ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
"ሥሉስ አምላክ" በሚል ትምህርት ተለቋል። “ሥሉስ” ማለት “ሥስት”three" ማለት ሲሆን "ሥሉስ አምላክ" ማለት "ሦስት አምላክ" ማለት ነው። ሥላሴአውያን "አምላክ ሦስት ነው" ብለው በትውፊታቸው ማስቀመጣቸው ዳሰናል። ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/iZuSQVwoI3A?si=8wQKlLznMBEH-fOd

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
የአሏህ እጆች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

38፥75 አሏህም «ኢብሊሥ ሆይ! "በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት" ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

አምላካችን አሏህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል የራሱ ባሕርያት አሉት፥ እርሱን የሚመስል ምንም ነገር የለም፦
42፥11 የሚመስለው ምንም "ነገር" የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሚስል" مِثْل በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው "ከ" كَ የሚል መስተዋድድ "በጭራሽ" ማለት ነው፥ "ነገር" በሚለው ቃል ውስጥ ሁሉም ፍጡራን የሚካተቱ ሲሆኑ ከፍጡራን መካከል እርሱን የሚመስል ብጤ በጭራሽ የለም። እዚሁ አንቀጽ ላይ አሏህ "ሰሚ እና ተመልካች" እንደሆነ ተገልጿል፥ ሰውም "ሰሚ እና ተመልካች" እንደሆነ ሌላ አንቀጽ ላይ ተገልጿል፦
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

የአሏህ መስማት እና ማየት ከፍጡራን ጋር እንደማይመሳሰል እና እንደማይነጻጸር ሁሉ የፈጣሪ ባሕርዮት ከፍጡራን ጋር አይመሳሰለም አይነጻጸርም። ይህንን መረዳት ይዘን ቁርኣን ላይ አምላካችን አሏህ እጆች እንዳሉት ይናገራል፦
38፥75 አሏህም «ኢብሊሥ ሆይ! "በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት" ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

"ሁለት እጆች" ለሚለው የገባው "የደይየ" ِيَدَىَّ ሲሆን ሙሰና"dual" እንደሆነ ልብ አድርግ! አምላካችን አሏህ ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰሉ እጆች አሉት፥ የእርሱ እጆች ፍጥረታዊ ሳይሆኑ መለኮታዊ እንዲሁ ሰዋዊ ሳይሆኑ አምላካዊ ናቸው። የአሏህ እጆች ቀኝ ናቸው፦
ሚሽካቱል መሷሒብ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 30
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ አል ዓሲ እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ፍትኸኞች አሏህ ዘንድ በብርሃን መንበሮች ላይ ከአር ረሕማን በስ ተቀኝ በኩል ይሆናሉ፥ "ሁለቱም እጆቹ ቀኝ ናቸው"። وَعَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: إِنَّ الْمُقْسِطِينَ عِنْدَ اللَّهِ عَلَى مَنَابِرَ مِنْ نُورٍ عَنْ يَمِينِ الرَّحْمَنِ وَكِلْتَا يَدَيْهِ يمينٌ

"የሚን" يَمِين ማለት "ጠንካራ" "አውንታዊ" "ሙሉነት" "ኃይል" በሚል ትርጉም ይመጣል፥ ለምሳሌ፦ "የሚን" يَمِين ማለት "ኃይል" በማል በቁርኣን ውስጥ መጥቷል፦
69፥45 በ-"ኃይል" በያዝነው ነበር፡፡ لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِالْيَمِينِ
37፥93 በ-"ኃይል" የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡ فَرَاغَ عَلَيْهِمْ ضَرْبًا بِالْيَمِينِ

"ሸማል" شِّمَال ማለት "ደካማ" "አሉታዊ" "ጎዶሎነት" በሚል ትርጉም ይመጣል። በዐማርኛችን "በቀኝ አውለኝ" እና "ግራ ያጋባል" በሚል ዐውድ ቀኝ እና ግራ አውንታዊ እና አሉታዊ ነገር ለማመልከት ይመጣሉ፥ እሩቅ ስንሄድ "left" የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል "ደካማ"weak" ማለት ነው። ስለዚህ "የአሏህ እጆች ቀኝ ናቸው" ማለት "ጠንካራ፣ አውንታዊ፣ ሙሉ፣ ኃይል ናቸው" ማለት ነው እንጂ አሏህ ቀኝ እና ግራ የሆኑ እጆች አሉት፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 52 ሐዲስ 7
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ዐዘ ወጀል በፍርዱ ቀን ሰማያትን ይይዛል፥ ከዚያም በቀኝ እጁ ያረግና፦ "እኔ ንጉሡ ነኝ፥ ትዕቢተኞች የት አሉ? ኩሩዎች የት አሉ?" ይላል፥ ከዚያም ምድርን በግራ እጁ አድርጎ፦ "ትዕቢተኞች የት አሉ? ኩሩዎች የት አሉ?" ይላል። عَبْدُ اللَّهِ بْنُ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يَطْوِي اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ السَّمَوَاتِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ثُمَّ يَأْخُذُهُنَّ بِيَدِهِ الْيُمْنَى ثُمَّ يَقُولُ أَنَا الْمَلِكُ أَيْنَ الْجَبَّارُونَ أَيْنَ الْمُتَكَبِّرُونَ ثُمَّ يَطْوِي الأَرَضِينَ بِشِمَالِهِ ثُمَّ يَقُولُ أَنَا الْمَلِكُ أَيْنَ الْجَبَّارُونَ أَيْنَ الْمُتَكَبِّرُونَ ‏"‏ ‏.‏
"በቀኝ እጁ" እና "በግራ እጁ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! የእርሱን እጆች ትርጉም በመስጠት ሳናራቁጥ እና ከፍጡራን እጆች ጋር ሳናነጻጽር እርሱ በነገረን መሠረት እንቀበላለን። ወደ ባይብሉ ስንገባ ያህዌህ አምላክ ሰውን ከምድር አፈር ያበጀው በእጆቹ ነው፦
መዝሙር 119፥73 "እጆችህ" ሠሩኝ አበጃጁኝም። יָדֶ֣יךָ עָ֭שׂוּנִי וַֽיְכֹונְנ֑וּנִי
ዘፍጥረት 2፥7 ያህዌህ አምላክ ሰውን ከምድር አፈር "አበጀው"። וַיִּיצֶר֩ יְהוָ֨ה אֱלֹהִ֜ים אֶת־הָֽאָדָ֗ם עָפָר֙ מִן־הָ֣אֲדָמָ֔ה

"እጆች" የሚለው ቃል "እጅ" ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "ጭቃ" ማለት "የውኃ እና የአፈር ቅልቅል ነው። ፈጣሪ ሰውን ከጭቃ በእጁ ለውሶ ሠራው፦
ኢዮብ 10፥8 እጅህ ለወሰችኝ ሠራችኝም። יָדֶ֣יךָ עִ֭צְּבוּנִי וַֽיַּעֲשׂ֑וּנִי
ኢዮብ 33፥6 እኔ ደግሞ ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ። מֵ֝חֹ֗מֶר קֹרַ֥צְתִּי גַם־אָֽנִי׃

ፈጣሪ ሰውን ከጭቃ በእጆቹ ካበጀ እና ከሠራ እጆቹ ቀኝ እና ግራ ናቸው፥ ምክንያቱም ፈጣሪ ቀኝ እና ግራ ካለው ቀኝ እና ግራ እጆች አሉት፦
1ኛ ነገሥት 22፥19 ሚክያስም አለ፦ እንግዲህ የያህዌህን ቃል ስማ! ያህዌህ በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ "በቀኙ" እና "በግራው" ቆመው አየሁ። וַיֹּ֕אמֶר לָכֵ֖ן שְׁמַ֣ע דְּבַר־יְהוָ֑ה רָאִ֤יתִי אֶת־יְהוָה֙ יֹשֵׁ֣ב עַל־כִּסְאֹ֔ו וְכָל־צְבָ֤א הַשָּׁמַ֙יִם֙ עֹמֵ֣ד עָלָ֔יו מִימִינֹ֖ו וּמִשְּׂמֹאלֹֽו׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀኝ" ለሚለው የገባው ቃል "የሚን" יָמִין ሲሆን "ግራ" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "ሸሙል" שְׂמֹאול ነው። "ሠለስቱ ምዕት" ማለት በ 325 ድኅረ ልደት በኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡት 318 ሊቃውንት ናቸው፥ እነርሱም "ፈጣሪ እጅ አለው" ሲባል የታመነ የተረዳ ነው፥ የተናገርነው ሁሉ አለው። ነገር ግን አይመረመርም አይታወቅም" ብለዋል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 28 ቁጥር 30
“ለእግዚአብሔር ዓይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር እንዳለው የተነገረው ሁሉ ስለ እግዚአብሔር በከበሩ መጻሕፍት የተጻፈ ሁሉ የታመነ የተረዳ ነው፥ የተናገርነው ሁሉ አለው። ነገር ግን አይመረመርም አይታወቅም”።

እርማችሁን አውጡ! ሠለስቱ ምዕት ፈጣሪ እጅ እንዳለው እንቅጩን ፍርጥ አርገው ተናግረዋል። ለእግዚአብሔር እጆች እንዳሉት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ተናግሯል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 1 ቁጥር 62
“እግዚአብሔር እጆች እና ክንድ፣ ጥፍር እንዳለው ዕወቁ”።

ስለዚህ "አሏህ እጆች አሉት" ሲባል በደምሳሳው የምትተቹ ሰዎች መጽሐፋችሁ ላይ ያህዌህ እጆች እንዳሉት ስትረዱ ምን ይውጣችሁ ይሆን? ቀኝ ለአውንታዊ ግራ ለአሉታዊ ጉዳይ እንደሚውል በቅጡ ተረዱ፦
መክብብ 10፥2 የጠቢብ ልብ በስተ ቀኙ ነው፥ የሰነፍ ልብ ግን በስተ ግራው ነው።

"ልብ" ውሳጣዊ፣ ረቂቅ እና ምጡቅ ሆኖ ሳለ "የጠቢብ ልብ በስተ ቀኙ ነው፥ የሰነፍ ልብ ግን በስተ ግራው ነው" ማለት ስለ አቅጣጫ እየተናገረ ሳይሆን ስለ አውንታዊ እና አሉታዊ ጉዳይ እየተናገረ ነው። የመነቸከ ሙግት ከምትሟገቱ ይልቅ የፋፋና የዳበረ እንዲሁ የላመና የጣመ ሙግት ለማደራጀት እና ለማዋቀር መሞከር አይሻላችሁምን? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ኤሎሂም" በሚል ትምህርት ተለቋል። "ኤሎሂም" ማለት ትርጉሙ "አማልክት" ማለት ሲሆን ፈጣሪ “ኤሎሂም” ሲባል ምን ማለት ነው? "አማልክት" የተባሉት ሥላሴ ከሆኑ ሥላሴ አማልክት ናቸው? እነዚህ የመሳሰሉ እሳቦት ዳሰሳ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/DYDqQqemDFk?si=qYY0t9HgIv-F0cvi

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
ሰማይ እና ምድር

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

አምላካችን አሏህ ሰማይን ጭስ"gas" አርጎ ከፈጠራት በኃላ በጭስ ደረጃ እያለች ለእርሷ እና ለምድር፦ "ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ" አላቸው፥ እነርሱም፦ "ታዛዦች ኾነን መጣን" አሉ፦
41፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

አሏህ ሰማይ እና ምድርን «ኑ» ሲላቸው እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» ማለታቸው የሚያስቅ እና የሚያሳልቅ ከሆነ እንግዲያውስ ያህዌህ በባይብል ምድርን እና ሰማያትን ሲጠራቸው በአንድነት እንደሚቆሙ ይናገራል፦
ኢሳይያስ 48፥13 እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፥ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ። אַף־יָדִי֙ יָ֣סְדָה אֶ֔רֶץ וִֽימִינִ֖י טִפְּחָ֣ה שָׁמָ֑יִם קֹרֵ֥א אֲנִ֛י אֲלֵיהֶ֖ם יַעַמְד֥וּ יַחְדָּֽו׃

"በአንድነት" ለሚለው የገባው ቃል "የሕዳው" יַחְדָּֽו ሲሆን "አንድ ላይ"together" ማለት ነው፥ የሚጠራቸው መቼ ነው? በአንድ ላይ ሲቆሙ የሚቆሙት አየር ላይ ነው ወይስ ሥፍራ አላቸው? እንኳን ሰማይ እና ምድር ከዋክብትም ሲጠራቸው፦ "ፈጣሪያችን ወደ አንተ መጣን" ይላሉ፦
መጽሐፈ ባሮክ 3፥29(1980 ዕትም) "ይጠራቸዋል እርሱን የሚመስል ሌላ የለምና "ፈጣሪያችን ወደ አንተ መጣን" ይላሉ።
Book of Baruch 3፥35 when he calls them, they answer፦ "Here we are" they shine to delight their Creator"

"ወሒድ ይህ እኮ ፈሊጣዊ አገላለጽ"idiomatic expression" ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح ማለት "ፈሊጣዊ አገላለጽ" ማለት ነውና አሏህ ሰማይ እና ምድርን «ኑ» ሲላቸው እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» ማለታቸው የሚያስቅ እና የሚያሳልቅ ነገር ሳይሆን ኢስጢላሕ ነው። ቢያንስ ቢያንስ የራሳችሁ መጽሐፍ አታነቡምን? አለዚያ እንደዚህ በሰፈራችሁት ቁና መሰፈራችሁ አይቀርም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"እንፍጠር" በሚል ትምህርት ተለቋል። ፈጣሪ “እንፍጠር” ሲል ምን ማለት ነው? "እንፍጠር" ያለው ማን ነው? "እንፍጠር" ያለው ለእነማን ነው? በዚህ ዙሪያ ዳሰሳ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/EJA9f_jrPwE?si=ut1YQ8G7a4DatjVc

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
"ከእኛ እንደ አንዱ" በሚል ደርሥ ተለቊል፥ በነገረ ሥላሴ"triadology" ከሚጠቀሱ ተወዳጆች ጥቅሳት አንዱ ዘፍጥረት 3፥22 ነው። በዚህ ዙሪያ ዳሰሳ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/t8ZAOLTG-6A?si=OwC0Yl-DKEgRK32D

ያዳመጣችሁ ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!
ሐውቀላህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥73 «ከአሏህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን "እርሱ አሏህ ምስጉን ክቡር ነውና» አሉ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ

"መጅድ" مَجْد የሚለው ቃል "መጀደ" مَجَدَ ማለትም "አከበረ" "ከፍ አረገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ክብር" "ከፍታ" ማለት ነው። በቁርኣን ከተጠቀሱ የአሏህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-መጂድ” الْمَّجِيد ሲሆን “እጅግ በጣም የተከበረ” ማለት ነው፦
11፥73 «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን "እርሱ አሏህ ምስጉን ክቡር ነውና» አሉ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 48
አቡ ሑመይድ አሥ-ሣዒዲይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ ”ሰዎች፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በእርሶ ላይ እንዴት ረድኤት እናውርድ? አሉ፤ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አሏህ ሆይ! ረድኤትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ! በረከትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ! አንተ የተመሰገንክ እና የተከበርክ ነህ" አሉ። أَخْبَرَنِي أَبُو حُمَيْدٍ السَّاعِدِيُّ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُمْ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ قُولُوا اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ‏”‌‏.‏

ይህ አሏህ በአምልኮ ከፍ ከፍ ማድረግ "ሐውቀላህ" حَوْقَلَة ይባላል። ይህም ተዝኪራ "ላ ሀውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" لا حَوْلَ وَلا قُوَّةَ إِلا بالله ነው። "ላ ሀውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" ማለት "በአሏህ ቢሆን እንጂ ብልሃት ሆነ ኃይል የለም" ማለት ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 170
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "ከጀነት ሃብት አንዱን ሃብት ልጠቁምህን? አሉኝ። እኔም፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! አዎ" አልኩኝ። እርሳቸውም፦ "በአሏህ ቢሆን እንጂ ብልሃት ሆነ ኃይል የለም" ነው፥ አሉ"። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ قَالَ لِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ أَلاَ أَدُلُّكَ عَلَى كَنْزٍ مِنْ كُنُوزِ الْجَنَّةِ ‏"‏ ‏.‏ قُلْتُ بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ ‏.‏ قَالَ ‏"‏ لاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ ‏

"አሏሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ ወአሊ ሙሐመድ" ٱللّٰهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ

"ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም" صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ኑ እንውረድ" በሚል ደርሥ ተለቋል፥ በነገረ ሥላሴ"triadology" ከሚጠቀሱ ተወዳጆች ጥቅሳት አንዱ ዘፍጥረት 11፥6-7 ነው። በዚህ ዙሪያ ዳሰሳ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/Ihf-WhiGhHk?si=Sko8EK2kj8qupQBd

ያዳመጣችሁ ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!
"የአብርሃሙ ሥላሴ" በሚል ርእስ ዙሪያ ዳሰሳ እና ሐተታ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/GMhX99TrVJI?si=eeVZkONW3y3GIzvW

ያዳመጣችሁ ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!
ሶሉ ዐላ ነቢይና"ﷺ"

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡

94፥4 መወሳትህንም ለአንተ ከፍ አድርገንልሀል። وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ

አንድ ሙሥሊም በአዛን፣ በቂያም፣ በሸሀዳህ "ሙሐመድ የአሏህ መልእክተኛ ነው" ብሎ ያውጃል፥ በዚህም አምላካችን አሏህ መወሳት ለነቢያችን"ﷺ" ከፍ አድርጎላቸዋል። እንዲሁ ስማቸው ሲወሳ "ሶለላሁ ዐለይሂ ወሠለም" صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم በማለት መወሳትን ከፍ አድርጎላቸዋል፦
94፥4 መወሳትህንም ለአንተ ከፍ አድርገንልሀል። وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ

"ሶለላሁ ዐለይሂ ወሠለም" صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم ማለት "የአሏህ ረድኤት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን" ማለት ነው። ስለ ሶለዋት ከዚህ በፊት የተጻፈ መጣጥፍ አንብቡ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/3317

"አሏሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ ወአሊ ሙሐመድ" ٱللّٰهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ

"ሶለላሁ ዐለይሂ ወሠለም" صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ኤኻድ እና ያኺድ" በሚል ርእስ ዙሪያ ዳሰሳ እና ሐተታ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/t2OwjlluSN0?si=Mm8ABvNu3B3XMXlT

ያዳመጣችሁ ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!
የተባረከ ወር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥185 የረመዷን ወር በእርሱ ውስጥ ቁርኣን ለሰዎች መሪ፣ የመመሪያ ግልጽ ማስረጃ እና ፉርቃን ሲሆን የተወረደበት ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

አምላካችን አሏህ በቁርኣን ከተገለጹት ስሞቹ አንዱ "አል-ከሪም" الْكَرِيم ሲሆን ትርጉሙ "ቸሩ" "ለጋሱ" ማለት ነው፦
82፥6 አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ
27፥40 እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየውም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፥ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊፈትነኝ ቸረልኝ፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ነው፥ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው» አለ፡፡ فَلَمَّا رَآهُ مُسْتَقِرًّا عِندَهُ قَالَ هَـٰذَا مِن فَضْلِ رَبِّي لِيَبْلُوَنِي أَأَشْكُرُ أَمْ أَكْفُرُ ۖ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّي غَنِيٌّ كَرِيمٌ

"ከሪም" كَرِيم የሚለው ቃል እንደየ ዐውዱ ዘርፈ ብዙ እና መጠነ ሰፊ ትርጉም አለው፥ "የተባረከ" "የተከበረ" "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" የሚል ፍቺ አለው። ለምሳሌ፦ መልአኩ ጂብሪል "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦ 
81፥19 እርሱ የ-"ክቡር" መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ ዐውድ ላይ ጂብሪል "ክቡር" ለተባለበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን "ንኡድ"noble" ለማለት እንጂ "ለጋሽ" "ቸር" ለማለት ተፈልጎ አይደለም፥ በተመሳሳይ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ "ከሪም" كَرِيم ተብለዋል፦
69፥40 እርሱ የ-"ተከበረ" መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ ዐውድ ላይ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "ክቡር" ለተባሉበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን "ንኡድ"noble" ለማለት እንጂ "ለጋሽ" "ቸር" ለማለት ተፈልጎ አይደለም። ስለዚህ አንድ ምንነት ወይም ማንነት "ከሪም" كَرِيم ስለተባለ አሏህ ከተወሰፈበትን ወስፍ ጋር ማምታታት አግባብ አይደለም። ቁርኣን "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦ 
56፥77 እርሱ "የከበረ" ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ ቁርኣን "የተከበረ" ለተባለበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን ሌላ አንቀጽ ላይ በተለዋዋጭ ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ተብሏል፦
6፥155 ይህም ያወረድነው የኾነ "የተባረከ" መጽሐፍ ነው፡፡ وَهَـٰذَا كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ مُبَارَكٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ ቁርኣን "የተባረከ" ለተባለበት የገባው ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ሲሆን "ሙባረክ" እና "ከሪም" የቃላት ልዩነት እንጂ የአሳብ ልዩነት የላቸውም። አትክልቶችን እና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ የሚበቅልበት ውኃ "ሙባረክ" مُّبَارَك ተብሏል፦
50፥9 ከሰማይም "ቡሩክን" ውኃ አወረድን፡፡ በእርሱም አትክልቶችን እና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን፡፡ وَنَزَّلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً مُّبَارَكًا فَأَنبَتْنَا بِهِ جَنَّاتٍ وَحَبَّ الْحَصِيدِ

እዚህ አንቀጽ ላይ ውኃ "ቡሩክ(የተባረከ) ለተባለበት የገባው ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ሲሆን ሌላ አንቀጽ ላይ በተለዋዋጭ ቃል "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦
79፥30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا
79፥31 ውኃን እና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡ أَخْرَجَ مِنْهَا مَاءَهَا وَمَرْعَاهَا
26፥7 ወደ ምድርም በውስጧ "ከ"መልካም" በቃይ ሁሉ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን?፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا إِلَى الْأَرْضِ كَمْ أَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ كَرِيمٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መልካም" ለሚለው የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሙባረክ" እና "ከሪም" ተለዋዋጭ ቃላት እንደሆኑ ለመረዳት ከላይ የቀረቡት ናሙናዎች በቂ ማሳያ ናቸው። እዚህ ድረስ ከተግባባን የረመዷን ወር ቁርኣን የወረደበት ወር ነው፦
2፥185 የረመዷን ወር በእርሱ ውስጥ ቁርኣን ለሰዎች መሪ፣ የመመሪያ ግልጽ ማስረጃ እና ፉርቃን ሲሆን የተወረደበት ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

"ፉርቃን" فُرْقَان ማለት "እውነት ከሐሰት፣ ትክክሉን ከስህተት፣ መልካሙን ከክፉ የሚለይ ሚዛን" ማለት ነው። "ሸህሩ ረመዷን" شَهْرُ رَمَضَان ማለት "የረመዳን ወር" ማለት ነው፥ "ረመዷን" رَمَضَان ደግሞ የዘጠነኛው ወር ስም ነው። "ረመዷን" የወር ስም እንጂ የጦም ስም አይደለም፥ ነገር ግን ይህ ወር ቁርኣን የተወረደበት ወር በመሆኑ "ሸህሩ ሙባረክ" شَهْرُ مُّبَارَك ማለትም "የተባረከ ወር" ተብሏል፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 17
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የተባረከው ወር ረመዷን መጣላችሁ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَتَاكُمْ رَمَضَانُ شَهْرٌ مُبَارَكٌ

ከዚህ አንጻር "ረመዷን ሙባረክ" رَمَضَان مُّبَارَك የሚለውን በቋንቋዬ ተርጉሜ "የተባረከ ረመዷን" ብል የቃላት ልዩነት እንጂ የአሳብ ልዩነት ከሌለው "ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم ሲባል "መልካም ረመዷን" "የተከበረ ረመዷን" ብል የቃላት እንጂ የአሳብ ልዩነት የለውም። "ኢማን" إِيمَان የሚለውን ቃል ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ በቁናህ ታገኘዋለህ፥ ቅሉ ግን የኢማን ተለዋዋጭ ቃል "ዐቂዳህ" عَقِيدَة የሚለውን በስም መደብ ቁርኣን ውስጥ አታገኘውም። ነገር ግን ዐቂዳህ እያልን እንማራለን እናስተምራለን፥ "ሙባረክ" እና "ከሪም" የሚለውን በዚህ ስሌት እና ሒሣብ መረዳት ይቻላል። ስለዚህ "ረመዷን ሙባረክ" رَمَضَان مُّبَارَك እና "ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم ተለዋዋጭ ቃላት እስከሆኑ ድረስ መርጠን መጠቀም እንችላለን።

"አሏሁ አዕለም! ይህ ሙግት የቋንቋን ሙግት ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ሙግት ነው።

"ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የረመዷን ስጦታ

ረመዷን ሙባረክ ያ ሙሥሊሙን ወሙሥሊማት!

በ 18 አርስት የተሰደረ መጣጥፍ በረመዷን ወር እንካችሁ ብለናል። ሊንኩን በማስፈንጠር ያግኙት!

1. ሶውም
https://tttttt.me/Wahidcom/3136

2. የጦም ትሩፋት
https://tttttt.me/Wahidcom/3470

3. ረመዷን
https://tttttt.me/Wahidcom/2727

4.. የረመዷን ወር
https://tttttt.me/Wahidcom/3107

5. የክርስትና ጦም
https://tttttt.me/Wahidcom/3176

6. የጨረቃ አቆጣጠር
https://tttttt.me/Wahidcom/2717

7. ጨረቃ እና ኮከብ
https://tttttt.me/Wahidcom/2360

8. የሚታሰሩ ሰይጣናት
https://tttttt.me/Wahidcom/2724

9. ሡሑር
https://tttttt.me/Wahidcom/2726

10. ተራዊህ
https://tttttt.me/Wahidcom/833

11. ኢዕቲካፍ
https://tttttt.me/Wahidcom/2286

12. ለይለቱል ቀድር
https://tttttt.me/Wahidcom/2289

13. መሓላ እና ማካካሻው
https://tttttt.me/Wahidcom/2336

14. ጦመኛ
https://tttttt.me/Wahidcom/3120

15. የተባረከ ወር
https://tttttt.me/Wahidcom/3707

16. ዘካቱል ማል
https://tttttt.me/Wahidcom/3126

17. ዘካቱል ፊጥር
https://tttttt.me/Wahidcom/3156

18. ተሀጁድ
https://tttttt.me/Wahidcom/3152

ሁሉም ቦታ ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ አሰራጩ!

ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
የአሏህ ምርጫ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥13 አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል፡፡ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ

"ኢንቲኻብ" اِنْتِخَاب ማለት "ምርጫ"election" ማለት ነው፥ ኢንቲኻብ እራሱ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ እና "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ።
፨ "ሹሩጢይ" شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ"conditional" ማለት ሲሆን በጥቅሉ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ ምርጫ"conditional election" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ አደም በሠራው ኃጢአት "ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፥ ለእኛ ባትምረን እና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን" ብሎ ተጸጸተ፦
7፥23 «ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፥ ለእኛ ባትምረን እና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡ قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ

አደም ተጸጽቶ በንስሓ ወደ አሏህ ሲመለስ አሏህ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፥ እነሆ አምላካችን አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፦
2፥37 አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ፡፡ በእርሱ ላይም ጌታው ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፥ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ فَتَلَقَّىٰ آدَمُ مِن رَّبِّهِ كَلِمَاتٍ فَتَابَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّهُ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

አደም ተጸጽቶ ንስሓ ወደ አሏህ በመግባቱ አሏህ ጸጸትን በመቀበል መረጠው፦
20፥122 ከዚያም "ጌታው መረጠው" ከእርሱም ጸጸቱን ተቀበለው መራውም፡፡ ثُمَّ اجْتَبَاهُ رَبُّهُ فَتَابَ عَلَيْهِ وَهَدَىٰ

"ጌታው መረጠው" የሚለው ይሰመርበት! ማንኛውም ሰው ከነበረበት ኩፍር ወይም ሺርክ አሊያም ዘንብ ወደ አሏህ በንስሓ ቢመለስ አሏህ ወደ ራሱ ለጀነት ይመርጠዋል፦
42፥13 አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል፡፡ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ

"አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል" የሚለው "ዓም" ሆኖ የመጣ ነው፥ "ዓም" عَامّ ማለት "ጥቅል"general" ማለት ነው። ነገር ግን "አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል" የሚለው ዓም "የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል" በሚል "ኻስ" ሆኖ እዛው ላይ መጥቷል፥ "ኻስ" خَاصّ ማለት "ተናጥል"specifical" ማለት ነው። መመራትን ሰው የሚያገኘው በማመን መሆኑ "ኻስ" ሆኖ የሚመጣ ነው፦
22፥54 አሏህ እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ "መሪ" ነው፡፡ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

"እነዚያን ያመኑትን" የሚለው ይሰመርበት! ያላመነው እና ንስሓ ያልገባ ሰው የሸይጧን ተከታይ ነው፥ ሸይጧን የተከተለውን ሰው ወደ ጀሀነም ይመራዋል፦
22፥4 "እነሆ! የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል፡፡ ወደ ነዳጅ እሳት ስቃይም ይመራዋል" ማለት በእርሱ ላይ ተጽፏል፡፡ كُتِبَ عَلَيْهِ أَنَّهُ مَن تَوَلَّاهُ فَأَنَّهُ يُضِلُّهُ وَيَهْدِيهِ إِلَىٰ عَذَابِ السَّعِيرِ

ሸይጧን ወደ ጀሀነም የሚመራው ሰው አሏህ ለጀነት ያልመረጠው በገዛ ፈቃዱ ሸይጧንን በመከተሉ ነው፥ ይህ የእኛ ጣልቃ ገብነት እና ድርሻ ያለበት የአሏህ ምርጫ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ ይባላል።
፨ "ገይሪ ሹሩጢይ" غَيْرِ شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ አልባ"unconditional" ማለት ሲሆን በጥቅሉ "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ አልባ ምርጫ"unconditional election" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፦
28፥68 ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ምርጫ የላቸውም፡፡ አሏህ ከማይግገባው ሁሉ ጠራ፡፡ ከሚያጋሯቸውም ላቀ፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

"የሚሻውን ይፈጥራል" በሚል ኃይለ ቃል "ይመርጣል" የሚለው ቃል አሏህ የሚሻውን ሰው፣ የሚሻውን እንስሳ፣ የሚሻውን አታክልት፣ የሚሻውን ማዕድን አርጎ መፍጠሩ የእርሱ ሁኔታዊ አልባ ምርጫ ነው፥ "ለእነርሱ ምርጫ የላቸውም" ማለት ፍጡራን "ይህንን ሆኜ ልፈጠር" የሚል ምርጫ የላቸውም። ወንድነት እና ሴትነት የእኛ ምርጫ ሳይሆን የእርሱ ምርጫ ብቻ ነው፦
42፥49 የሰማያትና የምድር ንግሥና የአሏህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፤ ለሚሻው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ወንዶችን ይሰጣል፡፡ لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ

"የሚሻውን ይፈጥራል" በሚል ኃይለ ቃል "ለሚሻው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ወንዶችን ይሰጣል" የሚለው ቃል ሴት መሆን እና ወንድ መሆን የአሏህ ሁኔታዊ አልባ ምርጫ ነው፥ የእኛ ምርጫ፣ ድርሻ፣ ፈቃድ ስለሌለበት ወንድነት እና ሴትነት ቅጣት እና ሽልማት አሊያም ተጠያቂነት የለበትም። አምላካችን አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፦
40፥7 እነዚያ "ዙፋኑን የሚሸከሙት" እና እነዚያ በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ
22፥75 አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፥ ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል። አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

"ከሩቢዩን" كَرُوبِيُّون የሚባሉት መላእክት የአሏህን ዐርሽ የሚሸከሙ ሲሆን በዐርሹ ዙሪያ ካሉት መላእክት ወደ ሰዎች የሚልካቸው መላእክት የእርሱ ሁኔታ አልባ ምርጫ ነው። "ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል" ስለሚል አሏህ ከሰዎች ለመልእክተኛነት መምረጡ ይህ የእርሱ ሁኔታ አልባ ምርጫ ነው፦
2፥105 አሏህም በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ وَاللَّهُ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
3፥74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አሏህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ

አሏህ አንድ ሰው በነቢይነት ቢመርጠው ሆነ ባይመርጠው ሽልማት እና ቅጣት አሊያም ተጠያቂነት ስለሌለበት ይህ "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ነው።
የአሏህን ምርጫ "አሚን" ብሎ መቀበል ከአርካኑል ኢማን ክፍል የሆነውን ቀደርን መቀበል ነው፥ አሏህ የእርሱን ምርጫ "አሚን" ብለው ከሚቀበሉት ምእመናን ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቁወቱል ኢማን

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

92፥6 በመልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ። وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ

"ቁዋህ" قُوَّة የሚለው ቃል "ቀዊየ" قَوِيَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ኃይል" ማለት ነው፥ "ኢማን" إِيمَٰن የሚለው ቃል "አሚነ" أَمِنَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው። በጥቅሉ "ቁወቱል ኢማን" قُوَّة الإِيمَان ማለት "የእምነት ኃይል" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ትልቁ የኢማን ቅርንጫፍ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፥ ትልቁ ቅርንጫፍ “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ማለት ነው። ትንሹ ደግሞ ከመንገድ ላይ እንቅፋት ማስወገድ ነው፥ ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏

"ሐያእ" حَيَاء ማለት "ዓይናፋርነት" "ጨዋነት" ማለት ነው፥ ሐያእ ከኢማን ነው። ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 115
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሐያእ ከኢማን ነው፥ ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል። ብልግና ከብሉሽነት ነው፥ ብሉሽነት ወደ እሳት ይመራል”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْحَيَاءُ مِنَ الإِيمَانِ وَالإِيمَانُ فِي الْجَنَّةِ وَالْبَذَاءُ مِنَ الْجَفَاءِ وَالْجَفَاءُ فِي النَّارِ ‏

"በዛእ" بَذَاء ማለት ደግሞ "ዓይናውጣነት" "ብልግና" ማለት ነው፥ ብልግና ከብሉሽነት(ኩፍር) ሲሆን ኩፍር ወደ እሳት ይመራል። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" መልካሚቱም እምነት ናት፦
92፥6 በመልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ። وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ
92፥7 ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْيُسْرَىٰ

"ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه በምትባለው መልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ አሏህ መልካም ሥራን ያገራለታል፥ "ዩሥር" يُسْرَىٰ ማለት "ቀላል" "ገር" "መልካም" ማለት ሲሆን ኢማን ወደ ጀነት የሚያመራው በመልካም ሥራ ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የምትለዋን መልካሚቱን እምነት ሰምቶ የካደ አሏህ መልካም ሥራን ያከብድበታል፦
92፥9 በመልካሚቱ እምነት ያሰተባበለም። وَكَذَّبَ بِالْحُسْنَىٰ
92፥10 ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْعُسْرَىٰ

"ዑሥራ" عُسْرَىٰ ማለት "ከባድ" "ሸካራ" "ክፉ" ማለት ሲሆን ኩፍር ወደ እሳት የሚመራው በመጥፎ ሥራ ነው። ኢማን የሚጨምር እና የሚቀንስ ነው፦
8፥2 ፍጹም ምእምናን እነዚያ አሏህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ ኢማን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
"አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ ኢማን የሚጨምሩላቸው" የሚለው ይሰመርበት! በኢማም አቡ መንሱር አል ማቱሪዲይ የተቀመረው ማቱሪዲያህ የሚባለው ስሑት ዐቂዳህ፦ "ኢማን የማይጨምር እና የማይቀንስ ቋሚ ነው" የሚል እሳቤ በዚህ ጥቅስ ድባቅ ይገባል። ኢማኑ በአሏህ አንቀጾች እየጨመረ የሚሄድ ሙእሚን አሏህ ዘንድ ደረጃዎች አሉት፦
8፥4 እነዚያ በእውነት አማኞች እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምሕረት እና የከበረ ሲሳይም አላቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

"ደረጃት" دَرَجَات የሚለው ቃል "ደረጃህ" دَرَجَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን አሏህ ዘንድ ጀናህ መቶ ጀረዎች አሏት፥ ተጀናህ ከፍተኛ ደረጃዋ ፊርደውሥ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4474
ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰማው ብሎ እንደተረከው፦ "እርሳቸውም አሉ፦ "ጀናህ መቶ ጀረዎች አሏት፥ ደረጃዎቿም ያላቸው እርቀት ልክ የሰማይ እና የምድር እርቀት ያክል ነው። ከፍተኛ ደረጃዋ ፊርደውሥ ነው፥ أَنَّ مُعَاذَ بْنَ جَبَلٍ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ "‏ الْجَنَّةُ مِائَةُ دَرَجَةٍ كُلُّ دَرَجَةٍ مِنْهَا مَا بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ وَإِنَّ أَعْلاَهَا الْفِرْدَوْسُ

አማኞች በእምነት የሚሠሩት መልካም ሥራ በሚሠሩት መልካም ሥራ መጠን የተለያየ ደረጃዎችን በጀነት ውስጥ ያገኙበታል፦
20፥75 በጎ ሥራዎችን በእርግጥ የሠራ ምእመን ኾኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለእነርሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አላቸው፡፡ وَمَن يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولَـٰئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَىٰ
3፥163 እነርሱ አላህ ዘንድ ባለ ደረጃዎች ናቸው፡፡ አላህም የሚሠሩትን ነገር ተመልካች ነው፡፡ هُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِمَا يَعْمَلُونَ
6፥132 ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አላቸው፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ
46፥19 ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አላቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው፥ እነርሱም አይበደሉም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۖ وَلِيُوَفِّيَهُمْ أَعْمَالَهُمْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

"ጀናህ" جَنَّة በ "ታ" ة መርቡጧህ በነጠላ ሲሆን አጠቃላይ ጀነትን ያመለክታል፥ በአጠቃላዩ ጀነት ውስጥ ለመግባት ቁልፉ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ሲሆን በጀነት ውስጥ ያሉትን ጀረጃዎች ውስጥ ለመግባት እና ለመመንዳት መልካም ሥራ ያስፈልጋል። በጀነት ውስጥ ያሉት መቶ የተለያዩ ደረጃዎች እራሱ "ጀናት" جَنَّات‎ ተብለዋል፥ "ጀናት" جَنَّات‎ በ "ታ" ت መፍቱሓህ ሲሆን በብዜት "ጀነቶች" "ገነቶች" ማለት ነው። እነዚህ የተለያየ ደረጃዎች የሆኑ ጀነቶች አምነው መልካም ለሚሠሩ የሚሰጥ ምንዳ፣ ትሩፋት፣ ወሮታ፣ ስርጉት፣ ትርሲት ነው፦
31፥8 እነዚያ ያመኑ እና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ "ገነቶች" አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتُ النَّعِيمِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ገነቶች" ለሚለው የገባው በብዙ ቁጥር "ጀናት" جَنَّات‎ እንደሆነ ልብ አድርግ! እያንዳንዱ ደረጃ "ጀነቱል ዐድን" جَنَّةُ العَدْن "ጀነቱ አን-ነዒም" جَنَّةُ النَّعِيمِ "ጀነቱል መእዋ" جَنَّةُ المَأْوَىٰ "ጀነቱል ፊርደውሥ" جَنَّةُ الفِرْدَوْسُ እየተባለ ይጠራል። አምላካችን አሏህ የኢማንን ኃይል ተረድተው መልካም ሥራ ከሚሠሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም