፩ ሃይማኖት
8.97K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ከመሰዉያዉ እና ከመስዋዕቱ የቱ ይበልጣል ? መስቀሉወይስ መስቀሉ ላይ የተሰቀለዉ?

@And_Haymanot

የተሃድሶ መናፍቃን የመስቀሉን ክብር አይቀበሉም የተቃውሟቸው መንገድም ፍጡርን ከፈጣሪ እኩል ክብር የምንሠጥ አድርገው ምዕመኑን ሊያታልሉ ይጥራሉ
የኑፋቄያቸው አላማም የክርስቶስ ኢየሱስን የደሙ እንጥፍጣፊ ያረፈበትን መስቀል፤አይጠቅምም ብለን እንድንተው ይተጋሉ
★ ★ ★
ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስትያን ፤ለልጆቹዋ ፤ ለአምላክ የሚሰጠውን አምልኮ ፤ምስጋ፤ስግደት ና ክብር ፤ ለቅዱሳኑ ና ለነዋየ ቅድሳቱ ከሚሰጠው አክብሮትና ምስጋና ስግደት ለይታ ታስተምራለች፡፡ ነገር ግን እንደ ሉተርያውያን፤የሐይማኖት ድርጅቶች የጌታ የሆኑትን ሁሉ ባጠቃላይ በመናቅ ባለማክበር ና በማንቁዋሸሽ፤ የጌታ
እውነተኛ ድህነት እንደማይገኝ ና ይልቁኑ በምትኩ እሱ የመረጣቸውን ቅዱሳንና የተቀደሱ ነገሮች ሁሉ ማክበር የአንድ ክርስትያን ሐይማኖታዊ ግዴታ እንደሆነ ትላንትም ዛሬም ነገም እስከ አለም ፍጻሜ ታስተምራለች፡፡
★ ★ ★
መደ ጥያቄው መልስ ስንመለስ ኦርቶዶክስ ተወህዶ መቼም ቢሆን መቼም፤ የክርስቶስን የመስቀል ላይ ቤዛነት፤ምንም ነገር ፤እንደማይተካው ስለምታውቅ ፤በአመቱ በሙሉ በቅዳሴዋ በኪዳንዋ፤ በማህሌቷ ፤በምህላው ጸሎቷ ባጠቃላይ በሁሉም የአምልኮ
ስርዐቷ፤ ላይ የክርስቶስ፤ስጋን እና ደም፤እንድንቀበል፤ ልጆቹዋን ታስተምራለች፤ትመክራለች፤ ንስሃ ግቡ በማለት ታበረታናለች፡፡ ቅዱሳኑ እራሱ ታስበው በሚውሉበት ቀን፤ ፍቅረ ክርስቶስ/የመስቀሉ ቤዛነት ቅዱሳኑንን ምን ያህል አለምን እንዲንቁ እንዳዳረጋቸውና ለስሙ ሲሉ
የታገሱትን መከራ ለልጆቹዋ ታስተምራለች፡፡
★ ★ ★
እለት እለት በሚካሄደው የቅዳሴ ስርዐት ላይ ከሌሎች በደሙ ድነናል ብለው
መፈከር ብቻ አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ተለይታ ድህነት በመፈክር ሳይሆን ጌታ ባዘዘው መሰረት
“””ስጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘላለም ህይወት አለው””
ዮሐ 6፥53 የሚለዉን ቃል መሰረት በማድረግ ለምዕመኗ ሁልጊዜ
ሳታቋርጥ የጌታን ስጋን ደም ታቀብላለች፡፡
★ ★ ★
ነገር ግን በዘመናችን የተነሱት መናፍቃንና የበኩር ልጆቻቸው
የተሃድሶዎ መናፍቃን፤ ቅድሥት ቤተክርስትያን ክርስቶስን አትሰብክም ለቅዱሳኑ ና ለነዋየ ቅድሳቱ እና ለጌታ ቅዱሳን የሚሰጠው ክብር አያስፈልግም፤ ብለው ሲሟገቱን እናያቸዋለን፡፡ በዚህም የተሳሳተ ትምህርት ብዙዎችን ፤ጌታችሁን አገኛችሁ ብለው ከስላሴ ልጅነት ፤ማህተባቸውን አስበጥሰው ወደማይወጡበት የጨለማ ህይወት ና ፤
ከባለጸጋዋ ቤተክርስትያን አውጥተው ባዶ አዳራሽ አውርሰዋቸዋል፡፡
★ ★ ★
~~~የክርስቶስን የመስቀል ላይ ቤዛነት ማንም ምንም ሊተካው እንደማይችል ኦርቶዶክስ ታስተምራለች ከላይ በገለጽኩዋቸው መልኩ ፡፡
ነገር ግን ይሄ ቤዛነት የተከፈለበት መስቀል ፤የጌታ ክቡር ደሙ የተንጠባጠበት መስቀል ፤የጌታ ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት መስቀል፤ሴጣንና ሰራዊቶቹ ድል የተደረጉበት መስቀል፤በሚገባ መክብር አለበት ብላ በየአመቱ በመስከረም 16 ታሪካዊ አንድምታውን ባለቀቀ መልኩ ታከብረዋለች፡፡
★ ★ ★
ቅዱስ መስቀሉ መክበሩ ፤የክርስቶስን ቤዛነት በይበልጥ ያጎላል እንጂ የክርስቶስን ቤዛነት አያስረሳንም፡፡
የሀዲስ ኪዳን መስዕዋት የቀረበበት የክርስቶስ ቅዱስ መስቀል ከከበረ በእርሱ ላይ ያለው ክርስቶስ ይከብራል ምክንቱም የመስቀሉ ባለቤት እራሱ ባለቤቱ ክርስቶስ ኢየሱስ ነውና።
★★ ★
ማስረጃ ማቴ23፥20-23
20 ---በመሰውያው የሚምል በእርሱ ይምላል በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል።
21 ---በቤተ መቅደስ የሚምል በእርሱና በውስጡ በሚኖረው ሁሉ ላይ ይምላል።
22 ---በሰማይ የሚምል በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል።
"ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 13:7)
★ ★ ★
ስለዚህ መናፍቃንና ልጆቻቸው ተሃድሶዎች ሆይ መስቀሉን
የሚጥል ፤በላዩ የተሰቀለውንም ይጥላል ይህ ደግሞ እጅግ በጣም አሳፋሪ ፤ ነውር ና፤ ሀጥያት የሚለው ቃል የሚያንሰው ነው፡፡
★ ★ ★
ስለሆነም መናፍቃን፤ ክርስቶስን ያከበራቹሁና ያስከበራችሁ እየመሰላችሁ ከክርስቶስ ህብረት ፍጹም እየራቃችሁነውና፤ ሳይመሽባችሁ፤ ጥላችዋት ወደ ሄዳችሁባት፤ አማነዊቷ ጌታና የጌታ የሆኑትን ሁሉ ወደያዘችው የ ከርስቶስ ደጅ ወደ ተሰኘችው ቅድስት ቤተክርስትያን ከራሳችሁ የፍልስፍና አለም ወጥታችሁ የጨዋይቱ ልጆች ተብላችሁ፤ ተመለሱ፡፡
#ፈጣሪንም_ከፍጡር_ጋር_ማወዳደር_ይብቃችሁ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት