አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጃገማ ኬሎ የህይወት ታሪክ በፍቅረ ማርቆስ ደስታ የተፃፈውን መፅሐፍ ሙሉውን በPdf ቀረቦላችኋል መልካም ንባብ📖👇👇👇
#ፍቅር #ፈራን

"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
#ፈራን
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
#ናቅን
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
#ናቅን
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
#ጠላን
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
#ራቅን
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
👍2
"በእጅህ ያለን አትልቀቅ ፤ ባለፈ ነገርም አትፀፀት"

ከቀናት በአንዱ ቀን ይህ ሆነ ።
አንድ ሰው ላባዋ በህብረ ቀለማት ያሸበረቀ የምታምር ወፍ አጥምዶ ያዘ ። በመዳፉ ላይም ጨፍልቆ ሊገድላት ሲሞክር ፤
ወፊቱም ፤" እባክህ ጌታዬ ህይወትህን በሙሉ ባለፀጋ ሆነህ እንድትኖርና ስኬታማም እንድትሆን የሚያስችሉ ሦስት ጠቃሚ ምክሮች አሉኝና እባክህን አትግደለኝ " ስትል ተማፀነችው ።
ይህ ሰውም ሦስቱን ጠቃሚ ያለቻቸውን ምክሮች ትናገር ዘንድ ፈቀደላት ።
................
"የመጀመሪያው ምክሬ በእጅህ የገባን ነገር አትልቀቅ ነው ።"
"ሁለተኛው ደግሞ ባለፈ ነገር አትፀፀት ነው ። ሦስተኛውና የመጨረሻው ምክሬ ግን ከአንተ አልፎ ለልጅ ልጆችህም የሚጠቅም ታላቅ ምክር በመሆኑ ካለቀከኝ አልነግርህም ።" አለችው ።
ይህ ሰውም ለምክሩ በጣም ጓግቶ ነበርና ከመዳፉ ለቀቃት ።
ወፊትም በርራ ዛፍ ላይ አረፈች ።
ሰውዬውም ሦስተኛውን ምክር ትነግረው ዘንድ ጠየቃት ።
............
ወፏም ፤ "በአንደኛና በሁለተኛ ምክሬ የነገርኩህ ነገር ምን ነበር አለችው ።"
"በእጅህ የያዝከውን አትልቀቅ ፤ ሁለተኛው ደግሞ ባለፈ ነገር አትፀፀት ነው ።" ሲል ሰውዬው መለሰ ።
"አየህ ምክሬን ሰምተህ ቢሆን ኖሮ ፣ ሆዴ ውስጥ ከአንተ አልፎ ለልጅ ልጆችህ የሚተርፍ ወርቅ ነበር ፤ ምክሬን ባለመቀበልህና ባለመስማትህ ግን ዕድሜህን ሙሉ ድሃ እንደሆንክ ትኖራለህ ። " አለችውና ክንፉን እያርገበገበች ርቃ በረረች ።
👍5
Re-post
#አሮጊቶ
አንድ ጠዋት አሮጊቷ መስታውት ፈትለፊት ቁማ እራሷን ስትመለከት ሦስት ፀጉሮች እንደቀሯት ተመለከተች፡፡ ነፍሷን ያስደሰተች ሴት ናትና እንዲህ አለች “ዛሬ ፀጉሬን ማበጠር፣ ቅባት መቀባት፣ መንከባከብ አለብኝ” ተንከባከበችውም፡፡ እናም ደስስስ…የሚል ቀን አሳለፈች፡፡ ከቀናቶች በኋላ በአንደኛው ጠዋት መስታውት ፊት ቁማ ለቀኑ መዘጋጀት ጀመረች፡፡ ወደ መስታውቱ ተጠግታም ስትመለከት ሁለት ፀጉሮች ብቻ እንደቀሯት ተመለከተች፡፡ ህምምም… ሁለት ፀጉር !!! በማለት ተገርማ ለቀኑ ዝግጅቷን ቀጠለች ሁለቱን ጸጉሮቿን አሰማምራ እንደተለመደው ሸጋ ቀን ዋለች፡፡ እንዲሁ ደግሞ ከሳምንት በኋላ አንዲት ፀጉር ብቻ እንደቀረቻት ተመለከተች አሃ… አንድ ፀጉር ብቻ! አለችና ለአንድ ፀጉር የሚመች ስታይል ተጠቅማ እንዲሁ ቀኗን አሳመረች፡፡ በማግስቱ ጠዋት መስታውት ፊት ላይ ቆመች ጭራሽ መላጣ እንደሆነች ተመለከተች፡፡ በመጨረሻም መላጣ! ኦሁሁሁ.. ስትል ለራሶ አሰምታ ተናገረች፡፡ እራሷ ራሷ እንዴት ያለ ድንቅ ነገር ነው! ከዚህ በኋላ ፀጉሬን ለመንከባከብ የማጠፋው ጊዜ አይኖረኝም ስትል ነገረቸው፡፡ እራሷን እንደራስ መቀበል መቻል ችግር ነው ያልነውን ችግር እንዳልሆነ መረዳት ያስችላል፡፡
መልካም ቀን💚💛❤️
👍2
#ጸሎተ #ደቂቃን

አባ ያለህ በሰማይ
አባ አንተ ትልቁ
ከጡቶች ብቻ ሳይሆን
ወተቶች ካ'የር ይፍለቁ...
እንጠጣ ያለ አንዳች እቅፍ
ተይዞ መጥባት ይቅርልን
እየሮጥን የምንጠጣው
እየዳህን የምንረካው
ያ'የር ላይ ጡት ፍጠርልን።
እነኾም አደራ ጌታ
ይቅርልን የቀን መኝታ
ይቅርልን የሌሊት እንቅልፍ
እናቶቻችን አይተኙ
አባቶቻችንም ይንቁ
ደቂቅ ናቸው አይበሉን
ጮርቃነታችን አይናቁ
በገዛ ሕልሞቻችን ላይ
ፍቃድ እንዳለን ይወቁ።
በዛውም አደራ አባ
አባ የሰማያቱ
አልበላችሁም ብለው
አልተኛችሁም ብለው
ቁጠርባቸው ሲማቱ...
በደፋን በገፋን
በሰበርን ቁጥር
የሚዘረጋውን
እጃቸውን ቁጠር።
አባ እንደምታውቀው
ለራስ ልጅ ሲቆርሱ፥ ከቶ አያሳንሱም
ያንተ አባትነት፥ ነውና ለእነሱም
ይቀጡናልና፥ ስናጠፋባቸው
እንዳባትነትህ፥
ጥፋቶቻቸውን፥ አትለፍባቸው።
ረድኤት አ
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በአጥናፍሰገድ ይልማ የተፃፈውን የበደል ካሳ የተሰኘውን ታሪካዊ ልብ ወለድ መፅሐፍ ያላነበበው ካለ ሙሉውን በPdf ቀርቦላችኋል መልካም ንባብ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#ለምን #መጣህ

ለምን መጣህ ትይኛለሽ ለምን እንደሆን እያወቅሽ

ለምን ብለሽ አጠይቂ ይሄንን ብቻ እወቂ

መምጣት ለኔ ያኖረኛል

ከሰፈርሽ እያመሸዉ መዋል ማደር ያረካኛል

ከሰፈርሽ ዉሾች መሀል እኔ ብቻ የምጮህዉ

ሂድ ብለሽኝ ካጠገብሽ ከጥላሽ ስር የማርቀዉ

ጠዋት ማታ ልሳለምሽ ደጅሽ ድረስ የምቆመዉ

ከእልፍ ሰዉ መሀል አንድ የኔ ቸግሮኝ አንችን

ፍለጋ ነዉ ለምን ማለት ምንድን
ለምንስ ምድን ነዉ።

*በባንቻየሁ አለሙ*
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍1
#የገጣሚዉ #ስእል

ከሰአሊዉ ስእል የሚታየው ቀለም
ዉስብስብ አደለም
ዝብርቅርቅ አደለም
ኑሮ ነዉ ህይወት ነዉ የኔና ያንተ አለም
ሰአሊዉ ጀመረ ሽርጡን ታጠቀ
ቀለም ደባለቀ
ሀሳቡ መጠቀ
ከስጋዉ ተለየ ሄደ ካንድ ስፍራ
ህይወት ልታርፍ ነው ከወጠረዉ ሸራ
ተመልከት ስእሉን
አስተዉል ምስሉን
በልቦናህ እይ እድሜዉ ገፋ ያለ አንድ ሽማግሌ ጭቃዉን ይረግጣል
የሚረግጠው ጭቃ በደም ተለዉሶል
እንደዚህ ነው ስእል
እንደዚህ ምስል
ልብ ያለው ልብ ይበል
ከየት መጣ ደሙ
ምንድን ነው ትርጉሙ
የጭቃ ረጋጭን እግር የፈተተ
ከዚህ ብትን አፈር እሾህ ማን ከተተ
የጭቃ ረጋጭን እግር የከፈተ
ከዚህ ልስን ጭቃ ስለት ማን ከተተ
ይሄዉ ነዉ ጥያቄዉ ይሄዉ ነዉ ትርጉሙ ከጭቃዉ መሀል ላይ ለሚላወስ ደሙ
እናም ስእል ማለት ዝብርቅርቅ አደለም
ዉስብስብ አደለም ኑሮ ነዉ ህይወት ነዉ
የኔና ያንተ አለም
ከሰዉ ልጅ በስተቀር ጭቃ ረጋጭ ማነዉ
በደም የሚለዉስ አፈር የሆነን ሰዉ
ደሞም አለ ክፋት ከጭቃዉ ስጋችን
ትጉህ ሰዉ የማይወድ እሾህ ሀሳባችን
ሰአሊዉ ቆም አለ ሽርጡን አጥብቆ
ቀለሙን ደባልቆ
ከማያዉቀዉ አለም በነፍስ እግር ቆሞ
ስእሉን ያይ ጀመር ደጋግሞ ደጋግሞ
ጭቃዉን የሚረግጠዉ ምስኪን ሽማግሌ የራስ ቅሉ ፀጉር ፈትል ጥጥ መሳይ ነው
ልብሱም ቁምጣ ነበር ባጭር የታጠቀው እንደዚህ ነው ስእል እንደዚህ ምስል
ልብ ያለዉ ልብ ይበል
ከህይወት በስተቀር
ከህይወት በስተቀር ምንድን ነው ትርጉሙ
ያጭሩ ቁምጣ ሀዘን ከበዛበት ከሀሳብ ሌላ ምን ታምር ይገኛል ፀጉር የሚያነጣ ከዚህ ሁሉ በላይ ልብህ የሚደማዉ
ዉስጥህ የሚቆስለው
ትንሽ ዝቅ ብለክ በጭድ ተሸፋፍና በደም ተለወሰ ደብዘዝ ብላብህ የአስር ብር ምስል ጭቃዉ ላይ ታያለህ ይሄዉ ነው ህይወቴ ይሄው ነው ህይወትህ ከሰአሊዉ ስእል ላይኔ የሚታየኝ ላይንህ የሚታይህ
ምስኪን ጭቃ ረጋጭ ምስኪን ሽማግሌ በስባሪ ጠርሙስ እግሩ ደምቶ ቆስሎ
አስር ብቻ ነበር የተቀበለዉ ብር ለድካሙ ዉሎ እናም ስእል ማለት ዝብርቅርቅ አደለም
ዉስብስብ አደለም
ኑሮ ነው ህይወት ነው
የኔና የአንተ አለም----
👍1
📕የሼህ ሁሴን ጅብሪልን ትንቢታዊ ግጥሞች በ PDF📙
👇👇👇
#የቅዳሜ #ማስታወሻ
.
.
ልባቸውን አይቶ
እግር የነሳቸው ፣ ቀርፋፋ ቀናቶች
ዘልዛላ ለሊቶች
እንደ ማቱ ሳላ ፣ እድሜ የሚያዘግሙ
ከሰኞ ተነስተው ፣ አርብ እስከሚያከትሙ
በስራ በትምህርት
በስብሰባ ብዛት
በሰበብ ባስባቡ ፣ ሲያቀጥኑኝ አክርረው
እንደ ጠቦት ቆዳ ፣ ሲሰቅሉኝ ወጥረው
በአማራሪ ቀኖች ፣ የማልማረረው
እራሴን ለማጥፋት
ብዙ ጊዜ አስቤ ፣ ሀሳብ ምቀይረው
ለቅዳሜ ስል ነው።
።።።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው ፣
አደረች አራዳ ፣ ዘፈን ይለቀቃል
አሳዳሪ አራዳ ፣አልጋቤቱ ያልቃል
እንደጉድ ይጠጣል ፣ ይሰከራል በጣም
ነይና ላሳይሽ
ቅዳሜ የቀረ ፣ ዘላለም አይመጣም።
።።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው
በየመጠጡ ቤት ፣ ገርበብ ያሉ ጭኖች
በየ ጎዳናው ላይ
ቆንጆ ሴት የጫኑ ፣ ጢኒኒጥ መኪኖች
በየ ፋርማሲው ቤት
ፅንስን የሚያመክኑ ፣ እንክብል ኪኒኖች
የሚያዘዋውረው
የሚመነዝረው
የሚያመነዝረው ፣ እንደጉድ ይበዛል
ፌስቡክ ላይ ምታውቂው ፣
በስካር ጠንብዞ
ፖስት የሚያደርገውን ፣ ሚሪንዳ ይገዛል
"ይህች ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው? " ፣ ብሎ ላይኩን ያባዛል።
።።።
ነይና ላሳይሽ
ጨዋ የሚባል ህዝብ ፣ ጠፍቶት ትርጓሜ
ቀሚስ የሚባለው
የት እንደሰረሰ ፣ አጥሮ እንደጷግሜ
የዝች ሀገር ጉዞ
ወዴት እንደሆነ ፣ መልስ አለው ቅዳሜ።
።።።
ነይና ላሳይሽ
የአልኮል ባህር ላይ ፣ የመረብ አጣጣል
መንግስት አልወርድ ያለው
ውስኪ እያወረደ ፣ ሴት ከቦት ይጠጣል
የቢራ ያጣ ሰው
ስለውስኪ አጠጣጥ ፣ አቃቂር ያወጣል
ጭፈራው ለጉድ ነው ፣
ጨፋሪው ብዙ ነው ፣ አያስጥልም ጠጠር
ዝቅ ቢሉ ጭን ነው
ጎንበስ ቢሉ ጡት ፣ ቀና ሲሉ ከንፈር
ነፃ ይታደላል
አንድ የሰከረ ሰው
እቺ ሀገር ወዴት ነው ፣ የምትሔደው ይላል።
።።።
ሁሉ እየተነሳ
ይቺ ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው ብሎ ፣ መጠየቅ ቢወድም
ነይ መልሱን ላሳይሽ
ወደ አልጋ ቤት እንጂ ፣ ወዴትም አትሔድም።
ዛሬ "ቅዳ" ሜ ነው
።።።
ግጥሟም ቅዳሜም ትደገም
።።በላይ በቀለ ወያ።።
#ብሂላዊ #ምክሮች

#ሀሜት:- ያለ መሳሪያ ሰዉን መግደል ነዉ
#ማጉረምረም:- ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።
#ቁጣ:- ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነው።
#ብስጭት:- የተበሳጩበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የሀጥያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነዉ።
#መርገም:- አቅም ሲያንስ ወደ ላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።
#መሳደብ:- ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸዉ ሰዎች ዱለ ነው።
#ዋዛ #ፈዛዛ:- በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው።
#ዘፈን:-😕ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ፍላፃ ነው።
#ድንፋታ:- የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ
ነው።
#በክፉ #ማንሾካሾክ:- ቀስ ብለዉ ሰዉን የሚገድልበት የአሳባቂዎች ጩህት ነው።
#ነገር:- ማመላለስ የሚዋደዱትን የሚለያዬበት የዲያቢሎስ የግብር ልጆች መሳርያ ነው።
#የአደራ #ገንዘብ #መብላት:- ሳይጥሩ ሳይግሩ የሰዉ ላብ ሲበሉ የሚኖሩበት የሰነፍ ሰዎች መሳርያቸዉ ነው።
#ሰዉን #ማስነወር:- ሰዉ የወደደዉን የተከበረዉን ስም ለማጥፋት የሚቀቡት የምቀኞች ቀለም ነው።
#መሳለቅ:- የማይታይ የቀናተኞች ጦር ነው።
#ተስፋ:- ከማጣት ወደ ማግኘት ለመሸጋገር የሚያገለግል ድልድይ ነው።
#ጠብ:- እሳትን ለማንደድ የሚጫር የነገረኞች የኪስ ክብሪት ነዉ።
#ችኮላ:- የትእግስት ጠላት የፀፀት አባት ነው ልጁም ወይኔ ይባላል።
#ሙከራ:- የስራ ጥልቀትን መለኪያና መመጠኛ ነው።
#የጥበብ #መጀመርያ #እግዚአብሔርን #መፍራት #ነው
ከ ያለ ጭንቀት የመኖር ምስጢር መፅሀፍ የተወሰደ በዲ/ን የሺጥላ ሞገስ
👍2
#ሰማይ_እና_ውዴ

ይሄውልሽ ውዴ
ባይኖቼ አማትሬ ፥ ሰማዩን እያየሁ
ውሎና አዳርሽን
ባፍቃሪ ልቦና ፥ መገመት ችያለሁ።
ሰማይ ፍንትው ሲል
ሰማያዊ መልኩን ፥ በገላው ሲደፋ
ከአድማስ መነሻ
እስከ አድማስ መቋጫ ፥ ሲያውለበልብ ተስፋ
አዋፋት ሳይሰጉ
ሲበሩ ሲቀዝፉት ፥ በላዩ ሲዋኙ
ንስንስ ነጫጭ ጌጦች
የዳመና ገጾች ፥ ገላው ላይ ሲገኙ
አንቺ ተደስተሽ
በፍፁም መፍለቅለቅ ፥ የዋልሽ ይመስለኛል
የሰማዩ ቀለም
ሰማያዊው መልኩም ፥ ምስክሬ ሆኗል።
ደግሞ ሌላ ጊዜ
ሰማይ መልኩን ቋጥሮ ፥ ደርሶ ሲያስገመግም
በመብረቅ ትርኢት
ብልጭ ድርግም ሲል ፥ ጩኸት ሲደጋግም
እዬመላለሰ
አሁንም አሁንም ፥ ሲያምቧርቅ ሲያጓራ
አዋፋት ሸሽተውት
እንሸሸግ ሲሉ ፥ በጎጆቸው ጣራ
ዛሬ ተናደሻል
ግልፍተኛ ቁጣ ፥ ወርሶሻል እላለሁ
የቋጠረ መልኩን
ከጩኸቱ ጋራ ፥ ሰማዩን እያዬሁ።
ደግሞ አንዳንድ ጊዜ
ዳመናን ሰብስቦ ፥ ሰማይ ሲዝረበረብ
ዶፍ ጥሎ በፍርጃ
ምድርን ሲያጨቀያት ፥ ገላዋ ላይ ሲሰንብ
የሀዘንሽ ምክንያት
ምሬትሽ ሳይገባኝ ፥ አለቀሽ እላለሁ
የእንባሽን ክብደት
በዝናቡ መጠን ፥ በዶፉ እለካለሁ።
ይሄውና እንግዲህ
ባፍቃሪ ልቦና
ውሎና አዳርሽን ፥ አይቼ ስመዝን
የውስጥሽን ስሜት
ደስታና ሀዘንሽን ፥ ቁጣሽን ስተምን
ሰማይ ነው ምስክር
በማይነጥፍ መልኩ ፥ የሚያሳዬኝ አንቺን፡፡

--ከሚኪ--
👍1
Re.Post
#ለመለስ #የተፃፈ #ደብዳቤ
፨ ፨
.
.
እንደምን ነህ ጋሼ ፣እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ፣ ቀረህ ሳትመለስ?!
.
እኛማ ይሔውልህ
ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ
በየአደባባዩ ስንል ነበር ዋይ ዋይ
አዎ ትዝ ይለናል
ጀነራልህ ሁሉ ፣ ተኩስ ነው ትእዛዙ
ወገን ይጥል ነበር ፣ የግፍ አፈሙዙ
ለምንድን ነው ስንል? ስምክን አስቀድመው
ከክርስቶስ በላይ ፣ምስልህን አትመው
ቅዱስ መፅሐፍ ይመስል
ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው
ቢረፈርፉንም አላለቅንምና
ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው!
~
የሆነስ ሆነና ግን አንተ ደህና ነህ
እኛማ ይኸውልህ
ደርሰህ ስትናፍቀን
አይሞትም የምትል ሙዚቃ ሞዝቀን
መቃብርህን ልንስም ፣አበባ ልናኖር ፣ስላሴ ብንመጣ
ፌደራል ያይሃል ፣ እስረኛ ይመስል ፣ ሾልከህ እንዳትወጣ
መቼም ስላሴ ውስጥ...
ባለስም ነውና ፣ የሚቀበርበት
አንተን አየት አርገን ፣ ዞር ስንል ድንገት
እነፊታውራሪ
ግራ'ዝማች
ቀኝ'ዝማች
ፊተኛ ባለስም ፣ የሆኑት አባቶች
ያለዘብ ቆመዋል ፣ እነ አብዲሳአጋ
ጀግና መሃል ሳለህ ፣ ምነው በድንህ ሰጋ?!
~
የሆነስ ሆነና
ሃየሎም ደህና ነው
እዛም ትግል ይመራል?
እስር ቤት ሰባብሮ ፣ታራሚ ያስፈታል
እዛም ከፊት ሆኖ ፣ ጭቁን ያታግላል
እዛም በጀግንነት ፣ በለኮሳት ሻማ
ነፃ ነኝ ባለባት ፣ ርዕሰ ከተማ
ትንሽ ግሮሰሪ ፣ ይገባ ይሆን ደፍሮ?
እዛስ ጀማል ያሲን ፣ ፈጠረ አምባጓሮ?
ሃየሎምን ሰዋው ፣ በሐሺሽ ናላው ዞሮ?
።።
እኛማ ይኸውልህ
ብዙ ሃየሎሞች ፣ ፈጥረን ስናበቃ
እልፍ ጀማል ያሲን ፣ ይሆናል ጥበቃ
ይኸው ባደባባይ
የጀግኖቻችን ደም ፣ በየቦታው ፈሶ
አለ ጀማል ያሲን ፣ ሞት ሚበይንበት ፣ ፍርድ ቤቱ ፈርሶ!!
~
ግን አንተ ደህና ነህ
አቡነ ጳውሎስስ ፣ብፁው እንዴት ናቸው
እዚያም እንደምድሩ
አንድ አንቀፅ ያክላል ፣ መጠሪያ ስማቸው?
ደረታቸው ግድም "ሽጉጥ" የሚያደርጉት ፣ አለ መስቀላቸው?
።።።
እኛማ ይኸውልህ
ጳጳሳት አስታርቀን ፣ ሾመን በአደባባይ
ቃላቸውን እንጂ ፣ ዘራቸውን ሳናይ
አለን በአንድ ላይ።
የሆነው ሆነና...
አቡነ ጳውሎስ ፣ ጳጳሱ እንዴት ናቸው
ደረታቸው ግድም ሽጉጥ የሚያደርጉት አለ መሥቀላቸው?
እዛም ትውልድ ሲያልቅ
ወገን ደሙ ሲፈስ
እምነትሲተራመስ ፣ አያውቁም ግሳጤ?
እዛም ታጋይ ናቸው?
ቆባቸው የጳጳስ ነብሳቸው የአጤ?
~
እንደምን ነህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ
~
~
~
ከቻልክ ፃፍልን ለደብዳቤያችን መልስ!!
👍1👎1