የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
2ኛ. ጌታ አላህ በቅዱስ ቁርኣኑ ላይ በሚገርም ሁኔታ የሚነግረን፡ የኛ የሰዎች መልክ መለያየት (ጥቁር፣ ቀይ፣ ነጭ…) ለሱ ከአስደናቂ ምልክቶቹና ከአምላካዊ መገለጫ ባሕሪያቱ እንደሆነ ነው፡፡ በዚህ መልኩ አድርጎ የሰራን እሱ ነውና፡-
"ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፥ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ታምራቶች አሉበት።" (ሱረቱ-ሩም 22)፡፡ ታዲያ እንዴት ብለን ተመልሰን ጌታ አላህ ጥቁር አድርጎ የፈጠረውን ፍጥረት በጣም ይጠላዋል እንላለን?
3ኛ. ቅዱስ ቁርኣን እንደሚያስተምረው አላህ ዘንድ የተጠሉት ከነጭም ሆነ ከጥቁር ሰው ወይም ቀይ ከሆነ ሰው የሚገኙ ክፉ ተግባራት እንጂ፡ ቀይ ወይም ጥቁር መልክ ያለው ሰው አይደለም፡፡ ቀጣዮቹም አንቀጾች ይህን ይገልጻሉ፡-
"ልጆቻችሁንም ድኽነትን በመፍራት አትግደሉ፤ እኛ እንመግባቸዋለን፣ (እናንተንም እንመግባለን)፤ እነሱን መግደል ኃጢአት ነውና። ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ! ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፤ የተበደለም ሆኖ የተገደለ ሰው፣ ለዘመዱ (በገዳዩ ላይ) በእርግጥ ስልጣንን አድርገናል፤ በመግደልም ወሰንን አይለፍ፤ እርሱ የተረዳ ነውና። የየቲምንም ገንዘብ፣ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በሆነች ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ፤ በኪዳናችሁም ምሉ፤ ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና። በሰፈራችሁም ጊዜ ስፍርን ሙሉ፤ በትክክለኛው ሚዛንም መዝኑ፤ ይህ መልካም ነገር ነው፤ መጨረሻውም ያማረ ነው። ለአንተም በርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፤ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም፣ እነዚህ ሁሉ (ባለቤታቸው) ከነሱ ተጠያቂ ነውና። በምድርም ላይ የተንበጣረርክ ሆነህ አትኺድ፤ አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና፣ በርዝመትም ፈጽሞ ጋራዎችን አትደርስምና። ይህ ሁሉ መጥፎው እጌታህ ዘንድ #የተጠላ ነው።" (ሱረቱል ኢስራእ 31-38)፡፡
4ኛ. በኢስላም ውስጥ የአላህን አምላክነትና ብጨኛ ተመላኪነት፡ እንዲሁም የነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይነት ከመመስከር በኋላ የሚከተለው ሁለተኛው የኢስላም ማእዘን ‹ሶላት› ነው፡፡ ሶላት ደግሞ ወቅቱ መግባቱን ለማረጋገጥና አማኞችን ወደ አላህ ቤት ለመጥራት የሚደረገው ጥርሪ ‹አዛን› ነው፡፡ ይህንን አዛን ለመጀመሪያ ጊዜ በካዕባ አናት ላይ በመውጣት እንዲያሰማ የተፈቀደለት፡ የጥቁሮችና የሀበሾች ኩራት የሆነው ‹ቢላል ኢብኑ-ረባሕ› (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነው፡፡ ኢስላም ጥቁሮችን ማግለልና አላህ ዘንድ የተጠሉ አድርጎ ማቅረቡ እምነቱ ቢሆን ኖሮ፡ ለቢላል ይህ ሁሉ ቦታ ባልተሰጠው ነበር፡፡
5ኛ. ዛሬም ላይ በተጨባጩ ዓለም የምናየው እውነታ ይህንን ሐቅ ይመሰክራል፡፡ በነጮቹ ሀገር (አውሮፓና አሜሪካ) ስንት ጥቁር ሙስሊሞች የኢማምነትን (መሪነት) ቦታ ይዘው ነጮችን ከኋላቸው አሰልፈው ሰግደዋል! ስንትና ስንት ጥቁሮችስ ከነጮቹ ጋር በመቀላለቀል በእኩልነት በመቆም በአላህ ቤት እና በዳዕዋ መድረኮች ላይ አብሮ በመቀመጥ አሳልፈዋል!! ታዲያ ይህ እኩልነት መጽሐፍ ቅዱስ ያስተማራቸው ነውን? ለእኩልነቱስ ከሐጅ ስነ-ስርአት የበለጠ ምን አይነት አስረጂ እንዲመጣ ትፈልጋላችሁ? እውነት በነጮቹ ቤተክርስቲያን ላይ ከጥቁሮች ጋር በአንድነት በመቀላቀል ‹አምላክ› የሚሉትን በጋራ ያመልካሉን? ነጮቹን የሚመራ ጥቁር ሰባኪ አለን? ለምን ቅድሚያ የራስን ጉድፍ ማጥራቱ ላይ ትኩረት ተነፈገው?
6ኛ. እኛም ተጠይቀንና መልስ ሰጥተን ብቻ አንቀርምና፡ እስኪ በተራችን ስለ እምነታችሁ አንድ ጥያቄ እንጠይቃችሁ፡-
"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው። ከዘርህ በትውልዳቸው ነውር ያለበት ሰው ሁሉ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። ዕውር፥ ወይም አንካሳ፥ ወይም አፍንጫ ደፍጣጣ፥ ወይም፤ ትርፍ አካል ያለው፥ ወይም እግረ ሰባራ፥ ወይም እጀ ሰባራ፥ ወይም ጐባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዓይነ መጭማጫ፥ ወይም እከካም፥ ወይም ቋቍቻም፥ ወይም ጃንደረባ፥ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ። ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ሰው የእግዚአብሔርን የእሳት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነው፤ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። የቅዱሱንና የቅዱስ ቅዱሳኑን የአምላኩን እንጀራ ይብላ፤ ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ሙሴም ይህን ለአሮን፥ ለልጆቹም፥ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ ነገረ።" (ኦሪት ዘሌዋውያን ምእ 21፡ ቁ 16-24)፡፡
ጥያቄ፡- ዕውር፥ ወይም አንካሳ፥ ወይም አፍንጫ ደፍጣጣ፥ ወይም፤ ትርፍ አካል ያለው፥ ወይም እግረ ሰባራ፥ ወይም እጀ ሰባራ፥ ወይም ጐባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዓይነ መጭማጫ፥ ወይም እከካም፥ ወይም ቋቍቻም፥ ወይም ጃንደረባ፥ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ ለምን ተባለ? እነሱስ የሱ ፍጥረት አይደሉምን? ከሆኑስ ለምን ለአምላካቸው መስዋትን ያቀርቡ ዘንድ ወደ መቅደሱ መቅረብን ለምን ተከለከሉ?
7ኛ. በመጨረሻም ክርስቲያን ወገኖች ሆይ! በውሸት ፕሮፖጋንዳ እውነትን ልትደበቅ አትችልምና ይህን እወቁ፡፡ እናንተ የምትናገሩት እውነት ከሌላችሁ፡ ኑ ወደ ኢስላም፡፡ እዚህ ተነግሮ የማያልቅ እውነት አለና፡፡
" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَكُونُوا مَعَ الصَّادِقِينَ " سورة التوبة 119
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከዉነተኞቹም ጋር ሁኑ።" (ሱረቱ-ተውባህ 119)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder