የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.2K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
ከንዲህ አይነቱ ከንቱ ምኞት አላህ ይጠብቀን
በአቡ ሀይደር
#ዘጠኙ ከንቱ ምኞቶች
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
ምኞት የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ባሕሪ ነው፡፡ የወደደውንና ያሰበውን ነገር ለማግኘት ይመኛል፡፡ በመሆኑም በኢስላም ምኞት አልተከለከለም፡፡ የሚከለከለው ምኞታችን እውን እንዲሆን የሚያግዙ ነገሮችን ከመስራት ችላ ብለን፡ ካለንበት ቦታ ሳንንቀሳቀስ: ራሳችንን ለመቀየር ጥረት ሳናደርግ ያሰብነውን ለመሆንና ለማግኘት መመኘት ነው፡፡
ዛሬ የምናየው ‹‹ከንቱ ምኞት›› የተሰኘው ርእስ፡- ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ የምንመኛቸው፡ መሆን በሚቻልበት ዘመን መሆን እየተቻለ፡ በስንፍናና በአልባሌ ነገር ተዘናግተን አሳልፈን ካጠፋነው በኋላ፡ ምነው ሰርቼ በነበር ብሎ መመኘት ነው፡፡ ጊዜው ካለፈ በኋላ ዳግም ላይመለስ፣ የጸጸቱ ብዛት ማስተዛዘኛ ላይደረግለት ሰው በከንቱ የሚመኛቸው በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የተጠቀሱ 9 ምኞቶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
1. ምነው ከአማኞች ጋር በነበርኩ!
" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا خُذُوا حِذْرَكُمْ فَانْفِرُوا ثُبَاتٍ أَوِ انْفِرُوا جَمِيعًا * وَإِنَّ مِنْكُمْ لَمَنْ لَيُبَطِّئَنَّ فَإِنْ أَصَابَتْكُمْ مُصِيبَةٌ قَالَ قَدْ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيَّ إِذْ لَمْ أَكُنْ مَعَهُمْ شَهِيدًا * وَلَئِنْ أَصَابَكُمْ فَضْلٌ مِنَ اللَّهِ لَيَقُولَنَّ كَأَنْ لَمْ تَكُنْ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُ مَوَدَّةٌ يَا لَيْتَنِي كُنْتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًا " سورة النساء 73-71
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄያችሁን ያዙ። ክፍልፍልም ጓድ ሆናችሁ (ለዘመቻ) ውጡ፤ ወይም ተሰብስባችሁ ውጡ። ከናንተም ውስጥ በእርግጥ (ከዘመቻ) ወደ ኋላ የሚንጓደድ ሰው አለ፤ አደጋም ብታገኛችሁ ከነሱ ጋር ተጣጅ ባልሆንኩ ጊዜ አላህ በእኔ ላይ በእርግጥ ለገሰልኝ ይላል። ከአላህም የሆነ ችሮታ ቢያገኛችሁ፣ በናንተና በርሱ መካከል ፍቅር እንዳልነበረች ሁሉ፣ ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በኾንኩ ወይ ምኞቴ! ይላል።" (ሱረቱ-ኒሳእ 71-73)፡፡
- የኢስላምን ዳር ድንበር ለማስጠበቅና የአማኞችን የነጻነት አምልኮ ለማስከበር ጠላትን መታገል ግድ ሆኖ ሳለ፡ ለህይወቱና ለንብረቱ በመሳሳት ከትግል ወደ ኋላ የቀረ ሰው፡ አማኞች በአላህ እርዳታ ድልን የተጎናጸፉ ጊዜ፡ እሱ ግን ውስጡ በቁጭት የተሞላ ሆኖ፡- ‹‹ምነው እኔም ከነሱ ጋር በነበርኩና የድሉም ባለቤት በሆንኩ!›› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ግን ከንቱ ምኞት ነው፡፡ በወቅቱ አብሯቸው ከመሆን ማን ከለከለውና!!፡፡ በመሆኑም ዛሬውኑ ከዱዓ ጀምሮ አቅሙ የቻለውን በማድረግ ለኢስላም የበኩሉን ግዳጅ ይወጣ፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡
2. ምነው ወደ ዱንያ በተመለስን!
" وَلَوْ تَرَى إِذْ وُقِفُوا عَلَى النَّارِ فَقَالُوا يَا لَيْتَنَا نُرَدُّ وَلَا نُكَذِّبَ بِآيَاتِ رَبِّنَا وَنَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ " سورة الأنعام 27
"በእሳትም ላይ በተቆሙ ጊዜ ምነው (ወደ ምድረ ዓለም) በተመለስን በጌታችንም አንቀጾች ባላስተባበልን ከምእምናንም በኾንን ዋ ምኞታችን! ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያሰደነግጥን ነገር ባየህ ነበር)፡፡" (ሱረቱል አንዓም 27)፡፡
- በምድረ ዓለም እያሉ ለጀነት ብቁ የሚያደርጋቸውን የተስተካከለ እምነትና መልካም ስራዎችን በመስራት በአላህ ራሕመት ከጀነት ሰዎች ለመሆን ዕድሉ የሰፋ ሆኖ ሳለ፡ ያንን ሳይጠቀሙበት ጊዜውን በከንቱና በመጥፎ አሳልፈው ነጌ የእሳት መሆናቸውን ሲያረጋግጡ፡- ‹‹ምነው አንዴ ወደ ዱንያ ተመልሰን አማኝና መልካም ሰሪ ሆነን በመጣን!›› ብሎ መመኘት ከንቱ የሆነ ምኞት ነው፡፡
እናም አሁንም ጊዜው አለንና ወደ ቀብር ዓለም ከመግባታችን በፊት፡ ለቀብርና ለዘለቄታው ዓለም (አኼራ) የሚጠቅመንን መልካም ስራ በመስራት ላይ እንበርታ እንጠናከር፡፡ በተለይም፡- በ5 ወቅት የፈርድ ሶላቶች፣ በዱዓእ፣ በዚክር፣ በወላጅ ሐቅና በመሳሰሉት፡፡
3. ምነው በጌታዬ ባላጋራሁ!
" وَأُحِيطَ بِثَمَرِهِ فَأَصْبَحَ يُقَلِّبُ كَفَّيْهِ عَلَى مَا أَنْفَقَ فِيهَا وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَى عُرُوشِهَا وَيَقُولُ يَا لَيْتَنِي لَمْ أُشْرِكْ بِرَبِّي أَحَدًا " سورة الكهف 42
"ሀብቱም ተጠፋ፤ እርሷ በዳሶችዋ ላይ የወደቀች ሆና በርሷ ባወጣው ገንዘብ ላይ (እየተጸጸተ) መዳፎቹን የሚያገላብጥና ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድንም ባላጋራሁ የሚል ሆነ።" (ሱረቱል ከህፍ 42)፡፡
- አላህ በሰጠው ሃብትና ንብረት ጌታውን እያመሰገነ መልካም ሊሰራበት ሲገባው፡ በትእቢቱና በክህደቱ ሰበብ አላህ የሰጠውን ሃብት ተመልሶ የወሰደበትና ያጠፋበት ጊዜ፡- ‹‹ምነው በጌታዬ ባላጋራሁ ኖሮ!›› ብሎ ቢመኝ የማይሆን ከንቱ ምኞት ነው፡፡ በመሆኑም፡- አላህ በሰጠን ንብረት የሚገባውን ሶደቃ በመስጠት፡ አላህን ሊያስቆጣ ከሚችል ተግባርና ከኢስራፍ (ማባከን) በመጠንቀቅ፡ አኼራችንን እናሳምርበት፡፡
4. ምነው እሱን ጓደኛ ባላደረኩ!
" وَيَوْمَ يَعَضُّ الظَّالِمُ عَلَى يَدَيْهِ يَقُولُ يَا لَيْتَنِي اتَّخَذْتُ مَعَ الرَّسُولِ سَبِيلًا * يَا وَيْلَتَى لَيْتَنِي لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا * لَقَدْ أَضَلَّنِي عَنِ الذِّكْرِ بَعْدَ إِذْ جَاءَنِي وَكَانَ الشَّيْطَانُ لِلْإِنْسَانِ خَذُولًا " سورة الفرقان 29-27
"በዳይም፦ ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ ዋ ምኞቴ! እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)።ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፤ (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ፤ (ይላል)፤ ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው።" (ሱረቱል ፉርቃን 27-29)፡፡
- አላህ የላከለትን መልክተኛ ማመንና የሱን መንገድ ተከትሎ ከአማኞች ጋር መሆን እየቻለ፡ የክህደትን መንገድ መርጦ ከክፉ ጓደኞች ጋር ተወዳጅቶ መጨረሻውም ተበላሽቶ የሞተ ሰው፡ የትንሳኤ እለት የቅጣቲቱ ቃል ሲረጋገጥበት ጣቶቹን እየነከሰ፡- ‹‹ምነው መልክተኛውን በተከተልኩና ከነ-እንትና ጋር ጓደኝነትን ባልመሰረትኩ!›› እያለ ቢመኝና ቢቆጭ የማይሰራ ከንቱ ምኞት ከመሆን አይዘልም፡፡
ስለዚህም፡- ለአኼራ የሚጠቅመንን ጓደኛ እንምረጥ፡፡ ስናየው አኼራን የሚያስታውሰን፣ ስናጠፋ የሚገስጸንና የሚመክረን፣ ያላወቅነውን የሚያስተምረን፣ ኢማንና መልካም ስነ-ምግባር ያለው ወዳጅ እንፈልግ፡፡