፩ ሃይማኖት
8.94K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
1፤ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።

2፤ እግዚአብሔርን። አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።

3፤ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።

4፤ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።

5፤ ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥

6፤ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።

7፤ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

8፤ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።

9፤ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።

10፤ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።

11፤ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤

12፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

13፤ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

14፤ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።

15፤ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።

16፤ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 91)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጠቅላይ ቤተ ክህነት የጂጂጋ ተጎጅዎችን በዘላቂነት ለመርዳት የሚከተለውን የባንክ አካውንት ከፍቷል፡፡ የገንዘብ ርዳታ ለመስጠት ያሰባችሁ በዚህ ተጠቀሙ፡፡

1000254922898
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡፡
አራት ኪሎ ቅርንጫፍ
Share share
@And_Haymanot
መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?
....የቀጠለ
_ማስረጃ 6. በዮሐንስ ወንጌል 10፡22 በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤ … ‹‹የመቅደስ መታደስ በዓል›› በሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አናገኘውም ግን ቅዱስ
ዮሐንስ ከመጽሐፈ መቃብያን 4 ላይ ጠቅሶ ተናገረ፡፡
_ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 7. በ ሮሜ 13፡1 ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር
ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። የሚለው ኃይለ ቃል ከሲራክ 17፡14 የተወሰደ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 8. አዳምና ሔዋን አቤልና ቃየልን ወለዱ፡፡ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ይላል ዘፍጥረት 4፡17 በ66ቱ
መጽሐፍት ላይ ስለ አቤልና ቃየል መወለድ እንጂ ሌላ የሰው ዘር በምድር ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አያወራም፡፡ ታድያ ይህቺ የቃየል ሚስት ከየት መጣች? ስለስዋ ምንም አይናገርም
በአለም ላይ የነበሩ ሰዎች አራት ብቻ እንደነበሩ ነበር የምናነበው፡፡ የዚህን መልስ የምናገኘው በኩፋሌ 5፡8-17 ላይ
ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 9. - ይሁዳ በመልዕክቱ ‹‹የሄኖክን ትንቢት ከመጽሐፈ ሄኖክ ጠቅሶ›› ጽፎታል (ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ
ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል (ይሁዳ 1፡ 14-15) መጽሐፈ ሄኖክ ደግሞ በስልሣ ስድስቱ መጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ የለም፡፡ ሄኖክ ትንቢት ተናገረ ብሎ ከትንቢቱ ጠቅሱ ይሁዳ በመልዕክቱ ጽፎልናል ይህም ትንቢት በሄኖክ 1፡9 ላይ በግልጹ ተቀምጦ እናገኘዋለን፡፡ እንግዲህ ይሁዳ ሄኖክ ትንቢት መናገሩን እየነገረን ተቃዋሚዎች ሄኖክ ትንቢት አልተናገረም ይሉናል፡፡ እኛስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የጻፈወን ይሁዳን እናምናለን፡፡ እሱ የተቀበለውን እንቀበላለን ጥበብ አይኮረጅም
(መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ የአምላክ ቃል)
- - - - - - -
@And_Haymanot
-+- በመጀመሪያ እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ መረጃ መሆኑን እንተማመን፡፡ ትውፊት ማለት ቅብብል፣ ርክክብ ወይም
ውርስ ማለት ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ውርስ ከቀደሙት አበው ለእኛ በርክክብ ደርሶናል፡፡ አንዱ ከሌላው የተቀበለውን ለሌላው አሳልፎ በመስጠት እስከ ዘመናችን የደረሰ እውነታ ነው፡፡
ትውፊት መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት ያለ የነበረ ነው፡፡ እንደውም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን አምነን የተቀበልነው የቀደሙት አባቶቻችን የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን
በትውፊት ስላስረዱን ነው፡፡
-ለምሳሌ፡-
1-ዓለም ከተፈጠረ ሺህ 486 ዘምን መጽሐፈ ሄኖክ ተጻፈ
2- እስራሄል በግብጽ ሳሉ በፈርሆን ዘመን የኢዮብ መጽሐፍ ተጻፈ
3- 3643 ዓ.ዓ. እስራሄል ከግብጽ ወጡ በዚህ ጊዜ ኦሪት ተጻፈ፣
ወዘተ. . . . . እንግዲህ ከ1486 ዘመን በፊት የተጻፈ ህግ አልነበረም፤ በዚያ ጊዜ የነበሩ አበው ይመሩ የነበሩት ሙሉ
በሙሉ በትውፊት ወይም በህገ ልቡና ነበር ማለት ነው፡፡ ከስልሳ ስድስቱ (66) መጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ሌሎች ቅዱሳት
መጻህፍትየለም የምትሉ ወይም ትውፊታዊ መረጃ አንቀበልም ለምትሉ እስኪ የሚከተለውን ጥያቄ ላቅርብ
_ _ _ _ _ _ _
1- በኦሪት ዘፍጥረት አገላለጥ ቃየንም ሆነ አቤል ሁለቱም ለእግዚሐብሔር ከስራቸው ውጤት መስዋዕት አቅርዋል፡፡ ዳሩ ግን የተቀበለው የአቤልን መስዋዕት ብቻ ነው፡፡ የቃየንን መስዋዕት ያልተቀበለው ለምንድን ነው? መቼም ለአቤል አድልቶ ነው የሚል መልስ እንደማይሰጥ እርግጣኛ ነኝ ምክንያቱም
እግዚሐብሔር ለሰው ፊት አያዳላም፡፡
2- አቤል ከበጎቹ በኩራትና ከሰቡ እግዚሐብሔር መስዋእት አቅርቧል፤ ከበጎቹ መካከል በኩራትና ስቡን ማቅረብ እንደሚገባ እንዴት አወቀ? ምክንያቱም የጽሁፍ ህግና ትዕዛዝ በዘመኑ አልነበረም
3- ‹ቃየንም ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ሄኖህንምም ወለደች› ይላል፡፡ እግዚሐብሔርወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው አዳምንና ሄዋንን ብቻ ነው፡፡ አዳምና ሄዋን ደግሞ የወለዱአቸው አቤልና ቃየንን እንደሆነ በምዕራፍ 4 ተገልጽዋል ፤ታዲያ የቃየን ሚስት
ማንነች? ከየትስ መጣች? ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከ66 መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑትን ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትንና ትውፍታዊ መረጃ መሰረት ማድረግ ይገባል ያለበለዚያ ጥያቄዎቹ የማይፈቱ እንቆቅልሽ ሆነው መቅረታቸው ነው?
_ _ _ _ _ _ _
- እስኪ ደግሞ ወደ ሐዲስ ኪዳን እንሂድ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ቢያንስ ቢያንስ ለ20 ዓመታት ያህል ስለ ጌታ ይማሩ የነበሩት በቃል ነበር ምክያቱም ሐዲስ ኪዳን ገና በጽሁፍ አልተቀረጸም ነበርና በቅብብል ወይም በሰሚ ያገኙትንም እነርሱ ራሳቸው ከጌታ እደተቀበሉት አድርገው ያስተምሩ ነበር ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ጳውሎስ ነው (1 ቆሮ. 11፥23-24)፡፡
ጳውሎስ ከሐዋርያት ቃል የተማረውን ለሌሎች ደግሞ አስተላለፈ፡፡ ስለዚህም ወንጌል የሚያሰኘው በጽሁፍ መስፈሩ
ብቻ ሳይሆን የሕያው የእግዚሐብሔር ቃልና የህይወት መንገድ መሆኑነው፡፡ በጌታ ጊዜ ወንጌል ገና አልተጻፈም ነበር፣
“ለሐዋርያቱም ወደ ዓለም ሒዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ”(ማር.16፥1) ይህም ሲል የሰሙት ተማሩት እንጂ በጽሁፍ ቀርጾ የሰጣቸው ወንጌል አልነበረም፡፡
_ በተጨማሪም በማርቆስ ወንጌል ም.1፥21-22 ‹ወደ ቅፍራንሆም ገቡ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ
ጸፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ›፡፡ ይህ የክርስቶስን ተቃዋሚዎች ራሱ ያስገረማቸው ትምህርት ምን አይነት ነበር ‹ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለእርሱ በመጻህፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ሉቃ 24-27
_ ከትንሳሄው በኋላ ለሁለቱ ደቀ መዝሙር ተረጎመላቸው የመጻህፍት ትርጓሜ በየትኛው ሀዲስ ኪዳን ላይ ይገኛል? “በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ. . . ናዝሬት
ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ” ማቴ 2፥23 ይህን የተናገረው ነቢይ ማነው? በየትኛው የትንቢት መጽሐፍ ይገኛል? ማቴ 27፥9 ‹በዚያን ጊዜ በነቢዩ ኤርምያስ የተባለው ከእስራሄል ልጆችም
አንዳንዶቹ የገመቱትን የተገመተውን ዋጋ ሰላሳ ብር ያዙ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሰሪ መሬት ሰጡት የሚል ተፈጸመ› ይህስ ከየት ተገኘ? በተጨማሪም ሉቃ 2፥25-32፣ 2ኛ ጢሞ 2፥ 8፣ ዕብ 12፥ 21 ፣ ራዕይ 2 ፥14፣ ዮሐ 20፥ 30 ፣ ዮሐ 21 ፥25፣ ይሁዳ 9 እንዲሁም ዮሐ 1 ፥48 ሌሎች ማሳያዎች ናቸው፡፡

_ በአጠቃላይ እነዚህ መረጃዎች ከ66ቱ መጻህፍት የማናገኛቸውና ነገር ግን ተዋህዶ እምነት በምትጠቀምበት
ሰማንያ አህዱ ውስጥ ፍንትው ብለው የተጠቀሱ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህን የመሳሰሉ ፍሬ ሃሳቦች ስለተቀመጡበት ነው ሰማንያ አሃዱን ከሌላው ጋር ይጋጫል የሚባለው?
_ ብርሃን ዓለም ጳውሎስ ‹እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን
ወግ ያዙ› ያለው (2ተኛ ተሰሎንቄ 2 15)፡፡ በቃላችንም በመልእክታችንም የተማራችሁትን ‹ወግ› ያዙ ሲል ትውፊትን ማለቱ ነው፡፡👇👇👇
መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?
👆👆👆...._ ፊልጵ 4፥9 ‹ከህኔ የተማራችሁትና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም እና ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ የሰላምም
አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል›፡፡ የቅዱስ ጳውሎሰ መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ በፊልጵስዮስ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ከእርሱ ከአንደበቱ የተማሩትንና በጽሁፍ የተቀበሉትንም የሰሙትንም
ያዩትንም ሁሉ እንዲይዙ እንደያደርጉ እንጂ የተጻፈውን ብቻ እንዲይዙና እንዲጠብቅ አልነበረም፡፡ ዛሬም እኛ በትውፊት የደረሰንን ሁሉ ልንጠብቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው ፡፡
_ 2ኛ ጢሞ ‹የእግዚሐብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለበትን መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም
ላለው ምክር ይጠቅማል›፡፡ ምክሩም ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑን ተዋህዶዋውያን እናምናለን፡፡ ስለዚህም
በቤተክርስቲያናችን ያሉትን የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለባቸውን
ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉ ለክርስቲያናዊ ህይወታችን እንገለገልባቸዋለን፡፡

--> በመጨረሻም ኦርቶዶክሳዊያን በቤታችን ያለን መጽሐፍ ቅዱስ:-
81: የኦርቶዶክስ
73: የካቶሊክ
66: የፕሮቴስታንት
24: የአይሁድ
በሆኑንና አለመሆኑን ለይተን ተረድተን የረሳችንን የሆነውን ትክክለኛውን 81 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስን እንጠቀም።

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን አትታደስም! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን
ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና
የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን

ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው
ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
#Zerihun_Eshetu
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጌታ ሆይ አሳ ያዝኩኝ ብዬ እባብ ጨብጫለሁ : ዳቦ አነሳሁ ብዬ ድንጋይ አንስቻለሁ። ለራሴ መምረጥ አላዉቅም። የነገሮች ዳሩ እንጂ ፍፃሜው አይታየኝም።
ድንበሩ እንጂ ግዛቱ ለኔ ስውር ነው። ሁሉን የምታይ ሁሉን
የምታውቅ አምላኬ ፍቃድህ ከሆነ ስጠኝ። ካልሆነ ከልክለኝ እንቢ ብዬ ባስቸግር እንኳ በፍቅር ቅጣኝ እንጂ ለፍቃዴ አሳልፈህ አትስጠኝ።
~~~~~~
መልካም ዕለተ ሰንበት
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ክርስቲያን ሁል ጊዜ ውጊያ አለብን ውጊያችን ከስጋና ከደም ጋር
አደለም። ወጊያችን ከመንፈስ ጋር ነው። ከማይታዩ ረቂቃን መናፍስት ጋር ከሴጣን ከዳቢሎስ ጋር ውጊያ አለብን! ማሸነፍ
የምንችለው በፃምና በፀሎት ነው!
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
"ተአምሯን የሰማ ስጋውን ደሙን እንደ ተቀበለ ይሆንለታል"።

@And_Haymanot
ለተሃድሶ መናፍቃን የተሠጠ መልሥ
(በድጋሚ የቀረበ)
ይህን ፅንሰ ሀሳብ ለመረዳት በመጀመሪያ በመቅደሙ የተፃፈውን
ቃል እንዳለ መመልከት ጠቀሜታ ይኖረዋል። አስቀድመን እንደተናገርን የታወቀ ምክንያት ኋጢአት ደዌ
ካልከለከለው በዚች ቀን ተአምሯን ሰምቶ ስጋውን ደሙን ይቀበል። ስጋውን ደሙን መቀበል ካልተቻለው ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሒድ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል ይደረግልኛል
በማለት ቢሰማ ይላል የዚህን አንቀጽ መልዕክት አንድ በአንድ በመተንተን ስንመለከት የሚከተሉትን ሶስት አበይት መልዕክቶች እናገኛለን።

👉ሀ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ፦

ይህ አንቀፅ በመጀመሪያ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚያስተላልፈው መልዕክት ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ የሚል ነው። ምክንያቱም በፍትሐ ነገስት ከቀዳም ሥዑር በቀር ቅዳሜ ቅዳሜ እና እሁድ እሁድ በቤተክርስቲያን ተሰብስባችሁ ስጋውን ደሙን ተቀብላችሁ ደስ ይበላችሁ ተብሎ ታዝዟል ይህም ብቻ ብቻ ሳይሆን በበረሃ ያሉ ባህታውያን ሳይቀሩ መልዐከ እግዚአብሔር ስጋወ ደሙን ሰንበት ነው። / በዓላት-ምን ?
ለምን ? እእንዴት ? ገፅ ፵፮ እና ፷፮ / ነገር ግን በስርዐተ ቤተክርስቲያን አንድ ሰው ስጋውን ደሙን እንዳይቀበል ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ይኖራሉ።
እነዚህም በዚህ አንቀፅ የተገለፁት አንደኛ የታወቀ ምክንያት / እንደ ወሊድ ፤ ሀዘን ፤ ለቅሶ ፤ ...የመሳሰሉት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ኃጢዐት ነው።
ይከለክሉታል ተብለው ከተጠቁሱት በመጨረሻ የተገለፀው ደግሞ ደዌ ነው። አንድ ሰው በደዌ ምክንያት ነገር ከሰውነቱ እየወጣ፤ ደም እየፈሰሰው ይህን የመሰሉ ነገሮች እያሉበት ስጋወ ደሙን ላይቀበል ይችላል እነዚህ ሁሉ ግን ሰውየውን በቤተክርስቲያን
ቅፅር ተገኝቶ ከመፀለይ፤ ቅዱሳት መፀሀፍትን ምንባባት ከመስማት ግን ላይከለክሉት ይችላሉ። ስለዚህ አንድ ሰው እነዚህ ምክንያቶች ካልከለከሉት በቀር ስጋወን ደሙን ይቀበል በማለት ወንጌልን ይሰብካል እንጅ ከወንጌል የወጣ ቃል የለውም።

👉 ለ ቤተክርስቲያን አትቅር ፦

ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልህ ግን ስጋውን ደሙን መቀበል አይቻለኝም ብለህ ወደ
ቤተክርስቲያን ከመሄድ አትከልከል የሚለው። ተአምረ ማርያም ከቅዳሴ በፊት ያለው የቤተክርስቲያን የፀሎት
ክፍል አንድ አካል ነው።
መቅድሙም የሚለው ፦
።።።///።።።።///።።።
#ስጋወ_ደሙን_መቀበል_ካልተቻለው_ተአምሯን_ሰምቶ_ወደ_ቤቱ_ይሂድ_ነው
።።።///።።።።///።።።
ይህም ማለት ባትቆርብም ቤተክርስቲያን አትቅር ማለት ነው።በፀሎቱ ትምህርትና በመሳሰለው መርሀግብር ሁሉ ተሳተፍ።
ዕለቱ ሰንበትና በዓላት ከሆነ አንድ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ካልሄደ በዚያም ተገኝቶ ካልተማረ ካላመሰገነ ክርስትናውን በምን ይገልፀዋል ?
በዚህ አገላለፅ ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሂድ የሚለውን በአስተውሎትና በቅንነት ከተመለከትነው የሚናገረው ስለተአምሯ ብቻ አይደለም። ታአምሯን አታስታጉሉ ሲል ወደ ቤተክርስቲያን ሂዳችሁ በዚያ ካለው ባለው አገልግሎት ተሳተፉ ማለት ነው። ምክንያቱም ተአምረ ማርያምን እንዴትና መቸ እንደሚነበብ
እናውቃለን። ከተአምሩም በፊት፤ ከተአምሩም በኋላ ሌሎች ፀሎቶችና
ምንባባት አሉ። ይህን አጠቃላይ አገልግሎት ለምዕመኑ በታወቀ በተረዳ ነገር በዚህ ስያሜ ማስታወቅ ክፋትም ኋጢአትም አይደለም። ሌላው አገልግሎት በዚህ አገላለፅ ለምን ጠሩት ቢባል በትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ላይ እንደተፃፈው ሌላውን አገልግሎት በመናቅ ማቅለል ሳይሆን ለእመቤታችን ባላቸው ፍቅር ነው።

👉 ሐ አትጠራጠር፦

ሶስተኛውና የየመጨረሻው የዚህ አንቀፅ መልዕክት በታወቀ ምክንያት
+++ በዚች ዕለት +++ ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልክ ለሌሎች የተደረገው አይደረግልኝም የዕለቱ በረከት አይደርሰኝም ብለህ አትጠራጠር የሚል ነው። መፀሀፉ የተአምራት መፀሀፍ እንደመሆኑ መጠን ተአምራትም
የሚደረገውና ተአምራትም የሚያሰኛቸው ከዘወትራዊ የህይወት ተግባራትና ድርጊቶች የተለየ ለሰው የማይቻል በእግዚአብሔር ብቻ የሚቻል ነገር መደረጉ በመሆኑ አንተም ይደረግልኛል
በማለት በዕምነት ከፀሎቱ ተካፍለህ ከተአምሯም ሰምተህ ብትሄድ #በዕለቱ የቆረቡትን ሰወች በረከት ታገኛለክ ማለት
ነው። ይህ ደግሞ በቅዱሳት መፀሀፍ የተፃፈ ነው። ራሱ ጌታችን በወንጌሉ የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ዕምነት
ቢኖራችሁ ተራራ ማፍለስ፤ ባህር መክፈል..........
ሌላም ሌላም ትችላላችሁ ሲል አስተምሯል። ይህም በዕምነት ሀይል እግዚአብሔርን በረከተ እግዚአብሔርን
ታገኛላችሁ ከእግዚአብሔር ትገናኛላችሁ ማለት ነው። ስጋወ ደሙ በየሳምንቱ ወይም ከዚህ ባነሰም ይሁን በበዛም
የምንቀበለውም ለዚሁ ሀይለ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርገን ኋጢያታችን አስተስርየን በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስ አግኝተን ለመኖር ነው። በዚያች ዕለት አልቻልክ ብሎ ባትቀበል በዕምነትም ይህን ታገኛለክና አትጠራጠር ይሉናል ሊቃውንቱ።
የየመቅደሙ መልዕክት ይኸ ሁኖ ሳለ
"አውቆ የተኛን " ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደሚባለው ሰወችን ሆን ብሎ ለማጠራጠር ከቅዱሳን በረከት ለመለየት አጋንንት በሰወች አድረው ሊቃውንቱ ያላሉትንና ሊሉም ያላሰቡትን
ያቀርባሉ። ቤተክርስትያኒቱ " ስጋውን ደሙን አትቀበሉ " ስጋወ ደሙን መቀበልና ስጋወደሙን ሳይቀበሉ ተአምረ ማርያምን መስማት እኩል ናቸው የሚል ትምህርት አስተምራ አታውቅም እእንዲህም አታምንም።
ተአምሯን የሚሰሙትና የሚያሰሙትም ስጋውን ደሙን የተቀበሉ ወደፊትም የሚቀበሉ ናቸው እንጅ አረማውያን ወይም በስጋወ ደሙ የሚጠራጠሩ አይደሉም።
/// ይደረግልኛል በማለት ቢሰማ /// የሚለው ጊዜ የተገደበ
ነው፡፡ ታዲያ ይህ በዕውኑ ለምዕመኑ መንፈሳዊ ህይወት መጨነቅ ወይስ ለኑፋቄ ሽፋን መፈለግ ???
ምንጭ ትምህርተ ተዋህዶ አፕሊኬሽን።
ልዑል እግዚአብሔር በተዋህዶ በረት እንድንፀና ያድርገን ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችንም ጋር
ይሁን አሜን::
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
Join @And_Haymanot
@And_Haymanot
🙏1
ትዝብት

@And_Haymanot

``አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን ወይም በኦርቶዶክስ ለምድ ያሉ ተኩላዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ጥጎች እንዲህ ሲሉ ይሰማል፡

«ድንግል ማርያም ታማልዳለች፤እስኪ አንድ ሰው አሜን ይበል»
የዚህችን ኃይለ-ቃለ ሥርወ-ውልደት እናያለን።


አዎ ድንግል ማርያም ታማልዳለች!

ግን ይህቺን ከማን ነው ያመጣኃት?«እስኪ አንድ ሰው አሜን ይበል፥ድንግል ማርያም ታማልዳለች»
ይህ የተቃዋሚዎች ይትባሃል ነው ወዳጄ!አሜን በማያስብል ነገር ሁሉ አሜን እንድንል ማስገደድ፡እስኪ አንድ ሰውም አሜን ይበል ማለት¡
አሜን ማለት እኮ ይሁን ይደረግልን ማለት ነው!ድንግል ማርያም ታማልዳለች ማለት አሜን አያስብልም!
ይልቁንም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን ብንል፤እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትጠብቀን ቢባል፤እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ቤተ-ዶኪማስን በበረከት እንደሞላች የእኛንም ቤት በበረከት በምህረት ትሙላልን ቢባል፤ቅድስት ድንግል ማርያም በላዔ ሰብዕን በአማላጅነቷ እንዳስማረች እኛንም እንዲሁ ታስምረን፡ታድነንም ቢባል፣ከአማላጅነቷ ፡ከዘላለማዊ ድንግልነቷ፣ወላዲተ-አምልካነቷ፣አቁራሪተ መዓትነቷ እንዲሁም ምዕራገ-ጸሎትነቷ ጋር በአጠቃላይ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሁለንተናዊ ባህርይ እና ተክለስብዕና ጋር አያይዘን ብንጸልይ አሜን እንላለን!

ከዚህ ውጪ ግን ፓስተራዊ ቃልን በኦርቶዶክሳውያን ማኅበር ላይ መናገር እጅግ ጸያፍ ነው!
እኛ ኦርቶዶክሳውያን አሜን በሉ ተብለን አይደለም አሜን ምንል፡አሜን ማለት ተዋህዶናል!አሜን ማለት ባህርያችን እንጂ በውትወታ ወይም አሜን በሉ ተብለን ምናደርገው አይደለም!
በቃላችን አሜን ስንል ከልባችን አምነን እንጂ አሜን ብለን አዳራሽ እስኪናወጥ ልንጮህ አይደለም!ኦርዶቶክሳዊ አሜን ወይም አሚን ለዛ አለው፣በምክንያት በእውነት ላይ የተመሰረተ ነው!
ኦርቶዶክሳዊው አሜን በቃል ሳይሆን በልብ ሚነገር፡ከልብም ሚመነጭ ነው!
በመጮኽ ፌሽታዊ ሆኖ ሚገለጽ ሳይሆን በአትኅቶ በተሰበረ ልብ ሚቀርብ መባዕ ነው።
እስኪ አንድ ሰው አሜን ይበል ሚል ኢ-ክርስቲያናዊ አባባልም ለእኛ ቤተክራቲያን አይመቻትም!
የእኛ እምነት በጋራ የመዳን እምንት ስለሆነ፡ማንም አሜን በሉ ሳይለን አሜን ብለን እምነታችን እንዲሁም መታመናችንን ምንገልፅበት ነው!

ለነገሩ ፕሮቴስታንታዊ ፓስተሮች እሚናገሩት ነገር አሜን ሚያስብል ስላልሆነ ሚከታተላቸውን ሕዝብ ቀድመው አሜን በል ካላሉት ስለማይል«እስኪ አንድ ሰው አሜን ይበል»ብለው ማወጃቸው አያስደንቅም!አያስደነግጥምም!
«ኢየሱስ አምላክ ነው፡ኢየሱስ ያድናል» እና ሌሎች ፓስተራዊ ሀረጋት በምን አግባብ ነው አሜን ሊያስብሉ ሚችሉት?ኢየሱስ አምላክ ነው ለሚለን አስተማሪ እኮ ሊኖረን ሚገባ አጸፋ በእውነት ኢየሱስ አምላክ ነው፡ወይም ደግሞ እንዴት አምላክ ሊሆን ይችላል ሚል አከራካሪ ጽንፍ እንጂ አሜን ማለት የአሜንን ትርጉም መሳት ነው!
«ኢየሱስ ያድናል»በዚህ ቃልስ አሜን ከማለት ይልቅ፡ኢየሱስ ማን ነው?እንዴትስ ያድናል?አዳኝነቱስ እንዴት ነው?እስከመቼስ ያድናል?ብሎ መጠየቁ የተሻለ አይመስላችሁም!
እኔ ለማለት የፈለግኩት ፕሮቴስታንታዊ አካሄድ ወደ ማኅበራችን አይግባ ነው!የመናፍቃንን ለመናፍቃን!


እኛ ግን ይሁን ይደረግልን ከማለታችን ቀድሞ በራሳችን ወይም በአባቶቻችን የተደረገ ጸሎት ስላለ ጸሎቱን ስናሳርግ የጸለይነው የሥጋም የነፍስም በረከት፡የሥጋና ነፍስን ድኅነት ያስገኝልን ስንል አሜን እንላለን!በጸሎት ውስጥ ደግሞ ምስጋና ወይም ልመና ወይም ደግሞ ምስጋናም ልመናም ይኖራሉ፡ስለሁለቱም አሜን እንላለን!

ለምሳሌ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ጸሎታችንን ስንጀምር«በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡አሜን!»እንላለን!
በዚህ ሆኅተ-ጸሎት ኃይለቃል ውስጥ ያለቸው አሜን ብዙ ትርጉም አላት!
ስናማትብ ከላይ ወደ ታች፡ከግራ ወደ ቀኝ መጨረሻ ላይም በረከት ለመቀበል የተዘጋጀ እጃችንን ወደ ሰውነታችን ማዕከላዊ ቦታ እናሳርፋለን!
ማማተብ ጸሎት ነው!ከማማተብ በኋላ አሜን ማለት ለጸለይነው ጸሎት አጸፋዊ ምላሽ ነው!
በአንድነት በሦስት ምትገለጽ እግዚአብሔር ሆይ ቅድመ ዓለም ከባህርይ አባትህ ከአብ የተወለድክ ድኅረ ዓለም ከሰማየ ሰማያት ወርደህ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልደህ ከጨለማ(ከሰዖል)ወደ ብርሃን ስለመለስኸን ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን ማለታችን ነው!
አንድም ደግሞ የቀደሙ አባቶቻችን አዳምና ወገኖቹን ከሲዖል ወደ ገነት እንደመለስ እኛንም እንዲሁ በምንጸልየው ጸሎት፡በምናቀርበው ምኅላ፡በምሰጠው መባዕ ከኃጢአት ባርነት አድነን ማለታችን ነው!
በሌላ ጊዜ ስለዚህ ኆኅተ-ጸሎት ሰፋ አድርገን ማውራት እንችላለን!



ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር!
@And_Haymanot
ተጽሀፈ በናዖድ፡
ወርኃ ነሐሴ 2010 ዓ.ም
🍋ኦሪት ምስክርነት በኹለት ወይም በሦስት እንደሚጸና ትናገራለች፡፡
በደብረ ታቦርም የወልድ የባሕርይ ልጅነት፣ የአብም የባሕርይ አባትነት በአምስት ሰማዕታት (ምስክሮች)
- በኹለት ነቢያትና በሦስት ሐዋርያት - ለሰው ኹሉ የታወቀ የተረዳ ኾነ፡፡ 🍋
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
📍 መልካም በአል📍
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@And_Haymanot
@And_Haymanot
በእንተ ቅድስት ድንግል ማርያም
@And_Haymanot

ከትውልድ ሊቆጠሩ ያልተገባቸው ሐሳውያን የክፋትና የክህደትን
ቃል እንደ ጸሎት ደጋግመው ስለሚናገሩና ስለሚጽፉ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም ያሰፈረውን ማስረጃ በአጭሩ እንዘረዝራለን ። በእምነት ያለነውን በእምነታችን ያጽናን በጥፋት መንገድ ያሉትንም ልቦናቸውን ያቅናልን ። አሜን ።

👉 1. ስለ ቅድስናዋ - የቅዱስ አምላክ እናት በመሆኗ [ኢየሱስ የጸነሰችው የወለደች ያሳደገችው የማህጸኗ ፍሬ ስለሆነ (ሉቃ 1:31:42 ፥ 2:7)] ወላዲተ አምላክ እያልን እንጠራታለን ። የቅዱስ አምላክ እናት ድንግል ማርያም ክርስቶስን ያህል መለኮታዊ አካል በማህጸኗ ስለወሰነች ቅድስት ትባላለች ። እኛ ክርስቲያኖችም ቅዱስ የተባልነው ቅዱሱ አምላክ ከርሷ ከተወለደና በቅዱስ ደሙ ከዋጀን በኋላ ነው ። ቅድስት ማርያም በነፍሷም በሥጋዋም ቅድስት ናት ። ሰው የሆነ ሁሉ ኃጢአትን ከመሥራት እንጂ ከማየት ፥ ከማሰብ ፥ ከመናገር የሚነጻ የለም። ርሷ ግን ከማየትና ከመስማት ፥ ከማሰብና
ከመናገር ሁሉ ንጽሕት ናት። ስለዚህም ድንግል በክልኤ (በሁለት ወገን ድንግል) ትባላለች። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከእግዚአብሔር ተልኮ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ ሲላት ፥ የተለየችና የተቀደሰች መሆኗን በምስጋና
ቃል መግለጡ ነው ። ቅድስት ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተነድታ ፥ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ብላ በመጮኽ ዳግም አረጋግጣለች ። ስለዚህም የመንፈስ ቅዱስ ቃል ፥ ድንግል ማርያም ቅድስት መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን እያልን በነፍስ በሥጋ ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን ።

👉 2. ድንግልናዋ - ቅድስት ማርያም እመቤትነትን ከገረድነት ፥ እናትነትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የያዘች ስለሆነችም የክብር ስሟ ድንግል ወእም እም ወዓመት የሚል ነው ። ድንግልናዋም ዘለዓለማዊ ስለሆነ ድንግል ዘለዓለም እንላታለን ። በአይሁድ ዘንድ ንጽሕናና ድንግልና የተወደደ፥ የተለመደ ፥ የተቀደሰም ህግ ነበር ። ይህን ህግ አፍርሶ የሚገኝ ወደ እሳት
ይጣላል ፥ በድንጋይም ተወግሮ ይሞታል። ስለዚህም ወንድ ሚስት እስኪያገባ ፥ ሴቷም ባል እስክታገባ ድረስ በድንግልና መኖር ግዴታቸው ነው ። በመሆኑም እነዚህ ደናግሎች ከጋብቻ
በመራቅ ማለት ከሥጋዊ ሥራ ድንግል ይሁኑ እንጂ ከሐሳብ ፥ ከማየት ፥ ከመስማትና ከመናገር ድንግሎች አልነበሩም ። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በዘመኗ ከነበሩት ደናግል
ተለይታ ፥ ከሐሳብ ድንግል ናት ፥ ከማየትና ከመስማት ድንግል ናት ፤ ክፋት ከመሥራትም ድንግል ናት ። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ንጽሕናና ቅድስና
በመረዳት "እሞሙ ለሰማዕታት ወእኅቶሙ ለመላእክት ትምክህቶሙ ለወራዙት ወለድንግል" ማለትም "ለሰማዕታት እናታቸው ለመላእክት እህታቸው ለደናግላን ትምክህታቸው"
እያለች ታመሰግናታለች ።

👉 3. ቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና እንዲገባት ፤ እመቤታችን ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ስለሆነች ፥ ዘወትር
ምስጋና ይገባታል ። የመጽሐፍ ማስረጃዎቻችንም የሚከተሉት
ናቸው
🙏 ሀ/ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምስጋና (ሉቃ 1:28)
🙏 ለ/ የቅድስት ኤልሳቤጥ ምስጋና (ሉቃ 1:42-43)
🙏 ሐ/ ትውልድ ሁሉ እንዲያመሰግናት የእመቤታችን የምስክርነት ቃል (ሉቃ 1:48)
🙏 መ/ አንዲት ሴት የተሸከመችህ ማኅጸን ቡርክት ናት አጥብተው ያሳደጉህ ጡቶችም ብሩካን ናቸው በማለት ያቀረበችው ምስጋና (ሉቃ 11:27)
🙏 ሠ/ ቅዱስ ጳውሎስም እግዚአብሔር ያከበረውንና የመረጣቸውን የሚከራከርና የሚወቅስ ማነው? እግዚአብሔር ያጸደቀውንስ የሚኮንን ማነው? በማለቱ (ሮሜ 8:33)
🙏 ረ/ ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ብሎ መጽሐፍ ስለሚዘንያ (ሮሜ 13:7) እመቤታችን ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል አለች እንጅ የተወሰነ ቀንና የተለየ ህዝብ አልጠቀሰችም ፤ መልአኩም ቡርክት ነሽ አለ እንጂ ነበርሽ ብሎ ስለአለፈው ብቻ አልተናገረም ፤ ቅድስት ኤልሳቤጥም ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ አለች እንጅ ነበረሽ አላለችም ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይኸን ሁሉ አስረጅ ገንዘቧ ስላደረገች ፥ ከቀድሞ ጀምሮ ዛሬም ወደፊትም ንጹሕ
ክብርና ምስጋናን ለእመቤታችን በሰፊው ሰጥታ ስታመሰግን ትኖራለች ።

👉 4. ክብር እንደሚገባት:- ቅድስት ድንግል ማርያም ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ እርሷ በማህጸኗ ወስናለችና ፥ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነ ክብር አላት ። እንዲህም ከሆነ ከሰማይ ከምድርም እርሷ
ትበልጣለች እርስዋም ትከብራለች ማለትም በሰማይና በምድር ካሉት ከግዙፋኑና ከረቂቃኑ ፍጥረታት ሁሉ እርስዋ ትበልጣለች እርስዋም ትከብራለች ። ልዑልና ኃያል እግዚአብሔር ማህጸኗን ዙፋኑ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን አድሯልና ።
እግዚአብሔር በመንፈሱ በሰው ላይ ለማደር እንኳን ሰው አላገኘም ነበር ። ነገር ግን ቅድስት ማርያም በንጽሕና
በድንግልና ብትገኝ የልዑል እግዚአብሔር ማኅደር ለመሆን
በቃች ።
ስለዚህ ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች የሆነ ክብር ተገባት ። ጌታችን ራሱን ከዓለም ግሳንግስ አንጽቶና በድንግልና ጠብቆ ህዝብን ስለንስሐ ያስተምር የነበረውን ዮሐንስን እንኳን፥ ሴቶች ከወለዱት እንደ ዮሐንስ የለም ብሎ ሲመሰክርለት እመቤታችንንማ ከንጽሕናዋ ከድንግልናዋ ጋር የአምላክ እናት ስለሆነች ከሁሉ በላይ እንዴት በበለጠ አትከብር? አምላክ የርሷን ሥጋ ተዋሕዷል ሰውም በዚህ ሥጋና ደም
ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆ የእግዚአብሔር መንግሥትን የሚወርስ
ሆኗልና በክርስቶስ ደም ድኛለሁ የሚል የሰው ልጅ ሁሉ ሊያከብራት ይገባል ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ምክረ አበው ❤️
ወዳጄ፥ ሕይወት አጭር ናት። ዛሬን እንጂ ነገን ስለመኖርህ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ስለዚህ ዛሬን መልካም አስብ፤ ለሌሎች መልካም አድርግ። በሙሉ ልብህ እመን። ስላለህ ነገር አመስግን። ሰው አትበድል ነገር ግን ብትበድል ይቅርታን ጠይቅ፤ 🙏 ቢበድሉህም ይቅርታ እስኪጠይቁህ ሳትጠብቅ ይቅርታን አድርግ። የዋህ ሁን ነገር ግን ይቅርታ ያደረክለት ሰው ዳግም ይበድልህ ዘንድ ሞኝ አትሁን።
@And_Haymanot
🌸🌸 መልካም ዕለተ ሰንበት🌸🌸
🌸🌸 መልካም በአል 🌸🌸
የእመቤታችን ዕርገት´´

በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን መምህር)
@And_Haymanot
በውሥጥ በጠየቃችሁን መሰረት ሥለ እመቤታችን ዕርገት ታሪክ እና ማሥረጃን በአንድ ላይ የተዘጋጀን ምላሽ ልናቀርብ ወደናል፡፡ የእናት ጡት ነካሽ ተሃድሶዎች ይህን እውነት መቀበል ቢከብዳቸው በዘርያዕቆብ ያመጣችሁት ታሪክ ነው ሢሉን ይደመጣሉ ይህ እነሱ እንደሚሉት የእመቤታችን ዕርገት ፈጠራ ሳይሆን(ላቲ ስብሃት) በአለም ላይ በተለያዩ ሃገራት የሚከበር እውነት ነው እንጂ፡፡ እነሆ ክፍል ፩
ነሐሴ 16 ቀን የእመቤታችንን ዕርገት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፤ የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር ከቆየች በኋላ፤ ዓለምን ለማዳን በዕለተ ዓርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜም የሚወድዳት እናቱን
ለሚወድደው ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ “እነኋት እናትኽ” በማለት አደራ በመስጠት በዮሐንስ በኩል ለሚወድደን ለእኛ የአደራ ልጆቿ እንድንኾንና የአደራ እናታችን እንድትኾን ታላቅ ስጦታን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ሥር ሰጠን (ዮሐ ፲፱፥፳፮‐፳፯)፡፡ በዚኽም መሠረት ሐዋርያትም ከአምላካቸው የተሰጠቻቸው የአምላካቸውን እናት ይዘው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ፸፪ት ቋንቋ ገልጾላቸው ታላቅ መንፈሳዊ ኀይልን ሰጣቸው (የሐዋ 1፥፲፬)፤ ዮሐንስም በእናትነት የተቀበላት ቅድስት ድንግል ማርያምን በቤቱ 15 ዓመት አኑሯታል፡፡ ከዚያም ልጇ ክርስቶስ
ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት፤ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን
ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ
አለቀሱ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ
እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ከዚያም ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፤
ሐዋርያት በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው ለምቀኝነት አያርፉምና
ቀድሞ ልጇ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ እያስተማሩ ኖሩ ከመቃብሩም ተአምራት ይደረጋል፤ አሁን ደግሞ ርሷ ሞተች፣
ተነሣች፣ ዐረገች ብለው ሊያስተምሩ አይደል፤ “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ
የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ይቤ ዮሐንስ ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ
ወዘንተ ብሂሎ ወድቀ በላዕሌሃ” ይላል (ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና
ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡
ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን
በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ወፍና ሠርክ ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡ ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር
እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ እነሱም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ
ሳናይ ብለው ሱባኤ ነሐሴ 1 ዠመሩ ነሐሴ 14 ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡
በተወደደች ዕለት ነሐሴ 16 “ወአዘዞሙ እግዚእነ ለሰብአቱ ሊቃነ መላእክት ከመ ይጸውዕዋ ለምድር” (ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ምድርን ይጠሯት ዘንድ አዘዛቸው)
እነርሱም ምድርን “ይኤዝዘኪ እግዚእነ ከመ ታውጽኢ ሥጋሃ ለእሙ ቅድስት” (ጌታችን የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ ያዝሻል) አሏት፤ ያን ጊዜ ልጇ “ንዒ ኀቤየ ወላዲትየ ከመ አዕርጊ ውስተ መንግሥተ ሰማያት” (ወደ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ እናቴ ወደኔ ነዪ) አላት፤ ያን ጊዜ በልጇ ሥልጣን የቅድስት
ድንግል ማርያም ነፍሷና ሥጋዋ ተዋሐዱ፤ ነሐሴ 16 ዕለትም ከሞት ተነሣች፡፡ ያን ጊዜ “ወረዱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት” ይላል ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ በታላቅ ግርማ ወረዱ፤ ነቢዩ ዳዊትም “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ” (ንግሥቲቱ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ደርባ ደራርባ በቀኝኽ ትቆማለች) እያለ ይዘምርላት ነበር፤ አየሩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመላ፤ እጅግ
የሚያስደንቅ መዐዛ አካባቢን ዐወደው፡፡ ያን ጊዜ በታላቅ ክብር በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ሰማዩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመልቶ የአምላክ እናት በክብር ስታርግ ተመለከተ፤ ያን ጊዜ ነገሩ ረቆበት ምን ይኾን እያለ ሲል ቅዱሳን መላእክት
የእመቤታችን ዕርገት እንደኾነና እጅ እንዲነሣ ነገሩት፡፡ ርሱም “ከቶ ምን አርጌ ይኾን፤ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ
ቀረኊ ዛሬ ደግሞ የርሷን ትንሣኤ ሳላይ ልቅር” ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ይላል ተበጻብጾ ሊወድቅ ወደደ፤ እመቤታችንም “አይዞኽ አትዘን እነሱ ሞቴን አይተዋል እንጂ ዕርገቴን አላዩም አኹንም እመቤታችን ተነሣች ዐረገች ብለኽ ንገራቸው” ብላ ለበረከት ሰበኗን ሰጠችው፡፡ ርሱም በደስታ
ተመልቶ ሐዋርያት ያሉበት በመኼድ የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ ብሎ ጠየቃቸው፤..... ይቀጥላል
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የእመቤታችን ዕርገት
ክፍል ፪
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን መምህር)
@And_Haymanot
ክፍል አንድን ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/795
....... እመቤታችን ሞተች ቀበርናት አሉት፤ “መቼ ሞተች?” አላቸው በጥር አሉት፤ “መቼ ቀበራችኋት?” አላቸው
በነሐሴ አሉ፤ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይኽ ነገር እንዴት ይኾናል አላቸው፤ ቅዱስ ጴጥሮስም ቶማስን ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ አላምን ብለኽ የጌታን ጐን የዳሰሰ እጅኽ ተቃጥሎ ነበር፤ አኹን ደግሞ እኛ ብንነግርኽ አላምን ትላለኽ ብሎ፤ “ወነሥአ መክርየ” ይላል መቆፈሪያ ይዞ ኼዶ ይቆፍር
ዠመር፤ ርሱም የያዘውን ይዟልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፤ ቈፍረው ሲያጧት ደነገጡ፤ ቶማስም አይዟችኊ አትደንግጡ እመቤታችን እኮ በመላእክት ምስጋና ወደ ሰማይ አረገች ብሎ
ሰበኑን አሳያቸው፤ እነርሱም ለበረከት ሰበኑን ተካፍለውታል፡፡ ዛሬም ሐዋርያዊት የኾነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያናችን ይኽነን በማሰብ በመስቀል ሥር የሰበኗ ምሳሌ
የሚኾን ሰፊ ጨርቅ ታደርጋለች፡፡
ባመቱ ቶማስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በድጋሚ ሐዋርያት ሱባኤ ሲገቡ ክብር ይግባውና ጌታችን በደመና ነጥቆ ወስዶ ሥርዓተ ቊርባንን ፈጽሞላቸው፤ ስለ እናቱ ዕርገት በዓለሙ ኹሉ ዙረው
እንዲያስተምሩ አዝዟቸዋል፡፡ እነርሱም ዓለምን ዞረው ወንጌልን ሲያስተምሩ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት ሰብከዋል አስተምረዋል፡፡
ጌታችን እንኳን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን በዠርባዋ ያዘለችውን በክንዶቿ የታቀፈችውን ከሥጋዋ ሥጋን
ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የኾነው ታቦቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን ትቅርና ያገለገሉት ወዳጆቹን እንኳን ሞትን ሳያዩ ወደ ሰማይ እንደወሰዳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስናነብብ፤ ለምሳሌ ሔኖክ ሞትን ሳያይ በሕይወቱ ሳለ እግዚአብሔር እንደወሰደው በዘፍ ፭፥፳፬ እና በዕብ ፲፩፥፭ ላይ ሲጠቀስ፤ ነቢዩ
ኤልያስም ሞትን ሳያይ በእሳት ሠረገላ ተነጥቆ ወደ ሰማይ እንደወጣ (፪ነገ ፪፥፲፩‐፲፪) ተጽፎልናል፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከእግረ መስቀሉ ሥር በጌታ ሥልጣን ስለተነሡ ቅዱሳን ማቴዎስ ሲጽፍ “መቃብሮችም ተከፈቱ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ” ይለናል (ማቴ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስም ወደ ሰማይ ስለመነጠቅ “ሰውን በክርስቶስ ዐውቃለኊ በሥጋ እንደ ኾነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጪ እንደ ኾነ አላውቅም እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲኽ ያለው ሰው ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ
ተነጠቀ” (፪ቆሮ ፲፪፥፪) በማለት ሲናገር፤
በዕለተ ምጽአት ስለሚከናወነው ደግሞ በ፩ተሰ ፬፥፲፯ ላይ “ከዚያም በኋላ እኛ
ሕያዋን ኾነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲኹም ኹልጊዜ ከጌታ ጋር እንኾናለን” በማለት እንደገለጸው የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግልን ወደ ሰማይ ማረግ በዐይኑ የተመለከተው ዮሐንስም “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት መስክሮላታል (ራእ ፲፩፥፲፱)፡፡....ይቆየን
፩ ኃይማኖት
ለአስተያየት 👉 @AHati_Haymanot
Join 👉 @And_Haymanot
የእመቤታችን ዕርገት
ክፍል ፫
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን መምህር)
@And_Haymanot
.... ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና እንደምናገኘው በመቃብር ውስጥ
መፍረስ መበስበስ የኀጢአት ውጤት ሲኾን ትእዛዝን የጣሰውን አዳምን “ዐፈር ነኽና ወደ ዐፈርም ትመለሳለኽና” በማለት ተረግሞ ነበር (ዘፍ ፫፥፲፱)፤ በዚኽም ጌታ እስኪመጣ ድረስ
ሥጋዊ ደማዊ የኾነው ኹሉ ወደ መቃብር ሲወድቅ፤ ርሷ ግን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ይኽነን መርገም ከመስማታቸው በፊት ከነበራቸው ንጽሕና
የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ስትኾን ክብር ይግባውና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና እናቱም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ዐርጋለች፤ ርሱን በመፅነስና በመውለድ ዕድፍ ጉድፍ
ያላገኘው ያልተለወጠ ድንግልናዋ፤ የተሸከመው ማሕፀኗ፤ የታቀፉት ክንዶቿና፣ የዳሰሱት እጆቿ፤ የሳሙት ከንፈሮቿ ያሳደጉት ጡቶቿ፤ ከርሱ ጋር የተመላለሱ እግሮቿና፤ ያዘለው ዠርባዋ፤
ብሩሃት የሚኾኑ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ያላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች የሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ብሥራትን የሰሙ ዦሮቿ ፈጽመው በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረት የለባቸውም፤ ከርሷ ሥሮችንና ጸጒርን፣ ደምንና ዐፅምን ነፍስንና ሥጋን ነሥቶ
አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮቱ ጋራ አንድ ያደረገው ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል
ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የቆየ አስተምህሮ ሲኾን በነሐሴ ወር የሚውለው የፍልሰቷ ክብረ በዓል በፍልስጥኤም ውስጥ ከ፬፻ ዓመት በፊት እንዲኹም ወደ ጋውል ከ፭፻ ዓመት በፊት ደርሷል ይኽ ኹሉ ለረዥም ዘመናት የተከናወነውና የተከበረው የታሪክ
ምስክርነት የሚያስረዳን ፍጹም የኾነውን ዕርገቷን ነው፤ ስለእመቤታችን ዕርገት ያስተማሩና የጻፉ በርካቶች ጥንታውያን
የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሲኖሩ ከእነዚኽ መኻከልም በ፫፻፹ ዓ.ም በኢየሩሳሌም ጳጳስ የነበረው ጢሞቴዎስ (ድንግል
እስካኹን ድረስ ሟች ያለመኾኗ ምክንያት በርሷ ውስጥ ያደረው ጌታ ወደ ማረጊያ ክልሎች ስለወሰዳት ነው) በማለት ሞት
በሌለበት በዕረፍት ስፍራ ልጇ ያሳረጋት መኾኑን መስክሯል፡፡ በተጨማሪም ከ70 ዓ.ም ዠምሮ ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ
በነበረው ስደት በክርስቲያኖች ዘንድ ዐፅመ ቅዱሳን ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ሲኾን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት በሙሉ እንደሚያስረዱን በዚያ የስደት ዘመን ክርስቲያኖች በድፍረትና ሐላፊነትን ተሸክመው በቈራጥነት የሰማዕታትን ሰውነት ከመግደያው ስፍራ በመውሰድ ዐፅማቸውን በክብር ይጠብቁ የነበረ ሲኾን ይኽነንም አጥብቀው በመጠበቃቸውና ለትውልድ
በማስተላለፋቸው የከበረ ዐፅማቸው ባረፈበት ቦታ ላይ ዛሬ አብያተ ክርስቲያን ታንጸውበት እጅግ በርካቶች ጐብኚዎች
እየጐበኙት ሲገኙ ለምሳሌ ያኽል የነቅዱስ ጴጥሮስ፣ የነቅዱስ ጳውሎስ፣ የነቅዱስ ቶማስ፣ የነያዕቆብ ወ.ዘ.ተ የከበረ ዐፅማቸው ስፍር ቊጥር በሌላቸው ሰዎች ከጥንት ዠምሮ እስከዛሬ ድረስ ሲጐበኝና ሲታይ የቅድስት ድንግል ማርያምን አንድ የራሷን ጠጒርና የእጇን ጥፍር አገኘኊ የምትል ምንም ሀገርና ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ፈጽማ የለችም ምክንያቱም አምላካችን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ያደረባት የአምላክ ታቦት
ክቡር ዳዊት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” ብሎ ትንቢት እንደተናገረላት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ በዕረፍቱ ስፍራ አለችና ነው፡፡ ይኸውም ሊታወቅ የዓለም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን በ፬፻ ዓ.ም አካባቢ ነግሦ የነበረው ንጉሡ ማርሲያን የኢየሩሳሌሙን ፓትሪያርክ የቅድስት ድንግል ማርያም ዐፅም ካለ ወደ ቊስጥንጥንያ እንዲያመጣለት ቢጠይቀው ርሱ ግን እመቤታችን እንዳረገችና ምንም ዐይነት የርሷ ቅሪት
እንደሌለ አስረድቶ ስለ ዕርገቷ ጽፎለታል፤ የሚገርመው ቅሪቶች
ከፍተኛ ዋጋ ስላላቸው ብዙ ሰዎች ወደ ከተማቸው ጐብኚዎችን ለመሳብ ሲሉ አስመስለው ለመሥራት በመሞከራቸው ብዙዎች ተከሰው የነበረ ሲኾን ለምሳሌ አክሊለ ሦኩን መስቀሉን አስመስለው ለመሥራት ከበፊት ዠምሮ ቢሞክሩም ኾኖም ግን የቅድስት ድንግል ማርያም አካል አለን የሚልና የሚሞክር
ከጥንት ዠምሮ እስከ ዛሬ በዓለም ላይ ለምን ጠፋ? ቢባል ማንም ሰው ይኽነን ሐሰት ስለማያምንና ከሐዋርያት ጊዜ ዠምሮ እስከ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እስከ አኹንም ድረስ
የቅድስት ድንግል ማርያም አካል ፈጽሞ በምድር ላይ እንደሌለና ወደ ሰማይ በአካል እንዳረገች ስለሚታወቅ ነው፡፡
በተጨማሪም ከመዠመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን-፲፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስም የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በቤተ ክርስቲያን፣ በነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ኹሉ ሙሉ
በሙሉ የታወቀ በመኾኑ በዕርገቷ ዙሪያ ምንም ዐይነት የጥርጥር ጥያቄን ያቀረበ ማንም የለም፡፡

ዛሬ በጭፍኑ አንዳንዶች
ፕሮቴስታንቶች የካዱትን ይኽነን እውነታ የእምነቶቻቸው መሥራቾች እንኳን ደፍረው አልተናገሩትም ለምሳሌ የፕሮቴስታንት ሪፎርመር የኾነው ሄንሪች ቡሊነግር በ፲፭፻፴፱ (1539 ዓ.ም) ላይ ጣዖታትን ተቃውሞ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስለማረጓ ሲገልጽ (ኤልያስ በሥጋና በነፍስ ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ወጣ፤ በርሱ ስም በተሠየሙ ባንዳቸውም ቤተ ክርስቲያን
አልተቀበረም፤ ይኽም ዘላለማዊነት እግዚአብሔር ለሚያምኑበት ለነቢያቱ ድንቅና ለማይነጻጸሩ ፍጡራኑ እግዚአብሔር እንዳዘጋጀ ያሳውቀናል … በዚኽ ምክንያት የአምላክ እናት የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ፣ አካሏ ንጹሕና ኀጢአት አልባ የኾነው የድንግል ማርያም ንጹሕ የተቀደሰ ሰውነቷ በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ እንዳረገ እናምናለን)

ዛሬ ደግሞ ጥቂቶች ይኽነን እውነት መቃወማቸው የእምነት መሪዎቻቸው እንኳን ያስተማሩትን ትምህርትና የጻፏቸውን መጻሕፍት እንዳላነበቡ ያጋልጥባቸዋል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ይከበራል፡፡
ወስብሃት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
በተጨማሪ ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/65
Join ====>👉 @And_Haymanot
የእመቤታችን ዕርገት.pdf
480.7 KB
``የእመቤታችን ዕርገት ´´
ተወዳጆች በዚህ ርዕሥ ሲቀርቡ የነበሩትን ሶስት ክፍላት በ Pdf አቅርበንላችኋል፡፡ እንድታነቡት እንጋብዛለን
ተጨማሪ ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/65
@And_Haymanot
❤️ሞትማ በሞት ተሸንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ሃይል ያገኛል❤️
“ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ እነሆ ክረምት አለፈ ዝናቡም አልፎ ሄደ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፡፡ የዜማም ጊዜ ደረሰ የቀረ… ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፡፡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ” መኃ 2፡10-13
እልልልልልልልልልል
✞ አርጋለች ማርያም ተነስታለች ✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት????
@And_Haymanot
አንድ እህታችን በውሥጥ የላከችልን መልዕክት ነው፡፡
ስለ እመቤታችን ሲነሳ አይናቸው ደም የሚለብሰው የተሃድሶ መናፍቃን ዛሬም ከእናታችን እቅፍ ሊለዩን ተነስተዋል ከጥፋት ትምህርታቸ አንዱ
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት። በዛ ዘመን ብንኖር ከእኛ መሃል ከአንዳችን ኢየሱስ ይወለድ ነበር ብለው ያስተምራሉ ያምናሉ።

-ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን ከመውለድዋ በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች ሴት ናት ።
እንኳን የአምላክ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለም ማንኛችንም እግዚአብሔር የፈጠረን ፍጡር ወደዚህ አለም ከመምጣታችን በፊት ለምን አላማ እንደምንወለድ
እንኳን ገና ሳንፈጠር እግዚአብሔር ያውቃል:: ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ኤርምያስ 1:5 እንዲህ ይላል ።
የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ
ለአህዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።

-ቅድስት ድንግል ማርያም ለአምላክ እናት እንድትሆን ገና ሳትፈጠር እግዚአብሔር የመረጣት ሴት ናት።
ከእሷም ባይሆን ከሌላ ይወለድ ነበር ለሚሉ የጥፋት ልጆች ከእግዚአብሔር አላማና ሃሳብ ጋር የተጣሉ የእግዚአብሔርን ሃሳብ በራሳቸው አመለካከት እና ሃሳብ ለመቀየር የሚያስቡ ደፋሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም
እንዲወለድ ነበር የእግዚአብሔር አላማ::
ከእሷ ባይሆን ለሚሉት የእግዚአብሔር ሀሳብ ሳይሆን የቀረበት ግዜ የለምና ከእሷ ውጭ ከማንም ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ሃሳብ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲወለድ እንጂ ሌሎች እንደሚፈላሰፉት ከአዳራሽ ጨፋሪዎቻቸው ሴቶች መሃከል ኢየሱስ ሊወለድ አይችልም::
ከፍጥረት ሁሉ ፣የአምላክ እናት እንድትሆን የተመረጠች ቅድስት ማርያም ብቻ ናት። ለመዳናችን ምክንያት ለሆነች ከሴቶች ሁሉ ለተለየች የአምላክ እናት ክብር ይገባታል ።

በተጨማሪም ሊታወቅ የሚገባው ማንኛውም ሠው በነብያትና በሐዋርያት መንገድ መጓዝ ከቻለ ሐዋርያት የደረሱበትን የክብር ደረጃ መድረስ ይችላል፡፡ ነገር ግን በክብር ላይ ክብር ብናገኝ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኝ ስራ ብንሠራ እንኳ ድንግል ማርያም የደረሰችበት የክብር ደረጃ ላይ መድረስ
የሚችል ሰው ማንም የለም፡፡ ወደፊትም እንደዚህ አይነት ክብር እና ጸጋ ለማንም አይሰጥም፡፡፡፡
.....ይቆየን ከሰሞኑ እመቤታችን አንዲት ድንግል እናት ሥለመሆኗ በሰፊው እንመለሳለን፡፡
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን
፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው
ለእኛም ግለጽልን።
አሜን አሜን አሜን!!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የድንግልን ትንሣኤ በኩረ ፕሮቴስታንት የኾነው ማርቲን ሉተርና ስዊዘርላንዳዊው ቡሊንገር እንኳ በአንክሮ ያምናሉ ቡሊንገር ትንሣኤዋን ከኤልያስ ዕርገት ጋር በማነጻጸር ሲያስተምር ሉተር ደግሞ እንዲኽ ይላል" there can be no doubt that the Virgin Mary is in heaven, how it happened we do not know ፤ ጥርጥር ሊኖር አይችልም፡ ድንግል ማርያም በሰማይ ናት፡ እንዴት ኾነ? እኛ አናውቅም" ብሏል Martin Luther's works,vol.10, pg.268
ድንግል ማርያም አልተነሣችም ለሚሉ እሆነ ብለናል፡፡
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
አንዲት ድንግል
@And_Haymanot
ሚያትተው፦
፩ ስለ እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና
፪ እመቤታችን አርጋ በ እግዚአብሔር ቀኝ ቆማ ስለ እኛ መማለዷ…

[[[[[[[[ተወዳጆች ነገረ ማርያምን ሥናነሳ በውሥጥ ጥያቄ የሚያነሱት በዝተዋልና የምትጠይቁ እንድትታገሱን ለማለት እንወዳለን፡፡ በተጨማሪም ሌሎች መምህራንንም ለማሳተፍ ስላሰብን Bot መሥራት የምትችሉ በውሥጥ አናግሩን
@AHati_Haymanot ]]]]]]]]]
``አንዲት ድንግል´´
የተሃድሶ መናፍቃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከሚቃወሙበት ነገሮቹ አንዱ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልና ላይ ነው ነገር ግን መታደስ ያለበት የራሳቸው አስተምሮ እንጂ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን አይደለችም እስቲ በምድር ላይ ብቸኛ ዘላለማዊ ድንግል ስለሆነችው ስለ"አንዲቷ"ድንግል ማርያም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ምን እንደሚል እንይ፦


✞ ቅዱስ ሉቃስ ☞ በሉቃ 1፥26 - 27 ላይ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ በማለት አንዲት ድንግል መሆኗን ጽፎልናል።

አንዲት የሚለው ቃል እንዲው ጽሁፍ ለማሳመር የገባ ቃል አይደለም መንትያ፣ አቻ፣ ወደር፣ ተወዳዳሪ... የሌለው ነገር "አንዲት" እየተባለ ይጠራል መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ "አንዲት" እያለ የገለጻቸው ነገሮች አሉ ለምሳሌ፦

☞ መዝ 26፥4 እግዚአብሔርን "አንዲት" ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ

☞ ኤፌ4፥ 5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት "አንዲት" ጥምቀት

☞ ሐዋ 4፥32 ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ "አንዲትም" ነፍስ ነበሩአቸው

☞ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት "በአንዲት" ክብርት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን ኃጢአት በሚሠረይባት "በአንዲት" ጥምቀትም እናምናለን ( የሃይማኖት ጸሎት)

በዚህ የተነሳ ቅዱስ ሉቃስ ሲጽፍልን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ "አንዲት" ድንግል ተላከ ብሎ ጽፎልናል ነገር ግን ልናስተውል የሚገባው ነገር የአጻጻፍ ዘይቤ ቢሆን ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ድንግል ተላከ ብሎ መጻፍ ይችል ነበር ነገር ግን የምስጢር፣ የክብር፣ የልዕልና ጉዳይ ስለሆነ ወደ "አንዲት" ድንግል ብሎ ጻፈልን ቅዱስ ሉቃስ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ሲያበስራት በቦታው አልነበረም ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ሲጽፍልን "አንዲት" ድንግል ብሎ እንዲጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶታል።

☞ ለምን ቅዱስ ሉቃስ "አንዲት" ድንግል ብሎ ጻፈልን?

1ኛ፦ የእመቤታችን ድንግልና ልዩ ስለሆነ፦ የእመቤታችን ድንግልና በዚህ ምድር ላይ ታይቶ ተሰምታ የማይታወቅ ነው ወደ ፊትም አይታወቅም ስለዚህ በተራ ቃል ሊገልጻት ስላልፈለገ "አንዲት" ድንግል ብሎ ገለጻት በምድር ላይ ብዙ ደናግላን ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን ድንግልናቸው ጊዜያው ነው የእመቤታችን ድንግልና ግን ዘላለማዊ ድንግልና ነው ብዙ ቅዱሳን ለክርስቶስ ፍቅር ሲሉ በምናኔ ጸንተው በድንግልና ኖረዋል ድንግልናቸው ግን በስጋ ነው እመቤታችን ግን በሐልዮ(በማሰብ) በነቢብ(በመናገር) በገቢር (በተግባር) ከሚሰሩ ሐጢአቶች በነፍስም በስጋም ጭምር ድንግል ናት እመቤታችን (ቅድመ ፀኒስ፣ጊዜ ፀኒስ፣ድህረ ፀኒስ፣ቅድመ ወሊድ፣ጊዜ ወሊድ፣ድህረ ወሊድ) ድንግል ነች።ስለዚህ ብቸኛ ተወዳዳሪ የሌላት ድንግል ስለሆነች ቅዱስ ሉቃስ "አንዲት" ድንግል ብሎ ገለጻት።
ልናስተውል የሚገባው ነገር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "አንዲት" ድንግል ያስባላት ድንግልናዋ ብቻ አይደለም ነገር ግን የድንግልናዋን ቅድስና ማንሳት ስለሚገባን ነው እንጂ እኛ ኦርቶዶክሳውያን እመቤታችንን ድንግል ብለን ስንጠራት ግን እናትነትንም አስተባብራ የያዘች ናት ስለዚህ እናትነትና ድንግልናን አስተባብራ የያዘች ብቸኛ ሰው ስለሆነች "አንዲት" ድንግል ተባለች ለዛም ነው ጠቢቡ ሰሎሞን ☞ በ መኃ 4፥12 ላይ "እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት" በማለት ያወደሳት።

ጠቢቡ ሰሎሞን እመቤታችንን እህቴ ያለበት ምክንያት አባቱ ዳዊት ☞ በ መዝ 44፥10 ላይ "ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ" ስላላት ነው አባት ልጄ ሲል ወንድም ደግሞ እህቴ እንደሚል ማለት ነው ነገር ግን ጠቢቡ ሰሎሞን እህቴ ብቻ ብሎ አልቀረም "ሙሽራዬ" ብሎ ቀጠለበት እንጂ እንደሚታወቀው ሙሽሪት በሰርጓ ቀን ከትኛውም ሰው በበለጠ ትልቅ ክብር ነው የሚሰጣት ስለዚህ ጠቢቡ ሰሎሞንም ሙሽራዬ በማለት ለእመቤታችን ያለውን ትልቅ ክብርና ፍቅር በመዝሙሩ ገልጿል በመቀጠልም የተቆለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ በማለት ዘላለማዊ ድንግልናዋን ነግሮናል ከተዘጋ ከታተመ ምንጭ እንዴት ፈሻሽ ይወጣል? ብለን ከጠየቅን አይወጣም ከእመቤታችን ግን በተዘጋ ድንግልና ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወት ውኃ ምንጭ የሆነ ጌታ ተወለደ ስለዚህ የተዘጋ የውኃ ምንጭ ተባለች ለዚህም ነው ነብዩ ህዝቅኤል በትንቢቱ ☞ ሕዝ 44፥2 ላይ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል በማለት የተናገረው በር የተባለው የእመቤታችን ድንግልና ነው ይህ በር ጌታ ገብቶበታልም ወጥቶበታልም ነገር ግን በሩ አልተከፈተም ስለዚህ የምስራቅ በር የተባለችው እመቤታችን ጌታን በህቱም ድንግልና ጸንሳ በህቱም ድንግልና በመውለዷ ቅዱስ ሉቃስ "አንዲት" ድንግል ብሎ ጠርቷታል።


2ኛ፦ በእግዚአብሔር መንግስት "አንዲት" ንግስት ስለሆነች፦ ይህን ስንል ለዚህ ነው ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ☞ መዝ 44፥9 ላይ ´´ወትቀውም ንግስት በየማንከ…በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች`` ያለው ምክንያቱ ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ በዙፋኑ ሲቀመጥ ንግስቱቲ ደሞ በቀኙ ትቆማለች ንግስቲቱ ደሞ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት እሷም "አንዲት" ንግስት ናት ለዚህም ነው ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ በቀራንዮ ክቡር መስቀሉን ዙፋን አድርጎ አዳምን ነፃ ሲያወጣውና ዲያብሎስን ሲያስረው በቀራንዮ በመስቀሉ ስር ´ቆማ´ የነበረው:: ንግስት ከሆነች ደግሞ ስልጣን ስላላት ለአዳም መዳን ምክንያተ ድህነት የሆነች ብቸኛዋና ተነፃፃሪ የሌላት "አንዲት" ናት ስለዚህ "አንዲት" እያልን እንጠራታለን።

3ኛ፦ "አንዲት" እመ እግዚአብሔር ስለሆነች፦ ግሪኮች እመቤታችንን "ቴኦቶኮስ" ይሏታል ትርጓሜውም "የአምላክ እናት" ማለት ነው ለዛም ነው ቅድስት ኤልሳቤጥ ☞ በሉቃ 1፥43 ላይ ''የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?'' ያለችው ስለዚህ ብቸኛዋ የአምላክ እናት ስለሆነች "አንዲት" እያልን እንጠራታለን ሌሎች እናቶች ቢመሰገኑ ቅዱሳንን፣ ነገስታትን፣ ነቢያትን፣ አዋቂዎችን... ስለወለዱ ይሆናል የእኛ እመቤት ግን የዓለማት ፈጣሪን ስለወለደች ነው የምትመሰገነው ስለዚህ ቀና ስንል ወደ ሰማይ ዝቅ ስንል ወደ ቀራንዮ የማናጣት እመ አዶናይ "አንዲት" ናት።...... ቀጥሏል
👇👇👇 https://tttttt.me/And_Haymanot/817
አንዲት ድንግል
...... የቀጠለ
4ኛ፦ በክርስቶስ የማዳን ጉዞ ውስጥ ''አንዲት'' ስለሆነች፦ ይህም
❖ ክርስቶስ በቤተልሄም ሲወለድ እናቱ እመቤታችን ነበረች
❖ ክርስቶስ ወደ ግብጽ ሲሰደድ ይዛው የተሰደደችው እመቤታችን ነበረች
❖ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም የፋሲካ በዓልን ሲከበር እመቤታችን ነበረች
❖ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ ውኃውን ወደ ወይን ሲለውጥ አማላጇ እመቤታችን ነበረች
❖ ክርስቶስ በቀራንዮ በመስቀል ላይ እንደ ብራና ተወጥሮ ዓለምን ሲያድንና የአዳም ፍዳን ተፈጸመ ሲል ከመስቀሉ ስር እመቤታችን ነበረች
❖ በቤተ ክርስቲያን በልደት ቀን በበዓለ ሀምሳ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል በኢየሩሳሌም በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ሲወርድ እመቤታችን ነበረች... ለዛም ነው ቅዱስ ሉቃስ ☞ በሐዋ 1፥14 ላይ እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር። ያለው ስለዚህ በክርስቶስ የማዳን ጉዞ ውስጥ ከቤተልሄም እስከ ቀራንዮ ድረስ ያለች ብቸኛዋ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ "አንዲት" ናት።

ማጠቃለያ
ተወዳጆች ብዙዎች "አንዲቷን" ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ክደዋታል፣ ንቀዋታል፣ አቃለዋታል፣ ረስተዋታል፣ ሸሽተዋታል... ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ግን የመድኀናችን ምክንያት፣ የድህነታችን ተስፋ የሆነች የማትካድ፣ የማትናቅ፣ የማትቃለል፣ የማትረሳ፣ የማትሸሽ... አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደች "አንዲት" ድንግል ናት ለዛም ነው ልበ አምልክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ☞ መዝ 86፥5 ላይ እምነ ፅዮን ይብል ሰብዕ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ ያለው ጠቢቡ ሰሎሞንም በመዝሙሩ ☞ መኃ 6፥9፤ ርግቤ መደምደሚያዬም "አንዲት" ናት፤ ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት ብሎ የዘመረላት በመሆኑም ከሰው ልጆች በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደች ብቸኛዋ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ስለዚህ ከ72 አርድእት የሚመደበውና ምስለ ፍቁር ወልዳ ስዕልን የሳለው ቅዱስ ሉቃስ "አንዲት" ድንግል ብሎ ክብሯን፣ ልዕልናዋን፣ አንዲትነቷን ገልጾልናል የተሃድሶ መናፍቃኑም የራሳቸው አስተምሮ ይታደስ እንጂ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ፈጽሞ አትታደስም።
[[[[[በቅርቡ በነገረ ማርያም ላይ የተለቀቁ ጽሑፎችን በአንድ ላይ እናቀርባለን]]]]]
✞ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ ፍቅሯ ረድኤት በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር!!! አሜን ✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot