#እፉዬ_ገላ_እኔ
መንገዴ
እንደ አዳል ጫማ፣
አይለይ ፊትና ኋላው ፤
የገዛ ዳናው፣
መርገጫው፣
ያልገባው።
አቅጣጫዬ ....
እንደ እንጀራዬ ፣
አድርሶ መላሽ፣
ሰርቶ አፍራሽ፣
ክብ፣
እልፍ መንገድ ፣ ነጠላ ግብ፡፡
መድረሻዬ....
ከጸሎቴ፣
ከስለቴ፣
ያልጻፍኩት፧
ስሸሽ የኖርኩት።
ህይወቴ!
ህይወቴ
በእግዜር የመዳፍ ምራቅ ጥፊ፣
ወደ ምድር የተጣለ፤
እፉዬ ገላ፣
አቅመ-ቢስ ያልታደለ፡፡
🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
መጋቢት 20, 2012፣ አዲስ አበባ፡፡
መንገዴ
እንደ አዳል ጫማ፣
አይለይ ፊትና ኋላው ፤
የገዛ ዳናው፣
መርገጫው፣
ያልገባው።
አቅጣጫዬ ....
እንደ እንጀራዬ ፣
አድርሶ መላሽ፣
ሰርቶ አፍራሽ፣
ክብ፣
እልፍ መንገድ ፣ ነጠላ ግብ፡፡
መድረሻዬ....
ከጸሎቴ፣
ከስለቴ፣
ያልጻፍኩት፧
ስሸሽ የኖርኩት።
ህይወቴ!
ህይወቴ
በእግዜር የመዳፍ ምራቅ ጥፊ፣
ወደ ምድር የተጣለ፤
እፉዬ ገላ፣
አቅመ-ቢስ ያልታደለ፡፡
🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
መጋቢት 20, 2012፣ አዲስ አበባ፡፡
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
....የስራ ባልደረባዉ ፍቃዱ ነበር
የፍቃዱ ፊት እንደበፊቱ እንደሚያዉቀዉ
ለፍፁም አልሆነለትም ተቀይሮዋል እንደ አብዛኛዉ ባላንጣ ጉዋደኛ ምቀኝነትን እና ተንኮልን የሚያንፀባርቅ
አስተያየት እያየዉ
ፍቃዱ
"ሰዉየዉ እዚህ ደሞ ምን ትሰራለህ"
እያለ የፍፁምን መልስ ሳይጠብቅ ቤዛዊትን እያያት
"በርታ በይ የኔ ቆንጆ አይዞሽ"
እያላት ከአባቷ ጋር ተጠግቶ በሹክሹክታ ማዉራት ቀጠለ።
ፍፁም የቤዛዊትን የተጨነቀ ብዙ ሀሳብ የሚያስብ ገፅታዋን እያየ በሀሳብ ነጎደ
ቤዛዊት ያለባትን የአይምሮ መታወክ ችግርን
አብሯት ከጎኗ ሆኖ መታከም ያለባት ባታ ሁሉ ሳይደክም
እና ሳይሰለች ከጎኗ ሆኖ እስክትድን ሲደግፋት
ተሽሏት አብረዉ የሚመሰርቱትን ጎጆ
ምን አይነት የፍቅር ህይወት እንደሚመሩ
እንደ ቤዛዊት ቆንጆ የሆኑ መንታ ልጆች ስትወልድለት
ከልጆቻቸዉ ጋር ተሰብስበዉ የሞቀዉ ቤታቸዉ ዉስጥ
ሲስቁ የልጆቹን ቡረቃ የቤዛዊትን ፈገግታ የእሱን ደስታ እያሰበ
ወጣቱ ዶክተር ቤዛዊት ከሆስፒታል ወጥታ ቤትዋ እንክብካቤ እንዲያረጉላት ለአባቷ መናገር
ሲጀምር ከቤዛዊት ጋር መሄድ አብሯት ሆኖ ማስታመም
ማቀፍ ከጎኗ መሆን ቢፈልግም እንደማይሆን
ልቡ ስላመነ ወደ ቤዛዊት ጆሮ ጠጋ ብሎ
"እወድሻለሁ አንቺ ብቻ ቶሎ ዳኚልኝ እኔ ሁሌም እጠብቅሻለሁ"
ሲላት ቤዛዊት ከጨፈገገዉ ፊትዋ ደማቁ ፈገግታዋ ብቅ አለ
"አሁን ቤት መሄድ አለብኝ"
ምላሿን ሳይጠብቅ ግንባሯን ሲስማት
ጉዋደኛዉ ፍቃዱ ቀኝ እጁን አፉ ላይ ጭኖ የታፈነ የፌዝ ሳቅ መሳቅ ጀመረ።
ፍፁም አይቶ እንዳላየ የቤዛዊትን እናት እና እህት በክብር ተሳናብቶ
ወደ አባትዋ እና ወደ መዉጫ በሩ እየተጠጋ
"እኔ እንደሚያስቡት አይነት ወጠጤ ሰዉ አደለሁ
ይቅርታ አድርጉልኝ ሰላም ዋሉ"
ብሎ ፍቃዱን ላለማየት እየቀፈፈዉ ከሆስፒታሉ ወጣ
መንገድ ላይ ቤዛዊት እና እሱ አብረዉ እንዲሆኑ
እናቷ እና እህቷ ያሳዩትን ፍቅር ሲያስብ
ወደዳቸዉ አመለካከታቸዉን እያደነቀ
የአባቷ ቁጣ እና ጥላቻ በጊዜ ሂደት እኔን ሲያዉቁኝ ሲረዱኝ ይጠፋል
የፍቃዱን መሀል ቤት መግባት ግን አልወደደዉም
"የኔ ቆንጆ"
የምትለዉ ቃል ከነከነችዉ
የሆነ ሸር እንደጠነሰሰበት ልቡ እየነገረዉ ነዉ።
ቤዛዊት ቤትዋ ገብታ ከሆስፒታል አልጋ
ወደ ራሷ አልጋ ተዘዋዉራለች ፍፁም ይቅርታ ስላረገላት
በአይኗ ስላየችዉ ፊትዋ መለስ ብሏል ጭንቀቷ ቀንሶላታል
እናትና እህቶ ከጎኗ ናቸዉ አባቷ ግን
ከፍቃዱ ጋር ምን እንዳጣመራቸዉ ባይገባትም
አንድ ላይ እንደሆኑ አዉቃለች።
በነጋታው ጠዋት ፍፁም ከእንቅልፉ እንደተነሳ ለቤዛዊት ደወለ ድምጿ ወደ ቀድሞዉ ተመልሷል
እንደተሻላት እየሳቀች ስለነገረችዉ
የፍቅር ህይወቱ እንደተስተካከለ እያመነ
ወደ ትምህርት ቤቱ አመራ።
ግቢዉ ዉስጥ የአብዛኛዉ አስተማሪ አስተያየት ተለዉጦበታል።
ፍቃዱ ከመምህራን ሀላፊዉ ቢሮ ሲወጣ አየዉ ግርምት እየፈጠረበት ሀላፊዉ ፍቃዱን ተከትለዉ ወጥተዉ
ፍፁም የቆመበት ጋር ሲደርሱ እጃቸዉ ላይ የያዙትን ወረቀት በብስጭት ዘረጉለት....
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
....የስራ ባልደረባዉ ፍቃዱ ነበር
የፍቃዱ ፊት እንደበፊቱ እንደሚያዉቀዉ
ለፍፁም አልሆነለትም ተቀይሮዋል እንደ አብዛኛዉ ባላንጣ ጉዋደኛ ምቀኝነትን እና ተንኮልን የሚያንፀባርቅ
አስተያየት እያየዉ
ፍቃዱ
"ሰዉየዉ እዚህ ደሞ ምን ትሰራለህ"
እያለ የፍፁምን መልስ ሳይጠብቅ ቤዛዊትን እያያት
"በርታ በይ የኔ ቆንጆ አይዞሽ"
እያላት ከአባቷ ጋር ተጠግቶ በሹክሹክታ ማዉራት ቀጠለ።
ፍፁም የቤዛዊትን የተጨነቀ ብዙ ሀሳብ የሚያስብ ገፅታዋን እያየ በሀሳብ ነጎደ
ቤዛዊት ያለባትን የአይምሮ መታወክ ችግርን
አብሯት ከጎኗ ሆኖ መታከም ያለባት ባታ ሁሉ ሳይደክም
እና ሳይሰለች ከጎኗ ሆኖ እስክትድን ሲደግፋት
ተሽሏት አብረዉ የሚመሰርቱትን ጎጆ
ምን አይነት የፍቅር ህይወት እንደሚመሩ
እንደ ቤዛዊት ቆንጆ የሆኑ መንታ ልጆች ስትወልድለት
ከልጆቻቸዉ ጋር ተሰብስበዉ የሞቀዉ ቤታቸዉ ዉስጥ
ሲስቁ የልጆቹን ቡረቃ የቤዛዊትን ፈገግታ የእሱን ደስታ እያሰበ
ወጣቱ ዶክተር ቤዛዊት ከሆስፒታል ወጥታ ቤትዋ እንክብካቤ እንዲያረጉላት ለአባቷ መናገር
ሲጀምር ከቤዛዊት ጋር መሄድ አብሯት ሆኖ ማስታመም
ማቀፍ ከጎኗ መሆን ቢፈልግም እንደማይሆን
ልቡ ስላመነ ወደ ቤዛዊት ጆሮ ጠጋ ብሎ
"እወድሻለሁ አንቺ ብቻ ቶሎ ዳኚልኝ እኔ ሁሌም እጠብቅሻለሁ"
ሲላት ቤዛዊት ከጨፈገገዉ ፊትዋ ደማቁ ፈገግታዋ ብቅ አለ
"አሁን ቤት መሄድ አለብኝ"
ምላሿን ሳይጠብቅ ግንባሯን ሲስማት
ጉዋደኛዉ ፍቃዱ ቀኝ እጁን አፉ ላይ ጭኖ የታፈነ የፌዝ ሳቅ መሳቅ ጀመረ።
ፍፁም አይቶ እንዳላየ የቤዛዊትን እናት እና እህት በክብር ተሳናብቶ
ወደ አባትዋ እና ወደ መዉጫ በሩ እየተጠጋ
"እኔ እንደሚያስቡት አይነት ወጠጤ ሰዉ አደለሁ
ይቅርታ አድርጉልኝ ሰላም ዋሉ"
ብሎ ፍቃዱን ላለማየት እየቀፈፈዉ ከሆስፒታሉ ወጣ
መንገድ ላይ ቤዛዊት እና እሱ አብረዉ እንዲሆኑ
እናቷ እና እህቷ ያሳዩትን ፍቅር ሲያስብ
ወደዳቸዉ አመለካከታቸዉን እያደነቀ
የአባቷ ቁጣ እና ጥላቻ በጊዜ ሂደት እኔን ሲያዉቁኝ ሲረዱኝ ይጠፋል
የፍቃዱን መሀል ቤት መግባት ግን አልወደደዉም
"የኔ ቆንጆ"
የምትለዉ ቃል ከነከነችዉ
የሆነ ሸር እንደጠነሰሰበት ልቡ እየነገረዉ ነዉ።
ቤዛዊት ቤትዋ ገብታ ከሆስፒታል አልጋ
ወደ ራሷ አልጋ ተዘዋዉራለች ፍፁም ይቅርታ ስላረገላት
በአይኗ ስላየችዉ ፊትዋ መለስ ብሏል ጭንቀቷ ቀንሶላታል
እናትና እህቶ ከጎኗ ናቸዉ አባቷ ግን
ከፍቃዱ ጋር ምን እንዳጣመራቸዉ ባይገባትም
አንድ ላይ እንደሆኑ አዉቃለች።
በነጋታው ጠዋት ፍፁም ከእንቅልፉ እንደተነሳ ለቤዛዊት ደወለ ድምጿ ወደ ቀድሞዉ ተመልሷል
እንደተሻላት እየሳቀች ስለነገረችዉ
የፍቅር ህይወቱ እንደተስተካከለ እያመነ
ወደ ትምህርት ቤቱ አመራ።
ግቢዉ ዉስጥ የአብዛኛዉ አስተማሪ አስተያየት ተለዉጦበታል።
ፍቃዱ ከመምህራን ሀላፊዉ ቢሮ ሲወጣ አየዉ ግርምት እየፈጠረበት ሀላፊዉ ፍቃዱን ተከትለዉ ወጥተዉ
ፍፁም የቆመበት ጋር ሲደርሱ እጃቸዉ ላይ የያዙትን ወረቀት በብስጭት ዘረጉለት....
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...ወረቀት በብስጭት ዘረጉለት።
ፍፁም እዛዉ በቆመበት ማንበብ ጀመረ
ወረቀቱ የሚገልፀዉ በአላስፈላጊ ከመምህር በማይጠበቅ ድርጊት ዉስጥ ተሳትፎ
ሌሎች አስተማሪወችም ተማክረዉበት እና ዉሳኔ ተሰጥቶበት ከማስተማር ስራዉ እንደተባረረ ይገልፃል።
ይሄ ሁሉ የፍቃዱ ተንኮል እና ስራ መሆኑ እያናደደዉ ከሱ ዉጪ ስለ ቤዛዊት እና እሱ ግንኙነት የሚያቅ እንደሌለ
እና ወሬዉን ፍቃዱ ነዝቶት እንዲባረረ እንዳረገዉ እያሰበ
ከፍቃዱ ጋር ሌላ ነገር ዉስጥ ላለመግባት
ከራሱ ስሜት ጋር እየተታገለ ወደ መምህራን ቢሮ ገብቶ
ወሬ ማብዛቱን ስላልወደደዉ በተፃፈበት ከስራ መባረርን ጉዳይ መከራከር ስላልፈለገ
ፍቅሩ የእዉነት መሆኑን በዚህ ሰአት
ማንም ስለማይረዳዉ እቃወቹን በቦርሳዉ መከታተት ጀመረ። አስተማሪ መሆኑ እና ማፍቀሩ
አይምሮዉ ላይ ግጭት እየፈጠረበት
እዉነት እና የሙያ ስነምግባር ተምታተዉበት
ግራ ግብት ያለዉ ስሜት ዉስጥ ገብቶ ነገር ግን በልቡ
"ለበጎ ይሆናል"
እያለ መጥፎ ነገሮች በህይወቱ እየተደጋገሙበት
የቤዛዊት ጮሀ እንዳሳሰረችዉ አሁን ደግሞ ከስራ ገበታዉ መባረሩ ዉስጡን እየጎዳዉ ቢሆንም
ችሎ ለማለፍ ከራሱ ጋር እየታገለ።
ከትምህርት ቤቱ መዉጫ በር ጋር
ቦርሳዉን በቀኝ ትከሻዉ አንግቦ ምስቅልቅል ባለ ስሜት
ወደ ኋላዉ ዞሮ ግቢዉን በአይኑ ቃኘዉ
የእነ ቤዛዊት ክፍልን በር በአትኩሮት እያየዉ በሀሳብ ተጓዘ
ቤዛዊት እጇን እያዉለበለበችለት ይመስለዋል
ፈገግታዋ ግን የለም ነገር ግን በሩ ላይ ቆማ የመሰናበት የሚመስል የእጅ እንቅስቃሴ ታሳየዋለች
ከአይኖቾ እንባወች እየፈሰሱ ነዉ
ቀርቦ እንባዋን ለማበስ አስቦ
አንድ እርምጃ ሲራመድ ከሀሳቡ ባነነ
ፊት ለፊቱ ፍቃዱ ቆሞ ነበር
"አበድክ እንዴ ሰዉየዉ"
ፍቃዱ የአሽሙር ፈገግታ ፈገግ እያለ
ሰዉ እንደዚህ ነዉ አንዳንዴ ሳያዉቅህ
ያወቀህ ለመምሰል ያከብርሀል
መልካም ሰዉ ለመምሰል ይሞክራል
እንዳወቀህ ሲገባዉ ሳያዉቅህ ይንቅሀል
ማስመሰሉን ትቶ እዉነተኛ መጥፎ በሀሪዉን ያሳይሀል።
ሄኖክ ፍቃዱን እየተገረመ እያየዉ
"እብደት አልከዉ አሳባጅ በሞላባት ምድር
የሚያብድ ሰዉ ቢበዛ አይገርምም... "
ጥሎት ግቢዉን ስራዉን ትቶ ወጣ
ወደ ፊት ምን ሊፈጠር እንደሚችል እያሰበ
ከቤዛዊት ጋር እንዴት ሊኖሩ እንደሚችሉ
እሷን ከህመሞ የትኛዉ ሀኪም ቤት እና
ዶክተር ጋር ቢወስዳት ጤናዋ እንደሚመለስ እያሰበ
እሱም ምን ስራ እንደሚሰራ እያሰበ ሌላ ትምህርት ቤት
እንኳን ምን ማድረግ እንደሚችል እያስጨነቀዉ።
ቤዛዊት ከአልጋዋ ተነስታ መንቀሳቀስ ጀምራለች
ሄኖክን እየደወለች ሁሌ ብታዋራዉም
ለማየት ጓጉታለች በጣም ናፍቋታል።
የመጀመርያዋ ነዉ እንደዚህ አይነት ስሜት ሲሰማት
ፍቅር የሚያረገዉን ነገር ሁሉ
ፍፁምን ካየችዉ ቀን ጀምሮ ነዉ ማወቅ የጀመረችዉ
ከዛ በፊት ብዙም እዉቀቱ አልነበራትም።
ፍፁምን ለማግኘት አስባ ከመኝታ ክፍሏ ስትወጣ አባቷ ከመምህር ፍቃዱ ጋር ሳሎን ተቀምጠዉ
"ቤዛዊት የምንነግርሽ ነገር አለ"
አሏት እንድትቀመጥ ፊት ለፊታቸዉ ያለዉን ሶፋ
በአይናቸዉ እንድትቀመጥ እየጋበዟት......
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...ወረቀት በብስጭት ዘረጉለት።
ፍፁም እዛዉ በቆመበት ማንበብ ጀመረ
ወረቀቱ የሚገልፀዉ በአላስፈላጊ ከመምህር በማይጠበቅ ድርጊት ዉስጥ ተሳትፎ
ሌሎች አስተማሪወችም ተማክረዉበት እና ዉሳኔ ተሰጥቶበት ከማስተማር ስራዉ እንደተባረረ ይገልፃል።
ይሄ ሁሉ የፍቃዱ ተንኮል እና ስራ መሆኑ እያናደደዉ ከሱ ዉጪ ስለ ቤዛዊት እና እሱ ግንኙነት የሚያቅ እንደሌለ
እና ወሬዉን ፍቃዱ ነዝቶት እንዲባረረ እንዳረገዉ እያሰበ
ከፍቃዱ ጋር ሌላ ነገር ዉስጥ ላለመግባት
ከራሱ ስሜት ጋር እየተታገለ ወደ መምህራን ቢሮ ገብቶ
ወሬ ማብዛቱን ስላልወደደዉ በተፃፈበት ከስራ መባረርን ጉዳይ መከራከር ስላልፈለገ
ፍቅሩ የእዉነት መሆኑን በዚህ ሰአት
ማንም ስለማይረዳዉ እቃወቹን በቦርሳዉ መከታተት ጀመረ። አስተማሪ መሆኑ እና ማፍቀሩ
አይምሮዉ ላይ ግጭት እየፈጠረበት
እዉነት እና የሙያ ስነምግባር ተምታተዉበት
ግራ ግብት ያለዉ ስሜት ዉስጥ ገብቶ ነገር ግን በልቡ
"ለበጎ ይሆናል"
እያለ መጥፎ ነገሮች በህይወቱ እየተደጋገሙበት
የቤዛዊት ጮሀ እንዳሳሰረችዉ አሁን ደግሞ ከስራ ገበታዉ መባረሩ ዉስጡን እየጎዳዉ ቢሆንም
ችሎ ለማለፍ ከራሱ ጋር እየታገለ።
ከትምህርት ቤቱ መዉጫ በር ጋር
ቦርሳዉን በቀኝ ትከሻዉ አንግቦ ምስቅልቅል ባለ ስሜት
ወደ ኋላዉ ዞሮ ግቢዉን በአይኑ ቃኘዉ
የእነ ቤዛዊት ክፍልን በር በአትኩሮት እያየዉ በሀሳብ ተጓዘ
ቤዛዊት እጇን እያዉለበለበችለት ይመስለዋል
ፈገግታዋ ግን የለም ነገር ግን በሩ ላይ ቆማ የመሰናበት የሚመስል የእጅ እንቅስቃሴ ታሳየዋለች
ከአይኖቾ እንባወች እየፈሰሱ ነዉ
ቀርቦ እንባዋን ለማበስ አስቦ
አንድ እርምጃ ሲራመድ ከሀሳቡ ባነነ
ፊት ለፊቱ ፍቃዱ ቆሞ ነበር
"አበድክ እንዴ ሰዉየዉ"
ፍቃዱ የአሽሙር ፈገግታ ፈገግ እያለ
ሰዉ እንደዚህ ነዉ አንዳንዴ ሳያዉቅህ
ያወቀህ ለመምሰል ያከብርሀል
መልካም ሰዉ ለመምሰል ይሞክራል
እንዳወቀህ ሲገባዉ ሳያዉቅህ ይንቅሀል
ማስመሰሉን ትቶ እዉነተኛ መጥፎ በሀሪዉን ያሳይሀል።
ሄኖክ ፍቃዱን እየተገረመ እያየዉ
"እብደት አልከዉ አሳባጅ በሞላባት ምድር
የሚያብድ ሰዉ ቢበዛ አይገርምም... "
ጥሎት ግቢዉን ስራዉን ትቶ ወጣ
ወደ ፊት ምን ሊፈጠር እንደሚችል እያሰበ
ከቤዛዊት ጋር እንዴት ሊኖሩ እንደሚችሉ
እሷን ከህመሞ የትኛዉ ሀኪም ቤት እና
ዶክተር ጋር ቢወስዳት ጤናዋ እንደሚመለስ እያሰበ
እሱም ምን ስራ እንደሚሰራ እያሰበ ሌላ ትምህርት ቤት
እንኳን ምን ማድረግ እንደሚችል እያስጨነቀዉ።
ቤዛዊት ከአልጋዋ ተነስታ መንቀሳቀስ ጀምራለች
ሄኖክን እየደወለች ሁሌ ብታዋራዉም
ለማየት ጓጉታለች በጣም ናፍቋታል።
የመጀመርያዋ ነዉ እንደዚህ አይነት ስሜት ሲሰማት
ፍቅር የሚያረገዉን ነገር ሁሉ
ፍፁምን ካየችዉ ቀን ጀምሮ ነዉ ማወቅ የጀመረችዉ
ከዛ በፊት ብዙም እዉቀቱ አልነበራትም።
ፍፁምን ለማግኘት አስባ ከመኝታ ክፍሏ ስትወጣ አባቷ ከመምህር ፍቃዱ ጋር ሳሎን ተቀምጠዉ
"ቤዛዊት የምንነግርሽ ነገር አለ"
አሏት እንድትቀመጥ ፊት ለፊታቸዉ ያለዉን ሶፋ
በአይናቸዉ እንድትቀመጥ እየጋበዟት......
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#በመጨረሻው_ቀን
.../ሣቅ/...
መለያየታችን የግድ ሆኖ ተበቃቅተን ልንራራቅ ነውና
በሔድህበት ቸር ይግጠምህ በል ክረም በደህና።
በፍቅር ተሳስበን ያሳለፍነው ዘመን እንዴት ጥሩ ነበር?!?
ሌላ ቃል የለኝም ከማዘን በስተቀር እንግዲ ምን ልበል?!?
በቃ ?... ልትሔድ ነው?
እንዴት እሆናለው?!?
ቆይ እስቲ አንድ ግዜ ዕቃህን ቁጭ አርገው፣
አንተም አረፍ በል፣ዕንባህን ጥረገው፣
አፈቅርሃለሁ እኮ!!!
...../ልቅሶ/.....
ባዶ ነኝ፥ወና ነኝ።
ብሆንም ውዴ ሆይ
ክረምቱን እንዳንቺ
እምጠለልበት
እማሳልፍበት
ባይኖረኝም ባዶ ቤት
ከልብ በመነጨ በእውነተኛ ስሜት
እኔስ እልሻለው ፍቅሬ ብቻ በርቺ
ውዴ የኔ እመቤት በይ ደህና ሰንብቺ።
🔘በፋሲል ተካልኝ🔘
.../ሣቅ/...
መለያየታችን የግድ ሆኖ ተበቃቅተን ልንራራቅ ነውና
በሔድህበት ቸር ይግጠምህ በል ክረም በደህና።
በፍቅር ተሳስበን ያሳለፍነው ዘመን እንዴት ጥሩ ነበር?!?
ሌላ ቃል የለኝም ከማዘን በስተቀር እንግዲ ምን ልበል?!?
በቃ ?... ልትሔድ ነው?
እንዴት እሆናለው?!?
ቆይ እስቲ አንድ ግዜ ዕቃህን ቁጭ አርገው፣
አንተም አረፍ በል፣ዕንባህን ጥረገው፣
አፈቅርሃለሁ እኮ!!!
...../ልቅሶ/.....
ባዶ ነኝ፥ወና ነኝ።
ብሆንም ውዴ ሆይ
ክረምቱን እንዳንቺ
እምጠለልበት
እማሳልፍበት
ባይኖረኝም ባዶ ቤት
ከልብ በመነጨ በእውነተኛ ስሜት
እኔስ እልሻለው ፍቅሬ ብቻ በርቺ
ውዴ የኔ እመቤት በይ ደህና ሰንብቺ።
🔘በፋሲል ተካልኝ🔘
#እስከ_እሁን_እወድሻለሁ
እንቺ ከሄድሽ በኋላ
ብዙ ትውልድ አለፈ
ዳዊት በጎልያድ ተሸነፈ
ብዙ ታሪክ ተፃፈ
ብዙ ገድል ተገደለ
ብዙ ጨለማ ተለኮሰ ፥ ብዙ ፀሐይ ከሰለ
በግ በተኩላ ተመካ
ደርግ በደርግ ተተካ
ደርግን ሚያስንቅ ደርግ ሲወርድ ፥ ስብከት ሆኖ ፖለቲካ
ህዝብ በቃል ተጠመቀ ፥ ህጎች በወንጌል ተጣሱ
ሸሆች እንባ አፈሰሱ
ጳጳሳት አለቀሱ
ብሔርተኛ አክቲቪስቶች
ለቄንጥ ሳቅ ተዘጋጅተው ፥ ጥርሳቸውን ተነቀሱ
ቤተክርስቲያኖች በእሳት ጋዩ ፥ ብዙ መሥጅዶች ፈረሱ
ብዙዎች ከሀገራቸው ላይ ፥ ወደሀገራቸው ፈለሱ
በደለኞች ፍርድ ሲሹ ፥ ምህረት ሆነ ፍትህ መልሱ
በገባኦን ሰማይ ላይ ፥ ፀሐይ የሚያቆም ኢያሱ
ጨለማን ማቆም ጀመሮ ፥ ትውልዱ ብርሐን ናፈቀ
ይነጋል በተባለው ቀን ፥ ብዙ ፀሐይ ተሰረቀ
ብዙ ሻማ በእንባ አለቀ።
አንቺ ከሔድሽ በኋላ..
ሰውነት ከሰው ተጣላ
ብሔርተኝነት አደገ ፥ የሰው ስጋ እየበላ
የሰውን ደም እየጠጣ ፥ ነፍስን አክስቶ ወፈረ
"የተማረ ይግደለኝ” ባይ
በሚበዛባት ሀገር ላይ
ብዙ ተማሪ ተገደለ ፥ ብዙ ተማሪ ተወገረ
ትውልድ ከትውልድ ተቃቃረ።
ሁሉ በሌላ ሲቀየር ፥ ዘመን በዘመን ሲታረም
ላንቺ ያለኝ ፍቅር ብቻ
እንደሀገሬ ፖለቲካ ፥ እስካሁን አልተቀየረም ።
🔘በላይ በቀለም ወያ🔘
እንቺ ከሄድሽ በኋላ
ብዙ ትውልድ አለፈ
ዳዊት በጎልያድ ተሸነፈ
ብዙ ታሪክ ተፃፈ
ብዙ ገድል ተገደለ
ብዙ ጨለማ ተለኮሰ ፥ ብዙ ፀሐይ ከሰለ
በግ በተኩላ ተመካ
ደርግ በደርግ ተተካ
ደርግን ሚያስንቅ ደርግ ሲወርድ ፥ ስብከት ሆኖ ፖለቲካ
ህዝብ በቃል ተጠመቀ ፥ ህጎች በወንጌል ተጣሱ
ሸሆች እንባ አፈሰሱ
ጳጳሳት አለቀሱ
ብሔርተኛ አክቲቪስቶች
ለቄንጥ ሳቅ ተዘጋጅተው ፥ ጥርሳቸውን ተነቀሱ
ቤተክርስቲያኖች በእሳት ጋዩ ፥ ብዙ መሥጅዶች ፈረሱ
ብዙዎች ከሀገራቸው ላይ ፥ ወደሀገራቸው ፈለሱ
በደለኞች ፍርድ ሲሹ ፥ ምህረት ሆነ ፍትህ መልሱ
በገባኦን ሰማይ ላይ ፥ ፀሐይ የሚያቆም ኢያሱ
ጨለማን ማቆም ጀመሮ ፥ ትውልዱ ብርሐን ናፈቀ
ይነጋል በተባለው ቀን ፥ ብዙ ፀሐይ ተሰረቀ
ብዙ ሻማ በእንባ አለቀ።
አንቺ ከሔድሽ በኋላ..
ሰውነት ከሰው ተጣላ
ብሔርተኝነት አደገ ፥ የሰው ስጋ እየበላ
የሰውን ደም እየጠጣ ፥ ነፍስን አክስቶ ወፈረ
"የተማረ ይግደለኝ” ባይ
በሚበዛባት ሀገር ላይ
ብዙ ተማሪ ተገደለ ፥ ብዙ ተማሪ ተወገረ
ትውልድ ከትውልድ ተቃቃረ።
ሁሉ በሌላ ሲቀየር ፥ ዘመን በዘመን ሲታረም
ላንቺ ያለኝ ፍቅር ብቻ
እንደሀገሬ ፖለቲካ ፥ እስካሁን አልተቀየረም ።
🔘በላይ በቀለም ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...እንድትቀመጥ ጋበዟት
ቤዛዊት አንዴ አባቷን አንዴ ከአባቷ አጠገብ ያዘነ መስሎ የተቀመጠዉን ፍቃዱን እያየች ፊት ለፊታቸዉ ተቀመጠች
ምን ሊሏት እንደሚችሉ እያሰበች።
"ትሰሚኛለሽ ልጄ"
አባቷ ቀጠሉ
"ፍፁም አንቺ እንደምታስቢዉ ጥሩ ሰዉ አደለም!"
ፍቃዱ አቋርጧቸዉ
"ሚስት እና ልጆቹን ትቶ ነዉ አንቺንም
ወደድኩሽ የሚልሽ አየሽ..."
ቤዛዊት የሚያወሩት ነገር ግራ ስለገባት እና ያልጠበቀችዉ ስለሆነ ከልቧ እየሰማቻቸዉ ነበር።
ፍቃዱ ከተቀመጠበት እየተነሳ ቤዛዊት አጠገብ እየተቀመጠ ከኪሱ ፎቶ አዉጥቶ እንድትቀበለዉ
ወደ እሷ እጇች ዘረጋቸዉ።
ቤዛዊት ማየት ሳትፈልግ በተረበሸ ስሜት ዉስጥ ሆና ተቀበለችዉ ፎቶዉ ቆየት ያለ መሆኑ ሲታይ ያስታዉቃል
ፍፁም ነጭ ሸሚዝ በጥቁር ሱሪ ለብሶ
ጥቁር ቆዳ ጫማ ተጫምቶ ፊቱ ላይ ደማቅ ፈገግታ
እየተነበበ አንዲት ህፃን ልጅ ያቀፈች ጠይም ሴት አቅፎዋል
እሷም ፈገግ ብላ ለካሜራዉ ፈገግታዋን ትለግሳለች
ደረቷ ላይ ያቀፈችዉ ህፃን ከሁለቱም ስሜት ሳይሆን
ካሜራዉን እረስቶ አይኖቹን ወደ ሰማይ ተክሎ ፎቶዉ ላይ ይታያል።
"አየሽ ቤዛዊት ፍፁም ትዳሩን ልጁን ጥሎ ነዉ እዚህ ከተማ የመጣዉ...አይሆንሽም..."
ቤዛዊት የፍቃዱን ወሬ መስማት አልቻለችም
ድብልቅ ያለ ስሜት ዉስጥ ሆና
ፎቶዉን መሬት ላይ ጥላዉ እረግጣዉ ወደ መኝታ ክፍሏ እንባዋን እንዳያዩባት እየሮጠች ገባች።
ፍፁም የተመነቃቀረ ቤቱን አፀዳድቶ
ከቤዛዊት ጋር የቀጠሮ ሰአታቸዉን እያሰበ
በተደጋጋሚ ሰአቱን እያየ ከቆየ በኋላ ሊደዉልላት
ስልኩን አዉጥቶ በተደጋጋሚ ቢደዉልም አይነሳም
"ምን አጋጥሞት ይሆን?"
እያለ በጭንቀት ተስፋ ሳይቆርጥ
የቀጠሮ ሰአታቸዉ አልፎም እየተንቆራጠጠ ሲሞክር
ስልኩ ተነሳ
"አቤት"
የተዘጋጋ ወፍራም ድምፅ ቤዛዊት ናት
ብዙ ከመነፋረቋ የተነሳ ጉሮሮዋ ተዘጋግቷል
ፍፁም በጥርጣሬ
"ቤዛዊት ቤዛዊት ምነዉ ድምፅሽ ምን ሆንሽብኝ"
ፈጣሪ ቸር ያሰማኝ እያለ የእሷን መልስ ለመጠበቅ
ሰፍ ቢልም የሚሰማዉ የታፈነ የለቅሶ ድምፅ ብቻ ነበር
"በፈጠረሽ ንገሪኝ ልምጣ እንዴ ቤት ነሽ"
ፍፁም የሚይዘዉ የሚጨብጠዉ ጠፍቶት ተጨነቀ
"ሚስት...እና ልጅ... አለክ"
የቤዛዊት የሚቆራረጥ ድምፅ በጆሮወቹ አስተጋባ
"የምን ሚስት እና ልጅ ቤዚ ምን አይነት ወሬ ነዉ የምታወሪዉ.."
ያልጠበቀዉ ጥያቄ ስለሆነ ምን ብላ ጠየቀችኝ እያለ
"አለክ አትዋሸኝ በአይኔ ነዉ ያሳዩኝ
እኔንም ጥለኀኝ ልትጠፋ ነዉ አደል
የዉሸት እወድሻለሁ የምትለኝ እኔ እየወደድኩክ...."
የቤዛዊትን ንግግር ሰምቶ መጨረስ አልቻለም
አልጋዉን በዳበሳ አጊንቶት ቁጭ አለ
"መልስ የለህም አደል በቃ ተወኝ እረሳካለሁ"
የቤዛዊት የመጨረሻ ቃል ጆሮዉ ላይ ስልኩን ከመዝጋቷ በፊት።
ፍፁም "በአይኔ ነዉ ያሳዩኝ"የሚለዉን ቃል እያስታዉሰ
እነማን ናቸዉ ሲል አሰበ አይምሮዉ ላይ
"ፍቃዱ ፍቃዱ"
የሚል ሲያስተጋባበት ወደ ሌላ ጥያቄ ተሸጋገረ
"ምን አሳያት"
ለዚህ የሚሆን መልስ ግን ስላጣ መጨነነቁ ጨመረ
ህይወቱ ምስቅልቅል እያለ መሰለዉ
ከስራ መባረሩ የተባረረበት ምክንያት የሆነችዉ ከልቡ የወደዳትም ቤዛዊት በዉሸት ወሬ ስለተለወጠችበት
እያዘነ አልጋዉ ላይ ጋደም ብሎ በሀሳብ ነጎደ።
አመሻሹ ላይ ሀሳቡ ወደ እንቅልፍ መርቶት
የልጅነት ህይወቱ በህልም አለም እየታየዉ ነቃ።
ከአልጋዉ በፍጥነት እየተነሳ
መደርደርያዉ ዉስጥ ያለዉን የፎቶ አልበም አዉጥቶ
ማገላበጥ ጀመረ።
ከመሀል ከተደረደሩ ፎቶወች መሀል
ዉጪ ሀገር ከሄደች ብዙ አመታት የሆናት ታናሽ እህቱ ከልጇ ጋር ሆነዉ እስዋን ሽኝት ሲያረግላት አብረዉ የተነሱት
ፎቶ መጥፋቱን አስታወሰ።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...እንድትቀመጥ ጋበዟት
ቤዛዊት አንዴ አባቷን አንዴ ከአባቷ አጠገብ ያዘነ መስሎ የተቀመጠዉን ፍቃዱን እያየች ፊት ለፊታቸዉ ተቀመጠች
ምን ሊሏት እንደሚችሉ እያሰበች።
"ትሰሚኛለሽ ልጄ"
አባቷ ቀጠሉ
"ፍፁም አንቺ እንደምታስቢዉ ጥሩ ሰዉ አደለም!"
ፍቃዱ አቋርጧቸዉ
"ሚስት እና ልጆቹን ትቶ ነዉ አንቺንም
ወደድኩሽ የሚልሽ አየሽ..."
ቤዛዊት የሚያወሩት ነገር ግራ ስለገባት እና ያልጠበቀችዉ ስለሆነ ከልቧ እየሰማቻቸዉ ነበር።
ፍቃዱ ከተቀመጠበት እየተነሳ ቤዛዊት አጠገብ እየተቀመጠ ከኪሱ ፎቶ አዉጥቶ እንድትቀበለዉ
ወደ እሷ እጇች ዘረጋቸዉ።
ቤዛዊት ማየት ሳትፈልግ በተረበሸ ስሜት ዉስጥ ሆና ተቀበለችዉ ፎቶዉ ቆየት ያለ መሆኑ ሲታይ ያስታዉቃል
ፍፁም ነጭ ሸሚዝ በጥቁር ሱሪ ለብሶ
ጥቁር ቆዳ ጫማ ተጫምቶ ፊቱ ላይ ደማቅ ፈገግታ
እየተነበበ አንዲት ህፃን ልጅ ያቀፈች ጠይም ሴት አቅፎዋል
እሷም ፈገግ ብላ ለካሜራዉ ፈገግታዋን ትለግሳለች
ደረቷ ላይ ያቀፈችዉ ህፃን ከሁለቱም ስሜት ሳይሆን
ካሜራዉን እረስቶ አይኖቹን ወደ ሰማይ ተክሎ ፎቶዉ ላይ ይታያል።
"አየሽ ቤዛዊት ፍፁም ትዳሩን ልጁን ጥሎ ነዉ እዚህ ከተማ የመጣዉ...አይሆንሽም..."
ቤዛዊት የፍቃዱን ወሬ መስማት አልቻለችም
ድብልቅ ያለ ስሜት ዉስጥ ሆና
ፎቶዉን መሬት ላይ ጥላዉ እረግጣዉ ወደ መኝታ ክፍሏ እንባዋን እንዳያዩባት እየሮጠች ገባች።
ፍፁም የተመነቃቀረ ቤቱን አፀዳድቶ
ከቤዛዊት ጋር የቀጠሮ ሰአታቸዉን እያሰበ
በተደጋጋሚ ሰአቱን እያየ ከቆየ በኋላ ሊደዉልላት
ስልኩን አዉጥቶ በተደጋጋሚ ቢደዉልም አይነሳም
"ምን አጋጥሞት ይሆን?"
እያለ በጭንቀት ተስፋ ሳይቆርጥ
የቀጠሮ ሰአታቸዉ አልፎም እየተንቆራጠጠ ሲሞክር
ስልኩ ተነሳ
"አቤት"
የተዘጋጋ ወፍራም ድምፅ ቤዛዊት ናት
ብዙ ከመነፋረቋ የተነሳ ጉሮሮዋ ተዘጋግቷል
ፍፁም በጥርጣሬ
"ቤዛዊት ቤዛዊት ምነዉ ድምፅሽ ምን ሆንሽብኝ"
ፈጣሪ ቸር ያሰማኝ እያለ የእሷን መልስ ለመጠበቅ
ሰፍ ቢልም የሚሰማዉ የታፈነ የለቅሶ ድምፅ ብቻ ነበር
"በፈጠረሽ ንገሪኝ ልምጣ እንዴ ቤት ነሽ"
ፍፁም የሚይዘዉ የሚጨብጠዉ ጠፍቶት ተጨነቀ
"ሚስት...እና ልጅ... አለክ"
የቤዛዊት የሚቆራረጥ ድምፅ በጆሮወቹ አስተጋባ
"የምን ሚስት እና ልጅ ቤዚ ምን አይነት ወሬ ነዉ የምታወሪዉ.."
ያልጠበቀዉ ጥያቄ ስለሆነ ምን ብላ ጠየቀችኝ እያለ
"አለክ አትዋሸኝ በአይኔ ነዉ ያሳዩኝ
እኔንም ጥለኀኝ ልትጠፋ ነዉ አደል
የዉሸት እወድሻለሁ የምትለኝ እኔ እየወደድኩክ...."
የቤዛዊትን ንግግር ሰምቶ መጨረስ አልቻለም
አልጋዉን በዳበሳ አጊንቶት ቁጭ አለ
"መልስ የለህም አደል በቃ ተወኝ እረሳካለሁ"
የቤዛዊት የመጨረሻ ቃል ጆሮዉ ላይ ስልኩን ከመዝጋቷ በፊት።
ፍፁም "በአይኔ ነዉ ያሳዩኝ"የሚለዉን ቃል እያስታዉሰ
እነማን ናቸዉ ሲል አሰበ አይምሮዉ ላይ
"ፍቃዱ ፍቃዱ"
የሚል ሲያስተጋባበት ወደ ሌላ ጥያቄ ተሸጋገረ
"ምን አሳያት"
ለዚህ የሚሆን መልስ ግን ስላጣ መጨነነቁ ጨመረ
ህይወቱ ምስቅልቅል እያለ መሰለዉ
ከስራ መባረሩ የተባረረበት ምክንያት የሆነችዉ ከልቡ የወደዳትም ቤዛዊት በዉሸት ወሬ ስለተለወጠችበት
እያዘነ አልጋዉ ላይ ጋደም ብሎ በሀሳብ ነጎደ።
አመሻሹ ላይ ሀሳቡ ወደ እንቅልፍ መርቶት
የልጅነት ህይወቱ በህልም አለም እየታየዉ ነቃ።
ከአልጋዉ በፍጥነት እየተነሳ
መደርደርያዉ ዉስጥ ያለዉን የፎቶ አልበም አዉጥቶ
ማገላበጥ ጀመረ።
ከመሀል ከተደረደሩ ፎቶወች መሀል
ዉጪ ሀገር ከሄደች ብዙ አመታት የሆናት ታናሽ እህቱ ከልጇ ጋር ሆነዉ እስዋን ሽኝት ሲያረግላት አብረዉ የተነሱት
ፎቶ መጥፋቱን አስታወሰ።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#በእምነት_የመጣ_እምነት
ከለታት አንድ ቀን
ከማጣ ከምሞት?” ፥ የሚል ምርጫ አቅርባ
የራሷን ጥያቄ ፥ በእንባዋ አጅባ
ብሞት ይሻለኛል ፥ ብላ ነገረችኝ
ስትነግረኝ አመንኳት
እፈትናት ብዬ ፥ እንድትሞት ራኳት
ሳልፈልግ ሸኘኋት ፥ ሳትፈልግ አጣችኝ።
*
ከእለታት ሁለት ቀን
“እሷ ዋሽታ አታውቅም ፥ ለቃሏ ታማኝ ነች
እንዳጣችኝ አውቃ ፥ ይሔኔ ሞታለች።”
በማለት አስቤ
ለቀብሯ ስዘጋጅ ፥ እሷ ትኖራለች
*
ከእለታት ብዙ ቀን
“እንዴት አልሞተችም ?”
የሚል የእምነት እዳ ፥ መች አብሰለሰለኝ?
አጥታኝ ስትኖር ባያት
እየኖረች መሞት ፥ ምታውቅ መሠለኝ።
አምናታለሁና!
እሷ አትዋሽምና!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ከለታት አንድ ቀን
ከማጣ ከምሞት?” ፥ የሚል ምርጫ አቅርባ
የራሷን ጥያቄ ፥ በእንባዋ አጅባ
ብሞት ይሻለኛል ፥ ብላ ነገረችኝ
ስትነግረኝ አመንኳት
እፈትናት ብዬ ፥ እንድትሞት ራኳት
ሳልፈልግ ሸኘኋት ፥ ሳትፈልግ አጣችኝ።
*
ከእለታት ሁለት ቀን
“እሷ ዋሽታ አታውቅም ፥ ለቃሏ ታማኝ ነች
እንዳጣችኝ አውቃ ፥ ይሔኔ ሞታለች።”
በማለት አስቤ
ለቀብሯ ስዘጋጅ ፥ እሷ ትኖራለች
*
ከእለታት ብዙ ቀን
“እንዴት አልሞተችም ?”
የሚል የእምነት እዳ ፥ መች አብሰለሰለኝ?
አጥታኝ ስትኖር ባያት
እየኖረች መሞት ፥ ምታውቅ መሠለኝ።
አምናታለሁና!
እሷ አትዋሽምና!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
....መጥፋቱን አስታወሰ
ህይወት ብዙ ሰወችን ታገናኘናለች የሚወዱን የምንወዳቸዉ
የሚጠሉን የምንጠላቸዉ
ይሄ ሁሌም ያለ እዉነት ነዉ ነገር ግን
ወዳጅ መስለዉ የቀረቡን ጠላቶቻችንን ማወቅ ይከብዳል
ለዚህም ነዉ አንዳንዴ የኔ ያልነዉ ሰዉ
ሳንጠብቀዉ ተለዉጦ ጋኔል ይሆንብናል
በተቃራኒዉም የጠላነዉ ሰዉ አልፎ አልፎ ስንቀርበዉ መልዓክ ይሆናል።
ፍፁምንም የገጠመዉ ይሄ ነዉ ፍቃዱን ቤቱ ያስገባበት ቀን
ዉስን ነዉ በጣት የሚቆጠር በጊዜዉ ዉስጡ ላይ የፍቃዱ ተንኮል ስላልታየዉ
ልብ ብሎ አልተከታተለዉም እንጂ ፍቃዱ የቤዛዊትን እና የፍቃዱን ፍቅር ያዉቅ ነበር
ፍፁም ስለቤዛዊት ሲጠይቀዉም ፍቃዱ የሚመልስለት
ስለ ቤዛዊት ህመም መጥፎ መጥፎዉን እንጂ ጥሩ እና መልካም ጎኗን ነግሮት አያዉቅም
ፍቃዱም በቤዛዊት ዉበት የቤዛዊትን አማላይ ሰዉነት
በፍትወት ሲመኛት አመታት አልፈዉታል
ለዚህም ነዉ የፍፁምን መልካም ጎን አይቶ እሱ በክፋት ተጠቅሞበት አሁን ሊያለያያቸዉ የበቃዉ።
ፍፁም ለሊቱን ሲብከነከን ማረግ ያለበትን ሲያስብ ሲጨነቅ አልፎ
የማይነጋ ለሊት የለም ነግቶ ከአልጋዉ ወርዶ
ለአለባበሱ ሳይጨነቅ ከላይ በተኛበት ቲሸርት ከስር የለበሰዉን
ሰፊ ቱታ ለብሶ ነጠላ ጫማ ተጫምቷ ወደ ቤዛዊት ቤት አመራ።
ቤዛዊት ሀዘኗ እንደጉም ትንን ብሎ በተለመደዉ ፈገግታዋ
እና ዉበቷ ደምቃ ለትምህርት ከቤቷ ቶሎ ወጥታለች
ፍፁም ቤቷ ደርሶ
በራቸዉን ለማንኳኳት አስቦ እያተጨነቀ በሩ ተከፍቶ እህቷ ወጣች።
"እንዴት አደርክ ፍፁም.."
የቤዛዊት እህት ፍፁምን ባላሰበችዉ ሰዓት ስላየችዉ
እየተገረመች እያየችዉ
"ቤዛዊት አለች"
አጭር ቃላት ከአፉ ወጡ
"ዉይ አሁን ወጣች ወደ ትምህርት ቤት.."
ሌላ የምታወራዉን አልሰማትም ፍፁም አንገቱን
መሬት ላይ አቀርቅሮ ወደ ትምህርት ቤቱ ወደሚወስደዉ
አቅጣጫ ተጓዘ እየተብከነከነ።
ቤዛዊት ወደ ትምህርት ቤት እያመራች ፍፁምን በልቧ
አስታዉሳዉ እንደ ጠላቷ እረገመችዉ
"እንዴት እንደዚህ ያረገኛል"
"እጠላዋለሁ!!"
እያለች ስትጓዝ ሳታስበዉ የትምህርት ቤቷ በር አካባቢ ደርሳ ፍቃዱ ፊት ለፊቷ ቆሞ አስቆማት።
"ሀይ ቤዚ"
ፍቃዱ ድምፁን እያስለመለመ እጁን ዘረጋ
"ደህና"
በግዴለሽነት እጇን ዘረጋችለት።
ከትምህርት ቤቱ መግቢያ ካለዉ ከስፓልት መንገድ
ባል መኪናዉን በፍጥነት እየነዳ
ከባለቤቱ ጋር ይጨቃጨቃል
እስዋ መሳደብ ጀምራለች እሱ መለመን እና ማባበል
ስላልሆነለት እና እየሰማችዉ ስላልሆነ በብስጭት
ስራዉም እንዳይረፍድበት እየተናደደ
የመኪናዉን መሪ ይዘዉራል።
ፍፁም በርቀት የትምህርት ቤቱን ግቢ እያየ
ቤዛዊት ናፍቃዉ በምን ቃል እዉነቱን እንደሚያስረዳት
እያሰበ ይራመዳል
በድንገት ባየዉ ነገር ደነገጠ ቤዛዊት ከጠላቱ ከከዳዉ
ወዳጁ ከሆነዉ ፍቃዱ ጋር ቆማ እያወራች ነዉ።
የልብ ምቱ ይሰማዋል
"ምን እየተፈጠረ ነዉ?"
አይምሮዉ ይጠይቃል በርቀት ያየዉን አላምን ስላለ
የለበሰዉ ሰፊ ቱታ ገላዉ ላይ በንፋስ እየተዉለበለበ
የተጫማዉን ነጠላ ጫማ ማንሳት እያቃተዉ
አስፓልቱን ማቋረጥ ጀመረ።
እየበረረ የሚመጣዉ በጭቅጭቅ የታጀበዉ
የባል እና ሚስት መኪና ከመኪናዉ የሞተር ጩህት
በላይ የእነሱ ቅጥ ያጣ ጩሀት እየተሰማ
ፍፁም በሚሻገርበት መንገድ እየከነፈ ነዉ።
የፍፁምን በሀሳብ በፍቅር በተንኮል
የሰከረ ደመ ነብስ ሊቀጥፍ
ጎማዉ መሽከርከሩን ቀጥሏዋል።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
....መጥፋቱን አስታወሰ
ህይወት ብዙ ሰወችን ታገናኘናለች የሚወዱን የምንወዳቸዉ
የሚጠሉን የምንጠላቸዉ
ይሄ ሁሌም ያለ እዉነት ነዉ ነገር ግን
ወዳጅ መስለዉ የቀረቡን ጠላቶቻችንን ማወቅ ይከብዳል
ለዚህም ነዉ አንዳንዴ የኔ ያልነዉ ሰዉ
ሳንጠብቀዉ ተለዉጦ ጋኔል ይሆንብናል
በተቃራኒዉም የጠላነዉ ሰዉ አልፎ አልፎ ስንቀርበዉ መልዓክ ይሆናል።
ፍፁምንም የገጠመዉ ይሄ ነዉ ፍቃዱን ቤቱ ያስገባበት ቀን
ዉስን ነዉ በጣት የሚቆጠር በጊዜዉ ዉስጡ ላይ የፍቃዱ ተንኮል ስላልታየዉ
ልብ ብሎ አልተከታተለዉም እንጂ ፍቃዱ የቤዛዊትን እና የፍቃዱን ፍቅር ያዉቅ ነበር
ፍፁም ስለቤዛዊት ሲጠይቀዉም ፍቃዱ የሚመልስለት
ስለ ቤዛዊት ህመም መጥፎ መጥፎዉን እንጂ ጥሩ እና መልካም ጎኗን ነግሮት አያዉቅም
ፍቃዱም በቤዛዊት ዉበት የቤዛዊትን አማላይ ሰዉነት
በፍትወት ሲመኛት አመታት አልፈዉታል
ለዚህም ነዉ የፍፁምን መልካም ጎን አይቶ እሱ በክፋት ተጠቅሞበት አሁን ሊያለያያቸዉ የበቃዉ።
ፍፁም ለሊቱን ሲብከነከን ማረግ ያለበትን ሲያስብ ሲጨነቅ አልፎ
የማይነጋ ለሊት የለም ነግቶ ከአልጋዉ ወርዶ
ለአለባበሱ ሳይጨነቅ ከላይ በተኛበት ቲሸርት ከስር የለበሰዉን
ሰፊ ቱታ ለብሶ ነጠላ ጫማ ተጫምቷ ወደ ቤዛዊት ቤት አመራ።
ቤዛዊት ሀዘኗ እንደጉም ትንን ብሎ በተለመደዉ ፈገግታዋ
እና ዉበቷ ደምቃ ለትምህርት ከቤቷ ቶሎ ወጥታለች
ፍፁም ቤቷ ደርሶ
በራቸዉን ለማንኳኳት አስቦ እያተጨነቀ በሩ ተከፍቶ እህቷ ወጣች።
"እንዴት አደርክ ፍፁም.."
የቤዛዊት እህት ፍፁምን ባላሰበችዉ ሰዓት ስላየችዉ
እየተገረመች እያየችዉ
"ቤዛዊት አለች"
አጭር ቃላት ከአፉ ወጡ
"ዉይ አሁን ወጣች ወደ ትምህርት ቤት.."
ሌላ የምታወራዉን አልሰማትም ፍፁም አንገቱን
መሬት ላይ አቀርቅሮ ወደ ትምህርት ቤቱ ወደሚወስደዉ
አቅጣጫ ተጓዘ እየተብከነከነ።
ቤዛዊት ወደ ትምህርት ቤት እያመራች ፍፁምን በልቧ
አስታዉሳዉ እንደ ጠላቷ እረገመችዉ
"እንዴት እንደዚህ ያረገኛል"
"እጠላዋለሁ!!"
እያለች ስትጓዝ ሳታስበዉ የትምህርት ቤቷ በር አካባቢ ደርሳ ፍቃዱ ፊት ለፊቷ ቆሞ አስቆማት።
"ሀይ ቤዚ"
ፍቃዱ ድምፁን እያስለመለመ እጁን ዘረጋ
"ደህና"
በግዴለሽነት እጇን ዘረጋችለት።
ከትምህርት ቤቱ መግቢያ ካለዉ ከስፓልት መንገድ
ባል መኪናዉን በፍጥነት እየነዳ
ከባለቤቱ ጋር ይጨቃጨቃል
እስዋ መሳደብ ጀምራለች እሱ መለመን እና ማባበል
ስላልሆነለት እና እየሰማችዉ ስላልሆነ በብስጭት
ስራዉም እንዳይረፍድበት እየተናደደ
የመኪናዉን መሪ ይዘዉራል።
ፍፁም በርቀት የትምህርት ቤቱን ግቢ እያየ
ቤዛዊት ናፍቃዉ በምን ቃል እዉነቱን እንደሚያስረዳት
እያሰበ ይራመዳል
በድንገት ባየዉ ነገር ደነገጠ ቤዛዊት ከጠላቱ ከከዳዉ
ወዳጁ ከሆነዉ ፍቃዱ ጋር ቆማ እያወራች ነዉ።
የልብ ምቱ ይሰማዋል
"ምን እየተፈጠረ ነዉ?"
አይምሮዉ ይጠይቃል በርቀት ያየዉን አላምን ስላለ
የለበሰዉ ሰፊ ቱታ ገላዉ ላይ በንፋስ እየተዉለበለበ
የተጫማዉን ነጠላ ጫማ ማንሳት እያቃተዉ
አስፓልቱን ማቋረጥ ጀመረ።
እየበረረ የሚመጣዉ በጭቅጭቅ የታጀበዉ
የባል እና ሚስት መኪና ከመኪናዉ የሞተር ጩህት
በላይ የእነሱ ቅጥ ያጣ ጩሀት እየተሰማ
ፍፁም በሚሻገርበት መንገድ እየከነፈ ነዉ።
የፍፁምን በሀሳብ በፍቅር በተንኮል
የሰከረ ደመ ነብስ ሊቀጥፍ
ጎማዉ መሽከርከሩን ቀጥሏዋል።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#የማሪያም #ንግስ #ዕለት
.
.
.
የማርያም ንግስለት
አዳፋ ነጠላ
በቀጠነ ገላ ÷ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ
ጥቁር ያዘን ቀሚስ ÷ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች ,,,,,,
ከቤተስኪያን አጸድ —ቆማ ከዋርካውስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት —,,,,,ትለማመንነበር
አደራሽ ን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶ ቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀረረባዬ በርዶታል ።
ወድቃ የተነሳች
እንባ ያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለምናት ነበር
ከቤተስኪያን ጓሮ ቆማ ከዋርካው ስር ።
*
የደብሩ አለቃ
ካ ባ ላንቃ ለብሶ ሞጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጬ ወደፊት ተስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክብሎ ያስተምራል ።
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደሞዝ ሊጨመር ይገባል
3
ደጀ ሰላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ,,,,
እናም ,,,
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እ ጃችሁ የታለ ?
እያለ ።,,,,
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል ።
ለንግሱ የመጡ
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች
ጥለት የለበሱ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ እፊት ተመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሰላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በ ሺ ሚቆጠሩ
ብሮች ወረወሩ
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ወዛ
የሚወረው ብሩም በጣም በዛ
*
የዛች የየምስኪን ነብስ
ያቺ ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኘኝም ማድጋዬ ጓድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬን በርዶታል
አንቺው ነሽ ተስፋዬ የኔ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ የተነሳች
እንባ ያፈሰሰች ።
ግና —ግን ለዛሬ —ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጅ አማሀዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የአንገት ሃብሌን፡፡
በኤፍሬም ስዩም
.
.
.
የማርያም ንግስለት
አዳፋ ነጠላ
በቀጠነ ገላ ÷ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ
ጥቁር ያዘን ቀሚስ ÷ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች ,,,,,,
ከቤተስኪያን አጸድ —ቆማ ከዋርካውስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት —,,,,,ትለማመንነበር
አደራሽ ን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶ ቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀረረባዬ በርዶታል ።
ወድቃ የተነሳች
እንባ ያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለምናት ነበር
ከቤተስኪያን ጓሮ ቆማ ከዋርካው ስር ።
*
የደብሩ አለቃ
ካ ባ ላንቃ ለብሶ ሞጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጬ ወደፊት ተስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክብሎ ያስተምራል ።
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደሞዝ ሊጨመር ይገባል
3
ደጀ ሰላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ,,,,
እናም ,,,
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እ ጃችሁ የታለ ?
እያለ ።,,,,
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል ።
ለንግሱ የመጡ
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች
ጥለት የለበሱ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ እፊት ተመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሰላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በ ሺ ሚቆጠሩ
ብሮች ወረወሩ
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ወዛ
የሚወረው ብሩም በጣም በዛ
*
የዛች የየምስኪን ነብስ
ያቺ ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኘኝም ማድጋዬ ጓድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬን በርዶታል
አንቺው ነሽ ተስፋዬ የኔ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ የተነሳች
እንባ ያፈሰሰች ።
ግና —ግን ለዛሬ —ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጅ አማሀዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የአንገት ሃብሌን፡፡
በኤፍሬም ስዩም
👍2
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በክፍለማርያም
... መሽከርከሩን ቀጥሏል
መኪናዉን አየዘወረ የነበረዉ የተናደደዉ ባል ወደ ሚስቱ ዞሮ
"ተይኝ.."
ብሎ ለአፍታ አንገቱን ወደ ፊት ለፊት ሲመልስ
መንገዱ ዉስጥ በቅርብ እርቀት
ሰዉ እየገባበት መሆኑን አስተዋለ
የመኪናዉን ማቆሚያ በድንጋጤ በሙሉ ሀይሉ እረገጠዉ መኪናዉ ለመቆም ሲታገል
ጎማወቹ ከአስፓልቱ ጋር ጥል ፈጥረዉ
የሚሰቀጥጥ ድምፅ አሰሙ።
"ሲ ጢ ጢጢ ጢጢጢ ጥ''
ፍፁም በደመ ነብስ እነ ቤዛዊትን እያየ
እየተራመደ ያልጠበቀዉ መኪና አጠገቡ ደርሶ የመኪናዉ የፊት አካል ሁለቱንም እግሮቹን
በሀይል መታቸዉ የእሱንም ሙሉ አካል በግፊት ተጎትቶት
ከሹፌሩ ትይዩ ካለዉ መስታወት ጋር ሲላተም ከግንባሩ የሚፈሰዉ ደም የተሰነጣጠቀዉ የመስታወት ቅርፅ
ይዘዉ መዉረድ ጀመሩ።
መኪናዉ ሙሉ ለሙሉ ሲቆም የፍፁም አካል ከመኪናዉ ኮፈን ተንሸራቶ መሬቱ ላይ ተዘረረ።
ፍፁም አሁን ደመነብሱም አይሰማዉም
ጆሮዉ ግንድ ላይ ሲሰማዉ የነበረዉ
"ጭ ዉዉዉዉዉዉ"
የሚል የሚመስል ድምፅ በሂደት ጥፍት አለ የሚያየዉም የሚሰማዉም ነገር በቀስታ ቆመ።
ቤዛዊት የመኪናዉን የግጭት ድምፅ ስትሰማ
አይኗን በእጇ ሸፍና ጥቂት ከቆየች በኃላ ላለማየት ፍቃዱን ጥላዉ ወደ ትምህርት ቤቱ መግቢያ በር አመራች
ብዛት ያላቸዉ ተማሪወች ግን ወሬዉን ለማየት ወደ መኪናዉ እየሮጡ ሄደዉ ከበቡት
"ፍፁም ነዉ
መምህር ፍፁም
ወይኔ ቲቸር"
ተማሪወቹ የተገጨዉን ሰዉ አይተዉ
ሀዘን የማይችሉት ሴት እና ወንዶች እያለቀሱ
ሌሎቹ በግርምት እና በድንጋጤ ሆነዉ ሁኔታዉን ያስተዉላሉ።
የገጪዉ ሚስት የቅድሙ ምላሷ አሁን ተጣጥፎ
የዋጠችዉ ይመስል የለም በፊት ሲከፈቱ የነበሩት አፎቿ
አሁን ተዘግተዉ በድንጋጤ ደርቀዉ አመድ መስለዋል
የእራሷ ጥፋት መሆኑ አሁን ገብቷት የባሏን ፊት ላለማየት በሀዘን ፈዛ ቀርታለች።
ባሏ መሪ ጨብጠዉ የነበሩት እጆቹ
የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዉ ይንቀጠቀጣሉ
ፖሊሶች ደርሰዉ የተሰበሰዉን ሰዉ እየበተኑ
ሹፊሩ ወደ ተዘረረዉ ፍፁም በቀስታ ተጠግቶ ቀኝ እጁን ወደ ገጨዉ ሰዉ አንገት ሰደደ
መሞት አለመሞቱን ለማረጋገጥ
ነገር ግን ምንም ነገር መስማት አልቻለም
"ተይኝ"
ያላት ቃል ብቻ ነዉ አይምሮዉ ላይ የሚያቃጭለዉ
በቆመበት ዝርግፍ ብሎ ተንበረከከ
ፊቱ ዶግ አመድ ሆኖዋል የሚፈስ እንባም የለዉም
ነገር ግን ዉስጡ እየደማ ነዉ።
ቤዛዊት የተማሪዎቹን ወሬ በርቀት እንደሰማች
ፍፁም የሚለዉን ባለማመን ደግማ ለማረጋገጥ ተጠግታቸዉ ሰማች
"መምህር ፍፁም መኪና ገጭቶት ሳይሞት አይቀርም..."
አንድ ቀጫጫ ተማሪ ያወራል
ዉስን ተማሪወች እየሰሙት ነዉ ቤዛዊት ወደ ግቢዉ በር
እራሷን እየወቀሰች ልትወጣ ስትል
"ቁሚ መዉጣት አይቻልም"
የግቢዉ ጥበቃ ጮሀባት
አንገቷን አዙራ የደፈረሰ አይኗን አጉረጠረጠችበት
"አንቺ ነሽ እንዴ አትቆዪ እሺ"
ፈገግ እያለ ፈቀደላት በልቡ ካበደ ጋር ምን አሳበደኝ እያለ
ስለቤዛዊት የሚወራዉን ስለሰማ ፈርቷት።
አንቡላንስ ቆሞ የፍፁም የተዝለፈለፈ አካል ሊጫነ ሲል
ደረሰች ከበዉ የቆሙትን ሰወች ገፈታትራ እንዳታልፍ
ያስቆማትን ፖሊስ በጉልበት አምልጣ
የፍፁምን ፊት ለማየት ቻለች ከግንባሩ የፈሰሰዉ ደም
ፊቱ ላይ ደርቆ የምታየዉ ፍፁም ስላልመሰላት
ለመንካት እጇቿን ስትዘረጋ
ከአንቡላንሱ ጋር የመጡት ሰወች ፍፁምን በተንቀሳቃሽ
አልጋ ላይ ጭነዉ ወደ አንቡላንሱ ዉስጥ እየተቻኮሉ
በፍጥነት ከተዉት እነሱም ዉስጥ ገብተዉ
በሩን ቤዛዊት ፊት ላይ ዘግተዉት ወደ ሆስፒታል ከነፉ።
ቤዛዊት በፍጥነት የተፈተለከዉን አንቡላንስ ተከትላ
ወደፊት ተንደረደረች ፍፁም ልበሺ ያላት ረጅም ቀሚስ
አላስሮጥ ስላላት ለአፍታ ተናዳ ቆመች
ትክክል እያሰበች አደለም የፍፁም እንደዚህ መሆን ህመሟን አስነስቶታል
ከጀርባ ያለዉን የቀሚሷን ዚፕ በሀይል ገነጠችዉ
ረጅም ቀሚሷ መሬት ላይ ሙሉ ለሙሉ ከላይዋ ላይ ወልቆ
መሬቱ ላይ አረፈ።
በለበሰችዉ የዉስጥ ሱሪ ፍፁምን ይዞ የጠፋዉን መኪና
መከተል እያሰበች መሀል አስፓልቱን ይዛ መሮጥ ጀመረች
በአፍዋ የማይሰሙ
"ፍፁም ፍፁም"
የሚል እረጅም መነባንብ እያነበበች
ብዙ መንገድ ከሮጠች በኃላ ያልተከተለችዉ
የአንቡላንሱ አቅጣጫ ጠፋባት
የመኪኖች የጥሩንባ ድምፅ አቀወሳት
የሁሉም አላፊ አግዳሚ አይን ገላዋ ላይ ይነወልላል
በትዝብት ያወራል
"አበደች ስታሳዝን"
አዛኝ የመሰለ አሳባጅ ሰዉ ያወራል
ቤዛዊት የፍፁም ደም እረፍት ነሳት
ሁለቱን እጆቿን ጇሮወቿ ላይ ጭናቸዉ
በነፃነት መሀል መጮህ ጀመረች።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በክፍለማርያም
... መሽከርከሩን ቀጥሏል
መኪናዉን አየዘወረ የነበረዉ የተናደደዉ ባል ወደ ሚስቱ ዞሮ
"ተይኝ.."
ብሎ ለአፍታ አንገቱን ወደ ፊት ለፊት ሲመልስ
መንገዱ ዉስጥ በቅርብ እርቀት
ሰዉ እየገባበት መሆኑን አስተዋለ
የመኪናዉን ማቆሚያ በድንጋጤ በሙሉ ሀይሉ እረገጠዉ መኪናዉ ለመቆም ሲታገል
ጎማወቹ ከአስፓልቱ ጋር ጥል ፈጥረዉ
የሚሰቀጥጥ ድምፅ አሰሙ።
"ሲ ጢ ጢጢ ጢጢጢ ጥ''
ፍፁም በደመ ነብስ እነ ቤዛዊትን እያየ
እየተራመደ ያልጠበቀዉ መኪና አጠገቡ ደርሶ የመኪናዉ የፊት አካል ሁለቱንም እግሮቹን
በሀይል መታቸዉ የእሱንም ሙሉ አካል በግፊት ተጎትቶት
ከሹፌሩ ትይዩ ካለዉ መስታወት ጋር ሲላተም ከግንባሩ የሚፈሰዉ ደም የተሰነጣጠቀዉ የመስታወት ቅርፅ
ይዘዉ መዉረድ ጀመሩ።
መኪናዉ ሙሉ ለሙሉ ሲቆም የፍፁም አካል ከመኪናዉ ኮፈን ተንሸራቶ መሬቱ ላይ ተዘረረ።
ፍፁም አሁን ደመነብሱም አይሰማዉም
ጆሮዉ ግንድ ላይ ሲሰማዉ የነበረዉ
"ጭ ዉዉዉዉዉዉ"
የሚል የሚመስል ድምፅ በሂደት ጥፍት አለ የሚያየዉም የሚሰማዉም ነገር በቀስታ ቆመ።
ቤዛዊት የመኪናዉን የግጭት ድምፅ ስትሰማ
አይኗን በእጇ ሸፍና ጥቂት ከቆየች በኃላ ላለማየት ፍቃዱን ጥላዉ ወደ ትምህርት ቤቱ መግቢያ በር አመራች
ብዛት ያላቸዉ ተማሪወች ግን ወሬዉን ለማየት ወደ መኪናዉ እየሮጡ ሄደዉ ከበቡት
"ፍፁም ነዉ
መምህር ፍፁም
ወይኔ ቲቸር"
ተማሪወቹ የተገጨዉን ሰዉ አይተዉ
ሀዘን የማይችሉት ሴት እና ወንዶች እያለቀሱ
ሌሎቹ በግርምት እና በድንጋጤ ሆነዉ ሁኔታዉን ያስተዉላሉ።
የገጪዉ ሚስት የቅድሙ ምላሷ አሁን ተጣጥፎ
የዋጠችዉ ይመስል የለም በፊት ሲከፈቱ የነበሩት አፎቿ
አሁን ተዘግተዉ በድንጋጤ ደርቀዉ አመድ መስለዋል
የእራሷ ጥፋት መሆኑ አሁን ገብቷት የባሏን ፊት ላለማየት በሀዘን ፈዛ ቀርታለች።
ባሏ መሪ ጨብጠዉ የነበሩት እጆቹ
የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዉ ይንቀጠቀጣሉ
ፖሊሶች ደርሰዉ የተሰበሰዉን ሰዉ እየበተኑ
ሹፊሩ ወደ ተዘረረዉ ፍፁም በቀስታ ተጠግቶ ቀኝ እጁን ወደ ገጨዉ ሰዉ አንገት ሰደደ
መሞት አለመሞቱን ለማረጋገጥ
ነገር ግን ምንም ነገር መስማት አልቻለም
"ተይኝ"
ያላት ቃል ብቻ ነዉ አይምሮዉ ላይ የሚያቃጭለዉ
በቆመበት ዝርግፍ ብሎ ተንበረከከ
ፊቱ ዶግ አመድ ሆኖዋል የሚፈስ እንባም የለዉም
ነገር ግን ዉስጡ እየደማ ነዉ።
ቤዛዊት የተማሪዎቹን ወሬ በርቀት እንደሰማች
ፍፁም የሚለዉን ባለማመን ደግማ ለማረጋገጥ ተጠግታቸዉ ሰማች
"መምህር ፍፁም መኪና ገጭቶት ሳይሞት አይቀርም..."
አንድ ቀጫጫ ተማሪ ያወራል
ዉስን ተማሪወች እየሰሙት ነዉ ቤዛዊት ወደ ግቢዉ በር
እራሷን እየወቀሰች ልትወጣ ስትል
"ቁሚ መዉጣት አይቻልም"
የግቢዉ ጥበቃ ጮሀባት
አንገቷን አዙራ የደፈረሰ አይኗን አጉረጠረጠችበት
"አንቺ ነሽ እንዴ አትቆዪ እሺ"
ፈገግ እያለ ፈቀደላት በልቡ ካበደ ጋር ምን አሳበደኝ እያለ
ስለቤዛዊት የሚወራዉን ስለሰማ ፈርቷት።
አንቡላንስ ቆሞ የፍፁም የተዝለፈለፈ አካል ሊጫነ ሲል
ደረሰች ከበዉ የቆሙትን ሰወች ገፈታትራ እንዳታልፍ
ያስቆማትን ፖሊስ በጉልበት አምልጣ
የፍፁምን ፊት ለማየት ቻለች ከግንባሩ የፈሰሰዉ ደም
ፊቱ ላይ ደርቆ የምታየዉ ፍፁም ስላልመሰላት
ለመንካት እጇቿን ስትዘረጋ
ከአንቡላንሱ ጋር የመጡት ሰወች ፍፁምን በተንቀሳቃሽ
አልጋ ላይ ጭነዉ ወደ አንቡላንሱ ዉስጥ እየተቻኮሉ
በፍጥነት ከተዉት እነሱም ዉስጥ ገብተዉ
በሩን ቤዛዊት ፊት ላይ ዘግተዉት ወደ ሆስፒታል ከነፉ።
ቤዛዊት በፍጥነት የተፈተለከዉን አንቡላንስ ተከትላ
ወደፊት ተንደረደረች ፍፁም ልበሺ ያላት ረጅም ቀሚስ
አላስሮጥ ስላላት ለአፍታ ተናዳ ቆመች
ትክክል እያሰበች አደለም የፍፁም እንደዚህ መሆን ህመሟን አስነስቶታል
ከጀርባ ያለዉን የቀሚሷን ዚፕ በሀይል ገነጠችዉ
ረጅም ቀሚሷ መሬት ላይ ሙሉ ለሙሉ ከላይዋ ላይ ወልቆ
መሬቱ ላይ አረፈ።
በለበሰችዉ የዉስጥ ሱሪ ፍፁምን ይዞ የጠፋዉን መኪና
መከተል እያሰበች መሀል አስፓልቱን ይዛ መሮጥ ጀመረች
በአፍዋ የማይሰሙ
"ፍፁም ፍፁም"
የሚል እረጅም መነባንብ እያነበበች
ብዙ መንገድ ከሮጠች በኃላ ያልተከተለችዉ
የአንቡላንሱ አቅጣጫ ጠፋባት
የመኪኖች የጥሩንባ ድምፅ አቀወሳት
የሁሉም አላፊ አግዳሚ አይን ገላዋ ላይ ይነወልላል
በትዝብት ያወራል
"አበደች ስታሳዝን"
አዛኝ የመሰለ አሳባጅ ሰዉ ያወራል
ቤዛዊት የፍፁም ደም እረፍት ነሳት
ሁለቱን እጆቿን ጇሮወቿ ላይ ጭናቸዉ
በነፃነት መሀል መጮህ ጀመረች።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#የይቅርታ_ልክ ፩
#አንቺ፤
በፍቅር ገለሽኝ ገንዘሽ ቀብረሽኝ
አፈር አልብሰሽኝ ሔደሻል ትተሽኝ።
ነፍሴ ፤
በፈጣሪዋ ዘንድ
አትሙት ያላላት የተሰጣት ክብር
ዳግም ነፍስ ዘርታ
ሞትሽን ድል ነሳች ወጣች ከመቃብር፡፡
#እኔ፣
ከጥልቁ ጉድጓድ በነፃነት ወጣህ-
ያለሽበት ድረስ ልፈልግሽ መጣሁ፡፡
እኔ እንደአንቺ አይደለህ
ስለፍቅር ብዬ ይቅር ብዬሻለሁ፡፡
ልቤንም አፅድቼ
እጆቼን ዘርግቼ
እንደድሮ ላቅፍሽ መንገድ ጀምሬያለሁ፡፡
አደራ ፍቅርዬ
ደመ ነብስሽ ነግሮሽ
ድንገት ቀና ብለሽ ስትመለከቺ
ከርቀት ብታዪኝ ስመጣ ወደ አንቺ ፤
ሙት መንፈስ መስዬሽ እንዳ ደነግጪ
ይኸውልሽ ካላመንሽ ቆይ እጅሽን አምጪ
ደረቴ ሥር አርገሽ
የልብ አመታቴን ከልብሽ አድምጪ
መላው አካላቴን
ዳብሰሽ በጣቶችሽ ዳሰሽ አረጋግጪ፡፡
እኔው እራሴ ነኝ!
ያጠፋሁት ካለ
ለሠራሁት ስህተት ፍቅሬ ይቅር በይኝ
ይቅርታ ቢስ ከሆንሽ
በይ እንደለመድሽው ካሰኘሽ ግደዪኝ፡፡
እሞትልሻለሁ!
እንዳንቺ አይደለሁም በፈጣሪ አምናለሁ።
ሞትሽን ድል ነስቼ ዳግም እነሳለሁ።
ሺ ጊዜ ብትገዪኝ
እልፍ አዕላፍ ጊዜ ይቅር እልሻለሁ ፤
ምክንያቱም ፍቅሬ
በንፁህ ልቦና እኔ አፈቅርሻለሁ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#አንቺ፤
በፍቅር ገለሽኝ ገንዘሽ ቀብረሽኝ
አፈር አልብሰሽኝ ሔደሻል ትተሽኝ።
ነፍሴ ፤
በፈጣሪዋ ዘንድ
አትሙት ያላላት የተሰጣት ክብር
ዳግም ነፍስ ዘርታ
ሞትሽን ድል ነሳች ወጣች ከመቃብር፡፡
#እኔ፣
ከጥልቁ ጉድጓድ በነፃነት ወጣህ-
ያለሽበት ድረስ ልፈልግሽ መጣሁ፡፡
እኔ እንደአንቺ አይደለህ
ስለፍቅር ብዬ ይቅር ብዬሻለሁ፡፡
ልቤንም አፅድቼ
እጆቼን ዘርግቼ
እንደድሮ ላቅፍሽ መንገድ ጀምሬያለሁ፡፡
አደራ ፍቅርዬ
ደመ ነብስሽ ነግሮሽ
ድንገት ቀና ብለሽ ስትመለከቺ
ከርቀት ብታዪኝ ስመጣ ወደ አንቺ ፤
ሙት መንፈስ መስዬሽ እንዳ ደነግጪ
ይኸውልሽ ካላመንሽ ቆይ እጅሽን አምጪ
ደረቴ ሥር አርገሽ
የልብ አመታቴን ከልብሽ አድምጪ
መላው አካላቴን
ዳብሰሽ በጣቶችሽ ዳሰሽ አረጋግጪ፡፡
እኔው እራሴ ነኝ!
ያጠፋሁት ካለ
ለሠራሁት ስህተት ፍቅሬ ይቅር በይኝ
ይቅርታ ቢስ ከሆንሽ
በይ እንደለመድሽው ካሰኘሽ ግደዪኝ፡፡
እሞትልሻለሁ!
እንዳንቺ አይደለሁም በፈጣሪ አምናለሁ።
ሞትሽን ድል ነስቼ ዳግም እነሳለሁ።
ሺ ጊዜ ብትገዪኝ
እልፍ አዕላፍ ጊዜ ይቅር እልሻለሁ ፤
ምክንያቱም ፍቅሬ
በንፁህ ልቦና እኔ አፈቅርሻለሁ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...መጮህ ጀመረች
ቤዛዊት ከስር እርቃኗን ከላይ በለበሰችዉ ሹራብ ቆማ
እግሯን ንፋስ እያገኘዉ የላይኛዉ አካሏ ወበቅ ስለለቀቀባት
ሹራቧንም አሽቀንጥራ ወረወረችዉ
በጡት ማስያዣ እና በዉስጥ ሱሪዋ ብቻ ቀርታ።
አሁን ስለሚያዩዋት አይኖች አትጨነቅም
የሚጮሁት የመኪና ጡሩንባወችም ለጇሮዋ ትርጉም የላቸዉም
ያለችበት አይታወቃትም ሀሳቧ ወሰድ መለስ ይላል ለአፍታ በደም የተጨማለቀዉ ፍፁም ወድያዉ
የገጪዉ ሹፌር ፊት ይመላለሱባታል ነገር ግን ዉሳኔዋ እራሱ ለራሷ አይገባትም
"ሞተ !?"
ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ለራሷ ጠየቀች
ወደ ሰማይ አንገቷን ቀና አድርጋ እያየች አይኖቿ እንባ እያቀረሩ
"እኔን ጥሎ!!አረ የትም አባቱ ጥሎኝ አይሄድም የኔ ፍቅር"
ወደ ከበቧት መኪኖች እያየች ጥሎኝ አይሄድም ብላ ስታስብ
የፍፁም ፊት ለአፍታ በሀሳቧ ታያት እና
ክትክት ብላ መሳቅ ጀመረች
" ኪ ኪኪ ኪኪኪ ኪኪኪ ኪኪ ኪኪ ኪኪኪኪኪ ኪ"
ወድያዉ ሳቋን አቋርጣ ፈጠን ፈጠን እያለች ከመሀል መንገዱ ወጥታ ወደ ዳር ወጣች ጥግ ጥጉን
በአይኗ ማሰስ ጀመረች ምን እንደምትፈልግ ባታዉቅም።
ከመንገዱ ጠርዝ ከወደቁ ወረቀቶች ልጣጮች መሀል
ክብ የሚመስል ድንጋይ ላይ አረፈ
ሰዉ እንዳያያት ይመስል ዙርያዋን ገልመጥ እያረገች
ድንጋዩን በቀኝ እጇ አነሳችዉ
ልክ ድንጋዩ እንደያዘች የልብ ልብ ተሰማት
ፍፁምን የገጨዉ ሹፌር ትዝ ስላላት ወደ ተገጨበት ቦታ
ድንጋዩን ደረቷ ላይ አስደግፋ ይዛዉ
ብቻዋን የማይሰሙ የማይገቡ ቃላቶችን እያወራች መራመድ ቀጠለች።
ከሰአታት በኃላ ፍፁም አይኑን እንደገለጠ እራሱን ብዙ አልጋ ላይ ከተኙ ሰወች
ጋር እሱም ለብቻዉ አልጋ ላይ ተኝቶ ነበር ።
ግንባሩን ስላሳከከዉ ለማከክ እጁን ሲሰድ
የተለጠፈለትን የቁስል ፕላስተር ነካ ሊፈነዳ የሚደርስ የእራስ ምታት እና የሰዉነቱ አቅም ሁሉ ሙጥጥ ብሎ
ያለቀ የሚመስል ድካም እየተጫጫነዉ ።
ሀይለኛ ዉሀ ጥም ስለተሰማዉ ጉሮሮዉን ለማራስ ምራቁን ለመዋጥ ታገለ ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም
የቻለዉ ከወገቡ በእጁ ድጋፍ እንደምንም ታግሎ
አልጋዉ ላይ ባለበት መቀመጥ እንጂ
እግሩን ማንቀሳቀስ አልቻለም
እግሩን ለማየት ሞከረ ቀኝ እግሩ በነጭ ፋሻ ተጠቅልሏል
"ዉሀ ዉሀ ዉሀ"
የሚያስበዉ እሱን ብቻ ነዉ አቅራቢያዉ የተኙ የታመሙ ሰወች ይታዩታል በርቀት የሚያስታምሙ ሰወችን
አይቶ በደከመ ድምፅ ቢጣራም የሚሰማዉ እና ልብ ብሎ የሚያየዉ ስላጣ ተደላድሎ ተቀምጦ
እንዴት ለዚህ ደረጃ ሊደርስ እንደቻለ ማሰብ ጀመረ ።
ከልቡ ያልጠፋችዉ ቤዛዊትም ትዝ እያለችዉ ማስታወስ የቻለዉ መንገድ ሊያቆርጥ ሲል
መኪናዉ ሲመታዉ ብቻ ነዉ ።
"መሞት ለካ ሁሉን መርሳት ነዉ !" አለ በልቡ ከህመሙ በላይ ቤዛዊትን የተፈጠረዉ ሁሉ
ዉሸት መሆኑን አስረድቷት
አምናዉ ሲታረቁ እያሰበ ደስ እያለዉ።
የሆስፒታሉን ጣርያ በአይኑ እያየ በልቡ ግን ወደ ሰማይ እያየ
በመትረፉ
"ተመስጌን አምላኬ"
ሲል አመሰገነ።
ቤዛዊት መራመዷን ቀጥላለች ያሰበችዉን ቦታ ፍፁም የተገጨበትን የትምህርት ቤቷን አካባቢ
ብታልፈዉም ግን መጓዟን አላቆመችም
ስለ ፍፁም መሞት በራሷ ሀሳብ ደምድማ
ሲላትም በህይወት አለ እያለች
ከአይምሮዋ ጋር ሙግት ገጥማ እራሷ ጠይቃ እራሷ እየመለሰች የማያልቀዉን መንገድ ሲላት አዉራ መንገዱን ሲያሻት ተሻግራ ዉስጥ ለዉስጥ
መንገዷች ዉስጥ የምትፈልገዉን ባታዉቅም በአይኗ የሆነ ነገር እየፈለገች በእግሯ መጓዝ ቀጠለች።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...መጮህ ጀመረች
ቤዛዊት ከስር እርቃኗን ከላይ በለበሰችዉ ሹራብ ቆማ
እግሯን ንፋስ እያገኘዉ የላይኛዉ አካሏ ወበቅ ስለለቀቀባት
ሹራቧንም አሽቀንጥራ ወረወረችዉ
በጡት ማስያዣ እና በዉስጥ ሱሪዋ ብቻ ቀርታ።
አሁን ስለሚያዩዋት አይኖች አትጨነቅም
የሚጮሁት የመኪና ጡሩንባወችም ለጇሮዋ ትርጉም የላቸዉም
ያለችበት አይታወቃትም ሀሳቧ ወሰድ መለስ ይላል ለአፍታ በደም የተጨማለቀዉ ፍፁም ወድያዉ
የገጪዉ ሹፌር ፊት ይመላለሱባታል ነገር ግን ዉሳኔዋ እራሱ ለራሷ አይገባትም
"ሞተ !?"
ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ለራሷ ጠየቀች
ወደ ሰማይ አንገቷን ቀና አድርጋ እያየች አይኖቿ እንባ እያቀረሩ
"እኔን ጥሎ!!አረ የትም አባቱ ጥሎኝ አይሄድም የኔ ፍቅር"
ወደ ከበቧት መኪኖች እያየች ጥሎኝ አይሄድም ብላ ስታስብ
የፍፁም ፊት ለአፍታ በሀሳቧ ታያት እና
ክትክት ብላ መሳቅ ጀመረች
" ኪ ኪኪ ኪኪኪ ኪኪኪ ኪኪ ኪኪ ኪኪኪኪኪ ኪ"
ወድያዉ ሳቋን አቋርጣ ፈጠን ፈጠን እያለች ከመሀል መንገዱ ወጥታ ወደ ዳር ወጣች ጥግ ጥጉን
በአይኗ ማሰስ ጀመረች ምን እንደምትፈልግ ባታዉቅም።
ከመንገዱ ጠርዝ ከወደቁ ወረቀቶች ልጣጮች መሀል
ክብ የሚመስል ድንጋይ ላይ አረፈ
ሰዉ እንዳያያት ይመስል ዙርያዋን ገልመጥ እያረገች
ድንጋዩን በቀኝ እጇ አነሳችዉ
ልክ ድንጋዩ እንደያዘች የልብ ልብ ተሰማት
ፍፁምን የገጨዉ ሹፌር ትዝ ስላላት ወደ ተገጨበት ቦታ
ድንጋዩን ደረቷ ላይ አስደግፋ ይዛዉ
ብቻዋን የማይሰሙ የማይገቡ ቃላቶችን እያወራች መራመድ ቀጠለች።
ከሰአታት በኃላ ፍፁም አይኑን እንደገለጠ እራሱን ብዙ አልጋ ላይ ከተኙ ሰወች
ጋር እሱም ለብቻዉ አልጋ ላይ ተኝቶ ነበር ።
ግንባሩን ስላሳከከዉ ለማከክ እጁን ሲሰድ
የተለጠፈለትን የቁስል ፕላስተር ነካ ሊፈነዳ የሚደርስ የእራስ ምታት እና የሰዉነቱ አቅም ሁሉ ሙጥጥ ብሎ
ያለቀ የሚመስል ድካም እየተጫጫነዉ ።
ሀይለኛ ዉሀ ጥም ስለተሰማዉ ጉሮሮዉን ለማራስ ምራቁን ለመዋጥ ታገለ ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም
የቻለዉ ከወገቡ በእጁ ድጋፍ እንደምንም ታግሎ
አልጋዉ ላይ ባለበት መቀመጥ እንጂ
እግሩን ማንቀሳቀስ አልቻለም
እግሩን ለማየት ሞከረ ቀኝ እግሩ በነጭ ፋሻ ተጠቅልሏል
"ዉሀ ዉሀ ዉሀ"
የሚያስበዉ እሱን ብቻ ነዉ አቅራቢያዉ የተኙ የታመሙ ሰወች ይታዩታል በርቀት የሚያስታምሙ ሰወችን
አይቶ በደከመ ድምፅ ቢጣራም የሚሰማዉ እና ልብ ብሎ የሚያየዉ ስላጣ ተደላድሎ ተቀምጦ
እንዴት ለዚህ ደረጃ ሊደርስ እንደቻለ ማሰብ ጀመረ ።
ከልቡ ያልጠፋችዉ ቤዛዊትም ትዝ እያለችዉ ማስታወስ የቻለዉ መንገድ ሊያቆርጥ ሲል
መኪናዉ ሲመታዉ ብቻ ነዉ ።
"መሞት ለካ ሁሉን መርሳት ነዉ !" አለ በልቡ ከህመሙ በላይ ቤዛዊትን የተፈጠረዉ ሁሉ
ዉሸት መሆኑን አስረድቷት
አምናዉ ሲታረቁ እያሰበ ደስ እያለዉ።
የሆስፒታሉን ጣርያ በአይኑ እያየ በልቡ ግን ወደ ሰማይ እያየ
በመትረፉ
"ተመስጌን አምላኬ"
ሲል አመሰገነ።
ቤዛዊት መራመዷን ቀጥላለች ያሰበችዉን ቦታ ፍፁም የተገጨበትን የትምህርት ቤቷን አካባቢ
ብታልፈዉም ግን መጓዟን አላቆመችም
ስለ ፍፁም መሞት በራሷ ሀሳብ ደምድማ
ሲላትም በህይወት አለ እያለች
ከአይምሮዋ ጋር ሙግት ገጥማ እራሷ ጠይቃ እራሷ እየመለሰች የማያልቀዉን መንገድ ሲላት አዉራ መንገዱን ሲያሻት ተሻግራ ዉስጥ ለዉስጥ
መንገዷች ዉስጥ የምትፈልገዉን ባታዉቅም በአይኗ የሆነ ነገር እየፈለገች በእግሯ መጓዝ ቀጠለች።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ከሞት_በኋላ_ሕይወት
ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ያወቀ
ፈጣሪው ብቻ ነው ከፍጡራን የላቀ፡፡
ስው የማይደርስበት መንገዱም የራቀ
ፅንፍየለሽ ነው ጉዞው ምስጢሩ የረቀቀ፡፡
“ከሞት በኋላ ሕይወት
በዕውን አለ ወይ?” ብሎ የጠየቀ
ከጥልቁ ሕዋው ሥር
ምላሹን ለመስጠት ደፍሮ የጠለቀ ፤
እስከዛሬ ድረስ
ሲገባ ነው እንጂ አይታይ ሲወጣ፣
ምስጢሩን ለመግለፅ
አንድም ፍጡር የለም ተመልሶ የመጣ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ያወቀ
ፈጣሪው ብቻ ነው ከፍጡራን የላቀ፡፡
ስው የማይደርስበት መንገዱም የራቀ
ፅንፍየለሽ ነው ጉዞው ምስጢሩ የረቀቀ፡፡
“ከሞት በኋላ ሕይወት
በዕውን አለ ወይ?” ብሎ የጠየቀ
ከጥልቁ ሕዋው ሥር
ምላሹን ለመስጠት ደፍሮ የጠለቀ ፤
እስከዛሬ ድረስ
ሲገባ ነው እንጂ አይታይ ሲወጣ፣
ምስጢሩን ለመግለፅ
አንድም ፍጡር የለም ተመልሶ የመጣ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#በክፍለማርያም
በእግሯ መጓዝ ቀጠለች
በርቀት የትምህርት ቤት መግቢያ በር አናት ላይ ግማሽ ጨረቃ የሚመስል የትምህርት ቤቱ ስም የተፃፈበት
ታፔላ ስታይ ተስባ ቆመች።
ለማንበብ እየሞከረች አንገቷን ቀና አድርጋ ብዙ ቆየች ቃላቶች ስትዘል ስትሳሳት ለማስተካከል ተመልሳ ስትደግም
ሰዓታት ገደለች ጊዜዉ ወደ መምሸት እየተጠጋ ነዉ
ከቆመችበት ቦታ ሳትነቃነቅ ዙርያዋን ተመለከተች ።
ጉሊት የሚቸረችሩ ሴቶች ብቻ በመሀል አንድ ጠይም ወንድ ሳያያት በሀሳብ እየተራመደ አጠገቧ ሲደርስ
አይቷት እርቃኗን መሆኗን ሲያስተዉል ደንግጦ መስመር ቀይሮ ሲራመድ ማንበቧን ትታ ልጁን መከተል ጀመረች
"ፍፁም አ.ን.ተ ፍፁም ጠ.ብ.ቀኝ እንጂ !!"
ከጀርባዉ እየተከተለችዉን ያለችዉን ሴት ዞሮ አየት አርጓት በልቡ
"ከየት የመጣች እብድ ናት"
እያለ በኃላዉ ለሚመጣዉ አደጋ ለማምለጥ አይኑን እያጉረጠረጠ ፍጥነቱን ጨምሮ ከአይኗ ተሰወረ።
ብርድ ብርድ አላት የሰዉነቷ ቆዳወችዋ ተቆጥተዉ ሽፍታ መስለዉ ይታያሉ ሙቀት ፍለጋ እጇቿን አጣምራ
ጥጉዋን ይዛ ተቀመጠች
ብርሀን ቀስ በቀስ ለጨለማ ጊዜዉን እየለቀቀ ነዉ
ቤዛዊት ስሟን እራሱ የምታስታዉስ አትመስልም የመንገድ ጠርዝ ላይ ተቀምጣ የምታያቸዉ አላፊ አግዳሚ
ሰወች መሀል አንዳንድ ወንዶችን ስታይ ፍፁምን እየመሰሏት
"ፍፁም ..ፍፁም..."
እያለች ስትከተላቸዉ
እየፈሯት እርቀዋት ሲሄዱ ተመልሳ ቦታዋ ስትቀመጥ ቆየች።አንድ እጆቹን እያወናጨፈ የሚመጣ ወጣት ስታይ
በንዴት ጦፋ ተነስታ ቆመች
ልጁን ለማየት አንገቷን ቀና አድርጋ ልጁ እንዳያመልጣት እያየች መሬት ላይ ያስቀመጠችዉን ድንጋይ ለማንሳት
መሬቱን በዳበሳ ስታስስ ልጁ አልፏት ሊሄድ ስለሆነ
እጇ በዳበሳ ያገኘዉን እየበቀለ ያለ ሳር
ከመሬቱ በጉልበት ነጭታዉ እየሮጠች ወደ ልጁ ተጠጋች
"አንተ ነብሰ በላ ገደልከዉ አደል"
"ምን አ አ"
ልጁ ደንግጦ የሚለዉ ጠፍቶት ተንተባተበ
እንዳትፈነክተዉ አንገቱን ለመደበቅ ጭንቅላቱን ለመከላከል
በእጁ እየተከለለ አጮልቆ አያት እርቃኗን መሆኗ አስፈራዉ
"ፍፁምን ገጨህዉ እኔንም ግጨኝ"
የያዘችዉን ሳር በተነችበት
ድንጋይ የወረወረችበት መስሎት ፈረጠጠ።
ለመከተል አልሞከረችም ሳሩ ሲበተን ይሆን ልጁ ሲሮጥ ባላወቀችዉ ምክንያት መሳቅ ጀመረች።
"ኪኪ ኪ ኪ "
እማማ ስንቅነሽ ከጉሊት ለእራት መስርያ የሚሆን ሽንኩርት
ሊገዙ ሲወጡ እርቃኗን የትምህርት ቤት በር ጋር የቆመች ሴት አይተዉ
"በትምህርት አስደግመዉባት ነዉ"
እያሉ ለራሳቸዉ እያወሩ አዝነዉላት አልፈዋት ሄዱ
ጉዳያቸዉን ጨርሰዉ ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ
"ፍፁምን ገጨሀዉ እኔንም ግጨኝ"
ያለችዉን ሲሰሙ ሀዘን መላ ሰዉነታቸዉን ወረራቸዉ
ልብ ብለዉ አዮዋት እርቃኗን የሆነች
የምትናገረዉ የምታረገዉ ነገር ለሰዉ ስለማይገባ
እብድ ተባለች እንጂ ስትታይ
"አረ እብድም አትመስል"
አሉ የሰዉነቷን ሁኔታ እያዩ
"ልጄ"
እያሉ ተጠጉዋት
በአይኗ በደንብ አየቻቸዉ ፈርታቸዉ ይመስል
ሁለቱንም አይኖቿን አጠናግራ
እማማ ስንቅነሽ ነጠላቸዉን አዉልቀዉ ጠጋ ብለዉ
ሲያቀብሏት ፍርሀቷ በፈገግታ ተለወጠ
"ስትስቂ ደሞ እንዴት ቆንጆ ነሽ"
አሏት እማማ ስንቅነሽ ስትለብሰዉ ያሳየቻቸዉን
ያልጠበቁትን የደስታፊት አይተዉ
"አትጓዳኝም አይነዉሀዋ ያስታዉቃል"
አሉና እራት እንድትበላ በማሰብ
"ነይ"
ብለዉ እጇን እነደመያዝ ሲያረጉ እጃቸዉን ሳም አረገቻቸዉ
ቢያንስ ብርድዋን አቃለዉላታል
አሁንም የት እንደሚወስዷት ባታዉቅም
ሌላ ችግሯን ካቃለሉላት ብላ ይሁን
መልካቸዉ ወዳዉ ተከተለቻቸዉ።
ምግብ ሰጥተዋት በልታ ጨርሳ
"ዉጪ"
ማለት አስበዉ ግን አሁን ፅድቅ ሰርተዉ የሚኮነኑ ስለመሰላቸዉ "የዛሬን ትደር መሽቷል"አሉ ቀልባቸዉ አዝኖላት
ለሊት ሰካራሙ የእማማ ልጅ በመጠጥ ደንዝዞ እየተንገዳገደ በእንጨት የተሸነቆረዉን በር ታግሎ ከፍቶ
ሲገባ የደፈረሱ አይኖቹ ቤዛዊት ላይ ቀሩ
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#በክፍለማርያም
በእግሯ መጓዝ ቀጠለች
በርቀት የትምህርት ቤት መግቢያ በር አናት ላይ ግማሽ ጨረቃ የሚመስል የትምህርት ቤቱ ስም የተፃፈበት
ታፔላ ስታይ ተስባ ቆመች።
ለማንበብ እየሞከረች አንገቷን ቀና አድርጋ ብዙ ቆየች ቃላቶች ስትዘል ስትሳሳት ለማስተካከል ተመልሳ ስትደግም
ሰዓታት ገደለች ጊዜዉ ወደ መምሸት እየተጠጋ ነዉ
ከቆመችበት ቦታ ሳትነቃነቅ ዙርያዋን ተመለከተች ።
ጉሊት የሚቸረችሩ ሴቶች ብቻ በመሀል አንድ ጠይም ወንድ ሳያያት በሀሳብ እየተራመደ አጠገቧ ሲደርስ
አይቷት እርቃኗን መሆኗን ሲያስተዉል ደንግጦ መስመር ቀይሮ ሲራመድ ማንበቧን ትታ ልጁን መከተል ጀመረች
"ፍፁም አ.ን.ተ ፍፁም ጠ.ብ.ቀኝ እንጂ !!"
ከጀርባዉ እየተከተለችዉን ያለችዉን ሴት ዞሮ አየት አርጓት በልቡ
"ከየት የመጣች እብድ ናት"
እያለ በኃላዉ ለሚመጣዉ አደጋ ለማምለጥ አይኑን እያጉረጠረጠ ፍጥነቱን ጨምሮ ከአይኗ ተሰወረ።
ብርድ ብርድ አላት የሰዉነቷ ቆዳወችዋ ተቆጥተዉ ሽፍታ መስለዉ ይታያሉ ሙቀት ፍለጋ እጇቿን አጣምራ
ጥጉዋን ይዛ ተቀመጠች
ብርሀን ቀስ በቀስ ለጨለማ ጊዜዉን እየለቀቀ ነዉ
ቤዛዊት ስሟን እራሱ የምታስታዉስ አትመስልም የመንገድ ጠርዝ ላይ ተቀምጣ የምታያቸዉ አላፊ አግዳሚ
ሰወች መሀል አንዳንድ ወንዶችን ስታይ ፍፁምን እየመሰሏት
"ፍፁም ..ፍፁም..."
እያለች ስትከተላቸዉ
እየፈሯት እርቀዋት ሲሄዱ ተመልሳ ቦታዋ ስትቀመጥ ቆየች።አንድ እጆቹን እያወናጨፈ የሚመጣ ወጣት ስታይ
በንዴት ጦፋ ተነስታ ቆመች
ልጁን ለማየት አንገቷን ቀና አድርጋ ልጁ እንዳያመልጣት እያየች መሬት ላይ ያስቀመጠችዉን ድንጋይ ለማንሳት
መሬቱን በዳበሳ ስታስስ ልጁ አልፏት ሊሄድ ስለሆነ
እጇ በዳበሳ ያገኘዉን እየበቀለ ያለ ሳር
ከመሬቱ በጉልበት ነጭታዉ እየሮጠች ወደ ልጁ ተጠጋች
"አንተ ነብሰ በላ ገደልከዉ አደል"
"ምን አ አ"
ልጁ ደንግጦ የሚለዉ ጠፍቶት ተንተባተበ
እንዳትፈነክተዉ አንገቱን ለመደበቅ ጭንቅላቱን ለመከላከል
በእጁ እየተከለለ አጮልቆ አያት እርቃኗን መሆኗ አስፈራዉ
"ፍፁምን ገጨህዉ እኔንም ግጨኝ"
የያዘችዉን ሳር በተነችበት
ድንጋይ የወረወረችበት መስሎት ፈረጠጠ።
ለመከተል አልሞከረችም ሳሩ ሲበተን ይሆን ልጁ ሲሮጥ ባላወቀችዉ ምክንያት መሳቅ ጀመረች።
"ኪኪ ኪ ኪ "
እማማ ስንቅነሽ ከጉሊት ለእራት መስርያ የሚሆን ሽንኩርት
ሊገዙ ሲወጡ እርቃኗን የትምህርት ቤት በር ጋር የቆመች ሴት አይተዉ
"በትምህርት አስደግመዉባት ነዉ"
እያሉ ለራሳቸዉ እያወሩ አዝነዉላት አልፈዋት ሄዱ
ጉዳያቸዉን ጨርሰዉ ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ
"ፍፁምን ገጨሀዉ እኔንም ግጨኝ"
ያለችዉን ሲሰሙ ሀዘን መላ ሰዉነታቸዉን ወረራቸዉ
ልብ ብለዉ አዮዋት እርቃኗን የሆነች
የምትናገረዉ የምታረገዉ ነገር ለሰዉ ስለማይገባ
እብድ ተባለች እንጂ ስትታይ
"አረ እብድም አትመስል"
አሉ የሰዉነቷን ሁኔታ እያዩ
"ልጄ"
እያሉ ተጠጉዋት
በአይኗ በደንብ አየቻቸዉ ፈርታቸዉ ይመስል
ሁለቱንም አይኖቿን አጠናግራ
እማማ ስንቅነሽ ነጠላቸዉን አዉልቀዉ ጠጋ ብለዉ
ሲያቀብሏት ፍርሀቷ በፈገግታ ተለወጠ
"ስትስቂ ደሞ እንዴት ቆንጆ ነሽ"
አሏት እማማ ስንቅነሽ ስትለብሰዉ ያሳየቻቸዉን
ያልጠበቁትን የደስታፊት አይተዉ
"አትጓዳኝም አይነዉሀዋ ያስታዉቃል"
አሉና እራት እንድትበላ በማሰብ
"ነይ"
ብለዉ እጇን እነደመያዝ ሲያረጉ እጃቸዉን ሳም አረገቻቸዉ
ቢያንስ ብርድዋን አቃለዉላታል
አሁንም የት እንደሚወስዷት ባታዉቅም
ሌላ ችግሯን ካቃለሉላት ብላ ይሁን
መልካቸዉ ወዳዉ ተከተለቻቸዉ።
ምግብ ሰጥተዋት በልታ ጨርሳ
"ዉጪ"
ማለት አስበዉ ግን አሁን ፅድቅ ሰርተዉ የሚኮነኑ ስለመሰላቸዉ "የዛሬን ትደር መሽቷል"አሉ ቀልባቸዉ አዝኖላት
ለሊት ሰካራሙ የእማማ ልጅ በመጠጥ ደንዝዞ እየተንገዳገደ በእንጨት የተሸነቆረዉን በር ታግሎ ከፍቶ
ሲገባ የደፈረሱ አይኖቹ ቤዛዊት ላይ ቀሩ
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1