አዲስ መጽሐፍ፣ አዲስ ርእስ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
"የመላእክ ዓለም"
የመላእክት ዓለም በሚል ርእስ: ስለ መላእክት ምንነትና ማንነት ቅዱስ ቁርኣንንና ነቢያዊ ሐዲሥን መሰረት ያደረገ ጥናታዊ ጽሑፍ። ያንቡት በአላህ ፈቃድ ይጠቀሙበታል። በተለይ ስለ መላእክት ማንነት በሰፊው የሚናገር በሀገራችን ቋንቋ የተዘጋጀ መጽሐፍ ገበያ ላይ አለመገኘቱ ይህን ክፍተት ይሞላዋል የሚል ተስፋ አለኝ።
ርእስ:– የመላእት ዓለም
ዝግጅት:– አቡ ሀይደር (ሳዲቅ መሐመድ)
ገፅ:– 200
መጽሐፉን ለማግኘት 0911 83 95 32 ሀይደር ጀማል በመደወል ያነጋግሩት

እንደምናውቀው Sadiq Mohammed Ahmed በየሀገሩ እየተዘዋወረ ዳእዋ ያደርጋልና በዚህ ዳእዋ የታዘባቸው ብዙ ነገሮች አሉ ተጀምረው የተተው መስጂዶች የኪታብና የቁርኣ እጥረት ሌሎችም እና በዚህ ዙርያ ሰብሰብ ብለን ያቅማችንን እለግስ።
ረመዳን ከመድረሱ በፊት የሚጠናቀቅ ትልቅ ኸይር ስራ ናትና እንዳያመልጣቹ።
https://chat.whatsapp.com/IlrTYYEbS05IgORHNzZm4l
ኃላፊ ፦
ኡስታዝ አቡ ሐይደር (ሷዲቅ ሙሐመድ)
ምክትል 😉 ፦ እህት የምን ሀዘን ( ሦፍያ) ያልገባችሁ ካለ 00971565542936 ቀጥታም ዋትሳፕም ቴሌ ግራምም ማናገር ትችላላቹ

ቁርኣንን አንብቡ!
በአቡ ሐይደር
በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን(አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
1/ እንደሚታወቀው የረመዷን ወር ከተቀሩት 11 ወራቶች በተለየ መልኩ የቁርኣን ወር ነው፡፡ በዚህ ወር ከሚሰሩት የዒባዳህ (አምልኮ) ተግባራት ውስጥ ከጾሙ ቀጥሎ ቁርኣን መቅራት ከፍተኛውን ስፍራ ይይዛል፡፡ በሐዲሥ እንደተነገረውም ከአላህ መጽሐፍ (ከቁርኣን) አንድን ፊደል የሚያነብ ሰው ከአስር እስከ ሰባት መቶ ከዛም በላይ አጅር (አምላካዊ ደሞዝን) እንደሚያገኝ ተገልጾአል፡፡ ከፊደል አልፎ ቃላትን፣ ከቃላት አልፎ አየትን (አንድን አንቀጽ)፣ ከአየት አልፎ ሱራን (አንድ ሙሉ ምእራፍ)፣ ከሱራ አልፎ ጁዝእን፣ ከጁዝእ አልፎ ሙሉ ቁርኣንን የቀራ ሰው፡ አላህ ከተቀበለው ምን ያህል ይሆን አጅሩ? አላህ ይወፍቀን፡፡
2/ አንዳንድ ሰዎች፡- እኔ ቁርኣን አላኸተምኩም (ሙሉ ሰላሳ ጁዝኡን አልቀራሁም)፡ የቀራሁት እስከ ሁለትና ሶስት ጁዝእ ድረስ ነው በማለት የቅሬታ ድምጽ ያሰማሉ፡፡ ሐቢቢ፡- በሐዲሡ ላይ እኮ ይህን ታላቅ አጅር ለማግኘት ቃል የተገባላቸው ‹‹ቁርኣንን ያኸተሙ›› ወይም ‹‹በቃል የሐፈዙ›› ሰዎችን አይደለም፡፡ ቃል የተገባው ከቁርኣኑ ውስጥ ከአንዲት ሐርፍ (ፊደል) ጀምሮ የቻሉትን ያክል ለመቅራት የወሰኑትን ነው፡፡ ታዲያ አንተና አንቺ ሁለት ወይም ሶስት ጁዝእ ከደረሳችሁ፡ ለምን እነዚህን በየቀኑ በመደጋገም አትቀሯቸውም? 30 ጁዝኡን የቀሩ ሰዎች ደጋግመው ሲያኸትሙ ካያችሁ፡ እናንተም 3ጁዝኡን ለምን ደጋግማችሁ አትቀሩም? አላህ ካደረሰን ደግሞ በቀጣዩ አመት ቁርኣንን ቀርተን እንደናንተው አኽትመን እንደርስባችኋለን የሚልን ተስፋ በልብ ሰንቃችሁ ማለት ነው፡፡
3/ አንዳንዶች ደግሞ፡- እኔ ምንም ቁርኣን አልቀራሁም በማለት ስሞታ ያቀርባሉ፡፡ አልገባችሁም እንጂ እናንተም የአቅማችሁን ቀርታችኋል!!፡፡ ምነው ሶላት ትሰግዱ የለም እንዴ? ብለን ብንጠይቃችሁ፡ እሱማ አዎ! የሚል መልስ ነው የምትሰጡን፡፡ ታዲያ ለሶላት ስትቆሙ ምንድነው የምትሉት? ብንላችሁስ፡ መልሳችሁ፡- ያው ፋቲሓና ቁል-ሁ ወይም ኢንና አዕጠይና የሚል ነው፡፡ እንግዲያውስ ሱረቱል ፋቲሓ፣ ኢኽላስ፣ ከውሠር የቁርኣን ክፍል አይደሉምን? እንዴታ! ናቸው እንጂ ብላችሁ ከተስማማችሁ፡ በሉ እናንተም እነዚህን የቁርኣን ክፍሎች ሶላት ላይ እንደምትቀሯቸው ሁሉ፡ ጊዜ ስጧቸውና ቁጭ ብላችሁ ደግሞ የቂርኣትን አጅር በመነየት በቃላችሁ ደጋግማችሁ ቅሯቸው፡፡ አላህ ዘንድ ተቀባይነትን ካገኘ ዋጋችሁ ታላቅ ይሆናልና፡፡
ምነው ዚክር የሚያበዙ ሰዎች አብዛኞቹ፡ የዚክሩን ምንጭ ከሐዲሥ የተማሩት መሰላችሁ እንዴ? ከመስጂድ በዓሊሞች፡ በዳዒዎች ሰበብ የሰሙት፣ ከመጽሐፍ ያነበቡት፣ በሲዲ ወይም በቴሌቪዥን ጣቢያ አማካኝነት በማዳመጥ የወረሱት እኮ ነው፡፡ እናንተም እነዚህን ቁርኣን በቃላችሁ ደጋግማችሁ ከመቅራት አትቦዝኑ እሺ? ለቀጣዩ ደግሞ ቁርኣንን ተምራችሁ፡ ሙስሐፉን (ዋናውን መጽሐፍ) በእጃችሁ ይዛችሁ በአላህ ፈቃድ ለመቅራት ከልባችሁ ወስኑ፡፡ አላህ ይርዳን፡፡
ወሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

ረመዷን መጣ!! 1
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ታላቁና ተወዳጁ ነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሶሐቦቻቸውን የረመዷንን መቃረብ አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ ብስራትን ሲገልጹ እንዲህ ይሏቸው ነበር፡- "የተባረከ ወር የሆነው ረመዷን መጣላችሁ!፡፡ አላህ ጾሙን በናንተ ላይ ግዳጅ አድርጓል፡፡ በዚህ ወር የሰማይ ደጃፎች ይከፈታሉ፡፡ የጀሀነም ደጃፎች ይዘጋሉ፡፡ አመጠኛ ሸይጧናት ይታሰራሉ፡፡ አላህ ከአንድ ሺህ ወር (ስራ) የምትበልጥ የሆነች አንድ ለሊት አለችው፡፡ የዚህን ወር መልካም ነገር የተነፈገ ሰው በርግጥም ከብዙ መልካም ነገራት የተነፈገ ነው፡፡" (አሕመድ 7148፣ ነሳኢይ 2106)፡፡
ይህ የነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ብስራት ዋና አላማው ሶሓባዎች ከወዲሁ ይህንን የተከበረ ወር ለመቀበል መንፈሳዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማነሳሳት ነው፡፡ እኛስ ምን ያህል ተዘጋጅተናል?
ለዛሬ መግቢያ እንዲሆነን ስለ ረመዷን ፈዷኢል (በረከቶች) የተወሰነ ነገር እንነጋገር፡፡
1. የረመዷን ወር ክብር፡-
የረመዷን ወር በኢስላማዊው የወር አቆጣጠር መሰረት፡ ዘጠነኛ ወር ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ ወር ከተቀሩት 11ዱ ወራቶች ለየት የሚያደርገው የራሱ የሆኑ መለያዎች አሉት፡፡ ከነዚህም መለያዎቹ መካከል፡-
ሀ. የጀነት በሮች የሚከፈትበት ወር መሆኑ፡-
የመልካም ስራ መንገዶችና የጥመት ጎዳናዎች በአስራ ሁለቱም ወራት (ሙሉ ዓመት) ለፈላጊዎችና ለሰሪዎች ክፍት ነው፡፡ የአላህ ባሮች ከረመዷን በፊት፣ በረመዷን ውስጥና ከረመዷን በኋላ ባሉት ወራቶች ላይ ወደ ጌታቸው አላህ የሚያቃርባቸውን መልካም ስራ ከመስራት አይቦዝኑም፡፡ የሸይጧን ሰራዊቶች ደግሞ (ተውፊቁን ካላገኙ) ከአላህ የሚያርቃቸውን የጥፋት መስመሮች ከመከተልና ክፋትን ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ የረመዷን ወር የሚለየው ግን ጀነት ለፈላጊዎቿ ተሸሞንሙና ደጃፎቿ ወለል ብለው ተከፍተው ሲታዩ፡ የጀሀነም በሮች ደግሞ የሚከረቸሙ መሆናቸው ነው፡፡
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የረመዷን የመጀመሪው ለሊት ላይ አመጸኛ ሰይጣናት ይታሰራሉ፣ የእሳት በሮች አንድም ሳይቀር ይከረቸማሉ፣ የጀነት በሮች አንድም ሳይቀር ይከፈታሉ፣ በእያንዳንዱ ለሊትም አንድ ተጣሪ እንዲህ በማለት ይጣራል፡- ‹‹መልካም ፈላጊ የሆንክ ሆይ! ፊትህን (ወደ መልካም ተግባር) አዙር፡፡ መጥፎን ፈላጊ የሆንከው ሆይ! (የምትሰራውን ክፋት) ቀንስ(አቁም)፡፡ በያንዳንዱ ለሊትም አላህ ከእሳት ነጻ የሚያደርጋቸው ባሮች አሉት" (አሕመድ 18438)፡፡
ለ. የኃጢአት ማስተሰረያ (ማጥፊያ) መሆኑ፡-
በማንኛውም ወቅት የሚሰራ መልካም ስራና ወደ አላህ የሚደረግ የንሰሀ ተውበት ኃጢአትን ያጠፋል (ሁድ 114፣ አዝ-ዙመር 53)፡፡ የረመዷን ወር ደግሞ በአግባቡ ከተጾመ፡ ቀጣዩ አመት ረመዷን እስኪመጣ ድረስ በመሀከሉ የተፈጸሙ ጥቃቅን ኃጢአቶችን በመላ ያጠፋል፡፡ ትላልቅ ኃጢአቶች (ከባኢረ-ዙኑብ) የግድ ባለቤቱ ተውበት ሊያደርግባቸው ያስፈልጋቸዋልና፡፡
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አምስት ወቅት ሶላቶችን መስገድ፣ ጁሙዓ ተሰግዶ ቀጣዩ ሳምንት ጁሙዓህ እስኪመጣ፣ ረመዷን ተጹሞ ቀጣዩ ረመዷን እስኪመጣ ድረስ ሰውየው ትላልቅ ኃጢአትን እስከተጠነቀቀ ድረስ በመሀከላቸው ያለውን ትናንሽ ኃጢአት ያስሰርዛሉ" (ሙስሊም)፡፡
ሐ. የዑምራህ ደረጃህ ከፍ ማለቱ፡-
ከሐጅ ስርዓት ውጪ ዑምራን ብቻ መፈጸም አጅር የሚያስገኝ የሱና (ሙስተሐብ) ተግባር ነው፡፡ በረመዷን የሚፈጸም ከሆነ ግን አጅሩ ከፍ ብሎ በማደግ የሐጅን ምንዳ ያህል ይደርሳል፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "በረመዷን የሚደረግ ዑምራ (ምንዳው) ከሐጅ ጋር ይስተካከላል" (ሙስሊም)፡፡
መ. ቁርኣን የወረደበት ወር መሆኑ፡-
የህይወታችን መመሪያ በመሆን፣ ማን እንደፈጠረን፡ ለምንስ እንደተፈጠርን፣ እንዴት መኖር እንዳለብንና ወደየት እንደምንጓዝ በቂ ምላሽን በመስጠት ማንነታችንን የጠራ መስታወት በመሆን የሚነግረን አምላካዊ ቃል የሆነው ቅዱስ ቁርኣን የወረደው በዚሁ የተከበረ ወር፡ በተከበረች ለሊት፡ በውሳኔዋ ምሽት (ለይለቱል ቀድር) ውስጥ ነው፡፡
"(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው…" (ሱረቱል በቀራህ 185)፡፡
"እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፤ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና።" (ሱረቱ-ዱኻን 3)፡፡
"እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛዪቱ ሌሊት አወረድነው።" (ሱረቱል ቀድር 1)፡፡
ቁርኣን በረመዷን ወር ‹‹ወረደ›› የሚለው ሁለት መልእክትን ያቀፈ ነው፡-
1ኛ፡- ከለውሐል መሕፉዝ (ጥብቅ ሰሌዳ) ወደ ምድራዊ ሰማይ የተከበረው ቤት (በይቱል-ዒዝዛህ) ሲወርድ በጠቅላላ አንድ ጊዜ በዚህ ወር ውስጥ ወርዷል ሲሆን፡-
2ኛ. ከምድራዊው ሰማይ (በይቱል-ዒዝዛህ) ወደ ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ልብ በመልአኩ ጂብሪል (ዐለይሂ-ሰላም) አማካኝነት ሲወርድ በዚሁ ወር ነው መውረድ የጀመረው ማለት ነው፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
ሠ. ለይለቱል-ቀድር (የውሳኔው ለሊት) የምትገኝበት ወር መሆኑ፡-
በዚህች አንድ ለሊት የሚሰራ መልካም ስራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ካገኘ፡ የስራው ደረጃ ሰውየው አንድ ሺህ ወራት (83 ዓመት ከ4 ወር) ተቀምጦ ከሚሰራቸው መልካም ስራዎች የበለጠ ይሆናል፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡
"መወሰኛይቱ ሌሊት ምን እንደ ሆነች ምን አሳወቅህ? መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት።" (ሱረቱል ቀደር 2-3)፡፡
ረ. ቂያሙ ረመዷን (ሶላቱ-ተራዊሕ) የሚገኝበት መሆኑ፡-
በረመዷን ወር ሙስሊሞች ተሰባስበው ከዒሻእ ሶላት በኋላ በጀመዓ የሚሰግዱት ሶላት፡- ቂያሙ ረመዷን (ሶላቱ-ተራዊሕ) ይባላል፡፡
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የረመዷንን ወር አምኖና (ምንዳውንም) ነይቶ (በዒባዳ) የቆመ ሰው፡ ከዚህ በፊት የፈጸማቸው (ጥቃቅን) ሃጢአቶቹ በመላ ይማራሉ" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
ሰ. ኢዕቲካፍ የሚገኝበት ወር መሆኑ፡-
በማንኛውም ቀንና ሰዓት አንድ ሙስሊም የተወሰነ ሰዓታትን በዒባዳ ለማሳለፍ ወስኖ በመስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ መቀመጥ ይችላል (አል በቀራህ 187)፡፡ በረመዷን ግን ለየት ባለ መልኩ የመጨረሻዎቹን ሙሉ አስር ቀናት በመስጂድ ውስጥ በዒባዳ ለማሳለፍ ራሱን በማገድ (ኢዕቲካፍ) ማድረግ ይቻላል፡፡
አዒሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የረመዷንን የመጨረሻ አስርት ቀናት እስኪሞቱ ድረስ ሁሌም ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር፡፡ ከሳቸውም ሞት በኋላ ሚስቶቻቸውም ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር" (ቡኻሪይ)፡፡

ሸ. የቸርነትና የለጋስነት ወር መሆኑ፡-
ቸር መሆን በማንኛውም ቀንና በማንኛውም ሰዓት የተወደደ መልካም ተግባር ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በረመዷን!
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሰዎች ሁሉ በላይ ቸርና ለጋስ ነበሩ፡፡ በተለይም እጅግ ቸርና ለጋስ ይሆኑ የነበረው በረመዷን ጂብሪል በሚገናኛቸው ወቅት ነበር፡፡ ጂብሪል (ዐለይሂ-ሰላም) በየለሊቱ እየመጣ ቁርኣንን ይጠናኑ ነበር፡፡ የሳቸው መልካም ነገር ላይ የነበራቸው ቸርነትም ከተላከ ነፋስ የፈጠነ ነበር" (ቡኻሪይ)፡፡
ቀ. አመጠኛ ሰይጣናት የሚታሰሩበት መሆኑ፡-
ሸይጧን በረመዷን ወር የሚታሰር መሆኑን ለማመን ከሐዲሡም ውጪ በተግባር የሚታይ እውነታ ነው፡፡ ቢያንስ ሁለት ምክንያቶችን ማቅረብ ይቻላል፡-
1ኛ. የአላህ ቤቶች ሁሉ በሰጋጅ ይጨናነቃሉ፡፡ መስጂዶች ይሞላሉ፡፡ ሁሉም ሙስሊም ይህ ሁሉ ሰው ከየት መጣ! በማለት ይገረማል፡፡ ኢስላምን የሚቀበሉ አዲስ ገቢዎች ጥቂት ቢሆኑም፡ አብዝኃኛው ግን በቤቱና በስራ ቦታው ይሰግድ የነበረ፡ እንዲሁም ከሶላት ጋር ትውውቅ ያልነበረው ሰው ነው፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ህዝብ ከረመዷን በፊት በአላህ ቤት ለመታየት ያልገራለት፡ አሁን በረመዷን ግን መምጣቱ ይፈታተነው የነበረው ሸይጧን መታሰሩን አያመላክትምን?
2ኛ. ዒባዳን ለመተግበር ይቀላል፡፡ ከረመዷን ውጪ ተዘግቶ በክብር ስፍራ የተቀመጠው ቁርኣን በረመዷን አንባቢው ይበዛል፡፡ 1ብር ለመለገስ የሰሰቱ የነበሩ ልቦች፡ በረመዷን ግን ለማስፈጠርና ለሶደቃ ግን ይቻኮላሉ፡፡ ይህን ኸይር ስራ አሁን ለመስራት ከገራልዎት፡ ከአላህ ተውፊቅ በኋላ የሸይጧን መታሰርን አይጠቁምምን?
"የተባረከ ወር የሆነው ረመዷን መጣላችሁ!፡፡ አላህ ጾሙን በናንተ ላይ ግዳጅ አድርጓል፡፡ በዚህ ወር የሰማይ ደጃፎች ይከፈታሉ፡፡ የጀሀነም ደጃፎች ይዘጋሉ፡፡ አመጠኛ ሸይጣናት ይታሰራሉ…" (አሕመድ 7148፣ ነሳኢይ 2106)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder

የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
"የአላህ መለኮታዊ መልካምና ውብ ስሞች" ክፍል 5 ☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ ➤ https://goo.gl/tjwV4t Join us➤ t.me/abuhyder
Audio
"የአላህ መለኮታዊ መልካምና ውብ ስሞች" ክፍል 6
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/tjwV4t
Join us➤ t.me/abuhyder
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/tjwV4t
Join us➤ t.me/abuhyder
ረመዷን መጣ!! ቁጥር 2
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
2. የጾም ትርጉምና ጠቀሜታው
ትላንት በአላህ ፈቃድ የመጀመሪያውን ፕሮግራም ‹‹ፈዷኢሉ-ረመዷን›› የረመዷን ወር ክብርና ደረጃዎች የሚለውን በመጠኑ ተመልክተናል አልሐምዱ ሊላሂ ረቢል-ዓለሚን፡፡ ዛሬ ደግሞ አላህ ፈቃዱ ከሆነ የጾምን ትርጓሜና ጠቀሜታዎችን በመጠኑ እንቃኛለን ኢንሻአላህ፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
ሰውም የሚለው የዐረብኛ ቃል ቀጥታ ፍቺው ‹‹መቆጠብ›› ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር ከመናገር ወይም ከመስራት መቆጠብ ሰውም (ጾም) ተብሎ ይጠራል፡፡ በንግግሩ ያሰለቸንን ሰው፡- ለምን አፍህ አይጾምም! ስንለው፡ የተፈለገው ለምን ዝም አትልም! ለማለት ነው፡፡ ይህንን ትርጉም የሚያመላክተን ቀጣዩ የቁርኣን አንቀጽ ነው፡-
" فَكُلِي وَاشْرَبِي وَقَرِّي عَيْنًا فَإِمَّا تَرَيِنَّ مِنَ الْبَشَرِ أَحَدًا فَقُولِي إِنِّي نَذَرْتُ لِلرَّحْمَنِ صَوْمًا فَلَنْ أُكَلِّمَ الْيَوْمَ إِنْسِيًّا " سورة مريم 26
"ብይም፣ ጠጭም፤ ተደሰችም፤ ከሰዎችም አንድን ብታይ ፦ እኔ ለአልረሕማን ዝምታን ተስያለሁ፤ ዛሬም ሰዉን በፍጹም አላነጋግርም በይ።" (ሱረቱ መርየም 26)፡፡
መርየም (ዐለይሃ-ሰላም) ሰዎችን ማናገር እንደሌለባትና ዝም እንድትል ትእዛዝ ሲሰጣት፡ ዝምታዋ በዐረብኛው ‹ሰውም› ተብሎ ነው የተጠቀሰው፡፡
የጾም ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ፡- ከጎህ መቅደድ (ፈጅር) እስከ ጸሀይ መጥለቅ (መግሪብ) ድረስ ወደ አላህ በመቃረብ ኒያ ከምግብና ከመጠጥ፣ ከባለቤት ጋር ግንኙነት ከመፈጸም፡ ከተቀሩትም ጾምን ከሚያበላሹ ነገራት መቆጠብ ማለት ነው፡፡
ለ. ጠቀሜታው፡-
ጾም ብዙ መንፈሳዊ ጠቀሜታዎችን ለጾመኛው ያስገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
1. ተቅዋ (አላህን መፍራት)፡- አንዱና ዋነኛው ጥቅሙ ነው፡፡ ጾመኛ ሰው በጾም ወቅት ደካማነቱን ይረዳል፡፡ በመጾሙ ሰበብ የሆዱን ፈቃድ ባለሟሟላቱ ምን ያህል እንደተቸገረ ይረዳል፡፡ ሲዘልና ሲጫወት የነበረው አሁን ተጠቅልሎ ሲተኛ የአቅሙን ውስንነት ይረዳል፡፡ በዚህም ሰበብ ለኃያሉ ጌታው አላህ ይተናነሳል፡፡ እሱንም ይፈራል፡፡ የበላና የጠገበ ሰው ግን ፍርሀት ምን እንደሆነ በምን ያውቃል? እንዴትስ ይረዳል? ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ " سورة البقرة 183
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 183)፡፡
‹‹ልትጠነቀቁ ይከጀላልና›› የሚለው የሚያመላክተን፡- አላህን የመፍራት ልብ ታገኙና ትወፈቁ ዘንድ የሚለውን ነው፡፡
2. ከእሳት መከላከያ ጋሻ ነው፡-
ዑሥማን ኢብኑ አቢል-ዓስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አለ፡- "ጋሻ ከግድያና ከሰይፍ እንደሚከላከለው፡ ጾምም ከእሳት የሚከላከልላቹሁ ጋሻችሁ ነው" (ነሳኢይ 2231)፡፡
3. ፊትን ከእሳት ያርቃል፡-
አቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አለ፡- "በአላህ መንገድ (በጂሀድ) ላይ ሆኖ አንድን ቀን የጾመ ሰው፡ አላህ ፊቱን ከጀሀነም እሳት የሰባ አመት መንገድ ያርቀዋል" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡
4. ከሀራም ይከላከላል፡-
ሰው ስሜት የሚኖረው ሲበላና ሲጠጣ ነው፡፡ ስሜቱን በሐላል መንገድ የሚያስተናግድበትን ካጣ ደግሞ ወደ ሐራም መሄዱ ነው፡፡ ለዚህ በሽታ ፍቱን መድሀኒቱ ደግሞ ጾም ነው፡-
ዐብደላህ ኢብኑ-መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው ነገሩን አለ፡- "እናንተ የወጣት ስብስቦች ሆይ! ከናንተ ውስጥ የትዳር ጣጣዎችን መሸፈን የቻለ ሰው ያግባ፡፡ እርሱም (ማግባቱ) አይኑን መስበሪያና ብልቱን መጠበቂያ ነው፡፡ ያልቻለ ሰው ደግሞ ጾምን (በማብዛት) አደራ! እሱ ከዝሙት መከላከያ ነውና" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
5. ለብቻው የተዘጋጀ የጀነት በር (V.I.P) ያለው መሆኑ፡-
አማኞች በጠቅላላ በምድራዊ ህይወታቸው በኢስላም ላይ ከሞቱ ያለጥርጥር ጀነት ይገባሉ፡፡ አላህ ከነሱ ያድርገን፡፡ ጀነትን ሙስሊም የሆነች ነፍስ እንጂ ሌላው አይገባትምና፡፡ ከነዚህ የጀነት ስምንት በሮች ውስጥ ደግሞ ‹‹አር-ረያን›› ተብሎ የሚጠራ በር አለ፡፡ በዚህ በር በኩል በስም ተጠርተው የሚገቡት ግን ጾመኞች ብቻ ናቸው፡፡ ይህ ለነሱ የተለየ ክብር ነው፡፡
ሰህል ኢብኑ ሰዕድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "በጀነት ውስጥ አር-ረያን የሚባል በር አለ፡፡ የውሙል ቂያም ጾመኞች ይገቡበታል፡፡ ጾመኞች የታሉ? በመባል ይጠራሉ፡፡ እነሱ ጨርሰው ከገቡ በኋላ በሩ ይዘጋል፡፡ ከነሱም ኋላ ማንም ሰው አይገባም" (ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም ሌሎች የዘገቡት)፡፡
6. ለጾመኛው አማላጅ መሆኑ፡-
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐምሩ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ጾምና ቁርኣን ለሰራባቸው የአላህ ባሪያ የቂያም ቀን ያማልዳሉ፡፡ ጾምም እንዲህ ይላል፡- ጌታዬ ሆይ! ባሪያህን ከምግብና ከስሜት ፍላጎት ከልክዬዋለሁና ዛሬ አማልደኝ (እሱን እንዳማልድ ፍቀድልኝ)፡፡ ቁርኣንም እንዲህ ይላል፡- ጌታዬ ሆይ! እኔን ለማንበብ ከሌሊት እንቅልፍ ከልክዬዋለሁና ዛሬ አማልደኝ (እሱን እንዳማልድ ፍቀድልኝ)፡፡ ሁለቱም እንዲያማልዱ ይፈቀድላቸዋል" (ሶሒሑ ተርጊብ ወት-ተርሂብ 984)፡፡
‹‹ማማለድ›› ማለት፡- ይህ የአላህ ባሪያ የኃጢአት ስርየትን እንዲያገኝና በአላህ ቸርነት ጀነት እንዲገባ አላህን መማጸን ማለት ነው፡፡
7. የአፉ ሽታ ያማረ መሆኑ፡-
የጾመኞች አፍ ጠረኑ በስጋዊ ስሜት ሲሸተት ይከረፋል፡፡ ጥሩ መዓዛም የለውም፡፡ አላህ ዘንድ ግን ከሚስክ ሽታ በላይ እጅግ ያማረ ነው የሚሆነው፡፡
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"…የጾመኛ ሰው የአፉ ክርፋት አላህ ዘንድ ከሚስክ መዓዛ በላይ ያማረ ነው" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡

8. የማትመለስ ዱዓ ያለበት መሆኑ፡-
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"ሶስት ሰዎች ዱዓቸው ተመላሽ አትሆንም፡- ፍትሀዊ መሪ፣ ጾመኛ እስኪያፈጥር፣ የተበዳይ ዱዓእ" (ኢብኑ ማጀህ 1752፣ ቲርሚዚይ 3598፣ ሶሒሕ ኢብኑ ማጀህ 2/86)፡፡
9. ደስታን ያመጣል፡-

"…ጾመኛ ሰው ሁለት ደስታዎች አሉት፡፡ በሚያፈጥር ጊዜ የሚሰማው ደስታ እና፡ ነጌ ከጌታው ጋር ሲገናኝ የሚሰማው ደስታ ነው" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
ይቀጥላል
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"ሶስት ሰዎች ዱዓቸው ተመላሽ አትሆንም፡- ፍትሀዊ መሪ፣ ጾመኛ እስኪያፈጥር፣ የተበዳይ ዱዓእ" (ኢብኑ ማጀህ 1752፣ ቲርሚዚይ 3598፣ ሶሒሕ ኢብኑ ማጀህ 2/86)፡፡
9. ደስታን ያመጣል፡-
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"…ጾመኛ ሰው ሁለት ደስታዎች አሉት፡፡ በሚያፈጥር ጊዜ የሚሰማው ደስታ እና፡ ነጌ ከጌታው ጋር ሲገናኝ የሚሰማው ደስታ ነው" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
ይቀጥላል
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
ረመዷን መጣ!! ቁጥር 3
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
3. የጾም መስፈርቶች
ዛሬ ደግሞ የምንመለከተው የጾምን መስፈርት (ቅድመ ዝግጅት) ነው፡፡ አንድ ሰው የረመዷን ጾም ግዴታ የሚሆንበት ምን ምን መስፈርቶችን (ሹሩጦችን) ሲያሟላ ነው? ግዴታው የሚነሳለትስ መቼ ነው? የሚለውን እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡፡
ከመስፈርቱ በፊት፡- ጾም በኢስላም ውስጥ ዋጂብ (ግዳጅ) የሆነ የአምልኮ ተግባር ነው፡፡ ከአምስቱ የኢስላም ማእዘናትም አንድ ማእዘን ነው፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ " سورة البقرة 183
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 183)፡፡
ዑመር ኢብኑል-ኸጣብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አለ፡- "ኢስላም በአምስት ነገራት ላይ ተመስርቷል፡፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩንና፡ ነቢዩ ሙሐመድም የሱ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሶላትን ደንቡንና ስርዓቱን ጠብቆ መስገድ፣ ዘካትና(ምጽዋት) መስጠት፣ የረመዷንን ወር መጾም እና የአላህን ቤት መጎብኘት (ሐጅ ማድረግ) ናቸው" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
ከላይ ያለው ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጽ ሁለት ነገር ያስረዳናል፡-
አንደኛ፡- ጾም በኛ ላይ የተደነገገ ሃይማኖታዊ ግዳጅ መሆኑን፡፡
ሁለተኛ፡- የጾም ስርዓት በዚህ ኡምማ የተጀመረ አዲስ አምልኮ ሳይሆን፡ ከዚህ በፊት በነበሩት የነቢያት ተከታዮችም ላይ የተደነገገ ስረ-መሰረት ያለው የአምልኮ ክፍል መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን አፈጻጸሙ ላይ እንደዘመኑ ልዩነት ሊኖር ይችላል፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ኡምማ ላይ ጾም ግዳጅነቱ የተደነገገው፡- በሂጅራ አቆጣጠር በ2ኛው ዓመት፡ በስምንተኛው ወር ሻዕባን፡ በሁለተኛው ቀን ሰኞ እለት ነው (مصدر:- المختصر في شرح أركان الإسلام: بعض طلبة العلم)፡፡
እንግዲያውስ ግዳጅነቱ በነማን ላይ ነው? የሚባል ከሆነ፡ መልሱም፡- ቀጥሎ ያለውን መስፈርት ባሟሉት ላይ የሚል ይሆናል፡፡ መስፈርቶቹም፡-
1. ሙስሊም በሆነ ላይ፡-
የመጀመሪያውና ዋነኛው መስፈርት ነው፡፡ ካፊር አብሮን ቢጾም ከጾሙ የሚያገኘው ትርፍ ረሀብ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ስራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው የግድ ሶስት መስፈርቶች መሟላት አለባቸው፡፡ ከዛ ውስጥ አንዱ ‹‹ሙስሊም›› መሆን ነው፡፡ የካፊር ስራ ከንቱ እንደሆነና ተቀባይነት እንደሌለው ቀጣዮቹ የቁርኣን ማስረጃዎች ያስረዳሉ፡-
"ከእናንተ ውስጥም ከሃይማኖቱ የሚመለስና እርሱም ከሐዲ ሆኖ የሚሞት ሰው እነዚያ (በጎ) ሥራቸው በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም አገር ተበላሸች፡፡ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 217)፡፡
"ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ለግሱ ከናንተ ተቀባይ የላችሁም እናንተ አመጠኞች ሕዝቦች ናችሁና በላቸዉ። ልግስናዎቻቸውን ከነሱ ተቀባይ የሚያገኙ ከመሆን እነሱ በአላህና በመልክተኛዉ የካዱ ሶላትንም እነሱ ታካቾች ሆነው በስተቀር የማይሰግዱ እነሱም ጠይዎች ሆነው በስተቀር የማይሰጡ መሆናቸዉ እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም።" (ሱረቱ-ተውባህ 53-54)፡፡
"እነዚያም የካዱት ለነሱ ጥፋት ተገባቸው፤ ሥራዎቻቸውንም አጠፋባቸው።ይህ እነሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው፤ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው።" (ሱረቱ ሙሐመድ 8-9)፡፡
ዐኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኢብኑ ጁድዓን በዘመነ ጃሂሊያ ዝምድና የሚቀጥልና ምስኪን የሚመግብ ነበር፡፡ እናም ይህ ይጠቅመዋልን? እሳቸውም፡- ምንም አይጠቅመውም፡፡እሱ አንድም ቀን ቢሆን፡- ጌታዬ ኃጢአቴን በፍርዱ ቀን ማረኝ ብሎ አያውቅምና" ብለው መለሱላት፡፡ (ሙስሊም የዘገበው)፡፡
ታዲያ ሙስሊም ያልሆነ ሰው(ካፊር) በመልካም ስራው ምን ይጠቀማል? ከተባለ ደግሞ ምላሽ የሚሆነው ተከታዩ የነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ሐዲሥ ነው፡-
አነስ ኢብኑ ማሊክ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ከአላህ መልክተኛ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የሰማውን እንደነገረን እንዲህ ብለዋል፡- "ካፊር መልካም ስራ ከሰራ ከዱንያ ሲሳይ (በምትኩ) ይሰጠዋል፡፡ ሙስሊም ከሆነ ግን አላህ ይህን መልካም ስራውን በአኼራ ያነባብርለታል፡፡ በዱንያም በታዛዥነቱ ልክ ሲሳይን ይተካለታል" (ሙስሊም)፡፡
በዚህ መሰረት ካፊር በሸሀደተይን ወደ ኢስላም ካልገባ በስተቀር መልካም ስራው ለሱ ዋጋ ቢስ ነው፡፡
2. አእምሮው ያልተዛባ መሆኑ፡-
ግለሰቡ ሙስሊም ሁኖ የአእምሮ ችግር ካለበት (በትክክል ማሰብ ካልቻለ) የጾም ግዳጅነት ይነሳለታል፡፡ አእምሮው በተመለሰለት ወቅትም ቀዷውን እንዲያወጣ አይጠየቅም፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ በንዴት ወይም በሃሳብ ብዛት ወሰድ አርጎ የሚመልሳቸውን ሰዎች ሑክሙ አይመለከታቸውም፡፡ እነሱ በታመሙበት ወቅት ግዳጅነቱ ቢነሳላቸውም፡ በዳኑበት ጊዜ ጾሙን መቀጠል፡ ያመለጣቸውንም ቀዷ ማውጣት አለባቸው፡፡ ዙሁር ሶላት ላይ ወሰድ አርጎት አፍጥር አካባቢ መለስ እንደሚያረገው ሰው አይነት ማለት ነው፡፡ በትክክል ከሚናገረው ይልቅ የሚቀባዥረው የበዛ፡ ህመሙ ደግሞ የሚዘወትር አይነት ከሆነ ግን ግዳጅነቱ ተነስቶለታል፡፡ ምናልባትም ወደፊት በአላህ ቸርነት በወንድሞች እርዳታ ቁርኣን ተቀርቶበት ቢድን እንኳ ላለፈው ነገር ቀዷ አውጣ አይባልም፡፡ ለዚህም ቀጣዩ ሐዲሥ መረጃ ይሆናል፡-
ከአዒሻ እና ከዐሊይ ኢብኑ አቢ-ጧሊብ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አሉ፡- "ቀለም (ኸይርና ሸር የሚመዘገብበት) ከሶስት ሰዎች ላይ ተነስቷል፡፡ የተኛ ሰው እስቂነቃ ድረስ (በተኛበት ቢለፈልፍ)፣ ህጻን ልጅ ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ፣ አእምሮው የተደበቀ (እብድ) እስኪድን ድረስ" (አቡ ዳዉድ 4400፣ ኢብኑ ማጀህ 2041፣ ቲርሚዚይ 1423፣ ነሳኢይ 3445፣ አሕመድ 952)፡፡
3. ለአካለ መጠን መድረስ፡-
በሶስተኛ ደረጃ መሟላት የሚገባው ደግሞ የዕድሜ ጉዳይ ነው፡፡ ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው (ዕድሜው 15 የሞላ፣ ወይም ከዛ በፊት ሐይድ ካየች/ኢሕቲላም ከሆኑ፣ ወይም በብልት ዙሪያ ጸጉር መብቀል ከጀመረ) ጾም መጾም ግዳጅ ይሆንባቸዋል ማለት ነው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ሶስት ምልክቶች (ዕድሜ፣ የዘር ፈሳሽ እና ጸጉር) አንዱም ካልታየ በነሱ ላይ ጾም ግዳጅ አይሆንም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እነሱን በጾም ማዘዝና ማለማመድ ያስፈልጋል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው የሐዲሥ ማስረጃ ለዚህም ማገልገል ይችላል፡፡

4. ጤናማ መሆን፡-
ህመምተኛ የሆነ ሰው የረመዷንን ጾም መጾሙ ህመሙን የሚያገረሽበት ከሆነ፡ እሱንም ከጎዳው መጾሙ አይፈቀድለትም፡፡ ለሱ መብላት ነው የተፈቀደለት፡፡ ህመሙ የሚሽር ሁኖ ወደፊት ከዳነ የበላበትን ቀን ቆጥሮ ቀዷውን በመጾም ያወጣል ማለት ነው፡፡ ህመሙ ለመጾም የሚከለክለው ካልሆነ ግን ግዴታ መጾም አለበት፡፡ ጉንፋን ያዘኝ፣ ራሴን አመመኝ ብሎ ማፍጠር የለምና! ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"…ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም…" (ሱረቱል በቀራህ 185)፡፡
5. የአካባቢው ነዋሪ መሆን፡-
በመኖሪያ አድራሻው ያለ ሰው መሆን አለበት፡፡ ከመኖሪያ ክልል ወጥቶ በጉዞ ላይ ሁኖ ሙሳፊር ሊሰኝ የሚችልበት ሌላ ከተማ ከገባ ጾም ለሱ ዋጂብ አይደለም፡፡ ከፈለገ መጾም ካልፈለገ ማፍጠር ይችላል፡፡ ለሱ መጾሙ ግን የበለጠ ተወዳጅ ነው፡፡ ከሰፈር ተመልሶ ወደ መኖሪያ ክልሉ ሲገባ ደግሞ ወደ ጾሙ ይመለሳል፡፡ በሰፈር እያለ ያልጾመባቸው ቀናት ካሉ ደግሞ በሌላ ጊዜ ቀዷውን ያወጣዋል፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ከላይ የተጠቀሰው የቁርኣን አንቀጽ ነው፡፡ በተጨማሪም ተከታዩ ሐዲሥ ነው፡-
አቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "በረመዷን ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋር ለዘመቻ እንወጣ ነበር፡፡ ከመሀከላችን የሚጾም አለ፡፡ የማይጾምም አለ፡፡ ጾመኛው የማይጾመውን (ባለመጾሙ) የማይጾመው ደግሞ ጾመኛውን (በሰፈር ላይ በመጾሙ) አይቃወመውም ነበር፡፡ ይልቁኑ ኃይልና ጉልበት አግኝቶ የጾመ ሰው መጾሙ ለሱ መልካም እንደሆነ፡ አቅምና ጉልበት አንሶት ያፈጠረ ሰው ደግሞ ለሱ ማፍጠሩ መልካም መሆኑን ይመለከቱ ነበር" (ሙስሊም 2674)፡፡
እነዚህ አምስቱ ወንድና ሴት በጋራ የሚመለከታቸው መስፈርት ሲሆን፡ ሴቷ ደግሞ በተጨማሪ፡-
6. ከሐይድና ከወሊድ ደም የጠራች መሆኗ፡-
በወር አበባ ወቅትና በወሊድ ደም ጊዜ መጾም አይፈቀድም ሐራም ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃው፡-
አቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ሴት ልጅ ሐይድ ካየች አትሰግድም አትጾምም አይደል!..." (ቡኻሪይ 1951)፡፡
እነዚህ 5/6 መስፈርቶች የተሟሉለት ሰው የረመዷን ጾም ግዳጅ የሚሆንበት ነው ማለት ነው፡፡ ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ደግሞ ጾም የማይወጅብባቸው ናቸው፡-
1. ሙስሊም ያልሆነ ካፊር
2. ለአካለ መጠን ያልደረሰ ህጻን
3. አእምሮው ያልተስተካከለ ህመምተኛ
4. ጾሙ የሚከብደው በሽተኛ
5. ከመኖሪያ አካባቢው የወጣ ሙሳፊር
6. እርጉዝና አጥቢ ሴት፡- ከጾምኩኝ ጽንሱ በምግብ እጦት ይጎዳል፡ ወይም እኔ አቅም ያንሰኛል ብላ ከፈራች መብላት አለባት፡፡ አጥቢዋም እንደዛው ለልጇ ወይም ለራሷ ከፈራች መብላት ትችላለች፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ በጾም ቀዷውን ትከፍላለች፡፡
7. በእድሜ የገፉ አዛውንቶች፡- የረመዷንን ጾም ለመጾም አቅሙ ከሌላቸው መብላት ይፈቀድላቸዋል፡፡ በእያንዳንዱ በሚበሉበት የጾም ቀን አንድ ምስኪን ማብላት (ማስፈጠር) አለባቸው፡፡ እሱ ማካካሻ ይሆናቸዋል፡፡
8. ተስፋ የሌለው ህመምተኛ፡- መዳኑ ተስፋ የማይደረግበት ህመምተኛ እሱም በረመዷን መብላት ይችላል፡፡ ቀዷ የለበትም ፡፡ በምትኩ በእያንዳንዱ የጾም ቀን ምስኪን ያበላል (ያስፈጥራል) ወላሁ አዕለም፡፡

"የአላህ መለኮታዊ መልካምና ውብ ስሞች" ክፍል 6 ☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ ➤ https://goo.gl/tjwV4t Join us➤ t.me/abuhyder
Audio
"የአላህ መለኮታዊ መልካምና ውብ ስሞች" ክፍል 7
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://bit.ly/2PnAxQd
Join us➤ t.me/abuhyder
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://bit.ly/2PnAxQd
Join us➤ t.me/abuhyder
ረመዷን መጣ!! ቁጥር 4
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
4. የጾም ማእዘናትና ተወዳጅ ተግባራት
የረመዷን ጾማችን የተሟላና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን በጾሙ ውስጥ መሟላት ያለባቸው ሁለት መስፈርቶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
ሀ. ኒያ ፡- ይህ ማለት ግለሰቡ በእያንዳንዱ የረመዷን ለሊት ላይ የነገውን የረመዷንን ቀን ጾም ለአላህ ብሎ በኢኽላስ እንደሚጾም ከልቡ መወሰን ማለት ነው፡፡ ኒያ የሚለው ቃል ፍቺው፡- አንድን ነገር ለማድረግ ወይም ለመናገር ከልብ ወስኖ መቁረጥ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ሰውየው ባይናገረውም ባይሰራውም በኒያው ሰበብ እንደሰራው ይቆጠርለታልና፡፡ ስራ በጠቅላላ (ኸይርም ሆነ ሸር) ዋጋው የሚገኘው በኒያ ነውና (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
የኒያ ቦታው ደግሞ ልብ ነው፡፡ በአንደበት መናገር ከሱና አይደለም፡፡ ሰውየው ነገን ለመጾም በዛሬው ለሊት ላይ ልቡን ሰብሰብ አድርጎ ይወስናል እንጂ በምላሱ፡- ‹‹ነወይቱ ሰውመ ገዲን አን-አዳኢ ፈርዲ ሸህሪ ረመዷነ ሀዚሂ-ሰነቲ ኢማነን-ወሕቲሳበን ሊላሂ-ተዓላ›› የሚለውን መናገር አይጠበቅብንም፡፡ እንደውም ቢድዓ ነው፡፡ ኒያ ግዳጅ ለመሆኑ በተጨማሪ ቀጣዩ ሐዲሥ ያስረዳል፡-
ሐፍሷ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከፈጅር በፊት የጾምን ኒያ (በልቡ) ያላሳደረ ሰው ጾም የለውም" (አቡ ዳዉድ 2456፣ ቲርሚዚይ 730)፡፡
ለ. መቆጠብ፡- ይህ ማለት በረመዷን የጾም ወቅት ከማንኛውም ጾምን አፍራሽ ከሆኑ (የሆድና የብልት ስሜቶችን) ነገራት መቆጠብ ማለት ነው፡፡ እሱም ከእውነተኛው ጎህ መቅደድ (ፈጅሩ-ሷዲቅ) አንስቶ እስከ ጸሀይ መጥለቅ (መግሪብ) ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማለት ነው፡፡
እነዚህ ዋና የጾም ማእዘናት ሲሆኑ፡ ተወዳጅ ተግባራቱ ደግሞ ቀጥሎ ባለው መልኩ ይቀርባሉ፡-
1. ሰሑርን መመገብ፡- ‹‹ሰሐር›› ማለት፡- ከሌሉቱ የመጨረሻው ክፍል ማለት ነው፡፡ በዛ ወቅት የምንመገበው ሲሳይ ሰሑር ተብሎ ይጠራል፡፡ ሰሑርን መመገብ ግዳጅ (ዋጂብ) ያልሆነ ተወዳጅ (ሙስተሐብ) ተግባር ነው፡፡ ቀጣዩም ሐዲሥ ይህን ይገልጻል፡-
አነስ ኢብኑ-ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ሰሑርን ተመገቡ፡ ሰሑርን በመመገብ በረካ ይገኛልና!" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
አንዳንድ ሰው ማታ እራቱን ግጥም አድርጎ ይበላና፡ ለቤተሰቡ ሰሑር ማንም ሰው እንዳይቀሰቅሰኝ ብሎ ተጠቅልሎ ይተኛል፡፡ ይህ ተግባር ስህተት ነው፡፡ ምንም ሰሑርን መብላት ዋጂብ ባይሆንም የተወደደ ተግባር ነው፡፡ በረካም ያስገኛል፡፡ ስለዚህ ተነስተን ለሱናው ተምርም ሆነ ወተት እንኳ ቢሆን እንጠቀም፡፡ በተጨማሪም ሰሁርን መመገብ ከአህሉል ኪታቦች ጾም የሚለየን ነገር ነው፡፡ እነሱ ሰሑርን አይመገቡም፡-
ዐብዱላህ ኢብኑ-ዐምር ኢብኑል-ዓስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "በኛና በአህሉል ኪታቦች ጾም መካከል ያለው ልዩነት ሰሑር መመገባችን ነው" (ሙስሊም 2604)፡፡
2. ሰሑርን ማዘግየት፡- ሰሑርን የሚመገብ ሰው ከቻለ ወደ መጨረሻው ሰዓት አዘግይቶ ከፈጅር በፊት መመገቡ ሱና ነው፡፡ ፈጅር ይወጣብኛል ብሎ የማይሰጋ እስከሆነ ድረስ ማለት ነው፡፡
አቢ ዘር (ረዲየላሁ ዐንሁ) (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ኡመቶቼ…ሰሑርን እስካዘገዩ ድረስ በመልካም ነገር ላይ ከመሆን አይወገዱም" (አሕመድ 21312)፡፡
3. ኢፍጣርን ማቻኮል፡- የጸሀይ መግባት ከተረጋገጠ ወይም የመግሪብን አዛን እንደሰማን ወዲያውኑ ማፍጠር ተወዳጅ ተግባር ነው፡፡
አቢ ዘር (ረዲየላሁ ዐንሁ) (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ኡመቶቼ ኢፍጣርን እስካፋጠኑ…ድረስ በመልካም ነገር ላይ ከመሆን አይወገዱም" (አሕመድ 21312)፡፡
4. በተምርና በውሀ ማፍጠር፡- ወደ ሆዳችን የሚገባው የማፍጠሪያ ሪዝቅ ከተገኘ የተምር እሸት (ሩጠባት) እሱ ከሌለ ተምርን እሱም ካልተገኘ ውሀ መጎንጨት ተወዳጅ ተግባር ነው፡፡ በሳንቡሳና በሾርባ ማፍጠር ቢቻልም ሱንና አይደለም፡፡
አነስ ኢብኑ-ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መግሪብን ከመስገዳቸው በፊት በተምር እሸት ያፈጥሩ ነበር፡፡ የተምር እሸት ከሌለም በተምር፣ እሱም ከሌለ ውሀን ይጎነጩ ነበር" (አቡ ዳዉድ 2358፣ አሕመድ 12705)፡፡
5. በኢፍጣር ጊዜ የሚባል ዱዓ፡- ሰውየው በሚያፈጥርበት ወቅት ይህንን ዱዓ ማለቱ ተወዳጅ ነው፡፡ ‹ዘሀበ-ዘመኡ፣ ወብተለቲል ዑሩቁ፣ ወሠበተል-አጅሩ ኢንሻአላሁ ተዓላ›፡-
ዐብዱላህ ኢብኑ-ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሚያፈጥሩ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፡- "ዘሀበ-ዘመኡ፣ ወብተለቲል ዑሩቁ፣ ወሠበተል-አጅሩ ኢንሻአላሁ ተዓላ" (አቡ ዳዉድ 2359)፡፡
ትርጉሙም፡- ጥሙም ተወገደ፣ የደም ስሮችም ረጠቡ፣ በአላህ ፈቃድም ምንዳ ጸደቀ ማለት ነው ወላሁ አዕለም፡፡

ረመዷን መጣ!! ቁጥር 5

5. ጾምን የሚያበላሹ ተግባራት
በጾም ወቅት መሟላት ያለባቸው ግዴታ ተግባራትና ተወዳጅ የሆኑ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ፡ በዚያው መልክም ጾሙን የሚያፈርሱ ተግባራትም አሉ፡፡ ለጥንቃቄ ይረዳን ዘንድ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፡-
1. አውቆ መብላትና መጠጣት፡-
በቀኑ ክፍል ጾመኛ መሆኑን እያወቀና እያስታወሰ ወደ ሆዱ ምግብና ውሀ ወይም እነሱን የሚተካ ነገር እንዲገባ ከፈቀደ የሰውየው ጾም ተበላሽቷል፡፡ ቀዷውንም በሌላ ጊዜ ይከፍላል፡፡ ይህን ነገር የፈጸመው ግን ረስቶና ዘንግቶ ከሆነ ጾሙ አይበላሽም፡፡ ይህ አላህ ወደሱ የላከው ሲሳይ ነውና፡፡
"…ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር (ከሌሊት ጨለማ) ለእናንተ እስከሚገልጽላችሁ ድረስ ብሉ፤ ጠጡም፡፡ ከዚያም ጾምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ…" (ሱረቱል በቀራህ 187)፡፡
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ሰው ባስታወሰ ጊዜ ጾሙን ይቀጥል፡፡ ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና" (ቡኻሪይ)፡፡
2. ከባለቤቱ ጋር መገናኘት፡-
በቀኑ ክፍል ላይ ከባለቤቱ ጋር የተገናኘ ሰው የሁለቱም ጾም ይፈርሳል፡፡ ትልቅም ኃጢአት ፈጽመዋል፡፡ ከፍፋራህ (ካሳ) መክፈልም ይጠበቅባቸዋል፡፡ እሱም፡- በባርነት ቀንበር ያለ ሰው ካለ በገንዘብ ገዝተው ነጻ ማውጣት፣ አቅሙ ከሌላቸው ወይም በባርነት ቀንበር ውስጥ ያለ ሰው ከሌለ 2 ወር በተከታታይ መጾም፣ እሱንም የማይችሉ ከሆነ 60ምስኪኖችን ማብላት ነው፡፡ 60 ምስኪን የማብላት አቅሙ ከሌላቸው ዲኑ ገር ነውና ከአቅም በላይ አይገደዱም፡፡ ከዚህ የካሳ ክፍያ ጋር በተጨማሪ ተውበት መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ግኑኝነት የተፈጸመው በባል አስገዳጅነት ሆኖ፡ ሚስት ራሷን ለመከላከል ጥረት አድርጋ ከአቅሟ በላይ ሆኖ ባል ቢፈጽምባት፡ እሷ ካሳ መክፈልም የለባትም ጾሟም አልተበላሸም፡፡ ጉዳዩ ከአቅሟ በላይ የማትቋቋመው ነገር ነውና፡፡ ስሜት አሸነፈኝ ማለት ግን ከአቅም በላይ ሆነብኝ ለማለት ምክንያት እንደማይሆን መረዳት ይገባናል፡፡ በለሊቱ ክፍል ግን ከሚስቱ ጋር መገናኘት ይፈቀዳል፡፡ እንደውም ኢፍጣር ላይ በሷ ማፍጠር እፈልጋለሁ ካለ መብቱ ነው፡፡ ሱናው ተምርና ውሀ ቢሆንም፡፡
"በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ…" (ሱረቱል በቀራህ 187)፡፡
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ዘንድ ተቀምጠን ሳለ፡ አንድ ሰው መጣና፡- ‹‹አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጠፋሁኝ›› አላቸው፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹ምን አጠፋህ?›› ሲሉት፡ እሱም፡- ‹‹እኔ ጾመኛ ሆኜ ባለቤቴን ተገናኘኋት›› ብሎ መለሰ፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹ባሪያን ነጻ ማውጣት ትችላለህን?›› አሉት፡፡ እሱም፡- ‹‹አልችልም›› አለ፡፡ ‹‹ሁለት ወር በተከታታይ መጾምስ?›› ሲሉት፡ በድጋሚ ‹‹አልችልም›› ብሎ መለሰ፡፡ ‹‹60 ምስኪኖችን ማብላትስ?›› ሲሉት፡ አሁንም ‹‹አልችልም›› ብሎ መለሰ፡፡ እሳቸውም ትንሽ በቦታው ቆዩና በተምር የተሞላ ዘንቢል እንዲመጣላቸው አደረጉ፡፡ ከዛም ‹‹የታለ ጠያቂው?›› ሲሉ፡ ሰውየውም አቤት! ብሎ መጣ፡፡ ከዛም- ‹‹በል እንካ ይሄን ውሰድና ሶደቃ አውጣበት›› ሲሉት፡ ሰውየውም፡- ‹‹አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! በዚህ በሁለቱ ጋራዎች መካከል (በመዲና ድንበሮች) ከኛ ቤተሰብ የባሰ ችግረኛ ማን አለና!›› ሲላቸው፡ እሳቸውም ክራንቻ ጥረሳቸው እስኪታይ ድረስ ሳቁና፡- ‹‹እሺ ውሰድና ቤተሰብህን መግብበት›› አሉት" (ቡኻሪይ)፡፡
3. የዘር ፈሳሽን ማውጣት፡-
በጾም ወቅት በገዛ ፈቃድ ብልትን በመነካካት ወይንም ወደ ባለቤት ገላ በመመልከት የዘር ፈሳሽ (መኒይ) እንዲወጣ ሰበብ ከሆነ የሰውየው ጾም ይፈርሳል፡፡ ቀዷውንም ያወጣል፡፡ ሆኖም ይህ ሁኔታ የተከሰተው እሱ በተኛበት ወይም በህልሙ ሳያውቅ ከሆነ ጾሙ አይፈርስም፡፡ ከቁጥጥሩ ውጪ ነውና፡፡
በሐዲሡል ቁድሲይ ላይ እንደተቀመጠው፡ ጌታችን አላህ ስለ መልካም ባሪያው ጾም ሲናገር፡- "እሱ የምግብና የስሜት ፍላጎቱን ለኔ ብሎ ይተዋልና" ብሏል፡፡ (ኢብኑ ማጀህ)፡፡ የስሜት ፍላጎት የሚለው ውስጥ ይህ ተግባር ይካተታል፡፡ ስሜታችንን ከተውን ይህንንም ለአላህ ብለን ልንተው ይገባናል፡፡
4. አውቆ ማስታወክ፡-
የእጅ ጣትን ወደ ጉሮሮ በመላክ ወይም በሌላ መንገድ የግድ ከሆድ የሆነ ነገር እንዲወጣ የታገለ ሰው ቢያስታውከው ጾሙ ይፈርሳል፡፡ ያለ ፍላጎቱ ግን ከሆነ የወጣው ጾሙ አይፈርስም፡-
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አውቆ ያስታወከ ሰው ቀዷውን ያውጣ፡፡ ትውከቱ ያሸነፈው (ያለ ፈቃዱ የወጣበት) ግን ቀዷ የለበትም" (አቡ ዳዉድና ቲርሚዚይ)፡፡
5. የምግብ መርፌ መጠቀም፡-
በጾም ወቅት ምግብን ሊተካ የሚችል የምግብ መርፌ (ጉሉኮስ..) መጠቀም ጾምን ያፈርሳል፡፡ ለመጠነኛ ህመም የሚወሰድ ደረቅ መርፌ ከሆነ ግን ጾምን አያበላሽም፡፡
6. የወር አበባና የወሊድ ደም መከሰት፡-
በእህቶች ላይ በጾም ወቅት ይህ ነገር ከተከሰተ ጾማቸው ይፈርሳል፡፡ ሌላው ይቅርና መግሪብ አዛን ሊወጣ (ጸሀይ ልትጠልቅ) 3 ደቂቃ ቀረው በተባለበት ሰዓት እንኳ ደሙ ቢታይ ጾሟ ይፈርሳል ማለት ነው፡፡ ልክ እንደዛው የፈጅር አዛን ሊወጣ 3 ደቂቃ በቀረው ጊዜ ውስጥ ደሟ ቢቆምላት፡ ጾሙን መጾም ይኖርባታል፡፡ ትጥበቱን ከፈጅር አዛን በኋላ ማድረግም ትችላለችና፡፡ ዋናው ከአዛኑ በፊት ለዛሬው ጾም በማለት ኒያን በልቧ ማሳደሯ ነው፡፡
አቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ሴት ልጅ ሐይድ ካየች አትሰግድም አትጾምም አይደል!..." (ቡኻሪይ 1951)፡፡
7. ለማፍረስ መነየት፡-
የሚያስጎመጅ ምግብን ወይም መጠጥን ተመልክቶ ለማግኘት በመመኘት፡- ምነው ዛሬ ባልጾምኩ ኖሮ! ብሎ በልቡ ቢያስብ፡ ይህ ሰው በኒያው ብቻ እንዳፈጠረ ይቆጠራል፡፡ ስራ ትርጉም የሚኖረው በኒያ ነውና (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡ ስለዚህም በኒያ ሰበብ ጾማችንን ከማበላሸት ጥንቃቄ እናድርግ፡፡
ሌላው ልናውቅ የሚገባን ነጥብ፡- ከላይ የተጠቀሱት ሰባት አፍራሽ ተግባራትና ሌሎችም አፍራሽ ነገሮች ካሉ፡ ህጉ የሚሰራው ከዚህ በታች የሚጠቀሱትን ሶስት መስፈርቶች ባሟላ ሰው ላይ መሆኑን ነው፡፡ እነሱም፡-
1. ዕውቀቱ ያለው፡-
ይህን የማያውቅ ሰው ይኖራል ብሎ በድፍረት መናገር ቢከብድም ህጉ ግን አስቀምጦታል፡፡ እሱም ከላይ የተጠቀሱ አፍራሽ ተግባራቶች ጾምን እንደሚያፈርሱ ያላወቀና የሚያስተምረው ያላገኘን ሰው አይመለከቱም፡፡ ባለማወቅ አንዳቸውን ቢፈጽም ጾሙ እንዳይበላሽ ጅህልና ለዚህ ሰው ዑዝር ይሆነዋል፡፡

2. አስታውሶ ከሆነ፡-
ከላይ እንዳየነው መርሳት ዑዝር ነው፡፡ ረስቶ በበላውና በጠጣው ነገር አይያዝም፡፡ እኛም ጌታችን አላህ በረሳነው ነገር እንዳይዘን እንድንለምነው ታዘናል፡፡ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
"…(በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)…" (ሱረቱል በቀራህ 286)፡፡
3. በምርጫው ያለ ሆኖ፡-
ማንም ሰው ያለ ራሱ ምርጫ ተገዶ በሚሰራው ላይ ተጠያቂ አይደለም፡፡ ጥያቄ የሚመረኮዘው ባለቤቱ ፈቅዶ በተገበረው ነገር ላይ ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ቀጣዩ የቁርኣን አንቀጽ ማስረጃ ነው፡-
"ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አለው)፤ ልቡ በእምነት የረጋ ሆኖ (በክሕደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር…" (ሱረቱ-ነሕል 106)፡፡