ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.4K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ለምሳሌ ፈጣሪ አዳም፦ "ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ" ብሎ በማዘዝ፥ በተቃራኒው "መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ" ብሎ በመከልከል ፈትኖታል፦
ዘፍጥረት 2፥16-17 *"እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ"* ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።

ብላ ብሎ ማዘዙና አትብላ ብሎ መከልከሉ ፈተና ነው። ፈጣሪ እያወቀ በምርጫችን ለእኛ እንድንመርጥ ነጻ ፈቃድን ፈተና አርጎ ሰቶናል። ነገር ግን በባይብሉ እግዚአብሔር አብርሃምን ልጅህን ሰዋልኝ ብሎ የፈተነው እርሱን ይፈራው ወይም አይፈራው እንደሆነ ለማወቅ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ *"እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው"*።
ዘፍጥረት 22፥12 *"አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ"* አለ።

"እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ" የሚለው ይሰመርበት፥ "አሁን" አውቄአለሁ ማለት በፊትስ አያውቅም ነበር? እንደ ባይብሉ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ ትእዛዙን ይጠብቅ ወይም አይጠብቅ እንደሆነ ያውቅ ዘንድ ፈትኖታል፦
ዘዳግም8፥2 አምላክህ *"እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ ያውቅ ዘንድ"*፥ ሊያስጨንቅህ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ።

ፈጣሪ በሰው ልብህም ያለውን ትእዛዙን ይጠብቅ ወይም አይጠብቅ እንደሆነ አያውቅምን? ይህ ወፍራም ጥያቄ ባይብል ላይ እያለ "አላህ ለምን ይፈትናል? ብሎ ቁርኣን ላይ መጠየቅ የተቆላበት እያለ የተጋፈበት መፈለግ፥ ወይም የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ፥ አሊያም ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀቃይዋን ምች መታት እንደ ማለት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሐላ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

21፥23 *ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ፍጥረቶቹ ግን ይጠየቃሉ*፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ

"ቀሠም" قَسَم የሚለው ቃል "ቃሠመ" قَاسَمَ ማለትም "ማለ" "አጸና" "አሳመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መሐላ" "አጽንዖት" "መተማመኛ" ማለት ነው። አማንያን አንድን ነገር አጽንዖትና አንክሮት ለመስጠት አስፈላጊ ከሆነ በአሏህ ስም "ወሏሂ" وَٱللّٰه "ቢሏሂ" بِاللَّهِ በማለት ይምላሉ። ከአላህ ውጪ በሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መማል ግን አይቻልም፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 20, ሐዲስ 13
ሠዕድ ኢብኑ ዑበይዳህ እንደተረከው፦
*"አንድ ሰው፦ "በከዕባህ እምላለው" ብሎ ሲናገር ኢብኑ ዑመር ሰምቶ እንዲህ አለ፦ "ከአላህ ውጪ በሌላ መማል ከንቱነት ነው፥ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ "ማንም ይሁን ከአላህ ውጪ በሌላ የማለ ከፍሯል ወይም አሻርኳል"*። عَنْ سَعْدِ بْنِ عُبَيْدَةَ، أَنَّ ابْنَ عُمَرَ، سَمِعَ رَجُلاً، يَقُولُ لاَ وَالْكَعْبَةِ ‏.‏ فَقَالَ ابْنُ عُمَرَ لاَ يُحْلَفُ بِغَيْرِ اللَّهِ فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ مَنْ حَلَفَ بِغَيْرِ اللَّهِ فَقَدْ كَفَرَ أَوْ أَشْرَكَ

እዚህ ሐዲስ ላይ "መን" مَنْ የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም የሚያመለክተው ከአላህ ውጪ የሆነን ምንነት ነው፥ ይህ ከአላህ ውጪ የሆነ ማንም ፍጡር በአላህ ስም ብቻ እንጂ በፍጡራን መማሉ ኩፍርና ሺርክ ነው። ነገር ግን ምን አይነት ኩፍርና ሺርክ? ይህንን ለመረዳት ስለ ኩፍርና ሺርክ በግርድፉና በሌጣው እንይ፦
“ኩፍር”
“ኩፍር” كُفْر የሚለው ቃል “ከፈረ” كَفَرَ ማለትም “ካደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክህደት” ማለት ነው፥ በኩፍር ድርጊት ያለ ሰው “ካፊር” كَافِر ይባላል። ኩፍር በሁለት ይከፈላል። አንደኛው "ኩፍሩል አክበር" ሲሆን ሁለተኛው "ኩፍሩል አስገር" ነው።

"ኩፍሩል አክበር" كُفْر الأَكْبَرْ ማለት "ትልቁ ክህደት" ማለት ነው፥ ይህም ሺርክ በአላህ ጌትነት፣ አምላክነት እና ስሞች ላይ መካድ ነው። ትልቁ ክህደት ከኢሥላም ሙሉ ለሙሉ የሚያስወጣ ሲሆን ሰውዬውም ሙዕሚን ሳይሆን ካፊር ሊባል ይችላል፡፡ ይህ ትልቁ ኩፍር አላህ እና መልእክተኛውንማስተባበል፣ በእንቢተኝነትና በኩራት ቁርአንና ሐዲስን አለመቀበል፣ ከቁርኣንና ከሐዲስ ማፈግፈል እና በመናፍቅነት መሠማራት ነው።

“ኩፍሩል አስገር” كُفْر الأَصْغَر ማለት ደግሞ "ትንሹ ክህደት" ማለት ነው። ትንሹ ክህደት ከኢሥላም የማያስወጣ ሲሆን ይህም በተግባር የሚገለፅ ኩፍር ነው፥ በቁርኣንና በሐዲስም ኩፍር ተብለው የተገለፁ ወንጀሎች ነገር ግን ትልቁ ኩፍር ደረጃ የማይደርሱ ወንጀሎች ከትንሹ ኩፍር ይመደባሉ፡፡ ለምሳሌ ሙሥሊም ሆኖ ሙሥሊምን መውጋት፣ ሴት ልጅ በመቀመጫዋ መገናኘት፣ በወረ አበባ ጊዜ ተራክቦ ማድረግ እና እንዲሁ ከአላህ ውጪ በሆነ ማንነትና ምንነት መማል ነው።

“ሺርክ”
“ሺርክ” شِرْك የሚለው ቃል “አሽረከ” أَشْرَكَ ማለትም “አጋራ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በአላህ ላይ “ማጋራት” ማለት ነው። ሺርክ ሁለት ነገርን ያቅፋል፥ አንደኛ “ሙሽሪክ” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “ሸሪክ” ነው። በአላህ ላይ የሚጋራው ማንነት “ሙሽሪክ” مُشْرِك ማለትም “አጋሪ” ሲባል በአላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት ደግሞ “ሸሪክ” شَرِيك ማለትም “ተጋሪ” ይባላሉ። ሺርክ ደግሞ በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም፦ ሺርኩል አክበር እና ሺርኩል አስገር ናቸው።

"ሺርኩል አክበር" شِرْك الأَكْبَرْ ማለት "ትልቁ ሺርክ" ማለት ነው፥ ይህም ሺርክ በአላህ ጌትነት፣ አምላክነት እና ስሞች ላይ ማጋራት ነው። ከአላህ ሌላ ማንነትና ምንነትን በዱዓ መቀላወጥ፣ ማሸርገድ፣ ማጎብደድ፣ መተናነስ ነው። ጥንቆላ፣ መተት፣ ድግምት፣ የሞተ ሰው መሳብ የመሳሰሉት ነው። ሺርኩል አክበር ከኢሥላም ያስወጣል፥ እንዲህ የሚያደርግ ሰው ሙሥሊም ሳይሆን ሙሽሪክ ይባላል።

“ሺርኩል አስገር” شِّرْكُ الأَصْغَر ማለት ደግሞ "ትንሹ ሺርክ" ማለት ነው። ለምሳሌ አር-ሪያዕ ትንሹ ሺርክ ነው፥ የኢኽላስ ተቃራኒ የሆነው “አር-ሪያዕ” الرياء ማለት “እዩልኝ ስሙልኝ” ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከአላህ ውጪ በሆነ ማንነትና ምንነት መማል ነው፥ ለምሳሌ እናቴ ትሙት፣ አባቴ ይሙት፣ ሚካኤልን፣ ገብርኤልን ወዘተ ብሎ መማል። እንዲሁ በእናትህ፣ በአባትህ፣ በሚካኤል፣ በገብርኤል ወዘተ መለመን ነው። ልመና "በአላህ" ብለን ብቻ ነው።
ይህንን ከተረዳን ከአላህ ሌላ በሆነ ማንነትና ምንነት የማለ ትንሹ ኩፍርና ሺርክ ውስጥ ተዘፍቋልና ተውበት ይወጅብበታል። ይህ እንዲህ በእንዲህ እንዳለ ሚሽነሪዎች ለምን አላህ ታዲያ በፍጡራን ይምላል? የሚል ጥያቄ ይጠይቃሉ፥ ሲጀመር አላህ ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፦
21፥23 *ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ፍጥረቶቹ ግን ይጠየቃሉ*፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ

ሲቀጥል አላህ መማሉ ጉዳዩን አጽንዖት መስጠቱን ያመለክታል። አላህ በራሱ ይምላል፦
70፥40 *"በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን"*፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ
92፥3 *"ወንድንና ሴትን በፈጠረውም እምላለሁ"*፡፡ وَمَا خَلَقَ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ

አምላካችን አላህ በምናየው ነገር ይምላል፦
69፥38 *"በምታዩትም ነገር እምላለሁ"*፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِمَا تُبْصِرُونَ

ከሚታዩ ነገሮች ውስጥ በጸሐይ፣ በጨረቃ፣ በኮከብ፣ በተራራ ወዘተ ምሏል፦
81፥ 1 *"በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ"*፡፡ وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا
74፥32 *"ከክህደት ይከልከሉ፡፡ በጨረቃ እምላለሁ"*፡፡ كَلَّا وَالْقَمَرِ
53፥1 *"በኮከብ እምላለሁ በወደቀ በገባ ጊዜ"*፡፡ وَالنَّجْمِ إِذَا هَوَىٰ
52፥1 *"በጡር ጋራ እምላለሁ"*፡፡ وَالطُّور

አምላካችን አላህ በማናየው ነገር ይምላል፦
69፥39 *"በማታዩትም ነገር እምላለሁ"*፡፡ وَمَا لَا تُبْصِرُونَ

ከማይታዩ ነገሮች ውስጥ በመላእክት፣ በጊዜ፣ በትንሳኤ ቀን፣ በነፍስ ወዘተ ምሏል፦
51፥4 *"ነገርን ሁሉ አከፋፋዮች በኾኑትም መላእክት እምላለሁ"*፡፡ فَالْمُقَسِّمَاتِ أَمْرًا
103፥1 *"በጊዜያቱ እምላለሁ"*፡፡ وَالْعَصْرِ
75፥1 *"ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ"*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِيَوْمِ الْقِيَامَةِ
75፥2 *"ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ"*፡፡ وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ

ሢሰልስ አላህ የከለከው ግን እራሱ የሚያደርገው ነገር አለ፥ ለምሳሌ ከእርሱ ውጪ ማንም እንዲመለክና "አምልኩኝ" እንዲሉ አይፈልግም፥ ግን እርሱ እንዲመለክ ይፈልጋል፤ "አምልኩኝም" ይላል።
ሲያረብብ ይህንን የሚጠይቁት ሚሽነሪዎች የራሳቸውን መጽሐፍ ጠንቅቀው ስለማያነቡ እንጂ እግዚአብሔር በፍጡር ምሏል፦
አሞጽ 8፥7 *"ያህዌህ “በያዕቆብ ትዕቢት” እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ ሥራቸውን ሁሉ ለዘላለም ምንም አልረሳም"*። נִשְׁבַּע יְהוָה, בִּגְאוֹן יַעֲקֹב; אִם-אֶשְׁכַּח לָנֶצַח, כָּל-מַעֲשֵׂיהֶם.

"ቢ" בִּ ማለት "በ" ማለት ሲሆን "የያዕቆብ ትዕቢት” መነሻ ቅጥያ ላይ የገባ መስተዋድድ ነው። እግዚአብሔር የማለው በያዕቆብ ትዕቢት ነው። "ጎውን" גְא֣וֹן ማለት "ትዕቢት" "ኩራት" ማለት ነው፥ ይህ ቃል እዚሁ መጽሐፍ ላይ የያዕቆብን ትዕቢት ተብሎ ተቀምጧል፦
አሞጽ 6፥8 አዶናይ ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ *"የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ አዳራሾቹንም ጠልቻለሁ፤ ስለዚህ ከተማይቱንና የሚኖሩባትን ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ"*። נִשְׁבַּע אֲדֹנָי יְהוִה בְּנַפְשׁוֹ, נְאֻם-יְהוָה אֱלֹהֵי צְבָאוֹת, מְתָאֵב אָנֹכִי אֶת-גְּאוֹן יַעֲקֹב, וְאַרְמְנֹתָיו שָׂנֵאתִי; וְהִסְגַּרְתִּי, עִיר וּמְלֹאָהּ.

እግዚአብሔር በተጸየፈበት በያዕቆብ ትዕቢት መማሉ ምን ይሆን? "ጉዳዩን አጽንዖት ለመስጠት ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ አላህ በተለያየ ነገር መማሉ ስለዚያ ነገር አጽንዖት ለመስጠት ነው። ሚሽነሪዎች የዕብራውያ ደብዳቤ መስፈት አርገው ነበር የአላህን መማል ለመኃየስ የበቁት፦
ዕብራውያን 6፥13-14 እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ፥ በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ፥ *"ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ፥ በራሱ ማለ"*።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ከእርሱ በሚያንስ በማንም ሊምል ስላልቻለ" የሚል ኃይለ-ቃል የለም። ባይሆን "ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ" የሚል ቃል አለ። ያ ማለት ከራሱ በላይ ማንም ስሌለ እንደ ፍጡራን በበላዩ ማንነት አይምልም ማለት እንጂ ከእርሱ በታች በሆነ ነገር አይምልም የሚለውን አያሲዝም። ሲቀጥል የዕብራውያን ደብዳቤ ተናጋሪ ማን እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። ምክንያቱም የካርቴጅ ጉባኤ በ 397 ድህረ-ልደት ማርኮናይት ከሚባሉ መናፍቃን የሰበሰበችው ደብዳቤ ነው፥ የፈጣሪ ወይም የነቢይ ንግግር ሳይሆን ማንነቱ የማይታወቅ ሰው የጻፈው ደብዳቤ ነው። በዚህ ደብዳቤ የፈጣሪ የአላህ ንግግር አይመዘንም።
ይህንን ደብዳቤ ጳውሎስ ነው የተናገረው ካላችሁ ጳውሎስ የሚምለው በራሱ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፥31 በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለኝ *“በእናንተ ትምክህት እየማልሁ”* ወንድሞች ሆይ፥ ዕለት ዕለት እሞታለሁ።
2ኛ ቆሮንቶስ 1፥3-14 እናንተ ደግሞ “ትምክህታችን እንደምትሆኑ” እንዲሁ *“ትምክህታችሁ እንድንሆን”*፥ በከፊል ስለ እኛ እንዳስተዋላችሁ ፈጽማችሁ ታስተውሉት ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ።

ጳውሎስ “ትምክህታችሁ እኛ ነን ብሎ ተመልሶ ራሱን ለማመልከት “በእናንተ ትምክህት እየማልሁ” ይላልን? ይህ ጥያቄአችን ተከድኖ ይብሰል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ለይለቱል ቀድር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

97፥1 *እኛ ቁርኣኑን በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ

የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው ረመዷን 9ኛው ወር ሲሆን ይህ ወር የሚጾምበት ምክንያት ቁርኣን ከጥብቁ ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የወረደበት ወር ስለሆነ ነው። ቁርኣን በዚህ ወር ውስጥ በአንድ በተባረከች ሌሊት በጠቅላላ አንድ ጊዜ ወርዷል፥ ይህም አወራረድ “ጁምለተን ዋሒዳህ” جُمْلَةً وَاحِدَةً ይባላል፦
፥185 *”እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ ያ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና እውነትን ከውሸት ከሚለዩም ገላጮች አንቀጾች ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው”*፡፡ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
44፥3 *እኛ ቁርኣኑን በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَة

“አወረድነው” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “አንዘልናሁ” أَنْزَلْنَاهُ ሲሆን “አንዘለ” أَنْزَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ቃል በቁርኣን ቋንቋ በአንድ ጊዜ መውረድን ያመለክታል። ይህቺ ሌሊት የተባረከች ስለሆነች “ለይለቱል ሙባረካህ” لَيْلَةٍ مُّبَارَكَة ተብላለች፥ በሌላ አንቀጽ ላይ ደግሞ “ለይለቱል ቀድር” لَيْلَةُ الْقَدْر ማለትም “የመወሰኛይቱ ሌሊት” ተብላለች፦
97፥1 *እኛ ቁርኣኑን በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ

ለይለቱል ቀድር በረመዷን መጨረሻ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ በጎደሎ ቁጥር”odd number” ማለትም በ 21ኛው፣ በ 23ኛው፣ በ 25ኛው፣ በ 27ኛው፣ ወይም በ 29ኛው ውስጥ ናት፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 32, ሐዲስ 4
ዓኢይሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ለይለቱል ቀድርን ከረመዷን መጨረሻ አስር ጎደሎ ሌሊቶች ውስጥ ፈልጓት”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ تَحَرَّوْا لَيْلَةَ الْقَدْرِ فِي الْوِتْرِ مِنَ الْعَشْرِ الأَوَاخِرِ مِنْ رَمَضَان

በረመዷን መጨረሻ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ በጎደሎ ቁጥር ውስጥ የምትገኘው ይህቺ ሌሊት ያላት የጊዜ ዋጋ ከሺሕ ወር በላጭ ናት፦
97፥2 *መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?* وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ
97፥3 *መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት*፡፡ لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ

ቁርኣን ላይ፦ “ወማ አድራ ከማ” وَمَا أَدْرَاكَ مَا ማለትም “ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?” የሚል መጠይቅ 13 ቦታ ሲኖር “ምን እንደ ኾነ ዕወቅ” የሚል ፈሊጣዊ አነጋገር”Idiomatic expression” ነው። ከሺሕ ወር በላጭ የሆነችውን ይህቺን ሌሊት ለማግኘት ሙሥሊሙ ኢዕቲካፍ ይገባል። “ኢዕቲካፍ” اعتكاف‌‎ ማለት “ማዘውተር” ማለት ሲሆን በስብስብ ሶላት ላይ በመስጂድ ውስጥ ለመዘውተር በመነየት የተወሰነ ጊዜ ቆይታ ማድረግ ነው። በተለይ የረመዷንን የመጨረሻዎቹን አሥርት ቀናት ላይ የሚደረግ ቆይታ ነው፦
2፥187 *”እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”*፡፡ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَٰجِد
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 2
የነቢዩ”ﷺ” ባልተቤት ዓኢይሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” እስኪሞቱ ድረስ ከረመዷን መጨረሻ አስር ቀናት ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከእርሳቸው በኃላ ባልተቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَعْتَكِفُ الْعَشْرَ الأَوَاخِرَ مِنْ رَمَضَانَ حَتَّى تَوَفَّاهُ اللَّهُ، ثُمَّ اعْتَكَفَ أَزْوَاجُهُ مِنْ بَعْدِهِ‏.‏

የሚያጅበው በዚህች ሌሊት መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፥ እስከ ፈጅር ሶላት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፦
97፥4 *”በእርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ*፡፡ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ
97፥5 *እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት*፡፡ سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ

ለይለቱል ቀድርን በኢማን እና በኢሕቲሣብ ያገኘ ሰው ከአላህ ዘንድ የሚኖረው ምንዳና ትሩፋት ያለፈው ኃጢአቶቹ ሁሉ ይቅር መባል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 28
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በለይለቱል ቀድር በኢማን እና ከአላህ አጅር አገኛለው ብሎ ሶላት የቆመ ያለፈው ኃጢአቶቹ ሁሉ ይቅር ይባልለታል”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ يَقُمْ لَيْلَةَ الْقَدْرِ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ

ምንኛ መታደል ነው? ኢሥላም ዐቂደቱል ረባኒያ ነው ስልን በዕውር ድንብር ጸለምተኛ ሙግት”Pessimistic approach” ሳይሆን በእማኝና በአስረጅ ሙግት”Optimistic approach” ነው። አላህ ለይለቱል ቀድርን በኢማን እና በኢሕቲሣብ ከሚያገኙት ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢዕቲካፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥187 *”እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”*፡፡ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَٰكِفُون فِى ٱلْمَسَٰجِد

