አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የትውልዱ_ድርሳን - 3

ቀረርቶው ጥላቻ ፣
ፉከራው ጭካኔ፣ ሽለላው ድንፋታ፤
መንፈሱ የታሰረ፣ አካሉ የተፈታ::
ልቦናን አስሮ፣ ለወስፋቱ ፈራጅ ፣
የገዛ ወንድሙን ፣ እንደሙክት አራጅ::
ፍቅሩ ያንዳፍታ፣
ህብረቱ ያንዳፍታ፣ የሳፋ ላይ ብቅል፤
መጽኛ ስር የነሳው ፣ መለምላሚያ ቅጠል፡፡

እድሩ የፈረሰ፣
አሟሟቱ ምጸት፣ መሾ ያነወረው ፤
በቁሙ የሞታ፣ ቀባሪ የቸገረው ፤
በጅምላ አሳቢ፣
በመንጋ ተዋጊ፣
የ'ራሱ ባላንጣ፣ ተስፋ የቆረጠ ፤
ሰብኣዊ ሚዛኑን፣ ለጎሳው የሸጠ፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

የካቲት፣ 2011፣ አዲስ አበባ፡፡
#የተከፈተ_በር

የቤታችን በሩ፣
ከፍተሽው እንደሄድሽ፣ ዛሬም አልተዘጋም
የነበረኝ የለም፣ ለቀማኛ አልሰጋም
እምቢ ካልሽ እምቢ ነው፣ ፅኑ ነው ያንች ቃል
እንደማትመለሽ፣ አእምሮየ ያውቃል።

ግን አልፈርድበትም፣ ልቤ ቢያመነታ
ምኞት በሞላው ቤት፣ እውቀት የለው ቦታ።
ተስፋ አይቆርጥም ደግሞ
ልቤ ህልሙን ያምናል
ይለኛል ደጋግሞ፣
“ትመለስ ይሆናል
ትመለስ ይሆናል
ትመለስ ይሆናል።”

እኔም በምላሹ፣ ልቤን ፊት ሳልሰጠው
እንዲህ እለዋለሁ፣ ተስፋ ላስቆርጠው
“ጠጠር ላይቀቀል፣ አልማዝ ላይከለስ
በደመና ራስጌ፣ ጎጆ ላይቀለስ
እኔም አልሻሻል፣ እሷም ኣትመለስ።

ሰማይ ሰም ይመስል፣ ሲንጠባጠብ ቀልጦ
የረር ፈልሶ ቢሸሽ፣ ቢከተል እንጦጦ
ባሕሮች ቢከስሙ፣ ምድር ብትናወጥ
እሷም አትመለስ፣ እኔም አልለወጥ።

በዙሪያየ ያለው ጸጋ ብዙ ነበር
ግና ክንፍ አብቅሎ
ፍቅርሽ ጥሎኝ ሲበር
ከኔ ጋር የቀረው
የተቆለፈ ልብ፣ የተከፈተ በር።

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰባት


#በክፍለማርያም

...የቤዛዊት አባት መሆናቸዉን እየተጠራጠረ።
ፍፁም እየተደናገጠ ፊቱን እንዳያዩት እየተሳቀቀ ወደ
መፀዳጃ ቤት ገብቶ ፊቱን ዉሀ አስነካዉ
ከዚህ በኃላ የሚፈጠረዉን የሱን እና የቤዛዊትን እጣ ፋንታ በአይነ ህሊናዉ እያሰበ።

ከማስተማሩ ሲታገድ የቤዛዊት አባት ተኩሰዉ ሲገሉት
ሲያይ በፍጥነት ፊቱን ድጋሜ ዉሀ አስነክቶት
የቤዛዊት አባት መሄድ አለመሄዳቸዉን
ለማረጋገጥ አንገቱን አጮልቆ ተመለከተ የሉም ሄደዋል።

እኔ እዚህ ማስተማሬን አዉቀዉ እንዳይሆን እያለ
ወደ መምህራን ማረፍያ ገብቶ ፍቃዱን ፈልጎ አገኘዉ።
"እሺ ፍቄ አብረዉክ የነበሩት ማናቸዉ"
የእጆቹን ጣቶች ያልበላዉን ፀጉሩን እንደማከክ እያረገ
"የቤዛዊት አባት ናቸዉ ስለልጃቸዉ ሁኔታ ለመጠየቅ ነዉ"
ቀለል አርጎ መለሰለት
የእፎይታ ተንፍሶ ለማስተማር ወደ ሌላ ክፍል አመራ።
ጊዜዉ እየገፋ ነዉ መስከረም አልፎ ለጥቅምት
ቦታዉን ለቋል ፍፁም እና ቤዛዊት በድብቅ
የፍፁም ቤት ዉስጥ ይገናኛሉ
አብረዉ የፍቅር ጊዜ ማሳለፍ ከጀመሩ ሰነባብተዋል
ስለ ቤዛዊት በፊት እንደሰማዉ እንደሰማዉ ወሬ
ምንም የአይምሮ ህመም አይታይባትም ጤነኛ ነበረች።

አንድ ቀን ፍፁም ከሌላ ሴት ተማሪ ጋር ቆሞ ስለ ትምህርት ጉዳይ እያወሩ ቤዛዊት አይታዉ
አዉርቶ ሲጨርስ የተጠቀለለ ወረቀት
ሰጥታዉ ሄደች።
ፍፁም ወረቀቱን ገልጦ አነበበዉ
"ከትምህርት በኃላ ቤትክ ቀስ ብለክ ና ስጦታ አለክ"
ደስ እያለዉ ወረቀቱን ኪሱ ከቶ ዛሬ ቤቱ ሲገባ
ምን አይነት አስደሳች የፍቅር ጊዜ እንደሚጠብቀዉ
አያሰበ ደስ አለዉ።
የቀኑ ትምህርት አልቆ ተማሪወች ወደ እየቤታቸዉ
መሄድ ጀምረዋል እሱም ቤዛዊት እንዳለችዉ
ትንሽ ስዓት ለመግደል አስቦ ወደ ላይብረሪ አመራ።
መንገድ ላይ ወደ ዉጪ በመዉጣት ላይ ያሉ ተማሪወች
ጮክ ብለዉ ያወራሉ
"ቤዛዊት"
የሚባል ስም ስለሰማ ከመሀል አንዱን ተማሪ ጠርቶ
"ምን ተፈጥሮ ነዉ"
አለዉ አንገቱን ከታች ወደ ላይ እየነቀነቀ
የጠየቀዉ ተማሪ እንደ ትወና እያረገዉ
እንዴት አይነት ድብድብ መሆኑን ለማሳወቅ እጆቹን እያወናጨፈ
"በለዉ ቲቸር ቤዛዊት እና ህሊና የሚገርም ፀብ ተጣሉ"
አለዉ በወኔ ድምፁን ከፍ አርጎ።
ፍፁም ማሰብ አቃተዉ ህሊና ቅድም ስለ ትምህርት
ሲያዋራት የነበረችዋ ልጅ ናት።
ወደ ቤቱ ሊደርስ ሲል አከራዩ ይዘዉ አስቆሙት
"አቶ ፍፁም እጮኛህ ምን ሆና ነዉ ብቻዋን የምታወራዉ
ዉስጥ ገብታለች ተጣልታችሁ ነዉ እንዴ "
አሉት ለማስታረቅ እንደ እናት እያዩት
አከራዩ ደርባባ የቤት እመቤት ናቸዉ ፊታቸዉ ደግነታቸዉን
እና አዛኝነታቸዉን ይናገራል ቤት ኪራይ እራሱ እሱ አስቦ ካልሰጣቸዉ ጠይቀዉት አያዉቁም
የዉሸት
"ትንሽ ተጋጭተን ነዉ "
እያለ ትላንት ኪሱ ውስጥ አስቀምጦት የነበረዉን
የቤት ኪራይ ብር ሰጥቷቸዉ ወደ ቤቱ አመራ።
ወደ ዉስጥ ሲዘልቅ አንጀት የሚያላዉስ የምግብ ሽታ
እየሸተተዉ ጠረጴዛው ላይ በሚስብ አቀራረብ
ምግብ ቀርቦ ከጎኑ ሁለት
ብርጭቆ ቀርቦ አንደኛዉ የተጋመሰ የተጠጣ ቢራ
በዉስጡ ይዞል እና የተደረደሩ የቢራ ጠርሙሶች ይታየዋል።
ቤዛዊት ስታየዉ አቅፋዉ ትንሽ ከቆየች በኃላ
እንዲቀመጥ ወንበር ሳበችለት ፍፁም ተቀምጦ
ለምን ተጣላሽ ሊላት አለና የምታረገዉን ነገር ሲያይ ደስ እንዲላት ዝምታን መረጠ።
ቤዛዊት ምግቡን በልተዉ ቢራዉን ጠጥተዉ ከጨረሱ በኃላ
አልጋ ላይ እንዲቀመጥ እና ልብሱን እንዲያወልቅ አዘዘችዉ
ማዉለቅ አልፈለገም ግራ የተጋባ ስሜት ውስጥ
ገብቷል አለማዉለቁን ስታይ ቀስ ብላ
በፍቅር እየተጠጋችዉ የሸሚዙን ቁልፍ ፈታታት
ሙሉ ለሙሉ ሸሚዙን አወለቀችዉ ቀጥላም
እስዋ የለበሰችዉን ቀሚስ አዉልቃ ፊቱ ቆመች።
ፍፁም ከጠጣዉ መጠጥ ጋ ተያይዞ አይኖቹ ፈዘዝ ብለዉ
ፊትዋን አየዉ አይኖቿ ደፍርሰዋል ፊትዋ ተለዋዉጧል
"ምን ሆንሽ ቤዚ"
አላት በለሰለሰ ድምፅ
ቤዛዊት የፍፁምን አይን እያየች የፊዝ ሳቅ ከሳቀች በኃላ ።
ከእሷ ይወጣል ብሎ በማያስበዉ ድምፅ
ጩሀቷን አቀለጠችዉ ...

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1👍1
ራሴን እያወኩ
የኔን ማንነት
ስንት አመትም ይዤው
እኔን በኔነት
ልመለከት ፈለኩ
ይዤ መስታዎት
ህይወት እንዳለኝ ሳውቅ
በሌላው ህይወት
አብሮኝ እንዳልኖረ እንዳላየሁት፡፡

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#የተፈታ_ትዳር

የኛ ነው ከምለው
የኔ ነው ብለሽኝ
አልማዝና ወርቁን
ብርና ነሃሱን ሁሉንም ወስደሻል
ተመልሰሽ ነይ
የኔ የማልለው
አንቺ ያፈራሽው እንባዬ ቀርቶሻል።

🔘ኤፍሬም ስዩም🔘
#ለልደቴ

እጣ ፈንታ
ባልመረጥሁት ዘመን፣ ባልመረጥኩት ቦታ
ጎዳና ላይ አውጥቶኝ
እንቅፋት በየርምጃው፣ ተለክቶ ተሰጥቶኝ
ሲሻኝ እየሸሸሁ፣ ሲሻኝ እየተዋጋሁ
እንቅፋቴን በባዶ እግሬ፣ እንደ እንቧይ እየለጋሁ
ሕምምን እየሸወድኩ፣ ሞትን እያዘናጋሁ።

መኖር ሳልጠላ
ግና ለመኖር ብዬ፤ የግብር እንጀራን ሳልበላ
አሜን የሚል ቃል ሳይወጣኝ
በጌቶች ፊት በፍርሃት፣ ጎንበስ ጎንበስ ሳያቃጣኝ
ነፃነቴን ከጥልቁ ሥር፣ እንደ ብርቅ አሳ አስግሬ

ያሻኝን ተናግሬ
ተጨብጭቦልኝ
አንዳንዴም ተወግሬ
ያለ አጀብ ያለጋሻ ጃግሬ
ባሻኝ እየገሰገስኩ
እንደ ወፍ በነፃነት፣ አገር ምድሩን እያዳረስኩ
በመረጥሁት ዛፍ ስር ተኝቼ
በጅሎች ካብ ስር ሸንቼ
እያወጋሁ፣ እየገጠምኩ፣ እያለመጥሁ፣ እያላገጥሁ
እንባዎቼን በቃል ምትሐት፣ ወደ ሣቅ እየለወጥሁ፡
እየጣልኩ እየወደቅሁ፤ እየማቀቅሁ እየደላኝ
እንሆ አርባ አመት ሞላኝ!

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ስምንት


#በክፍለማርያም

...ጩሀቷን አቀለጠችዉ
ፍፁም ያልጠበቀዉ እና ያላሰበዉ ነገር ስለተፈጠረ ዉሀ ሆኖ ቀረ እግሮቹ መንቀጥቀጥ ጀምረዋል
የቤዛዊት መታመም አሁን ሁሉ ነገር ግልፅ ሆነለት
ነገር ግን ከረፈደ በኃላ ነዉ ምንም ማረግ አልቻለም።

በተቀመጠበት አልጋ የቤዛዊት ጩሀት ጆሮዉ ላይ ያስተጋባል
ጭ ዉ የሚል ስሜት ጆሮዉን አልፎ አይምሮዉ
ዉስጥ ያለማቋረጥ ይዞራል።
"ደፈረኝ"
የሚሉ ቃላት ከጩሀቱ ገዝፈዉ ይሰሙታል ነገር ግን
ከአልጋዉ ተነስቶ እንኳን ለመቆም አቅም አጣ።

የቤዛዊትን ጩሀት የሰሙ የፍፁም አከራዮች ከነሱ አልፎ
የሰፈሩ ነዋሪወች ጠባቡን የፍፁምን ቤት
በርግደዉ ሲገቡ ጩሀቱን የሰሙ በአቅራቢያዉ የነበሩ
የፖሊስ አባሎችም ተከታትለዉ ገቡ።

ቤዛዊት በፍጥነት ልብሷን ለባብሳ የፍፁም ቤት አከራይ
ሴትዮ ላይ ተጠመጠመችባቸዉ።
ፍፁምን የተከራየበት አካባቢ የነበሩ ወጣቶች እንደ በ'ዳይ በጥያቄ እያዋከቡት ነዉ።

ከፓሊሶቹ አንዱ
"ልብስ ደርብ እና ለጥያቄ ጣብያ እንሄድ"
ስላለዉ ፍፁም በሀፍረት እና በድንጋጤ አጠገቡ
ወልቆ የተቀመጠዉን ሸሚዙን እየለበሰ ቤዛዊትን ለመፈለግ አይኖቹን ቤቱ ዉስጥ ወሬ ለማድመቅ የቆሙትን
ሰወች ማየት ጀመረ የሁሉም ሰዉ ፊት እሱን በንቀት አስተያየት እያዩት ነዉ አከራዩም ሳይቀሩ
ተለወጡበት እየገላመጡት ነዉ።

ቤዛዊት ግን ከሰወቹ መሀል የለችም በግርግሩ ወሀል ወጥታ ሄዳለች።
ፍፁም በምሽት ፖሊስ ጣብያ አግዳሚ ላይ ቁጭ ብሎ
ማሰብ ተስኖት ትካዜ ዉስጥ ገብቶ የመርማሪዉ ፖሊስ ድምፅ አባነነዉ።

ለመርማሪዉ የተጠየቀዉን ሀሉ መመለስ ጀመረ ወደ መጨረሻ ለተጠየቀዉ መልስ ቤዛዊት ፍቅረኛዉ እንደሆነች
እና በጊዜያዊ ፀብ ከሌላ ሴት ጋ አይታዉ በስህተት ተርጉማዉ እንደተጋጩ አርጎ ነግሯቸዉ ከሳሽ ከመጣ
ብለዉ እዛዉ አሳድረዉት በነጋታዉ ከረፋፈደ በኃላ ለቀቁት።

ከፖሊስ ጣብያዉ እንደወጣ በተስፋ መቁረጥ ዉስጥ ሆኖ ቤዛዊትን እየረገማት እንባ እየተናነቀዉ ላለማልቀስ
ከራሱ ጋር እየታገለ ከተከራየበት ቤት ደረሰ።
ገና የግቢዉን በር ሲገባ በፊት በፈገግታ እና በፍቅር የሚያዩት አከራዩ እሳት ጎርሰዉ እና ተኮሳትረዉ ጠበቁት
"ዛሬዉኑ ቤቴን ለቀህ እንድትወጣ"
ፍፁም ንፁህነቱን ሊያወራ ሲሞክር ጉሮሮዉ ደረቀበት
ቃላቶች ከአፉ ማዉጣት አቃተዉ

"እ እ ማዘር..."

"ምንም ወሬ አልፈልግም ዉልቅ በል"
ሁለት ቦታ የታጠፈ ወረቀት በእጁ እየሰጡት ።

ወደ ቤታቸዉ
"እንዲህ ነችና"እያሉ ገቡ።
ቤቱ ክፍት አድሮ ነዉ የዋለዉ እንደዛ የተስተካከለ እና
ዉበት ያለዉ ቤት ምንቅርቅሩ ወጥቷል በቆመበት እጁ ላይ
ያለዉ ወረቀት የማን እንደሆነና ምን እንደሚል ለማንበብ ገለጠዉ።
የቤዛዊት እጅ ፅሁፍ ነዉ እስዋ ናት በወረቀት አየፃፈች መስጠት ያስለመደችዉ ገና ሳያነበዉ እንባዉ ወረቀቱ ላይ ዱ ብ ዱብ ማለት ጀመረ አይኖቹ በእንባዉ ጭጋግ
ስለተሸፈኑ ማንበብ አልቻለም።
ቤዛዊትን ከልቡ ወዷት ነበር "ፍቅር ይሄ ነዉ" እያለ
ለራሱ የማይመልሰዉ ጥያቄ እየጠየቀ እንባዉን
በቀኝ እጁ እየጠረገ ወረቀቱን ድጋሜ አየዉ።
"ፍፁም ምን እንደሆንኩ...ምን እንዳረኩ አላዉቅም..
ማጥፋቴ ጠዋት ነዉ የገባኝ
እወድሃለሁ
ይቅርታ አርግልኝ
አንተን አጥቼ ግን መኖር አልችልም እራሴን አጠፋለሁ"
እየቀለደችበት መሰለዉ ስለሚያማት ይሆናልም ብሎ አሰበ
ነገር ግን ንዴቱ ስለበለጠበት ወረቀቱን ቅድድድ አርጎ መሬት ላይ ወርዉሮት ሌላ ቤት ለመፈለግ ቤቱ እንኳን
ሳይዘጋ ወደ ደጅ ወጣ።
ደላሎች ወደ ሚቆሙበት መንገድ እየተጎዘ
በሀሳብ ብቻዉን እያሰበ ሲጎዝ ከጀርባዉ
የሆነ ነገር ዉርር አረገዉ እየተጫጫነዉ ዞረ
ቤዛዊት ነጭ የሀበሻ ቀሚስ ለብሳ
በእጇ ቀይ አበባ ይዛ እየተከተለችዉ ነበር.....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍4
#ጥሬ_ጨው

መስለውኝ ነበረ ፥
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች፥
ለካ እነሱ ናቸው፥
ጥሬ ጨው...... ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች፥
መፈጨት - መሰለቅ - መደለዝ-መወቀጥ
መታሸት-መቀየጥ
ገና የሚቀራቸው፤
'እኔ የለሁበትም!'
ዘወትር ቋንቋቸው።

🔘ደበበ ሰይፉ🔘
👍1
#ሀዘንን_በደስታ

ማልቀሴ ቢረዝም
መቋጫው ቢጠፋኝ
ማልቀስና መሳቅ
ማልቀስ ቢሆንብኝ
ራሴን ጠየኩኝ
ለቅሶዬን በሳቅ መልክ
አርጎ እንዲቆጥርልኝ
ሜዳ ነው ገደሉ
ከዛማ ይሻለኛል
በቀሪው ዘመኔም
ደስታ ይሰጠኛል
ውስጤ ያልቅስ እንጂ
እኔ ምን ገዶኛል፡፡
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
Forwarded from አትሮኖስ via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ዘጠኝ


#በክፍለማርያም

...አበባ ይዛ እየተከተለችዉ ነበር
ፍፁም ገና እንዳያት እንደ ሁል ጊዜዉ ዝም ሊላት አቅም ስላጣ።

"ምን ፈልገሽ መጣሽ!!"

ሲል እየጮሀ ፊት ለፊትዋ ቆመ
ግንባሩ ላይ ያሉት የደም ስሮች ፊቱ ላይ ገዝፈዉ ይታያሉ
በጥፊ መምታት አስቦ እጃቹን ካወራጨ በኃላ ፊትዋ ላይ ያለዉ የልመና አስተያየት
ከእንባዋ ጋ ተጨምሮ አላረገዉም የዘረጋዉን እጅ ኪሱ ዉስጥ ከቶ
"እባክሽ ተይኝ ልለምንሽ ተይኝ"
ድምፁ ሳይታወቀዉ ጮክ ብሎ ስለነበር
መንገዱ ላይ የሚያልፋ የሚያገድመዉ እየዞረ ሲያዩዋቸዉ
ቤዛዊትን በቆመችበት ጥሏት ሄደ።
ፍፁም አሁን ስለቤዛዊት ላለማሰብ እና ላለማስታወስ እየታገለ
አነስተኛ መኪና እቃዉን የሚጭንበት አናግሮ
አዲስ ደላላዉ ወዳገኘለት ቤት ለመግባት
እቃዉን ማስተካከል ጀመረ።
ቤዛዊት አበባዉን እንደያዘች እያለቀሰች ወደ ቤቷ ገባች ቤትዋ ዉስጥ ወደ ሳሎን እንደገባች እናትዋ እና እህቷ
ተቀምጠዉ ጠበቋት።

"ምን ሆንሽ ልጄ"

እያሉ በልጃቸው የማይጨክን እናትዋ ሮጠዉ ፊትዋን ለመደባበስ ሲሞክሩ
"እንዳትነኪኝ እንደዉም እሞትላችሁዋለሁ"
እያለች ወደ መኝታ ክፍሎ እየሮጠች ሄደች።

እናትዋ ቤዛዊት እንደዚህ አይነት ቃላት ሲያማት ሲያማት ስለምትናገር ብዙም አልተደናገጡም ግን የዛሬዉ
የተለየ የመሰላቸዉ አበባ በእጇ ይዛ ስላዩ ተጨንቀዉ ተከትለዋት እሮጡ

"ልጄ ልግባ?"

አሏት ሆዳቸዉ ስፍስፍ እያለ

"ማንንም ማናገር አልፈልግም"

አለች ቤዛዊት እያለቀሰች ስለሆነ ሳግዋ እየተናነቃት
በመሀል ታላቅ እህቷ እናታቸዉን ቀነስ ባለ ድምፅ
"እኔ አዋራታለሁ እማ አንቺ አትጨነቂ"
ብላ የቤዛዊትን የመኝታ ቤት በር ከፍታ ገባች
መልሳ ዘግታዉ በዝግታ ትራስ ታቅፋ
የምታለቅሰዉ እህቷ ጎን ተቀመጠች።

"ቤዚ ምን ሆነሽ ነዉ"

ዝም አለቻት

"ንገሪኝ እኔ እህትሽ አደለሁ ምንም ይሁን እረዳሻለሁ"

"ለነ አባቢ" አትናገሪም እያለች ቀና አለች
"አዎ ቃል እገባለሁ ማልቀስ አሁን አቁሚና ንገሪኝ"
አለቻት በእጇ እየደባበሰቻት።
ቤዛዊት አንድ ሳታስቀር እዉነቱን ነገረቻት ፍፁምን እንደምትወደዉ
አስተማሪዋ እንደሆነ ሌላዉ ደሞ በፊት ስትክደዉ የነበረዉ
እንደሚያማት እርግጠኛ እንደሆነች እና
ፍፁምንም እንዳስከፋችዉ አንድ ሳታስቀር ሁሉንም ነገረቻት።

እህቷም ቀለል አርጋ
"በቃ ለዚህ ነዉ ዋናዉ አንቻ ጥፋትሽን ማመንሽ ነዉ
ስለ ህመምሽ ደሞ አትጨነቂ ህክምና ታገኛለሽ
ትድኛለሽ ማሰብ የለብሽም ፍፁምን ደሞ ነገ ትምህር ቤታችሁ ሄጄ አዋራዋለሁ"
አለቻት
ቤዛዊት አይሆንም አሁኑኑ አዋሪዉ ተናዶብኛል ይጠላኛል
ብላ ስላስቸገረቻት የቤቱን አድራሻ ተቀብላ
ፍፁምን ለማዋራት ታላቅ እህቷ ወጣች።

በሰወች ጥቆማ የፍፁምን ግቢ አገኘችዉ
በሩጋ እቃ የተጫነበት መኪና ቆሞል ወደ ሹፌሩ ጠጋ ብላ
"ፍፁም የሚባል ሰዉ ታዉቃለህ"
እያለችዉ
ፍፁም እራሱ ፍራሹን ተሸክሞ መኪናዉ ላይ ከጫነዉ በኋላ

"እኔ ነኝ"

አላት በጥርጣሬ ማን ናት ምን ፈልጋ ነዉ እያለ
"ይቅርታ አታዉቀኝም ትርሲት እባላለሁ"
እጇን ዘረጋችለት
ፍፁም እያለ የዘረጋችለትን እጇች ጨበጣቸዉ
"ማዉራት ትችላለህ ቁጭ ብለን?"
ጠየቀችዉ
አንዴ ወደ መኪናዉ አንዴ ቤት ዉስጥ ስለቀሩት እቃወች እያሰበ
"እዚሁ ማዉራት አንችልም"
አላት ያለበት ሁኔታ ተቀምጦ ለማዉረራት እንደማይመች
በአይኑ እያሳያት
"እሺ የቤዛዊት እህትነኝ ስለሷ ላዋራክ ነበር"
ፍፁም የቤዛዊት ስም ሲነሳ ፍቅሩ አገረሸበት
ቅድም ያለችዉን ሲያስታዉስ ደንግጦ

"ምን ሆነች"

አላት ሰፍ ብሎ ትርሲት የእህቷን ስም ስትነግረዉ ባየችዉ ነገር
ይወዳታል ያስብላታል እያለች ነበር ስልኳ ሲጠራም ልብ አላለችም
"ተረጋጋ ምንም አልሆነችም ይቅርታ ስልኩን ላንሳዉ ማዘር ናት" ብላ የስልኩን ማንሻ ጫር አድርጋ ወደ ጆሮዋ አሰጠጋችዉ
እናትዋ እየጮሁ እያለቀሱ ነዉ
ስልኩን ይዛ መንቀጥቀጥ ጀመረች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#ዘመን

ቀን ምን አግቦቶት
ይነጋል ይመሻል፣
በወራጅ ጅረት
ይጠባል ያረጃል፣
ባህሪውንስ መች...
ቀይሮ ያውቃል?፣

ትውልድ ነው....
ዕለት እየቆጠረ....
ሲያሻው እያቀላ
ሲለው እያጠቆረ፣
በፈፀመው ነገር
አንድም እያሳመረ፣
........አንድም እያሳከረ፣
በድርጊቱ ሁነት
ዘመን የቀየረ!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
#አይገርምም ???

ዓለም ቅብዝብዟ ማፍቀርን ብታውቅም
ከልቧ የከረመ አንድም ሰው አይገኝም
ለህያው ፍጡር ለሰው ክብር ነስታ
ኪሱን ተመልክታ .
ቀበቶ አስፈትታ
ምንተ እፍረቱን አዛ ምንተ እፍረቷን ሰጥታ
ከምንተ እፍረት ከታ
ጊዜያዊ ወዳጇን ውስጧ አስገብታ
ከውስጧ አስወጥታ
ሜዳ ትጥላለች ባዶ አስቀርታ
የተሻለ አግኝታ
አይገርምም ... ???

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስር


#በክፍለማርያም

...መንቀጥቀጥ ጀመረች
ወድያዉ ስልኳን ወደ ቦርሳዋ በድንጋጤ እየከተተች
"ቤዛዊት ስለሚያማት ነዉ ተረዳት ደሞም ትወድሀለች"
ድምፅዋም በፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ነዉ።

ፍፁም የፊትዋን መለዋወጥ አይቶ
"ምን ሰምተሽ ነዉ?"
አላት ለአመል የመስማትም ያለመስማትም ፍላጎት አጥቶ
"ምን እንደተፈጠረ አላወኩም ግን ቤዛዊት ሆስፒታል ናት
እኔም መሄድ አለብኝ በቅርቡ ተገናኝተን ግን ማዉራት አለብን"
ብላዉ የሱን መልስ ሳትጠብቅ
ጥላዉ ወደ እህቷ መሮጥ ጀመረች
ፍፁምን በቆመበት ሳትሰናበተዉ።

(ቀደምት ታሪክ)
ቤዛዊት እህቷ አዋርታት ፍፁምን ልታናግርላት ስትወጣ
እራስዋን ስላመማት ህመሙን ቀለል እንዲያረግላት
መድሀኒት ዉጣ አልጋዋ ላይ ትራሷን አቅፋ በጎኗ አረፍ አለች።

ደግማ ደጋግማ ስለፍፁም ታስባለች
ልቧ ለሁለት ተከፍሎ ፍፁም እኔን ይቅርታ ያረግልኛል
ብላ ታስባለች በተቃራኒዉ አንቺ ጤነኛ ሰዉ አደለሽም
ፍፁም እብድ አይፈልግም ይላታል።

ህመሙ ግን ሊለቃት አልቻለም
በተኛችበት ሀሳቧ ፍፁምን ከሩቁ ሙሉ ሱፍ ለብሷ
አሳያት እየቀረበችዉ ስትመጣ ብቻዉን አደለም
ነጭ ቬሎ የለበሰች ሴት ታየቻት
የደበደበቻት ህሊና ናት።

ሀሳብዋን እዉነት አርጋ ተቀበለችዉ
በንዴት ግላ ከተኛችበት ቀና ብላ እግሮቿን መሬት
አስነካቻቸዉ አሁንም አይኗ ፍፁም እና ህሊና ላይ ነዉ
ዉስጧ አንቺን ትቶ ሌላ አገባ ይላታል

"እንዴት እያለች?"

እስዋ አፍዋን እያንቀሳቀሰች ታወራለች
"ግደይዉ!!"
ብሎ ሹክ አላት አንገራገረች
"አንቺን በሌላ ቀይሮሽማ አትዘኚለት ተነሽ ግደይዉ!!"
ደገመላት
በባዶ እግሯ ቆማ መራመድ ጀመረች
ታማለች እራሷን አደለችም ነገር ግን ለእሷ አይታወቃትም
የመኝታ ቤቷን በር ከፍታ ወደ ማዕድ ቤት
በደመነፍስ ተጓዘች ከመክተፍያ አጠገብ ያገኘችዉን
ስል ቢለዋ አንስታ ፊት ለፊትዋ የቆሙት ሙሽሮችን
ለመዉጋት እጇን ቀስ አርጋ ዘረጋች
ዉሸት አጥፊዉ ሁለቱንም ግደያቸዉ ይላታል
እዉነት ማረግ የለብሽም እያለ ሲሞግታት
በባዶ ሜዳ የዘረጋችዉን ቢለዋ የራሷ አንገት ላይ አሳረፈችዉ እጇን ማንቀሳቀስ ስትጀምር
ህመም እና የሚፈሳት ደም ተቀላቅሎ
የሲቃ ድምፅ አወጣች ድምፁን የሰሙት እናቷ እና
ሰራተኛቸዉ ማዕድ ቤት በፍጥነት ሲደርሱ
ቤዛዊት በደም እርሳለች ቢላ የያዘ እጇን ከአንገቷ
እየጮሁ ቢለዋዉን መነተፏት እስዋ አቅም እያነሳት ተዝለፍልፋ ወደቀች።

የቤዛዊት እናት አንፑላንስ ጠርተዉ
ልጃቸዉን ሆስፒታል አሰገብተዉ ትንሽ ሲረጋጉ
ድንጋጤ ሲለቃቸዉ ነገር ግን የቤዛዊትን የመጨረሻ
ዉጤት ስላልሰሙ አብራቸዉ ያለችዉ
ሰራተኛቸዉ እየጮኸች እሳቸዉ እያለቀሱ
ቅድምያ ለባለቤታቸዉ ቀጥለዉ ለእህቷ ደወሉ
ሆስፒታል ቶሎ እንዲመጡ።

ፍፁም አዲስ የተከራየዉ ቤት እቃወቹን እንደነገሩ
ካራገፈ በኃላ ልቡ እርብሽ ስላለበት በቆመበት ወለሉ ላይ
ቀስ ብሎ ቁጭ አለ።

እህቷ ሆስፒታል ያለችዉን ሲያስታዉስ
ቤዛዊት እንዳለችዉ እራሷን አጥፍታ ቢሆንስ እያለ
እያሰበ ያላሰበዉ እንባዉ ቀድሞት መፍሰስ ጀምሮ ነበር
"አይሆንም አታረጊዉም ይቅርታ አረግልሻለሁ"
ሊደዉልላት ሆስፒታል በሞት እና በህይወት መሀል
ወዳለችዉ ቤዛዊት ስልኩን ከኪሱ አወጣ።

💫ይቀጥላል💫


ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1
#በአንድ_ጎጆ_እንሁን

የነገን ገጠመኝ፥የዛሬን አናውቅም
በአንድ ጎጆ እንሁን፥በፍቅር እንሙቅም
ይመረግ ጎጇችን፥ክዳን እናልብሰው
እንጀራው ይጋገር፥ከሰው አንዋሰው።

🔘ተስፋ አማረ🔘
#አይኖቼ_ምንጭ_ሆኑ

አይኖቼ ምንጭ ሆኑ
በሚያዩበት ፈንታ፥በእንባ ተሸፈኑ
ብሶቴን ሊያወጡ፥አይኖቼ ምንጭ ሆኑ
አካሌ ቢጎዳ፥ቢሰብረው ሃዘኑ
እንፋሎቶች ወተው፥ከውስጤ ደመኑ
መዘነቢያ ሆኑአቻው፥አይኖቼ ምንጭ ሆኑ
በሚያዩበት ፈንታ፥በእንባ ተሸፈኑ
ብሶቴን ሊያወጡ፥አይኖቼ ምንጭ ሆኑ።

🔘ተስፋ አማረ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በክፍለማርያም

...ስልኩን አወጣ
ይጠራል ይጠራል ነገርግን የሚመልስለት የለም የቤዛዊት ድምፅ ለጆሮዉ ናፈቀዉ

"ሄሎ"

ስትል አንስታዉ የሚወጣዉ የአነጋገርዋ ለዛ
ይሰማዋል ነገርግን እዉነት አደለም
ከተቀመጠበት ተነስቶ መቁነጥነጥ ጀመረ

"ምን ሆና ይሆን"

የሚል ጥያቄ እረፍት ነሳዉ
መጨረሻ ሲያዋራት እራሴን አጠፋለሁ ያለችዉን ሲያስታዉስ
ትኩስ መርዶ እንደተነገረዉ እንባወቹን በባዶ ቤት ዉስጥ ዘራቸዉ
እያለቀሰ በሄደ ቁጥር መሞቷን ልቡ እያመነ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ።

"ወይኔ ቤዛ አ ሀ ሀ ወይኔ ወይኔ ቤዛ ገደልኩሽ ወይይይ
ስላልተረዳሁሽ እኮ ነዉ እኔ ነኝ ገዳይሽ ...."
ድምፁ ከሱ ክፍል አልፎ ጎረቤቱ ከሆኑት አዲሱ አከራዩ ሻንበል
ሰመረ ጋር ደርሶ ሳያንኮኩ ገብተዉ ማፅናናት ሲገባቸዉ አብረዉት
ማልቀስ ተያያዙ
ጥቂት እንባ ከተራጩ በሆላ ስልኩ ጮሀ
እያለቀሰ ስለነበር ቤዛዊት የሚለዉን ሲያነብ ወድያዉ ድምፁን ዉጦ እየተንቀጠቀጠ ዝም አለ
አከራዩ አቶ ሰመረ ግን በፍፁም ሀዘን ይሁን?
የሞተ ዘመዳቸዉን አስታዉሰዉ እያለቀሱ ነዉ።

"ሀ ሎ ቤ ዛ "አለ ተጠራጥሮ ማመን አቅቶት
"ፍፁም ቤዛ አደለሁም እህቷ ነኝ ስልኮ ላይ
ብዙ ምልክት ሳይ ነዉ የደወልኩልክ.."
"አ.ረ.ፈ.ች ይሄን ልትነግሪኝ ነዉ "እያለቀሰ ጠየቃት
"ሆስፒታል ናት እስካሁን አልነቃችም ተረጋጋ አንተም እንደዚህ አትሁን"
ፍፁም ይሄን እንደሰማ የሆስፒታሉን አድራሻ ጠይቋት
"መጣሁ መጣሁ "እያለ ስልኩን ዘጋዉ
አቶ ሰመረ በፊት በዉትድርና ያሳለፉ ቆፍጣና
ቢመስሉም ዉስጣቸዉ የዋህ እና ቡቡ ናቸዉ ፍፁም ስልኩን ዘግቶ ቤቱን በእርጋታ ሲያስተዉል
እሳቸዉ እየየ እያሉ ነዉ ሰዉ ሞቶበት የተረዳ መስሏቸዉ
ፍፁም ፈጠን ፈጠን እያለ
"ጋሼ መሄድ አለብኝ.."
ሲላቸዉ ድምፅ ሳይመልሱለት ወደ ቤታቸዉ ገብተዉ
ጃኬት ደርበዉ ለፍፁም አዲስ ያለበሱትን ጋቢ ከሳጥናቸዉ አዉጥተዉ ተመልሰዉ ወደሱ ቤት ሲገቡ ፍፁም
የዉሀ ሽታ ሆኗል።
ሆስፓታሉ ዉስጥ የቤዛዊት አባት
"ልጄን ቀጨሁዋት"
እያሉ ከወድያ ወዲህ ይንጎራደዳሉ ተናደዋል አዝነዋል
የእሳቸዉም ጤና ትክክል አደለም እናቷም ጥግ ላይ ካለዉ
ወንበር ኩርምተ ብለዉ ተቀምጠዉ ይብከነከናሉ
እህቷ እናት እና አባትን ለማረጋጋት
የእሷን ሀዘን ዋጥ አርጋ እንዲረጋጉ እየለመነቻቸዉ ነዉ።

በስንት ድካም እና ልመና ንፋስ እንዲቀበሉ በማሰብ ወደ ዉጪ
ወስዳቸዉ እንዲቀመጡ ካረገች በኃላ እስዋ
እህቷ የተኛችበት በር ጋር መንቆራጠጥ ጀመረች
ፈጣሪን እንዲምራት እየለመነች
ፍፁም ሆስፒታል ደርሶ የተኛችበትን ክፍል ጠይቆ
ፈጠን ፈጠን እያለ እየተራመደ
በፍርሀት ዉስጥ ሆኖ ሲደርስ የቤዛዊትን እህት አያት
ምንም አላዋራትም
"መግባት አይቻልም"
እያለችዉ ሳይሰማት ቤዛ የተኛችበትን ክፍል ከፍቶ ገባ።

ቤዛዊት አልጋዉ ላይ በጀርባዋ ተኝታለች አትንቀሳቀስም
ከአንገቷ በታች ብርድ ልብስ ስለለበሰ የሰዉነቷ ቅርፅ ብቻ
ነዉ የሚታየዉ አንገቷ በነጭ ፋሻ ተጠቅልሎ
ፊትዋን ማየት ስለከለለዉ እያለቀሰ
በአንድ እጁ ወገቡን በአንድ እጁ አፉን አፍኖ
ከራሱ ጋር አየታገለ ተጠጋት
ያ ዉበት ያለዉ ማራኪ ፊትዋ ጥዉልግ ብሏል ፈገግታዋ አይታይም ከንፈሮቿ ደርቀዋል አይኗ ተከድኖ
መኖሯን ተጠረጥሮ በጣም ቀረባት ...
ከኋላዉ

"ማነዉ እሱ?"

የሚል የቤዛዊት አባት ጎርናና ድምፅ ሊነካት የዘረጋዉን
እጅ እንዲሰበስበዉ አረገዉ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍42
#ኦና_ልቦች

ፍቅርን የሚቀበሉ
ባዶ ልቦች ሞልተው፥
ጎራ የሚሉ እንግዶች
የሚያንኳኩ ጠፍተው፣

ኦና ነው ቤታቸው
የሚገባ ጠፍቶ፣
ስንት ዘመን ሁሉ
ልባቸው ተከፍቶ !!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
#ጦርነት_ጨረሰው

በችግር ተበልቶ አጥንቱ ያገጠጠ፣
ገፅታው ደምኖ ወዙ የተመጠጠ ፣
ምስኪን ህዝብ እያለሽ በችግር የኖረ፣
መጠልያ አጥቶ ሜዳ የሰፈረ፣
ድህነት ሳይገለው-ማጣት ሳያጠፋው፣
ደጉን ወገንሽን -ጦርነት ጨረሰው፣

🔘አማኑኤል ብርሃኑ🔘
#በሸንጎ_ተጀንኘ

ፍቅሬን ብግልጥ፣ ባደባባይ
ደስታየን በድንጋይ ሰሌዳ ላይ
መናዘዜ
ቅሬታየን በደብዛዛ ርሳስ
መከራየን በለሆሳስ
ጭንቄን በምስጢር መያዜ
ካዘናጋሽ

አንድ ቁምነገር ላውጋሽ!
ተከፍቼ
ግና ፊቴ ላይ የብርሃን ዱቄት ነፍቼ
ምድር አትችለውን ችየ፣ ሆዴን ከጠረፍ አስፍቼ
ከሾህ አክሊሌ በላይ፣ ያልማዝ ዘውዴን ደፍቼ
በሸንጎ ተጀንኘ፣ በእልፍኜ ብስለመለም
ሕመምን አለማወጅ፣ አልታመምኩም ማለት አይደለም።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
👍1
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በክፍለማርያም

...የዘረጋዉን እጅ እንዲሰበስብ አደረገዉ
"አንተ ውርጋጥ ብለህ ብለህ እዚህ መጣህ!!"
የቤዛዊት አባት የደፈረሰ አይናቸዉን አጉረጠረጡበት
እህቷ እና እናትዋ ምን ይፈጠራል በማለት ደንግጠዉ እያዩዋቸዉ ነዉ።

ፍፁም ደፈር ብሎ
"ልጠይቃት ነዉ የመጣሁት"
አላቸዉ እንባ ካቀረሩት አይኖቹ የእንባ ዘለላወች እየወረዱ
ስለሆነ በቀኝ እጁ ለማበስ እየሞከረ
አባትዋ ግን በልጃቸዉ ድንገተኛ አደጋም ተደናግጠዉ ስለነበር
ፍፁምንም ልጃቸዉ የተኛችበት ክፍል ስላዩ ፍፁምን በንቀት አይን እያዩት የአንገቱን ኮሌታ አንቀዉ
እንዲወጣ መጎተት ጀመሩ።
ፍፁም እጃቸዉን ለማስለቀቅ ሲታገል

"ል.ቀ.ቀ.ዉ አ.ት.ንካ.ዉ"

የሚል የደከመ የቤዛዊት ድምፅ ተሰማ
ቤዛዊት ነቃች አንገቷን በትግል ትራሱ ላይ እያለ በቀስታ
አዙራዉ አይኖቾ ድክም ብለዉ በግድ ለመግለጥ እየሞከረች
አንዴ አባትዋን አንዴ ፍፁምን እያየች ነዉ ።
እህቷ እና እናትዋ በደስታ ሮጠዉ ከበቧት
የማያልቅ ፍቅር ያለቸዉ እናትዋ ስትነቃ የደስታ እንባ
እያነቡ ግንባሯን ስመዋት አቅፈዋት ቀሩ
እህቷ የቤዛዊትን ዝልፍልፍ ያለ እጅ ይዛለች
አባቷ የፍፁምን ኮሌታ ለቀዉ ዶክተር ሊጠሩ
"ተመስጌን"
እያሉ ወጡ መትረፏ እና ማዉራት በመጀመሯ ተደስተዉ።
የቤዛዊት እናት ልጃቸዉን አቅፈዉ ጥቂት ከቆዩ በኃላ ፍፁምን መለመን ጀመሩ
"ልጄ አለሜ ናት እኔ ብቻ ነኝ ስቃይዋ የሚገባኝ
አንተም የማትወዳት የማትሆናት ሰዉ ከሆንክ ከአሁኑ እራቃት"
እንባቸዉ እየወረደ ነዉ።
ፍፁም የቤዛዊትን ግርጥት ያለ ፊት እያየ ከልቡ እያሳዘነችዉ
እናቷ የሚሉትን ልብ ብሎ አልሰማቸዉም
ቤዛዊት ከቆንጅናዋም በላይ ዉብ ባህሪ አላት ግን ህመሟ ህይወቷን እና በዙርያዋ ያሉትን ሰወች እያስጨነቀ ነዉ።

"ልጄን አደራ የምትወዳት ከሆነ ግን ሁሉ ነገሯን አምነህ ተቀበል
መልኳን ወዶ ችግር እና ጥፋትዋን መጥላት መልካም አደለም"
እናቷ መናገር ቀጠሉ
ፍፁም አሁን ያወሩትን ግን ከልቡ ሰማቸዉ እራሱን ጠየቀ
ምኗን ነዉ የወደድኩት መልክ እና ዉበቷን?
አሁን አልጋ ላይ የተኛችዉን የፍቅረኛዉን የገረጣ ፊት እያየ
በሌላ በኩል ግልፅነቷ ደግነቷን መልካም አስተሳሰቧን
ሲያስብ ከዉበቷም አልፎ ዉስጧም አሸንፎታል
ህመሟንም አምኖ ተቀብሎ እስኪሻላት
ጤነኛ እስክትሆንም ባይሆን እንኩዋን ላይለያት በልቡ
እየማለ አልጋዉ ላይ ወደ ተኛችዉ ቤዛዊት ተጠጋ።

እረጃጅም ጣቶቹን ወደ ቤዛዊት ፀጉሮች ሰደዳቸዉ በቀስታ እያንቀሳቀሰ እራሷን እንደማከክ እያረገ
አይኑን ወደ አይኗ ላካቸዉ።
የቤዛዊት አይኖች አንዴ ክድን አንዴ ግልጥ እያረገች
በፍቅር እና በፀፀት እያየችዉ ነዉ
አፍዋ የሆነ ነገር ማዉራት ፈልጋ ሲንቀሳቀስ
የምትለዉን ለመስማት ጎንበስ ብሎ ጆሮዉን ወደሷ አፍ
ጠጋ አረገዉ።

"ይ.ቅ.ር.ታ አ.ረ.ክ.ል.ኝ"

በሚያሳዝን አንጀት በሚበላ ድምፅ ተናገረች
ፍፁም ማዉራት አልቻለም ላለማልቀስ እየታገለ ግንባሯን እየሳማት
"አርጌልሻለዉ አታስቢ ድነሽ ስትነሺ እናወራለን"
ድምፁን ቀስ አርጎ አወራት

"እ.ወ.ድ.ሀ.ለ.ሁ"

መናገር እያቃታት አይኖቿን እያንከራተተች።
"እኔም እወድሻለሁ"
አላት ክፍሉ ዉስጥ ያሉትን እናቷን እና እህቷን ሳይፈራ
በመሀል ቤዛዊት የተኛችበት ክፍል በር ተከፍቶ
አንድ ወጣት ዶክተር ገባ ተከትለዉት አባቷ እና የማያዉቀዉ የመሰለዉ ወንድ ወደ ውስጥ ገቡ።
ፍፁም ከቤዛዊት ላይ እጆቹን ሳያነሳ አንገቱን
ቀና አድርጎ የሰዉየዉን ማንነት ለማወቅ ሲሞክር የሚያዉቀዉ ፊት ነዉ
የስራ ባልደረባዉ አቶ ፍቃዱ ነበር።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
2