የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.2K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ትምሕርት ሁለት"🎧አዲስ ሙሐደራ 🎧
በቀዷ ወል–ቀደር ማመን
ክፍል አንድ

🎙 ኡስታዝ አቡ ሐይደር
በዩቱብ መከታተል ከፈለጉ🔎
https://youtu.be/yO_V-Q4cq6s
የዐረፋ ቀን

በአቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

የዐረፋ ቀን የሚባለው የዙል-ሒጃ 9ኛ ቀን ነው፡፡ ሓጅ አድራጊዎች ያለ ፆም በዐረፋ ተራራ ላይ ከእኩለ-ቀን (ዙህር) አንስቶ መግሪብ እስኪደርስ ይቆያሉ: በዱዓም ጌታቸውን ይማጸናሉ፡፡ ዙህርንና ዐሱርንም በአንድ ላይ ወደ ዙህር በማምጣት አሳጥረው ይሰግዳሉ፡፡ ጌታቸውም ወደነሱ ይቀርባል፡፡ በዚያም ቀን ብዙዎች በክፉ ተግባራቸው እሳት የተገባቸው: በአላህ ቸርነት ከእሳት ነጻ ይባላሉ፡፡ ሓጅ ያላደረጉት ደግሞ ቀኑን በፆምና በተለያየ ዒዳባህ ያሳልፉታል፡፡
ይህ ቀን ከሌሎች ቀናት ከሚለይባቸው ውስጥ፡-

1. ዲኑ የተሟላበት ቀን መሆኑ፡-

"...الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا..." سورة المائدة 3
"…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ…" (ሱረቱል ማኢዳህ 5:3)፡፡

ይህ ቅዱስ አንቀጽ የወረደው በዙል ሒጃ ወር፡ ሐጀተል ወዳዕ(የመሰናበቻው ሐጅ) በ 9ኛው ቀን: በዕለተ ጁምዓ በዐረፋ ተራራ ላይ ነበር፡፡

2. የሙስሊሞች ዒድ መሆኑ:–

ዑቅበተ ኢብኑ ዐሚር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን፣ የእርዱ ቀን፣ ቀጣዮቹም 3ቱ ቀናት የኛ ዒዳችን ነው" (ሶሒሑል ጃሚዕ 8192)።

3. ፆሙ የሁለት አመት ኃጢአት ያስምራል:–

አቢ ቀታዳህ እንዳሉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም የሁለት ዐመት (ያለፈውንና የሚመጣውን) ኃጢአት ያስምራል" (ከቡኻሪ በስተቀር ሁሉም የዘገበው)፡፡

4. ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን መሆኑ:–

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከዐረፋ ቀን ተሸሎ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን የለም" (ሙስሊም)፡፡

5/ ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ በዚህ ቀን መሆኑ:–

በማንኛውም ቀንና ለሊት፣ በማንኛውም ስፍራና ሁኔታ ወደ አላህ የሚደረገው ዱዓ በሩ ክፍት ነው። ተመላሽነት የለውም። ሆኖም በዐረፋ ቀን የሚደረገው ዱዓእ ግን ከየትኛውም ቀን የተሻለ ነው። ከዐብዱላህ ኢብኑ አምሩ ኢብኑል–ዓስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:– "ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓእ ነው፡፡ እኔና ከበፊቴ የነበሩት ነቢያት ከተናገርነው ቃላት ሁሉ በላጩ፡- ‹‹ላ ኢላሀ ኢልለሏሁ፡ ወሕደሁ፡ ላ-ሸሪከ ለህ፣ ለሁል-ሙልኩ፡ ወለሁል-ሐምድ፣ ወሁወ ዐላ-ኩሊ ሸይኢን ቀዲር›› የሚለው ነው" (ቲርሚዚይ 3585፣ ሶሒሑል-ጃሚዕ 3274)፡፡

6/ ለአምስት ቀናት የሚቆየው ተክቢራም የሚጀምረው በዚሁ በዐረፋ በዘጠነኛው ቀን ፈጅር ሶላት ጀምሮ ስለሆነ: በዚሁ ቀን ከፈርድ ሶላት በኋላ ሶስት ጊዜ አስተግፊሩላህ እንበልና ከዛም አላሁመ አንተ–ሰላም ...... ካልን በኋላ በቀጥታ ወደ ተክቢሩ በመግባት:– "አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር። ላ ኢላሀ ኢልለሏህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ" እንበል።

ዑዝር ላይ ላሉ ወንድም/እሕቶች:–

የዐረፋን ቀን ፆም ከልቡ ለመፆም የወሰነ ወንድም/እሕት፣ ነገር ግን በዑዝር ሰበብ (በሽታ፣ ሰፈር፣ ሐይድ፣ የወሊድ ደም፣ ወዘተ) ቀኑን መፆም ባይችልስ? ለሚለው ሸይኽ ስዑድ ከረመዷን ዐሽሩል አዋኺር ጋር ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው መልስ ስለሰጡበት: መልሱን እንዲህ አቅርበነዋል:–

ተጠያቂው ሸይኽ ኻሊድ ቢን ሱዑድ

ጥያቄ፡- አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ሸይኽ! በሐይድ ላይ ያለች ሴት ወይም የወለደች እንዴት አድርጋ የረመዷንን የመጨረሻ አስር ቀናት መጠቀም ትችላለች? ያ ሸይኽ! እኔ በጣም በመጨናነቄ ሰበብ እርሶ እንዲረዱኝና እንዲሁም ሀሳቡና ጭንቀቱ እንዲቀልልኝ እፈልጋለሁ፡፡ አላህም የለይለቱል-ቀድርን ምንዳ እንዳይከለክለኝ ዱዓእ እንዲያረጉልኝ እማጸንዎታለሁ፡፡

ምላሽ፡- ወዐለይኩሙ-ሰላሙ ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ የተከበርሽ እህቴ! ከሁሉ በፊት ቀድመሽ ልታውቂው የሚገባ ነገር፡- የወር አበባና የወሊድ ደም አላህ እሱ ብቻ ለሚያውቀውና ለፈለገው ጥበብም በአንቺ ላይ የወሰነው የተፈጥሮ ህግ መሆኑን ነው፡፡ መልካም ነገር ደግሞ አላህ ላንቺ የመረጠልሽ ነገር እንጂ አንቺ ለራስሽ የመረጥሽው አይደለም፡፡ አላህ ለወሰነው (ቀዷ ወል-ቀደር) እጅ ስጪ፡፡ ደግሞም አንቺ ለነፍሲያሽ ከጓጓሽው በላይ አላህ ላንቺ አዛኝ ጌታ መሆኑን እርግጠኛ ሁኚ፡፡

በተጨማሪም ልታውቂው የሚገባ ነገር፡- አንድ ሰው በዑዝር ወቅት በሰላም ጊዜ ይፈጽመው የነበረውን ነገር መቀጠል ቢያቅተው እንኳ አጅሩ ግን እንደማይቋረጥበት ነው፡፡ ተወዳጁ የአላህ ነቢይም (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡- "አንድ የአላህ ባሪያ ከታመመ ወይም ከመኖሪያ ክልል ርቆ (ሙሳፊር የሚሰኝበትን ያህል) ከተጓዘ: ጤነኛና የአካባቢው ነዋሪ ሆኖ ይፈጽመው የነበረው (መልካም ስራ) ሳይቋረጥ ይጻፍለታል" (ቡኻሪይ 2996)፡፡

አንቺ ደግሞ በሐይድ ወቅት ያለ ጥርጥር ዑዝር ያለሽ ነሽ፡፡ ምክንያቱም፡- ያለ ምርጫሽና ፍላጎትሽ የመጣ በመሆኑ፡፡ እንዲሁም ልትከላከዪውና ልታስቀሪው የማትችዪው ነገር ስለሆነ፡፡ በድጋሚም ማወቅ ያለብሽ ነገር፡- አንድ የአላህ ባሪያ አንድን ነገር ለመስራት ከልብ የቆረጠ ኒያ ካለው ከዛም ያንን የነየተውን ነገር ለመስራት ድንገተኛ ሁኔታና ክስተት ቢከለክለውና ቢያግደው፤ አላህ ግን እንደሰራው በመቁጠር ሙሉ አጅሩን የሚጽፍለት መሆኑን ነው፡፡ ይህንን አስመልክቶ የአላህ ነቢይም (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡-

"በመዲና ውስጥ ሰዎች አሉ፡፡ እናንተ አንድንም ሸለቆ አታቋርጡም መንገድንም አትዘልቁም እነሱ በአጅር ቢጋሯችሁ እንጂ፡፡ ከናንተው ጋር አብረው እንዳይጓዙ ዑዝር ከለከላቸው" (ቡኻሪይ)፡፡

በሌላ ቅዱስ ትምህርታቸው ላይ ደግሞ እንዲህ አሉ፡- "አላህን በፍጹም ልቡ ሸሂድነትን (ለዲን ሰማእት ሆኖ መሞትን) እንዲወፍቀው የለመነ ሰው ቀኑ ደርሶ በፍራሹ ላይ እንኳ ቢሞት(በኒያው ሰበብ) የሸሂዶችን (ሰማእታት) ደረጃ ያጎናጽፈዋል" (ሙስሊም)፡፡

ታዲያ አንቺም እንደ ሌሎቹ ሙስሊም እህቶችሽና ወንድሞችሽ እነዚህን አስር ቀናት በዒባዳ ለማሳለፍ ገና ከመጀመሪያው የነየትሽና የጓጓሽለት ከነበር ጌታሽ ኒያሽን ከንቱ እንደማያረግብሽ ባለሙሉ ተስፋ ሁኚ አብሽሪ፡፡

ሌላው ደግሞ ይህ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ሶላት ከመስገድ፣ ጾም ከመጾምና መስጂድ ከመግባት ቢያግድሽም ሌሎች ያልተከለከልሻቸው ዒባዳዎች መኖራቸውንም አትዘንጊ፡፡ ከነዚም መካከል፡- (ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር…) አዝካሮችን ማለት፣ ዱዓእ ማድረግ፣ በነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ላይ ሶላዋት ማውረድ፣ ሶደቃ ማውጣት፣ ኢስቲግፋር ማብዛት፣ በአላህ ስሞችና በሱ ስራዎች ማስተንተንን የመሳሰሉት፡፡
በመጨረሻም ማወቅ ያለብሽ ነገር፡- እነዚህ አስር ቀናት በዑዝር ሰበብ ሊያመልጠኝ ነው ብለሽ ማሰብና መጨነቅሽ በራሱ የሚያመላክተው የኢማንሽን ታላቅነት፣ ወደ አላህ ለመቃረብ ያለሽን ጉጉት ነው ኢንሻአላህ፡፡ ስለዚህም የቻልሽውን ያህል ኸይር ስራ ለመስራት ታገዪ፣ ተረጋጊ አትጨናነቂ፣ አይዞሽ፣ አላህ ላይ ያለሽን ተስፋ ከፍ አድርጊ እሱ ኒያሽንም ሆነ መልካም ስራሽን አያባክነውም ምንዳውንም አይከለክልሽም፡፡ የሱ እዝነት አንቺን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን ሁሉ የሰፋና ያካለለ ነውና፡፡ ወሰሊላሁመ ወሰለም ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ ወዓላ ኣሊሂ ወሰሕቢሂ ወሰለም፡፡

ስለዚህ መጪው ሐሙስ የዐረፋ ቀን ነውና ይህን ቀን እንጹመው እንዳያመልጠን፡፡ በእስር ያሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንንም እንዲሁም ዓለም ላይ ያሉ የሚሰቃዩትን ሙስሊሞችን በዱዓ እንዳንረሳቸው፡፡ አላህ ይወፍቀን አሚን፡፡
Join us➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Click and Like ➤➤
ኢድ ሙባረክ

በመላው አለም ለምትገኙ ሙስሊም ወንድም እና እህቶቼ እንኳን አላህ ለ1441ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሰን ፤አደርሳችሁ ለማለት እወዳለሁኝ

ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኸል ዓዕማል
ነጌም ፆም የለም!

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال : ( نَهَى النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنْ صَوْمِ يَوْمِ الْفِطْرِ وَالنَّحْرِ) . رواه البخاري (1992) ، ومسلم (827) .

ከአቢ ሰዒድ አል–ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ አለ:– " የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዒዱል ፊጥር ቀንና የውሙ–ነሕር (ዒዱል አድሓ 10ኛው የዙል–ሒጅጃህ ቀንን) መፆምን ከለከሉ" (ቡኻሪና ሙስሊም)።

كما يحرم صيام أيام التشريق وهي الأيام الثلاثة بعد يوم عيد الأضحى ( الحادي عشر ، والثاني عشر ، والثالث عشر ، من شهر ذي الحجة ) لقوله صلى الله عليه وسلم : ( أيام التشريق أيام أكل وشرب وذكر لله ) رواه مسلم (1141) .

በሌላ ሐዲሥም የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "አያሙ ተሽሪቅ (የዙል–ሒጅጃህ 11ኛ 12ኛና 13ተኛ ቀናት) የመብያ፣ የመጠጫ እና አላህን በብዛት የማውሻ ቀናት ናቸው" ብለዋል። (ሙስሊም 1141)።

وروى أبو داود (2418) عَنْ أَبِي مُرَّةَ مَوْلَى أُمِّ هَانِئٍ أَنَّهُ دَخَلَ مَعَ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو عَلَى أَبِيهِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ فَقَرَّبَ إِلَيْهِمَا طَعَامًا ، فَقَالَ : كُلْ . فَقَالَ : إِنِّي صَائِمٌ . فَقَالَ عَمْرٌو : كُلْ فَهَذِهِ الأَيَّامُ الَّتِي كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَأْمُرُنَا بِإِفْطَارِهَا ، وَيَنْهَانَا عَنْ صِيَامِهَا . قَالَ الإمام مَالِكٌ : وَهِيَ أَيَّامُ التَّشْرِيقِ . وصححه الألباني في صحيح أبي داود .

አቢ ሙርራህ ከዐብዱላህ ኢብኑ ዐምሩ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ጋር ወደ አባቱ ዐምሩ ኢብኑል–ዓስ ጋር ገቡ። ምግብም አቀረበላቸውና ብላ አለው። አቢ ሙራህም <<እኔ ፆመኛ ነኝ>> አለ። ዐምሩ ኢብኑል–ዓስም:– <<ብላ! እነዚህን ቀናት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንድንበላ ያዙን ነበር። ቀናቱን ከመፆምም ይከለክሉን ነበር >> ኢማሙ ማሊክም (ረሒመሁላህ) እነዚህ ቀናት አያሙ ተሽሪቅ ናቸው አሉ" (አቡ ዳዉድ የዘገበው። ሸይኽ አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል)።

የአያሙል–ቢድ ደንበኞች ለኾናችሁ!

አያሙል–ቢድ በመባል የሚታወቁት ቀናቶች በእስልምናው አቆጣጠር የወሩ 13ኛ, 14ኛ እና 15ኛ ቀናት ናቸው። በየወሩ ሶስት ቀናትን በመፆም ከጌታቸው እጥፍ ድርብ የኾነ መልካም ምንዳን የሚከጅሉ ሙስሊም የአላህ ባሪያዎች: በብዛት ለፆም የሚያውሉት እነዚህን የአያሙል–ቢድ ቀናት ነው። አሁን ያለንበት 12ኛው የዙል–ሒጃህ ወር 13ኛው ቀን የአያሙ–ተሽሪቅ ቀን ነገ ሰኞ ነው። አያሙ ተሽሪቅ በመባል የሚጠሩት የዙል–ሒጃህ 11ኛ, 12ኛ እና 13ኛ ቀናት ደግሞ የሙስሊሞች ዒድ በመኾናቸው: በነዚህ ቀናት አይፆምም። በመኾኑም አያሙል–ቢድን በፆም የሚያሳልፉ አንዳንድ እሕቶች የነገውን 13ኛ ቀን ምን እናድርገው? በማለት ጥያቄን አቅርበዋል። ለዚህ የሚሰጠው መጠነኛ ምላሽም:–

ሀ/ በየወሩ ሶስት ቀናትን የሚፆም የአላህ ባሪያ: እነዚህን ሶስት ቀናት ለመፆም የግድ የወሩን 13ኛ, 14ኛ እና 15ኛ ቀናት መጠበቅ የለበትም። ዋናው ነገር የገባው ወር ተጠናቅቆ ከመውጣቱና ሌላ ቀጣዩ ወር ከመምጣቱ በፊት ሶስት ቀናትን መርጦ መፆሙ ነው። አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገው:– "ወዳጄ (ረሱል ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እስክሞት ድረስ በየወሩ ሶስት ቀናትን በመፆም፣ ሶላተ–ዱሓን በመስገድ፣ ዊትርን ከሰገድኩ በኋላ መተኛትን እንዳዘወትርና እንዳልተዋቸው መክረውኛል" ይለናል (ቡኻሪና ሙስሊም)።

ሙዐዘቱል–ዐደዊያ (ረሒመሃላህ) እናታችንን ዓኢሻን (ረዲየላሁ ዐንሃ) :– የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በየወሩ ሶስት ቀናትን ይፆሙ ነበርን? በማለት ጠየቀቻት። እናታችንም "አዎን!" በማለት መለሰች። እሷም:– "ከወሩ የትኞቹን ቀናት ነበር?" ብላ ስትጠይቃት: እናታችንም:– "እሳቸው የሚፆሟቸውን የወሩን ቀናት (መምረጥ) ግድ አይላቸውም" ነበር በማለት መለሰችላት። (ሙስሊም 1160)።

ለ/ እነዚህ የወሩ ሶስት ቀናቶች ደግሞ የግድ ተከታታይ መኾን የለባቸውም። የፈለገ ሰው ሶስቱንም ቀናት አከታትሎ፣ የፈለገ ደግሞ ቀናቱን አለያይቶና አፈራርቆ ወሩ ከመውጣቱ በፊት መፆም ይችላል። ሐዲሡም የሚናገረው "ሶስት ቀናትን ስለመፆም" እንጂ: እነዚህን ቀናት ስለማከታተል አይደለም። የኢስላም ሊቃውንትም እነዚህን ቀናት በማፈራረቅ መፆም እንደሚቻል ፈትዋ ሰጥተዋል። (ኢብኑ ዑሠይሚን: መጅሙዕ ፈታዋ ወረሳኢል ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን: ጥራዝ 20: ኪታቡ–ሲያም: ጥያቄ ቁ· 376)።

ሐ/ እነዚህን ሶስት የፆም ቀናት በአያሙል–ቢድ ማድረጉ ግን በላጭና ተወዳጅ ነው። አቢ ዘር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል:– "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉኝ:– ከወሩ ውስጥ የተወሰነ ቀናትን ከፆምክ: 13ኛውን, 14ኛውንና 15ኛውን ቀን ፁም" (ቲርሚዚይ 761፣ ነሳኢይ 2424፣ አልባኒይ: ሶሒሑ ተርጚብ ወት–ተርሂብ 1038)።

ሆኖም እነዚህን አያመል–ቢድ መፆም ያስለመደ የአላህ ባሪያ በሐይድ ወይም በህመም እና መሰል ዑዝር ሰበብ ቀናቶቹ ቢያመልጡት: ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት በቀሪዎቹ 15 ቀናት ውስጥ መፆም ይችላል። ወላሁ አዕለም።

3/ ሌላው ማወቅ የሚገባን ነገር: በወሩ ውስጥ ሶስት ቀናትን መርጦ መፆም ሲባል: የወር አቆጣጠሩ ኢስላማዊውን የሂጅሪ ካላንደር መሠረት ያደረገ እንጂ: የአውሮፓውያንን ወይም ሀገር ቤት ያለውን የቀን አቆጣጠር የተረመኮዘ አለመሆኑን ነው። አንደኛው ወር ተጠናቅቆ ቀጣዩ ወር መግባቱን የምናውቀው በሒጅራው አቆጣጠር ብቻ ነው። ይህን ለማወቅ እንዲረዳችሁ በሞባይላችሁ ላይ Hijri calander የሚለውን አፕ በማውረድ ይጠቀሙ።

Click and Like ➤➤ http://fb.com/Ustaz.Abuhyder
👍1
Audio
"ትምሕርት ሁለት"🎧አዲስ ሙሐደራ 🎧
በቀዷ ወል–ቀደር ማመን
ክፍል ((3))

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/3adCGZz

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join us➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder