አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ለራስ_የተፃፈ_ውዳሴ

ስላንቺ ቁንጅና
ስላንቺ ቁመና
ከንፈር እና ዳሌ
ጥርስና ተረከዝ ፥ ፀጉር ገለመሌ
ለጡት ለወገብሽ ፥ ለፀባይሽ ጭምር
በግጥም በዝርው ፥ ባድናቆት ስዘምር
እስከዛሬ ድረስ...
ውበትሽን አግንኜ ፥ ሰርክ መለፈፌ
እኔ ስለራሴ
አንዳች ቀን እንኳ ፥ ግጥም አለመፃፌ
ሲትጠዪኝ ቆጨኝ
ቢሆንም ቆንጆ ነኝ፡፡
እርግጥ ነው ብዙዎች
ስለኔ ሳወራ ፥ ድንገት ያኮርፉኛል
"ያንተን ሌሎች ያውሩ” ፥ ብለው ይነግሩኛል
እኔ ግን እላለሁ!
“እኔን ከኔ በላይ
እርግጠኛ ሆኖ ፣ ሌላ እንዴት ያውቀኛል?!”
እናም እኔ ማለት
ቁመቴ ከአክሱም ፥ በእጥፍ ይረዝማል
ጣፋጭ አንደበቴ
መስማት ለተሳነው ፥ ለስልሶ ይሰማል
ውብ አረማመዴ
እንኳን መንገደኛን ፥ መንገድን ያቆማል፡፡
የከንፈሬ ወዙ ፥ ጥፍጥናው አያልቅም
ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው!
ሺ ሟች ላለማየት ፥ ኗሪ ፊት አልስቅም፡፡
ከዐይኖቼ ብሌን ውስጥ ፥ ብርሐን ይፈልቃል
አይኔን ያየ ሁሉ
ብርሃን እንዳይጎዳው
በእጆቹ መዳፍ ; ዐይኑን ይደብቃል።
የገላዬ ጠረን ፥ ከሽቱ እጥፍ ነው
መልካም ጠረን ሁሉ
አለ ባሉት ስፍራ ፥ እኔ አለሁ ማለት ነው፡፡
ፀባየ ትሁት ነኝ ፥ ምጡቅ ነው እውቀቴ
ግርማ ሞገሳም ነው ፥ ተክለ ሰውነቴ
ሁሉ ይወደኛል
የወደየኝ ሁሉ ፥ መቼም አይጠላኝም
ከዚ በላይ እንኳን
ብዙም ስለራሴ ፥ የማውቀው የለኝም፡፡
እንደውም እንደውም...
አልጎርርም እንጂ !
ያ'ፈር ሰውነቴን ፥ በቁንጅና አብየው
ቆንጆ ማየት ሲያምረኝ ፥ ራሴን ነው ማየው፡፡
ቢሆንም ቆንጆ ነኝ!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅርን


#ምእራፍ_ሁለት


#ክፍል_አንድ

#በክፍለማርያም

ፀሀይዋ ለመጥለቅ ጥቂት ሰዐታት ይቀራታል እስዋን እየተመለከቱ ብዛት ያላቸዉ ወንዶች ግቢዉ ዉስጥ ከወዲህ ወድያ ይንጎማለላሉ።

ፍፁም በብቸኝነት ተቆራምቶ ከተቀመጠበት ጥግ ተነስቶ ቆመና ወደ ሰፊዉ ክፍል አምርቶ ወረቀት እና እስኪርቢቶ አንስቶ መፃፍ ጀመረ።
ለመጀመርያ ጊዜ ቤዛዊትን ያገኛት ቀን ሰአት ጠይቃዉ ስትሰድበዉ ታሪኩን እየፃፈ ከታሰረ ለመጀመርያ ጊዜ ፊቱ ላይ ፈገግታ ተነበበ መፃፉን አላቋረጠም የሚያስታዉሳቸዉን የእሱን እና የቤዛዊትን ታሪክ ወረቀቱ ላይ እየከተበዉ ነዉ።
ትምህርት ቤት ዉስጥ የጠቀሰችዉን ሲያስታዉስ ድምፅ አዉጥቶ መንከትከት ጀመረ ከጎኑ የነበሩት እስረኞች እየገላመጡት ከአጠገቡ ተነስተዉ እራቁት ማንም ሰዉ ያንተን ህመም እንዳንተ አያመዉም
ማንም ሰዉ አንተ ያሳለፍከዉ ከባድ ነገር ለእሱ ክብደቱ አይታወቀዉም
መሸከም ስትችል ተቋቁመሀዉ ስታልፍ ያበረታሀል እንጂ አቅቶህ ስትወድቅ የሚያነሳህ ውስን ነዉ።

መፃፉን እየቀጠለ ነዉ ቤዛዊት ፅፋ የምትሰጠዉን ወረቀቶች አሁንም ድረስ ያስታዉሳቸዋል
ህመሟን እብደቷን ሳያዉቅ ቀሚስሽ አጥሯል ሲላት ጠልፎ የሚጥል እረጅም ቀሚስ ለብሳ ቤቱ የመጣችዉንም አልረሳዉም አሁንም እንደታመመች አዉቆ ስላልተዋት ስላልራቃት በራሱ ደስተኛ ነዉ።

ቤዛዊትን ሲያስብ ፈገግታዋ የፊቷ እንቅስቃሴ አይኑ ላይ ይታየዋል ሳቋ በጆሮወቹ ዛሬም ያስተጋባሉ
ንዴትዋን ኩርፊያዋን ህመሟን ሲያስብ ብታናድደዉም ስለተላመዳቸዉ እንደ እንከኖቿም አይቆጥርባትም
የእሱን በድንገት በአጋጣሚ ፍቃዱ የሚባልን የተረገመን ፍጥረት በንዴት ተገፋፍቶ መግደሉን ሲያስብ ፀፀት መላ ሰዉነቱን እየወረረዉ የጀመረዉን ፅሁፍ አቁዋርጦ ማልቀስ ጀመረ።

ፍፁም እስር አልተመቸዉም ለነገሩ መታሰር ለማን ይመቻል ገና አሁን ወዳለበት የእስር ግቢ እንደገባ የሬሽን መዝገብ ዉስጥ ስሙ ስላልተካተተ ደረቅ ዳቦ ብቻ ቀምሶ ትራስ እያስፈለገዉ
ፍራሽ ላይ ጋደም አለ ለማሰብ ግዜ አላገኘም እራሱን ሀይለኛ ህመም እየተሰማዉ ነዉ።
ሰዉነቱ በትኩሳት ግሎ ነገር ግን ብርድብርድ እያለዉ እየተንቀጠቀጠ ለሊቱን እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነጋ
የመከራ ለሊት ይረዝማል ከታሰረ ሳምንት ወራት የቆየ ይመስለዋል ጠዋት ለህክምና የእስር ቤቱ ግቢ ካለዉ ክሊኒክ ለመሄድ ቢሞክርም ወረፋ ስላለ እንዲታገስ
ስለተነገረዉ መራመድ እያቃተዉ በልቡ
"መሞቴ ነዉ"
እያለ እንደምንም ፍራሹ ላይ ወድቆ ለመተኛት ሞከረ።

ቤዛዊት አይምሮዋ እየተረጋጋ ሲመጣ እማማ ስንቅነሽን ለፍፁም ምግብ እንዲቋጥሩለት አርጋ በተዘበራረቀ ስሜት ዉስጥ ሆና እንባ እየተናነቃት ወደ ፍፁም አመራች
እስካሁን ፍፁም ፍቃዱን መግደሉን አላመነችም
"የማይሆን የማይታሰብ ነገር"
ትላለች ከአፏ እያመለጣት ስትራመድ
የእስር ቤቱ ግቢ መግቢያ ስትደርስ የልብ ምቷ መፍጠን ጀመረ
ፍፁምን ካየችዉ ቆይታለች በፖሊሶች ታጅቦ ሲያልፍ ካየችዉ ወድያ ምንም የምታስታዉሰዉ ነገር አልነበረም እድሜ ለእማማ ስንቅነሽ እና ለልጃቸዉ ለጌታቸዉ ስታስቸግር ስትረብሽ ተንከባክበዉ ለዛሬ እንድትበቃ ላገዟት
ዉስጥ ገብታ የምትፈልገዉን ሰዉ ስም ተናግራ ቆማ መጠበቅ ጀመረች።
ፍፁም አይኖቹ ቀልተዉ ደም መስለዋል በተኛበት ፍራሽ እንደሰመመን "ፍፁም ደምሴ"
እየተባለ ሲጠራ ይሰማዋል መነሳት ግን አልቻለም
በሞት እና በህይወት መሀል ያለ እየመሰለዉ ሲያጣጥር ቆይቶ የቤዛዊት ምስል ፊቱ ላይ ድቅን ስላለበት አይኖቹ እንባ አዝለዉ እንደምንም ተነስቶ ለመቀመጥ ሞከረ
"ፍፁም ደምሴ ጠያቂ መጥቶሎታል"
የሚል ድምፅ ስለሰማ እያቃሰተ ወደ ዘመድ ጥየቃዉ ቦታዉ ለመሄድ መታገል ጀመረ።
ቤዛዊት እንደሆነች አስቀድሞ ልቡ አዉቆታል ጥቂት እንደተራመደ ግን የማጥወልወል ስሜት
ስለተሰማዉ ለመረጋጋት አስቦ ለመቆም ሲሞክር ወደቀ ጨለማ እየታየዉ የነበረ ቢሆንም ቀስበቀስ ጨለማዉም ጠፍቶ እራሱን ስቶ ወድቆ ቀረ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍3
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ምእራፍ_ሁለት (#ክፍል_ሁለት)


#በክፍለማርያም

...ወድቆ ቀረ
ቤዛዊት ከዘመድ መጠየቅያዉ ስፍራ ቆማ የፍፁምን መምጣት እየተጠባበቀች እንደ መለያ ከታጠረዉ ጥልፍልፍ የሽቦ አጥር መሀል ጥዉልግ ያለዉ ፍፁም እየተንቀራፈፈ ሲራመድ
እሱን እያየች ዉስጧ ስለተረበሸ በቆመችበት

"እኔን እኔን እኔን"

እያለች ለእሱ ያመጣችለትን ምግብ የያዘ ጎድጓዳ የምሳ እቃ መሬት ላይ እያስቀመጠች
በሁለቱም እጆቿ ደረቷን ለኮፍ ለኮፍ እያረገች መድቃት ጀመረች
"ምነው ለኔ ለበሽተኛዋ ባረገዉ እሱን ፈተዉ እኔን ባሰሩኝ"
ስትል ቆይታ ፍፁም መራመድ አቅቶት ሲቆም የእሷም ልብ በድንጋጤ ቆመ
መሬት ላይ ዝልፍልፍ እያለ ሲወድቅ እስዋም እንደሱ ወደ መሬት ተንበረከከች የለበሰችዉ ጥቁርበጥቁር ቀሚስ አዋራ ለበሰ ከአይኗ እንባ እንደ ዉሀ ትኩስ ሆኖ ጉንጮቿን አቁዋርጦ ይፈሳል
አጠገቧ የነበሩት እስረኛ ጠያቂዎች እና የማረምያ ቤቱ ፖሊሶች ሊያነሷት ቢጠጉም በጉልበቷ እንደተንበረከከች አንገቷን መሬቱ ላይ ደፍታ
"አስተማሪዬን አስተማሪዬን መልሱልኝ እኔ የሚያመኝን እሰሩኝና ፍፁሜን ፍቱልኝ"
ጩሀቷን የታመቀ ብሶቷን ማሰማት ጀመረች።

ፍፁምን እስረኞች በጥንቃቄ ደግፈዉ አቅፈዉ ወደ ክሊኒኩ ለመዉሰድ ሲሞክሩ ጠዋት የመለሰዉ ህክምና ወረፋ የሚያሲዘዉ ሰዉ እየተፀፀተ እና
"ምን አለ ጠዋቱኑ እንዲታከም በፈቀድኩለት"
በሚል ስሜት ዉስጥ ሆኖ ፍፁም ህክምናውን በፍጥነት እንዲያገኝ እረዳዉ
ፍፁም አይኑን ሲገልጥ ያስተዋለዉ አሁንም እስር ቤት ግቢ ዉስጥ መሆኑን ነዉ
አካባቢዉን እየቃኘ አንድ ወጣት ነጭ ገዋን የለበሰ ሀኪም መጥቶ
"ተከተለኝ"
አለዉ ፍፁምም ከተኛበት የክሊኒኩ አልጋ ቀስ እያለ ተነስቶ ተከተለዉ
ብዛት ያላቸዉ መድሀኒት ሰጥቶት ሰዐቱን ጠብቆ እንዲዉጥ ከመከረዉ በኋላ የደንብ ልብስ የለበሰ የማረምያ ቤቱ ፖሊት ወደ መታሰርያዉ ግቢ እየመለሰዉ።

መንገድ ላይ ለዘመድ ጥየቃ እንደተጠራ ሲያስታዉስ ከጎኑ ያለዉን ፖሊስ
"ዘመድ ፈልጎኝ ነበር እባክህ አንዴ ላናግራት"
አለ በተያያዘ አንደበት በህመም ቅላፄ ባለዉ አወራር
"ምንህ ናት"
ሲል ፖሊሱ ጥያቄዉን በጥያቄ መለሰለት
"ጉዋደኛዬ ፍቅረኛዬ "
እየተንተባተበ መለሰለት
"ትንሽ አስቸግራ ነበር አልወጣም ብላ ትንሽ ቆይተን ተሽሎታል ሌላ ግዜ ነይ ስንላት ተመልሳ ሄዳለች"
አለዉና ፍፁም የታሰረበት ግቢ ሲደርሱ ለሌላኛዉ ፖሊስ አስረክቦ
"ፈጣሪ ይማርህ"
ብሎ ተለየዉ።

(ከደቂቃወች በፊት)
ቤዛዊት በርቀት ፍፁምን በሽቦዉ አጮልቃ አፋፍሰዉ ሲወስዱት እየች
ሽቦዉን እየነቀነቀች መጮኋን አላቋረጠችም ነበር ፖሊሶች ሊያረጋጓት ቢሞክሩም የምትሰማበት ጆሮም ልብም አልነበራትም እናት አባት እንደተሞተበት ትኩስ ሀዘን ከልቧ አምርራ
"አረ ወገን አረ ፖሊስ አረ ወንድም አረ እህቴ"
እያለች ፊት ለፊቷ ያየችዉን ሰዉ ሁላ በለቅሶ እየለመነች
"አስፈቱልኝ አስለቅቁልኝ አስተማሪዬ እኮ ነዉ
ወደቀ እኮ ወ ደ ቀ አረ ላንሳዉ ኡኡኡኡ አረ የሰዉ ያለ..."
ልብሷ እንዳለ በአቧራ ተላዉሶ ፀጉሯን እያመነቃቀረች ደረቷን እየደቃች ስታስቸግር በሁኔታዋ ግራ የተጋቡት ፖሊሶች በስንት ልፋትና ትግል አረጋግተዋት ፍፁም ደህና እንደሆነና ህክምና እያገኘ እንደሆነ አስረድተዋት በፈለገችዉ ሌላ ቀን መጥታ ማየት እንደምትችል ነግረዋት እስከግቢዉ በር ደግፈው ሸኙዋት።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ስድስት


አሁንም ፡ ፡ ይሻላል ፡ ብታየው ፡ አስተውለህ ፤

የደረቀ፡ደም፡ነው፡ዝገት፡የመሰለህ

#ቲባልት
ኧረግ ፡ እንዲህ ፡ነው ፡ ወይ ! የበግ ፡ ነው ፡ የዶሮ ?

#ቤንቮሊዎ
ፈሶ : የተገኘ ፡ ካንገቱ ፡ ጕረሮ ፡
የወገንህ ፡ ደም ፡ ነው ፡ ከበግ ፡ የማይሻል

#ቲባልት
በመሳደብ ፡ ብቻ ፡ ጊዜያችን ፡ ይመሻል ፡
እንግዲህ፡ ይቀጥል ፡ የወንዶቹ ፡ ሥራ ።
(#ሻምላ#መዘዘ)።

#ሜርኩቲዎ
ዘወትር፡ዝግጁ፡ነኝ፡ማንንም፡አልፈራ፤(#ሜርኩቲዎም #መዘዘ)
(ሮሜዎ ፡ መጣ) ።

#ቲባልት
ከናንተ ፡ ኣልዋጋም ፡ መጣ ፡ የኔ ፡ እኩያ ፤
ስማኝ ፡ ሮሜዎ ፡ ወጥቼ ፡ ገበያ ፡
አቃተኝ ፡ ለማግኘት ፡ ፈልጌ ፡ ክፉኛ ፡
አንተን ፡ የመሰለ ፡ የወንድ ፡ መናኛ ።

#ሮሜዎ
ተፍቋል ፡ ጨርሶ ፡ ቂም ፡ በቀል ፡ ከልቤ ፤
በመጥፎ ፡ ንግግር ፡ ሮሜዎን ፡ ሰድቤ ፡
ላስቈጣው ፡ በማለት ፡ ቂሙን ፡ ልቁስቀሰው ፡ ማለት በከንቱ ፡ ይደክማል ፡ የተጣጣረ ፡ ሰው' .
የፍቅሬ ፡ ምክንያት ፡ ሆኗልና ፡ ብርቱ ፡
ቲባልት ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ አትድከም ፡ በከንቱ

#ቲባልት
ኀይለኛው ፡ ቂማችን ፡ ያከማቸው ፡ ዕዳ ፡
መች ፡ እንዲህ 'ይፋቃል ፡ ይልቅ ፡ ተሰናዳ

#ሮሜዎ
ቲባልት ፡ ስማኝ ፡ እኔ ፡ ንጹሕ ፡ ነኝ፡ ከቂሙ
ካፑሌ ፡ የሚሉት ፡ የዘራችሁ ፡ ስሙ ፡
እንደ ማር፡ ጣፋጭ ነው፡አይመረኝም ለኔ
ጠባችሁ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ በውነቱ ፡ ሐዘኔ ።
የፍቅሬን ፡ ምክንያት ፡ ሳታውቀው ፡ መርምረህ ፤
አትድከም ፡ በከንቱ ፡ ክፉ ቃል ፡ተናግረህ፡
ቲባልት ፡ እኔና ፡ አንተ መቼም : አንጣላም
ደኅና ፡ ዋል ፡ ወዳጄ ፡ እንሂድ ፡ በሰላም ፡
ደግሞም ፡ ከዚህ በቀር ፡ የሕጉን ፡ ወቀሣ
የመስፍኑን ፡ ዐዋጅ ፡ ልብህ ፡ እንዳይረሳ ።

#ሜርኩቲዎ
ዦሮዬ ፡ አይሰማም እንዲህ ፡ ያለ ፡ ፍራት
ቲባልት ፡ እይ ፡ ሻምላዬ ፡ ሲያበራ ፡ እንደ ፡ መብራት ። (መዘዘ)።
ተመልሶ ፡ እንግዴህ ፡ ኣይገባም ፡ ካፎቱ ፡
በደም ፡ ካልታጠበ ፡ የዛገው ፡ ስለቱ ።
(አቲባልት'ጋራ ውጊያ'ገጠሙ)•

#ሮሜዎ
ፍጠን ፡ ቤንቮሊዎ ፡ እንገላግላቸው ፤
ሁለቱም አይረቡ በውነት እብዶች ፡ ናቸው
ቲባልት ! ሜርኩቲዎ ! አስቡት ፥ አትርሱ ፤
ልዑል ፡ በቀደም ፡ ለት ፡ ደም ፡ እንዳታፈሱ
ብለው ፡ የሰጡትን ፡ ዐዋጁን ፡ አስታውሱ
(ገላገላቸወ፡ ቲባልት' ከወገኖቹ'ጋራ'ሄደ)

#ሜርኩቲዎ
ቈስያለሁ ፡ እኮ ፡ በቃ ፡ የኔ ፡ ነገር ፤
ተበላሸሁ ፡ እኔ ፡ ወይ ፡ አለመመከር ።
ቤንቮሊዎ ፡(ቁስሉን'ያያል)"
ለካ ፡ ቁስለሃል ፡ ወይ ? አላየሁም ፡ እኮ !

#ሜርኩቲዎ
ሐኪም ፡ ይጠራልኝ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ተልኮ
(የልፍኝ' አሽከር መሄዴ) "

#ቤንቮሊዎ
አይዞህ ፡ የኔ ፡ ወንድም፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ቍስሉ ፤

#ሜርኩቲዎ
ምንም ፡ ትንሽ ፡ ቢሆን ፡ አይቀርም ፡ መግደሉ'ካፑሌና ፡ ሞንታግ ፡ ትውልዳቸው ፡ ይጥፋ፤
በነሱ፡ ምክንያት ፡ ስንት ፡ ሰው ፡ ተደፋ፡
በምን ፡ ኀጢአታችን ፡ እንሞታለን ፡ እኛ ፡
ለማይረባ፡ ነገር ፡ ተሳድቦ ፡ እንደ እረኛ ፡
በሰው፡እጅ፡ መሞት ፡ በሆነ ፡ ባልሆነው '
ከንቱ ፡ ሞት ይሉሃል ፡ እንደዚህ ፡ ያለ ነው
ተመቸውና ፡ ነው ፡ ይኸ ፡ ፈሪ፡ መጥፎ ፡
በሮሜዎ ፡ እጅ ፡ ሥር ፡ ታቹን ፡ አሳልፎ ፡
በድንገት ፡ የወጋኝ ፡ በቃ ፡ የኔ ፡ ነገር ፤
ባትገላግሉኝ ፡ አይነካኝም ፡ ነበር ።
(ሜርኩቲዎን'ቤንሾሊዎ 'ደግፎት ፡ አብረው ሄዱ)”

#ሮሜዎ ፡ (ወቻውን)
ወዳጄ ፡ ሜርኩቲዎ ፡ የመስፍኑ፡ ዘመድ ፡
አባቴን ፡ ወገኔን ፡ እኔንም ፡ በመውደድ
እንሆ ፡ቈሰለ ፡ ለኛ ፡ ሲል ፡ ተጣልቶ ፤
ቲባልት ፡ አዋረደኝ ፡ ከመሬት' ተነሥቶ
ዡልዬትን • ወድጄ ፡ ፍቅር ፡ መፈለጌ ፡
ስድቡንም ፡ ሸሽቼ ፡ ከጠብ ፡ ማፈግፈጌ፡
ወደ 'መለማመጥ ወገኖቼን ' መሪ
ወንድነት 'ያነሰኝ'አስመሰለኝ ' ፈሪ ።
(ቤንቮሊዎ መጣ)

#ቤንቮሊዎ
አልቅስ ፡ሮሜዎ ' እንባህን 'አፍስሰው
ሜርኩቲዎ ፡ ሞተ፡ መልካሙ 'ደጉ' ሰው ።
መልካሙ ፡ ወዳጄ ፡ ሜርኩቲዎ ' ከሞተ '
እንግዴህ ፡ መታረቅ ፡ ሰላም ፡ ተከተተ ፥
ጠባችን ፡ ነደደ ፡ በሉ ፡ የተነሣ ፤
ወደ ፡ ፊት ፡ ይወድቃል ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ ሬሳ
(ቲባልት' ተመልሶ ፡ መጣ)

#ቤንቮሊዎ
ቲባልት ፡ ይኸ ሰይጣን መጥፎ ፡ ጥጋበኛ
እየው ተመልሶ ፡ ሲመጣ ፡ ወደ ፡ እኛ ።

#ሮሜዎ ፡ ለብቻው' ይናገራል) "
ወይ ፡ ጥሎኝ ወይ ፡ ጥዬው አንጀቴን ላርሰው ፤
ቆይ ፡ ይምጣ ፡ ግድ ፡ የለም ፡ ደም ፡ ነው፡ የመለሰው።
ዡልዬት ፡ ደግነቷ ፡ ፍቅሯ ፡ ሰላም ፡ ሆኖ ፡
ይዞህ ፡ የነበርከው ፡ በትዕግሥት ፡ ሸፍኖ ፡
በልቤ ፡ ያለኸው ፡ የቂሜ ፡ ትኵሳት ፡
ለብልበኝ ፥ ጠበሰኝ ፡ አቃጥለኝ ፡ እንደ ፡ እሳት ።
(ለቲባልት • ይናገራል) "
ቲባልት ፡ በል ስደበኝ፡ አሁን እንደ ቅድም
የሜርኩቲዎ ፡ ነፍስ ፡ ብቻዋን ፡ አትሄድም
ወይ ፡ እኔን ፡ ወይ ፡ አንተን ፡ አንዱን ፡ ሳያስተክትል፤
ሻሞላህን ፡ ምዘዘው ፡ ዛሬ ፡ ነገ ፡ ሳትል ፡
የምትሻው ፡ ቂሜ ፡ የነደደ ፡ ይሁን ።

#ቲባልት ። ..
አንተም፡ ከሱ ፡ ጋራ ፡ ትሞታለህ ፡አሁን ።
(ይዋጉና'ቲባልት 'ይወድቃል )

#ቤንቮሊዎ
ሮሜዎ ፡ አትቁም ፡ ቶሎ ፡ ከዚህ ፡ ጥፋ ፤
ቲባልት ፡ ከሞተ ፡ ምንም ፡ የለህ ፡ ተስፋ፡
መስፍኑ ፡ ሲያገኝህ ይህን ፡ነገር ፡ ሰምቶት
ዕወቅ ፡ አይምርህም ፡ ይቀጣሃል ፡ በሞት
(ሮሜዎ 'ሸሸ ፡ ሰዎች፡ መጡ)

#ወታደር
እንዴህ ፡ ያለ ነገር ዘለዓለም ፡ የማይበርድ
ነጋ ፡ ጠባ ፡ ሬሳ ፡ በየዋናው ፡ መንገድ ፡
ጠብ መሆኑን፡ሰምተው ይኸው፡ልዑል መጡ፤
ማነው ፡ የገደለው ? አሁን ፡ በቶሎ ፡ አውጡ ።

#መስፍን
አወይ ፡ ዘመዴ ፡ ሆይ፡ ሜርኩቲዎ ፡ ሞተ፤
ማነው ፡ ጠብ ፡ ሲጀመር 'የተመለከተ?

#ቤንቮሊዎ
ልዑል ሆይ፡እኔ ነኝ'ያየሁ፡ሁሉንም ፡ ነገር !
ፈቃድዎ ፡ ቢሆን' ፈጥኝ፡ ልናገር ።

#መስፍን
ንገረኝ ፡ ሁሉንም ፡ ከምንጩ ፡ ጀምሮ፤

💫ይቀጥላል💫
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ምእራፍ_ሁለት (ክፍል ሶስት)


#በክፍለማርያም

ቤዛዊት ቤትዋን እነ እማማ ስንቅነሽ ቤት ካረገች ሰነባበተች ይሄ ሁሉ ምስቅልቅል ይፈጠራል ብላ አልነበረም ወደ እነ እማማ ቤት አመጣጧ ፍፁምንም የጋበዘችዉ በነፋሻዉ አየር ከሰዉ እራቅ ብለዉ የሰላም የፍቅር ጊዜ ለማሳለፍ ነበር
ነገር ግን አንዳንዴ ሀሳብ እንደ ንፋስ የማይታይ ሆኖ ይነፍከሳል ሀይል ካለዉም ነገሮችን ሳይጠበቅ እያንሳፈፈ እንደሚወስደዉ የታሰበዉ ሳይሆን ቀርቶ ያልተጠበቀ ነገር ይፈጠራል
ከእስር ቤቱ በር ጥቂት እንደወጣች ድንጋይ አጊንታ አረፍ አለች ጭንቅላቷ ዉስጥ ፍፁም ሲወድቅ ያለዉ ሁኔታ አሁንም ይታያታል አይኖቿ በለቅሶ ብዛት እንባ ማዉጣት ቢያቅታቸዉም ለአመል በቀስታ የሚፈሱ የእንባ ዘለላወች የአፍንጫዋን መስመር አቋርጠዉ አፍዋን እያራሱ በአገጯ አርገዉ ልብሷን እያረጠቡት ነዉ።

"ፍፁም ፍፁም ፍፁም"
በልቧ ይሄን ቃል ታነበንባለች እስካሁን መታሰሩ እዉነት አልመስልሽ እያላት እራሷን
"እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ"
እያለች ትጠይቃለች መመለስ እና መፍታት የማትችለዉ ጥያቄ ሲሆን አይምሮዋ እየተቃወሰም ቢሆን ከተቀመጠችበት ተነስታ እንባዋን በእጆቿ እያበሰች ወደ እነ እማማ ስንቅነሽ ቤት አመራች።

ፍፁም ለመጀመሪያ ግዜ መድሀኒቱን ዉጦ የሰላም እንቅልፍ ወሰደዉ በህልሙ
ቤዛዊት ፊት ለፊቱ ተቀምጣ ስትስቅ እያያት ከጀርባዋ ጥቁር አሞራ እየበረረ ትከሻዋ ላይ ተቀምጦ የማያስፈራ ድምፅ እያወጣ ሲጮህ ባኖ ተነሳ
እየነጋጋ ነበር ከእስር ቤቱ ሚዲያ ክፍል መዝሙር ድምፁ ከፍተደርጎ ተከፍቷ ይሰማዋል እስረኞች ከእንቅልፋቸዉ እየተነሱ ወደ ዉጪ እየወጡ ነዉ ተነስቶ ለመቀመጥ ሞከረ ህመም አልተሰማዉም ተነስቶ ቆመ እራሱን ለቆታል
ፊቱ ላይ ጥልቅ ብሎ የጠፋ ፈገግታ ታይቶ እየተራመደ ወደ ዉጪ ወጣ አለ።
ቤዛዊት ከተኛችበት ስትነቃ የእማማ ስንቅነሽ ልጅ ጌታቸዉ በጥቂት ተገልጧ ወደ ሚታየዉ ባቷ ሲያፈጥ ያዘችዉ ቀሚሷን እያስተካከለች ተነሳች ጌታቸዉ ግን አሁንም በአይኑ እየተከታተላት ነዉ
"ቆንጆ እንደሆንሽ ታዉቂያለሽ"
አላት ማታ የጠጣዉ መጠጥ አሁንም አለቀቀዉም አፉን አሳስሮታል
ቤዛዊት ልብ ብላ አልሰማችዉም እማማ ስንቅነሽ ቤተክርስቲያን ለመሳለም በጠዋት ስለወጡ ሁለቱ ብቻ ናቸው ቤቱ ዉስጥ ያሉት።

(ከደቂቃ በፊት)
ቤዛዊት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ዉስጥ ሆና እማማ ስንቅነሽ
"ልጄ ቤዛዊት ቤተስኪያን ደርሰን እንምጣ"
እያሉ ሊቀሰቅሷት ቢሞክሩም አልሰማም ስላለቻቸዉ እሳቸዉ ደጅ ወጥተዉ ልብሳቸዉን ቀያይረዉ ነጠላ ቢጤ ደርበዉ እንደወጡ በሩን ለመዝጋት ሲሞክሩ ልጃቸዉ ጌታቸዉ ከእንቅልፉ ይነቃል
ጥቂት አልጋዉ ላይ ሆኖ ስለ ቤዛዊት ቆንጅና ስለ ገላዋ ስለ ሰዉነቷ በህሊናዉ ሲስል ቆይቶ በቀስታ ከአልጋዉ ይነሳና ወደ እማማ እና ቤዛዊት ወደ ተኙበት ክፍል ያመራል
ቤዛዊት ብርድ ልብስ ተሸፋፍና ጥቅልል ብላ ተኝታለች ጌታቸዉ ፊት ለፊቷ እያያት ከቆመ በኋላ ብርድ ልብሱን ቀስ አርጎ ገለጠዉ ቤዛዊት አሁንም የእንቅልፍ ልብ ዉስጥ ናት
ቀስ ብሎ እረጅሙን ቀሚሷን እየገለጠዉ እና ታፋዋን እየተመለከተ ቤዛዊት ተገላብጣ ስትነቃ ፈንጠር ብሎ ቆሞ ማየቱን ቀጠለ።

(አሁን)
ጌታቸዉ ከቤዛዊት ጀርባ ቀስ ብሎ እየተጠጋ ሊያቅፋት ሲሞክር
"ምን መሆንህ ነዉ"
እያለች ገፍትራዉ አይኗን አጉረጠረጠችበት
እንደ መፍራት እያለ
"ምንም ምን አረኩ ደህና መሆንሽን ለማወቅ ነው "
እያለ ወደኋላ አፈገፈገ ነገር ግን በልቡ መጥፎ ሀሳብ ጠንስሶ ጠብቂ አገኝሻለሁ እያለ ነበር።

"ደህና ነኝ "
እያለችዉ ቤዛዊት ዛሬስ ፍፁምን አየዉ ይሆን እያለች እራሶን እየጠየቀች ለእራሷ
ዛሬማ አገኘዋለሁ አዋራዋለሁ እያለች ወጣች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ሰባት

#ቤንቮሊዎ
ጠቡን ፡ የጀመረው ፡ ክፉ ፡ ቃል ፡ ተናግሮ
ይኸው ፡ ቲባልት ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፤
ከሱ ፡ በቀር ፡ ዛሬ ፡ ጠብ ፡ ያነሣ ፡ የለም ።
እኔና ፡ ሜርኩቲዎን ፡ ሰደበን ፡ ሳንሰድበው
ሮሜዎ ፡ ደረሰ ፡ ድንገት ፡ ሳናስበው ።
እሱም ፡ በደግነት ፡ ቃሉን ፡ አለስልሶ ፡
ልዑል ፡ የሰጡትን ያዋጅ ፡ ቃል ፡ ኣስታውሶ ፡
ቲባልትን ፡ ለመነው ፡ ጠብ ፡ እንዳያነሣ ፤
መቼም ፡ መጥቷልና ፡ እሱ ፡ ግን ፡ ላበሳ ፡
በእልህ ፡ እንቢ ፡ ብሎ ስድቡን ፡ ሲቀጥል
ከሜርኩቲዎ ፡ ጋራ ፡ ተማረሩ ፡ በጥል ፤
ሻምላ ፡ ቢማዘዙ ፡ ቶሎ ፡ መገላገል ፡
አሰብንና ፡ ገባን ፡ ከነሱ ፡ መካከል ።
እኔና ፡ ሮሜዎ ፡ ስንገላግላቸው ፡
ሜርኩቲዎን ለመውጋት ቲባልት ተመቸው
እኛም ፡ አላየንም ሜርኩቲዎን ፡ ሲወጋው
ኋላ ፡ ግን ፡ አየነው ፡ ቁስሉን ፡ ከነ አደጋው
ከሽሸ ፡ በኋላ ፡ ቲባልት ፡ እንደ ፡ ገና ፡
ቢመጣ ፡ ሮሜዎ ፡ ነዶት ፡ ነበርና ፤
ደሙን ፡ ለመበቀል ፡ በንዴት ፡ ተነሥቶ ፡
ከቲባልት ፡ ጋራ ፡ በቅጽበት ፡ ተዋግቶ ፡
ወዲያው በደቂቃ ውጊያው በጣም ሲግል
እኔም ፡ ሳያደርሰኝ ፡ ችዬ ፡ ሳልገላግል ፡
ቲባልት ፡ ቆሰለና ፡ በፍጥነት ፡ ወደቀ ፥
ሮሜዎም ፡ ሸሸና ፡ በዚሁ ፡ አለቀ ፤
ከተናገርኩትም ፡ ከውነቱ ፡ የራቀ ፡
ውሸት ፡ ቢገኝብኝ ፡ ተደርጎ ፡ ምርመራ ፡
ይድረስብኝ ፡ በኔ ፡ የቅጣት ፡ መከራ ።

የካፑሌ ፡ ሚስት (መጣች)

መሠረት ፡ የለውም ፡ ምስክርነቱ ፤
ከእውነተኛው ፡ ነገር ፡ ይበልጣል ፡ ሐሰቱ '
ይህንን ፡ ቢናገር ፡ እያስመሰለ ፡ እሱ ፡
የሞንታግ ወገን ነው ልዑል ሆይ አይርሱ!
በፍርድ ሮሜዎ ፡ ይሙት ፡ ነው ፡ የምለው

#መስፍን
ሮሜዎ ፡ ቲባልትን ፡ ወግቶ ፡ ከገደለው ፡
እናንተ ፡ ስለሱ ፡ ፍርድ ፡ ስጥ ፡ ስትሉ ፡
የሜርኩቲዎን ፡ ደም ፡ ማን ይክፈለኝ ፡ለኔ
ዘመዴ ፡ ነው ፡ እኮ ፥ ሥጋዬ ፡ወገኔ ።

#ሞንታግ
ልዑል ፡ሆይ ሜርኩቲዎን ቲባልት ገደለው
ዐዋጁ 'ቲባልትን ፡ ይሙት' ነው ' የሚለው
ስለዚህ ፡ ቢያስቡት ፡ አሁን ፡ የኔ ፡ ልጅ ፤
ቲባልትን ሲገድለው ፡ዐዋጅ ፈጸመ ፡ እንጅ
ሌላ ፡ ምን ፡ ጨመረ ፡ እስቲ ምን አጠፋ ?

#መስፍን
ሞንታግ ምሕረት አለ ብለህ ፡ እንዳትለፋ፡
ሮሜዎ ፡ በፍጥነት ፡ ዛሬ ፡ ካገር ፡ ይውጣ
ጠባችሁ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ይኸው ዞሮ ፡ መጣ
በናንተ ፡ ምክንያት ፡ የሞተው ፡ ደጉ ፡ ሰው
ሥጋዬ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው ፡
በሰጠሁት ፡ ዐዋጅ ፡ ራሴ ፡ ወስኜ ፡
እገኛለሁ ፡ እኔ ፡ ጨካኝ ፡ ቀጭ ፡ ሆኜ፡
የፍርዴንም ፡ ሥራ ፡ በቅጣት ፡ ስሠራ ፡
ይቅርታ ፡ የለኝም ፡ ለማንም ፡ አልራራ ።
አማላጅ ፡ ልመና ፡ ጸጸትና ፡ ለቅሶ ፡
ፍርዴን ፡ ሊመልሱት ፡ አይችሉም ፡ ጨርሶ
ስማ ፡ ልጅህ ፡ ዛሬ ፡ የኔን ፡ ትእዛዝ ፡ ሽሮ ፡
የተገኘ ፡ እንደሆን ፡ በከተማው ፡ አድሮ ፡
ዛሬ ፡ ከቬሮና ፡ በፍጥነት ፡ ካልወጣ '
ዕወቀው ' ያለፍርድ' በሞት እንዲቀጣ ።

#ዡልዬትና#ሞግዚቷ ፡ (በቤታቸው) "

#ዡልዬት
እኔና ፡ ሮሜዎ ፡ ዕድላችን ፡ ክፉ ፤
ይደንቃል ፡ ሰርጋችን ፡ እንደዚህ ፡ ማለፉ፡
ሰርጉ አልነበረም ወይ የሰው ፡ልጅ ደስታ
እኛ ፡ ግን ፡ምስኪኖች በዚህ ፡ ሁሉ ፈንታ፡
መሥጋትና ፡ መፍራት ፡ ያባት የናት ፡ ቁጣ
ሆነና ፡ ተገኘ ፡ የተሰጠን ፡ ዕጣ ።
አልገሠግሥ ፡ አለ ፡ ጊዜና ፡ ሰዓቱ ፤
ምነው ፡ የዛሬ ፡ ቀን ፡ ደከመ ፡ ፍጥነቱ ?
ሰዓቱም ፡ ለገመ ፡ ዳተኛ ፡ መሆኑ ፡
ሮሜዎን ፡ ስጠብቅ ፡ አልመሽ ፡አለኝ ፡ ቀኑ
ደግሞ ፡ ሞግዚቴ ፡ ነች ፡ ዋና ፡ ጥፋተኛ ፤
ምነው ፡ ሆነችብኝ ፡ እንደዚህ ፡ ዳተኛ ?
በፊት ፡ ደኅንነቱን ፡ ነግራኝ ፡ ተመልሳ ፡
መሄድ ፡ ትችል ፡ ነበር ዳግም ፡ በግሥገሣ
ሌሊቱ ፡ ሲጨልም ፡ ጨረቃ ፡ ሳትወጣ ፡
ንገሪው ፡ አልኩና ፡ ሮሜዎ ፡ እንዲመጣ '
ብልካት ፡ እንሆ ፡ ቀረች ፡ እዚያው ፡ ቀልጣ
እባክህ ፡ ጨለማ ፡ ፍጠን ፡ በቶሎ ፡ ና ፤
ካልመሸ ፡ ሮሜዎ ፡ ደፍሮ ፡ አይመጣምና
ሌሊቱ' ይተካ ፡ የቀን ፡ ብርሃን ፡ ሄዶ፤
ሮሜዎን ወደ እኔ እንዲያስገባው ፡ ጋርዶ።
ቀኑ ፡ እየደከመ ፡ ብርሃን ፡ እየሸሸ ፡
ፀሓይ ፡ እየጠፋች ፡ ሰዓቱ ፡ እየመሸ ፡
አንተ ፡ ከባድ ፡ ጽልመት፡የሌሊት ፡ ጨለማ
ፈጥነህ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ አትሁን ፡ ደካማ ።
ገሥግሠህ ፡ ሸፍናት ፡ ዓለምን ፡ በጥላ ፤
ጥላህ ፡ ለሮሜዎ ፡ ይሁነው ፡ ከለላ '
ፀሓይም ፡ ጥለቂ ፤ ብርሃንን ፡ አትስጪ ፤
ኮከብ ፡ ተሰወሪ ፡ ጨረቃም ፡ አትውጪ'
ካለም ፡ ገለል ፡ በሉ ፡ ብርሃንና ፡ ፋና ፡
ብርሃን ፡ እሱ፡ ራሱ ፡ ሮሜዎ ፡ ነውና ፡
ያቻት ወዲህ መጣች ብቅ አለች ሞግዚቴ
ደርሳ እስክትነግረኝ ፡ ወሬውን ፡ ከፊቴ ፡
ቸኩያለሁ ፡ በጣም ፡ እንዴት ፡ ያለ ፡ ወሬ ፡
ይዘሽልኝ ፡ መጣሽ ፡ ሞግዚቴ ፡ ሆይ ፡ ዛሬ ?
ምነው ፡ ምን ፡ ሆነሻል ፡ ፊትሽ ፡ ተለወጠ ?

#ሞግዚት
አዬ 'ከንቱ ፡ ነገር ፡ በቃ ፡ ተቈረጠ'
ባጭር ፡ ተቀጠፈ ' ያን ፡ መሳይ ፡ መኰንን
አዬ ፡ጉድ አዬ ፡ ጉድ! ጠላሁ ሰው መሆንን

#ዡልዬት
አሁን ፡ ባሁን 'ሄደሽ ፡ ከኔ ዘንድ ፡ ከወጣሽ'
ምን ፡ዐይነት ፡ኀዘን ነው ይዘሽው የመጣሽ

#ሞግዚት
አወይ 'ሮሜዎ 'ቲባልት ፡ መልካሙ ፡ ሰው፡
እንደ ፡ፋሲካ ፡ በግ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው ።

#ዡልዬት
ሐዘኑን ' ሰምቼ ፡ ልቤ ፡ ሳይመታ፡
መናገር' አቃተሽ ፡ አፍሽ ፡ አመነታ '
ሮሜዎ ፡ ሞተ፡ ወይ ? ሞቶም ፡እንደ ፡ ሆነ
ንገሪኝ ፡ ምላስሽ ፡ እየሸፋፈነ ፡
ሳይደብቅ ፡ ገልጦልኝ ፡ መርዶውን ፡ ልረዳ
ልቤም ፡ ተሠንጥቆ ፡ በሐዘን ፡ ይፈንዳ ።

#ሞግዚት
ቍስሉንም ፡ አየሁት ፡ በጣም ፡ ያሳዝናል ፤
ሐኪም 'አይጠሩለት ፡ ሞቶ፡ ምን ፡ ይሆናል
ምንም' ትንፋሽ የለው አልፋለች ፡ ሕይወቱ፡
ደሙ ፡ ይመነጫል ፡ ቆስሎ ' ከደረቱ ፤
ከሞተ 'ቁይቷል ደርቋል ፡ ሰውነቱ "
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ሥራ መቼም ፡ አልተሠራም
ዥልዬት ፡ የዛሬ ፡ ጉድ ፡ ይቅር ፡ አይወራም
ቲባልት ! ሮሜዎ ! አየሁ ፡ ደሙ ፡ ፈሶ :
ልብሱ ፡ ተበክሎ ፡ መሬቱም ፡ ርሶ ።

#ዡልዬት
ቲባልት ! ሮሜዎ ! ሁለቱንም ፡ ጠርተሽ ፡
ከምታስጨንቂኝ ፡ ንገሪኝ ፡ ለይተሽ '
ሮሜዎ ፡ ባሌ ፡ ነው ፡ ቲባልት ፡ ዘመዴ ፤
የቱ ፡ ነው ፡ የሞተው ፡ ተጨነቀ ፡ ሆዴ
ባለም ፡ ላይ ፡ ከሌሉ ፡ እነዚህ ፡ ሁለቱ ፡
መታከት ፡ ነውና ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ከንቱ ፡
የምጽኣት ፡ ቀን ፡ ይሁን ፡ መለከት ፡ ይነፋ ፤
አሁን ፡ ተደምስሶ ፍጥረተ ዓለም ፡ ይጥፋ፡
ባሕር ፡ ጫካ ፥ ገደል ፥ ጅረትም ፡ ተራራ ፡
ፍጡር ፡ እዬዬ ፥ በል ፡ አልቅስ ፡ ከኔ ፡ ጋራ

#ሞግዚት
ሟቹ ፡ ቲባልት ፡ ነው ፡ ካለም ፡ ላይ ፡ የሄደ
ገዳዩ ፡ ሮሜዎ ፡ ካገር ፡ተሰደደ ።

#ዡልዬት
ሮሜዎ ፡ ቲባልትን ፡ ብትዪኝ ፡ ገደለው ፡
አይችልም ፡ መንፈሴ ፡ አምኖ ፡ ሊቀበለው

💫ይቀጥላል💫
#የስህተት_ሰልፍ

አንቺም የምትስቺው
እኔም ምከተልሽ ወደ ስህተት ገደል
አዳምና ሄዋን
በአርኣያ አምሳላቸው ሰርተውን ነው መሰል።
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ምእራፍ_ሁለት ( #ክፍል_አራት)


#በክፍለማርያም

..ፍፁም ወረቀቱን ገልጦ ስለቤዛዊት እና ስለሱ መከራ የበዛበት የፍቅር ታሪክ መፃፉን ተያይዞታል
ህመሙ እየተሻለዉ ስለሆነ ጥሩ ስሜት ዉስጥ ነዉ ስላለፈዉ ታሪክ እያሰበ ይፅፋል አስደሳች ጊዜወቹ ታዉሰዉት ፊቱ ላይ ደማቅ ፈገግታ እየተነበበ አእምሮዉ ላይ ያለዉን ከወረቀቱ ጋር እያዋሀደዉ ነዉ።

እንደምትወደዉ የነገረችዉን ቀን አስታወሰ ፅፋ የሰጠችዉ ወረቀት ዉል አለበት የተጣሉበትን ቀን መሀል ላይ ፍቃዱ መሀላቸዉ ገብቶ የእህቱን ፎቶ ሚስቱ ናት ብሎ ያወራ ቀን የተፈጠረዉን ሲያስታዉስ የሚፅፉት እጆቹ መንቀጥቀጥ ጀመሩ
ለቤዛዊት ሊያስረዳት ዉሸት መሆኑን ሊያብራራላት ሲጣደፍ መኪና የገጨዉን ሲያስታዉስ መፃፍ ስላልቻለ እስኪቢርቶዉን ወረቀቱላይ ጥሎ በዝምታ ተቀመጠ
ከጎኑ አብሮት የታሰረዉ ማስረሻ የተባለ ታሪሚ የፍፁምን ሁኔታ በአይኖቹ ሲከታተል ስለነበረ
"ምን እየፃፍክ ነዉ ወዳጄ?"
ሲል ለዉቀት መከላከያ ብሎ ዉሀ ዉስጥ ነክሮ አናቱ ላይ ያስቀመጠዉን ፎጣ እያወረደ
ፍፁም የጠየቀዉን ልጅ ትኩር ብሎ ተመለከተዉ ማስረሻ ቀጠን ብሎ ቀዉላላ የሚባል ወጣት ነዉ አይኖቹን ሲያስተዉላቸዉ ከተረገመዉ ፍቃዱ ጋር ተመሳሰሉበት
ለመጀመርያ ግዜ ከተቀመጠበት ተነስቶ ጮሀ
"ምን አገባት ምን አገባህ"
ደም ስሮቹ ተገታትረዉ ንዴት እያንቀጠቀጠዉ መናገሩን ተያያዘዉ
"ለምን አተወኝም ተዉኝ ተዉኝ"
እጆቹን እያወራጨ ወደ ማስረሻ ተጠጋዉ
ማስረሻ በፍፁም ሁኔታ እየተገረመ እና ጥሎት እንደመሄድ እያለ
"እብድ ድሮስ ነብሰ በላ መጨረሻዉ ማበድ ነዉ"
ብሎት ወደ ዉጪ ፍፁምን ትቶት ወጣ።
ፍፁም ግን ማስረሻ የተናገረዉ ንግግር አይምሮዉ ላይ እያቃጨለበት ነበር
"ነብሰበላ ነብሰ በላ ማበድ ማበድ"
እዉነት ነዉ የሰዉ ደም ወደ ሰማይ ይጮሀል ገዳይም የሰላም እንቅልፍ አያገኝም ማንም መጥፎ ሰው ቢሆን እንኳን የፈጠረዉ ፈጣሪ በሞት ካልወሰደዉ በቀር በሰዉ ቢገደል
ገዳዩ ሀጥያቱን ይሸከማል
ቤዛዊት መንገድ ላይ ወደ እስር ቤቱ አቅራቢያ ስትደርስ ካገኘችዉ ጥሩ ምግብ ይሰራሉ ብላ ካሰበችበት ምግብ ቤት ገብታ ለፍፁም በገዛችዉ ሰፊ የምግብ መያዣ ምግብ አስቋጠረችለት
ደስ እያላት ነው በልቧ ፍፁምን ዛሬ እንደምታገኘዉ እንደምታዋራዉ እርግጠኛ ሆናለች።
ዘመድ መጠየቅያዉ ቦታ ላይ ቆማ የፍፁምን ሙሉ ስም ተናግራ መጠበቅ ጀመረች
ፍፁም ከላይ የተጣበቀ ቲሸርት ከስር ያረጀ ቁምጣ በሲሊፐር ለብሶ ሲመጣ በርቀት ተመለከተችዉ ልቧ እየተረበሸ ነዉ አሳዘናት የሴትነት አንጀቷ ባሀሪዋም እሩሩ ስለሆነች ሆድ ብሷት እንባ ማንባት ጀምራ ሲያየኝ እሱም ይጨነቃል ብላ አስባ እንባዋን ወድያዉ ጠራረገች።
የያዘችዉን ምግብ ፖሊሶቹ ፊት ለፊታቸዉ እንድትጎርስ አዘዟት እየጎረሰች ፍፁምን በከርታታ አይኗ እያየችዉ ነዉ ፍፁም አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬቱን እያየ ምግቡን በግዴለሽነት ተቀብሏት
መሬት ላይ አስቀምጦ በጨረፍታ እያያት
"ለምን ተቸገርሽ ለኔ ብለሽ መልፋት የለብሽም እኔ የብዙ አመት ፍርደኛ ነኝ..."
የጀመረላትን ሳታስጨርሰዉ
"ሁሌም ቢሆን እጠብቅካለሁ ሁሌም"
ቅድም ያስቆመቻቸዉ እንባወቿ መፍሰስ ጀመሩ።
"አስራ ምናምን አመት..."
አለና የፌዝ ሳቅ ሳቀ
ፍፁም እራሱ ማስረሻ ካዋራዉ ጀምሮ ፀባዩ እየተቀያየረ ነበር ዉስጡ ሰላም እየተሰማዉ አደለም
እሱ በእስር እየበሰበሰ የወጣቷን የቤዛዊትን ህይወትም የቁም እስር ዉስጥ አትክተተዉ የሚል እርኩስ መንፈስ ልቡ ዉስጥ ማደግ እየጀመረ ነበር መንፈሱ ህፃን ስለሆነም እያነጫነጨዉ ነዉ።
"እንዋደድ የለ አትወደኝም ስትል ጠየቀችው ?"
ቤዛዊት አይን አይኑን እያየች
"እወድሻለሁ"
አላትና ጥቂት አስቦ
"ነብሰ ገዳይ ሰው ግን ላንቺ አይጠቅምሽም ሌላ አዲስ ህይወት መጀመር ትችያለሽ አልቀየምሽም ባንቺ ደስተኛ ነኝ ሁለተኛ ግን እኔ ጋር እንዳትመጪ"
አላትና አይኗን ላለማየት እየተጣደፈ ሳይሰናበታት ወደ እስር ቤቱ አመራ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ስምንት


#ሞግዚት
የተሠራውን ፡ ጉድ ፡ እንግዲህ ፡ ዕወቂው
እርገሚው ፡ ሮሜዎን ፡ ከልብሽም ፡ ናቂው
በቀልሽን ፡ ቂምሽን ፡ አድርጊው ፡ የጸና ፤
በውነቱ ፡ ሮሜዎ ፡ ሰው ፡ አይደለምና ።
አብነት ፡ ይሁንሽ ፡ ይህ ፡ መጥፎ ፡ ደመኛ
ሰውን ፡ አትመኝ ፡ እንግዲህ ፡ ዳግመኛ ፡
ፍቅሩም ፡ደግነቱም ፍሬ ቢስ ፡ ነው ፡ ከንቱ
ፈጽሞ ፡ ሰው ፡ የለም መጥፎ ፡ነው ፡ ሰዓቱ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ነገር ፡ ሮሜዎ ፡ ሲሠራ ፡
ማነው ፡ የሚታመን ? ማነው ፡ ባለአደራ ?

#ዡልዬት
ምንም ፡ አልተገኘ ፡ የሚበጀኝ ፡ ለኔ ፤
ሁለት ፡ ስለት ፡ ያለው ፡ ሰይፍ ፡ ነው ፡ ኀዘኔ
ቲባልት ፡ ባይሞት ኖሮ ሮሜዎ ፡ ይሞታል፤
ቲባልት ፡ ባይሸነፍ ፡ ሮሜዎ ፡ ይረታል!
ሮሜዎን ፡ ከልብሽ ፡ ትይኛለሽ ፡ ጥዪው ፤
ምነው ልቤን ገብተሽ መርምረሽ ብታዪው
ለኔም ፡ገዳይ ፡ ቢሆን ፡ ለናቴም ፡ ላባቴ ፡
ሮሜዎን ፡ ለመጥላት አይችልም ፡አንጀቴ
ቲባልትም ፡መጥፎ ነህ ፡ሮሜዎም አትረባ
መሪር ፡ ነው ፡ ከናንተ ፡ የሚተርፈኝ ፡ እንባ
ባሌ ፡ ካገር' ወጣ ፤ቲባልት ፡ ሞተ ፡ በፊት፤
ሐዘኔ ፡ ዐጓጕል ፡ የሌለው ፡ መድኀኒት ፡
እንደ ምን ፡ አድርጌ ደግሞስ ፡ እስከ መቼ
እኖራለሁ ፡ እኔ ፡ እናንተን ፡ አጥቼ ፡
ከቲባልት ፡ መሞት ፡ ሮሜዎ ፡ ስደቱ ፡
ከሮሜዎ ፡ ስደት ፡ ቲባልት ፡ መሞቱ ፡
ቢሆን ፡ ምን ፡ ቸግረው ፡ ሐዘኔ ፡ በተራ ፤
ለማንኛው ፡ ላልቅስ ፡ ወይ ፡ የኔ ፡ መከራ !
ዛሬ ፡ በሠርጌ ፡ ቀን ፡ ደስ ፡ብሎኝ ፡ መዋሌ
ቀረና ፡ ሰው ፡ ገድሎ ፡ እንዲሰደድ ፡ ባሌ '
ቲባልትም ፡ እንዲሞት ፡ አድርጎ ፡ ዕድሌ ፡
ሐዘን ፡ ከሆነ ፡ ለኔ ፡ የደገሰው ፡
ልቤ ፡ ሳያደላ ፡ እንባዬን ፡ ላፍስሰው ።

#ሞግዚት
በእውነት፡ሴት ልጅ ባሏን፡ከወደደች አይቀር
እንዳንች ፡ አድርጎ ፡ ነው ከልቡና ማፍቀር
ከልብ ፡ አዘንኩልሽ ፡ በጣሙን ፡ አድርጌ ፤
አለበት ፡ ገብቼ ፡ ሮሜዎን ፡ ፈልጌ ፡ .
እኔ ፡ አመጣዋለሁ ፡ እንባሽን ፡ አድርቂው
እመኝታ ፡ ቤትሽ ፡ ግቢና ፡ ጠብቂው ።
በስደተኛነት ፡ ሳይሄድ ፡ ነገ ፡ ርቆ ፡
ተሰነባበቱ ፡ ይምጣ ፡ ተደብቆ ።

#ዡልዬት
መልካም ፡ ነው ፡ ሞግዚቴ ፡ሙሽራ ፡ ሲገባ
አጊጦ ፡ ታጅቦ ፡ በዘፈን ፡ ባበባ ፡
በወግ ፡ በማዕርግ ፡ ባለም ፡ በደስታ ፡
በክብር ፡ ነበረ ፡ በብዙ ፡ እልልታ ፤
ሌሊት ፡ ጨለማውን ፡ ከለላው ፡ አድርጎ ፡
የኔ ፡ ሙሽራ ፡ ግን ፡ ይግባ ፡ ተሸሽጎ ።
እንቢ ፡ ብሎ ፡ እንዳይቀር ፡ጠርተሽ ፡ ስታመጪው
እንቺ ፡ ለምልክት ፡ቀለበቴን ፡ ስጪው ፡
(ቀለበቷን ፡ ሰጠቻት)

#አባ_ሎራ (ባባ ሎራ ፡ ቤት)
ሮሜዎ ፡ ብቅ ፡ በል ፡ውጣ ፡ ከጨለማ ፤
የፍርዱን ፡ ቃል ፡ ይዤ ፡ መጣሁ ልጄ ስማ

#ሮሜዎ
ሳልሰማው ፡ ቢዘገይ ፡ ይሻለኝ ፡ ነበረ ፤
ፍርዱ ፡ ምን ፡ ዐይነት ነው ? ልቤ ፡ ተሸበረ

#አባ_ሎራ
መስፍኑ ፡ ፈቀደ ፡ በቀላል ፡ ሊቀጣ ፤
የሞት ፡ ፍርድ ፡ ቀርቶ ፡ካገር ፡ እንድትወጣ

#ሮሜዎ
ጨካኝ ፡ ቅጣት ፡ እንጂ ፡ ከሞትም ፡ የከፋ
ይህ ፍርድ መሪር ነው ያስቈርጣል ፡ ተስፋ
ዥልዬት ፡ ካለችበት ፡ ከተማ ፡ ወጥቼ ፡
ስደተኛ ፡ ሆኜ ፡ አገሬንም ፡ ትቼ ፡
የምኖረው ፡ ኑሮ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ይገፋል ፣
ቀኑና ፡ ሰዓቱ ፡ ደቂቃው ፡ መች ፡ ያልፋል ፡
እንዴት ፡ እችላለሁ ፡ ዡልዬትን ፡ ለመርሳት
ሲኦል ፡ ነው ፡ ኵነኔ ፡ ሞት ፡ገሃነመ ፡ እሳት

#አባ_ሎራ
ደስታህ ፡ ቀረና ፡ በማመስገን ፡ ፈንታ ፡
ለምን ፡ ትረሳለህ ፡ የእግዜርን ፡ ውለታ ፡
ዐዋጁ ፡ የሚያዘው ፡ የሞት፡ ቅጣት ፡ ነበር'
ለምን ፡ አታስብም ፡ ይህን ፡ ትልቅ ፡ ነገር ፡
ሄደህ ፡ ብትቀመጥ ፡ በማንቱ ፡ ከተማ ፡
አገሩ ፡ ጥሩ ፡ ነው ፡ በጣም ፡ የሚስማማ
ልጄ ሆይ ፡ ቅጣቱ ፡ በጣም ፡ የቀለለ ፡
ጥሩ ፡ ነው ፡ ሺ ፡ ጊዜ ፡ ከሞት ፡ የተሻለ ።

#ሮሜዎ
ያስቡት ፡ አባቴ ፡ ነገሩን ፡ ያስተውሉት ፤
ምኑን ፡ ነው እርስዎ ቀላል ነው ፡ የሚሉት

#አባ_ሎራ
ብስጭት ፡ አታብዛ ፡ በጣም ፡ አትናደድ ፤
ከመሞት ፡ ይሻላል ፡ ሺ ፡ ጊዜ ፡ መሰደድ
ልጄ ፡ ዓለም ፡ሰፊ ፡ ነች ወጥተህ ከቬሮና
የትም ፡ ሄደህ ፡ መኖር ፡ ትችላለህና ።

#ሮሜዎ
ወጥቼ ፡ ከሄድኩኝ ፡ እኔ ፡ ከቬሮና ፡
ውሸት ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ምን ፡ዓለም ፡ አለና፡
ሕይወት ፡ ነው ፡ አይበሉት የምኖረው ኑሮ
ዓለም ፡ እዚህ ፡ ቀረ ፡ ከሚስቴ ጋር አብሮ'
ሰው ነህ እንስሳ ዕንጨት አበባና ፡ቅጠል ፡
ፀሐይ ፡ ተከልሎ ፡ አየር ፡ ሳይቀበል ፡
የኖረ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ይሞታል ፡ ይደርቃል፤
ለኔም ፡ እንደዚህ ነው ፡ ስደት የሚሉ፡ ቃል
አገሬ ፡ ንብረቴ ፡ አየሬ ፡ ፀሓዬ ፡
ዓለሜ ፡ ትንፋሼ ፡ ሕይወቴ ፡ ሰማዬ ፡
የነበረችውን ፡ ዝልዬትን ፡ አጥቼ ፡
እሷ ፡ ካለችበት ፡ ከተማ ፡ ወጥቼ ፡
መሄዴ ፡ ከሆነ ፡ እሷም ፡ ከኔ ፡ ርቃ ፡
ነጣጥለው ፡ ከለዩን ፡ የኔ ፡ ነገር ፡ በቃ ።
ሕይወቴም ፡ ኑሮዬም ፡ ሞተ ፡ ተበላሸ ፤
ደስታ ፡ ተለየኝ ፡ ከኔ ፡ ርቆ ፡ ሸሸ ፡
እንግዲህ ፡ መቆሜ ፡ ለምንም ፡ አይበጅ ፤
ይህን ፡ኑሮ ፡አይበሉት መናወዝ ነው እንጅ
ፍርድ ፡ ማሻሻያ ፡ የተባለው ፡ ዘዴ ፡
ከመርዝም ፡ ይብሳል ፡ ከጦር ፡ ከጐራዴ '
ስደት ፡ የሚሉ ፡ ቃል ፡ ጨለማ ነው ፡ ገደል
እኔን ፡ አስጨንቆ ፡ መጣ ፡ ለመግደል ።

