ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱሳን አባቶች ምስክርነት
@And_Haymanot
✍ የተሃድሶ መናፍቃን እኛ ኦርቶዶክሳውያን መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርገን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ አድርገን ስናከብራት አምላክ ያደረግናት እየመሰላቸው ማርያምን አታምልኩ መመለክ ያለበት እግዚአብሔር አምላክ ብቻ ነው ብለው ይተቹናል ነገር ግን አበው ሲተርቱ አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል እንዲሉ የተሃድሶ መናፍቃኑም የማያውቁትን በመዘባረቅ የማትታደስ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን ለማደስ ይጥራሉ ዳሩ ግን እኛ ኦርቶዶክሳውያን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእግዚአብሔር ወልድ እናትነት ከአዳም ልጆች ሁሉ የተመረጠች በመሆኗ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነውን ክብሯን እያሰብን እናከብራታለን፣ የፀጋ ስግደትን እንሰግድላታለን እንጂ አናመልካታም በመሆኑም ቀደምት ቅዱሳን አባቶቻችን ያስተማሩንን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ተከትለን ለትውልድ እናስተላልፋለን እንጂ ሃራጥቃውያን ስለተቹን አስተምሮታችንን አናቋርጥም ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንም አትታደስም ነገር ግን ለተሃድሶ መናፍቃኑ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቅዱሳን አባቶቻችንን ስለእመቤታችን ክብርና ቅድስና ከተናገሩትን ምስክርነት ውስጥ በጥቂቱ እነሆ፦
☞ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘቆጵሮስ፦ "ማርያምን አክብሩ፤ መመለክ ያለባቸው ግን አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ናቸው ማርያም ቅድስት፣ ክብርት እና ውብ ብትሆንም እንኳን አናመልካትም፣ ጌታን የሚያከብር ማንም ቢኖር ማደሪያውን ያከብራል የተቀደሰ ማደርያውን የማያከብር ግን ጌታን አያከብርም"።
☞ ቅዱስ አምብሮዝ፦ "በመንፈስ ቅዱስ ግብር ሰው የሆነውን ባመለክን ጊዜ መንፈስ ቅዱስንም እናመልከዋለን፤ ነገር ግን ይሔንን ለእመቤታችን ለማርያም ማንም እንዳያደርግ ይጠንቀቅ፤ እርሷ የጌታ የአምላክ ቤተ መቅደስ ናት እንጂ የመቅደሱ ጌታ አይደለችም፤ በመቅደሱ ውስጥ ሆኖ የሠራ እርሱም ብቻ ይመለካልና"።
☞ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፦ "የማይወሰን እግዚአብሔር በድንግል ማኅፀን እንደተወሰነ ማን አየ? ማን ሰማ? ሰማያት ለማይወስኑት ለእርሱ የድንግል ማኅፀን አልጠበበውም ባሕርዩ ሳይለወጥ ከእርስዋ ተወለደ እንጂ"።
☞ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፦ "እመቤታችን ሆይ!! ከፍጡራን ሁሉ ሰይጣን አንቺን ይጠላሻል፤ ካንቺ የተወለደው እራስ እራሱን ብሎ ቀጥቅጦታልና"።
☞ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ፦ "አማኑኤል እግዚአብሔር ነው፤ እመቤታችንን ወላዲተ አምላክ አይደለችም የሚል፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በሥጋ እንደወለደችው የማያምን ቢኖር የተወገዘ ይሁን"።
☞ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ፦ "እመቤታችንን ወላዲተ አምላክ መሆንዋን የማይቀበል ከእግዚአብሔር የተለየ ነው"።
☞ አባ ሕርያቆር ዘብሕንሳ፦ "የቀደሙት ሰዎች እነ አብረሃም ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት የተሸጋገሩብሽ አንቺ ነሽ"።
☞ ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፦ "ማንም ለወላዲተ አምላክ የሚያገለግል ቢኖር ፈጽሞ አይጠፋም"።
☞ ቅዱስ አውግስጢኖስ፦ "ማርያም በሔዋን ውስጥ ነበረች፤ ነገር ግን ሔዋን ማን እንደሆነች ያወቅነው ማርያም ወደ እኛ ስትመጣ ነው"።
☞ ቅዱስ ኤፍሬም፦ "ድንግል ሆይ፣ ቅድስት ሆይ፣ ጌታን የወለድሽ ሆይ እኛን ለማዳን ድንቅ ምስጢር /ተዋህዶ/ በአንቺ ቢደረግ ንጉሡን ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በልዩ መልክ የፈጠረ የእርሱን ነገር መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል"።
☞ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ፦ " ...መልአኩ ባነጋገራት ጊዜ ርሷ ድንግል ነበረች፣ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ወልድን ስትቀበልም ድንግል ነበረች፡፡ የአብ ጸዳል በርሷ ባደረ ጊዜ ርሷ ንጽሕት ድንግል ነበረች፣ ሕጻኑ በማሕፀኗ በየጥቂቱ ያድግ በነበረበት ጊዜም ድንግል ነበረች፣ ድንግሊቱ ያንን ፍጥረትን የሚሸከመውን ኀያሉን ተሸከመችው፣ ኀይሉ ለአብ የተባለ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታን በወለደችውም ጊዜ እርሷ ድንግል ነበረች"፡፡
☞ ቅዱስ ያሬድ፦ "ማርያም ግን በአዳም ባሕርይ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ እንደነጭ እንቁ ታበራለች"።
☞ ቅዱስ አትናቴዎስ፦ ... "ንጹሕና ያልተነካች ድንግል... የተከበርሽ የተደነቅሽ ድንግል ሆይ በእውነት አንቺ ከማንኛውም ሌላ ታላቅነት የበለጥሽ ነሽ፤ የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ የሆንሺው ካንቺ ጋር ማን በእኩልነት ይወዳደራል?፤ ድንግል ሆይ ከፍጥረታት ሁሉ አንቺን ከማን ጋር ላነጻጽርሽ? ፤ በቃል ኪዳን ከሁሉም በላይ የሆንሽ ሆይ በወርቅ ፈንታ ንጽሕናን የተጎናጸፍሽ አንቺ እውነተኛውን መና የያዘችውን የወርቅ መሶብ ነሽ ይኸውም መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ነው"።
☞ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ፦ "ጸጋን የተመላሽ ሆይ ማኅበረ መላእክትና የሰው ዘር ፍጥረታት ሁሉ በአንቺ ይደሰቱብሻል፤ የተቀደሰች ቤተ መቅደስና ነባቢት (የምትናገር) ገነት የደናግል ክብራቸው ሆይ ከአንቺ ከዘመናት አስቀድሞ የነበረ እግዚአብሔር ሥጋን ተዋሕዶ ሕፃን ሆኗልና፤ ከአንቺ የነሣውን ሥጋ በዙፋን ላይ አኑሮታል፤ ማሕፀንሽንም ከሰማያት የበለጠ በጣም ምቹ መኖሪያ ስፍራ አድርጎታል፤ ፍጥረታት ሁሉ በአንቺ የሚደሰቱብሽ ምልእተ ጸጋ ሆይ ላንቺ ውዳሴ ይገባል"።
☞ ቅዱስ ጀሮም፦ "ድንግል ልጇን ፀንሳ ከወለደችልን በኃላ ርግማን ተወገደ፤ ሞት በሔዋን ሆነ፤ በማርያም ድንግል ግን ሕይወትን አገኘን"።
☞ ፕሮክልዩስ ዘቁስጥንጥንያ፦ "ያለ ስሕተት ከርሷ ተገኘ፤ ርሷንም ያለነውር እንድትሆን አደረጋት፤ እንዲሁም ማርያም የዐዲስ ፍጥረት ሰማያዊ ምልክት ምሕዋርን ሆነች፤ በዚህም ምሕዋር የጽድቅ ፀሓይ ለዘላለም ያበራል፤ ርሷንም የኀጢአት ጨለማ ፈጽሞ አላያትም... ከእግዚአብሔር እናት የምትበልጥ ታገኝ እንደሆነ ሰው ሆይ ፍጥረቱን ሁሉ በሐሳብህ ዞረህ እይ፤ ዓለምንና ውቅያኖሶችን ሁሉ ዙር፤ አየሩን ሁሉ መርምር፤ ሰማያትን ጠይቅ፤ የማይታዩትን ኀይላት ሁሉ ዐስብ፤ በድንቅ የሚመስላት ካገኘክ መርምር ርሷ ብቻ ከቃላት በላይ የሆነች መንገድ ናት፤ በሰርጓ አዳራሽ በማህፀኗ ፍጥረት ሁሉ በፊቱ በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚንበረከኩለትን ያሳደረች ናት"።
.
.
.
✍ ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካስተማሩት ትምህርቶች ውስጥ በጥቂቱ ያህን ያህል ለምስክርነት ካየን የተሃድሶ መናፍቃኑም ይህንን እውነታና የአባቶቻችንን ምስክርነትን አምነው ወደ ማትታደሰው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ልብ ገዝተው ይመለሱ ዘንድ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፀሎት ነው።
✞ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ ፍቅሯ ረድኤት በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር!!! አሜን ✞
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?
📕 ክፍል ሁለት
📜 @And_Haymanot
እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት(ወልዳለች) በማለት ኑፋቄያቸውን ለሚዘሩ የተሃድሶዎ መናፍቃን በተከታታይ በዚህ ርእሥ የቤተክርስቲያናችንን ምላሽ ማቅረባችንን ቀጥለናል
@Konobyos
✍‹‹‹ የእጮኛ ትርጉም ›››
እጮኛ የሚለው ቃል ጠባቂ ማለት ነው፡፡ ሌላ ከሰው ልብ የፈለቀ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡ 👉ለምሳሌ ‹‹እናንተን ለዘለዓለም ለእኔ እንድትሆኑ አጭቻችኋለሁ ›› ሆሴ 2፥21 ማለት ለጋብቻ ነውን? ያሳዝናል አጣመው ለተረጎሙት፡፡ 👉አሁንም ሐዋርያው ከጌታችን ጋር ስላዋሐዳቸው ‹‹ ለእርሱ አጭቻችኋለሁ›› 2ኛ ቆሮ 11፥3 ማለቱን እናስተውል፡፡
👉እንደገናም ምእመናንን የከበረች ማደርያው ስላደረጋቸው ‹‹ለሰማያዊው ክብር አጭቻችኋለሁ ›› ኤፌ 5፥26 ታዲያ እንዲህ ሲል ላጋባችሁ ነው ማለት ይሆን(ሎቱ ስብሐት) ፡፡
እመቤታችን ንግሥተ ሰማይ ወምድር ነችና በ15 ዓመቷ መለኮት ተዋሐዳት ፡፡ ሲዋሐዳትም ለዮሴፍ ታጨች ሉቃ1፥26፡፡ እንግዲህ እጮኛ ማለት ትርጉሙን ያላወቁ ይወቁ እንላለን ፡፡ ነገር ግን ሰው በራሱ ፍቃድ አይተርጉም !!! ሌላው እጅግ የሚደንቀው ነገር ደግሞ ድንግል ማርያም ክርስቶስን ከመውለዷ በፊት እንጂ ከወለደች በኋላ ዮሴፍ ‹‹ እጮኛ›› ተብሎ በአንድም ስፍራ አለመጠቀሱ ነው
👉ማስረጃ ‹‹ ሕጻንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ ›› ማቴ 2፥3 እንዲሁም በግብጽ 3 ዓመት ከ3ወር በስደት ከቆዩ በኋላ ይህንኑ ቃል ለዮሴፍ በህልም ተነግሮት ‹‹ ሕጻኑን የሚፈልጉት ሞተዋልና ሕጻንና እናቱን ይዘህ ወደ ናዝሬት ተመለስ ›› አለው እንጂ እጮኛህን (ሚስትህን) ይዘህ
ተመለስ አላለውም ማቴ 2፥20፡፡
✍‹‹‹ የበኩር ትርጉም ›››
የበኩር ልጇን ወለደች የሚለው ቃል ብዙዎችን አሳስቷል ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በተለምዶ የበኩር ልጅ የሚባሉ የግድ ተከታይ ያላቸው መሆን አለባቸው የሚል አስተሳሰብ በመናፍቃን ክፉ ልቦና ስለሰረጸነው፡፡ ነገር ግን በተለምዶ የሚባል ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ጋር አይሰራምና እንዲህ ይታረማል
👉፡- ‹‹ እግዚአብሔር ሙሴን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳትም ማኅጸንን የሚከፍት በኩር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ አለው ›› ዘጸ 13፥1-2 ይህ ቃል እንደሚገልጸው በኩር የሚባሉት ለመጀመርያ ጊዜ ከእናታቸው ማኅጸን የሚወጡ መሆናቸውን እንጂ ግዴታ ተከታይ ሊኖራቸው እንደማይገባ ያረጋግጣል ፡፡ አንድም ብቻ ቢሆን የእናቱም ማኅጸን ለመጀመርያ ጊዜ ከፍቶ ከወጣ ተከታይም ባይኖረው በኩር ነው ፡፡ ይሄ የበኩር ትርጉም ካልገባን ወደ ሌላ ፤ ይልቁን ወደ ማንወጣው አዘቅት መዘፈቃችን አይቀሬ ነው ፡፡
👉ለምሳሌ ቆላስየስ 1፥7 ላይ ስለ ክርስቶስ ሲናገር ‹‹ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው ›› ይላል እዚህ ጋር በኩር የሚለው ቃል ተወዳዳሪ ላላቸው ነገሮች የሚጠቀስ ሆኖ ከቀረበ ጌታን ፍጡር አድርጎ ከፍጡራን ጋር አነጻጽሮ እርሱ ከፍጥረታት በፊት ቀደም ብሎ የተፈጠረ ፍጡር ነው እንደማለት ይሆናልና(ሎቱ ስብሐት)፡፡
እንደገናም በኩር የሚለውን ቃል በሥጋዊ ደማዊ ሃሳብ ከተረጎምነው ዕብ 1፥6 ላይ 👉‹‹በኩርን ወደ ዓለም ሲያገባ ›› የሚል ቃል አለ እዚህ ላይ የክርስቶስ በኩር ተብሎ መጠራት አብ ቀዳሚ ተከታይ የሌለውን የባሕርይ ልጁን ወደ መሬት ሂድ ፣ ውረድ ተወለድ ፣ ሙት ተሰቀል ብሎ እንደላከው ለመግለጽ ነው ፡፡ ታድያ አብ በኩርን ወደ ዓለም ሲልክ በኩር የሚለው ቃል ተጠቅሷልና አብም ከክርስቶስ ሌላ ልጅ አለው ማለት ነውን? እናንት ግብዞች መናፍቃን የመጽሐፍን ቃል በግርድፍ መረዳት ምን ያህል እንደሚያስት ይረዱ ድንግል ማርያምን የነኩ እየመሰላቸው ባለቤቱን መንቀፋቸው ያሳፍራል !!!
እርሷስ ክብር ይግባትና በተቃዋሚዎች አፍ አትረክስም እርሱ ባለቤቱ አንዴ አክብሯታልና ፡፡ ‹‹ የበኩር ልጇን ወለደች›› መባሉ መጀመርያና መጨረሻ የሌለውን አምላከ አዶናይ ፣ ልዑለ ባሕርይን ወለደች ማለቱ ነው፡፡
ይቀጥላል
📝 ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Join
@Konobyos
Join
@And_Haymanot
Join
@And_Haymanot
ለሌሎች ሼር በማድረግ ኑፋቄያቸውን አብረን እንዋጋ
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡ ♥️