አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስር


የካፑሌ ፡ ሚስት (የዡልዬት እናት)
ወዴት ፡ ነው ፡ ያለሽው ፡ ልጄ ፡ ተነሣሽ ፡ ወይ ?

#ዡልዬት
ይኸው ፡ ተነሣሁኝ ፡ ምነው ፡ እናቴ ሆይ ?
(ለብቻዋ ፡ ቀስ ብላ)
ምን ፡ ነካት ፡ እናቴ ፡ እንዲህ ፡ ጧት ፡ ተነሥታ ፈልጋኝ አታውቅም በማለዳ መጥታ ።
(የካፑሌ ሚስት ' ወደልጅዋ፡ወደ፡ዡልዬት መኝታ' ቤት፡ገባች

#የካፑሌ_ሚስት
ዐፈር ፡ አስመሰለሽ ፡ የቲባልት ፡ ሐዘን ፡
ያስፈልጋል ፡ ልጄ ፡ ማሰብ ፡ ማመዛዘን '
እንባ ፡ ቢያፈሱለት ፡ ቢያለቅሱለት በጣም
ሰው ፡ አንዴ ከሞተ ተመልሶ ፡ አይመጣም
ሐዘን ፡ የሚያስረሳ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ወሬ
ይዤ ፡ ወዳንቺ ፡ ዘንድ ፡ መጥቻለሁ' ዛሬ "

#ዡልዬት
እናቴ ፡ ንገሪኝ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ያለ ፡ ነው ?

#የካፑሌ_ሚስት
በቲባልት ፡ መሞት ፡ በብዙ ፡ ያዘነው ፡
ልብሽ ፡ እንዲጽናና ፡ በጣም ፡ በማሰቡ ፡
መልካሙ ፡ አባትሽ ፡ አላረፈም ፡ ልቡ ፤
በዚሁ ፡ ምክንያት ፡ ሳይውልም ፡ ሳያድር ፡
ቈርጧል ለጥሩ ባል ኀሙስ አንቺን ሊድር
ባልሽ ፡ የሚሆነው ቆንዦ ነው ፡ ጌታ ሰው
በዘርም ፡ በገንዘብ ፡ ምንም ፡የማያንሰው !
እንዲያውም ፡ ገልጨ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ ፤
መልካሙ ፡ፓሪስ ፡ ነው ፡ ወጣት ፡ መኰንኑ

#ዡልዬት
እናቴ ፡ ሆይ ፡ምነው ፡ በፊት ፡ ሳንማከር ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ እንዲህ ያለ ፡ ነገር
አስቀድመን ፡ እኛ ፡ ተጫጭተን ፡ በደንቡ፡
ሳላውቀው ሳያውቀኝ ፡በፍጥነት ፡ ተጋቡ !
እንዴት ፡ ትላላችሁ ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ?
አሁንም ፡ በቶሎ ፡ ፈልጉለት ፡ መላ'
እኔ ፡ አልችልምና ፡ ለማግባት ፡ በቶሎ ፤
አባቴን 'ንገሪው ፡ እንደ ፡ ምንም ፡ ብሎ
ቃል ቢኖር ምናልባት ለፓሪስ የሰጠው
አንድ' ዘዴ ፡ ፈጥሮ ፡ ቶሎ ፡እንዲለውጠው

#የካፑሌ_ሚስት
አፍሽን ፡ አታጥፊ ፡ ምክንያት ፡ አታምጪ '
ያለቀ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ዐርፈሽ ፡ ተቀመጪ ።

#ዡልዬት
አድምጪኝ ፡ እናቴ ፡ እንግዲያውስ ፡ ስሚ
አባቴም ፡ አይልፋ ፡ አንቺም ፡ ኣትድከሚ'
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ መቼም ፡ቢሆን ደግሞ
እኔ ፡ አላገባም ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።

#የካፑሌ_ሚስት
አልገባም ፡ ጨርሼ ፡ እኔ ፡ በዚህ ፡ ጣጣ ፤
ንገሪው ፡ ላባትሽ ፡ ይኸው ፡ወዲህ ፡ መጣ

#ካፑሌ ፡ (ገባ)
ምነው ፡ ምን ሆናችሁ ? በይ ልመለስ ሄጄ
ታዲያስ ፡ ነገርሻት ፡ ወይ ነገሩን ፡ ለልጄ ?

#የካፑሌ_ሚስት
እኔ ፡ ከሷ'ጋራ ፡ አልችልም ፡ ክርክር ፤
ትችል ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡አስረዳት ፡ በምክር ።

#ካፑሌ
እስቲ ፡ እኮ ፡ ንገሪኝ ፡ ምንድነው ፡ ነገሩ ፡
አሁን ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ደርሶ ፡ ግርግሩ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ትችል ፡ ትመስላለህ አንተ ፡ ደግሞ ፡ ደርሶ
የምሥራች ፡ « እንቢ» ፡ ብላለች ፡ ጨርሶ ፡
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ ይልቁንም ፡ ደግሞ ፡
አላገባም ፡ አለች ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።

#ካፑሌ
እግራችንን ፡ ስማ ፡ እኛን ፡ አመስግና ፡
በትልቅ ፡ ደስታ ፡ መቀበል 'ቀረና ፡
እንቢ ፡ አለች ፡ ብትይኝ ጆሮዬም ፡ አይሰማ
እስቲ ፡ ልስማው ፡ እኔ ፡ ትናገረው ፡ ደግማ

#ዡልዬት
ለክፋት ፡ አይደለም ፡ አትቈጣ ፡ አባቴ ።

#ካፑሌ
እረግ ፡ የኛ ፡ ሕፃን ፡ ትንሿ ፡ ማሚቴ ፡
የማነሽ ፡ ለዛ ፡ ቢስ ፡ የማነሽ ፡ ወልጋዳ ፤
የማነሽ ፡ አመዳም ፡ የማነሽ ፡ ገዳዳ'
ባለወግ ፡ አድርገን እኛ ፡ ነን ያጠፋን ፡
ብታውቂው ፡ ባታውቂው ኧረ ምን ፡ አለፋን
በግድ፡ ነው ፡ እንጂ፡ በኅይል ፡ የምንድር ፡
መች ፡ ያስፈልግና ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ንግግር
ነገ ፡ በማለዳ ፡ ተዘጋጅተሽ ፡ ውጪ ፣
ከተክሊሉ ፡ ቦታ ፡ ዐውቀሽ ' እንድትመጪ,
ታዛዤ ፡ ነሽና ፡ የወለድኩሽ ፡ ልጄ ፣
እኔ ፡ እድርሻለሁ ፡ በኀይል' አስገድጄ ፤
ለወግ ፡ መጠየቄ ፡ ቅብጠት ፡ነው ፡ አብጄ
እስከዚያ ፡ ድረስ ፡ ግን ፡ በፊቴ ፡ አትለፊ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ ካጠገቤ ፡ ጥፊ ።

#ዡልዬት
ነገሩን ፡ ላስረዳህ ፡ አባቴ ፡ አድምጠኝ ፤
ጋብቻው ፡ ፈጠነ ፡ ጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ስጠኝ

#ካፑሌ
ነገርሽ እሬት ነው ፡ መሪር ነው ፡ ኮምጣጣ
ካፍሽ ፡ ካንደበትሽ ፡ አንድ ፡ቃል፡ አይውጣ'
ሴት ልጅ እንቢ፡ብትል፡አለው አንድ አገባብ
መች ተሠርቶ ያውቃል እንዲህ፡ያለ ጥጋብ
ዘሩ ፡ የታወቀ ነዉ መልኩ ፡ የሚያኰራ ፡
ገንዘብ ፡ የተረፈው ፡ ስሙ ፡ የተጠራ፡
ደኅና ፡ ባል ፡ ፈልጎ ፡ በስንት ፡ መከራ፡
አባቷ ፡ ሲያመጣ ፡ ወዲያ ፡ ወዲህ ፡ ዞሮ '
ከቤት ፡ ተወዝፋ ፡ የኛ ፡ ሴት ፡ ወይዘሮ ፡
እኔ ፡ ባል ፡ አልሻም ፡ ትላለች ፡ ሞጋጌ ፤
መካን ፡ ሰው ፡ ይሻላል ከመውለድ ፡ ባለጌ
ጥኀጋብሽ ፡ ነው ፡ እኮ ደሜን ፡ የሚያፈላው ፤
ምኑ ፡ ነው ፡ እባክሽ ፡ፓሪስ ፡ የሚጠላው ?
ያለባል ፡ ለመኖር ፡ ከሆንሽ ፡
የምትወጂ ፡
ምን ፡ ቸገረኝ፡ እኔ ፡ ወደ ፡ ገዳም ፡ሂጂ ፡
ነገር ፡ ግን ፡ ከሆነ ፡ ማግባትሽ ፡ የማይቀር ፡
የመረጥኩልሽን ፡ ይገባሻል ፡ ማፍቀር ፡
ያላንድ ፡ ክርክር ፡ ያላንድ ፡ ቅሬታ ፡
ፈቃዴን ፡ መቀበል ፡ አለብሽ ፡ ግዴታ ።
የምትይ ፡ ከሆነ ፡ የኔን ፡ ፈቃድ ፡ እንቢ ፡
ከዛሬ ፡ ጀምረሽ ፡ ሂጂ ፡ ገደል ፡ ግቢ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ በዚህ ፡ በኔ ፡ ግቢ ።
የካፑሌ ፡ ሚስት ።
ቀስ ፡ ብሎ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አባት ፡ ከመከረ ፡
አንተም ፡ አበዛኸው ፡ ነገርህ ፡ ከረረ ።
ካፑሌ ።
አትግቢ ፡ ፈጽሞ ፡ አንቺ ፡ በኔ ፡ ሥራ ፤
ሂጂ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፡ ከሴቶቹ ፡ ጋራ ፡
ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ ባሳብ ፡ ሌሊቱን ፡ በሕልሜ ፡
ባል ፡ ስፈልግላት ፡ በመኖር ፡ ደክሜ ፡
በስንት 'ዐይነት ፡ ዘዴ ፡ እኔ ፡ ተጣጥሬ፡ .
እግዚአብሔር ረድቶኝ ፡ ይኸውና ፡ ዛሬ ፡
የሚሆን ፡ ሰው ፡ ባገኝ ፡ ጨዋ ፡ባለገንዘብ፡
እሜቴ ፡ ፈጠሩ ፡ ሠላሳ ፡ ሺሕ፡ ሰበብ ።
ስሚኝ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ፤
እሱን ፡ ካላገባሽ ፡ ታዘቢኝ ፡ በውኑ
የትም ፡ ትሄጃለሽ ፡ አብርሬሽ፡ ከቤቴ፤
እርሜን ፡ አወጣለሁ ፡ ቆርጬሽ ፡ ካንጀቴ
ልጅና ፡ አባት ፡ ሆነን ፡ መኖራችን ፡ ቀርቶ ፡
ክጄሽ ፡ ትሄጃለሽ ፡ አልምርሽም ፡ ከቶ ፡
ስለዚህ ፡ አስቢ፡ ከልብሽ ፡ ምከሪ፤
የሚከተለውን ፡ ተመልክተሽ ፡ ፍሪ'
ካሁኑ ፡ ጀምረሽ ፡ በነገሩ፡ ሥጊ፤
ቃሌ ፡ አይታጠፍም ፡ ኋላ ፡ ልብ ፡ አድርጊ
(ካፑሌ "ከቤት " ወጥቶ ሄደ)

#ዡልዬት
እባክሽ ፡ እናቴ ፡ ለልጅሽ ፡ እዘኚ፤
ባይሆን ፡እንኳን ፡ አንቺ ፡ ከኔ ፡ ወገን ፡ ሁኚ'
ቀኑ ፡ ረዘም ፡ ይበል ጥቂት ፡ ጊዜ ስጡኝ፤
አሳቤን ፡ ሳታውቁ ፡ በከንቱ ፡ አትቁጡኝ ።

ግዴታ፡ ካልሆነ' በጣም ' ካልቸረኝ፡
እንቢ ፡ አልልምና ፡ ምክንያት ፡ ካልኖረኝ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ዕዳሽን ፡ በጨርቅሽ ፡ እንደምትፈልጊ '
አንቺ ፡ እንደ ፡ ፈቃድሽ 'እንዳሻሽ አድርጊ ።
(እናቷም' ወጥታ ሄደች)

#ዡልዬት
ርጂኝ ፡ አንቺ ፡ እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡

#ሞግዚቴ
ምስጢር፡ ተካፋዬ፡አንቺ፡ነሽ ፡እናቴ '
የኛን ተክሊል ማንም አይችልም፡ሊያፈርሰው፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ድብቅ ፡ ነው አያውቅም፡ማንም፡ሰው፡
እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡ ዘዴ ፡ አታጭምና ፤
ጨነቀኝ ፡ ጠበበኝ'አገኘኝ ፡ ፈተና ።

#ሞግዚት
ቃሌን ፡ ብትሰሚ ፡ ተራዬን ፡ ልናገር ፤
ሮሜዎ ፡ ሰው ፡ ገድሎ ፡ ተሰደደ ፡ ካገር፡
ልትኖሩ ፡ ከሆነ ፡ ለብቻ ፡ ለብቻ ፡
በዚሁ ፡ ይፈርሳል ፡ የናንተ ፡ ጋብቻ ፡
በዚሁ ፡ ላይ ፡ ደግሞ ፡ አባትሽ ፡ ላባቱ
👍1
ቂመኛ ፡ ነውና 'ደመኛ ፡ ጠላቱ ፤
ዕርቅ ፡ይኖራል ፡ ማለት ፡ መጓጓት ፡ ነው ፡ ከንቱ ።
ስለዚህ ፡ ፓሪስን ፡ እሺ ፡ ብለሽ ፡ አግቢ ፤
ሮሜዎን ፡ በልብሽ ፡ በቃሽ ፡ አታስቢ '
ደግሞስ ፡ ምንና፡ ምን ፡ እነዚህ ፡ ሁለቱ ፤
ፓሪስ ፡ የላቀ ፡ ነው ፡ በውበት ፡ በሀብቱ ፡
በዘር፡ በጌትነት'ይበልጣል' በሁሉ ፤
ደግሞስ ፡ ከዚህ ፡ በላይ፡ ሕግስ ፡ ቢሆን ፡
በድብቅ ፡ የሆነው ፡ አይረጋም ፡ተክሊሉ ።

#ዡልየት
እውነት ፡ ካንጀት ነው ወይ ፡ የምትናገሪ ?

#ሞግዚት
ከልቤ ፡ መሆኑን ፡ አትጠራጠሪ ።

#ዡልዬት
መልካም ፡ ነው በይ ሄደሽ ንገሪያት ለናቴ
መሄዴ ፡ ነውና ፡ በፍጥነት ፡ መውጣቴ ፡
ወደ ፡ አባ ፡ ሎራ ፡ ዘንድ በፍጥነት ፡ ደርሼ
እመጣለሁ፡በያት፡አሁን፡ተመልሼ ። (ሞግዚት ' ሄደች) "

(#ዡልዬት ብቻዋን) •
ለማ ፡ ልናገረው ፡ ምስጢሬን ፡ ገልጩ፡
ወደ ፡ አባ ፡ ሎራ ፡ ዘንድ ፡ ልሂድ ፡ እንጂ ፡
ከካህናቶች ፡ ዘንድ ፡ ቢበጅም ፡ ቢከፋ፡
የነፍስ ፡ መድኀኒት፡ ምን ጊዜም ፡ አይጠፋ

💫ይቀጥላል💫
#በጠራ_ጨረቃ

በጠራ፡ ጨረቃ ፡ በእኩላ ፡ ሌሊት ፡
ዓይኖቿ ፡ እያበሩ ፡እንደ ፡ ከዋክብት ፡
«ሳማት ፡ ሳማት » አሉት ፡«ዕቀፍ፡ ዕቀፋት
አላወላወለም ፤ ወጣቱ ፡ ታዘዘ ፤
ወገቧን ፡ አንገቷን ፡ በእጅና ፡ እጁ ፡ ያዘ ፤
ከንፈሩ ፡ በረአድ ፡ ወደ ፡ አፏ፡ ተጠጋ ።

-~ምንም ፡ እንኳ፡ ጡቷ እንደሾህ ፡ ቢዋጋ
ጣቷ ፡ በመሆኑ ፡ የጉማሬ ፡ አለንጋ፤
ጆሮው ፡ ግንዱን ፡ ሰማው ፡ በጥፊ ፡ ሲናጋ ።
በጠራ ፡ ጨረቃ ፡ በእኩለ ፡ ሌሊት ፡
ዋ ፡ ጀማሪ ፡ መሆን ፤ ዋ ፡ ተማሪነት ፤
ዋ ትእዛዝ ፡ መፈጸም ፤ ዋ ፡ ምክር ፡ መስማት ።

🔘መንግስቱ ለማ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ስምንት


#በክፍለማርያም

...ብርድ ልብሱን መሬት ላይ ጣለዉ
ጌታቸዉ የለበሰዉን ሱሪ እያወለቀ ከእንቅልፏ ያልነቃችዉን አይምሮዋ በትክክል እያሰበ ያልሆነዉ ምስኪኗ በሽተኛዋ ቤዛዊት ላይ ተከመረባት
የቤዛዊት አይኖች በድንጋጤ አብርተዉ መቁለጭለጭ ጀመረች የት እንዳለች ለማስታወስ አልቻለችም እላይዋ ላይ የተከመረ ነገር እንዳለ ለማዉረድ እየታገለች ነበር
አቅም ግን እያነሳት ሲመጣ ዝልፍልፍ ብላ ተሸንፋ የጌታቸዉ መጫወቻ ሆነች።

ቀሚሷን አዉልቆ የዉስጥ ሱሪዋን እያወለቀዉ መታገሏን ስላቆመች
"ምን አስባ ነዉ"
ብሎ ለአፍታ ተመለከታት
አንገቷ ወደ ቀኝ ዘመም ብሎ በትራስ ተደግፎ ከአፏ ምራቅ ይወርዳል አይኗቿ እንደቀሉ ናቸዉ ህመሟ ብሶባታል እሷ አደለችም ስትታይ አንጀት ትበላለች
እላይዋ ላይ የተከመረዉ ሰዉ ግን ስሜቱ አሸንፎት ህመሟ አይታየዉም ቢታየዉም ምንም አልመሰለዉም የእሱንም የዉስጥ ሱሪ ቀስ ብሎ አዉልቆት ተገናኛት እላይዋ ላይ መጨፈር ጀመረ
የቤዛዊት አይኖች ግን ካረጀዉ ኮርኒስ ዉስጥ የሚፈሩት አይጥ መኖር አለመኖሩን ፈዘዉ እያዩ ይመራመራሉ።

ፍፁም በጠዋት ቤዛዊት ያመጣችለትን ምግብ ሊበላ ሲከፍተዉ እስረኞች አብረዉት ሊበሉ ከበቡት
ከእነሱም መሀል ፎጣ አናቱ ላይ የማይለየዉ ማስረሻ ሁሉ ነገር አብቅቷል የትላንቱ ፀብ ተረስቷል ብሎ ለመጉረስ እጁን ዘረጋ ነገር ግን በዘረጋዉ እጁ እንጀራ ጠቅልሎ ወደ አፉ እያስጠጋ የፍፁም ቡጢ አርፎበት እጁ ላይ የነበረዉ ምግብ ተበታተነ ማስረሻ ግን ለመማታት እጁን አልዘረጋም የተቀጡት ቅጣት አስተምሮት ነበር
ፍፁም አንድ ቡጢ ሰንዝሮ አልበቃዉም ማስረሻ ሆድ ላይ ተቀመጠ
በተመሳሳይ ስዓት ቤዛዊት ገላ ላይ ጌታቸዉ ተቀምጧባት ነበር
ፍፁም እየደጋገመ ቦክስ መሰንዘር ማስረሻን ማድማት ጀመረ
በዛዉ ሰዐት የታመመችዋ ቤዛዊት ምስኪን ልብ እየደማ ነበር
ፍፁምን እስረኞች ተረባርበዉ ከማስረሻ ሰዉነት ላይ አነሱት ማስረሻ በደም ተላዉሶ እያቃሰተ ነዉ
ፖሊሶች እየተሯሯጡ መጡ በአሁኑ ለፍፁም አላዘኑለትም እያዳፉ እየገፈታተሩ ከግቢዉ ይዘዉት ወጥተዉ ለብቻ ሰዉ የሚታሰርበት ጨለማ እና አስፈሪ ጠባብ ክፍል ዉስጥ ወርዉረዉ ቆለፉበት
ፍፁም እራስህን አጥፋ አጥፋ የሚል ጥሪ ጭንቅላቱ ዉስጥ ሲያቃጭልበት እራሱን እንዴት ማጥፋት እንዳለበት እያሰበ
"መሞት አለብኝ"
ሲል ደመደመ በሀሳብ ዉስጥ ሆኖ እጆቹን ወደ ኪሱ ሲከት የእሱን እና የቤዛዊትን ከመጀመርያው ጀምሮ የያዘዉን ወረቀት ነካዉ አዉጥቶ በደበዘዘ ብርሀን ለማንበብ ሞከረ
ወደ ቤቴ እያነከስኩ ስገባ አልገዬ ላይ ተኝታ ጠበቀችኝ ሳያት ደስ አለኝ አጠገቧ እንዳልቀሰቅሳት ተጠንቅቄ ተኛሁ ነገር ግን ነቅታ በአይኖቿ እያየችኝ የዛን ለት ክብሯን ሴትነቷንም ሰጠችኝ.....
ይሄንን አያነበበ የመሞት ሀሳቡ ከልቦናዉ ተገፎ እላዩ ላይ ለዉጦት የነበረዉ የተለየ ፀባይ ጠፍቷ የድሮዉ ፍፁም እየሆነ
"ፈጣሪ እስኪወስደኝ አልተዋትም "
ሲል በልቡ ቃል ገባ

ጌታቸዉ በጀብደኝነት የቤዛዊትን እርቃን ገላ እየዳሰሰ ከላይዋ ላይ ተነስቶ ወደ መሬት ወርዷ በድጋሜ ተመለከታት ልብሷን እንኳን ለመልበስ አልሞከረችም አይኖቿ ኮርኒሱ ላይ ተተክለዉ ደርቃ ቀርታለች እየተገላመጠ ሱሪዉን ለባብሶ ወደ ዉጪ ወጣ
ከደቂቃወች በኋላ ሲመለስ ቤዛዊት ሲወጣ እንዳያት አሁንም ደርቃለች ደስ አለዉ የሰራዉ ክፉ ስራ እነደማይጋለጥበት እረግጠኛ ሆነ
በመታመሟ ሊያዝንላት ሲገባ ተደሰተ በታመመች ልክና እራሷን ባልቻለች ወቅት ሁሉ የእሱ ሀጥያት ተደብቆ የሚቆይ የማይታወቅበት ስለመሰለዉ ተደሰተ
እርቃን ገላዋ አሁንም የተረገመ አይኑ ዉስጥ ስለገቡ እየተቻኮለ ሀጥያቱን ደገመዉ ሲጨርስ ቤዛዊትን ልብሷን አለባብሶ ከላይ ብርድ ልብስ ደርቦላት ምንም እንዳልተፈጠረ ወጥቶ ሊሄድ ሲል እማማ ስንቅነሽ ደረሱ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2👏1
#ለሟች_ብር_መዝከሪያ

ሰማዓት ለሆኑ
ጀብዱ ለፈጸሙ
ብር እረሽናችሁ
ሃውልት ስታቆሙ
እኔም ሃውልት አቆምኩ
ለሟች ብር በስሙ
ድንጋይ ተፈጭቶበት
ድንጋይ ተቦክቶበት
ድንጋይ ሆኖ እንዲቆም
ለፈሰሰ ደሙ፡፡
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ዘጠኝ


#በክፍለማርያም

....እማማ ስንቅነሽ ደረሱበት
ቤዛዊት እዉነተኛዉ አለም ላይ አልነበረችም ህመሟ በሰራላት አለም ዉስጥ ሰምጣ ጠፍታለች አካሏ አልጋዉ ላይ ይጋደም እንጂ አይምሮዋ በትክክል እየሰራ አይደለም
አይኖቿ ኮሮኒሱ ላይ ተተክለዉ የምታስበው ባይታወቅም ተክዛ እሩቅ ሄዳለች የደፈረሱት አይኖቿ ግን መደፈሯን ያወቁ የጠረጠሩ ይመስል ያልፈሰሱ እንባወች አቅርረዋል የተንጨባረረዉ ፀጉሯ ትራሱ ያስጠላዉ ይመስል ተመነቃቅሮ ይታያል።

እማማ ስንቅነሽ የሆነ ነገር እንደተፈጠረ የጠረጠሩት የልጃቸዉ ፊት ላይ የመደናገጥ የመቻኮል የመቅበዝበዝ ምልክት እንዳዩ ነው።
"ምን አረካት አንተ አዉሬ"
ሲሉ ልጃቸዉ ላይ ጮሁበት
"ምንም ምንም"
እያለ እናቱን ገፍቷቸዉ ሊወጣ ሲል ቤዛዊት ከተኛችበት አልጋ ተነስታ ስትቆም ሁለቱም ዞረዉ አዩዋት
ቤዛዊት በቆመችበት አይኖቿን ወደ መሬት ልካ የምትፈልገዉ ነገር ያለ ይመስል ዙርያዋን ስታስስ ቆይታ ጥግ ላይ ከድስት አናት ላይ የተቀመጠ ማማሰያ አንስታ ወደ ጌታቸዉ በፍጥነት ተጠግታ ጌታቸዉን መምታት ጀመረች።

ጌታቸዉ
"ምን መሆኗ ነዉ ይቺ እብድ"
እያለ እራሱን ለመከላከል ፊቱን በእጆቹ ሲከላከል ቆይቶ ቤዛዊትን በሀይለኛ ጥፊ መሬት ላይ ጣላት
እማማ ስንቅነሽ የድረሱልኝ ጩሀት መጮህ ጀመሩ
"ልጄን ገደላት ድረሱልኝ
ልጄን ገደላት"
ጌታቸዉ እየተንጎማለለ በፍጥነት ቤቱን ለቆ ወጣ የእማማ ስንቅነሽንም ጩሀት ሰምቶ የመጣ ማንም ሰዉ አልነበረም።
እንደ እማማ አይነት መልካም ልብ ሲኖርህ ለልጄ ለዘመዴ እያልክ አትወግንም ለእዉነት ብቻ ነዉ የምትቆመዉ።

ጌታቸዉ ከዛን ቀን በኋላ ወደ ቤቱ አልተመለሰም ምን አልባት አደጋ ደርሶበት ሊሆን ይችላል
አልያ ስራ አጊንቶ ቀንቶት ሌላ ቦታ እየኖረ ከሆነ እንኳን ጤነኛ አይምሮ ኖሮት ይኖራል ብሎ ማመን ይከብዳል።
እማማ ስንቅነሽ እንግዳ የሆነች በህይወት የሌለች የልጃቸውን አምሳል የምትመስል ምስኪን ልጅ ይዘዉ ተሰቃዩ በየፀበሉ ፈጣሪን እየለመኑ መንከራተት ቤዛዊትን ከጉያቸዉ ሳይነጥሉ የጎረሱትን እያጎረሷት የጠጡትን እያጠጧት አብረዋት ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ።
እማማ ስንቅነሽ ቤዛዊትን በጠዋት ፀበል ይዘዋት ሄደዉ ወደ ቤት ሲመለሱ ቤዛዊት አልጋ ላይ ተቀምጣ በራሷ አለም እየዋኘች እማማ ስንቅነሽም ከጎኗ ተቀምጠዉ በሀሳብ ጭልጥ አሉ።
የቤዛዊት ነገር እያሳሰባቸዉ ነዉ ትንሽ ለዉጥ ስላላዩባት ፈጣሪን ማማረር እየጀመሩ ነዉ በዛላይ የሚላስ የሚቀመስ ነገር ቤት ዉስጥ የለም እጃቸዉ ደርቋል የሚረዳቸዉ ሰዉም ጠፍቷል
ከሀሳባቸዉ ሲባንኑ ወደ መሶቡ አምርተዉ ሲከፍቱት ባዶ መሆኑን አረጋገጡ
"ምን አረኩህ ፈጣሪ"
እያሉ ሲዞሩ ከታመመችዋ ከቤዛዊት አይን ጋር ተገጣጠሙ
እንደድሮ ጤነኛ በነበረች ሰአት እንደምታያቸዉ አይነት አስተያየት ስታያቸዉ ፀበሉ ለዉጥ እንዳለዉ ጠርጥረዉ ፊታቸዉ ላይ ፈገግታ እየተነበበ
"ጨርሰህ ማርልኝ አይ እኔ ማማረር ብቻ ሆነ ኑሮዬ ተመስገን"
እያሉ ወደ ቤዛዊት ቀርበዉ በእጃቸዉ ፊቷን ደበስበስ እያረጓት
"እራበሽ አደል ሆዴ ገዝቼ መጣሁ"
አሉና እያዘገሙ ወጡ ነገር ግን መግዣ ብር እንደሌላቸዉ ልባቸዉ ያዉቃል ጎረቤት ሁሌ መለመን ማስቸገር ታክቷቸዋል የማያዉቁትን ሰዉ ለመለመን ድፍረቱ ባይኖራቸዉም
ቤዛዊትን በረሀብ አልገላት ነገር እኔስ ብሞትም እድሜዬን ጨርሻለሁ እያሉ ለልመና ወደ ጎዳና መጡ።
"የሰዉ ፊት ለካ ዱላ ነዉ "
ጥቂት እጃቸዉን ዘርግተዉ እንደቆሙ ነገር ግን በአይኑ ገርመም አርጎ እያየ የሚያልፋቸዉ እንጂ ሳንቲም የሚሰጣቸዉ ጠፍቶ ሲተክዙ አንዲት ሴት የታሰረ ምግብ በፌስታል እያደለች እሳቸዉ ጋር ደረሳ እጇን ስትዘረጋላቸዉ እያመሰገኑ ተቀብለዋት
ቤት ዉስጥ ብቻዋን ጥለዋት ወደ ወጡት ወደ ቤዛዊት አመሩ።
የቤቱን በር ገፋ አርገዉት እንደገቡ የቤዛዊት ቦርሳ ተከፍቶ ዉስጡ ያሉት እቃወች መሬት ላይ ተበታትነዉ አዩ ቤዛዊት ግን አልነበረችም።

💫ይቀጥላል....💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍4
#በዘመ_አርተፊሻል

ሎሚ ብወረውር
ስፖንጁን መታሁት
አሁን ነው የቆጨኝ
ምነው በመጠጥኩት።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
ሎሚ ብወረውር ፣ ወግ ደርሶኝ እንደሰው
አርቴፊሻል ጡቷ ፣ አንጥሮ መለሰው😁

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስር


#በክፍለማርያም

...ቤዛዊት ግን አልነበረችም
ምግቡን መሶብ ዉስጥ አስቀምጠዉ ጉዋሮ ለጎዋሮ ቤዛዊትን አሰሷት ወደ ዉጪም ወጥተዉ አላፊ አግዳሚዉን ቤዛዊትን ያየ በማለት ጠየቁ ነገር ግን ቤዛዊት የዉሀ ሽታ ስለሆነች ወደ ቤታቸዉ በረንዳ ተመልሰዉ ተቀምጠዉ በነጠላቸዉ እያበሱት ነገር ግን የሚፈስ ድምፅ የሌለዉ የእዉነት እንባ ማንባት ጀመሩ።

ማልቀሱ ብቻዉን ግን ትርጉም እንደሌለዉ ሲገባቸዉ ቤዛዊትን ፍለጋ አስበዉ ሲቆሙ ቤዛዊት ከዉጪ እየገባች አጠገባቸዉ ቆመች
ፊቷ ላይ ደስታ ይነበባል ደረቷ እንደማበጥ ብሏል እማማ ስንቅነሽን በፍቅር አይን እያየቻቸዉ ደረቷ ዉስጥ የደበቀችዉን ብዛት ያለዉ ብር አዉጥታ ደንግጠዉ የቋሙት እማማ ስንቅነሽ እጅ ላይ አስቀመጠችዉ።

(ከደቂቃወች በፊት)
ቤዛዊት ከፀበል ስትወጣ ቅልል የሚል ስሜት እየተሰማት ነበር አይምሮዋም ሙሉ ለሙሉ ባይባልም እየስተካከለ ማሰብ ማገናዘብ እየጀመረች ነበር
ቤት ገብተዉ እማማ ስንቅነሽ በሀሳብ እርቀዉ ሲሄዱ አስተዋለቻቸዉ ባዶዉን መሶብ ሲከፍቱ እንደቸገራቸዉ ገባት ለዛም ነዉ አይን ላይን የተያዩት ገዥቼ መጣሁ ሲሏት ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸዉ አሰበች
እሳቸዉ እንደወጡ እስዋ ቦርሳዋን መፈለግ ጀመረች ዉስጡ ብር እንደሌለዉ ስታይ ተናደደች ነገር ግን የባንክ ደብተሯን ስላየችዉ እና ማዉጣት እንደምትችል ሲገባት እየተቻኮለች ወጣች"
አሁን
እማማ እጃቸዉ ላይ ያለዉን ብር እያዩ ደንግጠዉ እና ከየት አምጥታዉ ሊሆን እንደሚችል እያሰቡ
"ከየት አመጣሽዉ ልጄ"
አሏት
"የኔ ነዉ ከባንክ አዉጥቼዉ ነዉ"
አለቻቸው ደስታ ባዘለ ንግግር
አላመኗትም ተጠራጠሯት ከሰዉ ነጥቃ ቀምታ ያመጣች መስሏቸዉ ነበር እየተሻላት እንደመጣ ግን በንግግሯ በሁኔታዋ እያረጋገጡ ሲመጡ አምነዋት ተያይዘዉ ወደ ዉስጥ ገቡ።

እማማ ስንቅነሽ በቤዛዊት የጤና ለዉጥ ደስተኛ ሆነዋል ማስታመማቸዉን ፍቅራቸዉንም ሳይቀንሱ ከጎኗ ናቸዉ ቤዛዊትም ከቀን ወደ ቀን ፍፁም ጤነኛ እየሆነች ነዉ አስተሳሰቧም ወደ ጤነኝነት ተመልሷል
እማማ ቤዛዊትን ያገኟትን ቀን አስታወሱ እርቃኗን ብርድ ላይ መንገድ ጥግ ተቀምጣ ነበር ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ ያዩዋት በሩቁ ልብስ መስጠት ምግብም ማቀበል ይችሉ ነበር ነገር ግን ከመልካምነታቸዉ ባሻገር የሆነ ሀይልም አብሯቸዉ ነበር።
ለቤዛዊት መዳን ምክንያት ለመሆን ነበር የዛን ቀን ያገናኛቸዉ
አንዳንድ አጋጣሚዎች አጋጣሚ የሚታለፉ ነገሮች ብቻ አደሉም ምክንያትም ዉጤትም ሊሆኑ ይችላለ።

ቤዛዊት ጤናዋ እንደተመለሰ ወደ ፍፁም ጋር ሄዳ ብታስጠራዉም እሱ ማግኘት ስላልፈለገ ሳታየዉ ሳታገኘዉ ተመለሰች
እንደበፊቷ ለምን አላገኘኝም ስትልግን አይምሮዋን አላጨናነቀችም
አንዳንድ ነገሮች በጭንቀት እና በትግል አይፈቱም ጊዜ ያስፈልጋቸዋል
ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት ስትመለስ ከባንክ ብር አዉጥታ ለቤት የሚያስፈልጉ በርካታ እቃወች ገዝታ ተመለሰች እሳቸዉም ጣፋጭ ምግብ እየሰሩ እየጠበቋት ነበር።
ምግቡ እስኪደርስ ለቤተሰቦቿ ስልክ ደወለች ድምፆን እንደሰሙ ድጋሜ ከሞት እንደተነሳች ቆጥረዋት በስልክ መሰማማት እስኪያቅታቸዉ ተጯጯሁ እናቷ እና እህቷ አሁን ካልመጣን ያለሽበትን ነገሪን ስላሏት ቤዛዊት የእማማ ስንቅነሽን ቤት አቅጣጫ ነግራቸዉ በደስታ ስልኩን ዘጋችዉ።
ከእማማ ስንቅነሽ ጋር ምግቡ ቀርቦ እየበሉ እማማ ማጉረስ ሲያበዙባት
"ጠገብኩ በአንድ ጉርሻ"
እያለቻቸዉ የማጥወልወል ስሜት ስለተሰማት ከገበታዉ ተነስታ እየተንደረደረች ማስታጠብያ ፈልጋ የጎረሰችዉን እንዳለ እየተፋች።
"ሆዴን ሳያመኝ አይቀርም"
አለች ትንሽ እንደ ቦርጭ ገፋ ያለዉን ሆዷን ዳበስ እያረገች
እማማ ስንቅነሽ ግን ልብ ብለዉ ሁኔታዋን ሲያስተዉሉት ነበር የሰዉነቷ ቅርፅ ለዉጥ ማስመለሷ ሁሉ ነገር ለቤዛዊት ባይገባትም እማማ ስንቅነሽ የቤዛዊት ማርገዝ ታዉቋቸዉ ነበረ።

ፍፁም ካለችዉ ሰዉ ይሁን ከተረገመዉ ልጃቸዉ ያወቁት ነገር ባይኖርም።

💫ይቀጥላል..💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2🥰1
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_አንድ

#አባ_ሎራና#ዡልየት

#ዡልዬት
ይዘኑልኝ ፡ በጣም ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ፤
በኔ ፡ ላይ ፡ ዘንድሮ ፡ የመጣው ፡ መከራ ፡
ፍጻሜ ፡ የለውም ፡ ቈርጫለሁ ፡ ተስፋ፤
ይርዱኝ ፡ እባክዎ ፡ ጨርሼ ፡ ሳልጠፋ ።

#አባ_ሎራ
አዝኛለሁ ፡ ልጄ ፡ ነገሩን ፡ ሰምቼው ፤
አሁን ፡ መጥቶ ፡ ነበር ፡ፓሪስን ፡ አግኝቼው
ተክሊሉን ፡ ለናንተ ፡ ኀሙስ ፡ እንድሞላ ፡
ለምኖኝ ፡ ነበረ ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ብዬ ፡ መለስኩለት፤
በነገሩ ፡ በጣም ፡ አዝኛለሁ ፡ በውነት ።

#ዡልዬት
እንግዲያው ፡ ከሰሙት ፡ እንሆ ፡ ችግሬ ፤
ሥቃዬ ፡ የጠና ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ አሳሬ
እሄድ ነበር በውነት ሴት፡ ባልሆን' ጠፍቼ
ለፓሪስ ፡ ሊድሩኝ፡ቈርጠው 'ዘመዶቼ
አስጨንቀው ያዙኝ'ይኸው ፡በግዴታ፤
አባትም እናትም የምድር'ሁሉ፡ ጌታ ፡
እግዜር ' የዳረውን ፡ አይችልም ሊያፋታ ።
እኔና 'ሮሜዎን ፡ ሁለቴ ' ሲድረን '
በፊት፡ በጥበቡ' ከልብ' አፋቀረን ፤
ቀጥሎ ፡ በርስዎ ፡ በካህኑ' ሥልጣን ፡
ባርኮ ፡አገናኘን' በተክሊል ፡ ቃል፡ ካዳን ።
አባቴና እናቴ ፡ ይህን ፡ አላወቁ ፤
ለፓሪስ ፡ ሊድሩኝ 'እንሆ 'ታጠቁ '
እንግዴህ ፡ አባቴ ፡ እርስዎ ፡ ከግዜር ፡ ጋራ
በርትተው ፡ ያድኑኝ ፡ ከዚህ ፡ ከመከራ ፡
የማይቻል ፡ ሆኖ ፡ ካልተገኘ ፡ ዘዴ !
ብልሃቱን ፡ መፈለግ ፡ አለብኝ ፡ በግዴ ፡
ይኸው ፡ በዚህ ፡ ጩቤ ፡ ሆዴን ፡ እቀድና ፡
እገላገላለሁ ፡ ከዚህ ፡ ከፈተና

#አባ_ሎራ
ኀጢአቱ ፡ትልቅ ነው ከነፍስ ፡ የሚያስቀጣ
በገዛ ፡ እጅሽ ፡ መሞት ባሳብሽ ፡ አይምጣ
ፓሪስን ለማግባት ልብሽ ፡ ካልፈቀደ
ይህን 'ያኽል፡ በውነት ፡ ሆድሽ ፡ ካልወደደ
ግልጥ ፡ አድርጊና ፡ ንገሪኝ አትፍሪ

#ዡልዬት
እግዚአብሔር ብቻ ነው መንፈስን መርማሪ
ፓሪስን ፡ ከማግባት ፡ በውነቱ ፡ አባቴ ፡
አሁን ባሁን ፡ ፈጥኖ፡ ይምጣ ጊዜ፡ ሞቴ ፡
ልገረፍ ልሰቀል ፥ በሥቃይ ፡ ልገደል ፤
ወስዳችሁ ፡ ወርውሩኝ ጣሉኝ ወደ ፡ ገደል
የትም ፡ ተረስቼ ፡ ልዋረድ ፡ ልጕላላ ፤
ብትፈልጉ ፡ ዳሩኝ ፡ ለዱር ፡ ወሮ ፡ በላ '
ከዥብ ፡ ጋራ ፡ እሰሩኝ ፡ ከነብር ፡ ካንበሳ ፤
ካፅም 'ጋራ ፡ ቅበሩኝ፣ ከትኵስ'ሬሳ፡
እሳት አንድዳችሁ፡ አሁን ፡ ከቶ ፡ ነፍሴ ፡
አቃጥሉኝ ፡ በቁሜ ፡ ከእግር እስከ ፡ ራሴ
ወደ ፡ አራዊት ፡ ጐሬ ጣሉኝ ፡ ወዶ ፡ ዋሻ ፣
ሮሜዎ ከቀረ ምንም ፡ ባል እልሻ

#አባ_ሎራ
እኔም ፡ ባንቺ፡ነገር፡እጅግ፡ተጠብቤ
ልጄ ፡ ሆይ ፡ሐዘንሽ ተሰማኝ፡ ለልቤ ፡
የሚቻልሽ ፡ ቢሆን ፡ ልብሽ ፡ የሚደፍር ፡
አድምጭኝ ልጄ ሆይ ልስጥሽ አንድ ምክር
አሁን ፡ ተመልሰሽ ፡ ስትገቢ ፡ ከቤትሽ ፡
እንደዚህ ፡ በዪና ፡ ንገሪው ፡ ላባትሽ ፡
« ፈቃድህን ፡ ልፈጽም ፡ ፓሪስን ፡ አግብቼ፡
« መጥቻለሁና ፡ ይኸው ፡ ተጸጽቼ ፡
« እንግዴህ ፡ ይደገስ ፡ ሰርጉ ፡ ይሰናዳ »
አባትሽ ፡ ይህነን ፡ ነግረሽው ፡ ሲረዳ '
ይታረቃል ፡ ካንቺ ፡ መንፈሱም ፡ ይረጋል ፤
ከንዴቱ ፡ በርዶ ፡ ይቅርታ ፡ ያደርጋል ።
እኔም ፡ የምሰጥሽ ፡እግዚአብሔር ፡ ቢረዳ
አንድ፡ መድኀኒት ነው ምንም ፡ የማይጎዳ ፡
ልብስሽን ፡ አውልቀሽ ፡ ስትተኝ ፡ ማታ ፡
ደብቀሽ ፡ ሰው ፡ ሳያይ ጠጪው ፡ በቀስታ
ሌሊቱን ፡ ሳትሰሚ ፡ መድኀኒቱ ፡ ሠርቶ ፡
ነገ ፡ ጧት ፡ ከእንቅልፍሽ መነሣትሽ ፡ ቀርቶ
ሞተሽ ፡ ትገኛለሽ ፡ ትንፋሽሽም ፡ ጠፍቶ ፡
ወስደው ፡ ይቀብሩሻል ፡ ሞታለች ፡ ተብሎ
ለቤተ ፡ ሰባችሁ ፡ በሰፊው ፡ ተንጣሎ ፡
አምሮ ፡ በተሠራው ፡በመቃብር ፡ ቤት ፡
ተኝተሽ ፡ ቈይተሽ ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡
ታዝኖ ፡ ተለቅሶልሽ ፡ ካለቀ ፡ በኋላ ፡
ዐውቀሽ ፡ ትነሻለሽ ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ሲሞላ
እስከዚያ ፡ እሠራለሁ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ ተግቼ ፤
ደብዳቤ ፡ እጽፍና ፡ ሮሜዎን ፡ ጠርቼ ፡
እሱም ፡ በቬሮና ፡ ተደብቆ ፡ ገብቶ ፡
ወዳንቺ ፡ መቃብር ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ መጥቶ ፡
አንቺ ፡ ሳትነሺ 'አጠገብሽ 'ደርሰን ፡
በምስጢር ፡ በፍጥነት ፡ ልብስሽን ፡ አልብሰን አንቺና ፡ ሮሜዎ ከዚህ ፡ ከከተማ
ማንም ሳይጠረጥር ማንም ሰው ሳይሰማ
ወጥታችሁ ፡ሄዳችሁ የትም ፡ በሌላ ፡ አገር
ዕረፍት ፡ አግኝታችሁ ፡ ያለ ፡ ክፉ ፡ ነገር
ኑሩልኝ ፡ በሰላም ፡ በፍጹም ፡ ደስታ ፡
ከናንተ ጋር ይሁን የእግዚአብሔር እርዳታ
ትጠጭው ፡ እንዲሆን ፡ ዡልዬት ፡ ሳትፈሪ'
አስቢና ፡ ቶሎ ፡ ገልጠሽ ፡ ተናገሪ ፡
እኔም ፡ መድኒቱን ልስጥሽ አሁን ፡ ሳልቈይ
ከዚህ በቀር ፡ ዘዴ ፡ የለኝም ፡ ልጄ ፡ ሆይ ።

#ዡልዬት
መልካም ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ያላንድ' ቅሬታ' .
ሳልፈራ፡እጠጣለሁ፡ በትልቅ ፡ ደስታ "
እባ፡ ሎራ ፡ ገብተው ጓዳ መድኀኒቱን በብልቃጥ አመጡ
ዶግሞስ በገዛ እጁ ለመሞት ሲቃጣ ከዚህ የተሻለ ምን ዘዴ ሊመጣ ።
እንግዲያውስ፡እንቺ ፡ ይኸው ፡ መድኀኒቱ :
እግዚአብሔር ልብሽን ፡ ያድርግልሽ ብርቱ

#ዡልዬት
አዝነው ፡ ስለ ፡ ረዱኝ ፡ ልብዎ ፡ ስለ ፡ ራራ
እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፡ አባቴ አባ ሎራ

#አባ_ሎራ
ግድ ፡ የለሽም ፡ ልጄ ፡ ሳልዘገይ ፡ ፈጥኜ ፡
እንደ ፡ ምንም ፡ ብዬ ፡ አንድ ፡ ቄስ ፡ ለምኜ
ወደ ፡ ሮሜዎ ፡ ዘንድ ፡ጒዳዩን ፡ ሸሽጌ፥
ደብዳቤውን ፡ ጽፌ ፡ በምስጢር ፡ አድርጌ
እልክለታለሁ ፡ በቶሎ ፡ እንዲመጣ '
ዡልዬት ፡ በኔ ፡ ጣዪው ፤ የቀረውን ፡ ጣጣ

#ካፑሌ#የካፑሌ_ሚስት #ዡልዬት
(ዡልዬት ' ከውጭ መጣች)

#ካፑሌ
በጣም ያሳዝናል ባሕሪሽ ፡ ተበላሸ ፤
ወዴት ሄደሽ ኖሯል ደግሞ ፡ እንዲህ ፡ ከመሽ

💫ይቀጥላል💫
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በክፍለማርያም

...ከማን ይሆን ብለዉ እየተጠራጠሩ
የቤዛዊት ቤተሰቦች ቤዛዊትን ፈልገዉ አስፈልገዉ ስላጧት ወደ ተስፋ መቁረጥ እየተጠጉ እናቷ ነጋ ጠባ ስታለቅስ ከቤት ወጥታ የጠፋች የታመመች ልጃቸዉ በድንገት ስትደዉል
ተአምር ነዉ የሆነባቸዉ
አባቷ ያለችበትን እንደሰሙ ከተቀመጡት ተነስተው ወደ ዉጪ በፍጥነት እየተራመዱ ወደ መኪናቸዉ አመሩ እናቷና እህቷ እየተደናገጡ እየተደሰቱም እኋላ ኋላ እያሉ ተከትለዋቸዉ መኪናው ዉስጥ ገብተዉ እንደተቀመጡ አባቷ መኪናዉን አስነስተዉ ወደ ቤዛዊት ገሰገሱ
የነገረቻቸዉ አካባቢ መኪናውን አቁመው ሁሉም ከመኪናዉ ወርደዉ የታመመች የተጎሳቆለች ወጣት ሴት እየጠበቁ ቤዛዊት የእማማ ስንቅህን የቆየ ቀሚስ ለብሳ ደንዳና ሴት ወይዘሮ መስላ ፊቷ እንደ ልጅነቷ ብርሀን እየፈነጠቀ ፊት ለፊታቸዉ ደርሳ ቆመች
እናቷ እንባ እያነቡ እላይዋ ላይ ተጠመጠሙባት
"ምን ነዉ ልጄ ምን በደልኩሽ"
እንባቸው እየወረደ ነው
"አረ ምንም አረ ምንም "
ትላለች ቤዛዊት የእናቷ ማልቀስ እሷንም ሆድ እያስባሳት ማልቀስ ጀምራ
እናቷ ለደቂቃወች አቅፈዋት ቆይተዉ ሲለቋት ታላቅ እህቷ በተራዋ አቀፈቻት
"ደህና ነሽ አደል ቤዚ"
የታናሽ እህቷን ጉንጭ እየሳመች
ቤዛዊት እህቷን ትጠላት እንደነበር ከአይምሮዋ ስላልተደበቀ
"ይቅርታ አርጊልኝ"
እያለች ታላቅ እህቷን ለመነቻት
"ምንም አደል አንቺ ብቻ እንኳን ሰላም ሆንሽ"
ስትል ታላቅ እህቷ የቤዛዊትን ጉንጮች መሳም ጀመረች።

አባቷ ሁሉንም እጃቸውን አጣምረዉ ሲመለከቱ ቆይተዉ
"መቼም ከዚህ በኋላ ህፃን አደለሽም በምርጫሽ አልገባም"
እያሉ ሊያቅፏት ተጠጉ
አንዳንዴ ነገሮች ከተበላሹ በኋላ ሰዉ ሊረዳን ሊያግዘን ይሞክራል በወቅቱ ግን አይደርስልንም

ፍፁም ሳይታሰር አባቷ ፍላጓቷን ቢያከብሩላት ይሄ ሁሉ ባልተፈጠረ
አባቷ እጇን ይዘዉ ወደ መኪናዉ ሊያስገቧት ሲሉ ቤዛዊት
"ሁለተኛዋ እናቴን ላስተዋዉቃችሁ
እያለች ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት ይዛቸዉ ገባች።

"እሳቸዉ ናቸዉ ለዚህ ያበቁኝ"
ስትል አንድ በአንድ እማማ ስንቅነሽን ለቤተሰቧቿ ማስተዋወቅ ጀመረች።
እማማ ስንቅነሽ በነደፈ ነጠላቸዉ ሸፍነዋታል ቁራሽ ዳቦ አካፍለዋታል በእድሜዋ ሙሉ ከፍላ የማታገኘዉ ደግነት ሰጥተዋታል ቤዛዊትም ጥላቸዉ መሄድ ስታስብ ዉስጧ ቅር እየተሰኘ እማማ ስንቅነሽን
"እኛ ቤት አብረን እንሂድ እንከባከቦታለሁ"
ስትል በስስት አይን እያየቻቸዉ
በመሀል በሀሳብ ጭልጥ ብለዉ የጠፉት የቤዛዊት መለወጥ ጤናዋ መመለሱ ያስገረማቸዉ አባቷም
"እባኮን እሺ ይበሏት ለኛም እናት ይሆኑናል ሸክም እሆንባችሁዋለሁ ብለዉ አያስቡ"
ብለዉ ጨመሩበት
እማማ ስንቅነሽ በሞጨሞጮ አይናቸዉ ቤታቸዉን እየቃኙት ሲያስቡ ቆይተዉ
"ምን አረኩልሽና ዉለታ ዋሉልኝ ብለሽ አታስቢ የሰማይ መግቢያዬን እያደላደልኩ ነዉ"
ብለዉ በነጠላቸዉ አይናቸዉ አካባቢ ዳበስ እያረጉ
"ስትችይ እኔም ስለምትናፍቂኝ እየመጣሽ እይኝ "
አሉና መምጣት እንደማይችሉ በሚገልፅ አኳሀን አንገታቸዉን አቀርቅረዉ ቀሩ።
በልባቸዉ ልጃቸዉ ዉልብ እያለችባቸዉ ላለማሰብ እየታገሉ ቤቱ ዉስጥ የነበሩት ሁሉ በሀዘን ተነክቶ ቤቱ በዝምታ ተዋጠ
በመሀል እማማ ስንቅነሽ ተነስተዉ ቆመዉ
"ምግብ ላቅርብ በልታችሁ ሂዱ"
አሉ ፊታቸዉ ላይ የፈገግታ ምልክት እየታየ
"ልጃችሁ ከሰዉ እኩል አርጋኛለች"
ሲሉ ከባንክ አዉጥታ የሰጠቻቸዉን ብርና ያሞላችላቸዉን የቤት ቁሳቁስ አስበዉ ቤዛዊትን እያመሰገኗት
ቤዛዊት እማማ ስንቅነሽን ስማ ተሰናብታቸዉ ወደ መኪና ዉስጥ ስትገባ እየመጣች ልትጠይቃቸዉ ቃል ገብታ ነበር።
መኪናዉ ተነስቶ መንቀሳቀስ ሲጀምር እማማ ስንቅነሽ በጭላንጭሉ አይናቸዉ መኪናዉን እያዩ ተክዘዉ ቀሩ መኪናዉ እርቆ ሄዶም በሀዘን ተዉጠዉ ቆመዉ እያሰቡ ነዉ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_ሁለት

#ዡልየት
ወደ ፡ አባ " ሎራ ፡ ዘንድ ፡ ደርሼ ፡ ነበረ ፤
ምክራቸው ፡ ገሠጸኝ ልቢ ፡ ተሰበረ ፡
ያንተን ፡ ያባቴን ፡ ቃል ፡ ልፈጽም ፡ ፈቅጄ ፡
የምጠላውን ፡ ሰው ፡ ስላንተ ፡ መድጄ፡
ፓሪስን ፡ ላገባ ፡ ሆኛለሁ ፡ ዝግጁ
ሰርጌ ፡ ይሰናዳ ፡ ሁሉንም ፡ አብጁ
ደግሞም ብለውኛል አጥብቀው በብርቱ
« ምሕረቱን ፡ ለምኚ፡ ወድቀሽ ፡ ከጕልበቱ
(ተንበረከከች)
ንዴት ፡ አይግባችሁ ፡ በኔ ፡ የተነሣ ፤
ያለፈው ፡ ጥፋቴ ፡ እንግዴህ ፡ ይረሳ፡
የሰላም ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ያለም ፡ የደስታ ፡
ለኔም ፡ ለልጃችሁ ፡ አድርጉ ፡ ይቅርታ ።

#ካፑሌ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ካህን ፡ እግዜር ፡ የባረከው
ምክሩ ፡ ንግግሩ ፡ ለሰው ፡ የሚሰብከው ፡
ከጻድቅ ፡ የመጣ ፡ ንጹሕ ፡ በመሆኑ ፡
ጠልቆ ፡ ልብ ፡ ይገባል ያጠግባል ፡ በውኑ
እስቲ ፡ አሁን ፡ ባሁን እንደ ፡ ምን ፡ አድርጎ
መልሶ ፡ ላከልኝ ፡ አንቺን ፡ ወደ ፡ በጎ ።
(ከተንበረከከችበት ቦታ'ያስነሣታል )

ተነሺ ፡ ከመሬት ፡ ይብቃ ፡ አትንበርከኪ ፡
ምክሩን ፡ መከተልሽ ፡ አንቺም ፡ ተባረኪ ።
(ወዴ ፡ ሚስቱ' መለስ ' ብሎ)
እንግዴህ ፡ ይፋጠን ፡ ይቀጥል ፡ ድግሡ፤
አሽከሮቹ ፡ ሁሉ ፡ በሌሊት ፡ ይነሡ ፡
ተክሊሉ ፡ እንዲፈጸም ፡ ነገ ፡ በማለዳ ፡
ማንኛውም ፡ ነገር ፡ ዛሬ ፡ ይሰናዳ ።
(በካፑሌ ፡ ቤት ጧት) ,

#ካፑሌ
ሰዎቼ ፡ ተኝተው ፡ ሳይነሡ ፡ ካልጋ ፡
ወፎቹ ፡ ተንጫጩ ፡ ይኸው ፡ ሌቱ ፡ ነጋ ፡
ተነሡ፡ረፈደ፡እሳቱን ፡ አንድዱ፤
መብሉን ፥ መጠጡን ፥ በቶሎ ፡ አሰናዱ ።

የዡልዬት ፡ ሞግዚት'
ርስዎ ፡ ዛሬ ፡ ሌሊት ፡ ጨርሰው ፡ ሳይትኙ
ቁጭ ፡ ብለው ፡ ነጋ ፡ ሥራውን ፡ ሲቃኙ፡
በጣም መልካም ነበር አሁን ጥቂት ቢያርፉ

#ካፑሌ
አታስቡ ፡ ለኔ ፡ ይልቅ ፡ አትስነፉ ፡
አያሸንፈኝም ፡ ዱሮም ፡ ቢሆን ፡ እንቅልፍ ፡
መብልና ፡ መጠጥ ፡ ደኅና ፡ የሚያሳልፍ ፡
ወዴት፡አገኝ፡ ይሆን ፡ የሠለጠነ ፡ ሰው ፤
ምንም ፡ ሳይዘጋጅ ፡ አንዱንም ፡ ሳንይዘው
ስትተራመሱ ፡ እንዲሁ ፡ በከንቱ ፡
የሙሽራው ፡ መምጫ ፡ ደረሰ ፡ ሰዓቱ ፡
ዕቃ ፡ ማነሱ፡ ነው ፡ አንዱም ፡ የሚያውከው ፡
(አሽከሮቹ'ገቡ' በያይነቱ፡ ዕቃ ፡ ይዘው)»
ምንድነው'ደግሞ አንተ ይህ የተሸከምከው ?

#አሽከር
የጠቦት፡ ሥጋ ነው፡ ለጥብስ ፡ የታረደ

#ካፑሌ
በል ፡ፍጠን ፡ ቶሎ ፡ በል ፡ ሰዓቱ ፡ ረፈደ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ከምን ጊዜ ነጋ አለፈ ሌሊቱ ካፑሌ
አንቺን ፡ አይጠብቅም ፡ ጊዜና ፡ ሰዓቱ
ሙሽራው ይመጣል አንዱን ሳትጨብጨው።
የሚያስፈልገውን ፡ ለወጥ ፡ ቤቱ ፡ ስጪው
አለዚያ ፡ ሲቸኵል ፡ ይበላሻል ፡ ወጡ!
አንችም ፡ ቶሎ ፡ ልበሽ ፡ ሰርገኞች ፡ ሳይመጡ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ዡልዬት ሳትነሣ እኔም ልብሴን ሳልለብስ ፡
በጣም ፡ ያስደንቃል ፡ የሰዓቱ ፡ መድረስ ፡
እመጣለሁ ፡ ብሏል ፡ ፓሪስ ፡ በሙዚቃ ፡
እንግዴህ ፡ ዡልዬትም ፡መተኛቷ ፡ ይብቃ።
(ሞግዚቷ ፡ ገባች)
እንዴት ፡ ረፈደ ፡ በጣም ፡ ያስገርማል ፤
ሰርገኞቹ ፡ መጡ ፡ ሙዚቃው ፡ ይሰማል !
እባክሽ ፡ ፍጠኚ ፡ ቶሎ ፡ በይ ፡ አስነሻት ፤
ገላዋን ፡ ትታጠብ ፡ ልብሷንም ፡ አልብሻት
ቶሎ ፡ እንደ ፡ ጨረሰች ፡ ለብሳና ፡ አጊጣ ፡
አብራችሁ ፡ ካንቺ ጋር ወደኛ እንድትመጣ
እኔም ፡ ሰርገኞቹን ፡ እስከዚያ ፡ ልቀበል ፤
አሽከር ፡ በሩን ፡ ክፈት እባክህ ፡ ቶሎ ፡ በል

በዡልዬት ፡ መኝታ ፡ ቤት ።

#ሞግዚት ፡ (ዡልዬትን፡ትቀሰቅሳለች) •
ተነሺ ፡ ረፈደ ፡ ዡልዬት ፡ እመቤቴ ፤
ተነሺ ፡ ይሉሻል ፡ እናትሽ ፡ እሜቴ ፡
ሰርገኞች ፡ ሲመጡ ፡ ሙዚቃ ፡ ሲሰማ
አትንቀሳቀስም ፡ እሷ ፡ ግን ፡ ፈጽማ ፤
ምነው ፡ ምን ሆንሽብኝ ተነሺ እንጂ ቶሎ
አንቺን ፡ ይጠብቃል ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ቸኩሎ
(ገልጣ' ታያታለች) •
እኔ ፡ ጠፋሁ ፡ ዛሬ ፡ ያለትንፋሽ ፡ ቀርታ ፡
ገላዋ ፡ ቀዝቅዟል ፡ እመቤቴ ፡ ሞታ፡
እረ ፡ ትልቅ ፡ጉድ፡ ነው ፡ ኑ፡ ቶሎ ፡ድረሱ !

#የካፑሌ_ሚስት
ማነው ይህን ያኽል የሚጮኸው እሱ ?

#ሞግዚት
አሁን ፡ በገደለኝ ፡ መሬት ፡ እኔን ፡ ውጦ ።

#የካፑሌ ፡ ሚስት ።
አትጩሂ ፡ እባክሽ ፡ እንግዳ ፡ ተቀምጦ ።

#ሞግዚት
ልጅዎን ፡ ያስተውሏት ፡ በመኝታ ፡ ቤቷ ፤

#የካፑሌ_ሚስት (ግባች) •
ስለምን፡ነው ፡ እስካሁን ፡ አለመነሣቷ ?
ልጄ ፡ ዡልዬት ፡ ተነሽ ፡ ዐይንሽን ፡ ግለጪ
አባቷን ጥሩልኝ ፡ በቶሎ ፡ ከውጪ
ልጄን ፡ ምን፡ አገኛት ፥ ሞታለች ፡ ጨርሶ ።

#ካፑሌ ፡ (ገባ) «
እንግዲህ ፡ መንጫጫት ይወዳሉ ፡ ደርሶ
ዡልዬት አትመጣም ወይ ሙሽራው ሲጠብቅ

💫ይቀጥላል💫
#እቴ_ምን_ሆነሻል ?

ሥራ በሌለበት
ሥለ ሥራ ቋንቋ ፥ የሚነታረኩ
የትውልድ ልብ ላይ
ቂምን ለመጋገር ፥ ጥላቻ ሚያቦኩ
በነፃነት ምድር
ነፃ አውጪ ነን ብለው ፥ ባርነት ሚሰብኩ
ትውልዶችን ፈጥሮ ፥ ዝም ሲል ፈጣሪው
“ትናገር አደዋ”
እያልሽ በድፍረት ፥ ምታንጎራጉሪው
ምን ነክቶሽ ነው እቴ?

ከኔ ቋንቋ በቀር ፥ ለማይናገሩ
መግባባት አይኖርም ፥ መስማማት ኢንጅሩ
ገለመሌ እያለ
ቋንቋ ተከፋፍሎ ፥ ሲፎክር ሀገሩ
ሀገር መንደር ሲሆን ፥ ውቅያኖሱ ኩሬ
አንቺ ባለማወቅ
“ትናገር አድዋ ፥ ትናገር ሀገሬ”
ብለሽ የምትዘፍኚው
ወይ ደሞ በድፍረት ፥ ምታቀነቅኚው
ምን ነክቶሽ ነው እቴ?

አዋቂ ነኝ ባዮች
ፍቅርን አቀጭጨው ፥ ጥላቻን ሲያሰቡ
ተማሪ ነን ባዮች
"ቋንቋ መግባቢያ ነው "
በሚል አስተምሮት ፥ ብለው አልግባቡ
ትናገር አደዋ”
ብለሽ የምትዘፍኚው ፥ መምህራቸውን ፥ ለሚደበደቡ
ምን ሆነሻል እቴ?

ለብዙ ሺህ ዘመን
እጇን ወደ አምላኳ
ዘርግታ ስትኖር ፥ ሰርቀዋት ፀሎቷን
የቆጡን ለማውረድ ፥ ጥላ የብብቷን
የፉክክር ሀገር
የሚዘጋት አጥታ ፥ እያደረች ክፍቷን
ሌባና ቀማኛ ፥ ለጉድ ተንሰራፍቶ
ፍቅር ያግባባቸው
ያያት ቅድም አያቶች ፥ ታሪክን አንስቶ
ቋንቋ ላያግባባን
እውነት እየሰቀልን ፥ ለምንፈታ በርባን
“ትናገር አድዋ”
የሚል አጉል ቅኔ ፥ ከምትደረድሪ
አድዋ ዝም ብላ ፥ አንቺ ተናገሪ።
አለበለዚያ ግን
ብሔር ተከፋፍሎ ፥ ለሚጣላ ሀገር
"ትናገር አድዋ
ትናገር ሀገሬ” ፥ የምትይው ነገር
ለእሳት ልጅ አመዶች ፥ ነገር ነው ሚጭረው
ልናገር ብትልስ
ቆይ በማን ቋንቋ ነው ፥ የምትናገረው?
ራስሽ ተናገሪ።

ይድረስ ለባለቅኔዋ ድምፃዊት ለእጅጋየሁ ሽባባው
#ጂጂ

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#በክፍለማርያም

... እያሰቡ ቆመዉ ቀሩ
ቤዛዊት ቤቷ ገብታ እንደ ቀድሞዉ ህይወቷን መምራት ጀምራለች ፍፁም ትዉስ እያላት ታስበዉና ትንሽ ይረጋጋ ብላ መሄዱን መጠየቁን ትተወዋለች ነጋ ጠባ ግን ሳታስበዉ ዉላም አድራም አታዉቅም።

በመሀል ግን ምግብ አልስማማ ሰዉነቷ በተለይ ሆዷ ከፍ ማለት ሲጀምር
"አርግዤ ይሆን"
እያለች መጠራጠር ጀመረች
"እንዴት"
እያለች እራሷን መጠየቅ ጀምራ ጥርጣሬዋ እየጎላ ሲመጣ ለመመርመር ወደ ሀኪም ቤት ተደብቃ ከቤት ወጣች።
ሀኪም ቤቱ ዉስጥ ካርድ አዉጥታ አግዳሚ ወንበር ላይ እንደተቀመጠች እናቱ ላይ ታቅፎ የተቀመጠ ህፃን ስታይ የልጁ ዉኔታ አስደስቷት ለማጫወት እጆቿን እያንቀሳቀሰች በፊቷ የተለያየ ገፅታ እየታየ እሷም አብራዉ ቆይታ ስሟ ስለተጠራ ወደ ዉስጥ ገባች።

ፍፁም ጨላማ ቤት ተብሎ ከሚጠራዉ ቤት ሲወጣ ፀባዩ ተስተካክሎ የበፊቱን ፍፁም መስሎ ነበር
የሟጠጠ ተስፋን ወደ እዉነተኛ ተስፋ ቀይሮ እስሩን ለመቀጠል እና አይምሮዉ ዉስጥ ያሉ መጥፎ ተዝታወቹን ሁሉ እረስቶ እንደሌሉ ቆጥሯቸዉ ወደ ቀድሞዉ ክፍል ተመለሰ
የእስር ህይወት ተመሳሳይ ተደጋጋሚ ቢሆንም ፍፁም ጠዋት ተነስቶ ለጤናዉ ይንቀሳቀሳል
ሲመለስ ወረቀቱ ላይ ሀሳቦቹን ይፅፋል አዘዉትሮ ግን መፅፍትን ላይብረሪ እየገባ ሲያነብ ይዉላል
ቤዛዊትን ሲያስታዉስ ምሽቱ ይገፋለታል መጨረሻ ቀን በተናገራት ንግግር ተከፍቶ ልትጠይቀዉ ዳግም ብትመጣ እያለ መመኘት ጀምሯል ከሱ ስም ጋር የሚመሳሰል ሰው
"ዘመድ ሊጠይቅህ መጥቷል"
ሲባል ጆሮወቹ ይሾላሉ የሱ አለመሆኑን ሲያዉቅ አንገቱን ደፍቶ ቤዛዊት እንድትመጣ ይፀልያል።
አንዳንዴ ቤዛዊት የሱ ሳትሆን የሌላ እቅፍ ዉስጥ የሌላ ፍቅር ዉስጥ ስትገባ በሀሳቡ ይስልና
ይበሳጫል እራሱን ይወቅሳል ሲረጋጋና ነገሩን አጢኖ ሲመለከተዉ ደሞ የእሷን ደስታ ብቻ ይመኛል
"እኔ ከታሰርኩ እሷ ቆማ ትቅር ማለት አይገባም"
ይልና ጥጉን ይዞ አርፎ ይቀመጣል
ፎጣ አናቱ ላይ ከሚያረገዉ ከተደባደበዉ ማስረሻ ጋም ስለታረቁ አብረዉ ስላሳለፉት ህይወት እያወሩ ቀኑ ይመሻል

ቤዛዊት ምርመራዋን አጠናቃ ዉጤት ለመስማት ዶክተሩ ፊት ተቀምጣለች
"እንዴት ነሽ ቤዛዊት"
አላት በእድሜ ገፋ ያለዉ ዶክተር አይኖቹ ላይ የነበረዉን መነፅር እያወለቀ
"ደህና ነኝ"
አለችዉ ቤዛዊት እንደማፈር እያለች
"በምርመራዉ ሆድሽ ዉስጥ የአንድ ወር ከ ሰባት ቀን ፅንስ እንዳለ ተረድተናል"
ቤዛዊት ዶክተሩ ደንግጣ አየችዉ
"ስንት ወር አልከኝ?"
ደገመላት
"ወር ከሰባት ቀን እኛ ጋር ክትትል ማረግ መጀመር አለብሽ..."
ቤዛዊት አልሰማችዉም ጣቶቿን እያንቀሳቀሰች መቁጠር ጀመረች
የፍፁም ቤት ከፍፁም ጋር ያሳለፉት የፍቅር ምሽት ተዝ እያላት ወደ ዛን ቀን በሀሳብ ተጉዛ የፍፁም ክንድን ተንተርሳ ደረቱ ላይ ተኝታ ፀጉሯን በእጆቹ እየደባበሰ እወድሻለሁ ያላት አየታወሳት
"አንድ ወር አንድ ወር ..ፈጣሪዬ "
አለችና ፊቷ ላይ ፈገግታ እየተነበበ በደስታ ተነስታ ቆመች
"ቤዛዊት ችግር አለ"
እያላት ዶክተሩም ተነስቶ ቆሞ
"የፍፁም ልጅ ነዉ ዘሩን ሰጥቶኝ ነዉ የሄደዉ"
ዶክተሩን በደስታ አቅፈችዉ የተደናገጠዉ ዶክተር በግድየለሽነት ታቀፈላት ወድያዉ ያቀፈችዉን የማታዉቀዉን እየለቀቀችዉ
"እመለሳለሁ እመጣለሁ..."
እያለች ፍፁምን አግኝታ የደስደሱን ለመንገር እየተጣድፋ ወጣች

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_ሁለት

#ሞግዚት
ሞታለች ፡ ሞታለች ፡ ጕድ ፡ ነው ፡ የሚያስደንቅ ,

#የካፑሌ_ሚስት
ምን ፡መድኀኒት ላምጣ ወዴት ስፍራ ሄጄ

#ካፑሌ
ቆዩ፡እስቲ፡እኔ፡ልያት፡ የታለች፡ ቀዝቃዛ ፡ (እየዳበሳት).
ፈጽማ ፡ ሞታለች ፡ በምን ፡ ጕዴ በዛ
ሌሊት፡ በጨለማ ፡ ፀሓይዋ፡ ሳትወጣ ፡
ልጄ ፡ አበባዬ ፡ ወድቃለች ፡ ተቋርጣ ።

#ሞግዚት
የተረገመ ፡ ነው ፡ አወይ ፡ የዛሬው ቀን ፤

#የካፑሌ_ሚስት
ምነው ፡ ብንቀበር ፡ ሁላችንም ፡ አልቀን !

#ካፑሌ
ምንም ፡ አልናገር' ምላሴ 'ታሰረ
ልሳኔ ፡ በሐዘን 'ተቁልፎ ፡ ቀረ ።
(አባ ' ሎራና 'ፓሪስ ' በሙዚቃ ገቡ ።)

#አባ_ሎራ
ወደ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን እንሂድ ፍጠኑ
ሙሽራዋን ጥሩ እናንተም ቶሎ'ኑ ።

#ካፑሌ
ጉድ ሆነናል ዛሬ ይተዉ አባቴ
ጕድ ፡ ለማየት ፡ ኖሯል ፡ የቈየች ፡ ሕይወቴ
እኔ ፡ ወዴት ፡ ልድረስ ፡ የት ፡ አባቴ ፡ ልግባ
ሞተች ፡ ተቀጠፈች ፡ ልጄ ፡ የኔ ፡ ኣበባ ።
እናቷ ፡ ሳታስብ ፡ ኣባቷ ፡ ሳይሰማ ፡
ሞት ፡ የሚባል ፡ ሌባ ፡ ሌሊት በለጨለማ
ለካ ፡ ከቤታችን ፡ ገብቶ ፡ ተደብቆ ፡
ይዟት ፡ ሄዶ ፡ ኖሯል ፡ ልጃችንን ፡ ሰርቆ ፤
እንዴት ፡ ጉድ፡ ሆነናል ፡ እንዲህ ፡ ተደግሶ
ሰርጓ ሐዘን ፡ ሆነ ደስታችን ለቅሶ ።

#ፓሪስ
እኔ ፡ ዕድለ ፡ ቢሱ፡ እንዴት፡ ያለ ፡ መርዶ፡
እንዴት ፡ ያለ ፡ሐዘን ፡ ጠበቀኝ ፡ ተወልዶ

#የካፑሌ_ሚስት
የተረገመ ፡ ነው ፡ አወይ ፡ የዛሬ ፡ ቀን
ቀረን ፡ እኮ ፡ ሰዎች ፡ እንደዚህ ፡ ተሳቀን ፡
ያይኖቼ ፡ ማረፊያ ብትኖረኝ አንዲት ፡ ልጅ
ያንድ ፡ ቀን 'ደስታ' ለማየት'ስዘጋጅ፡
ለማን ኣቤት ልበል ፡ ሞት ፡ ይዞብኝ ፡ ሄደ
ሆዴ ተቃጠለ አንጀቴ ፡ ነደደ

#አባ_ሎራ "
ይብቃ ፡ ለሐዘኑ ፡ አድርጉለት ፡ መጠን ፤
አስቡ ፡ ይችን 'ልጅ' እግዜር ፡ ነው' የሰጠን
አሁንም ፡እግዚአብሔር ወሰዳት መልሶ :
ሐዘናችሁ ፡ አይሁን ፡ ያረመኔ ፡ ለቅሶ ፡
ቀረባት ፡ ብላችሁ ፡ የመሬት ፡ ደስታ ፡
ጸጸታችሁ ፡ አይሁን ፡ በጣም ፡ የበረታ ፡
የመሬት ፡ ደስታ ፡ ምንም ፡ የለው ፡ ዋጋ ፤
ይልቅ አይበልጥም ወይ የሰማይቤት ጸጋ፡
ከሚያልፍ ፡ዓለም ወጥታ፡ ከዘለዓለም ቤቷ
መተላለፍ፡ ነው ፡ በሰላም ፡ መግባቷ ፡
መሆኑ ፡ ቀረና፡ ሰርጓ በመሬት ላይ፤
ብርሃን ፡ ወዳለበት፡ሄደች፡ ወደ ፡ ሰማይ ፡
እናድርጋት ፡ ስንል ፡ ምድራዊት ፡ ሙሽራ ፡
አይሆናትም ፡ ብሎ ፡ የመሬት ፡ መከራ ፡
ሺሕ ፡ ጊዜ ፡ የላቀ ፡ ደስታ፡ አዘጋጅቶ ፡
እግዚአብሔር ፡ ወሰዳት ፡በፈቃዱ ፡ ጠርቶ
የሰርግ ልብሷን ለብሳ እንዳማረች በክብር
በሉ ፡ ያዟትና ፡ እንሂድ ፡ መቃብር ።

#ሮሜዎ ። (በተሰደደበት ፡ አገር 'ሆኖ)
መሠረት ፡ ቢኖረው ፡ የኔ ፡ ሕልም፡ ዛሬ ፡
አገኝ ፡ ይመስለኛል ፡ ደስ የሚያሰኝ ፡ ወሬ
ዡልዬት ፡ ስትመጣ ፡ ስታገኘኝ ፡ ሞቼ ፡
አልቅሳ ፡ ስትስመኝ ፡ እኔ ፡ ተዘርግቼ ።
ኋላም ፡ በሷ ፡ ትንፋሽ ፡ ሕይወቴን ፡ አድሼ
ከሞት ፡ ተነሥቼ ፡ አየሁኝ ፡ ነግሼ ።
በጣም ፡ ደስ ፡ ብሎኛል ፡ ዛሬ ጧት፡ጀምሮ
ሰላም ፡ ይሰማኛል ፡ የመንፈስ ፡ የአእምሮ
(ቤልሻጥር ቦት ጫማ አድርጎ፡ መጣ)
ቤልሻጥር ፡ጐበዙ፡ እንኳን ፡ ገባህ ፡ ደኅና'
ምን ወሬ ይዘህ መጣህ ዛሬ ከቤሮና ?
ዡልዬት ደኅናነች ወይ አባቴስ እንዴት ነው ?
እሷ ፡ ደኅና፡ ብትሆን ፡ግድ የለም የቀረው
ዡልዬት ፡እንደ ፡ምን ነች ? አሁንም አድሼ
ልጠይቅህ ፡ በጣም ሺሕ ፡ ጊዜ ፡ መልሼ

#ቤልሻጥር
ደኅና ፡ ነች ፡ ልበልህ ፡ አልነካትም ፡ ዐፈር
እንደሌላው ፡ ፍጥረት ፡ መሬት ፡ ሳትቀበር
ከመቃብሩ ፡ ቤት፡ ሠርተው ፡ አባቷ
ካዘጋጁት ፡ ገብታ ፡ እግሮቿም ፡ እጆቿ ፡
ታስረው ፡ ሳትገነዝ ፡ በማዕርግ ፡ ተንጋላ ፡
ተኝታ ፡ ኣየናት ፡ ያንቀላፋች ፡ መስላ ።
እንዲህ ፡ በጌትነት ፡ ዡልዬት ፡ ተቀበረች ፤
በቃ ፡ የሷ፡ ነገር ፡ እንደ ፡ ዘበት ፡ ቀረች ።
ነፍሷ ፡ ግን ወደ እግዜር ዐረገች ወደ ላይ
ዐርፋ ፡ ከዚህ ዓለም ወጣች ፡ ወደ ሰማይ

#ሮሜዎ ። (በድንጋጤ ፊቱ ተለወጠ)
ምን ፡ አገኛትና ? በምን ፡ የተነሣ ?

#ቤልሻጥር
ጧት፡ ባልጋዋ ፡ ላይ ፡ በድን ሆና ሬሳ፡
ተገኘች ፡ ከእንቅልፍ፡ ሳትነቃ ፡ ሞታ ፤

#ሮሜዎ
እንደዚህ ፡ ከሆነ 'የዡልዬት ፡ ሁኔታ ፡
ደግ ፡ ነው መልካም ፡ ነው ፤ ብዕር፡ቀለም፡ኣምጣ፡
ፈረሶች ፡ ተከራይ ፈጥነህ መንደር ፡ውጣ
ማንም ሰው ሳያየኝ ማንም ሰው ሳይሰማ
መሄዴ' ነውና ፡ ሌሊት ፡ በጨለማ ።

#ቤልሻጥር
እባክህ ፡ ጌታዬ ፡ ፊትህ ፡ ተለወጠ ፤
ደምህም ፡ ጠቈረ ፡ ልቤ ፡ ደነገጠ '
ቻለው ፡ ሐዘንህን ፡ ከትዕግሥት ፡ ጋራ

#ሮሜዎ
አትሥጋ ፡ ግድ የለም ፡ ቤልሻጥር አትፍራ
የማይሆን አይሆንም የሚሆን ፡ ይሆናል !

ይልቅ ፡ቶሎ ፡ ፍጠን ፡ ጊዜው ፡ ያልፍብናል
(ቤልሻጥር ሄደ፤ ሮሜዎ'ብቻውን) »
እንገናኛለን ፡ ዥልዬት ፡ ዛሬ ፡ ማታ ፤
ወዳንቺ ፡ ለመድረስ ፡ ቶሎ ፡ በደስታ ፡
መንገዱን ፡ መፈለግ ፡ አለብኝ ፡ ግዴታ ፡
መድኀኒት ፡ የሚሸጥ ፡ አንድ ፡ ጎረቤቴ ፡
መኖሩን ፡ ዐውቃለሁ ፥ እኔ ፡ በሕይወቴ ፡
አይቼ ፡ አላውቅም ፡ ችግረኛ ፡ እንደ ፡ እሱ
ሁል ፡ ጊዜ ፡ ያደፈ፡ ቀዳዳ ፡ ነው ፡ ልብሱ ፡
የተጐዳ ፡ ሰው ፡ ነው ፡ ድህነት ፡ ያጠቃው
ሰውነቱ ፡ ከስቷል ፡ የመደብር ፡ ዕቃው ፡
አሮጌ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ቈሻሻ ፡ ሰባራ ፤
ተጠርጎ ፡ የማያውቅ ፡ የለበሰ ፡ ዐቧራ ።
ከሱቁ ፡ ስገባ ኔም አስተውዬ
እሱን ፡ባየሁ ቍጥር አሰብኩ እንዲህ ብዬ
በማንቱ ፡ ከተማ ፡ ለሰው ፡ መርዝ ፡ የሸጠ
በምንም ፡ አኳኋን ፡ አውጥቶ ፡ የሰጠ ፡
ምንም ፡ እንኳ፡ የሚያዝ ፡ በሞት ፡ እንዲቀጣ ፡
ኀይለኛ ፡ ዐዋጅ ፡ ቢኖር ፡ ተጽፎ ፡ የወጣ ፡
መርዝ ፡ የሚፈልግ ፡ ሰው ፡ ብዙ ፡ ገንዘብ ፡ ሰጥቶ ፡
ይህን ችግረኛ፡ ቢጠይቀው ፡ መጥቶ ፡
አይጠረጠርም : እንቢ ፡ እንደማይለው ፤
ስለዚህ ፡ ጠርቼ ፡ እስቲ ፡ ልሞክረው ፡
አንተ ፡ መድኀኒት ፡ ሽያጭ፡ እባክህ ፡ ወዲህ ፡ ና ።

#መድኀኒት_ሽያጭ
ምነው ፡ ሮሜዎ አይዶለም ወይ ፡ ደኅና ?

#ሮሜዎ
ሰው ፡ አንተን ይሻሃል ባጣ ፡ ጊዜ ፡ ጤና፡
አንድ ፡ ነገር ፡ አሁን ፡ ልንገርህ ፡አድምጠኝ
ቶሎ ፡ የሚገድል ፡ ብርቱ ፡ መርዝ ፡ ስጠኝ፡
አርባ ፡ ዱካ ፡ ልስጥህ ለመርዝህም ዋጋ
አንተም ፡ ትሆናለህ ፡ በዚህ ፡ ባለጸጋ ፡
አንተን ፡ ለመሰለ ፡ በጣም ፡ ለተጐዳ ፡
ይህ ፡ ብዙ ፡ ገንዘብ ነው በጣም የሚረዳ

#መድኅኒት ፡ ሽያጭ ።
ኀይለኛ ፡ መርዝ አለኝ በመደብሬ ውስጥ
ግን ፡ ባዋጅ ፡ ክልክል ነው፡ለማንም፡ እንዳልሸጥ ።

#ሮሜዎ
ሞኝ ፡ ነህ ፡ መሰለኝ ፡ ዐዋጅ ፡ብሎ ፡ ጣጣ
ራብ ፡ ለገደለህ ፡ ዐጥንትህ ' ለወጣ'
ላንተ ፡ ምን ' ጠቀመህ ይልቅ ስጠኝ' ቶሎ
ድኽነት ፡ ይታያል ፡ በመልክህ ፡ ተሥሎ'
ጒዳት ፡ አቈራምዶ፡ ችግር ፡ ያሸነፈህ

💫ይቀጥላል💫
👍1
#የኔ_ቢጤ

ከሰዎች መካከል ተሸሎክልካ መጥታ
ፊት ለፊቴ ቆማ እጆቿን ዘርግታ
“ስለ እግዚአብሔር!” ብላ
ምፅዋት ጠየቀችኝ ፍፁም በሐዘኔታ፡፡
ብሰጣት ደስ ባለኝ ባይፀድቅ እንኳ ነፍሴ
ነገር ግን እውነቱ
ባዶ ነው ወና ነው ምንም የለም ኪሴ ፤
“እግዜር ይስጥሽ!" አልኳት አዝኜ ለራሴ፡፡
በብርሐን ፍጥነት ከአፊ ተቀብላ
“አብሮ ይስጠን!” ብላ
ሔደች ከአጠገቤ እኔን ለሐሳብ ጥላ፡፡
እጅግ ገረመችኝ!.. እጅግ ደነቀችኝ!
የለኝም አላልኳት እንዴት እንዲ አለችኝ?!?
“ኪሴ ባዶ እንደሆን
በምን አወቀችው?” እያልኩኝ በውስጤ፤
በዓይኔ ተከተልኳት ይችን የኔ ቢጤ፡፡
ሁሉም አጥቶ ነጥቶ
የልመና ባሕል ጨርሶ ሳይውጠን፤
እውነቷን ነው አሜን ፈጣሪ አብሮ ይስጠን፡፡

🔘በፋሲል🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_አራት


#በክፍለማርያም

...እየተጣደፈች ወጣች
መንገድ ላይ በደስታ ብዛት ፊቷ ላይ ጤነኛ የሆነ ፈገግታ እየታየባት ወደ ማረምያ ቤቱ ከመግባቷ በፊት ከለመደችዉ ምግብ ቤት ምግብ አስቋጥራ
አዲስ ህይወት አዲስ ጅማሬ እንዳገኘ ሰዉ መንፈሷ ብሩህ ሆኖ ስትከንፍ ደርሳ ፍፁምን አስጠርታዉ በሽቦ በታጠረዉ ክልል አሻግራ የፍፁምንን መምጣት መጠባበቅ ጀመረች።

ፍፁም የጀመረዉን የህይወቱን መፅሀፍ እየፃፈ የእሱ መታሰር ከቤዛዊት በአካል እርቋ ተስፋዉ ጨልሞ ፍቅራቸዉ ያሰበዉ ሳይሆን በጅምር ቀርቶ እሱም እሷም በየራሳቸዉ መንገድ ላይ ተራርቀዉ መቅረታቸዉን ፅፎ እስከዛሬ ቀን ያለዉን የህይወቱን ምስቅልቅል ወረቀቱ ላይ ካሰፈረ በኋላ ወደ ፊት የሚፈጠረዉ ስለማይታወቅ የታሪኩን ፍፃሜ ገና እያየ የሚቀጥለዉ ስለሆነ
በተቀመጠበት እየተከዘ የስሙን መጠራት ገና እንደሰማ ተስፈንጥሮ ቆሞ በደስታ ልቡ ጮቤ እየረገጠ እየጨፈረ መራመድ ጀመረ።

ከቤዛዊት ዉጪ ማንም ሊጠይቀዉ እንደማይመጣ ልቡ ስለዋቀዉ ነዉ መደሰቱ
ካስከፋት ቀን ጀምሮ የእሷን መምጣል በጉጉት በልመና ሲጠብቅ ስለነበር
አይኖቿ እየናፈቁት አየተደሰተ ወደ ዘመድ መጠየቅያዉ ስፍራ ደረሰ።
አይን ለአይን በርቀት ሲተያዩ ሁለቱም ፊት ላይ ብልጭ ብሎ የጠፋ ፈገግታ ታየ
አይናቸዉ ሳይነቀል ተጠጋጉ በተወሰነ እርቀት ተጠጋግተዉ አቅራቢያቸዉ ያለች የማረምያ ቤቱ ፖሊስ ቤዛዊት የያዘችዉን ምግብ ለፍፁም ጎርሳ እንድታቀብለዉ በማንክያ ውስጡን ነካ ነካ ካረገች በኋላ ነገረቻት ቤዛዊት መጠነኛ ጉርሻ በአፍዋ እያኘከች
"እንዴት ነህ ፍፄ"
እያለች ምግቡን አቀበለችዉ አፏ ላይ የያዘችዉ ምግብ አላስወራ ስላላት ተረጋግታ አኝካ እዋጠችዉ
ፍፁም በደስታና በፍቅር እያያት ነበር ፊቷ ላይ የማይነበብ ፍፁም ሰላም ይነበብባታል ጤናዋ እንደተስተካከለ ገምቶ በልቡ ተመስጌን እያለ የአፍ አመል ስለሆነ
"ደህና ነኝ አንቺስ እንዴት ነሽ?"
ተነፋፍቀዋል መሀላቸዉ ላይ ግን የሚያስተያይ ነገር ግን የማያገኛኝ አጥር አለ
እስርም እንደዚህ ነዉ
"ልጅ ልወልድልህ ነዉ"
እያለች እጆቿን ወደ ሆዷ ሰዳቸዉ ሆዷን በቀስታ መዳበስ ጀመረች
ፍፁም መልስ ሳይሰጣት አብረዉ ያደሩበትን ቀን አስታወሰ ተሽሎት ከሆስፒታል የወጣቀን
አሰላዉ አንድ ወር ከሳምንት አካባቢ
"እርግጠኛ ነሽ ሀኪም ቤት ሄደሽ ነበር? "
ጠየቃት በማመን እና ባለ ማመን መሀል ባለ ግር የማለት ስሜት ዉስጥ ሆኖ
ቤዛዊት ፊቷን ከላይ ወደ ታች እየነቀነቀች
"አዎ የአንድ ወር ከሰባት ቀን ልጅ ሆዴ ዉስጥ አለ"
ፍፁም ጥርጣሬዉ እነደጉም በኖ ጠፋ በቤዛዊት እና በእሱ አንድ አምሳል እንዳለ ልቡ አሰየነገረዉ ፊቱ በደስታ እየፈካ ጣቶቹን በአጥሩ ላይ እደገፈ ባይነካኩም እሷም በሱ ትይዩ እጆቿን ዘረጋች
"እወድሻለሁ "
ሲል በቀስታ አወራ
"እኔም እወድሃለሁ "
የእሷ ድምፅ ከሱ በጣም ቀንሶ በዉስጡ አብረሀኝ ከጎኔ ብትሆን ልጃችንን አብረን እናሳድግ የሚል አስተያየት አብሮት ነበረ።

💫ይቀጥላል 💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ #በክፍለማርያም ...እየተጣደፈች ወጣች መንገድ ላይ በደስታ ብዛት ፊቷ ላይ ጤነኛ የሆነ ፈገግታ እየታየባት ወደ ማረምያ ቤቱ ከመግባቷ በፊት ከለመደችዉ ምግብ ቤት ምግብ አስቋጥራ አዲስ ህይወት አዲስ ጅማሬ እንዳገኘ ሰዉ መንፈሷ ብሩህ ሆኖ ስትከንፍ ደርሳ ፍፁምን አስጠርታዉ በሽቦ በታጠረዉ ክልል አሻግራ የፍፁምንን መምጣት መጠባበቅ ጀመረች። ፍፁም…»
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_ሶስት

#በአባ_ሎራ_ቤት

አባ ፡ ዮሐንስ ፡ (ከውጭ ፡ መጣ) ።
ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ?

#አባ_ሎራ
ተሳሳትኩ ፡ ብዬ ፡ በልቤ ፡ ባልፈራ ፡
በድምፅህ ፡ መሰልከኝ ፡ የኛ ፡ አባ ፡ ዮሐንስ ።

#አባ_ዮሐንስ
ዐውቀሃል ፡ እኔ ፡ ነኝ ።

#አባ_ሎራ
አንተ ፡ እስክትመለስ ፡
እጠብቅህ ፡ ነበር ፡ ቸኩዬ ፡ ባሳቤ ፡
ፈጥነህ ፡ ደረስክልኝ ፡ ስሥጋ ፡ በልቤ ፡
መልሱን ፡ ከሮሜዎ ፡ ለጻፍኩት ፡ ደብዳቤ አመጣህልኝ ፡ ወይ ?እስቲ ቶሎ ፡ ስጠኝ፤

#አባ_ዮሐንስ
የሆንኩትን ፡ ነገር ፡ ልንገርህ ፡ አድምጠኝ
ደብዳቤህን ፡ ቶሎ ፡ ለመስጠት ፡ ወስጄ
አንዱን ፡ የኛ ፡ ካህን ፡ ልፈልገው ፡ ሄጄ ፡
ወደ ፡ ሮሜዎ ቤት፡ እንዲወስድኝ መርቶ :
እሱም ፡ እሺ ፡ ብሎ ፡ ሊወስደኝ ፡ ተነሥቶ
ዘበኞች ፡ መጡና ፡ ከቤት ፡ እንዳንወጣ ፡
ዘግተውብን ፡ ሄዱ፤ ከውጭ ፡ የመጣ ፡
በሽታ ፡ ስላለ ማንም ፡ ከሌላ ፡ አገር፡
ሲመጣ ፡ አስቀድሞ ፡ ለካ ፡ እስቲመረመር
ለብቻው ፡ እንዲሆን ፡ የመጣው ፡ ሥራቱ፡
የሚያስገድድ ፡ ኖሮ ፡ ሳልሄድ ወደ ፡ማንቱ
ሮሜዎን ፡ ሳላገኝ ፡ ሳላየው ፡ ደርሼ
ያንተንም ፡ ደብዳቤ ፡ አመጣሁ ፡ መልሼ
ልልከው ፡ አስቤ ፡ ብሞክር ፡ ብለፋ:
ብጠይቅ ባስጠይቅ የሚላክ ሰው ፡ ጠፋ፡
አልሆንልህ ፡ አለኝ ፡ ነገር ፡ አልሳካ ፤
ይቅርታ ፡ አድሮግልኝ ፡ ደብዳቤህን፡እንካ ። (ሰጠው)

#አባ_ሎራ
ምንኛ ፡ መጥፎ ፡ ነው ፡ያመጣኸው ወሬ !
አይ ፡ አባ ፡ ዮሐንስ ፡ ጉድ ሰራኸኝ ፡ ዛሬ ።
መልክቴ ፡ በውነቱ፡ ትልቅ ጕዳይ ፡ ነበር ፤
በጣም ፡ የከበደ ፡ ከፍ ያለ'ቁም ፡ ነገር ፡
ባለመፈጸሙ ፡ የመልክቴ ፡ አደራ ፡
እጅግ ፡ የሚያሳዝን በጣም የሚያስፈራ፡
ነገር ፡ ለማስከተል ፡ ይችላል ፡ ወዳጄ ፤
ጽፌ ፡ የሰጠሁህ ፡ ያ ፡ ወረቀት ፡ በእጄ ፡
ለሮሜዎ ፡ ቶሎ ፡ መድረስ ፡ ነበረበት ፤
አይ ፡አባ ዮሐንስ ጕድ ሠራኸኝ በውነት !
እባክህ ፡ አሁንም ፡ ቶሎ ፡ እንረዳዳ ፤
ጕጠት ፡ ፈልግና ፡ አምጣልኝ ፡ ከጓዳ ።

#አባ_ዮሐንስ
ሳልችል ፡ ቀርቼ ፡ ነው ፡ በጣም ፡ ተቸግሬ ፡
ምን ፡ ሁን ፡ ትለኛለህ ፡ ስቀመጥ ፡ ታስሬ ፡
እንዴት ፡ ብዬ ፡ ልሂድ እንደ ፡ ምን ፡ አድርጌ
መልካም ነው ጕጠቱን ላምጣልህ ፡ ፈልጌ
(አባ ፡ ዮሐንስ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፡ ገባ) ።

#አባ_ሎራ ፡ (ብቻውን) ።
ከዡልዬት ፡ መቃብር ፡ ብቻዬን ፡ ገሥግሼ ፡
መዝጊያውን ፡ ልከፍተው ፡ በቶሎ ፡ ደርሼ
መድረስ ፡ ይገባኛል ፡ በቶሎ ፡ በቅጽበት
ጊዜው ፡ ደርሷልና ፡ የምትነሣበት ።
በተነሣች ፡ ጊዜ ፡ ሮሜዎን ፡ ስታጣ ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ትረግመኝ ፡ በንዴት ፡ በቍጣ
አምጥቼ ፡ ላስቀምጣት ፡ በቤቴ ፡ ሸሽጌ ፤
ከዚያም ፡ እንደ ፡ ገና ፡ አንድ ፡ሰው ፡ ፈልጌ
ደግሞ ፡ ለሮሜዎ ፡ ሲሆን ፡ ዛሬ ፡ ማታ ፡
ጽፌለት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉንም ፡ ሐተታ ።

(ፓሪስ ፡ ካሽከሩ ፡ ጋር ፡ አበባና 'መብራት ፡ ይዞ ፡ ወደ ፡ ዡልዬት ፡መቃብር ፡ መጣ) "

#ፓሪስ
መብራቱን አጥፋው እንግዲህ ይበቃል
ሰው የመጣ፡እንደሆን ምናልባት ማን ያውቃል
እዚህ ፡ ሰው ፡ እንዲያየኝ ፡ አልፈልግምና
በል ፡ ቅረብ ፡ተጠጋ ፡ አንተም ወደዚህ ፡ና።
ጀሮህን ፡ አቁመህ ፡ ተጠንቅቀህ ፡ ስማ ፤
ኰሽታ ፡ ስትሰማ ፡ ወይም ፡ የሰው ፡ ጫማ
ምልክት እንዲሆን አፏጭተህ አስታውቀኝ ፡
አስቀድሜ ፡ እንዳውቀው ፡ ፈጥነህ ፡ አስጠንቅቀኝ፤
በል ፡ እንግዲህ ፡ አሁን ፡ አበባውን ፡ ስጠኝ ።
(ፓሪስ ፡ ሄደ) ።

#አሽከር ፡ (ብቻውን) ።
የተሻለ ፡ ስፍራ ፡ ባገኝ ፡ ደግ ፡ ነበር ፤
ይህ ፡ ቦታ ፡ ቀፈፈኝ ፡አልወድም ፡ መቃብር
(እልፍ ፡ ብሎ ፡ ሄደ ) ።

#ፓሪስ ። (በዥልዬት ፡ መቃብር ፡ ላይ) ።
ይህንን ፡ አበባ ፡ መርጨ፡ ፈልጌ ፡
ላቀርብልሽ ፡ መጣሁ ፡ በረከት ፡ አድርጌ
ገጸ ፡ በረከቴ ፡ ጸጸት ፡ ነው ፥ አበባ ፤
ሐዘን ፡ ነው ፡ ለቅሶ ፡ ነው ፡ የመረረ ፡ እንባ
ትተሽኝ ፡ ብትሄጂ ፡ ብቻዬን ፡ ቀርቼ ፡
ልጐበኝሽ ፡ መጣሁ ፡ ሌሊት ፡ ተነሥቼ ።
(አሽከሩ ፡ አፏጨ) ።
እንሆ ፡ አፏጨ ፡ ሰማሁት ፡ አሽከሬ ፤
አሁን የሚመጣ ሰው፡ ነው ወይስ አውሬ ?
ሰላም ፡ የሚነሳኝ ማነው፡ ባሁን ፡ ሰዓት ?
እንዴት ? ደግሞ ፡ ያውም፡ይዟል ፡ በእጁ ፡ መብራት!
እስክረዳው ፡ ድረስ ፡ ምስጢሩን ፡ ዐውቄ ፡
ከለላ፡ፈልጌ፡ልየው ፡ተደብቄ (እልፍ፡ ብሎ ተደበቀ)

(ሮሜዎና ፡ ቤልሻጥር ፡ መብራትና ጉጠት ፡ ይዘው ፡ መጡ) ።

#ሮሜዎ
በል መብራቱን ስጠኝ፤ አንተ ግን ተመለስ
እገባለሁ ፡ እኔ ፡ መቃብሯ ፡ ድረስ ፤
አንተ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡ እንዳትንቀሳቀስ ፡
ዦሮህን ፡ አቁመህ ፡ ሰው ፡ ሲመጣ ፡ ስማ
ተደብቀህ ፡ ጠብቅ ፡ እዚህ ፡ በጨለማ ።
ያየህ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ሰው ወዲህ ሲመጣ፡
ከተደበቅህበት ፡ ቦታ ፡ ሳትወጣ ፡
በፉጨት ፡ ምልክት ፡ እኔን ፡ አስጠንቅቀኝ
ምናልባት ፡ ሰው ደርሶ ድንገት ፡ እንዳያየኝ
የዡልዬት ፡ ሬሳ ፡ ካለበት ፡ ገብቼ ፡
በመቃብሯ ፡ ውስጥ ፡ እሷን ፡ ተመልክቼ ፡
ካየኋት ፡ በኋላ ፡ ከልቤ ፡ አልቅሼ ፡
አንብቼ ፡ ሲያበቃኝ ፡ ሐዘኔን ፡ ጨርሼ ፡
የጣቷን ፡ ቀለበት ፡ አውልቄ ፡ ከሷ ፡ ላይ ፡
ልወስድ ፡አስቤያለሁ ላንድ ብርቱ ጕዳይ
ከወጣሁ ፡ በኋላ ፡ እኔ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡
ይህንን ፡ ደብዳቤ ፡ ጨምረህ ፡ ሰላምታ ፡
ላባቴ ፡ ስጥልኝ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ ተጠንቀቅ ፤
ምን ፡ ይሠራል ፡ ብለህ፡ አሳቤን ፡ ለማወቅ
መሰለል ፡ አስበህ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ አትጠጋ ፤
ያገኝሃልና ፡ የመሞት፡ አደጋ ፡
በውነቱ ፡ ባገኝህ ፡ ይህንን ፡ ስትሠራ ፡
እጄም ፡ አያዝንልህ ፡ መንፈሴም ፡ አይራራ
ልብ ፡ በል ፥ተጠንቀቅ ለሕይወትህ ፡ ፍራ

#ቤልሻጥር
እኔ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡ አልንቀሳቀስም !
ስታስጠነቅቀኝ፡ትእዛዝ ፡ አላፈርህም። (ሮሜዎ'ሄደ)።

#ሮሜዎ ፡ (የዡልዩትን መቃብርዋን ' በር
ሊከፍት ፡ ይታገላል) ።
ከጥንት ፡ ጀምረህ ፡ ብትበላ ፡ ብትበላ ፡
ጠገብኩኝ ፡ የማትል ፡ ሆድህ ፡ የማይሞላ
መቃብር ፡የሚሉህ አንተ መጥፎ ከርሣም
ለወጣት ፡ አታዝን ፥ ለቆንዦ ፡ አትሣሣም
ዡልዬትን ፡ ከጥርስህ ፡ ፈልቅቄ ፡ ላወጣ ፡
መጥቻለሁና ፡ የዋጥከውን ፡ አምጣ ፡
አንዴ ፡ ልያትና ፡ እንባዬን ፡ አፍስሼ ፡
እርሜንም ፡ አውጥቼ ፡ ተራዬን ፡ አልቅሼ ፡
ሐዘኔን ፡ ገልጬ ፡ ከበቃኝ ፡ በኋላ ፡
እኔንም ፡ ከሷ ፡ ጋር ፡ አብረህ ፡ እንድትበላ

#ፓሪስ
መብራት ፡ በጁ ፡ ይዞ ፡ የመጣው ፡ ከደጅ
ሮሜዎ ፡ ይመስላል ፡ ያ የሞንታግ ፡ ልጅ፡
ጐበዙን ፡ ቲባልትን ፡ የዡልዬትን ፡ ዘመድ ፡
አሁን ፡ በቅርብ ፡ቀን ተጣልቶት ፡ በመንገድ
ገድሎ ፡ ተፈርዶበት ፡ ተሰዶ ፡ የወጣ ፡
አሁን ፡ ደግሞ ፡ እዚህ ፡ ምን ፡ ሊፈጥር፡ መጣ?

💫ይቀጥላል💫
#ነፍስ_አድን

የሥጋና የነፍስ ጠብ
የሕይወት ውስጥ ፍልሚያ
ንሮ ንሮ
ከሮ ከሮ
ድል ነሺውም በማክተሚያ
ሥጋን ገሉ ቀብሮ
ቆጥሮ እንደ በድን
ያዳም ዘርን ከጣር
ከሥቃይ ሚያድን
የነፍስ ነፃ አውጪ
ጎን ሚያደነድን
ሞት ኮ ብቻ ነው
የነፍስ ነፍስ አድን፡፡

🔘በፋሲል🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በክፍለማርያም

...አብረን እናሳድግ በሚል አስተያየት
ቤዛዊት እና ፍፁም ለደቂቃዎች ቃላት ሳያወጡ ማሃላቸዉ ባለዉ ሽቦ በአይኖቻቸው እየተያዩ ነገር ግን ሁለቱም ልቦቻቸዉ ተጨንቀዉ ሀዘን የተበረዘበት ፍንጣቂ ደስታን ተሸክመዉ በአይኖቻቸዉ ፍቅርን አብሮ መሆንን ተርበዉ ጥቂት ከተያዩ በኋላ
"ልጃችንን ወልጄ በፍቅር አሳድገዋለሁ"
ቤዛዊት ይሄን ስታወራ የእንባ ሳግ አፍዋ ዉስጥ እንቅ እያረጋት ለማልቀስ እያኮበኮበች ነበር
ፍፁም ከእስር የመፈቻ ጊዜዉ በጣም እሩቅ ስለሆነ ያለእሱ የምታሳለፍቻዉ አመታት እየታያት
በተለይ ያ ጠይም መጀመርያ የትምህርት ቤቱ በር ላይ አይታዉ ደስ ብሏት ሰአት የጠየቀችዉ
ነገሮችን ያስተማራት የመከራት ህመሟን ችሎ እያስታመማት ስታጠፋ ስትበድለዉ ከጎኗ ያልራቃት ሁሉ ነገሯ የሆነዉ ፍፁም በእሷ ህይወት በተያያዘ ጉዳይ በድንገተኛ ፀብ የሰዉ ነብስ አጥፍቶ ለእስር ተዳርጎ ፊት ለፊቷ ቆሞ ስታየዉ ልጅ ከእሱ ማርገዟን የደስታ ዜና ይዛ እንኳን ደስታዋ ሙሉ ሊሆን አልቻለላትም
የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ልቦናዋ ያዉቀዋል የጎደለዉ
ፊት ለፊቷ የቆመዉ የቀድሞዉ አስተማሪ ፍፁም ደምሴ ነበር።

"የምታለቅሺ ከሆነ እቀየምሻለሁ"
ፍፁም ቆጣ ሲልባት ማልቀሷን ተወችዉ
ከቤዛዊት ጋር እንደተለያየ ፍፁም ልጁን መዉለዷ መልካም ነዉ ወይ ሲል እራሱን ጠየቀ
ባትወልደዉ እና ወደ ፊት ሌላ ጥሩ አሳቢ መልካም ባል አግብታ ከእሱ ብትወልድ እያለ አስቦ ነበር ቤዛዊት ወልጄ በፍቅር አሳድገዋለሁ ያለችውን ሲያስታዉስ ሀሳቡን በምንም ተአምር እንደማትቀበለዉ ሲገባዉ ያሻዋን ታርግ ሲል ማሰቡን እርግፍ አርጎ ተወዉ።

መታሰር ከማሰብ ባያግድም ከተግባር ግን ስለሚያግድ ከጎኗ ሆኖ ምንም ሊያረግላት ስለማይችል ለመምከር ይሞክራል እንጂ እሷ የፈቀደችዉን ሁሉ እንድታረግ ከልቡ ፈቅዶላት ነበር
ቤዛዊት ፍፁምን ጠይቃዉ እየተመለሰች መንገድ ላይ ለፍፁም የነገረችዉን የምስራች ለቤተሰቦቿም መናገር እንዳለባት ገምታ የሚሰጡዋትን መልስ ለመስማት ጉዋጉታ ወደ ቤቷ አመረች ።

ቤት ዉስጥ ሁሉም ተሰብስበዉ ምግብ ቀርቦ ከተመገቡ በኋላ ማእዱ ተነስቶ ቡና ለመጠጣት አየጠበቁ ቤዛዊት
"የምነግራችሁ ትልቅ ጉዳይ አለ"
የሁሉም ሰዉ ጆሮ እና ቀልብ እሷ ላይ አረፈ።
ቤዛዊት በሽታዋ የተነሳባት አሁን ደሞ ምን ልትለን ይሆን እያሉ ነበር ቤተሰቦቿ
ቤዛዊት ወሬዉን ከመጀመሯ በፊት ኮስታራዉን አባቷን በቀስታ አይታቸዉ
"ይሄን የምነግራችሁ እናንተ የኔ የምወዳችሁ ቤተሰቦቼ ስለሆናችሁ ስለማከብራችሁም ነዉ
ነገር ግን የራሴን ዉሳኔ እንድትጋፉኝ አልፈልግም.."
ትንፋሽ ለመሳብ ንግግሯን ገታ አረገች
እናት እና አባቷ እየተያዩ ነበር ቀጥላ የምትለዉ ለመስማት ወደ ዋና ሀሳቧ እንድትገባ አስበዉ ምን ልትላቸዉ እንደ ሆነ ለመገመት እንኳን ስላልቻሉ ታላቅ እህቷ ከተቀመጠችበት ተነስታ ከቤዛዊት አጠገብ ቆማ እህቷን እያቀፈቻት
"ምን ለመናገር ፈልገሽ ነዉ ምንም ይሁን ግን እኔ ሁሌም ከጎንሽ አለሁ"
ድጋፏን አቅፋ ገለፀችላት
ቤዛዊት ካቆመችበት አንገቷን ወደ መሬት አቀርቅራ
"እኔና ፍፁም ልጅ ልንወልድ ነዉ"
ይህንን እንዳለች አባቷ ከተቀመጡበት ተነስተዉ ቆመዉ
"እየቀለድሽ መሆን አለበት ከነብሰ ገዳይ አርግዣለሁ እያልሽን ባልሆነ"
የፌዝ ሳቅ እየሳቁ
ቤዛዊት ካቀረቀረችበት አንገቷን ቀና እያረገች አባቷን እያየቻቸዉ
"አባ አብጄ ታምሜ እኔን ማየት ካልወደድክ የኔን ተስፋ የኔን ፍላጓትን ለማሙዋላት ምን
የሚይዝህ ነገር አለ ነዉ የኔ ሀዘን እንጂ ደስታዬ ትርጉም አይሰጥህም"
ቤዛዊት አባቷን እንዴት ታስረዳቸዉ በምንም ሊረዷት አይችሉም በቆመችበት ልብሶቿን እያወላለቀች
"ይሄ ከሆነ የሚያስደስትህ ኡ ኡ እያልኩ ከዚህ ቤት አወጣለሁ"
ቤዛዊት ሆን ብላ የአባቷን ልብ ለማየት ነበር ይሄንን ማረግ የጀመረችዉ ያሰበችዉም ተሳካላት አባቷ ልብስ እያወላለቀች ሲያይዋት ተጠግተዉ ያወለቀችዉን ልብስ እንድትለብስ እየረዷት
"ያንቺን ደስታ እነጂ ሀዘንሽን መቼም አስቤ አላዉቅም"
ሲሏት ቤዛዊት የጀመሩትን ወሬ ሳታስጨርስ አቀፈቻቸዉ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1