ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የቲም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥2 *"የቲሞችንም ገንዘቦቻቸውን ስጡ፡፡ መጥፎውንም በመልካሙ አትለውጡ፡፡ ገንዘቦቻቸውንም ወደ ገንዘቦቻችሁ በመቀላቀል አትብሉ እርሱ ታላቅ ኃጢአት ነውና"*፡፡ وَآتُوا الْيَتَامَىٰ أَمْوَالَهُمْ ۖ وَلَا تَتَبَدَّلُوا الْخَبِيثَ بِالطَّيِّبِ ۖ وَلَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَهُمْ إِلَىٰ أَمْوَالِكُمْ ۚ إِنَّهُ كَانَ حُوبًا كَبِيرًا

"የተም" يَتَم የሚለው ቃል "የቲመ" يَتِمَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የቲምነት" ማለት ነው። "የቲም" يَتِيم ተባታይ መደብ ሲሆን የየቲም ብዙ ቁጥር ደግሞ "አይታም" أَيْتَام‎ ወይም "የቲሙነ" يَتِيمُونَ‎ ነው። "የቲማህ" يَتِيمَة‎ አንስታይ መደብ ሲሆን የየቲማህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "የቲማት" يَتِيمَات‎ ወይም "የታኢም" يَتَائِم‎ ነው። ለሁለቱም ማለትም ለተባታይ ሆነ ለአንስታይ መደብ የምንጠቀምበት ቃል "የታማ" يَتَامَى‎ ነው። ነገር ግን "የቲም" يَتِيم ስንል አጠቃላይ "ወላጅ-አልባ" ማለትም "እናትና አባቱ" ወይም "አባቱን በልጅነቱ በሞት የተነጠቀ ሕጻን" ማለት ነው። "orphan" የሚለውም ቃል "ኦርፋን" ορφανός ከሚል ግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ "ወላጅ-አልባ" ነው። ነቢያችን"ﷺ" አባታቸው በሞት ያጡት እናታቸው ሆድ ውስጥ እያሉ ነበር፥ እናታቸውን ያጡት ደግሞ በተወለዱ በስድስት ዓመታቸው ነበር። አምላካችን አላህ ስለ እርሳቸው የቲምነት ሲናገር፦
93፥6 *የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን?* ፡፡ أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًۭا فَـَٔاوَىٰ

የቲምን መንከባከብ በጎ አድራጎት እና ከአላህ ዘንድ አጅር አለው፥ በጀነት የነቢያችን"ﷺ" ጎረቤት ለመሆን ጉልህ ሚና አለው፦
4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ *"በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ባደረጓቸው ባሮች፣ መልካምን ሥሩ"*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
76፥8 *"ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ"*፡፡ وَيُطْعِمُونَ الطَّعَامَ عَلَىٰ حُبِّهِ مِسْكِينًا وَيَتِيمًا وَأَسِيرًا
90፥15 *የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም*። يَتِيمًا ذَا مَقْرَبَةٍ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 36
ሠህል ኢብኑ ሠዕድ ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"እኔ እና አንድ የቲም የሚንከባከብ ልክ የአመልካች ጣቱ ከመሃል ጣቱ እንደሚቀራረብ በጀነት እንሆናለን"*። سَمِعْتُ سَهْلَ بْنَ سَعْدٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ أَنَا وَكَافِلُ الْيَتِيمِ، فِي الْجَنَّةِ هَكَذَا ‏"‌‏.‏ وَقَالَ بِإِصْبَعَيْهِ السَّبَّابَةِ وَالْوُسْطَى

አምላካችን አላህ የቲምን መጨቆን ሐራም አርጓል፥ ነቢያችንም"ﷺ" በአደራነት ከአስጠነቀቁት አንዱ የየቲም ጉዳይ ነው፦
4፥2 *"የቲሞችንም ገንዘቦቻቸውን ስጡ፡፡ መጥፎውንም በመልካሙ አትለውጡ፡፡ ገንዘቦቻቸውንም ወደ ገንዘቦቻችሁ በመቀላቀል አትብሉ እርሱ ታላቅ ኃጢአት ነውና"*፡፡ وَآتُوا الْيَتَامَىٰ أَمْوَالَهُمْ ۖ وَلَا تَتَبَدَّلُوا الْخَبِيثَ بِالطَّيِّبِ ۖ وَلَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَهُمْ إِلَىٰ أَمْوَالِكُمْ ۚ إِنَّهُ كَانَ حُوبًا كَبِيرًا
93፥9 *"የቲምንማ አትጨቁን*፡፡ فَأَمَّا الْيَتِيمَ فَلَا تَقْهَرْ
89፥17 *ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም*፡፡ كَلَّا ۖ بَل لَّا تُكْرِمُونَ الْيَتِيمَ
107፥2 *ይህም ያ የቲምን በኀይል የሚገፈትረው*። فَذَٰلِكَ الَّذِي يَدُعُّ الْيَتِيمَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 22
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ሆይ! ምስክር ሁን! እኔ ያስጠነቀቁት ሁለት ድኩማን ጉዳይ አሉኝ፥ እነርሱም የቲም እና እንስት ናቸው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ اللَّهُمَّ إِنِّي أُحَرِّجُ حَقَّ الضَّعِيفَيْنِ الْيَتِيمِ وَالْمَرْأَة
በቂ የመኖሪያ ገንዘብ ያለው የየቲም ሞግዚት የየቲም ገንዘብ መንካት የለበትም። ነገር ግን ምንም የሌለው መናጢ ከሆነ በፍትሐዊና በምክንያታዊ መጠቀም ይችላል፦
4፥6 *የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ ከእነርሱም ቅንነትን ብታውቁ ገንዘቦቻቸውን ወደ እነርሱ ስጡ፡፡ በማባከንና ማደጋቸውንም በመሽቀዳደም አትብሏት፡፡ ከዋቢዎች ሀብታምም የኾነ ሰው ይከልከል፡፡ ድሃም የኾነ ሰው ለድካሙ በአግባብ ይብላ፡፡ ገንዘቦቻቸውንም ወደ እነርሱ በሰጣችሁ ጊዜ በእነርሱ ላይ አስመስክሩ፡፡ ተጠባባቂነትም በአላህ በቃ*፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ فَإِنْ آنَسْتُم مِّنْهُمْ رُشْدًا فَادْفَعُوا إِلَيْهِمْ أَمْوَالَهُمْ ۖ وَلَا تَأْكُلُوهَا إِسْرَافًا وَبِدَارًا أَن يَكْبَرُوا ۚ وَمَن كَانَ غَنِيًّا فَلْيَسْتَعْفِفْ ۖ وَمَن كَانَ فَقِيرًا فَلْيَأْكُلْ بِالْمَعْرُوفِ ۚ فَإِذَا دَفَعْتُمْ إِلَيْهِمْ أَمْوَالَهُمْ فَأَشْهِدُوا عَلَيْهِمْ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ حَسِيبًا
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 158
ሂሻም እንደተረከው፦ "ዓዒሻህ እንዲህ ስትል ሰምቻለው፦ *"ከዋቢዎች ሀብታምም የኾነ ሰው ይከልከል፡፡ ድሃም የኾነ ሰው ለድካሙ በአግባብ ይብላ" የሚለው አንቀጽ የወረደው ስለ የቲም ሞግዚት በሚመለከት ለማስጤን ነው። የእነርሱን የንዋይ ጉዳይ ለማስተዳደር ነው። ግን ሞግዚቱ ድሃ ከሆነ በፍትሐዊና በምክንያታዊ መጠቀም ይችላል"*። أَخْبَرَنَا هِشَامٌ، وَحَدَّثَنِي مُحَمَّدٌ، قَالَ سَمِعْتُ عُثْمَانَ بْنَ فَرْقَدٍ، قَالَ سَمِعْتُ هِشَامَ بْنَ عُرْوَةَ، يُحَدِّثُ عَنْ أَبِيهِ، أَنَّهُ سَمِعَ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ تَقُولُ ‏{‏وَمَنْ كَانَ غَنِيًّا فَلْيَسْتَعْفِفْ وَمَنْ كَانَ فَقِيرًا فَلْيَأْكُلْ بِالْمَعْرُوفِ‏}‏ أُنْزِلَتْ فِي وَالِي الْيَتِيمِ الَّذِي يُقِيمُ عَلَيْهِ، وَيُصْلِحُ فِي مَالِهِ، إِنْ كَانَ فَقِيرًا أَكَلَ مِنْهُ بِالْمَعْرُوف

አምላካችን አላህ፦ "የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ" የሚለውን ካወረደ በኃላ "ስለ የቲሞችም ይጠይቁሃል፡፡ ለእነርሱ ገንዘባቸውን በማራባት ማሳመር በላጭ ነው፡፡ ብትቀላቀሏቸውም ወንድሞቻችሁ ናቸው" የሚለውን አንቀጽ አወረደ፦
17፥34 *"የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ፡፡ በኪዳናችሁም ሙሉ፡፡ ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና"*፡፡ وَلَا تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ حَتَّىٰ يَبْلُغَ أَشُدَّهُ ۚ وَأَوْفُوا بِالْعَهْدِ ۖ إِنَّ الْعَهْدَ كَانَ مَسْئُولًا
4፥10 *እነዚያ የየቲሞችን ገንዘብ በመበደል የሚበሉ በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉት እሳትን ብቻ ነው፡፡ እሳትንም በእርግጥ ይገባሉ*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ أَمْوَالَ الْيَتَامَىٰ ظُلْمًا إِنَّمَا يَأْكُلُونَ فِي بُطُونِهِمْ نَارًا ۖ وَسَيَصْلَوْنَ سَعِيرًا
2፥220 በቅርቢቱ ዓለምና በመጨረሻይቱ ታስተነትኑ ዘንድ ይገለጽላችኋል፡፡ *"ስለ የቲሞችም ይጠይቁሃል፡፡ «ለእነርሱ ገንዘባቸውን በማራባት ማሳመር በላጭ ነው፡፡ ብትቀላቀሏቸውም ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡ አላህም የሚያጠፋውን ከሚያበጀው ለይቶ ያውቃል*፡፡ አላህም በሻ ኖሮ ባስቸገራችሁ ነበር፤ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና» በላቸው፡፡ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۗ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الْيَتَامَىٰ ۖ قُلْ إِصْلَاحٌ لَّهُمْ خَيْرٌ ۖ وَإِن تُخَالِطُوهُمْ فَإِخْوَانُكُمْ ۚ وَاللَّهُ يَعْلَمُ الْمُفْسِدَ مِنَ الْمُصْلِحِ ۚ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَأَعْنَتَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 10
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"የላቀው እና ክቡሩ አላህ፦ "የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ" እና "እነዚያ የየቲሞችን ገንዘብ በመበደል የሚበሉ" ባወረደ ጊዜ ማንም የቲም ያለው ምግቡን ከየቲም ምግብ፣ መጠጡን ከመጠጡ ተለየ። የቲም በራሱ የሚበላው ወይም የሚያባክነው ዝርዝር ቀሪ ሲጀመር ይህ ለሞግዚቶች ከባድ ሆነ። ይህንን ጉዳይ ለአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሲያቀርቡ የላቀው እና ክቡሩ አላህ፦ "ስለ የቲሞችም ይጠይቁሃል፡፡ ለእነርሱ ገንዘባቸውን በማራባት ማሳመር በላጭ ነው፡፡ ብትቀላቀሏቸውም ወንድሞቻችሁ ናቸው" የሚለውን አንቀጽ አወረደ። ከዚያም ምግባቸውን ከምግቡ፥ መጠጣቸውን ከመጠጡ ቀላቀሉ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ لَمَّا أَنْزَلَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ وَلاَ تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلاَّ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ ‏}‏ وَ ‏{‏ إِنَّ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ أَمْوَالَ الْيَتَامَى ظُلْمًا ‏}‏ الآيَةَ انْطَلَقَ مَنْ كَانَ عِنْدَهُ يَتِيمٌ فَعَزَلَ طَعَامَهُ مِنْ طَعَامِهِ وَشَرَابَهُ مِنْ شَرَابِهِ فَجَعَلَ يَفْضُلُ مِنْ طَعَامِهِ فَيُحْبَسُ لَهُ حَتَّى يَأْكُلَهُ أَوْ يَفْسُدَ فَاشْتَدَّ ذَلِكَ عَلَيْهِمْ فَذَكَرُوا ذَلِكَ لِرَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَأَنْزَلَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الْيَتَامَى قُلْ إِصْلاَحٌ لَهُمْ خَيْرٌ وَإِنْ تُخَالِطُوهُمْ فَإِخْوَانُكُمْ ‏}‏ فَخَلَطُوا طَعَامَهُمْ بِطَعَامِهِ وَشَرَابَهُمْ بِشَرَابِه
“ኢንፋቅ” إِنفَاق ማለት “ልግስና” ማለት ሲሆን ልግስና ከሚለገሱት አንዱ የቲሞች ናቸው፦
2፥215 ምንን ለማንም እንደሚለግሱ ይጠይቁሃል፡፡ *ከመልካም ነገር የምትለግሱት፤ ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች፣ "ለየቲሞችም"፣ ለድሆችም፣ ለመንገደኞችም ነው፡፡ ከበጎ ነገርም ማንኛውንም ብትሠሩ አላህ እርሱን ዐዋቂ ነው በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ ۖ قُلْ مَا أَنفَقْتُم مِّنْ خَيْرٍ فَلِلْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۗ وَمَا تَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ فَإِنَّ اللَّهَ بِهِ عَلِيمٌ

"ነፈል" نَفَل ማለት "ስጦታ" ማለት ነው፥ የነፈል ብዙ ቁጥር "አንፋል" أَنْفَال‎ ነው። አንፋል በምርኮ ጊዜ የሚገኝ ገንዘብ ነው፥ ይህ የምርኮ ገንዘብ አንድ አምስተኛው ከሚሰጠው መካከል አንዱ ለየቲሞች ነው፦
8፥41 *ከማንኛውም ነገር የማረካችኩት አንድ አምስተኛው ለአላህ እና ለመልክተኛው፣ ለዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም የተገባ መኾኑን ዕውቁ"*። وَاعْلَمُوا أَنَّمَا غَنِمْتُم مِّن شَيْءٍ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَابْنِ السَّبِيلِ

"ሑምሥ" خُمُس ማለት "አንድ አምስተኛ" ማለት ነው። እንግዲህ ስለ የቲም በኢሥላም ይህን ያክል አጽንዖትና አንክሮት የተሰጠው ነጥብ ከሆነ ሁላችንም የቲሞችን የመንከባከብ አላፍትና አለብን፥ ሐቃቸውንም መብላት የለብንም። የቲምን በመርዳት ላይ የተሰማሩትን ወንድምና እህት አላህ ወሮታና አጸፌታውን፥ ምንዳና ትሩፋቱን በጀነቱል ፈርደውስ ይወፍቃቸው! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሐዲስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

"ሐዲስ" حَدِيث የሚለው ቃል "ሐደሰ" حَدَّثَ‎ ማለትም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንግግር" ማለት ነው፦
53፥59 *"ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?"* أَفَمِنْ هَـٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ንግግር" ለሚለው የተቀመጠው ቃል "ሐዲስ" حَدِيث መሆኑ ልብ በል። እዚህ ድረስ የሐዲስ ቃል ምን ማለት እንሆነ በግርድፉና በሌጣው ካየን ዘንዳ ነቢያችን"ﷺ" በዐቂዳህ እና በፊቅህ ነጥብ ላይ የሚናገሩት ንግግር ሁሉ ወሕይ ነው፦
53፥3 *ከልብ ወለድም አይናገርም*፡፡ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ወሕይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

“ወሕይ” وَحْي የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት”Revelation” ማለት ነው። ነቢያችን"ﷺ" የሚያስጠነቅቁት በተወረደላቸው ወሕይ ብቻ ነው፦
21፥45 *«የማስጠነቅቃችሁ በተወረደልኝ ወሕይ ብቻ ነው*፡፡ ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩ ጊዜ ጥሪን አይሰሙም» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا أُنذِرُكُم بِالْوَحْيِ ۚ وَلَا يَسْمَعُ الصُّمُّ الدُّعَاءَ إِذَا مَا يُنذَرُونَ

ነቢያችን"ﷺ" በግል አመለካከታችሁ የሚሰጡት አስተያየት ግን ወሕይ ሳይሆን የወቅቱን ባህሉን፣ ወጉን፣ ትውፊቱን ያማከለ ጥሩ ምክር ነው፥ ይህ ዲናዊ እስካልሆነ ድረስ እንደ አመለካከት እንይዘዋለን እንጂ ዐቂዳህ እና ፊቅህ አይመሠረትበትም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 185
ራፊዕ ኢብኑ ኸዲጅ እንደተረከልኝ፦ "ነቢዩ"ﷺ" ወደ መዲና ሲመጡ ሰዎች ዛፍ እየቆረጡ ነበር። እርሳቸው፦ *"ምን እያረጋችሁ ነው? ብለው አሉ፥ እነርሱም፦ "እየቆረጥናቸው ነው" አሉ። እርሳቸውም፦ "ያንን ባታደርጉ ለእናንተ ጥሩ ይሆናል" አሉ። እነርሱም ይህን ልምምድ ተዉና የዘንባባም አነስተኛ ፍሬ ማፍራት ጀመሩ፥ ይህንን ጉዳይ ለነቢዩ አነሱት። ከዚያም እሳቸው፦ "እኔ ሰው ነኝ፥ እኔ ከዲናችሁ ስላለ ነገር ባዘዝኳችሁ ጊዜ ለመተግበር ውሰዱት፥ ነገር ግን እኔ ከግሌ አመለካከት ስላለ ነገር ባዘዝኳችሁ ጊዜ በአእምሯችሁ ያዙት፤ እኔ ሰው ነኝና"*። حَدَّثَنِي رَافِعُ بْنُ خَدِيجٍ، قَالَ قَدِمَ نَبِيُّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَهُمْ يَأْبُرُونَ النَّخْلَ يَقُولُونَ يُلَقِّحُونَ النَّخْلَ فَقَالَ ‏"‏ مَا تَصْنَعُونَ ‏"‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَصْنَعُهُ قَالَ ‏"‏ لَعَلَّكُمْ لَوْ لَمْ تَفْعَلُوا كَانَ خَيْرًا ‏"‏ ‏.‏ فَتَرَكُوهُ فَنَفَضَتْ أَوْ فَنَقَصَتْ - قَالَ - فَذَكَرُوا ذَلِكَ لَهُ فَقَالَ ‏"‏ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ إِذَا أَمَرْتُكُمْ بِشَىْءٍ مِنْ دِينِكُمْ فَخُذُوا بِهِ وَإِذَا أَمَرْتُكُمْ بِشَىْءٍ مِنْ رَأْىٍ فَإِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ

"ያንን ባታደርጉ ለእናንተ ጥሩ ይሆናል" የግላቸው አመለካከት ነው። ከዚህ ሐዲስ የምንረዳው ከዲናዊ ውጪ ግላዊ አመለካከትን እንደ አንቀጸ-እምነት እና እንደ መርሕ መውሰድ እንደሌለብን ነው። አምላካችን አላህ ነቢያችን"ﷺ" እንዲያስጠነቅቁ ቁርኣን እና ሐዲስ አውርዷል፦
4፥113 *"አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍን እና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ"*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኪታብ" كِتَاب የተባለው የአላህ ንግግር ቁርኣን ሲሆን "ሒክማህ" حِكْمَة የተባለው የነቢያችን"ﷺ" ሡናህ ነው፥ በኪታብ እና በሒክማህ መካከል "ወ" وَ የሚል መስተጻምር ቁርኣን እና ሡናህ ሁለት ጉዳዮች እንደሆነ አብክሮና አዘክሮ ያሳያል። "አወረደ" የሚለውም ቃል ቁርኣን እና ሡናህ የተወረዱ ወሕይ መሆናቸው ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 9
አል-ሚቅዳም ኢብኑ መዕዲከሪብ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ለእኔ መጽሐፍ እና መሰሉን ተሰቶኛል"*። عَنِ الْمِقْدَامِ بْنِ مَعْدِيكَرِبَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ "‏ أَلاَ إِنِّي أُوتِيتُ الْكِتَابَ وَمِثْلَهُ

"ሚስለሁ" مِثْلَهُ የሚለው ቃል ይሰመርበት። የአላህ ንግግር ቁርኣን ሆነ የቁርኣን አተገባበር ሐዲስ ከአላህ የተሰጡ መሆናቸው ይህ ሐዲስ አስረግጦና ረግጦ ያስረዳል። ቁርኣን ልክ እንደ ዐብይ ዕቅድ"master plan" ነው፥ ዐብይ ዕቅድ የአንድ ቤት ጥቅል ማብራሪያ ነው። ሡናህ ደግሞ ዝርዝር"specification" ነው፥ ዝርዝር መግለጫ የአንድ ቤት ተናጥል ማብራሪያ ነው። "ሡናህ" سُنَّة‎ ማለት "መንገድ" "ዘይቤ" "ወግ" "ፈለግ" ማለት ነው፥ የቁርኣን ዘይቤና ወጉ የሚገኘው የመልእክተኛው ፈለግ በመከተል ነው፦
33፥21 ለእናንተ አላህን እና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ *በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ*፡፡ لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

መልእክተኛው ቁርኣንን እንዴት እንደምንረዳውና እንደምንተገብረው ያብራሩት ትእዛዝ ከአላህ የመጣ ወሕይ ነው፥ መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፦
4፥80 *"መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ"*፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው አያሳስብህ፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አላክንህምና፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا
47፥33 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"አላህን ታዘዙ፥ መልክተኛውንም ታዘዙ"*፡፡ ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَلَا تُبْطِلُوا أَعْمَالَكُمْ
"አላህን ታዘዙ" ሲል አላህ በቁርኣን ያዘዘውን ትእዛዝ ሲሆን "መልክተኛውንም ታዘዙ" ሲል ደግሞ መልእክተኛው በሐዲስ ያዘዙንን ትእዛዝ ነው፥ "መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ" የሚለው ይህንኑ ሡናህ ዋቢና ታሳቢ ያደረገ ነው፦
29፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ታዲያ ቁርኣን እና ሐዲስ ልዩነቱ ምንድን ነው? አዎ! ቁርኣን ለፍዙ ሆነ መዕናው የአላህ ነው፥ ሐዲስ ግን ለፍዙ የነቢያችን"ﷺ" ሲሆን ማዕናው የአላህ ነው። "ለፍዝ" لَفْظ ማለት "ቃል"Verbatim" ማለት ሲሆን "መዕና" مَعْنًى ማለት "መልእክት" "እሳቤ" "አሳብ"notion" ማለት ነው። የቁርኣን ተናጋሪ አላህ ብቻ ነው፥ ቃሉም የወከለው መልእክቱ፣ "እሳቤው፣ አሳቡ የራሱ ነው። ሐዲስ ደግሞ መልእክቱ፣ "እሳቤው፣ አሳቡ የአላህ ሲሆን ቃሉ ግን የራሳቸው የነቢያችን"ﷺ" ነው። አላህ የሐዲስን መልእክት ሲያወርድላቸው እሳቸው በራሳቸው ባህል፣ ወግ፣ ልምድ፣ ክህሎት፣ ትውፊት ያብራሩታል።
ስለዚህ አንድ ሙሥሊም በአላህ እና በመጨረሻ ቀን የሚያምን የሚያከራክር ጉዳይ ሲኖረው ጉዳዩን ወደ አላህ ቁርኣን እና ወደ መልእክተኛው ሐዲስ ያመጣዋል፥ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውን እና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ *"በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا
60፥6 *"ለእናንተ አላህን እና የመጨረሻውን ቀን ለሚፈራ ሰው በእነርሱ መልካም መከተል አላችሁ"*፡፡ የሚዞርም ሰው ራሱን ይጎዳል፡፡ አላህ ተብቃቂው ምስጉኑ እርሱ ብቻ ነውና፡፡ لَقَدْ كَانَ لَكُمْ فِيهِمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ ۚ وَمَن يَتَوَلَّ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

በአላህ የሚያምን አላህ በልቤ ያለውን ያውቃል፣ የምናገረውን ይሰማል፣ የማደርገውን ያያል ብሎ አላህን ይፈራል፥ በመጨረሻው ቀን የሚያምን አላህ በትንሳኤ ቀን ይተሳሰበኛል፣ ለምሠራው ይጠይቀኛ፣ ለማደርገው እኩይ ሥራ ይቀጣኛል ብሎ ያንን ቀን ይፈራል። አላህን እና የመጨረሻውን ቀን ለሚፈራ ሰው በእነርሱ መልካም መከተል አለው፥ "በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት" ማለት ዝንባሌን መከተል ትተት የሚያከራክረውን ጉዳይ ወደ ቁርኣን እና ወደ ሐዲስ መመለስ ነው። ከጌታችን አላህ ወደ እኛ የተወረደውን ቁርኣን እና ሡናህ ብቻ መከተል ነው፥ ዝንባሌን መከተል ግን ጉንጭ አልፋ ንትርክ እና የጨባራ ተስካር ነው፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ
5፥49 *"በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ፡፡ ዝንባሌአቸውንም አትከተል"*፡፡ وَأَنِ احْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ

አምላካችን አላህ ዝንባሌአችንን ከመከተል ይጠብቀን፥ ቁርኣንን እና ሐዲስን ብቻ የምንከተል ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን አወራረድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥106 *ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፥ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*። وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

“ኑዙል” نُزُل ማለት “አወራረድ” ማለት ሲሆን “ተንዚል” تَنزِيل ማለት ደግሞ “የተወረደ”Revelation” ማለት ነው፤ ሁለቱም ቃላት “አንዘለ” أَنْزَلَ ወይም “ነዝዘለ” نَزَّلَ ማለትም “አወረደ” ወይም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጡ ናቸው። የቁርኣን አወራረዱ ሁለት አይነት ነው፤ አንዱ በጠቅላላ አንድ ጊዜ ከለውሐል መሕፉዝ ማለትም ከተጠበቀው ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ሲሆን ሁለተኛው ከቅርቢቱ ሰማይ ወደ ነብያችን”ﷺ” ልብ ቀስ በቀስ ለ 23 ዓመት ወረደ፤ ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ አርገን እንመልከት።
የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው ረመዷን 9ኛው ወር ሲሆን ይህ ወር የሚጾምበት ምክንያት ቁርኣን ከጥብቁ ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ወደ እልቅና ቤት የወረደበት ወር ስለሆነ ነው። ቁርኣን በዚህ ወር ውስጥ በአንድ በተባረከች ሌሊት በጠቅላላ አንድ ጊዜ ወርዷል፥ ይህም አወራረድ “ጁምለተን ዋሒዳህ” جُمْلَةً وَاحِدَةً ይባላል፦
2፥185 *”እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ ያ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና እውነትን ከውሸት ከሚለዩም ገላጮች አንቀጾች ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው”*፡፡ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 2፥185
በሠዒድ ኢብኑ ጀሪር ሪዋያህ ኢብኑ ዐባሥ እንደተናገረው፦ *”ቁርኣን በአንድ ጊዜ የተወረደበት በረመዳን ወር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ በሚገኘው ወደ በይቱል ዒዛህ ነው። ከዚያም የሰዎችን ጥያቄ ለመመለስ ወደ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ቀስ በቀስ ለ 23 ዓመታት ወረደ”*።
በዒክራማህ ሪዋያህ ኢብኑ ዐባሥ እንደተናገረው፦ *”ቁርኣን በረመዳን ወር በለይለቱል ቀድር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ አንዴ በጠቅላላ ሆኖ ወርዷል”*።
وفي رواية سعيد بن جبير ، عن ابن عباس قال : أنزل القرآن في النصف من شهر رمضان إلى سماء الدنيا فجعل في بيت العزة ، ثم أنزل على رسول الله صلى الله عليه وسلم في عشرين سنة لجواب كلام الناس
وفي رواية عكرمة ، عن ابن عباس ، قال : نزل القرآن في شهر رمضان في ليلة القدر إلى هذه السماء الدنيا جملة واحدة
44፥3 *”እኛ ቁርኣኑን በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስጠንቃቂዎች ነበርንና”*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ

“አወረድነው” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “አንዘልናሁ” أَنْزَلْنَاهُ ሲሆን “አንዘለ” أَنْزَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ቃል በቁርኣን ቋንቋ በአንድ ጊዜ መውረድን ያመለክታል። አምላካችን አላህ ምን ጥሩ ነገር እና ምን መጥፎ ነገር እንዳለ ያስጠነቅቃል። ይህቺ ሌሊት የተባረከች ስለሆነች “ለይለቱል ሙባረካህ” لَيْلَةٍ مُّبَارَكَة ተብላለች፥ በሌላ አንቀጽ ላይ ደግሞ “ለይለቱል ቀድር” لَيْلَةُ الْقَدْر ማለትም “የመወሰኛይቱ ሌሊት” ተብላለች፦
97፥1 *እኛ ቁርኣኑን በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ

ከቅርቢቱ ሰማይ ወደ ነቢያችን”ﷺ” ልብ ሲወርድ አወራረድ የሚጀምረው ከሱረቱል ዐለቅ 96፥1-5 ሲሆን የሚጠናቀቅ ደግሞ በሱረቱል በቀራህ 2፥281 ነው። ግን ወሕይ በ 40 ዓመታቸው መውረድ ሲጀምር የተጀመረው በረመዳን ወር ሲሆን ቀኑ ደግሞ ሰኞ ነው፦
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 13, ሐዲስ 256
አቢ ቀታደህ አንሷሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሰኞ ቀን ስለሚጾምበት ተጠየቁ፤ እርሳቸውም፦ “የተወለድኩበት እና ወሕይ የወረደልኝ ቀን ነው” አሉ*። عَنْ أَبِي قَتَادَةَ الأَنْصَارِيِّ، رضى الله عنه أَنَّرَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سُئِلَ عَنْ صَوْمِ الاِثْنَيْنِ فَقَالَ ‏ “‏ فِيهِ وُلِدْتُ وَفِيهِ أُنْزِلَ عَلَىَّ ‏”‏ ‏.‏

ቁርኣን ከቅርቢቱ ሰማይ ወደ ነብያችን”ﷺ” ልብ በጨረቃ አቆጣጠር ከ 610 ዓመተ-ልደት እስከ 632 ዓመተ-ልደት ለ 23 ዓመት ቀስ በቀስ ወረደ፤ ለ 13 ዓመት 86 ሱራዎች በመካ ሲሆን 28 ደግሞ የወረዱት ለ 10 ዓመት በመዲና ነው፣ ይህ ወሕይ በ 40 ዓመታቸው ጀምሮ በ 63 ዓመታቸው ቀስ በቀስ ወረደ፤ ይህም ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ አወራረዱ “ተርቲል” تَرْتِيل ይባላል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 63, ሐዲስ 128
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ወሕይ መቀበል ጀመሩ፤ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ቆይተው በ 63 ዓመታቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ بُعِثَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَرْبَعِينَ سَنَةً، فَمَكُثَ بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ سَنَةً يُوحَى إِلَيْهِ، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ فَهَاجَرَ عَشْرَ سِنِينَ، وَمَاتَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ‏.‏
25፥32 እነዚያ የካዱትም *«ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፤ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا
17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا
“አወረድነው” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “ነዝዘልናሁ” نَزَّلْنَاهُ ሲሆን “ነዝዘለ” نَزَّلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ቃል በቁርኣን ዐረቢኛ ቋንቋ ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ መውረድን ያመለክታል፤ እዚሁ አንቀጽ ላይ “ተንዚላ” تَنزِيلًۭا የሚለው የተንዚል ሌላኛው መደብ ነው፥ “ተንዚል” تَنزِيل የሚለው ቃል 15 ጊዜ ለቁርኣን ተጠቅሷል፦
26፥192 *እርሱም ቁርኣን በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَإِنَّهُ لَتَنزِيلُ رَبِّ الْعَالَمِين

ከሱረቱል ዐለቅ 96፥1-5 እስከ ሱረቱል በቀራህ 2፥281 ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ ከዐለማቱ ጌታ ወደ ነቢያችን”ﷺ” ልብ ሲያወርድ የነበረው ጂብሪል ነው። አላህ ወደ ነብያት ወሕይ የሚያወርድበት መንገድ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም፦ በራዕይ፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ያወርዳል፦
42:51 ለሰው” አላህ *“በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም*፤ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው፤ ይህም የወህይ መልአክ ጂብሪል”አ.ሰ.” ነው፤ አላህ በሦስተኛው መንገድ ነው ቁርኣን ለነብያችን”ﷺ” ያወረደው፤ “መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን የሚያወርድለት ቢሆን እንጅ” የሚለው ይሰመርበት፤ ጂብሪልም መልአክ እንደመሆኑ መጠን ከአላህ ወደ ነብያችን”ﷺ” ቀልብ ቁርኣንን በአላህ ፈቃድ አውርዶታል፦
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ *እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

“በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና” የሚለው ሃይለ-ቃል እና “መልክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን የሚያወርድለት ቢሆን እንጅ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ጅብሪል ተልኮ የመጣ መልአክ ነውና ከራሱ አመንጭቶ አይደለም ያወረደው፤ ከዛ ይልቅ ባይሆን ጅብሪል እራሱ የዙፋኑ ባለቤት በሆነው በአላህ ዘንድ የአላህ ባለሟል ነው፤ የአላህ ታማኝ መልእክተኛ ነው፦
81፥20 የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለቤት ዘንድ *ባለሟል* የኾነ፡፡ ذِى قُوَّةٍ عِندَ ذِى ٱلْعَرْشِ مَكِينٍۢ
81፥21 በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ *ታማኝ የኾነ ነው*፡፡ مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ

ጂብሪል “ባለሟል” እና “ታማኝ” መባሉ በራሱ ላኪ እንዳለው ያሳያል፤ ላኪው አላህ፣ ተላኪው ጂብሪል፣ መልእክቱ ቁርአን ነው፤ ጂብሪል ታማኙ መንፈስ ሆኖ ከአላህ ዘንድ ቁርኣንን አውርዶታል፦
26፥193 እርሱን *ታማኙ መንፈስ* አወረደው፤ نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ
16፥102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር *ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው* በላቸው፡፡ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ

“ረቢከ” رَّبِّكَ ማለትም “ጌታህ” ከሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ “ሚን” مِن ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህ የሚያሳየው ታማኙ መንፈስ ከነብያችን”ﷺ” ጌታ ከአላህ በታማኝነት ቁርኣንን እንዳወረደው ነው፤ ስለዚህ ነው አላህ ስለ ጂብሪል ሲናገር፦ “ወደ ባሪያውም አላህ ያወረደውን አወረደ” ብሎ ያለው፦
53፥10 *ወደ ባሪያውም አላህ ያወረደውን አወረደ*፡፡ فَأَوْحَىٰ إِلَىٰ عَبْدِهِ مَا أَوْحَىٰ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአላህ ባሕርይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

"ሲፋህ" صِفَة የሚለው ቃል "ወሰፈ" وَصَفَ‎ ማለትም "ገጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ባሕርይ" ወይም "መገለጫ"description" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር "ሲፋት" صِفَات‎ ነው፦
21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
43፥82 *የሰማያትና ምድር ጌታ የዙፋኑ ጌታ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ*። سُبْحَانَ رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
37፥180 *የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ*። سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ

"ከሚሉት" ለሚለው ቃል የገባው “የሲፉነ” يَصِفُونَ ሲሆን “ባሕርይ ካደረጉለት”they attribute” ማለት ነው፥ ፍጡራን ከወሰፉት ሲፋህ ሁሉ የጠራ ነው። “ሡብሓን” سُبْحَٰن የሚለው ቃል “ሠበሐ” سَبَّحَ ማለትም “አጠራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስብሐት” ማለት ነው፥ “ተሥቢሕ” تَسْبِيح ማለት ደግሞ “ተስብሖት” ማለት ሲሆን አላህ ከወሰፉት የነውርና የጎደሎ ባሕርይ ማጥራት ነው። አላህ እራሱ በራሱ የእኔ ሲፋህ ይህ ነው ብሎ ከተናገረበት ውጪ ውድቅ ማድረግ ተስቢሕ ነው። እራሱን በራሱ ከገለጣቸው ባሕርይ መካከል ደግሞ እርሱ ከዐርሽ በላይ መሆኑ ነው፦
20፥5 እርሱ አር-ረሕማን ከዐርሹ ላይ *የተደላደለ* ነው። ٱلرَّحْمَٰنُ عَلَى ٱلْعَرْشِ ٱسْتَوَىٰ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የተደላደለ" ለሚለው ቃል የገባው “ኢሥተዋ” اسْتَوَىٰ ሲሆን የቋንቋ ሊሂቃን፦ "ኢሥተዋ" የሚለው ቃል በተለየየ ዓይነት ትርጉም ይመጣል" ይላሉ፤ ይህ ትርጉም ለሁለት ከፍለው ያዩታል፥ አንዱ “ሙቀየድ” ሲሆን ሌላው “ሙጥለቅ” ነው።
"ሙጥለቅ” مُطْلَق ማለትም “ያልተገደበ”un-restricted” ሆኖ ሲመጣ ነው፥ ለምሳሌ “ኢሥተዋ” ከሚለው ቃል በፊትና በኃላ ምንም መስተዋድድ ሳይመጣ ኢስተዋእ ሳይገደብ ሲቀር “በሰለ” “ተስተካከለ” “ሞላ” በሚል ቃል ይመጣል፦
28:14 ብርታቱንም በደረሰ እና *በተስተካከለ* ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ እንዲሁም መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥ وَٱسْتَوَىٰٓ ءَاتَيْنَٰهُ حُكْمًۭا وَعِلْمًۭا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ

ሁለተኛው ደግሞ “ሙቀየድ” مُقَيَّد ማለትም “የተገደበ”restricted” ማለት ሲሆን “ኢሥተዋ” ከሚለው ቃል በፊትና በኃላ መስተዋድድ ሲመጣ ነው፥ ለምሳሌ "ኢሥተዋ" ከሚለው ቃል በኃላ “ኢላ” إِلَى ማለትም “ወደ” የሚለው መስተዋድድ ከመጣ “አሰበ” በሚል ይመጣል፦
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ *አሰበ*፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ

ነገር ግን ሱረቱ ጣሀ 20፥5 ላይ አላህ ከዐርሽ በላይ ለመሆኑ የዋለው “ኢሥተዋ” የሚለው ቃል ላይ “ዐላ” عَلَى በሚል መስተዋድድ መምጣቱ “ተዓላ” تَعَالَى ማለትም “ከፍ አለ” የሚል ትርጉም ይኖረዋል። የነቢያችን”ﷺ” የቅርብ ዘመድ እና ሶሐቢይ የሆነው ኢብኑ ዐባሥ ሲሆን የእርሱ ተማሪ ሙጃሂድ "ኢሥተዋ" የሚለውን “ዓላ” عَلاَ ማለትም "በላይ" በማለት ፈሥሮታል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 51 ኪታቡል ተውሒድ ባብ 22
ሙጃሂድም አለ፦ *”ኢሥተዋ” ማለት “ዓላ ዐለል ዐርሽ” ማለት ነው”*። وَقَالَ مُجَاهِدٌ: {اسْتَوَى} عَلاَ عَلَى الْعَرْشِ

አምላካችን አላህም እራሱን በሶስተኛ መደብ “አል-አዕላ” الْأَعْلَى መሆኑን ተናግሯል፦
87፥1 *ከሁሉ በላይ የሆነዉን* ጌታህን ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى

ይህም የሚያሳየው አላህ ከፍጥረት ሁሉ በላይ መሆኑን ነው፥ አላህ በፈጠረው ፍጥረታት ላይ ሁሉ የበላይ ታላቅ ስለሆነ እራሱን “አል-ዓሊይ” العَلِيّ ብሏል፦
42፥4 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፥ *እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው”* لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ

አላህ ከትልቁ ፍጥረት ከዐርሽ በላይ እንዴት እንደሚኖር ከይፊያው አልተገለጸም፤ “ከይፊያህ” كَيْفِيَّة ማለትም “እንዴትነት”howness ማለት ነው፦
አል-ኢሥቲዝካር መጽሐፍ 2, ቁጥር 529
ዐብደላህ ኢብኑ ናፊዕ እንደዘገበው፦ *"ማሊክ አላህ ይርሓመውና ስለ የአላህ አዘ ወጀል ንግግር፦ "እርሱ አር-ረሕማን ከዐርሹ ላይ የተደላደለ ነው" ብሎ ጠየቀ። አንድም ሰው፦ "እንዴት ነው የተደላደለው? አለ። ማሊክም፦ "መደላደሉ የታወቀ ነው፥ "እንዴትነቱ" ግን ዐይታወቅም" እንዴትነቱን መጠየቅ ግን ቢድዓ ነው። አንተም በዚህ እኩይ ጥያቄ መለከፍህን አያለው" አለ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ نَافِعٍ قَالَ سُئِلَ مَالِكٌ رحمه الله عَنْ قَوْلِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى قَالَ كَيْفَ اسْتَوَى فَقَالَ اسْتِوَاؤُهُ مَعْلُومٌ وَكَيْفِيَّتُهُ مَجْهُولَةٌ وَسُؤَالُكُ عَنْ هَذَا بِدْعَةٌ وَأَرَاكَ رَجُلَ سُوءٍ
ታላቁ ሙፈሢር ኢሥማዒል አብኑ ከሲር "ኢሥተዋ" የሚለውን እውነታውን ያለ እንዴትነት፣ ያለ ማመሳሰል፣ ያለ ትርጉም አልባ እንደሚቀበሉ ተናግረዋል፦
አት-ተፍሢሩል አብኑ ከሲር ሱሩቱል አዕራፍ 7፥54
*አላህ እንዳለው፦ "እርሱ ከዐርሽ በላይ ነው" በሚለው ትርጉም ላይ ሰዎች ብዙ የግጭት አመለካከት አላቸው፥ ምንም ይሁን እኛ ከቀደምት መዝሃብ ከሠለፉ-ሷሊሑን ከማሊክ፣ ከአል-አውዛዒይ፣ ከአስ-ሰውሪይ፣ ከአል-ለይስ ኢብኑ ሠዒድ፣ ከአሽ-ሻፊሪይ፣ ከአሕመድ፣ ከኢሥሐቅ ኢብኑ ራህወያህ እና ከተቀሩት የኢሥላም የጥንትና የአሁን ምሁራን ተከትለን እንወስዳለን። "ኢሥተዋ" የሚለውን ቀጥተኛ ትርጉም እውነታውን ያለ እንዴትነት፣ ያለ ማመሳሰል፣ ያለ ትርጉም አልባ እንቀበላለን። እንዲሁ ለእነዚያ አላህን ከፍጥረቱ ጋር እኩል ለሚያደርጉት ውድቅ በማድረግ እና ለአላህ ምንንም ሳናመሳስል እናምናለን። "የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው" 42፥11 ። ከኢማሞች ለተጠቃሽ ያክል የኢማም ቡኻሪይ አስተማሪ ኑዐይም ኢብኑ ሐመዱል ኹዛዒይ፦ "ማንም አላህን ከፍጥረቱ ያመሳሰለ ከፍሯል፥ ማንም አላህ ስለራሱ የወሰፈውን ባሕርይ ያስተባበለ ከፍሯል" ብሏል*። وأما قوله تعالى : ( ثم استوى على العرش ) فللناس في هذا المقام مقالات كثيرة جدا ، ليس هذا موضع بسطها ، وإنما يسلك في هذا المقام مذهب السلف الصالح : مالك ، والأوزاعي ، والثوري ، والليث بن سعد ، والشافعي ، وأحمد بن حنبل ، وإسحاق بن راهويه وغيرهم ، من أئمة المسلمين قديما وحديثا ، وهو إمرارها كما جاءت من غير تكييف ولا تشبيه ولا تعطيل . والظاهر المتبادر إلى أذهان المشبهين منفي عن الله ، فإن الله لا يشبهه شيء من خلقه ، و ( ليس كمثله شيء وهو السميع البصير ) [ الشورى : 11 ] بل الأمر كما قال الأئمة - منهم نعيم بن حماد الخزاعي شيخ البخاري - : " من شبه الله بخلقه فقد كفر ، ومن جحد ما وصف الله به نفسه فقد كفر

እንግዲህ እኛም ከላይ ያሉትን የቀደምት ሠለፍ አረዳድ ያለ ተክዪፍ፣ ያለ ተሽቢህ፣ ያለ ተሕሪፍ፣ ያለ ተዕጢል "አላህ ከዙፋኑ በላይ ነው" ብለን እናምናለን።
1. “ተክዪፍ” تَكْيِيف ማለት "እንዴት ብሎ መፈላሰፍ" ነው፣
2. "ተሽቢህ" تَشبِيه‎ ማለት "ከፍጡር ጋር ማመሳሰል" ነው፣
3. "ተሕሪፍ" تَحْرِيف ማለት "ትርጉሙን ማዛባት" ነው፣
4. “ተዕጢል” تَعْطِيل ማለት "ትርጉም የለሽ ማድረግ" ነው።
ያለ ተክዪፍ፣ ያለ ተሽቢህ፣ ያለ ተሕሪፍ፣ ያለ ተዕጢል "አላህ ከዙፋኑ በላይ ነው" ብሎ ማመን የሠለፍ መንሃጅ ነው፥ ይህ ቅኑ የሠለፎች መንሃጅ ከተገለጸ በኃላ ከምእመናኑ መንሃጅ ሌላ የኾነን መንሃጅ መከተል በዲንያህ ጥመት ነው፥ በአኺራ የእሳት መሆን ነው፦
4፥115 *ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእመናኑ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን*፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا

ነገር ግን ሚሽነሪዎች "ኢሥተዋ" የሚለውን "ጀለሠ" በማለት ተሕሪፍ ለማድረግ ሲዳዱ ይታያል። "ጀለሠ" جَلَسَ ማለት "ተቀመጠ" ማለት ሲሆን የራሳቸው ባይብል ላይ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀመጠ ይላል፦
ኢሳይያስ 6፥1 ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት *እግዚአብሔርን በዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት*፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። فِي سَنَةِ وَفاةِ المَلِكُ عُزِّيّا، رَأيتُ الرَّبَّ جالِساً عَلَى عَرشٍ عالٍ، وَأطرافُ ثَوبِهِ تَملأُ الهَيكَلَ
1 ነገሥት 22፥19 ሚክያስም አለ፦ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ *እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ*፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ። فَقالَ مِيخا: «فاسْمَعْ إذاً ما يَقُولُهُ اللهُ! فَقَدْ رَأيتُ اللهَجالِساً عَلَى عَرْشِهِ فِي السَّماءِ. وَرَأيتُ المَلائِكَةَ واقِفِينَ عِندَهُ، بَعضٌ عَنْ يَمِينهِ وَبَعضٌ عَنْ شمالِهِ
ራዕይ 21፥5 *"በዙፋንም የተቀመጠው"*፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፡ አለ። ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፡ አለኝ። ثُمَّ قالَ الجالِسُ عَلَى العَرشِ: «ها إنِّي أجعَلُ كُلَّ شَيءٍ جَدِيداً!» وَقالَ لِي: «اكتُبْ، لِأنَّ هَذِهِ الكَلِماتُ مُعتَمَدَةٌ وَصَحِيحَةٌ.»
ራእይ 19፥4 ሀያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው *በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር*፦ አሜን፥ ሃሌ ሉያ፡ እያሉ ሰገዱለት። ثُمَّ انحَنَى الأربَعَةُ وَالعِشرُونَ شَيخاً وَالكائِناتُ الحَيَّةُ الأربَعَةُ وَسَجَدُوا للهِ الجالِسِ عَلَى العَرشِ وَهُمْ يَقُولُونَ: «آمِين! هَلِّلُويا!»

እነዚህ አናቅጽ ላይ እግዚአብሔር "ጃሊሥ" جَالِس‎ ማለትም "ተቀማጭ" ይለዋል። ነገር ግን በኢሥላም አስተምህሮት ውስጥ አላህ "ጁሉሥ" جُلُوس‎ ማለትም "መቀመጥ" የሚባል ባሕርይ እንዳለው አልተወሠፈም። አላህ "ዩጃሊሥ" يُجَالِسْ ማለትም "አስቀማጭ" ነው፦
አል-ሙዕጀሙል ከቢር 12524
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ የትንሳኤ ቀን በዙፋኑ በስተቀኝ የሚያስቀምጣቸው አሉ፥ ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው። እነርሱ በብርሃናማ መንበሮች ላይ ይሆናሉ፥ ፊቶቻቸውም ብርሃናማ ይሆናል። እነርሱ ነቢያትም አይደሉም፣ ሰማዕታትም አይደሉም፣ ጻድቃንም አይደሉም። እንዲህ ተባለ፦ " የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ታዲያ እነርሱ ከእነማን ናቸው? እርሳቸውም፦ "እነዚህ ለአላህ ተዓላ ክብር ብለው የተዋደዱ ናቸው"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ إِنَّ لِلَّهِ جُلَسَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ عَنْ يَمِينِ الْعَرْشِ وَكِلْتَا يَدَيِ اللَّهِ يَمِينٌ عَلَى مَنَابِرَ مِنْ نُورٍ وُجُوهُهُمْ مِنْ نُورٍ لَيْسُوا بِأَنْبِيَاءَ وَلا شُهَدَاءَ وَلا صِدِّيقِينَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ مَنْ هُمْ قَالَ الْمُتَحَابُّونَ بِجِلالِ اللَّهِ تَعَالَى
"ጁለሣእ" جُلَسَاء ሥርወ-ቃሉ "አጅለሠ" أَجْلَسَ‎ ማለትም "አስቀመጠ" ነው። አላህ "መጅሊሥ مَجْلِس‎ ማለትም "መቀመጫ" የለውም። ዐርሽ የንግሥናው ምልክትና መገለጫ እንጂ መቀመጫ አይደለም። አላህ የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው፦
27፥26 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ *የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው*፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ
9፥129 ቢያፈገፍጉም አላህ በቂዬ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ እርሱም *"የታላቁ ዐርሽ" ጌታ ነው* በላቸው፡፡ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ ۖ وَهُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ

"ዐዚም" عَظِيم ማለት "ታላቅ" ወይም "ትልቅ" ማለት ነው። ትልቁ ፍጥረት ዐርሽ ነው። ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር "የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው" የሚለውን አንቀጽ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦
አት-ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 9፥128
*"የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው" እርሱ ንጉሥ፣ የሁሉ ነገር ፈጣሪ እና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው። ያ እርሱ(ዐርሽ) የፍጥረታት ጣሪያ ነው። ሰማያት፣ ምድር፣ በውስጣቸው ያለ፣ በመካከላቸውም ያለ ሁሉም ፍጥረት ከዐርሽ ሥር ለአላህ ተዓላ ተገዢ ነው። ዕውቀቱ ሁሉን ነገር ያካበበ ነው፣ እርሱ በሁሉ ነገር ላይ መመኪያ ነው"*። ( وهو رب العرش العظيم ) أي : هو مالك كل شيء وخالقه ، لأنه رب العرش العظيم ، الذي هو ، سقف المخلوقات وجميع الخلائق من السماوات والأرضين وما فيهما وما بينهما تحت العرش مقهورون بقدرة الله تعالى ، وعلمه محيط بكل شيء ، وقدره نافذ في كل شيء ، وهو على كل شيء وكيل

እዚህ ተፍሢር ላይ"ሠቅፍ" سَقْف ማለት "መጠናቀቂያ" "ማብቂያ" "ጣሪያ" ማለት ነው፥ "ኸልቅ" خَلْق ማለት ደግሞ "ፍጥረት" ማለት ሲሆን የፍጥረት መጠናቀቂያ፣ ማብቂያ፣ ጣሪያው ዐርሽ ነው። "መኽሉቅ" مَخْلُوق‎ ማለት "ፍጡር" ማለት ሲሆን ዘመካን ነው፥ "ዘመካን" زَمَكَان ማለት የዘማንና የመካን ቃላት ውቅር ነው። "ዘማን" زَمَان ማለት "ጊዜ"time" ማለት ነው፥ "መካን" مَكَان ደግሞ "ቦታ"space" ማለት ነው። አላህ ደግሞ ጊዜና ቦታ ከሚጠናቀቅነት ከዐርሽ በላይ ሆኖ ሁሉን ነገር ያካበበ "ኻሊቅ" خَالِق‎ ማለትም "ፈጣሪ" ነው። ስለዚህ አላህ በቅዱስ ቃሉ በወሰፈው መሠረት፦
ሁኔታው እንዲህ ነው ሳንል
ከፍጡራን ጋር ሳናመሳስል
ትርጉሙን ምንም ሳንቀይር
ትርጉም አልባ ሳናደርግ
"አላህ ከዐርሽ በላይ ነው" ብለን እናምናለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈጣሪ አይተኛም አያንቀላፋም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ሰው በፍጡርነቱ ያንቀላፋል ይተኛልም፤ ፈጣሪ ግን ፍጡር ስላልሆነ አይተኛም አያንቀላፋም፦
መዝ.121:4 እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ #አይተኛም #አያንቀላፋምም

ኢየሱስ ደግሞ በተቃራኒው ፍጡር ስለሆነ ይተኛን ያንቀላፋል፦
ማርቆስ 4:38 እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ #ተኝቶ ነበር፤ #አንቅተውም። መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።

መቼም ኢየሱስ ለእኛ ሲል ነው የተኛውና ያንቀላፋው ከተባለ ለምን ማንቀላፋትና መተኛት አላቆማችሁም? "እኔ የምተኛው የማይተኛ አምላክ ስላለኝ ነው" ተብሎ የተፓሰተው እጅግ በጣም ስህተት ነው፤ የፈጣሪን ባህርይ ለፍጡር መስጠት አይገባም፤ ይህ ቃል መባል ያለበት ፍጡር ለሆነው ለሚተኛው ለኢየሱስ ሳይሆን ኢየሱስ ሲተኛ ሲጠብቀው ለነበረው ለአላህ ብቻ ነው፤ አላህ በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሚባል ባህርይ የለውም፦
2፥255 አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ "#ማንገላጀትም #እንቅልፍም አትይዘውም"፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? ከፍጡሮች በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡

አንዱ አምላክ የማይተኛና የማያንቀላፋ ከሆነ፣ ኢየሱስ ደግሞ የሚተኛና የሚያንቀላፋ ከሆነ ፣ የሚተኛና የሚያንቀላፋ ኢየሱስ ፣ የማይተኛና የማያንቀላፋውን አንዱን አምላክ በምን አይነት መልኩ እንዴት አድርጎ ሊሆን ይችላል?

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የክርስትና የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት አራት ነጥብ ናቸው፦
1ኛ ሦስት ማንነቶችን ማለትም ሥላሴን ማምለክ፥ ግን መመለክ ያለበት አንድ ማንነት ብቻ ነው።
2ኛ ሰው ማምለክ፤ ኢየሱስ ሰውነቱ ይመለካል፤ በሰውነቱ ፍጡር ነው ይላሉና፥ ሰው አይመለክም።
3ኛ ፍጡራንን በሌሉበት ይጣራሉ፤ ፍጡራንን በሌሉበት ወደ እነርሱ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መለማመን፣ መጸለይ፣ ስለት መሳል፣ መስዋዕት ማቅረብ፣ ስማቸውን መጥራት የአምልኮ ክፍል ነው፤ ሁሉን የሚሰማ፣ የሚያይ፣ የሚያውቅ አንድ መለኮት ብቻ ሆኖ ሳለ ወደ መላእክትና ቅዱሳን ይህንን ማድረግ ሺርክ ነው።
4ኛ. ለተቀረጸ ምስል የጸጋ ስግደት ይሰግዳሉ፤ ለተቀረጸ ምስል አትስገድ ተብሎ ነገር ግን በተቃራኒው ከእንጨት፣ ከብር፣ ከወርቅ፣ ከብረት፣ ከድንጋይ ለተቀረጹ መስቀል፣ ስዕል እና ሃውልት ይሰግዳሉ። 

ይህንን ሲረዱ ክርስትናን ለቀው ወደ ኢሥላም ይመጣሉ። ምክንያቱም በኢሥላም አምላክ በአንድ ምንነቱ ላይ ሁሉት ወይም ሦስት ማንነት የሌለበት፤ በአምላክነቱ ላይ ሰውነት የሌለበት፣ በጌትነቱ ላይ ባርነት የሌለበት፣ በሕያውነቱ ላይ ሞት የሌለበት፣ በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሌለበት፣ በኀያልነቱ ላይ ድካም የሌለበት፣ በፈጣሪነቱ ፍጡርነት የሌለበት ነው። መከፋፈል፣ ሰው መሆን፣ ባሪያ መሆን፣ መሞት፣ ማንቀላፋት፣ መድከም፣ መፈጠር የፍጡር ባህርይ ናቸው፤ ፈጣሪ እነዚህን የፍጡራን ባህርይ አይሆንም፤ በእርሱ ባህርይ ውስጥ ማስሆን እንጂ መሆን የሚባል ባህርይ የለውም።

ከአንድ ማንነት ብዙ ማንነት ማምለክ፣ ሰውን ማምለክ፣ ፍጡራንን መለማመን፣ ለተቀረጸ ምስል መስገድ እሥልምና ጋር የለም።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዓሹራእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

“ወር” የሚለው ቃል “ሸህር” شَهْر ሲሆን በቁርኣን 12 ጊዜ ሰፍሮ ይገኛል፦ (1ኛ. 2:185 2ኛ. 2፥194 3ኛ. 2፥196 4ኛ. 2፥217 5ኛ. 5፥2 6ኛ. 5፥97 7ኛ. 9፥36 8ኛ. 9:37 9ኛ. 34:12 10ኛ.46፥15 11ኛ.58፥4 12ኛ.97፥3)፤ የሚያጅበው የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ እነዚህም፦
1ኛ ወር ሙሐረም
2ኛ ወር ሰፈር
3ኛ ወር ረቢዑል-አወል
4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ
5ኛ ወር ጀማዱል-አወል
6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ
7ኛ ወር ረጀብ
8ኛ ወር ሻዕባን
9ኛ ወር ረመዷን
10ኛ ወር ሸዋል
11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ
12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦
9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ

ከእነዚህ 12 ወራት አራቱ የተከበሩ ወሮች፦
1ኛው ወር ሙሐረም
7ኛው ወር ረጀብ
11ኛው ወር ዙል-ቀዒዳህ
12ኛው ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 4662
አቡበከር”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ዘመን አላህ ሰማያትን እና ምድር በፈጠረበት ቀን የቀድሞ ሁኔታ ይመለሳል፤ አንድ ዓመት ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ ከእነርሱም አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ ሦስቱ ተከታታይ ዙል-ቀዒዳህ፣ ዙል-ሒጃህ፣ ሙሐረም ናቸው፥ አራተኛው በጀማዱ-ሣኒ እና በሻዕባን መካከል ያለው ረጀብ ነው*። عَنْ أَبِي بَكْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ إِنَّ الزَّمَانَ قَدِ اسْتَدَارَ كَهَيْئَتِهِ يَوْمَ خَلَقَ اللَّهُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ، السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا، أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ، ثَلاَثٌ مُتَوَالِيَاتٌ، ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ

ከእነዚህ አራት ወራት ደግሞ ሙሐረም ክብር ያለው የአላህ ወር ነው፦
ጃሚዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8 ሐዲስ 59
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “የአላህ መልክእተኛ”ﷺ” እንዲህ ብለዋል፡- *”ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ صِيَامِ شَهْرِ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّم

“አሽ-ሸምሲያህ” الشَمْسِيَّة አቆጣጠር 365 ቀናት የያዘ የፀሐይ አቆጣጠር”solar calended” ሲሆን “አል-ቀመርያ” الْقَمَرِيَّة ደግሞ 354 ቀናትን የያዘ የጨረቃ አቆጣጠር”lunar calender” ነው፤ በጨረቃ አቆጣጠር አዲስ ጨረቃ ሲታይ አዲሱ ወር ሙሐረም ይጀምራል፤ የጨረቃ አቆጣጠር የዓመታትን ቁጥር መቀየሪያ፤ ጾምን መጾሚያ እና ሐጅን ማድረጊያ ምልክት ነው፦
10፥5 *እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው*፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ ۚ مَا خَلَقَ اللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُون
2፥189 *ከለጋ ጨረቃዎች ይጠየቁሃል፤ “እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ፥ ለጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው” በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 170
አል-ሐከም ኢብኑል አዕረኽ እንደተረከው፦ “ወደ ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” ስሄድ እርሱ በዘምዘም ምንጭ አቅራቢያ በልብሱ ተቀምጦ ነበር፤ እኔም ለእርሱ፦ *” ስለ ዓሹራ ጾም ንገረኝ! አልኩት፤ እርሱም፦ “የሙሐረም አዲስ ጨረቃ ስታይ ቁጠር፥ በዘጠነኛው ቀን ጾም መሆኑን አጢን” አለኝ። እኔም ለእርሱ፦ “ስለዚህ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ያጤኑት ነበር? አልኩት፤ እርሱም፦ “አዎ” አለኝ*። عَنِ الْحَكَمِ بْنِ الأَعْرَجِ، قَالَ انْتَهَيْتُ إِلَى ابْنِ عَبَّاسٍ – رضى الله عنهما – وَهُوَ مُتَوَسِّدٌ رِدَاءَهُ فِي زَمْزَمَ فَقُلْتُ لَهُ أَخْبِرْنِي عَنْ صَوْمِ عَاشُورَاءَ ‏.‏ فَقَالَ إِذَا رَأَيْتَ هِلاَلَ الْمُحَرَّمِ فَاعْدُدْ وَأَصْبِحْ يَوْمَ التَّاسِعِ صَائِمًا ‏.‏ قُلْتُ هَكَذَا كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَصُومُهُ قَالَ نَعَمْ

ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አሥረኛው ቀን በላጭ ቀን ነው፤ ይህ ዐሥረኛው ቀን “ዓሹራእ” ይባላል፤ “ዓሹራእ” عَاشُورَاء‎ የሚለው ቃል “ዐሽር” عَشْرٍ ማለትም “ዐሥር” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ዐሥረኛ” ማለት ነው፤ ይህ ቀን በፈቃደኝነት የሚጾምበት ቀን ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 30 ሐዲስ 107
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የዓሹራን ቀን ቁሬይሾች ይጾሙ ነበር፤ በዚህ ቀን የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ወደ መዲና በመጡ ጊዜ ይጾሙ እና እንዲጾም ያዙ ነበር፤ የረመዷን ወር ጾም በተደነገገ ጊዜ ግን የዓሹራእ ቀን ጾም ያሻው የሚጾመው፥ ያሻው የማይጾመው ሆነ*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ كَانَ يَوْمُ عَاشُورَاءَ تَصُومُهُ قُرَيْشٌ فِي الْجَاهِلِيَّةِ، وَكَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَصُومُهُ، فَلَمَّا قَدِمَ الْمَدِينَةَ صَامَهُ، وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ، فَلَمَّا فُرِضَ رَمَضَانُ تَرَكَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ، فَمَنْ شَاءَ صَامَهُ، وَمَنْ شَاءَ تَرَكَهُ‏.‏
ጥቂት ቁሬይሾች በመዲና ላይ ያሉት አይሁዳዊያን ይህንን ቀን ይጾሙ ነበር። ይህ ቀን የኢሥራዒል ልጆች ከፈርዖን ነጻ የወጡበት ቀን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13 ሐዲስ 162
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ወደ መዲና በመጡ ጊዜ አይሁዳውያን የዓሹራን ቀን ሲጾሙ አጤኑ፤ አይሁዳውያን ስለዚያ ቀንም ይጠይቁና፦ “አላህ ለሙሳ እና ለኢሥራዒል ልጆች በፈርዖን ላይ ድል የሰጠበት ነው” ብለው ይመልሱ ነበር። ነቢዩም”ﷺ”፦ “ከእናንተ ይልቅ እኛ ለሙሳ ቅርብ ነን” አሉ፤ ይህ ቀን እንዲጾም አዘዙን*። عَنِ ابْنِ، عَبَّاسٍ – رضى الله عنهما – قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ فَوَجَدَ الْيَهُودَ يَصُومُونَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ فَسُئِلُوا عَنْ ذَلِكَ فَقَالُوا هَذَا الْيَوْمُ الَّذِي أَظْهَرَ اللَّهُ فِيهِ مُوسَى وَبَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَى فِرْعَوْنَ فَنَحْنُ نَصُومُهُ تَعْظِيمًا لَهُ ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ نَحْنُ أَوْلَى بِمُوسَى مِنْكُمْ ‏”‏ ‏.‏ فَأَمَرَ بِصَوْمِهِ

ሚሽነሪዎች በኢሥላም ያሉትን ሕግና ሥርዓት በመጽሐፋቸው መኖሩን ይጠይቃሉ፤ ከሌለ ለምን የለም? ብለው ይጠይቃሉ፤ ካለ ደግሞ ያው ተኮረጀ ይላሉ። ግን የሚገርመው ነገር ስለ ዓሹራ ቀን መጽሐፋቸው ላይ እያለ እንደማያነቡት ነው፦
ዘሌዋውያን 23፥34 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ *በዚህ በሰባተኛው ወር ከአሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የዳስ በዓል ይሆናል*።
ዘሌዋውያን 23፥42-43 ሰባት ቀን በዳሶች ውስጥ ትቀመጣላችሁ፤ *ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በዳስ ውስጥ እንዳስቀመጥኋቸው የልጅ ልጆቻችሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእስራኤል ያሉት የአገር ልጆች ሁሉ በዳስ ውስጥ ይቀመጡ*፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

“ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ያ ወር በዕብራውያን አቆጣጠር ሰባተኛው ወር ሲሆን በእኛ ሙሐረም ነው፤ የሚያጅበው በዚህ ወር በዐሥረኛው ቀን እንዲጾሙ መታዘዙ ነው፦
ዘኍልቍ 29፥7 ከዚህም *ከሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቁት*፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታድርጉ።
ዘሌዋውያን 16፥30 *በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት*፥ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤

“እራሳችሁን አስጨንቋት” ለሚለው ቃል የገባው “ወኢንኒተም” וְעִנִּיתֶ֖ם ሲሆን በኢንግሊሽ ትርጉም እና የተለያዩ ማብራሪያዎች ጾምን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፤ አይሁዳውያን ይህንን ቀን እንደሚጾሙ እሙንና ቅቡል ነው። እኛም ነቢያችን”ﷺ” የሰጡንን ነገር ሁሉ እንድንይዝ አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ ነግሮናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ስለዚህ በዚህ ቀን መጾሙ ሙስተሃብ ነው፤ በዚህ ቀን መጾሙ ያለው ትሩፋት የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” ተጠይቀው “ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል” ብለዋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 1810
አቢ ቀታዳህ እንዳስተላለፉት፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *”የዓሹራእ ቀን መጾም ያለፈውን አንድ ዓመት ወንጀል ከአላህ ያስተሰርያል”*። عَنْ أَبِي قَتَادَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ إِنِّي أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሦስቱ መልእክተኞች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

40፥78 *ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ

አምላካችን አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት መልእክተኞች ልኳል። ከእነርሱ ውስጥ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ስማቸው የተተረኩ አሉ፥ ከእነርሱም ውስጥ ስማቸው ያልተተረኩ አሉ፦
40፥78 *ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ

ስማቸው ካልተተረኩት መልእክተኞች መካከል ሦስት መልእክተኞች ወደ አንዲት ከተማ ልኳል፦
36፥13 *ለእነርሱም የከተማይቱን ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ የኾነውን ግለጽላቸው*፡፡ وَٱضْرِبْ لَهُم مَّثَلًا أَصْحَٰبَ ٱلْقَرْيَةِ إِذْ جَآءَهَا ٱلْمُرْسَلُونَ
36፥14 *ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክን እና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታን እና "እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን" ባሏቸው ጊዜ የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው*፡፡ إِذْ أَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمُ ٱثْنَيْنِ فَكَذَّبُوهُمَا فَعَزَّزْنَا بِثَالِثٍۢ فَقَالُوٓا۟ إِنَّآ إِلَيْكُم مُّرْسَلُونَ

ታላቁ ሙፈሢር ኢሥማኢል ኢብኑ ከሲር በተፍሢራቸው ላይ ስለ እነዚህ ሦስት መልእክተኞች ማንነት በነቢብ እና በነሲብ የተተረከውን አስቀምጠዋል፦
አት-ተፍሢል ኢብኑ ከሲር ሱረቱ ያሲን 36፥13-14
*"ለእነርሱም የከተማይቱን ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ የኾነውን ግለጽላቸው" ኢብኑ ኢሥሓቅ ከከዕብ አል-አሕባር፣ ከወህብ ኢብኑ ሙነቢህ በተላለፈው ኢብኑ ዐባሥን መሠረት አድርጎ በዘገበው፦ "ያቺ ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት፥ በእርሷም አንጢሕሥ የሚባል ንጉሥ ጣዖት የሚያመልክ የአንጢሕሥ ልጅ፣ የአንጢሕሥ ልጅ ነበረ። አላህ ወደ እርሱ ሦስት መልእክተኞችን ላከ፥ እነርሱም፦ ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም ናቸው። እርሱም በእነርሱ አስተባበለ።
ቡረይዳህ ኢብኑል ሑሰይብ ከዒክረማህ፣ ከቀደታህ እና ከአዝ-ዙህሪይ እንዳገኘው ያቺ ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት ብሏል"*።

*"ከተማይቱ አንጧኪያህ ስለመሆኗ እና ከዚህ በታች የምንመለከተውን ትረካ ዐበይት ኢማሞች በታሪኩ ማብራሪያ እርግጠኛ አይደሉም። ኢንሻላህ ተዓላ "ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክን እና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታን እና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው" ሸዕይብ አል-ጀባኢይ ከወሕብ ኢብኑ ሡለይማን፣ ኢብኑ ጁረይጅ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ "የመጀመሪያዎቹ ሁለት መልእክተኞች ስም ሸሙን እና ዩሐና ናቸው፥ ሦስተኛው ቡሉስ ነው። ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት"*።
( مثلا أصحاب القرية إذ جاءها المرسلون ) .
قال ابن إسحاق - فيما بلغه عن ابن عباس ، وكعب الأحبار ، ووهب بن منبه - : إنها مدينة أنطاكية ، وكان بها ملك يقال له : أنطيخس بن أنطيخس بن أنطيخس ، وكان يعبد الأصنام ، فبعث الله إليه ثلاثة من الرسل ، وهم : صادق وصدوق وشلوم ، فكذبهم .
وهكذا روي عن بريدة بن الحصيب ، وعكرمة ، وقتادة ، والزهري : أنها أنطاكية .

وقد استشكل بعض الأئمة كونها أنطاكية ، بما سنذكره بعد تمام القصة ، إن شاء الله تعالى .
وقوله : ( إذ أرسلنا إليهم اثنين فكذبوهما ) أي : بادروهما بالتكذيب ، ( فعززنا بثالث ) أي : قويناهما وشددنا أزرهما برسول ثالث .
قال ابن جريج ، عن وهب بن سليمان ، عن شعيب الجبائي قال : كان اسم الرسولين الأولين شمعون ويوحنا ، واسم الثالث بولص ، والقرية أنطاكية .

ከላይ እንደተገለጸው የእነዚህ ሦስት መልእክተኞች ስም እና የከተማይቱ ስም በቁርኣን ላይ አልተገለጸም። ግን በተፍሢሩ ላይ ሁለት ዘገባዎች ተቀምጠዋል።
የመጀመሪያው ዘገባ ሦስት መልእክተኞች ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም የተባሉት ትረካ የተፋሰስ ወይም የላይዮሽ ትረካ”vertical narration” ሲሆን ከታች ትውልድ ወደ ላይ ትውልድ ሲወርድና ሲወራረድ ኢብኑ ኢሥሓቅ ከከዕብ አል-አሕባር፣ ከዕብ አል-አሕባር ደግሞ ከወህብ ኢብኑ ሙነቢህ፣ ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ደግሞ ከኢብኑ ዐባሥ የተገኘ ትረካ ነው፦
ኢብኑ ዐባሥ
|
ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ
|
ከዕብ አል-አሕባር
|
ኢብኑ ኢሥሓቅ
ይህ የላይዮሽ ዘገባ ሙተሲል ነው። “ሙተሲል” مُتَّصِل ማለት ሰንሰለት የተቀበለበት “አያያዥ ማንነት” ነው። “ኢሥናድ” اِسْنَاد ማለት “ትርክት” ማለት ነው፥ ትረካው የሚተላለፍበት ሰንሰለት ደግሞ “ሠነድ” سَنَد ሲባል የሚያስተላልፈው “ተራኪ” ደግሞ “ሙሥነድ” مُسْنَد ይባላል። ኢሥናዱ፦ "አላህ ወደ እርሱ ሦስት መልእክተኞችን ላከ፥ እነርሱም፦ ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም ናቸው" የሚል ነው፥ ሠነዱ ከዕብ አል-አሕባር እና ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ሲሆን ሙሥነድ ደግሞ ኢብኑ ዐባሥ ነው። ኢብኑ ዐባሥ ደግሞ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ሶሓቢይ ነው። ስለዚህ የኢብኑ ኢሥሓቅ ዘገባ አስተማማኝ ነው።
አንጢሕሥ በታሪክ ሦስተኛ አንጥያኮስ የተባለው ንጉሥ አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ ሲሆን አያቱ ሁለተኝ አንጥያኮስ ቴኦስ፥ ቅድመ-አያቱ አንደኛው አንጥያኮስ ሶተር ይባላሉ። ይህ ንጉሥ በ 175 ቅድመ-ልደት ንግሥናን ጨብጧል፥ ዚየስ ኦሊምፒየስ የተባለውን ጣዖት በማምለክና የአሳማ ስጋ መስዋዕት በመሰዋቱ ይታወቃል። አንጧኪያህ በታሪክ አንጾኪያ የሚለው "አናጽ" ከምትባለው የጦርነት አምላክ ወይም "አንጥያኮስ" ከተባለው የነገሥታቱ ስም እንደመጣ ይነገራል። እንደ ኢብኑ ዐባሥ ትርክት አላህ ወደ እነርሱ ሦስት መልእክተኞችን ልኳል።
ሁለተኛው ዘገባ ሦስት መልእክተኞች ሸሙን፣ ዩሐና እና ቡሉስ የተባሉት ትረካ የአግድም ወይም የጎንዮሽ ትረካ”horizontal narration” ሲሆን በአንድ ትውልድ ሸዕይብ አል-ጀባኢይ ከወሕብ ኢብኑ ሡለይማን፥ ወሕብ ኢብኑ ሡለይማን ደግሞ ከኢብኑ ጁረይጅ የተገኘ ትረካ ነው፦
ሸዕይብ አል-ጀባኢይ – ወሕብ ኢብኑ ሡለይማን – ኢብኑ ጁረይጅ
ኢብኑ ጁረይጅ ከሦስተኛው ትውልድ ታቢዑ አት-ታቢዒን ከሚባሉት ነው።
ብዙ ጊዜ "ኢሥራኢሊያት" إِسْرَائِيلِيَّات ማለትም "የአይሁድ እና የክርስትና ትረካ" ያስተላልፋል። አባቱ ጁረይጅ ሲሆን የሮማ ክርስቲያን የነበረ፥ ስሙም ግሪጎሪ ነበር። የእርሱ ዘገባ ከሁለተኛ ትውልድ ከታቢዒይ እና ከመጀመሪያ ትውልድ ከሶሓቢይ የመጣ ኢሥናድ የለም። ሠነድ እና ሙሥነድ የሌለው ኢሥናድ ሙዐለቅ ነው፥ “ሙአለቅ” مُعَلَّق ማለት በሙሐዲስ እና በሙሥነድ መካከል ምንም አይነት ተራኪና ትረካ ሳይኖር ሲቀር “ሙዐለቅ” ይባላል። "ሙሐዲስ" مُحَدِيث ማለት "ዘጋቢ" ማለት ነው። ስለዚህ ከሸዕይብ አል-ጀባኢይ የተገኘው ዘገባ ደካማ ስለሆነ ውድቅ ነው።
ሲቀጥል ሸሙን ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዩሐና ዮሐንስ እና ቡሉስ ጳውሎስ ከሆኑ እነዚህ ሦስት ሰዎች በዒሣ እና በነቢያችን"ﷺ" መካከል ያሉ ናቸው፥ በዒሣ እና በነቢያችን"ﷺ" መካከል ደግሞ ምንም ነቢይ የለም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 190
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ። እነርሱም፦ "ይህ እንዴት ይሆናል? የአላህ መልእክተኛም፦ ሆይ!" አሉ። እርሳቸው፦ "ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው፣ እናቶቻቸው ይለያያሉ፣ ነገር ግን ሃይማኖታቸው አንድ ነው። በእኔ እና በእርሱ መካከል አንድም ነቢይ የለም" አሉ"*። قَالَ هَذَا مَا حَدَّثَنَا أَبُو هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَذَكَرَ أَحَادِيثَ مِنْهَا وَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَنَا أَوْلَى النَّاسِ بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ فِي الأُولَى وَالآخِرَةِ ‏"‏.‏ قَالُوا كَيْفَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ الأَنْبِيَاءُ إِخْوَةٌ مِنْ عَلاَّتٍ وَأُمَّهَاتُهُمْ شَتَّى وَدِينُهُمْ وَاحِدٌ فَلَيْسَ بَيْنَنَا نَبِيٌّ ‏

ስለዚህ በኢየሱስ እና በነቢያችን"ﷺ" መካከል ያሉት ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ እና ጳውሎስ ነቢይ ካልነበሩ ከሸዕይብ አል-ጀባኢይ የተገኘው ዘገባ ሙድጠሪብ ነው፥ “ሙድጠሪብ” مُضْطَرِب ማለት አንድ ዘገባ የተቃረኑ የዘገባ ሰነድ ሲኖረው ወይንም ዘገባው የተቃረነ መትን ሲኖረው “ሙድጠሪብ” ይባላል። ሢሰልስ ኢብኑ ከሲር፦ "ከዚህ በታች የምንመለከተውን ትረካ ዐበይት ኢማሞች በታሪኩ ማብራሪያ እርግጠኛ አይደሉም" ብሎ አስተማማኝ ትርክት እንዳልሆነ አበክሮና አዘክሮ አስቀምጧል። ሚሽነሪዎች ጳውሎስን በኢሥላም ውስጥ ለማስገባት እና "የአላህ መልእክተኛ ነው! ተቀበሉት" ለማለት ያቀረቡት ስሁት ሙግት ለዛሬ አልተሳካም። እዛው መንደራችሁ አቧራ አስነሱ እንጂ እዚህ እኛ ጋር ቅቤ ጥበሱልኝ፥ ዕጣን አጭሱልኝ፣ በሞቀበት ጣዱኝ የምትሉት ነገር በስሙር ሙግት ድባቅ ይገባል። "አምልጦኝና አዳልጦኝ ነው" ብትሉ ውልፍጥና ዝልፍጥ አንልም።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንዲት ከተማ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

26፥208 *"አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስጠንቃቂዎች ያሏት እና ያስተባበለች ኾና እንጅ አላጠፋንም"*፡፡ وَمَا أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ

አምላካችም አላህ ለአንዲት ከተማ መልእክተኛ ልኮ መልእክቱን ከማስተባበሏ በፊት ማንንም አይቀጣም፥ ለእርሷ አስጠንቃቂ መልእክተኛ ከመጣላት በኃላ ያንን መልእክት ስታስተባብል ትጠፋለች፦
17፥15 *መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም*፡፡ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا
26፥208 *"አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስጠንቃቂዎች ያሏት እና ያስተባበለች ኾና እንጅ አላጠፋንም"*፡፡ وَمَا أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ

አንዲት ከተማ ስትበድል አላህ በበደሏ ለማጥፋት ሲፈልግ ቅድሚያ መልእክተኛ ልኮ፥ ከዚያ በመልእክተኛው የተላለፈውን ትእዛዝ ሲያምጹ ያቺ ያመጸችውን ከተማ ቅጣቱ ይፈጸምባታል፥ ማጥፋትንም ያጠፋታል፦
17፥16 *"ከተማንም ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ነዋሪዎችዋን "እናዛለን"፡፡ በውስጧም ያምጻሉ፡፡ በእርሷም ላይ ቃሉ ቅጣቱ ይፈጸምባታል፡፡ ማጥፋትንም እናጠፋታለን"*፡፡ وَإِذَا أَرَدْنَا أَن نُّهْلِكَ قَرْيَةً أَمَرْنَا مُتْرَفِيهَا فَفَسَقُوا فِيهَا فَحَقَّ عَلَيْهَا الْقَوْلُ فَدَمَّرْنَاهَا تَدْمِيرًا

"እናዛለን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ይህንን ትእዛዝ በመልእክተኞቹ አንደበት ነዋሪዎችን እንዲታዘዙ ያዛል፥ ነዋሪዎች በእርሱ ሲያምጹ ያጠፋል፦
ተፍሢሩል ጀላለይን 17፥16
*"ከተማንም ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ነዋሪዎችዋን እናዛለን" በመልእክተኞቻችን አንደበት ነዋሪዎችን እንዲታዘዙ እናዛለን፥ "በውስጧም ያምጻሉ" ወጥተው በትእዛዛችን ላይ ያምጻሉ። "በእርሷም ላይ ቃሉ ቅጣቱ ይፈጸምባታል" በቅጣት ይፈጸምባታም፥ "ማጥፋትንም እናጠፋታለን" ሕዝቡን እና አበላሾችን በጥፋት እናጠፋታለን"*። { وَإِذآ أَرَدْنَا أَن نُّهْلِكَ قَرْيَةً أَمَرْنَآ مُتْرَفِيهَا } مُنَعمِّيها بمعنى رؤسائها بالطاعة على لسان رسلنا { فَفَسَقُواْ فِيهَا } فخرجوا عن أمرنا { فَحَقَّ عَلَيْهَا ٱلْقَوْلُ } بالعذاب { فَدَمَّرْنَٰهَا تَدْمِيرًا } أهلكناها بإهلاك أهلها وتخريبها.

ይህ የሚያዘውን ትእዛዝ ያመጸች መጥፎንም ቅጣት የቀጣት ብዙ ናት፥ በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስጠንቃቂ መልእክተኛ ሲላክ ነዋሪዎችዋ፦ "እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት ላይ አገኘን፥ እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተከታዮች ነን" ይሉ ነበር፦
65፥8 *ከከተማም ከጌታዋ ትዕዛዝ እና ከመልክተኞቹም ያመጸች፣ ብርቱንም ቁጥጥር የተቆጣጠርናት፣ መጥፎንም ቅጣት የቀጣናት ብዙ ናት*፡፡ وَكَأَيِّن مِّن قَرْيَةٍ عَتَتْ عَنْ أَمْرِ رَبِّهَا وَرُسُلِهِ فَحَاسَبْنَاهَا حِسَابًا شَدِيدًا وَعَذَّبْنَاهَا عَذَابًا نُّكْرًا
43፥23 ነገሩ እንደዚሁም ነው፡፡ *ከበፊትህ በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስጠንቃቂን አላክንም፤ ነዋሪዎችዋ እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት ላይ አገኘን፤ እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተከታዮች ነን ያሉ ቢኾኑ እንጅ*፡፡ وَكَذَٰلِكَ مَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ فِي قَرْيَةٍ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتْرَفُوهَا إِنَّا وَجَدْنَا آبَاءَنَا عَلَىٰ أُمَّةٍ وَإِنَّا عَلَىٰ آثَارِهِم مُّقْتَدُونَ

17፥16 እና 43፥23 ላይ "ሙትረፊን" مُتْرَفِين ማለት "ነዋሪዎች" ማለት ነው። የከተማ ነዋሪዎችዋ አስጠንቃቂ ሲላክላቸው፥ አስጠንቃቂ መልእክተኛ በተላከበት ትእዛዝ ከሓዲዎች ይሆናሉ፥ አላህ ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ ያላት ሆና፥ የአላህ አንቀጽ በእነርሱ ላይ የሚያነብ መልክተኛን ከላከ በኃላ ያንን ትእዛዝ ሲያስተባብሉ ያጠፋል፦
34፥34 *"በከተማም አስጠንቃቂን አላክንም፥ "ነዋሪዎችዋ" «እኛ በዚያ በእርሱ በተላካችሁበት ከሓዲዎች ነን» ያሉ ቢኾኑ እንጂ*"፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا فِي قَرْيَةٍ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتْرَفُوهَا إِنَّا بِمَا أُرْسِلْتُم بِهِ كَافِرُونَ
15፥4 *"ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ ያላት ኾና እንጂ አላጠፋንም"*፡፡ وَمَا أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلَّا وَلَهَا كِتَابٌ مَّعْلُومٌ
28፥59 *"ጌታህም ከተሞችን በዋናዋ ውስጥ አንቀጾቻችንን በእነርሱ ላይ የሚያነብ መልክተኛን እስከሚልክ ድረስ አጥፊ አልነበረም፡፡ ከተሞችንም ባለቤቶቿ በዳዮች ሆነው እንጅ አጥፊዎች አልነበርንም"*፡፡ وَمَا كَانَ رَبُّكَ مُهْلِكَ الْقُرَىٰ حَتَّىٰ يَبْعَثَ فِي أُمِّهَا رَسُولًا يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِنَا ۚ وَمَا كُنَّا مُهْلِكِي الْقُرَىٰ إِلَّا وَأَهْلُهَا ظَالِمُونَ

ስለዚህ "እናዛለን" የሚለው ትእዛዝ መጽሐፉን ወይም አንቀጹን ነው እንጂ "እንዲያምጹ እናዛለን" ማለት በፍጹም አይደለም፥ ለማንሸዋረር አትሞክሩ። የቁርኣን አናቅጽ ነቅሶና ወቅሶ ለማውጣት እና እርሾና ጌሾ ጨምሮ ለማብኳትና ለማስከር ብትዳዱም በኢሥላም ዐቅብተ-እምነት ትጥቅና ስንቅ ይዘን መሞገትና መሟገት እንደሚቻል ምንጨታዊ ሙግታችን ጉልህ ማሳያ ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ከሺርክ በስተጀርባ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

36፥60 *"የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አታምልኩ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?* أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው። ዒባዳህ በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦
1ኛ. "ዒባደቱል ቀልቢያ" عِبَادَة قَلْبِيَّة ማለት "የኃልዮ አምልኮ” ማለት ነው፥ "ቀልብ" قَلْب ማለት "ኃልዮ" ወይም "ልብ" ማለት ነው።
2ኛ. "ዒባደቱል ቀውልያ” عِبَادَة قَوْلِيَّة ማለት "የነቢብ አምልኮ" ማለት ነው፥ "ቀውል" قَوْل ማለት "ነቢብ" ወይም "አንደበት" ማለት ነው።
3ኛ. "ዒባደቱል ዐመልያ" عِبَادَة عَمَلِيَّة ማለት "የገቢር አምልኮ" ማለት ነው፥ "ዐመል" عَمَل ማለት "ገቢር" ወይም "ድርጊት" ማለት ነው።

"ዱዓ" ደግሞ በቀውል ከሚከናወን ዒባዳህ አንዱ ነው፥ “ዱዓእ” دُعَآء የሚለው ቃል "ደዓ" دَعَا ማለትም "ለመነ" "ጠራ" "ጸለየ" "ተማጸነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልመና" "ጥሪ" "ጸሎት" "ተማጽንዖ" ማለት ነው። ዱዓእ የአንድ አምላክ የአላህ ሐቅና ገንዘብ ነው፦
2፥186 *”ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ “እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ*”፡፡ ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ
40፥60 ጌታችሁም አለ *«ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ"*፡፡ وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 2
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ዱዓእ ዒባዳህ ነው፥ ከዚያም፦ "ጌታችሁም አለ *«ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና" የሚለውን አንቀጽ ቀሩ"*። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ إِنَّ الدُّعَاءَ هُوَ الْعِبَادَةُ ‏"‏ ‏.‏ ثُمَّ قَرَأَ ‏{وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}‏

ዱዓእ አምልኮ ከሆነ አምልኮ የአላህ ብቻ ሐቅ እና የባሕርይው ገንዘቡ ነው፥ አላህ ወደ እርሱ ዱዓእ ለሚያደርጉት ቅርብ ነው፥ አላህ መለኮት ነው። መለኮት በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፣ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፣ ሁሉን ሰሚ ነው፣ ሁሉን ተመልካች ነው፣ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነው፦
29፥20 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው”*። إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
65፥11 *”አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው”*፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
58፥1 *”አላህ ሰሚ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِير
2፥110 *”አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
4፥86 *አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَسِيبًا

ነገር ግን ሰዎች ከዚህ በተቃራኒው ወደ ፍጡራን ዱዓእ ያረጋሉ። ፍጡራን ሁሉን የማወቅ፣ የመስማት፣ የማየት፣ የመቆጣር ችሎታ ውስንነት አለባቸው፥ ስለዚህ ወደ እነርሱ የሚደረግ ዱዓእ አይመልሱም፦
7፥194 *"እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው እና ለእናንተ ይመልሱላችሁ አይችሉም"*። إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ ።

እነርሱ እንደ ማንኛውም ፈጣሪን አምላኪ አምላኪዎች ናቸው እንጂ ተመላኪዎች አይደሉም። በክርስትና ዱዓእ ከሚደረግላቸው ፍጡራን መካከል መላእክት ናቸው፥ አላህ የትንሳኤ ቀን መላእክትን፦ "እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፤ እነርሱም በፍጹም፦ "ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ" ብለው ይመልሳሉ፦
34፥40 *"ሁሉንም በሚሰበስባቸው እና ከዚያም ለመላእክቶቹ፦ «እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚኾነውን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ أَهَـٰؤُلَاءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا يَعْبُدُونَ
34፥41 *መላእክቶቹም፦ «ጥራት ይገባህ "ከእነርሱ ይልቅ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፥ እንደሚሉት አይደለም፥ ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ*፡፡ قَالُوا سُبْحَانَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم ۖ بَلْ كَانُوا يَعْبُدُونَ الْجِنَّ ۖ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ

ልብ አድርግ አድርግ ሰዎች ወደ መላእክት በዱዓእ ዒባዳህ ቢጠቀሙም ግን ያንን ዒባዳህ የሚቀበሉት ጂኒዎች ናቸው። እዚህ ዐውድ ላይ ጂን የተባሉት ሸያጢን ናቸው፥ አንድ ሰው ጣዖት ሲያመልክ ከጣዖቱ በስተኃላ አምልኮ የሚቀበለው ሸይጧን ነው፦
19፥42 *"ለአባቱ «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን ጣዖት ለምን ታመልካለህን? ባለ ጊዜ አስታውስ"*። إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنكَ شَيْئًا
19፥44 *«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አታምልክ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና"*፡፡ يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَـٰنِ عَصِيًّا
የኢብራሂም አባት የማይሰማና የማያይ ጣዖት ሲለማመን ከዚያ በስተኃላ የሚመለከው ሸይጧን ስለነበር፦ "አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አታምልክ" አለው። እንግዲህ አንድ ሰው ፍጡራንን ሲጠራ ከአላህ ሌላ እረዳት አድርጎ በአላህ ላይ የሚያሻርከው ኩፋሩል ጂን የሆኑትን ሸያጢንን ነው፦
6፥100 *"ለአላህም ተጋሪዎች የፈጠራቸውን ጂንዎችን አደረጉ"*፡፡ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችንም ያለ ዕውቀት ለእርሱ ቀጠፉ፡፡ አላህ ጥራት የተገባው ከሚሉት ነገር የላቀ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ الْجِنَّ وَخَلَقَهُمْ ۖ وَخَرَقُوا لَهُ بَنِينَ وَبَنَاتٍ بِغَيْرِ عِلْمٍ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يَصِفُونَ
7፥30 ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ፡፡ ከፊሎቹም በእነሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል፡፡ *እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና"*፡፡ እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡ فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيْهِمُ الضَّلَالَةُ ۗ إِنَّهُمُ اتَّخَذُوا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ اللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ

አላህ ሰዎችን በቀጥተኛው መንገድ በኢሥላም ላይ ፈጥሮ ሳለ ሸያጢን ግን ከዚህ ዲን በሺርክ ምክንያት ሰዎችን ያርቃሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐግ 53, ሐዲስ 76
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ኹጥባህ በሚደረግበት ቀን እንዲህ አሉ፦ *"ለእናንተ ያስተማርኩት ጌታዬ ያዘዘኝ፥ እናንተ የማታውቁትን እርሱ ዛሬ ያሳወቀኝን። አላህም አለ፦ "እኔ የሰጠኃቸውንና ሕጋዊ የሆነላቸው ያ ሁሉ ንብረት ነው። እኔ ሁሉንም ባሮቼን በቀጥተኛው መንገድ ላይ ፈጠርኳቸው፥ ሸያጢን መጥተው ከዲናቸው አራቋቸው"*። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ الْمُجَاشِعِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ذَاتَ يَوْمٍ فِي خُطْبَتِهِ ‏"‏ أَلاَ إِنَّ رَبِّي أَمَرَنِي أَنْ أُعَلِّمَكُمْ مَا جَهِلْتُمْ مِمَّا عَلَّمَنِي يَوْمِي هَذَا كُلُّ مَالٍ نَحَلْتُهُ عَبْدًا حَلاَلٌ وَإِنِّي خَلَقْتُ عِبَادِي حُنَفَاءَ كُلَّهُمْ وَإِنَّهُمْ أَتَتْهُمُ الشَّيَاطِينُ فَاجْتَالَتْهُمْ عَنْ دِينِهِم

እዚህ ሐዲስ ላይ "ሁነፋእ" حُنَفَاءَ የሚለው ቃል "ሐኒፍ" حَنِيف ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት “ሐኒፋ” حَنِيفًا ናት፦
30፥30 *”ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው”*፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀጥተኛ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐኒፋ” حَنِيفًا ሲሆን አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም “ሐኒፋ” መሆኑን ያሳያል። አንድ ሰው ፍጡርን በዱዓእ ከጠራ ከዱዓእ በስተኃላ ሸይጧን አምልኮ ስለሚቀበል አምላካችን አላህ በትንሳኤ ቀን፦ "ሸይጧንን አታምልኩ" "አምልኩኝ" ብሎ አዞ እንደነበር ይናገራል፦
36፥60 *የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አታምልኩ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?* أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
36፥61 *"አምልኩኝ! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፤ በማለትም አላዘዝኩምን?"*፡፡ وَأَنِ اعْبُدُونِي ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ሺርክ በአላህ ላይ ሌሎች ማንነትንና ምንነትን በአምልኮ ማሻረክ ነው፥ ከሺርክ በስተጀርባ ይህንን አምልኮ የሚቀበሉት ሸያጢን ናቸው። ክርስቲያኖች ሆይ! ሳታውቁ የመስማት፣ የማየት፣ የማወቅ፣ የመቆጣጠር ውስንነት ባሕርይ ያለባቸውን ፍጡራንን ስትለማመኑ፣ ስትማጸኑ፣ ስትጠሩ ከነበረ እንግዲያውስ ባለማወቅ ነውና የተውበት በር ሳይዘጋ ወደ ዲኑል ኢሥላም ኑ እና የመስማት፣ የማየት፣ የማወቅ፣ የመቆጣጠር ውስንነት ባሕርይ የሌለበትን ፈጣሪን አላህን በብቸኝነት አብረን እናምልክ። ወደ ፍጡራን ዱዓእ በማድረግ በአላህ ላይ በማሻረክ ለሸያጢን አምልኮ ከመስጠት አላህ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የፀሐይ መጥለቂያ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥86 *"ወደ ፀሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት"*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغَ مَغْرِبَ الشَّمْسِ وَجَدَهَا تَغْرُبُ فِي عَيْنٍ حَمِئَةٍ

ቀኝና ግራ፣ ታችና ላይ፣ ፊትና ኃላ፣ ውስጥና ውጪ፣ እዚህና እዚያ አንጻራዊ እውነት እንጂ ፍጹማዊ እውነት አይደም፥ እነዚህን ስምንቱን አመላካች አንጻራዊ ነጥብ ይወስነዋል። እንዲሁ ምስራቅና ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ አንጻዊ እውነታ ናቸው፦
18፥86 *"ወደ ፀሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት"*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغَ مَغْرِبَ الشَّمْسِ وَجَدَهَا تَغْرُبُ فِي عَيْنٍ حَمِئَةٍ

"መግሪብ" مَغْرِب የሚለው ቃል "ገረበ" غَرَبَ ማለትም "ገባ" "ጠለቀ" "ተሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መግቢያ" "መጥለቂያ" "መሰወሪያ" ማለት ነው። ከመነሻው ፀሐይ በፍጹማዊ እውነታ መግቢያና መውጫ የላትም፥ ከእኛ እይታ አንጻር የምትገባ እና የምትወጣ ስለሚመስለን ነው። ይህንን ከተረዳን እዚህ አንቀጽ ላይ "ስትጠልቅ" ለሚለው ቃል የገባው "ተግሩቡ" تَغْرُبُ ሲሆን “አል-ሙዷሪዕ” ٱلْمُضَارِع ነው። ስለዚህ ፀሐይ የጠለቀችው ለዙል-ቀርነይን ሲያያት እንጂ ቃል በቃል ፀሐይ አትጠቅም፤ አትወጣም። "ሐሚአህ" حَمِئَة ማለት "ጥቁር ጭቃ" ማለት ሲሆን ዙል-ቀርነይን ባደረገው ጉዞ ሜድትራትንያን ባሕር ውስጥ ስትገባ ታየችው፥ "ወጀደ" وَجَدَ ማለት "አገኘ" ማለት ሲሆን ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ እንዳያት ሁሉ ሕዝቦች ላይ ስትወጣ አገኛት፦
18፥90 *"ወደ ፀሐይ መውጫ በደረሰም ጊዜ ለእነርሱ ከበታችዋ መከለያን ባላደረግንላቸው ሕዝቦች ላይ ስትወጣ አገኛት"*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغَ مَطْلِعَ الشَّمْسِ وَجَدَهَا تَطْلُعُ عَلَىٰ قَوْمٍ لَّمْ نَجْعَل لَّهُم مِّن دُونِهَا سِتْرًا

"መጥሊዕ" مَطْلِع የሚለው ቃል "ጠለዐ" طَلَعَ ማለትም "ወጣ" "ተገለጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መውጫ" "መገለጫ" ማለት ነው። አሁንም "አገኘ" ለሚለው የተጠቀመበት ቃል "ወጀደ" وَجَدَ እንደሆነ አስተውል። ስትወጣ ለእነርሱ ከበታችዋ መከለያን በተደረገላቸው ሕዝቦች ላይ አንጻራዊ ከሆነ እንግዲያውስ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ ማየቱ አንጻራዊ ነው። መውጣቷ ላይ "ዐላ" عَلَىٰ የሚለው መስተዋድድ አንጻራዊነትን እንደሚሳይ ሁሉ መግባቷ ላይም "ፊ" فِي የሚለው መስተዋድድ አንጻራዊነትን ያሳያል። እዚህ አንቀጽ ላይ "ስትወጣ" ለሚለው ቃል የገባው "ተጥሉዑ" تَطْلُعُ ሲሆን “አል-ሙዷሪዕ” ٱلْمُضَارِع ነው። ስለዚህ ፀሐይ የወጣችው ለዙል-ቀርነይን ሲያያት እንጂ ቃል በቃል ፀሐይ እንደማትወጣ ሁሉ ቃል በቃልም አትገባም።
እዚህ ድረስ ከተግባባን ሁለት ናሙና ከባይብል እንይ፦
ኢያሱ 1፥1 እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ *እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው*፦
ኢያሱ 1፥4 ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ *"እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ"* ዳርቻችሁ ይሆናል።

እዚህ አንቀጽ ላይ ታላቁ ባሕር የፀሐይ መግቢያ እንደሆነ ይናገራል። ታዲያ የፀሐይ መግቢያ ታላቁ ባሕር ነውን? አይ "ይህ የተናገረው ኢያሱ ነው" እንዳትሉ "እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው" በማለት ይህንን የሚናገረው እግዚአብሔር መሆኑን ዐውዱ አስረግጦና ረግጦ ያስረዳል። ይህ ታላቁ ባሕር የሜዲትራኒያን ባሕር ነው፥ ኢያሱ ከነበረበት ከምድረ በዳው ከሊባኖስ አንጻር የተነገረ እንጂ ቃል በቃል ፀሐይ ታላቁ ባሕር ውስጥ በፍጹም አትገባም" ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን የቁርኣን አንቀጽ በዚህ ልክና መልክ ተረዱት፦
1 ነገሥት 22፥36 *"በሠራዊቱም መካከል ፀሐይ ስትገባ"*፦ ንጉሡ ሞቶአልና እያንዳንዱ ወደ ከተማው፥ እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሂድ፡ የሚል ጩኸት ሆነ።

"በሠራዊቱም መካከል ፀሐይ ስትገባ" የሚለው ይሰመርበት። በሠራዊት መካከል ፀሐይ ቃል በቃል ትገባለችን? እረ ይህ የሰው እይታ እንጂ ነባራዊ እውነታ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን የቁርኣን አንቀጽ በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። ኢንሻአላህ ይቀጥላል....

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም