ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.1K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጥያቄአችን!

ዳዊት የእሴይ ስንተኛ ልጅ ነው? 7ኛ ወይስ ስምንተኛ?

A. ሰባተኛ፦
1ኛ ዜና መዋዕል 2፥13-15 እሴይም የበኵር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሣማን፥ አራተኛውንም ናትናኤልን፥ አምስተኛውንም ራዳይን፥ ስድስተኛውንም አሳምን፥ *ሰባተኛውንም ዳዊትን ወለደ*፤

እዚህ ዐውደ ንባብ ላይ እሴይ ሰባት ልጆች እንዳሉት እና የመጨረሻ ሰባተኛው ዳዊት እንደሆነ ተገልጿል።

B. ስምተኛ፦
1 ሳሙኤል 16፥10-13 እሴይም *ከልጆቹ ሰባቱን በሳሙኤል ፊት አሳለፋቸው*። ሳሙኤልም እሴይን፦ እግዚአብሔር እነዚህን አልመረጠም፡ አለው። ሳሙኤልም እሴይን፦ *የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው። እርሱም፦ ታናሹ ገና ቀርቶአል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል፡ አለ። ሳሙኤልም እሴይን፦ እርሱ እስኪመጣ ድረስ አንረፍቅምና ልከህ አስመጣው፡ አለው። ልኮም አስመጣው፤ እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፦ ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው፡ አለ። ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ*። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።

እዚህ ዐውደ ንባብ ላይ ደግሞ እሴይ ሰባት ልጆች አሳልፎ፥ ከሰባቱ ሌላ ትንሹ የመጨረሻው ዳዊት እንደሆነ ተገልጿል። ስምንተኛም እንደሆነ ቅቡል ነው።

ጥያቄአችን፦ "ዳዊት የእሴይ ስንተኛ ልጅ ነው? 7ኛ ወይስ ስምንተኛ?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
የአንባቢያን ጥያቄ ምላሽ!

1ኛ. "እንኳን አደረሳችሁ" ወይም "እንኳን አብሮ አደረሰን" የመልካም ምኞት መግለጫ ነው። "ገና ማለት አምላክ የተወለደበት፥ ፋሲካ ማለት ሞቶ የተነሳበት" ብለው የሚያምኑበት ነው። ይህ እምነት ከኢሥላም ዐቂዳችን ጋር ስለሚጋጭ እንኳን አምላካችሁ ተወለደ ወይም ሞተ ማለት አይቻልም።
"እንኳን አደረሳችሁ" ቢሉን መልሳችን "እናመሰግናለን" ነው። "እንኳን አብሮ አደረሰን" የማንልበት ምክንያት እነርሱን የእኛ በዓል አላደረሳቸው፥ አብረውን አልጾሙም አብረውን ሰግደው ስለማያከብሩ። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *”አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው”*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”በሁለቱ በአል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

2ኛ. "አሥ-ሠላም ዐለይኩም" የሙሥሊም ሃይማኖታዊ ሠላምታ ነው። ግን ሰላም፣ ጤና ይስጥልኝ፣ እንዴት ነህ ወዘተ አገራዊ ሰላምታ ማቅረብ ይቻላል። "አሥ-ሠላም ዐለይኩም" ካሉን እኛ "ወዐለይኩም" ብቻ ማለት ነው ያለብን፦
አል-አደበል ሙፍረድ መጽሐፍ 44, ሐዲስ 2
አቢ በስረል ጊፋሪይ እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ነገ ወደ አንድ አይሁድ እጓዛለው፤ በመጀመሪያ ሰላም(አሠላሙ አለይኩም) አትበሏቸው፤ አሠላም አለይኩም ቢሏችሁ ግን ወአለይኩም በሉ*። عَنْ أَبِي بَصْرَةَ الْغِفَارِيِّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنِّي رَاكِبٌ غَدًا إِلَى يَهُودَ، فَلاَ تَبْدَأُوهُمْ بِالسَّلاَمِ، فَإِذَا سَلَّمُوا عَلَيْكُمْ فَقُولُوا‏:‏ وَعَلَيْكُمْ‏.‏
አል-አደበል ሙፍረድ መጽሐፍ 44, ሐዲስ 3
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”የመጽሐፉ ሰዎችን ቅድሚያ ሰላም(አሠላሙ አለይኩም) አትበሏቸው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ أَهْلُ الْكِتَابِ لاَ تَبْدَأُوهُمْ بِالسَّلاَمِ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 41
ዐነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም ከመጽሐፉ ሰዎች ሠላም(አሠላሙ አለይኩም) ብሎ ሰላምታ ከሳጣችሁ፥ “ወአለይኩም” በሉ*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِذَا سَلَّمَ عَلَيْكُمْ أَحَدٌ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ فَقُولُوا وَعَلَيْكُمْ‌‏.‏

ወሏሁ አዕለም!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
አሕዛብ ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

አንዱ ክርስቲያን በውይይት ላይ ሲናደድ አሕዛብ ብሎ ተናገረኝ፤ እኔም አህዛብ ምን ማለትና ምን እንደሆነ ብታውቅ ኖሮ ይቺን ቃል አትደፍራትም ነበር ብዬ ምላሽ ሰጠሁት፤ "አህዛብ" ተብሎ በግሪክ ብሉይ ሰፕቱአጀን እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ላይ "ኤትኖስ" ἔθνος የሚለው የግሪኩ ቃል "ኤትኒኮስ" ἐθνικός ከሚለው ገላጭ የመጣ ሲሆን በዕብራይስጡ ደሃራይ እደ-ክታባት ላይ ደግሞ "ጎይ" גוי ተብሎ ተቀምጧል፤ ይህ ቃል እንደየ አውዱ ለተለያየ ትርጉም አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን "ህዝብ" "ብሔር" "አረማዊ" "ይሁዲ ያልሆነ" የሚል ፍቺ እንዳለው የግሪክና የዕብራይስጥ ሙዳየ-ቃላት ያትታሉ፤ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እዚህ አርስት ላይ "አህዛብ" ብለን የምንመለከተው "አረማዊ"pagan" የሚለው እሳቤ ነው፤ ሰዎች ይህ ስም የአብርሃምን አምላክ ለሚያመልኩ ለሙስሊሞች እንደ ቅፅል ስም ሲጠቀሙ እጅግ ስላስደመመኝ ይህ ስም ማንን እንደሚመለከትና ማንን አህዛብ እንደሚል ለመፅሐፍ ቅዱስ ቦታውን እንልቀቅ፦

ነጥብ አንድ
"ርኵሰት"
በመፅሐፍ ቅዱስ "የአሕዛብን ርኵሰት" ተብሎ የተቀመጠው ምዋርት፥ ሞራ ገላጭ፥ አስማት፥ መተተት፥ ድግምት፣ ጥንቆላ፥ መናፍስትንም መጥራት፥ ሙታን መሳብ ነው፦
ዘዳግም 18፥9-11 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ ""አሕዛብ"" የሚያደርጉትን "ርኵሰት" ታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።

ታዲያ ይህ በኢስላም ትልቁ ሽርክ ነው፤ ከኢስላም አጥርስ የሚያስወጣ አይደለምን? ይህንን ድርጊትስ ማን ነው በዘመናዊ መልክ የሚያደርገው ሙስሊሙ ወይስ ስም ለጣፊው?

ነጥብ ሁለት
"ግብረ-ሰዶም"
አላህ የፈጠረው ተቃራኒ ፃታ"hetro-sexual" እያለ ዛሬ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሆነው ግብረ-ሰዶም"homo-sexual" ማድረግ የአሕዛብን ርኵሰት ነው፦
1ኛ ነገሥት 14፥24 በምድርም ውስጥ "ሰዶማውያን" ነበሩ፤ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸውን ""የአሕዛብን ርኵሰት" ሁሉ ያደርጉ ነበር።

ታዲያ ይህ በኢስላም አይደለም መጋባት ይቅርና ድርጊቱ ሃራም ነው፤ ማን ነው ታዲያ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሚያጋባው ቤተክርስቲያን ወይስ መስኪድ? ህሊና ይፍረደዋ።

ነጥብ ሶስት
"የተቀረፀ ምስል"
ነቢያት "የአሕዛብ ልማድ" ብለው ያስቀመጡት ከእንጨት፣ ከብረት፣ ከብር እና ከወርቅ የተሰሩትን የተቀረፁ ምስሎች ነው፤ እነዚህ ምስሎች አፍ አላቸው አይናገሩም፤ ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፤ እጅ አላቸው አይዳስሱም፤ እግር አላቸው አይሄዱም፤ ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፣ አህዛብ ግን ወደ እነርሱ ይፀልያሉ፣ ይለማመናሉ፣ እጣን ያጨሳሉ፣ ይጎባደዳሉ፣ ያሸረግዳሉ፣ ይሰግዳሉ፣ -ያመልካሉ፦
2ኛ ነገሥት17፥41 እነዚህም "አሕዛብ" እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር፤ ደግሞም "የተቀረጹ ምስሎቻቸውን" ያመልኩ ነበር፤
2ኛ ዜና 16፥26 "የአሕዛብ አማልክት" ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
መዝሙር 115፥4-7 የአሕዛብ ጣዖታቶች "የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ" ናቸው፤ አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም።
ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ "ከአሕዛብ" ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ "የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት" የሚሸከሙና ያድን ዘንድ "ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ" እውቀት የላቸውም።
ኤርምያስ 10፥2-5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። "የአሕዛብ ልማድ" ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።
እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።

ማን ነው የተቀረፀ ምስል አድርጎ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት እና ለሶስቱ አካላት የአምልኮ ስግደት የሚሰግደው? በስዕልና በሃውልት ፊት የሚለማመን፣ የሚያመልክ፣ እጣን የሚያጨስ፣ ስለት የሚሳል? ሙስሊሙ ወይስ እውነተኛው አህዛብ? ህሊና እያለ ምን ይኮናል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፅንስ እና ቁርኣን

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥6 *እርሱ ያ በማኅፀኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው*፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

ሥነ-ፅንስ ጥናት”Embryology” በማኅፀን ውስጥ ያለውን ሒደት የሚያጠና የዕውቀት ዘርፍ ነው። "በጥን" بَطْن የሚለው ቃል "በጠነ" بَطَنَ ማለትም "ተደበቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስውር" ማለት ነው፦
7፥33 «ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውን እና *"የተደበቀውን* ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን ጣዖት በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተደበቀ" ለሚለው የግስ መደብ የገባው "በጠነ" بَطَنَ ሲሆን በስም መደብ "በጥን" بَطْن የሚለው ቃል "ማኅጸን" ለሚለው ቃል ገብቷል፦
16፥78 *አላህም ከእናቶቻችሁ "ማኅፀኖች" ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ*፡፡ وَاللَّهُ أَخْرَجَكُم مِّن بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئً

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቡጡን" بُطُون የሚለው "በጥን" بَطْن ለሚለው ቃል ብዙ ቁጥር እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቁርኣን ማኅፀን የሚለው ከሴቷ ብልት ከንፈር ጀምሮ ለዓይን የተደበቀውን ክፍል ሁሉ ነው። ለዚያ ነው ሌላ አንቀጽ ላይ ማኅፀን ውስጥ ያለውን "ሽል" ለዓይናችን የተደበቀ ስለሆነ "አጂናህ" የሚለው፥ "አጂናህ" أَجِنَّة የሚለው ቃል “ጀነ” جَنَّ ማለትም “ሰወረ” ወይም “ደበቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፦
53፥32 *ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ማኅፀኖች ውስጥ "ሽሎች" በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በእናንተ ሁኔታ ዐዋቂ ነው*፡፡ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَإِذْ أَنتُمْ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ ۖ فَلَا تُزَكُّوا أَنفُسَكُمْ

ስለዚህ አምላካችን አላህ ማኅፀን ያለው እና ዛሬ የሥነ-ፅንስ ጥናት "ማኅፀን"uterus" ያለው ይለያያል፥ ቁርኣኑ ጥቅላዊና ሰፊ ቦታን ሲያመለክት፤ የሥነ-ፅንስ ጥናት ተናጥሏዊና ጠባብ ቦታን ያመለክታል። ቁርኣን ቅልቅል የፍትወት ሕዋስ ድቅለት"fertilization" ቦታ "የተጠበቀ መርጊያ" ይለዋል፦
23፥13 *ከዚያም "በተጠበቀ መርጊያ" ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው*፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ
77፥21 *"በተጠበቀ መርጊያ" ውስጥም አደረግነው*፡፡ فَجَعَلْنَاهُ فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ

ይህንን ከተረዳን ዘንድ አንድ ፅንስን በእናቱ ማኅፀን ውስጥ በሚፈልገው መልኩ የሚቀርፀው አንዱ አምላክ አላህ ነው፥ ሴት ሁሉ ቀድሞውኑ የምታረግዘውን ያውቃል፡፡ በማኅፀኖች የሚያጎድሉትን የሚጨምሩትንም ያውቃል፥ በማኅፀኖች ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል፦
3፥6 *እርሱ ያ በማኅፀኖችም ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው*፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
13፥8 *"አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ያውቃል፡፡ ማኅፀኖችም የሚያጎድሉትን የሚጨምሩትንም ያውቃል፡፡ ነገሩም ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው"*። اللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَحْمِلُ كُلُّ أُنثَىٰ وَمَا تَغِيضُ الْأَرْحَامُ وَمَا تَزْدَادُ ۖ وَكُلُّ شَيْءٍ عِندَهُ بِمِقْدَارٍ
31፥34 *"አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ዝናብንም ያወርዳል፡፡ በማኅፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም፡፡ አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ عِندَهُ عِلْمُ السَّاعَةِ وَيُنَزِّلُ الْغَيْثَ وَيَعْلَمُ مَا فِي الْأَرْحَامِ ۖ وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ مَّاذَا تَكْسِبُ غَدًا ۖ وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ بِأَيِّ أَرْضٍ تَمُوتُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 9
ኢብኑ ዑመር"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከአላህ በቀር ማንም የማያውቃቸው የሩቅ ነገር መክፈቻዎች አምስት ናቸው። በማኅፀን ውስጥ ምን ሁሉ እንዳለ ከአላህ በቀር ማንም ዐያውቅም፣ ነገ ምን እንደሚከሰት ከአላህ በቀር ማንም ዐያውቅም፣ ዝናብ መቼ እንደሚመጣ ከአላህ በቀር ማንም ዐያውቅም፣ ማንኛይቱም ነፍስ በየትኛው ምድር እንደሞትሞት ከአላህ በቀር ማንም ዐያውቅም፣ ሰአቲቱ መቼ እንደምትቆም ከአላህ በቀር ማንም ዐያውቅም"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَفَاتِيحُ الْغَيْبِ خَمْسٌ لاَ يَعْلَمُهَا إِلاَّ اللَّهُ، لاَ يَعْلَمُ مَا تَغِيضُ الأَرْحَامُ إِلاَّ اللَّهُ، وَلاَ يَعْلَمُ مَا فِي غَدٍ إِلاَّ اللَّهُ، وَلاَ يَعْلَمُ مَتَى يَأْتِي الْمَطَرُ أَحَدٌ إِلاَّ اللَّهُ، وَلاَ تَدْرِي نَفْسٌ بِأَىِّ أَرْضٍ تَمُوتُ إِلاَّ اللَّهُ، وَلاَ يَعْلَمُ مَتَى تَقُومُ السَّاعَةُ إِلاَّ اللَّهُ

በማኅፀን ያለውን ክንውን ሁሉ የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፥ ሰው ሁሉንም ነገር የማወቅ ውስንነት አለበት። “ዒልም” عِلْم‎ ማለት “ዕውቀት” ማለት ሲሆን “ጀህል” جَهْل ማለት ደግሞ “መሃይምነት” ማለት ነው። ከእናቶቻችን ማኅፀኖች ምንም የማናውቅ ሆነን ወጥተናል፦
16፥78 *አላህም ከእናቶቻችሁ "ማኅፀኖች" ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ*፡፡ وَاللَّهُ أَخْرَجَكُم مِّن بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئً
ስለ ፅንስ ዕውቀት ያገኘነው አንደኛ በነቅል ነው፥ "ነቅል" نَقْل ማለት በቁርኣን እና በሐዲስ የሚገኝ ዕውቀት ነው፦
4፥113 *አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍን እና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا

"ዐለመከ" عَلَّمَكَ ማለት "ዐሳወቀህ" ማለት ነው። ሁለተኛው ስለ ፅንስ ዕውቀት ያገኘነው በዐቅል ነው፥ "ዐቅል" عَقْل ማለት በምርምር እና በአሰሳ የሚገኝ ዕውቀት ነው፦
96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

"ዐለመ" عَلَّمَ ማለት "ዐሳወቀ" ማለት ነው። በነቅል ሆነ በዐቅል የሚገኘው ዕውቀት የሚያሳውቅ አሏህ ነው፥ ሁለቱንም ዕውቀት መፈለግ ለእኛ ግዴታችን ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 229
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"*" አሉ፦ *"ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ

ይህንን እሳቤ ይዘን ወደ ፅንስ ጥናት እናመራለን። ሴት ሁሉ የምታረግዘው ሒደት መነሻው ተራክቦ ነው፥ ከራሳችን ጥንድ የምንረካበት ነገር መፈጠሩ ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አሉ፦
30፥21 *"ለእናንተም ከራሶቻችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራት አሉ*"፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

"በዚህ ውስጥ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። "በዚህ" የሚለው ተራክቦ የሚፈጸምበትን ሩካቤ ያሳያል። በዚህ በራሳችን ውስጥ ያለው ሩካቤ ከአስደናቂ ታምራቱ ነው፥ ይህንን ታምራት ወደ ፊት እንደሚያሳየን እና እንደሚያሳውቀን ቃል ገብቶልናል፦
6፥93 ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ *”ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፥ ታውቁታላችሁ»* በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
41፥53 እርሱም ቁርኣን እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ *”በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን*”፡፡ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን? سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِي الْآفَاقِ وَفِي أَنفُسِهِمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الْحَقُّ ۗ أَوَلَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

"በራሳቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃንምን? ቁርኣን ሐቅ መሆኑ ለሁሉም የሚገለጸው የትንሳኤ ቀን ነው። ቁርኣን እውነት ሆኖ በመጣላቸው ጊዜ እነዚያ የካዱት፦ “ይህ ግልጽ ድግምት ነው” አሉ። ነገር ግን አላህ በትንሳኤ ቀን ስለ ቁርኣኑ፦ “ይህ እውነት አይደለምን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ “እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን” ይላሉ፦
46፥7 *”በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ”*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ
46፥34 *”እነዚያም የካዱት ሰዎች በእሳት ላይ በሚቀረቡ ቀን «ይህ እውነት አይደለምን?» ይባላሉ፡፡ «እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን» ይላሉ፡፡ አላህም «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል”*፡፡ وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَلَيْسَ هَـٰذَا بِالْحَقِّ ۖ قَالُوا بَلَىٰ وَرَبِّنَا ۚ قَالَ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

ቁርኣን እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳችን ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቹን በዘመናችን እያሳየን ነው። "ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፥ ታውቁታላችሁ" ያለንን የዕውቀት ዘርፍ በቁርኣን ውስጥ ከተገለጹት የፅንስ ሒደት ጋር እያዛመድን ኢንሻላህ እናቀርባለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፅንስ እና ቁርኣን

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ

"ኑጥፋህ” نُّطْفَة ማለት "የፍትወት ፈሳሽ"sexual fluid" ማለት ነው፥ ይህምም የፍትወት ፈሳሽ የወንዱ የዘር ሕዋስ"sperm cell" እና የሴቷ የእንቁላል ሕዋስ"egg cell" ነው፦
76፥2 *እኛ ሰዉን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንሆን ”ቅልቅሎች” ከሆኑ “የፍትወት ጠብታ” ፈጠርነዉ*፤ ሰሚ ተመልካችም አደረግነዉ። إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

የወንዱ 23 ነጠላ ሕዋስ"haploid" እና የሴቷ 23 ነጠላ ሕዋስ"haploid" በተራክቦ ጊዜ አምሻጅ ይሆናል፥ “አምሻጅ” أَمْشَاج ማለት “ቅልቅል"diploid" ማለት ነው። ከዚህ ቅልቅል የፍትወት ሕዋስ ድቅለት"fertilization" ፅንስ ይፈጠራል፥ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚለው መስተዋድድ ሁለቱን ተቃራኒ ጾታ የሚያመለክት ነው፦
49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ
4፥1 *እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً

"ዘከር" ذَكَر ማለት "ወንድ" ማለት ሲሆን "ኡንሳ" أُنثَىٰ ማለት ደግሞ "ሴት" ማለት ነው። “ከእነርሱም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሁማ” مِنْهُمَا ሲሆን “ሙሰና” مُثَنًّى ነው፥ ሁለቱን ጥንድ ያሳያል። ከሁለቱ ተቃራኒ ፆታ ወንድ እና ሴት ይፈጠራል። የአባት ሀብለ በራሂ"paternal chromosome" ግማሽ 23% የእናት ሀብለ በራሂ"maternal chromosome" 23% ተገናኛተው 46% ሀብለ በራሂ ሕዋስ"diploid" ሆነው ይዋሐዳሉ፦
56፥58 *"በማኅፀኖች የምታፈሱትን አያችሁን?"* أَفَرَأَيْتُم مَّا تُمْنُونَ
56፥59 *እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን?* أَأَنتُمْ تَخْلُقُونَهُ أَمْ نَحْنُ الْخَالِقُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የምታፈሱ" ለሚለው የግስ መደብ የገባ ቃል "ቱምኑ" تُمْنُو መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ማኅፀን ውስጥ የሚፈሰውን የፍትወት ሕዋስ ልጅ አድርጎ የሚፈጥረው አላህ ነው፦
53፥45 *እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድን እና ሴትን ፈጠረ*፡፡ وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ
53፥46 *ከፍትወት ጠብታ በማህጸን ውስጥ በምትፈሰስ ጊዜ*፡፡ مِن نُّطْفَةٍ إِذَا تُمْنَىٰ

"ኢዛ" إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ አንድን ፅንስ ወንድ አሊያም ሴት የሚያደርገው ጥንዶች አውስቦ በሚያደርጉበት ጊዜ ነው። "ቱምና" تُمْنَىٰ ወይም "ዩምና" يُمْنَىٰ የግስ መደብ ሲሆን "የምትፈሰስ" ማለት ነው፥ የስም መደቡ ደግሞ "መኒይ" مَّنِىّ ማለትም "የዘር ሕዋስ"semen" ነው፦
75፥37 *የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?* أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ
75፥38 *ከዚያም "የረጋ ደም" ሆነ፥ ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም*፡፡ ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ
75፥39 "ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን አደረገ"፡፡ فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ

"ዐለቃህ" عَلَقَة ማለት "የረጋ ደም" ማለት ሲሆን የሰዋስው መደቡ “ሙአነስ” مُؤَنَّث ማለትም “አንስታይ መደብ" ነው፥ ምክንያቱም “ታ” ة የምትባለው “ታእ-መርቡጧህ” تَاء مَرْبُوطَة በ "ዐለቅ" عَلَق ላይ መድረሻ ቅጥያ ሆና ስለመጣች ነው። ከረጋው ደም የፆታ ውሳኔ"Sex-determination" ቢሆን ኖሮ "ሚን-ሃ" مِنْهَا ማለትም "ከእርሷ" የሚል መስተዋድ ያለበት ተሳቢ ይጠቀም ነበር፥ ቅሉ ግን የተጠቀመው "ሚን-ሁ" مِنْهُ ማለትም "ከእርሱ" የሚል መስተዋድ ያለበት ተሳቢ ስለሆነ "እርሱ" የተባለው ዐውደ-ንባቡ ላይ ያለው "መኒይ" مَّنِىّ ነው፥ "መኒይ" ደግሞ የሰዋስው መደቡ “ሙዘከር” مُذَكَّر ማለትም “ተባዕታይ መደብ" ነው።
የወንዱ መንይ "XY" ነው፥ ወንዱ "Y" ከላከ ከሴቷ "X" ጋር ሲገናኝ ወንድ ይሆናል፥ ወንዱ "X" ከላከ ከሴቷ "X" ጋር ሲገናኝ ሴት ትሆናለች። ከወንዱ የዘር ፈሳሽ ወንድ ወይም ሴት ፆታ ውሳኔ ስለሚወሰን "ከእርሱም" ማለትም "ከመንይ" ሁለት ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን አደረገ" ይለናል፥ የሚያጅበው ወንድ ወይም ሴት መሆን በቅድመ-ተከተል ከኑጥፋህ ቀጥሎ መሆኑ ነው፦
35፥11 *"አላህም ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም "አዝዋጅ" አደረጋችሁ"*፡፡ وَاللَّهُ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ جَعَلَكُمْ أَزْوَاجًا
"አዝዋጅ" أَزْوَاج የሚለው ቃል "ዘውጅ" زَوْج ለሚለው ብዜት ሲሆን ለወንድ እና ለሴት ተቃራኒ "ዘውጀይኒ" زَّوْجَيْنِ በሚል መጥቷል፥ "ከእርሱ(ከመንይ) ሁለት ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን አደረገ" የሚለው ይህንኑ ነው።
የወንዱ የዘር ሕዋስ"semen" ሆነ የሴቷ እንቁላል ሕዋስ ከጀርባ እና ከእርግብግብቶች "መካከል" ይወጣል፦
86፥5 *ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት*፡፡ فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ
86፥6 *"ከተስፈንጣሪ ውኃ ተፈጠረ"*፡፡ خُلِقَ مِن مَّاءٍ دَافِقٍ
86፥7 *"ከጀርባ እና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ"*፡፡ يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ

"ሱልብ" صُّلْبِ የሚለው የወንዱን የዘር ሥርወ-አብራክ"loin" ለማመልከት "ዘህር" ظَهْر በሚል መጥቷል፦
7፥172 *ጌታህም "ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን" ባወጣ እና «ጌታችሁ አይደለሁምን?» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ የኾነውን አስታውስ*፡፡ وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِن بَنِي آدَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ

"ዙሁር" ظُهُور የሚለው "ዘህር" ظَهْر ለሚለው ብዜት ነው። ልክ እንደ ባይብሉ በፍካሬአዊ ሥርወ-አብራክን ለማመልከት "ከጉልበት" "ከወገብ" "ከሆድ" ዘር ይወጣል" እንደሚለው ማለት ነው፦ 2ኛ ሳሙኤል 7፥12 1ኛ ነገሥት 8፥19 መዝሙር 132፥11 ሐዋርያት ሥራ 2፥30 ዘፍጥረት 15፥4 ዘጸአት 1፥5

በተመሳሳይ የሴቷን እንቁላል ሥርወ-አብራክ "ተራኢብ" تَّرَائِبِ ይለዋል፥ "ተራኢብ" የሚለው ቃል "በጥን" بَطْن በሚል ይመጣል፦
3፥35 *የዒምራን ባለቤት «ጌታዬ ሆይ! እኔ "በሆዴ" ውስጥ ያለውን ፅንስ ከሥራ ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና» ባለች ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

"ሆዴ" ለሚለው ቃል "በጥኒ" بَطْنِي ሲሆን "በጥን" بَطْن ለሚለው አገናዛቢ ነው። "ሆድ" የሚለው "ማኅፀን" የሚለውን ለማመልከት ባይብሉ ላይም መጥቷል፦
ዘፍጥረት 30፥2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ *የሆድን ፍሬ* በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት።

እዚህ ጋር "ፍሬ" የተባለው የራሔል እንቁላል ሲሆን "የሆድ ፍሬ" ተብሏል። የሴት እንቁላል ሆድ ውስጥ የለም። ቅሉ ግን "ሆድ" የሚለው ማኅፀንን ለማመልከት፥ ማኅፀንም እንቁልጢን እንደሚያጠቃልል እሙን ነው።
"ሱልብ" صُّلْبِ የሚለው "ዘህር" ظَهْر በሚለው፥ "ተራኢብ" تَّرَائِبِ የሚለው "በጥን" بَطْن በሚለው ፍካሬአዊ ሆኖ የመጣው ልክ "ሶድር" صَدْر ማለትም "ደረት" የሚለው "ቀልብ" قَلْب የሚለውን ፍካሬአዊ ሆኖ በመጣበት ስሌትና ቀመር ነው፦
64፥4 *አላህም "በደረቶች" ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው*፡፡ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ
15፥51 *”አላህም "በልቦቻችሁ" ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል*፡፡ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِي قُلُوبِكُمْ

እዚህ ድረስ ከተግባባን የወንድ ሀብለ በራሂ "XY" ሲሆን የሴት ሀብለ በራሂ ደግሞ "XX" ነው። ከወንድ "Y" መጥቶ ከሴት "X" ከመጣ ሽሉ የአባቱን ፆታ በመያዝ "ወንድ" ይሆናል፥ ከወንድ "X" መጥቶ ከሴት "X" ከመጣ ሽሉ የእናቱን ፆታ በመያዝ "ሴት" ይሆናል። ይህ የዘረ-መል ጥናት"genetics" ከመምጣቱ በፊት ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በሐዲስ እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60 , ቁጥር 4
አነሥ"ረ.ዐ." እንደተተከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ልክ የልጆች ከወላጆቻቸው መመሳሰል እንዲህ ነው፥ ተባዕቱ ከእንስቱ ጋር ተራክቦ ባደረገ ጊዜ የእርሱ ውኃ ከቀደመ እርሱን ይመስላል፤ የእርሷ ውኃ በቀደመ ጊዜ ደግሞ እርሷን ይመስላል"*። عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَمَّا الشَّبَهُ فِي الْوَلَدِ فَإِنَّ الرَّجُلَ إِذَا غَشِيَ الْمَرْأَةَ فَسَبَقَهَا مَاؤُهُ كَانَ الشَّبَهُ لَهُ، وَإِذَا سَبَقَ مَاؤُهَا كَانَ الشَّبَهُ لَهَا

"ማእ" مَاء ማለት "ውኃ" ማለት ሲሆን ሀብለ በራሂ"chromosome" ነው። አር-ረጁል" الرَّجُل ማለት "ተባዕት" ወይም "ወንድ" ማለት ነው፥ "አል-መርኣህ" الْمَرْأَة ደግሞ "እንስት" ወይም "ሴት" ማለት ነው። "ለ-ሁ" لَهُ ማለትም "ለ-እርሱ" ለወንዱ የእርሱ ሀብለ በራሂ "XY" ከሆነ ሽሉ ወንድ ይሆናል፥ በተቃራኒው "ለ-ሃ" لَهَا ማለትም "ለ-እርሷ" ለሴቷ የእርሷ ሀብለ በራሂ "XX" ከሆነ ሽሉ ሴት ይሆናል። "ነሥል" نَسْل ማለት "ዘር" ማለት ሲሆን ይህም ዘር የተንጣለለ ውኃ ነው፦
32፥8 **ከዚያም ዘሩን ከተንጣለለ፣ ከደካማ ውኃ ያደረገ ነው"*፡፡ ثُمَّ جَعَلَ نَسْلَهُ مِن سُلَالَةٍ مِّن مَّاءٍ مَّهِينٍ
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ 32፥8 *"ከዚያም ነሠሉን" ማለት "ዘሩን ማለት ነው፣ "ከተንጣለለ" ማለት "የፍትወት ሕዋስ"(ኑጥፋህ) ማለት ነው፣ "ከደካማ ውኃ" ማለት "ከወንድ እና ከሴት ውኃ ደካማው የፍትወት ሕዋስ(ኑጥፋህ) ነው"*። { ثُمَّ جَعَلَ نَسْلَهُ } ذريته { مِن سُلاَلَةٍ } نطفة { مِّن مَّآءٍ مَّهِينٍ } من نطفة ضعيفة من ماء الرجل والمرأة
የሚያጅበው ሕዋስ"cell" በራሱ 80% ሳይቶፕላዝም"Cytoplasm" የሚባል ውኃ ነው። በተራክቦ ዙሪያ ወንድ እና ሴት ሁለት ዐበይት የፍትወት ፈሳሽ አላቸው። አንደኛው "መዝይ" مَذْي ማለት ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግና የሚያጣብቅ ቀለም አልባ እና ሽታ አልባ ቀጭን ፈሳሽ"Squirting fluid" ነው፥ መዝይ የሚመነጨው "Skene's gland" ከሚባል ቦታ ነው። ሁለተኛው "መኒይ" مَّنِىّ ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ የወንዱ ነጭና ወፍራም ፈሳሽ ሴቷ ብልት ውስጥ የሚፈስ ሲሆን የሴቷ ደግሞ ቀጭንና ቢጫ"follicle" ውስጧ የሚፈስ ነው። የወንዱ ከቆለጥ"testicle" ሲመጣ የሴቷ ከእንቁልጢ"ovary gland" የሚመጣ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 543
ዐሊይ እንደተረከው፦ *የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ስለ መዝይ ተጠየቁ። እርሳቸውም፦ "እርሱ(መዝይ) ውዱእ ያስፈልገዋል፥ መኒይ ደግሞ ጉሥል ያፈልገዋል" አሉ"*። عَنْ عَلِيٍّ، قَالَ سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنِ الْمَذْىِ فَقَالَ ‏ "‏ فِيهِ الْوُضُوءُ وَفِي الْمَنِيِّ الْغُسْلُ

"ጉሥል" غُسْل ማለት "ሙሉ ትጥበት" ማለት ነው። የወንዱ ሆነ የሴቷ መዲይ ለተራክቦ መሰናዶ እንጂ በሽል ላይ የሚያበረክተው ነገር የለም፥ የወንዱ ሆነ የሴቷ መኒይ ግን ለአንድ ሽል መፈጠር መንስኤ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 3, ሐዲስ 32
ዐነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገበው፦ "ኡሙ ሡለይም እንደተረከችው፦ *"ወንድ እንደሚያይ ሴትም በህልሟ እደምታይ የአላህን ነቢይ"ﷺ" ጠየቀች፥ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "ሴት ተጸዐቦ በምታደርግ ጊዜ ጉሥል ታድርግ" አሉ። ኡሙ ሡለይምም፦ "ከዚያ ጉዳይ አሳፈረኝ" አለች፥ በመቀጠል፦ "ይህ ይሆናልን? አለች። የአላህ ነቢይም"ﷺ"፦ "አዎ! ካልሆነ ልጁ እናቱን እንዴት ይመስላል? የወንዱ ውኃ ነጭና ወፍራም ሲሆን የሴቷ ውኃ ደግሞ ቀጭንና ቢጫ ነው። መመሳሰል የሚሆነው ከሁለቱ የበላይ ከሆነው ወይም ከቀደመው ነው" አሉ"*። أَنَّ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ، حَدَّثَهُمْ أَنَّ أُمَّ سُلَيْمٍ حَدَّثَتْ أَنَّهَا، سَأَلَتْ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنِ الْمَرْأَةِ تَرَى فِي مَنَامِهَا مَا يَرَى الرَّجُلُ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ إِذَا رَأَتْ ذَلِكِ الْمَرْأَةُ فَلْتَغْتَسِلْ ‏"‏ ‏.‏ فَقَالَتْ أُمُّ سُلَيْمٍ وَاسْتَحْيَيْتُ مِنْ ذَلِكَ قَالَتْ وَهَلْ يَكُونُ هَذَا فَقَالَ نَبِيُّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ نَعَمْ فَمِنْ أَيْنَ يَكُونُ الشَّبَهُ إِنَّ مَاءَ الرَّجُلِ غَلِيظٌ أَبْيَضُ وَمَاءَ الْمَرْأَةِ رَقِيقٌ أَصْفَرُ فَمِنْ أَيِّهِمَا عَلاَ أَوْ سَبَقَ يَكُونُ مِنْهُ الشَّبَهُ

ለወንዱ የእርሱ ሀብለ በራሂ "XY" ከሆነ የበላይ ሆኖ ይቀድምና ሽሉ ወንድ ይሆናል፥ በተቃራኒው ለሴቷ የእርሷ ሀብለ በራሂ "XX" ከሆነ ከሆነ የበላይ ሆኖ ይቀድምና ሽሉ ሴት ይሆናል። "ተጸዐቦ"nocturna sex" ሳንፈልግ በህልም የሚደረግ ተራክቦ ነው። ይህ ተጸዐቦ ልክ እንደ እውኑ ተራክቦ ጉሥል ይወጅብብናል።ኢንሻሏህ ስለ ተቀሩት የፅንስ ደረጃ በሚቀጥለው ክፍል እናያለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፅንስ እና ቁርኣን

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

23፥67 *"እርሱ ያ ከዐፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሕጻናት አድርጎ ያወጣችኋል"*፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ يُخْرِجُكُمْ طِفْلًا

የወንዱ የዘር ሕዋስ እና የሴቷ እንቁላል ሕዋስ የሕውደት ሕዋስ"zygote" ከሆነ ከሠላሳ ሰዓት በኃላ 2 ሕዋስ ይሆናል፥ ከአርባ ሰዓት በኃላ 4 ሕዋስ ይሆናል። ከዚያ 8 ሕዋስ፣ በሦስተኛው ቀን ከ 12-16 ሕዋስ ይሆናል። ከዚያ በአራተኛ ቀን 32 ሕዋስ ይሆንና ወደ ማኅፀን ግድግዳ ይለጠፋል። ይህ ኑጥፋህ በ 21 ቀን "ዐለቃህ" ይሆናል፦
75፥37 *የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?* أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ
75፥38 *ከዚያም "የረጋ ደም" ሆነ፥ ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም*፡፡ ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ

"ካነ" كَانَ ማለትም "ሆነ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በ 21 ቀናት ሒደት ዐለቃ የሆነው መንይ ነው፥ “ዐለቃህ” عَلَقَة ማለት “አልቅት”leech” ወይም “የረጋ ደም”blood-clot” ማለት ነው። ይህን የፅንስ ሁለተኛው ደረጃ ከሚታይ አልቅት ከሚባል የባህር ትል”insect” እና ከረጋ ደም ጋር ስለሚመሳሰል ነው፦
40፥67 *እርሱ ያ ከአፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው*። هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ يُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوا أَشُدَّكُمْ ثُمَّ لِتَكُونُوا شُيُوخًا
23፥67 *"እርሱ ያ ከዐፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሕጻናት አድርጎ ያወጣችኋል"*፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ يُخْرِجُكُمْ طِفْلًا

“ሱመ” ثُمَّ ማለት “ከዚያም” ማለት ሲሆን ቅድመ-ተከተልን ያሳያል። ይህ ዐለቃህ ከ 24-26 ባሉት ቀናት በሒደት ሙድጋህ ይሆናል፥ “ሙድጋ” مُضْغَة ማለት “ቁራጭ ስጋ”embryonic lump” ወይም “የታኘከ ስጋ”chewed gum” ማለት ሲሆን ልክ ጥርስ እንዳረፈበት ስጋ የሚመስልበት የፅንስ ደረጃ ነው፦
23፥14 *ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን*። ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً

ከ 21-24 ቀናት የረጋ ደም ጊዜ ሲሆን 24ኛ ቀን ላይ በቅፅፈት የታኘከ ስጋ ቅርፅ ይጀምና ከዚያ እስከ 42ኛው ቀን ይቆያል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 80
ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ "እውነተኛ ታማኝ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የእያንዳንዳቹህ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ሂደቱ በአርባ መአልትና ሌሊት ይሰበሰባል። ከዚያም በተመሳሳይ ጊዜ ዐለቃህ ይሆናል፣ ከዚያም በተመሳሳይ ጊዜ ሙድጋህ ይሆናል። ከዚያም መልአክ ወደ እርሱ ይላካል፥ አራት ነገሮች እንዲጽፍ ይታዘዛል"*። سَمِعْتُ زَيْدَ بْنَ وَهْبٍ، سَمِعْتُ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ مَسْعُودٍ ـ رضى الله عنه ـ حَدَّثَنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَهْوَ الصَّادِقُ الْمَصْدُوقُ "‏ إِنَّ خَلْقَ أَحَدِكُمْ يُجْمَعُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا وَأَرْبَعِينَ لَيْلَةً، ثُمَّ يَكُونُ عَلَقَةً مِثْلَهُ، ثُمَّ يَكُونُ مُضْغَةً مِثْلَهُ، ثُمَّ يُبْعَثُ إِلَيْهِ الْمَلَكُ فَيُؤْذَنُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ،

"ሚስለ-ሁ" مِثْلَهُ ማለት "ተመሳሳይ ጊዜ" ማለት ነው፥ "ሚስል" مِثْل በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ የገባው ተሳቢ "ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የተባለው መጀመሪያ የተጠቀሰው 40 መአልትና ሌሊት የሚለው ተክቶ የመጣ ነው። እዚህ ሐዲስ ላይ የጽንሱ ሁለቱ ሒደት በአርባ መአልትና ሌሊት እንደሚካሄድ ይናገራል፥ ይህም ሂደት "ዐለቃህ" عَلَقَة ማለትም "የረጋ ደም" እና "ሙድጋህ" مُضْغَة ማለትም "ቁራጭ ስጋ" መሆን ነው። ይህ ዘገባ በኢማም ሙሥሊም እንዲህ ተዘግቧል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 1
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "እውነተኛ ታማኝ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የእያንዳንዳቹህ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ሂደቱ በአርባ ቀናት ይሰበሰባል። ከዚያም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ያ ዐለቃህ ይሆናል፣ ከዚያም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ያ ሙድጋህ ይሆናል። ከዚያም መልአክ ወደ እርሱ ይላካል እና በእርሱ ሩሕ ይነፋል። እርሱም አራት ነገሮችን ሲሳዩን፣ ፍጻሜውን፣ ሥራውን እና ሐዘኑን ወይም ደስታው እንዲጽፍ ይታዘዛል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ حَدَّثَنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَهُوَ الصَّادِقُ الْمَصْدُوقُ "‏ إِنَّ أَحَدَكُمْ يُجْمَعُ خَلْقُهُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا ثُمَّ يَكُونُ فِي ذَلِكَ عَلَقَةً مِثْلَ ذَلِكَ ثُمَّ يَكُونُ فِي ذَلِكَ مُضْغَةً مِثْلَ ذَلِكَ ثُمَّ يُرْسَلُ الْمَلَكُ فَيَنْفُخُ فِيهِ الرُّوحَ وَيُؤْمَرُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ بِكَتْبِ رِزْقِهِ وَأَجَلِهِ وَعَمَلِهِ وَشَقِيٌّ أَوْ سَعِيدٌ

"ሚስለ ዛሊከ" مِثْلَ ذَلِكَ ማለት "ተመሳሳይ ጊዜ" ማለት ነው፥ "ዛሊከ" ذَلِكَ ማለትም "ያ" የተባለው መጀመሪያ የተጠቀሰው 40 መአልትና ሌሊት ነው። "ፊ ዛሊከ" فِي ذَلِكَ ማለት "በዚያ ውስጥ" ማለት ሲሆን በአርባ ቀናት ውስጥ ኑጥፋህ የነበረው ዐለቃህ እና ሙድጋህ ይሆናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 4
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ኑጥፋህ ወደ ማኅፀን ከገባ አርባ ሁለት ሌሊት በሆነ ጊዜ አላህ ወደ እርሱ መልአክ ይልክና ቅርጹን ያሳምራል። አላህ ለእርሱ መስሚያውን፣ ማያውን፣ ቆዳውን፣ ጡንቻ፣ አጥንት ይፈጥርለታል"*። فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ إِذَا مَرَّ بِالنُّطْفَةِ ثِنْتَانِ وَأَرْبَعُونَ لَيْلَةً بَعَثَ اللَّهُ إِلَيْهَا مَلَكًا فَصَوَّرَهَا وَخَلَقَ سَمْعَهَا وَبَصَرَهَا وَجِلْدَهَا وَلَحْمَهَا وَعِظَامَهَا
እዚህ ጋር ልብ አድርግ በኑጥፋህ እና በመአልኩ መላክ ያለው የጊዜ ክፍተት 42 ቀናት ከሆነ በአርባ ቀናት ውስጥ ኑጥፋህ የነበረው ዐለቃህ እና ሙድጋህ ይሆናል ማለት ነው፥ ምክንያቱም መልአኩ የሚመጣው ኑጥፋህ የነበረው ዐለቃህ እና ሙድጋህ ከሆነ በኃላ ስለሆነ ነው። ሙድጋህ ጅማት፣ አንጀት፣ ስስ ጡንቻ፣ ስስ የደም ስር ነው። ከ 42-56 ባሉት ቀናት የፆታ ብልት ይታያሉ። ከዚያም ሙድጋህ ዒዛም ይሆናል፦
23፥14 *ቁራጯንም ሥጋ “አጥንቶች” አድርገን ፈጠርን*። فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا

“ዐዝም” عَظْم ማለት “አፅም”skeleton” ወይም “አጥንት”bone” ማለት ነው፥ የዐዝም ብዙ ቁጥር ደግሞ “ዒዛም” عِظَام ነው። በአጥንት ወቅት የደም ዝውርውር፣ የነርቭ ሥርዓት፣ አፅም ወዘተ የሚፈጠርበት ሂደት ነው። ስስ ጡንቻ እና አጥንት ከመካከለኛ ክፍል"Meso-derm" አብረው የሚያድጉ ናቸው፥ ከዚያም በቅጽፈት ዒዛምን ስጋ ይለብሳል፦
23፥14 *አጥንቶቹንም “ሥጋን” አለበስናቸው*። فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا

“ለህም” لَحْم ማለት “ስጋ” ማለት ሲሆን ይህ ስጋ ጠንካራ ጡንቻ ያለው ስጋ ነው፥ በዚህ ደረጃ ላይ ልብ፣ አንጎል፣ ቆዳ፣አይን፣ አፍንጫ ወዘተ የሚፈጠርበት ሂደት ነው። ከዚያም ሌላ ፍጥረት አድርጎ ያስገኘዋል፦
23፥14 *ከዚያም “ሌላ ፍጥረትን” አድርገን “አስገኘነው”*። ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡ ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

“ነሽአህ” نَّشْأَة የሚለው ቃል “አንሸአ” أَنشَأَ ማለትም “አስገኘ” ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን “ግኝት”production” ማለት ነው፥ አላህም “አንሸናሁ” أَنْشَأْنَاهُ ማለትም “አስገኘነው” ይለናል። ይህም ፅንስ እስከ መወለድ ጊዜ ያለው ሽልን የሚያመለክት ሲሆን “ሌላ ፍጥረትን” ይለዋል፥ በዚህ ጊዜ ከንፈር፣ ጥፍር፣ ፀጉር ወዘተ የሚገኘበት ጊዜ ነው። ፍጥረትዋ ሙሉ ካልሆነች ጅማት፣ አንጀት፣ ስስ ጡንቻ፣ ስስ የደም ስር ወዘተ የነበረችው ከመፍጠር በኋላ ፍጥረትዋ ሙሉ ትሆንና ይፈጥረናል፥ ከዚያስ? ከዚያማ የሚሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማሕፀን ውስጥ ያቆየንና ከዚያም ሕፃን ሆነን ያወጣናል፦
22፥5 እናንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ በመጠራጠር ውስጥ እንደ ሆናችሁ አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ፡፡ እኛም ከዐፈር ፈጠርናችሁ፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ ሥጋ፣ *ፍጥረትዋ ሙሉ ከሆነችና ሙሉ ካልሆነች ችሎታችንን ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፡፡ የምንሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማሕፀን ውስጥ እናረጋዋለን፡፡ ከዚያም ሕፃን ሆናችሁ እናወጣችኋለን*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِن كُنتُمْ فِي رَيْبٍ مِّنَ الْبَعْثِ فَإِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ مِن مُّضْغَةٍ مُّخَلَّقَةٍ وَغَيْرِ مُخَلَّقَةٍ لِّنُبَيِّنَ لَكُمْ ۚ وَنُقِرُّ فِي الْأَرْحَامِ مَا نَشَاءُ إِلَىٰ أَجَلٍ مُّسَمًّى ثُمَّ نُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوا أَشُدَّكُمْ

የአምላካች የአላህ ፍጥረት የሚያጅብ ነው። በማኅፀን ውስጥ ሽል የተለያየ ደረጃ ኖሮት በተለያየ ኹኔታዎች እንደሚፈጠር በተከበረ ቃሉ ነግሮናል፦
71፥14 *በልዩ ልዩ ኹኔታዎች በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲኾን*፡፡ وَقَدْ خَلَقَكُمْ أَطْوَارًا

ሥነ-ፅንስ ጥናት አንድ ርእሰ ጉዳይ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ አርስት ነው፥ ይህ ተከታታይ መጣጥፍ ስንክሳር አርጋችሁ እንደምትይዙት ተስፋ አደርጋለው። አላህ በቁርኣን ዕውቀት ተጠቃሚ ያድርገን! አሚን።

"""""""""""ተፈጸመ""""""""""""

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዲሞክራሲ ወይስ ቴኦክራሲ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥48 በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

ኢሥላም አጠቃላይ የሕይወት ዘይቤ እና እሴት አቅፏል፥ ይህም ዘይቤ እና እሴት መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ነው። “ፓለቲካ” πολιτικά ማለት "ሥነ-መንግሥት" ማለት ነው፥ “ሥን” የሚለው ቃል "ጥናት"logy" ማለት ነው። በጥቅሉ ስለ መንግሥት የሚያጠናው የዕውቀት ዘርፍ ፓለቲካ ይባላል። በመንግሥት ውስጥ ሁለት ተቃራኒ ሥርዓት አሉ፥ አንደኛው የዲሞክራሲ ሥርዓት ሲሆን ሁለተኛው የቴኦክራሲ ሥርዓት ነው።
"ዲሞክራሲ" δημοκρατία ማለት የሁለት ግሪክ ቃላት ውቅር ነው፥ “ዴሞስ” δημος ማለት “ሕዝብ” ማለት ሲሆን “ክራቶስ” κράτος ማለት "አገዛዝ" ማለት ነው። በጥቅሉ “የሕዝብ አገዛዝ” ማለት ነው። ይህ አሠራር ከቴኦክራሲ ጋር የሚቃረን ሦስት የተዛቡ የሥነ-መንግስት ቅርፅ አለው፥ እርሱም "አት-ተሽሪዒይ” التَشْرِعِي "አል-ቀዷእ" القَضَاء እና "አት-ተንፊዝ" التَنْفِذ ናቸው። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"አት-ተሽሪዒይ"
"ተሽሪዒይ” تَشْرِعِي የሚለው ቃል “ሸረዐ” شَرَّعَ‎ ማለትም “ደነገገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ድንጋጌ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው። ይህ ሕግ ከአላህ ዘንድ ወደ ነቢያቱ የሚወርድ ነው፥ “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት እራሱ “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው፦
45፥18 ከዚያም ከትእዛዝ *በትክክለኛይቱ ሕግ* ላይ አደረግንህ፡፡ ስለዚህ ተከተላት፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَاتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَ الَّذِينَ لَا يَعْلَمُون

እዚህ አንቀጽ ላይ “ትክክለኛይቱ ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሸሪዓህ” شَرِيعَة የሚል ነው፥ ይህም ቃል “ሺርዓህ” شِرْعَة ማለትም “ሕግ” ከሚል ቃል የመጣ ነው፦
5፥48 በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አምላካችን አላህ”ﷻ” ለሁሉም መልእክተኞች ሕግን እና መንገድን አድርጓል፥ ይህ ሕግ ሰዎች እውነትን ከሐሰት፣ መልካሙን ከክፉ፣ ትክክሉን ከስህተት የሚለዩበት ሚዛን ነው፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችን እና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን፥ *፡፡لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ

ይህንን ሕግ የሚያወጣው ሕግ አውጪ አላህ ብቻ ሆኖ ሳለ በዲሞክራሲ ፓርላማ ውስጥ ሕግን የሚያረቁት ሕግ አውጪዎች ሰዎች ናቸው፥ እነርሱም ወንድና ወንድ እና ሴት እና ሴት መጋባትን፣ ኸምር መጠጣት፣ የእሪያ ስጋ መብላት ሐላል አርገውቷል። በቅርቡ ሰው ከእንስሳ ጋር መጋባት ሐላል እንዲሆን ወረቀት ገብቷል፥ ከአንድ በላይ ማግባት ሐራም ነው ይላል፤ ከአንድ በላይ ዝሙት ማድረግ አያስጠይቅም ሐላል ነው ይላል። ስለዚህ የዲሞክራሲ ፓርላማ ከመነሻው ዝንባሌን ከመከተል የሚመጣ ነው፦
4፥135 *”እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

“አህዋእ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” ማለት ነው፥ ዝንባሌ ደግሞ ቦታ ከተሰጠው ሊመለክ የሚችል ጣዖት ነው፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا
ነጥብ ሁለት
"አል-ቀዷእ"
"ቀዷእ" قَضَاء የሚለው ቃል "ቀደ" قَضَى ማለትም "ፈረደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፍርድ" ማለት ነው፥ የቀዷእ ተለዋዋጭ ቃል "ሑክም" حُكْم‎ ሲሆን "ፍርድ" ማለት ነው፦
5፥48 በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

“ፍረድ” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “ፈሕኩም” فَاحْكُمْ ሲሆን “ሑክም” ለሚለው የግስ መደብ ነው፥ “አሕካም” أَحْكَام‎ ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فَرْد‎ ማለትም “የታዘዘ” ግዴታ ነው።
2ኛ. “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ሡናህ ነው።
3ኛ. “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ ማለትም “የተፈቀደ” ሐላል ነው።
4ኛ. “መክሩህ” مَكْرُوه‎ ማለትም “የተጠላ” ድርጊት ነው።
5ኛ. “ሐራም” حَرَام ማለትም “የተከለከለ” ድርጊት ነው።

አንድን ነገር ፈድር፣ ሙስተሐብ፣ ሙባሕ፣ መክሩህ፣ እና ሐራም ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፥ የካፊርን ፍርድ መፈለግና ከአላህ ይበልጥ ፍርዱ ያማረ ማንነት መሻት ቂልነት ነው፦
5፥50 *"የመሃይምንነትን ፍርድ ይፈልጋሉን? ለሚያረጋግጡም ሰዎች ከአላህ ይበልጥ ፍርዱ ያማረ ማን ነው?* أَفَحُكْمَ الْجَاهِلِيَّةِ يَبْغُونَ ۚ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّهِ حُكْمًا لِّقَوْمٍ يُوقِنُونَ
12፥40 *ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፡፡ እርሱን እንጅ ሌላን እንዳታመልኩ አዟል*፡፡ ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ إِنِ الْحُكْمُ إِلَّا لِلَّهِ ۚ أَمَرَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

ሑክም የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፡፡ እርሱን እንጅ ሌላን እንዳታመልኩ አዟል። አላህም ባወረደው ነገር አለመፍረድ አመጽ ነው፦
5፥45 *አላህም ባወረደው ነገር የማይፈርዱ እነዚያ አመጸኞቹን እነርሱ ናቸው*፡፡ وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

ለዚህ ነው እኛ ሙሥሊሞች የሙሥሊም የሸሪዓህ ፍርድ ቤት ያለን። የሴኩላሩ ፍርድ ቤት በፓርላማ የረቀቀውን ሰው ሠራሽ ሕግ ይፈርዳል። አላህ ያወረደው ከመከተል ይልቅ ዝንባሌን መከተል ማዳላት ያመጣል፦
4፥135 *”እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

ነጥብ ሦስት
"አት-ተንፊዝ"
"ተንፊዝ" تَنْفِذ የሚለው ቃል "ነፈዘ" نَفَّذَ‎ ማለትም "አስፈጸመ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማስፈጸም"execution" ማለት ነው። ሕጉ ከቁርኣን እና ከሐዲስ ታይቶ በቃዲእ ከተበየነ በኃላ ወደ ፍጻሜ ይሄዳል፥ ይህ አፈጻጸም ነው።

እንግዲህ ከላይ ያሉትን ሦስት የተዛቡ የሥነ-መንግስት ቅርፅ "አት-ተሽሪዒይ” "አል-ቀዷእ" እና "አት-ተንፊዝ" መያዝ ያለበት ቴኦክራሲ ሆኖ ሳለ ከዘመነ-አብርኆት ጊዜ በኃላ ድብቁ የኢሉሚናቲ ሴራ የሆነው ዲሞክራሲ ቦታውን ይዞታል። "ቴኦክራሲ" θεοκρατία ማለት የሁለት ግሪክ ቃላት ውቅር ነው፥ “ቴኦስ” θεός ማለት “አምላክ” ማለት ሲሆን “ክራቶስ” κράτος ማለት "አገዛዝ" ማለት ነው። በጥቅሉ “የአምላክ አገዛዝ” ማለት ነው። የዛሬን አያርገውና የክርስትናው "ሲኖዶስ" σῠ́νοδος ማለትም "ጉባኤ" መመሪያው ቴኦክራሲ ነበር፥ ሲገዝቱና ሲያወግዙ "በሕግ አምላክ" ነበር። በቴኦክራሲ ሥርዓት ውስጥ ሕገ-መንግሥቱ የአምላክ ንግግር ነው። ዲሞክራሲ ማለት ነጻነት ማለት ሳይሆን የኢሉሚናቲ መጫረቻና መጫወቻ ልቅነት ነው፥ ሥልጣኔ በምጣኔ አውንታዊ ነገር ሆኖ ሳለ የኢሉሚናቲ ዲሞክራሲ መሠልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው። የቱን ትመርጣለህ የኢሉሚናቲ ሴራ ዲሞክራሲ ወይስ የነቢያት ትምህርት ቴኦክራሲ? ምርጫው የአንተ ነው። ግን በዲሞክራሲ ሥርዓት ተገደን የምንኖር ሰዎች ልክ እንደ ሐራሙ የወረቀት ንዋይ”Fiat money” ስለተገደድን ምርጫ የለንም፥ "የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም" فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ምን ይደረጋል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገደዱበትን ነገር አንስቷል"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ

አላህ ቴኦክራሲን በማምጣት ነስሩን ያቅርብልን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሚን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

1፥7 *የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፥ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ*፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ

"አሚን" أَمِين የሚለው ቃል "አሚነ" أَمِنَ‎ ማለትም "አመነ" "ተስማማ" "ተዋዋለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አምኛለው" "ተስማምቻለው" "ተዋውያለው ይሁንልኝ" ማለት ነው። "አሜን" የሚለው የግዕዙም ቃል ተመሳሳይ ትርጉም አለው፦
1፥7 *የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፥ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ*፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4475
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ኢማሙ፦ “ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” ባለ ጊዜ "አሚን" በሉ። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ إِذَا قَالَ الإِمَامُ ‏{‏غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ فَقُولُوا آمِينَ‏.

አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፥ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው። ነገር ግን ከአይሁዳውያን ጥቂት ያልተቆጣህባቸውን እና ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱትንም ተውሒድን የሚከተሉ ሰዎች ከቁርኣን መውረድ በፊት ስላሉ፥ እነርሱ የሄዱበትት ቀጥተኛው መንገድ ምራን ብለን ዱዓእ እናደርግና ስንጨርስ አሚን እንላለን፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3212
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፥ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው። ‏ عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ

ይህ ሶላት ላይ ሱረቱል ፋቲሓህ በሚቀራበት ጊዜ ነው። የሰው አሚን ከመላእክት አሚን ጋር ከተስማማ አላህ ለእርሱ የቀደመውን ኀጢአቱን ይቅር ይለዋል፦
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 11, ሐዲስ 50
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *"ቃሪእ "አሚን" ባለ ጊዜ እናንተም እንዲሁ "አሚን" በሉ! መላእክትም ይላሉ። የሰው አሚን ከመላእክት አሚን ጋር ከተስማማ አላህ ለእርሱ የቀደመውን ኀጢአቱን ይቅር ይለዋል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِذَا أَمَّنَ الْقَارِئُ فَأَمِّنُوا فَإِنَّ الْمَلاَئِكَةَ تُؤَمِّنُ فَمَنْ وَافَقَ تَأْمِينُهُ تَأْمِينَ الْمَلاَئِكَةِ غَفَرَ اللَّهُ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ

በተጨማሪም ነቢያችን”ﷺ” ሱረቱል ፋቲሓን ላይ ያለው ዱዓእ የአላህ ባሪያ አላህን የሚያነጋግርበት ዱዓእ እንደሆነ አበክረውና አዘክረው ነግረውናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4 ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው *ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ “የቁርኣን እናት ሳያነብ የሰገደ ሰው ሶላቱ ጎዶሎ ነው”* አንድ ሰው ለአቢ ሁረይራህ፦ “ከአሰጋጁ በኋላ ብንሆንም እንኳን? አለው። እርሱም አለ፦ “ለራስህ አንብብ ምክንያቱም ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁና፦ *”ኃያሉና የተከበረው አላህ እንዲህ ብሏል፦ “ሶላትን በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፍየዋለሁ፥ እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል፤ ባሪያው፦ ”ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው” ሲል አላህ፦ “ባሪያዬ አመሰገነኝ” ይላል። ባሪያው፦ ”እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ” ሲል ደግሞ አላህ፦ “ባሪያዬ አሞገሰኝ’ ይላል። ባሪያው፦ ”የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው” ሲል አላህ፦ ባሪያዬ አላቀኝ” ይላል። ባሪያው፦ ”አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን” በሚል ግዜ አላህ፦ “ይህ በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ነው እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል” ይላል። ባሪያው፦ ”ቀጥተኛውን መንገድ ምራን የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” በሚል ግዜ ደግሞ አላህ፦ “ይህ ለባሪያዬ ነው፤ እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል” ይላል"*፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ صَلَّى صَلاَةً لَمْ يَقْرَأْ فِيهَا بِأُمِّ الْقُرْآنِ فَهْىَ خِدَاجٌ – ثَلاَثًا – غَيْرُ تَمَامٍ ‏”‏ ‏.‏ فَقِيلَ لأَبِي هُرَيْرَةَ إِنَّا نَكُونُ وَرَاءَ الإِمَامِ ‏.‏ فَقَالَ اقْرَأْ بِهَا فِي نَفْسِكَ فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى قَسَمْتُ الصَّلاَةَ بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي نِصْفَيْنِ وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ فَإِذَا قَالَ الْعَبْدُ ‏{‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى حَمِدَنِي عَبْدِي وَإِذَا قَالَ ‏{‏ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى أَثْنَى عَلَىَّ عَبْدِي ‏.‏ وَإِذَا قَالَ ‏{‏ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ مَجَّدَنِي عَبْدِي – وَقَالَ مَرَّةً فَوَّضَ إِلَىَّ عَبْدِي – فَإِذَا قَالَ ‏{‏ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏.‏ فَإِذَا قَالَ ‏{‏ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ * صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا لِعَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ سُفْيَانُ حَدَّثَنِي بِهِ الْعَلاَءُ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ يَعْقُوبَ دَخَلْتُ عَلَيْهِ وَهُوَ مَرِيضٌ فِي بَيْتِهِ فَسَأَلْتُهُ أَنَا عَنْهُ ‏.‏

አምላካችን አላህ የሁላችንን አሚንን ታሳቢ ያደረገ ዱዓእ ይቀበለን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አዛን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥58 *"ወደ ሶላትም በጠራችሁ ጊዜ ጥሪይቱን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው ይይዟታል፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው"*፡፡ وَإِذَا نَادَيْتُمْ إِلَى الصَّلَاةِ اتَّخَذُوهَا هُزُوًا وَلَعِبًا ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْقِلُونَ

"አዛን" أَذَان የሚለው ቃል "አዚነ" أَذِنَ‎ ማለትም "ጠራ" ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥሪ" ማለት ነው። "ሙአዚን" مُؤَذِّن የሚለው ቃል "አዘነ" أَذَّنَ‎ ማለትም "ተጣራ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጠሪ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ፦ "በጁሙዓህ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ" ብሎናል፦
62፥9 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በጁሙዓህ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

"ፈርድ" فَرْض የሚለው ቃል "ፈረደ" فَرَضَ ማለትም "ተገደደ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ግዴታ" ማለት ነው። ፈርድ በሁለት ይከፈላል፥ እርሱም "ፈርዱል ዐይን" فَرْض العَيْن እና "ፈርዱል ኪፋያህ" فَرْض الكِفَايَة ናቸው።
"ዐይን" عَيْن የሚለው ቃል "ዓነ" عَانَ‎ ማለትም "ነጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተናጥል" ማለት ነው። "ፈርዱል ዐይን" فَرْض العَيْن ማለት "የተናጥል ግዴታ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ ሶላት፣ ሓጅ፣ ዘካህ፣ ፆም ወዘተ።
"ኪፋያህ" كِفَايَة የሚለው ቃል "ከፋ" كَفَى ማለትም "ጠቀለለ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥቅል" ማለት ነው። "ፈርዱል ኪፋያህ" فَرْض الكِفَايَة ማለት "የጥቅል ግዴታ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ "ሶላቱል ጀናዛህ" صَّلَات الجَنَازَة እና "ሶላቱል ጁሙዓህ" صَّلَات الْجُمُعَة ናቸው።
አንዳድ ጊዜ ሰዎች በሶላቱል ጁሙዓህ እና በአዘቦቱ ሶላት አዛን ሲሰሙ ጥሪይቱን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው ይይዟታል፦
5፥58 *"ወደ ሶላትም በጠራችሁ ጊዜ ጥሪይቱን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው ይይዟታል፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው"*፡፡ وَإِذَا نَادَيْتُمْ إِلَى الصَّلَاةِ اتَّخَذُوهَا هُزُوًا وَلَعِبًا ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْقِلُونَ

ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው። እኛም የአዛኑን ትርጉም ሙሥሊም ላልሆኑ ሰዎች እንዲያውቁ ማድረግ አለብን፥ ለናሙና ያክል የጁምዓ አዛን እንይ፦
1. "አሏሁ አክበር" ٱللهُ أَكْبَر ማለት "አሏህ ታላቅ ነው" ማለት ሲሆን የሚባለው 4 ጊዜ ነው።
2. "አሽሀዱ አነ ላ ኢላሀ ኢለሏህ" أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلٰهَ إِلَّا ٱلله ማለት "ከአሏህ በስተቀር አምላክ እንደሌለ እመሰክራለው" ማለት ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
3. "አሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሡሉሏህ" أَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ ٱلله ማለት "ሙሐመድም የአሏህ መልእክተኛ መሆኑን እመሰክራለው" ማለት ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
4. "ሐየ ዐለስ ሶላህ" حَيَّ عَلَى ٱلصَّلَاة ማለት "ወደ ሶላት ኑ" ማለት ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
5. "ሐየ ዐለል ፈላህ" حَيَّ عَلَى ٱلْفَلَاح ማለት "ወደ መዳን ኑ" ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
6. "አሏሁ አክበር" ٱللهُ أَكْبَر ማለት "አሏህ ታላቅ ነው" ማለት ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
7. "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا ٱلله ማለት "ከአሏህ በስተቀር አምላክ የለም" ማለት ሲሆን የሚባለው 1 ጊዜ ነው።

ሙአዚኑ ይህንን ጥሪ በተጣራ ጊዜ ሙሥሊሙ በተመሳሳይ ከላይ ያለውን ቃል ይላል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 9
አቢ ሠዒድ አል-ሑድሪይ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ጠሪው የሚለውን በተመሳሳይ በሉ"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا سَمِعْتُمُ النِّدَاءَ فَقُولُوا مِثْلَ ما يَقُولُ الْمُؤَذِّنُ

የመጀመሪያው ሙአዚን ሐበሻዊ ቢላል ኢብኑ ረባሕ ወይም ኢብን ሪያሕ"ረ.ዐ." ነው። ይህ ሰሓቢይ ለአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ሙአዚን ነበረ፥ እኛም ሐበሾች በቢላል አዛን መገለጫችን ሆኗል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 700
አሥ-ሣኢብ እንደተረከው፦ *"ለአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ጠሪ አልነበራቸው አንድ ቢላል እንጂ"*። عَنِ السَّائِبِ، قَالَ لَمْ يَكُنْ لِرَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم إِلاَّ مُؤَذِّنٌ وَاحِدٌ بِلاَلٌ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 46, ሐዲስ 3936
አቢ ሁራይራህ እንደሚተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ንግሥና ከቁራይሽ፣ ፍርድ ከአንሷር፣ አዛን ከሐበሻ፣ አማናህ ከየመን ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الْمُلْكُ فِي قُرَيْشٍ وَالْقَضَاءُ فِي الأَنْصَارِ وَالأَذَانُ فِي الْحَبَشَةِ وَالأَمَانَةُ فِي الأَزْدِ ‏"‏ ‏.‏ يَعْنِي الْيَمَنَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተሸካሚ ነፍስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

በቁርአን እስተምህሮት ውስጥ እንደ ክርስትናው “ጥንተ-ተአብሶ”Original sin” ማለትም እንደ ስኳርና ሳይነስ ለትውልድ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት የለም፤ ኃጢአት ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም፤ አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾቹ ላይ፦ “ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም” እያለ ይነግረናል፦
17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሚሽነሪዎች፦ “በኢስላም አስተምህሮት ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት ትሸከማለች” በማለት ሐዲሱ ለማለት ያልፈለገውን እጁን ጠምዝዘው ለማስባት ይሞክራሉ፤ ይህ በሥነ-አፈታት ጥናት”hermeneutics” ውስጥ “ስሁት ትርጓሜ”Eisegesis” ይባላል፤ አብዛኛውን ሳይፈሩና ሳያፍሩ ሳይማሩና ሳይመራመሩ ስሁታን የሆኑ ታካቾች ይጠቀሙበታል። በተቃራኒው ተረድቶ ለማስረዳት ዐውቆ ለማሳወቅ አምኖ ለማሳመን የአንድ ዓረፍተ-ነገር ዐውዱ ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ተብሎ እራሱ እንዲናገር ማድረግ ደግሞ “ስሙር ትርጓሜ”Exegesis” ይባላል፤ ይህንን አብዛኛው ጊዜ የሚጠቀሙበት ሊኅቃን የሆኑ ምሁራን ናቸው። እስቲ ሐዲሱን በአጽንኦትና በአንክሮት እንየው፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 50, ሐዲስ 60
አቢ ቡርዳ እንዳስተላለፈው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ከሙስሊሞች ሰዎች እንደ ተራራ ከሚመስል ወንጀላቸው ይመጣሉ፤ አላህም ይቅር ይላቸዋል። በእነርሱ ምትክ አይሁዳውያንን እና ክርስቲያኖችን ያስቀምጣል*። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ يَجِيءُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ نَاسٌ مِنَ الْمُسْلِمِينَ بِذُنُوبٍ أَمْثَالِ الْجِبَالِ فَيَغْفِرُهَا اللَّهُ لَهُمْ وَيَضَعُهَا عَلَى الْيَهُودِ وَالنَّصَارَى ‏”
እዚህ ሐዲስ ላይ የሙስሊሞችን ኃጢኣት አይሁድ እና ክርስቲያን ይሸከማሉ የሚል ሽታው እንኳን የለም፤ ከሙስሊሞች እንደ ተራራ ከሚመስል ወንጀላቸው ሲመጡ አላህ ይቅር ይላቸዋል፤ አንደኛ ይቅርታ የሚያገኙት በነብያችን”ﷺ” ምልጃ ሁለተኛ እስካላሻረኩት ድረስ ተቀጥተው ምህረትን ያገኛሉ እንጂ የእነርሱ ኃጢኣት በአይሁድ እና በክርስቲያን ላይ ያደርጋል የሚል ሽታው እንኳን የለም፤ ታዲያ “ምትክ” የሚለው ምንድን ነው? ሐዲሱ እዛው ላይ ይቀጥላል፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 50, ሐዲስ 58
አቢ ቡርዳ እንዳስተላለፈው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ሙስሊም አይሞት የእርሱ ቦታ አላህ አይሁድ ወይም ክርስቲያንን በእሳት ቢያደርግ እንጂ*። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لاَ يَمُوتُ رَجُلٌ مُسْلِمٌ إِلاَّ أَدْخَلَ اللَّهُ مَكَانَهُ النَّارَ يَهُودِيًّا أَوْ نَصْرَانِيًّا ‏
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 50, ሐዲስ 57
አቡ ሙሣ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ የትንሳኤ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ *አላህ ለሁሉም ሙስሊም አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን ያስቀምጣል፤ “ይህ ከእሳት የእናንተ ምትክ ነው” ይባላል*። عَنْ أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِذَا كَانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ دَفَعَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ إِلَى كُلِّ مُسْلِمٍ يَهُودِيًّا أَوْ نَصْرَانِيًّا فَيَقُولُ هَذَا فَكَاكُكَ مِنَ النَّارِ ‏”

አንድ አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን ቢያምን ኖሮ በጀነት የሚያገኘውን ቦታ ስላላመነ ሙስሊሙ በማመኑ የእርሱን ቦታ በገነት ያገኛል። በተቃራኒው አንድ ሙስሊም ቢክድ ኖሮ በገሃነም የሚያገኘውን ቦታ ስላልካደ አንድ አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን በመካዱ የእርሱን ቦታ በገሃነም ያገኛል። ይህ ነው የሐዲሱ እሳቤ እንጂ ስለ ኃጢኣት መሸከም አይናገርም። የሚናገረው ስለ ጀሃነም ቦታ ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ: መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4485
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሁለት ቦታ የሌለው ከእናንተ ማንም የለም፤ አንዱ መኖሪያ በጀነት ሌላው መኖሪያ በጀሃነም፤ የካደ ቢሞትና ጀሃነም ቢገባ የጀነት ባለቤት የእርሱን ቦታ ይወርሳል፤ ይህንን አላህ ሲናገር፦ “እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው” ብሏል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ مَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلاَّ لَهُ مَنْزِلاَنِ مَنْزِلٌ فِي الْجَنَّةِ وَمَنْزِلٌ فِي النَّارِ فَإِذَا مَاتَ فَدَخَلَ النَّارَ وَرِثَ أَهْلُ الْجَنَّةِ مَنْزِلَهُ فَذَلِكَ قَوْلُهُ تَعَالَى ‏{أُولَئِكَ هُمُ الْوَارِثُونَ }‏ ‏”‏
23፥10 *እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው*፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْوَارِثُون
23፥11 *እነዚያ ፊርደውስን የሚወርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው*፡፡ الَّذِينَ يَرِثُونَ الْفِرْدَوْسَ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

ስለዚህ ካፊር በመክፈሩ ጀሃነም ይገባል፤ ባይከፍር በጀነት የሚያገኘውን ቦታ ሙዕሚኑ ይወርሰዋል፤ ሙዕሚን በማመኑ ጀነት ይገባል፤ ባያምን በጀሃነም የሚያገኘውን ቦታ ካፊሩ ይወርሰዋል። ይህ ነው የሐዲሳት ጭብጥ፤ የነብያችንን”ﷺ” መልእክት ሰምቶ ያላመነ አይሁድ ወይም ክርስቲያን ጀሃነም እንደሚገባ እሙንና ቅቡል ነው፦
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 1, ሐዲስ 293
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው እምላለው፤ ከዚህ ሕዝብ አይሁዳዊም ሆነ ክርስቲያን የእኔን መላክ ሰምቶ ሳያምን ቢሞት የጀሃነም ጓድ እንጂ ሌላ አይሆንም”*። حَدَّثَهُ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لاَ يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الأُمَّةِ يَهُودِيٌّ وَلاَ نَصْرَانِيٌّ ثُمَّ يَمُوتُ وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ إِلاَّ كَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ ‏”

ቅሉ ግን አይሁዳዊም ሆነ ክርስቲያን የእርሳቸውን መላክ ሰምቶ ሳያምን ከመሞቱ በፊት ካመኑ ሊያገኙት የሚችሉት የጀነት ቦታ ለማግኘት ቶሎ መስለም ነው፤ አይ አስተባብዬ እሞታለው ካላችሁ ብታምኑ የምታገኙትን ቦታ ያመነ ሙስሊም ቦታችሁን ይወርሰዋል። እርሱ ቢክድ የሚያገኘውን የጀሃነም ቦታ በማመኑ የእርሱ ቦታ እናንተ ትወርሳላችሁ። የንስሓ በሩ ሳይዘጋ በጊዜ ሰልሞ ማምለጥ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
መረዳዳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥2 *”በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና”*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

አምላካችን አላህ ከሰው ጋር በሚኖረን ማሕበራዊ ዘይቤ እንዴት መኗኗር እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥36 *አላህንም አምልኩ፤ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው መልካምን ሥሩ*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
4፥135 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ይህ ቃል የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ሲሆን “ፍትሕ” ማለት ነው፤ ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ ተብሎ እና አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ተብሎ የሚደረግ ነው። ይህ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ፍትሕ ለአማንያን ብቻ ሳይሆን ለከሃድያንም ጭምር ነው፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፣ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ዲናችንን አክብረው ካልተጋደሉንና ካላሳደዱን ከሃድያን ጋር በዝምድና፣ በባልደረባ፣ በጉርብትና መልካም መዋዋል እና ማስተካከል ይቻላል። “ብታስተካክሉ” ለሚለው ቃል አሁንም የገባው “ቱቅሢጡ” َتُقْسِطُوا ሲሆን የስም መደቡ “ቂሥጥ” قِسْط ማለትም “ፍትሕ” ነው፤ ለአላህ ብለን ስናስተካክል “ሙቅሢጢን” مُقْسِطِين ማለትም “ፍትኸኞችን” “ትክክለኞች” “አስተካካዮች” እንሰኛለን፤ አላህ ሙቅሢጢንን ይወዳልና። በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም መረዳዳት ተፈቅዷል፦
49፥9 *በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
5፥2 *”በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና”*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

“በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ” የሚለው ይሰመርበት። ወደ ኩፍርና ሺርክ ሊያስገባ የሚችለውን ሥራ ከሌላ እምነት ጋር መሥራት ከኢሥላም ያስወጣል፥ ይህ ወሰን ማለፍ ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 311
ሰሙራህ ኢብኑ ጁንዱብ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እዲህ አሉ፦ *”ከሙሽሪክ ጋር ያበረ እና የተኗኗረ እርሱን(ሙሽሪኩን) ይመስላል”*። أَمَّا بَعْدُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ جَامَعَ الْمُشْرِكَ وَسَكَنَ مَعَهُ فَإِنَّهُ مِثْلُهُ ‏
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12, ሐዲስ 34
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም አሉ፦ *”ከማንኛውም ሕዝብ ጋር የሚመሳሰል ከእነርሱ ነው”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
ስለዚህ የማይመለከተን ነገር ውስጥ ለመመሳሰል ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያን ማጽዳት፣ የመስቀል ደመራ ቦታ ማጽዳት፣ የጥምቀት ቦታ ማጽዳት፥ ታቦት መሸኘት፣ በዓላቸውን ማክበር፣ መዝሙራቸውን መዘመር ከኢሥላም አጥር ያስወጣል። አንዳንድ ቂሎች፦ “ለመረዳዳት ነው” ይሉናል። በጋራ እሴት ማለትም በልማት፣ በጉርብትና፣ በአስኳላ ትምህርት፣ በሰብአዊነት ወዘተ… ልንረዳዳ እንችላለን፥ ነገር ግን በእምነት ጉዳይ እረዳቶች አድርገን ከያዝናቸው ከእነርሱ እንደ አንዱ ነን፦
4፥144 *”እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ*፤ ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን? يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجْعَلُوا لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا مُّبِينًا
5፥51 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው*፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 2939
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የሙሽሪክ እርዳታ አያስፈልገንም”* عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّا لاَ نَسْتَعِينُ بِمُشْرِكٍ ‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥምቀት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥138 *የአላህን የተፈጥሮ ጥምቀት ያዙ፡፡ በማጥመቅም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? ማንም የለም፤ እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን በሉ*። صِبْغَةَ اللَّـهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّـهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُون

"ጥምቀት" የሚለው የግሪኩ ቃል "ፓፕቲዝማ" βαπτισμός ሲሆን "ፓፕቲዞ" βάπτω ማለትም "ጠለቀ" ወይም "ተነከረ" ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ "መነከር" ወይም "መጥለቅ" የሚል ፍቺ አለው። ጥምቀት በባይብል የተለያየ ጥምቀት አለ፦ የውኃ ጥምቀት፣ የንስሐን ጥምቀት፣ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፣ የእሳት ጥምቀት፣ የመከራ ጥምቀት ወዘተ.. እነዚህን ነጥብ በነጥብ እስቲ እንያቸው፦

ነጥብ አንድ
"የውኃ ጥምቀት"
የውኃ ጥምቀት ሙሉ ሰውነትን ወደ ውኃ ውስጥ ማስገባትን ወይም ወደ ውኃ ውስጥ መጥለቅን ወይም ውኃው በሰው ላይ መፍሰሱን አሊያም መረጨቱን የሚያሳይ ነው፤ ለምሳሌ እስራኤላውያን በኤርትራ ባህር ሲሻገሩ እና በደመናው ዓምድ ሲያልፉ ከደመናው እና ከባህር ተጠመቁ ተብሏል፦
1ኛ ቆሮንቶስ 10፥1-2 ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ "በደመናና በባሕር ተጠመቁ""፤

የክርስቶስን ጥላነት"typology" ያሳያል የሚባለው ትምህርት ላይ ልዩ ልዩ የመታጠብ ስርዓት በመሴ ህግ ሰፍሮ ይገኛል፤ ይህ መታጠብ ግሪኩ ጥምቀት ይለዋል፤ "መታጠብ" ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል "ፓፕቲዞሞስ" βαπτισμοῖς ሲሆን መጠመቅ ማለት ነው፤ ይህም ልዩ ልዩ መታጠብ "ጥምቀቶች" ተብሏል፦
ዕብራውያን 9:10 እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ""ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም"" βαπτισμοῖς የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም።"
ዕብራውያን 6:1-2 ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ""ጥምቀቶች"" እና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።

ነጥብ ሁለት
"የንስሐን ጥምቀት"
በተመሳሳይ ይህ የውኃ ጥምቀት መጥምቁ ዮሐንስ ለንስሃ የኃጢአት ስርየት ያጠምቅ ነበር፤ ይህ ጥምቀት የንስሐን ጥምቀት ይባላል፦
ማርቆስ 1:4 ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ "የንስሐንም ጥምቀት" ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።

ይህ የንስሐን ጥምቀት በውኃ ሲሆን ለመሲሁ መምጣት መስተንግዶ ነበር፤ ከዚህ ውጪ ኢየሱስ የውኃ ጥምቀት ተጠመቁ ወይም አጥምቁ ብሎ አላስተማረም። ማርቆስ 16፥16 ላይ "ያመነ የተጠመቀም ይድናል" ተብሎ ኢየሱስ እንደተናገረ የሚነገርለት ይህ ጥቅስ ኢየሱስ በሕይወት ዘመኑ የተናገረው ንግግር አይደለም ብለው ምሁራን ያትታሉ፥ ማርቆስ 16.9-20 ያለው የማርቆስ ክፍል አይደለም። በጣም ስመጥርና ገናና የሚባሉ የግሪክ እደ-ክታባት"manuscripts" በሆኑት በሳይናቲከስ፣ በቫቲካነስ፣ በአሌክሳንዲረስ፣ በኤፍሬማይ ላይ የሉም። ይህን ጉዳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ኦርቶዶስ፣ ካቶሊክና ፕሮተስታንት 1980 ባሳተሙት የአዲስ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ ላይ አስፍረውታል፣ ከዚያም ባሻገር ይህ ቃል የኢየሱስ ንግግር እንዳልሆነ በውጪው ዓለም አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። በተጨማሪ ማቴዎስ 28፥19 ላይ "በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው" ተብሎ ኢየሱስ እንደተናገረ የሚነገርለት ይህ ጥቅስ ኢየሱስ በሕይወት ዘመኑ የተናገረው ንግግር አይደለም ብለው ምሁራን ያትታሉ፣ ማቴዎስ 28፥19 ያለው ክፍል "በስሜ ደቀመዛሙርት አድርጉ" በሚል የተለወጠ ነው ብለው የተለያዩ መድብለ-እውቀቶች"Encyclopedias" ሆነ የባይብል ማብራሪያዎች ያትታሉ። ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. The Interpreters Dictionary of the Bible, 1962, page 351
2. The Anchor Bible Dictionary, Vol. 1, 1992, page 585:
3. The International Standard Bible Encyclopedia, Vol. 4, page 2637,
4. Word Biblical Commentary, Vol 33B, 1975, page 887-888:

ነጥብ ሶስት
"የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት"
የብዙዎች ክርስቲያኖች ጥምቀት ሲባል ሁልጊዜ በውኃ መጠመቅ ብቻ አርገው ያስባሉ፤ ነገር ግን በአንድ ነገር ውስጥ መጥለቅ ወይም መነከር እራሱ ጥምቀት ነው፤ ይህንን በየመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማየት ይቻላል፦
ማርቆስ 1:8 እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን "በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል" እያለ ይሰብክ ነበር።"
የሐዋርያት ሥራ 1:5 ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ ""በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ"" አለ።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፥13 "በአንድ መንፈስ" አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና።

መቼም በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ማለት በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር መሆን እንጂ ሌላ በውኃ እንደመጠመቅ አይደለም።