አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_ሰባት(የመጨረሻ ክፍል)

#በክፍለማርያም

..ልጄን አደራ እያለች ነበር
ፍፁም እስር ቤት ዉስጥ የቤዛዊትን ልጃቸዉን አቅፋ መምጣት በጉጉት ይጠብቃል ነገር ግን ቤዛዊትን በላሁ የሚል ጅብ አልጮህ አለ።

የቤዛዊት ቀብር ተፈፅሞ ልጇን ቤዛዊት ባወጣችላት ስም አየጠሩ ቤተሰቦቿ በከባድ ሀዘን ዉስጥ ሆነዉም ቢሆን በእሷ ምትክ ልጅ ሰጥታቸዉ አልፋለች እና የወለደቻትን ቆንጅዬ ሴት ልጅ እንደቤዛዊት አይተዉ እየተንከባከቧት ነበር።

እስር ቤት ቀን ወራት ነዉ አመት ዘመን ነዉ ደቂቃ እየተንቀራፈፉ ነዉ የሚጓዙት ፍፁም ጥግ ላይ ተቀምጦ ወረቀት እና እስኪቢርቶዉን ይዞ
የህይወቱን የመጨረሻ ክፍል በመፃፍ ላይ ነዉ
ቤዛዊት ምን ገጥሟት ቀረች ለሚለዉ መልስ እንኳን መልስ ማግኘት አልቻለም በልቡ ቤተሰቦቿ አስገድደዋት ልጁን አስወርዳ ሌላ ባል አግብታ ይስላል
እስር ቤቱ ዉስጥ የመጀመርያዎቹ ሳምንታት ቤዛዊት
"የምስራች ልጅ ልወልድልህ ነዉ"
ብላዉ የጠፋችበት ወቅት ለእሱ ከባድ ነበር ስሙ የተጠራ እየመሰለዉ በለሊት
"አቤት"
ይል ነበር አንዳንዴ ቤዛዊት ያስጠራችዉ እየመሰለዉ
በህልሙ ሁሌ ልጇን አቅፋ እየሳቀች ትቀርበዉና አጠገቡ ስትደርስ የዉሀ ሽታ ሆና እንደጉም ትበተናለች ይጨነቅ ይረበሽ ነበር።
ሰከንዶች እያዘገሙ ደቂቃ ይሆናሉ ደቂቃወች ወደ ሰአት ለማደግ ይንቀራፈፋሉ ሰአታት ሰአት ሆነዉ ለመቆጠር አቅም ያንሳቸዋል ቀን እና ለሊት ለመለዋወጥ በጣም አሰልቺ ጊዜን የሚወስዱ እየመሰለው ቀን በመቁጠር ተጠምዶ ሲዉል ነበር።

አመት አመትን እየተካ ፍፁምም የወጣትነት ፊቱ በጎልማሳ ፊት እየተቀየረ የጭንቀት ሀሳቦቹ ቀስ በቀስ እየቀለሉት
ቀን መቁጠሩን ትቶ የተፈረደበትን ብዙ አመታትን ወደማገባደዱ ሲደርስ ጭንቀቱ ዳግም ማገርሸት ጀመረ።

ፍፁም እድሜዉ ወደ ሀምሳወቹ እየተጠጋ ነዉ መፈቻዉ እየደረሰ ሲመጣ ወደ በፊቱ ሀሳብ ተመለሰ
"ፍቅር አያረጅም ትዝታ አያረጅም
እድሜ ቢጠወልግ ሰውነት ቢጃጅም"
ቤዛዊት እሱን ለመጠየቅ መጥታ ልጅ አርግዤልሀለዉ ያለችዉን ቀን እያስታወሰ አሁን ቤዛዊት እና ልጁ ሊኖሩ የሚችሉበትን ሁኔታ እያሰበ ይቆዝም ገባ።
የቤዛዊት ቤተሰቦች ለፍፁም ልጁን ለማሳየት ማረምያ ቤት ለመምጣት ያስቡና የተፈረደበት ፍርድ ብዙ አመታት መሆኑን ሲያዉቁ ልፋት እና ልጅቷን ማንከራተት እየመሰላቸዉ ጥቂት ጊዜያት በተግባር ባያረጉትም ያስቡት ነበር
አመት እየተለወጠ በአመት ሲተካ እረሱት የቤዛዊት አባትም በህመም ተይዘዉ ብዙም ሳይቆዩ ስለሞቱ እህቷ ባል አግብታ የራሷን ሁለት ልጆች ወልዳ ከእናቷ ጋር የቤዛዊትን ልጅም ጭምር ፍቅር ሰጥተዉ እየተንከባከቧት አሳደጓት እድሜዋም ወደ ሀያወቹ እየተጠጋ ወጣት ሆናለች
ፍፁም የመፈቻ ስሙ ተጠርቶ የነበረውን ሁሉ ታሪኩን ከፃፈበት ወረቀት ዉጪ ሁሉንም ለታሳሪወች አከፋፍሎ ሁሉንም አቅፎ ተሰናብቶ ከማረምያ ቤቱ ወጣ
የብዙ አመት መኖርያ የነበረዉን እስርቤቱን ለመጨረሻ ጊዜ ተመልክቶት ግቢዉን ለቆ ወደ ቤዛዊት እና ልጁ ገሰገሰ።

የእነ ቤዛዊት በር ጋር ደርሶ ቆመ በር ማንኳኳት አልቻለም ቆሞ ልቡ ሲመታ እና ሲጨንቀዉ የግቢያቸዉን በር ተደግፎ ለመረጋጋት እየሞከረ በሩ ተከፍቶ ወጣት ሴት ወጥታ
"ምን ሆነዉ ነዉ አሞት ነዉ ዉሀ ላምጣሎት?"
ፍፁም አንገቱን ቀና አርጓ አያት የቤዛዊትን አይን የያዘች ደግነቷም እንደሷ የሆነ ቆንጆ ልጅ
ልቡ ልጁ እንደሆነች እየነገረዉ የጥንቱ ፈገግታ ፊቱ ላይ ባይኖርም ለመሳቅ እየታገለ
"ስምሽ ማነዉ?"
ብሎ ጠየቃት
ደንግጣ የፍፁምን የተዳከመ የከፋዉ የሚመስል ፊት ለአፍታ አይታ
"ዳግማዊት"
አለችዉ
"የአባትሽን ስምም ንገሪኝ"
ፍፁም መጀመርያ የቤዛዊትን ስም ሲጠይቃትም እንደዚህ ነበር ያላት
ዳግማዊት ማን ነዉ ምን ፈልጎ ነዉ...በሚል የጥርጣሬ አይን እያየችዉ
"ዳግማዊት ፍፁም"
እያለችዉ አያቷ
"ከማን ጋር ነዉ ደሞ የምታወሪዉ"
እያሉ ወደ ደጅ ሲወጡ አብራዉ የቆመችዉን ሰዉዬ ተመለከቱት እርጅናዉ በርቀት አላሳይ እያለ ስለሚያስቸግራቸዉ በጣም ቀርበዉ ተጠግተዉ እያዩት
"ማን ነህ አንተ"
ፊቱ ዉስጥ የተደበቀ የበፊቱ ፍፁም እየታያቸዉ
"ዉይ ዉይ አፈር በበላሁ ልጄ ልጄ ልጄ"
ማልቀስ ጀመሩ ለፍፁም ሳይሆን ከሞተች አመታቶች ያለፋት ቤዛዊት ፍፁምን ሲያዩት ፊታቸዉ ላይ ድቅን ብላባቸዉ እንጂ።
ፍፁም የቤዛዊት በህይወት አለመኖር ዉስጡ እየነገረዉ ነበር ወደ ቤት ዉስጥ እያለቀሰ ገብቶ ተቀመጠ ማዉራት አቅቶት በአይኑ ዳግማዊትን አያት
አይኖቿ ላይ ለማታዉቃት ለወለደቻት እናቷ እንባወች ይታዩበታል
ከተቀመጠበት ተነስቶ ተጠጋት
"ዳግማዊት አባትሽ ነኝ"
አቀፋት ወደ ደረቱ አስጠግቶ የብዙ አመት ናፍቆቱን ሀሳቡን በለቅሶ እየተንሰቀሰቀ ልጁን አቅፎ
ማንባት ቀጠለ ቤዛዊት አለመኖሯን የሚያስረሳ ምትክ ስለሰጠችዉ ልጁን ደግሞ ደጋግሞ አቀፋት እስከ ህይወቱ ማብቅያ ለልጁ ለመኖር ቃል እየገባ።

💫ተፈፀመ💫

ስለ ድርሰቱ ያሎትን አስተያየት በ @atronosebot ላይ እንጠብቃለን መልካም ጊዜ
👍3
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_አራት

ለክፋት ፡ ነው ፡እንጂ አልመጣም ፡ በደኅና
እንግዴህ ፡ ልያዘው ፡ ድንገት ፡ ልድረስና ።
(ቀረበ) ።
አንተ ፡ የሞንታግ ፡ ልጅ ፡ዐመፀኛ ፡ መጥፎ
በሰላም ፡ ጸጥታ፡ የተኛውን ፡ ዐርፎ ፡
ምን ፡ ልታደርግ ፡ ነው ፡ ትኵሱን ፡ ሬሳ ፡
ከመቃብሩ ፡ ላይ ፡ በል ፡ እጅህን ፡ አንሣ ፡
ና፡ ወዲህ ፡ ልያዝህ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡ ውጣ
ኣሳልፌ ፡ ልስጥህ ፡ በሞት ፡ ለሚቀጣ ።

#ሮሜዎ
አንተ መልካም ወጣት፡ዐርፈህ ሂድ በደኅና
እኔ ፡ ሞገደኛ፡ አጥፊ ፡ ሰው ፡ ነኝና ፡
መዘዜ፡ የበዛ ፡ አሳር ፡ የጐተተኝ፡
ሕይወቴን ፡ የጠላሁ፣ ኑሮ ፡ የታከተኝ፡
ሞትና ፡ መቃብር ፡ ጥፋት ፡ የሸተተኝ ፡
የከፋው ፡ ወንድ ፡ ነኝ ፡ ወደኔ ፡ አትጠጋ ፤ .
ጠብ ፡ አትፈልገኝ' ለሕይወትህ ፡ ሥጋ ።
ቲባልት ፡ እንደዚሁ ፡ ደርሶ : ሳይቸግረው ፡
በመጥፎ፡ ንግግር ፡ ሆዴን ፡ አሳረረው ፡
ሳልፈልግ ፡ ገደልኩት እሱ ባነሣው ፡ ጠብ
አሁን ፡ ደግሞ ፡ አንተ ይብቃህ ፡ አትሳደብ
ነፍሴን ፡ የጠላሁ፡ ሰው ፡ በመሆኔ ፡ ፍራኝ
ሳልወድ ፡ በግዴታ ፡ ዐመፅ ፡ አታሠራኝ ፡
የሚወጣው ፡ ምክር ፡ አሁን ፡ ከመላሴ ፡
አልሠራሁበትም ፡ እኔ ፡ እንኳ ፡ ለራሴ ፡
ስለዚህ ፡ ከራሴ ፡ አብልጬ ፡ ስወድህ ፡
እኔን ፡ አመስግነህ ፡ ይሻላል ፡ መሄድህ ፡
አንድ፡ እብድ ፡ ሰው ዛሬ የሰጠኝን ምክር
ሰምቼ ፡ ድኛለሁ ፡ ብለህ ፡ ይልቅ ፡ ፎክር ።

#ፓሪስ
እኔስ ፡ ኣለቅህም ፡ ከያዝኩህ ፡ በኋላ ፤
መስጠት ፡ ትችላለህ ፡ ምክርህን ፡ ለሌላ

#ሮሜዎ
መሞት ፡ ከፈለገህ ፡ እንቢ ፡ ብለህ ፡ በጄ ፡
እንግዲያው ሞክረኝ መልካም፡ነው ወዳጄ
(ይዋጉና'ፓሪስ ፡ ይወድቃል) ።.
ቲባልትና ፣ፓሪስ ፡ እኔን እያስቆጡ ፣
እኔ ፡ ሳልነካቸው ፡ በግድ ፡ እየመጡ፡
በእጄ ፡ እየተወጉ' ክዚህ ፡ ዓለም ፡ ወጡ ።
እንዲህ ፡ መሞታቸው ፡ ተናግረውኝ ፡ ክፉ
ተፈርዶባቸው ፡ ነው ፡ በኔ' እጅ እንዲጠፉ
እንደዚህ ፡ ከሆነ ፡ ፓሪስ ፡ ያንተም ፡ ዕጣ ፡
ጥፋቱ ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ በኔ ፡ እንዳትቈጣ ፡
የዡልዬት ፡ ቁንዥና፡ ደምቆ እንደ ፡ ብርሃን
ጽርሐ አርያም ፡ መስሎ የሰማይ ፡ ውጋጋን
እያንጸባረቀ ፡ ከኮከብ ፡ ሲያበራ ፡
ግርማ፡ተጐናጽፎ፡ በታየበት፡ ስፍራ፡
እንሙት' ወዳጄ ፡ ኣብረን ፡ ከሷ ፡ ጋራ።
(ሮሜዎበዝልዬት፡መቃብር፡ላይየሐዘን ' ንግግር ፡ ያደርጋል)።
ይህችን ፡ ውብ ፡ አበባ ፡ ፍቅር ፡ አሳማሪ ፡
ውሏን ፡ የማትረሳ ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ አክባሪ ፡
ትወድ ፡ የነበረች ፡ ቁም ፡ ነገር ፡ ጨዋታ፡
እዩልኝ ፡ ከዘመድ ፡ ከሰው ፡ ተለይታ ፡
የኔ ፡ ሆደ፡ ባሻ ፡ ብቻዋን ፡ ተኝታ፡
ተመልከቱት ፡ እጅዋ ፡ ተመልከቱት ፡ ፊቷ ፤
ወዟ ፡ ገና፡ አልጠፋም ። ከሠራ፡ አካላቷ፡
ግንባሯን ፡ ከንፈራን ፡ ተመልከቱ ፡ ጣቷን ፤
ይህን ፡ አበቃቀል ፡ ተክለ ፡ ሰውነቷን ፡
ገላዋ ፡ ያበራል ፡ በደም ፡ ተሸልሞ ፤
ዡልዬት ፡ሞት የነካት፡አትመስልም ፈጽሞ
እባካችሁ ፡ ሰዎች ፡ ሐዘን፡ ተካፈሉኝ፤
ዡልዬት ፡ አልሞተችም ፡ ተኝታለች ፡ በሉኝ
ታውቂ ፡ የነበርሽው ፡ ፍቅራዊ ፡ አቀባበል ፡
ሽቍጥቀጥ ፡እመቤት ባለመልካም ዐመል
ተወዳጁ ፡ ድምፅሽ ፡ ውብ ፡እንደ ፡ ሙዚቃ
በበገናው ፡ ቃሉ ፡ መንፈስ ፡ የሚያነቃ ፡
ዛሬ ፡ ወዴት ፡ ጠፋ? የት ፡ ቦታ ፡ ደረሰ ? .
ደግሞስ ዐይንሽ ፡ ቆቡን ስለ ምን ለበሰ ?
ዡልዩት ፡ ባትሞት ኖሮ፡ በውነት ፡ ባትቀበር
ሮሜዎ ፡ እዚህ ፡ ቆሞ ዝም አትልም ነበር
ባለም ፡ ላይ ፡ ብንሻ ፡ በውነቱ ፡ የት ፡ ኣለ ፡
ጨካኝ አረመኔ ፡ ሞትን ፡ የመሰለ ፡
ጥቂት ፡ አላዘነም ፡ አልሣሣም ፡ ጨርሶ ፡
ይችን ፡ ጽጌ ፡ ረዳ ፡ ሲጥላት ፡ በጥሶ :
ይችን ፡ አሳዛኝ ፡ ልጅ ፡ ትተዋት ፡ ሲሄዱ፡
በሩን ፡ የዘጋ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ቻለ ፡ ሆዱ
እይዋት ይችን ቄንጥ እይዋት ይችን ሎጋ
በባዶ፡ አዳራሽ ፡ በመቃብር ፡ ኣልጋ ፡
ወፍ ፡ በማይዞርበት ፡ ጭር ፡ ባለ ፡ ስፍራ ፡
ብቻዋን ፡ ቀርታለች ፡ አዲሷ ፡ ሙሽራ ።
በመከራ ፡ ቅመም ፡ ባሳር ፡ ተለውሶ :
ዡልዬት፡ ሕይወታችን ፡ መሮን ፡ እንደ ፡ኮሶ
ወጣን ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ያላንድ ፡ ደስታ .
እንግዲህ ፡ እንኑር ፡ እዚህ ፡ በጸጥታ ።
ባለም ፡ ቦታ፡ ጠፍቶ ፡ ለመኖር'ተዋደን ፡
እዚህ ፡ ተገናኘን ፡ ካለም ፡ ላይ ፡ ተሰደን
አይቈጨን እንደዚህ ካለም መውጣታችን
በጣም ፡ ደስ ፡ይበለን ፡ በዛሬው ፡ ዕጣችን
ላለሙ ፡ ደስታ ፡ ለረዥሙም ፡ ዕድሜ ፡
ያው ሞት አይደለም ወይ የሁሉ ፍጻሜ ?
ገላዬን ፡ ከገላሽ ፡ ዐፅምሽን ፡ ካዕፅሜ ፡
ሥጋዬን ፡ ከሥጋሽ ፡ ደምሽን ፡ ከደሜ ፡
ቀላቅሎ ፡ የሚያኖር፡ ከተገኘ ፡ ቦታ ፡
ዡልዬት፡ ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ ምን አለ ፡ ደስታ
ይቅር ፡ ደኅና ፡ ይሁን ፡ ዓለም ፡ ከነቂሙ ፤
እዚህ ፡ እኔና፡ አንቺ ፡ እስከ ፡ ዘላለሙ ፡
መቃብር፡ ሆኖልን ፡ የጸጥታ ፡ ገዳም ፡
ከዛሬ ፡ ጀምሮ ፡ እንኑር ፡ በሰላም ።
ከሚወዱት፡ጋራ፡ እንዲህ ፡ ጐን ፡ ለጐን ፡
ምንኛ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዐፈር ፡ ትቢያ ፡ መሆን ።
(ሮሜዎ ፡ መርዝ ፡ ጠጥቶ ፡ ሞተ ።)

#አባ_ሎራ መብራትና፡ጕጠት፡ ይዞ ፡
ወደ፡መቃብሩ፡ ቦታ፡ መጣ ።

#አባ_ሎራ
ስፍራው ፡ አያስኬድም ፡ ሆነና ፡ መቃብር
እያደናቀፈ ፡ ያስቸግራል ፡ ለእግር ፡
አዬ ፡ መከራዬ ፡ በዚሁ ፡ ላይ ፡ ደግሞ ፡
ምንም ፡አይታየኝ ፡ዐይኔ ፡ በጣም ፡ ደክሞ
ማነህ አንተ እዚህ የቆምከው እንደ አጥር ?

#ቤልሻጥር
የሚያውቁኝ ፡ወዳጅዎ ፡እኔ፡ ነኝ ቤልሻጥር ።

#አባ_ሎራ
እግዚአብሔር ይባርክህ በል ልጄ ንገረኝ ፤
በሩቅ ፡ አላይ ፡ ብሎ ፡ ዐይኔ ፡ አስቸገረኝ፡
እዚያ ፡ በካፑሌ ፡ የመቃብር ፡ ስፍራ ፡
መብራት አይደለም፡ ወይ የማየው ፡ ሲበራ?

#ቤልሻጥር
አዎን ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ሄዷል ፡ እዚያ ፡ ቦታ ፡
ወዳጅዎ ፡ ሮሜዎ ፡ የኔ ፡ መልካም ፡ ጌታ

#አባ_ሎራ
ማን ፡ አልከኝ ?

#ቤልሻጥር
ሮሜዎ ።

#አባ_ሎራ
አዬ ፡ የእግዜር ፡ ቀጣ
ምን ፡ ያኽል ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ እሱ ፡ እዚህ ፡ ከመጣ ?

#ቤልሻጥር
ልክ ፡ እኩል ፡ ሰዓት ፡ ነው ።

#አባ_ሎራ
ና፡ እንሂድ፡ ወደ ፡ እሱ

#ቤልሻጥር
አልችልም ፡ አባቴ ፡ አስጠንቅቆ ፡ ራሱ ፡
ወደ ፡ መቃብሩ፡ እሱ ፡ ወዳለበት ፡
ከቶ ፡ እንዳልጠጋ ፡ ሥራውን ፡ ለማየት ፡
ከልክሎኛልና ፡ በሞት ፡ አስፈራርቶ ፤
ትእዛዙን ፡ ለመጣስ ፡ እኔ ፡አልችልም ፡ ከቶ

#አባ_ሎራ
በል ፡ ተወው፡ ልጄ ፡ ሆይ፡ ሠግቷልና፡ ልቤ
እስቲ ፡ ልመልከተው ፡ ብቻዬን፡ቀርቤ።(አባ፡ሎራሄደ)

#ቤልሻጥር ፡ (ብቻውን ) ።
ዛፍ ፡ ተደገፍኩና ፡ እንቅልፍ ወስዶኝ ፡ ኖሮ
በሕልማ፡ ሮሜዎ ፡ አድርጎ ፡ አምባጓሮ ፡
ውጊያ፡ገጠሙና ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ሲጥል ፡
አየሁ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሲገድል

#አባ_ሎራ ፡(ብቻውን) ።
ይህ ፡ ደም ፡ ከየት ፡ መጣ ? ይህ ሻምላ ፡ ምንድነው?
እዚህ ፡ የወደቀ ፡ ባለቤት ፡ የሌለው ።
(ዡሊዬት ነቃች ፤ አባ ፡ ሎራ፡ ጥግ ፡ ይዞ ፡ ቆመ) ።

#ዡልዬት
ሮሜዎ ፍቅሬ ሆይ ማን አምጥቶ ጣለህ ?
ይኸ ፡ ደም ምንድነው ? ፓሪስ ፡ ማ፡ገደለህ ?
ጨርሰው ፡ አይሰሙም ፡ ሞተዋል ፡ እነሱ
ትንፋሽም ፡ የላቸው ፡ አይንቀሳቀሱ ፡
የእንቅልፍ ፡ የመኝታ ፡ የዕረፍት ፡ የጸጥታ :
መሆኑ ፡ ቀረና ፡ ሰላማዊ ፡ ቦታ ፤
ከእንቅልፌ ፡ ስነቃ ፡ አወይ ፡ መቃብሬ ፡
የጦር ፡
👍1
ሜዳ ፡ ሆኖ ፡ ጠብቆኛል ፡ ዛሬ ።
ሮሜዮ፡ ምን ፡ ነካው ? ፓሪስን ማ መታው ?
ይህን ፡ እንቆቅልሽ ፡ማነው ፡ የሚፈታው ?

#ኣባ_ሎራ
ይኸውልሽ ፡ ልጄ ፡ እግዜር ፡ አልፈቀደም
እንዳሰብኩት ፡ ሆኖ ፡ ነገሩ ፡ አልሄደም ።
ኣሁንም ፡ ቶሎ ፡ በይ ፡ ውጪ ከዚህ ፡ ቦታ
ሰዎች ፡ መጡ ፡ ከደጅ ይሰማል ፡ ጫጫታ
እንድትገቢ ፡ አድርጌ አንቺን ካንድ ገዳም
እዚያ ፡ ትኖሪያለሽ ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ በሰላም ፡
እባክሽ ቶሎ በይ፡ ሰዎች ወዲህ መጡ፡

#ዡልዬት
ከዚህ ፡ እኔ ፡ አልሄድም ፡ እርስዎ ፡ ፈጥነው፡ይውጡ።
(ዡልዬት ፡ ብቻዋን ፡ )፣ ( አባ ' ሎራ' ሄደ)
ደግሞ ፡ ይህ ፡ ኩባያ ፡ እዚህ ፡ ምን ፡ አመጣው ?
ምን ፡ ይሆን ሮሜዎ አግኝቶ የጠጣው ?

አሁን ፡ ገና ፡ ገባኝ ፡ ዐይኔ ፡ ተከፈተ ፤
መርዝ ፡ ጠጥቶ ፡ ነው ፡ ሮሜዎ ፡ የሞተ ።
ጥንቱን ፡ ተፈጥሬ ፡ ለዬዬ ፡ ለለቅሶ ፡
እንዴት ፡ ያለው ፡ ሐዘን ፡ ቈየኝ ፡ ተደግሶ :
እኔ ፡ እሱን ፡ ስጠብቅ ፡ እዚህ ፡ ተቀብሬ ፡
በድን ፡ ሆኜ ፡ ሬሳ ፡ቆየሁ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡
ወይ ፡ አለ ፡ መታደል ፡ መፈጠር፡ ላበሳ ፤
ይኸ ፡ ሁሉ ፡ ድካም ፡ይህ ሁሉ ፡ ግሥገሣ
ለማየት ፡ ኖሯል ፡ ወይ ወድቆ ያንተ ሬሳ፤
ለካ ፡ መልካም ፡ ኖሯል ፡ ብቀር ፡ ሳልነሣ ።
ወደ፡እሱ፡ብመጣ ፡ እኔ አድርጌው ዘመድ፡
እሱስ ቀድሞኝ ሄዷልባላሰብኩት መንገድ
እንዳልቀየመው ፡ የኔ ፡ ከዳተኛ ፡
መጥቶ ፡ ካጠገቤ ፡ እዩት፡እንደ፡ተኛ ።
አወይ ፡ ሮሜዎ ፡ የኔ ፡ ሆደ ፡ ባሻ ፡
አንተ፡ እኔን ፡ ስትፈልግ እኔም አንተን ፡ ስሻ
ብቻህን ፡ ሄደሃል ፡ ሰው ፡ ቀርቶኛል ፡ ሳትል
የጭንቅ ፡ ወዳጅህን ፡ እኔን ፡ ሳታስከትል ፡
አልቀርም ፡ ጠብቀኝ ፡ ባለህበት ፡ ቦታ ፤
ኩባያህ ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ የለውም ፡ ጠብታ ፡
አንተ ፡ ቢስ ፡ ሥሥታም ፡ ንፉግ ፡ መኰንኔ
ጨልጠህ ፡ ጠጣኸው ፡ ሳታስተርፍ ፡ ለኔ
ቆየኝ ፡ ደረስኩብህ ፡ በርሬ፡ እንደ ፡ አሞራ፤
ይኸው ፡መምጣቴ ነው ፡ እኔም ካንተ፡ ጋራ
አልሠራህበትም ፡ አንተ ፡ ባለቤቱ ፡
እስቲ ፡ ልታቀፈው ፡ ይግባ ፡ በስለቱ ፡
አንጀቴ ፡ ለጩቤህ ፡ ይሁነው ፡ አፎቱ ።
(በሮሜዎ ፡ ልቤ ፡ ሆዷን ' ወግታ ፡ ሞተች)

#የመጀመሪያ_ዘበኛ
በልምራን ወዴት ነው መንገዱና ስፍራው ?

#የፓሪስ_አሽከር
ይኸው እዚህ ነበር መብራት ፡ የሚበራው

#የመጀመሪያ_ዘበኛ
ምድሩ ፡ ደም ፡ ብቻ፡ነው፡ምድነው፡ ነገሩ?
እስቲ ፡ ቶሎ ፡ ግቡ ፡ ወደ ፡ መቃብሩ፡
ትልቁ ፡ መኰንን ፡ ፓሪስ ፡ ይኸው ፡ ሞቶ ፡
ቀርቷል ፡ በመሬት ፡ ላይ ፡እዚህ ፡ ተዘርግቶ
ከሁለት ፡ ቀን ፡ በፊት ፡ የቀበሯት፡ ሞታ ፡
ዝልዬትም ፡ ወድቃለች በጨቤ ፡ ተወግታ፡
እዩ ፡ ተመልከቱ ፡ በደም ፡ ተለውሳ ፤
አልብሶት ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ሜዳውን 'ሬሳ ።
ደግሞስ ፡ ሮሜዎ ፡እዚህ ፡ምን አመጣው፤
እሱም ደግሞ ሞቷል ትንፋሽም አይወጣው ።
ቶሎ ፡ ንገሯቸው ፡ መስፍኑ፡ይጠሩ፤
ደግሞም ፡ ግማሻችሁ ፡ ስፍራውን ፡ መርምሩ ፡
ይጠሩ፡ እነ ፡ ሞንታግ ፡ ይምጡ ፡ እነ ፡ ካፑሌ ፤
ፍተሻ ፡ይደረግ ፡ በዚሁ ፡ ቀበሌ ፡
ምስክር ፡ ተገኝቶ ፡ታሪኩ ፡ እስቲሰማ ፡
የተሰወረ፡ ነው፡ ምስጢሩ ፡ ጨለማ ።

💫ይቀጥላል💫
#ቁዘማ

በራፌን ቆልፌ፣ ትላንትና ሌሊት፤
አዳፋ ተስፋዬን፣ በእንባዬ አጠብኩት፡፡
ጠምዝዤ ላሰጣው፤
አልነጋ አለኝ - ጓጓሁ፡፡

አልወጣ አለች ጸህይ፣
እረፋዱ አለፈ፤
ከደመና ይጋፋል፤
ጨረሯ ስነፈ፡፡
ብርዱ ያንዘፈዝፋል፤
ቆፈነ ይቆርጣል፤
እርጥብ ተስፋ ለብሶ፣ ቀኑ እንዴት ይገፋል?
ይበርዳል፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

ጥር 19፣2012፡፡
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_አምስት(የመጨረሻ
ክፍል)

#ሁለተኛ_ዘበኛ
ይኸው ፡ አገኘነው ፡ የሮሜዎን ፡ አሽከር ።

#የመጀመሪያ_ዘበኛ
መስፍኑ ፡ እስቲመጡ፡ እንዳይመረመር ።
(ሦስተኛ ፡ ዘበኛ ፡ ከአባ ' ሎራ፡ጋራ፡ መጣ)

#ሦስተኛ_ዘበኛ
እያንቀጠቀጠው ፡ ጥግ ፡ ይዞ ፡ ሲያለቅስ
ይኸውና ፡ ደግሞ ፡ አገኘሁ ፡ አንድ ፡ ቄስ ፡
ለምን ፡ እንደ ፡ ያዘው ፡ አልታወቀም፡ ከቶ ፡
ጕጠቱን ፡ ቀማነው ፡ በእጁ ፡ ላይ ፡ተገኝቶ

#የመጀመሪያ_ዘበኛ
መስፍኑ ፡ እስቲመጡ ፡ እሱን ፡ አትልቀቁ ፤
የሚጠረጠር ፡ ነው ፡ ይዛችሁ ፡ ጠብቁ ።
(መስፍኑ ፡ ታጅቦ ፡ መጣ) ።

#መስፍን
እኔን ፡ የሚያስጠራ ፡ ሳይነጋ ፡ ሌሊቱ ፤
ምንድነው ፡ንገሩኝ ፡ እስቲ ፡ ምክንያቱ ? ..
(ካፑሌ ' ፤ ሚስቱና ሌሎች ሰዎች መጡ)

#ካፑሌ
ምስጢሩ ፡ ምንድነው ፡ የሰዉ ጫጫታ ?

#የካፑሌ_ሚስት
እረ ፡ እንዲህ ፡ አይደለም ፡ የሕዝቡ ጋጋታ ፡
ግማሹ ፡ ሮሜዎ ፡ ግማሹ ፡ ዡልዬት ፡
ግማሾቹም ፡ ፓሪስ ፡ እያሉ ፡ በጩኸት ፡
ወደ ፡ እኛ ፡ መቃብር ፡ ገቡ ፡ እየተጋፉ ።

#መስፍን
ነገሩን ፡ ንገሩኝ፡ ደግም ፡ ሆነ፡ ክፉ ።

#የመጀመሪያ_ዘበኛ
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ያስተውሉ'ፓሪስን ፡ተገድሎ
እዩት ፡ ሮሜዎ ፡ መሬት ፡ ላይ ፡ ተንጋሎ ፡
ቀድሞ ፡ የሞተችው ፡ ዡልዬት ፡ ተመልሳ፣
እይዋት ፡ እሷ ፡ ደግሞ ፡ በደም ተለውሳ ።

#መስፍን
ይህ ፡ ዐመፅ ፡ እንደ፡ምን ፡ ሆኖ ፡ እንደ ፡ ተሠራ ፍጠኑ ፡ በቶሎ ፡ይደረግ ፡ ምርመራ

#የመጀመሪያ_ዘበኛ
የሮሜዎ ፡ ሎሌ ፥ ካንድ ፡ ካህን ፡ ጋራ ፡
እነሆ ፡ ተገኝቷል ፡ አሁን ፡ በዚህ ፡ ስፍራ ።

#ካፑሌ
ሚስቴ ፡ ተመልከቺ ፡ ልጃችን ፡ ተኝታ ፥
እዪው ፡ ደሟ ፡ ሲፈስ ሆዷ ላይ ፡ ተወግታ
አስተውዪው ይህ ጩቤ ከመጣበት ፡ ቦታ
ከሞንታግ ልጅ ላይ ነው ተመልከች አፎቱ
ባዶውን ፡ ይታያል ፡ ይግባሽ ፡ ምክንያቱ ።

#የካፑሌ_ሚስት
እባክህን ፡ ተወኝ ፡ እኔ ፡ አልችልም ፡ ማየት
ወይ፡ልጄ ፡ ወይ ልጄ ፡ ወይ፡ ልጄ ፡ ዝልዬት
ሐዘን ፡ ጨፈለቀኝ ፡ ውሃ ፡ ሆንኩኝ ፡ እኔ ፤
ይህንን ፡ ትልቅ ፡ ጕድ ፡ ይህንን ፡ ጭካኔ፡
ኣይችልም ፡ አይችልም። ሊመለከት ዐይኔ
(ሞንታግና ፡ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ መጡ) "

#መስፍን
ሞንታግ ፡ ወዲህ ፡ ቅረብ ፡ ተመልከተው ፡ አንተ ፡ልጅህን ፡ አስተውለው ፥ እየው ፡ እንደ ፡ ሞተ ።

#ሞንታግ
የልጅዋ ፡ መሰደድ ፡ ሆኖባት ፡ በሽታ ፡
ሚስቴ ፡ ሌሊት ፡ ሞተች በሐዘን ተጐድታ
ያሁን ፡ ሐዘኔ ፡ ግን በጣም ፡ ትልቅ መዓት
የባሰ ፡ ጐዳት፡ ነው ፡ የመጣ ፡ ለቅጣት ።

#መስፍን
እንባህን ፡ አግደው ፡ አትቸኵል ፡ ለማልቀስ
በፊት ፡ ምርመራውን ፡ ይገባል ፡ መጨረስ
ያመፁን ፡ ምክንያት፡ ምንጩን ፡ እንወቀው
ምርመራው ይጀመር አብረን ፡ እንዝለቀው
የተያዙት ፡ ሰዎች ፡ በፍጥነት ፡ ይቅረቡ ።

#አባ_ሎራ
እዚህ ፡ ያላችሁት ፡ አሁን ፡ ስታስቡ ፡
እኔ ፡ መገኘቴ ፡ በዚህ ፡ ዐመፅ ፡ ቦታ ፡
ያስጠረጥረኛል ፡ ገፍቶ ፡ በግዴታ ፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ ነገሩን ፡ ልናገረውና ፡
ተረዱት ፡ ዕወቁት ፡ የኔን ፡ ንጽሕና ።

#መስፍን
ታሪኩን ፡ እንስማ ፡ በሉ ፡ ይናገሩ ።

#አባ_ሎራ
ሐተታ ፡ አላበዛም ፡ ልናገር ፡ ባጭሩ ፤
ረዥም ፡ አይደለም ፡ቀላል፡ ነው ምስጢሩ
መልካሙ ፡ ሮሜዎ ፡ ይህ አሁን ፡ የሞተው ለዡልዬት ፡ባሏ ነው በተክሊል ተጋብተው
ቃል ኪዳን ሞልተዋል ቈርበው እንደ ሕጉ
በሃይማኖት ሥራት ቃል፡ ኪዳን ሲያደርጉ
የተክሊሉን ፡ ሥራት ፡ ባርኮ ፡ የቀደሰው ፡
እኔው ፡ ራሴ ፡ ነኝ፤ አይደለም ፡ ሌላ ፡ ሰው
በዚያው ቀን ቲባልትን ቢገድለው ፡ ተፈርዶ
ከዚህ ፡ አገር ፡ ወጣ ፡ ሮሜዎ ፡ ተሰዶ፡
ዡልዬት ፡ ዘመዶቿ ፡ ይህንን ፡ ሳያውቁ ፡
ለፓሪስ ፡ ሊድሯት ፡ እሷን ፡ ቢያስጨንቁ ፡
በሐዘን ፡ አልቅሳ ፡ ነገረችኝ ፡ መጥታ ፤
ዘዴ ፡ ካልተገኘ ፡ በገዛ ፡ እጅዋ ፡ ሞታ ፡
ልትድን ፡ አሰበች ፡ ካገኛት ፡ ፈተና ፤
እኔም ፡ በዚህ ፡ ነገር ፡ በጣም ፡ አዘንኩና ፡
መድኀኒት ፡ ሰጠኋት ሕይወት ፡ አጠውልጎ
እንቅልፍ ፡ የሚያስተኛ እንደ ሞት ፡ አድርጎ
ከዚያም ፡ ለሮሜዎ ፡ ወረቀት ፡ ጽፌለት ፡
እንዲመጣ ፡አዘዝኩት ገሥግሦ በፍጥነት
ከእንቅልፋ፡ ስትነቃ የመርዙ ኃይል ፡ አልቆ
እንዲወስዳት ፡ ነበረ ውጭ ፡ አገር ፡ ደብቆ
የኔንም ፡ ወረቀት ፡ የወሰደልኝ ፡ ሰው ፡
የኛ ፡ ካህን ፡ ነበር ፤ እሱም ፡ ሳያደርሰው ፡
እክል፡ ስላገኘው ፡ በሄደበት ፡ ቦታ ፡
መልሶ ፡ አመጣልኝ ፡ ትናንትና ፡ ማታ ።
የዡልየት ፡ መነሻ ፡ ሌሊት ፡ ስለ ፡ ነበር ፡
እኔም ፡ በጨለማ ፡ መጣሁ ፡ ስደናበር ፡
አሳቤ ፡ ነበረ ፡ ሮሜዎ ፡እስቲመጣ ፡
ደብቄ ፡ ላቆያት ፡ ከቤት ፡ ሳላስወጣ ፡
ዳሩ፡ግን ፡ ገሥግሼ ፡ እኔ ፡ ከዚህ ፡ ስደርስ
ወድቀው ፡ አየኋቸው ፡ ሮሜዎና፡ ፓሪስ ።
እሷም ፡ ነቃችና ፡ ወዲያው ፡ ስትነሣ ፡
እግዜር ፡ ያመጣውን ፡ ብትቀበል ፡ ታግሣ
የሚሻል ፡ መሆኑን ፡ ላስረዳት ፡ ሞክሬ ፡
ከደጅ ፡ ድምፅ ሰማሁ ሳጥናናት በምክሬ
ለመንኳት ፡ እንድትሄድ ፡ እኔን ፡ ተከትላ ፥
ምክሬን ፡ አልሰማችም ቀረች እንቢ ፡ ብላ
እኔም ፡ የመጣውን ፡ ለማየት ፡ በኋላ ፤
ወጥቼ ፡ መጣሁኝ ፡ ይኸው ፡ እዚህ ፡ ቦታ
ያስረዳ፡ ነበረ ፡ የዡልዬት ፡ ሁኔታ ፡
ሐዘኗ ፡ መሆኑን ፡ በጣም ፡ የበረታ ።
ከዚያ በኋላ ፡ ግን ፡ የሆነውን ፡ ነገር ፡
አላየሁምና ፡ አልችልም ፡ መናገር ፡
ዡልዬት ፡ ሮሜዎን በተክሊል ፡ ማግባቷን
ታውቀዋለችና ፡ ጠይቁ ፡ ሞግዚቷን ፡
እንግዴህ ፡ ልቀጣ ፡ ቃሌ ፡ ቢገኝበት ፡
በውስጡ ፡ የገባ ፡ ሐሰትና፡ ውሸት

#መስፍን
ጻድቅ ፡ሰው ኣድርገን ፡እርስዎን ከማክበር
አቋርጠን ፡ አናውቅም የሮሜዎን ፡ አሽከር
በፍጥነት ፡ አቅርቡት ፡ ያየውን ፡ ይናገር ።

#ቤልሻጥር
የዡልዬትን ፡ መሞት ፡ ጌታዬ ፡ ብነግረው ፡
መርዶውን ፡ ሲሰማ ፡ ሐዘን ፡ አሰከረው ፡
ወዲያው ፡ ተነሣና ፡ እየገሠገሠ ፡
ሌሊት ፡ እዚህ ፡ ቦታ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ደረሰ ።
ይህንን ፡ ደብዳቤ ፡ ላባቴ ፡ ስጥ ፡ ብሎ ፡
እኔን ፡ እንዳልገባ ፡ በብርቱ ፡ ከልክሎ ፡
ትእዛዙን ፡ ባልፈጽም ፡ በሞት ፡ አስፈራርቶ
አየሁት ፡ ሲገባ ፡ እኔን ፡ እዚህ ፡ ትቶ ።

#መስፍን
ደብዳቤውን ፡ ስጠኝ እስቲ ፡ ልመልከተው
የፓሪስም ፡ አሽከር ፡ ይጠራ ወዴት ፡ ነው ?
(የፓሪስ • አሽከር ፡ ቀረበ) ።
ሌሊት ፡ በጨለማ ፡ ደግሞ ፡ ያንተ ፡ ጌታ ፡
እዚህ ፡ ለምን ፡ መጣ ፡ እመቃብር ፡ ቦታ ?

#የፓሪስ_አሽከር
አበባ ፡ ሊያስቀምጥ ፡ እመቃብሯ ፡ ላይ ፡
መጣና ፡ እኔንም ፡ እዚሁ ፡ ሁኜ ፡ እንዳይ ፡
አዞኝ ፡ እንድጠብቅ ፡ እዚህ ፡ እንድቀመጥ
ሰው ፡የመጣ እንደሆን ምልክት እንድሰጥ
ስጠብቅ አንድ፡ ሰው፡ መብራት ይዞ መጣ
አፍጨሁ ፡ ጌታዬም ፡ ከመቃብር ፡ ወጣ ።
ሁለቱ ፡ ሲዋጉ ፡ ይኸው ፡ እዚህ ፡ ስፍራ ፡
ቶሎ ፡ ሮጬ ፡ ወጣሁ ፡ ዘበኛ ፡ ልጠራ ።

#መስፍን
አምነን ፡ ለመቀበል ፡ እኛ ፡ የቄሱን ፡ ቃል ፡
ተመልክቼዋለሁ ፥ ደብዳቤው ፡ ይበቃል ።
የፍቅራቸው ፡ ነገር ፡ የዡልዬትም ፡ መሞት
ይኸው ፡ ይነበባል ፡ በደብዳቤው ፡ ጽፎት
ሁሉንም ፡ ገልጦታል ፤ ከዡልዬትም ፡ ጋራ
ለመሞት መምጣቱን ይኸው እዚህ ስፍራ
መድኀኒት የሚሸጥ ድኻ ሰው ፡ አግኝቶ
መርዝ
👎1
፡ ይዞ ፡ እንደ መጣ በገንዘቡ ገዝቶ
ይኸው ፡ ተናግሮታል ፡ የሠራውን ፡ ሥራ ፤
ማስረጃው ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ትክክል ፡ የጠራ
ካፑሌና ፡ ሞንታግ ፡ የት ናችሁ? አስተውሉ
የበቀልን ፡ ፍሬ ፡ ዛሬ ፡ ተቀበሉ ፡
እንሆ ፡ ይኸ ፡ ነው ፡ የቂማችሁ ፡ ዋጋ ፤
እዩት ፡ ይህን ፡ መዓት ፡ ይህንን ፡ አደጋ ፡
እግዚአብሔር ፡ አስቦ ፡ እናንተን ፡ ሊቀጣ ፡
እንዴት ፡ ያለ መቅሠፍት በኛ ላይ አመጣ
በኛ ፡ ላይ ፡ እላለሁ ፤ ምክንያቱም ፡ ዛሬ ፡
ይኸው ፡ ሁለተኛ ፡ ዘመዴን ፡ ቀብሬ ፡
እኔም ፡ ከናንተ ፡ ጋር ፡ ተቀጣሁ ፡ አብሬ ።
ዘላለም ፡ ቂመኞች ፡ የማትመከሩ ፡
ደም ፡ ለማፍሰስ ፡ ብቻ ፡ የምትጣጣሩ ፡
ፍቅርን ፡ የጠላችሁ ፡ ሆናችሁ ፡ ስትኖሩ ፡
ትልቅ ፡ ትምህርት ፡ ነው ፡ ብትመለከቱ ፡ .
ዛሬ ፡ ልጆቻችሁ ፡ ለፍቅር ፡ ሲሞቱ ።
ሌላ ፡ ልጅ ፡ የላችሁ ፡ አለነሱ ፡ በቀር ፤
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ቅጣት ፡ መቼም ፡ አይፈጠር ።

#ካፑሌ
ይህ ፡ የወደቀብኝ ፡ የዛሬው ፡ ቅጣቴ ፡
ከሥጋዬ ፡ ዘልቆ ፡ ተሰማኝ ፡ ላጥንቴ ፡
ለኔ ፡ ሆኖ ፡ ሳለ ፡ የሚገባኝ ፡ ሞቱ ፡
ንጹኋ ፡ የኔ ፡ ልጅ ፡እንደዚህ ፡ በከንቱ ፡
ደሟን ፡ በኔ ፡ ክፋት መሬት ፡ ላይ ፡ አፍስሳ
መሥዋዕት ፡ ሆና ፡ ሞተች ፡ ለክፋቴ ፡ ካሳ
ሞንታግ ወንድሜ ሆይ በል እጅህን ስጠኝ፤
ይብቃን ' እንታረቅ ፡ በፍቅር ፡ ጨብጠኝ ።
(እጅ ፡ ለጅ ፡ ይጨባበጣሉ) ።
ደኅና ፡ አድርገን ከፈልን የኀጢአትን ዋጋ
እየው ሲያንገበግብ የእግዚአብሔር አለንጋ ፡
ክፉዎች ፡ ብንሆንበት እሱም ፡ ክፉ ፡ ሆኖ
ድብን፡ አደረገን ፡ ሳይራራ ፡ ጨክኖ ፡
በውነት ፡ ሆንኩ ዛሬ ፡ ዕርቅን የምሻ ፡ ሰው
በልጄ ፡ ንጹሕ ፡ ደም ፡ መሬት ፡ በፈሰሰው

#ሞንታግ
እኔም ፡ ለዡልዬት ፡ ይኸው ፡ በዚህ ፡ ስፍራ
ሐውልት ፡ አቆማለሁ ፡ በወርቅ ፡ የተሠራ :
ዜናዋ ፡ እንደ ፡ ወርቅ ፡ ያማረ ፡ ነውና ፤
ዘለዓለም ፡ እንዲኖር ፡ ስሟ' በቬሮና ፡
ከልብ ፡ ለሆነ ፡ ለእውነተኛ ፡ ፍቅር ፡
ምሳሌ ፡ ይሆናል ፡ አብነት ፡ ምስክር ።

#መስፍኑ
ተመልከቱት ፡ ፊቷን ፡ የዛሬ ፡ ጧት ፡ ፀሓይ
ደመና ፡ ለብሳለች ፡ ውበቷ ፡ እንዳይታይ ፤
ሆናለች ፡ ከሰው ፡ ጋር ፡ ሐዘኑን ፡ ተካፋይ ።
በሉ ፡ ሁላችሁም ፡ ሥራችሁን ፡ ሥሩ ፤
ሐዘን ፡ ያለው ፡ ያልቅስ ፡ ሙታን ፡ ይቀብሩ፡
እንደ ፡ ሙታን ፡ ሁሉ ፡ እኛን ፡ በሙቅጣቱ ፡
ነፍሳቸውን ፡ ያድን ፡ እግዜር ፡ በምሕረቱ ፡
መቼም ፡ መቼም ፡ቢሆን ታይቶ ፡ አያውቅና
እንደ ፡ እነዚህ ፡ ልጆች ፡ የሚያሳዝን ፡ ዜና

💫ተፈፀመ💫

ለደራሲው ዊሊያም ሼክስፒር ለትርጉሙ ከበደ ሚካኤል አመሰግናለው።

እንደተለመደው አስተያየታችሁን በ @atronosebot አድርሱን ትላንት በተጠናቀቀው #ህመም_ያዘለ_ፍቅር ላይ የሰጣችሁት አስተያየት ደርሶኛል በጣም ብዙ ነው ለሁሉም መመለስ አዳጋች ሆኖብኛል ግን ለሁላችሁም። እጅግ እጅግ አመሰግናለው 🙏
#ልጩህበት !


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በጥላሁን

ስራዬን በጀመርኩ በ ሀያኛው ቀን ላይ እንደተለመደው እራቴን በልቼ ቡናዬን ጠጥቼ ከምሽቱ 3:15 ላይ ወደ ስራ ወጣሁ እስከ ምሽቱ አምስት ሰአት ድረስ ሲዝናኑ ካመሹት መሀል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ቤታቸው ከፊሉን ከመጠጥ ቤት አልጋ ወደያዙበት ሌላ ሆቴል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ሌላ መጠጥ ቤት ሳገላብጥ ቆየሁ።

ከምሽቱ 5:10 አከባቢ አንድ
ቀን ቀን ሆቴል ሆኖ ማታ ማታ ቅልጥ ወዳለ ጭፈራ ቤት ወደ ሚቀየር ሆት-ጭፈራ ቤት ከውስጥ የሚወጣ እና ትራንስፖርት መጠቀም የሚፈልግ ሰው እስኪወጣ ለመጠባበቅ ጠጋ ብዬ እንደቁምኩ አይኔ አንዲት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሚጣል ነገር የሌላት በዛው ሰአት ሰማይ ላይ እንዳለችው ጨረቃ ደስ የሚል ውበት ያላት ልጅ መግቢያ በሩ በስተቀኝ ብርዱን ለመቋቋም ከጡቶቿ በታች እጆቿን አጠላልፋ በማጣመር ቆማለች።
ሁኔታዋ ሲታይ ግራ ግብት ያላት ትመስላለች እዛው ቆማ አንዴ ቁልቁል አንዴ ሽቅብ ትገላመጣለች ።

እድሜዋ በግምት በ 19 እና በ21 መካከል ቢሆን ነው ይቺን የመሰለች ልጅ በዚህ ሳአት ሊያውም ብቻዋን እንዴት? ትልቁ የውስጤ ጥያቄ ነበር ።
አከባቢው ለኔ አዲስ ባይሆንም ልጅቷ ግን ለአከባቢው እዲስ ሳትሆን አትቀርም ከዚህ በፊት አይቻት አላውቅም ከባጃጄ ወርጄ ምነው ብቸሽን ልበላት አልበላት እያልኩ ከፍርሀቴ ጋር ስነታረክ አንዱ ስልክ ሊያናግር ከውስጥ ወደ ውጪ ወጣና ወድያው ስልኩን አናግሮ እንደጨረሰ አብረን እንግባ ብሎ ልጅቷ ላይ ሙዝዝ አለባት ከዛ በፊት እንደማይተዋወቁ ከሁኔታዋ ተረዳሁ።

ድርቅ ሲልባት ብስጭት ብላ ውዝውዝ ቅንጥስ ብጥስ እያለች ቀጥታ ወደኔ ባጃጅ መጣች ከመድረሷ በፊት ባላየ ፊቴን ወደ ፊት ለፊት አዞርኩ።
ደርሳ " ይቅርታ ወንድም ግቢ ትወስደኛለህ? ኮንትራት "
አለች ዩንቨርስቲ ማለቷ ነው ልጅቷ የዩንቨርስቲ ተማሪ እንደሆነች ለማወቅ ግዜ አላጠፋሁም ዩንቨርስቲው ደግሞ ከከተማው ትንሽ ወጣ ይላል
200 ብር ትከፍያለሽ አልኳት
ግማሽ ፊቷ ላይ ዘንፈል ብሎ ጋደም ያለውን ፀጉሯን በቀኝ እጃ ሁለት ጣቶች ወደ ጀርባዋ ብትን አደረገችና
"200 ብር ለተማሪ አይበዛም ወንድሜ ቤተሰብ በወር የሚልክልኝ እኮ 300 ብር ነው !" አለችኝ

መጀመሪያ አሳዘነችኝ !

ቆይቼ ደግሞ ታድያ አርፈሽ ትምህርትሽን አታጠኝም በዚህ ሰአት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ?!ልላት ፈለኩና እሷን እንዲህ ለማለት ምንም አይነት መብት እንደሌለኝ ቶሎ በማስታወሴ ምላሴን ሰበሰብኩ።

"እ ምናልክ " አለችኝ ።

በደንብ ተመለከትኳት። ውስጤ ተላወሰ ።
እሺ ግቢ እንሂድ አልኳት
"በስንት?" አለችኝ
ደስ ያለሽን ትከፍያለሽ ዘላ ገባች ። ትንሽ በዝምታ እንደተጓዝን ድንገት ዘወር አልኩና•••
•••ሂሳብም አስቀንሰሽ ዝምም ብለሽ አያዋጣኝም !
"ኦኬ እእእእእ ግን ይቅርታ በናትህ ከሚከብዱኝ ነገሮች አንዱ ጫወታ ቀድሞ መጀመር ነው" አለች እየተቁነጠነጠች
ምን አይነት ጫወታ ? አልኳት
"ያው ወሬ ነዋ ሌላ ምን አለ?"
ኧረ ብዙ አይነት ጫወታ አለ ተጫውተሽ አታውቂም እንዴ?
"እንዴ ! ክክክክክ እሱማ ብዙ አይነት ጫወታ አለ እኔ ለማለት የፈለኩት ግን ወሬውን ነው"
ሳቋ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ ደስ የሚል ለዛ አለው ።
ምን አይነት ጫወታ ይቀልሻል? ወይም ትወጃለሽ?
"እቃቃና እኩኩሉ ልበልህ "
ተሳሳቅን ሳቋን ወደድኩት።
ወደ ዩንቨርስቲው እየተቃረብን ነው።
እሺ እኔ ጫወታ በመጀመር ላግዝሻ?
"ከዚህ በላይ እሄው ጀመርከው እኮ! አለችኝ
እኔ ግን ጥያቄ ነበረኝ
የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆነሽ በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ወይ ገብተሽ አልተዝናናሽ
በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••
አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!
ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።
​​#ልጩህበት !


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በጥላሁን

...በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••
አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!
ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች••
••••
እንደፈራች ገባኝ
እኔ ሽምቅቅ ልበልልሽ አልኩ በሆዴ
ዝም ብዬ ሳያት ሳቋ መጣ ፍርሀት የተቀላቀለበት ሳቅ ሳቀች

የፈለከውን አርገኝ ስትይ?

"በቃ ብዙ ሳናወራና ሳንቀራረብ ልንገርህ ብዬ ነው "

እኮ የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ነው?

"እየተጫናነኩኝ ነበረ እኮ እይታይክም እንዴ በቃ ሲጨንቀኝ ነው እንጂ አንተ ባጃጅ ውስጥ የገባሁት ምንም ብር የለኝም ለዛ እኮ ነው ጨንቆኝ እኮ ነው ዝም ብዬ ግንቡን ተደግፌ ስቆም የነበረው"
ከጥያቄዬ እየሸሸች ስትቀበጣጥር የኔም ሳቅ መጣ ቢሆንም ለሶስተኛ ግዜ ጥያቄዬን ሰነዘርኩ
በዚህ መሀል መልሷን በጉጉት እየጠበኩ
አንድ ሰካራም ለሱ ያቆምኩ መስሎት ነው መሰለኝ ኬት መጣ ሳይባል ግራ ቀኝ እየተጋጨ ከውሃላ ገብቶ አጠገቧ ተቀመጠ።

ድንገት ስለገባ ደንግጣ •••

"እማ"

ብላ እየተጣራች ከነበረችበት መሀል ወደ ጥግ ተጠጋች ከሰውየው ራቅ ለማለት።
እሱም መደንገጧን አይቶ ዘወር አለና ወደሷ •••
በመሀል በመሀል ስቅ እያለው•••

"አይዞሽ የኔ ቆንጆ አስደነገጥኩሽ አደል ይቅርታ አንቺኮ - ሀበሻ ሴት ስለሆንሽ ብቻ በጭለማ ውስጥ ያለሽ የ-የ-የ-የ የብርሀን ጭላንጭል ነሽ አይገርምሽም"
አይገርማትም አሁን ባጃጁን ያቆምኩት ላንተ አይደለምና ውረድ አልኩት ድንገት በንዴት!።
ለኔ ንዴት ቦታም አልሰጠው •••
"ለኔማ ነው ያቆምከው! ለሌላ የቆምክ መስሎህ ነው እንዴ?
እኔን እኮ ነው እዛ ጋር ቆሜ ያየከኝ። ሌላ ሰው ቢኖር ለምን እስካሁን አልመጣም? ይልቅ አንተ ስራህን ስራ ከልጅቷ ጋር ላውራበት" ብሎ ሲመልስልኝ ልጅቷ ሳቋን ለቀቀችው።

ሰካራሙ ሰውዬ አንገቱን ከኔ ላይ መንጭቆ በፍጥነት ወደሷ ዞረና•••
"ምን ምን ምን ምን እስቲ በናትሽ ሳቅሽን ድገሚው የተኮረኮረ ህፃን ልጅ እኮ ነው እምትመስይው !
ወይኔ ልጄ ለምን እንደምጠጣ ታውቂያለሽ የልጄን ናፍቆት ለመርሳት !
ልጅ በልጅነት ሲሉ ሰምቼ ምንም ሳይኖረኝ ወልጄ ፍቅረኛዬ እኔ ላይ ጥላብኝ ስትሄድ እኔ ደግሞ አሮጊቷ እናቴ ላይ ጥየባት መጣሁ።

እናቴ ግን መጣያም ቢኖራት የሚጥል አንጀት የላትም እና እኔን ፍዳዋን በልታ ያሳደገችኝ እንዳይበቃት ላስርፋት ሲገባኝ እረፍት እምትነሳ የአንድ አመት ህፃን ልጅ ጥየባት ከመጣሁ ስድስት አመት ሞላኝ አንዴ ብቻ ነው ልጄን ያየሁዋት!!
ግን ግን በናትሽ ካላስቸገርኩሽ ያሁኑን ሳቅ አንዴ ድገሚልኝ !"

ተበሳጨሁ።

ስማ የሷ ሳቅ ስትጋት ያመሸከው ጠጅ መሰለህ እንዴ እሚደገመው አሁን እምትወርድ ከሆነ በፀባይ ውረድልኝ? አልኩት።
"ጠጅ አልጠጣሁን አረቄ ነው ጠጅ ስጠጣ አይተሀል? ነበርክ? ደሞ ሳቅ እንጂ ሌላ ነገር ድገሚኝ አላልኳት ምን አቃጠለክ ኪኪኪኪ " ብሎ ሳቀና ደሞ ወደሷ ዞሮ
"እኔኮ ተሳፋሪ መስለሽኛል ! ፍቅረኛሽ ነው እንዴ ለካ! በቅናት አንገበገብኩልሻ አንበሳ ነኝ አደል አንበሳ••••" እያለ ሳቁን ቀጠለው።
ትግስቴ አለቀ ጎትቼ ላወርደው ተፈናጥሬ ስወርድ•••
"በናትህ ተው እንዳትጣላ " ብላ ጮከች ልጅቷ እጇን እያውለበለበች እና እንዴ ወደኔ አንዴ ወደሱ እየተመለከተች
"አፌ ቁርጥ ይበልልሽ አንቺ ባትኖሪ ምን ይውጠኝ ነበር
ሆሆሆሆ ሊበላኝ ነው እንዴ?
እውነቴን ነው እድሜ ለሴቶች እንበል እናንተ ባትኖሩ እኮ እኛ ወንዶች እሄን ግዜ እንደ ዳይኖሰር እርስ በርስ ተበላልተን ከምድረገፅ በጠፋን ነበር!
አሁን እራሱ ኮረና ያላጠፋን ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? አታውቂም?
እንደኔ ከሆነ ኮረና ድምጥማጣችንን ያላጠፋን ኢትዮጲያዊያን ሴቶች ጨዋዎች ስለሆናችሁ ነው
እድሜ ለናንተ!
እውነቴን ነው አሁን እኔ ልሙት እንኳን ማክስ ሱሪስ እምታስወልቁን እናንተው አደላችሁ ።
እናንተ ጨዋ ባትሆኑ ማነው ማክስ አላወልቅም የሚለው እንደ ብራዚል ሴቶች ብትሆኑ ማን ይተርፋል ? አልቆልን ነበር ሙች እውነቴን ነው!
እሱ ይለፈልፋል እሷ ትስቃለች !
ሰውየው የባጥ የቋጡን እየቀባጠረ ደሜን ቢያፈላውም ለምን እንደሆነ ባላውቅም በሱ ንግግር የምትሰቀውን ልጅቷን ማየት ስላስደሰተኝ ነው መሰለኝ ሳላስበው ብዙ ታገስኩት
አሁን ትወርዳለህ አትወርድም አልኩት ወደሱ እየተጠጋሁ
"እራስህ እኮ ነህ አቁመህ የጫንከኝ !"
ላንተ አልቆምኩም አልኩህ እኮ!
"ታድያ ለማን ነው የቆምከው?"
ለሷ!
"ለሷ ካካካ እሷኮ አብራህ ነው የመጣችው••••
እሀሀሀ ልታወርዳት ነበር እንዴ የቆምከው ገባኝ !
ታድያ ምን አጣደፈህ ቀስ ብለህ አትቆምም ብቻሽንማ አትወርጂም ነይ በይ እንውረድ!"
ሲላት•••
ሳላውቀው በንዴት ውስጥ ሆኜ ሳቄ መጣብኝ እንደምንም ላለመሳቅ እየታገልኩ ኮሌታውን ይዤ ጎትቼ ላወርደው ስል•••
"እባክህ ተወው እንደዛ አታድርግ ! ቆይ የት ነው መሄድ እምትፈልገው አንተ ?!" አለችው።
"ብዙ አርቅም እኮ እሄኛው መጠጥ ቤት ስለተዘጋብኝ እቅዴ ደሞ አዳሬን መጠጣት ስለሆነ ቤት ልቀይር ነው እዛች ጋ ያለችው ግሮሰሪ ደሞ ካልታሸገች በስተቀር አትዘጋም ወደዛ ነው እምሄደው " ሲላት
"በናትህ ጣል አርገነው እንለፍ ?" እለችኝ ባይኗ እያባበለች
ምነው በሱ ምክንያት የምታመልጪ መሰለሽ እንዴ እሱን አውርጄው የጀመርነውን እንጨርሳለን እሺ አልኳት ኮስተር ልልባት እየሞከርኩ።
ባጃጁን አስነስቼ ከነፍኩ።
"ምን አርጊ ነው እምትላት እነጨርሳለን እንጫረሳለን እያልክ ታስፈራራለህ እንዴ?" አለ
እስቲ ዝምበል ስለው ጭራሽ ባሰበት•••
"ዝም አልልም እንደውም እሱን ተይው አንቺ ብቻ ፍቀጅልኝ?"
"ምን ?"
"አንዴ ልጩህ በናትሽ ?"
"እንዴ ለምን ምን ሆንክ?" አለችው ግራ ተጋብታ ሰውየው መች ያልቅበትና እኔ በማታ ስራ ብዙ ሰካራም ጭኛለሁ እንደዚህ ሰውዬ ግራ ያጋባኝ ሰው አልገጠመኝም ቀጠለ••
"አንቺ ምን ስትሆኚ ነው እምትጮሂው?"
"ምን አይነት ጩኸት?"
"እሄውልሽ እኔ ደስ ሲለኝም እጮሀለሁ ሲጨንቀኝም እጮሀለሁ በናትሽ አሁን አንዴ ልጩህ ? ፈቀድሽልኝ አለና
በጣም በሚያስፈራ ድምፅ አቀለጠው።
እሷም ደነገጠች እኔም ባጃጁን አቁሜ በደምፍላት ወደሱ ዞርኩና
አንተ ሰውዬ እብድ ነህ እንዴ?ስለው
"የፈለከውን በለኝ ግን በናትህ ልጩህበት ተወኝ ?"
እስቲ ወንድ ነህ ድገመው አልኩት። የጉድ ቀን አይመሽም አሉ ዛሬ የጉድ ለሊት አይነጋም ሆነብኝ እሷ በኔና በሱ ሁኔታ ትስቃለች ሰውየው ቀጠለ
ልጩህበት ተወኝ ተወኝ ልጩህበት
በአፌ ቢወጣ የውስጤ እንፋሎት
ለየልኝ እሄ ሰውዬ አላበዛውም እንዴ ግጥምህንም አንተንም አልፈልግም ውረድልኝ
እቺን ግጥም ሳልጨርስልህማ አልወርድም
ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ
ንዴቴን
ብሶቴን
ናፍቆቴን ባከስመው
እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!!
••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ•••
"አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍21
#የብይ_ጨዋታን_የምትወክል_ሀገር

ሃገር ገደል ስትሆን ብይ ናቸው ልጆች
ጉድጓድ የሚገቡ
ለጉድጓድ ሚቀርቡ፣ተጥለው በእጆት፡፡
እመለከታለሁ!
እንደ ብይ ጉድጓድ ፣ ተስሎ ሀገሩ
እጆች ይታዩኛል
ትውልድ ወደ ገደል ፥ የሚገፈትሩ።

እመለከታለሁ!
ብዙ ብይ ህይወቶች፧ ጉድጓዱን ሲስቱ
ብዙ ብይ ህይወቶች ፥ ጉድጓድ ሲከተቱ
እመለከታለሁ!
ከጉድጓድ የወጡት ፥ የቀረባቸውን እየፈነከቱ

ደግሞ እታዘባለሁ!
በብዮች ሀገር ላይ ፥ የብዮችን ጥፋት
ከጉድጓድ ሲወጡ
የገፋውን ሳይሆን
አብሮ ተገፊውን ፥ እንደገና መግፋት
ከክፋት ሚወርሱት ፥ ሌላ አይነት ክፋት!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ዐይቶ_መጠራጠር

ሳያዩ የሚያምኑን ፥ አይተህ ተጠራጠር
ተእምር አየሁ" አትበል !
ጋንን ያህል ነገር ፥ ሲደገፍ በጠጠር
ይልቅ ተአምር ሥራ
ከሚታይ መልስ ላይ ፧ ጥያቄ በመፍጠር።

ሁሉንም አትመን ፥ ግን ሁሉን ተጠንቀቅ
“ቤትህ በሰማይ ነው”
ብሎ ለሚሰብክህ ፥ ምድርህን አትልቀቅ።
ከስጋ ፍላጎት
አርቀህ ስቀለው፥ የነፍስያህን ልክ
የቄስን ቃል ስትሰማ ፣ ቄሱን ግን አታምልክ።
ሁሉ ካህን ላይሆን
ሁሉን ፍቱኝ እያልክ ፥ ነፍስህን አታክስር
ስንቱ በካህን ለምድ
እባብ ይደብቃል በጠመጠመው ስር።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
1👍1
​​#ልጩህበት !!


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በጥላሁን

ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ
ንዴቴን
ብሶቴን
ናፍቆቴን ባከስመው
እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!!
••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ•••
"አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ •••
እኔ ከባጃጅህ አልወረድኩ አንተ ግን ከገባሁ ጀምሮ ዝም ብለህ ትጮሀለህ ስማኝ የት እና መቼ እንደምትጮህ ካላወክ ዝም ብትል ይሻላል
ያለበለዚያ ሰሚ ሳይኖር ዝም ብለህ ብትጮህ የራስህ ጩኸት እራስህን ያደነቁርህ እንደሆን እንጂ ምንም አታመጣም !"
ብሎኝ ሲያበቃ ደሞ ወድያው ወደሷ ዞረና
"አንድ ግዜ ብቻ ልጩህ በናትሽ ?"
ሲላት ቀርታኝ የነበረችው እንጥፍጣፊ ትግስት ተሟጠጠች •••

አቦ ባባ ክብር ካልወደደልህ እንዴት እንደምትወርድ ላሳይሀ እንግዲህ ብዬ እጄን ለፀብ እያሰናዳሁ ወርጄ ስጠጋው
"ተው ተው ተው ቦክስ አታባክን ወጣቱ መጀመሪያውኑ እንደዚህ ወንድ ብትሆን ኖሮ አንተ ባጃጅ ውስጥ እስካሁን ማን ይቀመጥ ነበር ፈሪ ፈሪ ነገር ነህ !"
እያለ ከባጃጇ ሲወርድ ልጅቷ በሳቅ ፈነደቀች
ግራ ቀኝ እየተወዛወዘ ትንሽ ከባጃጇ ራቅ እንዳለ ዘወር አለና
"ሞት ይርሳኝ ቻው እሺ የኔ ልጅ ልጅ አልኩ እንዴ አንቺን እንኳን አላደርስም !
ቻው እሺ የኔ ልእልት አንቺን የመሰለች ልጅ ከዚህ አስቀያሚ ሹፌር ጋር በማየቴ ደንግጫለሁ !
ፍችው በናትሽ! " እላት።
"እሺ "አለችው በሳቋ መሀል
"ግን መች ትፈችዋለሽ በናትሽ! እ••• እ ••እ ንገሪኛ?" እያለ ሊመለስ ሲል እኔም እየሳኩ ወደሱ ስጠጋ ፊቱን አዙሮ ከቆምንበት በስተቀኝ መንገድ ዳር ወዳለችው የማትዘጋዋ መጠጥ ቤት አመራ።

ባጃጃን አስነስቼ ከዩንቨርስቲው በቅርብ ርቀት
ጨለማ ውስጥ አቆምኳትና ከመሪው ላይ ተነስቼ እሷ አጠገብ ተቀመጥኩ ። ፊቷ ተቀያየረ።
ካቆምንበት እንቀጥላ አልኳትና
ቅድም የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ፈልገሽ ነበር ?
"በቃ ከፈለክ ልትሰድበኝም ከፈልክ ልታወርደኝም ትችላለህ ሌላ ምንድን ነው?" አለችኝ የጭንቀቷን
ወደ ዩንቨርስቲው ዞሬ ተመለከትኩ አጠገባችን ነው ግቢው ከሩቅ ይታያል ሳቄ መጣ አብራኝ ሳቀች።
ሀይ ስትደርሺ ነው እንዴ ልታወርደኝ ትችላለህ እምትይው? ስላት•••
ጭንቅላቷን ወደ ግራ ሰበቀችና በዝምታ እጇን እያፍተለተለች አይን አይኔን ታየኝ ጀመር
የሆነ ስሜት ተሰማኝ
ታውቂያለሽ ሁለት ወንድሞች አሉኝ ግን እህት የለኝም ቢሆንም እናት አለኝ የማይሆን ቢሆንም እናትም ባይኖረኝ እራሱ አንቺ ላይ የሚጨክን አንጀት የለኝም
ምንም አልደርግሽምም አልሰድብሽምም አላወርድሽምም እሺ መጀመሪያውኑ ብር እንደሌለሽ ብትነግሪኝና በነፃ እንዳደርስሽ ብትጠይቂኝ ለስራ ብወጣም ከሰአቱ አንፃር ላውሬ ጥዬሽ አልሄድም ነበር ።

እያሰብኩ የነበረው ምናልባት መጥፎ ባህሪ ያለው የባጃጅ ሹፌር አጋጥሟት ቢሆን ኖሮስ እያልኩ ነው።
ግን ምን አጋጥሞሽ ነው ማለቴ
በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ?ስለራስሽም ብትነግሪኝ ደስ ይለኛል
"አጋጣሚው ከብዙ ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው ኬቱ ጋር ልጀምርልህ?
ከፈለግሽው።
"በናትህ አሁን መሽቷል ሞባይሌን ዶርም ጥዬው ወጥቼ ነው ከፈለክ ስልኬን ያዝና ነገ ወይ በሚመችህ ቀን ደውልልኝ አወራሀለሁ!"
እዚሁ ባጃጅ ውስጥ እናድራታለን እንጂ አልፋታሽም አልኳት ኮስተር ብዬ
" እያስገደድከኝ ነው ማለት ነው አለች እሷም በስሱ ከስተር ብላ
ስትስቅም ስትኮሳተርም የሚያምርባት ሴት እሷን አየሁ።

አሁን ከተለያየን ቡሀላ ልታገኝኝ ፍቃደኛ ሁኚ አትሁኝ እርግጠኛ ስላልሆንኩ አሁኑኑ እንድትነግሪኝ እየለመንኩሽ ነው! ከተጫንኩሽ ይቅር ብትነግሪኝ ግን የመጣሽበትን ሂሳብ እንደከፈልሽ እቆጥረዋለሁ አልኳትና አሁንም እኩል ሳቅን።
"ክትክትክትክት ኧረ ባክህ
እሺ ግን ባጭሩ ነው በደንብ እንድትረዳው ገባ ብዬ ብጀምርልህ ይረዝምብኛል?"
አቦ ንገሪኝኛ አታጓጊኝ!።
" እኔ
እኔ
እኔ ማለት እኔ ደሀ ከሚባል ቤተሰብ ነው የተወለድኩት ።
አባቴ አናፂ ነው እናቴ ደግሞ ሽንኩርት ቲማቲም ምናምን ነው ጉሊት ውስጥ የምትቸረችረው
ሁለቱም ፀሀይ ላይ ውለው ፊታቸው ጠቁሮ ከሚያገኙት ገቢ ውስጥ አብዛኛውን እኔን ከሰፈሬ እና ከትምህርት ቤት ጓደኛቼ እኩል ማድረግ ባይችሉ እንኳን ክፍተቱን በመጠኑ አጥብበው ብዙ ሳይሰማኝ እንዳድግ ለማድረግ አውለውታል።
ሳይለብሱ ያለብሱኛል
ለነሱ ርካሽ የተባለውን ጫማ እየተጫሙ ለኔ ውድና ሁለት ሶስት ቅያሪ ጫማ እንዲኖረኝ ለማድረግ ለነሱ የሚያስፈልጉዋቸውን ሁሉ ወደ ጎን ትተዋል !
ሳይደሰቱ እኔን ለማስደሰት የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል!
ቢኮራረፉ እኔ ፊት ይስቃሉ!
ቢያዝኑ እኔ ፊት ደስተኛ ለመምሰል ይሞክራሉ!
በአጠቃላይ ለራሳቸው ሳይኖሩ ለኔ ደክመው ለኔ ኖረው ያስተማሩኝን ቤተሰቦቼን ለማስደሰት የምችለው በትምህርቴ ስጎብዝ ነውና ምንም ነገር ሳያታልለኝ በርትቼ በመማር ወደ ዩንቨርስቲ መግቢያ የሚሆን ውጤት አምጥቼ ባስደሰትኳቸው ማግስት ነበር አባዬ እኔ ወደዚህ ለመምጣት የሚያስፈልገኝን ነገር ለሟሟላት ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ ያገኘውን ስራ በሙሉ እየሰራ ገንዘቡን እኔው ጋር ማጠራቀም የጀመረው •••"
አለችና ዝም አለች።
ምነው ቀጥይ እንጂ ስላት
"ስላባዬ ሳወራ ጨነቀኝ !
ትንሽ ዝምታ ተፈጠረ በመሀላችን።
ሲጨንቀኝ ደሞ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ?"
ምን ትዝ አለሽ ?
አንዴ ልጩህ እሚለው የቅድሙ ሰካራም ።
አንዴ ልጩህ እንዴ?"
ስትለኝ ሁለታችንም ባንድ ግዜ ከነበርንበት ሙድ ወጥተን ከባጃጇ ጣራ በላይ ሳቅን።
በናትሽ ቀጥይልኝ ? አልኳት ሳቄን ስጨርስ። ካሳቁ መልስ ደሞ ባንዴ ፊቷን ቅጭም አርጋ ቀጠለች•••
አባዬ ድካሙና እንቅልፉ ተደራርቦበት ነበር ።
ልመጣ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ •••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#የሰካራም_ግጥም

የማብድ ቢመስለኝ ፥ ድንገት አንቺን ሳጣ
አረቄ ቤት ሔጃ ፥ አረቄ ስጠጣ
አንድ ግጥም ሰማሁ
ፍቅርሽን ከልቤ ፥ ነቅሎ የሚያወጣ፡፡
ያውም “መንገድ” በሚል
ለመንገደኛ ሰው ፥ ሰካራም የፃፈው
እዛ ጋ ቁጭ ብሎ...
“ከዳችኝ” እያለ ፥ የሚለፈልፈው
“መንገድ” የሚል ግጥሙ ፥ ጆሮዬን ገረፈው።
ጆሮዬ ሲገረፍ ...
ጠባሳ ካለብኝ ፥ ግጥሙን እንዳልረሳ
“መንገድ አያደርስም
መንገድ አይመልስም ፥ እግር ካልተነሳ!”
እያለ ይገጥማል..
ደጋግሞ ደጋግሞ ፥ ሌላ አይናገርም
እሱም ልክ እንደኔ ...
አንዷን በመሔዷ ፥ ሳያት አይቀርም፡፡
ብቻ ሰክሪያለሁ!
ለመንገደኛ ሴት
የተፃፈ ግጥምን ፥ ጆሮዬ ያደሞጣል
መሔድሽን ያየ
እንደሌሌሽኝ ሲያውቅ ፥ ሊኖረኝ ይመጣል
ይህ ነው መንገድ ማለት!
የሰካራም ግጥምን ሰክሬ ስረዳው
መሔድ ሳይሆን ለኔ ፥ መርሳት ነው ሚጎዳው!
ረስቼሻለሁ!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ፍል_ስንፍና (2)

ጌታ ሆይ….
“ድንገት እንደ ሌባ
እመጣለሁ” ብለህ ፥ ከሔድክ በኋላ
ጌታ እየመሠለኝ ፥ የሰረቀኝ ሁላ
ሲዘርፉኝ እምነቴን
ሲዘርፉኝ ሀገሬን ፥ ሲነጥቁኝ ርስቴን
ሲጠፋብኝ እንባ ፥ ሲሰርቁኝ ምሬቴን
ሲሰርቁኝ ብሶቴን
“እርሱ ነው” እያልኩኝ
መጥቶ ነው እያልኩኝ
አይቶ እንዳላየ ፥ በዝምታ አልፌ
ሀገሬን እምነቴን ፥ ሁሉን ተዘርፌ
ካበቃሁ በኋላ ፥ ሲያማርረኝ ማጣት
መፈላሰፍ ጀመርኩ!
"ልክ አይደለም” ብዬ
ጌታ ሆኖ ሔዶ ፥ ሌባ መስሎ መምጣት!"

🔘በፋሲል🔘
​​#ልጩህበት ! !


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በጥላሁን

"ስላባዬ ሳወራ ጨነቀኝ !
ትንሽ ዝምታ ተፈጠረ በመሀላችን።
ሲጨንቀኝ ደሞ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ?"
ምን ትዝ አለሽ ?
አንዴ ልጩህ እሚለው የቅድሙ ሰካራም ።
አንዴ ልጩህ እንዴ?"
ስትለኝ ሁለታችንም ባንድ ግዜ ከነበርንበት ሙድ ወጥተን ከባጃጇ ጣራ በላይ ሳቅን።

በናትሽ ቀጥይልኝ ? አልኳት ሳቄን ስጨርስ። ካሳቁ መልስ ደሞ ባንዴ ፊቷን ቅጭም አርጋ ቀጠለች•••
አባዬ ድካሙና እንቅልፉ ተደራርቦበት ነበር ።
ልመጣ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ •••
••••
ልመጣ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ በሂወቴ እማረሳው መጥፎ አጋጣሚ ተፈጠረ ቀኑ አርብ ነበር አባዬ እንደተለመደው በለሊት ነበር ወደ ስራ የወጣው
ያን ሰሞን የሚሰራበት ቦታ ከኛ ቤት ብዙ ስለማይርቅ እንደነገ ልጀምር ማታ እማዬን በጥዋት እየተነሳሽ ምሳ አትቋጥሪልኝ ቀስ ብለሽ ስሪና አለሜ ታምጣልኝ አላት ስሜ ኤደን ቢሆንም አባ ግን አለሜ የኔአለም እያለ ነው እሚጠራኝ።

ለአራት ቀናት ምሳውን ስራ ቦታ እየወሰድኩለት እስኪበላ እያዋራሁት እምለሳለሁ በአምስተኛው ቀን ጓደኛዬ አርብ እለት ከማዬ ጋር ልብስ ይዥበት የምመጣውን ቦርሳ ለመግዛት አብረን ወጥተን ስለነበር ምሳውን ሳላደርስለት ሰአቱ ሄደብኝ በውስጡ ልጄን ምን አጋጠማት እያለ ሲጨነቅ ነበር ለካ ከቀኑ ሰባት ሰአት ተኩል ላይ ምሳውን ይዤ ከቤት ወጣሁ ከ15 ደቂቃ ቡሀላ ደረስኩ።
ቀና ስል•••
አባዬ በግምት ከመሬት አምስት ሜትር ከፍታ ላይ ተሰቅሎ ስራውን እየሰራ ነው አባ ብዬ ጮክ ብዬ ስጣራ ስቆይበት ጭንቀት ላይ የነበረው አባዬ የኔን የልጁን ድምፅ ድንገት ሲሰማ ደነገጠ መስለኝ ሳይጠነቀቅ እኔን ለማየት የያዘውን ለቆ ዞረ!
ወድያው ከላይ ቁልቁል ሲምዘገዘግ አይኔን ማመን ተሳነኝ በሂወቴ እንደዛን ቀን ደንግጬ አላውቅም ውሃ ሆንኩ ወደ ወደቀው አባቴ መጠጋት ፈርቼ በቆምኩበት ስጮህ ባከባቢው የነበሩ ሰራተኛች ከወደቀበት አንስተው አናቱ ላይ ውሀ ሲያፈሱበት ተመለከትኩ
ተርፏል አባቴ !
ተርፏል አባቴ !
እያልኩ ወደሱ በመሮጥ እያለቀስኩ አንገቱ ላይ ተጠመጠምኩበት።
እግሩና የጎን አጥንቱ ላይ ጉዳት ደረሰበት ያን ቀን አሰሪው ሀኪም ቤት ወስዶ ህክምና ተደረገለት ከዛን ቀን ቡሀላ ግን ዘወር ብሎም አላየውም
ከ አምስት ቀን ቡሀላ እኔ ጋር ያለው ለዩንቨርስቲ ጉዞዬ ብሎ ያጠራቀመው ገንዘብ ለሱ ህክምና እንዳልጠቀምበት ብሎ ሳይሻለው ተሽሎኛል ብሎ ከሀኪም ቤት ወጣና እቤታችን ተኛ
ለሊት ለሊት ሲያቃስት ስለሰማሁት አባ እሺ በለኝ እና በደንብ ታከም እኔ ጋር ባለው ብር ታክመህ ካልዳንክ ወደ ዩንቨርስቲ እንደማልሄድ እወቀው ስለው እሺ አለኝ።
አሳክሜው የተረፈችኝን ይዤ መጣሁ እዚህ ከመጣሁ አራት ወር ሊሞላኝ ነው ግን እስካሁን ስራ አልጀመረም እማዬ በምትሰራው ብቻ ስለሚኖሩ እማን ላለማጨናነቅ ብዬ ምንም ወጪ የለብኝም ብር እንዳትልኪልኝ አልኳት
እዚህ ደግሞ ብዙ ወጭዎች አሉ ኖቶችን(ሀንድ አውቶችን) ኮፒ ከማረግ ጀምሮ ብዙ ነገሮች አሉ በተለይ ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ በባሰ ሁኔታ እጇ ላይ ሳንቲም ያስፈልጋታል ሁሉንም ፍላጎቷን ማስቀረት ብትችል የሞድየስን እና የአንዳንድ ነገር ወጪዎቿ ግድ ናቸው።
በዚህ ግቢ ማደሪያ ክፍላችን (ዶርም) ውስጥ በጣም የምቀርባቸው ሁለት ጓደኛች አሉኝ የመጣን ሰሞን ስለሂወታችን ስናወራ የሶስታችንም ቤተሰቦቻች በተቀራራቢ የድህነት ህይወት ውስጥ ያሉ እድሚያችን ፣አለባበሳችን፣ ፍላጎታችን ፣ ችግራችን ባጠቃላይ በተመሳሳይ ህይወት ውስጥ ማለፋችን ነው መሰል ቶሎ ለመቀራረብና እንደህታማቾች ለመተሳሰብ እና ለመተዛዘን ግዜ አልፈጀብንም።
እማንለያይ አንዳችን ላንዳችን የምንጨነቅ ሆንን ከቅባት ጀምሮ የሚያስፈልጉንን አዋጥተን እንገዛለን አንዳችን ያንዳችንን ልብስ ለመልበስ ፍቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም የነሱን ባላውቅም እኔ ሁለቱንም በጣም ነው እምወዳቸው ።
ትንሽ እንደቆየን በተለይ አንዲት የሶስተኛ አመት ተማሪ ባጋጣሚ ከአንደኛዋ ጋደኛዬ ጋር ተዋውቋ ዶርማችን መጥታ ከተዋወቀችንና በየቀኑ መምጣት ከጀመረች ቡሀላ ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ጀመሩ።
እኔ ልጅቷ የምታወራው ነገር ሁሉ ስለማይጥመኝ ብዙም አልቀርባትም ነበር ።
ከሁለቱ ጋር ግን በጣም ተቀራረበች ጭራሽ ከግቢ ውጪ አምሽተው አንዳንዴም አድረው መምጣት ጀመሩ የት ሄዳችሁ ነው? ስላቸው ከሷ ጋር እንደነበሩ ይነግሩኛል የጓደኝነቴን ትምህርታቸው ላይ እንዱያተኩሩና ከሷ ልጅ ጋር መዞሩን እንዲቀንሱ ብነግራቸውም ጭራሽ ባሰባቸው ። እንደውም እኔም አብሬያቸው ዘና እንድል በተለያየ መንገድ ሊያሳምኑኝ ይሞክሩ ጀመር።

በተዋወቋት ባጭር ግዜ ውስጥ እኔ ለፎቶ ኮፒ ተቸግሬ ፍዳዬን ሳይ እነሱ ልብስና ጫማ በየሳምንቱ መቀያየር ጀመሩ ከኔ ጋር ያላቸው ልዩነት እየሰፋ እየሰፋ መጣ የነበሩት ነገሮች በሙሉ ተለዋወጡ እንኳን ከኔ ጋር ቅባት አዋጥተው ሊገዙ እንኳን ከኔ ጋር ልብስ ሊቀያየሩ የበፊቶቹን ልብሶቻቸውን ከፈለኩ መውሰድ እንደምችል ይነግሩኝ ጀመር።
ቅባት ሻንፖ ሎሽን የመሳሰሉትን ነገሮች ገዝተው ሲሰጡኝና እና ለፎቶ ኮፒ የሚሆነኝን ገንዘብ ስፈልግ እንድጠይቃቸው ሲነግሩኝ ከምልህ በላይ ይሰማኝ ጀመር በቃ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ የበታችነት ስሜት ተረጋግቼ ማጥናት እስክቸገር ድረስ መጥፎ ሁኔታ ውስጥ ከተተኝ።
በዛ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ደግሞ ያቺ ጓደኛቸው እና እነሱ እነሱን እንድመስል አብሬያቸው እንድውል እና እንዳመሽ ባገኙት አጋጣሚ ይወተውኛል ።
በቅርቡ የመጀመሪያው ሴሚስተር ፈተና ነበርና በየትምህርት አይነቱ ያሉትን ኖቶች ኮፒ ለማድረግ በጣም ሳንቲም ያስፈልገኝ ነበር።
ያቺ ጓደኛቸው ያዘነች መስላ ያንን ወጪ በነሱ በኩል
በመሸፈን በውለታ ከያዘችኝ ቡኋላ
ዶርም መጥታ ፈተና ስንጨርስ አብሬያቸው ወጣ ብዬ ለመዝናናት ፍቃደኛ እንድሆንና ቃል እንድገባላት በነሱ ፊት ጠየቀችኝ ለሶስት ሲያዋክቡኝ ግራ ገባኝ !
ደስ ባይለኝም ያቀደችልኝን ቀድሜ መረዳት አልችልም ነበርና ቃል ገባሁ።
ፈተናው ሊያልቅ አንድ ቀን ሲቀረው ጨነቀኝ
ዛሬ ጥዋት ስድስት ሰአት አከባቢ እነሱ ፈተናው በማለቁ ደስ ሲላቸው እኔን ግን ፍርሀት ፍርሀት አለኝ •••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ከዕንቁላልነት_እስከ_ቢራቢሮነት

ስትይ , “ምን ይመስላል?!”
ነበርኩኝ - “ዕንቁላል”፡፡
ስትይ .. “የማይረባ!”
ነበርኩኝ - “ኩብኩባ”፡፡
በረሳሽኝ ጊዜ
ከነመፈጠሬ
ሆንኩ - “አባ ጨጓሬ” ፡፡
ኖሬ ኖሬ ኖሬ..ኖሬ
በቀለም ተውቤ ከወትሮው አምሬ
እንዳሻኝ ሳማርጥ አበባቱን ዞሬ
ጎልቼ ብታይሽ ብለይብሽ ዛሬ ፤
በዕንቁላልነቴ
ያጣጣልሽኝ ድሮ፤ ያናናቅሽኝ ድሮ፤
ልትይዥኝ አማረሽ
በነፃነት ስበር ስሆን “ቢራቢሮ”፡፡

🔘በፋሲል🔘
#ከሳቅ_በስተጀርባ

የጢንጧ ልጅ ፈገግታ የሰው ቀልብ ይሰርቃል
ስሜትን ቀስቅሶ መንፈስ ያነቃቃል
ይህ ፈገግታ ሚሉት ምንኛ ይደንቃል?!?
የስንቶቹን ምሥጢር ጥርስ ውስጥ ይደብቃል::
በፈገግታዋ ሥር ከሩቅ ተደብቄ
ስታየኝ አየዋት ልጅቷን እርቄ::
ያማል!
ያሳምማል!
ፈገግታዋ ሲከስም ሐዘኗ ይደምቃል
ዓይኗም አፍ አውጥቶ ሁሉን ያሳብቃል
ልጅቷ ሕይወት ውስጥ
አያሌ መከራ እንዳለ ያስታው ቃል
አይገለጽ በቃል::
ከሳቅ በስተጀርባ
የታቆረ ዕንባ!!!

🔘በፋሲል🔘
#ስንቶች_ናቸው

ሰቅለው ሁለት ባላ
ሲሰበርባቸው አንዱ
በአንዱ 'ሚንጠለጠሉ
ነፍስና ሥጋቸው እየተጣላ
አልስማማው ሲላቸው
ወስን ሲያልፍባቸው ሲጥስባቸው ሌላ
በስመ-ፍቅር ከለላ ይዘው የነፍስ ምህላ
ዕላተ ልቡናቸውን አክብረው
ሸፍነው በትዕግሥት ጥላ
ሳይፈቀሩ አፍቅረው
ዘመናቸውን ሲፈጁ ኖረው ኖረው ኖረው
መግቢያ መውጫ ሲቸግራቸው
የፍቅረ ረቂቅ ኃይል ውስብስቡ ውጥንቅጡ
መስመራቸውን ሲያስታቸው ሲጠፋባቸው መላቅጡ
ሌላ አማራጭ ሲያጡ
በዕልመት ውስጥ ሲዋጡ ቶሎ ተስፋ ሲቆርጡ
ከራሳቸው ጋር ተጣልተው ከራሳቸው ጋር ሳይታረቁ
ጀንበራቸው አዘቅዝቀው የሰውን ፀሐይ እየጠበቁ
የሚሞቁ
ልባቸውን አቀዝቅዘው የሌላን ልብ እያሞቁ
መሪር ሐዘን ውጧቸው በሰው ደስታ እየቦረቁ
የራሳቸውን ጥርስ አኑረው በሰው ጥርስ እየሳቁ
“የእኔ” ከሚሉት በቀር ማፍቀር እንደማይችሉ እያወቁ
ያፈቀሩ መስለው ሳያፈቅሩ
አኗኗሪ ሆነው እሚኖሩ
የሚቆጠሩ እያሉ እንደሌሉ
በየቤቱ ስንቶች አሉ?!?
…..
ከሚያፈቅሩት ሰው እየሸሹ ከሚያፈቅሩት ሰው እየራቁ
ለሚጠሏቸው እጅ የሰጡ በማይፈልጉት ሰው እጅ የወደቁ
ገና የቃልኪዳኑን ቀለበት በጣታቸው ላይ ሲያጠልቁ
የሚያፈቅሩትን ሰው እየናፈቁ
ስንቶች ናቸው ፍቺያቸውን በጋብቻቸው ዕለት ያፀደቁ?!?
ስንቶች ናቸው
ተለይቶ ከራሳቸው
ተቦጭቆ ከገፃቸው የነፍስና ያካላቸው ግማሹ
ከሚያፈቅሩት ጋር እንደቀረ እያወቁ እየዋሹ
የሚያፈቅሩትን ሰው እያሰቡ
ከማይወዱት ጋር የሚቆርቡ
ላይፋቱ ያለፍቅር የሚጋቡ፡፡
ስንቶች ናቸው፡፡
ራሳቸውን በራሳቸው የቀጡ
ራሳቸውን በራሳቸው የገደሉ
የፅድቅ መንገዳቸውን ያበላሹ
ፀዓዳ መንፈሳቸውን ያቆሸሹ
ከማያፈቅሩት ጋር እየኖሩ
የሚያፈቅሩትን ሰው እሚሹ፡፡
ስንቶች ናቸው?!?

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ልጩህበት !!


#ክፍል_አምስት


ድርሰት_በጥላሁን

ደስ ባይለኝም ያቀደችልኝን ቀድሜ መረዳት አልችልም ነበርና ቃል ገባሁ።
ፈተናው ሊያልቅ አንድ ቀን ሲቀረው ጨነቀኝ
ዛሬ ጥዋት ስድስት ሰአት አከባቢ እነሱ ፈተናው በማለቁ ደስ ሲላቸው እኔን ግን ፍርሀት ፍርሀት አለኝ •••
ወደ ዶርም ገባሁ። በፈተናው ምክንያት የተጠራቀመ እንቅልፍ አለብኝ።ጋደም አልኩ ። ይዞኝ ሄደ።
አንድ ሳአት ያክል እንኳን ሳልተኛ የሆነ ከሩቅ የመጣ የመሰለኝ ጫጫታ ቀሰቀሰኝ።

ብርግግ ብዬ እዛው በጀርባዬ በተኛሁበት አይኔን ገለጥ ሳደርግ ሶስቱም አልጋዬ ጠርዝ ላይ ተደርድረው ቁልቁል እያዩኝ ይንጫጫሉ።
"ኧረ መተኛት እስቲ በዛሬ ቀን ይተኛል!"
"እኛኮ ገና ከፈተና ያልወጣሽ መሰለን?"
"ዛሬ ወሳኝ ቀጠሮ ከኛ ጋር መያዝሽን ረስተሽው ባልሆነ በይ ተነሽ አሁን!
" ውሃ አምጪና ድፉባት በናትሽ!"
ህልም ላይ ነበርኩ አቋረጣችሁኝ አልኳቸው ቀና እያልኩ።

ከሁለቱ ጓደኛቼ አንደኛዋ ትግስት(ቲጂ) ስትባል ሌላኛዋ ደግሞ ረድኤት(ረዱ) ትባላለች
የሶስተኛ አመት ተማሪዋ ስንተዋወቅ መሲ እንዳለችኝ ትዝ ይለኛል ግን በሌላ ስም ሲጠሯት ሰምቻለሁ።
"ምን አንቺ ህልም ብታይ ካባትሽ አታልፊ አሁን ብናቋርጥሽም ነገ ወይ ከነገ ወድያ ማየትሽ ስለማይቀር ትቀጥይዋለሽ ግን አብዝተሽ ስለሳቸው ስለምትጨነቂ እኮ ነው አደል ኤዱ ? አለችኝ ቲጂ
ንግግሯ ስላልጣመኝ መልስ ሳልሰጣት ፊቴን ልታጠብ ወጣሁ።
ስወጣ ግን •መሲ ተብዬዋ•••
" አባቷ ምን ሆነዋል ?ለምንድን ነው ስላባቷ የምትጨነቀው? ብላ ስትጠይቃቸው ሰምቻታለሁ።
ታጥቤ ስመለስ ስላባቴ ስትጠይቅ የነበረችው ያቺው መሳይ•••
"አንቺ እኮ በዚህ ውበትሽ እሄ ድርቅናሽን ትተሽ ፈጠን ያልሽ ልጅ ብትሆኚ እንኳን አባትሽ ጋር ደርሶ ለመመለስ መሳፈሪያ ሊቸግርሽ ለሌላም በተረፍሽ ለማንኛውም የሆነ ብር ከገባልኝ እኔ እራሴ እሰጥሻለሁ እሺ ኤዱዬ ሄደሽ ታያቸዋለሽ!"
አለችኝ ።
አባቴ በጣም ስለናፈቀኝ መጨረሻ ላይ የተናገረቻት ነገር የልብ ትርታዬን ጨምራው ሰፍ እንድል ብታደርገኝም በመጀመሪያው ንግግሯ ላይ ጥያቄ ነበረኝ•••
ድርቅናሽን ትተሽ ፈጠን ያልሽ ልጅ ብትሆኚ ስትይ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው? አልኳት
ቀበጣጠረች•••
"ማለቴ ጭምት ነሽ ፣ሰው አትቀርቢም
ከሰው ጋር መቀራረብ መተዋወቁ ጥሩ ነው: ብቸኝነት አታብዢ ለማለት ፈልጌ ነው
"ለሰው መድሀኒቱ ሰው ነው"ሲባል አልሰማሽም?"
አባባሉ እውነት ነው ግን የዚህ አባባል ተቃራኒውም እውነት እንደሆነ አትርሺ! ስላት
" ማለት?" አለችኝ
የሰው ትልቁ ጠላቱም ሰው መሆኑን ነዋ ።
ለማንኛውም ቃልሽን እምታከብሪ ሰው ከሆንሽ ብትመጪ ደስ ይለኛል ብላ እየተመናቀረች ወጥታ ሄደች።
ሁለቱ ጓደኜቼ ስላናደድኳት ሲከፋቸው አየሁ። ከዛ ቡሀላ ዝም አልኩ።
ፀጉር ቤት እንሂድ ሲሉ ሄድኩ።
ልብስ ከገዟቸው አዳዲሶቹ ልብሶች መሀል በነሱ ምርጫ ልበሽ ሲሉኝ ለበስኩ ።
አስር ሰአት አከባቢ ከግቢ እንውጣ ሲሉኝ
ወጣሁ ።
ትንሽ እንደሄድን ግን ወዴት እየሄድን እንደሆነ ጠየኩ••
"መሲ ቤት ትንሽ እናመሽና ከዛ እንወጣለን"
አሉ። መሲ የግቢ ተማሪ ሆና የምን ቤት?
"እንዴ እሷኮ ካፌም አትጠቀምም ግቢም አትኖርም ውጪ ተከራይታ ነው እምትኖረው " አሉኝ እየተጋገዙ ።
ከግቢ በር እስከ ሰይዶ ሄድንና ከሰይዶ እስከ አሸዋ የሚሄድ ሌላ ፎርስ ይዘን ከዚራ ጋ እንደደረስን ወራጅ ወራጅ አሉ ተራ በተራ።
አንድ ሰርቢስ ያለው ድሮ እንደተሰራ አሰራሩ የሚመሰክር ትልቅ ግቢ ውስጥ ገባን።
መሲ ከሰርቢሶቹ አንዷን ይዛለች።
ከዛ ቡሀላማ ጦጣ ታውቃለህ ጦጣ ሆንኩልህ በቃ ምን አለፋህ
የመሲ ቤት ውስጡ በጭራሽ የተማሪ ቤት አይመስልም የተሟላ ነው በዛ ላይ እስከ ማታ ድረስ ከጫት ጀምሮ እስከ ሺሻ ታዛቢ ልትሆኚ ነው እንዴ የመጣሽው እንቺ ሞክሪ እያሉ እርስ በርስ እየተቀባበሉ ሲፈጩና ሲምጉት ዋሉ እሷን አላውቃትም በትንሹም ቢሆን የማውቃቸው ጋደኛቼ ግን እንዲህ ለመለወጥ የፈጀባቸው ግዜ ምን ያህል አጭር እንደሆነ ሳስበው ምን እንዳስነካቻቸው ግራ ገባኝ ።
ወሬያቸው ሁሉ እንቆቅልሽ ሆነብኝ።
በኔ በግዜ እንውጣ ውትወታ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ አንተ ያገኘከኝ ቦታ ላይ ወዳለው ሆቴል ነበር የገባነው።
ጓደኛቼ ሁኔታቸው ምንም አልጥምሽ አለኝ በኮድ ይነጋገራሉ ፣ በዛ ላይ ሰላም የማይሉት የማይጠመጠሙበት የለም ደሞ በየደቂቃው ልዩነት ስልክ ይደወልላቸዋል የሚያናግሩት ካጠገቤ ዘወር እያሉ ነው ። ጨነቀኝ ።
ላለመጨቃጨቅ ስል አንድ ቢራ ያዝኩ።
ትንሽ እንደቆየን በቃ ቤት እንቀይር ሲሉ ቆሌዬ ተገፈፈ ገና ከዚህ ቡሀላ ሌላ ቤት ካጠገባቸው እሩጭ እሩጭ አለኝ።
ሌላ ጭፈራ ቤት ሄደን ብዙም ሳንቆይ ረዱ ቅድም የነበርንበት ሆቴል ስልኬን ጥየው መጣሁ ብላ ጮኸች ።
ከቲጂ ጋር ተያይዘው ሮጡ ። እኔ ከሷ ጋር እንደተፋጠጥኩ እነሱ በሄዱ በሰከንዶች ውስጥ አንድ ሰውዬ ካያት ረጅም ግዜ የሆነው ይመስል መሲ ላይ እየጬኸ ተጠመጠመባት።
ሰላም ብሏት የሚሄድ መስሎኝ ነበር። ግን እዛው እኛው ጋር ቁጭ ብሎ ውስኪ በማለት መጠጥ አዘዘ።
ፈራሁ ። ሽንቴ መጣ። ሸንቼ እንደተመለስኩ።
"ተጫወቺ እንጂ አንቺ ቆንጆ ምንድን ነው ዝምታ አበዛሽኮ? አለኝ ሰውየው።
ቀጠል አርጋ•••
"ተዋወቂው አሌክስ ይባላል " አለችኝ
ፈጠን ብሎ "አሌክስ" አለና እጁን ዘረጋ
ኤደን አልኩና እጄን ሰጠሁት ። ጨበጠኝ ። ትንሽ አቆይቶ ሲለቀኝ አሁንም ሽንቴ መጣ ።
ተነስቼ ወደ ሽንት ቤት ሄድኩ።
ከጀርባዬ የሆነ ሰው በፍጥነት ሲከተለኝ ይታወቀኛል።
ልጅ የክፍላችን ተማሪ ነው። ግን አንግባባም ሰላምም አንባባልም። ባጋጣሚ እዛ እየተዝናና ነበረ ለካ።
ድንገት ሳላየው እሱ አይቶኝ ነው መሰለኝ ተከተለኝና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ቀጥታ •••
"እቺ አስተኳሽ አንቺንም አገኘችሽ!" አለኝ ።
አልገባኝም ማነች እሷ? አልኩት
"ብዙ ግዜ እምናያት ከሁለቱ ጓደኛሽ ጋር ነበር እነሱን አስበልታ ከስንቱ ተቀባብላለች አሁን ደሞ አንቺን ልታስበላሽ ነው?"
በፈጠረህ ምን እያልክ እንደሆነ በሚገባኝ አማርኛ ንገረኝ አልኩት።
ይበልጥ ወደኔ ጠጋ አለና •••
"እሄውልሽ እኔም አንቺም ወደዚህ ግቢ እኩል ነው የመጣነው ስለሷ የነገረኝ ድሮ ከታላቅ ወንድሜጋ ጋደኛ የነበረ እዚሁ ግቢ የሚማር የሶስተኛ አመት ተማሪነው።
አብራሽ ያለችው ልጅ የግቢ ተማሪዎችን በተለይ ፍሬሾቹን ለዚህ ሀገር ወንዶች በማቀባበል ቢዝነስ የምትሰራ አደገኛ ሴት ነች።
በርግጠኝነት አንቺንም ልታቀባብልሽ ነው ያጠመደችሽ ሞባይሏን ብትቀበያት እና ብታይው ለገበያ ልታቀርብሽ አንቺ ሳታያት ያነሳችሽ ብዙ ፎቶ አለ
ያንን ፎቶሽን ያየ ሰው እቺን ልጅ ካስበላሽኝ እሄን ያክል እሰጥሻለሁ ይላታል አለቀ ተሟሙታ ታጠምድሻለች !
አንዴ ከግቢ በሆነ መንገድ አብረሻት ወጥተሽ እምትፈልገው ቦታ ከደረሽላት ቡሀላ አለቀ ከተስማማሽ በፀባይ ካልተስማማሽ ደሞ በግድም ቢሆን ለእርድ ታቀርብሻለች !
ቢዝነሱ ስለጣማት ሆን ብላ ሶስተኛ አመት ላይ አንዳንድ ኮርስ እያፈላች እዚሁ ግቢ ውስጥ አምስት አመት ሆናታል !
ከየክፍለ ሀገሩ እዚህ ደርሷቸው የሚመጡ ስንት አበባዎችን እንዳስቀጠፈች ብትሰሚ እንኳን እንደዚህ አጠገባ ልትቀመጪ ከሩቁ ስታያት ትሸሻት ነበር!
ስንቶቹ ሳያውቋት አስበልታቸዋለች አንቺም ሳታውቂያት አብረሻት እንደመጣሽ ስለገባኝ ነው የነገርኩሽ
እኔ እንደነገርኩሽ እንዳትነግሪያት ዱሩዬ ገዝታ ታስቀጠቅጠኛለች !!"
ብሎኝ ካጠገቤ እብስ አለ ።
እኔ ግን እዛው በቆምኩበት ዞረብኝ ።እንደምንም ጠጋ አልኩና
ሳያት እምጠጣው ቢራ ውስጥ የሆነ ነገር ስትጨምር
👍1
​​የተመ​​ለከትኩ መሰለኝ ጭውውው አለብኝ ••••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#መንገድ_እንይ

ወደፊት ስንሄድ...
መንገዳችን ደሞ፤ወደ ኋላ ይሄዳል
መድረሻ ብናጣም
መንገዱ ርቆናል
ወደ ወጣንበት ፥ መመለስ ይከብዳል።
በየ መንገዱ ላይ ...
እየተጠላለፍን ፥ እየተገፋፋን
ወደ ፊት ስንጎዝ
መንገድ ወደኋላ ፥ ተጉዞ ሲያለፋን
“እግር እንይ" ብለን
እግር እግር ስናይ : መንገድ እንዳይጠፋን
እስቲ መንገድ እንይ!
እግሮችን እያየን ፥ መከተሉን እንተው
መንገድ ወደ ኋላ
እየሔደብን ነው
ወደ ፊት እየሔድን ፥ የምንጎተተው፡፡
እስቲ መንገድ እንይ!
የሚከተሉ አይኖች ፥ ከእግሮች ይነቀሉ
ትክክል መንገድ ላይ
ትክክል ያልሆኑ ፣ እርምጃዎች አሉ።
​​#ልጩህበት!!


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰትበ_ጥላሁን

ስንቶቹ ሳያውቋት አስበልታቸዋለች አንቺም ሳታውቂያት አብረሻት እንደመጣሽ ስለገባኝ ነው የነገርኩሽ
እኔ እንደነገርኩሽ እንዳትነግሪያት ዱርዬ ገዝታ ታስቀጠቅጠኛለች !!"
ብሎኝ ካጠገቤ እብስ አለ ።

እኔ ግን እዛው በቆምኩበት ዞረብኝ ጭውውውው አለብኝ ••••
•••
ለዚህ አብሯት ላለው ነው ማለት ነው እኔን ያጠመደችለት አልኩ እያየሁዋቸው
ሰውየውን እኮ ብታየው ምን እንደሚያህል! ማጅራቱ ላይ ያለው ስጋ ለብቻው ቢመዘን ከኔ ኪሎ እኩል ይሆናል!"
ስትለኝ ከመመሰጤ የተነሳ ሁለመናዬ እንቅስቃሴ አቁሞ ትንፋሼን አጥፍቼ ሳዳምጥ ከነበርኩበት ሁኔታ ውስጥ አውጥታ አሳቀችኝ።

አቦ እሄ ሁሉ ነገር ተፈጥሮ ትቀልጃለሽ አደል በይ አሁን ቀጥይ አልኳት
"ለመሆኑ ስምህ ማነው? " ድንገተኛ ጥያቄ ።
እስካሁን ስሜን አለማወቋ ሳይሆን የጠየቀችበት ሁኔታ እያሳቀኝ
ዳኒ እባላለሁ ዳንኤል አልኳት።
የሷን በወሬዋ መሀል ስለነገረችኝ መጠየቅ ሳያስፈልገኝ
በናትሽ ኤዱ ከዛ ቡሀላ ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ ቀጥያ አልኳት
ዘወር ብላ ወደ ግቢው ስትመለከት •••
አቦ ተይና እንግዲህ ድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ እንደሆነ አጥር የለው ምንድን ነው ወደዛ እምታይው
የማጅራቱ ስጋ ከኔ ክብደት ጋር እኩል ይሆናል እሚለው ጋር ነው የቆምሽው ስላት ፈገግ ብላ•••
"እውነቴን እኮ ነው በጣም ግዙፍ ሰው ነው!
እኔን ከዛ ሳሎን ቤት ከሚያህል ሱውዬ ጋር አንሶላ ልታጋፍፍ ማሰቧ የጭካኔዋን ልክ ያሳያል !
ብታየው ሲተነፍስ እራሱ ያስፈራል የታፈነ ነው እሚመስለው እኔን ደሞ እንደምታየኝ ቀጭን ነኝ ብብቱ ስር ደብቆኝ ወደ ፈለገበት ቢወስደኝ እራሱ ማን ያየዋል?"
አቦ እቺ ልጅ እኔ እንዴት እንዳመለጠች ለመስማት ጆሮዬ ቆሟል እሷ ትቀልዳለች ስል ሳቅ ብላ
"በገባንበት በር ቀጥ ብዬ ብወጣ ያዩኛል።
ግቢውን ካወከው የተወሰነ ቦታ ጭላንጭል ብርሀን የተወሰነ ቦታ ደግሞ ጭለማ ነው ስለሷ የነገረኝ ልጅ ጥግ ላይ ወዳለችው ጎጆ ቤት ውስጥ ነው የገባው ጎጆ ቤቷ ደግሞ እየጠጡ በሚጨፍሩ ሰዎች ጢም ብላለች ከመሀል ልጁን ማየት አልቻልኩም።
ሞባይል ረሳን ብለው የሄዱት ጓደኛቼ እስኪመለሱ ሽንት ቤት ገብቼ ከውስጥ ዘጋሁ።
ሽንት ቤት ሆኜ ልጁ ያለኝ ነገርና ቀን
እቺው መሰረት ቤት ሆነን ስልክ ሲደወልላት ምንም እንኳን እምታናግረው ከቤት እየወጣች ቢሆንም ከመራቋ በፊት ስታነሳው በንግግሯ መሀል አልፎ አልፎ ጆሮዬ ጥልቅ ሲሉ የነበሩ ቃላቶቿ አቃጨሉብኝ
በተለይ ደግሞ "እጄ ላይ አዲስ እቃ የለም " ያለችው ነገር
እቃዎቹ እኛ ነን ማለት ነው ።
እንደ እቃ ልትሸጠኝ እያመቻቸችኝ " እሄን ድርቅናሽን ተይና ፈጠን ያልሽ ሁኚ "
ማለቷን ሳስበው ነደድኩ መፍጠን እንደጓደኛቼ ከሆነ ዘላለሜን ላዝግም !
መፍጠን መበላሸት ፣ መፍጠን ያሳደጉኝን ወላጆቼን መርሳት እና ድካማቸውን መና ማስቀረት ከሆነ ባፍንጫዬ ይውጣ!
መፍጠን በተስፏ ደረሰች ደረሰች ተምራ ለሀገሯም ለኔም የምትጠቅም ዜጋ ሆነችልኝ እያለች በጉጉት የምትጠብቀኝን እናቴን እና ሀገሬን በማይሆን ተግባር ውስጥ ገብቶ ባጭሩ በመቀጨት ተስፋዋን ማጨለም ከሆነ •
በዚህ መልኩ ፈጥኜ ፈጣን ከምባል ፋራ፣ ፈዛዛ፣ ደንዛዛ፣ ገገማ ፣ሰገጤ ልባል !!
በሌሎቹ ተሳክቶልሻል በኔ ግን አይሳካልሽም መሲ ሀሳብሽ እሚሳካው ከገደልሽኝ ብቻ ነው እያልኩ እየፎከርኩ ከሽንት ቤት ስወጣ አሁንም ጋደኛቼ አልመጡም ። ሞባይል ጠፋ ብለው የሄዱት ሆን ብለው እኔን ለዛች አውሬ ጥለው ለመሄድ ሲሉ የፈጠሩት ምክንያት እንደሆነ የገባኝ ያኔ ነው።
ግራ ገብቶኝ ጥግ ይዤ እንደቆምኩ መሲ ምነው ቆየች ብላ ነው መሰለኝ ወደ ጀርባዋ ስትገላመጥ አየሁዋት ለሷ ግን አልታያትም ተነስታ ልትፈልገኝ ወደ ሽንት ቤት ብትሄድ እሄን ዝፍዝፍ ሸውጄ መውጣት አያቅተኝም በናትሽ ተነሽና ፈልጊኝ እያልኩ በመሀል ከጎጆ ቤቷ መሲና ሰውየው ወዳሉበት ሶስት ወጣቶች እየተጨቃጨቁና እየተጓተቱ መጡና አጠገባቸው እንደደረሱ ቅልጥ ያለ ፀብ ውስጥ ገቡ ደነገጥኩ ።
ትርምስምስ አለ በዚህ መሀል ልውጣ ?ታየኝ ይሆን?እያልኩ ስወዛገብ የቅዱሙ ልጅ ድንገት እጄን አፈፍ አርጎ
"ትፈዧለሽ እንዴ ፀቡ እኮ ድራማ ነው ውስጥ ሆኜ ስከታተልሽ ነበር ሆን ብዬ ነው ጀለሶቼ እዛጋ ሄደው ወከባ እንዲፈጥሩ ያመቻቸሁዋቸው
ከሷ ጋር ፊት ለፊት ተቃብቼ አንቺን ማስመለጥ ስላልፈለኩ ነው ልጅቷ ብዙ ኔት ወርክ ስላላት ሌላ ግዜ እንዳታስጠባኝ ብዬ ነው እንጂ እኛ አራት ሆነን ያንን አብሯት ያለውን ዘረጦ ፈርተነው እንዳይመስልሽ "
እያዋከበ ይዞኝ ከወጣ ቡሀላ
" እዛጋ ባጃጅ ታገኛለሽ ቆይ ትንሽ ላስጠጋሽ" እያለ ቁልቁል ወረድን ። እሱ እሄን ሁሉ ሲያወራ ስለደነገጥኩ ነው መሰለኝ ትንፍሽ አላልኩም በቃ ተመለስ ብዬው ቆም እንዳልን ከጀርባው ከሆቴሉ እየተምዘገዘገ የሚመጣውን ሰው ተመለከትኩና
በቆምኩበት በድን ሆንኩ ሁኔታዬ ግራ ገብቶት ሲያፈጥብኝ በጄ ወደሚመጣው ሰው እያመለከትኩ እንደምንም
ወይኔ ተከትለውን መጡ መሰለኝ አልኩት ደንግጦ ዞረ..

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1