#አባ_ሎራ
እረ ፡ ስማኝ ፡ ልጄ ፡ ምክሬንም ፡ ተቀበል ፡
ሞትና ፡ መሰደድ ፡ እኩል ፡ ነው ፡ አትበል

#ሮሜዎ
ተመልሰው ፡ ስደት ፡ ወደሚባለው ፡ ቃል ፡
ሊመጡ ፡ ነውና ፡ አባቴ ፡ ይበቃል ፡
ምን ፡ አደከመዎት ፡ በቃ በዚህ ፡ ዓለም ፡
እኔን ፡ የሚያጥናና ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ የለም
ከሞት ፡ የባሰ ፡ ነው ፡ የመከራ ፡ ጭቃ ፤
የሮሜዎ ፡ ነገር ፡ ተከተተ ፡ በቃ ።

#አባ_ሎራ
ዐውቃለሁ ፡ እንዲሆን ፡ ስደትህ ፡ መራራ ፤
ግን ፡ መድኀኒት ፡ አለው ለዚህ ፡ ለመከራ'
ዕረፍት ፡ እንድታገኝ ፡ ባሳብ ፡ በኅሊና ፡
የደረሰብህን ፡ ጭንቅህን ፡ እርሳና ፡
ልብህን ፡ መልሰው ፡ ወደ ፡ ፍልስፍና ።

#ሮሜዎ
ዡልዬትን ፡ ፈጥሮልኝ ካልሰጠኝ ፡ አምጥቶ
የመስፍኑን ፡ ብይን ፡ በጥበብ ፡ አጥፍቶ ፡
እኔን ፡ ካላዳነኝ ፡ የርስዎ ፡ ፍልስፍና ፡
ለምንም ፡ አይበጀኝ ፤ የለውም ፡ ርባና ።
(የዡልዬት'ሞግዚት'ከደጅ'ሆና'በር መታች)

#አባ_ሎራ
ተነሣ ፡ ሮሜዎ ፡ ግባ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፤
ስማ ፡ በር ፡ ይመታል ፡ መጣብን ፡ እንግዳ
ተደበቅ ፡ በቶሎ ፡ ጥግ ፡ ይዘህ ወደ ፡ ጐን
ይይዙሃልና ፡ ያገኙህ ፡ እንደሆን ።
(በሩ ይመታል)

#ሮሜዎ
በስደት ፡ ከሆነ ፡ እኔ ፡ የምቀጣ ፡
ምን ፡ ያስጨንቀኛል ፡ የፈቀደው ፡ ይምጣ

#አባ ፡ ሎራ ።
ለምን ፡ ትሆናለህ ፡ አንተ ፡እንደዚህ ፡ ደረቅ
እባክህ ፡ ግባና ፡ በቶሎ ፡ ተደበቅ ፡ (ሮሜዎ ሄደ)
እንዲህ ፡ ባሁን ፡ ሰዓት ፡ የመጣ ፡ በማታ ፡
ማነው ፡ በጨለማ ፡ በሬን ፡ የሚመታ ?

#ሞግዚት
መጥቻለሁና ፡ ልካኝ ፡ እመቤቴ ፤
የዡልዬት ፡ ሞግዚት ፡ ነኝ ያስገቡኝ ፡ አባቴ

#አባ ፡ ሎራ ።
እንኳን ፡ ደኅና መጣሽ ፡ ነይ ግቢ ወዳጄ፤
(ከፍተውላት ገባች)

#ሞግዚት
ሮሜዎን ፡ አጣሁት ፡ ብፈልገው ፡ ሄጄ ።
ይንገሩኝ ፡ አባቴ ፡ ከመሸ ፡ አሁን ፡ ማታ
አይተው ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ያለበትን ፡ ቦታ ፡

#አባ ፡ ሎራ ።
በሐዘኑ ፡ ሰክሮ ፡ ያለቅሳል
👍1
፡ ተጨንቆ ፤
ያውልሽ ፡ ከጓዳ ፡ እመሬት ፡ ላይ ፡ ወድቆ

#ሞግዚት
ዠልዬት ፡ እመቤቴም ፡ በዚሁ ፡ ሁኔታ ፡
ስታለቅስ ፡ ዋለች ፡ ይኸው ፡ እስከ ፡ ማታ ፡
ጥሩልኝ ፡ አባቴ ፡ መልክቴን ፡ ልንገረው ።
ሮሜዎ ፡ (ከጓዳ ' ወጣ) ።
ዡልዬት ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ነች?መልካም ፡ የነበረው
ልቧ ፡ ተለውጦ ፡ ባደረግሁት ፡ ነገር ፡
አልጠላችኝም ፡ ወይ ? ምላስሽ ፡ ይናገር ፡
ልብሽ ፡ አይደብቀኝ ፡ ንገሪኝ ፡ አትፍሪ ፤
ያየሽውን ፡ ሁሉ ፡ አስተካክለሽ ፡ አውሪ ።
በሠራሁት ፡ ሥራ ፡ ፍቅራችን ፡ መጥፋቱ ፡
እንግዴህ ፡ ወደ ፡ ፊት ፡ ተቀብሮ ፡ መቅረቱ
እርግጥ፡አይደለም ፡ ወይ ? እንዴት፡ ነው ፡መንፈሷ ፤
እኔን ፡ ስታነሣ ፡ ምን ፡ ትላለች ፡ እሷ ።

#ሞግዚት
በሐዘን ፡ ተጨንቃ ፡ ከማልቀስ ፡ በስተቀር ፡
ክፉም ፡ ሆነ ፡ በጎ ፡ ምንም ፡ አትናገር ፡
ቲባልት ሮሜዎ ! አዬ ፡ ጕድ ፡ እያለች ፡
እንባዋን ፡ በማፍሰስ ፡ ቀኑን ፡ሙሉ ፡ ዋለች
ሐዘኗ ፡ ግን ፡ ሆኗል፡ አለመጠን ፡ ብርቱ ፥
ከመሄድህ ፡ በፊት ፡ ተሰነባበቱ ፤
እንሂድ ፡ በቶሎ ፡ መሸብን ፡ ሰዓቱ ።

#ሮሜዎ
ገላዬን ፡ ብወጋ ፡ እስቲ ፡ ከምን ፡ ቦታ ፡
መሞት እንደምችል በቅጽበት ፡ አንዳፍታ
ብልኅ ፡ ነዎትና ፡ ጥበብን ፡ መርማሪ ፤
ተምረው ፡ እንደሆን ፡ ያከላትን ፡ ባሕሪ ፡
በፍጥነት ፡ ይንገሩኝ ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ፤
የት ፡ ነው የሰው ነፍሱ ያለችበት ፡ ስፍራ ?
አድርጊያለሁና ፡ ጸጸቷን ፡ መራራ '
ሐዘኔ ፡ጥልቅ ፡ ነው ፡ አልችልም ፡ ልጥናና
በገዛ ፡ እጄ ፡ ልሞት ፡ ቁርጫለሁና ። (ሰይፉን መዘዘ።)

💫ይቀጥላል💫
#እንዲያው_ዝም

ወድሻለሁ ፡ ማለት ፡ አይጠቅም፤አይበቃ
ፍቅሬ ነሽ ማለትም አይጠቅም አይበቃ !
ነፍሴ ፡ ነሽ ፡ ማለትም ፡ ልቤን ፡ አያርሰው

የፍቅራችን ፡ነገር ፡ ዝም፡ ነው ፤ ዝም ፡ ነው

ምን ፡ላርገው፡መውደዴን ፡ለመግለጽ በሙሉ ?
ልሳምሽ ልቀፍሽ ፡ ላልቅስ ወይ ላመሉ ?
እግርሽን ልሳም ወይ ልስገድልሽ ፡ ወይ ?
ዓዋጅ ፡ ልናገረው ፡ በያደባባይ ?
ወረቀት ልጻፍ ወይ ፤ ልላክ ወይ ደብዳቤ
እያንዳንዱን ፡ ቃላት ፡ ወልጄ ፡ ከልቤ ፤?
ገንዘቤን ልስጥሽ ወይ ሳይቆጨኝ መክሰሬ ?
ልታረድ ፡ ልሰዋ ፤ ለፍቅርሽ ፡ ለፍቅሬ ?

ይህ ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው
የልብ ፡ አያደርስም ።
በቃል ፡ ወይ ፡ በሥራ ፡ ፍቅር ፡ አይገለጽም
ይሻላል ፡መሰለኝ፡ እንዲያው ፡ ዝም ፡ እንዲያው ፡ ዝም፤
እንዲያው ፡ በደፈና ፡ ፤ እንደ ፡ ሃይማኖት ፤
ፍቅሬን ፡ ማወቅሽን ፡ ማመን ፡ መረዳት ።

🔘መንግስቱ ለማ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አምስት


#በክፍለማርያም

....ወደ እስር ቤቱ አመራ
ከጀርባው በህይወቴ አጊንቼ አጣሁዋት ብሎ በትዝታ በናፍቆት እስሩን እስኪጨርስ ከልቡ የማያወጣትን ቤዛዊትን ጨክኖባት ትቷት ጀርባውን ሰጥቷት ከእይታዋ እየራቀ ሄደ
እየተራመደ ዞረህ ተመለስ ዞረህ አዋራት ተስፋ ስጣት ስወጣ ተጋብተን ልጆች ወልደን በፍቅር እንኖራለን በላይ የሚለዉ ስሜት ቢኖርም
መጥፎዉ ስሜት በተቃራኒዉ የምን ተስፋ ነዉ የምታስበዉ ልጅቷም ህይወት አላት አንተ ህይወትህ አበቃ ታሰርክ እና እስዋ ሌላ ህይወት የላትም የሚለዉ ስሜት አሸንፎ ወደ ኋላም ሳይዞር እየተንቀራፈፈ እየተጎተተ መራመዱን ቀጠለ።

ህይወት ግን እስትንፋስ ይዛ እስከቀጠለች ድረስ የሚፈጠረው አይታወቅም አበቃ ተዘጋ ተደመደመ የተባለዉ አንድ ቀን ጊዜዉን ጠብቆ ይጀምራል ይከፈታል
ተጀመረ ተከፈተ የተባለዉም በድንገት ሊዘጋ ይችላል
ህይወትንም ዉስብስብ የሚያረጋት ገፅታ ይሄ ነዉ የተዘጋዉ በር ሲከፈት የሚገኘዉ ደስታ እና የተከፈተዉ በር ሲዘጋ የሚገኘዉ ሀዘን ሲፈራረቅ የህይወት መስመርም ከዚህ ጋር ተቆራኝቶ ይሄዳል።

ቤዛዊት ከአይኗ እየራቀ ያለዉን ከቤተሰብ ከአባት ከእናት ከእህቷ ያስበለጠችዉ ፍቅርን በእሱ የጀመረችዉ ሰዉ እርቋት ሲሄድ በቆመችበት ምንም ሳትንቀሳቀስ ከአይኗ እስኪርቅ ካየችዉ በኋላ በጥልቅ ዝምታ ዉስጥ ሆና መራመድ ጀመረች።

ትላንት ስትጮህ ስታለቅስ ያዩዋት የማረምያ ቤቱ ፖሊሶች
"እንዴት ነሽ እህት..."
እያሉ ሊያዋሯት ሊያፅናኗት ቢሞከሩም ልትመልስላቸዉ ልታዋራቸዉ ይቅርና በዙርያዋ ምን እንደሚፈጠር ሁሉ የምታዉቅ አትመስልም
የቀኝ እጇን የሌባ ጣት ጥፍር አፍዋ ዉስጥ ከታ እየቆረጠች ቢመስላትም በሀሳብ ግን ጀርባዉን ሰጥቷት የሄደዉን ፍፁምን እያሰበች
ህመሞም መጣሁ መጣሁ እያለ አይኖቿ ፍዝዝ እያሉ ትራንስፖርት ይዛ ከኋላ ወንበር ተቀምጣ መጉዋዝ ጀመረች።

"እናቱ ሂሳብ"

በተደጋጋሚ ይጮሀል የታክሲዉ ረዳት ቤዛዊት የፈዘዙት አይኖቿ እየቀሉ ታክሲዉ ላይ ከተለጠፈዉ ጥቅስ ላይ አይኖቿን ተክላ እየሰማችዉ አደለም
ከጎኗ የተቀመጠችዉ ተሳፋሪ ቤዛዊት የምታየውን ጥቅስ አየችዉ
"ቀን ሲጥል ፈራጁ ብዙ ነዉ"
የቤዛዊትን አይኖች ስታይ የሆነ ችግር ዉስጥ ያለች ስለመሰለቻት
"ከኔ ላይ ቁረጥ"
ብላ ለእረዳቱ እየነገረችዉ ወደ ቤዛዊት ተመልሳ ዞራ
"ደህና ነሽ ?"
ስትል ጠየቀቻት የቤዛዊትን ትከሻ ነካ ነካ እያረገች
ቤዛዊት አጠገቧ እያዋራቻት ያለችዉን ልጅ በሚንከራተቱት አይኖቿ እያየቻት
"እ ኔ እንጃ "
ስትል መለሰችላት
"እና አሁን ወዴት እየሄድሽ ነዉ?"
ለቤዛዊት አዝናላት አሟት ይሆን ስትል እያሰበች ልትረዳት ፈልጋ
አለም ላይ ብዙ የሰዉን መጥፎ ማየት የሚፈልጉ ለሰው መልካም የማያስቡ የተረገሙ ሰወች ቢኖሩም ሌሎች ለቁጥር የሚታክቱም ደግ እና መልካም ሰወችም አሉ።
"እማማ ስንቅነሽ ቤት እየሄድኩ ነዉ"
ቤዛዊት አፏ እየተሳሰረ ነገረቻት
ተሳፉሪዋ ከቤዛዊት ጋር አብራት ወርዳ የምትሄድበትን ቀጠሮ ሰርዛ ለመራመድ አቅም ያጣችዉን
ለህመሞ መነሳት ቋፍ ላይ ያለችውን ቤዛዊትን እያታለለች በዘዴ የእማማ ስንቅነሽን ቤት አቅጣጫ እያወጣጣቻት በእግር መጉዋዝ ጀመሩ።

"እማማ ስንቅነሽ እርሶ ኖት አደል"
አለች ተሳፋሪዋ የእማማን ግቢ ቆርቆሮ አጥር አልፈዉ ሲገቡ ቤዛዊትን ገብታ እንድትተኛ እየነገረቻት በእድሜ ገፋ ያሉ ሴትዮ ስታይ እማማ ስንቅነሽ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ ብላ
እማማ ለልጅቷ መልስ አልመለሱላትም ፈዛ ነዉልላ የቆመችዉን ቤዛዊትን እሮጠዉ አጠገቧ ደርሰዉ በእጃቸዉ ፊቷን እየደባበሱ
"ምን ሆንሽብኝ ምትኬ ምን ነካብኝ "
እያሉ ደግፈዋት ወደ ዉስጥ ካስገቧት በኋላ አልጋ ላይ እንድትተኛ ነግረዋት ልጅቷን
"የተባረክሽ ልጅ ፈጣሪ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሽ ግቢና ሻይ ጠጪ"
እያሉ እየመረቁ እንድትገባ ቢለምኗትም
"ሌላ ግዜ እመጣለሁ"
እያለች
"ልጆትን ፈጣሪ ይማርሎት"
ብላ ተሰናብታ ወጣች።
ቤዛዊት የአልጋዉን ፍራሽ እየነጨች መሬት ላይ እንደ ቄጤማ እየጎዘጎዘችዉ ነበረ።

💫ይቀጥላል...💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_ዘጠኝ


#አባ_ሎራ
ለምን ፡ ታስባለህ ፡ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ነገር ፤
ብላሽ ፡ ሰው ፡ አትሁን ፡ ሲመክሩህ ፡ ተመከር ,እንደ ፡ ሴት ፡ አታልቅስ ፡ እንዳውሬ ፡ አትቈጣ
እንደ፡እብድ፡አትበሳጭ ፥ ከሰው፡ ግብር፡ አትውጣ
ትመስለኝ ፡ ነበረ ፡ በውነቱ ፡ ጠንካራ ፤
ሰው ፡ ለምን ፡ ይረባል ፡ ካልቻለ ፡ መከራ
መቀጣት ፡ ከወደድህ ፡ በገዛ ፡ እጅህ ፡ ሞተህ ፡
ስለምን ፡ ገደልከው ፡ ቲባልትን ፡ ተዋግተህ ?
በገዛ ፡ እጅህ ፡ ብትሞት ፡ ባለማመዛዘን ፡
መግደልህ ፡ እኮ ፡ ነው ሚስትህን ፡ በሐዘን '
ለዚህ ፡ ነው ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ ኅሊናና ፡ አእምሮ ፡
ከእግዜር ፡ የተሰጠ ፡ ለሰው ፡ ልጅ ፡ ተፈጥሮ'
ዡልዬት ፡ ጠልታኛለች ፡ ብለህ ፡ ስትሠጋ፡
ሰው ፡ ልካ ፡ ጠራችህ ምሕረትን ፡ አድርጋ
ቲባልት ፡ ሊገድልህ ፡ ቢመጣ ፡ ደንፍቶ ፡
በገዛ ፡ ጥጋቡ ፡ ወደቀ ፡ ተወግቶ "
ባንተም የሞት ቅጣት ሊወድቅ የነበረው
በስደት ፡ ለውጦ ፡ መስፍናችን ፡ ሻረው '
ብትመለከተው : በውነቱ ፡ የት ፡ አለ ፤
እንዳንተ ፡ የቀናው ፡ በጣም ፡ የታደለ ፡
ተጠንቀቅ ፡ በውነቱ ፡ ልጄ ፡ በጣም ፡ ሥጋ
ሳታውቀው ፡ ብትቀር ፡ የደስታን ፡ ዋጋ ፡
ኑሮህ ፡ይበላሻል ፡ አለመጠን ፡ ፍራ ፡
ምን ፡ጊዜም ፡ አይለቅህ ፡ ጭንቅና ፡ መከራ ።
ሚስትህን ምከራት ፡ እንዳትሞት ፡ አልቅሳ
መምሸቱ፡ነውና፡ በል ቶሎ ፡ ተነሣ፡
ነገ ፡ ግን ፡ ለመሄድ ፡ ልብህ ፡ይሰናዳ ፤
ውጣ ፡ ከቬሮና ፡ ሌሊት ፡ በማለዳ
ተዛውረህ ተቀመጥ ፡ ሄደህ ፡ ወደ ፡ ማንቱ
እኛ ፡ ጊዜ ፡ አግኝተን ፡ ሲመቸን ፡ ሰዓቱ ፡
ወገኖቻችሁን ፡ በምክር ፡ አስታርቀን ፡
ጋብቻችሁንም ፡ በገሃድ ፡ ኣስታውቀን ፡ .
ላንተም ፡ ከመስፍኑ ፡ ምሕረትን ፡ ጠይቀን
እንጣጣራለን ፡ ቶሎ ፡ እንድትመለስ
እግዜር ፡ይጠብቅህ በል እስከዚያ ፡ ድረስ
አሁን ፡ ወደ ፡ ዡልዬት ፡ በቶሎ ሂድ ፡ ተነሥ

የካፑሌ ሚስት #ካፑሌ #ፓሪስ

#ፓሪስ
ጉዳዩ ዘገየ ፡ በመዋል' በማደር ፤
ታዲያስ እንዴት ፡ ሆነ ፡የጋብቻው ፡ ነገር ?

#ካፑሌ
ነገሩን ፡ ለዡልዬት ፡ ሳልነግር ፡ መቅረቴ ፡
ወድጄን ፡ አይደለም ፡ እንዲህ ፡ መዘግየቴ
በቲባልት ፡ መሞት ፡ አዝናለች ፡ በብርቱ ፤
ታፈቅረው ፡ ነበረ ፡ ከልቧ ፡ በውነቱ ፡
ስለዚህ ፡ ሐዘኑ ፡ ጥቂት ፡ ሳይረሳ ፡
አልቻልኩም ፡ ጕዳዩን ፡ ለጊዜው ፡ ላነሣ ፡
አድርግልኝና ፡ ከልብህ ፡ ይቅርታ ፤
እኔ ፡ እጨርሳለሁ ፡ ነገሩን ፡ አንድ ፡ አፍታ

#ፓሪስ
እውነት ፡ ነው ሐዘኑ ፈጽሞ ፡ አልተመቸም
ተስማምተንበታል ይህን ጕዳይ ፡ መቼም
እሷም እንቢ እንዳትል ፡ እናንተ ፡ አስቡበት

#የካፑሌሚስት _ ።
ግድ የለም ሠርጋችሁ ይሆናል በፍጥነት

#ካፑሌ
ፓሪስ ሆይ አትሥጋ አይዞህ ይህን ጕዳይ
መሄድ ፡ ትችላለህ ፡ ጥለኸው ፡ በኔ ፡ ላይ
እንዴት ፡ ትወጣለች ፡ ከኔ ፡ ፈቃድ ፡ ልጄ ፤
ያቀረብኩላትን ፡ መርጬ ፡ ወድጄ
ያላንድ ፡ ቅሬታ ፡ አለባት ፡ መቀበል ፤
እንዲያውም ፡ እንፍጠን ፡ ዛሬ ነገ ፡ አንበል
በይ ፡ ፍጠኝ ፡ ሚስቴ ፡ ወደ ፡ ልጅሽ ፡ ሂጂ
በዘዴ ፡ በርጋታ፡ነገሩን አስረጂ ፡
መልካሙ ፡ ልጃችን 'ፓሪስ ፡ አንቺን ፡ ወዶ ፡
እኔም ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ አባትሽም ፡ ፈቅዶ ፡
ይኸው ፡ በዚህ መሰሞን ሊያገባሽ ፡ ነውና
ተዘጋጂ፡ በያት ፡ በሙሉ ፡ ልቡና '
በል ፡ አንተም ፡ ንገረኝ ፡ እንደምትፈልገው
ሰርጉ ፡ እንዲፈጸም ለመቼ እናድርገው ?

#ፓሪስ
እንደ ፡ እኔ ፡ ሰርጋችን ፡ የራቀ ፡ ከሚሆን ፡
ቢፈጸም ፡ ይሻላል ፡ አሁን ፡ በዚህ ፡ ሰሞን

#ካፑሌ
እንግዲያው መልካም ነው ባጭር እንደግስ
ተክሊሉም ፡ ይፈጸም ፡ በሚመጣው ፡ ኀሙስ ፡
ጃጃታ ፡ አላበዛም ብዙም ፡ ሰው ፡ አልጠራ ፤
ልጄን ፡ እድራለሁ ፡ ብዬም ፡ አላወራ ፡
ሐዘን ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ቲባልት፡ በመሞቱ ፡
ቅር ፡ ያሰኛልና ፤ ዘመድ ፡ በጥቂቱ ፡
በድብቅ ፡ እንጥራ ፡ ነገር ሳናበዛ ፤
እንደዚህ 'ብናደርግ ፡ ወሬው ፡ ሳይነዛ ፡
ጉዳያችን'ያልቃል፡ያግር፡ ሰው ፡ ሳይሰማ ፤
እንግዲህ ፡ መልካም ፡ ነው ፤ በዚሁ 'እንስማማ ።

#ፓሪስ
እኔም ፡ እስማማለሁ ፡ ይሁን ፡ በዚሁ ፡ ቀን
በሉ ፡ እስከዚያው፡ድረስ፡እግዜር፡ይጠብቀን ። (ሄዳ).

#ካፑሌ ፡ (ለሚስቱ )
እንደዚህ ፡ ያለ ፡ ባል ፡ ትልቅ ፡ ሰው ፡ የበቃ
ቢሄዱ ፡ አይገኝም ፡ እግር ፡ እስቲነቃ ፡
በይ ፡ ቶሎ ፡ ፍጠኚ ፡ ወደ ፡ ልጅሽ ፡ ሂጂ ፤
ነገ ፡ ጧት ፡ አሳቧን ፡ ልቧን ፡ አዘጋጂ ።

#ሮሜዎና #ዡልዬት ፡ (በዥልዬት ' መኝታ ፡ ቤት) ።

#ዡልዬት
አይዞህ፡አትቸኵል ፡ አልነጋም ፡ ሌሊቱ ፤
ቁጭ ፡ በል ፡እናውጋ ፡ ገና ፡ ነው ፡ ሰዓቱ ፡
ተመልከት ጨለማ መሬቱን
ሲሸፍን ፡
የሰማናትም ፡ ወፍ ፡ አሁን ፡ ስትዘፍን ፡
ዞትር ፡ ልማዴ ፡ ነው ፡ ሌሊቱ ፡ ሳይነጋ ፡
መጮህ ፡ ትወዳለች ፡ እመነኝ ፡ አትሥጋ

#ሮሜዎ
ይህች ፡ የንጋት ፡ ወፍ ፡ ነች ፡ አሁን ፡ የጮኸችው ፤
ትክክል ፡ ይታያል ፡ ዡልዬት ፡ ተመልከችው
ሰማይ ወገግ፡ አለ ፡ ያው በምሥራቅ በኩል ፤
ሰዓቱ ፡ ደረሰ ፡ እንግዴህ ፡ ልቸኵል ፡
በቬሮና ፡ አድሬ ፡ ቢያገኙኝ ፡ ሳልወጣ ፡
መስፍኑ ፡ ፈርደዋል ፡ በሞት ፡ እንድቀጣ ፡
ልዳን ፡ ያልኩ ፡ እንደሆን ፡ ሕይወቴን ፡ ወድጄ ፡
መሄድ ፡ ይገባኛል ፡ አሁን ፡ ተሰድጄ ።

#ዡልዬት
እኔ ፡ መች ፡ አጣሁት ፡ ይህ ፡ ያሁኑ ፡ ብርሃን ፡
የሰማይ ፡ ፋና ፡ ነው ፡ የኮከብ ፡ ውጋጋን
ሌሊት ፡ በጨለማ ፡ ሳይነጋ ፡ ሌሊቱ ፡
ለምን ፡ ትሄዳለህ ፡ አሁን ፡ ወደ ፡ ማንቱ ፡
አይዞህ ፡ እንጫወት ሌቱ ፡ አልነጋም ፡ ገና
ጊዜ ፡ አለን ፡ እስኪታይ ፡ የንጋቱ ፡ ፋና ።

#ሮሜዎ
ዘፈኑ ፡ ሲወጣ ፡ አልሰማንም ፡ ካፍ
አልነጋም ፡ ሌሊቱ ፡ አልጮኸችም ፡ ወፍ፡
ይህም ፡ በሰማይ ላይ የሚታይ ፡ ውጋጋን አይደለም ፡ የመጣ ፡ ከፀሓይዋ ፡ ብርሃን ፡
ብለን ፡ እንካደው ፤ አምኜ፡ ልቀበል !
ሳልወጣ ፡ ይያዙኝ ፡ ተይዤም ፡ ልገደል "
ካንቺ ፡ ተለይቼ ፡ የሐዘን ፡ ኵነኔ ፡
ከሚያገኘኝ፡ መሞት ፡ እመርጣለሁ ፡ እኔ ።
አልፈራም ፡ ፈጽሞ ፡ በሞት ልቀጣ
ዡልዬት ፡ ከፈቀደች ፡ የፈለገው ፡ ይምጣ ፡
ወፎች አልተንጫጩም ሌሊቱም ፡ አልነጋ
ዡልዬት ጨዋታ አምጪ እንግዴህ እናውጋ፡

#ዡልዬት
እኔ ፡ ብዬ ፡ ነበር ፡ ገና ፡ ነው ፡ ሌሊቱ፤
አሁን ፡ ገና ፡ታየኝ ፡ ትክክል ፡ መንጋቱ ፡
ንጋት ፡ ነው ፡ የመጣው ፡ ሂድ ፡ ቶሎ ፡ ተነሣ፤
አምልጠህ ፡ ሽሽ ፡ ቶሎ ፡ ብረር ፡ በግሥገሣ ፡
እየው ፡ ተመልከተው ፡ የንጋት ፡ ወገግታ፤
ጨለማውን ቀዶ፡ ሄደ ፡ እየበረታ ፡
አስተውለው ፡ መሬቱ ፡ ሲታየን ፡ ተገልጦ ፤
አሞኘችኝ፡ ወፏ ድምፅዋ ፡ ተለውጦ ፡
ፍጠን ፡ ቶሎ ውጣ እየው፡እንደ፡ ነጋ ፤
ተነሥ ፡ ቶሎ ፡ ጥፋ፤ አይንካህ ፡ አደጋ ።

#ሞግዚት
እናትሽ ፡ ነቅተዋል' እመቤቴ ፡ ዕወቂ፤
መንጋቱ ፡ ነውና ' በጣም' ተጠንቀቂ "
ደኅና ሰንብት ፡ ልበል ፡ እኔው ፡ አስቀድሜ
እንግዴህ ፡ ደኅና'ሁን'ሮሜዎ ፡ ወንድሜ ።

#ሮሜዎ
ዡልዬት ደኅና ሁኝ ፡ ደኅና ሰንብች ፡ ፍቅሬ

#ዡልዬት
አደራ ፡ እንዳገኘው ፡ እኔ ፡ ያንተን ፡ ወሬ ፡
ሁል ፡ ጊዜ ጻፍልኝ ፡ መሆንህን ፡ ጤና ፤
መቼ ፡ እንደማገኝህ ፡ አላውቀውምና ።

#ሮሜዎ
መቼም ፡ ቢሆን ፡ ካንቺ ፡ አይለይም ፡ ልቤ
እጽፍልሻለሁ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡
ደብዳቤ ።

#ዡልዬት
አንተ ፡ ስታስበው ፡ ወደ ፡ ፊት ፡ ዳግመኛ ፡
እንገናኛለን ፡ ትላለህ ፡ ወይ ፡ እኛ?

#ሮሜዎ
አምናለሁ ፡ ፍቅሬ ፡ ሆይ ፡ አምላክ ፡ እንዲራራ፤
ትምህርት ፡ ይሆነናል 'ያሁኑ ' መከራ ።

#ዡልዬት
የሆንኩትን ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ ለራሴ ፤
መጥፎ' መጥፎ ነገር ያስባል' መንፈሴ

#ሮሜዎ
ያገኘን ፡ መከራ ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ ብርቱ ፡
ከመንፈሳችን ውስጥ አይጠፋም
ስሜቱ ፤
ዡልዬት ፡ ደኅና ፡ ሁኝ ፡ ረፈደ ፡ ሰዓቱ ፡(ሄዳ).

💫ይቀጥላል💫
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ስድስት


#በክፍለማርያም

...እየጎዘጎዘች ነበር
እማማ ስንቅነሽ እንግዳዋን ሸኝተዉ የቤዛዊት ጤንነት ፊቷን አንብበዉ እየሰጉ
"ደሞ እንዳይጀምራት"
በልባቸዉ እያሉ ወደ ቤታቸዉ ወደ ዉስጥ ሲዘልቁ ቤታቸዉ በብጥስጣሽ እስፖንጅ ተሞልቶ ቤዛዊት የማይሰሙ ቃላቶች እያነበነበች በእጆቿ ቀሪዉን የፍራሹን አካል እየቧጠጠች እና እየነጨች እየወረወረችዉ ነበር።

እንባ ተናነቃቸዉ በድህነታቸዉ በቅጡ የማያዉቋት ሴት በልፋት የገዙት ፍራሽ ተበታትኖ በማለቁም አልተፀፀቱም ሁሌ የቤዛዊትን ሲያዩዋት በህይወት የሌለችዉን ልጃቸዉ ስለምትታያቸዉ እንደ ልጃቸዉ ህመም አስበዉ
"ቤዛዊቴ ቤዛዊት ምን ሆንሽብኝ ምን ነካብኝሳ"
ከጎኗ እንደ ህፃን ልጅ ኩርምት ብለዉ ተቀመጡ
ቤዛዊት መልስ አልመለሰችላቸዉም እጆቿ ይቧጥጣሉ ከባድ ስራ እንደያዘ ሰዉ ተመስጣ ጥፋት ታጠፋለች ለእሷ የሚታወቃት ነገር የለም
"እ እህህ እህህህ እህ እህ እህህ"
ነገር እንደሚበላ ሰዉ ከንፈሮቿን በቀስታ እያኘከች ታጉተመትማለች የምታስበዉ ለእማማ ስንቅነሽ ስላልገባቸዉ እያቀፏት እና ፍፁም ብላ ያወራችላቸዉ ሰዉዬ ትዝ ብሏቸዉ
"ፍፁም ጋር ሄደሽ ነበር?"
ሲሉ ጠየቋት
ቤዛዊት የፍፁምን ስም እንደሰማች እማማ ስንቅነሽ ላይ አፈጠጠችባቸዉ
"ፍፁም ፍፁም ፍፁም"
ቃላቶቹን እየደጋገመች አይኖቿን እማማ ስንቅነሽ ላይ ተክላ ቆይታ
"ቤቴ ልሂድ ፍፁም አይመጣም"
አለችና ትንሽ እንደማሰብ ብላ
"ይመጣል እንዴ?"
እማማ ስንቅነሽን አፋጠጠቻቸዉ
"ታስሮ የለ ሲፈታ ይመጣል"
አሏት የእርጅና ነገር ሀቅ ሀቁን ሳይደብቁ እያወሩ
ቤዛዊት የሆነ ነገር ያሰበች ይመስል የእማማ ስንቅነሽን የተገነጣጠለ ኮርኒስ ላይ ካፈጠጠች በኋላ
"አይጥ ማታ ማታ በዚህ ላይ ይሄዳል አደል
እኔኮ አይጥ እፈራለሁ..."
እማማ ስንቅነሽ እንዳመማት በጤናዋ እንዳልሆነች አሁን አረጋገጡ እንባ ያቀረረ ፊታቸዉን በነጠላቸዉ እያበሱ የቆመችዉን ቤዛዊትን ወደ እራሳቸዉ አልጋ ወስደዉ እያስተኟት
"አይ ሰዉ መሆን"
እያሉ እየተብከነከኑ ቤዛዊት እንቅልፍ እስኪወስዳት ፀጉሯን እየደባበሱ አስተኝተዋት ሰካራሙ ልጃቸዉ ጌታቸዉ እንዲገባ በሩን ሳይቀረቅሩት ዘጋ አርገዉት ከጎኗ እሳቸዉም ስለቤዛዊት እና ስለበፊት ልጃቸዉ መመሳሰል እያሰቡ አሸለቡ።

ፍፁም ቤዛዊትን አዋርቶ እንደተመለሰ እሱ የሚተኛበት አቅራቢያ አናቱ ላይ ፎጣ የደረበ ሰዉ ወረቀት እያነበበ አይቶ እንዳላየ ሊያልፈዉ ሲል ማስረሻ መሆኑን ሲያረጋግጥ ፍቃዱን እንዳያስታዉስበት ፊቱን አዙሮ አልፎት ቦታዉ ደርሶ እንደተቀመጠ የቤዛዊትን እና የሱን ታሪክ የፃፈበት ወረቀት ከቦታዉ እንደሌለ ሲያስታዉስ እንደማበድ አረገዉ።
ፍቃዱን በያዘዉ ክራንች በንዴት አናት አናቱን ሲመታዉ የነበረዉ ሁኔታ አይምሮዉ ላይ ታየዉ
ክራንቹ በፍቃዱ ደም ተላዉሶ የፍቃዱ ፀጉር በደም ተለዉሶ ታየዉ አፉ ዉስጥ የሚጎመዝዝ ነገር ያለ እየመሰለዉ ምራቁን እየተፋ እየተበሳጨ ወደ ማስረሻ ተንደረደረ
"አምጣ የወሰድከዉን አምጣ አምጣ"
ሲል ማስረሻ ላይ አንባረቀበት
ማስረሻ የፌዝ ሳቅ እየሳወቀ
"እብድ አፍቅረህ ነዉ ለካ"
ሲል በንቀት ወረቀቱን የፍፁም ፊት ላይ በተነለት
"ቤዛዊት እብድ አደለችም "
መሬት ላይ የተበተነዉን ወረቀት እየሰበሰበ አጣጥፎ ኪሱ ዉስጥ ከከተተ በኋላ
"ቤዛዊትን እብድ እንድትላት ማን ፈቀደልህ
ማንስ ህይወቴን አንብብ አለህ"
ፍፁም በንዴት እየተለዋወጠ ነዉ
ማስረሻ በፍፁም ሁኔታ እየሳቀ ነዉ
በቀልድ ለዛ ባለዉ ንግግር
"ታሪክህ ሰዉ በመግደል ስላለቀ ያሳዝናል"
አለዉና አክሎበት
"ቤዛዊትን አንዱ ላፍ ያረግልሀል ኪኪ ኪኪኪ ኪኪኪኪኪ"
ተንከተከተ
አብዛኛው ሰዉ በታሪክህ ይስቅብሀል በዉድቀትህ ያላግጥብሀል በድክመትህ ይመጣብሀል
ቀን ሲጥልህ ብዙ ብዙ ነገሮች ይቀያየሩብሀል ከተከበረ አስተማሪነት ወደ ወንጀለኛ በአንዴዉ ስትለወጥ የሰዉ ደም አእምሮህ ዉስጥ ሲመላለስ ፍቅር ያልከዉ ነገር እሩቅ ሲሆንብህ አለም የተደፋችብህ ሲመስልህ የምታየዉ የሚያጋጥምህ ነገር ሁሉ አስከፊ ይሆናል
"ምንድነዉ ያልከዉ"
አለ ፍፁም ሁለቱንም እጆቹን ገትሮ ፊቱ ተቀያይሮ ወደ ማስረሻ አንገት እየተንደረደረ ደርሶ ማስረሻን ሲጥ አርጎ ይዞት ተያይዘዉ ወደ መሬት ወደቁ ማስረሻ ከስር ተኝቶ ይንፈራፈራል ፍፁም
ከላይ ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ አንቆታል።

💫ይቀጥላል ...💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ቅዥት

እኔ የሩቅ ተጓዢ - እየሔድኩ ተኝቼ
ቤት ሔጄ ልገባ - ከቤት ተነስቼ፤

በቀዳዳ አገልግል - ስንቅ ቋጠርኩና
ትሪና ብርጭቆ - ፊቴ አቀረብኩና፣
ዳቦዋን ጠጥቼ
ሻይየን ጎምጄ
ውሐየን በልቼ
ቆሜ ቶሎ ደረስኩ - ሮጨ ዘግይቼ፡፡
#አንቺ_ሙቺ ...

ኑርልኝ ብትይኝ
እንዳሻሽ ኖርኩልሽ፣
ሙትልኝ ስትይኝ
እንዴት ልቀበልሽ፣
እኔ ከሞትኩ ወድያ
ማን ያሞላቅሽ፣
ይልቅ አንቺ ሙቺ
ልውጣ ከእስርሽ !

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
👍1
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰባት


#በክፍለማርያም

በቅርብ እርቀት የነበሩ እስረኞች ለማገላገል መሯሯጥ መጯጯህ ጀመሩ
የተጣሉትን ሁለቱንም ሰወች በመከራ አለያዩዋቸዉ በፍጥነት ባይደርሱ ከባድ ነገር ይፈጠር ነበር
ፍፁም ኑሮ አለሙ ህይወቱ የጠፋ ስለመሰለዉ ተስፋ ቆርጧል
"ከዚህ በላይ ምን መከራ ይፈጠራል ከእስር ሳልፈታም እዚሁ ልሞት እችል ይሆናል ታስሬ ተቀጥቼ እንኳን እንደ ፍቃዱ አይነት መሰሪ ሰዉች ለምን አይተዉኝም"
ሲል በልቡ ይጠይቃል
የእስረኞችን መጣላት እና የገላጋዮችን መጯጯህ የሰሙ የማረምያ ቤቱ ፖሊሶች ዱላቸዉን ይዘዉ እየሮጡ ገቡ ፍፁም ማስረሻን ለቆት ጭንቅላቱን ይዞ ቆሟል ማስረሻ አንገቱን እየነካካ
"ይሄ ሰዉዬ ጤነኛ አይመስለኝም "
እያለ ያወራል
ከፖሊሶቹ አንዱ
"የተጣላችሀት ሁለታችሁም ተከተሉኝ "
ሲል ትህዛዝ ሰጠ ፍቃዱና ማስረሻ በሌላ ፖሊስ ተይዘዉ ወጡ
አንድ ረዘም ያለ ዱላ የያዘ ፖሊስ ዉጪ የነበሩት ሌሎች እስረኞች ወደ ቤታቸዉ ዉስጥ እንዲገቡ ሲያዝ ሁሉም ወደ የክፍሉ ገብቷ ግቢዉ ጭር አለ
ጭር ካለዉ ግቢ ዉስጥ ጥቂት ፖሊሶች እና የተደባደቡት ሁለቱ እስረኞች እየተፋጠጡ ለጥቂት ግዜ በመሀላቸዉ ዝምታ ሰፍኖ ቆይቶ
ፍፁምን እና ማስረሻን እያፈራረቀ ፖሊሱ እያያቸዉ
"የምን ጥጋብ ነዉ የሚያጣላችሁ"
ሲል ሁለቱም ላይ ጮሀባቸዉ ከእግር እስከራሳቸዉ በአይኑ እየቃኛቸዉ
ማስረሻ ፈጠን ብሎ
"እሱ ነዉ እኔ አደለሁም...."
እያወራ ፖሊሱ በያዘዉ ዱላ የማስረሻን እግር እየቀለጠመዉ
"ወረኛ አትለፍልፍ ዳይ ቁጭ ብድግ"
አለና ለመማታት ዱላዉን ሲያነሳ ማስረሻና ፍፁም ቁጭ ብድግ ማለቱን ተያያዙት
"እዚህ የመጣችሁት ፀባያችሁን እንድታርሙ መሰለኝ"
ፖሊሱ ቆጣ ብሎ
ፍፁም እግሩም ችግር ስላለበት እያመመው እየደከመዉ ከማስረሻ እኩል ተቀምጦ መነሳት ሲያቅተዉ ለመጀመርያ ግዜ ዱላ አረፈበት ሀይለኛ ህመም ተሰማዉ ጀርባዉን በድጋሜ በዱላዉ ሲደግመዉ በእልህ ከማስረሻ እኩል መስራት ጀመረ።
"ዳይ እንደዛዉ ቁጭ ብድግ እያላችሁ እዛ ጋር ደርሳችሁ ኑ"
ፖሊሱ ሌላ ትህዛዝ አዘዘ ወደ ኋላ የቀረ ዱላ እየቀመሰ ነበር።
ፍፁም ግን መሀል ላይ እግሩ መንቀሳቀስ ስላልቻለ መሬቱ ላይ ላቡን እየጠረገ ተቀመጠ ማስረሻም እያለከለከ ነበር
ፖሊሱም እየገላመጣቸዉ
"ሁለተኛ ፀብ ዉስጥ እንዳላገኛችሁ"
ብሎ ዝቶባቸዉ ትቷቸው ሄደ።

የእማማ ስንቅነሽ ልጅ ጌታቸዉ ለሊት እንደገባ መብራት አብርቶ ቤዛዊትን በአይኑ ፈለጋት ከእናቱ አጠገብ ሽጉጥ ብላ ተኝታለች
"ጠዋት አገኝሻለሁ"
ሲል በተኮለታተፈ ድምፅ አወራ
የቤዛዊትን ገላ መመኘት ከጀመረ ሰነባብቷል በህልሙ ሳይቀር ትታየዋለች መጠጥ እየጠጣ የሚያስበው ቤዛዊትን በፍቅርም ይሁን በጉልበት ገላዋን አቅፎ ለመቅመስ ሲቋምጥ ነበር
በፍቅር እንደማይሆን ከንግግሯ ከሁኔታዋ ስለተረዳ በጉልበት አሰገድዶ ሊደፍራት እማማ ስንቅነሽ የማይኖሩበትን ቀን በጉጉት እየጠበቀ ነዉ
ሁሌ በጠዋት ደሞ እናቱ ቤተክርስቲያን ስለሚሄዱ
"ነገ እቅዴን ለማሳካት ሁነኛ ቀኔ ነዉ"
እያለ ወደ ጉዋዳ መኝታዉ እየንገዳገደ ገባ።

ሲነጋጋ በጣም በጠዋት የተነሱት እማማ ስንቅነሽ የቤዛዊትን ሰላም ማደር በእጃቸዉ ዳበስ ዳበስ አርገዉ ካረጋገጡ በኋላ ወደ ቤተክርስቲያን አመሩ።
ለክፋት እንቅልፍ አጥተዉ የሚያድሩ አይኖች አሉ ሰዉን ለማዋረድ ለመጣል ጉድጉዋድ የሚቆፍሩ እጆች አሉ
ምንም ቢሆን ግን በመጥፎ ጎንህ በማታዉቀዉ የኔ ብለህ በተጠጋሀዉ ወዳጄ ባልከዉ ሰዉ መጠቃት ደሞ ህመሙ እጥፍ ድርብ ነዉ
የእግራቸዉን መዉጣት ሲጠባበቅ የነበረው ጌታቸዉ ሹክክ እያለ ከተኛበት ተነስቶ በሩን ከቀረቀረዉ በኋላ ቤዛዊት የለበሰችዉን ብርድ ልብስ ጎትቶ መሬት ላይ ጣለዉ።

💫ይቀጥላል ..💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍21
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስር


የካፑሌ ፡ ሚስት (የዡልዬት እናት)
ወዴት ፡ ነው ፡ ያለሽው ፡ ልጄ ፡ ተነሣሽ ፡ ወይ ?

#ዡልዬት
ይኸው ፡ ተነሣሁኝ ፡ ምነው ፡ እናቴ ሆይ ?
(ለብቻዋ ፡ ቀስ ብላ)
ምን ፡ ነካት ፡ እናቴ ፡ እንዲህ ፡ ጧት ፡ ተነሥታ ፈልጋኝ አታውቅም በማለዳ መጥታ ።
(የካፑሌ ሚስት ' ወደልጅዋ፡ወደ፡ዡልዬት መኝታ' ቤት፡ገባች

#የካፑሌ_ሚስት
ዐፈር ፡ አስመሰለሽ ፡ የቲባልት ፡ ሐዘን ፡
ያስፈልጋል ፡ ልጄ ፡ ማሰብ ፡ ማመዛዘን '
እንባ ፡ ቢያፈሱለት ፡ ቢያለቅሱለት በጣም
ሰው ፡ አንዴ ከሞተ ተመልሶ ፡ አይመጣም
ሐዘን ፡ የሚያስረሳ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ወሬ
ይዤ ፡ ወዳንቺ ፡ ዘንድ ፡ መጥቻለሁ' ዛሬ "

#ዡልዬት
እናቴ ፡ ንገሪኝ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ያለ ፡ ነው ?

#የካፑሌ_ሚስት
በቲባልት ፡ መሞት ፡ በብዙ ፡ ያዘነው ፡
ልብሽ ፡ እንዲጽናና ፡ በጣም ፡ በማሰቡ ፡
መልካሙ ፡ አባትሽ ፡ አላረፈም ፡ ልቡ ፤
በዚሁ ፡ ምክንያት ፡ ሳይውልም ፡ ሳያድር ፡
ቈርጧል ለጥሩ ባል ኀሙስ አንቺን ሊድር
ባልሽ ፡ የሚሆነው ቆንዦ ነው ፡ ጌታ ሰው
በዘርም ፡ በገንዘብ ፡ ምንም ፡የማያንሰው !
እንዲያውም ፡ ገልጨ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ ፤
መልካሙ ፡ፓሪስ ፡ ነው ፡ ወጣት ፡ መኰንኑ

#ዡልዬት
እናቴ ፡ ሆይ ፡ምነው ፡ በፊት ፡ ሳንማከር ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ እንዲህ ያለ ፡ ነገር
አስቀድመን ፡ እኛ ፡ ተጫጭተን ፡ በደንቡ፡
ሳላውቀው ሳያውቀኝ ፡በፍጥነት ፡ ተጋቡ !
እንዴት ፡ ትላላችሁ ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ?
አሁንም ፡ በቶሎ ፡ ፈልጉለት ፡ መላ'
እኔ ፡ አልችልምና ፡ ለማግባት ፡ በቶሎ ፤
አባቴን 'ንገሪው ፡ እንደ ፡ ምንም ፡ ብሎ
ቃል ቢኖር ምናልባት ለፓሪስ የሰጠው
አንድ' ዘዴ ፡ ፈጥሮ ፡ ቶሎ ፡እንዲለውጠው

#የካፑሌ_ሚስት
አፍሽን ፡ አታጥፊ ፡ ምክንያት ፡ አታምጪ '
ያለቀ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ዐርፈሽ ፡ ተቀመጪ ።

#ዡልዬት
አድምጪኝ ፡ እናቴ ፡ እንግዲያውስ ፡ ስሚ
አባቴም ፡ አይልፋ ፡ አንቺም ፡ ኣትድከሚ'
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ መቼም ፡ቢሆን ደግሞ
እኔ ፡ አላገባም ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።

#የካፑሌ_ሚስት
አልገባም ፡ ጨርሼ ፡ እኔ ፡ በዚህ ፡ ጣጣ ፤
ንገሪው ፡ ላባትሽ ፡ ይኸው ፡ወዲህ ፡ መጣ

#ካፑሌ ፡ (ገባ)
ምነው ፡ ምን ሆናችሁ ? በይ ልመለስ ሄጄ
ታዲያስ ፡ ነገርሻት ፡ ወይ ነገሩን ፡ ለልጄ ?

#የካፑሌ_ሚስት
እኔ ፡ ከሷ'ጋራ ፡ አልችልም ፡ ክርክር ፤
ትችል ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡አስረዳት ፡ በምክር ።

#ካፑሌ
እስቲ ፡ እኮ ፡ ንገሪኝ ፡ ምንድነው ፡ ነገሩ ፡
አሁን ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ደርሶ ፡ ግርግሩ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ትችል ፡ ትመስላለህ አንተ ፡ ደግሞ ፡ ደርሶ
የምሥራች ፡ « እንቢ» ፡ ብላለች ፡ ጨርሶ ፡
የመጣ ፡ ቢመጣ ፡ ይልቁንም ፡ ደግሞ ፡
አላገባም ፡ አለች ፡ ፓሪስን ፡ ፈጽሞ ።

#ካፑሌ
እግራችንን ፡ ስማ ፡ እኛን ፡ አመስግና ፡
በትልቅ ፡ ደስታ ፡ መቀበል 'ቀረና ፡
እንቢ ፡ አለች ፡ ብትይኝ ጆሮዬም ፡ አይሰማ
እስቲ ፡ ልስማው ፡ እኔ ፡ ትናገረው ፡ ደግማ

#ዡልዬት
ለክፋት ፡ አይደለም ፡ አትቈጣ ፡ አባቴ ።

#ካፑሌ
እረግ ፡ የኛ ፡ ሕፃን ፡ ትንሿ ፡ ማሚቴ ፡
የማነሽ ፡ ለዛ ፡ ቢስ ፡ የማነሽ ፡ ወልጋዳ ፤
የማነሽ ፡ አመዳም ፡ የማነሽ ፡ ገዳዳ'
ባለወግ ፡ አድርገን እኛ ፡ ነን ያጠፋን ፡
ብታውቂው ፡ ባታውቂው ኧረ ምን ፡ አለፋን
በግድ፡ ነው ፡ እንጂ፡ በኅይል ፡ የምንድር ፡
መች ፡ ያስፈልግና ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ንግግር
ነገ ፡ በማለዳ ፡ ተዘጋጅተሽ ፡ ውጪ ፣
ከተክሊሉ ፡ ቦታ ፡ ዐውቀሽ ' እንድትመጪ,
ታዛዤ ፡ ነሽና ፡ የወለድኩሽ ፡ ልጄ ፣
እኔ ፡ እድርሻለሁ ፡ በኀይል' አስገድጄ ፤
ለወግ ፡ መጠየቄ ፡ ቅብጠት ፡ነው ፡ አብጄ
እስከዚያ ፡ ድረስ ፡ ግን ፡ በፊቴ ፡ አትለፊ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ ካጠገቤ ፡ ጥፊ ።

#ዡልዬት
ነገሩን ፡ ላስረዳህ ፡ አባቴ ፡ አድምጠኝ ፤
ጋብቻው ፡ ፈጠነ ፡ ጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ስጠኝ

#ካፑሌ
ነገርሽ እሬት ነው ፡ መሪር ነው ፡ ኮምጣጣ
ካፍሽ ፡ ካንደበትሽ ፡ አንድ ፡ቃል፡ አይውጣ'
ሴት ልጅ እንቢ፡ብትል፡አለው አንድ አገባብ
መች ተሠርቶ ያውቃል እንዲህ፡ያለ ጥጋብ
ዘሩ ፡ የታወቀ ነዉ መልኩ ፡ የሚያኰራ ፡
ገንዘብ ፡ የተረፈው ፡ ስሙ ፡ የተጠራ፡
ደኅና ፡ ባል ፡ ፈልጎ ፡ በስንት ፡ መከራ፡
አባቷ ፡ ሲያመጣ ፡ ወዲያ ፡ ወዲህ ፡ ዞሮ '
ከቤት ፡ ተወዝፋ ፡ የኛ ፡ ሴት ፡ ወይዘሮ ፡
እኔ ፡ ባል ፡ አልሻም ፡ ትላለች ፡ ሞጋጌ ፤
መካን ፡ ሰው ፡ ይሻላል ከመውለድ ፡ ባለጌ
ጥኀጋብሽ ፡ ነው ፡ እኮ ደሜን ፡ የሚያፈላው ፤
ምኑ ፡ ነው ፡ እባክሽ ፡ፓሪስ ፡ የሚጠላው ?
ያለባል ፡ ለመኖር ፡ ከሆንሽ ፡
የምትወጂ ፡
ምን ፡ ቸገረኝ፡ እኔ ፡ ወደ ፡ ገዳም ፡ሂጂ ፡
ነገር ፡ ግን ፡ ከሆነ ፡ ማግባትሽ ፡ የማይቀር ፡
የመረጥኩልሽን ፡ ይገባሻል ፡ ማፍቀር ፡
ያላንድ ፡ ክርክር ፡ ያላንድ ፡ ቅሬታ ፡
ፈቃዴን ፡ መቀበል ፡ አለብሽ ፡ ግዴታ ።
የምትይ ፡ ከሆነ ፡ የኔን ፡ ፈቃድ ፡ እንቢ ፡
ከዛሬ ፡ ጀምረሽ ፡ ሂጂ ፡ ገደል ፡ ግቢ ፤
ዐይንሽን ፡ አልየው ፡ በዚህ ፡ በኔ ፡ ግቢ ።
የካፑሌ ፡ ሚስት ።
ቀስ ፡ ብሎ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አባት ፡ ከመከረ ፡
አንተም ፡ አበዛኸው ፡ ነገርህ ፡ ከረረ ።
ካፑሌ ።
አትግቢ ፡ ፈጽሞ ፡ አንቺ ፡ በኔ ፡ ሥራ ፤
ሂጂ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፡ ከሴቶቹ ፡ ጋራ ፡
ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ ባሳብ ፡ ሌሊቱን ፡ በሕልሜ ፡
ባል ፡ ስፈልግላት ፡ በመኖር ፡ ደክሜ ፡
በስንት 'ዐይነት ፡ ዘዴ ፡ እኔ ፡ ተጣጥሬ፡ .
እግዚአብሔር ረድቶኝ ፡ ይኸውና ፡ ዛሬ ፡
የሚሆን ፡ ሰው ፡ ባገኝ ፡ ጨዋ ፡ባለገንዘብ፡
እሜቴ ፡ ፈጠሩ ፡ ሠላሳ ፡ ሺሕ፡ ሰበብ ።
ስሚኝ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ልንገርሽ ፡ ካሁኑ፤
እሱን ፡ ካላገባሽ ፡ ታዘቢኝ ፡ በውኑ
የትም ፡ ትሄጃለሽ ፡ አብርሬሽ፡ ከቤቴ፤
እርሜን ፡ አወጣለሁ ፡ ቆርጬሽ ፡ ካንጀቴ
ልጅና ፡ አባት ፡ ሆነን ፡ መኖራችን ፡ ቀርቶ ፡
ክጄሽ ፡ ትሄጃለሽ ፡ አልምርሽም ፡ ከቶ ፡
ስለዚህ ፡ አስቢ፡ ከልብሽ ፡ ምከሪ፤
የሚከተለውን ፡ ተመልክተሽ ፡ ፍሪ'
ካሁኑ ፡ ጀምረሽ ፡ በነገሩ፡ ሥጊ፤
ቃሌ ፡ አይታጠፍም ፡ ኋላ ፡ ልብ ፡ አድርጊ
(ካፑሌ "ከቤት " ወጥቶ ሄደ)

#ዡልዬት
እባክሽ ፡ እናቴ ፡ ለልጅሽ ፡ እዘኚ፤
ባይሆን ፡እንኳን ፡ አንቺ ፡ ከኔ ፡ ወገን ፡ ሁኚ'
ቀኑ ፡ ረዘም ፡ ይበል ጥቂት ፡ ጊዜ ስጡኝ፤
አሳቤን ፡ ሳታውቁ ፡ በከንቱ ፡ አትቁጡኝ ።

ግዴታ፡ ካልሆነ' በጣም ' ካልቸረኝ፡
እንቢ ፡ አልልምና ፡ ምክንያት ፡ ካልኖረኝ ።

#የካፑሌ_ሚስት
ዕዳሽን ፡ በጨርቅሽ ፡ እንደምትፈልጊ '
አንቺ ፡ እንደ ፡ ፈቃድሽ 'እንዳሻሽ አድርጊ ።
(እናቷም' ወጥታ ሄደች)

#ዡልዬት
ርጂኝ ፡ አንቺ ፡ እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡

#ሞግዚቴ
ምስጢር፡ ተካፋዬ፡አንቺ፡ነሽ ፡እናቴ '
የኛን ተክሊል ማንም አይችልም፡ሊያፈርሰው፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ድብቅ ፡ ነው አያውቅም፡ማንም፡ሰው፡
እባክሽ ፡ ምከሪኝ ፡ ዘዴ ፡ አታጭምና ፤
ጨነቀኝ ፡ ጠበበኝ'አገኘኝ ፡ ፈተና ።

#ሞግዚት
ቃሌን ፡ ብትሰሚ ፡ ተራዬን ፡ ልናገር ፤
ሮሜዎ ፡ ሰው ፡ ገድሎ ፡ ተሰደደ ፡ ካገር፡
ልትኖሩ ፡ ከሆነ ፡ ለብቻ ፡ ለብቻ ፡
በዚሁ ፡ ይፈርሳል ፡ የናንተ ፡ ጋብቻ ፡
በዚሁ ፡ ላይ ፡ ደግሞ ፡ አባትሽ ፡ ላባቱ
👍1
ቂመኛ ፡ ነውና 'ደመኛ ፡ ጠላቱ ፤
ዕርቅ ፡ይኖራል ፡ ማለት ፡ መጓጓት ፡ ነው ፡ ከንቱ ።
ስለዚህ ፡ ፓሪስን ፡ እሺ ፡ ብለሽ ፡ አግቢ ፤
ሮሜዎን ፡ በልብሽ ፡ በቃሽ ፡ አታስቢ '
ደግሞስ ፡ ምንና፡ ምን ፡ እነዚህ ፡ ሁለቱ ፤
ፓሪስ ፡ የላቀ ፡ ነው ፡ በውበት ፡ በሀብቱ ፡
በዘር፡ በጌትነት'ይበልጣል' በሁሉ ፤
ደግሞስ ፡ ከዚህ ፡ በላይ፡ ሕግስ ፡ ቢሆን ፡
በድብቅ ፡ የሆነው ፡ አይረጋም ፡ተክሊሉ ።

#ዡልየት
እውነት ፡ ካንጀት ነው ወይ ፡ የምትናገሪ ?

#ሞግዚት
ከልቤ ፡ መሆኑን ፡ አትጠራጠሪ ።

#ዡልዬት
መልካም ፡ ነው በይ ሄደሽ ንገሪያት ለናቴ
መሄዴ ፡ ነውና ፡ በፍጥነት ፡ መውጣቴ ፡
ወደ ፡ አባ ፡ ሎራ ፡ ዘንድ በፍጥነት ፡ ደርሼ
እመጣለሁ፡በያት፡አሁን፡ተመልሼ ። (ሞግዚት ' ሄደች) "

(#ዡልዬት ብቻዋን) •
ለማ ፡ ልናገረው ፡ ምስጢሬን ፡ ገልጩ፡
ወደ ፡ አባ ፡ ሎራ ፡ ዘንድ ፡ ልሂድ ፡ እንጂ ፡
ከካህናቶች ፡ ዘንድ ፡ ቢበጅም ፡ ቢከፋ፡
የነፍስ ፡ መድኀኒት፡ ምን ጊዜም ፡ አይጠፋ

💫ይቀጥላል💫
#በጠራ_ጨረቃ

በጠራ፡ ጨረቃ ፡ በእኩላ ፡ ሌሊት ፡
ዓይኖቿ ፡ እያበሩ ፡እንደ ፡ ከዋክብት ፡
«ሳማት ፡ ሳማት » አሉት ፡«ዕቀፍ፡ ዕቀፋት
አላወላወለም ፤ ወጣቱ ፡ ታዘዘ ፤
ወገቧን ፡ አንገቷን ፡ በእጅና ፡ እጁ ፡ ያዘ ፤
ከንፈሩ ፡ በረአድ ፡ ወደ ፡ አፏ፡ ተጠጋ ።

-~ምንም ፡ እንኳ፡ ጡቷ እንደሾህ ፡ ቢዋጋ
ጣቷ ፡ በመሆኑ ፡ የጉማሬ ፡ አለንጋ፤
ጆሮው ፡ ግንዱን ፡ ሰማው ፡ በጥፊ ፡ ሲናጋ ።
በጠራ ፡ ጨረቃ ፡ በእኩለ ፡ ሌሊት ፡
ዋ ፡ ጀማሪ ፡ መሆን ፤ ዋ ፡ ተማሪነት ፤
ዋ ትእዛዝ ፡ መፈጸም ፤ ዋ ፡ ምክር ፡ መስማት ።

🔘መንግስቱ ለማ🔘