፩ ሃይማኖት
8.96K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
"ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡ ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ፡፡ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ
ክርስቶስን እየሰደብከው እንደኾነ አስተውል፡፡ #እንዴት? ያልከኝ እንደኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል፡፡ የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቅኸው ማለት
ክርስቶስን ናቅኸው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከኾነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ሐሞትን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም፡፡ ስለዚህ ወንድምህን እኅትህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥
ምንጭ፡- ሰማዕትነት አያምልጣችሁ
@And_Haymanot
@And_Haymanot