አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደለም፡፡ ድሕነትም የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ የአርባ ቀን ዕድል አይደለም፡፡››
‹‹ሕይወት ረቂቅ ሚስጥር ናት፡፡ አምላክ በጥበቡ በዚህ ዓለም ላይ ይህቺን ሚስጥራዊ ሕይወት ዕድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን፡፡ ይህቺም ከረጢት በውስጧ ዕድል በተሠኙ ፈርጦች ተሞልታለች፡፡ ከረጢቷን እንዳትሠረቅና ያለጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጪ እንዳትሆን ኃላፊነቱን ፈጣሪ ለእኛው ነው የሠጠን፡፡ በከረጢቷ ውስጥ ያሉትም ፈርጦች አንድ በአንድ በአንዴ እያብለጨለጩ ከባለከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና፡፡ በጊዜው ያልተጠቀምንባቸው ዕድሎች ከጊዜ ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈውን ይነጉዳሉ፡፡ ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደለም፡፡ ድሕነትም የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ የአርባ ቀን ዕድል አይደለም፡፡››

ከየተቆለፈበት ቁልፍ መፅሀፍ የተቀነጨበ
👍3
"ሰውረን!"

እነ ወልዋሎን ከመዳኘትግር
በወልዲያ ሜዳ ከመገኘት
ከነኃይሌ ሀገር አዳኝ ፖለቲካ
ከድሮው ጠጠር ማስቲካ
በዝናብ አር ከመወጠር
የአብይን ቀናት ከመቁጠር
ከፌዴራል ዱላ
በአደባባይ ከሚቆም *ላ
ይሄንን ግጥም ከመጨረስ
እኔን ስድ ብሎ ከመክሰስ
ሰውረን!!
ገመቹ ሜራ ፍና..
LikeBot:
በዘመናችን ብሄርተኝነት ማለት ሳይደክሙ የሌሎችን የድካም ውጤት መቀማት መሆኑን አውቃለው።አንድ ሰው በግሉ ስኬት መቀዳጀት ሲያቅተው በጥረታቸው ብልጫ ያስመዘገቡ ግለሰቦችን ስኬት ወደ ብሔር ስኬት ለውጦ ባዶነቱን ለመሙላት ይሞክራል።ሌላው፤እልም ያለ ፈሪ ሆኖ ሳለ "የበላይ ዘር "እያለ ይፎክራል።ብብቱ ውስጥ ገብተው ካልደገፉት በቀር አልጋ ላይ መውጣት የማይችል ሰውዬ፤ አበበ ቢቂላ በተነሳ ቁጥር "አበበ ኬኛ"እያለ ይኩራራል።በላይና አበበ ይስመዘገቡት ድል በላብና በደም የተገኘ የግለሰብ ጥረት ውጤት ነው። ድል በዘር አይተላለፍም የአባቶች ታላላቅነት በዘር ወደ ልጆች የሚተላለፍ ቢሆን ኖሮ ግሪኮች በዛሪይቱ የአውሮፓ እግር ሥር እንደ ጉድፍ ወድቀው ባልተገኙ ነበር። ብሔርተኝነት የግለሰብ ጥረትን ሰርቆ የራስን ድክመት ለመሙላት የሚደረግ መሰሪ እንቅስቃሴ ነው።

ከአሜን ባሻገር መፅሀፍ የተቀነጨበ
👍5
Re post..

(ጡ)

ከእኛ በላይ በልተው፣ከእኛ በላይ ጠጡ፥
በእኛ መንገድ ሄደው፣ከፍታ ላይ ወጡ፥
በሥጋ ገዘፉ፣በንዋይ ናጠጡ።
ይህን ሁሉ ይዘው፣ዛሬም ተራወጡ፥
እኛ ስላልጠፋን፣መረጋጋት አጡ።
(ምፅ!) (ምፅ!)
- - - - -
(ጢ)

ወያ.ን በቡጢ
ባፍጢሙ ገልብጦ ፥ እንትኑን በሰንጢ!
ይህ የታሪክ ትንኝ ፥ የታሪክ ሚጢጢ!
የባህል ሶዶማይ ፥ የማንነት ሉጢ!
እንረብሸው ወጥተን እናድርገው ቀውጢ!
(ምፅ!)
- - - - -
(ጣ)

ይች ድሀ ሀገር ባለ ብዙ ጣጣ፣
የተሻለዉ ሄዶ የባሰው ሲመጣ፣
የተቃናው ሁሉ ይሆናል ጎባጣ፣
ሞት ለያንዳንችን ይወጣል እንደጣ፣
እግዜር በጥበቡ ካላወጣን ነጣ።
(ምፅ!) (ምፅ!) (ምፅ!)
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
(ፊ)

" . . .ተው ተመከር ተው! አለም አላፊ ነው፤ መልክ ረጋፊ ነው፤"ብሎ ተከዘ::
እኔም መልሼ፤"ስማ! አለም አቃፊ ነው:: መልካችን ሰልፊ ነው:: ችግራችን ሰፊ ነው፤ ጭቆና ተላላፊ ነው:: መንግስት ተጋፊ ነው:: ዛሬ ብርቱ ቢመስልም ነገ ረጋፊ ነው:: እኔን ያስጨነቀኝ የኑሮ ጥፊ ነው"😁😁
(ምፅ!)
👍4
"እመጣልሻለው!"

ወርቅ ስትይ ወርቅ ጨርቅ ስትይ ጨርቅ

አንባር ስትይ አንባር አልቦም ስትይ አልቦ

ምን ያላኩት አለ ምንድን ቅራቅንቦ

ላክ ያልሽኝን ሁሉ ስልክ ጃጅቻለሁ

አሁንም ና ስትይ ቦርቄልሻለው

ደሞ አንቺ ብለሽኝ እንዴት እቀራለሁ

ይዘህ ና ያልሽኝን ሁሉን ሸምቻለው

ታማኝ ሰው ካገኘው እልክልሻለው

ደሞ አንቺ ብለሽ ኝ እንዴት እቀራለው

አንድ ቀን አንድ ቀን ካልሽኝ ነገር ተርፎ

መሳፈርያ ሳገኝ እኔም እመጣለሁ።

..ኑረዲን ኢሳ..
3
አምስት ስድስት ሰባት እና ሌሎችም ታሪኮች
በ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Re post

ፈሪ ነህ ስትዪኝ ፣ እልህ ተጋብቼ
ደፋር እንደሆንኩኝ ፣ ላሳይሽ ጓጉቼ
አንቺን ደስ እንዲልሽ
ታጣቂ ፌደራል ፣ ሰደብኩኝ ጠርቼ፡፡
ከዛስ ነው ያልሽኝ
ከዛማ በኀላ ...
ጀግና አፍቃሪነቴን ፣ ታሪክ አይረሳውም
መድፈሬን ነው እንጂ
ሌላ ምን እንደሆንኩ ፣ አላስታውሰውም፡፡
😁7👍3
ልጁ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነው። ይታመምና ፀበል ይሄዳል።
ቄስ፦ ይሄማ "ሰይጣን" ነው የሰፈረበት። ለመሆኑ መች ነው የያዝከው?
ሰይጣን፦ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ እያለ
ቄስ፦ አ…ሃ… ኖረህበት የለ እንዴ?! በል አሁን ቶሎ ልጁን ልቀቅና ውጣ።
ሰይጣን፦ ከኤለመንተሪ ጀምሮ አብሬው ተምሬማ ሳልመረቅ አለቅም😂😂
😁1
ይሰውረን (2)

መግቢያ አጥቶ ከደነበረ በሬ፤
አበሉን ተቀምቶ ካኮረፈ ካድሬ፤
የፈረንጅ ቋንቋ ስላወራ፤
ተምሬያለሁ ከሚል ዲያስፖራ፤
ከራዲዮ ፋና ጋዜጠኛ፤
አሜሪካ ከተደበቀ ፖለቲከኛ፤
ከኃይሌ ገብረሥላሴ ትንተና፤
በጃዋር ከሚሰረቅ ፈተና፤
እስረኛ እየፈለገ ፎቶ ከሚነሳ አክቲቪስት፤
ሃብቴ ህዝብ ነው ብሎ ከሚፍግር አርቲስት፤
ከኢቲቪ ውሸት፤
ከሰራዊት ፍቅሬ ቅጥፈት፤
ከሚሚ ስብሃቱ ፍንጭት፤
ከግርማ ወልደጊዮርጊስ ውፍረት፤
ይሰውረን።
በውቀቱ ስዩም..
👍51
..ዕድሌ ነው..

ዕድሌ ነው
በሚስት ልወሰን እኔ ትዳር ሲያምረኝ
ሳታገባ ምትቆይ አንድም ሴት አትገኝ

ዕድሌ ነው
እኔ ዲግሪ ስይዝ ዲግሪ ዋጋ ያጣል
ገንዘብ ያለው ሁሉ ዶክትሬት ያመጣል

ዕድሌ ነው
እኔ መድረክ ስይዝ ይፈታል ጉባኤ፤
እኔ መጾም ሲያምረኝ ይሆናል ትንሣኤ

ዕድሌ ነው
በቁርባን ለመኖር ንሰሐ ስገባ
አቁራቢው ፖትልኮ ቤተመንግሥት ገባ

ዕድሌ ነው
እኔ ኳስ ስገዛ ሜዳው ይታረሳል
እኔ ቤት ሲኖረኝ ሰፈሬ ይፈርሳል

ዕድሌ ነው
ለተሾመ ሁሉ እንዳልኖርሁ ስለፋ
እኔ አለቃ ስሆን የሚታዘዝ ጠፋ

ዕድሌ ነውና
ከዕለታት አንድ ቀን መንገሤ ባይቀርም
እኔ ንጉስ ስሆን ሀገሪቶ አትኖርም
..መላኩ አላምረው..
👍7
ውድ የቻናላችን ተከታዮች በዳኛቸው ወርቁ የተደረሰውን አደፍርስ የተሰኘውን መፅሐፍ ሙሉውን በPdf አቅርበንላችሆል መልካም ንባብ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
እያንዳንድሽ!
ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ ፤ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ
በፀደይ ወቅት፤ የስሚዛ አበባ የጠባሽ
ድድሽን ባጋም እሾህ ፤የተነቀስሽ
ጡትሽን ለማስተለቅ፤አጎጠጎጤሽን በውሃ እናት ያስነከስሽ
ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፤ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ
በቃቃ ጨዋታ ወግ፤ በሽቦ መኪና አጀብ የተዳርሽ
ሳይማር በሚያስተምር፤ መምህር የተማርሽ፤
ሲያደንቁሽ የተሽኮረምምሽ፤
ሲነኩሽ የተስለመለምሽ
ሲስሙሽ ፤አገር ለቀሽ ለመመነን ያለምሽ
በቸርቺል ጎዳና ላይ፤ ሰኞ ማክሰኞ የተጫወትሽ
የኔ ትውልድ አባል ነሽ
ብትኮሪ ምክንያት አለሽ
እያንዳንድህ
በጅምር አስፋልት ላይ ፤ሽኩኔታ የነዳህ
ወይራ ከታጠነ ማድጋ ፤በመርቲ ጣሳ የቀዳህ
በጥቂቱ የረካህ ፤በመናኛው የተደነቅህ
ድንኩዋን ሰብረህ፤በቅልውጥ ፤የጎረቤት ሰርግ ያደመቅህ፤
ካባትህ ሽልንግ ሰርቀህ “ዲስኮ ዳንሰርን” ያየህ
ባስር ሳንቲም ፤ትኩስ ሽልጦ የገበየህ
በየመስኩ በየፈፋው፤ ፋንድያህን የነሰነስህ
በብሳና ቅጠል፤ የጅራት ማብቀያህን ያበስህ፤
በችፍርግ ጥርስህን ያነጣህ
ከጆሮህ ውስጥ፤ ሰርጎ ገብ በረሮ ያወጣህ፤
በቃቃ ጨዋታ ላይ፤ የህልምህን ቆንጆ ያጨህ
ራስህን በቤሳ ምላጭ የተላጨህ
ጎረምሳና ኮረዳ ተቃቅፈው ሲሄዱ ስታይ፤ እየተከተልህ ድንጋይ የወረወርህ
ገራም ፍቅርን የወገርህ፤
የሩፋዔል ቀን ታጥበህ፤ ዐመቱን ሙሉ ያደፍህ
በውሃ ቀጠነ የተገረፍህ
ከፖሊዮ በክትባት፤
ከብሄራዊ ውትድርና በብልሃት -
የተረፍህ፤
ከገበሬ ማሳ ላይ በቆሎ እሸት የዘረፍህ
በዳጥና በሸርተቴ ፤ቁምጣ ሱሪህን የጨረስህ
ስሚዛ ስር ተደብቀህ፤የሲጃራ ቂጥ ያጨስህ
ያያትህን የማያልቅ ተረት ፤ያባትህን የማያባራ ኩርኩም የታገስህ
ያለህን ያልቆጠብህ፤ በስስት ያልተንገበገብህ
እንደ አቡየ አይንህን ለወፍ ማጠጣት ባትችል እንኩዋ፤ ጣትህን ለሙጀሌ የመገብህ
የኔ ትውልድ አባል ነህ
ብትኮራ ምክንያት አለህ!

በውቄ....
👍3
..ሚስቴና ባሎቿ..

ሸማኔ ነሽ ስልሽ ወናፍ ነህ ስትይኝ
አንድ ጊዜ ወደ ዚ አንድ ጊዜ ወደዛ ስትቀባበይኝ
ዘመናት አለፉ በቅጡ ሳታይኝ
በባሎችሽ ብዛት መች እገረማለው
ጥላሽ ነኝ ዘውሪኝ እዚም እዛም አለው
ስለማገጥሽብኝ አ ደለም ያመመኝ
ስላልታመንሽልኝ አይ ደለም ያመመኝ
እናም የኔ ፍቅር እኔን የገረመኝ
ሙሰኛው ወዳጅሽ ጭንሽን የወደደ
ሲያማግጥሽ ከርሞ ከኔ እየወሰደ
የአገርህን ንዋይ መዝርበሀል ተብሎ ዘብጥያ ወረደ
አደራሽን ውዴ እኔ የቀጠርኩሽ ቀን
ባለበሰሽ ቀሚስ አልይ ተዘናፍለሽ
እሱ በሰጠሽ ጌጥ አትምጪ ተኩለሽ
ከመንግስት ካዝና ጋር ታነካኪኛለሽ
እናም የኔ ፍቅር እኔን የገረነኝ
ዲያስፖራው ባልሽ እንደውም አንዳንዴ ዶላር ሲልክልሽ
የራቁት ፎቶሽን አሳይኝ የሚልሽ
አዎ እሱ ባልሽ
ከጠፋ በኃላ ኢህአዴግ ለስራ አሜሪካን ልኮት
ቀን ቀን ጋዝ ስቴሽን ማታ ማታ ቦይ ኮት
ሆኖል አሉ ስራው ምከሪው እባክሽ
ዘፍኝ እንዳታጣ አገሬ አገርሽ
እናም የኔ ፍቅር እኔን የገረመኝ
በተድላ በንዋይ የተንቆጠቆጠው
ያ ነጋዴው ባልሽ እጣን የሚቸጠው
ካሳበዱት በኃላ ግብር ክፈል ብለው
መቶ ሺ ገምተው ወይ ግብሩን መክፈል አልያም ንግዱን መተው
በሚል ተወዛግቦ
ሱቁን ባድማ ዘግቶ እጣኑን ሰብስቦ
ግብር የሌለው ንግድ ወጪ የሌለው ትርፍ አውርዶ አውጥቶ
ጠንቋይ ቤት ከፈት እመሀል መርካቶ
ይሄ ጠንቋይ ባልሽ የነገን የሚያውቀው
ሄደሽ ከካደምሽው አለኝ የምጠይቀው
ያገሬ መከራ መቼ ነው የሚያልቀው
እናም የኔ ፍቅር እኔን የገረመኝ
ያ ወያኔው ባልሽ ስልጣን ሊሰጡት ነው ብለሽ የዋሸሺኝ
ደህና ሆኖ የማያውቅ ደህንነት ነው ያልሽኝ
ወጣቱን በሙሉ ሲያስር ሰንብቶ
ከአራት ካድሪዎች ጋር አንድ ለ አምስት ተደራጅቶ
ቢዝነስ ሊሰራ ሲል ትልቅ ጫት ቤት ከፍቶ ያቢዮት ሱሰኞች ስለመብት የቆሙ
አድማ ሰለመቱ እሱ ጋር ላይቅሙ
ችላ ብሎ ትቶት ለጫት ቤት የወጣውን የመንግስትን እዳ
ክፍለ ሀገር አየሁት ሰላም ባስ ሲነዳ
እናም የኔ ፍቅር የለም የማይገርመኝ
ካንቺ ጋር እስካለሁ እኔ ራሱ አላቅም ምን እንደሚገጥመኝ
አንቺን ተከትለው ቱጃሮች ሲከስሩ
አንቺን ተከትለው ሌቦች ሲታሰሩ
እከተልሻለው ማቅ ውስጥ እስክገባ
ለብርቱ ወንድ ሁሉ ከስኬቱ ጀርባ አስቀምጦል እግዜሩ እንዳንቺ አይነት ሌባ...
..ግሩም...
👍9
. 人 ★* 。 • ˚* ˚ 🌙
. (__ _) *ዒድ ሙባረክ* ★
. ┃口┃ *ተቀበለሏሁ ሚና*
. ┃口┃★ *ወሚንኩም *˛•
. ┃口┃★ 。* •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)
┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ┃. ┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ||三||_||三三三三三||

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዬች የቻናላችን ተከታዬች እንኳን ለ1439ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም በአል..