የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አላህ "አል-ፈታሕ" በመሆኑ ለባሪያዎቹ የሚከፍተውን ሲሳይ ማንም ሊያጠፋውም ወይም ሊያጎድለው አይችልም፡-
"مَا يَفْتَحِ اللَّهُ لِلنَّاسِ مِنْ رَحْمَةٍ فَلَا مُمْسِكَ لَهَا وَمَا يُمْسِكْ فَلَا مُرْسِلَ لَهُ مِنْ بَعْدِهِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة فاطر 2
"አላህ ለሰዎች ከችሮታ #የሚከፍታት ለርሷ ምንም አጋጅ የላትም፤ የሚያግደውም ከርሱ በኋላ ለርሱ ምንም ለቃቂ የለውም፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" (ሱረቱ ፋጢር 2)
2. አላህ "አል-ፈታሕ" በመሆኑ በባሪያዎቹ መካከል ለማንም ሳያዳላ ማንንም ሳይበድል በዚህ በዱንያ፡ የቂያም ዕለትም በፍትህ ይፈርዳል፡-
"قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ " سورة سبأ 26
"ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፤ ከዚያም በመካከላችን በውነት #ይፈርዳል፤ እርሱም #በትክክል_ፈራጁ ዐዋቂው ነው በላቸው።" (ሱረቱ ሰበእ 26)፡፡
"قَالَ رَبِّ إِنَّ قَوْمِي كَذَّبُونِ * فَافْتَحْ بَيْنِي وَبَيْنَهُمْ فَتْحًا وَنَجِّنِي وَمَنْ مَعِيَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ " سورة الشعراء 118-117
"(እርሱም) አለ «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ አስተባበሉኝ፡፡ «በእኔና በእነርሱም መካከል (ተገቢ) #ፍርድን_ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም ምእምናን፡፡»" (ሱረቱ-ሹዐራእ 117-118)፡፡
"قَدِ افْتَرَيْنَا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا إِنْ عُدْنَا فِي مِلَّتِكُمْ بَعْدَ إِذْ نَجَّانَا اللَّهُ مِنْهَا وَمَا يَكُونُ لَنَا أَنْ نَعُودَ فِيهَا إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّنَا وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا عَلَى اللَّهِ تَوَكَّلْنَا رَبَّنَا افْتَحْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ قَوْمِنَا بِالْحَقِّ وَأَنْتَ خَيْرُ الْفَاتِحِينَ " سورة الأعراف 89
"አላህ ከርሷ ካአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ ውሸትን ቀጠፍን፤ አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለኛ ወደርሷ ልንመለስ አይገባንም፤ ጌታችን እውቀቱ ሁሉን ነገር ሰፋ በአላህ ላይ ተጠጋን፤ ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን መካከል በውነት ፍረድ፤ አንተም #ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ (አለ)።" (ሱረቱል አዕራፍ 89)፡፡
3. ጌታችን "አል-ፈታሕ" በመሆኑ ወደ አላህ ቤት (መስጂድ) ስንገባ የራሕመት በሮቹን እንዲከፍትልን ‹‹አልላሁመ-ኢፍተሕ-ሊ አብዋበ ፈድሊክ›› በማለት ልንለምነው ይገባል፡-
عَنْ أَبِى حُمَيْدٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم « إِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمُ الْمَسْجِدَ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ افْتَحْ لِى أَبْوَابَ رَحْمَتِكَ. وَإِذَا خَرَجَ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّى أَسْأَلُكَ مِنْ فَضْلِكَ » رواه مسلم.
አቢ ሑመይድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አንዳችሁ መስጂድ በገባ ጊዜ፡- ‹‹አላህ ሆይ! የእዝነት በሮችን (ሰበቦችን) ክፈትልኝ›› ሲወጣ ደግሞ፡- ‹‹አላህ ሆይ! ከትሩፋቶችህ እንድትለግሰኝ እለምንሀለሁ›› ይበል" (ሙስሊም 1685)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder