ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.4K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
"ኑ እንውረድ" በሚል ደርሥ ተለቋል፥ በነገረ ሥላሴ"triadology" ከሚጠቀሱ ተወዳጆች ጥቅሳት አንዱ ዘፍጥረት 11፥6-7 ነው። በዚህ ዙሪያ ዳሰሳ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/Ihf-WhiGhHk?si=Sko8EK2kj8qupQBd

ያዳመጣችሁ ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!
"የአብርሃሙ ሥላሴ" በሚል ርእስ ዙሪያ ዳሰሳ እና ሐተታ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/GMhX99TrVJI?si=eeVZkONW3y3GIzvW

ያዳመጣችሁ ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!
ሶሉ ዐላ ነቢይና"ﷺ"

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡

94፥4 መወሳትህንም ለአንተ ከፍ አድርገንልሀል። وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ

አንድ ሙሥሊም በአዛን፣ በቂያም፣ በሸሀዳህ "ሙሐመድ የአሏህ መልእክተኛ ነው" ብሎ ያውጃል፥ በዚህም አምላካችን አሏህ መወሳት ለነቢያችን"ﷺ" ከፍ አድርጎላቸዋል። እንዲሁ ስማቸው ሲወሳ "ሶለላሁ ዐለይሂ ወሠለም" صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم በማለት መወሳትን ከፍ አድርጎላቸዋል፦
94፥4 መወሳትህንም ለአንተ ከፍ አድርገንልሀል። وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ

"ሶለላሁ ዐለይሂ ወሠለም" صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم ማለት "የአሏህ ረድኤት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን" ማለት ነው። ስለ ሶለዋት ከዚህ በፊት የተጻፈ መጣጥፍ አንብቡ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/3317

"አሏሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ ወአሊ ሙሐመድ" ٱللّٰهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ

"ሶለላሁ ዐለይሂ ወሠለም" صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ኤኻድ እና ያኺድ" በሚል ርእስ ዙሪያ ዳሰሳ እና ሐተታ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/t2OwjlluSN0?si=Mm8ABvNu3B3XMXlT

ያዳመጣችሁ ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!
የተባረከ ወር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥185 የረመዷን ወር በእርሱ ውስጥ ቁርኣን ለሰዎች መሪ፣ የመመሪያ ግልጽ ማስረጃ እና ፉርቃን ሲሆን የተወረደበት ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

አምላካችን አሏህ በቁርኣን ከተገለጹት ስሞቹ አንዱ "አል-ከሪም" الْكَرِيم ሲሆን ትርጉሙ "ቸሩ" "ለጋሱ" ማለት ነው፦
82፥6 አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ
27፥40 እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየውም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፥ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊፈትነኝ ቸረልኝ፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ነው፥ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው» አለ፡፡ فَلَمَّا رَآهُ مُسْتَقِرًّا عِندَهُ قَالَ هَـٰذَا مِن فَضْلِ رَبِّي لِيَبْلُوَنِي أَأَشْكُرُ أَمْ أَكْفُرُ ۖ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّي غَنِيٌّ كَرِيمٌ

"ከሪም" كَرِيم የሚለው ቃል እንደየ ዐውዱ ዘርፈ ብዙ እና መጠነ ሰፊ ትርጉም አለው፥ "የተባረከ" "የተከበረ" "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" የሚል ፍቺ አለው። ለምሳሌ፦ መልአኩ ጂብሪል "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦ 
81፥19 እርሱ የ-"ክቡር" መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ ዐውድ ላይ ጂብሪል "ክቡር" ለተባለበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን "ንኡድ"noble" ለማለት እንጂ "ለጋሽ" "ቸር" ለማለት ተፈልጎ አይደለም፥ በተመሳሳይ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ "ከሪም" كَرِيم ተብለዋል፦
69፥40 እርሱ የ-"ተከበረ" መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ ዐውድ ላይ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "ክቡር" ለተባሉበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን "ንኡድ"noble" ለማለት እንጂ "ለጋሽ" "ቸር" ለማለት ተፈልጎ አይደለም። ስለዚህ አንድ ምንነት ወይም ማንነት "ከሪም" كَرِيم ስለተባለ አሏህ ከተወሰፈበትን ወስፍ ጋር ማምታታት አግባብ አይደለም። ቁርኣን "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦ 
56፥77 እርሱ "የከበረ" ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ ቁርኣን "የተከበረ" ለተባለበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን ሌላ አንቀጽ ላይ በተለዋዋጭ ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ተብሏል፦
6፥155 ይህም ያወረድነው የኾነ "የተባረከ" መጽሐፍ ነው፡፡ وَهَـٰذَا كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ مُبَارَكٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ ቁርኣን "የተባረከ" ለተባለበት የገባው ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ሲሆን "ሙባረክ" እና "ከሪም" የቃላት ልዩነት እንጂ የአሳብ ልዩነት የላቸውም። አትክልቶችን እና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ የሚበቅልበት ውኃ "ሙባረክ" مُّبَارَك ተብሏል፦
50፥9 ከሰማይም "ቡሩክን" ውኃ አወረድን፡፡ በእርሱም አትክልቶችን እና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን፡፡ وَنَزَّلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً مُّبَارَكًا فَأَنبَتْنَا بِهِ جَنَّاتٍ وَحَبَّ الْحَصِيدِ

እዚህ አንቀጽ ላይ ውኃ "ቡሩክ(የተባረከ) ለተባለበት የገባው ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ሲሆን ሌላ አንቀጽ ላይ በተለዋዋጭ ቃል "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦
79፥30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا
79፥31 ውኃን እና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡ أَخْرَجَ مِنْهَا مَاءَهَا وَمَرْعَاهَا
26፥7 ወደ ምድርም በውስጧ "ከ"መልካም" በቃይ ሁሉ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን?፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا إِلَى الْأَرْضِ كَمْ أَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ كَرِيمٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መልካም" ለሚለው የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሙባረክ" እና "ከሪም" ተለዋዋጭ ቃላት እንደሆኑ ለመረዳት ከላይ የቀረቡት ናሙናዎች በቂ ማሳያ ናቸው። እዚህ ድረስ ከተግባባን የረመዷን ወር ቁርኣን የወረደበት ወር ነው፦
2፥185 የረመዷን ወር በእርሱ ውስጥ ቁርኣን ለሰዎች መሪ፣ የመመሪያ ግልጽ ማስረጃ እና ፉርቃን ሲሆን የተወረደበት ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

"ፉርቃን" فُرْقَان ማለት "እውነት ከሐሰት፣ ትክክሉን ከስህተት፣ መልካሙን ከክፉ የሚለይ ሚዛን" ማለት ነው። "ሸህሩ ረመዷን" شَهْرُ رَمَضَان ማለት "የረመዳን ወር" ማለት ነው፥ "ረመዷን" رَمَضَان ደግሞ የዘጠነኛው ወር ስም ነው። "ረመዷን" የወር ስም እንጂ የጦም ስም አይደለም፥ ነገር ግን ይህ ወር ቁርኣን የተወረደበት ወር በመሆኑ "ሸህሩ ሙባረክ" شَهْرُ مُّبَارَك ማለትም "የተባረከ ወር" ተብሏል፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 17
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የተባረከው ወር ረመዷን መጣላችሁ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَتَاكُمْ رَمَضَانُ شَهْرٌ مُبَارَكٌ

