አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በክፍለማርያም

....መጥፋቱን አስታወሰ
ህይወት ብዙ ሰወችን ታገናኘናለች የሚወዱን የምንወዳቸዉ
የሚጠሉን የምንጠላቸዉ
ይሄ ሁሌም ያለ እዉነት ነዉ ነገር ግን
ወዳጅ መስለዉ የቀረቡን ጠላቶቻችንን ማወቅ ይከብዳል
ለዚህም ነዉ አንዳንዴ የኔ ያልነዉ ሰዉ
ሳንጠብቀዉ ተለዉጦ ጋኔል ይሆንብናል
በተቃራኒዉም የጠላነዉ ሰዉ አልፎ አልፎ ስንቀርበዉ መልዓክ ይሆናል።

ፍፁምንም የገጠመዉ ይሄ ነዉ ፍቃዱን ቤቱ ያስገባበት ቀን
ዉስን ነዉ በጣት የሚቆጠር በጊዜዉ ዉስጡ ላይ የፍቃዱ ተንኮል ስላልታየዉ
ልብ ብሎ አልተከታተለዉም እንጂ ፍቃዱ የቤዛዊትን እና የፍቃዱን ፍቅር ያዉቅ ነበር
ፍፁም ስለቤዛዊት ሲጠይቀዉም ፍቃዱ የሚመልስለት
ስለ ቤዛዊት ህመም መጥፎ መጥፎዉን እንጂ ጥሩ እና መልካም ጎኗን ነግሮት አያዉቅም
ፍቃዱም በቤዛዊት ዉበት የቤዛዊትን አማላይ ሰዉነት
በፍትወት ሲመኛት አመታት አልፈዉታል
ለዚህም ነዉ የፍፁምን መልካም ጎን አይቶ እሱ በክፋት ተጠቅሞበት አሁን ሊያለያያቸዉ የበቃዉ።

ፍፁም ለሊቱን ሲብከነከን ማረግ ያለበትን ሲያስብ ሲጨነቅ አልፎ
የማይነጋ ለሊት የለም ነግቶ ከአልጋዉ ወርዶ
ለአለባበሱ ሳይጨነቅ ከላይ በተኛበት ቲሸርት ከስር የለበሰዉን
ሰፊ ቱታ ለብሶ ነጠላ ጫማ ተጫምቷ ወደ ቤዛዊት ቤት አመራ።

ቤዛዊት ሀዘኗ እንደጉም ትንን ብሎ በተለመደዉ ፈገግታዋ
እና ዉበቷ ደምቃ ለትምህርት ከቤቷ ቶሎ ወጥታለች
ፍፁም ቤቷ ደርሶ
በራቸዉን ለማንኳኳት አስቦ እያተጨነቀ በሩ ተከፍቶ እህቷ ወጣች።
"እንዴት አደርክ ፍፁም.."
የቤዛዊት እህት ፍፁምን ባላሰበችዉ ሰዓት ስላየችዉ
እየተገረመች እያየችዉ
"ቤዛዊት አለች"
አጭር ቃላት ከአፉ ወጡ
"ዉይ አሁን ወጣች ወደ ትምህርት ቤት.."
ሌላ የምታወራዉን አልሰማትም ፍፁም አንገቱን
መሬት ላይ አቀርቅሮ ወደ ትምህርት ቤቱ ወደሚወስደዉ
አቅጣጫ ተጓዘ እየተብከነከነ።
ቤዛዊት ወደ ትምህርት ቤት እያመራች ፍፁምን በልቧ
አስታዉሳዉ እንደ ጠላቷ እረገመችዉ
"እንዴት እንደዚህ ያረገኛል"
"እጠላዋለሁ!!"
እያለች ስትጓዝ ሳታስበዉ የትምህርት ቤቷ በር አካባቢ ደርሳ ፍቃዱ ፊት ለፊቷ ቆሞ አስቆማት።
"ሀይ ቤዚ"
ፍቃዱ ድምፁን እያስለመለመ እጁን ዘረጋ
"ደህና"
በግዴለሽነት እጇን ዘረጋችለት።
ከትምህርት ቤቱ መግቢያ ካለዉ ከስፓልት መንገድ
ባል መኪናዉን በፍጥነት እየነዳ
ከባለቤቱ ጋር ይጨቃጨቃል
እስዋ መሳደብ ጀምራለች እሱ መለመን እና ማባበል
ስላልሆነለት እና እየሰማችዉ ስላልሆነ በብስጭት
ስራዉም እንዳይረፍድበት እየተናደደ
የመኪናዉን መሪ ይዘዉራል።
ፍፁም በርቀት የትምህርት ቤቱን ግቢ እያየ
ቤዛዊት ናፍቃዉ በምን ቃል እዉነቱን እንደሚያስረዳት
እያሰበ ይራመዳል
በድንገት ባየዉ ነገር ደነገጠ ቤዛዊት ከጠላቱ ከከዳዉ
ወዳጁ ከሆነዉ ፍቃዱ ጋር ቆማ እያወራች ነዉ።
የልብ ምቱ ይሰማዋል
"ምን እየተፈጠረ ነዉ?"
አይምሮዉ ይጠይቃል በርቀት ያየዉን አላምን ስላለ
የለበሰዉ ሰፊ ቱታ ገላዉ ላይ በንፋስ እየተዉለበለበ
የተጫማዉን ነጠላ ጫማ ማንሳት እያቃተዉ
አስፓልቱን ማቋረጥ ጀመረ።
እየበረረ የሚመጣዉ በጭቅጭቅ የታጀበዉ
የባል እና ሚስት መኪና ከመኪናዉ የሞተር ጩህት
በላይ የእነሱ ቅጥ ያጣ ጩሀት እየተሰማ
ፍፁም በሚሻገርበት መንገድ እየከነፈ ነዉ።
የፍፁምን በሀሳብ በፍቅር በተንኮል
የሰከረ ደመ ነብስ ሊቀጥፍ
ጎማዉ መሽከርከሩን ቀጥሏዋል።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
Forwarded from አትሮኖስ via @like
#የማሪያም #ንግስ #ዕለት
.
.
.
የማርያም ንግስለት
አዳፋ ነጠላ
በቀጠነ ገላ ÷ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ
ጥቁር ያዘን ቀሚስ ÷ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች ,,,,,,
ከቤተስኪያን አጸድ —ቆማ ከዋርካውስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት —,,,,,ትለማመንነበር
አደራሽ ን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶ ቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀረረባዬ በርዶታል ።
ወድቃ የተነሳች
እንባ ያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለምናት ነበር
ከቤተስኪያን ጓሮ ቆማ ከዋርካው ስር ።
*
የደብሩ አለቃ
ካ ባ ላንቃ ለብሶ ሞጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጬ ወደፊት ተስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክብሎ ያስተምራል ።
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደሞዝ ሊጨመር ይገባል
3
ደጀ ሰላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ,,,,
እናም ,,,
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እ ጃችሁ የታለ ?
እያለ ።,,,,
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል ።
ለንግሱ የመጡ
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች
ጥለት የለበሱ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ እፊት ተመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሰላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በ ሺ ሚቆጠሩ
ብሮች ወረወሩ
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ወዛ
የሚወረው ብሩም በጣም በዛ
*
የዛች የየምስኪን ነብስ
ያቺ ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኘኝም ማድጋዬ ጓድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬን በርዶታል
አንቺው ነሽ ተስፋዬ የኔ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ የተነሳች
እንባ ያፈሰሰች ።
ግና —ግን ለዛሬ —ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጅ አማሀዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የአንገት ሃብሌን፡፡
በኤፍሬም ስዩም
👍2
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በክፍለማርያም

... መሽከርከሩን ቀጥሏል
መኪናዉን አየዘወረ የነበረዉ የተናደደዉ ባል ወደ ሚስቱ ዞሮ
"ተይኝ.."
ብሎ ለአፍታ አንገቱን ወደ ፊት ለፊት ሲመልስ
መንገዱ ዉስጥ በቅርብ እርቀት
ሰዉ እየገባበት መሆኑን አስተዋለ
የመኪናዉን ማቆሚያ በድንጋጤ በሙሉ ሀይሉ እረገጠዉ መኪናዉ ለመቆም ሲታገል
ጎማወቹ ከአስፓልቱ ጋር ጥል ፈጥረዉ
የሚሰቀጥጥ ድምፅ አሰሙ።

"ሲ ጢ ጢጢ ጢጢጢ ጥ''

ፍፁም በደመ ነብስ እነ ቤዛዊትን እያየ
እየተራመደ ያልጠበቀዉ መኪና አጠገቡ ደርሶ የመኪናዉ የፊት አካል ሁለቱንም እግሮቹን
በሀይል መታቸዉ የእሱንም ሙሉ አካል በግፊት ተጎትቶት
ከሹፌሩ ትይዩ ካለዉ መስታወት ጋር ሲላተም ከግንባሩ የሚፈሰዉ ደም የተሰነጣጠቀዉ የመስታወት ቅርፅ
ይዘዉ መዉረድ ጀመሩ።

መኪናዉ ሙሉ ለሙሉ ሲቆም የፍፁም አካል ከመኪናዉ ኮፈን ተንሸራቶ መሬቱ ላይ ተዘረረ።
ፍፁም አሁን ደመነብሱም አይሰማዉም
ጆሮዉ ግንድ ላይ ሲሰማዉ የነበረዉ
"ጭ ዉዉዉዉዉዉ"
የሚል የሚመስል ድምፅ በሂደት ጥፍት አለ የሚያየዉም የሚሰማዉም ነገር በቀስታ ቆመ።
ቤዛዊት የመኪናዉን የግጭት ድምፅ ስትሰማ
አይኗን በእጇ ሸፍና ጥቂት ከቆየች በኃላ ላለማየት ፍቃዱን ጥላዉ ወደ ትምህርት ቤቱ መግቢያ በር አመራች
ብዛት ያላቸዉ ተማሪወች ግን ወሬዉን ለማየት ወደ መኪናዉ እየሮጡ ሄደዉ ከበቡት
"ፍፁም ነዉ
መምህር ፍፁም
ወይኔ ቲቸር"
ተማሪወቹ የተገጨዉን ሰዉ አይተዉ
ሀዘን የማይችሉት ሴት እና ወንዶች እያለቀሱ
ሌሎቹ በግርምት እና በድንጋጤ ሆነዉ ሁኔታዉን ያስተዉላሉ።
የገጪዉ ሚስት የቅድሙ ምላሷ አሁን ተጣጥፎ
የዋጠችዉ ይመስል የለም በፊት ሲከፈቱ የነበሩት አፎቿ
አሁን ተዘግተዉ በድንጋጤ ደርቀዉ አመድ መስለዋል
የእራሷ ጥፋት መሆኑ አሁን ገብቷት የባሏን ፊት ላለማየት በሀዘን ፈዛ ቀርታለች።

ባሏ መሪ ጨብጠዉ የነበሩት እጆቹ
የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዉ ይንቀጠቀጣሉ
ፖሊሶች ደርሰዉ የተሰበሰዉን ሰዉ እየበተኑ
ሹፊሩ ወደ ተዘረረዉ ፍፁም በቀስታ ተጠግቶ ቀኝ እጁን ወደ ገጨዉ ሰዉ አንገት ሰደደ
መሞት አለመሞቱን ለማረጋገጥ
ነገር ግን ምንም ነገር መስማት አልቻለም
"ተይኝ"
ያላት ቃል ብቻ ነዉ አይምሮዉ ላይ የሚያቃጭለዉ
በቆመበት ዝርግፍ ብሎ ተንበረከከ
ፊቱ ዶግ አመድ ሆኖዋል የሚፈስ እንባም የለዉም
ነገር ግን ዉስጡ እየደማ ነዉ።
ቤዛዊት የተማሪዎቹን ወሬ በርቀት እንደሰማች
ፍፁም የሚለዉን ባለማመን ደግማ ለማረጋገጥ ተጠግታቸዉ ሰማች
"መምህር ፍፁም መኪና ገጭቶት ሳይሞት አይቀርም..."
አንድ ቀጫጫ ተማሪ ያወራል
ዉስን ተማሪወች እየሰሙት ነዉ ቤዛዊት ወደ ግቢዉ በር
እራሷን እየወቀሰች ልትወጣ ስትል
"ቁሚ መዉጣት አይቻልም"
የግቢዉ ጥበቃ ጮሀባት
አንገቷን አዙራ የደፈረሰ አይኗን አጉረጠረጠችበት
"አንቺ ነሽ እንዴ አትቆዪ እሺ"
ፈገግ እያለ ፈቀደላት በልቡ ካበደ ጋር ምን አሳበደኝ እያለ
ስለቤዛዊት የሚወራዉን ስለሰማ ፈርቷት።
አንቡላንስ ቆሞ የፍፁም የተዝለፈለፈ አካል ሊጫነ ሲል
ደረሰች ከበዉ የቆሙትን ሰወች ገፈታትራ እንዳታልፍ
ያስቆማትን ፖሊስ በጉልበት አምልጣ
የፍፁምን ፊት ለማየት ቻለች ከግንባሩ የፈሰሰዉ ደም
ፊቱ ላይ ደርቆ የምታየዉ ፍፁም ስላልመሰላት
ለመንካት እጇቿን ስትዘረጋ
ከአንቡላንሱ ጋር የመጡት ሰወች ፍፁምን በተንቀሳቃሽ
አልጋ ላይ ጭነዉ ወደ አንቡላንሱ ዉስጥ እየተቻኮሉ
በፍጥነት ከተዉት እነሱም ዉስጥ ገብተዉ
በሩን ቤዛዊት ፊት ላይ ዘግተዉት ወደ ሆስፒታል ከነፉ።

ቤዛዊት በፍጥነት የተፈተለከዉን አንቡላንስ ተከትላ
ወደፊት ተንደረደረች ፍፁም ልበሺ ያላት ረጅም ቀሚስ
አላስሮጥ ስላላት ለአፍታ ተናዳ ቆመች
ትክክል እያሰበች አደለም የፍፁም እንደዚህ መሆን ህመሟን አስነስቶታል
ከጀርባ ያለዉን የቀሚሷን ዚፕ በሀይል ገነጠችዉ
ረጅም ቀሚሷ መሬት ላይ ሙሉ ለሙሉ ከላይዋ ላይ ወልቆ
መሬቱ ላይ አረፈ።
በለበሰችዉ የዉስጥ ሱሪ ፍፁምን ይዞ የጠፋዉን መኪና
መከተል እያሰበች መሀል አስፓልቱን ይዛ መሮጥ ጀመረች
በአፍዋ የማይሰሙ
"ፍፁም ፍፁም"
የሚል እረጅም መነባንብ እያነበበች
ብዙ መንገድ ከሮጠች በኃላ ያልተከተለችዉ
የአንቡላንሱ አቅጣጫ ጠፋባት
የመኪኖች የጥሩንባ ድምፅ አቀወሳት
የሁሉም አላፊ አግዳሚ አይን ገላዋ ላይ ይነወልላል
በትዝብት ያወራል
"አበደች ስታሳዝን"
አዛኝ የመሰለ አሳባጅ ሰዉ ያወራል
ቤዛዊት የፍፁም ደም እረፍት ነሳት
ሁለቱን እጆቿን ጇሮወቿ ላይ ጭናቸዉ
በነፃነት መሀል መጮህ ጀመረች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ስቅለት

ቢያቅትሽ መውጣቱ
ቢከብድሽ ማውረዱ
ሔደሻል ትተሽኝ፤
ከተራራው ጫፍ ላይ
ከፍ አርገሽ ሰቅለሽኝ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
👍2
#ፊርማው

የእኛ የሰው ልጆች
ክፋታችን ከፍቶ ኃጢአታችን ልቆ
መጠን አልፎ ገዝፎ ሲታይ ገ'ኖ ደምቆ
እርሱን አስደንቆ
ልቡን በሐሴት ሞልቶ የእውነት ሳቅ ስቆ
ፍቅሩን ሊገልፅልን ከጥላቻ ርቆ
ራሱን ዝቅ አርጉ ከመንገድ ጠብቆ
ወረቀት አውጥቶ ክብር ሳያሳጣን፤
አድናቂያችን ሆኖ አስፈረመን ሠይጣን፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
28/09/06
#የይቅርታ_ልክ

#አንቺ
በፍቅር ገለሽኝ ገንዘሽ ቀብረሽኝ
አፈር አልብሰሽኝ ሔደሻል ትተሽኝ።
ነፍሴ ፤
በፈጣሪዋ ዘንድ
አትሙት ያላላት የተሰጣት ክብር
ዳግም ነፍስ ዘርታ
ሞትሽን ድል ነሳች ወጣች ከመቃብር፡፡
#እኔ
ከጥልቁ ጉድጓድ በነፃነት ወጣህ-
ያለሽበት ድረስ ልፈልግሽ መጣሁ፡፡
እኔ እንደአንቺ አይደለህ
ስለፍቅር ብዬ ይቅር ብዬሻለሁ፡፡
ልቤንም አፅድቼ
እጆቼን ዘርግቼ
እንደድሮ ላቅፍሽ መንገድ ጀምሬያለሁ፡፡
አደራ ፍቅርዬ
ደመ ነብስሽ ነግሮሽ
ድንገት ቀና ብለሽ ስትመለከቺ
ከርቀት ብታዪኝ ስመጣ ወደ አንቺ ፤
ሙት መንፈስ መስዬሽ እንዳ ደነግጪ
ይኸውልሽ ካላመንሽ ቆይ እጅሽን አምጪ
ደረቴ ሥር አርገሽ
የልብ አመታቴን ከልብሽ አድምጪ
መላው አካላቴን
ዳብሰሽ በጣቶችሽ ዳሰሽ አረጋግጪ፡፡
እኔው እራሴ ነኝ!
ያጠፋሁት ካለ
ለሠራሁት ስህተት ፍቅሬ ይቅር በይኝ
ይቅርታ ቢስ ከሆንሽ
በይ እንደለመድሽው ካሰኘሽ ግደዪኝ፡፡
እሞትልሻለሁ!
እንዳንቺ አይደለሁም በፈጣሪ አምናለሁ።
ሞትሽን ድል ነስቼ ዳግም እነሳለሁ።
ሺ ጊዜ ብትገዪኝ
እልፍ አዕላፍ ጊዜ ይቅር እልሻለሁ ፤
ምክንያቱም ፍቅሬ
በንፁህ ልቦና እኔ አፈቅርሻለሁ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በክፍለማርያም

...መጮህ ጀመረች
ቤዛዊት ከስር እርቃኗን ከላይ በለበሰችዉ ሹራብ ቆማ
እግሯን ንፋስ እያገኘዉ የላይኛዉ አካሏ ወበቅ ስለለቀቀባት
ሹራቧንም አሽቀንጥራ ወረወረችዉ
በጡት ማስያዣ እና በዉስጥ ሱሪዋ ብቻ ቀርታ።

አሁን ስለሚያዩዋት አይኖች አትጨነቅም
የሚጮሁት የመኪና ጡሩንባወችም ለጇሮዋ ትርጉም የላቸዉም
ያለችበት አይታወቃትም ሀሳቧ ወሰድ መለስ ይላል ለአፍታ በደም የተጨማለቀዉ ፍፁም ወድያዉ
የገጪዉ ሹፌር ፊት ይመላለሱባታል ነገር ግን ዉሳኔዋ እራሱ ለራሷ አይገባትም

"ሞተ !?"

ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ለራሷ ጠየቀች
ወደ ሰማይ አንገቷን ቀና አድርጋ እያየች አይኖቿ እንባ እያቀረሩ
"እኔን ጥሎ!!አረ የትም አባቱ ጥሎኝ አይሄድም የኔ ፍቅር"
ወደ ከበቧት መኪኖች እያየች ጥሎኝ አይሄድም ብላ ስታስብ
የፍፁም ፊት ለአፍታ በሀሳቧ ታያት እና
ክትክት ብላ መሳቅ ጀመረች
" ኪ ኪኪ ኪኪኪ ኪኪኪ ኪኪ ኪኪ ኪኪኪኪኪ ኪ"
ወድያዉ ሳቋን አቋርጣ ፈጠን ፈጠን እያለች ከመሀል መንገዱ ወጥታ ወደ ዳር ወጣች ጥግ ጥጉን
በአይኗ ማሰስ ጀመረች ምን እንደምትፈልግ ባታዉቅም።
ከመንገዱ ጠርዝ ከወደቁ ወረቀቶች ልጣጮች መሀል
ክብ የሚመስል ድንጋይ ላይ አረፈ
ሰዉ እንዳያያት ይመስል ዙርያዋን ገልመጥ እያረገች
ድንጋዩን በቀኝ እጇ አነሳችዉ
ልክ ድንጋዩ እንደያዘች የልብ ልብ ተሰማት
ፍፁምን የገጨዉ ሹፌር ትዝ ስላላት ወደ ተገጨበት ቦታ
ድንጋዩን ደረቷ ላይ አስደግፋ ይዛዉ
ብቻዋን የማይሰሙ የማይገቡ ቃላቶችን እያወራች መራመድ ቀጠለች።

ከሰአታት በኃላ ፍፁም አይኑን እንደገለጠ እራሱን ብዙ አልጋ ላይ ከተኙ ሰወች
ጋር እሱም ለብቻዉ አልጋ ላይ ተኝቶ ነበር ።
ግንባሩን ስላሳከከዉ ለማከክ እጁን ሲሰድ
የተለጠፈለትን የቁስል ፕላስተር ነካ ሊፈነዳ የሚደርስ የእራስ ምታት እና የሰዉነቱ አቅም ሁሉ ሙጥጥ ብሎ
ያለቀ የሚመስል ድካም እየተጫጫነዉ ።
ሀይለኛ ዉሀ ጥም ስለተሰማዉ ጉሮሮዉን ለማራስ ምራቁን ለመዋጥ ታገለ ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም
የቻለዉ ከወገቡ በእጁ ድጋፍ እንደምንም ታግሎ
አልጋዉ ላይ ባለበት መቀመጥ እንጂ
እግሩን ማንቀሳቀስ አልቻለም
እግሩን ለማየት ሞከረ ቀኝ እግሩ በነጭ ፋሻ ተጠቅልሏል

"ዉሀ ዉሀ ዉሀ"

የሚያስበዉ እሱን ብቻ ነዉ አቅራቢያዉ የተኙ የታመሙ ሰወች ይታዩታል በርቀት የሚያስታምሙ ሰወችን
አይቶ በደከመ ድምፅ ቢጣራም የሚሰማዉ እና ልብ ብሎ የሚያየዉ ስላጣ ተደላድሎ ተቀምጦ
እንዴት ለዚህ ደረጃ ሊደርስ እንደቻለ ማሰብ ጀመረ ።

ከልቡ ያልጠፋችዉ ቤዛዊትም ትዝ እያለችዉ ማስታወስ የቻለዉ መንገድ ሊያቆርጥ ሲል
መኪናዉ ሲመታዉ ብቻ ነዉ ።
"መሞት ለካ ሁሉን መርሳት ነዉ !" አለ በልቡ ከህመሙ በላይ ቤዛዊትን የተፈጠረዉ ሁሉ
ዉሸት መሆኑን አስረድቷት
አምናዉ ሲታረቁ እያሰበ ደስ እያለዉ።

የሆስፒታሉን ጣርያ በአይኑ እያየ በልቡ ግን ወደ ሰማይ እያየ
በመትረፉ
"ተመስጌን አምላኬ"
ሲል አመሰገነ።
ቤዛዊት መራመዷን ቀጥላለች ያሰበችዉን ቦታ ፍፁም የተገጨበትን የትምህርት ቤቷን አካባቢ
ብታልፈዉም ግን መጓዟን አላቆመችም
ስለ ፍፁም መሞት በራሷ ሀሳብ ደምድማ
ሲላትም በህይወት አለ እያለች
ከአይምሮዋ ጋር ሙግት ገጥማ እራሷ ጠይቃ እራሷ እየመለሰች የማያልቀዉን መንገድ ሲላት አዉራ መንገዱን ሲያሻት ተሻግራ ዉስጥ ለዉስጥ
መንገዷች ዉስጥ የምትፈልገዉን ባታዉቅም በአይኗ የሆነ ነገር እየፈለገች በእግሯ መጓዝ ቀጠለች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ከሞት_በኋላ_ሕይወት

ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ያወቀ
ፈጣሪው ብቻ ነው ከፍጡራን የላቀ፡፡
ስው የማይደርስበት መንገዱም የራቀ
ፅንፍየለሽ ነው ጉዞው ምስጢሩ የረቀቀ፡፡
“ከሞት በኋላ ሕይወት
በዕውን አለ ወይ?” ብሎ የጠየቀ
ከጥልቁ ሕዋው ሥር
ምላሹን ለመስጠት ደፍሮ የጠለቀ ፤
እስከዛሬ ድረስ
ሲገባ ነው እንጂ አይታይ ሲወጣ፣
ምስጢሩን ለመግለፅ
አንድም ፍጡር የለም ተመልሶ የመጣ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#አንድ_ጣት

ሰው ትንሽ ነው” ተብሎ
እንደምን ይናቃል
ለማብራት ለማጥፋት
አንድ ጣቱ ይበቃል።
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በክፍለማርያም

በእግሯ መጓዝ ቀጠለች
በርቀት የትምህርት ቤት መግቢያ በር አናት ላይ ግማሽ ጨረቃ የሚመስል የትምህርት ቤቱ ስም የተፃፈበት
ታፔላ ስታይ ተስባ ቆመች።

ለማንበብ እየሞከረች አንገቷን ቀና አድርጋ ብዙ ቆየች ቃላቶች ስትዘል ስትሳሳት ለማስተካከል ተመልሳ ስትደግም
ሰዓታት ገደለች ጊዜዉ ወደ መምሸት እየተጠጋ ነዉ
ከቆመችበት ቦታ ሳትነቃነቅ ዙርያዋን ተመለከተች ።

ጉሊት የሚቸረችሩ ሴቶች ብቻ በመሀል አንድ ጠይም ወንድ ሳያያት በሀሳብ እየተራመደ አጠገቧ ሲደርስ
አይቷት እርቃኗን መሆኗን ሲያስተዉል ደንግጦ መስመር ቀይሮ ሲራመድ ማንበቧን ትታ ልጁን መከተል ጀመረች
"ፍፁም አ.ን.ተ ፍፁም ጠ.ብ.ቀኝ እንጂ !!"
ከጀርባዉ እየተከተለችዉን ያለችዉን ሴት ዞሮ አየት አርጓት በልቡ
"ከየት የመጣች እብድ ናት"
እያለ በኃላዉ ለሚመጣዉ አደጋ ለማምለጥ አይኑን እያጉረጠረጠ ፍጥነቱን ጨምሮ ከአይኗ ተሰወረ።

ብርድ ብርድ አላት የሰዉነቷ ቆዳወችዋ ተቆጥተዉ ሽፍታ መስለዉ ይታያሉ ሙቀት ፍለጋ እጇቿን አጣምራ
ጥጉዋን ይዛ ተቀመጠች
ብርሀን ቀስ በቀስ ለጨለማ ጊዜዉን እየለቀቀ ነዉ
ቤዛዊት ስሟን እራሱ የምታስታዉስ አትመስልም የመንገድ ጠርዝ ላይ ተቀምጣ የምታያቸዉ አላፊ አግዳሚ
ሰወች መሀል አንዳንድ ወንዶችን ስታይ ፍፁምን እየመሰሏት

"ፍፁም ..ፍፁም..."

እያለች ስትከተላቸዉ
እየፈሯት እርቀዋት ሲሄዱ ተመልሳ ቦታዋ ስትቀመጥ ቆየች።አንድ እጆቹን እያወናጨፈ የሚመጣ ወጣት ስታይ
በንዴት ጦፋ ተነስታ ቆመች
ልጁን ለማየት አንገቷን ቀና አድርጋ ልጁ እንዳያመልጣት እያየች መሬት ላይ ያስቀመጠችዉን ድንጋይ ለማንሳት
መሬቱን በዳበሳ ስታስስ ልጁ አልፏት ሊሄድ ስለሆነ
እጇ በዳበሳ ያገኘዉን እየበቀለ ያለ ሳር
ከመሬቱ በጉልበት ነጭታዉ እየሮጠች ወደ ልጁ ተጠጋች
"አንተ ነብሰ በላ ገደልከዉ አደል"

"ምን አ አ"

ልጁ ደንግጦ የሚለዉ ጠፍቶት ተንተባተበ
እንዳትፈነክተዉ አንገቱን ለመደበቅ ጭንቅላቱን ለመከላከል
በእጁ እየተከለለ አጮልቆ አያት እርቃኗን መሆኗ አስፈራዉ
"ፍፁምን ገጨህዉ እኔንም ግጨኝ"
የያዘችዉን ሳር በተነችበት
ድንጋይ የወረወረችበት መስሎት ፈረጠጠ።
ለመከተል አልሞከረችም ሳሩ ሲበተን ይሆን ልጁ ሲሮጥ ባላወቀችዉ ምክንያት መሳቅ ጀመረች።

"ኪኪ ኪ ኪ "
እማማ ስንቅነሽ ከጉሊት ለእራት መስርያ የሚሆን ሽንኩርት
ሊገዙ ሲወጡ እርቃኗን የትምህርት ቤት በር ጋር የቆመች ሴት አይተዉ
"በትምህርት አስደግመዉባት ነዉ"
እያሉ ለራሳቸዉ እያወሩ አዝነዉላት አልፈዋት ሄዱ
ጉዳያቸዉን ጨርሰዉ ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ
"ፍፁምን ገጨሀዉ እኔንም ግጨኝ"
ያለችዉን ሲሰሙ ሀዘን መላ ሰዉነታቸዉን ወረራቸዉ
ልብ ብለዉ አዮዋት እርቃኗን የሆነች
የምትናገረዉ የምታረገዉ ነገር ለሰዉ ስለማይገባ
እብድ ተባለች እንጂ ስትታይ
"አረ እብድም አትመስል"
አሉ የሰዉነቷን ሁኔታ እያዩ
"ልጄ"
እያሉ ተጠጉዋት
በአይኗ በደንብ አየቻቸዉ ፈርታቸዉ ይመስል
ሁለቱንም አይኖቿን አጠናግራ
እማማ ስንቅነሽ ነጠላቸዉን አዉልቀዉ ጠጋ ብለዉ
ሲያቀብሏት ፍርሀቷ በፈገግታ ተለወጠ
"ስትስቂ ደሞ እንዴት ቆንጆ ነሽ"
አሏት እማማ ስንቅነሽ ስትለብሰዉ ያሳየቻቸዉን
ያልጠበቁትን የደስታፊት አይተዉ
"አትጓዳኝም አይነዉሀዋ ያስታዉቃል"
አሉና እራት እንድትበላ በማሰብ
"ነይ"
ብለዉ እጇን እነደመያዝ ሲያረጉ እጃቸዉን ሳም አረገቻቸዉ
ቢያንስ ብርድዋን አቃለዉላታል
አሁንም የት እንደሚወስዷት ባታዉቅም
ሌላ ችግሯን ካቃለሉላት ብላ ይሁን
መልካቸዉ ወዳዉ ተከተለቻቸዉ።
ምግብ ሰጥተዋት በልታ ጨርሳ
"ዉጪ"
ማለት አስበዉ ግን አሁን ፅድቅ ሰርተዉ የሚኮነኑ ስለመሰላቸዉ "የዛሬን ትደር መሽቷል"አሉ ቀልባቸዉ አዝኖላት
ለሊት ሰካራሙ የእማማ ልጅ በመጠጥ ደንዝዞ እየተንገዳገደ በእንጨት የተሸነቆረዉን በር ታግሎ ከፍቶ
ሲገባ የደፈረሱ አይኖቹ ቤዛዊት ላይ ቀሩ

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#እግዜር_እንደ_ሠይጣን

አምነን የተከዳን
አምነን የተጐዳን
አጠፋፋቶ ያስቀረን
በከንቱ ያተጣጣን
ክብርንም ያሳጣን፤
ማሰብ ጀምሮ ይሆን?
እግዜር እንደ ሠይጣን፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
1👍1
#ላይ_እና_ታች

እስቲ ልዘቅዘቀው ልውረድ ተደረጃ
ፍቅር ውሉን ስቶ ተሆነ ጠብ መንጃ
ተቁዋቁሜው ልለፍ የፈጣሪን ፍርጃ::
ዝንታለም አምኜ በሰላም በፍቅር
እታች ሆኜ ልነር ተዘቅዝቄ ልቅር::
ተዕለታት አንድ ቀን ሲጠራ መንገዴ
ያበቃ ይሆናል እታች መውረዴ
ሸክሜን ላክብደው
ወደታች ልውረደው መውረጃዬ ሲቀል
ያኔ አይቸግረኝም
ከፍ ከፍ ለማለት እላይ ለመሰቀል።

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ


#በክፍለማርያም

አንይኖቹ ቤዛዊት ላይ ቀሩ
እማማ ስንቅነሽ ሰፋ ያለ የአበባ ቅርፅ ያለዉ የጨርቅ ልብስ ሰጥተዋት እሱን ለብሳ ከላይ ብርድ ልብስ
ጨምረዉላት እራት ቢጤ ከቀማመሰች በኋላ መሬት ላይ ተነጥፎላት ቤዛዊት አሸልባለች።

እማማ ስንቅነሽም እንቅልፍ አልወስድ ብሏቸዉ በጥሩ ጎኑ የቤዛዊት ነገር ሲያሳስባቸዉ ምን ሊረዷት
እንደሚችሉ እየተብሰለሰሉ ሲያስቡ
በመጥፎ ጎኑ የማላዉቃትን ሴት ቤቴ አስገብቼ አንድ ነገር ብታረገኝስ እስዋስ አንድ ነገር ሆና
እዳ ዉስጥ ብትከተኝስ እያሉ ሲብሰለሰሉ
ባረጀዉ ጋቢያቸዉ አይናቸዉን ብቻ እርቃን አስቀርተዉ ቤዛዊትን እያዩ እሳቸዉንም የማይቀረዉ እንቅልፍ
በሀሳብ አስመስሎ አሸነፋቸዉ።

ቤዛዊት በጆሮዋ ሹክሹክታ መሰል ድምፅ ስትሰማ ከተኛችበት አይኗን ገለጠች
ያለችበትን ማወቅ ተስኗታል ጤንነቷ ግን የተመለሰ ይመስላል እራሷን በማወቅ ላይ ነች ወሰድ መለስ ነዉ የህመሟ ባህሪ አሁን የፍፁም
መገጨት ሁኔታዉን ሁሉ ለዋዉጦት ለዚህ አበቃት እንጂ...

"የት ነኝ?"

ፍርሀት እና ጥርጣሬ ያዘለ ቀጭን ድምጿን ለቀቀችዉ

"አንቺ ...ማን ነሽ?"

አላት የእማማ ስንቅነሽ ልጅ በሰከረ አንደበት እየተኮለታተፈ ደንገዝ ገዝ ባለዉ የቤቱ ጨለማ ዉስጥ ጃኬት ለብሶ
የቆመ የሚመስል ሰዉ ታያት ደንግጣ እጆቿን በፍጥነት
ከብርድ ልብሱ አዉጥታ ከጀርባዋ ያለዉን ግድድዳ
በእጆቿ ማሸት ጀመረች ቤቷ ይመስል ማብርያ ማጥፍያ ፍለጋ።

ሰካራሙ ልጅም ግርግዳዉን እየፎከተች መሆኑን በአትኩሮት
አይኖቹን ባለማመን አፍጥጦ ካያት በኋላ ሲያረጋግጥ
እንደመፍራት እያለ ወደ ኋላ ሲራመድ ሳያስበዉ ጥግ ይዞ የተቀመጠን ባዶ ድስት በእግሩ ስለነካዉ የድስቱ ክዳን
ድምፅ እየፈጠረ መንከባለል ጀመረ።

"ኪልልልል ኪል ኪል ኳ"

እማማ ስንቅነሽ መብራቱን ሲያበሩት ቤዛዊት እና ልጃቸዉ
ተፋጠዉ ቆመዋል

"የት ነኝ..ማን ነህ..እነ ማን ናችሁ?"

ቤዛዊት ደጋግማ ትጠይቃለች ያለችበት ግራ ገብቷት ሁለቱንም
እያፈራረቀች እያየች
"ምኗን ደሞ ይዘሽ መጣሽ"
እናቱን በአሽሙር እየተናገረ መደ መኝታ ክፍሉ እየተንገዳገደ ሄደ
"የት ነኝ ....."ቤዛዊት ያወራችዉን ደጋግሞ እያወራ እያሾፈባት
እማማ ስንቅነሽ ከአልጋቸዉ ተነስተዉ አማተቡ
ጨንቋቸዋል ምን ብለዉ ያስረዷት ነግቶ ከቤታቸዉ
በሰላም እንድትወጣ በልባቸዉ መለመን ጀመሩ።

ቤዛዊት ሁለት ክፍል ያለዉ ደሳሳ ቤት ዉስጥ እንዴት
ልትገባ እንደቻለች ስታስብ ገርሟታል ሌላ አለም ላይ ያለች
ይመስል እማማን ሌላ ፍጥረት ከሆኑ በሚል አስተያየት
እያየቻቸዉ ማሰብ ጀመረች።

ምንም የምታስታዉሰዉ ነገር የለም
አይምሮዋን አስጨነቀችዉ ማስታወስ የቻለችዉ
በመኪና ፍፁም ተገጭቶ አንፑላንስ ዉስጥ እሱ ሲገባ
ብቻ በአይምሮዋ ተቀርጿል ሌላዉን ሁሉ አታስታዉስም

"እማማ ልሂድ"

አስፈቀደቻቸዉ
"ለሊት እኮ ነዉ ልጄ ሲነጋ ትሄጃለች"
ሀዘን ባዘለ ድምፅ በጭላንጭል የሚገባዉ ብርሀን የጨረቃ
መሆኑን እየነጠሯት
እሺ ለማለት ጭንቅላትዋን ከታች ወደ ላይ ነቀነቀች
የለበሰችዉ ልብሰ የእሷ አለመሆኑን ስታስታዉስ ፊት ለፊቷ
ያሉት ሴትዮ እንዳለበሷት ገምታ እንደማፈር አለች
ቀኑን ሙሉ እርቃኗን ስትዞር መዋሏን ዘንግታዉ
እግሯ አካባቢ የድካም እና የህመም ስሜት ይሰማታል ቀኑን
ሙሉ ስትባክን የዋለችበት
ምን እንደተፈጠረ እየተሽኮረመመች እማማን ጠየቀቻቸዉ
እንደ ልጃቸዉ ቀርበዉ የሆነዉን ሁሉ እማማ ስንቅነሽ ነገሯት።

የቤዛዊት ቤተሰቦች ልጃቸዉ ከትምህርት ቤት ሳትመለስ ስታመሽ ተጨንቀዉ አባቷ ወደ ፍቃዱ ደወሉ
ፍቃዱ ትምህርት ቤት ዉስጥ ቀኑን ሙሉ እንዳላያት
ነገራቸዉ እና ስልኩ ሊዘጋ ሲል የፍፁምን በመኪና መገጨት
በማስመሰል ከንፈሩን እየመጠጠ ስለነገራቸዉ እሱ ጋር ሄዳ ይሆናል ብለዉ ተናደዉ ስልኩን ዘጉት።

ፍፁም የተኛበትን ሆስፒታል በመከራ አጊንተዉ የቤዛዊት አባት
ከብዷቸዉ ሚስታቸዉን እና ታላቅዋን ልጃቸዉን ሄደዉ
እንዲያመጧት አዘዙዋቸዉ።
የተባለዉ ሆስፒታል ደርሰዉ ወደ ዉስጥ ሲገቡ ከንፈሩ ደራርቆ
አስታዋሽ ያጣዉ ፍፁም ከህመሙ ጋር እየታገለ ነበር።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍21
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ #በክፍለማርያም አንይኖቹ ቤዛዊት ላይ ቀሩ እማማ ስንቅነሽ ሰፋ ያለ የአበባ ቅርፅ ያለዉ የጨርቅ ልብስ ሰጥተዋት እሱን ለብሳ ከላይ ብርድ ልብስ ጨምረዉላት እራት ቢጤ ከቀማመሰች በኋላ መሬት ላይ ተነጥፎላት ቤዛዊት አሸልባለች። እማማ ስንቅነሽም እንቅልፍ አልወስድ ብሏቸዉ በጥሩ ጎኑ የቤዛዊት ነገር ሲያሳስባቸዉ ምን ሊረዷት እንደሚችሉ እየተብሰለሰሉ ሲያስቡ…»
#እኛ

ሥጋና ነፍስ ያደለን
ሰምና ወርቅ ያለን
በቃል ሕብር የተፃፍን
በሆሄያት የገዘፍን
የእግዜር ቅኔዎች ነን
እኛ የተዘረፍን፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ነገረ ሕልም

በምቹ አልጋ ላይ ጐኑን አሳርፎ
በእንቅልፍ ልቡ የታየው ችግር ሁሉ አልፎ
ሲነቃ “ሕልም አለኝ አለ ያ ወገኛ፤
በደንብ ተመችቶት እንቅልፉን የተኛ፡፡
የረባ መኝታ ምቹ አልጋ ያላደለኝ
በችግሬ ብዛት እንቅልፍ እንኳ የሌለኝ
እንደምን እላለሁ?! ሳልተኛ “ሕልም አለኝ”

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#እጠብቅሻለሁ!

ከባባድ ጉዳዬን አቅልዬ ጣጥዬ
ያንቺን አስበልጬ ትመጪያለሽ ብዬ
ያንቺን አስቀድሜ
ከቀጠርሽኝ ሥፍራ
መጣሁኝ ቀድሜ
በሥፍራው የለሽም
ጭራሽ አልመጣም።
አሥሬ እያየሁኝ ሰዓት ደጋግሜ
አንቺን በመጠበቅ
በዕድሜዬ ላይ ጨመርኩ የሰዓታት እድሜ
እጠብቅሻለሁ
ካሻው ይህ ቅጽበት
የሕይውቴ ፍፃሜ
ይሁን ዘላለሜ
በአትቀሪም ተስፋ
ራሴን ስቅቅል በናፍቆት ስበስል
ትመጪያለሽ ብዬ አገኝሻለሁ ስል
ገዢ ሐሳቤ ሆነሽ አንቺን ሳብሰለስል
ጭራሽ ላትመጣ ልትቀር ነውወይ ስል
ክፉ ክፉ ሳስብ በቅናት ስከስል
መጥፎ መጥፎ ሳሳብ በአዕምሮዬ ስስል
“በሐሳብ እያነሱ
ዕድሜ ከመጨመር በጭንቅ በትካዜ
ዕድሜ መቀነሱ ይሻላል ሺ ጊዜ
በማለት ወስኜ
ደግሞም ተማምኜ
እርግጠኛ ሆኜ
ዕድሜ ይቀንሳል
አንችንም ያስረሳል
ያዋጣኛልም ስል
ሲጃራ ለኩሼ
አጭሼ አጭሼ
አንዱንም ጨርሼ
አንቺን ላለማሰብ
ዳግመኛ መልሼ
ያረሳሳኛል ስል
ደገምኩኝ ሲጃራ
አጭሼ አጭሼ
ዳግም ተመልሼ
ለኩሼ ጨርሼ
እረሳሻለሁ ስል
በሲጃራው ጭስ ውስጥ
ካንቺ ወዲያ ሃሳብ
የሌለኝ ይመስል
ጭሱ ቅርጽ ሠርቶ
ቅርጽሽን አጉልቶ
ያሳየኝ ጀመረ
ፈጥሮ ያንቺን ምስል::
የተማመንኩበት
ያረሳሳኛል ስል
መልሶ አስታወሰኝ
ወዳንቺው መለሰኝ..
ሲጃራ እያጨስኩኝ
ዕድሜ እየቀነስኩኝ
እጠብቅሻለሁ እያሰላሰልኩኝ
አንቺን እያሰብኩኝ
በጭሱ ቅርጽሽን..
አንቺን እየሳልኩኝ።

🔘ፋሲል ተካልኝ 🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በክፍለማርያም

...ከህመመ ጋር እየታገለ ነበር
የቤዛዊት እናት እና እህት ወደ ፍፁም ተጠግተዉ

"ፈጣሪ ይማርህ"

ሁለቱም በአንድነት አወሩ
ፍፁም ከአልጋዉ እንደ መነሳት እየሞከረ እና እያቃተዉ የቤዛዊት እናት እና እህት ከመምጣታቸዉ በፊት ሰዓታት ቀደም
ብላ የመጣችዉ ፍፁም ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽፆ ያላት
የገጪዉ ሚስት ጠዋት ባሏን ፖሊስ ጣቢያ ጠይቃዉ ለፍፁም ለሆስፒታል የሚከፈል እና ለአንዳንድ ነገር የሚሆን
እንደ ካሳ አስባ ጠቀም ያለ ገንዘብ ይዛ ሆስፒታል ደርሳ
መክፈል የነበረበትን ክፍያ ከፋፍላ እየተመለሰች ስለነበር
ቀና እንዲል እረዳችዉ አጠገቡ ቆመች የሰማችዉ ነገር ስላለ
እያዘነች እና እንዴት መናገር እንዳለባት እየጨነቃት

"አሜን"

አለ ተደላድሎ ከተቀመጠ በኋላ
ቤዛዊት እንዴት ናት ብሎ ለመጠየቅ እና ልትጠይቀዉ ስላልመጣች የማይፀና ቅያሜ እየተሰማዉ
"ቤዛዊት እዚህ ነበረች አደል?"
እናቷ እርግጠኛ ሆነዉ ጠየቁት አዎ ነበረች የሚል መልስ እየጠበቁ
ፍፁም ምን ማለታቸዉ ነዉ ሲል አሰበ
"ከትላንት ጀምሮ ጠፍታብናለች ተስፋ ያረግነዉ አንተ ጋር ነበር
ትምህርት ቤትም አልገባችም ምን አልባት
አንተን እያስታመመችህ ከሆነ ብለን ነዉ"
የቤዛዊት እህት ቃላቶቹን ጎተት እያረገች አወራች።

ፍፁም አይኖቹን ለማሰብ አርቆ ወረወራቸዉ ልቡ የመምታት ፍጥነቱ እየጨመረ ነዉ የት ልትሄድ እንደምትችል
አሰበ ግን ቦታ አጣ የምትገኝበት ፍፁም ቤዛዊትን ከልቡ
ስለሚረዳት የእሱን መገጨት ስትሰማ ታማ ይሆን አለና ተነስቶ ለመፈለግ እግሩን ለማዉረድ ሲታገል
አጠገቡ የነበረችዉ የገጪ ሚስት
የማስመሰል ያልሆነ የእዉነትም የማይመስል ለቅሶ አለቀሰች
ታግሎ ያቃተዉ ፍፁም የሆነ ችግር እንዳለ ስለጠረጠረ
እንድትነግረዉ አንገቱን አዙሮ አፈጠጠባት

"ለጊዜዉ እግሮችህ መንቀሳቀስ አይችሉም"

የፍፁምን የታሸገ እግር እያይ ቀጠለች
"በህክምና ግን ወደፊት ይሻልሀል"
ጥርጣሬ ያለበት አወራር
ፍፁም ሳያስበዉ አይኖቹ እንባወች አቅረዉ እንዳይወርዱ
የቤዛዊት ቤተሰቦች እንዳያዩት ሲታገል ቀድመዉት ጉንጩ ላይ
የእንባ ዘለላወቹ አረፉ።

"አትዘን ደህና ትሆናለህ"

የቤዛዊት እህት በእጇ ይዛ የነበረዉን ምግብ እና ፈሳሽ ነገር
አጠገቡ ካለዉ ማስቀመጫ እያስቀመጠች እና በርታ እንዲል
የፍፁም ትከሻወች ላይ እጇቿን ጭና
"በየ ጊዜዉ እየመጣሁ እጠይቅሀለዉ
ስለ ቤዛዊትም ያለዉን ነገር አሳዉቅሀለዉ እንደሚሻልህ እርግጠኛ ነኝ"
ተስፋ ለመስጠት አስባ በእጇቿ ነካ ነካ አረገችዉ ጀርባዉን
የቤዛዊት እናትም እንዲሻለዉ እየተመኙ ነገር ግን የልጃቸዉ
መጥፋት እና እወደዋለሁ የምትለዉ ፍፁም ጋር እንኩዋን
አለመገኘትዋ እየጨነቃቸዉ ከታላቅዋ ልጃቸዉ ጋር የት መሄድ
እንዳለባቸዉ እያወሩ ፍፁምን ተሰናብተዉት ወጡ።

እማማ ስንቅነሽ ቀደም ብለዉ ተነስተዉ ትላንት እብድ ብለዉ
እየፈሩ ያስገቧት ሴት ማታ እንደጤነኛ ሰዉ ስታወራ ስለነበር
ደስ እያላቸዉ ቁርስ በልታ እንድትሄድ ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ

"ልሂድ"

ያለቻቸዉን አስታዉሰዉ ባዶ ሆዷን እንዳትሄድ ቤዛዊትን ከዚህ በፊት አያዉቋትም እስዋም አታዉቃቸዉም
ነገር ግን ከልባቸዉ እራሩላት
ነገ በኔ የሚል ሰዉ የሰዉ ህመም ይገባዋል ሰዉን ለመርዳትም
ይሞክራል እንደ እማማ ስንቅነሽ ያለ በእድሜ የበሰለ እና ፈጣሪን
የሚፈራ ደግሞ ከሚችለዉ በላይ ያረጋል።

ዉጪ እንዳለች የሚለበስ ነገር መስጠት ብቻ ሲችሉ ቤታቸዉ አሰገብተዉ አስጠለሏት ምግብም በፌስታል አርገዉ ማቀበል እየቻሉ አንድ ላይ ገበታ
አቆደሷት

"እንደምን አደሩ እማማ"

ቤዛዊት ማት በስንት ጭንቀት አስፈቅዳ የሸናችበትን ማስታጠብያ
ይዛ ሀፍረት እየያዛት ለመድፋት የተከፈተዉን በር አልፋወጣች
በትክክል ማሰብ ጀምራለች
በዛፎች የተከበበ ስፍራ አንዳንድ አነስ አነስ ያሉ የጭቃ ቤቶች
ይታያሉ እስዋ ከለመደችዉ በህንፃ ከተከበበ ሰፈር ተለየባት እንዴት እዚህ እንደመጣች ግን ማስታወስ አልቻለችም
አቅራቢያዋ ካለዉ ቦይ የያዘችዉን ደፍታ እየሮጠች ወደ እማማ
ቤት ገባች
"የት ነዉ ያለሁት ማለት የአካባቢዉ ስም"ጠየቀቻቸዉ
እማማ ስንቅነሽ የከተማ ልጅ መሆኗን በአነጋገርዋ አዉቀዋል
"የከተማ አዋሳኝ ቦታ ነዉ ያለሽዉ አሁን ቁጭ ብለሽ ቁርስ ብዪ"
አሏት እንድትታጠብ ዉሀ እያቀረቡላት በልባቸዉ የመንገዱን
እርቀት እየገመቱ መንፈስ ካላገዛት ብቻዋን በእግሯ
እዚህ ድረስ መምጣቷ እየገረማቸዉ።
እንደ ነገሩ በላ በላ ካደረገች በኋላ የፍፁምን ሁኔታ ማወቅ
ስለጓጓች ለመሄድ ተነሳች እማማ ስንቅነሽ ያለበሷትን ቀሚስ
እያየች እና ስለደግነታቸዉ እያመሰገነች ተመልሳ እንደምትመጣ
ቃል ገብታላቸዉ ስትወጣ
"አንዴ ቁሚ ልጄ"
አሉ እርጅና በተጫጫነዉ እና በደከመ ድምፅ
የሆነ የተቋጠረ ጨርቅ መፍታት ጀመሩ ዉስጡ ጥቂት ብሮች
ይታያሉ ለእራሳቸዉ ጥቂት አስቀርተዉ አብዛኛዉን የቤዛዊት እጅ
ላይ እያስቀመጡ
"በእግርሽ ይርቅሻል ባይሆን መኪና ኮረኮንቹን እደጨረሽ
ታገኚያለሽ ተሳፈሪ"
አሏት የምትሄድበትን መንገድ በእጃቸዉ እየጠቆሟት
በአይምሯቸዉ በልጅነት ወልደዋት ነገር ግን በልጅነትዋ በድንገት
የሞተችባቸዉን ሴት ልጃቸዉ ስለመጣችባቸዉ
ሀዘን መላ ሰዉነታቸዉን እየወረራቸዉ
ቤዛዊት የሰጧትን ገንዘብ ጭምድድ አድርጋ ይዛ
የእማማ ስንቅነሽ ዉለታ እና ሸክም ስለበዛባት በተለይ አሁን
ምንም ማረግ ስላልቻለች ጥምጥም ብላ አቀፈቻቸዉ።

ጥቂት አቅፋቸዉ ድጋሜ አመስግናቸዉ መራመድ ጀመረች
የፍፁም ሁኔታን ለማወቅ እየጎጎች ቀድማ የት መሄድ እንዳለባት
እያሰበች እማማ ስንቅነሽ ከአይናቸዉ እየራቀች የምትሄደዉን ልጅ እያዩ
ቅድም ያመቁትን ያጡዋትን የልጃቸዉን ሀዘን በለቅሶ ቀጠሉት
ልጃቸዉን በቤዛዊት አይን ዉስጥ ያዩ ይመስል የሆነ ነገር ሊነግሯት ያሰቡ ይመስል ሊያስቋሟት እንደመሮጥ
እየሞከሩ ወደ ፊት ለፊት ሲመለከቱ ቤዛዊት ላትታይ ጠፍታለች
በነጠላቸዉ እንባቸወን እያበሱ ሰላም እንድትሆን ለቤዛዊት
ጤናዋን እየተመኙላት ቤታቸዉ ገቡ።

ቤዛዊት ወደ ቤቷ አቅራቢያ ስትደርስ ከነ ቤዛዊት ቤት ወሬ ፈትፍቶ የሚመለሰዉ ፍቃዱ አገኛት

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1👍1
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #በክፍለማርያም ...ከህመመ ጋር እየታገለ ነበር የቤዛዊት እናት እና እህት ወደ ፍፁም ተጠግተዉ "ፈጣሪ ይማርህ" ሁለቱም በአንድነት አወሩ ፍፁም ከአልጋዉ እንደ መነሳት እየሞከረ እና እያቃተዉ የቤዛዊት እናት እና እህት ከመምጣታቸዉ በፊት ሰዓታት ቀደም ብላ የመጣችዉ ፍፁም ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽፆ ያላት የገጪዉ ሚስት ጠዋት ባሏን ፖሊስ…»
#በጥሩምባ_ድምፅ

ጡ .. ጡ... ው.. ጡ!..
ውጡ... ውጡ!.ውጡ ውጡ! ..
ዝለሉ!.. ቅበጡ ተረቱን ለውጡ፡፡
አዲስ ዘመን ባተ አሮጌው ተሽኘ
ተረት ተለወጠ ዘበትም ተሰኘ
የቀበጡ ዕለትም መሞትም ተገኘ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ፍታት

እሪ በሉ አርበኞች እሪ በይ ሀገሬ
በነጭ ያልተፈታሽ ተፈታሽ በወሬ