ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
በጉራጊኛ ደርሥ ተለቋል። ጉራጊኛ የምትችሉ አሊያም ለጉራጊኛ ተናጋሪ ሼር ማድረግ የምትፈልጉ ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦ https://tttttt.me/wahidcomguragiga/20
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

ትግራይ ክልል
ሱማሌ ክልል
አፋር ክልል
ያላችሁ ሙሥሊም ወጣት ወንዶች እና ሴቶች አድሚናትን በቴሌ ግራም አግኙ፦
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://tttttt.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://tttttt.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://tttttt.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://tttttt.me/selemtewa

ለጥብቅ ጉዳይ ትፈለጋላችሁ!

ከወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገድለ ተክለ ሃይማኖት ገጽ 8 ቁ. 24 "የሥላሴ ሦስትነታቸው እና አንድነታቸው ወልድ ሰው እስከሆነ ድረስ አይታወቅም ነበር"፡፡

ይህ ሆኖ ሳለ ዶክተር ዘበነ ለማ ግን "ጥንት የነበሩት አይሁዳውያን በሥላሴ ያምኑ ነበር" በማለት እልም ያለ ቅጥፈት ቀጥፏል። እስቲ ታሪካዊ ማስረጃ አቅርብ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
የሚያሞት አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

26፥81 ያም የሚያሞተኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡ وَالَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحْيِينِ

አምላካችን አሏህ ሕያዋን ሰዎችን በሞት የሚያሞት ነው፥ ኢብራሂም፦ "ያም የሚያሞተኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው" ያለው ይህንን ዋቢ እና ታሳቢ ያደረገ ነው፦
26፥81 ያም የሚያሞተኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡ وَالَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحْيِينِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሚያሞት" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሚቱ" يُمِيتُ ሲሆን በዐማርኛ "የሚገል" በሚል ተቀምጧል። በተመሳሳይ በባይብል በሞት የሚያሞት አንድ አምላክ ነው፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥6 ያህዌህ ያሞታል፥ ሕያው ያደርጋል። ወደ መቃብር ያወርዳል፥ ያወጣል። יְהוָ֖ה מֵמִ֣ית וּמְחַיֶּ֑ה מֹורִ֥יד שְׁאֹ֖ול וַיָּֽעַל׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያሞታል" ለሚለው የገባው ቃል "መሚት" מֵמִ֣ית ሲሆን በዐማርኛ "ይገላል" በሚል ተቀምጧል፥ አምላክ ወደ መቃብር በማውረድ እንደሚያሞት ሁሉ በትንሳኤ ቀን ከመቃብር በማውጣት ሕያው ያደርጋል። በዕብራይስጥ "ሺኦል" שְׁאוֹל የሚለው ቃል እና በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ሐዴስ" ᾍδης የሚለው ቃል መሠረታዊ ትርጉሙ "መቃብር" ማለት ነው፥ ለዛ ነው አዲሱ መደበኛ ትርጉም እና በጣም ስመ ጥር እና ዝነኛ የእንግሊዝኛ መተርጉማን "መቃብር"grave" ብለው ያስቀመጡት። የሰውን መንፈስ ከሰው በማውጣት የሚያሞት ይህ አንዱ አምላክ ነው፦
መዝሙር 104፥29 መንፈሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ። תֹּסֵ֣ף ר֭וּחָם יִגְוָע֑וּן וְֽאֶל־עֲפָרָ֥ם יְשׁוּבֽוּן׃

እዚህ አንቀጽ ላይ በተለያየ የትርጉም ሥራ ላይ "እስትንፋስ" "ነፍስ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሩሓህ" רוּחַ ሲሆን "መንፈስ" ማለት ነው። አምላክ የሰውን መንፈስ ሲያወጣ ሥጋ ደግሞ ወደ አፈር ይመለሳል፦
መዝሙር 146፥4 መንፈሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል። תֵּצֵ֣א ר֭וּחֹו יָשֻׁ֣ב לְאַדְמָתֹ֑ו
ኢዮብ 34፥14-15 መንፈሱን እና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል። וְ֝נִשְׁמָתֹ֗ו אֵלָ֥יו יֶאֱסֹֽף׃ יִגְוַ֣ע כָּל־בָּשָׂ֣ר יָ֑חַד וְ֝אָדָ֗ם עַל־עָפָ֥ר יָשֽׁוּב׃

እዚህ ጥቅስ ላይ የሰውን አካል ሕያው የሚሆንበትን "መንፈስ" ወደ አምላክ በማስጠጋት ለእልቅና "መንፈሱ"his spirit" ተብሏል። የሰው መንፈስ የአምላክ መንፈስ መባሉ ካላወዛገበ በተመሳሳይ አምላካችን አሏህ የሰውን መንፈስ ወደ ራሱ በማስጠጋት ለእልቅና "መንፈሴ" ማለቱ አያወዛግብም፦
38፥72 ፍጥረቱንም ባስተካከልኩ እና በእርሱ ውስጥ "ከ-መንፈሴ" በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» አልኩ፡፡ فَإِذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُوا لَهُ سَاجِدِينَ

የሚያሞት አንድ አምላክ ከሆነ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው፥ ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው። ይህንን ነገር ውብ አድርጎ የሠራው ይህ አንድ አምላክ ነው፦
መክብብ 3፥1 ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።
መክብብ 3፥2 ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው።
መክብብ 3፥11 ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው።

"የመሞት ጊዜ" የሰው ልጆች እና የእንስሳ እድል ፈንታ ነው፥ የሰው ልጆች እና የእንስሳ በተፈጥሮአዊ ሞት ድርሻቸውም እኩል ነው። የሰው ልጆች እና እንስሳ ከአፈር ናቸውና ወደ አፈር ይመለሳሉ፦
መክብብ 3፥19 የሰው ልጆች እና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፥ ድርሻቸውም ትክክል ነው። አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፥
መክብብ 3፥20 ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፤ ሁሉ ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል።

ሰው አካሉ ሕያው የሚሆንበት መንፈስ እንዳለው ሁሉ እንስሳም አካሉ ሕያው የሚሆንበት መንፈስ አለው፥ ቅሉ ግን የእንስሳ መንፈስ ወደ ላይ ሳይወጣ ሲቀር የሰው መንፈስ ግን ወደ ሰጠው ወደ ፈጣሪ ይመለሳል፦
መክብብ 3፥19 የሁሉም መንፈስ አንድ ነው፤ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም። וְר֥וּחַ אֶחָ֖ד לַכֹּ֑ל וּמֹותַ֨ר הָאָדָ֤ם מִן־הַבְּהֵמָה֙ אָ֔יִן כִּ֥י הַכֹּ֖ל הָֽבֶל׃
መክብብ 3፥21 የሰው ልጆች መንፈስ ወደ ላይ እንደምትወጣ የእንስሳም መንፈስ ወደ ታች ወደ ምድር እንደምትወርድ የሚያውቅ ማን ነው? מִ֣י יֹודֵ֗עַ ר֚וּחַ בְּנֵ֣י הָאָדָ֔ם הָעֹלָ֥ה הִ֖יא לְמָ֑עְלָה וְר֙וּחַ֙ הַבְּהֵמָ֔ה הַיֹּרֶ֥דֶת הִ֖יא לְמַ֥טָּה לָאָֽרֶץ׃
መክብብ 12፥7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ። וְיָשֹׁ֧ב הֶעָפָ֛ר עַל־הָאָ֖רֶץ כְּשֶׁהָיָ֑ה וְהָר֣וּחַ תָּשׁ֔וּב אֶל־הָאֱלֹהִ֖ים אֲשֶׁ֥ר נְתָנָֽהּ׃

ሦስቱም አናቅጽ ላይ "እስትንፋስ" "ነፍስ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሩሓህ" רוּחַ ሲሆን "መንፈስ" ማለት ነው። የሰው መንፈስ ወደ አምላክ እንዲሁ አካሉ ወደ አፈር የሚመለስበት የሞት ጊዜ ከፍጥረት በፊት በአምላክ መጽሐፍ ተጽፏል፦
መዝሙር 139፥16 የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ
አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። καὶ ἐπὶ τὸ βιβλίον σου πάντες γραφήσονται· ἡμέρας πλασθήσονται καὶ οὐθεὶς ἐν αὐτοῖς.

"መጽሐፍህ" የሚለው ይሰመርበት! እዚህ አንቀጽ ላይ በግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ "መጽሐፍ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ቢብሊዮን" βιβλίον ነው፥ "አንድ ስንኳ ሳይኖር" ማለት "ምንም ነገር ሳይኖር" ማለት ሲሆን ምንም ነገር ሳይፈጠር የሰዎች ዕድሜ በአምላክ መጽሐፍ ተጽፏል። ሰውን የሚያሞት፣ መንፈሱን የሚያወጣ እና የሞትን ጊዜ የወሰነው አንዱ አምላክ ከሆነ ተፈጥሯዊ ሞት የአምላክ ሥራ እንጂ በአዳም አሊያም በሰይጣን የመጣ አይደለም። ሐሊቁ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢየሱስ ድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ ከመፈጠሩ በፊት "ነበረ" ብለው ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸውን ጥቅሳት ዳሰሳ አርገናል። ያድምጡ ያስደምጡ፦ https://youtu.be/UY98XH1DKP8?si=aOv0_AEYOG4jMi_k

ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ መልእክቱ ተደራሽነት እንዲኖረው ላይክ፣ ኮሜንት፣ ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን። ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን፦ "ወደ መንፈስ ቅዱስ አንጸልይም፥ ወደ ኢየሱስ አንጸልይም። የምንጸልየው በኢየሱስ ስም ወደ አብ ነው" ብሏል። It's so wonderful that.
ይህ ትልቅ ለውጥ ነው። እኛም የምንለው ይህንን ነው። መመለክ የሚገባው ኢየሱስ ሳይሆን ኢየሱስ የላከ የኢየሱስ አምላክ ብቻ እና ብቻ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቲክ ታክ ላይ ያሉት የፕሮቴስንታንት ዐቃቢያነ ክርስትና ጋጠወጥ፣ ተሳዳቢ፣ ዘላፊ፣ አላጋጭ፣ ተበሻሻቂ እንደሆኑ እና ዕውቀት አልባ መሆናቸውን መምህራቸው ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ በአጭሩ እዚህ ላይ አስቀምጠዋል። እናመሰግናለን ዶክተር
የክርስቶስ ተቃዋሚ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي

"የክርስቶስ ተቃዋሚ" ማለት "ጸረ ክርስቶስ"antichrist" ማለት ሲሆም በግሪክ ኮይኔ "አንቲኽሪስቶስ" ይባላል፥ "አንቲኽሪስቶስ" ἀντίχριστος የሚለው ቃል "አንቲ" ἀντί ማለትም "ተቃራኒ" "ተቃዋሚ" "ሐሳዌ" እና "ኽሪስቶስ" Χριστός ማለትም "መሢሕ" "ቅቡዕ" "ክርስቶስ" ከሚል ሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "የክርስቶስ ተቃራኒ" "የክርስቶስ ተቃዋሚ" "ሐሳዌ መሢሕ" ማለት ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥18 ልጆች ሆይ! መጨረሻው ሰዓት ነው፥ "የክርስቶስም ተቃዋሚ" ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ። Παιδία, ἐσχάτη ὥρα ἐστίν, καὶ καθὼς ἠκούσατε ὅτι ἀντίχριστος ἔρχεται,

እዚህ አንቀጽ ላይ በነጠላ "የክርስቶስም ተቃዋሚ" የተባለው ዋናው ሐሳዌ መሢሕ ሲሆን ከእርሱ መምጣት በፊት የመጡት አሳቾች እራሱ "የክርስቶስ ተቃዋሚዎች" ተብለዋል፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥18 አሁን እንኳ ብዙዎች "የክርስቶስ ተቃዋሚዎች" ተነሥተዋል፥ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን። καὶ νῦν ἀντίχριστοι πολλοὶ γεγόνασιν· ὅθεν γινώσκομεν ὅτι ἐσχάτη ὥρα ἐστίν.

ግዕዙ "ሐሳውያነ መሢሕ" ይለዋል፥ ሐሳውያነ መሢሕ እነዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፦
2ኛ ዮሐንስ 1፥7 ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹ እና "የክርስቶስ ተቃዋሚው" ነው። ὅτι πολλοὶ πλάνοι ἐξῆλθον εἰς τὸν κόσμον, οἱ μὴ ὁμολογοῦντες Ἰησοῦν Χριστὸν ἐρχόμενον ἐν σαρκί· οὗτός ἐστιν ὁ πλάνος καὶ ὁ ἀντίχριστος.

እኛ ሙሥሊሞች ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ፣ ክርስቶስ ከአባቶች በሥጋ እንደመጣ፣ አንዱ አምላክ ኢየሱስን የዳዊት ዘር ከሆነችው ከማርያም ካለመኖር ወደ መኖር እንዳመጣው እናምናለን፦
ሮሜ 9፥5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ "ከእነርሱም" ክርስቶስ በሥጋ መጣ። καὶ ἐξ ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 ከዚህም ሰው ዘር አምላክ እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ። τούτου ὁ Θεὸς ἀπὸ τοῦ σπέρματος κατ’ ἐπαγγελίαν ἤγαγεν τῷ Ἰσραὴλ Σωτῆρα Ἰησοῦν,

እኛ ሙሥሊሞች ኢየሱስ መሢሕ እንደሆነ ስለምናምን "አል መሢሑ ዒሣ" الْمَسِيحُ عِيسَى በሚል ማዕረጋዊ ስም ብዙ ቦታ በቁርኣን ተጠቅሷል። 3፥45 4፥171 ተመልከት!
በተቃራኒው ግን "ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም" ብሎ የሚክድ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥22 "ክርስቶስ አይደለም" ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብን እና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።

"አብ" ማለት በፍካሬአዊ ቃል "አስገኚ" "ምንጭ" "ፈጣሪ" ማለት ሲሆን "ወልድ" ማለት በፍካሬአዊ ቃል "ተገኝ" "ተመንጭ" "ፍጡር" ማለት ነው። ኢየሱስ "በአምላክ እመኑ" ሲል እና "በእኔም ደግሞ እመኑ" ሲል አንዱ አምላክ ላኪ ኢየሱስ ተላኪ መሢሕ መሆኑን የሚያሳይ ነው፦
ዮሐንስ 14፥1 በአምላክ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። πιστεύετε εἰς τὸν Θεόν, καὶ εἰς ἐμὲ πιστεύετε.

"በእኔ" በሚለው ቃል ላይ “ም” የሚለው ጥገኛ ምዕላድ በዐማርኛ ተጨማሪ ነገርን ለማሳየት የገባው በግሪኩ "ካይ" καὶ ማለትም "እና" የሚለውን መስተጻምር ለማሳየት የገባ ነው፥ ይህም አምላክ እና መልእክተኛው ሁለት የተለያዩ ሃልዎት እና ኑባሬ እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። በእርግጥም በመልእክተኛው ማመን በላከው ማመን የሚሆንበት ምክንያት መልእክቱ የላኪው እንጂ የተላኪው ስላልሆነ ነው፦
ዮሐንስ 12፥44 ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።

እውነት ነው! ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክን አብ እና መሢሑን ኢየሱስ የሚክዱ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον δεσπότην θεὸν καὶ κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ዴስፖቴን ቴዎን" δεσπότην θεὸν የሚለው ኮዴክስ ቤዛይ ላይ ሲሆን 1611 ድኅረ ልደት በታተመው ቅጂ The King James Version (KJV) ላይ ልክ እንደ ኮዴክስ ቤዛይ፦ "ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ"and denying the only Lord God, and our Lord Jesus Christ" ብለው አስቀምጠውታል።
አምላካችን አሏህ ለዒሣ በሰጠው ወሕይ በኢንጂል ለሐዋርያት፦ "በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ" ብሎ አዟቸው ነበር፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي

እዚህ አንቀጽ "ባዘዝኩ" ለሚለው የገባው ቃል "አውሐይት" أَوْحَيْتُ የግሥ መደብ ሲሆን የስም መደቡ "ወሕይ" وَحْي ማለትም "ግልጠተ መለኮት"revelation" ነው፥ በአሏህ አምላክነት በመልእክተኛው በኢየሱስ መሢሕነት ማመን የአርካኑል ኢማን ክፍል ነው። እንደተግባባን ተስፋ አደርጋለው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያ ጀመዓህ ክፍል ሁለት ተለቋል። ኢየሱስ ድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ ከመፈጠሩ በፊት "ነበረ" ብለው ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸውን ጥቅሳት ዳሰሳ አርገናል። ያድምጡ ያስደምጡ፦ https://youtu.be/ThIlPF3mQLY?si=s4DKbS6L5dTmINb-

ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ መልእክቱ ተደራሽነት እንዲኖረው ላይክ፣ ኮሜንት፣ ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን። ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
የመስቀል አምልኮ በሚል ርእስ በአፋርኛ ተለቋል። የአፋርኛ ተናጋሪዎች ግቡ እና አንብቡ፦ https://tttttt.me/wahidcomafarega/14
በጉራጊኛ "የክርስቶስ ተቃዋሚ" በሚል ደርሥ ተለቋል። ጉራጊኛ የምትችሉ አሊያም ለጉራጊኛ ተናጋሪ ሼር ማድረግ የምትፈልጉ ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦ https://tttttt.me/wahidcomguragiga/22

በተጨማሪ የወንድም አቡ ዑሥማን(አኬል) ሥራዎች በጉራጊኛ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦ @AkeelComparative
ሥነ ፈለክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

21፥33 እርሱም ሌሊትን እና ቀንን፣ ፀሐይን እና ጨረቃን የፈጠረ ነው፡፡ ሁሉም በምህዋራቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ فِي فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

"ፈለክ" فَلَك የሚለው ቃል "ፈለከ" فَلَك ማለትም "ሖረ" "ሔደ" አለፈ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ምሕዋር"orbit" ማለት ነው፥ የፈለክ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አፍላክ" أَفْلَاك ሲሆን "ምሕዋራት" ማለት ነው፦
21፥33 እርሱም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው፡፡ ሁሉም በምህዋራቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ فِي فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ምሕዋር" ለሚለው የገባው ቃል "ፈለክ" فَلَك ሲሆን በዐማርኛ ላይ "ፈለክ" የሚለው ቃል የተወሰደው ከዐረቢኛው እንደሆነ እሙን እና ቅቡል ነው፥ ስለ ከዋክብት፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ የሚያጠና የዕውቀት ዘርፍ "ፈለኪያህ" فَلَكِيَّة ማለትም "ሥነ ፈለክ"astronomy" ይባላል። "አስትሮኖሚ"astronomy" የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል "አስትሮኖሚያ" ἀστρονομία ከሚል የግሪክ ቃል የተወሰደ ነው። "አስትሮን" ἄστρον ማለት "ኮከብ" ማለት ሲሆን "ኖሞስ" νόμος ማለት "ሕግ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "አስትሮኖሚያ" ἀστρονομία ማለት "የከዋክብት ሕግ" ማለት ነው።

“መሽሪቅ” مَشْرِق የሚለው ቃል "ሸረቀ" شَرَقَ ማለትም "ወጣ" "ታየ" "ተገለጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መውጪያ” “መታያ” “መገለጪያ” "ምሥራቅ" ማለት ነው፥ “መግሪብ” مَغْرِب የሚለው ቃል “ገረበ” غَرَبَ ማለትም “ገባ” “ጠለቀ” “ተሰወረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መግቢያ” “መጥለቂያ” “መሰወሪያ” "ምዕራብ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ የምሥራቅ እና የምዕራብ ጌታ ነው፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፦
73፥9 እርሱም የምሥራቅ እና የምዕራብ ጌታ ነው፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው፡፡ رَّبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا

ከመነሻው ፀሐይ በፍጹማዊ እውነታ መውጫ እና መግቢያ የላትም፥ መውጣት እና መግባት አንጻራዊ እውነታ ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ የመሽሪቅ ሙሰና "መሽሪቀይኒ" مَشْرِقَيْنِ ሲሆን "ሁለቱ ምሥራቆች" ማለት ነው። ፀሐይ በበጋ ጊዜ በሰሜን ንፍቀ-ክበብ”north pole” ስትወጣ አንደኛው መውጫ ይህ ሲሆን በክረምት ጊዜ ደግሞ በደቡብ ንፍቀ-ክበብ”south pole” መውጣቷ ሁለተኛው መውጫ ይህ ነው፥ ሁለቱ ምሥራቆች የሚለው ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።
የመግሪብ ሙሰና “መግሪበይኒ” مَغْرِبَيْنِ ሲሆን "ሁለቱ ምዕራቦች" ማለት ነው። ፀሐይ በበጋ ጊዜ በሰሜን ንፍቀ-ክበብ”north pole” ስትገባ አንደኛው መግቢያ ይህ ሲሆን በክረምት ጊዜ ደግሞ በደቡብ ንፍቀ-ክበብ”south pole” መግባቷ ሁለተኛው መግቢያ ይህ ነው፥ ሁለቱ ምዕራቦች የሚለው ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፦
55፥17 "የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ እና የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው"፡፡ رَبُّ الْمَشْرِقَيْنِ وَرَبُّ الْمَغْرِبَيْنِ

ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር ይህንን አንቀጽ የፈሠረው በዚህ መልኩ እና ልክ ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 55፥17
*"የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ እና የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው" ማለት "የበጋ እና የክረምት የፀሐይ መውጫዎች እና የበጋ እና የክረምት የፀሐይ መጥለቂያዎች" ማለት ነው። አላህ በሌላ አንቀጽ፦ "በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ" አል-መዓሪጅ 40 ፥ ይህ የሚያመላክተው በእያንዳንዱ ቀን ለሰዎች የተለያዩ የፀሐይ መውጫዎች እና የፀሐይ መጥለቂያዎች ቦታዎች እንዳሉ ነው። አላህ በሌላ አንቀጽ፦ "እርሱም የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው" አል-ሙዘሚል 9 ፥ ይህ የሚያመላክተው የተለያዩ የፀሐይ መውጫዎች እና የፀሐይ መጥለቂያዎች ቦታዎች እንዳሉ እና ይህ ልዩነት ለተፈጠሩት ለጂኒዎችም ሰዎችም ጥቅም ያመጣል"*።
( رب المشرقين ورب المغربين ) يعني مشرقي الصيف والشتاء ، ومغربي الصيف والشتاء . وقال في الآية الأخرى : ( فلا أقسم برب المشارق والمغارب ) [ المعارج : 40 ] ، وذلك باختلاف مطالع الشمس وتنقلها في كل يوم ، وبروزها منه إلى الناس . وقال في الآية الأخرى : ( رب المشرق والمغرب لا إله إلا هو فاتخذه وكيلا ) [ المزمل : 9 ] . وهذا المراد منه جنس المشارق والمغارب ، ولما كان في اختلاف هذه المشارق والمغارب مصالح للخلق من الجن والإنس
እውነት ነው! አሜሪካ የፀሐይ መውጫ እና መጥለቂያ ከኢትዮጵያ፥ የኢትዮጵያ ከአውሮፓ፣ የአውሮፓ ከሩቅ ምሥራቅ ለየቅል ነው። ለዛ ነው በብዜት "ምሥራቆች እና ምዕራቦች" የተባለው። የመሽሪቅ ጀምዕ “መሻሪቅ” مَشَارِق ሲሆን "ምሥራቆች" ማለት ነው። የመግሪብ ጀምዕ "መጋሪብ" مَغَارِب ሲሆን "ምዕራቦች" ማለት ነው፦
70፥40 በምሥራቆች እና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፥ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን"፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ

ፀሐይ የፕላኔታችን ሥርዓተ-ብርሃን”Solar System” እምብርት እና ከህልቆ መሳፍርት ከዋክብት አንዷ የንጋት ኮከብ ናት፥ የእኛ የንጋት ኮከብ ፀሐይ ለእኛ ሥርዓተ-ብርሃን መውጣትና መግባት እንዳላት ሁሉ እያንዳንዳቸው ከዋክብትም በራሳቸው ሥርዓተ-ብርሃን ስላላቸው ለእኛ እይታ ላይ መውጣትና መግባት አላቸው። ከዋክብት በሌሊት ይወጣሉ፥ በንጋት ይገባሉ፥ ይህ የእነርሱ መውጫዎችና መግቢያዎች ምሥራቆችና ምዕራቦች ይባላሉ፦
52፥49 ከሌሊቱም አወድሰው፥ በከዋክብት መደበቂያ ጊዜም ላይ አወድሰው፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَسَبِّحْهُ وَإِدْبَارَ النُّجُومِ
56፥75 በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِمَوَاقِعِ النُّجُومِ
89፥15 ተመላሾችም በኾኑት እምላለሁ፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِالْخُنَّسِ
89፥16 ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት ከዋክብት፡፡ الْجَوَارِ الْكُنَّسِ

"ምሥራቆችና ምዕራቦች" የሚለው ሲገርማቸው መጽሐፈ ሄኖክ ላይ ያለውን ፀሐይ የሚወጣባቸው ስድስት መስኮቶች እና ፀሐይ የሚገባባቸው ስድስት መስኮቶች ሲያነቡ ምን ይውጣቸው ይሆን? እንመልከት፦
ሄኖክ 21፥6 ፀሐይ የሚወጣባቸው ስድስት መስኮቶችን አየሁ፥ ፀሐይም ሚገባባቸው ቦታዎች ስድስት መስኮቶችንም አየሁ።

መርፌ የራሷን ቀዳዳ ሳትሰፋ የሰውን ልብስ ትሰፋ? ይላል የአገሬ ሰው። ለመሆኑ እነዚህም መስኮቶች ስድስቱ በምሥራቅ ስድስቱ በምዕራብ ናቸው፦
ሄኖክ 21፥8 እነዚህም መስኮቶች ስድስቱ በምሥራቅ ስድስቱ ፀሐይ በሚገባበት በምዕራብ ናቸው።

ይኸው መጽሐፍ የፀሐይ እና የጨረቃ መጠናቸው እኩል እንደሆነ እና ጨረቃም በምሥራቅ ስድስቱ መስኮቶች ይወጣል በምዕራብ ስድስቱ ስድስቱ መስኮቶች ይገባል፦
ሄኖክ 21፥57 የሁለቱ ሁሉ የፀሐይ እና የጨረቃ መጠናቸው የተካከለ ነው።
ሄኖክ 21፥7 ጨረቃም በእነዚያ መስኮቶች ይወጣል ይገባል።

የሚገርመው በምሥራቅ ፀሐይ የምትወጣበት ስድስቱ መስኮቶች እና በምዕራብ የምትገባበት ስድስቱ መስኮቶች በሰማይ ውስጥ ነው፦
ሄኖክ 21፥5 ፀሐይ ብርሃን ነው፥ መውጫውም በምሥራቅ በኩል በሰማይ መስኮቶች ነው፥ መግቢያውም በምዕራብ በኩል በሰማይ መስኮቶች ነው።

በሰማያት ውስጥ የፀሐይን ድንኳን እንዳለ መናገሩ የሚያጅብ ነው፦
መዝሙር 19፥1 "ሰማያት" የአምላክን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል። הַשָּׁמַ֗יִם מְֽסַפְּרִ֥ים כְּבֹֽוד־אֵ֑ל וּֽמַעֲשֵׂ֥ה יָ֝דָ֗יו מַגִּ֥יד הָרָקִֽיעַ׃
መዝሙር 19፥5 በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ። לַ֝שֶּׁ֗מֶשׁ שָֽׂם־אֹ֥הֶל בָּהֶֽם

"እነርሱ" የሚለው "ሰማያት" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። ስለዚህ ሁሌ ትችት ከማቅረባችን በፊት የራሳችንን ጉድ መመልከት ይገባል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ ዙፋን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

11፥7 ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች የፈጠረው ነው፤ ዙፋኑ በውኃ ላይ ነበር"። وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ

"ከሩቢይ" كَرُوبِيّ ማለት "ቡሩክ" ማለት ነው፥ "ከሩቢዩን" كَرُوبِيُّون ማለት ደግሞ የከሩቢይ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ቡሩካን" ማለት ነው። የግዕዙ "ኪሩብ" የሚለው ቃል እና "ክሩቭ" כְּרוּב የዕብራይስጡ ቃል "ባሩኽ" בָּרוּךְ ከሚለው ከአካድ ቃል የተወሰደ ሲሆን "ቡሩክ" ማለት ነው፥ የኤርሚያስ ብርቱ ጸሐፊ "ባሮክ" ስሙ የተወሰደው "ባሩኽ" בָּרוּךְ ከሚለው ነው። የአሏህን ዙፋን የሚሸሙት መላእክት ኪሩቤል ለአሏህ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክት ናቸው፦
4፥172 አል መሢሕ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም አይጠየፉም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ
40፥7 እነዚያ "ዙፋኑን የሚሸከሙት" እና እነዚያ በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 132
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ዙፋኑን ከሚሸከሙት ከአሏህ መላእክት ስለ አንዱ መልአክ እንድናገር ተፈቅዶልኛል፥ እርሱም በጆሮው እና በትከሻው መካከል ያለው ርቀት የሰባት መቶ ዓመት ጉዞ ነው"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ أُذِنَ لِي أَنْ أُحَدِّثَ عَنْ مَلَكٍ مِنْ مَلاَئِكَةِ اللَّهِ مِنْ حَمَلَةِ الْعَرْشِ إِنَّ مَا بَيْنَ شَحْمَةِ أُذُنِهِ إِلَى عَاتِقِهِ مَسِيرَةُ سَبْعِمِائَةِ عَامٍ ‏"‏ ‏.‏

"ዐርሽ" عَرْش የሚለው ቃል "ዐረሸ" عَرَشَ ማለትም "ተቆናጠጠ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መቆጣጫ" "ዙፋን" ማለት ነው፥ ዙፋን የሉዓላዊነት እና የልዕልና መቆናጠጥ እንዲሁ የንግሥና ምልክት እና መገለጫ ነው፦
27፥23 እኔ "የምትገዛቸው" የሆነችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ፥ ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አላት። إِنِّى وَجَدتُّ ٱمْرَأَةًۭ تَمْلِكُهُمْ وَأُوتِيَتْ مِن كُلِّ شَىْءٍۢ وَلَهَا عَرْشٌ عَظِيمٌۭ

"የምትገዛ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ተምሊኩ" تَمْلِكُ ሲሆን ዙፋን የንግሥና ምልክት እና መገለጫ መሆኑን ድብን አርጎ ያሳያል። "መሊክ" مَلِيك ማለት "ንጉሥ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ እውነተኛ ንጉሥ ስለሆነ የንግሥናውን ምልክት የሚያምር ዙፋን አለው፦
23፥116 እውነተኛም ንጉሥ አሏህ ከፍተኛነት  ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም። የሚያምረው “ዙፋን” ጌታ ነው፡፡ فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلْمَلِكُ ٱلْحَقُّ ۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلْعَرْشِ ٱلْكَرِيمِ

አምላካችን አሏህ በተከበረ ቃሉ እንዲሁ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በነቢያዊ ቃላቸው የአሏህ ዐርሽ በውኃ ላይ እንደነበር ተናግረዋል፦
11፥7 ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች የፈጠረው ነው፤ ዙፋኑ በውኃ ላይ ነበር"። وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 2
ዒምራም ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ "ምንም ነገር ሳይኖር አሏህ ነበረ፥ ዙፋኑ በውኃ ላይ ነበረ"። عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ، قَالَ إِنِّي عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ، وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ،
ሚሽነሪዎች "ዙፋኑ በውኃ ላይ ነበረ" የሚለው ይዘው በቁርኣን እና በሐዲስ ሲስቁ እና ሲሳለቁ ማየት ይገርማል፥ ከዓይን ለተወረወረ ጦር ጋሻ አይያዝምና ይህ የሚያሳየው መጽሐፋቸው በቅጡ እና በአግባብ አለማየታቸው ነው። በባይብል በግልጽ "ሰባት ሰማያት" የሚል ባይኖርም ብዙ ሰማያት እንዳሉ ከበቂ በላይ ማስረጃ አለ፦
1ኛ ነገሥት 8፥27 እነሆ ሰማይ እና ከሰማያት በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም። הִ֠נֵּה הַשָּׁמַ֜יִם וּשְׁמֵ֤י הַשָּׁמַ֙יִם֙ לֹ֣א יְכַלְכְּל֔וּךָ
ዘዳግም 10፥14 እነሆ ሰማይ፣ ሰማየ ሰማያት፣ ምድር፣ በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የያህዌህ ነው። הֵ֚ן לַיהוָ֣ה אֱלֹהֶ֔יךָ הַשָּׁמַ֖יִם וּשְׁמֵ֣י הַשָּׁמָ֑יִם הָאָ֖רֶץ וְכָל־אֲשֶׁר־בָּֽהּ׃
ነህምያ 9፥6 አንተ ብቻ ያህዌህ ነህ፤ ሰማዩን፣ የሰማያት ሰማይን፣ ሠራዊታቸውንም ሁሉ፣ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፣ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ ፈጥረሃል።

'ሰማይ" አንድ፣ "ሰማያት" ብዙ እና ከሰማያት በላይ ያለው "ሰማይ" ከቆጠርን በትንሹ አምስት ሰማያት አሉ፥ "ሰማየ ሰማያት" ወይም "የሰማያት ሰማይ" ማለት "ከሰማያት በላይ ያለው ሰማይ" ማለት ነው። ይህ ከሰማያት በላይ ያለው ሰማይ እራሱ ውኃ ነው፦
መዝሙር 148፥4 ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት የሰማያት በላይም ውኃ። הַֽ֭לְלוּהוּ שְׁמֵ֣י הַשָּׁמָ֑יִם וְ֝הַמַּ֗יִם אֲשֶׁ֤ר ׀ מֵעַ֬ל הַשָּׁמָֽיִם׃
ሄኖክ 14፥32 ውኆችም(ውኃዎች) ሁሉ "ከሰማያት በላይ ካሉ ውኃዎች" ጋር ይጨመራሉ።
ሄኖክ 14፥31 "ከሰማያት በላይ ያሉ የውኃዎች" መዛግብት ሁሉ፥ ከሰማያት በታችና፥ ከምድር በላይ ያሉ ምንጮችም ይከፈታሉ።
ሄኖክ 14፥33 "ከሰማያት በላይ ያለ ውኃ" ግን ተባዕታይ ነው፥ ከምድር በታች ያለችው ውኃም አንስታይ ናት።

"ውኆች" የውኃ ብዙ ቁጥር ነው። "ጽርሐ አርያም" ማለት ሰማየ ሰማያት ወይም ከሰማያት ኹሉ በላይ ያለው ሰማይ ነው፦
ኢዮብ 16፥19 አሁንም እነሆ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ የሚመሰክርልኝም በአርያም ነው። גַּם־עַ֭תָּה הִנֵּה־בַשָּׁמַ֣יִם עֵדִ֑י וְ֝שָׂהֲדִ֗י בַּמְּרֹומִֽים
ኢሳይያስ 33፥5 ያህዌህ በአርያም ተቀምጦአልና፥ ከፍ ከፍ አለ። נִשְׂגָּ֣ב יְהוָ֔ה כִּ֥י שֹׁכֵ֖ן מָרֹ֑ום

"በአርያም ተቀምጦአል" የሚለው ይሰመርበት! "አርያም" ማለት "ከፍተኛ" ማለት ሲሆን "ጽርሕ" ማለት "ስገነት" "እልፍኝ" "አዳራሽ" "ሳሎን" ማለት ነው፥ ፈጣሪ ይህንን ጽርሐ አርያም የሠራው በውኃ ነው፦
አሞጽ 9፥6 አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ הַבֹּונֶ֤ה בַשָּׁמַ֙יִם֙ [מַעֲלֹותֹו כ] (מַעֲלֹותָ֔יו
መዝሙር 104፥3 እልፍኙን በውኃ የሠራ፥ הַ֥מְקָרֶֽה בַמַּ֗יִם עֲ‍ֽלִיֹּ֫ותָ֥יו

ጽርሐ አርያም በውኃ እንደተሠራ ስታዩ ኩሽ እና ኩምሽሽ እንደምትሉ ይታየኛል። ጽርሐ አርያም በውኃ እንደተሠራ ካየን ዘንድ ይህ ከሰማያት በላይ ያለው ውኃ ላይ ዙፋኑን አዘጋጅቷል፦
መዝሙር 103፥19 ያህዌህ ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ። יְֽהוָ֗ה בַּ֭שָּׁמַיִם הֵכִ֣ין כִּסְאֹ֑ו
ኢሳይያስ 66፥1 ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው። כֹּ֚ה אָמַ֣ר יְהוָ֔ה הַשָּׁמַ֣יִם כִּסְאִ֔י

ከሰማያት በላይ ያለው ሰማይ ውኃ መሆኑን እና ይህም ሰማይ ዙፋኑ መሆኑን ካየን ዘንዳ አልምጥ እና አልግጥ ሆናችሁ "ዙፋኑ በውኃ ላይ ነበረ" የሚለውን ይዛችሁ መሳቅ እና መሳለቅ የራስ እያረረ የሰውን ማማሰል ነው። ስትሟገቱ ግራ እና ቀኝ ያማከል ውል ያለው ሙግት ተሟገቱ እንጂ ያልፋፋ እና ያልዳበረ አርቲ ቡርቲ ቶራ ቦራ ሙግት አትሟገቱ!
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እኛ ሙሥሊሞች ክርስቲያኖችን፦ ኢየሱስ "እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ" ያለበት ጥቅስ ስጡን ስንላቸው እነርሱ፦ "ኢየሱስ አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ" ብሏል ብለው ይመልሳሉ፥ እውን "አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ" የሚለው ማን ነው? ኢየሱስ ወይስ የኢየሱስ አምላክ? ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/U0JrbUdiW2Y?si=zh10yRilGdpxDPgb
ፋኑኤል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

22፥75 አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፥ ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል። አሏህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

"መለክ" مَلَك ወይም "መልአክ" مَلْأَك የሚለው ቃል "ለአከ" لَأَكَ ማለትም "ላከ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ተላላኪ" ማለት ነው፥ የመለክ ብዙ ቁጥር ደግሞ "መላኢክ" مَلَائِك‎ ወይም "መላኢካህ" مَلَائِكَة‎ ነው። መላኢካህ ሰማያውያን ፍጥረታት ሲሆኑ ከእነርሱ የአሏህን ትእዛዝ ለማስፈጸም ወደ ሰዎች ልጆች ለመላክ የሚመረጡ መላእክት አሉ፦
22፥75 አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፥ ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል። አሏህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

በቁርኣኑ እዚህ ድረስ ስለ መላእክት በግርድፉ ካየን ዘንዳ በባይብል ደግሞ ስለ መልአኩ ፋኑኤል እንመልከት!
"ፐኑኤል" פְנוּאֵל ማለት "የአምላክ ፊት" ሲሆን በአገራችን ቋንቋ "ፋኑኤል" ይሉታል። ፋኑኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው፦
ዳንኤል 10፥13 ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ። וְהִנֵּ֣ה מִֽיכָאֵ֗ל אַחַ֛ד הַשָּׂרִ֥ים הָרִאשֹׁנִ֖ים בָּ֣א לְעָזְרֵ֑נִי
ጦቢት 12፥15 "ከከበሩ ሰባት አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ" አላቸው።
ሄኖክ 10፥15 አራተኛውም የዘለዓለም ሕይወትን ለሚወርሱ ሰዎች ተስፋ በንስሓ ላይ የተሾመ "ፋኑኤል" ነው።

ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤል፣ ራጉኤል፣ ዑራኤል፣ ፋኑኤል፣ ሳቁኤል ናቸው። "የአምላክ ፊት" የሚል ትርጉም ያለው መልአክ "ፋኑኤል" ያዕቆብ ሲታገል የነበረው መልአክ ነው፦
ዘፍጥረት 32፥24 ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ "ሰውም" እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። וַיִּוָּתֵ֥ר יַעֲקֹ֖ב לְבַדֹּ֑ו וַיֵּאָבֵ֥ק אִישׁ֙ עִמֹּ֔ו עַ֖ד עֲלֹ֥ות הַשָּֽׁחַר׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል "ኢሽ" אִישׁ ሲሆን በነጠላ "ሰው" የተባለው መልአኩ እንደሆነ ቅቡል ነው፦
ሆሴዕ 12፥3 በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱ ጊዜ "ከ-"አምላክ ጋር ታገለ"።
ሆሴዕ 12፥4 "ከ-"መልአክ" ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም "ከእኛ ጋር ተነጋገረ"።

"ከእኛ ጋር ተነጋገረ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! "እኛ" በሚለው እኛነት ውስጥ "አናሺም" אֲנָשִׁ֖ים የተባሉት መላእክት የሚያካትት ነው፦
ዘፍጥረት 32፥28 ከአምላክ እና "ከ-"ሰዎች" ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና። אֱלֹהִ֛ים וְעִם־אֲנָשִׁ֖ים וַתּוּכָֽל׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "አናሺም" אֲנָשִׁ֖ים የሚለው ቃል የኢሽ ብዙ ቁጥር ሲሆን በብዜት "ሰዎች" ማለት ነው፥ በግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ "አንትሮፖን" ἀνθρώπων ማለት "ሰዎች" ማለት ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰዎች" የተባሉት ዐውደ ንባቡ ላይ የአምላክ መላእክት ናቸው፦
ዘፍጥረት 32፥1-2 ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፥ የአምላክ መላእክትም ተገናኙት። ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፦ “እነዚህ የአምላክ ሠራዊት ናቸው፡” አለ፤ የዚያንም ስፍራ ስም መሃናይም ብሎ ጠራው።

"የአምላክ መላእክት" "የአምላክ ሠራዊት" የሚለው ይሰመርበት! በመቀጠል ያዕቆብ እንዲህ አለ፦
ዘፍጥረት 32፥30 ያዕቆብም፦ “አምላክን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች” ሲል የዚያን ቦታ ስም "ፐኑኤል" ብሎ ጠራው። וַיִּקְרָ֧א יַעֲקֹ֛ב שֵׁ֥ם הַמָּקֹ֖ום פְּנִיאֵ֑ל כִּֽי־רָאִ֤יתִי אֱלֹהִים֙ פָּנִ֣ים אֶל־פָּנִ֔ים וַתִּנָּצֵ֖ל נַפְשִֽׁי׃

"ፐኑኤል" פְנוּאֵל ማለት "የአምላክ ፊት" ማለት ሲሆን ያዕቆብ መልአኩን ያየበት ቦታ "ፐኑኤል" ማለቱ በራሱ የታየው መልአክ "አምላክ" ስለተባለ ነው፥ "አምላክን ፊት ለፊት አየሁ" ሲል ፊት ለፊት ያየው የአምላክ ፊት የተባለውን ፋኑኤልን ነው። መላእክት "አምላክ" እንደሚባሉ እሙን እና ቅቡል ነው፦
መዝሙር 138፥1 "በአማልክትም" ፊት እዘምርልሃለሁ። אֹודְךָ֥ בְכָל־לִבִּ֑י נֶ֖גֶד אֱלֹהִ֣ים אֲזַמְּרֶֽךָּ׃
መዝሙር 8፥5 "ከአማልክትን" እጅግ ጥቂት አሳነስኸው"። וַתְּחַסְּרֵ֣הוּ מְּ֭עַט מֵאֱלֹהִ֑ים

በዕብራይስጥ "ኤሎሃህ" אלוהּ ማለት "አምላክ" ማለት ነው፥ የኤሎሃህ ብዜት ደግሞ "ኤሎሂም" אלהים ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው። መላእክት መልእክተኞች ሲሆኑ በመላእክት የአምላክ መታየት "አስተርዮተ አምላክ"theophany" ስለሆነ ሰዎች የያህዌን መልአክ ሲያዩ "አምላክን አይተናል" ይሉ ነበር፦
መሣፍንት 13፥21 ያን ጊዜም ማኑሄ "የያህዌህ መልአክ" መሆኑን አወቀ። אָ֚ז יָדַ֣ע מָנֹ֔וחַ כִּֽי־מַלְאַ֥ךְ יְהוָ֖ה הֽוּא׃
መሣፍንት 13፥22 ማኑሄም ሚስቱን፦ "አምላክን አይተናልና ሞት እንሞታለን" አላት። וַיֹּ֧אמֶר מָנֹ֛וחַ אֶל־אִשְׁתֹּ֖ו מֹ֣ות נָמ֑וּת כִּ֥י אֱלֹהִ֖ים רָאִֽינוּ׃

መላእክት ተጠሪነታቸው ለአምላክ ስለሆነ እና የአምላክ ቃል አቀባይ፣ አፈቀላጤ፣ እደራሴ፣ ልኡክ፣ ወኪል ስለሆኑ "አምላክ" መባላቸው ግብራዊ ስያሜ"functional term" እንጂ ባሕሪያዊ ስያሜ"ontological term" አይደለም። ባሕሪያዊ ስያሜ ያለውን የአንዱን አምላክ ፊት ግን ሰው ማየት አይቻለውም፦
ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ "ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም" አለ።

ፋኑኤል የሚባለው መልአክ "ማላህ ሀ ፐኒም" מלאך הפנים‎ ይባላል፥ "ማላህ ሀ ፐኒም" מלאך הפנים‎ ማለት "የፊቱ መልአክ" "መልአከ ገጹ" ማለት ነው፦
ኢሳይያስ 63፥9 በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ "የፊቱም መልአክ" አዳናቸው። בְּֽכָל־צָרָתָ֣ם ׀ [לֹא כ] (לֹ֣ו ק) צָ֗ר וּמַלְאַ֤ךְ פָּנָיו֙ הֹֽושִׁיעָ֔ם

ይህ መልአክ አምላክ የሚታይበት ስለሆነ "የአምላክ ፊት" "የፊቱ መልአክ" ተብሏል። በኩፋሌ ላይ በእስራኤል ሠራዊት ፊት የሚሄድ የፊቱ መልአክ "አምላካችን እግዚአብሔር እኛን እንዲህ አለን" ማለቱ በራሱ ሩፋኤል ፍጡር መልአክ መሆኑ በቂ ማሳያ ነው፦
ኩፋሌ 2፥1 በእስራኤል ሠራዊት ፊት የሚሄድ "የፊቱ መልአክ" የዘመኖች አከፋፈል የተጻፈበትን ጽላት ያዘ።
ኩፋሌ 10፥13 አምላካችን እግዚአብሔር እኛን እንዲህ አለን፥

በተረፈ ያዕቆብ ሲታገል የነበረው የአምላክ መልአክ "ኢየሱስ" ስለመሆኑ ምንም ዓይነት የዐውደ ንባብ፣ የተዛማች ጥቅስ፣ የአይሁድ ትውፊት ማስረጃ የለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢየሱስ የባሕርይ ልጅ አይደለም! በሚል ክፍል አንድ ትምህርት ተለቋል። ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/uMWBkbcbR64?si=GdAwgw3qxfr7OZfA

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
ኢየሱስ ፍጡር ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

19፥35 ለአሏህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ግሪካውያን "አምላክ አንድ ነው" ብለው ስለማያምኑ "እኛ የአምላክ ውልደት ነን" ብለው ያምናሉ፥ ለምሳሌ፦ ከ 315-310 ቅድመ ልደት ይኖር የነበረው ባለ ቅኔው አራተስ"Aratus" እራሱ ይህንን ይናገር ነበር፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥28 "ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ፦ "እኛ ደግሞ ውልደት ነንና" ብለው እንደ ተናገሩ። τινες τῶν καθ’ ὑμᾶς ποιητῶν εἰρήκασιν Τοῦ γὰρ καὶ γένος ἐσμέν.

"ጌኖስ" γένος ማለት "ውልደት" ማለት ሲሆን ጳውሎስ ከአራተስ ጠቅሶ "የአምላክ ውልደት ከሆንን" በማለት አጽድቆላቸዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥29 እንግዲህ የአምላክ ውልደት ከሆንን..። γένος οὖν ὑπάρχοντες τοῦ Θεοῦ
1ኛ ዮሐንስ 5፥1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከአምላክ "ተወልዶአል"። Πᾶς ὁ πιστεύων ὅτι Ἰησοῦς ἐστιν ὁ Χριστὸς ἐκ τοῦ Θεοῦ γεγέννηται,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተወልዶአል" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔሳንታ" γεννήσαντα ሲሆን ሥርወ ቃሉ በተመሳሳይ "ጌናኦ" γεννάω ነው፥ ኢየሱስ በጊዜ ውስጥ ለተወለደበት የሚጠቀምበት ቃል በተመሳሳይ ይህንን ነው፦
ዕብራውያን 1፥5  እኔ ዛሬ "ወልጄሃለሁ"። ἐγὼ σήμερον γεγέννηκά σε;

እዚህ አንቀጽ ላይ "ወልጄሃለሁ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ጌኔካ" γεγέννηκά ሲሆን ሥርወ ቃሉ በተመሳሳይ "ጌናኦ" γεννάω ነው። ኢየሱስ ከአምላክ ለተወለዱት "በኵር" ነው፦
ዕብራውያን 1፥6 ደግሞም "በኵርን" ወደ ዓለም ሲያገባ። ὅταν δὲ πάλιν εἰσαγάγῃ τὸν πρωτότοκον εἰς τὴν οἰκουμένην,
ሮሜ 8፥29 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል "በኵር" ይሆን ዘንድ፥ εἰς τὸ εἶναι αὐτὸν πρωτότοκον ἐν πολλοῖς ἀδελφοῖς·

"በኵር" ማለት "የመጀመሪያ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ የወንድሞቹ የኢዲስ ፍጥረት በኵር ስለሆነ የፍጥረት በኵር ተብሏል። ወንድሞቹ አዲስ ልደት ያገኙ አዲስ ፍጥረት ከሆኑ "ተወለዱ" ማለት "ተፈጠሩ" ማለት ነው፦
ቆላስይስ 1፥15 እርሱም የማይታይ አምላክ መልክ እና "የፍጥረት በኵር" ነው። ὅς ἐστιν εἰκὼν τοῦ Θεοῦ τοῦ ἀοράτου, πρωτότοκος πάσης κτίσεως,
2 ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን "አዲስ ፍጥረት" ነው። ὥστε εἴ τις ἐν Χριστῷ, καινὴ κτίσις·
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን "ለአዲስ ልደት" በሚሆነው መታጠብ እና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን። οὐκ ἐξ ἔργων τῶν ἐν δικαιοσύνῃ ἃ ἐποιήσαμεν ἡμεῖς ἀλλὰ κατὰ τὸ αὐτοῦ ἔλεος ἔσωσεν ἡμᾶς διὰ λουτροῦ παλινγενεσίας καὶ ἀνακαινώσεως Πνεύματος Ἁγίου,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልደት" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔሲስ" γένεσις ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "የሆነ" ማለት ነው፥ "ልደት" የሚለው ቃል "ፍጥረት" በሚል ተለዋዋጭ ቃል "አዲስ ፍጥረት" "አዲስ ልደት" በሚል መጥቷል። በተመሳሳይ "ዘፍጥረት" እራሱ "ዘልደት" ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 የሰማይ እና የምድር "ልደት" መጽሐፍ ይህ ነው። Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς,

"ጌኔሴኦስ" γενέσεως ማለት "ልደት" ማለት ሲሆን ዘፍጥረት በግዕዝ "ዘልደት" የሚባልበት ምክንያት ይህ ነው፥ "ዘ" ማለት "የ" ማለት ሲሆን "ዘ-"ፍጥረት" ማለት "የ-ፍጥረት" እንዲሁ "ዘ-"ልደት" ማለት "የ-ልደት" ማለት ነው። ሰማይ እና ምድር ደግሞ የተፈጠሩ እንጂ በእማሬአዊ የተወለዱ አይደሉም፥ ልደቱ በፍካሬአዊ ፍጥረቱን የሚያሳይ ከሆነ ኢየሱስ ሆነ ወንድሞቹ የተፈጠሩ እንጂ ቃል በቃል የተወለዱ አይደሉም። አምላክ ፆታ የለውም፥ አይባዛም አይከፋፈልም። ተራሮች የተፈጠሩ ቢሆንም በፍካሬአዊ እንደተወለዱ ይናገራል፦
አሞፅ 4፥13 እነሆ ተራሮችን "የሠራ"፥
መዝሙር 89(90)፥2 ተራሮች "ሳይወለዱ"፥ πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι