አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
574 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰላምታ

ጊዜ ጊዜን ሲወልድ
ዘመን ተቀይሮ
ወግ ባህል ተሽሮ
ሰላምታም አጠረ
መጣጥፍ ቁምጣ ሆኖ።

🔘በሰላም ዘውዴ🔘
#ልጩህበት!!


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በጥላሁን


መናደድ ጀመርኩ። ልጁ እኔ ብቻ ላውራ አድምጡኝ በማለት የሚከተለውን ሙድና የኔን ንዴት በመጠኑም ቢሆን የተረዳችው ኤዱ ጀርባዋን ለሱ ሰጥታ እኔን ለማዋራት ሞከረች።

ከቆይታ በኋላ ካርድ ልግዛ በሚል ሰበብ ወጣ ብሎ ሲመለስ በፊት የነበረበትን ቦታ ትቶ እኔና ኤዱ መሀል ገብቶ ሲቀመጥ ንዴቴን መመጠንም መቆጣጠርም አቅቶኝ ጠፍቶ ድንገት ሀይል ጨምሮ እንደመጣ መብራት ሁለመናዬ ቦግ
••••
ቦግ አለ። ነደድኩ!፤ ፊቴ ተቀያየረ!፤ ደምስሬ ተወጣጠረ!
ልጁ ግን አየት አደረገኝና ከቁብም ሳይቆጥረኝ •••
"ኤድሻ ፌስ ቡክ ላይ የሆነ ፈን ነገር አይቼ እኮ ነው ቆይ ላሳይሽ እይውሟ እሄንን፤ እሄን አየሽው"እያለ ከሞባይሉ ላይ አይኗ እንዳይነቀል ስላደረጋት እሷም ሳታየኝ ተንጨርጭሬ እንደቀዘቀዝኩ ሆን ብሎ እኔን ለማናደድ እንደዛ እንደሚያደርግ በደንብ ያስታውቃል ብድግ አልኩና•••
እቤቴ ባትመጣ በዚህ አመት ከተጣላኋቸው ሰዎች አንዱ ትሆን ነበር ግን ምን ያረጋል
እቤቱ የመጣን ሰው ካልነከስኩ የሚለው ውሻ ብቻ ነው ውሻ ነገር ነህ አቦ! ገገማ! እያልኩ በውስጤ እየተሳደብኩ ተነስቼ ወጣሁና ግቢ ውስጥ ፊቴን መታጠብ ጀመርኩ።
ተመልሼ ስገባ እራሱ እያወራ እነሱ ሳይስቁ እራሱ ይስቃል ። የነበረን ቆይታ በልጁ ምክንያት ምኑም ሳይጥመኝ በሱ ውትወታ " በቃ እንሂድ" ብለው ተነሱ አላግደረደርካቸውም።

ከቤት እንደወጣን ግቢ ላድርሰችሁ ? አልኳቸው።
ከልቤ ነበር ከኛ ሰፈር ግቢ ድረስ ኮንትራት ካልያዙ በስተቀር ቀጥታ የሚወስዳቸው ታክሲ የለምና እንዳይቸገሩ ብዬ በማሰብ
"ስራ ትወጣለህ እንዴ ከዚህ ቡሀላ? አለችኝ ኤዱ
ስራ እንደማልወጣና እነሱን ብቻ አድርሻቸው ወደ ቤት እንደምመለስ ስነግራት•••
" አይሆንም በቃ ለኛ ብለህማ እዛ ድረስ መድከም የለብህም በትራንስፖርት እንሄዳለን!" ብላ ድርቅ አለች!
ተሰነባብተን ወደ ቤት ተመለስኩ።

አመሻሹ ላይ ጆሲ ድንገት በሩን ብርግድ አድርጎ ሲገባ ደንብሬ ተነሳሁ•••
"በለው በለው በቅዳሜ ቀን መጋደም ! ምን ሆነሀል አንተ ? እኔኮ የዳኒ እንግዳ ሄደች እንዴ ብዬ ሚሚ ባለሱቋን ስጠይቃት " ቆዩኮ ከወጡ!" ስትለኝ ገርሞኛል ቆይ ቆይ•••
በማህበር ተደራጅተው ነው እንዴ የመጡት?
እኔ እሷን ብቻ የቀጠርካት መስሎኝ አደል እንዴ የተቀየስኩት እዚሁ ደቅ ብዬ የቅዳሜ በርጫየን እንዳላጣጥም መሄድ እማልፈልግበት ቦታ ሄጄ ተጦልቤ ነው የመጣሁት ሰራህልኝ አቦ ቀጥሪያታለሁ ትመጣለች ከምትለኝ ይመጣሉ አትለኝም ወይ ምናለ ከመጡ ቡሀላስ ብትደውል መጥቼ ጀማውን እቀላቀል አልነበር እንዴ ! ግን እንዴት ነበር ውሎ?"
ኧረ ብትኖርልኝ ይሻለኝ ነበር ጆስዬ እኔም የመጨረሻ ተደውኬ ነው የዋልኩት !።

"እንዴ ለምን?" አለኝ ከበር ላይ ወደ ውስጥ ገብቶ አጠገቤ እየተቀመጠ
አላ! አብሯት የመጣው ልጅ ደዋኪ ነገር ነው ባክህ
"ማነው ልጁ ዝም ብሎ ጀለሳቸው ነው ወይስ•••?
አቦ ! ያ ነዎ! ባለፈው መሲ ልታስበላት ስትል ከጀለሶቹ ጋር ቀመር ቀምረው አስመለጣት ብዬ የነገርኩሁ የክፍሏ ልጅ
የፈራሁት ደረሰ ወይኔ ወንድሜን አንተ በህትነት ምናምን ነው እምንከባከባት እያልክ እራስህንም እኔንም ስትሸውድ በፍቅር የሚንከባከባትን አምጥታ አስተዋወቀችህ? ፍቅረኛዬ ነው ተዋወቀው ብላህ እጅ አፈችው አደል ?"
ውይይይይ ጆሲ ደግሞ እስቲ አሁን ማን እንደዛ አለ ? እንደዛ አለችኝ አልኩህ? ወጣኝ!?
"ታድያ እንደዛ ካልሆነ ምን አናደደህ? ብዬ ነዋ!"
አሃ! እኔ እምናደደው እሱ ስለጠበሳት ብቻ ነው ማለት ነው?
"ታድያ ፍላጎቱ እንደዛ መሆኑን ወይ አብሯት መሆኑን ብታውቅ እንጂ በምን ትናደዳለህ በዚ የማትናደድ ከሆነማ በምንም ልትናደድ አትችልም!"
ማለት?
"በዚህ ካልተናደድክ ሌላው ምክንያት እንዳለ ከዚህ በታች ነው ብዬ ነዋ!"
ይሆናል ብሎ ከመደምደም በምን ተናደድክ ብሎ መጠየቅ አይሻልም?
"እሺ በምን ተናደድክ?"
በቃ ልጁ እኔን ብቻ አድምጡኝ ከኔጋ ብቻ አውሩ ሙድ የሚያራምድ ነገር ነው ማለት•••አልኩና ከመጡ ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ ነግሬው ሳበቃ••••
"ካካካካካ•••!" ሳቁን ለቀቀው!።
ምን ያስቅሀል?! አልኩት ተናድጄ!
" አይ ዳንዬ በዚህ ያልተሳቀ በምን ይሳቃል የፍቅርን አመል ስለማውቀው ነው አንድ ፈላስፋ ምን እንደሚል ታውቃለህ••••"
አላውቅምም ደሞም እንዳታወራልኝ ! ኤጭ አሁንስ አንተና ያ ጓደኛህ ወሬያችሁ ጅማሮውን በሙሉ
" አንድ ፈላስፋ ምን እንዳለ ታውቃለህ?
"እገሌ የተባለው መፅሀፍ ላይ ምን እንደሚል ታውቃለህ?
አንድ ምሁር ሰው ምን እንዳለ ልንገርህ?
በሚል እያሟሻችሁ የራሳችሁን ሀሳብ በቀላሉ ሰው እንዲቀበለው ለማድረግ የምትሄዱበት መንገድና
አለም ላይ ምን ተፈጠረ ብዬ ዜና ለማዳመጥ በተቀመጥኩ ቁጥር የሀገራችን የቲቪና ራድዬ ሚድያዎች
"ምሁራን ተናገሩ!
የህግ ባለሞያዎች ገለፁ!።
ነዎሪዎች እንዲህ አሉ !/
እገሌ እንዲህ አለ
እገሊት እንዲህ አለች" እያሉ የግልን አስተያየት ምልከታ አንድ ሰአት በሙሉ ዜና ብለው የሚያደርቁን ነገር እንዴት እንደሰለቸኝ •••
"በናትህ ይጠቅምሀል እቺን ብቻ አድምጠኝ ፈላስፋው እውቅ የግሪክ ፈላስፋ ነው ምን አለ መሰለህ ••••" ብሎ ሊቀጥል ሲል•••
በናትህ ተወኝ አልኩትና በንዴት ተነስቼ ክፍሉን ለቅቄለት ወጣሁ ። ስራ አልወጣም ያልኩት ሰውዬ ባጃጄን አስነስቼ ወደ ከተማ ከነፍኩ።
ንዴቴን በስራ ለመርሳት ተፍ ተፍ ስል አምሽቼ ልክ ከምሽቱ አራት ሰአት አከባቢ ከገንደቆሬ ወደ ሼል እየመጣሁ ብሎሰም ሆቴል ኩርባው ጋር እንደደረስኩ አንድ እድሜው በአርባዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚሆነው ፈርጠም ያለ ጎልማሳ ሰው ሁለት እጁን በየተራ እያርገበገበ•••
"ባጃጅ ኮንትራት ኮንትራት " አለኝ ። አቆምኩና
የት? አልኩት ፊቱ ላይ እንደእሳት የሚንቀለቀለውን ንዴቱን እያስተዋልኩ
"የት እንደሆነች አላውቅም !
የገባችበት ጉድጓድ ውስጥ ገብቼ እስካገኛት ከኔ ጋር ነህ!
ያልከኝን እከፍላለሁ !"
አለኝና መጀመሪያ የምንሄድበትን ሆቴል ነገረኝ።
እየሄዱን በየመሀሉ •••
" እኔ ላይ! ለኔ እሄ ይገባኛል!" እያለ የአንዱ እጁን መዳፍ በሌላኛው እጁ ቡጢ ያጎነዋል።
ተናድጄ ብወጣ ከኔ የባሰ በንዴት የተከነ ሰው አጋጠመኝና የራሴን ንዴት ረሳሁት። ምን ሆኖ ይሆን እንዲህ ግብግብ ያለው? አልኩ ለራሴ።
ምን ሆነህ ነው ዘመዴ? አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ•••
"ወይይይ ሴት ! አይይይ ሴት ገና ለገና ለሳምንት ያህል ለስልጠና ሀረር ሄጃለሁ ስላልኳት በከተማው የለም ብላ እግሬ ከመውጣቱ ቱ የማትረባ !
እሄማ መጀመሪያ የተቀባበለ እንጂ ሄጄ ገና ሶስት ቀን እንኳን ሳይሞላኝ ኬት ይመጣል እስካሁንም እየተጫወትሽብኝ ነበር ማለት ነው እኔ አንቺ ለማግባት ስሰናዳ በግዜ ጉድሽን ያሰማኝ!
ዛሬ ምን እንደሚውጥሽ አያለሁ "! አለ ።
ከንግግሩ ለኔ ጥያቄ መልስ እየሰጠኝ ይሁን ብሶቱን እየተነፈሰ መረዳት ተሳነኝና ግራ ተገብቼ ዝምታን መረጥኩ ። ትንሽ ቆየና •••
"የገዛ ጓደኛዬ አይቷት አይቷት እኮ ነው የደወለልኝ በአይነ ብረቱ ነው ያያት ወይኔ ደጉ ደግነቴን የዋህነቴን አይታ ነው የተጫወተችብኝ እነሱ እኮ ደግ ወንድ አይወዱም ዛሬ እጅ ከፍንጅ ስይዛት ምን እንደሚውጣት አያለሁ አጠገባ ያለውን ሰውዬ ትውጠው እንደሆነ እንተያያለን !"አለ።
ሁሉም ነገር ገባኝ። ፍቅረኛውን ከሰው ጋር ያያት ጓደኛው ደውሎለት እንደመጣ ተረዳሁ። በዚህ ሁኔታው ቢያገኛት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳስበው ጨነቀኝ ።
ከሰው ጋር ታየች የተባለበት ሆቴል በር ላይ እንደደረስን በፍጥነት
👍1
​​​​በመውረድ እጁን እያወናጨፈ ወደ ሆቴሉ ቅጥር ግቢ ሲግሰግስ ወርጄ ተከተልኩት

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#የህይወት_ታሪክ

አሁን እኔ ብሞት ፥ ከኔ ምን ይቀራል?
ስኖር “ክፉ” ያለኝ
“ደግ ሰው ነበረ " ; እያለ ያወራል
“እሱ ሰው አይደለም” ፥ ሰይጣን ነው መሠሪ"
ሲለኝ የከረመ
“መልካም ሰው ነበረ ፥ መልአክ መሥሎ ኗሪ”
ብሎ ቀብሬ ላይ ፥ እንባውን ይዘራል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የተናቀ ፥ ሲሞት ይከበራል ።
•••
የሚጠላኝ ሁላ
ተወዳጅነቴን ፥ ቀብሬ ላይ ያወሳል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የሚነቀፍ ፥ ሲሞት ይወደሳል
ሲኖር የተረሳ ሲሞት ይታወሳል ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#እንሆ_ነፃነት 💚 💛 ❤️

“የጠላህ ይጠላ ፥ ብድሩ ይድረሰው”
ያጎደፈህ ይጉደፍ ፥ ጭቅቅት ያልብሰው።”
ብዬ አልራገምም!
ጠላትህ ጠላቴ ፥ ነፍሴን ሲያስጨንቃት
የእውነት አንገትህን
የተረት ሸምቀቆ ፥ አስገብቶ ሲያንቃት
አንተን ለሚረግሙ
አንተ እንዳስተማርከኝ ፥ እነሆ ምርቃት።
የጠላህ ይወደድ ፥ ይራቀው አመፃ
ያጨቀየ ይጥራ ያጎደፈህ ይንፃ!
ባንተ የጨቆነኝ
ቂም በቀል ጥላቻን ፥ ፈፅም አይቅመሰው
አንተ እንዳስተማርከኝ ፥ ነፃነት ላውርሰው
እነሆ ነፃነት
እነሆ አንድ እውነት
ሚኒሊክ ጥቁር ሰው!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ልጩህበት!!


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በጥላሁን

ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳስበው ጨነቀኝ ።
ከሰው ጋር ታየች የተባለበት ሆቴል በር ላይ እንደደረስን በፍጥነት በመውረድ እጁን እያወናጨፈ ወደ ሆቴሉ ቅጥር ግቢ ሲግሰግስ ወርጄ ተከተልኩት•••
ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ያን ያህልም ሰው ስላልነበረ አየት አየት አድርጎ እየወጣን•••
"የለችም ባክህ••• እዚህ መጥታ ጭር ሲል ደብሯት ቦታ እንቀይር ብላው ይሆናል አውቃታለሁ እኮ ልትዝናና ስትወጣ ግርግር ትወዳለች ሰው ከማን ጋር እንደሆነች እንዳያስተውላት ነው መሰለኝ ከኔም ጋር ስትዝናና ቦታው በሰዎች ጢም ካላለ አይመቻትም!
ወይኔ ደጉ ያኔ መች ገባኝ !
አሁን አሁን እኮ ነው ቀስ እያለ ነገረ ስራዋ በሙሉ የሚገለጥልኝ
የባጥ የቋጡን እየለፈለፈ ተመልሰን ባጃጇ ውስጥ እንደገባን
"ንዳው! ንዳው! አለኝ።
ወዴት ልንዳው? ስለው•••
"ከሶስቱ ውጪ አትሆንም!" አለና
ትኖራለች ብሎ የሚጠረጥርባቸውን ሶስት ጭፈራ እና ሆቴል ቤቶች ነግሮኝ
"ከሚቀርብህ ጀምር" አለኝ።
በቅርብ ወዳለው አዙሬ መንዳት እንደጀመርኩ ፍቅረኛውን ከሌላ ሰው ጋር ስትቀብጥ ያያት ጓደኛው ሲደውልለት ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል አልፎ እንደነበርና በብስጭት ከሀረር ብቻውን አንድ ሚኒባስ በመያዝ የሙሉ ሰው ከፍሎ እንደመጣ ነገረኝ።
አሳዘነኝ።
ምናልባት የእውነት ሆኖ ከሆነ የሆነው ሆነ የኔ ስጋት ግን በሷ መከዳቱ ሳያንስ በብስጭት ያልሆነ ፀብ ውስጥ ገብቶ መታሰር የሚሉት ሌላ ጣጣ ውስጥ እንዳይገባ ነው።

ቢረጋጋ ጥሩ ነበር ምን ብዬ ላረጋጋው ? ትንሽ አሰብ አደረኩና
ቆይ ብታገኛት••• ማለቴ እንደተባለው ከሰው ጋር ሆና ብታገኛት ምን ልታደርግ ነው?
"እኔ እንጃ ብቻ ላግኛት ያኔ የሚሆነው ይሆናል በናትህ ራቅ ስለሚል ፍጠን!
በበኩሌ ከወንድ ልጅ ጋር ተዝናናች ማለት ወሰለተች ማለት ነው ብዬ አላምንም!
ተዝናንታ ክብሯን ጠብቃ ወደ ቤቷ ልትመለስ አስባ ሊሆን እንደሚችልም ማሰቡ ጥሩ ነው ያንን ካሰብክ ቡሀላ የሚፀፅትህን ነገር ከማድረግ ትቆጠብና ቅድሚያ ቢያንስ እርግጠኛ ለመሆን ትሞክራለህ አይመስልህም ስለው
አይመስለኝም በጭራሽ አይመስለኝም እኔ የፍቅር ሂወቴን በመሰለኝ ሳይሆን ልቤ በሚለኝ በራሴ እምነት ነው የምመራው
በኔ እምነት ሴት ልጅ አንሶላ የተጋፈፈች ቀን ሳይሆን ወንዶችን ቀለል ብላ የመቅረብ ባህሪ ያላት መሆኑን ያወኩ ቀን ነው እምነቷንና እምነቴን የምታጎድለው!"
ማለት?
ቀለል ብላ የመቅረብ ስትል ጭራሽ የወንድ ዘር መቅረብ የለባትም እያልከኝ እንዳይሆን?! ስለው
"አንድ ነገር ልጠይቅህ ?" አለ ።
ጠይቀኝ
"ለግዜው የማይፈልገው ገንዘብ እንዳለው ማበደር እንደሚችል እያወክ 300 ብር አበድረኝ ስትለው የለኝም ብሎ የከለከለህን ሰው በሌላ ግዜ አንድ ሺ ብር አበድረኝ ብለህ ትጠይቀዋለህ?
ካላበድኩ በስተቀር እንኳን ሺ አንድ ብርም አልጠይቀውም ግን እሄ ከፍቅር ወይም ካነሳነው ጉዳይ ጋር ምን አገናኘው?
"ሌላ ጥያቄ ልድገምህ ያኔ በምን መልኩ እንደሚገናኝ ሳልነግርህ እራስህ ትረዳዋለህ"
እሺ ቀጥል
"ታክሲ ውስጥ ባጋጣሚ አጠገብህ የተቀመጠችውን ሴት ልታዋራት ልታጫውታት ስትሞክር ፊቷን እንዳኮማተረች ወደ አንተ አንድም ግዜ እንኳን ዞራ ሳታይ ልክ እንደሹፌሩ ፊት ለፊቷን ብቻ እየተመለከተች ጫወታህን ባጭር ባጭሩ ዝግት የሚያደርግ መልስ እየመለሰች ብታከሽፍብህ ከመለያየታችሁ በፊት ስልክ ቁጥሯን ለመጠየቅ ትደፍራለህ?"
ሰውየው ነገሮችን ቤት በኩል እያገናኛቸው እንደሆነ እያሰላሰልኩ መልስ ሳልሰጠው ስለ ዘገየሁ
"መልስልኛ! ትጠይቃታለህ?!
እንዴ ፊቷን አጨማዳው እንዴት ልጠይቃት እችላለሁ አልጠይቃትም መጀመሪያ ልግባባት ስሞክር ፊት ከነሳችኝ ከታክሲው እስክወርድ ዞሬም ሳላያት እንደምሄድ እርግጠኛ ነኝ።
" አየህ መጀመሪያ ቀለል ብላ አንተ የባጥ የቆጡን ስትቀባጥር ከገለፈጠችልህ ግን ስልክ ለመጠየቅ ቀለለህ ማለት ነው!
ስልክ ስጠይቅ በቀላሉ ከተሰጠህ ደግሞ ደውሎ እንገናኝ ልጋብዝሽ ለማለት ቀለለህ
ግብዣህን በቀላሉ ከተቀበለች ወደ ቀጣዩ ጉዳይህ ለመግባት አልጋ ባልጋ ሆነልህ ማለት ነው ስለዚህ እቺ ሴት የኔዋ ብትሆን እምነቷን የሸረሸረችው መቼ ነው? ብዬ እራሴን ብጠይቅ
በኔ እምነት አልጋ ውስጥ ሳይሆን ታክሲ ውስጥ የተገናኛችሁ ቀን ነው ያን ቀን እኔ ባጋጣሚ እሷ ሳታየኝ ከጀርባችሁ ቁጭ ብዬ ቢሆን መጨረሻችሁን አልጠብቅም እንደከዳችኝ የምቆጥረው ያኔውኑ ነው!"
ሲለኝ የእውነት ነበርና አመለካከቱ ያስደነገጠኝ
በዚህ ሀሳብህ በፍፁም አልስማማም እስቲ አንተንም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ አንዳንድ ሴቶች
ፍቅረኛም ባልም ሳይኖራቸው ፣ ያሉበት ሁኔታ ፍቅር ለመጀመር ፈቅዶላቸው፣ ውስጣቸውም ፍቅር ለመጀመር ፍላጎት እያለው
በዛ ላይ ሽቅርቅር ብለው እየወጡ በተለያየ አጋጣሚ ከወንዶች ጋር በተገናኙ ቁጥር ወንዶቹ ሊቀርቧቸው ሲሞክሩ ኮሶ የጋቷቸው ይመስል
ፊታቸውን ከስክሰው የወንዶችን ቆሌ የሚገፉት በምን ምክንያት ነው?ስለው•••
"አይነጥላ ነው አዎ አይነ ጥላ ያለባት ሴት ካልሆነች በስተቀር በዚህ ሁኔታ ላይ ሆና በጤናዋ እንደዚህ የምትሆን ሴት ብዙ የምትኖር አይመስለኝም! ብሎኝ አረፈው። ሳይታወቀኝ እየጮህኩ
አትሳሳት ይልቅ
የተግባባች ፣ የሳቀች፣ ወንዶችን በቀላሉ የቀረበች ሴት ሁሉ ሌላ ፍላጎት አላት የተኮሳተረች ሴት ሁሉ ደግሞ ፍላጎት ስለለላት ነው ብለህ መደምደም ትልቅ ስተት መሆኑንን ብታምን የተሻለ ይመስለኛል!
አንተ ምናልባት ከፍቅረኛህ ውጪ ልክ እንደወንዶች ጓደኛችህ በጓደኝነት የምትቀርባቸው ሴቶች ከሌሉ አላቅም!
እኔም ወንድሜቼም ጋደኞቼም በዚህ መልኩ የምንቀርባቸው ሴቶች አሉ አንዳንድ ሴቶች እንደውም ሁሉም ወይም አብዛኛቹ የቅርብ ጋደኛቻቸው ወንዶች እንዲሆኑ እንደሚፈልጉና እንደሆኑም የሚናገሩ አሉ ።
በጋደኝነት ህይወታቸው ወጣ ብሎ ከመዝናናት አንስቶ ብዙ ነገሪችን በጋራ ያሳልፋሉ ያ ማለት በተገኘው አጋጣሚ በሙሉ ሌላ ጉዳይ ውስጥ ይገባሉ ማለት አይደለም!።
"እሱማ ፍቅረኛ ወይም ባል ሳይኖራቸው ሊሆን ይችላል"
ኧረ እያላችው ! እሄውልህ ማናችንም ብንሆን የምንፈልገውን ነገር ለማድረግ የሚከለክለን የፍቅር ጓደኛ መኖር ወይም አለመኖሩ ሳይሆን የውስጣችን ስብእናና የልባችን ትርታ ብቻ ነው
ምንም ነገር ለማድረግ መቀራረብ ሳይሆን መተዋወቅ በማያስፈልግበት በዚህ ዘመን ፍቅረኛህን ታሟኝ የምታደርገው ወንድ አትቅረቢ እያልክ በመጮህ ሳይሆን እራስህን ልቧ ውስጥ ማስቀመጥ ከቻልክ ብቻ ነው ያለበለዚያ ፍቅረኛ ሳይሆን እረኛ ሆነህ ትቀራለህ"! አንተን ለማለት ፈልጌ አይደለም ይቅርታ አመለካከቴን ነው ያወራሁት አልኩትና በዛው ቀጠል አድርጌ•••
ወደ ሆቴሉ እየደረስን ነው ይልቅ አሁን ወደ ጉዳያችን እንመለስና እንደታናሽ ወንድም እምመክርህ ምናልባት ከሰው ጋር ሆና ብታገኛት በኔ በኩል ኩሩና በሳል ወንድ ሆነህ ብታሳያት ደስ ይለኛል!
"ማለት?!"
የተባለው እውነት ሆኖ ከተገኘ በቃ አለ አይደል ምንም ሳትናደድ
ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ እንኳንም በግዜ አወኩሽ መልካሙን ሁሉ እመኝልሻለህ!" ብለህ ብቻ ብትለያት
"ምንምንምምን !? "ያልተነካ ግልግል ያውቃል" አሉ ደሞ መች በግዜ አወኳት ከዛ በፊት ያንከራተተችኝን ተወው እሺ ብላኝ አብረን ከሆንን እንኳን አንድ አመት ከስድስ ወር ሆኖናል እኮ!"
ቢሆንም ገና አልተጋባችሁም ብዬ ነዋ!
"እና ባንጋባስ?!"
ማለቴ እንደምታገባት እርግጠኛ ካልሆነች•••
አልኩና መናደዱን ከድምፁ በመረዳቴ ያሰብኩትን ሳልጨርሰው ዝም አልኩ•••
"ካልሁነች ምን?! ጨርሰዋ !
ኧረ በናትህ ተወኝና
👍2
​​ዝም ብለህ ንዳ አንተ ደሞ
ነው ወይስ አብሯት ያለው ሰውዬ አጎትህ ነው ብዙ ተከራከርክላት እኮ !"
ሲለኝ እውነትም ዝም ብዬ ብነዳስ አልኩና ዝም አልኩ ።
እንደደረስን ምንም ሳይለኝ ወርዶ ወደ ሆቴሉ ሲገባ ተከትየው ገባሁ።
በር ላይ ቆም ሲል ቆምኩ።
ወደውስጥ ገልመጥ ገልመጥ አደረገና ካጠገቤ ድንገት ተፈናጥሮ በመሄድ ቀዝቀዝ ባለው ዘፈን ጥንድ ጥንድ ሆነው ተጣብቀው ከሚወዘወዙት መሀል•••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
​​#ልጩህበት!!


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በጥላሁን

ኧረ በናትህ ተወኝና ዝም ብለህ ንዳ አንተ ደሞ
ነው ወይስ አብሯት ያለው ሰውዬ አጎትህ ነው ብዙ ተከራከርክላት እኮ !"
ሲለኝ እውነትም ዝም ብዬ ብነዳስ አልኩና ዝም አልኩ ።
እንደደረስን ምንም ሳይለኝ ወርዶ ወደ ሆቴሉ ሲገባ ተከትየው ገባሁ።
በር ላይ ቆም ሲል ቆምኩ።
ወደውስጥ ገልመጥ ገልመጥ አደረገና ካጠገቤ ድንገት ተፈናጥሮ በመሄድ ቀዝቀዝ ባለው ዘፈን ጥንድ ጥንድ ሆነው ተጣብቀው ከሚወዘወዙት መሀል•••
በስተግራዋ እስከ ባቷ መገባደጃ የተቀደደ ትከሻውን በዞሩ ሁለት ቀጫጭን ገመዶች ተንጠልጥሎ ከደረቷ ጀምሮ ቁልቁል ገላዋ ላይ ቀዳዋ እስኪመስል የተጣበቀ እሮዝ ቀለም ያለው የራት ልብስ ለብሷ አብሯት እሚደንሰው ሰው አንገት ውስጥ በፍቅር መርከብ እየተንሳፈፈች የምትደንሰውን ሴት ክንዷን ይዞ በመጎተት ከሰውየው እቅፍ ውስጥ መንጭቆ አወጣት!
እሷ ምን መጣ ብላ በድንጋጤ ስትዞር፤ እሱ ፊቷን አይቶ የሱ ፍቅር አለመሆኗን ሲረዳና አብሯት ያለው ሰው ይቅርታ የምትለውን ቃል ከፉ አውጥቶ እስኪጨርሳት እንኳን ግዜ ሳይሰጠው ተደፈርኩ በሚል ስሜት እንደነብር ተወርውሮ አንገቱን ሲያንቀው ዘልዬ መሀላቸው ገባሁ!
ይቅርታ አርግለት ባባ በስተት ነው በስተት ነው ስለው መጀመሪያውኑ ፊቷን እንዳየ ሲደነግጥ አስተውሎት ነበር መሰለኝ ከማነቅ ውጪ ቦክስ እንኳን ሳይሰነዝር•••
"እብድህን ወደዛ ይዘህልን ውጣ ባክህ ! ብሎ እሱን ገፈተረውና ሽምቅቅ ብላ ወደቆመችው ፍቅሩ ዞሮ •••
" አስደነገጠሽ አይደል የኔ ማር?!" አላት። እኛም በፍጥነት ተያይዘን ውልቅ አልን።
ባጃጅ ውስጥ ገብተን ወደሶስተኛው ቤት ጉዞ እንደጀመርን ድንጋጤው ለቀቀው መሰለኝ•••
"አይገርምም የሰይጣን ስራ ቁመቷ፣ ከለሯ፣ ፀጉራ ከነ አያያዟ እራሷን ቁጭ እኮ ነች በዛላይ የለበሰችው ልብስ ተውሳት ነው እንዴ እውነቴን ነው ሀሉንም ነገር ከፍቅረኛዬ የተዋሰችው እኮ ነው እምትመስለው ቢያንስ እንኳን በውፍረት መለያየት የለባቸውም ደባዋ እራሱ ቁጭ የኔዋን!" ሲል
ሳቄን በጭራሽ መቆጣጠር አልቻልኩም ኪኪኪኪኪ•••
"ሳቅ አንተ ምን አለብህ!"
እና በዛች ሰከንድ ውስጥ እሄን ሁሉ ደባዋን (ቂጧን ) ሳይቀር ማየትህ ቢያስቀኝ በኔ ይፈረዳል?
"ኧረ አይፈረድም"
እሄኔ ልጅቷ ከፍቅረኛህ ጋር በብዙ ነገሯ ትለያይ ይሆናል አንዳንዴ ውስጣችን የሚፈልገውን ነው አይናችን የሚያየው ለዛ ይሆናል።
አልኩትና በሆዴ ዛሬማ የከተሟዋ ሴቶች ሁሉ እሷን መስለው ነው እሚታዩህ ብዬ አከልኩበት።
ሶስተኛው ቤት ገባን እዛም አልነበረችም።
አሁን የቀረን አንድ ቦታ ብቻ ነው ወደዛው መብረር ጀመርን።
ልንደርስ ትንሽ ሲቀረን መንገድ ላይ ወዳለ ወደ አንድ ከፍንዳታዎችና ከዩንቨርስቲ ተማሪዎች ውጪ ሌላ ሰው ወደማይገባበት ቀውጢ ጭፈራ ቤት እየተገላመጥኩ መቸስ እዚህ አትኖርም አደል ስለው•••
ድንገት በሩ ላይ ኤዱን አየኋት ሊያውም ከዛ ልጅ ጋር!
በፍጥነት እየነዳ ድንገት ሰው እንደገባበት ሹፌር ልቤ ስንጥቅ ሲል ፍሬኑን ጭምቅ አደረኩት ባጃጇ ሲጢጢጢጢጢጢ ብላ ቀጥ ስትል ሰውየው ተፈናጥሮ ወደ ትከሻዬ መጣና ሳይመለስ •••
"ምነው! ሰው ገባብህ? ውሻ ገባብህ?" እያለ ወደ ፊት በማንጋጠጥ ምን እንደገባብኝ ለማየት ሲሞክር •••
ሰው አይቼ ነው።አልኩት።
"ማንን? አየሀት? እሷን ነው? የቱጋ? የታለች?" ሲል •••
ማነች እሷ አልኩት ግራ ተጋብቼ
" የኔዋ ነቻ! የኔዋ ጉድ ሌላ ማንን ታያለህ!"
ወይ ጉድ••••
"የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ብለው ከሚተርቱ የጨነቀው የሚናገረውን አያውቀው ቢሉ ኖሮ ሳይሻል አይቀርም እስቲ አሁን የሱን ፍቅረኛ የት አውቂያት ነው የማያት ?
እንኳን ለኔ ለራሱም ሳትጠፋበት አትቀርም እያልኩ ውስጥ ጫጫታው ስላልተመቻቸው ሳይሆን አይቀርም ስልክ ለማናገር ወጥተው አንድ ስልክ እየተቀባበሉ በጋራ ከሚያውቁት ከሌላ ሰው ጋር እያወሩና እርስ በርስ እየተያዩ ወደ ሚሳሳቁት ወደ እነ ኤደን ከርቀት እንዳፈጠጥኩ •••
ወርደህ ቀጥ ብለህ ሂድላት ከዛ ኤዱ ቅድም ከቤት ስትወጡ ወደ ግቢ ነው እምንሄደው ብለሽ መዋሸቱ ለምን አስፈለገ እኔን ዋሽኝ ችግር የለውም ግን በዚህ ሰአት ሊያውም እዚህ በየቀኑ ፀብ በማያጣው ጭፈራ ቤት ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ በላት በላት የሚል ስሜት ተሰማኝ።
ዘወር ብዬ ሰውየውን ሳየው እሱም ግራ ተጋብቶ እኔን ተከትሎ እነ ኤዱ ላይ አፍጥጧል።
መለስ አለና " ማነች? ታውቃታለህ? " አለኝ
ማነች ልበለው? አዎ ያክስቴ ልጅ ነች፤ የዩንቨርስቲ ተማሪ ነች በዚህ ሰአት ከወንድ ጋር ጭፈራ ቤት••••
አላስጨረሰኝም •••
"ታድያ ምን ችግር አለው አለው አብረው ተዝናንተው የሚለያዩ ንፁህ ጋደኛሞች ሊሆኑ ይችላሉ ። አለኝ በስላቅ ።
በንዴት •••
አዎ ችግር የለውም ይዝናኑ እኛም እንሂድ አልኩና ባጃጇን አስነስቼ ወደ መጨረሻው ቤት ጋለብኳት።
ደርሰን እሱ ከፊት እኔ ከጀርባው ተከታትለን እንደገባን
"ያቿትና"
አለኝ ፊት ለፊት ካንድ ሰው ጋር የተቀመጠች ቆንጂዬ ሴት ተመለከትኩ ።
ወደሱ ስዞር አራት ጣቶቹን ከንፈሩ ላይ ጭኖ እንዳፈጠጠባቸው ትንሽ ቆየና
"ውይ ውርዴት !
አቤት ቅሌት !
እሄ እኮ ውጪ ሀገር የነበረ ያክስቷ ልጅ ነው የሰርጋችሁን ግማሽ ወጪ እኔ እችላችሃምሀለሁ ብሎ ቃል ገብቶልናል! በቅርብ ነው የመጣው።
ጓደኛዬም ያላወቀው ለዛ ነው!
እነደመጣ አዲስ አበባ ነበር ያረፈው ሰሞኑን ወደ ድሬ ይመጣል ስትለኝ ነበር እንደዛ ሲፎክር የነበረው ሰው ጭራሽ "ደብቀኝ እንዳታየኝ ! "
እያለ እኔን ጎትቶ ከጀርባዬ ተደበቀና
"ዝም ብለህ ወደ ኋላ ና እንውጣ!" አለኝ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
​​#ልጩህበት!!


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በጥላሁን

ደርሰን እሱ ከፊት እኔ ከጀርባው ተከታትለን እንደገባን
"ያቿትና"
አለኝ ፊት ለፊት ካንድ ሰው ጋር የተቀመጠች ቆንጂዬ ሴት ተመለከትኩ ።
ወደሱ ስዞር አራት ጣቶቹን ከንፈሩ ላይ ጭኖ እንዳፈጠጠባቸው ትንሽ ቆየና
"ውይ ውርዴት !
አቤት ቅሌት !
እሄ እኮ ውጪ ሀገር የነበረ ያክስቷ ልጅ ነው የሰርጋችሁን ግማሽ ወጪ እኔ እችላችሃምሀለሁ ብሎ ቃል ገብቴልናል! በቅርብ ነው የመጣው።
ጓደኛዬም ያላወቀው ለዛ ነው!
እነደመጣ አዲስ አበባ ነበር ያረፈው ሰሞኑን ወደ ድሬ ይመጣል ስትለኝ ነበር እንደዛ ሲፎክር የነበረው ሰው ጭራሽ "ደብቀኝ እንዳታየኝ ! "
እያለ እኔን ጎትቶ ከጀርባዬ ተደበቀና
"ዝም ብለህ ወደ ኋላ ና እንውጣ!" አለኝ።
እየተጓተትን ወጣን።
እሺ አሁን ወዴት እንሂድ? ስለው•••
"ዛሬ በቃ ካንተ ጋር የመረጥከው ቦታ ስጠጣ አድሬ ጥዋት በዛው ወደሀረር መመለስ ነው
እምፈልገው ግን ፍቃደኛ ከሆንክ ነው ?"
አለኝ እኔም በኤዱ ተከፍቼ ስለነበር መጠጣት ፈለኩ በሀሳቡ ተስማማሁና ተያይዘን ሄድን እየጠጣን ስለራሱ ብዙ እያወራልኝ ቆየና ድንገት በመሀል •••
"ቅድም ከልጁ ጋር ያየሀት ልጅ ግን እውነት ያክስትህ ልጅ ነች እንዳትዎሸኝ በናትህ እ ያክስትህ ልጅ ነች?"
ለምን ጠየከኝ ? አልኩት
"እኔ እንጃ የሆነ የፍቅር ስሜት አይንህ ውስጥ ያነበብኩ መስሎኝ ነው እ ተሳሳትኩ?!"
ኧረ በጭራሽ የፍቅር ስሜት እኔ ላይ ልታነብማ አትችልም ግን ያክስቴ ልጅ አይደለችም ብዬ ስለኤዱ በስሱ ነገርኩት ጎህ ሲቀድ ትዝ ይለኛል ግን ብዙ ከመጠጣቴ የተነሳ መች? እና እንዴት? እሱ ወደ ሀረር እኔም ወደ ቤት እንደገባሁ ትዝ አይለኝም።
በነጋታው ስድስት ሰአት አከባቢ ተነሳሁና ገላዬን ተጣጥቤ ወደ ስራ ወጣሁ።
በአከባቢያችን ባለ አንድ ምግብ ቤት ገብቼ ምሳ አዘዝኩና ከመምጣቱ በፊት ኤደንጋ ደወልኩ።
አነሳችው ድምፁዋ ስትጨፍር ማደሯን ይመሰክራል ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ•••
የት ነሽ?
"ዶርም ነኝ ጋደም ብዬ !
ትናንት ታክሲ አገኛችሁ?
አዎ ዳንዬ ካንተ ጋር እንደወጣን ወድያው ነው ያገኘነው;"
በግዜ ገባችሁ?
አዎ ምነው?
አይ ምንም ከአንደበትሽ ልስማው ብዬ ነው!
ምኑን ዳኒ?
በቃ ተይው!
ምን ሆነሀል ዳኒ!?
ምን ሆንኩ?!
"አይ ምን እንደጠየከኝ እንኳን ሳይገባኝ በቃ ተይው ስትለኝ ግራ ገብቶኝ ነው"
በቃ እንደውም እንኳን ያልገባሽ ወሬ እንቀይር••
እሺ ካልክ!
እሺ!
"እሺ ምን!"
እሺ ምንም!
እንዴ ዳኒ ግራ አጋባከኝ እኮ ወሬ እንቀይር አላልክም እሺ ስለ ምን እናውራ?"
ምን አዲስ ነገር አለ?
"ምንም ዳኒዬ ምን አዲስ ነገር ይኖራል ብለህ ነው"
በቃ እሺ
በቃ እሺ ምን?
በቃ እሺ ቻዋ አዲስ ነገር ከሌለ!
"እሺ ቻው ግን•••" እያለች ስልኩን ዘጋሁት።
ስራው አስጠላኝ ባጃጄን ላጣቢ ሰጥቼ ገብቼ ተኛሁ።
ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ጆሲ እና ያ ጅምር እብድ ጓደኛው በርጫቸውን ይዘው እየተሳሳቁ ሲገቡ በሆዴ ተደፍቼ በመተኛት የተኛ ሰው መሰልኩ።
ጆሲ••••" እንዴ ዳኒ ስራ ወጥተህ አልነበር እንዴ በል ተነስ አትደብረን •••" ምናምን እያለ ሊቀሰቅሰኝ ቢሞክርም አውቆ የተኛን እንዲሉ ዝም አልኩ።
ከቆይታ ቡሀላ ከነመኖሬም ረስተውኝ ጆሲ እና ጓደኛው በራሳቸው አለም ውስጥ ገብተው የባጥ የቋጡን መዘባረቅ ጀመሩ።
የተኛሁ መስዬ ብተኛም ወሬያቸው እረፍት ነሳኝ ከአንዱ ርእስ ወደ ሌላ ለመሄድ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ አይጠብቁም ወሬያቸውን ይጀምሩታል እንጂ አያልቅም።
ብስጭትጭት ብዬ በመነሳት ቤቱን ጥየላቸው ስወጣ ጆሲ•••
"ና እንጂ ዳንዬ! ወዴት ልትሄድ ነው? ረበሽንህ እንዴ! ማታ ሰክረህ ምን ስትል እንደነበር ልንገርህ ክክክክ !"
መልስ ሳልሰጠው ወጥቼ ሄድኩ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ህይወቴ እራሱ የሰከረ ሆኖ ታየኝ ከኤዱ ጋር እንኳን ልንገናኝ ስልክ ተደዋውለን ሰላም ሰላም ከመባባል ውጪ የረባ ነገር ሳናወራ ወራቶች ተቆጠሩ የሷን ባላውቅም እኔ ግን ከራሴ ጋር ስለሷ ሳላወራ አድሬ አላውቅም ።
ጥፋተኛዋ እሷ ሆና ሳለ ስለመገናኘት አንስታብኝ ስለማታውቅ እልህ ያዘኝ ።አንድም ቀን ላግኝሽ ሳልላት አልፎ አልፎ በስልክ ድምጿን ብቻ እየሰማሁ ብቆይም ጤነኛ አለነበርኩም።
ለካ ከፍቅር ጋር እንደመጣላት ከባድ በሽታ የለም ቆይ በአለም ላይ ከፍቅር ጋር ተጣልቶ ያሸነፈ ጀግና አለመኖሩን እያወቁ ፀብ መግጠም ምን ይሉታል እኔ ማነኝ እናነው እንኳን ተራው እኔ ክርስቶስም የተረታው ለፍቅር አይደል እንዴ?! ምን እሚሉት ነው እሄ ትንቅንቅ ! እውነታውን ብረዳም ብቻየን መታመም ብቻ ሆነ ስራዬ ያለሁበትን ሁኔታ እንኳን ለሷ ለጓደኛዬ ለጆሲም አልነገርኩትም ።
ሁኔታዬን ተረድቶ ሲጠይቀኝም መልሴ ቀና አልነበረም በብስጭት እጬህበታለሁ።
"ማፍቀር እኮ መታደል ነው ዳንዬ አፍቅረሀታል በቃ ለምን አታምንም?!" ሲለኝ
ቁስሉን እንደነኩበት አንበሳ ቁጣዬ ገንፍሎ እጮሀለሁ እሱም ድርቅ ያለ ደረቅ አደል ይስቅና •••
"ጩኸትህ መሸነፍህን በደንብ በፍቅሯ መንበርከክህን ያረጋግጥልኛል እንጂ ሀሳቤን አያስቀይረኝም ይልቅ ብናወራ ይሻላል በጩኸት ዝም ልታስብለኝ አትሞክር!
ጓደኛዬ አንተኮ መፍታት ያቃተህ እራስህ ያሰርከውን ገመድ ነው አውቃለሁ እራስህ ያሰርከውን ገመድ መፍታት አለመቻል እጅግ ያበሳጫል ነገር ግን እየተበሳጨህ አልፈታ ያለህን ቋጠሮ ጎትተህ ልትበጥሰው በሞከርክ ቁጥር ጭራሽ እያጠበከው እንደምትሄድ እወቀው!!
በቃ ልትበጥሰው ልታስቀረው አለመቻልህን እመን ያኔ ቢያንስ ላትበጥሰው እየጎተትክ ከማጥበቅ ትቆጠብ ይሆናል!
ለማንም ሳትናገር ብቻህን በተብሰከሰክ ቁጥር መጨረሻህ ማበድ ይሆናል እሺ እሄን እወቀው ብሎኝ ካጠገቤ ይሄዳል!
ቤቱን ብቻውን አገኘዋለሀ!
ያኔ "" ኤዱን በናትሽ አንዴ ብቻ ልጩህ!?" ያላት ሰካራም ፊቴ ድቅን ይላል በሩን እዘጋና ልክ እንደሱ እጬሀለሁ !
በዚህ ሁኔታ ብዙ ታገልኩ ዛሬ ግን አልቻልኩም!
ለሊቱን ሙሉ በህልሜ ሳያት ስላደርኩ ነው መሰለኝ ናፍቆቴ ልኩን አለፈ ባላገኛት እንኳን ወደዛ አጥር ወደለለው ዩንቨርስቲያቸው ሄጄ ከሩቁ አይቻት ልመለስ ሄድኩ።
ደርሼ አምስት ደቂቃ ያክል እንኳን ሳልቆም ከሩቅ ኤዱን አየኋት !
ግን ብቻዋን አልነበረችም ከልጁ ጋር ነች ውስጤ ሲፈነቃቀል ታወቀኝ እዛው በቆምኩበት
ጩህ ጩህ ስሟን ከፍ አድርገህ ጥራት ጥራት አለኝ••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «​​#ልጩህበት!! ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ ፡ ፡ #ድርሰት_በጥላሁን ደርሰን እሱ ከፊት እኔ ከጀርባው ተከታትለን እንደገባን "ያቿትና" አለኝ ፊት ለፊት ካንድ ሰው ጋር የተቀመጠች ቆንጂዬ ሴት ተመለከትኩ ። ወደሱ ስዞር አራት ጣቶቹን ከንፈሩ ላይ ጭኖ እንዳፈጠጠባቸው ትንሽ ቆየና "ውይ ውርዴት ! አቤት ቅሌት ! እሄ እኮ ውጪ ሀገር የነበረ ያክስቷ ልጅ ነው የሰርጋችሁን ግማሽ ወጪ እኔ እችላችሃምሀለሁ…»
#ያ_ሞኙ_ወዳጄ

አንገበጀበችኝ ፈጀችኝ ይለኛል ያ...ሞኙ ወዳጄ
የታደለለትን እግዜር የሰጠውን አምኖ ሳይል በጄ
የኔስ አንገብግቢኝ በደንብ ይረር ቆሽቴ
ደጋግመሽ ለብልቢኝ ሳትሰለቺ በሞቴ
እሰት ሆነሽ ኑሪ ሰደዱ የከፋ
እኔን ውሃ አድርጎኝ የብቻዬ አድርጌ
ይዤሽ እንድጠፋ።
#የሸተተ_ሽቶ

ብሩ ይገማል አለኝ ቱጃሩ ወዳጄ
እንኳን ላፍንጫዬ መቼ ተርፎ ከእጄ
እንካ አሽትተው አለኝ ፊቱን አጨፍግጎ
አንዳች የብር ክምር በቃጫ ጠፍንጎ
እየተንቀ ቀጥኩ ተቀበልኩትና
በሸተው........ባሸተው
እንደ እቅፍ አበባ
ከገንዘቡ ቀድሞ ችግሬ ጠነባ።
​​#ልጩህበት!!
:
:
#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በጥላሁን

በዚህ ሁኔታ ብዙ ታገልኩ ዛሬ ግን አልቻልኩም!
ለሊቱን ሙሉ በህልሜ ሳያት ስላደርኩ ነው መሰለኝ ናፍቆቴ ልኩን አለፈ ባላገኛት እንኳን ወደዛ አጥር ወደሌለው ዩንቨርስቲያቸው ሄጄ ከሩቁ አይቻት ልመለስ ሄድኩ።
ደርሼ አምስት ደቂቃ ያክል እንኳን ሳልቆም ከሩቅ ኤዱን አየኋት !
ግን ብቻዋን አልነበረችም ከልጁ ጋር ነች ውስጤ ሲፈነቃቀል ታወቀኝ እዛው በቆምኩበት
ጩህ ጩህ ስሟን ከፍ አድርገህ ጥራት ጥራት አለኝ••
ግን አልጮሆኩም ዝም ብዬ ፈዝዤ ስመለከታቸው ሁለት የማላውቃቸው ሴቶች መጥተው ተቀላቀሏቸው ወድያው ልጁ ሁለቱን እጃቸውን ጨብጦ ትከሻቸውን በመግጨት ኤዱን ግን ጉንጯን በመሳም ተሰናበታቸውና በርምጃ ከግቢው መውጣት ጀመረ ውስጤ በልጁ እና በኤዱ መካከል የሆነ ነገር እንዳለ እርግጠኛ ሆነ መሰለኝ ፍርሀት ፍርሀት ሲለው ታወቀኝ።
የቆመ ባጃጅ ውስጥ ገብቶ ሲሄድ ተከተልኩት።
ከዚራ አከባቢ ሲደርስ ወርዶ የሆነ ካፍቴርያ ውስጥ ገባ ።
ትንሽ ቆየት አልኩና እዛ ካፍቴሪያ ውስጥ ድንገት እንደተከሰተ ሰው መስዬ ገባሁ ።
ልጁና አንዲት የምታምር ሴት ጎን ለጎን ተቀምጠው ጭማቂ በስትሮ እየማጉ ያወራሉ።
ክው አልኩ እሄ ልጅ ኤዱን እያጃጃላት ባልሆነ እቺ ደሞ ማነች እያልኩ በውስጤ ፈንጠር አልኩና ጀርባዬን ሰጥቻቸው ተቀመጥኩ። ስልኬን አውጥቼ ለኤዱ ደወልኩላት•••
"ወዬ የዘጋከኝ ወንድሜ!" አለች እየሳቀኝ እቺ ልጅ ደግሞ እሄ ወንድሜ እምትለውን ነገር አፏ ላይ ነው እንዴ ያተሙባት እያልኩ ለራሴ የት እንደሆነች ጠየኳት ግቢ ከጓደኛቿ ጋር መሆኗን እንደነገረችኝ
ጓደኛሽ ደና ነው? ስላት ደህና መሆኑን ነግሯት ዛሬ እሚገርም ኳስ አለ ብሏት እኛ ሰፈር ወዳለው ድሬ ዳዋ እስታዲየም ኳስ ሊመለከት መሄዱን አከለችበት"
ተሰናብቻት ስልኩን ዘጋሁትና ። ኳስ ሜዳው ካፌ ኳሷ ደሞ ልጅቷ እንዳትሆን ብቻ አልኩና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ወደ ልጅ በመሄድ ድንገት እንዳየሁት ሆኜ ሰላምታ ተለዋውጠን ፍቃደኛ ከሆነ አንድ ግዜ ለ አምስት ደቂቃ ላናግረው እንደምፈልግ ስነግረው ፍቃደኛ ቢሆንም ከኤዱ ጋር ምን አይነት ግኑኝነት እንዳላቸው ስጠይቀው
በጣም በሚያስጠላ ሁኔታ ምን አገባህ የሚል ስሜት ባዘለ መልኩ መልስ ሊሰጠኝ ሲሞክር አቋርጬው ቤተሰቦቿ እንዴት ሆነው እንዳስተማሯት ስለነገረችኝ እንዳትሰናከል በማሰብ እንጂ እሱ እንዳለው እንደማያገባኝና ያንንም ጠንቅቄ እንደማውቅ ነግሬው መልስ ሳይሰጠኝ በቆመበት ጥዬው ሄድኩ።
እንዲሁ እንደተወዛገብኩ ቀን ቀኖችን ቀኖች ሳምንትን ሳምንት ወርን ወሮች አመትን እያስከተሉ ነጎዱ እነኤዱም ሁለት አመት ተምረው የመጨረሻውን አንድ አመት መማር ከጀመሩ አንድ ወር ሆናቸው።
ያሁኖቹን ባላውቃቸውም መጀመርያ ላይ ጓደኛቿ ከነበሩት ትግስት ከመሲ ጋር አብሯ ስታብድ ትምህርቷን በአግባቡ ስላልተከታተለች እስከመጨረሻው ላትመለስ ከትምህርት ቤቱ ተባራ እዚሁ ድሬ ዳዋ ልዩ ስሙ ነምበር ዋን በመባል ወደ ሚታወቀው አከባቢ አንድ ሆቴል ውስጥ በአስተናጋጅነት ስትቀጠር ረድኤት ደሞ ለአንድ አመት ተቀጥታ ወደ ቤተሰቦቿ መሄዷን ነግራኛለች ።
ኤዱ ግን ልትመረቅ ወራቶች ብቻ ቀርተዋታል ልትመረቅ መሆኑን ባሰብኩ ቁጥር ጭንቀቴ ይጨምራል ስጨነቅ እንቅልፍ አጣለሁ ከጭንቀቴ ለመደበቅ እንቅልፍ ለመተኛት ስል ማታ ማታ ቋሚ ጠጪ ከሆንኩ ቆየሁ።
ሁሌም የምጠጣው ለመጀመሪያ ግዜ ኤዱን በሩ ላይ ቆማ ያየኋት ጭፈራ ቤት ውስጥ ነው ።
ወደ ውስጥ ከመግባቴ በፊት የቆመችባትን ቦታ ቆም ብዬ አያለሁ ኤዱ ግን የለችም ጠጥቼ ስወጣ ግን ወደዛ ከተመለከትኩ ቆማ ትታየኛለች እራሴንም እሷንም እየተሳደብኩ ወደ ቤት እንደምገባ ብዙ ግዜ ዳኒ ነግሮኛል ዛሬም እዛው እየጠጣሁ ነው።
በግዜ ስለገባሁ ሙዚቃው በስሱ ነው የተከፈተው ነገር ግን ከኔ በሁለት እርምጃ ርቀት እንደኔው ብቻውን የሚጠጣው ሰው ሰላሜን አሳጣኝ በሱ ምክንያት እራሴን ማዳመጥ አልቻልኩም ሰውየው አስተናጋጇን ያለ ምንም ምክንያት ይሰድባታል።
እሱ በሰደባት ቁጥር እኔ እናደዳለሁ።
የማይሆን ጥያቄ ይጠይቃትና መልስ አልሰጥ ስትለው ይሰድባታል •••
"ቆይ እሄ ቂጥሽ ሀይ ኮፒ ነው ኦርጅናል? ንገሪኝ ሀይ ኮፒ ነው ? ሳላረጋግጥ እማ ወይ ፍንክች "
ይላል እሚፈነክት ይፈንክተውና ምን ማረጋገጥ እንደፈለገ ሳስበው ደሞ ሳቄ ይመጣል ።
ትንሽ ቆይቶ ያጨበጭብና ሌላ ይዛለት እንድትመጣ ያዛል። ልክ እንዳመጣችለት ሊነካት እየሞከረ•••
" እንዴ ንገሪኛ እኛ ሀይኮፒም ዩዝድም ባንድ ላይ ጉዳት ነው ንገሪኛ በናትሽ !"
ሲል ልጅቷ ተበሳጭታ መልስ ስለሰጠችው ብድግ አለ ሊመታት ያኔ የኔም ንዴት ገነፈለና ተንደርድሬ በጥፊ ከመሬቱ ጋር አላትሜ አርፎ እንዲጠጣ አስጠነቅቄው ወደ ቦታዬ ተመለስኩ ።
ሰውየው መለፍለፉን አላቆመም ወይ እሱ ወይ እኔ ከዛ ቤት ካልወጣን ዝም እንደማይል ስለገባኝ ተነስቼ ወጣሁና ግማሽ ኪሎ ሜትር አከባቢ በግሬ ተጉዤ " ጨለማው ቤት" በመባል ወደ ሚታወቀው ሆቴል ገባሁ።
ብዙ ግዜ ጥንዶች የሚዝናኑበት ሆቴል ቢሆንም እኔ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ስጠጣ ሁለት ቢራ ጨርሼ ሶስተኛውን እንዳገባደድኩ ከፊት ለፊቴ በቅርብ ርቀት ከተቀመጡት ሶስት ሰዎች መካከል ድንገት ቦግ ብሎ በበራው የሞባይል መብራት የመሀለኛዋን እየኋት•••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
አትሮኖስ pinned «#ምርጫ_አልባ_ምርጫ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ ሁሌም ዛሬ ላይ ቆመህ ሁለት ምርጫ አለክ ትናንት ወይም ነገ ትዝታ ወይም ተስፋ! ።።።።። #ረቂቅ ከወንድምና ከህሊና የቱ ይበልጣል? ወይም ከእናት እና ከህሊና? እሺ ከነገና ከህሊና ?ህሊና እንጀራ ይሆናል? የህሊና ንፅህና ለነፍስ ምግብ ይሆን ይሆናል። በነፍስ እርካታ ስጋ ይጠግባል እንዴ? ነፍስ ጠገበች ብሎስ ሆድ ይጠግባል? ኸረ እንደውም…»
​​#ልጩህበት!!


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በጥላሁን

ሰውየው መለፍለፉን አላቆመም ወይ እሱ ወይ እኔ ከዛ ቤት ካልወጣን ዝም እንደማይል ስለገባኝ ተነስቼ ወጣሁና ግማሽ ኪሎ ሜትር አከባቢ በግሬ ተጉዤ " ጨለማው ቤት" በመባል ወደ ሚታወቀው ሆቴል ገባሁ።
ብዙ ግዜ ጥንዶች የሚዝናኑበት ሆቴል ቢሆንም እኔ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ስጠጣ ሁለት ቢራ ጨርሼ ሶስተኛውን እንዳገባደድኩ ከፊት ለፊቴ በቅርብ ርቀት ከተቀመጡት ሶስት ሰዎች መካከል ድንገት ቦግ ብሎ በበራው የሞባይል መብራት የመሀለኛዋን እየኋት•••
ያቺን እርኩስ አየኋት እስከዛሬ ሳያት ከሚሰማኝ የንዴት ስሜት በተለየ ሁኔታ ጠላቴ መስላ ታየችኝ የግቢ ሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን እኔ ሂወት ላይም የተጫወተች መስሎ ተሰማኝ።

አዎ እሷ ነች ለኔ እና ለኤዱ መተዋወቅ ምክንያት ሆና እዚህ የማልወጣው የፍቅር ገደል ውስጥ ወድቄ የመንፈስ ስብራት እንዲያጋጥመኝ የሞራል የደስታ ባጠቃላይ የኑሮ ጣእምና ለዛዋ ሁሉ እንዲጠፋብኝ ቀንደኛዋ ተዋናይ እሷ ነች ብዬ አሰብኩኝ ።
አዋ! እሷ ነች ያን ቀን ኤዱን አታላ ለዛ ፀያፍ ስራዋ አመቻችታ ይዛት ባትወጣ ኖሮ እኔና ኤዱ ባልተዋወቅን ባላየኋት ባላየችኝ እህቴ ብዬ ስቀርባት ዉንድሟ አርጋኝ ባላረፈችው ነበር
እሷ እስከዛሬም እንደወንድሟ እያየችኝ የኔ ግን ምን እንደገለበጠው ባይገባኝም ወደማላውቀውና ለኔ አዲስ ወደሆነ ከባድ የፍቅር ስሜት ተገልብጦ እንዲህ ቀንና ለሊቱ ባልተገለባበጠብኝ ነበር።
አንዳንዴ ኧረ የምን አንዳንዴ ሁሌም ቢሆን በተለይ ከራሴ ጋር የሚያላትመኝ ፍቅር ከያዘኝ ወዲህ ምነው ባላወኳት እላለሁ ።

ደሞ መልሼ በተለይ ከተዋወቅን ጀምሮ በቃሌ መሰረት እንዳትሳቀቅ በማሰብ ያሰፈልገኛል ብላ ጠየቀችኝም አልጠየቀችኝም በየወሩ አቅሜ የፈቀደውን ያህል በባንክ አካውንቷ ሳስገባላት ወድያው ትደውልና•••
"በመጀመሪያ አንተን ሳይሆን ከናት እና አባቴ ባትወለድም አንተን የመሰለ ወንድም በስጦታ የሰጠኝ ፈጣዬን ሁሌም አመሰግናለሁ በመቀጠል ደሞ አንተንም እመሰግናለሁ እሺ ወንድሜ "
የምትለኝ ሁሌም የማይቀየር ንግግሯ
ሀሳቤን ያስቀይረኝና መተዋወቃችንን ሳይሆን ማፍቀሬን በመኮነን ከራሴ ጋር እጣላለሁ
ሆነም ቀረ ከብዙ ግዜ ቡሀላ ያጋጠመችኝን አሁን ከፊቴ ሶስት ደረጃ ከፍ ብላ ከአንድ ክልስ ከሚመስል ሰውና ከሌላ አዲስ እንቡጥ ሴት ጋር ተቀምጣ የምታስካካውን መሲን በጭራሽ እንደማላልፋት ወሰንኩ!
ሞባይሌን አወጣሁ!
በሁለተኛው ሲም ካርድ ስም ቀይሬ በከፈትኩት ቴሌግራም•••
ካሁን ቡሀላ የግቢ ሴቶችን እያወጣሽ እንደእቃ ስትቸረችሪ ቢያጋጥመኝ ወይ ብሰማ እሄን ጉድሽን በሁሉም ማህበራዊ ሚድያ ለቅቄ መደበቂያ እንደማሳጣሽ እወቂ!
አሁንም አብራሽ ያለችውን ልጅ ቶሎ ወደ ግቢ መልሻት ከሚል አጭር ትእዛዝ ጋር ያ ሰውዬ የላከልኝን የራሷን ቪድዮ ወደ ቴሌግራም አካውንቷ ላኩላትና ወድያው ሞባይሌን ኪሴ ከትቼ እምትሆነውን መጠባበቅ ጀመርኩ።

የቴሌግራም ማሳወቂያውን (notification) አጥፍታዋለች መሰለኝ አዲስ መልክት እንዳላት ስላልነገራት ጭራሽ ሞባይሏን ከፍታ ሳታየው ቆየች።
ስልኳ ላይ መልክት መላክ ግድ ሆነብኝ ቴሌግራም አካውንትሽ ላይ መልክት አለሽ ገብተሽ ተመልከችው ብዬ ላኩ።
ወድያው ሞባይሏ ብልጭ ብሎ ድርግም ሲል አየሁት።
ከፍታ እየተመለከተችው ነው
ቪድዮውን አይታው ነው መሰለኝ በርግጋ ከመቀመጫዋ ተነሳች ፀጉሯን እንደመንጨት እያደረጋት ቪድዮውን የላከልሽ ሰው ውጪ በር ላይ ነው ያሏት ይመስል ያደረገችው ተረከዘ ረጅም ጫማ መሆኑን ረስታ እየተውረገረገች በፍጥነት ደረጃውን ለመውረድ ስትሞክር ባየር ላይ ተበረጋግዳ መሬት ተሰጣች ።

ፈገግ አልኩ አናቴ ላይ ያለውን ኮፍያ ዝቅ እያደረኩ።
ሁሉም ተደነጋግጦ ወደሷ ሲሮጥ ለቅሶ በተናነቀው ድምፅ
"ምንም አልሆንኩም እንዳትጠጉኝ!" ብላ በእልህ ተነሳችና የተጎዳ እግሯን እየጎተተች እና እስከባቷ የተሰነጠቀውን ሮዝ የራት ልብሷን ለማራገፍ እየሞከረች በደመነፍስ የሆቴሉ የውጪ በር ላይ ደረሳ ወደላይና ወደ ታች እየተገላመጠች የጠረጠረችውን ሰው መፈለግ ጀመረች።
ምንም ማየት ባለመቻሏ ተስፋ ቆረጠች ያኔ ስትወድቅ የተመታችበት ቦታ ህመመ ተሰማት ጎኗ አከባቢ ይዛ እያቃሰተች መቆም ስላቃታት ቁጭ ብላ ማልቀስ ጀመረች።
ሰውየውና አብራት የነበረችው ልጅ አጠገቧ እንደደረሱ ልጅቷ በጣም ተጨንቃ ዝቅ ብላ ልታናግራት ልታባብላት በምትሞክርበት ሰአት መሲ ተቀየረችባት•••
"ዞወር በይልኝ ወደዛ ያንቺ ገዳፋ ነው እሄ ሁሉ መጀመሪያም ምንሽም አልጣመኝም ነበር ካሁን ቡሀላ ላይሽ አልፈልግም አሁኑኑ ባጃጅ ያዢና ቀጥ ብለሽ ወደ ግቢ ሂጂ !" በማለት ስታምባርቅባት ልጅቷ ሽምቅቅ ብላ ዘወር አለች ሄደች ወደግቢ ።
"ጎበዝ መሲ ትዛዝ ታከብሪያለሽ ማለት ነው!" ብዬ መልክት ላኩላትና ስልኬን አጥፍቼ ኪሴ ውስጥ ከተትኩ እሄን ግዜ እንደ እብድ አደረጋት መልክቱ እየደረሳት ያለው እዛው ሆቴል ውስጥ እየተዝናና ካለ በቅርብ ርቀት ከሚያያት ሰው መሆኑን እርግጠኛ ሆነች ።

እንደምንም ተነስታ ስልክ መደወል ጀመረች ወደኔ እምትሞክር መስሎኝ ነበር ጎረምሶቿን እየጠራች እንደሆነ የገባኝ ሶስት
ክብደት ገፊ ፣ደረተ ሰፋፊ ፣ ባስተሳሰብ ደሞ ቀፋፊ የሆኑ በጭንቅላታቸው ሳይሆን በተከመረው ጡንቻቸው የሚያስቡ ወጣቶች ከመቅስፈት ደርሰው መሲን በመክበብ ምን እንደፈጠረ ሲጠይቋት እንደተመለከትኩ ነው ።
በመሲ ጥሪ በዛ ፍጥነት ሰው ሊደበድቡ መምጣታቸውን ሳስበው ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው የሚኖሩ አሳሞች መስለው ታዩኝ
መሲ ማነች ? ምንድን ነች? ስራዋ ምንድን ነው ማንን ነው የምታስደበድበን ? ለምን?
አያገባቸውም ብቻ ትክፈላቸው እንጂ እንደ እንስሳ ወደፈለገችበት ትነዳቸዋለች ። ገልቱዎች ።
ዘበኛውን ሰው እንዳይወጣ አስጠነቀቁትና
መሀላቸው አድርገዋት ግቢ ውስጥ መዟዟር ጀመሩ ብዙ ሰው የለም ያሉትም ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የተቀመጡት ብቻዬን ቁጭ ያልኩት እኔ ብቻ ነኝ ።
ደረታቸውን ገልብጠው እየተሽከረከሩ የሚዝናኑትን ሰዎች ምን እንደሚሏቸው ባላውቅም አንዳንዶቹን ጠጋ ብለው እያናገሩ ያንዳንዶቹን ሞባይላቸውን ተቀብለው እየመለሱላቸው እኔ ወዳለሁበት ቦታ መጠጋት ጀመሩ።
ሂሳብ ዘጋሁ።
እነዚህን ዱባ ጭንቅላቶች ፈርቼ ሳይሆን የሰው ሆቴል ውስጥ ብጥብጥ ተፈጥሮ ላለመታሰር ስል ተነስቼ ወደ መውጫው በር ስጠጋ•••
" እንዳታስወጣው! ጥበቃ እንዳታስወጣው !"
የሚለው የመሲ ጩኸት ጆሮዬ ላይ አንቃጨለብኝ ዘወር ስል እሷ ከጀርባቸው ቆማ ሶስቱም ወደኔ ሲመጡ እየኋቸው•••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#እህ_እኔ

ሰማይ ጠቋቆረ ጀንበሯ ጠለቀች
ፀሐይ ለጨለማ ብርሃኗን ለቀቀች
ብቅ አሉ ከዋክብት ከያሉበት ወጡ
ምሽቱን ሊያደምቁ
ተፈጥሮን ሊያበሩ
ፈረቃ ቀየሩ
እህኔ ነው ታዲያ
የኔ ልብ ሚመታ
እህህ የሚያሰኘው
አሻግሮ እሚቃኘው
ማረፊያ የሚያጣ
የሚያብከነክነው ትዝታ እየመጣ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ማን_አንኳኳ
ልብሽን ክፈች ሰው ተቀበይ
ብቸኛ ልሁን አትባይ
ይለኛል አጅሬ ሰው
ይሁን ብዬ ብስማማ እንኳ
ቀድሞውንስ ደጄን እንጂ
የልቤን በር ማን አንኳካ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
​​#ልጩህበት!!


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በጥላሁን

በመሲ ጥሪ በዛ ፍጥነት ሰው ሊደበድቡ መምጣታቸውን ሳስበው ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው የሚኖሩ አሳሞች መስለው ታዩኝ መሲ ማነች ? ምንድን ነች? አያገባቸውም ብቻ ትክፈላቸው እንጂ እንደ እንስሳ ወደፈለገችበት ትነዳቸዋለች ። ገልቱዎች ።
ጥበቃውን ሰው እንዳይወጣ አስጠነቀቁትና
መሀላቸው አድርገዋት ግቢ ውስጥ መዟዟር ጀመሩ ብዙ ሰው የለም ያሉትም ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የተቀመጡት ብቻዬን ቁጭ ያልኩት እኔ ብቻ ነኝ ።
ደረታቸውን ገልብጠው እየተሽከረከሩ የሚዝናኑትን ሰዎች ምን እንደሚሏቸው ባላውቅም አንዳንዶቹን ጠጋ ብለው እያናገሩ ያንዳንዶቹን ሞባይላቸውን ተቀብለው እየመለሱላቸው እኔ ወዳለሁበት ቦታ መጠጋት ጀመሩ።
ሂሳብ ዘጋሁ።

እነዚህን ዱባ ጭንቅላቶች ፈርቼ ሳይሆን የሰው ሆቴል ውስጥ ብጥብጥ ተፈጥሮ ላለመታሰር ስል ተነስቼ ወደ መውጫው በር ስጠጋ•••
" እንዳታስወጣው! ጥበቃ እንዳታስወጣው !"
የሚለው የመሲ ጩኸት ጆሮዬ ላይ አንቃጨለብኝ ዘወር ስል እሷ ከጀርባቸው ቆማ ሶስቱም ወደኔ ሲመጡ እየኋቸው•••
ጥበቃው ወደኔ ተጠግቶ አየት አደረገኝና ጠቀስ አርጎኝ ሳቁ ልገንፍልብህ እንዳለው ሰው በእጁ አፉን ይዞ ወደነሱ ዞረና
" ማንን ዳኒን?" አላቸው በአመልካች ጣቱ ወደኔ እያመላከታቸው •••
" እሱን ነው እንዳይወጣ ያልሽው አንቺ ልጅ? "የቀበጡ ለት•••"
አለ የሀገር ሰው ትሰሚያለሽ እሱን እንኳን እኔ ታንክ አያቆመውም ቅድም ስትፎክሪ የነበረው እሱን ለማስመታት ነው እንዴ ?
ቆይ ዛሬ ነው ድሬ የገባችሁት? እንግዶች ናችሁ እንዴ?
ዳኒኮ በካራቴ ትምህርት ጥቁሩን ቀበቶ እንደ አባቶቹ ዝናር ደጋግሞ ወገቡ ላይ የጠመጠመ የድሬ ዥግና ነው !
ቆይ ቆይ ቆይ በወፈረ መስሎሽ ነው እነኝህን ይዘሽ የመጣሽው ምነው "ለሀምሳ ጋን አንድ አሎሎ ይበቃል " ብለው ቲተርቱ ውልእንኳ ብሎብሽ አያውቅም?
ታይነኩት አይነካም ምላሳችሁንም እግራችሁንም ሰብስባችሁ ሂዱ ዳንዬ በል አንተም ሂድ ምን ይደረግ
አንዳንዱ ተማን ጋር እንደተጣላ የሚገባው ተተወቀጠ ቡሀላ ነው !
ቢያውቁህማ እንኳንስ ለጠብ አስቁመው ሊሉኝ ሰአት ጠይቀው ለማለትም ባልደፈሩ ነበር በል ሂድ መሽቷል!"
ሲለኝ ገለማምጫቸው ሁለት እጄን ኪሴ ውስጥ ከትቼ ብወጣም ከወጣሁ ቡሀላ ካልወጣሁ እያለ ከሚታገልኝ ሳቅ ጋር መታገል ፈተና እንደሆነብኝ ጉንጬን ነፍቼ ትንሽ ራቅ እንዳልኩ ሳቄን ለቀኩት!
ወይ ጥቁር ቀበቶ! ኬት አምጥቶት ነው?
የባጃጇ ነው እንዳልል ባጃጄ ቀበቶ የላትም ።
ከጥበቃው ጋር የምንተዋወቀው በስራ ነው
አልፎ አልፎ ቀን ቀን በብዛት ደሞ ማታ ማታ ሆቴሉ ውስጥ የሚዝናኑ ብሎም እዛው አልጋ ይዘው ድሬ ሰንበትበት ብለው የሚሄዱ ደንበኞቻቸው ታክሲ እንዲጠራላቸው ሲነግሩት ደውሎ ይጠራኛል የተወሰነ ኮምሽን አስብለታለሁ እሄን እማደርገው ከብዙ ሆቴል ጥበቃዎች ጋር ነው አንድ ሁለቴ እዛ ስጠቀም ጋብዤዋለሁ አለቀ ከዚህ ያለፈ ቅርርብ አልነበረንም ።
ባንድ ግዜ የከተማው አክተር አድርጎኝ ቁጭ ሲል እንኳን እነመሲ እኔ እራሴ እራሴን ሳልፈራው አልቀረሁም ወይ የሰው ነገር እራሴን ታዘብኩት እሱ በካበኝ ቁጥር ፍታቸው ሁለት እግሬን ከፈት አድርጌ ፊቴን አጨፍግጌ በመቆም በለለኝ ደረት ስወጣጠር ፈንድቼ ነበርኮ እያልኩ በራሴው ንግግር እኔው እየሳኩ ወደቤት ስገባ ደንግጦ ከንቅልፉ የባነነው ጆሲ ቀና ብሎ አየኝና •••
"ወይኔ ወንድሜን ለየልህ በቃ!?"አለኝ።
ስማ ጆስዬ በዚህ ሰአት ቢለይልኝማ በምን እድሌ እየውልህ ጆስዬ ሁሉንም ነገር ስንፈልግ የምንሆነው ሳንፈልግ የማንሆነው ቢሆን ኤዱን እስክረሳት ብቻ ባብድ ደስ ይለኝ ነበር!
"ከዚህ በላይ! በል ተኛ አሁን ጥዋት እናወራለን" ሲለኝ ተኛሁ።
ረፋድ አራት ሰአት አከባቢ ከንቅልፌ ነቃሁ።
ማታ የዘጋሁትን ስልኬን ስክፍተው መሲ ሶስት መልክቶችን በተከታታይ ስልኬ ላይ ልካልኛለች ።
ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ•••
የመጀመሪያው መልከት እባክህ ወንድሜ እንደዛ እንዳታረግ ትንሽ አላሳዝንህም ? ቆይ እህት የለህም ?" ይላል
ሁለተኛው መልክቷ" ያንን ቪድዬ እንዳልከው እምትለቀው ከሆነ እራሴን እንደማጠፋ እወቅ! ይፀፅትሀል!" ይላል
ሶስተኛው መልክቷ" ጨነቀኝ ኧረ በናትህ መልስ እንኳን ስጠኝ!" ይላል ።
አሳዘነችኝ ልበል ኧረ አልልም !።
መልስ መፃፍ ጀመርኩ•••
አንቺ ክፉ ልታደርጊባቸው ስለቻልሽ ሌሎች ላይ ክፉ ስታደርጊ አንቺ ላይ ክፉ የማረግ አቅም ያለው ሌላ ሰው እንዳለ አትርሺ ቢሆንም ከስተትሽ ተምረሽ ክፋትሽን ካቆምሽ አንቺን በመጉዳቴ ሳይሆን በማስተማሬ ብዙ አተርፋለሁና በጭራሽ አልጎዳሽም!
መልክቱን ልክ እንደላኩት ስራ ሄዷኩ ያለው ጆሲ ተመልሶ መጣ ።
ምነው ጆሲ ስራ የለም እንዴ ለምን መጣህ?
"አንተን ላናግር መነጋገር አለብን ዳኒ!"
ስለምን?
"ስላንተ ነዋ!"
ስለኔ ምን ?
"ቆይ ዳኒ ለምን እኔንስ ታስጨንቀኛለህ እንደወንድሜ እማይህ ጓደኛዬ ነህ ያንተ እንዲህ መሆን የሚያስደስተኝ ይመስልሀል እንዴ?
ምን ሆንኩ?
ምን ያልሆንከው አለ! ስራህን በአግባቡ እየሰራህ
አይደለም ፣ ማታ ማታ አዘውትረህ ትጠጣለህ ከኔ ጋር እንኳን ማውራት አስጠልቶካል የኔስ ችግር የለውም ቤተሰብጋም እኮ ሄደህ አታውቅም እናትህ ሳያዩህ ሲያድሩ ምን ያህል እንደሚጨነቁ ታውቃለህ አንተን ፍለጋ እዚህ ድረስ መምጣት አለባቸው ዳኒ! ቆይ እስከመቼ እውነቱን ልንገርህ እኔ ወስኛለሁ ይቺ ኤደን የምትላትን ልጅ ሄጄ አናግራታለሁ!"
ብሎኝ ከቤት ሲወጣ ተከትዬው ወጥቼ አንገቱን አነኩትና
አታደርገውም ዳኒ አልኩት
"ቆይ ለምን" አለኝ እጄን እያስለቀቀ
ለምን እንደሆነ እነግርሀለሁ።
እሺ ወይ ያቺ የምትወድህን የኔን ሲስተር ጓደኛ ጀምራትና ይቺን ኤደን ተብዬዋን እርሳታ በቃ ዳኒ !"
ካካካካካ ኤዱን ነው በሷ እምረሳት አልኩት ከልቤ ነበር የሳኩበት!
አትሳቅ ዳኒ እንድትስቅብኝ አደለም ስራ አስፈቅጄ የመጣሁት ሁለት አማራጭ አለህ አንዱን ካልመረጥክ ከኔጋም ትጣላለህ!
ምኑን ከምኑ ነው እምመርጠው?
"ወይ ኤደንን እኔ ሄጄ እንዳናግራት መፍቀድ ካልሆነ ከልጅቷ ጋር ፍቅር ጀምረህ ኤደንን መርሳት!"
ጆሲ አምርሯል ግራ ገባኝ ። ኤዱን እንዲያናግራት በጭራሽ እንደማልፈልግ አውቃለሁ ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ ጡጫ ሆነብኝ ቢሆንም•••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «​​#ልጩህበት!! ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በጥላሁን በመሲ ጥሪ በዛ ፍጥነት ሰው ሊደበድቡ መምጣታቸውን ሳስበው ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው የሚኖሩ አሳሞች መስለው ታዩኝ መሲ ማነች ? ምንድን ነች? አያገባቸውም ብቻ ትክፈላቸው እንጂ እንደ እንስሳ ወደፈለገችበት ትነዳቸዋለች ። ገልቱዎች ። ጥበቃውን ሰው እንዳይወጣ አስጠነቀቁትና መሀላቸው አድርገዋት ግቢ ውስጥ መዟዟር ጀመሩ ብዙ ሰው የለም…»
#ርምጃ

ሰው
ካለበት ቦታ ተነስቶ
ሩቅ ለመሄድ ቢመኝ
ሩቅ ለመጓዝ ቢያምረው፤

ያንን የተስፋ ርምጃውን
አንድ ብሎ ነው የሚጀምረው

አንድ አልኩ....
#ራሴን_በላሁት

ገብቼ ሱባኤ
ከብቻ ጉባኤ፣
ላያሌ አመታት
በእኔነት ማሳ ተመላልሼበት፣
ወጥቼ ወርጄበት፣
አዝመራ ባጣበት፥
ራሴን በላሁት
እየመነዘርኩት፣
እያመናዘርኩት።

🔘ደበበ ሰይፉ🔘