#የቆሰለ_አቁሳይ
፡
፡
#ክፍል_ሶስት(የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#በዳኒ
የምሽቱ ቀዝቃዛ ንፋስ በተከፈተው በር ገብቶ የትህትናን ደረት ደለቀው የስዩምም መጥቶ የኔ ፍቅር ማለቱ ከብርዱ ዠተኋኍ ቆዳዋንና የልቧን መከላካያ አጥንት በትሩፎት በመገባት ልቧን በድንጋጤ ሰነጠቀው ዓይኖቿ በድንጋጤ ፈጠጡ ልቧ ለሌላ ሰው ባይሰማም ድው ድው እያለ እንደ ከበሮ ይደልቃል ስዩም በጣም ከመስከሩ የተነሳ አቅም አንሶታል ደጋግሞ አክታ ያለው ሳል ይስላል መቆም አይደለም በቅጡ አይኑን መግለጥ ማውራትም አልቻለም ።
" ምን አልከኝ ?..... ምነው ጠፋሁብህ እንዴ ትህትና እኮ ነኝ"
" አውቃለው...የሰከርኩ መስሎሽ ነው ጠንጋራ ዝንብ አውቃለው እሺ ደግሞ አንቺም ታፈቅሪኛለሽ እኔም አፈቅርሻለው " አላት ለመውደቅ እየተገዳገደ አልኮል በቋጠረው አፍ አይጥ የሞተበት ጉድጓድ ጉድጓድ በሚመስል ሽታ በሚከረፋው አፍ።
" አንተ የወንድምህ ሚስት እኮ ነኝ እንዴት እንደዚህ አይነት ነገር እኔን ትለኛለህ ድፍረት እኮ ነው አሁን ደግሞ እሱ እየመጣልህ ነው ይገልሀል " አለችው። ስዩም ከት ብሎ ሳቀ ደጋግሞ ሳቀ በግርምት አየቺው በሩን አጥበቃ ያዘቺው ድንገት በሀይል ቢመጣ ፊቱ ላይ በሩን ወርውራ ለመዝጋት እየተዘገጀች ። ስዩም ለመተንፈስ እንኳን አቅሙን የያዘው መጠጥ እንዴት ብሎ ከት ብሎ ይሳቅ ግን የሞት ሞቱን ሞኩሮ ተሳካለት ሳቀበት።
" ወንድም የማን ወንድም በምን እሱ የኔ ወንድም መሆን አይችል በዘር በሀይማኖት በብሄር በምን ትሰሚያለሽ .... በጥይት ደረቱን በዬ ገደልኩትና ሰው ሆይ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ የሚለው የፈጣሪ ቃል በእሱ ተገበርኩት" አለ ለአንድነት ለፍቅር በጀግንነት ተፋልመው ግንባራቸውን ለጥይት ደረታቸውን ለፍቅር ሰጥተው አጥታቸውን ለተራራ ደማቸውን ለጥ ባለ መሬት እንደ አዝመራ ረጭተው ለዘሩት ስጋቸውን ለአሞራ ሰጥተው እንደ ተሰው ጀግኖች አባቶቻችን እሱ ወንድሙን ለመግደል ስለት አንስቶ ጥይት ደረቱ ላይ ተኩሶ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ ፎከረ ጋሻ ጎራዴ ይዞ በአውላላ ሜዳ አሽላላላ እረ ያዙኝ ልቀቁኝ አለ ወይ ዘድሮ!!!!! ትህትና በተናገረው ነገር ደነገጠች ።
"አንተ ደደብ ባለጌ እዛ በመጠጥ ቤትህ በመንገድ ላይ ወሬ ጨክነህ ወድምህን ለመግደል እጅህን አነሳህ ? " አለችው አይኖቿ እንባ ሞልቶ ። ስዩም በአዎንታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።
" አሁን ደግሞ ደስ የሚል ለሊት እናሳልፋለን " አላት ፈገግ ብሎ ። እሷ በድንጋጤ አይኗ ፈጦ ተመለከተቺውና በሩን ወርውራው በላዩ ላይ ዘጋቺበት በሩን ወርውራ ስትዘጋው ፊቱን መታውና ወደ ኋላው ወደቀ ። ትህትና በሩን ከውስጥ ቆልፋ ቁና ቁና እየተነፈሰች ወደ መኝታ ክፍሏ በመሄድ ዘግታው ቆለፈቺው ።
ትህትና ለሊቱን ተኮራምታ ከአሁን አሁን ይደወልልኛል ብላ ስትጠብቅ ስታለቅስ ስልክ በተደጋጋሚ እሷም እየደወለች ነጋ ። በጠዋት ተነስታ በር ላይ ተለጥፋ ሰማች ምንም ድምፅ የለም።በእርጋታ በሩን ከፍታ አጮልቃ ተመለከተች ስዩም በጀርባው እንደተዘረረ ነበር በደንብ ከፍታ ስትመለከት ግንባሩ አፍጫው ደም ፈሶበት ደርቋል በአፍ ግን ከውስጥ እንደወጣ የሚያስታውቅ የጓጎለ ደም ከአፍ ጀምሮ እስከ መሬቱ ተቆራርጦ ፈሷል ያቃስታል የግድ የበርበሬ ወፍጮ በመሰለው አይኑ በሚያሳዝን ሁኔታ አያት ።
ትህትና ለሊት ስትደውልላቸው የነበሩት ሰዎች መጡላት አዩት ደነገጡ አፋፍሰው ይዘውት ወደ ሆስፒታል ሄዱ።
ቀናቶች እንደ ቀለድ ነጎዱ ጥቂት ሳምንታት አለፍ ስዩም አንድም ሰው መጥቶ አልጠየቀውም ሰው እራበው ጠማው አጠገቡ ያለውን ወንድሙን ገሎ ዘሬ ብሄሬ ጓደኞቼ ማንም የለም ወንድሙ ቢኖር እንዴት እንደሚሰፈሰፍ ታወሰው ሁሌም ከአጠገቡ ቀን ከለሊት እንደማይለይ አወቀው ግን ከየት ያምጣው ሆስፒታል ከገባ አንድ ወር ከ15 ቀን ሆኖቷል አንድ ብር አልከፈለም ዶክተሮቹ እየመጡ ክፈል ይሉታል ብር የለው መሬቱን ቤቱን ለማስያዝ ሞከረ ዓለማየሁ ካልመጣ ቤቱንም ንብረቱንም ምንም ማድረግ እንደማይችል ነገሩት ዕለት ዕለት ማንባት ማልቀስ ስራው ሆነ ። ግን ፖሊሶች መጥተው ለምን እንዳልያዙት ሲያስብ ወዲያው በሩ ተከፍቶ ትህትና ገባች እንዳያት ደነገጠ ለመነሳት ሞከረ አልቻለም።
" ትህተና ልታሲዢኝ መጣሽ ...... ጉበቴ ተበተኖ ምንም የለም አሉኝ ደግሞ እኮ ማንም መጥቶ አላየኝም አላሳዝንም " አላት ፍፁም በሚያሳዝን ድምፅ በጉንጩ ላይ እንባ በአራት አቅጣጫ ፈሰሰ ትህትናም እያየቺው አለቀሰች።
" የታሉ ስዩሜ የተመካህባቸው ታውቃለህ እኔም አለማየሁም እናውቅ ነበር አንድ ቀን የሆነ ነገር እንደምታደርግ ህሊናህ በመጥፎ ሰዎች ወሬ ስለተመረዘ እናም የተኮስከው ጥይት ዓለማየሁን አልገደለውም ተቀብሎ ደረት ኪሱ የከተተው ብር አድኖታል ሁሌም ህክምናህን ይከታተል ነበር ዶክተሮቹ ክፈል የሚሉሁ እንድትማር ነው እሺ " እያያት በዝምታ ተውጦ አለማየሁን በአይኑ ሲፈልግ በሩ ላይ አየው ለቅሶው ገንፍሎ ወጣ አለማየሁም ተጠግቶት አቀፈው ስዩም እየደጋገመ ይቅርታ አርግልኝ አለው ተለቃቀሱ።
💫አለቀ💫

❤1
#ከፍቃድ_በላይ_ነሽ
ሰው መርጦ አይታመም ፤
ዛፍ ፈቅዶ አይጣመም፤
ከፍቃድ በላይ ነሽ፣ ከልቦና መሻት
አንቺ የፍቅር ጽዋ፣
ህመምም ፈውስም ነሽ፣ ልዩ ነሽ ምትህት፡፡
ወላጅ እንዳወጣው፣
እንደ መጠሪያ ስም፣
ከፍቃድ በላይ ነሽ፡፡
ሬትን አጣፍጠሽ፣ ማርን ታመሪያለሽ፤
ህልምን አስደልዘሽ፣ ቅኝት ታኖሪያለሽ፤
ከፍቃድ በላይ ነሽ፡፡
🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
ታህሳስ፣ 2012
ሰው መርጦ አይታመም ፤
ዛፍ ፈቅዶ አይጣመም፤
ከፍቃድ በላይ ነሽ፣ ከልቦና መሻት
አንቺ የፍቅር ጽዋ፣
ህመምም ፈውስም ነሽ፣ ልዩ ነሽ ምትህት፡፡
ወላጅ እንዳወጣው፣
እንደ መጠሪያ ስም፣
ከፍቃድ በላይ ነሽ፡፡
ሬትን አጣፍጠሽ፣ ማርን ታመሪያለሽ፤
ህልምን አስደልዘሽ፣ ቅኝት ታኖሪያለሽ፤
ከፍቃድ በላይ ነሽ፡፡
🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
ታህሳስ፣ 2012
#ያልተቋጨ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በክፍለማርያም
የእረፍት ሰአት እንደተደወለ ግቢዉ በተማሪወች ጫጫታ ተሞላ እሮጠዉ ያልጠገቡ ህፃናት ከወዲህ ወድያ ይሯሯጣሉ ትንሽ የሚሻሉት ደግሞ ጥጋቸዉን ይዘዉ ጨዋታ ይጫወታሉ
በእድሜ እና ክፍል ከፍ ያሉት ተማሪዎች ሁሉም በየራሱ ሀሳብ ተዉጦ ገሚሱ ቆሞ ገሚሱ ተቀምጦ ያስባል የሚያወራም አለ።
ትንሳኤ ከጉዋደኛው ዮናስ አጠገብ ቢቀመጥም ሀሳቡ ያለዉ ግን ህሊና ጋር ነዉ አይኖቹን በማይታየዉ አየር ላይ ተክሎ እያሰበ ቆይቶ ፊቱ ላይ የጀግንነት የድፍረት ወኔ እየታየ
"የመጣው ይምጣ ዛሬማ እነግራታለሁ"
አለ እጁን ጨምድድ እያረገ
"እስቲ እናያለን"
ጉዋደኛዉ ዮናስ ትንሳኤን በሚያሳዝን አስተያየት እያየዉ
ይሄ ለመጀመርያ ግዜ አደለማ
እንደዚህ ሲለዉ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ትንሳኤ የወደዳትን ያፈቀራትን ህሊናን በድፍረት ዛሬ የልቤን እነግራታለሁ ብሎ እንደዛሬዉ ይፎክር እና ልክ ህሊና ከጉዋደኞቿ ጋር በእነሱ በኩል ስታልፍ ምንም እንዳልተፈጠረ አንገቱን ደፍቶ ላብ በላብ ሆኖ ያሳልፋታል መጨረሻም ጉዋደኛዉ ዮናስ
"አይ አንተ አፍቃሪ"
እያለ ሲስቅበት ይዉላል
"ዛሬ ግን የመጨረሻ ነው ወደድኩሽ እንጂ ሌላ ምንም አልላት ታየኛለህ አሁን"
አለ ትንሳኤ የህሊናን መምጣት በጉጉት እየጠበቀ
ህሊና ከጉዋደኞቿ ጋር እያወራች ወደ እነ ትንሳኤ አቅጣጫ እየመጣች ነዉ
ዮናስ የጉዋደኛዉን የትንሳኤን ድፍረት ለማየት እና መልሷን ለመስማት ከትንሳኤ ጎን ጥቂት ፈንጠር ብሎ ቆሞዋል
ህሊና ቀስ እያለች እየተራመደች በትንሳኤ አጠገብ ስታልፍ ደፍሮ እንደማያዋራት የገመተዉ ዮናስ
"አዋራት ምን ያስፈራሀል!"
ይለዋል ድፍረት ለመስጠት ይመስል የትንሳኤን ትከሻ በእጆቹ ነካ ነካ እያደረገ
"ዛሬ ይቅር ነገ ልንገራት"
አለና ትንሳኤ ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ ክፍል ተመልሶ ገባ ዮናስም እየሳቀ ተከተለዉ።
ትንሳኤ 18 አመት ከሞላው ወር አይሞላዉም ከቤት ወጥቶ የማያዉቅ ልጅ ነበር የእናቱ ህይወት ካለፈ በኋላ ግን አባቱ ሌላ ፀባይ ስላመጣ እሱንም ችላ ስላለዉ ወጣ ወጣ ማለት ጀምሯል ማንም የሚቆጣጠረዉ የሚናገረዉ
ሰው የለም ቢሆንም በትምህርቱ ጎበዝ ነዉ ጭንቅላቱ ፈጣን ነገሮችን ቶሎ የመቀበል ችሎታ አላቸዉ።
ከትምህርት ቤት ሲለቀቁ ትንሳኤ እና ዮናስ በጠዋቱ ጉዳይ እያወሩ ከትምህርት ቤቱ እየወጡ
ነው
"የኛ ደፋር እኔ እኮ የሚያስቀኝ አሁን ዛሬ እነግራታለሁ እያልክ የምትምለዉ ነገር ነው "
ሲል ዮናስ ትንሳኤን ገፍተር እያረገዉ እየቀለደበት
ትንሳኤ በአይምሮዉ ወደ ኋላ ሄዶ አስታወሰ የሆነ ቀንም አዋራታለሁ ብሎ ምሎ ተገዝቶ ህሊና አጠገቡ ስትደርስ አደለም መናገር መላ ሰዉነቱም የሚሰሩም አይመስሉም
በሩቁ እየሰረቀ ያያታል እንጂ አይን ካይን እንዲገጣጠሙ እራሱ አይፈልግም እንደሚፈራት አስታዉሶ
እሱም ትንሽ እንደመሳቅ አለና
"ለምን አሁን ወደ ቤት ስትወጣ አላናግራትም"
ትከሻው ላይ ያነገበዉን ቦርሳ ወደ ዮናስ እንዲይዝለት እየሰጠዉ
"የማታረገዉን አረ አታስቀኝ አርፈን ወደ ቤት እንሂድ እርቦኛል"
ዮናስ አልይዝም አለዉ ቦርሳዉን
"እንደዉም አሁን ብነግራት ጥሩ ነዉ ምክንያቱም ነገ ቅዳሚ ከነገ ወድያ እሁድ አንተያይም አላፍራትም እስዋም አስባበት መልሷን ትነግረኛለች "
ትንሳኤ ይሄን ሲል ዮናስ አዘነለት በልቡ ምን አይነት ፍቅር ቢይዘዉ ነዉ እያለ
ከትምህርት ቤቱ መዉጫ በር ፊት ለፊት ቆመዉ የህሊናን መዉጣት በአይናቸዉ እየፈለጉ ነዉ
ትንሳኤ አይኖቹን ወደ ትምህርት ቤቱ ህንፃ ሲወረዉር ህሊና በደረጃ እየወረደች ተመለከታት አይኖቹ ፈዘዉ እያያት ነዉ በድንገት እሷም አየችዉ ተያዩ አይኖቹን ሰበር አድርጎ ድጋሜ አያት አሁንም እያየችዉ ነዉ የልብ ልብ ተሰማዉ
"ትዉረድ ብቻ ማን እንደሆንኩ አሳይሀለዉ "
ፊቱን አበስ አበስ አፍንጫውን ነካ አርጎ በተጠንቀቅ ቆመ
ዮናስ ዝግ ባለድምፅ
"አሁን ካልነገርካት እኔ እነግርልሀለዉ አለው "
ትንሳኤ ደረቱን ነፋ እያደረገ
"እኔ ምን ሆኜ ነዉ አንተ የምትነግርልኝ"
አለና ደፈር ብሎ ከደረጃዉ ወርዳ ወደ መዉጫዉ በር ወደ ምትመጣዋ ህሊና መራመድ ጀመረ.....0
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

👍1
#ሮሚዮና_ዡልየት ።
እስቲ #በትያትር ደግሞ ዘና በሉ
#ክፍል_አንድ
ካፑሌና ፡ ሞንታግ ፡ ሁለት ፡ ባላባቶች ፡
ሆነው ፡ የሚኖሩ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ ጠላቶች ፡
የእነሱም ፡ ወገኖች ፡ ባገረ ፡ ቬሮና ፡
ድንገት ፡ ሲገናኙ ፡ ሲያልፉ ፡ በጐዳና ፡
ጠብ ፡ እያበቀሉ ፡ በተንኰል ፡ በዘዴ ፡
ይተላለቃሉ ፡ በሰይፍ ፡ በጐራዴ ።
ሮሜዎና ዡልዬት ፡ ሁለት ፡ ልጆቻቸው ፡
በጣም ፡ ተዋደዱ ፡ ፍቅር ፡ አድሮባቸው፡
ግን ፡ አባቶቻቸው ፡ በነሱ ፡ መካከል ፡
ብርቱ ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ የነበረው ፡ በቀል ፡
ዕርቅን ፡ እንቢ ፡ ብለው ፡ ከቂም ፡ ስላልወጡ ፡በእነሱ ፡ ኀጢአት ፡ ልጆቹ ፡ ተቀጡ ።
ሆኖ ፡ የተገኘ ፡ ባገረ ፡ ቬሮና፡
እጅግ ፡ የሚያሳዝን ፡ የሚያስለቅስ ፡ ዜና ፡
አንባቢ፡ ተመልከት ፥ እንግዲህ፡ አስተውለው፤የምናቀርብልህ ፡ ታሪኩ ፡ ይኸ ፡ ነው ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
#በቤሮና_ከተማ_አውራ_መንገድ_ላይ
#ሶምሶንና ፡ #ጎርጎርዮስ ፡
#ሶምሶን
ዛሬ ፡ ሣር ፡ ቅጠሉ ፡ ዐፈርና ፡ ሙጃ ፡
ደም ፡ ደም ፡ ይሸተኛል ፡ ምክንያቱን ፡ እንጃ ።
#ጎርጎርዮስ
የሞንታግ ፡ ወገኖች ፡ ሸተውህ ፡ ይሆናል
#ሶምሶን ።
የነሱማ ፡ ጠረን ፡ በሩቅ ፡ ይቀረናል ።
#ጎርጎርዮስ ።
ምን ፡ ታደርግ ፡ ኖሯል ፡ አሁን ፡ ብቅ ፡ ቢሉ ?
#ሶምሶን ።
ኣይዞህ ፥ በኔ ፡ በኩል ፡ አይነሣም ፡ ጥሉ ፡
ግን ፡ እኔ ፡ በሰላም ፡ ብሄድም ፡ ዐርፌ ፡
ሳይጣላ ፡ አይቀርም ፡ ዐመለኛው ፡ ሰይፌ
#ጎርጎርዮስ
አይጠረጠርም ፤ መቼም ፡ ካየናቸው ፤
እነሱም ፡ አይለቁን ፥ እኛም አንተዋቸው ።
#ሶምሶን ።
እኔማ ፡ እንኳንስ ፡ እነሱን ፡ አይቼ ፡
ውሻቸውን ፡ ሳየው ፡ በድንገት ፡ አግኝቼ ፡
ያንቀጠቅጠኛል ፡ ደሜ ፡ እየተቈጣ ።
#ጎርጎርዮስ ።
ከሞንታግ ፡ አሽከሮች ፡ ያው ፡ አንደኛው ፡ መጣ ፡አንዱም፡ተከተለ ፡ ብቅ፡አሉ፡ሁለቱ ።
#ሶምሶን ።
ይንቀሳቀስ ፡ ጀመር ፡ የሰይፌ፡ ስለቱ ።
#ጎርጎርዮስ ።
እንግዲህ ፡ ተጠንቀቅ ፡ ሶምሶን ፡ ተሰናዳ
#ሶምሶን ።
ብቻ ፡ እንዳያገኘን ፡ የዳኝነት ፡ ዕዳ ፡
አንድ፡ ዘዴ ፡ እናምጣ ፡ ጠቡን ፡ እንዲያነሡ ፡እዚህ ፡ ከኛ ፡ አጠገብ ፡ ጠብቄ ፡ ሲደርሱ ፡ ፊቴን ፡ ወደ ፡ እነሱ ፡ እንዲያዩኝ ፡ መልሼ ፡
አስቆጣቸዋለሁ ፡ ከንፈሬን ፡ ነክሼ ።
( #አብርሃምና #ቤልሻጥር #መጡ ) ።
👇👇
#አብርሃም ።
አንተ ፡ በኛ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ከንፈር ፡ የምትነክሰው ፤
#ሶምሶን ።
እኔን ፡ አይጠይቅም ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ሰው ።
#አብርሃም ።
በኛ፡ ላይ ፡ እንደሆን ፡ ንገረኝ ፡ በፍጥነት ፡
#ሶምሶን ።
መጠየቅ ፡ አያሻም፡ ከኖረህ ፡ ወንድነት ።
#አብርሃም ።
ሁሉም ፡ በጃቸው ፡ ነው ፡ ሻምላ ፡ ሆነ ፡ ሰይፉም ፤
#የሞንታግ ፡ ወገኖች ፡ ተሰድበው ፡ አያልፉም ።
#ሶምሶን ።
የት ፡ አይተሃል ፡ ቀርተው ፡መዋጋት ፡ ሳያውቁ ፤
#የካፑሌ ፡ አሽከሮች ፡ በናንተ ፡ ሲጠቁ ?
#አብርሃም ።
ሊታይ ፡ ነው ፡ እኮ ፡ የናንተ ፡ ጕብዝና ፤
#ሶምሶን ።
መች፡ አጣህ ፡ መሆኑን ፡ የኛ ፡ ወገን ፡ ጀግና ።
( #ውግያ' #ይገጥማሉ )
#ቤንቮሊዎ ። (ይመጣል) ።
ያላንድ ፡ ምክንያት ፡ በከንቱ ፡ ሳይቸግር ፡
አሁን ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ የናንተ ፡ ግርግር ።
ሁል ፡ ጊዜ ፡ ጧት ፡ ማታ ፡ ስታልፉ፡ በመንገድ ፡ልማድ ፡ ሆነባችሁ ፡ ደርሶ ፡ ማንገራበድ ።
ለማምጣት ፡ ነው ፡ እኮ ፡ በናንት ፡ የተነሣ
በጌቶቻችሁ ፡ ላይ ፡ የዳኛ ፡ ወቀሣ።
#ቲባልት ፡ (ሻምላውን መዞ እያወዛወዘ ' መጣ )
እየው ፡ ቤንቮሊዎ ፡ ጥላውን ፡ ዘርግቶ
ሞት ፡ የያዘ ፡ ሻሞላ ' በራስህ ፡ ላይ፡ መጥቶ ፡ ተመልከት ፡ ሲያንዣብብ ፡ እንደ ፡ ጆፌ አሞራ
#ቤንቮሊዎ ።
መንፋትህ ፡ ይቅርና ፡ የማይረባ ፡ ጉራ
እንገላግላቸው ፡ ይልቅ ፡ ተረዳድተን ።
#ቲባልት ።
ልገጥምህ ፡ ነውና ፡ የመጣሁት ፡ አንተን ፡
ይልቅ ፡ ተሰናዳ ፡ ሻምላህን ፡ ምዘዘው ፤
ሳትዋጋ ፡ እንዳትሞት ፡ ቶሎ ፡ በጅህ 'ያዘው "
ቲባልት ፡ ሻምላ ፡ መዞ ፡ እጁን ፡ ከዘረጋ ፡
ሊመለስ ፡ አይችልም ፡ ጠላቱን ፡ ሳይወጋ
ወይም ፡ ደግሞ ፡ ራሱ ፡ ቀድሞ ፡ ካልወደቀ ።
#ቤንቮሊዎ ።
ፉከራህ ፡ ከንቱ ፡ ነው፡ በጣም ፡ የተናቀ ።
(#ውጊያ #ይገጥማሉ) ።
#ሞንታግ ፡ (መጣ)
ወገኖቼ ፡ ሁሉ ፡ ድረሱ ፡ በፍጥነት ፤
እነሆ ፡ ሰዎቼን ፡ ፈጁዋቸው ፡ በድንገት ።

#መርቆ_መርገም
እማራለሁ እንጂ ፥ አልመራመርም
“እግር አለኝ” ብዬ መንገድ አልጀምርም
ክንፍ ስለሰጠኝ ፥ እግሮቼን አልሰብርም
" አልጣፍጥህ " ያለኝ
ኮሶ መድሀኒት ነው !
ከህመሜ አንፃር ፥ ጣፋጭ ነው ቢመርርም፡፡
ለዛም ነው የምለው
“ አምላክ ያለምክንያት ፥ ምክንያትን አይፈጥርም።
ላፈጣጠራችን ፥ ተፈጥሮ ሲመርጠን
እንደ አባ ጨጓሬ
ከ"አባ" ነት ክብር ጋር ፥ መቶ እግር ቢሰጠን
እግር የነሳውን
የእባብን ያህል ፥ አንችልም መፍጠን ።
የፈጣሪን ያህል
በተፈጥሮ ጉዳይ ፥ ማን ይፈላሰፋል
ልክ እንደ ሰጎኖች
ላባ ሸክም ሆኖህ
መብረር እንዳትችል ፥ ክንፍህን ያገዝፋል።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
እማራለሁ እንጂ ፥ አልመራመርም
“እግር አለኝ” ብዬ መንገድ አልጀምርም
ክንፍ ስለሰጠኝ ፥ እግሮቼን አልሰብርም
" አልጣፍጥህ " ያለኝ
ኮሶ መድሀኒት ነው !
ከህመሜ አንፃር ፥ ጣፋጭ ነው ቢመርርም፡፡
ለዛም ነው የምለው
“ አምላክ ያለምክንያት ፥ ምክንያትን አይፈጥርም።
ላፈጣጠራችን ፥ ተፈጥሮ ሲመርጠን
እንደ አባ ጨጓሬ
ከ"አባ" ነት ክብር ጋር ፥ መቶ እግር ቢሰጠን
እግር የነሳውን
የእባብን ያህል ፥ አንችልም መፍጠን ።
የፈጣሪን ያህል
በተፈጥሮ ጉዳይ ፥ ማን ይፈላሰፋል
ልክ እንደ ሰጎኖች
ላባ ሸክም ሆኖህ
መብረር እንዳትችል ፥ ክንፍህን ያገዝፋል።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ምኞተ_አዳም ----
'አርብን ተደግፎ ፥ ያ ታላቅ ደራሲ ፣
ከተረጋጭ አፈር ......
............. ጠፍጥፎ ቀራርፆ
ትንፋሹን ለግሶ ፥ ለነብሴ ነጋሲ ፣
ባይሰጣት ህላዌ ......
........... ቢገደው ፅማዌ
እንደ ፅጌሽ ቅጠል ፥ ዳሰሳሽን ለምደው ፣
ንጋትን በማምለክ ...........
............ አለንጋ ጣትሽን
እንደሚናፍቀው ፣
በርሽ ላይ ነበረ - መብቀል የምመኘው።
አዬዬዬ.....አለ 'አዳም !
°°°°° © ሲራክ ወንድሙ.
-------- //// //// //// /// .........
ሲራክ @siraaq
.
'አርብን ተደግፎ ፥ ያ ታላቅ ደራሲ ፣
ከተረጋጭ አፈር ......
............. ጠፍጥፎ ቀራርፆ
ትንፋሹን ለግሶ ፥ ለነብሴ ነጋሲ ፣
ባይሰጣት ህላዌ ......
........... ቢገደው ፅማዌ
እንደ ፅጌሽ ቅጠል ፥ ዳሰሳሽን ለምደው ፣
ንጋትን በማምለክ ...........
............ አለንጋ ጣትሽን
እንደሚናፍቀው ፣
በርሽ ላይ ነበረ - መብቀል የምመኘው።
አዬዬዬ.....አለ 'አዳም !
°°°°° © ሲራክ ወንድሙ.
-------- //// //// //// /// .........
ሲራክ @siraaq
.
#ያልተቋጨ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#በክፍለማርያም
ወደ ህሊና አመራ ትንሳኤ ከደረጃ እየወረደች ወደሱ ትይዩ እየመጣችዉ ያለችውን ህሊናን ሲያያት ፊቱ እየቀላና ድንብርብሩ እየወጣ በር ላይ እየጠበቀዉ ወዳለዉ ጉዋደኛዉ ጋር ደርሶ
"ባክህ ፈራሁዋት አፍቃሪዉ ምናምን እያልክ ደሞ እንዳትሰድበኝ"
እያለ ቦርሳዉን ከጉዋደኛዉ ተቀብሎ ወደ ቤቱ አመራ።
ቅዳሜ እና እሁድን በጠዋት እየተነሳ ለሰኞ የፍቅር ጥያቄ ለማቅረብ እና እስዋ ፊት ሲደርስ ወንዳወንድ ለመምሰል ፑሽ አፕ ፑል አፕ በተጨማሪም ቤቱ ዉስጥ በስንሚንቶ በሰራዉ ክብደት ስፖርት ሲሰራ ፍርሀቱን ለማስወገድ እንደ እብድ መስታወት ፊት ቆሞ ሲለፈልፍ ሰኞ ደረሰ።
እንደወትሮዉ የህሊና ክፍል ከትንሳኤ ክፍል ቀጥሎ ስለሆነ ባንዲራ ተሰቅሎ ተማሪ ወደየ ክፍሉ ከገባ በኋላ አይኗን ሳያይ መዋል ስለማያስችለዉ ቀስ እያለ እየተራመደ ወደሱ ክፍል ከመግባቱ በፊት የህሊናን ክፍል በር አሻግሮ በአይኑ ህሊናን መፈለግ ጀመረ።
የቀረች መስሎት ሊበሳጭ ነበር ነገር ግን ፊቷን አዙራ ወሬ እያወራች ስለነበር ነዉ።
መጥታለች በርቀት ሲመለከታት ደስ አለዉ ደስታው በምንም የማይተካ ነበር ፈገግ እያለ በልቡ ስላያት ተመስጌን መጥታለች እያለ ወደሱ ክፍል ሲገባ ጉዋደኞቹ በሳቅ ተቀበሉት
ከዮናስ ጎን የተቀመጠዉ እዮብ በትንሳኤ አፍቅሮ እንደዚህ መሆን አይስቅበትም ምን አልባት እሱም ከሌላ ፍቅር ሊኖርበት ይችላል ዮናስም ቢሆን በሀሪዉ ሆኖ የትንሳኤ ሁኔታ ስለሚገርመዉ ይስቅበታል እንጂ ጨክኖበት አልነበረም።
የህሊና ጉዋደኞች እነ ትንሳኤ ክፍል ስላሉ ሁሌ ህሊና ምሳ ለመብላት እነሱጋር ትመጣለች ትንሳኤም መጀመርያ በህሊና ፍቅር የወደቀዉ እሷ ስትመላለስ አይቷት ነዉ
ቀኑን ያስታዉሰዋል ምሳ ስዓት ላይ አሸናፊ የሚባሉ አብሮት አንድ ዴስክ ላይ የሚቀመጥ ተማሪ በስልኩ ሙዚቃ ከፍቶ ነበር
"ለምን አየኝ አለች ሳያት እሷን ብቻ
መዉደዴን ስነግራት አርጋዉ የጥላቻ.."
እያለ የሚቀጥል የመስፍን በቀለን ዘፈን ህሊና ቦርሳ አንግባ በምን እንደምትስቅ ባያዉቅም አነስአነስ ያሉ ነጭ ጥርሶቿን እያሳየች ወደነትንሳኤ ክፍል ገባች።
ወደ ክፍሉ ብቻ አደለም የገባችዉ እንደሙዚቃዉ በልቡ ግጥምና ዜማዋ ሳቋና ሁሉነገሯ ልቡ ዉስጥ ገባ።
ዛሬም ምሳ ስዓት ሲደወል ጉዋደኞቹ
"እንዉጣ"
ቢሉትም በልቡ ያሰበዉ ነገር ስለነበር
"አልወጣም የምፅፈዉ ነገር አለ"
ሲላቸዉ ጉዋደኞቹ ጥለዉት ወጡ
ትንሳኤ ጠዋት ቁርስ በልቶ ከቤቱ ስላልወጣ ሆዱ የርሀብ ጥያቄ እያሰማ ነበር
ህሊና ወደ ጉዋደኞቿ ክፍል ስትገባ ትንሳኤ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ በረንዳ ወጥቷ በልታ እስክትጨርስ ሠንጎማለል ጀመረ።
እርቦታል ቤቱ ቅርብ ስለነበር ሄዶ መብላት ይችላል ነገር ግን ልቡ ዉስጥ ያለዉን ለመናገር ቻል አርጎ ከአሁን አሁን በልተዉ ጨረሱ እያለ በአይኑም ለማረጋገጥ እያያቸዉ ቆይቶ በልታ ጨርሳ እጇን ታጥባ እንደጨረሰች።
ለመጥራት ፈልጎ እንዴት መጥራት እንዳለበት ግራ ገብቶት ለጉዋደኞቹ እንደለመደዉ በቅርብ እርቀት ላይ ሆና አፉዋጨላት ደፋር ደፋር እያጫወተዉ ነበር።
ህሊና ዞራ እያየችዉ እኔን ነዉ ለማለት ሌባ ጣቷን ወደ ደረቷ አስጠግታ ስታሳየዉ አዎ ለማለት አንገቱን ከላይ ወደታች እየነቀነቀ በእጆቹ ጠራት
"አንዴ መጣሁ"
አለችዉና ወደ ጉዋደኞቿ ተመለሰች
ትንሳኤ ፍርሀት አይን አዉጥቶ ሂድ ሂድ ቢለዉም ቅዳሜና እሁድ የለፋበት ስፖርት ጥቂት ወኔ ሰጥቶት ደረቱን ነፍቶ ጠበቃት አጠገቡ ህሊና
"አቤት"
ብላ ስትጠጋዉ ግን ተንፍሶ ጥቂት ዝም አለና
እጁን እየዘረጋ
"ትንሳኤ"
አላት ስሙን ለመናገር እየፈለገ
"ህሊና"
ብላዉ የሚነግራትን ለመስማት አይን አይኑን አየችዉ
ትንሳኤ አይኗን እያየ በልቡ
"አቤት ሲያምር ደሞ የሆነ የሚያሳዝን ነገር አላት "
ብሎ በድንጋጤ ሊያዋራት አፉን ከፈተ
"ካየሁሽ ቀን ጀምሮ እወድሻለሁ"
የማይባል ነገር አለ
መሸወዱ አመታት አልፎ ነዉ የገባዉ እንዴት አዉርተሀት በደንብ እንኳን አይታህ የማታዉቅ ሴትን እንደዚህ ይባላል
💫ይቀጥላል 💫

❤1👍1
#ሮሚዮና_ዡልየት
#ክፍል_ሁለት
#ሞንታግ ፡ (መጣ)
ወገኖቼ ሁሉ ድረሱ በፍጥነት
እንሆ ሰውቼን ፈጅዋቸው በድንገት
ሰይፌን ፡ አቀብሉኝ፡ በቶሎ፡ ፍጠኑ ።
የሞንታግ ፡ ሚስት ፡(ተከትላ ፡ መጣች) "
እስቲ፡ ባዶ ፡ እጅዎን ፡ አሁን ፡ ምን ፡ ሊሆኑ ?
#ካፑሌ ፡ (መጣ)
ሰይፌን ፡ አቀብለኝ፡ ማነህ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ
የካፑሌ ፡ ሚስት ፡(ተከትላ ፡ መጣች) ።
ሽማግሌው ፡ አብዷል ፡ ድረሱልኝ ፡ በነፍስ
#ወታደር ።
ይርጋ ፡ በየቦታው ፡ ሁሉም ፡ ጠቡን ፡ ትቶ
ልዑልነታቸው ፡ መጣ ፡ ተቆጥቶ ።
#መስፍኑ ፡ (አገረ ገዥ) ።መጣ
መልካም ፡ ነው ፡ አየነው ፤ ይብቃ ፡ አሁን ፡ እርጉ፤ውጊያውን ፡ ትታችሁ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ተጠጉ ፡
#ካፑሌና ፡ #ሞንታግ ፡ ልንገራችሁ ፡ ስሙ
የናንተ ፡ አምባጓሮ ፡ በመደጋገሙ ፡
አልነቀል ፡ ብሎ ፡ የቂማችሁ ፡ መርዙ ፡
ሥር ፡ ስለ ፡ ሰደደ ፡ ጠንቃችሁ ፡ መዘዙ ፡
ደከመኝ ፡ ሰለቸኝ ፤ ታከተኝ ፡ በብዙ ።
ምንድንነው ፡ በውነቱ ፡ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ነገር፤ ሰላም 'እያወኩ' ዘለዓለም ፡ ማስቸገር ።
ሁል ፡ ጊዜ፡ ግርግር' ሁል፡ጊዜ ፡
ሁል ፡ ጊዜ ፡ አምባጓሮ 'ሁል ፡ ጊዜ ጫጫታ ።
በናንተ ፡ ምክንያት ፡ ስንት ፡ ደም ፡ ፈሰሰ፤
ስንት፡ጊዜ፡አገሩ፡ጸጥታው፡ ፈረሰ ፡
ስንት ፡ ጊዜ ፡ በጠብ ፡ ከተማው ፡ ታመሰ ?
አገሬ ፡ በናንተ ፡– ንገሩኝ ፡ በሉ ፡ እኮ ፡
እስከ ፡ መቼ ፡ ድረስ ፡ ይኖራል ፡ ታውኮ ?
እስቲ ፡ በማን ፡ አገር ፡ እስቲ ፡ በማን ፡ ዕድሜ፡ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ጥጋብ ፡ የሌለው ፡ፍጻሜ፡
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ይታወቃል 'ታይቶ ፤
ማንም ፡ ሰው ፡ ይፍረደው ፡ ይህን ፡ተመልክቶ ።
እስከ ፡ መቼ፡ድረስ ሕዝቤ ፡ በሰይፍ፡ያልቃል?
ትሰሙኝ ፡ እንደሆን ፡ እንግዴህ ፡ ይበቃል
በእውነቱ ፡ ዕወቁት' ከዛሬ ፡ ጀምሮ '
በናንተ ፡ መካከል ፡ ቢሆን ፡ አምባጓሮ '
አዝዣለሁ ፡ አጥፊው ፡ በሞት ፡ እንዲቀጣ
አለዚያም ፡ ጨርሶ ፡ ካገር ፡ እንዲወጣ ።
እንግዴህ ፡ ልባችሁ ፡ የኔን ፡ ፍቅር ፡ ቢሻ ፡
የዛሬው ፡ ጠባችሁ ፡ ይሁን ፡ መጨረሻ ፡
ስታዝኑ ፡ እንዳልሰማ ፡ በኋላ ፡ በፈራጅ ፡
ይህን ' ያሁን 'ቃሌን ፡ ቁጠሩት፡ እንዳዋጅ"
#ካፑሌ ፥ #ፓሪስ ፡ አንድ ፡ #አሽከር ።
#ካፑሌ ።
የመስፍኑ'ትእዛዝ ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ ብርቱ ፡
ሞንታግና ፡ እኔ ፡ ሳስበው ፡ በውነቱ ፡
እንግዲህ ፡ ጠባችን ፡ እየቀዘቀዘ :
ይሄድ' ይመስለኛል ፡ ባዋጅ ፡ ከተያዘ ።
#ፓሪስ ።
ስማችሁ ፡ ዝናችሁ፡ በጣም ፡ የታወቀ ፡
እንዲሁም ፡ ክብራችሁ ፡ ከሁሉም ፡ የላቀ ፡
ሆኖ ይህን ፡ ያኽል ፡ ጊዜ ፡ ተጣልታችሁ ፡
በጣም ፡ ያሳዝናል ፡ በጠብ ፡ መኖራችሁ ፤
እረ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ሆነ ፡ ደግሞስ ፡ የኔ ፡ ነገር ?
ልጅዎን ፡ ለማግባት ፡ ጠይቄዎት ፡ ነበር ።
#ካፑሌ ።
ችላ ፡ ብዬ ፡አይደለም ፡ ጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ታገሥ ፤
ዡልዬት ፡ ከፍ ፡ ትበል ፤ ለመታጨት ፡ ትድረስ ፡
አሁን ፡ አእምሮዋ ፡ ዕውቀቷም ፡ አልጠና
ከልጅነት ፡ ዕድሜ ፡ አልወጣችም ፡ ገና ፡
እስከዚያ ድረስ ፡ ግን 'አንተ ፡ ተላመዳት ፤
ትወቅህ ፡ ዕወቃት ፡ትውደድህ ውደዳት
አሁን ፡ ለምሳሌ ፡ ይኸው ፡ ዛሬ ፡ ማታ ፡
ትልቅ ፡ ግብዣ ፡ አድርጌ ፡ በቤቴ ፡ ጨዋታ፡
ደስታም ፡ ይሆናል ፡ አንተም ፡ እንዳትቀር ፤
ናና፡ ከሷ ፡ ጋራ ፡ ቀርበህ ፡ ተነጋገር ።
በጣም ፡ ተዋወቁ፤
ና፡ እባክህ ፡ አንተ ፡ #አሽከር ፡
በዚህ ፡ ወረቀት፡ ላይ ፡ ተጽፎ ፡ ስማቸው ፡
የሚነበበውን ፡ ቶሎ ፡ ፈልጋቸው ፤
ውጣ ፡ ከከተማ ፡ ዙር ፡ በየመንገዱ ፤
ታገኛቸዋለህ ፡ በድንገት ፡ ሲሄዱ ።
አደራ ፡ በላቸው ፡ ማታ ፡ እንዲመጡ ፤
ከግብዣዬ ፡ ቀርበው ፡ በልተው ፡ እንዲጠጡ ፡
እንዲጫወቱልኝ ፡ ፈቃዴ ፡ መሆኑን ፡
ፈጥነህ ፡ ንገራቸው ፤ ቶሎ ፡ ሂድ ፡ አሁኑን
#አሽከር ፡(ወረቀት ፡ ተቀብሎ ፡ ሄዴ) ።
(#ሮሜዎና • #ቤንሾሊዎ) "
#ሮሜዎ ።
የነካፑሌ ፡ አሽከር ፡ አንድ ፡ ወረቀት ፡ ይዞ ፡
መንገድ ፡ አገኘሁት ፡ ሲመለከት ፡ ፈዞ ፡ .
እሱስ ፡ ለካ ፡ ማንበብ ፡ የማያውቅ ፡ ኖሮ ፡
የሚያነብለት ፡ ሰው ፡ በጣም ፡ ተቸግሮ ፡
እኔን ፡ ቢለምነኝ፡ እኔም ፡ የነሱ፡አሽከር ፡
ሳላውቅ ፡ መሆኑን ፡ ባለመጠራጠር፡
ምንም ፡ ሳልተረጒም ፡ በደግም ፡ በመጥፎ ፡
የብዙ ፡ ሰዎች ፡ ስም ፡ አየሁኝ ፡ ተጽፎ ።
አንብቤ ፡ ስጨርስ ፡ ከሰማ ፡ በኋላ ፡
በወረቀቱ ፡ ላይ ፡ ስማቸው ፡ የሞላ፡
ምንድናቸው ፡ ብዬ ፡ እኔ ፡ ብጠይቀው ፡
ዛሬ ፡ ካፑሌ ፡ ቤት ፡ ማታ ፡ራት፡ተጋብዘው ፡
የሚመጡ ፡ ናቸው ፡ አለና ፡ ነገረኝ ።
#ቤንቮሊዎ ።
- እኔም ፡ ሰምቻለሁ ፡ እንኳን ፡ አስታወስከኝ ፡
እርግጥ፡በነሱ ፡ ቤት ፡ ይኸው ፡ ዛሬ ፡ ማታ
ትልቅ ፡ ግብዣ ፡ ሆኖ ፡ የዳንስም ፡ ጨዋታ ፡ብዙ፡ሰው፡ተጠርቷል፤ሰውም፡ የሚሄደው!
ፊቱን ፡ በመሰውር ፡ እየሸፈነ ፡ ነው ።
ስለዚህ ፡ አያውቅም ፡ አንዱን፡አንዱን ፡ ለይቶ ፤
አንተና፡እኔ ፡ብንሄድ ፡ ማንም ፡ ቢሆን ፡ ከቶ
አያውቀንምና ፡ እንሂድ ፡ ሳንፈራ ፤
እዚያም ፡ ከሮዛሊን ፡ ካንተ ፡ እጮኛ፡ጋራ ፡
እንገናኛለን ፡ ተጠርታለችና።
#ሮሜዎ ።
እውነት ፡ ቤንቮሊዎ ፡ አስበሃል ፡ ደኅና ፡
በል'እንግዴህ ፡ ፍጠን ፡ ቶሎ ፡ እንሰናዳ
እውነትም ፡ ባስበው ፡ የኔን ፡ ጽጌ ፡ ረዳ ፡
ካየኋት ፡ ቈይቷል ፡ ወር ፡ ሆኖኛል ፡ ይኸው ፤
በጣም ፡ ጥሩ'አሳብ' ነው፡አሁን'ያመጣኸው ።
(#ሮሜዎና' #ሜርኮቲዎ)
#ሜርኩቲዎ ።
ወዴት ፡ ትሄዳለህ ፡ እንዲህ ፡ በጨለማ ?
#ሮሜዎ ።
ዐይንህ፡እንዳላየ ፡ ጆሮህ'እንዳልሰማ ፡
ሆነህ ፡ ዝም ፡ ብለህ ፡ እለፍ ፡ በጐዳና ፤
ማንም ፡ ሰው ፡ እንዲያውቀኝ ፡ አልፈልግምና ።
#ሜርኩቲዎ ።
ባሁን ፡ ሰዓት ፡ ስትሄድ ፡ ብቻህን ፡ አይቼ ፡
ለመቅረት ፡ አልችልም ፡ ካንተ ፡ ተለይቼ ።
#ሮሜዎ ።
ልብህ 'እንዳይሠጋ፡ ሆድህ ፡ እንዳይፈራ ፡
ምስጢሬን ፡ ልንገርህ ፡ የኔ ፡ ባልንጀራ ፤
ዛሬ ፡ ካፑሌ ፡ ቤት፡ ትልቅ ፡ ግብዣ ፡ ሆኖ ፡
ሰዉ ፡ በመሰውር ፡ ፊቱን ፡ ተሸፍኖ ፡
ዳንስ ፡ ይጫወት፡ ነበር፡ ከቤንቮሊዎ፡ጋራ፡
ማንም ፡ ሰው ፡ ሳያየን ፡ ገባን ፡ ሳንፈራ ፡
የቀድሞ ፡ እጮኛዬን ፡ ሮዛሊንን' ልሻ '
ሄጄልህ ፡ ነበረ ፤ ኋላም ፡ መጨረሻ ፡
በጣም ያስገርማል ፡ ይደንቃል ፡ ወዳጄ፤
አልማዝ አገኘሁኝ ፡ ወርቅ ፡ ልሻ 'ሄጄ
የነካፑሌን ፡ ልጅ ፡ ዡልዬትን ፡ አይቼ ፡
በውበቷ ፡ ብርሃን ፡ መጣሁ ፡ ተረትቼ ፡
ግብዣው ፡ ስላለቀ ፡ ሰዉ ፡ ተበትኖ ፡
ብቅ ፡ ብትልልኝ ፡ ምናልባት ፡ ልቧ ፡ አዝኖ
ይኸው ፡ መሄዴ ፡ ነው ፡ ደግሞ ፡ ተመልሼ
እመጣለሁ ፡ አሁን ፡ በፍጥነት ፡ ደርሼ ።
#ሜርኩቲዎ ።
እንዴት ፡ ትሄዳለህ፡ደፍረህ ፡ ከነሱ ፡ቤት ?
አንድ ፡ ሰው ፡ ከነሱ ፡ ቢያገኝህ ፡ በድንገት
ዕወቅ ፡ ይገድልሃል ፡ አብደሃል ፡ ፈጽሞ ፤
በራቸው ፡ ይዘጋል ፡ ለመግባትስ ፡ ደግሞ
እንዴት ፡ ትችላለህ ? ይቅርብህ ፡ ተመለስ
#ሮሜዎ ።
ማ ፡ ሊያየው ፡ ይችላል ፡ ሰው ፡ ጨለማ ፡ ሲለብስ ?
አጥሩ ፡ ቢረዝም ፡ በሩ፡ ቢጠነክር ፡
ጠላትም ፡ አድፍጦ ፡ ሊገድለው ፡ ቢሞክር
ሰው ፡መውደድ፡አድሮበት፡ፍቅር ካሰከረው
ምንም ፡ አያግደው ፤ምንም አይበግረው
ባገኛት ፡ ቢቀናኝ ፡ ቶሎ ፡ ልምጣ ፡ ሄጄ ፤
ሜርኩቲዎ ፡ደኅና ፡ እደር ፡ አትሥጋ ፡ ወዳጄ።

#በገና_ጨዋታ
#እንኳንና_መንግስት_አይቆጣም_ጌታ
እንደምነህ መንግስት ፣ እኛ አለን በቁንጣን
ጠግበን እየበላን ፣ ጠግበን እየጠጣን
"በገና ጨዋታ
አይቆጡም ጌታ ፣ ሚል ድምፅ እያወጣን
አለን አረቄ ቤት
አንተን ሚመለከት ፣ ስድብ እያዋጣን፡፡
፡፡፡፡፡፡፡
መቼም ስካር ደጉ ፣ ልብ ያደነድናል
ሰክሬ ነው ብሎ
እውነትን መናገር ፣ ከፍርሀት ያድናል፡፡
።
እናልህ አንድ ሰው ፣ ያውም የሰከረ
አጠገቤ ሆኖ ፣
በድፍረት በወኔ ፣ እንዲህ ሲል ነበረ
እያንጎራጎረ
"በገና ጨዋታ ፣ መንግስት አይቆጣም
እቆጣለሁ ቢልም ፣ ምንም አያመጣም
ቢያመጣም አንፈራም ፣
ደፋር ነው ሰካራም
ይልቅ ከኛ በላይ ...
ፖለቲካ ይሉት ፣ ገዳይ አልኮል ልፎ
አሻጋሪ ያልነው ፣ አሸባሪ አቅፎ
ከሚያሳይ ፎቶ ጋር
"ፍቅር እና ሰላም ፣ ሚል ስብከት ሚያጋራን
መንግስት ደፋር ነው ፣ ሰክሮ ነው ሚመራን
ፍትህ ስንጠይቅ ፣ ምህረት ነው ቁጣው
በስካር መንፈስ ነው
ምኑም ግልፅ ያልሆነ ፣ መግለጫ ሚያወጣው፡፡
እያለ ይዘፍናል...
በጉልድፍ አንደበት ፣ ቃላት እያወጣ
እኔ ግን በቁጭት ፣ እኔ ግን በቁጣ
ስካር ይህን ያህል
ደፋር ካደረገ
ህዝቡ እቁብ ጥሎ ፣ ምናለ ቢጠጣ፡፡"
እያልኩ እመኛለሁ።
።፣፣፣፣።።።።።።።።
አንዱ ደሞ እዛ ጋ ፣
ነጋዴ ነው መሰል ፣ጥግ ላይ ቁጭ ብሎ
"መንግስት ነው ይላል ፣ አጉል ግብር ጥሎ
አረቄ ሚያስጠጣኝ ፣
የውስኪ መጠጫ ፣ ከኔ ተቀብሎ
እያለ ይጮሀል ፣ ደጋግሞ ደጋግሞ
አቦ ስካር ይኑር
እላለሁኝ እኔ
እንዲ ሲሉ ነበር ፣ የተቀሩት ደሞ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደምነህ መንግስት ፣ እኛ አለን ስንበግን
አንተ ህንፃ ስትሰራ
በግርግም ያደረን ፣ ምን ብናመሠግን
አለን አረቄ ቤት ፣ ላንተ ውስኪ ጋብዘን
ስካርና ብሶት እየወዘወዘን
በገዛ ሀገራችን ፣ በእዳ ተይዘን
በአመት ባል ቀናችን ፣ ያመት ባል ቀን አዘን
አለነው ተክዘን፡፡
፡፡፡፡፡፡
እንደምነህ መንግስት ፣ እኛ አለን በደለህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
ስናከብር ገና
ባመት ባል ቀናችን ፣ አመትባል እያጣን
"በገና ጨዋታ
መንግስት አይቆጣም ፣ ሚል ዜማ እያወጣን
በተረፈን ገንዘብ ፣ አረቄ እየጠጣን
ሰክረን እያማንህ ፣ እኛ አለን በተድላ
ከበግ ነጋዴ ላይ ፣ እየገዛን ተኩላ
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#እንኳንና_መንግስት_አይቆጣም_ጌታ
እንደምነህ መንግስት ፣ እኛ አለን በቁንጣን
ጠግበን እየበላን ፣ ጠግበን እየጠጣን
"በገና ጨዋታ
አይቆጡም ጌታ ፣ ሚል ድምፅ እያወጣን
አለን አረቄ ቤት
አንተን ሚመለከት ፣ ስድብ እያዋጣን፡፡
፡፡፡፡፡፡፡
መቼም ስካር ደጉ ፣ ልብ ያደነድናል
ሰክሬ ነው ብሎ
እውነትን መናገር ፣ ከፍርሀት ያድናል፡፡
።
እናልህ አንድ ሰው ፣ ያውም የሰከረ
አጠገቤ ሆኖ ፣
በድፍረት በወኔ ፣ እንዲህ ሲል ነበረ
እያንጎራጎረ
"በገና ጨዋታ ፣ መንግስት አይቆጣም
እቆጣለሁ ቢልም ፣ ምንም አያመጣም
ቢያመጣም አንፈራም ፣
ደፋር ነው ሰካራም
ይልቅ ከኛ በላይ ...
ፖለቲካ ይሉት ፣ ገዳይ አልኮል ልፎ
አሻጋሪ ያልነው ፣ አሸባሪ አቅፎ
ከሚያሳይ ፎቶ ጋር
"ፍቅር እና ሰላም ፣ ሚል ስብከት ሚያጋራን
መንግስት ደፋር ነው ፣ ሰክሮ ነው ሚመራን
ፍትህ ስንጠይቅ ፣ ምህረት ነው ቁጣው
በስካር መንፈስ ነው
ምኑም ግልፅ ያልሆነ ፣ መግለጫ ሚያወጣው፡፡
እያለ ይዘፍናል...
በጉልድፍ አንደበት ፣ ቃላት እያወጣ
እኔ ግን በቁጭት ፣ እኔ ግን በቁጣ
ስካር ይህን ያህል
ደፋር ካደረገ
ህዝቡ እቁብ ጥሎ ፣ ምናለ ቢጠጣ፡፡"
እያልኩ እመኛለሁ።
።፣፣፣፣።።።።።።።።
አንዱ ደሞ እዛ ጋ ፣
ነጋዴ ነው መሰል ፣ጥግ ላይ ቁጭ ብሎ
"መንግስት ነው ይላል ፣ አጉል ግብር ጥሎ
አረቄ ሚያስጠጣኝ ፣
የውስኪ መጠጫ ፣ ከኔ ተቀብሎ
እያለ ይጮሀል ፣ ደጋግሞ ደጋግሞ
አቦ ስካር ይኑር
እላለሁኝ እኔ
እንዲ ሲሉ ነበር ፣ የተቀሩት ደሞ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደምነህ መንግስት ፣ እኛ አለን ስንበግን
አንተ ህንፃ ስትሰራ
በግርግም ያደረን ፣ ምን ብናመሠግን
አለን አረቄ ቤት ፣ ላንተ ውስኪ ጋብዘን
ስካርና ብሶት እየወዘወዘን
በገዛ ሀገራችን ፣ በእዳ ተይዘን
በአመት ባል ቀናችን ፣ ያመት ባል ቀን አዘን
አለነው ተክዘን፡፡
፡፡፡፡፡፡
እንደምነህ መንግስት ፣ እኛ አለን በደለህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
ስናከብር ገና
ባመት ባል ቀናችን ፣ አመትባል እያጣን
"በገና ጨዋታ
መንግስት አይቆጣም ፣ ሚል ዜማ እያወጣን
በተረፈን ገንዘብ ፣ አረቄ እየጠጣን
ሰክረን እያማንህ ፣ እኛ አለን በተድላ
ከበግ ነጋዴ ላይ ፣ እየገዛን ተኩላ
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ያልተቋጨ
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...እንዴት ይባላል
ህሊና ደንገጥ ብላ አየችዉ እብድም ሳይመስላይ አይቀርም ፊቷ ላይ የመደንገጥ እና የመገረም የሚመስል ድባብ ይታይባታል ቶሎ ለመራቅ አስባ አፏ ላይ የመጣላትን
"ጉዋደኛ አለኝ"
ብላዉ ጥላዉ ወደ ጉዋደኞቿ ገባች።
የዛን ለት ወድያዉ እሷ ጥላዉ ስትገባ ደብተሩን እንኳን ሳይዝ እየተበሳጨ እየተመናቀረ ከትምህርት ቤቱ ግቢ ወጣ
ግራ የተጋባ ስሜት መናገሩ የልቡን መተንፈሱ ቢቀለዉም የመለሰችለት መልስ ያሳየችዉ ፊት ግን አስከፍቶታል
አፍቃሪ የሚጠብቀዉ እንደልቡ ፍላጎት ህልሙ ተሳክቶ ማየት ነዉ
ህይወት ግን ወጥንቅጧ የበዛ ስለሆነ አንዳንዴ በአንድ ወገን ያለ ፍቅር ለብቻዉ እንደሻማ በርቶ ይቀልጣል እንጂ አይሰምርም
መንገድ ላይ እየተሪመደ አንድ መንገድ ዳር የተቀመጠ ሲጋራ የሚያጨስ ከትንሳኤ እድሜ የሚበልጥ ልጅ
"ና" ብሎ ጠራዉ
ትንሳኤ እየተወዛገበ
"አቤት" እያለ ተጠጋዉ
"ስንት ብር ይዘሀል "
እያለ ልጁ ቆመ
ትንሳኤ ለራሱ ከባድ የፍቅር ረመጥ ዉስጥ ነዉ አደለም የማንም ጉልበተኛ ነኝ ባይ
"ና ያለህን አምጣ" ብሎት
ትንሳኤ ሳያንገራግር ወደ ልጁ ቦክስ ሰደደ ልጁም ወደ ትንሳኤ የመልስ ምት ላከ ገላጋይ ባይገባ ሁለቱም ይጎዳዱ ነበር። ትንሳኤን ሲያገላግሉ የያዙት ሰወች
"ምን አይነት ልብ ነዉ ያለህ ከታላቅህ ጋር ትጣላለህ"
እያሉ ሲመክለሩት የልብ ልብ ተሰምቶት ድጋሜ ካልተጣላሁ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ቢልም ጉልቤ ለመሆን የሞከረዉ ልጅ ግረግሩ እና የትንሳኤ ፉከራ ስላልጣመዉ ከአካባቢዉ ተሰወረ።
በነጋታዉ ትንሳኤ ወደ ክፍል እንደገባ ዮናስ በፈገግታ ተቀበለዉ
"ጀግናችን ወሬ አይደበቅም ስታዋራት ሰው አይቶካል ምን ተፈጠረ ጭዌዉን እንደወረደ"
ሲለዉ ሌሎች ጉዋደኞቹም በተሰበሰቡበት ትንሳኤ የተፈጠረዉን በሙሉ ነገራቸዉ ዮናስ ተበሳጨ
"አረ አፍቃሪዉ ተበልተሀል የሆነ በሙድ አትገባላትም ነበር ዝም ብለህ እወድሻለሁ አረ አይነፌክስ"
ትንሳኤ ላይ የእዉነት ወረደበት ተናዶ
ለትንሳኤ መልካም ስለሚያስብ ነበር
ምክንያቱም ሲጨነቅ ስለሷ ሲያስብ የእዉነት እንደወደዳት አስተዉሎታል
ትንሳኤም ግልፅ ስለሚያወራ ቀንም ማታም ስለሷ ቢያወራ ስለማይጠግብ ሁሉንም ስሜቱን ሳይደብቅ ይነግራቸዉ ስለነበረ ነዉ
በተቃራኒዉ እዮብ
"ዋናዉ ማዋራትህ ነዉ አንበሳ እኔኮ ትመቺኛለሽ"
ሲል በእጁ የትንሳኤን ትከሻ ከነካ በኃላ
"በቅርቡ የሆነ ብር አገኛለሁ እጋብዝሀለዉ ጭንቀትህንም ትረሳለህ"
ሲል አከለበት
ታሪኩ እንዲህ እያለ ቀጠለ ትንሳኤ እወድሻለሁ ካላት በኋላ ህሊና ገና ከሩቁ ትንሳኤን ካየችዉ መሸሽ መንገድ መቀየር በተለይ የትንሳኤ ክፍል ካሉት ጉዋደኞቿ ጋር ትንሳኤን ላለማየት እሱ ክፍል መምጣት ተወች
በተለይ የጉዋደኞቿ አይን ትንሳኤ ላይ በረታበት በአይናቸዉ ያወራሉ ሁሌ ሲያያቸወ እያሽሟጠጡበት እየተረቡት ይመስለዋል አንዳንዴ ወንድ ቢሆኑና ብደባደባቸዉ ብሎ ያስባል
በአይናቸዉ ጥንብእርኩሱን ያወጡት ጀመር።
ህሊናም ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ተጠየፈችዉ ትሸሸዉ ጀመር
ትንሳኤ ፍቅር ብሎ የጉዋደኛዉን የዮናስን ምክር ሳይሰማ ዘባርቆ የተምታታ ስሜት ዉስጥ ገብቶ
በተቀመጠበት ስዓት እዮብ
"ፈታ ላርግህ ወንድሜ"
ብሎ ይዞት ከትምህርት ቤቱ ግቢ ምሳ ሰአት ላይ ይዞት ወጣ
በአቅራቢያቸዉ ካለ ጠላ ቤት ገብተዉ የሚጣፍጥ ድንች በሚጥሚጣ ከበሉ በኋላ ጠላ በጣሳ ይዘዉ እየጠጡ ተቀመጡ
ትንሳኤ ስለ ህሊና መለዋወጥ በልቡ እያሰበ ጠላዉን መጎንጨት ተያያዘዉ ወደ ሞቅታ ሲገባ ተነስቶ ቆሞ
የለበሰዉን የትምህርት ቤቱን ሸሚዝ አዉልቆ በቲሸርት ሆኖ ወደ ትምህርት ቤቱ በፍጥነት መራመድ ጀመረ
ሁኔታዉ ያልጣመው እዮብ ሂሳብ ከፍሎ እየሮጠ ተከተለው
ትንሳኤ ደረጃ ወጥቶ ወደ ህሊና ክፍል ሊደርስ ሲል አፍንጫዉን ነካ አርጎ አየር ከሳበ በኋላ
ወደ ህሊና ክፍል ስትት ብሎ ገባ
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ

#ሮሜዎና_ዡልዬት
#ክፍል_ሶስት
#ሜርኮቲዎ
የሆነስ ሆነና ቀጠሮ ግን አለክ?
#ሮሜዎ ።
የወጣ ፡ ቃል ፡ የለም ፡ አፋችን ፡ ተናግሮ ፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ ተያይተን ፡ ባይን ፡ ስንገናኝ ፡
ለኔ ፡ መፈጠሯ ፡ ለልቤ ፡ ተሰማኝ ።
እሷም ፡ እንደዚሁ ፡ በውስጣዊ ፡ ልቧ ፡
አይጠረጠርም ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማሰቧ ።
እጅግ ፡ የሚያስደንቅ ፡ ለብልኋ፡ አስተዋይ
እነሆ ፡ ይኸ ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ፍቅር ፡ ጠባይ
አፍ ፡ ሳይንቀሳቀስ ፡ ታስሮ ፡ በዝምታ ፡
ልብ ፡ ከልብ ፡ ጋራ ፡ ያደርጋል ፡ ጨዋታ ፡
ተወኝ ፡ ልሂድበት ፡ እንግዲህ ፡ ደኅና ፡ እደር ፤
እኔን ፡ አየሁ ፡ ብለህ ፡ ለሰው ፡ አትናገር ።
(ሮሜዎ ፡ ሄደ) ።
#ሮሜዎ ፡ (በዡልዬት ፡ መኝታ ፡ ቤት ፡ አጠገብ • ማታ፡በጨረቃ ከውጭ ፡ ሆኖ)
የሚያፈቅራትን ፡ ልጅ ፡ የሚጠብቅ ፡ ወጣት ፡ ረዝሞ ፡ ይታየዋል ፡ ደቂቃ ፡ እንደ ሰዓት ፤ሰዓቱም ፡ እንደ ፡ ቀን ፥ ቀኑም ፡ እንደ ፡ ዘመን እኔስ ፡ መሞቴ ፡ ነው ፡ በፍቅሯ ፡ ሰመመን ።
(#ዡልዬት ፡ መስኮት ከፍታ'ብቅ'አለች "
አሳቤ ፡ ተነሣ 'ተከፈቱ'ዐይኖቼ፤
ደሜ ፡ ተንቀሳቀስ፡ተፍታቱ ፡ ሥሮቼ ።
ልቤ ፡ ተስፋ፡ ሲቈርጥ ፡ የማትወጣ ፡ መስሎት ፡ ያቻት፡ የኔ ፡ ሥራ ፡ ብቅ አለች ፡ በመስኮት ።
ልቤ ፡ ደስ ፡ ይበልህ ፡ መንፈሴ ተሸበር ፤
የዡልዬትን ፡ ውበት ፡ እንግዴህ 'ልናገር ፤
መስኮቷ ፡ ምሥራቅ ፡ ነው' ፊቷ' የጧት'ጀንበር ብርሃኗ' የለውም ፡ የሚያግደው ' ድንበር ።
ሰላም ፡ ላንቺ ፡ ይሁን ፡ ትልሻለች ፡ ነፍሴ ፤
ጮራሽ፡ ኣለበሰኝ ፡ ከእግር ፡ እስከ ፡ ራሴ ፡
እኔ ፡ እንደምወድሽ ፡ አታውቂውም ፡ ፍቅሬ ፤
አላጫወትኩሽም ፡ ባፌ ፡ ተናግሬ ፡
ካየሁሽ ፡ ይበቃል ፡ ቆሜ' ከሩቅ ፡ ቦታ፤
ያጠግበኛልና 'ያይኖችሽ ፡ ጨዋታ ፡
ዐይንሽ ፡ የሚመስለው ' የርግብ ፡ የሚዳቋ ፣
እኔ ፡ የማልጠግበው 'አለው ፡ ልዩ ፡ ቋንቋ
ዐይኔ ፡ እንደ ፡ ቀለበት ፡ ጣትሽ ፡ ላይ ፡ ተሰካ ፤
እዩት ፡ በቀኝ ፡ እጅዋ 'ጕንጮቿን ' ስትነካ ፡
የእጅ ፡ ሹራብ ፡ ሆኜ፡ ገላሽን ፡ ባለብሰው ፡
ፊትሽን ፡ ጕንጭሽን' ዡልዬት፡ብዳብሰው ፡
ደስታ፡ሕይወቴን'እንደ 'ምን' ባደሰው !
#ዡልዬት ።
ሮሜዎ፡ሮሜዎ'የልቤ'ወለላ '
እባክህ ፡ ለውጠው ፡ ስምህን ፡ በሌላ ፡
ፍቅራችንን 'ገደል ፡ ሆኖ ፡ የሚያግደው
ቂም ፡ በቀል ፡ ስላለ ፡ ኀጢአት ፡ የወለደው ,
እኔም ፡ ዘሬን ፡ ልካድ፤ አንተም'ዘርህን ፡
የኔ ፡ አባት ፡ ላንተ' አባት ፤ የናንተ ፡ ዘር ፡ ለኛ መሆኑን ' አትርሳ ፡ ባላንጣ 'ደመኛ ።
#ሮሜዎ ።
ይህን ፡ ኣልዘነጋም ፡ ዡልዬት ፡ ይሰማኛል
ነገር ፡ ግን 'ምን ፡ በቀል'ምንስ'ቂም ፡ ይገኛል ፡
ምንስ ' ጠላትነት ስታስቢው ፡ በሰው ፡
የፍቅር ፡ ማዕበል ፡ የማይደመስሰው ፡
የኔ ፡ አባት ፡ ላንች ፡ አባት' ቢሆንም ፡ ባላንጣ ፡
እኔ ፡ እወድሻለሁ ፡ ነፍሴ ፡ እስክትወጣ ።
#ዡልዬት
ሮሜዎ ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ዕድሜ ፡ ለሰው ፡ ክፋት !
በፍቅር ፡ መካከል ፡ አለ ፡ ብዙ፡ ዕንቅፋት ፡
የጌታ ፡ ልጅ'ድኻን 'አይውደድ' ይላሉ ፤
ብዙዎች ፡ ልጃቸውን ' በዚህ ' ይክዳሉ ፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ የሰው ፡ ልብ ፡ በሰው ፡ አይመራም
የፍቅራችን ፡ መብራት፡በትእዛዝ አይበራም
ልጅ' ካባት 'አጣልቶ፡ብዙ፡ ሰው ፡ የጐዳ '
ይህን'የመሰለ'አለብን'ብዙ ዕዳ "
ቂም ፡ በቀል ፡ የሚሉት ፡ መከረኛ' ጣጣ'
ካያት ፡ ካባት ' ከናት ' ከዘር ፡ የሚመጣ
እኛ ፡ እንዳንፋቀር ፡ ማንንም ፡ ሳንፈራ ፡
ሆኖብን ፡ ተገኘ ፡ የፍቅር 'ደንቃራ ፤
ዳሩ ፡ ግን ፡ ይህ ፡ እክል ፡ ለሰው ፡ የማይራራ
እጅ ፡ እግር ፡ የሌለው ፡ እኛ፡ የማናውቀው፡
አይችልም ፡ ልብህን ፡ ከልቤ ፡ ሊያርቀው :
ሞንታግስ ምንድነው ፡ ፊደል አይደለም፡ ወይ ?
እኛን ፡ ሊለያየን'አይችልም ፡ ፍቅሬ ፡ ሆይ ፡
ስሟን 'ብንለውጠው ፡ እስቲ ፡ ጽጌ'ረዳ ፡
ይችላል ፡ ወይ ፡ መልኳ፡ ሊለወጥ ' ሊጐዳ
አይችልም ፡ ውሸት ፡ ነው ፡ በማዛ ፡ በውበት ፤
ጽጌ ረዳ'ያው ፡ ነች፡አይነካትም ፡ጕድለት ፡
ሮሜዎም ፡ እንዲሁ ፡ ስሙን ፡ ቢለውጠው ፡
ባሕርዩን 'ኣይችልም ፡ ከቶ ፡ ሊያናውጠው
ተወዳጅነቱ ፡ እስከ ፡ ዘላለሙ ፡
በጠባይ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ በስሙ ።
ያንተ ፡ ስም ፡ ቢለወጥ፡ ዋጋህን ፡ አትርሳ ፡
እኔን ፡ ማግኘትህ ፡ ነው ፡ ያንተ ፡ ትልቅ ፡ ካሳ ።
#ሮሜዎ ።
በመካከላችን ፡የተገኘው ፡ እክል ፡
ስሜ ፡ ከሆነማ ፡ የኛ ፡ መሰናክል ፡
አጭር ፡ ነው፡ ነገሩ፡ ዡልዬት፡ የኔ፡ ፋና ፡
አንቺን ፡ ደስ ፡ እንዲልሽ ፡ ለፍቅሬ ፡ ዋስትና ፡
ላደርገው ፡ የማልፈቅድ ፡ ነገር ፡ የለምና ፤
ቢያስፈልግ ፡ ልነሣ ፡ ዳግም ፡ ክርስትና ፡
ሲሰማ ፡ እንዳይቀፈው ፡ ስሜን ፡ ያንቺ ፡ ዦሮ ፡
ሮሜዎ ፡ኣይደለሁም ፡ ከዛሬ፡ ጀምሮ ፤
ፍቅርሽና ፡ ፍቅሬ ፡ በዘር ፡ ቂም ፡ ኣይፈርስም ፤
ከዛሬ ጀምሮ' ይለወጥ ፡ የኔ ፡ ስም ።
#ዡልዬት ።
ማነህ ፡ አንተ ፡ ከዚህ ፡ የቆምከው ፡ ከደጄ ?
ባይኔ ፡ የማላይህ ፡ የማልነካህ ፡ በእጄ ፡
ጨለማ ፡ የለበስክ ፡ የፍቅር ፡ ማዕበል ፡
የልቤ ፡ ነበልባል ፡ ስምህን ፡ ማ ፡ ልበል?
#ሮሜዎ ።
ባንቺ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ፡ የሚኖር ፡ ከርታታ፡
የቀን ፡ ብርሃን ፡ ሸሽቶ ፡ የመጣ ፡ በማታ ፡
አንቺን በመውደዱ ፡ ከራሱ'አብልጦ ፡
ያለ ፡ ስም ፡ የቀረ ፡ ስሙንም ፡ ለውጦ ።
#ዡልዬት ።
ያጥራችን ፡ ግንቡ ፡ ትልቅ ፡ አይበገር ፤ ..
እንዴት ፡ ነው ፡ የገባህ ፡ አንተም ሳትቸገር ? .
መች ፡አጥር ፡ብቻ ነው ፡ ትልቁን ፡ጉድ ትቼ
ደግሞም ፡ ይገድሉሃል ፡ቢያዩህ ፡ ዘመዶቼ
#ሮሜዎ ።
ፍቅር ፡ ስለ ፡ ሆነ ፡ ጕልበቴና ፡ ክንፌ ፡
ግንቡ ፡ ሳያግደኝ መጣሁኝ ፡ አልፌ ፡
ጨለማም ፡ አጥርም ፡ ሳያሰናክለኝ ፡
እንዴት ፡ ያለ ፡ ሰው ፡ ነው ፡የሚከለክለኝ ?
#ዡልዬት ።
ታዲያ ፡ እዚህ ፡ ቢያገኙህ፡ይገድሉህ ፡ የለም ፡ ወይ?
#ሮሜዎ ።
ለኔ ፡ ምንም ፡ አይዶል ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ፍቅሬ ፡ ሆይ ፡
አጥር ፡ እጥሳለሁ ፡ ጦርም ፡ አያግደኝ ፤
ብርሃን ፡ የሞላበት ፡ እኔን ፡ ያሳበደኝ ፡
ጦሩስ ፡ ያንቺ ፡ ዐይን ፡ ነው ፡ የኔን ፡ ልብ ፡ የወጋ
በፍቅር ፡ ኣይተሽኝ ፡ መንፈሴ ፡ ቢረጋ ፤
ምንም ፡ ባላሠጋኝ ፡ የቀረው ፡ አደጋ ።
#ዡልዬት ።
ሳይህ ፡ በኛ ፡ ግቢ ፡ ይሰማኛል ፡ ሥጋት ፤
በሻምላ ፡ ወይ ፡ በጦር ፡ ልብህን ' ለመውጋት ፡
ስለማይመለስ ፡ ወገኔ ፡ አንተን ፡ አይቶ ፡
ቢያዩህ ፡ አልፈልግም ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ ከቶ ።
#ሮሜዎ
ዥልዬት ፡ አታስቢ ፡ አትሥጊ ፡ለነፍሴ
ወዳንቺ' ስመጣ፡ ጨለማ ፡ ነው ፡ ልብሴ ፡
ትወጂኝ ፡ አትወጂኝ ፡ ባለመለየቴ ፡
ይህ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ሕመሜና' ሞቴ ፤
ስለዚህ ፡ ንገሪኝ፡ ምንም ፡ አትደብቂ ፤
ሌላውን'አደጋ ፡ ግድ ፡ የለሽም ፡ ናቂ ።
አትወጂኝ' እንደሆን ፡ ሰፊ ፡ ነው፡ ሐዘኔ ፤
በዚህ ፡ ሕመም ፡ ብቻ ፡ እሞታለሁ ፡ እኔ ።
#ዡልዬት ።
እፍረት ፡ እንዳይዘኝ ፡ ጨለማ ፡ ለብሼ ፡
እንግዲያው ' ልንገርህ ፡ አሳቤን ፡ ጨርሼ
እፍረት'ደኅናሰንብት መግደርደር ደኅና ሁን
ሮሜዎ 'አንድ ፡ ነገር ፡ ልጠይቅህ ፡ አሁን ፡
ከፊቴ የቆምከው ፡ ወዳጄ ፡ ፍቅሬ 'ሆይ'
ካንጀትህ ' ከልብህ ፡ ትወደኛለህ ' ወይ ?
ማንንም ፡ አልወድም ፡ ብለህ ፡ካንቺ ፡ሌላ
ትናገራለህ ፡ ወይ ፡ አሁን ፡ በመሐላ ?
እኔ ፡ ባንተ ፡ ፍቅር በጣም ፡ ተጨንቄ '
ስለምወድህ ፡ ነው ይህን

መጠየቄ '
እኔስ ፡ የት'ዐውቃለሁ፡ትወደኝ' አትወደኝ
ይህንን • ከድፍረት' ቆጥረህ 'አትፍረደኝ "
ካፌ፡ በመውጣቱ ፡ እንደዚህ ፡ ያለ ፡ ቃል ፡
እንዳትገምተው ፡ ጠባዬን ፡ በቀላል ፥
ከልብህ ፡ እንደሆን ፡ መንፈሴ ፡ ይረጋል ፤
መሠረት ፡ ከሌለው ፡ ፍቅር ፡ ምን ፡ ያደርጋል ።
#ሮሜዎ ።
እንደ ኣልማዝ እንደ ፡ዕንቍ ውበቷ' በጠራ'
በመስክ ፡ በሸለቆ ፡ በዱር ፡ በተራራ ፡
ብርሃን ፡ በዘረጋች ፡ መሬት ፡ ላይ ፡ ፈንጥቃ ፡
እምልልሻለሁ ፡ በዚች ፡ በጨረቃ ።
#ዝልዬት ።
ተው ፡ አስብ ፡ ተመልከት ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ፍራ ፤
ፍቅርህ ፡ ተለዋዋጭ ፡ እንዳይሆን ፡ አደራ
በጨረቃ ' አትማል ፡ በዚች ፡ ወረተኛ፤
ሁሉ ፡ ቀን ፡ አትገኝ ፡ ዘወትር ፡ መንገደኛ ፡
ወር፡አይሞላምና ፡ ይህ ፡ የሷ ፡ ግሥገሳ፤
ምን ፡ ጊዜም ፡ ያስታውሰው ፥ ልቡናህ ፡ አይርሳ '
አለች ፡ ስንል ፡ ኰርተን ፡ በብርሃን ፡ ሞገሷ፡
ለጨለማ ፡ ትታን ፡ ትጠፋለች ፡ እሷ ።
#ሮሜዎ ።
በምን 'ልማልልሽ ንገሪኝ' ዥልዬት !
💫ይቀጥላል💫
እኔስ ፡ የት'ዐውቃለሁ፡ትወደኝ' አትወደኝ
ይህንን • ከድፍረት' ቆጥረህ 'አትፍረደኝ "
ካፌ፡ በመውጣቱ ፡ እንደዚህ ፡ ያለ ፡ ቃል ፡
እንዳትገምተው ፡ ጠባዬን ፡ በቀላል ፥
ከልብህ ፡ እንደሆን ፡ መንፈሴ ፡ ይረጋል ፤
መሠረት ፡ ከሌለው ፡ ፍቅር ፡ ምን ፡ ያደርጋል ።
#ሮሜዎ ።
እንደ ኣልማዝ እንደ ፡ዕንቍ ውበቷ' በጠራ'
በመስክ ፡ በሸለቆ ፡ በዱር ፡ በተራራ ፡
ብርሃን ፡ በዘረጋች ፡ መሬት ፡ ላይ ፡ ፈንጥቃ ፡
እምልልሻለሁ ፡ በዚች ፡ በጨረቃ ።
#ዝልዬት ።
ተው ፡ አስብ ፡ ተመልከት ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ፍራ ፤
ፍቅርህ ፡ ተለዋዋጭ ፡ እንዳይሆን ፡ አደራ
በጨረቃ ' አትማል ፡ በዚች ፡ ወረተኛ፤
ሁሉ ፡ ቀን ፡ አትገኝ ፡ ዘወትር ፡ መንገደኛ ፡
ወር፡አይሞላምና ፡ ይህ ፡ የሷ ፡ ግሥገሳ፤
ምን ፡ ጊዜም ፡ ያስታውሰው ፥ ልቡናህ ፡ አይርሳ '
አለች ፡ ስንል ፡ ኰርተን ፡ በብርሃን ፡ ሞገሷ፡
ለጨለማ ፡ ትታን ፡ ትጠፋለች ፡ እሷ ።
#ሮሜዎ ።
በምን 'ልማልልሽ ንገሪኝ' ዥልዬት !
💫ይቀጥላል💫
#ያልተቋጨ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...ስተት ብሎ ገባ ህሊና ጥግ ላይ ወሬ እያወራች ነበር ስታየዉ በትንሹ ደንገጥ ብላ አፈጠጠችበት
ትንሳኤ ፊት ለፊቷ ቆሞ እጁን ወደ ኋላ ማረጉን ሲያስተዉል አሁን የመጣሁት ልለምናት እንዳይመስላት አለና እጆቹን አፍታቶ የእስዋ ዴስክን አሰደግፏቸዉ ጎንበስ ብሎ ቆመ
ህሊና ምን ሆኖ ነዉ እያለች በመገረም ታየዋለች
"ምን ሆነሽ ነዉ ግን"
አላት ቆጣ ብሎ
"ምን ሆንኩ"
አለችዉ ለስለስ ባለ ዜማ ባለዉ አነጋገር
ትንሳኤ ለአፍታ የጎዋደኞቿ ግልምጫ የእሷ መደባበቅ የእሱ የፍቅር ጥያቄ አለመሳካት ከጠጣዉ መጠጥ ጋር ተደራርቦ
"የወደድኩሽ መስሎሽ ነዉ እንደዚህ የሚያረግሽ አልወድሽም እሺ አልወድሽም"
ጮክ ብሎ ተናገረ ጉዋደኛዉ እዮብ ደርሶ እንዳይመታት ይሄ እብድ እያለ ይዞት ሊወጣ ሲሞክር
ትንሳኤ አስቸገረ አፉ
"አልወድሽም አልወድሽም "
ይበልእንጂ አሁንም ልቡ ዉስጥ ናት
ህሊና ምን ነካዉ በሚል አስተያየት እያየችዉ ትንሳኤ በጉዋደኛዉ እየተጎተተ ወጣ።
ከዛን ቡሀላ ህሊና ጭራሽ ከአይኑም እየራቀች መጣች
ሁሌ ሲገባ ግን በእሷ ክፍል እያለፈ አንገቱን ሰገግ አርግ በአይኖቹ ሳይፈልጋት ክፍሉ አይገባም
የጉዋደኞቿም አይን አፈር ከመሬት የሚያበላ ነበር
በዛ ሁሉ መሀል ግን ጉዋደኞቹ ሲያስባት እና ሲያስታዉሳት በቀልድ እያሳቁ እያስረሱት በተለይ ጠጥቶ
"አልወድሽም አልወድሽም"
ብሎ የጮሀዉን እያነሱ እሱንም ሲያፅናኑት በአይን ብቻ ጠዋት እና ከትምህርት ቤት ሲለቀቁ ስትወጣ ተደብቆ እያያት አመቱ አልቆ ክረምት ሲገባ በልቡ ብቻ ይዞ እያሰባት ተቀመጠ
በዛን ክረምት ትንሳኤ ብዙ አይነት መፅሀፍቶችን ሲያነብ ከጉዋደኞቹም ጋር ሲያዝግ ከሴቶች ጋር መቀራረብ መነጋገር የመሳሰሉት ፍርሀቶቹ ዘበት ሆነዉ ጠፍተዉ
በሚቀጥለዉ አመት ትምህርት ሲጀምሩ ምላስ አርዝሞ ከትምህርቱ ቀንሶ ሌላ ሰዉ ሆኖ ገባ
ያልተቀየረዉ የህሊና ፍቅር ግን አሁንም ልቡ ዉስጥ ነበር ትምህርት ቤት ውስጥ መጀመርያ ከህሊና ጋር ሲተያዩ በረንዳ ላይ ቆማ ነበር
እንዳያት ደስ አለዉ ፈገግ እያለ ተጠጋትና
"እዚህ ምን ትሰርያለሽ ገብተሽ አትማሪም"
አላት ህሊና አይኖቿን ወደ ላይ አርጋ
"ምን አገባህ"
አለችዉ
"ዋ ስትፎርፊ እንዳላይሽ"
እያለ ቆመዉ ወደሚጠብቁት ጉዋደኞቹ አመራ።
የሆነቀን ምሳ ሰአት ናፍቃዉ ወደሷ ክፍል አመራ
አሁንም ቢሆን ግን ከሌላ ሴት ልጅ ጋር ሲሆን እንደሚያወራዉ ከበፊቱ ፍርሀቱ ቀንሷል እንጂ እሷ ጋር ሲደርስ ቃላት ይጠፉበታል ሲገባ ነጭ ወረቀት ላይ ስዕል እየሳለች አገኛት
"ቆይ እኔ ልሳልልሽ"
እያለ እስራሱን ከእሷ እጅ ተቀበላት ከጎኗ ያሉት ገዋደኞቿ እሷ እርሳሱን ለማስመለስ ስትሞክር እያዩ ይስቃሉ
ትንሳኤ በቆመበት ሳያስበዉ አፍንጫውን ሲነካ የደረቀ ን ጥ ከአፍንጫዉ ወድቆ ወረቀቱ ላይ አረፈ ህሊና
"እእይይይይይ"
እያለች ወረቀቱን አራገፈችዉ።
ትንሳኤ ጀርባዉን ሲያልበዉ ይታወቀዋል
ከአጠገቧ ገፋ አርጓት አይኑን በጨዉ አጥቦ ተቀመጠ።

ይቅርብኝ 'አትማል በውነትም ፡ በውሸት ፡
ደግሞም ፡ ልማል ፡ ብለህ፡አሳብህ ፡ ከጸና
ምን ጊዜም ፡ ጣዖቴ ፡ ፍቅሬ ፡ አንተ ፡ ነህና
በራስህ ፡ ማልልኝ ፡ የኔ ፡ ሁለንተና ።
#ሮሜዎ ።
እንግዲያውስ ፡ ስሚ ፡ እኔ ፡ አንቺን ፡ መውደዴ ፡
#ዡልዬት
ይቅር ፡ በቃ ፡ አትማል ፤ ተናወጠ ፡ ሆዴ ፡
ፈጥነህ ፡ ብትምልልኝ ፡ አሁን ፡ ዛሬ ፡ ማታ
ምንም ፡ አይሰማኝ ፡ ለልቤ ፡ ደስታ ፡
እንደዚህ ፡ በድንገት ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ፡
እንደዚህ ፡ በቶሎ ፡ የሆነ ፡ መሓላ ፡
መሠረት ፡ የለውም ፡ ይጠፋል ፡ ባንዳፍታ፤
አላፊ ፡ ነፋስ ፡ ነው ፡ የሰማይ ፡ ብልጭታ
የፍቅሩ፡ ቡቃያ ፡ ከዛሬ ፡ ጀምሮ ፡
ለምልሞ ፡ ይጠንክር ፡ በልባችን ፡ አድሮ ፡
እኛም ፡ እዚያ ፡ ድረስ ፡ሆነን ፡ ትዕግሥተኛ
ወደየቤታችን ፡ ገብተን ፡ እንተኛ ።
#ሮሜዎ ።
ልትሄጂ ፡ ነወይ ፡ ትተሽኝ ፡ በከንቱ ?
#ዥልየት ።
ይበቃል ፡ ለዛሬ ፡ መሽብን ፡ ሰዓቱ ።
#ሮሜዎ ።
ስጭኝ ፡ የሚያጠግብ፡አንድ ፡ ቃል ፡ የበቃ
#ዡልዬት ።
አንተ ፡ ሳትጠይቅ ፡ በፊት፡ዡልዬት ፡ዐውቃ
ሰጥታህ፡ወስደኸዋል፡የፍቅሯን፡ቃል ኪዳን
የተረፈው ፡ ይደር ፡ ለነገ ፡ እንዲረዳን ።
#ሮሜዎ ።
መልሰሽ ወስደሺው ፡'መልካሙን ፡ ስጦታ
#ዡልዬት ።
ቃሌን ፡ እሰጣለሁ ፡ ላንተ ፡ በችሮታ
የልቤ ፡ ደግነት ፡ ባሕር ፡ ነው ፡ ስፋቱ ፤
ፍቅሬም ፡ እንደዚሁ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ርቀቱ
መልካም ፡ ጠባዮቼ ፡ እነዚህ ፡ ሁለቱ ፡
ሰፊ ፡ ሀብት ፡ናቸው፡ ከሁሉም ፡ የላቁ ፤
ብሰጥህ ፡ ብሰጥህ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ አያልቁ ።
(#ሞግዚቷ' #ጠራቻት ) ።
ጠሩኝ ፡ ድምፅ ፡ ሰማሁ ፡ በል ፡ ሄድኩኝ፡ደኅኖ፡እደር።
ሞግዚቴ ፡ እሺ ፡ መጣሁ ፤ ሮሜዎ ፡ አንድ ነገር ፡ አለ ፡ የምነግርህ፡አትሂድ፡ጠብቀኝ ፣ (ወደቤት'ግባች) »
#ሮሜዎ : (ብቻውን) "
የዛሬው ፡ ደስታ ፡ ምንኛ ፡ ደነቀኝ ።
ሕልም ፡ ነው ፡ ራእይ፡ ወይስ ' ደግሞ ቅዠት አልችልም ፡ ይህ ፡ ነገር ፡ ከቶ'ልደርስበት ፤
ፀሓዬ ፡ ጠለቀች ፡ ገባች ፡ ወደ ፡ ቤቷ ።
አሁን ፡ ተመልሳ ፡ ዳግም ፡ በመስኮቷ ፡
ብቅ ፡ እስክትል ፡ ድረስ ፡ ሆነብኝ ፡ ጨለማ ፡
ይኸው ፡ ተመለሰ ፡ የብርሃኗ ፡ ግርማ ።
#ዡልዬት ፡(ተመልሳ • መጣች
ሮሜዎ ፡ ልንገርህ ፡ የመጨረሻ ፡ ቃል ፤
እንደምታፈቅረኝ ፡ ዐወቅሁት ፡ ይበቃል ፡
ዳሩ ፡ ግን ፡ ፍቅራችን ፡ መሠረት ፡ አግኝቶ
በተክሊል ፡ ጋብቻ ፡ እንዲፈጸም ፡ ጸንቶ ፡
ትፈቅድ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ እልካለሁና ፥
ነገ ፡ ሰው ፡ ወዳንተ ፡ ጒዳዩን ፡ ካጠናህ ፡
ካሰበ ፡ በኋላ ፡ መንፈስህ ፡ መርምሮ ፡
የተክሊሉ ፡ ሰዓት ፡ ይሁን ፡ በቀጠር ።
ወስነህ ፡ ላክብኝ ፤ ከዚያ ፡ በኋላ ፡ ግን ፡
ማመንታት ፡ ሳይኖረው ፡ ልቤ ፡ ሳይገነግን
ችግር ፡ ሳያግደኝ ፡ አደጋና ፡ ሞትም ፡
አንተን ፡ ተከትዬ ፡ እሄዳለሁ ፡ የትም ።
ነገር ግን ፡ ያንተ ፡አሳብ ከሌለው ፡ ንጽሕና
የማይሄድ ፡ ከሆነ ፡ እንደኔ ፡ ኅሊና ፡
አትምጣ፡ ወደኔ ፡ አትድከም ፡ በከንቱ
እንግዴህ ፡ ደኅና ፡ ሁን ፡ አለፈ ፡ ሰዓቱ '
ግባ ፡ ወደ ፡ ቤትህ ፡ ፍጠን ፡ አታመንታ ፤
ሊነጋ ፡ ነውና ፡ ይታያል ፡ ወገግታ ፡
ጨለማ ፡ ለቀቀ ፡ ብርሃን ፡ ተከፈተ ፡
ስንት ፡ ሰዓት ፡ ሲሆን ፡ ሰው ፡ ልላክ ፡ ወዳንተ ?
#ሮሜዎ
ሦስት ፡ ሰዓት ሲሆን መልክተኛሽ ፡ ይምጣ
#ዡልዬት ።
እንግዴህ ፡ ደኅና ፡ ሁን ፡ ፀሓይ ፡ ሳትወጣ
እንግባ ፡ ቤታችን ። (ሄደች)•
#ሮሜዎ ።
ዡልዬት ፡ ደኅና ፡ ሁኝ፤
ልቤ ፡ ካንቺ ፡ ጋራ ፡ መቅረቱን ፡ እመኝ ። (ሄዴ) •
#ሮሜዎና #ኣባ_ሎራ ፡ (ባባ ' ሎራ' ቤት)
#ሮሜዎ ።
እንደምን ፡ አድረዋል፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ?
#አባ_ሎራ
ከምሥራቅ ፡ ሳይታይ ፡ የፀሓይዋ ፡ ሥራ ፡
ማነህ ፡ በማለዳ ፡ የመጣህ ፡ ከቤቴ ?
በጣፋጩ ፡ ድምፅህ ፡ የምትል ፡ አባቴ ።
እረግ ! አንተ ፡ ነህ ፡ ወይ ፡ሮሜዎ ፡ ጐበዙ
ዐይኔ ፡ ደከመና ፡ አላየም ፡ በብዙ ፡
እንደ ፡ ምን ፡ አድረሃል ፡ የምወድህ ፡ ልጄ
ዐይንህ፡በጣም፡ቀልቷል፡ምን ነካህ ወዳጄ ?
አንድ ፡ ሰው ፡ እንደዚህ ፡ በጧት ፡ የሚነሣ
ነገር ፡ ሲያገኘው ፡ ነው ፡ እንቅልፍ ፡ የሚነሳ ፡
አሳብ ፡ የምንለው ፡ የሰላም ፡ መጋኛ ፡
መንፈሱን ፡ ሰፍሮበት ፡ እንቅልፍ ፡ የማይተኛ ፡
ሽማግሌ ፡ ሰው ፡ ነው ፤ ወጣት ፡ ግን ፡ በውኑ ፡
ከእንግዲህ ፡ ያለ ፡ ነገር ፡ ነጻ ፡ በመሆኑ ፡
ተኝቶ ፡ ያነጋል ፡ እንቅልፉን ፡ በሰላም ፤
ስለዚህ ፡ ይህ ፡ ዐይንህ ፡ በደኅናው ፡ አልቀላም ፡
ሮሜዎ ፡ ምን ፡ ሆኖ ፡ ሳይተኛ ፡ ያደረ ?
አለመተኛቱን ፡ ዐይኑ ፡ መሰከረ ።
#ሮሜዎ ።
እውነት ፡ ነው ፡ ነገር ፡ ግን ፡አርፌያለሁ ፡ በጣም
#አባ_ሎራ ።
ብታርፍማ ፡ ኖሮ ፡ በሌሊት ፡ አትመጣም ፡
ንገረኝ ፡ አትደብቅ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያደርከው ?
#ሮሜዎ ።
ድል ፡ አድራጊው : ፍቅሯ ፡ መንፈሴን ፡ ማረከው
አባቴ ፡ እጅዎ ፡ ተክሊሌን ፡ ይባርከው ።
#አባ_ሎራ ።
ያሰብከውን ፡ ነገር ፡ ንገረኝ ፡ አትፍራ ፤
ከመልካሟ ፡ እጮኛህ ፡ ከሮዛሊን ፡ ጋራ ፡
የተክሊል ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ ዛሬ ፡ ልትሞላ ፡
የመጣህ ፡ መሰለኝ ፡ ሳስበው ፡ በመላ ።
#ሮሜዎ ።
ሮዛሊን ፡ ቀርታለች ፡ አያንሷት ፡ አባቴ ፡
ትናንትና ፡ ማታ ፡ ተመታ ፡ ደረቴ ፡
ባዲስ ፡ የፍቅር ፡ ጦር ፡ በሰላ ፡ ጐራዴ ፤
ከመውደዷ ፡ ጋራ ፡ ገጠመ ፡ መውደዴ፡
ስሜታችን ፡ እኩል ፡ ፍቅራችን ፡ የጋራ ፡
ሆኖ ፡ ከተገኘ ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ፡
ተክሊሉን ፡ ይሙሉልን ፡ በሥልጣንዎ ፡ ባርከው ፡
እኛ ፡ ቂም ፡ የለንም ፤
#አባ_ሎራ ።
መንፈሴን ፡ ኣወከው
ምን ፡ አመጣህብኝ ፡ የማላውቀው ፡ ምስጢር ፥
መላ ፡ መትቶ ፡ ያውቃል ፡ ብለህ ፡ አትጠርጥር ፤
አልገባኝምና ፡ ያሁኑ ፡ ንግግር ።
ይህን ፡ እንቆቅልሽ ፡ እንደ ፡ ሾላ ፡ ድፍን ፡
ትተህ ፡ ፡ ግለጥልኝ ፡ ነገሩን ፡ ሳትሸፍን ።
#ሮሜዎ ።
አባቴ ፡ አልደብቅም ፡ ሁሉንም ፡ ገልጬ ፡
ለርስዎ ፡ ልነግር፡ ነው ፡ የመጣ ፡ ሮጬ፡
የነካፑሌን ፡ ልጅ ዡለየትን ፡ ወድጄ ፤
ራሴ ፡ እስቲጠፋ ፡ በፍቅር አብጄ ፡
እሷም ፡ በጣም ወዳኝ፡አድርገን ፡ መሐላ ፡
ተስማምተን ተዋደን ከቈረጥ ኋላ ፡
አሁን 'የሚቀረን'ተክሊል ፡ የሚሞላ ፡
ካህን ፡ ስለ ፡ ሆነ የሚሰጥ፡ ቡራኬ ፡
ከሷ ጋር ፡ መጥቼ ፈትዎ' ተንበርክኬ ፡
ሞልተው 'ያሰናብቱን የተክሊሉን ፡ ሥርዐት
ሰዓቱን 'ይንገሩኝ መቼ እንደምጠራት ።
#አባ_ሎራ
አይጣል፡ነው፡እናንተ፡ የወጣቶች ፡ ወረት፤
ፍቅራቸው ፡ ቃላቸው ፡ የለውም መሠረት፡
የቀድሞ ፡ እጮኛህ ፡ ሮዛሊን 'ተረስታ፡
ሌላ ፡ ልጅ ፡ አግኝተህ አሁን ትናንት ፡ ማታ
እንዴት ተለወጠ፡ ኣሳብህ ፡ ባንድ ፡ አፍታ፡
በሮዛሊን ፡ ፍቅር ፡ ልብህ ፡ እንዲያ፡ግሎ ፡
ዘላለም ፡ የማይበርድ፡እውነተኛ፡መስሎ ፡
ታጫውተኝ ፡ ነበር አሁን ፡ ይኸውና ፡
ያ ፡ ሁሉ ፡ መውደድህ 'ከመቼው 'ቀረና ፡
መጣህ ' ባዲስ ፡ ፍቅር ፡ ልብህ ፡ ተብረክርኮ ፡
ለምታያት፡ሁሉ፡መንፈስህ ፡ ተማርኮ፡

#መስቀልና_እና_ወንበር
“ከሰይጣን እስራት
ነፃ ልትወጡ ነው "
ይለናል አንደኛው ፥ መስቀል ላይ ተሰቅሎ
“ካንባገነን ገዢ
ነፃ ልትወጡ ነው
ይለናል ሌላኛው ፣ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ።
እኛ ህዝቦች ግን...
በወንበዴ መሃል ፥ ለሚሰቀል እውነት
ከወንበዴ መሃል ፥ለሚታጭ ሹመት
ስለሌለን እምነት
“ውረዱልን” እያልን ፥ እንጮኻለን በጣም
እነሱም አይወርዱም
እኛም ሳንገድላቸው ፥ አርነት አንወጣም ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
“ከሰይጣን እስራት
ነፃ ልትወጡ ነው "
ይለናል አንደኛው ፥ መስቀል ላይ ተሰቅሎ
“ካንባገነን ገዢ
ነፃ ልትወጡ ነው
ይለናል ሌላኛው ፣ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ።
እኛ ህዝቦች ግን...
በወንበዴ መሃል ፥ ለሚሰቀል እውነት
ከወንበዴ መሃል ፥ለሚታጭ ሹመት
ስለሌለን እምነት
“ውረዱልን” እያልን ፥ እንጮኻለን በጣም
እነሱም አይወርዱም
እኛም ሳንገድላቸው ፥ አርነት አንወጣም ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ያልተቋጨ
#ክፍል_አምስት (የመጨረሻ ክፍል)
#በክፍለማርያም
ህሊና
"አይይይይይይይ" እያለች ወረቀቱን አራገፈችዉ ትንሳኤ ጀርባዉን ሲያልበዉ ይታወቀዋል
ከአጠገቧ ገፋ አርጓት አይኑን በጨዉ አጥቦ ተቀመጠ
አንዳንዴ ተዋረድ ካለህ እንደዚህ ነዉ
አጠገቧ ተቀምጦ እጆቹን ወደ ሰደርያዋ ኪስ በቀስታ ሰዶ ከኪሷ ሶፍት አወጣ
አንደኛዋ ጉዋደኛዋ አይታዉ ሳቀች ህሊናም እንደወሰደባት ስታዉቅ ተናዳ አፈጠጠችበት
ትንሳኤም በሶፍቱ አፍንጫዉን እያበሰ በመዋረዱ በልቡ በጣም እያዘነ ሲወጣ በር ላይ ዮናስ ጠበቀዉ
"ባክህ ተዋረድኩልህ"
አለዉ ትንሳኤ በንዴት ከንፈሩን ነክሶ
"ምን ተፈጠረ"
ሲል ዮናስ አፋጠጠዉ
"ደረቅ መሆኑ ጠቅሞኛል ...."
እያለ ትንሳኤ የተፈጠረዉን ነገረዉ ከዛን ቀን ጀምሮ ነገሮች በህሊናና በእሱ መሀል ሴጣን እንዳለ ተገነዘበ እየወደዳት እያፈቀራትም ቢሆን ሌላ ሌላ ነገር ዉስጥ ገባ
የሆነ ቀን ሲያገረሽበት ለጉዋደኛዉ
"ጥራልኝ ላዋራት ናፈቀችኝ"
አለዉ
"ምን ጣጣ አለዉ"
ተከተለኝ አለዉና ወደ ህሊና ክፍል አምርተዉ ትንሳኤ በረንዳ ሲቆም ደፋሩ ጉዋደኛዉ ህሊናን አቀፍ አርጎ እያዋራት ይዧት ከወጣ በኋላ
"ተነጋገሩ "
ብሏቸዉ ትንሳኤን እና ህሊናን አገናኝቷቸዉ ሄደ።
"የመጀመርያ ቀን ቦርሳ በትከሻሽ ይዘሽ እየሳቅሽ ስትገቢ ነዉ ያየሁሽ
ደሞ በግራ እጅሽ ነዉ የምትፅፊዉ አደል"
ትንሳኤ ሊያዋራት የመጣዉ ሌላ ቢሆንም የልቡን በቻለዉ ቋንቋ መናገር ቀጠለ
ነገር ግን የህሊና መልስ
"ጉዋደኛ አለኝ አንደዉም አሁን እራሱ ሰዉ አይቶኝ ካንተ ጋር መቆሜን እንዳይነግሩት"
አለችዉ
ሀሳቡ ተበታተነ እኔ ነኝ እንጂ እስዋ አትወደኝም ሲል አስቦ በልቡ እሳት እየነደደ ዉስጡ በንዴት ግሎ
"እሺ ስታገኚኝ ግን አትዝጊኝ ሰላምታ እንኳን"
"እሺ"
ብላዉ ጥላዉ ገባች
ነገር ግን አንዴ ታክሲ ስትጠብቅ ከሩቅ አይቷት በደስታ ክንፍ ብሎ ሲጠጋት እየገላመጠች እራቀችዉ
ተከትሏት ጥቂት ለማዋራት እየሞከረ ተከተላት ነገር ግን እሷ ማዋራት አልፈለገችም
ትንሳኤ አመታት አልፈዉም አሁንም እንደ መጀመርያዉ ቦርሳ ይዛ እየሳቀች ስትገባ ያለዉ ምስል አይምሮዉ ዉስጥ አለ ፍቅሯ አመታት አልፎ እንደ ትላንት ይታወሰዋል መልኳ አይኗ ሰዉነቷ አወራሯ ሁሉ ነገሯ አይረሳዉም
ማፍቀር ማለት የማያገኙትን ሰዉ በተስፋ እንደመጠበቅ ነዉ ስሜቱ ያማል ያስከፋል መንገዱ ዉስጥ ግን አይረሴ ታሪኮች አሉ
አንድ ቀን አጊንቷት ያለ ፍርሀት ያለ ሰቀቀን እንደ ጉዋደኛ እንኳን ቢያዋራት ህልሙ ነዉ አንዳንዶች ለቀልድ ተዋዉቀዉ ይጋባሉ አንዳንዶች የእዉነት አፍቅረዉ ያጣሉ አለም ትገርማለች ፍቅርም ይገርማል ይሄ ታሪክ ለትንሳኤ የህይወቱ ክፍል ለህሊና ተራ ወሬ ሊሆን ይችላል
ትንሳኤ በልቡ የያዘዉ ታሪክ ነዉ ህሊና የናቀችዉ ተራ ነገር
ትንሳኤ በህሊና መፍረድ አቁሟል ምክንያቱም ሰዉ የፍላጎቱ ዉጤት ነዉ
የእሷ ምርጫና ፍላጎት የራሷ ዉሳኔ ነዉ
💫አለቀ💫
ነገ በተለመደው ሰዓት #ህመም_ያዘለ_ፍቅርን #ምእራፍ_ሁለት እንጀምራለን እሰከዛው መልካም ቆይታ🙏

👍3
#ሮሜዎና_ዡልዬት
#ክፍል_አምስት
ከተሸንፍክማ ' በጕንጮቿ ፡ ቅላት '
በወገቧ ቅጥነት፡ በደረቷ፡ ሙላት'
አበድኩ ፡ ካልክማ፡ ለጥርሶቿ 'ንጣት '
ለባቷ፡ አቀራረጽ ለጠጕርዋ ፡ቀለም ፡
ፍቅርህ ፡ ባይንህ ፡ ላይ ፡ነው፤ በልብህ ፡ አይደለም ይቅር በለኝ፡ልጄ፡ ባሁኑ ፡ ወቀሣ
ለዚች ፡ ከንፈህላት፡ ያችን ' ስትረሳ ፡
አመዛዘንኩና' ሠጋሁ፡ ኣስተውዬ '
ይችንም ፡ እንደዚያች' ትረሳለህ ፡ ብዬ ።
#ሮሜዎ ።
አባቴ ፡ በፍጹም ፡ ይህን ፡ አይጠርጥሩ፤
የዚችና ፡ የዚያች ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ነገሩ
በምን ፡ ቃል ፡ ልናገር ፡ ይህን ፡ ለማሳመን
በግሪክ ፡ በሮማ ፡ በጥንታዊው ፡ ዘመን ፡
ያነቡ፡ እንደ'ነበር' የእንስሳውን ፡ ሞራ ፡
ይችሉ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ አባቴ ፡ አባ፡ ሎራ '
እርስዎም ፡ እንደዚሁ፡ የልቤን ፡ ብራና፡
በጥበብ ፡ አውጥተው ፡ገልጠው፡ያንቡና '
የወረት ፡ ምልክት ፡ ቢያገኙ፡ በውስጡ '
ያን ፡ ጊዜ 'ይገባል ፡ ቢንቁኝ ፡ ቢቈጡ ።
#አባ_ሎራ ።
መልካም ነው አመንኩህ ፡ግን ከዚህ ፡ በኋላ
አንድ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ የሚያስቸግር ፡ ሌላ ፤
ካፑሌና ፡ ሞንታግ ፡ የናንተ ፡ አባቶች ፡ .
ወገኖቻቸውን ፡ ጨምረው ፡ ጠላቶች ፡
ባላንጦች ፡ ቂመኞች ፡ ደመኞች ፡ ሲሆኑ ፤
በየመንገዱ ፡ ላይ ፡ እንዳውሬ ፡ እያደኑ ፡
አንዱ ፡ አንዱን ፡ ሲገድለው ፡ ባይኑ ፡ ሲያየው፡ብቻ
እንዴት ፡ ሊፈጸም ፡ ነው ፡ የናንተ ፡ ጋብቻ ? .
ይኖሩ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ዘወትር ፡ በዘመቻ ፡
ዘለዓለም ፡ ለውጊያ ፡ ለጠብ ፡ ተሰልፈው ፡
ለቄስ ፡ ላስታራቂ ፡ ለዳኛ ፡ አሸንፈው ።
#ሮሜዎ ።
ይኸው፡አባቴ ሆይ ይህ ነው፡ ዋናው ነገር
በዚህ ፡ ላይ ፡ ይገባል ፡ በብዙ ፡ መማከር ፡
እውነት፡ ነው ፡ ቢኖሩ፡ ዘለዓለም ፡እነሱ፡
በጠብ ፡ ባምባጓሮ ፡ ደም ፡ እያፈሰሱ ፡
ለፍርድ ፡ ቢያስቸግሩ የቄስ ፡ ቃል ፡ ባይሰሙ ፡
እኔና ፡ ዡልዬት ፡ ግን ፡ንጹሕ ፡ ነን ፡ ከቂሙ፡
አለ ፡ ወይ ፡ አባቴ ፡ በሃይማኖት ፡ መንገድ
የሚከለክል ፡ ሕግ ፡ እኛ ፡ እንዳንዋደድ ፡
እንግዲህ ፡ አባቴ ፡ ይህንን ፡ ካወቁ ፡
ዘዴውን ፡ ለማግኘት ፡ እርስዎም ፡ ይጨነቁ ፡ቤተ ሰቦቻችን ወሬውን ፡ ሳይሰሙ
ተክሊሉን ፡ በምስጢር ፡ እርስዎ፡ ይፈጽሙ ።
፡
#አባ_ሎራ ።
ይህንን ፡ ታልህማ ፡ ዘዴ ፡ ጠፍቶ ፡ ለርቁ ፡
ካህንም ፡ አልቀረም ፡ አብሮ ፡ መጨነቁ ፡
ለሁለቱ ፡ ወገን ፡ ሰላምን ፡ መልሶ ፡
ያባቶቻችሁን ፡ ክፉ ፡ ቂም ፡ ደምስሶ ፡
ስለታቸው ፡ ዘወትር ፡ የሰው ፡ ደም ፡ ከማፍሰስ ፡
እንዲቆም ፡ ለማድረግ ፡ ትንሽ ፡ እንዲታገሥ ፡
ለሻምላ ፥ ለጩቤ ፥ ለሰይፍ ፡ ለጐራዴ ፡
ከዚህ ፡ የተሻለ ፡ መች ፡ ይገኛል ፡ ዘዴ ።
የናንተ ፡ ጋብቻ ፡ ይህን ፡ ቂም ፡ አብርዶ ፤
ዕርቅ ፡ ይመሠረታል ፡ ሰላምን ፡ አውርዶ ።
#ሮሜዎ ።
እንግዴህ፡ አባቴ ፡ እንፍጠን ፡ በቶሎ ፡
ተክሊሉ ፡ ይፈጸም ፡ በዛሬ ፡ቀን ፡ ውሎ ፡
ጊዜና ሰዓቱን ፡ ካልተሻማን ፡ በጣም :
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ዕንቅፋት ፡ አያጣም
#አባ_ሎራ ።
እንግዲያው ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ኑና ፡ ባሥር ፡ ሰዓት፡
ትፈጽማላችሁ ጋብቻችሁን በስራት
#የዡዬየት_ሞግዚትና #ሮሚዎ ።
#ሞግዚት ።
መልሱን ፡ ተቀብለሽ ፡ እንድትመጪ ' ብላ
ልካኝ' እመቤቴ ፡ በቶሎ ፡ አስቸኵላ '
ይኸው ፡ መጥቻለሁ፡ መልሱን ፡ ለመቀበል ፤
ቸኩያለሁና ፡ ንገረኝ፡ ቶሎ ፡ በል ።
#ሮሜዎ ።
ምላሴ 'ያሞግስ ፡ አፌም ፡ ያመስግናት ፤
በውነት' ያንቺ ፡ እመቤት ፡ የተባረከች ፡ ናት
ዐመሏ ' ጠባይዋ ፡ በለጠ ' ከመልኳ፤
ቃሏን ፡ ፈጸመችው ፡ አንቺን ፡ በመላኳ
ዥሮቼ ፡ ተከፍተው 'እሰማለሁና፡
እንግዴህ ፡ ንገሪኝ የዡልዬትን ፡ ዜና ።
#ሞግዚት
ለተነጋገርነው ፡ ትናንትና ፡ ማታ ፡
እንድትልክብኝ' ያሳብህን ፡ ሁኔታ ፡
በመጠበቅ ፡ ላይ ፡ ነኝ ፡ አስታውቀኝ ፡ በቶሎ ፤
በዪና፡ ንገሪው ፤እንደዚህ ፡ ነው፡ ብሎ ፡
አሳቡን ፡ ሲነግርሽ ፡ ተቀብለሽ ፡ አምጪ፡
ብላኝ ' መጥቻለሁ ።
#ሮሜዎ ።
መልሴን ፡ ስትሰጪ '
እንግዲያው ፡ ንገሪያት ፡ ሮሜዎ ፡ ከልቡ ፡
ይወድሻል ፡ ብለሽ ፡ መንፈሱም ፡ አሳቡ ፡
ወዳንቺ ፡ ነው ፡ በያት ፡ ንገሪያት ፡ አደራ ፤
እስቲ ፡ ልለምንሽ ፡ እባክሽ ፡ ሳልፈራ ፡
እኔ ፡ እንደምወዳት፡ እንደዚሁም ፡ እሷ'
ትወደኝ ፡ እንደሆን ፡ ዡልዬት፡ በመንፈሷ፡
ታውቂዋለሽና ፡ እባክሽ ፡ ንገሪኝ ፡
አሳቧን ፡ ጠባይዋን 'እንዳውቀው ፡
ምከሪኝ ።
#ሞግዚት ።
ምንም ፡ አልደብቅህ ፡ ልንገርህ ፡ ካንዠቴ
አንተን ፡ ስታፈቅር ፡ ዝልዬት ፡ እመቤቴ'
እመነኝ ፡ ልንገርህ ፡ በውነት ፡ ከልቧ' ነው
የመስፍኑ ዘመድ፡ፓሪስ የሚባለው፡
ሊያገባት፡ ፈልጎ ፡ መሞቱ ፡ ነው ፡ ደክሞ ፡
ጨርሳ ፡ አትወደውም፡ እሷ ፡ ግን ፡ ፈጽሞ
አታንሡ፡ትላለች ፡ የሱን ፡ ስም ፡ ከፊቴ ፤
ትቈጣለችና ፡ ስቈይ ፡ እመቤቴ ፡
ልመለስ ፡ እባክህ ፡ መልሱን ፡ ስጠኝና ፤
#ሮሜዎ
አቀርብልሻለሁ'በሰፊው ፡ ምስጋና ።
እንደዚህ ' በዪና ፡ መልሱንም ፡ ንገሪያት ፤
ከቀትር ፡ በኋላ ፡ ዛሬ ፡ ባሥር ፡ ሰዓት ፡
አባ 'ሎራ፡ ድረስ ፡ አስፈቅዳ ፡ ትምጣ፤
ተናዘን ፡ ተባርከን ፡ የተክሊሉን ፡ጣጣ፡
ደብቀው ፡ በሙሉ ፡ ሊፈጽሙ፡ ቄሱ ፡
ተስማምተናል ፡ በያት ፡ ዛሬ ፡ ሊጨርሱ ።
#አባ_ሎራ #ዡልዬት #ሮሜዎ ።
#አባ_ሎራ ።
የናንተ ፡ ጋብቻ ፡ ፍጻሜው ፡ እንዲያምር ፡
ፈጣሪ ፡ ጸጋውን ፡ ምሕረቱን ፡ ይጨምር ።
#ሮሜዎ ።
አሳቤ ' ሞላልኝ ፡ እንግዲህ ፡ አባቴ ፡
ይህ ፡ ብቻ፡ ነበረ ፡ የቀረኝ ፡ ምኞቴ ።
ከሷ'ጋራ ፡ መጥቼ ፡ ቀርበን ፡ ከመንበሩ፡
ሥራቱን ፡ ከሞላን ፡ አለቀ ፡ ነገሩ ፡
እንግዲህ ፡ ግድ ፡ የለም የመጣ ፡ ቢመጣ
#አባ_ሎራ ።
ልጄ ፡ ሆይ ፡ ብዙ ነው የዚህ ዓለም ፡ ጣጣ
ለደስታ ፡ ሐዘን ፡ ለማር ፡ አለው ፡ እሬት ፤
ጠፊ ፡ ካጥፊው ፡ ጋራ ፡ ይኖራል ፡ በመሬት
ስለዚህ ፡እግዚአብሔር መጥፎውን ፡ አርቆ
ልጄ ፡ ያኑራችሁ ፡ በሰላም ፡ ጠብቆ ።
(ዡልዩት ፡ መጣች) ።
ፍቅሯንና ፡ ጌጧን ፡ በልቧ ፡ ሸፍና ፡
አልማዟ ፡ ማስተዋል ፡ ወርቋ ፡ ትሕትና ፡
ምስጢሯን ፡ ባሳቧ ፡ በጥበብ ፡ ሰውራ ፡
ይኸው ፡ መጣችልን ፡ መልካሟ ፡ ሙሽራ
#ዡልዬት ።
ሰላም ፡ ለርስዎ ፡ ይሁን ፡ ኣባቴ ፡ አባ ሎራ
#አባ_ሎራ ።
ደኅና ፡ ነሽ ወይ? ልጄ። ወጣት ፡ ሴት ፡ ወይዘሮ ፤
መልካም ፡ ጊዜ ፡ መጣሽ ፡ ልክ ፡ በቀጠሮ
#ዡልዬት ።
አመሰግናለሁ ፡ ለኔም ፡ ለሮሜዎ ፡
አባቴ ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ በመቸገርዎ ።
#ሮሜዎ ።
እንዳንቺ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ በፍቅር ፡ ተሳስረው
ለመጡ ፡ ወጣቶች ፡ ሥራቱን ፡ አክብረው
ፍቅራቸውን ፡ ባርኮ ፡ በእጁ ፡ ሊቀድሰው ፡
ምን ፡ ጊዜም ፡ ሥራው ፡ ነው ፡ ካህን ፡ የሆነ ፡ሰው።
#አባ_ሎራ ።
እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ ካህን ፡ ይጠብቃል ፤
እውነት ፡ ነው ፡ ሮሜዎ ፡ የተናገረው ፡ ቃል'
ከቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ እንግባና ፡ በሉ ፡
ሳይዘገይ ፡ በቶሎ ፡ ይፈጸም ፡ ተክሊሉ ።
(ቤተ ፡ ክርስቲያን'ገቡ)
(#በቬሮና #ከተማ' #መንገድ) •
#ሜርኩቲዎ #ቤንቮሊዎ ፡ አንድ ፡ የእልፍኝ #አሽከር።
#ቤንቮሊዎ ።
ሜርኩቲዎ ፡ እንሂድ ፡ የካፑሌ ፡ ሰዎች ፡
ይጠፉ ፡ አይመስለኝም በነዚህ መንደሮች
ድንገት ፡ ብንገናኝ ፡ ኋላ ፡ ጠብ ፡ ይነሣል ፤
ደግሞ ፡ ጠብ ሲነሣ ፡ ጸጥታ ፡ ይፈርሳል ፡
ብንሸሽ ፡ ይሻላል ፡ ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ ጣጣ ።
#ሜርኩቲዎ ።
እነሱም ፡ አስበው ፡

ነገር ፡ እንዳይመጣ ' .
እንደ እኛ ፡ ሰላም ፡ ካልተጠነቀቁ ፡
ዳኝነትን ፡ ፈርተው ፡ ሕጉን ፡ ካልጠበቁ ፡
ዕወቅ ፡ እንዳይበቃ ፡ ጠብ ፡ ብንሸሽ ፡ እኛ
ለምሳሌ ፡ መጥቶ ፡ አንዱ፡ ጥጋበኛ ፡
ያላንድ ፡ ምክንያት ፡ ከመሬት ፡ ተነሥቶ :
እንዴት ፡ ታደርጋለህ ፡ ቢጣላህ ፡ ደንፍቶ ?
ያውም ፡ ደግሞ አንተ ፡ የባስክ ፡ ነህ ፡ ከኛ
ትንሽ ፡ የሚበቃህ ፡ ቍጡ ፡ ግልፍተኛ ።
#ቤንቮሊዎ ።
እኔስ ፡ ቢዋጣልን ፡ እወድ ፡ ነበረ ፤
ዳሩ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ ዐዋጁ ፡ አስቸገረ፡
ለጠብ ፡ ይነሣና ፡ ልቤም ፡ ሰውነቴ ፡
የመስፍኑ ፡ ቁጣ ፡ ይመጣል ፡ ከፊቴ ።
#ሜርኩቲዎ ።
የፈራኸው ፡ ነገር ፡ አልቀረም ፡ ደረሰ ፤
ቲባልት ፡ ይመስለኛል ፡ ጥቍር ፡ የለበሰ '
እነሱ ፡ አይደሉም ፡ ወይ ፡ ወዲህ ፡ የሚመጡት ?
#ቤንቮሊዎ ።
ተመልከት ፡ ካሁኑ ፡ ደሜን ፡ እንዳስቈጡት
(ቲባልት ' ለወገኖቹ ")
ነቃ ፡ ነቃ ፡ በሉ ፡ አሳዩ ፡ ጕብዝና ፤
ጠብ ፡ ቆስቋሽ ፡ ለመሆን ፡ ፈልጌያለሁና'
ይህ፡የማነው፡ሻምላ፡የዛገ፡ሳይሠራ?(ወደ 'ጠላቶቸእያየ)»
#ሜርኩቲዎ ።
ምነው ፡ ቢመለከት ፡ ዐይንህ ' እያጠራ'
💫ይቀጥላል💫
እንደ እኛ ፡ ሰላም ፡ ካልተጠነቀቁ ፡
ዳኝነትን ፡ ፈርተው ፡ ሕጉን ፡ ካልጠበቁ ፡
ዕወቅ ፡ እንዳይበቃ ፡ ጠብ ፡ ብንሸሽ ፡ እኛ
ለምሳሌ ፡ መጥቶ ፡ አንዱ፡ ጥጋበኛ ፡
ያላንድ ፡ ምክንያት ፡ ከመሬት ፡ ተነሥቶ :
እንዴት ፡ ታደርጋለህ ፡ ቢጣላህ ፡ ደንፍቶ ?
ያውም ፡ ደግሞ አንተ ፡ የባስክ ፡ ነህ ፡ ከኛ
ትንሽ ፡ የሚበቃህ ፡ ቍጡ ፡ ግልፍተኛ ።
#ቤንቮሊዎ ።
እኔስ ፡ ቢዋጣልን ፡ እወድ ፡ ነበረ ፤
ዳሩ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ ዐዋጁ ፡ አስቸገረ፡
ለጠብ ፡ ይነሣና ፡ ልቤም ፡ ሰውነቴ ፡
የመስፍኑ ፡ ቁጣ ፡ ይመጣል ፡ ከፊቴ ።
#ሜርኩቲዎ ።
የፈራኸው ፡ ነገር ፡ አልቀረም ፡ ደረሰ ፤
ቲባልት ፡ ይመስለኛል ፡ ጥቍር ፡ የለበሰ '
እነሱ ፡ አይደሉም ፡ ወይ ፡ ወዲህ ፡ የሚመጡት ?
#ቤንቮሊዎ ።
ተመልከት ፡ ካሁኑ ፡ ደሜን ፡ እንዳስቈጡት
(ቲባልት ' ለወገኖቹ ")
ነቃ ፡ ነቃ ፡ በሉ ፡ አሳዩ ፡ ጕብዝና ፤
ጠብ ፡ ቆስቋሽ ፡ ለመሆን ፡ ፈልጌያለሁና'
ይህ፡የማነው፡ሻምላ፡የዛገ፡ሳይሠራ?(ወደ 'ጠላቶቸእያየ)»
#ሜርኩቲዎ ።
ምነው ፡ ቢመለከት ፡ ዐይንህ ' እያጠራ'
💫ይቀጥላል💫