“ኢዕቲካፍ” اعتكاف‌‎ ማለት “መቀመጥ” ማለት ሲሆን የረመዷንን የመጨረሻዎቹን አሥርት ቀናት ላይ በመስጂድ ውስጥ ለመዘውተር በመነየት የተወሰነ ጊዜ መጠነ-ሰፊና ዘርፈ-ብዙ ዒባዳህ በማድረግ መቀመጥ ነው፦
2፥187 *”እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”*፡፡ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَٰكِفُون فِى ٱلْمَسَٰجِد

በመሥጂድ ኢዕቲካፍ ለማድረግ የሚቀመጠው “ዓኪፍ” عَاكِف ሲባል፥ እነዚህ አንቀጽ ላይ “ተቀማጮች” ለሚለው ቃል የገባው የዓኪፍ ብዙ ቁጥር “ዓኪፉን” عَٰكِفُون መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ እሳቤ በሐዲስም ላይ ተቀምጧል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 2
የነቢዩ”ﷺ” ባልተቤት ዓኢይሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” እስኪሞቱ ድረስ ከረመዷን መጨረሻ አስር ቀናት ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከእርሳቸው በኃላ ባልተቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَعْتَكِفُ الْعَشْرَ الأَوَاخِرَ مِنْ رَمَضَانَ حَتَّى تَوَفَّاهُ اللَّهُ، ثُمَّ اعْتَكَفَ أَزْوَاجُهُ مِنْ بَعْدِهِ‏.‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዒባዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አምልኮ" ማለት ነው። ዒባዳህ ማለት በቀልብያ፣ በቀውልያ፣ በዐመልያ ለአንድ ምንነት እና ማንነት የሚደረግ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ፣ መተናነስ ነው። የመስኩ ልሂቃን፦ "አምልኮ" ማለት "ለአንድ ምንነትና ማንነት በፍጹም ሁለንተናዊነት ማለትም በኃልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር መገዛት ነው" ይላሉ።
ዒባዳህ በተመላኪ እና በአምላኪ መካከል ያለ መርሕ ነው፥ "መዕቡድ" مَعْبُد ማለት "ተመላኪ" ማንነት ማለት ሲሆን “ዐብድ” عَبْد ወይም “ዐቢድ” عَابِد ደግሞ "አምላኪ" ማንነት ነው። አምላካችን አላህ በመጀመሪያ መደብ ብዙ ቦታ "አምልኩኝ" እያለ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
20፥14 *እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ

ሰው የተፈጠረበት አላማ እና ኢላማ የፈጠረውን አላህን በብቸኝነት እንዲያመልክ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

አምላካችም አላህ ኑሕን፣ አዩብን፣ ዳውድን እና ነቢያችንን”ﷺ” ጨምሮ “ዐብደና” عَبْدَنَا ማለትም “ባሪያችን” በማለት አምልኮ የእርሱ ሃቅና ገንዘብ መሆኑን ይናገራል፦
54፥9 ከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፡፡ *ባሪያችንንም* ኑሕን አስተባበሉ፡፡ «ዕብድ ነውም» አሉ፡፡ ተገላመጠም፡፡ كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ فَكَذَّبُوا عَبْدَنَا وَقَالُوا مَجْنُونٌ وَازْدُجِرَ
38፥41 *ባሪያችንን* አዩብንም አውሳላቸው፡፡ «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ وَاذْكُرْ عَبْدَنَا أَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ مَسَّنِيَ الشَّيْطَانُ بِنُصْبٍ وَعَذَابٍ
38፥17 በሚሉት ነገር ላይ ታገስ፡፡ የኀይል ባለቤት የሆነውን *ባሪያችንንም* ዳውድን አውሳላቸው፡፡ እርሱ መላሳ ነውና፡፡ اصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَاذْكُرْ عَبْدَنَا دَاوُودَ ذَا الْأَيْدِ ۖ إِنَّهُ أَوَّابٌ
2፥23 *በባሪያችንም* ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ፡፡ وَإِن كُنتُمْ فِي رَيْبٍ مِّمَّا نَزَّلْنَا عَلَىٰ عَبْدِنَا فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِّن مِّثْلِهِ وَادْعُوا شُهَدَاءَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

ዒባዳህ በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦
1. ዒባደቱል ቀልቢያ"የልብ አምልኮ"
2. ዒባደቱል ቀውልያ"የንግግር አምልኮ"
3. ዒባደቱል ዐመልያ"የድርጊት አምልኮ" ነው።
1. ዒባደቱል ቀልቢያ የሚባሉት ዒልም፣ ኢማን፣ ኢኽላስ፣ ኢሕሣን፣ ተቀዋ፣ ተወኩል፣ ሰብር እና ሙአበቱላህ ናቸው።
2. ዒባደቱል ቀውልያ የሚባሉት ሸሃደተይን፣ ተውበት፣ ዱዓ፣ ዳዕዋህ፣ ዚክር እና ቂርኣት ናቸው።
3. ዒባደቱል ዐመልያ የሚባሉት ሶላት፤ ፆም፣ ዘካህ፣ ሃጅ እና ጅሃድ ናቸው።

አርካኑል ዒባዳህ ማለትም "የአምልኮ ማዕዘናት" በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦
1. ሙሃባህ"ፍቅር"፣
2. ተቅዋ"ፍራቻ" እና
3. ረጃእ"ተስፋ" ናቸው።
አላህን ስናመልክ አላህ አፍቅረነው፣ ፈርተነው እና ተስፋ አድርገነው ነው።
ዒባዳህ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉት፥ እነርሱም፦
1. ኢማን፣
2. ኢኽላስ እና
3. ኢቲባዕ ናቸው።
1. “ኢማን” إِيمَٰن ማለት “እምነት” ሲሆን ያለ ኢማን ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
2. “ኢኽላስ” إخلاص ማለት ደግሞ ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚነየት መተናነስ፣ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ እና ማጥራት ሲሆን ያለ ኢኽላስ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
3. ሦስተኛው “ኢቲባዕ” إتباع ነው፥ “ኢቲባዕ” የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢቲባዕ ቁርኣንና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን *ተከተሉ*፤ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
6:106 ከጌታህ ወደ አንተ *የተወረደውን ተከተል* ፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ
6፥50 ወደ እኔ *የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም*» በላቸው፡፡ قُل لَّا أَقُولُ لَكُمْ عِندِي خَزَائِنُ اللَّهِ وَلَا أَعْلَمُ الْغَيْبَ وَلَا أَقُولُ لَكُمْ إِنِّي مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰ إِلَيَّ ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الْأَعْمَىٰ وَالْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “አተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢቲባዕ” إتباع ማለት እንግዲህ ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ነው፤ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደው ደግሞ ቁርኣን እና ሰሒሕ ሐዲስ ነው፦
4፥113 አላህም በአንተ ላይ *መጽሐፍን እና ጥበብን አወረደ*፤ وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَة

“ኪታብ” كِتَٰب የተባለው ቁርኣን ሲሆን “ሒክማህ” حِكْمَة የተባለው ደግሞ ሰሒሕ ሐዲስ ነው፣ ኪታብ እና ሒክማህ በተባሉት ቃላት መካከል “ወ” وَ ማለትም ‘’እና‘’ የሚል መስተጻምር መኖሩ አንባቢ ልብ ይለዋል። በተጨማሪም “አንዘለ” أَنْزَلَ ማለትም “አወረደ” የሚል ቃላት መጠቀሙ ሁለቱም ተንዚል መሆናቸውን ያረጋግጥልናል። በቁርኣን ውስጥ አላህን በብቸኝነት ለሚያመልኩ አምላኪዎች በቂነት አለ፦
21፥106 *በዚህ ቁርኣን ውስጥ ለአምላኪዎች ሕዝቦች በቂነት አለ*፡፡ إِنَّ فِي هَـٰذَا لَبَلَاغًا لِّقَوْمٍ عَابِدِينَ
2፥138 የአላህን የተፈጥሮ መንክር ያዙ፡፡ በመንከርም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? ማንም የለም፤ *እኛም ለእርሱ ብቻ አምላኪዎች ነን* በሉ፡፡ صِبْغَةَ اللَّهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُونَ

አምላካችን አላህ ዓቢዱን ከሚላቸው ምዕመናን ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነጻ ፈቃድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

“ሻእ” شَآء ማለት “ፈቃድ” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ በፍጥረተ-ዓለማት ውስጥ የሚሻውን ይፈጥራል፦
24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير
86፥16 *የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው*፡፡ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ
5፥17 *የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
3፥47 *አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"የሚሻውን" ለሚለው ቃል የገባው "የሻኡ" يَشَاءُ ማለትም "የሚፈቅደውን" ነው። ማንኛውም ነገር ሲከሰት፣ ሲከናወንና ሲሆን አላህ ፈቅዶ ነው፥ ያለ አላህ ፈቃድ ምንም እኩይ ወይም ሰናይ ነገር አይከሰትም፤ አይከናወንም፣ አይሆንም። የአላህ ፈቃድ በሁለት መልክ ለፍጡራን ሆኗል፥ አንዱ ያለፈቃዳቸው ሲሆን ሁለተኛው በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ላይ ነው።
የመጀመሪያው ፍጥረት ሲፈጠር ያለፈቃዱ በአላህ ፈቃድ ብቻ የሚከናወነው "ተሐዚዝ" تحديد ማለት "የተቆረጠ"determination" ይባላል። ይህም ሰው በመወለድ፣ በሞት፣ በመተኛት፣ በማስነጠስ ምርጫ የለውም። ልጅ እንኳን ሲወልድ ወንድ ወይም ሴት እወልዳለው ብሎ ምርጫ የለውም፤ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ ለሚሻው ሰው ሴቶችን ይሰጣል፤ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል። ለሚሻው መንታ ያደርጋል፤ የሚሻውን መካን ያደርገዋል። ለፍጡራን ግን ይህንን ለማድረግ ምርጫ የላቸውም፦
42፥49 *የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል*፡፡ لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ
42፥50 *ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና*፡፡ أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا ۖ وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيمًا ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ
28፥68 *ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ለፍጡራን ምርጫ የላቸውም*፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَة

ሰው ወንድ ወይም ሴት ለመሆን ለመወለድ ለመሞት ምርጫ የለውም። አላህ የሚሻውን በምርጫው ይህንን ይፈጥራል። በዚህ ምርጫ በሌለው ነገር ሰው አይጠየቅበትም፤ አይቀጣበትም፣ አይሸለምበትም።
ሁለተኛው ፍጥረት በተሰጠው ነጻ ፈቃድና ምርጫ ይጠየቃል፦
21፥23 *ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ፍጥረቶቹ ግን ይጠየቃሉ*፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ
16፥93 *ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ*፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون

አላህ በሚሠራው ሥራ አይጠየቅም። እርሱ ፈጣሪ ስለሆነ ፍጡራን ግን በሚሠሩት ሥራ ይጠየቃሉ። አላህ ትዳርን ፈቅዶ ዝሙትን መከልከሉ፥ ንግድን ፈቅዶ አራጣን መከልከሉ፥ መጠጥን ፈቅዶ ኸምርን መከልከሉ፥ ምግብን ፈቅዶ እሪያን መከልከሉ፥ እርሱን እንድናመልክ ፈቅዶ ጣዖትን መከልከሉ ይህ ተጠያቂነትን ያሳያል። መስሚያ የሚሰማውን የመምረጥ ነፃነቱ፣ ማያም የሚያየውን የመምረጥ ነፃነቱ፣ ልብም የሚያስበውን የመምረጥ ነፃነቱ የተሰጠን ጸጋ ነው። የዚህ ጸጋ ባለቤት ሰው በተሰጠው ጸጋ ተጠያቂ ነው፦
23፥78 *እርሱም ያ መስሚያዎችን፣ ማያዎችን እና ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው*፤ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنشَأَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۚ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُون
17፥36 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፤ መስሚያ፣ ማያም እና ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና*። وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَاد3َ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا
102፥8 ከዚያም *ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ*። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ

“ነዒም” نَّعِيمِ ማለት “ጸጋ” ማለት ነው። ነጻ ፈቃድ አድርግ የተባለውን የመታዘዝዝና ያለመታዘዝ፥ አታድርግ የተባለውን የመከልከልና ያለመከልከል ነጻነት ነው። ይህ አላህ የፈቀደልን ነጻ ፈቃድ "ሚሣን" ميسان ማለትም "ነጻነት"Libration" ይባላል። ይህ ጸጋ ሁሉም ሰው ጋር በተፈጥሮ የተቸረ ጸጋ ነው። በተሰጠን ነጻ ፈቃድና ምርጫ የምንሰራው መልካም ሥራ ሆነ ክፉ ሥራ ያስጠይቀናል። የተሰጠን ጸጋ ነጻ ፈቃድ"free will" ይባላል። ሰው በነጻ ፈቃዱ መብቱና ነጻነቱን መጠቀም ይችላል፥ "መብት" ማለት ማድረግ አለማድረግ ተጠያቂነት የሌለው ነገር ሲሆን "ነጻነት" ግን ባለማድረግ እና በማድረግ ተጠያቂነት ያለው ነገር ነው።
ሰዎች የሚፈጽሙ እውነትና ውሸት፣ ትክክልና ስህተት፣ መልካሙና ክፉ አላህ ፈቅዶ ነው የሚከናወኑት። ያለ አላህ ፈቃድ ምንም የሚሆን ነገር የለም፣ አላህ ፈቀደ ማለት ግን ጉዳዩን ወዶታል አሊያም ተስማምቶበታል ማለት አይደለም፣ አላህ ስለፈቀደ ነው ሰው ነጻ ፈቃድ ያለው፣ አላህ ሳይፈቅድ ሰው ነጻ ፈቃድ አይኖረውም ነበር፦
81፥29 *የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም*፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
76፥30 *አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና*፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

"ማ የሻኡነ ኢላ አን የሻኣሏህ" وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّه ማለትም "አላህ ካልፈቀደ አትፈቅዱም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ሰው ይህ ነጻ ፈቃድ ስላለው በፈቃዱ ማመን ወይም መካድ ይችላል፦
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

"የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ" ዛቻ ነው። በኃላ ይጠየቃል፥ ትሩፋትና ቅጣት ይቀበላል። አምላካችን አላህ እርሱ የሚወደው እምነት እና የሚጠላው ክህደት ይህ ነው ብሎ ሁለቱንም የእምነት መንገድ እና የክህደት መንገድ በተከበረ ቃሉ ነግሮናል፦
39፥7 *ብትክዱ አላህ ከእናንተ የተብቃቃ ነው፡፡ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም፡፡ ብታመሰግኑም፤ እርሱን ይወድላችኋል*፡፡ إِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنكُمْ ۖ وَلَا يَرْضَىٰ لِعِبَادِهِ الْكُفْرَ ۖ وَإِن تَشْكُرُوا يَرْضَهُ لَكُمْ
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ *ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ
90፥10 *ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?* وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ
76፥3 *እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን ገለጽንለት*፡፡ إِنَّا هَدَيْنَاهُ السَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًا وَإِمَّا كَفُورًا

ቅኑ የእምነት መንገድ ከጠማማው የክህደት መንገድ ተገልጧል፥ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ የመሆን ያለመሆን ምርጫው ተገልጿል። ለዚያ ነው ዛሬ በዓለማችን ላይ ሁለት ተቃራኒ የሆኑ አማኝ እና ከሓዲ ያሉት፦
64፥2 እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፡፡ *ከእናንተም ከሓዲ አለ፡፡ ከእናንተም አማኝ አለ*፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ فَمِنكُمْ كَافِرٌ وَمِنكُم مُّؤْمِنٌ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
14፥7 ጌታችሁም *«ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም እቀጣችኋለሁ፤ ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ አስታውሱ*፡፡ وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٌ

"ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ" ማለት ለአማንያን የተዘጋጀ ትሩፋት ጀነት እንዳለ የሚጠቁም ነው፥ "ብትክዱም እቀጣችኋለሁ" ማለት ለከሓድያን የተዘጋጀ ቅጣት ጀሃነም እንዳለ የሚጠቁም ነው። ስለዚህ ቅጣትና ሽልማት፣ የተፈቀና የተከለለ ነገር መኖሩ፥ እኩይና ሰናይ ነገር መኖሩ በራሱ ሰው ነጻ ፈቃድ እንዳለው የሚያሳይ ማስረጃ ነው። አንድ ሰው ነጻ ፈቃድ የለኝም ብሎ ሰው ቢገድል፣ ቢሳደብ፣ ቢማታ ወዘተ አይደለም አላህ በአኺራ ሰዎች በዱንያህ ይጠይቁታል።
በኢሥላም ዐቂዳህ ውስጥ ሁለት ጠርዘኛ እሳቦት ነበሩ፥ አንደኛው እሳቤ "አል-ጀቢሪያህ" الجبرية ማለትም ሰው በአላህ ዕውቀትና ፈቃድ ብቻ የሚኖር ነጻ ፈቃድ የሌለው ፍጡር"Necessitarian" ነው የሚሉ እና ሁለተኛው እሳቤ "አል-ቀደሪያህ" القدريه‎ ማለትም ሰው ያለ አላህ ዕውቀትና ፈቃድ ብቻውን በራሱ ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር"Libriterian" ነው የሚል ነው። ሁለቱም ጽንፍ ያላቸው እሳቦት በኢሥላም ዐቂዳህ አንዳች ቦታ የላቸውም። ሰው በአላህ ዕውቀትና ፈቃድ ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር ነው።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዘካህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥277 እነዚያ ያመኑ፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ፣ ሶላትንም ያስተካከሉ፣ *"ዘካንም የሰጡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም"*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

“ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መታዘዝ” ማለት ነው። “አርካን” أَرْكان‎ ማለት “ምሰሶ” ማለት ነው፥ "አርካኑል ኢሥላም" أَرْكان‎ إِسْلَٰم ማለት "የኢሥላም ምሰሶ" ማለት ነው። የኢሥላም ምሰሶ ደግሞ አምስት ናቸው፥ እነርሱም፦ ሸሃደተይን፣ ሶላት፣ ዘካህ፣ ሰውም እና ሐጅ ናቸው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፤ እነርሱም፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው” በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ ቤት በመጎብኘት”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ

“ዘካህ” زَكَوٰة የሚለው ቃል "ዘካ" زَكَىٰ ማለትም "ጠራ" ከሚል የግስ መደብ የመጣ ሲሆን "መጥራራት" ማለት ነው፦
20፥76 ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ አሏቸው፡፡ *ይህም "የተጥራራ" ሰው ምንዳ ነው*፡፡ جَنَّاتُ عَدْنٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ وَذَٰلِكَ جَزَاءُ مَن تَزَكَّىٰ

"የተጥራራ" ለሚለው ግስ የገባው ቃል "ተዘካ" تَزَكَّىٰ ሲሆን የስም መደሙ "ዘካህ” زَكَوٰة ነው። ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ "ዘካህ" ማለት “የግዴታ ምጽዋት” ማለት ነው፥ አምላካችን አላህ ከሰጠን ሲሳይ ላይ የምንለግሰው ልግስና ዘካህ ይባላል፦
2፥277 እነዚያ ያመኑ፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ፣ ሶላትንም ያስተካከሉ፣ *"ዘካንም የሰጡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም"*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
8፥3 እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ *”ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው”*፡፡ الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُون

ዘካን የሚሰጡ አላህ ዘንድ ምንዳ አላቸው፥ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም። "ሪዝቅ" رِزْق ማለት "ሲሳይ" ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ደግሞ "አር-ረዛቅ" الرَّزَّاق ማለትም "ሲሳይን ሰጪ" ነው። “ኢንፋቅ” إِنفَاق ማለት “ልግስና” ማለት ሲሆን “ሙንፊቂን” مُنفِقِين ደግሞ “ለጋሾች” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ከሰጠን ሲሳይ የምለግሰው ልግስና የበረከት ምንጭና ለአላህ ውዴታ ያለን መገለጫ ነው። ዘካህ መስጠት በረከትን ያፋፋል፥ ነገር ግን መስጠት ያለብን የአላህን ውዴታ ለመሻት እንጂ ትርፍ ፈልገን መሆን የበትም፦
2፥276 *"አላህ አራጣን በረከቱን ያጠፋል፡፡ ምጽዋቶችንም ያፋፋል"*፡፡ አላህም ኃጠኢተኛ ከሓዲን ሁሉ አይወድም፡፡ يَمْحَقُ اللَّهُ الرِّبَا وَيُرْبِي الصَّدَقَاتِ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ كَفَّارٍ أَثِيمٍ
30፥39 *"ከሪባም በሰዎች ገንዘቦች ውስጥ ይጨመር ዘንድ የምትሰጡት አላህ ዘንድ አይጨምርም፡፡ ከምጽዋትም የአላህን ፊት የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት እነዚያ ሰጪዎች አበርካቾች እነርሱ ናቸው"*፡፡ وَمَا آتَيْتُم مِّن رِّبًا لِّيَرْبُوَ فِي أَمْوَالِ النَّاسِ فَلَا يَرْبُو عِندَ اللَّهِ ۖ وَمَا آتَيْتُم مِّن زَكَاةٍ تُرِيدُونَ وَجْهَ اللَّهِ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُضْعِفُونَ

ዘካህ ከጥንት ጀምሮ ነቢያት እስካሉ ድረስ የነበረ ከኢሥላም ምሰሶ አንዱ ነው፥ አላህ ዘካንም ስለ መስጠት ትእዛዝ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት ወደ ነበሩት ነቢያት አውርዷል፦
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ዘካህ ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው። ዘካህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት በነበሩት ነቢያት ጊዜ ከመቶ 2.5 % ላይሰጥ ይችል ይሆናል፥ ወይ ያንሳል አሊያም ይበዛ ይሆናል። ምናልባት ከመቶ 10 % አሥራት ሊሆን ይችል ይሆናል፥ ወሏሁ አዕለም።
በነቢያችን"ﷺ" ሸሪዓህ ግን ዘካህ ከካፒታል ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5% ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 5፥2=2.5 ይሆናል፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ"*። عَنْ عَلِيٍّ، - رضى الله عنه - عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏"‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ - يَعْنِي فِي الذَّهَبِ - حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا
በዚህ ሐዲስ መሠረት የአንድ ሰው ካፒታል 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ዘካህ ይወጅበታል፥ በሸሪዓህ የዘካህ አነስተኛ የክፍያ መጠን "ኒሷብ" نِصاب ይባላል፥ ይህም ኒሷብ የሚለካው 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ነው። “ዲናር”  دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ማለት ሲሆን “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ማለት ደግሞ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው። ይህ በጥንት "የኮሞዲቲ ገንዘብ"commodity money" ይባላል።
"ዲናር” እና “ዲርሀም” የሚለኩት በሚስቃል ነው፥ "ሚስቃል" مِثْقَال የሚለው ቃል "ሰቀለ" ثَقَلَ ማለትም "ከበደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ክብደት" ማለት ነው።
1 ሚስቃል ወርቅ 4.25 ግራም ነው፥ 20 ሚስቃል ወርቅ ደግሞ 4,25x 20 = 85 ግራም ወርቅ ይሆናል ማለት ነው።
1 ሚስቃል ብር 2.975 ግራም ነው፥ 200 ሚስቃል ብር ደግሞ 2.975x 200= 595 ግራም ብር ይሆናል ማለት ነው።

በዘካህ ላይ የሚወጅበው ኒሷብ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ነው።
አንድ ሙሥሊም ያለው ካፒታል በዓመት ውስጥ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ያክል ከሆነ ዘካህ ማውጣት ግዴታው ነው። ይህ ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ"Fiat money" ለመቀየር ወርቅን ዛሬ ባለው በ 24 ካራት የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል፦
1. በስውዲን አንድ ግራም ወርቅ 396 ክራውን ነው፥ 396×85= 33,660 ክራውን ይሆናል።
2. በኢትዮጵያ አንድ ግራም ወርቅ 1,181 ብር ነው፥ 1,181×85= 100,385 ብር ይሆናል።
3. በአሜሪካ አንድ ግራም ወርቅ 41.30 ዶላር ነው፥ 41.30×85= 3,510.30 ዶላር ይሆናል።

ስለዚህ አንድ ሙሥሊም ያለው ካፒታል በገንዘብ ሲተመን በስውዲን 33,660 ክራውን፣ በኢትዮጵያ 100,385 ብር፣ በአሜሪካ 3,510.30 ዶላር ወዘተ ከሆነ ከዚያ ወዲህ ዘካህ ማውጣቱ ፈርድ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው በኢትዮ 100,385 ሺ ብር ካለው ከ 100,385 ሺ ብር ላይ 2.5% ዘካ ያወጣል፥ ያ ማለት የዘካው ብር 100,385×2.5÷100= ውጤቱ 2,509 ብር ይሆናል ማለት ነው። ይህ በጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር የ 2019 ድኅረ-ልደት ግብይት ነው።
ዘካን የማይሰጥ በመጨረሻይቱ ዓለም ከአላህ ዘንድ መተሳሰብ የለም ብሎ የሚክድ ሰው ነው፦
41፥7 *"ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች ለኾኑት ወዮላቸው"*፡፡ الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ

አንድ ሙሥሊም ይህንን ዘካ ካላወጣ የትንሳኤ ቀን ገንዘቡ እንደ ሁለት አይኖቹ ላይ ጥቁር ነጥቦች የተጣሉበት ወንድ መላጣ እባብ ተመስሎ ይመጣና ማንገጭላውን አጥብቆ በመያዝ፦ "እኔ ገንዘብህ ነኝ፥ እኔ ድልብህ ነኝ" ይለዋል፦
3፥180 *"እነዚያም አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለእነርሱ ደግ አይምሰላቸው፡፡ ይልቁንም እርሱ ለእነርሱ መጥፎ ነው፡፡ ያንን በእርሱ የነፈጉበትን በትንሣኤ ቀን እባብ ኾኖ ይጠለቃሉ"*፡፡ የሰማያትና የምድርም ውርስ ለአላህ ብቻ ነው፡፡ አላህም በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ وَلَا يَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَبْخَلُونَ بِمَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ هُوَ خَيْرًا لَّهُم ۖ بَلْ هُوَ شَرٌّ لَّهُمْ ۖ سَيُطَوَّقُونَ مَا بَخِلُوا بِهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ وَلِلَّهِ مِيرَاثُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 90, ሐዲስ 5
አቢ ሁራይራ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"አላህ ገንዘብ ሰጥቶት የእሱን ዘካህ ያላወጣ የትንሳኤ ቀን ገንዘቡ እንደ ሁለት አይኖቹ ላይ ጥቁር ነጥቦች የተጣሉበት ወንድ መላጣ እባብ ተመስሎ ይመጣና ማንጋጭላውን አጥብቆ በመያዝ፦ "እኔ ገንዘብህ ነኝ፥ እኔ ድልብህ ነኝ ይለዋል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ يَكُونُ كَنْزُ أَحَدِكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ شُجَاعًا أَقْرَعَ، يَفِرُّ مِنْهُ صَاحِبُهُ فَيَطْلُبُهُ وَيَقُولُ أَنَا كَنْزُكَ‏.‏ قَالَ وَاللَّهِ لَنْ يَزَالَ يَطْلُبُهُ حَتَّى يَبْسُطَ يَدَهُ فَيُلْقِمَهَا فَاهُ

አላህ ከዚህ ቅጣት ይጠብቀን። የዘካህ ብር የሚውለው ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ ዘካን በማሰጠት ለሚያስተባብሩ፣ ልቦቻቸውም በኢሥላም ለሚለማመዱት፣ በባርነት ተገዢዎችን ነጻ ለማውጣት፣ ለባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም ለሚሠሩ፣ ለመንገደኛ ነው፦
9፥60 *ግዴታ ምጽዋቶች የሚከፈሉት ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም በኢሥላም ለሚለማመዱት፣ በባርነት ተገዢዎችን ነጻ በማውጣት፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት"*፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

አምላካችን አላህ ሙንፊቂን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዲርሃም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

12:20 *በርካሽ ዋጋም በሚቆጠሩ ዲርሃሞች ሸጡት*፤ በእርሱም ከቸልተኞቹ ነበሩ። وَشَرَوْهُ بِثَمَنٍ بَخْسٍ دَرَاهِمَ مَعْدُودَةٍ وَكَانُوا فِيهِ مِنَ الزَّاهِدِينَ

“ደራሂም” دَرَاهِم ብዜት ሲሆን በነጠላ ደግሞ “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ነው፥ ትርጉሙ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው፣ “ዲናር”  دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ነው። ነቢያችን”ﷺ” በመጡበት ዘመን አላህ ቁርአንን ሲያወርድ በዐረቢኛ ቋንቋ ስለሆነ በወቅቱ ዩሱፍን የሸጡትን በብር ሳንቲም ስለሆነ የብር ሳንቲም ደግሞ በዐረቢኛ “ዲርሃም” ይባላል፣ አምላካችን አላህ ይህ የዩሱፍን ታሪክ ከመጀመሩ፦ “ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርአን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው” በማለት ይናገራል፦
12:2 እኛ *”ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርአን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው”*። إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

በዐረቦች የብር ሳንቲም መጠቀም የተጀመረው ከዩሱፍ በኃላ ቢሆንም በዩሱፍ ዘመንና ቦታ ግን የብር ሳንቲም እንደነበረ ባይብሉ እራሱ ይናገራል፤ በዮሴፍ ዘመን ግብጻውያን የሚገበያዩበት ገንዘብ ምን እንደነበረ የሥነ-ቅርጽ ጥናት ባያረጋግጥም የዘፍጥረት ጸሐፊ ግን ከዮሴፍ 1200 አመት በኋላ የሥነ-ቅርጽ ጥናት በፋርሳውያን ዘመን 612-330 BC ኮይኑ እንደተጀመረ ያረጋገጠውን የመገበያያ ገንዘብ ይጠቀማል፦
ዘፍጥረት 37፥28 የምድያም ነጋዶችም አለፉ፤ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት፤ *ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ “ብር” כָּ֑סֶף ሸጡት*፤

ካሴፍ כָּ֑סֶף የብር ግብይት በፋርሳውያን ዘመን 612-330 BC ከተጀመረ በዮሴፍና በበፋርሳውያን መካከል የ 1200 አመት ልዩነት ካለ ታዲያ ለምንድን ነው የዘፍጥረት ጸሐፊ በዮሴፍ ዘመን መገበያያው ያልነበረውን ገንዘብ ካሴፍን የተጠቀመው? ብለን ጥያቄ ስናቀርብ አይ የዘፍጥረት ጸሐፊ በወቅቱ የነበረውን የመገበያያ ገንዘብ ሊገባው በሚችለው በወቅቱ የግብይት ስርዓት ተጠቅሞ ጽፏል ብለው ይመልሳሉ። ከላይ ያለውንም አንቀጽ በዚህ መልኩ መረዳት ይቻላል።
ሌላው በዳዊት ዘመን የነበሩ ሰዎች ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት አሥር ሺህ “ዳሪክ” እንደሰጡ የዜና መዋዕል ጸሐፊ ይነግረናል፦
1ዜና.29:7፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት *አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና አሥር ሺህ “ዳሪክ”፥ አሥር ሺህም መክሊት ብር፥ አሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ*።

ዳሪክ ደግሞ መገበያያነቱ የተጀመረው በ 521-486 BC በፐርሺያን ንጉስ በዳሪዮስ ዘመነ-መንግሥት ነው፣ ታዲያ በዳዊትና በዳሪዮስ መካከል የ 400 አመት ልዩነት ካለ ለምንድን ነው የዜና መዋዕል ጸሐፊ በዳዊት ዘመን መገበያያው ያልነበረውን ገንዘብ ዳሪክን የተጠቀመው? ብለን ጥያቄ ስናቀርብ አይ የዜና መዋዕል ጸሐፊ በወቅቱ የነበረውን የመገበያያ ገንዘብ ሊገባው በሚችለው በወቅቱ የግብይት ስርዓት ተጠቅሞ ጽፏል ብለው ይመልሳሉ። በተመሳሳይ መልኩም ታዲያ አላህ የወቅቱን ቋንቋ መሰረት አድርጎ ለነቢያች”ﷺ” ቢናገር ምን ይደንቃል? ምንስ ሚዛን ተይዞ ነው ሚሽነሪዎች የአላህ ንግግር የሚተቹት? ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነው ነገሩ፣ ጥያቄ ሲጠየቁ በመዋተት እና በመቃተት መቆዘም ልማዳቸው ነው፤ ሲጠይቁ ግን ለማንኳሰስና ለማሸማቀቅ አንደኛ ናቸው፤ ለማንኛውም ያልተጠረጠረ ተመነጠረ የተጠረጠረ አስመነጠረ ይሉሃል እንደዚህ ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣቸው ለእኛም ጽናቱን አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዒድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፤ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፤ ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ታዲያ በየዓመቱ የሚከበረው ሥስተኛው በዓል መውሊድ ምንድን ነው? አዎ ይህ ድብን ያለ ቢድዓ ነው፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።
ሲጀመር ነብያችን”ﷺ” የተወለዱበት ሳምንት እንጂ የተወለዱበት ቀን በሐዲስ አልሰፈረም።
ሲቀጥል አላህም እና መልእክተኛው መውሊድ አክብሩ አላሉም።
ሢሰልስ ነቢያችን”ﷺ” የተወለዱበትን ቀን ከቀደምት ሰለፎች ማለትም ሶሐባህ ወይም ታቢኢይ አሊያም አትባኡ ታቢኢይ ያከበረ የለም።
ስለዚህ መውሊድ በቁርኣንና በሐዲስ አሕካሙ ካልተቀመጠ እና አይ የፈለግነውን በዲኑ ላይ እንጨምራለን ከሆነ ቢድዓ ነው፤ ሑክም የአላህ እና የመልክተኛ ብቻና ብቻ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏

“ከትእዛዛችን” የሚለው ይሰመርበት። አንድ ነገር ፈርድ ነው፣ ሙስተሐብ ነው፣ ሙባሕ ነው፣ መክሩህ ነው፣ ሐራም ነው ማለት የሚቻለው ከአላህ እና ከመልእክተኛ ትእዛዝ ሲመጣ ብቻና ብቻ ነው፦
3፥32 *አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ*፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» በላቸው፡፡ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ
4፥80 *መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው አያሳስብህ*፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا
“ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም” የሚለው የነብያችን”ﷺ” ንግግር ይሰመርበት፤ ማንኛውም መመሪያ ቁርአን እና የነብያችን”ﷺ” ሐዲስ ላይ ይገኛል፤ አላህን የሚወድ መልእክተኛውን ይከተላል፤ አላህም፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ብሎናል፦
3፥31 *በላቸው፡- አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ “ተከተሉኝ*፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኀጢኣቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና፤ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው” قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ፡፡
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ ፡፡

ጥሩ ቢድዓ ካለ የሌሎችን ነብያት ልደት ለምን አይከበርም? ለምሳሌ “ገና” የዒሳ ልደት አይከበርም? ነብያችን”ﷺ” ወሕይ የመጣላቸው ቀን፣ ያረፉበት ቀን ወዘተ እየተባለ ልክ እንደ ኦርቶዶክስ ሰላሳውም ቀን ለምን አይከበርም? ይህ ደግሞ ዲኑን ያባሻል። አይ ዝንባሌአችን ደስ ያለውን መልካም ነገር በዒባዳህ ላይ እናካትት ማለት ዲኑ ሙሉ ነው የሚለንን አምላካችን አላህን እየተቃረንን ነው፦
5፥3 *ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ*፡፡ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا

“ነፍስያ” نفسيه ማለትም “የራስ ዝንባሌ” ጌታችን የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ነው፤ ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْ

سَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ቢድዓ፣ ኩርፍ፣ ሽርክ እና ኒፋቅ ምንጫቸው ዝንባሌ ነው፤ ብዙ ጊዜ ሰርጎ-ገብ የሆኑት ቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት መነሻቸው ዝንባሌ ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

አላህ ከነፍሲያ ከሚመጣ ዝንባሌ ጠብቆን፤ እርሱንና መልእክተኛው ባስቀመጡልን ሑክም የምንመራ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሸዋል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ሚሽነሪዎች የማያውቁትን ከመጠየቅ ይልቅ፦ "ዘካህ ከመቶ 2.5% ስጡ የሚል መረጃ የለም፣ ሪባህ ማለት አራጣ ማለት እንጂ ወለድ ማለት አይደለም፥ የቁርኣን አወራረድ ሁለት አይነት ነው የሚል መረጃ ከቁርኣንም ከሐዲስም መረጃ የለም" እያሉ ዲስኩራቸውን ሲደሶክሩ ነበር። ለእናንዳንዱ አርስት ከቁርኣና ከሐዲስ ከዚህ ቀደም ምላሽ ሰተናል። ዛሬ ደግሞ፦ "ሸዋልን ጹሙ! የሚል ቁርኣን ላይ የለም" እያሉ ይደሶክራሉ። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ጠይቁ መልስ ይሰጣችኃል። ከሆያሄዬ ወደ አንቺሆዬ ትንሽ እንኳን እደጉ።
የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ እነዚህም፦
1ኛ ወር ሙሐረም
2ኛ ወር ሰፈር
3ኛ ወር ረቢዑል-አወል
4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ
5ኛ ወር ጀማዱል-አወል
6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ
7ኛ ወር ረጀብ
8ኛ ወር ሻዕባን
9ኛ ወር ረመዷን
10ኛ ወር ሸዋል
11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ
12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦
9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ

ከእነዚህ አስራ ሁለት ወራት አንዱ 10ኛ ወር "ሸዋል" ነው፥ "ሸዋል" شَوَّال ማለት "ማንሳት" ወይም "መሸከም" ማለት ሲሆን የወር ስም ነው። ነቢያችን"ﷺ" እንድናደርገው ሙስተሐብ አድርገው ከሰጡት ሱና መካከል ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን መጾም ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78
አቢ አዩብ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው"*። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏

የረመዷን ሰላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን ጾም ጾመን ዓመት እንደጾምን የሚያስቆጥርበትን ስሌት ማወቅ ይቻላል። አምላካችን አላህ አንድ መልካም ሥራ ምንዳው አሥር እጥፍ እንደሆነ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦
6፥160 *"በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት"*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ስለዚህ አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው። 1×10=10 ወር ይሆናል። እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ ስድስት ቀናት በአሥር እጥፍ ስድሳ ቀን ነውና፥ 6×10=60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል። ሲጠቀለል የረመዷን የአሥር ወር ምንዳ እና የሸዋል ሁለት ወር ምንዳ 12 ወር ይሆናል፥ 10+2=12 ወር ይሆናል። አንድ ዓመት 12 ወር መሆኑ እሙን ነው። አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ፦ "መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት" ይለናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ስለዚህ ኢሥላም ሰው ሰራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱል ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሁትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ግብረ-ሰዶም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ

ሥነ-ጋብቻ ጥናት””matrimony” ስለ ጋብቻ ሲናገር በዋነኝነት ለሁለት ይከፍሉታል፦ አንደኛ “ተቃራኒ ጾታ ጋብቻ”Hetero-sexual” ሲሆን ሁለተኛው “ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ”homo-sexual” ” ነው።
ተቃራኒ ጾታ ጋብቻ በመለኮት መጽሐፍት ውስጥ የተቀመጠ ሲሆን ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ግን በመለኮት መጽሐፍት ውስጥ አንዳች ድጋፍ የሌለው ነው።
ግብረ-ሰዶም”homosexual” ማለት የሰዶማውያን ሥራ ማለት ነው፤ ግብረ-ሰዶም በራሱ ለሁለት ይከፈላል፤ እርሱም፦ በወንድ እና በወንድ መካከል ያለው የግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት”Gays” አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ በሴት እና በሴት መካከል ያለው የግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት”Lesbians” ነው። አምላካችን አላህ ነብዩ ሉጥን በዚህ ድርጊት በተሰማሩ ሕዝቦች መካከል ፍርድንና ዕውቀትን ሰጥቶ ላከው፤ ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ አንዱ ነው፦
37፥133 *ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው*። وَإِنَّ لُوطًا لَّمِنَ الْمُرْسَلِينَ
21፥74 *ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ ከዚያችም መጥፎ ሥራዎችን ትሠራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው፡፡ እነርሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና*፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا وَنَجَّيْنَاهُ مِنَ الْقَرْيَةِ الَّتِي كَانَت تَّعْمَلُ الْخَبَائِثَ ۗ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمَ سَوْءٍ فَاسِقِينَ

የሰዶም ከተማ ይሰሩት የነበረው መጥፎ ሥራ ይህ ነው፤ በዚህ ሥራቸው ክፉ ሰዎችና አመጸኞች ናቸው። ሉጥንም ለሕዝቦቹ፦ “እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም” አላቸው፦
27፥54 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *”እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን?”* وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ
29፥28 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *”እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም”*፡፡ وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ
7፥80 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *”አስቀያሚን ሥራ ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም”*፡፡ وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ

“ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም” ማለት ይህንን ድርጊት ጀማሪዎቹ እነርሱ መሆናቸውን ያሳያል። ወንዶቹ ሴቶች እያሉ ከወንድ ጋር መዳራታቸው ወሰን ማለፍ ነው፦
7፥81 *”እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁን? በእውነቱ እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ”*፡፡ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ النِّسَاءِ ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ
26፥166 *”ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን? በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦ ናችሁ”*፡፡ وَتَذَرُونَ مَا خَلَقَ لَكُمْ رَبُّكُم مِّنْ أَزْوَاجِكُم ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ عَادُونَ

ይህንን ድርጊት በጀመሩት በሰዶማውያን ላይ አላህ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን በመላክ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነበባቸው፦
54፥34 *እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱን በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው*፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ
15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
7፥84 *በእነርሱም ላይ ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት*፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ
26፥173 *በእነርሱም ላይ የድንጋይን ዝናምን አዘነምንባቸው፤ የተስፈራሪዎቹም ዝናም ምንኛ ከፋ*፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَسَاءَ مَطَرُ الْمُنذَرِينَ

ይህ ድርጊት አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ ስለነበር ከተማዎቹ ላይዋንም ከታችዋ ተገለበጡ፦
15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
9፥70 የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑሕ ሕዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም፣ የኢብራሂምም ሕዝቦች የመድየን ባለቤቶች እና *የተገልባጮቹም ከተሞች ወሬ አልመጣላቸውምን?* أَلَمْ يَأْتِهِمْ نَبَأُ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَقَوْمِ إِبْرَاهِيمَ وَأَصْحَابِ مَدْيَنَ وَالْمُؤْتَفِكَاتِ
53፥53 *የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ*፡፡ وَالْمُؤْتَفِكَةَ أَهْوَىٰ

ከላይ ያየነው የሰዶማውያን ሥራ ወሰን ማለፍ እንደሆነ ሉጥ እንዳስጠነቀቃቸው ሀሉ አላህም በቁርኣን የነገረን ከተቃራኒ ጾታ ውጪ የያደርጉ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፤ ወሰንንም አትለፉ ተብለናል፦
23፥6 *በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ላይ ሲቀር፤ እነርሱ በእዚህ የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው*፡፡ إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ
11፥112 *እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
ይህ ድርጊት በማድረግ ወሰን ያለፈ የሚጠብቀው ቅጣት በአኺራ እሳት ነው፦
4፥30 *ወሰን በማለፍና በመበደልም ይህንን የሠራ ሰው እሳትን እናገባዋለን*፡፡ ይኸም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا

በዱኒያህ ደግሞ ያለው ቅጣት በኢስላም የሙስሊም ሸሪዓ ባለበት ህገ-መንግሥት ግድያ ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 20, ሐዲስ 2658
ከኢብኑ ዐባሥ እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም የሉጥ ሕዝብ የሚያደርጉት ድርጊት ሲያደርጉ ብታገኙ ሁለቱንም ግደሏቸው”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَنْ وَجَدْتُمُوهُ يَعْمَلُ عَمَلَ قَوْمِ لُوطٍ فَاقْتُلُوا الْفَاعِلَ وَالْمَفْعُولَ بِهِ ‏”‏ ‏

ሚሽነሪዎች፦ “በኢስላም ግብረ-ሰዶም ሃራም የሆነበት ጥቅስና ቅጣት የለም” ብለው ሲቀጥፉ ተመልሰው ደግሞ፦ “እንዴት ይገደላል? መብቱ ነው” ይላሉ፤ ይህንን የሚሉት የምዕራባውያንን እሳቦትና ዕርዮት ይዘው ነው። መብቱ ከሆነ ለምን ፈጣሪ ሰዶማውያንን በዚህ ድርጊታቸው አጠፋቸው? ለምንስ ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ ይገደሉ አለ?፦
ዘፍጥረት 19፥24 *እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ*።
ዘሌዋውያን 20፥13 *ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው*።

ይህ ብሉይ ኪዳን ላይ ነው እንዳትሉ በአዲስ ኪዳን የተፈቀደበትን ጥቅስ ማምጣት ይጠበቅባችኃል። በአዲስ ኪዳን መፍቀድም መከልከልም የሚችል ነብይ ኢየሱስ ነው፤ ኢየሱስ ሕግን ለመሻር አልመጣሁም ብሏል፤ እንደውም ሰማይና ምድር እስከሚያልፍ ድረስ የሙሴ ሕግ እንደሚሰራ ይናገራል፦
ማቴዎስ 5፥17 *እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኅሊና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

51፥21 *”በራሳችሁም ውስጥ” ምልክቶች አሉ፤ ታዲያ አትመለከቱምን?* وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

“ኅሊና"Conscience" የሚለው ቃል “ኀለየ” ማለትም “አሰበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማሰቢያ” ማለት ነው። ኅሊና በሦስት ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦
1. ታህታይ ኅሊና"sub-Conscience
2. መደበኛ ኅሊና"normal-Conscience
3. ላዕላይ ኅሊና"super-Conscience

ነጥብ አንድ
"ታህታይ ኅሊና"
ታህታይ ኅሊና ማለት ከተፈጠርንበት ጊዜ ጀምሮ በስሜት የምናውቃቸው ግን በትውስታ ትዝ የማይሉን ነገር በኅሊና ተደብቀው የሚኖሩ ነገር፥ ለምሳሌ እናታችን ማህጸን ውስጥ እያለን የምንሰማው ድምጽ፣ ሕጻን ሆነን የምናየው ነገር ወዘተ ያጠቃልለ። ለምሳሌ አላህ ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣ ጊዜ «ጌታችሁ አይደለሁምን?» በማለት ጥያቄ ያቀርባል፤ እኛም «ጌታችን ነህ መሰከርን» በማለት መልስ የሰጠንበት ነው፦
7:172 ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው *ዘሮቻቸውን ባወጣ”* እና «ጌታችሁ አይደለሁምን» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ *”ባስመሰከራቸው”* ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡ *«ጌታችን ነህ መሰከርን»* አሉ፡፡ «በትንሣኤ ቀን ከዚህ ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ፡፡» وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِنۢ بَنِىٓ ءَادَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ ۖ قَالُوا۟ بَلَىٰ ۛ شَهِدْنَآ ۛ أَن تَقُولُوا۟ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّا كُنَّا عَنْ هَٰذَا غَٰفِلِينَ

ይህ ማንም ትዝ የሚለው የለም። ይህ የተነጋገርንበት የምናስታውሰው "በትንሣኤ ቀን ከዚህ ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ" ነው ይለናል። በትንሳኤ ቀን ይህ ውስጣችን ያለው ሚስጥር ይገለጻል፦
100፥10 *"በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ እንዴት እንደሚኾን"*፡፡ وَحُصِّلَ مَا فِي الصُّدُورِ
86፥9 *"ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን"*፡፡ يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ

ነጥብ ሁለት
"መደበኛ ኅሊና"
መደበኛ ኅሊና ማለት በስሜት ሕዋሳት የምንረዳው ውጫዊና ውስጣዊ ነው፥ ለምሳሌ "ሕውስታ"sensation" የሚባለው ነው፦
16፥78 አላህም *"ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም አደረገላችሁ"*፡፡ وَاللَّهُ أَخْرَجَكُم مِّن بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئًا وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۙ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

በመደበኛ ኅሊና ምንም ሳናውቅ እንወለዳለን። "ሕዋስ"Sense" ከውጪ ማየትና መስማት ሲሆኑ ከውስጥ ደግሞ ልብ ነው፥ “ልብ” የሚለው ቃል “ለበወ” ማለትም “አመዛዘነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመዛዘኛ” ማለት ነው። ይህ ዕውቀት በእርጅና ምንንም ነገር ወደ ዐለማወቅ ይሄዳል፦
16፥70 አላህም ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ይገድላችኋል፡፡ *"ከእናንተም ከዕወቅት በኋላ ምንንም ነገር እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አለ"*፡፡ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነው፡፡ وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ ثُمَّ يَتَوَفَّاكُمْ ۚ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰ أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْ لَا يَعْلَمَ بَعْدَ عِلْمٍ شَيْئًا ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ قَدِيرٌ

ነጥብ ሦስት
"ላዕላይ ኅሊና"
ላዕላይ ኅሊና ከሰው በተለየ መልኩ የሚያሳውቀው ዕውቀት ነው፥ ለምሳሌ ነቅል ነው። “ነቅል” نقل ማለት "ግልጠተ-መለኮት" ማለት ነው፥ ለምሳሌ ቁርኣን ነቅል ነው፦
55፥2 *"ቁርኣንን ዐሳወቀው"*፡፡ عَلَّمَ الْقُرْآنَ
96፥5 *"ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን"*፡፡ عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

“ዐቅል” عقل ማለት ከእንስሳ በተለየ መልኩ በውስጣዊ ስሜት የምንረዳው አእምሮ ነው፥ “አእምሮ” የሚለው ቃል “አእመረ” ማለትም “ዐወቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማወቂያ” ማለት ነው። ነቅል ግን ከአላህ ዘንድ የሚወርድ ዕውቀት ነው፦
4፥113 አላህም *"በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ "የማታውቀውንም ሁሉ ዐሳወቀህ"*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًۭا

"የማታውቀውንም ሁሉ ዐሳወቀህ" የሚለው ይሰመርበት። ይህንን ዕውቀት የተረዳ ላዕላይ ኅሊና አለው። ሰው በውስጡ ያለውን ውሳጣዊ ተፈጥሮ ሰፊ ነው። ሙሉውን የሚያውቀውም አላህ ብቻ ነው፦
17፥25 *ጌታችሁ በራሳችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው*፡፡ ታዛዦችም ብትኾኑ በመሳሳትም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች መሓሪ ነው፡፡ رَّبُّكُمْ أَعْلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمْ ۚ إِن تَكُونُوا صَالِحِينَ فَإِنَّهُ كَانَ لِلْأَوَّابِينَ غَفُورًا

ይህንን ውሳጣዊ ማንነት በማጥራት ማስተንተን “አት-ተሰዉፍ” الْتَّصَوُّف‎ ይባላል፤ በማጥራት የሚያስተነትነው ሰው ደግሞ “ሙተሰዉፍ” مُتَصَوُّف‎ ይባላል። በራሳችን ውስጥ ያለው ውሳጣዊ ምልክትቶች ብዙ ናቸው፥ አላህ ይህንን ውሳጣዊ ነገር አትመለከቱምን? ይለናል፦
51፥21 *”በራሳችሁም ውስጥ” ምልክቶች አሉ፤ ታዲያ አትመለከቱምን?* وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈራጅ ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

95፥8 *አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? ነው*፡፡ أَلَيْسَ اللَّهُ بِأَحْكَمِ الْحَاكِمِين

“አል-ሐከም” الحَكَم ከአላህ ስሞች አንዱ ሲሆን ትርጉሙ “ፈራጅ" ወይም "ዳኛ” ማለት ሲሆን “ሁክም” حُكْم ማለትም “ፍርድ” ደግሞ የእርሱ ባሕርይ ነው። አምላካችን አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ በትክክል ፈራጅ ነው፥ በፍርዱ ቀን ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው። በዚያ ቀን በፍርዱ ማንንም አያጋራም፦
95፥8 *አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? ነው*፡፡ أَلَيْسَ اللَّهُ بِأَحْكَمِ الْحَاكِمِين
34፥26 «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ *እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው» በላቸው*፡፡ قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ
18፥26 ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ *በፍርዱም አንድንም አያጋራም*፡፡ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

አምላካችን አላህ የፈራጆች ሁሉ ፈራጅ ሲሆን በዱኒያህ ግን ለሁሉም ነቢያት ማለትም ለሉጥ፣ ለዩሱፍ፣ ለሙሳ፣ ለዳውድ፣ ለሱለይማን ወዘተ የሚፈርዱበት ፍርድ ሰቷቸዋል፦
21፥74 *ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا
12፥22 *ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ፍርድን እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንደዚሁም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
28፥14 ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ *ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንዲሁም መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَاسْتَوَىٰ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
21፥79 *ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው፡፡ ለሁሉም ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠን*፡፡ فَفَهَّمْنَاهَا سُلَيْمَانَ ۚ وَكُلًّا آتَيْنَا حُكْمًا وَعِلْمًا
5፥42 *ብትፈርድም በመካከላቸው በትክክል ፍረድ፤ አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና*፡፡ وَإِنْ حَكَمْتَ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِالْقِسْطِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

“ፈራጆች” የሚለው ቃል ይሰመርበት። በተመሳሳይም በባይብል ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል የሁሉ ዳኛ አንድ ነው፦
ያዕቆብ 4፥12 *"ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ “አንድ” ነው፤ “እርሱም” ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው"*።
ዕብራውያን 12፥24 *“የሁሉም ዳኛ” ወደሚሆን ወደ “እግዚአብሔር”፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ የአዲስም ኪዳን “መካከለኛ” ወደሚሆን ወደ “ኢየሱስ" ደም ደርሳችኋል*።

በተለይ የመጨረሻው ጥቅስ ላይ አንዱ እግዚአብሔር “የሁሉም ዳኛ” ተብሎ ተቀምጦ ኢየሱስን ግን በአንዱ እግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ያለ “መካከለኛ” አርድጎ አስቀምጦታል፦
1ኛ ጢሞ 2፥5 *“አንድ እግዚአብሔር” አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው “መካከለኛው” ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም “ሰው” የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው"*።

ታዲያ አንዱ አምላክ የሁሉ ፈራጅ ከሆነ ኢየሱስ እንዴት ይፈርዳል? የሚል ጥያቄ ከተነሳ የሚፈርደው ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካላትም ናቸው፣ ኢየሱስ ሆነ ሌሎች አካላት የመፍረድ ስልጣንና ፍርድ የተሰጣቸው ከአንዱ አምላክ ነው። ኢየሱስ ሰውና የሰው ልጅ ስለሆነ የመፍረድ ስልጣንና ፍርድ የተሰጠው ከፈጣሪው ነው፣ የሚፈርደው ከላከው ከአንዱ አምላክ እየሰማ እንጂ ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም፦
ዮሐንስ 5፥27 *“የሰው ልጅም” ስለ ሆነ “ይፈርድ” ዘንድ “ሥልጣን ሰጠው”*።
ዮሐንስ 5፥30 “እኔ ከራሴ” አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ *“እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም”* ቅን ነው።
ዮሐንስ 5፥23 ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ *“ፍርድን” ሁሉ ለወልድ “ሰጠው”"*።

በተለይ “ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ሰጠው” የተባለው ለሰሎሞን ፍርድን በሰጠበት ስሌት ነው፦
መዝሙር 72፥1 አቤቱ፥ *“ፍርድህን” ለንጉሥ “ስጥ”*፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥

እንደ ባይብል ተስተምህሮት በፍርድ ቀን የሚፈርዱት የነነዌ ሰዎችና ንግሥተ ዓዜብ ናቸው፦
ማቴዎስ 12፥41 የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው *“ይፈርዱበታል”*።
ማቴዎስ 12፥42 ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ *“ትፈርድበታለች”*።

እንደ ባይብል ተስተምህሮት በፍርድ ቀን የሚፈርዱት ሐዋርያት ናቸው፦
ማቴዎስ 19፥28 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ *እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ “ስትፈርዱ” በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ"*።
ራእይ 20፥4 *"ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት “ዳኝነት” ተሰጣቸው"*።
1ኛ ቆሮ 6፥2 *"ቅዱሳን በዓለም ላይ “እንዲፈርዱ”* አታውቁምን?

አይ የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን "የሚፈርዱት" ማለት "የሚመሰክሩት" ማለት ነው፥ ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን "ትፈርድበታለች" ማለት "ትመሰክርበታለች" ማለት ነው፥ ሐዋርያት በፍርድ ቀን በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ “ስትፈርዱ" ማለት "ስትመሰክሩ' ማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ኢየሱስ በፍርድ ቀን በሐሰተኛ አስተማሪዎቹ ላይ ይመሰክርባቸዋል፥ ለአማኙ ደግሞ በእግዚአብሔር እና በመላእክቱ ፊት ይመስክርለታል፦
ማቴዎስ 7፥22-23 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ *በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል*። የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ፡ ብዬ *"እመሰክርባቸዋለሁ"*።
ማቴዎስ 10፥32 ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ *እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ*፤
ራእይ 3፥5 ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፥ *"በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ"*።

እውነት ነው ዒሣ በትንሣኤም ቀን በአህለል ኪታብ ላይ መስካሪ ይኾናል፦
4፥159 ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ (በዒሳ) በእርግጥ የሚያምን እንጅ አንድም የለም፡፡ *"በትንሣኤም ቀን በእነርሱ ላይ መስካሪ ይኾናል"*፡፡ وَإِن مِّنْ أَهْلِ الْكِتَابِ إِلَّا لَيُؤْمِنَنَّ بِهِ قَبْلَ مَوْتِهِ ۖ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكُونُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا
በቁርኣን አናቅጽ ላይ “ሻሂድ” شَاهِد ማለት የሚመሰክር “መስካሪ” ማለት ሲሆን “መሽሁድ” مَشْهُود ማለት ደግሞ የሚመሰከርበት “ተመስካሪ” ማለት ነው። በተቀጠረው ቀን መስካሪ በተመስካሪ ላይ ይመሰክራሉ፦
85፥2 *”በተቀጠረው ቀንም እምላለው”*። وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ
85፥3 *”በመስካሪ እና በተመስካሪ እምላለሁ”*፡፡ وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ
And by the witness and the witnessed.

አላህ በቁርኣን የማለባቸው ነገሮችን ሁሉ ጉዳዩን አጽንዖትና አንክሮት መስጠቱን የሚያመላክት ነው። ያ የተቀጠረው ቀን ሙታን የሚቀሰቀሱበት የትንሳኤ ቀን ነው፦
34፥30 *«ለእናንተ ከእርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም “የቀጠሮ ቀን” አላችሁ»* በላቸው፡፡ قُل لَّكُم مِّيعَادُ يَوْمٍ لَّا تَسْتَأْخِرُونَ عَنْهُ سَاعَةً وَلَا تَسْتَقْدِمُونَ
36፥52 *«ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? “ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን” እና መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው»* ይላሉ፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ
11፥103 በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ፡፡ *”ይህ የትንሣኤ ቀን ሰዎች በእርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው፡፡ ይህም የሚጣዱት ቀን ነው”*፡፡ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ الْآخِرَةِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّجْمُوعٌ لَّهُ النَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّشْهُودٌ

የተቀጠረው ቀን የመሽሁድ ቀን ነው። አላህ፦ “በመስካሪው እና በሚመሰከርባቸው እምላለው” ብሏል፤ “መስካሪ” የተባሉት “ነቢያት” ሲሆኑ “የሚመሰከርባቸው” ደግሞ “ኡማቸው” ናቸው፦
16፥84 *”ከየሕዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ”*፡፡ وَيَوْمَ نَبْعَثُ مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا
4፥41 *”ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን ባመጣን ጊዜ አንተንም በእነዚህ ሕዝብ ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊዜ የከሓዲዎች ኹኔታ እንዴት ይኾን?”* فَكَيْفَ إِذَا جِئْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ بِشَهِيدٍ وَجِئْنَا بِكَ عَلَىٰ هَـٰؤُلَاءِ شَهِيدًا
16፥89 *”በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ከራሳቸው በእነርሱ ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን አንተንም በእነዚህ ሕዝብ ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣህን ቀን አስታውስ”*፡፡ وَيَوْمَ نَبْعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا عَلَيْهِم مِّنْ أَنفُسِهِمْ ۖ وَجِئْنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَـٰؤُلَاء
28፥75 *”ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ ያን ጊዜ እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል”*፡፡ وَنَزَعْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا فَقُلْنَا هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ فَعَلِمُوا أَنَّ الْحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ

ስለዚህ ፈራጅ አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው። መስካሪዎች ነቢያት ናቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም