፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
በክርስቶስ ኢየሱስ የተከፈለልን ቤዛነት እና የቅዱሳን ምልጃ!

@And_Haymanot
ክፍል ፩
በኦርቶዶክስውያንና በፕሮቴስታንት በካከል ካሉ የእምነት ልዩነቶች አንዱና ዋነኛው የምልጃ ትምህርት ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ አላማም ስለምልጃ ማብራሪያ ለመስጠት ሳይሆን ልዩነቶቻችንን ነቅሶ ለማውጣትና ከልዩነቶቻችን በመነሳት ለፕሮቴስታንት ወገኖቻችንን መልስ የሚሻ ጥያቄ ማንሳት ነው፡፡

👉 1. አማላጃችን ማነው?

ኦርቶዶክስ፡- በምድርም በሰማይም ያሉ ቅዱሳን!
ፕሮቴስታንት፡- አንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ!
ጥያቄ ለፕሮቴስታንቶች
1.1) አማላጅነት በምድርም በሰማይም አለ፤ በምድር በሕይወት ያሉ የሰው ልጆች /ቅዱሳን/ ያማልዳሉ፤ በሰማይ ደግሞ ኢየሱስ ያማልዳል በሚለው አስተሳሰብ ብዙ ፕሮቴስታንት ይስማማሉ፡፡ ጥቂቶች ባይስማሙም /አማላጃችን አንድ ኢየሱስ ብቻ ነው ቢሉም/፡፡ አማላጅ አንድ ኢየሱስ ብቻ ነው? ወይስ ምልጃ በምድርም በሰማይም ይሰራል?

1.2) ምልጃ በሁለቱም ካለ በምድር ያሉ የሰው ልጆች /ቅዱሳን/ ምልጃ እና በሰማይ በኢየሱስ የሚደረግ ምልጃ አንድነት ወይም ልዩነት እንዴት ሊብራራ ይችላል? ማለትም የቅዱሳም ምልጃ ልመና ነው፤ የኢየሱስም ምልጃ ልመና ነው፤ ስለዚህ ተመሳሳይ ነው፤? አሊያም የቅዱሳኑ ምልጃ ልመና ነው፤ የኢየሱስ ምልጃ ግን ከዛ በላይ ነው፤ ይለያያል ብሎ ማብራራት ይቻል ይሆን?

👉 2. አማላጅነት ምን ማለት ነው?

ኦርቶዶክስ፡- አማላጅነት በሁለት ይከፈላል፡፡ የልመናና የተገብኦ በመባል፡፡
#የተገብኦ_ልመና ማለት ክርስቶስ በስጋው ወራት የፈጸመው ምልጃ ነው፡፡ ይህ ምልጃ የሰው ልጆችን ከማዳን ስራው ጋር የሚጠቃለል ነው፡፡ በጸሎት /ልመና/ ብቻ ሳይሆን በመከራ ጭምር የተፈጸመ ፣ በቤዛነት የተዋጀ፣ በሞት የተቋጨ ነው፡፡ በንጹሕ ደሙም መፍሰስ የኃጢያት ስርየት ያገኘንበት ነው፡፡ ቤዛነት ማለት ስለሌላው /ስለአዳምና ልጆቹ የተከፈለ ዋጋ ማለት ሲሆን መዋጀት ስንል መልሶ መግዛት ወይም ወደቀደመ ክብር መመለስ ማለታችን ነው/፡፡ ይህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የተፈጸመና ቅዱሳኑን ጨምሮ ሁላችንም የሰው ልጆች ድህነት ያገኘንበት ነው፡፡ ይህን በክርስቶስ በተገብኦ የተፈጸመ ምልጃ ከቅዱሳን ምልጃ ጋራ በንጽጽርና በምርጫ የማይቀርብ የመዳናችን ምስጢር ነው፡፡

#የቅዱሳን_ምልጃ፡- አንዱ ስለሌላው የሚያደርገው ጸሎት ነው፡፡ “ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ስለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በስራዋ እጅግ ኃይልን ታደርጋለች“ ያዕ.5፣16፡፡ ይህ ጸሎት ሁላችንም ዕለት ዕለት አንዳችን ስለሌላው በመጸለይ የምንፈጽመው ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው፡፡ ለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ የጥቅስ ማስረጃ መደርደር ጊዜ ማጥፋት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ምድር ላይ ስለሌላው የማይለምን፣ እኔን ብቻ ማረኝ ስለሌላው አያገባኝም ያለ ክርስቲያን ኖሮ አያውቅም፤ የለምም፡፡ ለዚህ ምስክሮች እኛ ሁላችን ነንና! ሁላችንም አንዳችን ስለሌላው የምናደርገው ጸሎት /ልመና/ ምልጃ ይባላል፡፡ ታዲያ ይህ ጸሎት ማንም ሰው የሚያደርገው ከሆነ ኦርቶዶክሳውያን በቅዱሳን ጸሎት መታመናችን አማልዱን ማለታችን ለምን ይሆን ቢሉ፤-
የጻድቅ ጸሎት በስራዋ እጅግ ኃይልን ታደርጋለችና ነው! ጸሎት ሁሉ እኩል መልስ አያመጣም፡፡ እኩል ኃይል የለውምም፡፡ የጻድቃን ጸሎት ግዳጅ ትፈጽማለች በስራዋም እጅግ ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ያዕ.5፤16 ፡፡ ይህ ልዩነት እግዚአብሔር አድሎ ያለበት ሆኖ ሳይሆን የቅዱሳን የእምነታቸውና የጽድቃችው ኃይል ነው፡፡
ስለቃልኪዳናቸው ነው፡፡ እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር የሚፈጽመው ቃልኪዳን ለትውልድ የሚሰራ ነውና፡፡ እግዚአብሔር ከወደደው ጋር ቃልኪዳን ይፈጽማል፡፡ ቃልኪዳኑም ይጠብቃል፤ በቃልኪዳኑ ይታመናል፤ ይምራልም፡፡ ስለሆነም በድፍረት ሳይሆን በትህትና፤ በብልጠት ሳይሆን በየዋህነትና በእምነት በቅዱሳን ቃልኪዳን ብንታመን ከቃልኪዳኑ ባለቤት ከእግዚአብሔር ምህረት እናገኛለንና ነው፡፡
ፕሮቴስታንት፡- በፕሮቴስታንት ዘንድ ግልጽ ያለ አስተምህሮ አይታይም፡፡ ምልጃን ከድህነት ጋር የሚያያይዙ ፕሮቴስታንቶች አማላጃችን ኢየሱስ ብቻ ነው ሲሉ፤ ምልጃን ከልመና ጋር የሚያያይዙና ለራሳቸው የምልጃ ጻሎት መልስ መስጠት የሚፈልጉ ፕሮቴስታንቶች ምልጃ በምድርም በሰማይም አለ ይላሉ፡፡ በምድር በስጋ ያሉ ሰዎች /እኛ/ ፤ በሰማይ ደግሞ በኢየሱስ ይፈጸማል ይላሉ፡፡ በዚህም የምልጃን ሰንሰለት ያረዝማሉ፡፡ ለአማኞቻቸው አገልጋዮቹ ወደኢየሱስ ያማልዳሉ፤ ኢየሱስ ወደአብ ያማልዳል፡፡ ምንም እንኳን ፕሮቴስታንት ወገኖቼ ብዙ ጊዜ ስለምልጃ ሲነሳ ምን ዙሪያ ጥምጥም አስኬደኝ፤ በቀጥታ ኢየሱስ ጋር መቅረብ እየቻልኩ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ነገር ግን በተግባር ሲታይ የፕሮቴስታንት የምልጃ ሰንሰለት ከኦርቶዶክሳውያን ይረዝማል፡፡ ምክንያቱም በኦርቶዶክስ ልመና ሁሉ ክርስቶስ ጋር ይቆማል፡፡ ለአብ ያለው ሁሉ የወልድ ነውና! በፕሮቴስታንት ግን ኢየሱስ የአማላጅነት ሚና ይኖረውና ልመናን ወደ አብ ያደርሳል፡፡ ምልጃን በሚመለከት በፕሮቴስታንቱ ዘንድ ግልጽ ያለ ዶክትሪንና አስተምህሮ እንደሚያስፈልግ ክፍተቱ ያመላክታል፡፡ በዝርዝር ከታች ተመልክቷል፡፡

👉 3. ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው ወራት አማልዷንል? ዛሬስ ያማልዳል?
3.1. ኦርቶዶክስ፡- በርግጥም ክርቶስ በስጋው ወራት ምልጃን ፈጽሟል፡፡ ይህ የተገብኦ ምልጃ የክርስቶስ የማዳን ስራው አንዱ አካል ነው፡፡ በስጋው ወራት የፈጸመውም ምልጃ የአማላጅነት ሚና ብቻ ካላቸው ከቅዱሳን ምልጃ ይለያል፡፡ ስለኃጢያት ይቅርታ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የቆሙ ብዙ ነቢያት ነበሩ፡፡ የነርሱ ልመና ጊዜያዊ እርቅ እንጂ ፍጹም መዳንን አላመጣም፡፡ የክርስቶስ ምልጃ የተገብኦ ነው ሲባል የነቢያትን፤ የኦሪት ካህናትን ልመና ሁሉ የሚወክልና የሚጠቀልል ነው፡፡ ጌታ ስለነቢያቱ ተገብቶ የፈጸመውና በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ፍጹም እርቅን ያስገኘ ነው፡፡ ይህ ምልጃ ከርሱ በፊት ሲለምኑ ስለበሩት ስለነቢያት ተገብቶ የፈጸመው ካሳ ነው፡፡ የክርስቶስ የማዳን ተግባሩ ልመና ብቻ ሳይሆን የመስቀልን መከራ በተገብኦ /በኃጢያተኛው ምትክ ስለኃጢያተኛው/ መከራ በመቀበል የተፈጸመበትና በሞት የተቋጨ ነው፡፡ ለዚህ ነው ጌታ በመስቀል ላይ ተፈጸመ ያለው፤ ዮሐ.19፤30፡፡
ማንም በክርስቶስ ድኛለሁ የሚል መዳኑ ስለነቢያቱ ተገብቶ በፈጸመው የካሳ ምልጃ ብቻ ሳይሆን፣ በቤዛነቱ፣ በመከራውና በሞቱም ጭምር ነው ብሎ ሊያምን ይገባዋል፡፡ ክርስቶስ በስጋው ወራት የፈጸመውን ምልጃ ከማዳን ስራው መነጠል አይቻልም፡፡ መዳን በክርስቶስ ምልጃ ብቻም አይባልም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ንጹሕ ደሙን ማፍሰስ መሞት ሳያስፈልገው በምልጃው ብቻ ባዳነን፡፡ ይህ ምልጃ የተፈጸመው ክርስቶስ የአማላጅነት ሚና ብቻ እንዳላቸው እንደቅዱሳን በመሆኑ አይደለም፡፡ የእርሱ ሚና መለመን የአብ ሚና ማለት ስለሆነም አይደለም፡፡ ክርስቶስ ጸለየ፤ ለመነ ብለን ይቅር አለም እንላለንና፡፡ አርሱ የለመነው ይቅር ማለት የማይችል ሆኖ ሳይሆን ይህ እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን የተጓዘበት መንገድ ነው፡፡
በሰው ልጅ የመዳን ጉዞ ድህነት የተፈጸመው ስለአዳም ኃጢያት ፍጹም ካሳ በመክፈልና፤ በፍርድ ነው፡፡ በአዳም ኃጢያት እግዚብሔር ተበድሏል፣ አዳም በድሏል፡፡ ድህነት ይፈጸም ዘንድ የበደለው አዳም ስለኃጢያቱ ካሳ መክፈልና ፍርድን መቀበል ነበረበት፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ሐጢያትን ምን ያህል እንደሚጸየፍና ከሐጢያት ፍጹም የራቀ ቅዱስ መሆኑን ተረጋገጠ፤
👍1