ከሞት በኋላ ያለ ህይወትና የፕሮቴስታንት አስተሳሰብ፡፡
@And_Haymanot
ከሞት በኋላ ስላለ ህይወትና በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን ምልጃን በተመለከተ ለፕሮቴስታንት ወገኖች ማስረዳት ብንሞክር ጥቅስ የሚል ጥያቄ ይከተላል፡፡ ከዚያ ጥቅሱን ማሳየት ሲጀመር ላለመረታት ስለጥቅሶቹ የተሳሳተ ትርጉም መስጠት ወይም
አልቀበልም ወደ ማለት ይኬዳል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በሰጠን ህሊና ነገሩን ማገናዘብ ከጥቅስ ያለፈ ተጨማሪ
ማስተዋል ነውና እንካችሁ፡፡ በውኑ በአጸደ ነፍስ ሆኖ ማማለድ? አለ ወይስ የለም?
የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ቀድሞ መጠየቅ ያለበት የሞት ትርጉምና ከሞት በኋላ ስላለው ሚና ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስለቅዱሳን ያላትን አስተምህሮና እምነት ለመቃወም ብቻ በተሳሳተ መነሻ ላይ ቆሞ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ መድረስ ራስን እንጂ ሌላ ማንንም አይጎዳም፡፡
ሞት ምንድነው? ከሞት በኋላ ያለንስ ሚና?
👉 #ፕሮቴስታንት ፡- ሞት ከምድራዊ ቤተክርስቲያንና ህብረት ፍጹም መለየት ነው፡፡ ከሞት በኋላ አንድ የፕሮቴስታንት አማኝ በምድር ስላለች ቤተክርስቲያንና አማኞች በፍጹም አይመለከተውም፡፡
ምንም ጥያቄ አያነሳም፡፡ አይጸልይምም፡፡ በሞት ምክንያት በሰማይ ያሉ የፕሮቴስታንት አማኞች ከምድራውያኑ ጋር የነበራቸው የግንኙነት ድልድይ ይቋረጣል፡፡ ሞት ፍጹም ወደ ሌላ የማይታወቅ አለም መሔድና በምድር ካለው ሕይወት መለየት
ነው፡፡ በምድር ስላለው ነገር በፍጹም ማወቅ አይችሉም፡፡ ቢችሉም ምንም ሚና የላቸውም፤ በምድር ካለች ቤተክርስቲያን ጋር በፍጹም ይቆራረጣሉ፤ በምድር ያሉትም እንዲሁ የሞቱ ፕሮቴስታንቶችን ፍጹም በሆነ መለየት ይለይዋቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ምንም ግንኙነት የለም፡፡ እንደ አለማውያን ሻማ
ከማብራት፣ ሐውልት ከመስራት ያለፈ ሌላ ነገር የለም፤ መንፈሳዊ ግንኙነቱ ፍጹም በሆነ ሁኔታ ይቋረጣል፡፡
👉 #ኦርቶዶክስ ፡- ሞት የቦታ ለውጥ እንጂ የግንኙነት መቋጫ አይደለም፡፡ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሞት ምክንያት በአጸደ ነፍስ ያሉና በምድር ያለች ቤተክርስቲያን ግንኙነት አይቋረጥም፡፡ እለት እለት ስለአብያተ ክርስቲያናት የሚያስጨንቃቸው
ክርስቲያኖች በስጋ ሲሞቱ፣ ወደ ናፍቆታቸው ወደ ክርስቶስ ሲሔዱ፤ በገነት ሲኖሩ እነርሱ ያዩትን ደስታ፣ ያገኙትን አክሊል፤ በምድር ያሉ ክርስቲያኖችም እንዲያገኙ የበለጠ ይናፍቃሉ፡፡ በምድር ሆነው የራሳቸውንም እድል ፈንታ ባላወቁበት ሁኔታ ስለሌላው ይለምኑ የነበሩ አሁን የናፈቁትን ሲያገኙ ያን ምህረትና ጽድቅ በምድር ያለነውም እንድናገኝ የበለጠ ይተጋሉ፡፡ ልዩነቱ
ቀድሞ በድካምና በትህትና ሆነው ይለምኑ ነበር፤ አሁን ግን ተሸልመዋልና በስልጣን ይለምናሉ፡፡ ቀድሞ የስጋ ድካምና ፈተና ነበረባቸው፣ አሁን ግን ከዚህ ነጻ በመሆናቸው ያለድካም ፍጹም
በሆነ ትጋት እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ ስለምድራዊቱም ቤተክርስቲያን ይለምናሉ፡፡
ስለሞትና ከሞት በኋላ ስላለን ሚና በምድር ያለን ኦርቶዶክሳውያንና ፕሮቱስታንቶች እንዲ ባለ ጽንፍ ተለያይተናል፡፡ ፕሮቴስታንቶች ስለሞቱ ወገኖቻቸው የሚሰጡት ትርጉምና ሚና
ኦርቶዶክሳውያን ስለሞቱና በሲኦል ካሉ ነፍሳት እንኳን ያነሰ ነው፡፡ በገነት በጽድቅ ያሉ ቅዱሳን ይቅርና በሲኦል ያሉ ነፍሳት እንኳን ቢሆኑ በዚያ ጽኑ መከራ ሆነው፣ በምድር በኃጢያት ስላለ ስለሚያውቁት ነፍስ ይገዳቸዋል፡፡ ራሳቸውን ማዳን ባይችሉ እንኳን እንደ ነዌ ያለ ልመና ማቅረብ አያቅታቸውምም፡፡ ነዌ
ስለራሱ ውኃ ለምኖ እንደማይቻል ሲረዳ ወዲያው በምድር ያሉ አምስት ወንድሞቹ ትዝ አሉት፡፡ እነርሱ ባለማወቅ ወደዚህ
መከራ እንዳይመጡ ናፈቀ፤ አብርሐምንም ለመነው፡፡ በሲኦል
ሆኖ እንዲህ ስለሌላ ሰው መጨነቅና፣ መለመን ከተቻለ በገነት ሆኖ ቢያንስ የነዌን ያህል እንኳን መጨነቅ፣ መለመን የለም ተብሎ እንዴት ይታሰባል? አንድ ፕሮቴስታንት ከሞትኩ በኋላ ገነትም ብገባ ሲኦልም ብገባ፣ በምድር ስላለችው ቤተክርስቲያን ቢያንስ እንደነዌ ወንድሞቼ ብዬ መጨነቅ፣ መለመን አልችልም ብሎ መደምደም እንዴት ያለ አስተሳሰብ ነው?
ፕሮቴስታንቶች ስለ ሞቱ ወገኖቻቸው የሚሰጡት ትርጉምና ሚና፤ በኛ በኦርቶዶክስሳውያን ዘንድ በገነት ካሉት ቅዱሳን ጋር ሳይሆን በሲኦል ካሉ ኃጥአን ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ኧረ እንዲያውም ያንሳል፡፡ እኛ በገነት ያሉ ቅዱሳን ይቅርና በሲኦል ያሉ ኃጥአን እንኳን በምድር ስላሉ ወንድሞቻቸው ሊጨነቁ፣
ሊለምኑ ይችላሉ እንላለን፡፡ ፕሮቴስታንት ግን ገነት ብንገባ እንኳን እንዲህ አናደርግም፤ በምድር ስላለች ቤተክርስቲያን አንለምንም ብለው ያምናሉ፡፡ የትኛውንም አስተሳሰብና እምነት ማራመድ ይቻላል፡፡ በአስተሳሰባችንና እምነታችን መካከል ግን የዚህን ያህል ልዩነት አለ፡፡ ከራሱ ህይወት ይልቅ ዕለት ዕለት ስለአብያተ ክርስቲያናት ሲጨነቅ የኖረው ቅዱስ ጳውሎስ አክሊል ሲሸለም፣ በገነት ሲሆን፣ ሲጸድቅ፣ ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልሆን እናፍቃለው እንዳለ፣ የሚናፍቀውን ካገኘ በኋላ በምድር ያለነውም ይህንን ክብር እንድናይ፣ የበለጠ ይተጋል፣ ይለምናል፣ እንደ ቀድሞ በትህትናና በድካም ሳይሆን በክብርና በስልጣን
ሆኖ ያለድካም ይተጋል እንጂ፣ ሁሉን እርግፍ አድርጎ ይተወዋል፤ አያገባውም ብሎ ማመን ምን ዓይነት የዋህነት ነው፡፡ ምንስ የሚሉት የመንፈሳዊ ህይወት ብስለት ማጣት ነው፡፡ የፕሮቴስታንት አገልጋይ የነበሩ ግን ከሞቱ በኋላ ፍጹም በሆነ ሁኔታ በምድር ካሉ ወንድሞቻቸው ይለያሉ፡፡ ምድራውያኑም ስለሞቱት ሻማ ከማብራትና ሐውልት ከማሰራት ያለፈ ምንም መንፈሳዊ ግንኙነት የላቸውም፡፡ ስለሆነም ኦርቶዶክሳውያን ስለዚህ ስናስብ የሞቱ ፕሮቴስታንቶች ግን ምን ነካቸው? እንዲህስ ሊሆኑ የሚችሉት የት ቢገቡ ነው? የሚል ጥያቄ ይፈጠርብናል፣ ክርስቶስ ራስ ሆኖ የመሰረታት ቤተክርስቲያንስ
በሞት ምክንያትስ እንዴት እንዲህ ትሆናለች?
በዲ/ን ሸዋፈራው አለነ
Join
👉 @And_Haymanot