ከዚህ አንጻር "ረመዷን ሙባረክ" رَمَضَان مُّبَارَك የሚለውን በቋንቋዬ ተርጉሜ "የተባረከ ረመዷን" ብል የቃላት ልዩነት እንጂ የአሳብ ልዩነት ከሌለው "ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم ሲባል "መልካም ረመዷን" "የተከበረ ረመዷን" ብል የቃላት እንጂ የአሳብ ልዩነት የለውም። "ኢማን" إِيمَان የሚለውን ቃል ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ በቁናህ ታገኘዋለህ፥ ቅሉ ግን የኢማን ተለዋዋጭ ቃል "ዐቂዳህ" عَقِيدَة የሚለውን በስም መደብ ቁርኣን ውስጥ አታገኘውም። ነገር ግን ዐቂዳህ እያልን እንማራለን እናስተምራለን፥ "ሙባረክ" እና "ከሪም" የሚለውን በዚህ ስሌት እና ሒሣብ መረዳት ይቻላል። ስለዚህ "ረመዷን ሙባረክ" رَمَضَان مُّبَارَك እና "ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم ተለዋዋጭ ቃላት እስከሆኑ ድረስ መርጠን መጠቀም እንችላለን።

"አሏሁ አዕለም! ይህ ሙግት የቋንቋን ሙግት ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ሙግት ነው።

"ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የረመዷን ስጦታ

ረመዷን ሙባረክ ያ ሙሥሊሙን ወሙሥሊማት!

በ 18 አርስት የተሰደረ መጣጥፍ በረመዷን ወር እንካችሁ ብለናል። ሊንኩን በማስፈንጠር ያግኙት!

1. ሶውም
https://tttttt.me/Wahidcom/3136

2. የጦም ትሩፋት
https://tttttt.me/Wahidcom/3470

3. ረመዷን
https://tttttt.me/Wahidcom/2727

4.. የረመዷን ወር
https://tttttt.me/Wahidcom/3107

5. የክርስትና ጦም
https://tttttt.me/Wahidcom/3176

6. የጨረቃ አቆጣጠር
https://tttttt.me/Wahidcom/2717

7. ጨረቃ እና ኮከብ
https://tttttt.me/Wahidcom/2360

8. የሚታሰሩ ሰይጣናት
https://tttttt.me/Wahidcom/2724

9. ሡሑር
https://tttttt.me/Wahidcom/2726

10. ተራዊህ
https://tttttt.me/Wahidcom/833

11. ኢዕቲካፍ
https://tttttt.me/Wahidcom/2286

12. ለይለቱል ቀድር
https://tttttt.me/Wahidcom/2289

13. መሓላ እና ማካካሻው
https://tttttt.me/Wahidcom/2336

14. ጦመኛ
https://tttttt.me/Wahidcom/3120

15. የተባረከ ወር
https://tttttt.me/Wahidcom/3707

16. ዘካቱል ማል
https://tttttt.me/Wahidcom/3126

17. ዘካቱል ፊጥር
https://tttttt.me/Wahidcom/3156

18. ተሀጁድ
https://tttttt.me/Wahidcom/3152

ሁሉም ቦታ ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ አሰራጩ!

ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
የአሏህ ምርጫ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥13 አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል፡፡ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ

"ኢንቲኻብ" اِنْتِخَاب ማለት "ምርጫ"election" ማለት ነው፥ ኢንቲኻብ እራሱ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ እና "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ።
፨ "ሹሩጢይ" شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ"conditional" ማለት ሲሆን በጥቅሉ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ ምርጫ"conditional election" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ አደም በሠራው ኃጢአት "ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፥ ለእኛ ባትምረን እና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን" ብሎ ተጸጸተ፦
7፥23 «ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፥ ለእኛ ባትምረን እና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡ قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ

አደም ተጸጽቶ በንስሓ ወደ አሏህ ሲመለስ አሏህ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፥ እነሆ አምላካችን አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፦
2፥37 አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ፡፡ በእርሱ ላይም ጌታው ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፥ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ فَتَلَقَّىٰ آدَمُ مِن رَّبِّهِ كَلِمَاتٍ فَتَابَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّهُ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

አደም ተጸጽቶ ንስሓ ወደ አሏህ በመግባቱ አሏህ ጸጸትን በመቀበል መረጠው፦
20፥122 ከዚያም "ጌታው መረጠው" ከእርሱም ጸጸቱን ተቀበለው መራውም፡፡ ثُمَّ اجْتَبَاهُ رَبُّهُ فَتَابَ عَلَيْهِ وَهَدَىٰ

"ጌታው መረጠው" የሚለው ይሰመርበት! ማንኛውም ሰው ከነበረበት ኩፍር ወይም ሺርክ አሊያም ዘንብ ወደ አሏህ በንስሓ ቢመለስ አሏህ ወደ ራሱ ለጀነት ይመርጠዋል፦
42፥13 አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል፡፡ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ

"አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል" የሚለው "ዓም" ሆኖ የመጣ ነው፥ "ዓም" عَامّ ማለት "ጥቅል"general" ማለት ነው። ነገር ግን "አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል" የሚለው ዓም "የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል" በሚል "ኻስ" ሆኖ እዛው ላይ መጥቷል፥ "ኻስ" خَاصّ ማለት "ተናጥል"specifical" ማለት ነው። መመራትን ሰው የሚያገኘው በማመን መሆኑ "ኻስ" ሆኖ የሚመጣ ነው፦
22፥54 አሏህ እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ "መሪ" ነው፡፡ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

"እነዚያን ያመኑትን" የሚለው ይሰመርበት! ያላመነው እና ንስሓ ያልገባ ሰው የሸይጧን ተከታይ ነው፥ ሸይጧን የተከተለውን ሰው ወደ ጀሀነም ይመራዋል፦
22፥4 "እነሆ! የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል፡፡ ወደ ነዳጅ እሳት ስቃይም ይመራዋል" ማለት በእርሱ ላይ ተጽፏል፡፡ كُتِبَ عَلَيْهِ أَنَّهُ مَن تَوَلَّاهُ فَأَنَّهُ يُضِلُّهُ وَيَهْدِيهِ إِلَىٰ عَذَابِ السَّعِيرِ

ሸይጧን ወደ ጀሀነም የሚመራው ሰው አሏህ ለጀነት ያልመረጠው በገዛ ፈቃዱ ሸይጧንን በመከተሉ ነው፥ ይህ የእኛ ጣልቃ ገብነት እና ድርሻ ያለበት የአሏህ ምርጫ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ ይባላል።
፨ "ገይሪ ሹሩጢይ" غَيْرِ شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ አልባ"unconditional" ማለት ሲሆን በጥቅሉ "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ አልባ ምርጫ"unconditional election" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፦
28፥68 ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ምርጫ የላቸውም፡፡ አሏህ ከማይግገባው ሁሉ ጠራ፡፡ ከሚያጋሯቸውም ላቀ፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

"የሚሻውን ይፈጥራል" በሚል ኃይለ ቃል "ይመርጣል" የሚለው ቃል አሏህ የሚሻውን ሰው፣ የሚሻውን እንስሳ፣ የሚሻውን አታክልት፣ የሚሻውን ማዕድን አርጎ መፍጠሩ የእርሱ ሁኔታዊ አልባ ምርጫ ነው፥ "ለእነርሱ ምርጫ የላቸውም" ማለት ፍጡራን "ይህንን ሆኜ ልፈጠር" የሚል ምርጫ የላቸውም። ወንድነት እና ሴትነት የእኛ ምርጫ ሳይሆን የእርሱ ምርጫ ብቻ ነው፦
42፥49 የሰማያትና የምድር ንግሥና የአሏህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፤ ለሚሻው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ወንዶችን ይሰጣል፡፡ لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ

"የሚሻውን ይፈጥራል" በሚል ኃይለ ቃል "ለሚሻው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ወንዶችን ይሰጣል" የሚለው ቃል ሴት መሆን እና ወንድ መሆን የአሏህ ሁኔታዊ አልባ ምርጫ ነው፥ የእኛ ምርጫ፣ ድርሻ፣ ፈቃድ ስለሌለበት ወንድነት እና ሴትነት ቅጣት እና ሽልማት አሊያም ተጠያቂነት የለበትም። አምላካችን አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፦
40፥7 እነዚያ "ዙፋኑን የሚሸከሙት" እና እነዚያ በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ
22፥75 አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፥ ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል። አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

"ከሩቢዩን" كَرُوبِيُّون የሚባሉት መላእክት የአሏህን ዐርሽ የሚሸከሙ ሲሆን በዐርሹ ዙሪያ ካሉት መላእክት ወደ ሰዎች የሚልካቸው መላእክት የእርሱ ሁኔታ አልባ ምርጫ ነው። "ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል" ስለሚል አሏህ ከሰዎች ለመልእክተኛነት መምረጡ ይህ የእርሱ ሁኔታ አልባ ምርጫ ነው፦
2፥105 አሏህም በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ وَاللَّهُ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
3፥74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አሏህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ

አሏህ አንድ ሰው በነቢይነት ቢመርጠው ሆነ ባይመርጠው ሽልማት እና ቅጣት አሊያም ተጠያቂነት ስለሌለበት ይህ "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ነው።
የአሏህን ምርጫ "አሚን" ብሎ መቀበል ከአርካኑል ኢማን ክፍል የሆነውን ቀደርን መቀበል ነው፥ አሏህ የእርሱን ምርጫ "አሚን" ብለው ከሚቀበሉት ምእመናን ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቁወቱል ኢማን

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

92፥6 በመልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ። وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ

"ቁዋህ" قُوَّة የሚለው ቃል "ቀዊየ" قَوِيَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ኃይል" ማለት ነው፥ "ኢማን" إِيمَٰن የሚለው ቃል "አሚነ" أَمِنَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው። በጥቅሉ "ቁወቱል ኢማን" قُوَّة الإِيمَان ማለት "የእምነት ኃይል" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ትልቁ የኢማን ቅርንጫፍ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፥ ትልቁ ቅርንጫፍ “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ማለት ነው። ትንሹ ደግሞ ከመንገድ ላይ እንቅፋት ማስወገድ ነው፥ ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏

"ሐያእ" حَيَاء ማለት "ዓይናፋርነት" "ጨዋነት" ማለት ነው፥ ሐያእ ከኢማን ነው። ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 115
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሐያእ ከኢማን ነው፥ ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል። ብልግና ከብሉሽነት ነው፥ ብሉሽነት ወደ እሳት ይመራል”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْحَيَاءُ مِنَ الإِيمَانِ وَالإِيمَانُ فِي الْجَنَّةِ وَالْبَذَاءُ مِنَ الْجَفَاءِ وَالْجَفَاءُ فِي النَّارِ ‏

"በዛእ" بَذَاء ማለት ደግሞ "ዓይናውጣነት" "ብልግና" ማለት ነው፥ ብልግና ከብሉሽነት(ኩፍር) ሲሆን ኩፍር ወደ እሳት ይመራል። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" መልካሚቱም እምነት ናት፦
92፥6 በመልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ። وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ
92፥7 ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْيُسْرَىٰ

"ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه በምትባለው መልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ አሏህ መልካም ሥራን ያገራለታል፥ "ዩሥር" يُسْرَىٰ ማለት "ቀላል" "ገር" "መልካም" ማለት ሲሆን ኢማን ወደ ጀነት የሚያመራው በመልካም ሥራ ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የምትለዋን መልካሚቱን እምነት ሰምቶ የካደ አሏህ መልካም ሥራን ያከብድበታል፦
92፥9 በመልካሚቱ እምነት ያሰተባበለም። وَكَذَّبَ بِالْحُسْنَىٰ
92፥10 ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْعُسْرَىٰ

"ዑሥራ" عُسْرَىٰ ማለት "ከባድ" "ሸካራ" "ክፉ" ማለት ሲሆን ኩፍር ወደ እሳት የሚመራው በመጥፎ ሥራ ነው። ኢማን የሚጨምር እና የሚቀንስ ነው፦
8፥2 ፍጹም ምእምናን እነዚያ አሏህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ ኢማን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
"አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ ኢማን የሚጨምሩላቸው" የሚለው ይሰመርበት! በኢማም አቡ መንሱር አል ማቱሪዲይ የተቀመረው ማቱሪዲያህ የሚባለው ስሑት ዐቂዳህ፦ "ኢማን የማይጨምር እና የማይቀንስ ቋሚ ነው" የሚል እሳቤ በዚህ ጥቅስ ድባቅ ይገባል። ኢማኑ በአሏህ አንቀጾች እየጨመረ የሚሄድ ሙእሚን አሏህ ዘንድ ደረጃዎች አሉት፦
8፥4 እነዚያ በእውነት አማኞች እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምሕረት እና የከበረ ሲሳይም አላቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

"ደረጃት" دَرَجَات የሚለው ቃል "ደረጃህ" دَرَجَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን አሏህ ዘንድ ጀናህ መቶ ጀረዎች አሏት፥ ተጀናህ ከፍተኛ ደረጃዋ ፊርደውሥ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4474
ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰማው ብሎ እንደተረከው፦ "እርሳቸውም አሉ፦ "ጀናህ መቶ ጀረዎች አሏት፥ ደረጃዎቿም ያላቸው እርቀት ልክ የሰማይ እና የምድር እርቀት ያክል ነው። ከፍተኛ ደረጃዋ ፊርደውሥ ነው፥ أَنَّ مُعَاذَ بْنَ جَبَلٍ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ "‏ الْجَنَّةُ مِائَةُ دَرَجَةٍ كُلُّ دَرَجَةٍ مِنْهَا مَا بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ وَإِنَّ أَعْلاَهَا الْفِرْدَوْسُ

አማኞች በእምነት የሚሠሩት መልካም ሥራ በሚሠሩት መልካም ሥራ መጠን የተለያየ ደረጃዎችን በጀነት ውስጥ ያገኙበታል፦
20፥75 በጎ ሥራዎችን በእርግጥ የሠራ ምእመን ኾኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለእነርሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አላቸው፡፡ وَمَن يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولَـٰئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَىٰ
3፥163 እነርሱ አላህ ዘንድ ባለ ደረጃዎች ናቸው፡፡ አላህም የሚሠሩትን ነገር ተመልካች ነው፡፡ هُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِمَا يَعْمَلُونَ
6፥132 ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አላቸው፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ
46፥19 ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አላቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው፥ እነርሱም አይበደሉም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۖ وَلِيُوَفِّيَهُمْ أَعْمَالَهُمْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

"ጀናህ" جَنَّة በ "ታ" ة መርቡጧህ በነጠላ ሲሆን አጠቃላይ ጀነትን ያመለክታል፥ በአጠቃላዩ ጀነት ውስጥ ለመግባት ቁልፉ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ሲሆን በጀነት ውስጥ ያሉትን ጀረጃዎች ውስጥ ለመግባት እና ለመመንዳት መልካም ሥራ ያስፈልጋል። በጀነት ውስጥ ያሉት መቶ የተለያዩ ደረጃዎች እራሱ "ጀናት" جَنَّات‎ ተብለዋል፥ "ጀናት" جَنَّات‎ በ "ታ" ت መፍቱሓህ ሲሆን በብዜት "ጀነቶች" "ገነቶች" ማለት ነው። እነዚህ የተለያየ ደረጃዎች የሆኑ ጀነቶች አምነው መልካም ለሚሠሩ የሚሰጥ ምንዳ፣ ትሩፋት፣ ወሮታ፣ ስርጉት፣ ትርሲት ነው፦
31፥8 እነዚያ ያመኑ እና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ "ገነቶች" አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتُ النَّعِيمِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ገነቶች" ለሚለው የገባው በብዙ ቁጥር "ጀናት" جَنَّات‎ እንደሆነ ልብ አድርግ! እያንዳንዱ ደረጃ "ጀነቱል ዐድን" جَنَّةُ العَدْن "ጀነቱ አን-ነዒም" جَنَّةُ النَّعِيمِ "ጀነቱል መእዋ" جَنَّةُ المَأْوَىٰ "ጀነቱል ፊርደውሥ" جَنَّةُ الفِرْدَوْسُ እየተባለ ይጠራል። አምላካችን አሏህ የኢማንን ኃይል ተረድተው መልካም ሥራ ከሚሠሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቀጥተኛው መንገድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

36፥4 "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ"፡፡ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

"ሲሯጥ" صِرَٰط ማለት በመነሻ እና በመዳረሻ መካከል ያለ "መንገድ" ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ "መንገድ" እያልን የምንጦምረው እማሬአዊ የሆነውን የአስፋት መንገድ ሳይሆን ወደ ጀነት የሚያደርሰውን ፍካሬአዊ የሆነውን መንገድ ነው። አምላካችን አሏህን በብቸኝነት ማምለክ ወደ ጀነት የሚያደርስ "ቀጥተኛው መንገድ" ነው፦
36፥61 "አምልኩኝ! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው" በማለትም አላዘዝኩምን? وَأَنِ ٱعْبُدُونِى ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

"ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "አምልኩኝ" የሚለውን ቃል አመላካች ነው። ዒሣም በተልኮው አሏህን በብቸኝነት ማምለክ "ቀጥተኛ መንገድ" እንደሆነ አበክሮ እና አዘክሮ ነግሮናል፦
3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነዉና "አምልኩት! ይህ "ቀጥተኛ መንገድ" ነው»። አላቸዉ። إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ
43፥64 «አሏህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና "አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው»። إِنَّ اللَّهَ هُوَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

እነዚህም አናቅጽ ላይ "ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "አምልኩት" የሚለውን ቃል አመላካች ነው። "ሙስተቂም" مُّسْتَقِيم ማለት "ቀጥተኛ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህን በብቸኝነት ማምለክ ቀጥተኛ መንገድ ነው፥ ከዚያ ውጪ ያሉት መንገዶች የጥመት መንገዶች ናቸው፦
6፥153 «ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና» በላቸው። وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ

ይህ አንዱን አምላክ በብቸንነት ማምለክ ለኢብራሂም የተገለጠ የኢብራሂም መንገድ ነው፥ አምላካችን አሏህ የኢብራሂምን መንገድ መርቶናል፦
6፥161 «እኔ ጌታዬ ወደ "ቀጥተኛው መንገድ" ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል፡፡ قُلْ إِنَّنِى هَدَىٰنِى رَبِّىٓ إِلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ دِينًۭا قِيَمًۭا مِّلَّةَ إِبْرَٰهِيمَ حَنِيفًۭا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

አሁንም "ቀጥተኛው መንገድ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! አንድ ሰው ከነበረበት ሺርክ እና ኩፍር ወደ አምላካችን አሏህ በንስሓ ከተመለሰ አሏህ በንስሓ የሚመለውን ሰው ወደ እርሱ ይመራዋል፦
42፥13 አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል፡፡ "የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል"፡፡ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ

"የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል" የሚለው በአጽንዖት ይሰመርበት! አንድ ሙሥሊም በቀጥተኛው መንገድ ላይ ስለሆነ አምላካችን አሏህ፦ "በቀጥታ መንገድ ላይ ነህ" ብሏል፦
36፥4 "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ"፡፡ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ
43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ! አንተ "በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና"።فَاسْتَمْسِكْ بِالَّذِي أُوحِيَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

ሙሥሊም በቀጥተኛው መንገድ እንደሆነ በቁና ጥቅስ ማቅረብ ይቻላል። አንድ ዳዒ ሙሥሊም በቀጥተኛ መንገድ ስለሆነ እና ይህም ቀጥተኛ መንገድ አሏህን በብቸኝነት ማምለክ እንደሆነ ተረድቶ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይጣራል፦
23፥73 አንተም ወደ "ቀጥተኛው መንገድ" በእርግጥ ትጠራቸዋለህ። وَإِنَّكَ لَتَدْعُوهُمْ إِلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ
16፥125 "ወደ ጌታህ መንገድ" በጥበብ እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ

አንድ ሙሥሊም በቀጥተኛ መንገድ ላይ ባይሆን ኖሮ ወደ ቀጥተኛ መንገድ መጥራቱ ትርጉም አልባ ይሆን ነበር። ይህ ቀጥተኛ መንገድ መነሻው ዱንያህ ሲሆን መዳረሻው አኺራ ነው፥ አሁን ጉዞ ላይ ነን።

ለምሳሌ፦ እኔ ፒያሳ መሄድ ፈልጌ የፒያሳን መንገድ መነሻውን አየር ጤና አንድ ሰው ከመራኝ በኃላ መንገዱ በጉዞ ላይ ጦር ኃይሎች ጋር ስደርስ ወደ ኮልፌ መንገዱት እንዳልስት፣ ልደታ ጋር ስደርስ ወደ መርካቶ አሊያ ወደ ኦልድ ኤር ፓርት መንገዱን እንዳልስት፣ ሜክሲኮ ጋር ስደርስ ወደ መካኒሳ አሊያም ወደ ተክለ ሃይማኖት መንገዱን እንዳልስት፣ ብሔራዊ ጋር ስደርስ መንገዱን ወደ ፍሉ ውኃ እንዳልስት እስከመጨረሻው ምሪት ያስፈልገኛል። በተመሳሳይ ይህ ቀጥተኛ መንገድ መነሻውን አሏህ ከመራን በኃላ በጉዞ ላይ እያለን ከመንገዱ እንዳንወጣ ምሪት እስከመጨረሻው ለማግኘት አሏህን "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" እያልን በሶላት ላይ ስንቆም እንጠይቀዋለን፥ አሏህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው፦
1፥6 "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን"። ٱهْدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلْمُسْتَقِيمَ
22፥54 አሏህ እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ "መሪ" ነው፡፡ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

አሏህ "ቀጥተኛ መንገድ ምራን" በሉ ሲለን እኛም "ቀጥተኛ መንገድ ምራን" ስንል ዳዊትም "መንገድህን ምራኝ" ብሏል፦
መዝሙር 86፥11 አቤቱ መንገድህን ምራኝ፥

ዳዊት "መንገድህን ምራኝ" ሲል መንገዱን አያቅም ማለት ካልሆነ እንግዲያውስ እኛ አሏህን "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" ስንል ቀጥተኛውን መንገድ አናቅም ማለት አይደለም፥ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው። አምላካችን አሏህ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ የምንጠራ ዳዒዎች ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙቀረቡን

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

56፥11 እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ الْمُقَرَّبُونَ

"ሙቀረብ" مُقَرَّب የሚለው ቃል "ቀሪበ" قَرِبَ ማለትም "ቀረበ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ቀራቢ" "ባለሟል" ማለት ነው፥ "ሙቀረቡን" مُقَرَّبُون ወይም "ሙቀረቢን" مُقَرَّبِين ደግሞ የሙቀረብ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ቀራቢዎች" "ባለሟሎች" ማለት ነው። ከአስሓቡል የሚን ለበጎ ሥራ ቀዳሚዎቹ ለገነት ቀዳሚዎች ሲሆኑ እነርሱ አሏህ ዘንድ "ሙቀረቡን" ናቸው፦
56፥11 እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ الْمُقَرَّبُونَ

የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ሲሆን እነርሱም "ሙቀረቡን" ናቸው፦
83፥21 "ባለሟልዎቹ" ይጣዱታል፡፡ يَشْهَدُهُ الْمُقَرَّبُونَ
83፥28 "ባለሟሎቹ" ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡ عَيْنًا يَشْرَبُ بِهَا الْمُقَرَّبُونَ

አንድ አማኝ ካመነ በኃላ የሚሠራው መልካም ሥራ ወደ አሏህ መቃረቢያ ሲሆን "ቁርባን" ይባላል፥ "ቁርባን" قُرْبَان ማለት "መቃረቢያ" ማለት ነው፦
5፥35 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ! ወደ እርሱም መቃረቢያ መልካም ሥራን ፈልጉ፡፡ ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
9፥99 ከአዕራቦችም በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን፣ የሚሰጣቸውን ምጽዋቶች አሏህ ዘንድ መቃረቢያዎች እና ወደ መልእክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ሰው አለ፡፡ ንቁ! እርሷ ለእነርሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት፥ አሏህ በችሮታው ውስጥ (በገነቱ) በእርግጥ ያስገባቸዋል፡፡ አሏህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ وَمِنَ الْأَعْرَابِ مَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ قُرُبَاتٍ عِندَ اللَّهِ وَصَلَوَاتِ الرَّسُولِ ۚ أَلَا إِنَّهَا قُرْبَةٌ لَّهُمْ ۚ سَيُدْخِلُهُمُ اللَّهُ فِي رَحْمَتِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

"አዕራብ" أَعْرَاب ማለት "ገጠሬ" ማለት ሲሆን ከዐረብ ገጠሬዎች በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን አምነው የሚሰጣቸውን ምጽዋቶች አሏህ ዘንድ መቃረቢያዎች አድርገው የሚይዙ ሰዎች አሉ፥ ስለዚህ አሏህ ዘንድ ከሰዎች መካከል ሙቀረቡን አሉ። በተመሳሳይ መላእክት የአሏህ ባመሟሎች ስለሆኑ "ሙቀረቢን" مُقَرَّبِين ተብለዋል፦
4፥172 አልመሢሕ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ "ቀራቢዎች" የኾኑት መላእክት አይጠየፉም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ

መላእክት ወደ መርየም መጥተው ለመርየም ያሏት "ባለሟል በኾነ ልጅ" ሳይሆን "ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ" የሚል ነው፦
3፥45 መላእክት ያሉትን አስታውስ፡- «መርየም ሆይ! አሏህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሢሕ ዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ ያበስርሻል»። إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አል ሙቀረቢን" الْمُقَرَّبِين የተባሉ ከላይ እንደተገለጸው የአሏህ ባሮች ሲሆኑ ይህ አንቀጽ ጭራሽኑ ከሙቃሪቢን መካከል አንዱ ዒሣ መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፥ "ዒሣ ብቻ "ባለሟል" ነው" የሚል ሽታው ቁርኣን ላይ የለም። አምላካችን አሏህ ሙቀረቡን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሥነ ፍጥረት

ክፍል አንድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام

አምላካችን አሏህ ሰማያትን፣ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠረ፦
50፥38 ሰማያትን፣ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

"ፊ" فِي ማለት "ውስጥ" ማለት ሲሆን በጥቅል ስድስት ቀናት ውስጥ ሰማያትን እና ምድርን እንደፈጠረ ጉልኅ ማሳያ ነው፦
7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام

"በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "ፊ" فِي የሚለው መስተዋድድ በጥቅል አገላለጽ ፍጥረት በስድስት ቀናት ውስጥ መፈጠራቸውን አመላካች ነው። በተናጥል ሌላ አንቀጽ ላይ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ መፍጠሩትን ይናገራል፦
41፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ "ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን?" ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "ሁለት ቀናት" የተባሉት የመጀመሪያው ቀን "አል አሐድ" ٱلْأحَد እና ሁለተኛው ቀን "አል ኢስነይን" ٱلْاِثْنَيْن‎ እንደሆኑ ሙፈሢሮች አስቀምጠዋል፦
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 41፥9 "ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው" ሲል "የመጀመሪያው ቀን እና ሁለተኛው ቀን ነው" ማለት ነው"። فقوله : ( خلق الأرض في يومين ) يعني : يوم الأحد ويوم الاثنين .

፨ "አሐድ" أحَد ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን "እሑድ" ማለት ነው፥ "እሑድ" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ “አሐደ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንድ" ማለት ነው።
፨ "ኢስነይን" اِثْنَيْن‎ ማለት "ሁለት" ማለት ሲሆን "ሰኞ" ማለት ነው፥ "ሰኞ" ማለት "ሰነየ" ማለትም "ደገመ" ከሚል የመጣ ሲሆን "ሁለተኛ" ማለት ነው።
አሏህ በምድር ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፥ በውስጧም ባረከ፦
42፥10 በእርሷ ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፥ በውስጧም ባረከ፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا

"ባረከ" بَٰرَكَ ማለት "ባረከ" ማለት ሲሆን በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦
42፥10 "በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ"፡፡ وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ

"በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ" አለ እንጂ "በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ፈጠረ" አላለም፥ "ወሰነ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን "መጠነ" "አዘጋጀ" በሚል ይመጣል፦
80፥19 ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው እና መጠነው፡፡ مِن نُّطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ
25፥2 ነገሩንም ሁሉ የፈጠረ እና በትክክልም ያዘጋጀው ነው፡፡ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ فَقَدَّرَهُ تَقْدِيرًا

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "መጠነ" "አዘጋጀ" ለሚለው የገባው ቃል ግን "ቀደረ" قَدَّرَ ነው፥ በአራት ቀናት የመጠነው እና ያዘጋጀው ምግቧን እንጂ ፈጠረ አይልም። ምድርን የፈጠረበት 2 ቀናት እና ምግቧን የወሰነበትን 4 ቀናት ደምራችሁ 6 ቀናት ብላችሁ ለማጋጨት የሞከራችሁት ሙከራ ፉርሽ ሆኗል።

ሲጀመር "ተዳኹል" تَدَاخُل የሚለው ቃል "ተዳኸለ" تَدَاخَلَ ማለትም "ተጠላለፈ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጠላለፍ"intersection" ማለት ነው፥ አራት ቀናት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ተዳኹል የሆኑት "አል አሐድ" ٱلْأحَد "አል ኢስነይን" ٱلْاِثْنَيْن‎ "አል ሱላሳእ" ٱلْثُّلَاثَاء "አል አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ናቸው፦
ተፍሢሩል ጀላለይን 41፥10 "በአራት ሙሉ ቀናት በሌላ አነጋገር በውስጧ ያለው የተራሮች አቀማመጥ ከሥስተኛው እና ከአራተኛው ቀን ጋር ተያይዞ የተከናወነው በትክክል "ሠዋእ" በተሳቢ ምክንያቱም ግሣዊ ስም ነው፥ አራቱ ቀናት ያነሱም ያልበዙም ለጠያቂዎች ሁሉ ስለ ምድር አፈጣጠር እና በውስጧ ስላለው ሁሉ በትክክል አራት ነበሩ"።

"ሠዋእ" سَوَآء ማለት "በትክክል" ማለት ሲሆን በሰዋስው አወቃቀር አራት ቀናት በሁለት ቀናት ውስጥ ተለጣጥፎ"overlap" የመጣ ነው።
፨ "ሱላሳእ" ثُّلَاثَاء ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ማክሰኞ" ማለት ነው። "ማክሰኞ" ማለት "ማግስት" ማለት ነው፥ የእሁድ ማግስት "ሦስተኛ" ቀን ነው።
፨ "አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ማለት "አራት" ማለት ሲሆን "ረቡዕ" ማለት ነው፥ "ረቡዕ" ማለት "ረበዓ" ከሚል የመጣ ሲሆን "አራተኛ" ማለት ነው።
አምላካችን አሏህ ምድርን በፈጠረበት ጊዜ ሰማይን ጋዝ አርጎ ፈጠራት፥ ሰማይ የተገነባችበት ጋዝ ምድር በተፈጠረች ጊዜ ከእርሷ የሚወጣውን ጋዝ ነበረ፦
79፥27 ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? አሏህ ገነባት፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 42፥11 እርሱ(ጋዙ) ምድር በተፈጠረች ጊዜ ከእርሷ የሚወጣው ጭስ ነው"። وهو : بخار الماء المتصاعد منه حين خلقت الأرض

“ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَان ሲሆን “ጋዝ”gas" ማለት ነው፥ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አሏህ ለሰማይ እና ለምድር፦ «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፦
42፥11 "ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ

ኢሻላህ ይቀጥላል.....

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሥነ ፍጥረት

ክፍል ሁለት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥47 እጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ ሺህ ዓመት ነው፡፡ إِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ

ሰማይን ከፈጠረ በኃላ በሁለት ቀን የፈጠራትን ምድርን የእንቁላል ቅርጽ አርጎ ዘረጋት፥ "ዘረጋ" እንጂ "ፈጠረ" አይልም። "ዘረጋ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ደሓ" دَحَا ሲሆን የስም መደቡ "አድ ደሕያ” الدِّحْيَّة ነው፦
79፥30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

"ከዚህ በኋላ" ማለት ከሰማይ መፈጠር በኃላ ማለት ነው፥ "አድ ደሕያ” الدِّحْيَّة ማለት “የሰጎን እንቁላል” ማለት ሲሆን አሏህ ምድርን “የሰጎን እንቁላል ቅርጽ አደረጋት” የሚል ትርጉም አለው።
፦ Dr. Kamal Omar Translation
፦ Ali Unal Translation
፦ Shabbir Ahmed Translation፦
“የሰጎን እንቁላል ቅርጽ አደረጋት”He made the earth egg-shaped”

ብለው ተርጉመውታል። አሏህ ምድርን እንደ ሰጎን እንቁላል ቅርጽ አርጎ ያደላደላት ለእኛ ስለሆነ "ለእናንተ" በማለት ይናገራል፦
55፥10 ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡ وَالْأَرْضَ وَضَعَهَا لِلْأَنَامِ
71፥19 አላህም ምድርን “ለእናንተ” ምንጣፍ አደረጋት፡፡ وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ بِسَاطًا
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا

አሏህ ምድርን እንደ ሰጎን እንቁላል ቅርጽ አርጎ አደላድሎ በምድር ያለውን ማዕድናት፣ እጽዋት እና እንስሳት ለእኛ ፈጠረ፥ "በምድር ያለውን ሁሉ" የሚለው ማዕድናትን፣ እጽዋትን እና እንስሳትን ያካትታል። ከዚያ በጭስ መልክ የነበረችውን ሰማይ ሰባት ሰማያት አርጎ ጨረሳት አስተካከላት፦
41፥12 በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት "አደረጋቸው"፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ
2፥29 ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፥ ሰባት ሰማያትም "አደረጋቸው"፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ

"ወደ ሰማይ አሰበ" "ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ" ማለቱ በራሱ ሰማይ በጋዝ ደረጃ ተፈጥራ እንደነበረ ጉልህ ማሳያ ነው፥ "ከዚያም" ማለት ምድር እና ምድር ላይ ያለውን ከፈጠረ በኃላ ማለት ነው። 41፥12 ላይ "አደረገ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀዷ" قَضَىٰ ሲሆን "ጨረሰ" በሚል ይመጣል፦
27፥29 ሙሳም ጊዜውን በ-"ጨረሰ" እና ከቤተሰቦቹ ጋር በኼደ ጊዜ ከጡር ተራራ ጎን እሳትን አየ፡፡ فَلَمَّا قَضَىٰ مُوسَى الْأَجَلَ وَسَارَ بِأَهْلِهِ آنَسَ مِن جَانِبِ الطُّورِ نَارًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጨረሰ" ለሚለው የገባው "ቀዷ" قَضَىٰ እንደሆነ በአጽንዖት ልብ አድርግ! በተጨማሪ 2፥29 ላይ "አደረገ" ለሚለው የገባው ቃል "ሠዋ" سَوَّىٰ ሲሆን "አስተካከለ" በሚል ይመጣል፦
87፥2 የዚያን ሁሉን ነገር የፈጠረውን እና ያስተካከለውን፡፡ الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያስተካከለ" ለሚለው የገባው "ሠዋ" سَوَّىٰ እንደሆነ በአንክሮት ልብ አድርግ! ስለዚህ ምድር እንደ ሰጎን እንቁላል ከመደላደሏ በፊት የፈጠራትን ጭሳዊ ሰማይ ሰባት ሰማያት አርጎ ፈጸማት አስተካከላት። "ቀዷሁነ" قَضَىٰهُنَّ "ሠዋሁነ" سَوَّىٰهُنَّ በሚል መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለው "ሁነ" هُنَّ የሚለው ሦስተኛ አንስታይ መደብ "ሂየ" ‏هِيَ ለሚለው ብዜት ነው፥ "ሂየ" ‏هِيَ ማለት "እርሷ" ማለት ሲሆን "ሠማእ" سَّمَآء የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። ሰማይን ሰባት ሰማያት አድርጎ የጨረሰው እና ያስተካከለው በሁለት ቀናት ውስጥ ነው፥ እነዚህ "ሁለት ቀኖች" የተባሉት አምስተኛው ቀን "አል ኸሚሥ" ٱلْخَمِيس እና ስድስተኛው ቀን "አል ጁሙዓህ" ٱلْجُمُعَة እንደሆኑ ሙፈሢሮች አስቀምጠዋል፦
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 41፥12 "በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው" ከዚያ ፈጽሞ በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት አስተካከላቸው፥ ሌላው ሁለቱ ቀናት አምስተኛው ቀን እና ስድስተኛው ቀን ናቸው።
( فقضاهن سبع سموات في يومين ) أي : ففرغ من تسويتهن سبع سموات في يومين ، أي : آخرين ، وهما يوم الخميس ويوم الجمعة .
፨ "ኸሚሥ" خَمِيس ማለት "አምስት" ማለት ሲሆን "ሐሙስ" ማለት ነው፥ "ሐሙስ" ማለት "አምሽት" "አምስት" ማለት ነው።
፨ "ጁሙዓህ" جُمُعَة ማለት "ስብስብ" ማለት ሲሆን "ዓርብ" ማለት ነው፥ "ዓርብ" የሚለው "ረበዐ" ማለትም "ሰበሰበ" ማለት ሲሆን "መሰብሰቢያ" "ስድስተኛ" ማለት ነው።
አሏህ ለመላእክት፦ "እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ፥ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ" ብሎ በነገራቸው መሠረት ሰውን በስድስተኛው ቀን ፈጠረ፦
38፥71 ጌታህ ለመላእክት «እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ! وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 7፥54 "እነዚህ ስድስት ቀናት አሐድ፣ ኢስነይን፣ ሱላሳእ፣ አርቢዓእ፣ ኸሚሥ፣ ጁሙዓህ ናቸው። ፍጥረት ሁሉ በጁሙዓህ ቀን ተሰብስቦ ነበር፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ። والستة الأيام هي : الأحد ، والاثنين ، والثلاثاء ، والأربعاء ، والخميس ، والجمعة - وفيه اجتمع الخلق كله ، وفيه خلق آدم.
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 1
አቡ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ فِيهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ

ለመሆኑ ባይብል ላይ ፈጣሪ ሰማይን እና ምድርን የፈጠረው በየትኛው ቀን ነው ይላል? ዘፍጥረት በመጀመርያው ቀን ይለናል፦
ዘፍጥረት 1፥1 በመጀመሪያ ኤሎሂም ሰማይን እና ምድርን ፈጠረ። בְּרֵאשִׁ֖ית בָּרָ֣א אֱלֹהִ֑ים אֵ֥ת הַשָּׁמַ֖יִם וְאֵ֥ת הָאָֽרֶץ׃
ዘፍጥረት 1፥5 ኤሎሂምም ብርሃኑን "ቀን" ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት፡ አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን። וַיִּקְרָ֨א אֱלֹהִ֤ים לָאֹור֙ יֹ֔ום וְלַחֹ֖שֶׁךְ קָ֣רָא לָ֑יְלָה וַֽיְהִי־עֶ֥רֶב וַֽיְהִי־בֹ֖קֶר יֹ֥ום אֶחָֽד׃ פ

"ዮም" י֥וֹם ማለት በነጠላ "ቀን" ማለት ሲሆን ይህ የመጀመሪያ ቀን ስለሆነ "አንድ" ለሚለው "ኤኻድ" אֶחָֽד በማለት ይነግረናል። ዘጸአት ደግሞ በስድስት ቀናት ይለናል፦
ዘጸአት 31፥17 ያህዌህ ሰማይን እና ምድርን በስድስት ቀናት ፈጠረ። כִּי־שֵׁ֣שֶׁת יָמִ֗ים עָשָׂ֤ה יְהוָה֙ אֶת־הַשָּׁמַ֣יִם וְאֶת־הָאָ֔רֶץ

"ያሚም" יָמִ֗ים ማለት "ቀናት" ማለት ሲሆን "ዮም" י֥וֹם ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ "ሼሼት" שֵׁ֣שֶׁת ማለት "ስድስት" ማለት ነው። ኤሎሂም ሰማይን እና ምድርን የፈጠረው በስድስት ቀናት ወይም በመጀመርያው ቀን?

"ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን" "ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን" "ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን" የሚሉ አገላለፆችን ስናይ "ቀን" የተባለው 12 ሰዓት የያዘውን የመአልት ክፍል እና 12 ሰዓት የያዘውን የሌሊት ክፍል በጥቅሉ ባለ 24 ሰዓቱን እንደሆነ አመላካች ነው።
በቁርኣን ግን ፍጥረት የተፈጠረበት "ቀን" የሚለው ባለ 24 ሰዓት ቀን ሳይሆን በትንሹ አንድ ሺህ ዓመት ነው፦
22፥47 እጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ ሺህ ዓመት ነው፡፡ إِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ
ተፍሢር ኢብኑ ዐባሥ 7፥53 "ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው" ከአያሙል ዱንያ እያንዳንዱ ቀን አንድ ሺህ ዓመት ነው"።
{ إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَمَاوَاتِ وَٱلأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ } من أيام الدنيا طول كل يوم ألف سنة

ሌላው ሰማያትን እና ምድርን እንዲሁ በውስጣቸው ያለው ሁሉ ኅልቅቆ መሳፍርት ፍጥረት ሁሉ በጥቅሉ በስድስት ቀናት ውስጥ እንደፈጠ አሏህ ነግሮናል፥ ባይብል ላይ መላእክት መቼ እንደተፈጠሩ በግልጽ አይናገርም። ከዚያ ይልቅ በጥቅሉ አምላክ ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳማያገኝ ይናገራል፦
መክብብ 3፥11 አምላክ ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው። גַּ֤ם אֶת־הָעֹלָם֙ נָתַ֣ן בְּלִבָּ֔ם מִבְּלִ֞י אֲשֶׁ֧ר לֹא־יִמְצָ֣א הָאָדָ֗ם אֶת־הַֽמַּעֲשֶׂ֛ה אֲשֶׁר־עָשָׂ֥ה הָאֱלֹהִ֖ים מֵרֹ֥אשׁ וְעַד־סֹֽוף׃

እኛም በሰማያት እና በምድር አፈጣጠር በማስተንተን፦ «ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከውም፥ ጥራት ይገባህ! ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» እንላለን፦
3፥191 እነርሱም እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም እና በጎኖቻቸው ተጋድመው አሏህን የሚያወሱ፥ በሰማያት እና በምድር አፈጣጠር የሚያስተነትኑ፦ «ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከውም፥ ጥራት ይገባህ! ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ

"ተፈኩር" تَفَكُّر የሚለው ቃል "ተፈከረ" تَفَكَّرَ ማለትም "አስተነተነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ማስተንተን" ማለት ነው፥ የአሏህ ፍጥረት ማስተንተን የሥነ ፍጥረት ዕውቀታችንን ያጎለብተዋል። አምላካችን አሏህ ፍጥረቱን ከሚያስተነትኑ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በጉራጊኛ ደርሥ ተለቋል። ጉራጊኛ ተናጋሪዎች ገብታችሁ ኮምኩሙ፦ https://tttttt.me/wahidcomguragiga/36
ታላቂቱ ባቢሎን

ክፍል አንድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥111 «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ

"አፓካሉፕሲስ" ἀποκάλυψις ማለት "ቀለምሲስ" "ራእይ" "መገለጥ"revelation" ማለት ሲሆን መሠረታዊ ትርጉሙ "የተሸፈ ነገር ማራቆት" ማለት ነው፥ ቀለምሲስ የጴጥሮስ ራእይ፣ የጳውሎስ ራእይ፣ የያዕቆብ ራእይ እና የዮሐንስ ራእይ ተብለው ይታወቃሉ።
፨ የጴጥሮስ ራእይ 1672 ድኅረ ልደት በሙራቶሪያን ቀኖና ውስጥ የተገኘ ሲሆን በ 170 ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣
፨የጳውሎስ ራእይ 1845 ድኅረ ልደት የናግ ሐማዲ ኮዴክስ 172 ውስጥ የተገኘ ሲሆን በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣
፨ የያዕቆብ ራእይ 1845 ድኅረ ልደት የናግ ሐማዲ ኮዴክስ 172 ውስጥ የተገኘ ሲሆን በ 200 ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣
፨ የዮሐንስ ራእይ ዲዮናስዮስ ዘእስክንድርያ በተናገረው መሠረት ከ 50-100 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የሴሪንቶሳውያን"Cerinthian" መሥራች ሴሪንቶስ"Cerinthus" እንደጻፈው ተናግሯል፦
"እንዲህም ይላሉ፦ "የዮሐንስ ሥራ አይደለም እንዲሁ መገለጥም አይደለም፥ ምክንያቱም በወፍራም እና ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ መጋረጃ የተሸፈነ ነው። እነሱም ከሐዋርያት፣ ከቅዱሳን አንዳቸውም ወይም ከቤተክርስቲያን ውስጥ አንድም ደራሲ እንዳልሆኑ ያረጋግጣሉ፥ ነገር ግን ሴሪንቶስ ከእሱ በኋላ ሴሪንቶሳውያን የተባለውን አንጃ የመሠረተው ለስሙ ልቦለድ የተከበረ ስልጣንን በመፈለግ ስሙን ቅድመ ቅጥያ አደረገ።
Church History (Eusebius) > Book VII(7) Chapter 25 Number 2

በ 363 የተካሄደው የሎዶቅያ ጉባኤ የዮሐንስን ራእይ በጉባኤ ደረጃ ውድቅ አድርጓታል፥ "Synod of Laodicea Canon 60" ተመልከት! አውሳብዮስ ደግሞ የዮሐንስ ራእይ ውድቅ ከተደረገባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ እንደሆነ ተናግሯል፦
"ውድቅ ከተደረጉ መጻሕፍት መካከል ደግሞ የጳውሎስ ሥራ፣ ኖላዊ ዘሔርሜንስ ተብሎ የሚጠራው፣ የጴጥሮስ ራእይ የግድ ይቆጠራሉ፥ በተጨማሪም የበርናባስ መልእክት እና ዲድስቅሊያ እንደነዚ ያሉት እና እኔ እንዳልኩት የዮሐንስ ራእይ ነው"።
Church History (Book III(3) Chapter 25 Number 4)

የፐሺታ(ቬሺታ) ቀኖና የሚባለው ቀኖና በ 3ኛ ክፍለ ዘመን ከግሪክ ወደ ዐረማይስጥ የተዘጋጀ ሲሆን ራእይ ዮሐንስን አያካትትም። በጣም ስመ ጥር እና ዝነኛ ኮዴክስ ቫቲካነስ የዮሐንስን ራእይ አያካትትም። ከቤተክርስቲያን አበው መካከል ዲዮናስዩስ ዘእስክንድርያ፣ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ጂሊየስ አፍሪካነስ፣ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ራእይ ዮሐንስን አይቀበሉም ነበር፦
"ከእኛ በፊት የነበሩት አንዳንዶቹ መጽሐፉን ወደ ጎን በመተው ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገዋል"።
Church History (Eusebius) > Book VII(7) Chapter 25 Number 1

A New Translation with Introduction and Commentary" የተባለው ማብራሪያ ራእየ ዮሐንስ በዲዮናስዮስ፣ በታላቁ ባስልዮስ፣ በጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ በዮሐንስ አፈወርቅ ዘንድ ከተቀጠፉ ሥራዎች ጋር እንደሚታይ ተናግሯል፦
"ራእይ ቀኖናዊ ጽሑፎች ባልሆኑ ስብስቦች ውስጥም ተቀምጧል፥ በዲዮናስዮስ፣ በታላቁ ባስልዮስ፣ በጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ በዮሐንስ አፈወርቅ እና በሌሎች ጸሐፊያን ከተቀጠፉ ሥራዎች ጋር ይታያል"።
Revelation: A New Translation with Introduction and Commentary. Page 145

የፕሮቴስታንት ሐዳሲያን ማርቲን ሉተር፣ ዮሐንስ ካልቪን እና ሉድሪች ዝውንግሊ የራእይን መጽሐፍ አይቀበሉም ነበር።
"አንቲሌ ጉሜና"antile gomena" የሚለው ቃል "አንቲሌጉሜንያ" ἀντιλεγόμενα ከሚል ቃል የመጣ ነው፥ "አንቲሌ ጉሜና" የሚባሉት በሁሉም የቀኖና ጉባኤ ጭቅጭቅ ያለባቸው የአዲስ ኪዳን 7 መጻሕፍት ሲሆኑ ከሰባቱ አንዱ ራእይ ዮሐንስ ነው።
የዮሐንስን ራእይ ታሪካዊ ዳራ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ካየን ዘንዳ በዮሐንስ ራእይ ላይ በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ ታይታለች፦
ራእይ 17፥3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶች እና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።

የዚህችን ሴት ማንነት ከማወቃችን በፊት ሰባት ራሶች እና አሥር ቀንዶች ስላሉት ስለ ቀዩ አውሬ እንመልከት!
"አውሬ" ማለት "ጨካኝ" "በላተኛ" "ረጋጭ" የሚል ጠባይ ሲኖረው በፍካሬአዊ "ጨካኝ መንግሥት" ያመለክታል፥ ለምሳሌ፦ "አራት ታላላቅ አራዊት" ማለት "አራት የምድር መንግሥታት" ለማመልከት መጥቷል፦
ዳንኤል 7፥3 አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ።
ዳንኤል 7፥17 እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው።

እነዚህ አራት መንግሥታት የፋርስ፣ የባቢሎን፣ የግሪክ እና የሮምን መንግሥታት ናቸው። ይህ ከተረዳን ቀዩ አውሬ የሮም መንግሥት ሲሆን ሰባት ራሶቹ ሰባቱ የሮም ተራሮች ናቸው፦
ራእይ 17፥9 ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው።

ሰባት ራሶቹ ሰባቱ የሮም አላውያን ነገሥታት ናቸው፥ አምስቱ የወደቁት ጂሊየስ ቄሳር፣ አውግስጦስ ቄሳር፣ ጢባርዮስ ቄሳር፣ ካልጉላስ ቄሳር እና ክላውዲዮስ ቄሳር ናቸው፦
ራእይ 17፥10 ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፥ አምስቱ ወድቀዋል። አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።

"አንዱም አለ" የተባለው ሴሪንቶስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ኔሮ ቄሳር ሲሆን 7ኛው ወደ ፊት የሚያንሰራራው የሮም መንግሥት ንጉሥ ነው፦
ራእይ 17፥11 የነበረው እና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል።

ከሰባቱ ራሶች አንዱ የሆነው እራሱ ስምንተኛ ሆኖ ወደፊት ይነሳል። በቀዩ አውሬ ላይ የተቀመጠችው ሴት በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠች ስትሆን የውኃዎቹ ትርጉም ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ አሕዛብ፣ ቋንቋዎች ናቸው፦
ራእይ 17፥1 ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ።
ራእይ 17፥15 ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ አሕዛብ፣ ቋንቋዎች ናቸው።

ይህቺ ሴት የታጨላትን ወንድ ትታ ከሮም መንግሥት ነገሥታት ጋር ጎልምታለች፥ በግምባርዋ ምሥጢር የሆነ ስም "ታላቂቱ ባቢሎን" የሚል ተጽፎዋል፦
ራእይ 17፥5 በግምባርዋ ምሥጢር የሆነ ስም፦ "ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎች እና የምድር ርኵሰት እናት" ተብሎ ተጻፈ።

"ባቬል" בבל የሚለው የዕብራይስጥ ቃል፣ "ባቤል" בבל የሚለው የዐረማይስጥ ቃል፣ "ባቢሎን" የሚለው የግዕዝ ቃል ትርጉማቸው "ድብልቅል" "ምስቅልቅል" ማለት ሲሆን ይህቺ ሴት የሙሽራውን ትምህርት ከዐረማዊ ትምህርት በመቀየጥ፣ በመደባለቅ፣ በማመሰቃቀል የጋለሞታዎች እናት ናት፥ እውነተኛ የኢየሱስን ተከታዮች በመግደል እና በማስገደል በደማቸው ስለሰከረች የምድር ርኵሰት እናት ናት፦
ራእይ 17፥6 ሴቲቱም በቅዱሳን ደም እና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት።

ይህቺ ሴት ማን ናት? ኢንሻላህ ይቀጥላል.....

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም