማዳበሪው ተቀብላ ቆሻሻ ማዳበሪያ ውስጥ ከተተችው፡፡ ጸአዳ የቸኮለች ይመስል ፊት ፊት ፈንጠር ብላ የንግሥትን እጅ ጎተት አድርጋት ስትሄድ ንግሥት የሆነ ነገር
ልትነግራት እንደሆነ ገብቷታል። በፍጥነት ከተል ብላ በጥያቄ አስተያየት አየቻት፡፡

“ይኸውልሽ ይሄ ሰውዬ ባለፈው የነገርኩሽ..”
“የቱ ነው?” ግንባሯን አኮሳትራ ወደ እርሷ አሰገገች።
“ባለፈው ሰርግ ሄጄ ስመለስ...”
“እንዴ! ያ እንኳን በመኪና ካላሳፈርኩሽ ብሎ ያደረሰሽ?”
ጸአዳ በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡
“አየሽ ልዩነታችንን! አየሽ! አሁን ሰላምታ እንኳን መች ሰጠን እግዚኦ ጌታዬ! የኛስ ነገር ምን ይሻለን ይሆን?” አለችና ወደ
ቀጣዩ በር እያመራች ንግግሯን ቀጠለች።
“አሁንማ ቆሻሻ መስዬ ቆሻሻ ለብሼ ስላገኘኝ ነው፡፡ የስርጉ እለት ደግሞ እግዚአብሄር ይስጣትና ዘመዴ ሰርጓ ላይ የምለብሰው እንዳላጣ ብላ ልባሽ ልብሶቿን እስከጫማዋ ሰታኝ ..”

“አቤት የፀጉርሽ ነገርማ አይነሳ! ጸዱ ሁልግዜ በቡቱቶ እየጠቀለልሽ ለካ እንደዛ አይነት ፀጉር ኖሮሻል? ኧረ ምነው አንዳንዴ ተሰሪው! የዛኔማ እንኳን እርሱን ለእኔስ ሌላ ሰው መስለሽኝ አልነበረም? አወይ ማማርሽ!” አለቻት ንግሥት ወደ ፀጉሯ እየተመለከተች።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍4
አትሮኖስ pinned «#ማሙሼ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በእየሩስአሌም_ነጋ “ኤድያ እኔን ብሎ ንግሥት! አሁን ምኑ ታይቷቸው ነው ንግሥት ያሉኝ? ባዶ ምኞት!" አለችና ከአንደኛው መኖሪያ ቤት ተጠራቅሞ የወጣውን ቆሻሻ ወደ ያዘችው ማዳበሪያ ገለበጠችው። “አሁን አንቺ ንግሥት ለመባል ምን ያንስሻል? ዘውዱን እንደሁ ጭነሽዋል።” አለቻት ጓደኛዋ ጸአዳ ንግሥት ለፀሐይ መከላከያ ራሷ ላይ የጠቀለለችውን ጨርቅ እያመለከተቻት፡፡ድምጻቸውን…»
#ነፍስ_ይማር

ገና ጨቅላ ሳለ በሕፃንነቱ
የት ልትደርስ እያሉ እያንገለታቱ
ደግሞ እየፎተቱ
ሊድህ ሲንገዳገድ
ለመቆም ሲሞክር
ለዳዴ ሲታትር
እየወዘወዙ ከምድር ይጥሉታል
አይበጅም እያሉ ይጨጸልቁታል
ሀሳቤ ተወልዶ ሳያድግ ይሞታል።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