#ዐሽሩል_አዋኺር
በ አቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
የረመዷን ሀያ ለሊቶች አለፉ፡፡ አላህ ወፍቆት ኸይር የሸመተበትም ሆነ ነፍሲያው አሸንፎት ወደ ኋላ ያስቀረው ይኖራል፡፡ አሁን የቀረውን ጌዜ ግን መጠቀም የሁሉም ድርሻ ነው፡፡ አላህ ዕድሜ ሰጥቶን የምንጠቀም ያድርገን፡፡ ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) በረመዷን የመጨረሻው አስርት ቀናት ውስጥ በዒባዳ በሌላው ጊዜ ከሚበረቱት የበለጠ ይበረቱ ነበር (ሙስሊም የዘገበው)፡፡
በዚህ ለሊት ውስጥ የምትጠበቅ አንድ ለሊት አለች፡፡ እሷም ‹‹ለይለቱል-ቀድር›› ትባላለች፡፡ ይህችን ለሊት አላህ ወፍቆት ምሽቷን በዒባዳና በመልካም ተግባር ያሳለፈ የአላህ ባሪያ፡ አላህ ስራውን ከተቀበለው የሚያገኘው ትርፍ እጥፍ ድርብ ነው፡፡ እሱም፡- በሌላ ጊዜ ለአንድ ሺህ ወራት (83 ዓመት ከ4 ወር) ያህል በዒባዳ በማሳለፍ ከሚያገኘው አጅር በላይ ይሆንለታል ነው፡፡ አንዷ ለሊት 83 ዓመታትን በልጣ ተገኘች፡፡ አላሁ አክበር! አላህ ይወፍቀን፡፡
ከዛሬ ማቅሰኞ ምሽት ጀምሮ የረመዷን 21ኛ ለሊት ይጀመራል፡፡ በተከታታይ የሚመጡትን ምሽቶች በዒባዳ ለማሳለፍ እኛም ከልብ ነይተን፡ በአላህ በመታገዝ ቆርጠን እንነሳ፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የረመዷን የመጨረሻው አስርት ቀናት ሲገባ ወገባቸውን ጠበቅ በማድረግ (በመዘጋጀት) ለሊቱን በዒባዳ ህያው ያደርጉት ነበር፣ ቤተሰቦቻቸውንም ይቀሰቅሱ ነበር (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
ለይለቱል-ቀድርን ለማግኘት ከልቡ አምኖና አላህ ዘንድም የሚያገኘውን ምንዳ በማሰብ በሶላት (በዒባዳ) ላይ ያሳለፋት ሰው ያለፈው ኃጢአቱ እንደሚማርለት በሐዲሥ ተገልጾአል (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
አላህ ወፍቆት ለይለቱል-ቀድርን ለማግኘት አስርቱን ቀናት በዒባዳ የሚያሳልፍ የአላህ ባሪያ ለይለቱል ቀድር በዛሬው ምሽት እንደተገኘች ሊያውቅበት የሚችልባቸው መንገዶች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡-
ሀ. ጸሀይ ጨረር አልባ መሆኗ፡- ኡበይ ኢብኑ ከዕብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን ለይለቱል-ቀድር በለሊቱ ክፍል ከታየች፡ በንጋቱ ጸሀይ በምትወጣ ግዜ እንደተለመደው ጨረር አይኖራትም፡፡ ያለ ጨረር ነጣ ብላ ብቅ ትላለች፡፡ (ሙስሊም 762)፡፡
ለ. ለሊቱ ብርዳማም ሞቃትም አይሆንም፡- ሁሉም ባለበት ሃገር ላይ ባለው የአየር ንብረት ሁኔታ የሚወሰን ነው፡፡ ለይለቱል-ቀድር በምትታይበት ለሊት፡ የለሊቱ ሁኔታ ከዛ በፊት ከነበሩትና ከዛ በኋላ ከሚመጡት ቀናቶች አንጻር ሞቃታማም ሳትሆን ቀዝቃዛም ሳትሆን፡ ሰላማዊ ሆና የምታነጋ ለሊት ነች በማለት ዐብዱላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ከነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የሰማውን ሐዲሥ አስተላልፎልናል (ሶሒሕ ኢብኑ ኹዘይማህ 2192)፡፡
በነጋታው ይህን ምልክት አየሁ ብሎ ግን ከዒባዳ መሸሽ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ይልቁኑ በቀጣዮቹ ተከታታይ ቀናት ያሳለፍነውን ቀን ለይለቱል-ቀድር ታይቶበት ከሆነ አላህ እንዲቀበለን ዱዓ በማድረግ የበለጠ ልንበረታ ይገባል፡፡ በዚህ ለሊት የሚሰሩ መልካም ተግባራትን በተመለከት ለቀባሪው ማርዳት ነውና ብዙም የምለው ነገር የለኝም፡፡ በዚክር፣ በዱዓእ፣ በኢስቲግፋር፣ በቁርኣን ንባብ፣ በለይል ሶላት፣ በነቢያችን ላይ ሶላዋት በማውረድ… እንበራታ፡፡ አላህ ይወፍቀን
Join ➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

Telegram
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።