ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነቢዩ ኢስማዒል

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥54 በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ *መልክተኛ ነቢይም ነበር*፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا

“ኢስማኢል” إِسْمَٰعِيْل የሚለው የዐረቢኛው ቃል የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ኢስማ” إِسْم ማለት “ሰማኝ” ማለት ሲሆን “ኢል” َٰعِيْل ማለት “አምላክ” ማለት ነው፤ “አምላክ ጸሎቴን ሰማኝ” ማለት ነው፤ ኢብራሂም ወደ አላህ ልመናው፦ “ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ” የሚል ነበር፤ አላህም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰረው፤ በዚህ ምክንያት “ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና” አለ፦
37፥100 *ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ*፡፡ رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
37፥101 *ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው*፡፡ فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢ
14፥39 «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ *ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ* አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ *ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና*፡፡ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي وَهَبَ لِي عَلَى الْكِبَرِ إِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ ۚ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ

አላህ ወደ ኢስማዒል ወሕይ አውርዷል፤ አላህ ስለ ኢስማኢል ሲናገር “በኢስማዒልም ላይ በተወረደው አመንን በሉ” በማለት ግህደተ-መለኮት ወርዶለት እንደነበር ይናገራል፦
3፥84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም፣ በኢብራሂምና *በኢስማዒልም*፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ *በተወረደው*፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው *አመንን*፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» *በል*፡፡ قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «በአላህ እና ወደኛ በተወረደው ወደ ኢብራሂምም *ወደ ኢስማዒል* እና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም *በተወረደው* በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከእነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን *አመንን*፤ እኛም ለእርሱ ለአላህ ታዛዦች ነን» *በሉ*፡፡ قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
4፥163 እኛ ወደ ኑሕ እና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ *ወደ ኢስማዒልም*፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም *አወረድን*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا

ኢስማዒልን መልክተኛ ነቢይም ነበር፦
19፥54 በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ *መልክተኛ ነቢይም ነበር*፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا
19፥55 ቤተሰቦቹንም *በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር*፡፡ እጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡ وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُ بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِ مَرْضِيًّا

“እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና” ይለናል፤ የትኛውን ቀጠሮ አክባሪ ነው? ይህም ቀጠሮ ኢብራሂም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፤ እርሱም «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፦
37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ *«ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ»* አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

እጌታውም ዘንድ ተወዳጅና ከመልካሞቹ የሆነ ይህ ልጅ አላህ ለኢብራሂም የሰጠው የበኩር ልጅ ነው፦
14፥39 «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ *ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ* አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና፡፡ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي وَهَبَ لِي عَلَى الْكِبَرِ إِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ ۚ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ

እዚህ አንቀጽ ላይ ከኢስሐቅ በፊት ኢስማዒል መጠቀሱ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ አላህ በልጅ ጉዳይ ኢብራሂም ያበሰረው ሁለት ጊዜ ነው፤ የመጀመሪያው፦ “ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው” የሚል ነው፦
37፥101 *ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው*፡፡ فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢا
በመቀጠል ሁለተኛው፦ “በኢስሐቅም አበሰርነው” የሚል ነው፦
37፥103 *በኢስሐቅም አበሰርነው*፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

“አበሰርነው” የሚለው ቃል አንድ ዐውድ ላይ ሁለቴ መምጣቱ ኢስሐቅ እና ከላይ የተጠቀሰው በዱዓ የመጣው ልጅ ይለያያሉ፤ በተጨማሪም “ወ” و የሚለው አርፉል አጥፍ ብስራቱ ሁለት ጊዜ መሆኑን ያሳያል፤ አንደኛው ረድፍ “ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅ” ሲሆን ሁለተኛው ረድፍ “በኢስሐቅም አበሰርነው” የሚለው ነው፤ ኢስሐቅ ደግሞ ኢብራሂም አላህን ለምኖ የተሰጠ ልጅ ሳይሆን አንወልድም ብለው ተስፋ በቆረጡበት የተበሰሩት ልጅ ነው፦
15፥53 «አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ *እናበስርሃለን*» አሉት፡፡ قَالُوا۟ لَا تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٍۢ
15፥54 *«እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ»* አለ፡፡ قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِى عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِىَ ٱلْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ
15፥55 «በእውነት *አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ بَشَّرْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْقَٰنِطِينَ
11፥71 ሚስቱም የቆመች ስትኾን አትፍራ አሉት፤ ሳቀችም፡፡ *በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በያዕቁብ አበሰርናት*፡፡ وَٱمْرَأَتُهُۥ قَآئِمَةٌۭ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَٰهَا بِإِسْحَٰقَ وَمِن وَرَآءِ إِسْحَٰقَ يَعْقُوبَ

ኢብራሂም በኢስሀቅ ሲበሰር፦ “እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ?” ማለቱ ለምኖ ያገኘው ልጅ ሳይሆን ያላሰበው ልጅ መሆኑ ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል፤ ኢብራሂም የተበሰረው በኢስሀቅ ብቻ ሳይሆን በልጅ ልጁ በያዕቁብም ነው፤ ኢብራሂም ኢስሀቅ ሳይታረድ ተርፎ የልጅ ልጁ ያዕቆብ እንደሚወለድ ካወቀ፤ ኢስሀቅ ያዕቁብ የሚባል ልጅ እንደሚኖረዉ አስቀድሞ ከተበሰረ ልጅህን እረድልኝ ብሎ ማዘዙ ፈተናው ትርጉም አልባ ይሆን ነበር፤ ምክንያቱም ልጅህን እረድልኝ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፤ ፈተና ትርጉም የሚኖረው ተፈታኙ የሚፈተነውን የማያውቅ ሲሆን ብቻ ነው፦
37፥106 ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْبَلَٰٓؤُا۟ ٱلْمُبِينُ
37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

በተጨማሪም አላህ ኢብራሂምንም በቃላት በፈተነው ጊዜ ተያይዞ ኢብራሂምና ኢስማኢል የአላህን ቤት መሠረቶቹን ከፍ በማድረግ እና አላህም፦ “ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ” ብሎ ያዘዘው ኢብራሂምና ኢስማኢል ነው፦
2፥124 *ኢብራሂምንም ጌታው በቃላት በፈተነው* እና በፈጸማቸው ጊዜ አስታውስ፤ «እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ» አለው፡፡ «ከዘሮቼም አድርግ» አለ፡፡ ቃል ኪዳኔ በዳዮቹን አያገኝም አለው፡፡ وَإِذِ ٱبْتَلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٍۢ فَأَتَمَّهُنَّ ۖ قَالَ إِنِّى جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامًۭا ۖ قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۖ قَالَ لَا يَنَالُ عَهْدِى ٱلظَّٰلِمِينَ
2፥127 *ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ *ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም* ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ *ስንል* ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

ይህ እርድ የሚካሄድበት ቦታ በመካ እንጂ በሻም አለመሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እንግዲህ ከእነርሱ የትውልድ መስመር በትንቢት ቃል ኪዳን የተገባላቸው የነብያት መደምደሚያ ነብያችን”ﷺ” መጥተዋል፦
2፥129 «ጌታችን ሆይ! *በውስጣቸውም ከእነርሱው የኾነን መልክተኛ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክ*፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» የሚሉም ሲኾኑ፡፡ رَبَّنَا وَٱبْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًۭا مِّنْهُمْ يَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
2፥151 *በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁና የሚያጠራችሁ፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ*፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ

በቁርአን ላይ ስለ ነቢዩ ኢስማዒል ያለውን ምልከታ ለእይታ ያክል ካየን ዘንዳ ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ነቢዩ ኢስማዒል በባይብል ላይ ያለውን ምልከታ ለእይታ ያክል እንመለከታለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነብዩ ኢስማዒል

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥54 በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ *መልክተኛ ነቢይም ነበር*፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا

ከነብያችን”ﷺ” በፊት የተከሰቱን የሩቅ ወሬዎች ቁርአን ላይ ያሉት ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አንዱ አምላክ አላህ ያወረደው ነው፤ ኢብራሂም እንዲህ ብለን “አበሰርነው” እያለን የሚተርክልን እራሱ ሁሉን ዐዋቂው አላህ ነው፦
25፥6 «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ ٱلَّذِى يَعْلَمُ ٱلسِّرَّ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ غَفُورًۭا رَّحِيمًۭا
11፥120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን *እንተርክልሃለን*፡፡ وَكُلًّا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ الرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِ فُؤَادَكَ ۚ وَجَاءَكَ فِي هَـٰذِهِ الْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
37፥101 *ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው*፡፡ فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢ
37፥103 *በኢስሐቅም አበሰርነው*፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

ነገር ግን የዘፍጥረት ትረካ የአምላክ ንግግር ሳይሆን በቶራህ ላይ የተጨመረ ታሪክ ነው፤ ይህንን ታሪክ የሚተርክልን ማን እንደሆነ አይታወቅም። “ቶራህ” תּוֹרָה የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “ሕግ” “ትዕዛዝ” “መመሪያ” “መርህ” ማለት ነው፣ ይህ ሕግ ለሙሴ የተሰጠው በ 1312 BC ሲሆን በዚህ ሕግ ላይ መጨመር ሆነ መቀነስ ክልክል ነው፦
ዘዳግም 4፥2 እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን *ትእዛዝ* ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ *አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም*።

ነገር ግን ከ 600 BC ተጀምሮ በ 400 BC ውስጥ “ፔንታተች” πεντάτευχος ተዘጋጀ፤ “ፔንታ” πεντά ማለት “አምስት” ማለት ሲሆን “ተች” τευχος ማለት ደግሞ “ጥቅል” ማለት ነው፤ አንድ የነበረውን መጽሐፍ ከፋፍለው አምስት አደረጉት፤ እነርሱም ዘፍጥረት፣ ዘጸአት፣ ዘሌዋውያን፣ ዘኁልቅ፣ ዘዳግም ናቸው፣ ዘፍጥረት ላይ ያለው ተራኪ ከ 600 BC ተጀምሮ በ 400 BC ያለ ታሪክ ዘጋቢ እንጂ ሙሴ ወይም ፈጣሪ የተናገረው አይደለም፤ ይህንን ለዘብተኛ ምሁራን ሆነ ጽንፈኛ ምሁራን ይስማማሉ፤ ከዚያም ባሻገር ከ 600 BC ተጀምሮ በ 400 BC የተዘጋጁት የመጀመሪያው “አሲል” أصیل ማለት “ሥረ-መሰረት”origin” የለም። ዛሬ ያለው ቀዳማይ እደ-ክታብ የግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX” ሲሆን ቅጂ ነው፤ የሙት ባህር ጥቅል የሚባሉትም ብጥስጣሽ ቅጂ እንጂ ኦርጅናል የሚባል ቃል የለም።

ያ ማለት ግን ውስጡ እውነታነት ያለው ቁም ነገር የለውም ማለት እንዳልሆነም አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ታሪክ ማስረጃ መሆን ባይችልም መረጃ ግን ይሆናል፤ ይህንን እሳቤ ይዘን ወደ ነብዩ ኢስማዒል ጉዳይ እንግባ፦

ነጥብ አንድ
“ኢሽማኤል”
“ኢሽማኤል” יִשְׁמָעֵאל‎ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ኢሽማ” שָׁמַע ማለት “ሰማኝ” ማለት ሲሆን “ኤል” אֵל ማለት “አምላክ” ማለት ነው፤ “አምላክ ጸሎቴን ሰማኝ” ማለት ነው፤ ይህ ስም የወጣበት ምክንያት አብራምም፦ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? ያለ ልጅ እሄዳለሁ” ብሎ ለለመነው ልመና መልስ ሲሆን “ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል” የሚል ምላሽ ነው፤ ሲወለድም፦ “ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ” በማለት የአብርሃም ልመና መሆኑን ያሳያል፦
ዘፍጥረት 15፥2 አብራምም፦ *አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ*፤ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው፡ አለ። አብራምም፦ *ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርሰኛል* አለ። እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን *ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል*።
ዘፍጥረት 17፥20 *ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ*፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፥ እጅግም አበዛዋለሁ፤ አሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።

ይህንን ስም ያወጣው ሰው ሳይሆን ፈጣሪ በመልአኩ ያወጣለት ስም ነው፤ ከዚያ አብርሃምም የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው፦
ዘፍጥረት 16፥11 የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ *ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ*፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
ዘፍጥረት16፥15 አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን *የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው*።
ነጥብ ሁለት
“የበኵር ልጅ”
ብዙ ሰዎች እስማኤል የአብርሃም ልጅ አይደለም፤ ጭራሽ አልተባረከም የሚል ሙግት አላቸው፤ ይህ የሚያሳየው ምን ያህል መጽሐፋቸውን እንደማያነቡት ነው፤ እስማኤል የአብርሃም ልጅና ዘር ስለመሆኑና ስለመባረኩ በቁና መረጃ ይኸው፦
ዘፍጥረት 17፥26 በዚያው ቀን አብርሃም ተገረዘ፥ *ልጁ እስማኤልም*።
ዘፍጥረት 16፥15 አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን *የልጁን ስም እስማኤል* ብሎ ጠራው።
ዘፍጥረት25፥9 *ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም* በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊ በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
ገላቲያ 4፥22 አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ *ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት* ተጽፎአልና።
ዘፍጥረት 21፥13 የባሪያይቱን ልጅ ደግሞ ሕዝብ አደርገዋለሁ፥ *ዘርህ ነውና*።
ዘፍጥረት 17፥20 *ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ*፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፥ እጅግም አበዛዋለሁ፤ አሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።

እስማኤል የአብርሃም የበኵር ልጅ ማለትም የመጀመሪያ ልጅ ነው፤ ምክንያቱም አብርሃምም ልጁ እስማኤልን ሲወልድ የሰማንያ ስድስት ዓመት ዕድሜ ነበረ፤ ይስሐቅን ሲወልድ ደግሞ የመቶ ዓመት ዓመት ዕድሜ ነበረ፤ ስለዚህ እስማኤል ይስሐቅን በአስራ አራት ዓመት ይበልጠዋል፦
ዘፍጥረት 16፥16 አጋር እስማኤልን ለአብራም በወለደችለት ጊዜ *አብራም የሰማንያ ስድስት ዓመት ሰው ነበረ*።
ዘፍጥረት 21፥5 አብርሃምም ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ *የመቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ*።

አብርሃም አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ነበሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ወልደውለታል፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ሲሆን፥ በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር አላደረገም፤ ነገር ግን ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ አስታውቋል፤ የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው፤ ይህንን ሕግ አብርሃም ጠብቋል፦
ዘፍጥረት 26፥5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን *ሕጌንም ጠብቆአልና*።
ዘዳግም 21፥15-17 *ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት*፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ *በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን*፥ ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት *ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው*።

ልጆቹ እስማኤልና ይስሐቅ ሲሆኑ ጽድቅና ፍርድ በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ አዟቸዋል፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ተፈጽሟል፦
ዘፍ 18፡18-19 ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ *የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹን እና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው*።

ነጥብ ሦስት
“የእርዱ ልጅ”
በሙሴ ሕግ አስቀድሞ የተወለደው የበኲር ልጅ ለእግዚአብሔር ይሆናል፤ የበኵር ልጅ በእርሱ ፋንታ እንስሳ ይታረዳል፦
ዘጸአት 13፥2 በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማሕፀንን የሚከፈት *በኵር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ የእኔ ነው*።
ዘጸአት 13፥12 ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ለይ፤ ከሚሆንልህ ከብት ሁሉ ተባት ሆኖ *አስቀድሞ የተወለደው ለእግዚአብሔር ይሆናል*።
ዘጸአት 13፥15 ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ *ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ፥ ነገር ግን የልጆቼን በኵር ሁሉ እዋጃለሁ*።

ይህንን የሙሴ ሕግ አብርሃም ፈጽሞታል፦
ዘፍጥረት 26፥5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን *ሕጌንም ጠብቆአልና*።
ዘፍጥረት 22፥16 እንዲህም አለው፦ እግዚአብሔር፦ በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ *አንድ ልጅህንም* አልከለከልህምና፤

“አንድ ልጅህን” የሚለው ይሰመርበት፤ አብርሐም አንድ ልጅ ብቻ ነው ያለው? በፍፁም ግን ሁለተኛ ልጅ እስኪመጣ ድረስ የበኲር ልጅ ለወላጅ አንድ ልጅ ነው፦
ዘካርያስ 12፥10 ሰውም *ለአንድያ ልጁ* እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም *ለበኵር ልጁ* እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።
ሉቃስ 7፥12 ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ የሞተ ሰው ተሸክመው አወጡ፤ እርሱም ለእናቱ *አንድ ልጅ* ነበረ፥ እርስዋም መበለት ነበረች፥ ብዙም የከተማ ሕዝብ ከእርስዋ ጋር አብረው ነበሩ።
ሉቃስ 9፥38 እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ መምህር ሆይ፥ ለእኔ *አንድ ልጅ* ነውና ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ።

እውን ይስሐቅ ቢሆን የእርዱ ልጅ አንድ ልጅህን የሚለው ትርጉም ይሰጣልን? ይስሐቅ ከመወለዱ በፊት አድጎ ዘር እንደሚኖረው ለአብርሃም ተነግሮታልም፤ ያውቃልም፦
ዘፍጥረት 17፥19 እግዚአብሔርም አለ፦ በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ *ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ* የዘላለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።

ታዲያ አብርሐም ልጁ ይስሐቅ ሳይወለድ ዘሩ እንደሚቀጥል እያወቀ ፈተና ነው ማለት ትርጉም ይኖረዋልን? ምክንያቱም ልጅህን እረድልኝ ፈተና ነው፤ ፈተና ትርጉም የሚኖረው ተፈታኙ የሚፈተነውን የማያውቅ ሲሆን ብቻ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ *እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው*፥ እንዲህም አለው፦ አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፦ እነሆ፥ አለሁ፡ አለ።
ነጥብ አራት
“የተስፋ ቃል”
እስማኤል በባይብል ነብይ መሆኑ አልተገለጠም፤ እርሱ ብቻ ሳይሆን ይስሐቅም ያዕቆብም ነብይ መሆናቸው አልተገለጠም፤ ስለዚህ ነብይ ነው ወይስ አይደለም ብለን አንሞግትም፤ ነገር ግን እንደ ነብይ አምላክ ከእስማኤል ጋር ነበረ፦
ዘፍጥረት 21፥20 *እግዚአብሔርም ከብላቴናው ጋር ነበረ*፤ አደገም፥ በምድረ በዳም ተቀመጠ፥ ቀስተኛም ሆነ።
ዘፍጥረት 39፥2 *እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ*፥
ዘጸአት 34፥28 በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት *ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ*፤
ኢያሱ 6፥27 *እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበረ*፤
1ኛ ሳሙኤል 3፥19 ሳሙኤልም አደገ፥ *እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ*፤
1ኛ ሳሙኤል18፥14 ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር፤ *እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ*።

አንድ ነብይ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር የሚሆነው ሊያናግረው ነው፤ ነብይ ማለት አምላክ የሚያናግረው ማለት ነው፤ እስማኤል እና እናቱ በፋራን ምድረ-በዳ ተቀመጡ፤ “ዐረብ” ማለት ትርጉሙ “ምድረ-በዳ” ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 21፥20 በ*ፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ*፤ እናቱም ከምድረ ግብፅ ሚስት ወሰደችለት።
ገላትያ 4፥25 ይህችም *አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ-ሲና ናት*፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።

“ደብር” ማለት “ተራራ” ማለት ነው፤ “አድባር” ማለት “ተራሮች” ማለት ነው፤ “ደብረ ሲና” ማለት “የሲና ተራራ” ማለት ነው፤ ሲና ዐረብ አገር እንዳለች ይህ ጥቅስ ያስረዳል፤ ፋራን ማለት መካ፣ መዲና እና ታቡክ እንደሆነ የታሪክ ምሁራን በመድብለ-ዕውቀት ላይ አስፍረዋል፤ ከዚያም ባሻገር የቂሳርያው አውሳቢዮስና የሮሙ ጄሮም ፋራን በዐረቢያ ውስጥ እንደምትገኝ በድርሳናቸው ውስጥ አስፍረዋል፦ “Eusebius of Caesarea, Onomasticon Biblical Dictionary (1971) Translation. pp. 1-75. entry for Pharan No 917“ ከዚህ ከዐረብ ቦታ ካለችው ከፋራን የአምላክ ቅዱስ እንደሚመጣ ትንቢት ነበረ፦
ዕንባቆም 3፥3 እግዚአብሔር ከቴማን፥ *ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል*። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።

“የእርሱ ቅዱስ”his holy one” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “ኤሎሃ” אֱל֙וֹהַ֙ ማለት “አምላክ” ማለት ሲሆን “የእርሱ ቅዱስ” ከአምላክ ለመለየት “ወ” וְ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፤ ይህ የአምላክ ቅዱስ “የቦው” יָב֔וֹא ማለትም “ይመጣል” በሚል በወደፊት ግስ ተተንብዮ ነበር፤ ይህ የአምላክ ቅዱስ ከፋራን የመጡት ነብያችን”ﷺ” ብቻ ናቸው፤ አይ ሌላ የአምላክ ቅዱስ ነው የመጣው አሊያም ወደ ፊት የሚመጣው ነው ከተባለ መረጃና ማስረጃ ማስቀመጥ ነው፤ ምን ይህ ብቻ ነብያችን”ﷺ” ከባልደረቦቻቸው ጋር በ 622 AD ያደረጉትን ስደት ቁልጭ እና ፍትንው ተደርጎ በትንቢት ተቀምጧል፦
ኢሳይያስ 21፥13-15 *ስለ ዓረብ የተነገረ ሸክም*፤ የድዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ውስጥ ታድራላችሁ። በቴማን የምትኖሩ ሆይ፥ *ወደ ተጠሙት ሰዎች ውኃ አምጡ እንጀራ ይዛችሁ የሸሹትን ሰዎች ተቀበሉአቸው*። *ከሰይፍ፥ ከተመዘዘው ሰይፍ፥ ከተለጠጠውም ቀስት ከጽኑም ሰልፍ ሸሽተዋልና*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ይፍረዱ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥47 የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ *አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ*፤ وَلْيَحْكُمْ أَهْلُ ٱلْإِنجِيلِ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فِيهِ

አምላካችን አላህ ለዒሣ ወንጌልን ሰጠው፥ በዚያ ወንጌል ውስጥ፦ “የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ” የሚል መመሪያ አለ፦
5፥46 በፈለጎቻቸውም ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን *አስከተልን፤ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሣጭ ሲሆን ሰጠነው*። وَقَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ ۖ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًۭى وَنُورٌۭ وَمُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَهُدًۭى وَمَوْعِظَةًۭ لِّلْمُتَّقِينَ
5፥47 የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ *አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ*። وَلْيَحْكُمْ أَهْلُ ٱلْإِنجِيلِ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فِيهِ

“ቀፈይና” قَفَّيْنَا ማለትም “አስከተልን” እና “አተይናሁ” آتَيْنَاهُ ማለትም “ሰጠነው” የሚሉት ያለቁ አላፊ ግስ ናቸው፤ “ልየሕኩም” َ لْيَحْكُم ማለትም “ይፍረዱ” የሚለው ትዕዛዛዊ ግስ መነሻ ላይ “ወ” وَ ማለትም “እና” የሚል አያያዥ መስተጻምር አለ፤ ያ ማለት “ይፍረዱ” የሚለው ትዕዛዛዊ ግስ “አስከተልን” እና “ሰጠነው” ከሚሉት ግስ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑ “ቁልና” قُلْنَا ማለትም “አልን” የሚል ቃል ሙሥተቲር አላፊ ሆኖ መጥቷል፥ “ሙሥተቲር” مُسْتَتِر ማለት በቃላት፣ በሃረግ እና በዓረፍተ-ነገር ተደብቆ የሚመጣ ግስ እና ተውላጠ-ስም ነው። ስለዚህ ‘’የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ አልን‘’ የሚል ፍቺ ይኖረዋል። ተፍሢሩል ጀላለይን በዚህ መልኩ ነው የፈሠረው፦
ተፍሢሩል ጀላለይን 5፥47
“እና”፦ *”የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ” አልን፥ “ይፍረዱ” የሚለው የቂርኣት ስልት “ሰጠነው” በሚለው ቀዳማይ ግስ በመስተጻምር ተያይዞ በመመራት የሚሟላ ነው”*።
{ وَ } قلنا { لِيَحْكُمَ أَهْلُ ٱلإنجِيلِ بِمَا أَنزَلَ ٱللَّهُ فِيهِ } من الأحكام وفي قراءة بنصب «يحكم» وكسر لامه عطفاً على معمول (آتيناه)

ለናሙና ያክል ሌላ ተጨማሪ ማሳያዎች ብንመለከት ነገሩን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፦
19:12 የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ *ያዝ*፣ ጥበብንም በሕጻንነቱ *ሰጠነዉ*። يَٰيَحْيَىٰ خُذِ ٱلْكِتَٰبَ بِقُوَّةٍۢ ۖ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْحُكْمَ صَبِيًّۭا

“ሑዚ” خُذِ ማለትም “ያዝ” የሚለቅ ትዕዛዛዊ ግስ ነው፤ “አተይናሁ” آتَيْنَاهُ ማለትም “ሰጠነው” የሚለው ቃል ደግሞ ያለቀ አላፊ ግስ ነዉ፣ “አተይናሁ” ከሚለው ቃል በፊት “ወ” وَ የሚል አያያዥ መስተጻምር አለ፤ ያ ማለት “ያዝ” የሚለው ትዕዛዛዊ ግስ “ሰጠነው” ከሚለው ግስ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑ “አልን” የሚል ሙሥተቲር አላፊ ሆኖ መጥቷል፣ ስለዚህ ‘’መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ አልነዉ‘‘’ የሚል ፍቺ እንደሚኖረው ሁሉ ከላይ ያለውንም በዚህ ሒሳብ እንረዳዋለን።
አላህ በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ሲናገር፦
2፥57 በእናንተም ላይ ደመናን አጠለልን፡፡ በናተም ላይ መንናን እና ድርጭትን አወረድን፡፡ *«ከሰጠናችሁም ጣፋጮች ብሉ»* አልበደሉንምም ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበር፡፡ وَظَلَّلْنَا عَلَيْكُمُ الْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْكُمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ ۖ كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ ۖ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَـٰكِن كَانُوا أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
አላህ መንናን እና ድርጭትን ጣፋጮች አድርጎ የሰጠው በሙሳ ዘመን እንደሆነ ቅቡል ነው፥ ግን “ከሰጠናችሁም ጣፋጮች ብሉ” የሚል ኃይለ-ቃል አለ። ያ ማለት “ከሰጠናችሁም ጣፋጮች ብሉ አልን” ይሆናል እንጂ “ብሉ” የተባለው በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ነው ብሎ ድርቅ ማለት እንደማይቻል ሁሉ “ፍረዱ” የተባለው በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ነው ብሎ ድርቅ ማለት አይቻልም፦
34፥10 ለዳውድም ከእኛ የኾነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው፡፡ *«ተራራዎች ሆይ! ከእርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ»* በራሪዎችንም ገራንለት፡፡ ብረትንም ለእርሱ አለዘብንለት፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا دَاوُودَ مِنَّا فَضْلًا ۖ يَا جِبَالُ أَوِّبِي مَعَهُ وَالطَّيْرَ ۖ وَأَلَنَّا لَهُ الْحَدِيدَ
34፥18 በእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን፡፡ በእርሷም ጉዞን ወሰንን፡፡ *«ጸጥተኞች ኾናችሁ በሌሊቶችም በቀኖችም ተጓዙ»*፡፡وَجَعَلْنَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ الْقُرَى الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا قُرًى ظَاهِرَةً وَقَدَّرْنَا فِيهَا السَّيْرَ ۖ سِيرُوا فِيهَا لَيَالِيَ وَأَيَّامًا آمِنِينَ

