Forwarded from ፩ ሃይማኖት
✟ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን✟
✟አብይ ሀይል ወበስልጣን✟
✟አሰሮ ለሰይጣን✟
✟አግአዞ ለአዳም✟
✟ሰላም✟
✟እምይዜየሰ✟
✟ኮነ✟
✟ፍስሀ ወሰላም✟
"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም"ሉቃ፦24፥5
"እንደተናገረ ተነስቷልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ" ማቴ፦28፥6
እንኳን አደረሰን መልካም በዓል ለሁላችንም!!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot

ለምን አንጾምም?
ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች?
ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም?
በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/።
"የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ
15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት
ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው።
በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ
እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም
ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም።

፩ ሃይማኖት
Photo
አንድ ጠያቂ እንዴት ወደ ድንግል ማርያም ልመና ይቀርባል ብሎአል:: በምድራዊ ኑሮ እርስ በእርሳችን በተለያየ ምክንያት እንዲህ አድርግልኝ ብለን ወንድሞቻችንን እኅቶቻችንን እንለምናለን:: ሀብት ሥልጣንና እውቀታቸው ከፍ ያለ ሰዎችን ደግሞ የበለጠ እንለምናለን:: ትብብራቸውን ምክራቸውን እንጠይቃለን:: በመንፈሳዊው ዓለም ደግሞ ወንድሜ በጸሎት አስበኝ አስቢኝ እንላለን:: ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆኑት የበለጠ ልመና ይቀርብላቸዋል::
ዝናም እንዳይዘንም ብትፈልግ ለእኔ ዓይነቱ ደካማ ሰው "እስቲ ዝናም እንዳይዘንም ጸልይልኝ" ትለዋለህ:: ይጸልይልሃል:: ጸሎቴ አልሰምር ካለ አብሬህ እጠለላለሁ::
በእኔ ፋንታ ነቢዩ ኤልያስ ቢጸልይልህ ግን "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች:: ኤልያስ እንደኛው ሰው ነበረ ዝናም እንዳይዘንም አጥብቆ ጸለየ በምድር ላይ አንድ ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም ሁለተኛም ጸለየ ሰማዩ ዝናብ ሰጠ" ያዕ. 5:16
አዎ ብዙ ልመና በመጽሐፍ ቅዱስ ለፍጡራን ቀርቦአል::
“አብርሃም አባት ሆይ ማረኝ" 16:24
"አሮንም እንዲህ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ቍጣህ አይቃጠል፤ ይህ ሕዝብ ክፋትን እንዲወድድ አንተ ታውቃለህ" ዘጸ. 32:22
ኦሪት ዘኍልቍ 12
11፤ አሮንም ሙሴን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ስንፍና አድርገናልና፥ በድለንማልና እባክህ፥ ኃጢአት አታድርግብን።
2ኛ ነገሥት 2
9፤ ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፦ ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን፡ አለው፤ ኤልሳዕም፦ መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ፡ አለ።
"እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፡ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን" ሐዋ.16:15
የምንለምነው ከፈጣሪ በተሠጣቸው ጸጋ እንዲፈውሱን እንዲጎበኙን እንዲጸልዩልን እንዲያማልዱን ነው::
©ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
🙏🙏🙏 እንኳን አደረሳችሁ🙏🙏🙏

ፀሎት ለሞተ ሰው ለምን ይደረጋል የሚሉ ሰዎች ክርስቶስ የሞተውን
ሀጢአተኛው ለዛውም በሲኦል ውስጥ ያለውን አዳም ሀጢአቱን ፍቆ ነፃ
እንደአወጣው የረሱ ናቸው፤የኢየሱስ ምሕረቱም ከሞት በኃላም አይቋረጥም !
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሀጢአተኛው ለዛውም በሲኦል ውስጥ ያለውን አዳም ሀጢአቱን ፍቆ ነፃ
እንደአወጣው የረሱ ናቸው፤የኢየሱስ ምሕረቱም ከሞት በኃላም አይቋረጥም !
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ጾመ ፍልሰታ
ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገው ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት ኦርቶዶክሳዊያን የሚጾሙት ጾም ነው።
ፍልሰታ የግዕዝ ቃል ሆኖ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል።
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለሆነ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን 48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች።
ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት ወደ መኖሪያ ቤቷ (የዮሐንስ ቤት) መጥተው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች አስከሬኗን ገንዘውና ከፍነው ወስደው
ለመቅበር ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንም ማድረግ
የፈለጉት የሐዋርያት ትምህርት የጌታችን ከሞት መነሣትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ
እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። የፈሩት ይነግሣል የጠሉት ይወርሳል እንዲሉ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት
አይቀሬ ሆኗል።
አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፊኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ
ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነትና ክብር ለመመስከር በቅቷል።
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር ይቀመጥ እንጂ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር
ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ዮሐንስ ስለሥጋዋ ነግሯቸዋል።
ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ለስድስት ወራት ከአሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህ በኋላም ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው
ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን
አምጥቶ ስለሰጣቸው ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።
ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት
አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ ፪፥፲/።
እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ /ሕንድ/ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ
ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በስተቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት
እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን /የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።
ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ
ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት
አስረዱት። እርሱ ግን ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን
ለማሳመን መቃብሯን ለማሳየት ወሰዱት ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት
የነበረውን ጨርቅ/ የራሱን ድርሻ አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው ዛሬም ካህናቱ ከእጅ መስቀላቸው ጋር መሐረብ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ
ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት
በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለሁለተኛ ጊዜ ለሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ
ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።
በአጠቃላይ የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ሐዋርያት ያገኙትን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በዶ/ር ሙሉጌታ ማርቆስ
@And\Haymanot

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት አስመልክቶ በጥያቄና መልስ የቀረበ ጽሑፍ ነው። እናንተም ተጋበዙልኝ።
ጥያቄ ፩፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም ዕርገት አይናገርም። ታድያ "ዐረገች" ማለታችሁ ስህተት አይኾንም?
መልስ ፩፦ አንድ ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስላልተጻፈ ብቻ "ሀሰት" ሊባል አይችልም። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የአምስት ሺሕ ዓመታትን ታሪክ የያዘ እንደ መኾኑ ኹሉንም ታሪኮች በአንድነት ጠቅልሎ ይይዛል ማለት ዘበት ነው። የአንድ ንጉሥ ታሪክ እንኳን እጅግ በጣም ብዙ ገጽ መጽሐፍ ሊወጣው እንደሚችል እናውቃለን። ታድያ "በግልጽ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስላልተጻፈ ሀሰት ነው" ልንል የምንችለው እንዴት ነው?
አንድም በመጽሐፍ ቅዱስ መገደብ አንችልም። ምክንያቱም "መጽሐፍ ቅዱስ እንደ እገሌ ከሰማይ ወረደ" ብለን አናምንም። መጻሕፍቱ በአበው፣ በነቢያትና በሐዋርያት እጅ በተለያየ ጊዜና በተለያየ ቦታ መጻፋቸውን እናውቃለን። ከእነዚህ ውጪም በሐዋርያቱ ስም የተጻፉ የሀሰት መጻሕፍትም ነበሩ። እነዚህን እውነተኛዎቹንና ሀሰተኛዎቹን መጻሕፍት ከዓለም ያሰባሰቡትና የለዩት አባቶች ናቸው። ለመጻሕፍቱም ቅድስና የሰጡት እነርሱ ናቸው።
በመኾኑም መጽሐፍ ቅዱስን ለማመን የአባቶችን አማናዊነት መቀበል ግድ ይለናል። ካልኾነ ግን እነርሱ የራሳቸውን አስተምህሮ ተከትለው እውቅና የሰጧቸው ቅዱሳት መጻሕፍት በጠቅላላ ጥርጣሬ ውስጥ ይገባሉ። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምን ኹሉ በእመቤታችን ዕርገት ማመን ይጠበቅበታል። ምክንያቱም ለመጻሕፍቱ ቅድስና እውቅና የሰጡ አባቶች በጠቅላላ በእመቤታችን ዕርገት ያምናሉ።
ጥያቄ ፪፦ እውን ድንግል ማርያም ዐርጋ ቢኾን ኑሮ ሐዋርያቱ በግልጽ ያልተናገሩትና በመጽሐፋቸው ላይ ያልጻፉት ለምንድን ነው?
......

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን 'ኢየሱስ ያድናል' ብላ ስትናገር በእውነተኛው (አማናዊው) የጌታ ሥጋና ደም በማመን እንጂ መታሰቢያ ነው በማለት አይደለም። ልዩነቱ ግልጽ ነው!
መልካም ወጣት
ነፍስህን ከቅድስና ህይወት ማሸሽህ ሳይታይህ ስጋህን ከሱስ ለማራቅ የምትታለልበት አዲሱ ጸረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮጀክት መሆኑን አውቀህ ንቃ
🙏 ቅዱስ ወጣት ሁን 🙏
@And_Haymanot
በስፋት እንመጣበታለን

+ ድንገት የተበጠሰ ገመድ +
የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል::
የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ)
በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት::
ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል::
በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም:: የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ::
ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም

👍1
+ ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +
ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::
እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::
ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::
ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::
ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::
እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::
እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::
©ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

👍2
መስቀል በኢትዮጵያ
✞ ተወዳጆች በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን!!! አደረሳችው ✞
❖ "ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ" ገላ 6፥14 ❖
@And_Haymanot
✍ ኢትዮጵያ ሃገራችን የክርስቲያን ደሴት ከመባሏም በላይ የእግዚአብሔር ቸርነት ያላት የበረከት የረድኤት ሀገር ናት ይኽም የጌታ ግማደ መስቀል በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል
☞ አመጣጡም የኢትዮጵያ ነገሥታት የግብጽ ካሊፋዎች ሀገረ ገዥዎች በኃይል ይጋፏቸው ስለነበር የግብጽ ሀገር ገዥዎች ደግሞ የግብጽን ክርስቲያኖች (ኮፕታውያን) ያሰቃዩአቸው ነበር ስለዚህ ይህ አለመግባባት እንዲወገድና የግብጽ ክርስቲያኖች ዕረፍት እንዲያገኙ በማሠብ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ከግብጽ የአህናስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስንና አባ ማዕምር የሚባሉ ሉዑካን ወደ ኢትዮጵያ መጡ በዚያን ጊዜ አጼ ሠይፈ አርዕደ አርፈው የልጃቸው ልጅ አጼ ዳዊት ነግሠው ነበር እነዚህ ልዑካን በኢትዮጵያውያንና በግብጻውያን ነገስታት መካከል ያለውን ቅራኔ አስወግደው ሲመለሱ አጼ ዳዊት በነበራቸው ቀና መንፈስ አቡነ ዮሐንስ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ እሌኒ ንግስት አስቆፍራ ከአስወጣችው ከጌታ ግማደ መስቀል ክፋይ ለበረከት እንዲልኩላቸው ወርቅ፣ አልማዝ፣ ገጸ በረከት አስጭነው ወደ ኢየሩሳሌም መልዕክተኞችን ላኩ መልእክተኞቹም ኢየሩሳሌም ደርሰው ገጸ በረከቱን ለፓትርያርኩ ከሰጡ በኃላ ፓትርያርኩ፦
፩፦ የጌታን ግማደ መስቀል፣ የቀኝ በኩሉን ክፋይ
፪፦ ጌታ ላይ አይሁድ የጫኑበትን (ያረጉለት) አክሊለ ሶኩን
፫፦ ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ የእመቤታችን ስዕል ላኩላቸው።
✍ መልዕክተኞቹም ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ አጼ ዳዊት መልእክተኞቹን ለመቀበል ሲሄዱ የተቀመጡባት ባዝራ ፈረስ ጥላቸው መሞታቸውን ታሪካቸው ይናገራል መስቀሉ ወደ ሀገራችን የገባው #መስከረም 10 ቀን ነው መስቀሉ የተቀመጠው መስከረም 21 ቀን በወሎ ክፍለ ሃገር በግሸን ማርያም ነው
✍ በዚህ ሁኔታ የገባው የጌታ መስቀል ዛሬም ድረስ ተአምራዊ ነው ይህም ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመስቀል ያላትን ታላቅ አክብሮትና ፍቅር የገለጸችበት አብይ ምስክር ነው ሕዝቡም ለመስቀል ያለውን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽ ይነቀሰዋል፣ በልብሱ ላይ ይጠልፈዋል ይህ ደግሞ የሚያሳየው መስቀል በኢትዮጵያውያን ዘንድ ምን ያህል ክብር እንዳለው ነው።
☞ ከተለያዩ ማዕድናት የሚሰራው መስቀል ትርጉም፦
✍ መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ሊሰራ ይችላል መስቀሉ የሚሰራባቸው ማዕድናት የራሳቸው ባህርያት እንዳላቸው ሁሉ ምሳሌውን ለመግለጽ ብቁ ናቸው ብለው አባቶች ያስቀመጡትን ማየት ይገባል።
✝ ከብረት ቢሰራ ክርስቶስ የተቸነከረበትን ችንካር ለማመልከት ነው
✝ ከወርቅ ቢሰራ ወርቅ ንጹህ እንደሆነ ክርስቶስን ንጹሀ ባህርይ እድፈት የሌለብህ ጽኑ አንተ ነህ ብሎ ለመመስከር ነው
✝ ከእንጨት ቢሰራ ክርስቶስ የተሰቀለው በዕጽ በእንጨት ላይ መሆኑን ለማመልከት ነው
✝ ከብር ቢሰራ ተስፋን፣ ዕድልን ያመለክታል ይኸውም ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ ቤዛን በደሙ ከፍሏልና በእርሱ ተስፋ እንድናደርግ ያመለክተናል
✍ መስቀል ለእኛ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ ጽንዐችን፣ ቤዛችን፣ መድኃኒታችን ነው "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና" /1ኛ ቆሮ 1፥18/ ለቅዱስ መስቀል ክብርና ስግደት ይገባል ምክንያቱም በመዝ 131፥7 ላይ "እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን" ተብሎ ተጽፏልና።
❖ ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው
❖ በዓለም ጥበብ ለሚኖሩ እውነት ተስኗቸው
❖ ለጠቢብ ሰው በመንፈስ የሚኖር
❖ የመዳን ቀን እውነተኛ አርማ ነው
❖ ከገሃነም እሳት የሚያድን ነው
✔ ያለ መስቀል ክርስትና ያለ ተጋድሎ ቅድስና የለም!!! ✔
✞ አምላከ ቅዱሳን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ጽላት ላይ ይጻፍልን!!! አሜን ✞✞✞
ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
✍ አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~Share~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~JoIN~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