“ተራራዎች ሆይ! ከእርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ” እና “ጸጥተኞች ኾናችሁ በሌሊቶችም በቀኖችም ተጓዙ” በሚለው ትእዛዛዊ ግስ ውስጥ “አልን” የሚል ቃል በውስጠ ታዋቂነት እንዳለ ሁሉ “የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ” በሚለው ትእዛዛዊ ግስ ውስጥ “አልን” የሚል ቃል በውስጠ ታዋቂነት አለ።

ሲቀጥል “ባወረደው” ስለሚል አላህ ያወረደው ኢንጅል ወደ ዒሣ ነው። አላህ በኢንጅል የኢንጅልም ባለቤቶች ለሆኑት ለሐዋሪይዩን፦ “በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ” በማለት ተናግሯል፦
5፥111 ወደ *ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ» በማለት “ባዘዝኩ” ጊዜ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى ٱلْحَوَارِيِّـۧنَ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِى وَبِرَسُولِى

“ባዘዝኩ” የሚለው “አውሐይቱ” أَوْحَيْتُ ሲሆን “ባወረድኩ” ማለት ነው። “ወሕይ” وَحْى የሚለው ለአውሐይቱ የስም መደብ ነው። የኢንጅል ባለቤቶች ቀዳማይ የዒሣ ተከታዮቹ የሆኑት ሐዋርያት ናቸው፦
3፥52 ዒሳ ከእነርሱ ክሕደት በተሰማዉም ጊዜ፦ ወደ አላህ *ረዳቶቼ እነማን ናቸዉ? አለ፤ ሐዋሪያት፦ እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህም አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መሆናችንን መስክር” አሉ”*። فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ ሐዋርያቱ “አንሷር” أَنصَار መባላቸውን አስተውል። “ነስራኒይ” نَصْرَانِيّ የሚለው ቃል በነጠላ ሲሆን በብዜት ደግሞ “ነሷራ” نَصَارَىٰ ነው። ይህም ቃል “ነሰረ” نَصَرَ ከሚል ግስ መደብ ወይም “ነስር” نَصْر ከሚል ከስም መደብ የረባ ሲሆን “ረዳቶች” ማለት ነው።
ስለዚህ አላህ በኢንጂል፦ “የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ” ብሏል ማለት ነው እንጂ በቁርኣን ዘመን በቤተክርስቲያን አበው ውጥንቅጡ፣ ቅጥአንባሩ፣ መላቅጡ በወጣውን በግሪክ እደ-ክታባት”manuscripts” ፍረዱ እያለ በፍጹም አይደለም። ዱባና ቅል፥ አብቃቀሉ ለየቅል! እንደሚባለው ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢሥላም ይዞት የመጣው እሳቦት እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ አዲስ ርዕዮት እና ዐብዮት ነው። ቢመርህም ዋጠው!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ሳታማኻኝ ብላኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥58 *እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሠሩት ነገር በመዝለፍ የሚያሰቃዩ ዕብለትን እና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ*፡፡ وَالَّذِينَ يُؤْذُونَ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ بِغَيْرِ مَا اكْتَسَبُوا فَقَدِ احْتَمَلُوا بُهْتَانًا وَإِثْمًا مُّبِينًا

አንድ የክርስትና ስም ያለው ሰው ወንጀል ሢሠራ የሚጠየቀው ወንጀለኛው እራሱ እንጂ ሃይማኖቱ ክርስትና አንድ ቀን ግምት ውስጥ ገብቶ ዐያውቅም። በተቃራኒው አንድ የሙሥሊም ስም ያለው ሰው ወንጀል ሢሠራ የሚጠየቀው ወንጀለኛው እራሱ ብቻ ሳይሆን የሚከተለው ሃይማኖትም ዲኑል ኢሥላም ይጠየቃል። ለነገሩማ “አያ ጅቦ ሳታማኻኝ ብላኝ” ያለችዉ የአህያ ተረት ካልሆነ በስተቀር እሥልምናን በምን እናጠልሸው ነው። በአገራችን ውስጥ የሙሥሊም መምህራን አንድም ቀን የሌላ እምነት ጥላቻ ሲሰብኩ አሊያም "ግደሉ፣ ፍለጡ፣ ቁረጡ" ብለው ሳያስተምሩ በተቃራኒው እነ መምህር ምሕረተ-አብ፣ እነ መምህር ዘመድኩን፣ እነ መምህር ታሪኩ እሥልምናን ሲያበሻቅጡ እና ሲያነውሩ፥ ከዚያም ባሻገር ሙሥሊሞች መጤ እንደሆንን ለሕዝባቸው ሲሰብኩ አንድ ቀን ንግግራቸው ክርስትናን ይወክላል ብለን አምነን ዐናውቅም።

እረ እሩቅ ሳንሄድ ሞጣ ላይ መሣጂድ ሲቃጠሉ እና የሙሥሊሙ የንግድ ቤት ከክርስቲያኑ ተለይቶ ሲወድም፣ ሲዘረፍ እና ሲቃጠል ክርስትና "አውድሙ፣ ዝረፉ፣ አቃጥሉ" ብሏቸው ነው" ብለን አስበን ዐናውቅም። በአሁኑ ሰዓት ሻሸመኔ ላይ ያለው እልቂት ሆነ ሌላ ቦታ ላይ ያለው እልቂት የፓለቲካ እና የዘር መንስኤ እና የፓለቲካ እና የዘር ይዘት ያለው ሆኖ ሳለ ቀጣፊ የኦርቶዶክስ መምህራን እሥልምና በክርስትና ላይ እንደተነሳ ለማሳየት ሌላ አገር የተደረጉ ቪድዮችን እና ምስሎችን በማቃናበር የክርስቲያኖችን ኅሊና ለማቆሸሽ እና የሙሥሊሙን ሞራል ለማሳቀቅና ለማሸማቀቅ የሚያደርጉት እጅግ ሲበዛ ቅጥፈት ነው። እነዚህ ጭፍን መምህራን ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ጣታቸውን እሥልምና ላይ የሚቀስሩ እና ባገኙት አጋጣሚ እሥልምናን የሚወቅጡ ናቸው። በጥቅሉ ሙሥሊሙን ሁሉ ባልሠሩት ነገር በመዝለፍ የሚያሰቃዩ ዕብለትን እና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ፦
33፥58 *"እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሠሩት ነገር በመዝለፍ የሚያሰቃዩ ዕብለትን እና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ"*፡፡ وَالَّذِينَ يُؤْذُونَ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ بِغَيْرِ مَا اكْتَسَبُوا فَقَدِ احْتَمَلُوا بُهْتَانًا وَإِثْمًا مُّبِينًا

ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው። “ዐድል” عَدْل የሚለው ቃል “ዐደለ” عَدَلَ ማለትም “አስተካከለ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስተካከል” “ፍርድ” “ፍትሕ” ማለት ነው፥ “ዐዲል” عَادِل‎ ማለት “ፍትሓዊ” ማለት ሲሆን “ተዕዲል” تَعْدِيل‎ ማለት ደግሞ “ፍትሐዊነት” ማለት ነው። አምላካችን አላህ በፍትሕ ያዛል፥ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፦
16፥90 *አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ “ማስተካከል” ለሚለው ቃል የገባው “ዐድል” عَدْل መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። የፍትሕ ተቃራኒ ዙልም ነው፥ “ዙልም” ظُلْم የሚለው ቃል “ዞለመ” ظَلَمَ ማለትም “በደለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በደል” ማለት ነው። “ከሚጠላ ነገር ሁሉ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት!" ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፦
5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

አሁንም “አስተካክሉ” ለሚለው የገባው ቃል “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا መሆኑ ልብ በል። “ሕዝቦችን መጥላት” ወደ ፍትሕ አልባ ይገፋፋል፥ ፍትሕ ግን ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። በፍትሕ የሚጠላ ነገር ሁሉ ለአላህ ብሎ ጠልቶ መከልከል ከመበደል ይታደጋል። ፍትሕ ከራስ፣ ከወላጅ እና ከቅርብ ዘመድ በላይ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ፣ ከዝንባሌ የጸዳ፣ ሀብታም ወይም ድኻ ሳይል፣ አላህ ውስጠ ዐዋቂ ነው ብሎ በትክክል መቆም ነው፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት። ማዳላት የሚመጣው ዝንባሌን ከመከተል ስለሆነ “እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ” ብሎ ነግሯናል፥ “አህዋ” أَهْوَآء ማለትም “ዝንባሌ”inclination” ነው። ስለዚህ ሰውን ለዘሩ፣ ለብሔሩ፣ ለጎጡ፣ ለቡድኑ ብሎ መግደል የሚመጣው ከዝንባሌ ነው፥ አሏህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የገደለ ማንም ምንም ይሁን በሕግ አግባብ መጠየቅ እና መቀጣት አለበት። ኢሥላም ለጥፋት ቅጣት ይበይናል እንጂ በዝምድና፣ በቅርበት፣ በትውውቅ አያዳላም፥ ነቢያችን"ﷺ" ፦ "ወሏሂ! ልጄ ፋጢማ ስርቆት መፈጸሟን ካወቅኩ እጇን ከመቁረጥ ወደኋላ አልልም" ብለዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 29, ሐዲስ 16
ጃቢር እንደተረከው፦ "ከበኒ መኽዙም አንዲት ሴት ሰረቀች፥ ወደ ነቢዩ"ﷺ" መጣች እና በነቢዩን"ﷺ" ባለቤት በኡሙ ሠላማህ ሽምግና ጠየቀች። ነቢዩም"ﷺ" ፦ *"ወሏሂ! ልጄ ፋጢማ ስርቆት መፈጸሟን ካወቅኩ እጇን ከመቁረጥ ወደኋላ አልልም" አሉ"*። عَنْ جَابِرٍ، أَنَّ امْرَأَةً، مِنْ بَنِي مَخْزُومٍ سَرَقَتْ فَأُتِيَ بِهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَعَاذَتْ بِأُمِّ سَلَمَةَ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ وَاللَّهِ لَوْ كَانَتْ فَاطِمَةُ لَقَطَعْتُ يَدَهَا ‏"‏ ‏.‏ فَقُطِعَتْ ‏.‏

ስለዚህ ኢሥላም ፍትሓዊ ሃይማኖት ነው። ሙሥሊምን በኢሥላም መዝን እንጂ ኢሥላምን በሙሥሊም አትመዝን! እኔ ካጠፋሁኝ እኔን ቅጣኝ ወይም አስቀጣኝ እንጂ ዲኔን አታንቋሽሽ። አሏህ ለሁላችንም ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተማሪው ነቢይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥48 *"መጽሐፍንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል"*፡፡ وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ

"ተዕሊም" تَعْلِيم የሚለው ቃል "ዐለመ" عَلَّمَ ማለትም "አስተማረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትምህርት" ማለት ነው። አምላካችን አላህ "ሙዐሊም" مُعَلِّم ማለትም "አስተማሪ" "ዐዋቂ" ነው፥ ዒሣ ደግሞ አላህ ያስተማረው "ሙዐለም" مُعَلَّم ማለትም "ተማሪ" ነው፦
3፥48 *"መጽሐፍንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል"*፡፡ وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያስተምረዋል" ለሚለው የገባው ግስ "ዩዐለሙ-ሁ" يُعَلِّمُهُ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አንድ ማንነትና ምንነት ከሌላ ኑባሬ ከተማረ ፊሽካው ተነፋ፥ ያ ማንነትና ምንነት "ሁሉን ዐዋቂ" አይደለም። በባይብልም ከሔድን ኢየሱስን የላከው ማንነት እንዳስተማረው እራሱ አበክሮና አዘክሮ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 8፥28 *"አባቴም "እንዳስተማረኝ" እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ*"።
ዮሐንስ 7፥15-17 አይሁድም፦ *"ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ "ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም። ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል*።

ምን ትፈልጋለህ? የላከው ካስተማረው ውጪ የራሱ ዕውቅት የሌለው አካል እንዴት ይመለካል? "ራስ"own self" የሚለው ድርብ ተውላጠ-ስም ነው፥ "ራሴ" የሚለው ማንነት "እግዚአብሔር" ከተባለው ማንነት በመደብ ተውላጠ-ስም መለየቱ በራሱ ያስተማረው እግዚአብሔር እና ተማሪው ኢየሱስ ሁለት መሆናቸውን ፍንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ከራሱ ምንም ማድረግ የማይችል እና ከተማረው ውጪ ከራሱ ምንም የማይናገር ኢየሱስ የጥበብ፣ የማስተዋል፣ የምክር፣ የኃይል፣ የእውቀት መንፈስ ስላረፈበት በሰዎች ያለውን ነገር ያውቅ ነበር፦
ኢሳይያስ 11፥2 *የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል*።

ፈጣሪ አንድ ነብይ ሲያስነሳ እውቀትን፣ ጥበብን፣ ማስተዋልን ይሰጠዋል፥ በዚህም የሩቅ ሚስጥራትን ያውቃል እንጂ በራሱ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም። አንድ ነብይ ከሰው በላይ የሆነ ዕውቀት እንዳለው ከአይሁዳውያን መረዳት ይቻላል፦
ሉቃስ 7፥39 የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ *"ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር"* አለ።
ዮሐንስ 4፥17-19 ሴቲቱ መልሳ፦ ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ፦ *ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፥ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም። በዚህስ እውነት ተናገርሽ" አላት። ሴቲቱም፦ *ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ*"።

አይሁዳውያን አንድ ሰው መጥቶ በልባቸውን ያለውን ቢነግራቸው "ፈጣሪ ነህ" ሳይሆን የሚሉት፥ "ነቢይ ነህ" የሚሉት። ምክንያቱም የልብን የሚያውቅ ፈጣሪ ስለሆነ ያ ሰው ነቢይ ካልሆነ የልብን ማወቅ አይችልም። ኢየሱስ ደግሞ ከራሱ ሳይሆን ከፈጣሪ እየሰማ የሚናገር ሰው ነበረ፥ አክሎም፦ "የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና" ማለቱ በራሱ ዕውቀቱ ሁሉ ከፈጣሪ የሰማው ነው፦
ዮሐንስ 12፥49 *"እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፥ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*"።
ዮሐንስ 5፥30 *እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ "እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ"*።
ዮሐንስ 8፥26 *"የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም "ከእርሱ የሰማሁትን" ይህን ለዓለም እናገራለሁ" አላቸው*።
ዮሐንስ 15፥15 *"ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና"*።
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን *ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?

መቼም "እግዚአብሔር ከእግዚአብሔር እየሰማ ሲናገር ነበር" ብላችሁ ዓይናችሁ በጨው አጥባችሁ እንደማታሞኙን ቅቡል ነው። ከእግዚአብሔር እየሰማ የሚናገረው ኢየሱስ ግን እዚሁ አንቀጽ ላይ "ሰው" ነው" ተብሏል። "ነቢይ" የሚለው የግዕዝ ቃል እራሱ "ነበየ" ማለትም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ነባቢ" "ተናጋሪ" ማለት ነው፥ ከፈጣሪ የሚመጣለት ንግግር ደግሞ "ነቢብ" ይባላል። ኢየሱስ ደግሞ ነቢይ ነው፦
ማርቆስ 6፥4 ኢየሱስም፦ *"ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም* አላቸው።
ማቴዎስ 21፥11 ሕዝቡም፦ *ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው* አሉ።
ሉቃስ 24፥19 *በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ"*።
ዮሐንስ 9፥17 አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ደግሞ አሉት። እርሱም፦ *"ነቢይ ነው* አለ።

ይህ አፍጦና አፋጦ፥ አግጦና አንጋጦ የሚታይ እውነት ነው። የናዝሬቱ ኢየሱስ በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ነው፥ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ተማሪ ነው። መቼም ይህንን ስትሰሙ ቆሌ ተገፎና ቆሽት አሮ፦ "ሰማይ ተንዶ ሊናጫነኝ ነው፥ ምድር ተከፍቶ ሊውጠኝ ነው" እንደምትሉ እሙን ነው። የክርስትና ደርዛዊ ሥነ-መለኮትን በዘመናዊነት ማዘመን መላላጫና መጋጋጫ በሌለው እፉቅቅ እና እንብርክክ እየተጎተቱ መሔድ ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ታላቁ ታምር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6:124 “ታምርም” በመጣላቸው ጊዜ፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ وَإِذَا جَآءَتْهُمْ ءَايَةٌۭ قَالُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ حَتَّىٰ نُؤْتَىٰ مِثْلَ مَآ أُوتِىَ رُسُلُ ٱللَّهِ ۘ ٱللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۥ ۗ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟ صَغَارٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعَذَابٌۭ شَدِيدٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَمْكُرُونَ ፡፡

መግቢያ
ቁርኣን ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ከተሰጣቸው ተአምራት ውስጥ ታላቁ እና ዋነኛው ነው፣ የቁርኣን ተአምራዊነት ከቀደምት ነቢያት ተአምራት በሁለት መልኩ ይለያል፦
አንደኛ የቀደምት ነቢያት ተአምራት በአይን የሚታይ፣ በእጅ የሚዳሰስ ነው፣ ይህም ታምር ”ሒስሲይ” ይባላል፣ የቀደምት ነቢያት ተአምር ከነቢይነት ዘመናቸው ጋር ብቻ የተቆራኘ ነው፣ ከእነርሱ ሞት በኋላ ያበቃል፣ ይህም ታምር ”ወቅቲይ” ማለትም ጊዜአዊ ይሰኛል፡፡
ሁለተኛ ለነቢያችን ነቢይነት እንደ ማስረጃ የተሰጣቸው ቁርኣን ግን ህሊናን የሚያናግር፡ አእምሮን የሚቆጣጠርና ልብን የሚገዛ፣ በሚያስተላልፋቸው መልእክቱ ሰዎችን ለለውጥ የሚዳርግ ነው፣ ይህም ታምር ”መዕነዊይ” ይባላል፣ ቁርኣን ከነቢያችን ሞት በኋላ እንኳ ተአምራዊነቱ አላከተመም፣ እስከ ቂያማ ድረስ በነበረው ተአምራዊነቱ ይቀጥላል፤ በዚህም ”አበዲይ” ይሰኛል፡፡ እስቲ ይህንን ታላቅ ታምር በወረደበት ወቅት ሰዎች እንዴት እንዳስተባበሉት እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“የአላህ ታምራት”
ቁርአን በወረደ ጊዜ ሰዎች፦ “ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም” አሉ፤ አምላካችን አላህም፦ “አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው” በላቸው ብሎ መለሰ ሰጠ፦
6:37 *«ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም»* አሉ፡፡ *«አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው*፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

አላህ ቁርኣንን ታምር አድርጎ ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ እንዳወረደው ይናገራል፦
3:108 ይህች በአንተ ላይ በእዉነት የምናነባት ስትሆን የአላህ *ታምራት* آيَاتُ ናት፤
45:6 እነዚህ፣ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤ ከአላህና *ከታምራቶቹም* وَآيَاتِهِ ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
2:252 እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤
3:58 ይህ *ከታምራቶች”* الْآيَاتِ እና ጥበብን ከያዘዉ ተግሣጥ ሲሆን በአንተ ላይ እናነበዋለን።

አላህ የሚነበብ ሆኖ ቁርአን መወረዱ ታምር እንደሆነ እንደነገረን ሁሉ ነብያችንም ቁርአን ለእሳቸው ነብይነት ታምር እንደሆነ በአጽንኦትና በአንክሮት ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 66 , ሐዲስ 3:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ማንኛውም ነብይ ህዝቦቹ ያምኑበት ዘንድ ታምር ተሰጠውታል፣ ነገር ግን ለእኔ የተሰጠኝ ታምር አላህ ወደ እኔ ያወረደው ወህይ ነው عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَا مِنَ الأَنْبِيَاءِ نَبِيٌّ إِلاَّ أُعْطِيَ مَا مِثْلُهُ آمَنَ عَلَيْهِ الْبَشَرُ، وَإِنَّمَا كَانَ الَّذِي أُوتِيتُ وَحْيًا أَوْحَاهُ اللَّهُ إِلَىَّ فَأَرْجُو أَنْ أَكُونَ أَكْثَرَهُمْ تَابِعًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏” ።
ነጥብ ሁለት
“ማስተባበያ”
ሰዎች ቁርአን ታምር ሆኖ በመጣላቸው ጊዜ፡- “የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም” ወይም “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” ብለው ይህንን ታምር አስተባበሉ፦
6:124 *”ታምርም በመጣላቸው ጊዜ”*፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ፡፡
28:48 እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ ። ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን? አሉም “የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” ፤ አሉም “እኛ በሁለቱም ከሀዲዎች ነን”።

ለሙሳ የተሰጠው ግልጽ የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” ናቸው፦
17:101 ለሙሳም ግልጽ የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” በእርግጥ ሰጠነው፤

አላህ ታምር ብሎ “ዘጠኝ ታምራቶች” ቢያሳይም በወቅቱ ሙሳና ሃሩንን “የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” አሉ፤ ከዚህ ታምር ይልቅ “ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም” አሉ፦
2:55 ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ በአንተ በፍጹም አናምንልህም ”

በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ስለ ነብያችን፦ “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ፤ አላህም፦ “ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን?” በማለት ያ የተባለው ታምር ተመልሶ ቢመጣ አሁን ማስተባበላቸውን እንደማይቀር ተናግሯል።

ነጥብ ሶስት
“አስጠንቃቂ”
እነዚያም የካዱት፦ “በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?” ብለው የጠየቁት ታምር የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ አይነት ታምር ነው፤ ይህንን ታምር ነብያችን በራሳቸው ማምጣት አይችሉም፤ እርሳቸው አስጠንቃቂ እንጂ በፍላጎታቸው ታምር እውራጅ አይደሉም፤ ታምር አውራጅ አላህ ነው፤ ስለሆነም ቁርአን በእርሳቸው ላይ ታምር አድርጎ አውርዷል፦
13:7 እነዚያም የካዱት፦ “በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?” ይላሉ፤ አንተ “አስጠንቃቂ” ብቻ ነህ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው።
10:20 በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ታምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡
6:37 «ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም» አሉ፡፡ «አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው፡፡

በእርግጥም አንድ መልእክተኛ ሲመጣ አላህ በፈቃዱ ከሚሰጠው ታምር በራሱ ሊያመጣ አይችል፦
13:38 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ፥ ታምር ሊያመጣ አይገባውም*፤
40:78 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ ታምርን ሊያመጣ አይገባውም*።
መደምደሚያ
በኢየሱስ ዘመንም ኢየሱስ ብዙ ታምር እያደረገ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች የሚጠይቁት ታምር ግን ከሰማይ ነው፤ ኢየሱስም እነርሱን የጠየቁትን ታምር ከመፈፀም ይልቅ “ለዚህ ትውልድ *”ምልክት አይሰጠውም”* ብሎ መለሰ፦
ማርቆስ 8፥11-12 ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት *”ከሰማይ ምልክት”* ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር። በመንፈሱም እጅግ ቃተተና፦ ይህ ትውልድ ስለ ምን *”ምልክት”* ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፥ ለዚህ ትውልድ *”ምልክት አይሰጠውም”* አለ።
ማቴዎስ 16:4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ *”ምልክት”* ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር *”ምልክት አይሰጠውም”*። *ትቶአቸውም ሄደ*።

ኢየሱስ፦ “ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም” ማለቱ ሰዎች የፈለጉት ከሰማይ ምልክት አላደርግም ማለት እንጂ ምልክት አለማድረግን አያሳይም፣ እነርሱ የፈለጉት ምልክት ከሰማይ ምልክት ነው፣ ነገር ግን ኢየሱስ እነርሱ ከጠየቁት ታምር በተቃራኒው ያደረገውን ታምር በፊታቸው ምንም ቢያደርግ በእርሱ አላመኑም፦
ዮሐንስ 12፥37-38 ነገር ግን ይህን ያህል *”ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ”* ነቢዩ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ *”በእርሱ አላመኑም”*።

በተመሳሳይም በነቢያችን ዘመን የነበሩት ሰዎች ታምር ብለው የሚሉትና አላህ ታምር የሚለው ሁለት ለየቅል ነው፣ የቁርአንን ታላቅ ታምርነት በወቅቱ የነበሩት ሰዎች እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ባይመጣም ለሰው የሚበጅ ታምር ማምጣት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፤ ከላይ የቀረበውን ነጥብ በኢየሱስ ታምር ማሳያነት በቀላሉ መረዳት ይቻላል። አላህ ታምር ሲመጣላቸው እነርሱ የሚፈልጉት ያንን ታምር ስላልሆነ ይሸሻሉ፦

36:46 ከጌታቸውም ታምራት ማንኛይቱም ታምር አትመጣላቸውም፤ ከእርሷ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ። وَمَا تَأْتِيهِم مِّنْ ءَايَةٍۢ مِّنْ ءَايَٰتِ رَبِّهِمْ إِلَّا كَانُوا۟ عَنْهَا مُعْرِضِينَ

እነዚያን በአላህ ታምራት ያስተባበሉ እሳት ይገባሉ፦
4፥56 እነዚያን *በተአምራታችን ያስተባበሉትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን*፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢትዮጵያ ጤፍ

መዝሙር 74፥14 አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ צִיִּ֔ים ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።

የእኛ ሕዝብ የራሱ ትርጉም አለው። ቅድሚያ "ኢትዮጵያ" የሚል ቃል እዚህ አንቀጽ ላይ የለም። "ሲዪም" צִיִּ֔ים ማለት "ምድረ በዳ" ማለት እንጂ "ኢትዮጵያ" ወይም "ኩሽ" ማለት በፍጹም አይደለም፦
ኢሳይያስ 13፥21 በዚያም *"የምድረ በዳ"* צִיִּ֔ים አራዊት ያርፋሉ፥ ጕጕቶችም በቤቶቻቸው ይሞላሉ፤ ሰጎኖችም በዚያ ይኖራሉ፥ በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ።

"ዘንዶ" የተባለው የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ነው፥ የግብጽ ንጉሥን በኤርትራ ባሕር ውስጥ በማስመጥ ቀጥቶታል፦
ሕዝቅኤል 29፥3 እንዲህም በል፡— ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡— በወንዞች መካከል የምትተኛና፡— ወንዙ የእኔ ነው ለራሴም ሠርቼዋለሁ የምትል ታላቅ ዘንዶ תַּנִּין ፥ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ።

"ሌዋታን" ማለት "በውኃ ውስጥ የሚኖር ዘንዶ" አንዳንድ ትርጉም "አዞ" ይሉታል። ባሕሩን አድርቆና ሰንጥቆ ይህንን ዘንዶ በባሕር ቀጥቅጦታል፦
መዝሙር 74፥15 አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ፤ አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ።

ከዚያስ? ከዚያማ በምድረ በዳ ላሉትን ምግብ መና አወረደላቸው፦
ዘጸአት 16፥32 ሙሴም፦ እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግብፅ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ ከእርሱ አንድ ጎሞር ሙሉ ለልጅ ልጆቻችሁ ይጠበቅ አለ።

"ምድረ በዳ" የሚለው "ኢትዮጵያ" ብሎ በመተርጎም፥ "ምግብ" የሚለውን "ጤፍ" ብሎ መተርጎም አግባብ ነውን?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ወሊይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥69 *«እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ፈጽሞ አይድኑም»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّ الَّذِينَ يَفْتَرُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ لَا يُفْلِحُونَ

ኢሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች፦ "በኢሥላም ሴት ልጅ የምትፈልገውን ወንድ የማግባት መብት የላትም፥ የምትፈልገውን ወንድ ካገባች ዝሙተኛ ናት" ተብሏል" ብለው ይቀጥፋሉ። ይህንን ቅጥፈት እንድትቀጥፉ ያነሳሳችሁ የትኛው የኢሥላም ትምህርት ነው? ስንላቸው፥ ይህንን ሐዲስ ይጠቅሳሉ፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 1956
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አንዲት ሴት ሌላዋን ሴት መዳር አትችልም፥ አንዲት ሴት እራሷን መዳር አትችልም። ዝሙተኛይቱ እርሷ እራሷን የዳረች ናት"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ لاَ تُزَوِّجُ الْمَرْأَةُ الْمَرْأَةَ وَلاَ تُزَوِّجُ الْمَرْأَةُ نَفْسَهَا فَإِنَّ الزَّانِيَةَ هِيَ الَّتِي تُزَوِّجُ نَفْسَهَا ‏"‏

እዚህ ሐዲስ ላይ፦ "ሴት ልጅ የምትፈልገውን ወንድ የማግባት መብት የላትም፥ የምትፈልገውን ወንድ ካገባች ዝሙተኛ ናት" የሚል ሽታው የለም። ከዚህ ይልቅ አንዲት ሴት እራሷን መዳር አትችልም ማለት ያለ ወሊይ ትዳሯ ሕጋዊ አይሆንም ማለት ነው። "ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ወኪል"guardian" ማለት ሲሆን የሚያገባት ወንድ ሊያገባት ሲል ወኪል የሚሆናት አባቷ ወይም ወንድሟ ወይም አጎቷ አሊያም አያቷ ወሊይ ይባላሉ። ሐዲሱን ከፍ ብለን እዚሁ ኪታብ ላይ ብናነበው ኖሮ "በወሊይ ቢሆን እንጂ ጋብቻ የለም" የሚለውን የነቢያችንን"ﷺ" ንግግር እናስተውል ነበር፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 1954
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በወሊይ ቢሆን እንጂ ጋብቻ የለም"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، ‏.‏ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ لاَ نِكَاحَ إِلاَّ بِوَلِيٍّ ‏"‏

በኢሥላም የሴት ልጅ ሕይወት ክቡርና ክቡድ ነው፥ ወሊይ ከሌለ ማንም ወጠብሻና ወጠጤ ጎሮምሳ እየተነሳ፦ "ላማግጥ" ሊል ይችላል። ቅሉ ግን ወሊይ ዕውቅና የሰጠው ኒካሕ ሐላል ነው። በጥቅሉ የነቢያችንን"ﷺ" ንግግር በሐዲስ ላይ፦ "ማንም ሴት ከወሊይዋ ውጪ ብትዳር ትዳሯ ሕገ-ወጥ ነው" የሚለውን ብትመለከቱ ኖሮ ይህንን ጥያቄ አትጠይቁም ነበር፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 11, ሐዲስ 23 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ሴት ከወሊይዋ ውጪ ብትዳር ትዳሯ ሕገ-ወጥ ነው፣ ትዳሯ ሕገ-ወጥ ነው፣ ትዳሯ ሕገ-ወጥ ነው"*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ

ሴት ልጅ ማንን ማግባት እንዳለባት በራሷ ተነሳሽነት ይሁን አሊያም በቤተሰቧ ምክር የምትወደውን ወንድ የማግባት ሙሉ መብት አሏት፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 11, ሐዲስ 29 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"መበለት በራሷ ላይ ከወሊይዋ ይበልጥ መብት አላት። ድንግሊት በራሷ ፈቃድዋ ትጠየቃለች፥ ፈቃዷም ዝምታዋ ነው"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ الأَيِّمُ أَحَقُّ بِنَفْسِهَا مِنْ وَلِيِّهَا وَالْبِكْرُ تُسْتَأْذَنُ فِي نَفْسِهَا وَإِذْنُهَا صُمَاتُهَا ‏"‏ ‏.‏

እኛ ዐቃቢያነ እሥልምና የኢሥላምን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ተረድተን ለሚቀጥፉት ቀጣፊዎች በምንተ አፍረት ሳይሆን በምንተ እዳ እንዲህ መልስ መስጠት እና የታሪክ ምፀት ከዐሊሞቻችን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይለናል። በዲን ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ፈጽሞ ከእሳት ቅጣት አይድኑም፦
10፥69 *«እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ፈጽሞ አይድኑም»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّ الَّذِينَ يَفْتَرُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ لَا يُفْلِحُونَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቡሄ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

መጣና መጣና
ደጅ ልንጥና፤
መጣና ባመቱ
እንዴት ሰነበቱ፣
ክፈት በለዉ በሩን
የጌታዬን፣
ክፈት በለዉ ተነሳ
ያንን አንበሳ፣
መጣሁኝ በዝና
ተዉ ስጠኝ ምዘዝና።
እየተባለ ሆያ ሆዬ በልጅነት ያለ ዕውቀት ሙሥሊሙ ከክርስቲያኑ ጋር ተደባልቆ የክርስቲያን ሠው ሥራሽ በዓል ሲያከብር አድጓል። "ቡሄ" ማለት "ገላጣ" "የተገለጠ" ማለት ነው፥ በአገራችን የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይህ ዕለት "ቡሄ" ተባለ። ኢየሱስ ሦስቱን ተከታዮች ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው፦
ማቴዎስ 17፥1 *ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው*።

ይህ ተራራ የትኛው ተራራ እንደሆነ በባይብል አልተጠቀሰም። አንዳንድ ምሁራን አርሞንኤም ነው ይላሉ፥ የእኛዎቹ ታቦር ነው ይላሉ። "ደብር" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን "ተራራ" ማለት ነው፥ የደብር ብዙ ቁጥር "አድባር" ሲሆን "ተራሮች" ማለት ነው። "ደብረ-ታቦር" ማለት "የታቦር ተራራ" ማለት ነው፥ ይህ ቡሄ በዓል ደብረ-ታቦር ይባላል።
በባይብል የተራራው ስም የለም፣ ይህ እለት ነሃሴ 13 ነው የሚል የለም፣ ይህንን ቀን አክብሩ የሚል የለም፣ በዚህ ቀን ዳንኪራ ሆያ ሆዬ አድርጉ የሚል የለም። ይህ ሁሉ ሰው ሠራሽ ሕግ ነው። በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። ቡሄ ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ በመስጠት እና ችቦ በማብራት በዓሉን ያከብራሉ። ይህ ሁሉ ከንቱ እዚሁ የሚቀር ምድራዊ ነገር ነው። ይህንን የክርስትና ሰው ሰራሽ በዓል ሙሥሊሙ ባለማወቅ ሲያከብረው ኖሯል። ይህ ስህተት ነው። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ቡሄ የአገር ባህል ይመስለን ነበር፥ ቅሉ ግን እንደዛ አይደለም። ይህንን በዓል መልእክተኛው ያልሰጡን ዕቡይ ተግዳሮት መሆኑን ዐውቀን መሳተፍ የለብንም። የታሪክ ምፀት ከዐሊሞቻችን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይለናል፥ ይህን ለማድረግ አስረግጦ እና ረግጦ መረዳትና ማስረዳት ይጠበቅብናል። ያኔ የኢሥላም ልዕልና ለካፊሩን የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት ኢንሻላህ ይሆናል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሒጅራህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥100 *በአላህም መንገድ የሚሰደድ ሰው በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል፡፡ ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም ስደተኛ ኾኖ ከቤቱ የሚወጣ ከዚያም በመንገድ ሞት የሚያገኘው ሰው ምንዳው በእርግጥ አላህ ዘንድ ተረጋገጠ*፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ وَمَن يُهَاجِرْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يَجِدْ فِي الْأَرْضِ مُرَاغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً ۚ وَمَن يَخْرُجْ مِن بَيْتِهِ مُهَاجِرًا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ يُدْرِكْهُ الْمَوْتُ فَقَدْ وَقَعَ أَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

ነቢያችን"ﷺ" ለመጀመሪያ ጊዜ ወሕይ ማለትም "ግልጠተ-መለኮት" የመጣላቸው በ 610 ድህረ-ልደት"AD" ነው፤ ከዚያም በ 613 ድህረ-ልደት የወሕይ ጭብጥ የሆነው ተህሊል ለመካ ሰዎች አወጁ፤ ይህንን አዋጅ ያልተቀበሉት መካውያን የነቢያችንን"ﷺ" ባልደረቦች በማሳደዳቸው የመጀመሪያው ስደት በ 615 ድህረ-ልደት ወደ ሃበሻ ምድር ወደ ኢትዮጵያ ሆኗል። አምላካችን አላህ በእርሱ መንገድ ስለሚሰደዱት ስደተኞች እንዲህ ይለናል፦
4፥100 *በአላህም መንገድ የሚሰደድ ሰው በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል፡፡ ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም ስደተኛ ኾኖ ከቤቱ የሚወጣ ከዚያም በመንገድ ሞት የሚያገኘው ሰው ምንዳው በእርግጥ አላህ ዘንድ ተረጋገጠ*፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ وَمَن يُهَاجِرْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يَجِدْ فِي الْأَرْضِ مُرَاغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً ۚ وَمَن يَخْرُجْ مِن بَيْتِهِ مُهَاجِرًا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ يُدْرِكْهُ الْمَوْتُ فَقَدْ وَقَعَ أَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
2፥218 *እነዚያ ያመኑትና እነዚያም ከአገራቸው የተሰደዱት በአላህም መንገድ ላይ የተጋደሉት እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ*፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أُولَـٰئِكَ يَرْجُونَ رَحْمَتَ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

"ሂጅራህ" هِجْرَة የሚለው ቃል "ሃጀረ" هَاجَرَ ማለትም "ተሰደደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስደት" ማለት ነው። ነቢያችን"ﷺ" እና ባልደረቦቻቸው ከሚኖሩበት ቀዬ ከመካ ወደ መዲና በ 622 ድህረ-ልደት ተሰደዋል፦
16፥41 *እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ መንገድ ላይ የተሰደዱት በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው*፡፡ ከሓዲዎች ቢያውቁ ኖሮ በተከተሏቸው ነበር፡፡ وَالَّذِينَ هَاجَرُوا فِي اللَّهِ مِن بَعْدِ مَا ظُلِمُوا لَنُبَوِّئَنَّهُمْ فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً ۖ وَلَأَجْرُ الْآخِرَةِ أَكْبَرُ ۚ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ
9፥20 *እነዚያ ያመኑት፣ ከአገራቸውም የተሰደዱት፣ በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው*፡፡ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ أَعْظَمُ دَرَجَةً عِندَ اللَّهِ ۚ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْفَائِزُونَ

"የተሰደዱ" ለሚለው ቃል የገባው "ሃጀሩ" هَاجَرُوا ሲሆን "ሃጀረ" هَاجَرَ ከሚለው ሥርወ-ቃል መምጣቱ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ "ሙሃጂር" مُهَاجِر ማለት ደግሞ "ስደተኛ" ማለት ሲሆን ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱትን መካውያን ሰሃባዎችን ያመለክታል፤ መዲና ላይ ከመካ የተሰደዱትን እረድተው የተቀበሉ "ነሲር" نَصِير ማለትም "ረዳት" ይባላሉ፦
8፥74 *እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉ እና የረዱ እነዚያ እነርሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ
9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

"ረዳቶች" ለሚለው ቃል የገባው "አንሷር" أَنْصَار ሲሆን "ነሲር" نَصِير ለሚለው ቃል ብዜት ነው፤ ይህም ስም መዲናውያን ሰሃባዎችን ያመልክታል፦
8፥72 *እነዚያ ያመኑና የተሰደዱ፡፡ በአላህም መንገድ ላይ በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸው የታገሉ፡፡ እነዚያም ስደተኞቹን ያስጠጉና የረዱ፡፡ እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ
622 ድህረ-ልደት በነቢያችን"ﷺ" ላይ የወረደው ወሕይ በነጻነት የተላለፈበት እና የአምልኮ ነጻነት የሆነበት ቀን ነው፤ በዚህ ዓመት በመዲና ውስጥ የቁባ መስጊድ የተገነባበት ነው፦
9፥108 በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ፡፡ *ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው የቁባ መስጊድ በውስጡ ልትሰግድበት ይልቅ የተገባው ነው*፡፡ በእሱ ውስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አሉ፡፡ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል፡፡ لَا تَقُمْ فِيهِ أَبَدًا ۚ لَّمَسْجِدٌ أُسِّسَ عَلَى التَّقْوَىٰ مِنْ أَوَّلِ يَوْمٍ أَحَقُّ أَن تَقُومَ فِيهِ ۚ فِيهِ رِجَالٌ يُحِبُّونَ أَن يَتَطَهَّرُوا ۚ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُطَّهِّرِينَ

በዚህ አንቀጽ ላይ "ከመጀመሪያ ቀን" የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ይህ ቀን መጀመሪያነቱ በአንጻዊ ደረጃ ሂጅራህን ያመለክታል። በዚህ ቀን የቁባ መስጊድ የተገነባበት ነው፤ በነቢያችን"ﷺ" በኩል የመጣው ግህደተ-መለኮት የቀን አቆጣጠሩም የሚጀምረው ከዚህ ቀን ጀምሮ ነው፤ ይህም የዘመን ቀመር"calendar" በኢስላም "አት-ተቅዊሙል ሂጅሪይ" التقويم الهجري ይባላል።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሁለት ዒዶችን በዓመት በዓመት እናከብራለን፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *“አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን”* አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፦ *የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

እነዚህን በዓላት ከሂጅራ ጀምሮ እስከ አሁን ስናከብር ለ 1440 ጊዜ ነው። ኢሥላም ዐቂደቱል ረባኒያ እንጂ ሰው ሰራሽ ሕግና ሥርዓት የለውም። ሱመ አል-ሐምዱ ሊሏህ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጌታ እና ባሪያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ዒሣ የትምህርቱ ጭብጥ፦ “አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት” የሚል ነው፤ አምላካችን አላህም ኢየሱስን ተናገር! ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
3፥51 *”አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”* ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ጌታችን አላህ ላኪ ባሪያው ኢየሱስ መልእክተኛ ነው። ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፥ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም፦
ዮሐንስ 13፥16 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ *ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም*።

ፈጣሪ ኢየሱስን “አብዲ” עַבְדִּי֙ ማለትም “ባሪያዬ” በማለት ፈጣሪ ተመላኪ ኢየሱስ አምላኪ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ *ደግፌ የያዝሁት “ባሪያዬ” עַבְדִּי֙፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ*፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።

ይህንን በኢሳያያስ በኩል “ባሪያዬ” የሚለውን ትንቢት ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ ተርጓሚዎች “ብላቴና” ማለትም “ልጄ” ብለው ለመለወጥ ቢዳዱም ግሪኩ ግን “ፔይስ ሞዩ” παῖς ማለትም “ባሪያዬ” ብሎ አስቀምጦታል፤ “ፔይስ” παῖς ማለት “ባሪያ” ማለት ነውና፦
ማቴዎስ 12፥17-18 በነቢዩ ለአሕዛብ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦እነሆ *"የመረጥሁት “ባሪያዬ” παῖς μου ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ*፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ያወራል።

በትርጉም ኢየሱስን “ልጅ” ብለው ቢቀይሩትም ግሪኩ ግን “ባሪያ” ብሎ ያስቀመጠበት ጥቅስ በቁና ነው፣ በተጨማሪም የአማርኛው ትርጉም እና KJV ትርጉም “ልጅ” እያሉ ቢለውጡም NIV ትርጉም በትክክል የግሪኩን ትርጉም ይዞ “ባሪያ” ብሎ አስቀምጦታል፦
የሐዋርያት ሥራ 3፥13 የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን *“ባሪያዬውን” παῖς ኢየሱስን አከበረው*።
የሐዋርያት ሥራ 3፥26 ለእናንተ አስቀድሞ *እግዚአብሔር “ባሪያዬውን” παῖς አስነሥቶ*፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።
የሐዋርያት ሥራ 4፥27-28 *"በቀባኸው በቅዱሱ “ባሪያህ” παῖς በኢየሱስ"* ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።
የሐዋርያት ሥራ 4፥29-30 አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ *በቅዱስ “ባሪያህም” παῖς በኢየሱስ"* ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው ።

በተለይ ጴጥሮስ አብን፦ "ጌታ ሆይ" ካለ በኃላ ስለ ኢየሱስ ለአብ፦ "ባሪያህ" ማለቱ አብ ጌታ ወልድ ባሪያ መሆኑን አስምሮበታል። በእርግጥም አብ የሰማይና የምድር ጌታ ነው፦
ማቴዎስ 11፥25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ *"አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ"*፥
የሐዋርያት ሥራ 17፥24 ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ *"እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና"* እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም።

"እርሱ" ተብሎ በነጠላ ተውላጠ-ስም የተቀመጠ አንድ ማንነት የሰማይና የምድር ጌታ ነው፥ ይህም አብ ነው። አብ በጌትነቱ ላይ ባርነት የለበትም። ማርያምና ዮሴፍ ይህንን የአብን ባሪያ ኢየሱስን በጌታ ፊት አቁመው ለጌታው መስዋዕት አቅርበዋል፤ ኢየሱስ በጌታ የተቀባና ለመፈወስ የጌታ ኃይል የሆነለት ባሪያ ነው፦
ሉቃስ 2፥24 እንደ ሙሴም ሕግ የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ፡— የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል፡ ተብሎ እንደ ተጻፈ፡ *"በጌታ ፊት ሊያቆሙት"*፥ በጌታም ሕግ፡— ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች፡ እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት።
ሉቃስ 2፥26 *"በጌታም የተቀባውን"* ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር።
ሉቃስ 5፥17 እርሱም *"እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት"*።

አንድ ህላዌ ባሪያ ከሆነ ተመልሶ ጌታ አይሆንም። ጌታ ከተባለ ደግሞ ግን ስልጣንና ሹመትን አሊያም እልቅናና ክብርን ያመለክታል። ስለዚህ የኢየሱስ ጌትነት የፍጡር ማእረግ ብቻ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ኢየሱስን ጌታ አደረገው ስለሚል፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 አለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን *ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው* የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

መቼም አንድ ጤነኛ የሆነ ሰው ፈጣሪን ፈጣሪ ጌታ አደረገው ብሎ እንደማይቀበል እሙን ነው፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ጌታ አደረግሁት ይላል፦
ዘፍጥረት 27፥37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው። እነሆ፥ *ጌታህ አደረግሁት*፥ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት፥

ይህም ስልጣንና ሹመትን አሊያም እልቅናና ክብርን ያመለክታል፤ ዮሴፍ፦ "እግዚአብሔር ጌታ አደረገኝ” ይላል፦
ዘፍጥረት 45፥9 *እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ*፤ ወደ እኔ ና፥ አትዘግይ፤

ኢየሱስ ጌታ ተደረገ ሲባል ያዕቆብ ጌታ ተደረገ ዮሴፍ ጌታ ተደረገ በተባለበት ሒሳብ እንጂ የዓለማቱ ጌታ የሚለውን አያመለክትም፤ ይህም በራሡ የተብቃቃ አሊያም የባህርይ ገንዘቡ ሣይሆን በስጦታ ያገኘው ነው። ታዲያ ኢየሱስ ለምን "አንድ ጌታ" ተባለ? አዎ "አንድ ጌታ" ማለት "አንድ መምህር" ማለት ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥6 ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን *"አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን"*።
ማቴዎስ 23፥8 እናንተ ግን፡- *መምህር* Ῥαββί ተብላችሁ አትጠሩ፤ *መምህራችሁ አንድ* ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።