ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.5K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ፍች በኢሥላም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥2 *"ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ"*፡፡ فَإِذَا بَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ فَارِقُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَأَشْهِدُوا ذَوَيْ عَدْلٍ مِّنكُمْ وَأَقِيمُوا الشَّهَادَةَ لِلَّهِ

“ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው፥ “አሕካም” أَحْكَام‎ ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فَرْد‎ ማለትም “የታዘዘ” ግዴታ ነው።
2ኛ. “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ሡናህ ነው።
3ኛ. “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ ማለትም “የተፈቀደ” ሐላል ነው።
4ኛ. “መክሩህ” مَكْرُوه‎ ማለትም “የተጠላ” ነገር ነው።
5ኛ. “ሐራም” حَرَام ማለትም “የተከለከለ” ነገር ነው።

"ጦላቅ" طَّلَاق የሚለው ቃል "ጦሉቀ" طَلُقَ‎ ማለትም "ፈታ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፍች"divorce" ማለት ነው፥ "አጥ-ጦላቅ" الطَّلَاق ደግሞ ከአምስቱ አሕካም መክሩህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2096
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አሏህ ዘንድ የተጠላ ግን የተፈቀደው ፍች ነው"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ أَبْغَضُ الْحَلاَلِ إِلَى اللَّهِ الطَّلاَقُ

ጋብቻው ከጥቅሙ ጉዳቱ ካመዘነ ፍች የተጠላ ቢሆንም መፍትሔ ነው፥ ፍች ለማድረግ የተለያዩ ቅድመ-ሁኔታዎች አሉት። ለምሳሌ ፍች ለመፈጸም በተራክቦ ካልተነካኩ እና መህር ካልተወሰነ በማንኛውም ጊዜ መሆን ይችላል፦
2፥236 *"ሴቶችን ሳትነኳቸው ወይም ለእነርሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም"*፡፡ لَّا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن طَلَّقْتُمُ النِّسَاءَ مَا لَمْ تَمَسُّوهُنَّ أَوْ تَفْرِضُوا لَهُنَّ فَرِيضَةً

ነገር ግን ተራክቦ ከተፈጸመ ፍች የሚፈጸመው የዒዳህ ጊዜ ሲገባደድ ነው፥ "ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው፦
65፥1 *"አንተ ነቢዩ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ ለዒዳቸው ፍቱዋቸው! ዒዳንም ቁጠሩ፡፡ አላህንም ጌታችሁን ፍሩ"*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِذَا طَلَّقْتُمُ النِّسَاءَ فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ وَأَحْصُوا الْعِدَّةَ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ رَبَّكُمْ

"ፍቱዋቸው" ለሚለው የገባው ቃል "ጦለቁሁነ" طَلِّقُوهُنَّ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ ባል የማሰላሰያ ጊዜ አግኝቶ ከተጸጸተ በመልካም ሚስት አድርጎ መያዝ አለበት፥ አሊያም ጉዳይ ከበድ ያለ እና የማያዛልቅ ከሆነ በመልካም መለያየት ይቻላል፦
65፥2 *"ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ"*፡፡ فَإِذَا بَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ فَارِقُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَأَشْهِدُوا ذَوَيْ عَدْلٍ مِّنكُمْ وَأَقِيمُوا الشَّهَادَةَ لِلَّهِ

"በመልካም ተለያዩዋቸው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! በጦላቅ "በኑናህ" ጥንቃቄ የተሞላበት እሳቤ ነው። "በኑናህ" بَيْنُونَة ማለት "መለየት" ማለት ሲሆን በኑናህ "በኑናቱ አስ-ሱጊራ" እና "በኑናቱል ኩብራ" ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ።
"ሱግራ" صُغْرَى የሚለው ቃል "አስገር" أَصْغَر ለሚለው አንስታይ መደብ ሲሆን "ትንሽ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "በኑናቱ አስ-ሱግራ" بَيْنُونَة الصَغِيرَة ማለት "ትንሹ መለየት" ማለት ነው። ይህ ትንሹ ፍች የሚቻለው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው፥ ከዚህ በኋላ በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው፦
2፥229 *"ፍች ሁለት ጊዜ ነው፥ ከዚህ በኋላ በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው"*፡፡ الطَّلَاقُ مَرَّتَانِ ۖ فَإِمْسَاكٌ بِمَعْرُوفٍ أَوْ تَسْرِيحٌ بِإِحْسَانٍ

ጥንዶቹ ሁለት ጊዜ ከተፋቱ በኃላ ከመማለስ በኃላ ለሦስተኛ ጊዜ ከተፋቱ ይህ ፍች በኑናቱል ኩብራ ነው። "ኩብራ" كُبْرَى የሚለው ቃል "አክበር" أَكْبَر ለሚለው አንስታይ መደብ ሲሆን "ትልቅ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "በኑናቱል ኩብራ" بَيْنُونَة الكُبْرَى ማለት "ትልቁ መለየት" ማለት ነው፦
2፥230 *"ሦስተኛ ቢፈታትም ከዚህ በኋላ ሌላን ባል እስከምታገባ ድረስ ለእርሱ አትፈቀድለትም፡፡ ሁለተኛው ባል ቢፈታትም የአላህን ሕግጋት መጠበቃቸውን ቢያውቁ በመማለሳቸው በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለባቸውም"*፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት ለሚያውቁ ሕዝቦች ያብራራታል፡፡ فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا تَحِلُّ لَهُ مِن بَعْدُ حَتَّىٰ تَنكِحَ زَوْجًا غَيْرَهُ ۗ فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا أَن يَتَرَاجَعَا إِن ظَنَّا أَن يُقِيمَا حُدُودَ اللَّهِ ۗ وَتِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ يُبَيِّنُهَا لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

ጥንዶቹ ለሦስተኛ ጊዜ ከተፋቱ በኃላ ሌላ ማግባታቸው ሐላል ነው፥ በተቃራኒው ጥንዶቹ ለሦስተኛ ጊዜ ከተፋቱ በኃላ ከሁለት አንደኛው ሌላ አግብቶ እንካልፈታ ድረስ ተመልሶ መጋባት ሐራም ነው። ነገር ግን አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የበፊት የትዳር አጋር ተመልሶ ለማግባት ሲባል በውስጥ ፍችን ነይተው የኃለኛውን የትዳር አጋርን ማግባት እና መፍታት ከሐራምም አልፎ እርግማንም ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 2011
ዑቅባህ ኢብኑ ዓሚር እንደተረከው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስለ ቅንዝንዝ ፍየል አልነገርኳችሁንም? አሉ፥ እነርሱም፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ሆይ! አዎ አሉ። እርሳቸው፦ "ቅንዝንዝ ፍየል ሙሐሊል ነው፥ አሏህ ሙሐሊልን እና ሙሐለል ለሁ እረግሟል" አሉ"*። قَالَ عُقْبَةُ بْنُ عَامِرٍ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِالتَّيْسِ الْمُسْتَعَارِ ‏"‏ ‏.‏ قَالُوا بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ هُوَ الْمُحَلِّلُ لَعَنَ اللَّهُ الْمُحَلِّلَ وَالْمُحَلَّلَ لَهُ ‏"‏ ‏.‏
"ሙሐሊል" مُحَلِّل ማለት ሁለተኛ የትዳር አጋር ሆኖ ለመጀመሪያዋ የትዳር አጋር ሲል ለጊዜው አግብቶ ተራክቦ አድርጎ ለመጀመሪያዋ ሲል የሚፈታ ነው። በዚህም ቅንዝንዝ ፍየል ተብሏል፥ ቅንዝንዝ ፍየል ተራክቦ ያደረጋትን ሴት ፍየል ለሌላ ወንድ ፍየል ተራክቦ ማስደረግ ልማዱ ነው። "ሙሐለል ለሁ" مُحَلَّلَ لَهُ ማለት ደግሞ የመጀመሪያው የትዳር አጋር ሆኖ ሁለተኛ የትዳር አጋር ለጊዜው አግብቶ ተራክቦ አድርጎ እንዲሰጠው የሚጠባበቅ ነው፥ ከተጋቡ በኃላ ለፍች ምክንያት ከተፈጠረ መፋታቱ መክሩህ ቢሆንም ለጊዜው ተብሎ ተነይቶ ማግባት ግን ከድጡ ወደ ማጡ ስለሆነ ዝሙት ነው። ስለዚህ በትዳር፣ በፍቺ እና በመማለስ ቀልድ የለም፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 20
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ሦስቱ ነገራት የምር ይሁን የምር፥ የቀልድም ይሁን የምር ናቸው። እነርሱም ትዳር፣ ፍች እና መማለስ ናቸው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ ثَلاَثٌ جِدُّهُنَّ جِدٌّ وَهَزْلُهُنَّ جِدٌّ النِّكَاحُ وَالطَّلاَقُ وَالرَّجْعَةُ ‏"‏

"ረጅዓህ" رَّجْعَة ማለት "መማለስ" ማለት ሲሆን ከተፋቱ በኃላ እንደገና መጋባትን የሚያመላክት እሳቤ ነው፥ ትዳር ላይ በመልካም መኗኗር እንጂ ማጉላላት አያስልግም። ለአላስፈላጊ ነገር ፍች መጠየቅ መዘዙና ጠንቁ ብዙ ነው፦
4፥19 *"እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱ እና ግልጽን መጥፎ ሥራ ካልሠሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱ ልታጉላሏቸውም ለእናንተ አይፈቀድም፡፡ በመልካምም ተኗኗሩዋቸው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا النِّسَاءَ كَرْهًا ۖ وَلَا تَعْضُلُوهُنَّ لِتَذْهَبُوا بِبَعْضِ مَا آتَيْتُمُوهُنَّ إِلَّا أَن يَأْتِينَ بِفَاحِشَةٍ مُّبَيِّنَةٍ ۚ وَعَاشِرُوهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2134
ሰውባን እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ባሏን ለአላስፈላጊ ነገር ፍች የምትጠይቅ ማንኛውም ሴት የጀነት ሽታ በእርሷ ላይ እርም ነው"*። عَنْ ثَوْبَانَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ أَيُّمَا امْرَأَةٍ سَأَلَتْ زَوْجَهَا الطَّلاَقَ فِي غَيْرِ مَا بَأْسٍ فَحَرَامٌ عَلَيْهَا رَائِحَةُ الْجَنَّةِ ‏"‏

ፍች አሏህ ዘንድ የተጠላ ነው፥ "የተጠላ" ማለት "የማይመከር" ወይም "የማይበረታታ" ማለት ነው። ተስማምቶ መኖር ኃጢአት አይደለም፥ ከተጣሉም መታረቅም መልካም ነው፦
4፥128 *"ሴትም ከባልዋ ጥላቻን ወይም ፊቱን ማዞርን ብታውቅ በመካከላቸው መስማማትን ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኀጢአት የለም፡፡ መታረቅም መልካም ነው"*፡፡ وَإِنِ امْرَأَةٌ خَافَتْ مِن بَعْلِهَا نُشُوزًا أَوْ إِعْرَاضًا فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا أَن يُصْلِحَا بَيْنَهُمَا صُلْحًا ۚ وَالصُّلْحُ خَيْرٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 140
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"ሴትም ከባልዋ ጥላቻን ወይም ፊቱን ማዞርን ብታውቅ" የሚለው ባሏ ከእርሷ ጋር መቆየት ስለማይፈልጋት ሴት እና ግን ፈቶ ሌላ ማግባት ስለሚፈልግ የሚናገር ነው። እርሷም ለእርሱ፦ "ያዘኝ፣ አትፍታኝ፣ ከዚያም ሌላ አግባ። እናም ከእኔ ጋር አታሳልፍ! አትተኛ" አለች። ""ሴትም ከባልዋ ጥላቻን ወይም ፊቱን ማዞርን ብታውቅ በመካከላቸው መስማማትን ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኀጢአት የለም፡፡ መታረቅም መልካም ነው" የሚለውን አሏህ የተናገረው ይህንን ለማመላከት ነው"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ ‏{‏وَإِنِ امْرَأَةٌ خَافَتْ مِنْ بَعْلِهَا نُشُوزًا أَوْ إِعْرَاضًا‏}‏ قَالَتْ هِيَ الْمَرْأَةُ تَكُونُ عِنْدَ الرَّجُلِ، لاَ يَسْتَكْثِرُ مِنْهَا فَيُرِيدُ طَلاَقَهَا، وَيَتَزَوَّجُ غَيْرَهَا، تَقُولُ لَهُ أَمْسِكْنِي وَلاَ تُطَلِّقْنِي، ثُمَّ تَزَوَّجْ غَيْرِي، فَأَنْتَ فِي حِلٍّ مِنَ النَّفَقَةِ عَلَىَّ وَالْقِسْمَةِ لِي، فَذَلِكَ قَوْلُهُ تَعَالَى ‏{‏فَلاَ جُنَاحَ عَلَيْهِمَا أَنْ يَصَّالَحَا بَيْنَهُمَا صُلْحًا وَالصُّلْحُ خَيْرٌ‏}‏

"ቋድይ" قَضْي የሚለው ቃል "ቋዶ" قَضَى ማለትም "አመዛዘነ" "በየነ" "ፈረደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አመዛዝኖ የሚበይን ፈራጅ ወይም ዋቢ" ማለት ነው፥ "ቋዲያህ" قَضِيَّة‎ ማለት ደግሞ "የፍርድ ጉዳይ" ማለት ነው። ቋዲዮች በባል እና በሚስት መካከል ጭቅጭቅ ሲያውቁ ከቤተሰቦቹ ሽማግሌን ከቤተሰቦችዋም ሽማግሌን ይልካሉ፥ ዋቢዎች ማስታረቅን ቢፈልጉ አሏህ ያስማማል። ቋድይ ኢ-ፍትሐዊ እስካልሆነ ድረስ አሏህ ከእርሱ ጋር ነው፦
4፥35 *"እናንተ ዋቢዎች የመካከላቸውንም ጭቅጭቅ ብታውቁ ከቤተሰቦቹ ሽማግሌን ከቤተሰቦችዋም ሽማግሌን ላኩ፡፡ ማስታረቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማል"*፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነውና፡፡ وَإِنْ خِفْتُمْ شِقَاقَ بَيْنِهِمَا فَابْعَثُوا حَكَمًا مِّنْ أَهْلِهِ وَحَكَمًا مِّنْ أَهْلِهَا إِن يُرِيدَا إِصْلَاحًا يُوَفِّقِ اللَّهُ بَيْنَهُمَا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا خَبِيرًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 10
ዐብደሏህ ኢብኑ አቢ አል-አውፋ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ቋድይ ኢ-ፍትሐዊ እስካልሆነ ድረስ አሏህ ከእርሱ ጋር ነው። ኢ-ፍትሐዊ በሆነ ጊዜ ግን አሏህ ከእርሱ ጋር አይደለም፥ እርሱን ሸይጧን ይፈልገዋል"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي أَوْفَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الْقَاضِي مَا لَمْ يَجُرْ فَإِذَا جَارَ تَخَلَّى عَنْهُ وَلَزِمَهُ الشَّيْطَانُ ‏"‏ ‏.‏

አሏህ መልካም እና ያማረ ትዳር ይስጠን! ከተጠላ ፍች ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፍች በባይብል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥35 *"እናንተ ዋቢዎች የመካከላቸውንም ጭቅጭቅ ብታውቁ ከቤተሰቦቹ ሽማግሌን ከቤተሰቦችዋም ሽማግሌን ላኩ፡፡ ማስታረቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማል"*፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነውና፡፡ وَإِنْ خِفْتُمْ شِقَاقَ بَيْنِهِمَا فَابْعَثُوا حَكَمًا مِّنْ أَهْلِهِ وَحَكَمًا مِّنْ أَهْلِهَا إِن يُرِيدَا إِصْلَاحًا يُوَفِّقِ اللَّهُ بَيْنَهُمَا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا خَبِيرًا

በሙሴ ሕግ አንድ ወንድ አንድ ሴት መፍታት የሚችለው የፍችዋን ወረቀት በመስጠት ነው፦
ዘዳግም 24፥1 *ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ ”የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፥ ከቤቱም ይስደዳት”*።
ዘዳግም 24፥3 *"ሁለተኛውም ባል ቢጠላት፥ “የፍችዋንም ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ቢሰጣት”፥ ከቤቱም ቢሰድዳት፥ ወይም ሚስት አድርጎ ያገባት ሁለተኛው ባልዋ ቢሞት"*።

ነገር ግን በአዲስ ኪዳን አንድ ወንድ አንድ ሴት መፍታት የሚችለው ዝሙት ስትሠራ ብቻ ነው፦
ማቴዎስ 5፥31-32 *"ሚስቱን የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል"*።
ማቴዎስ 19:9 እኔ ግን እላችኋለሁ *"ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል አላቸው"*።

አንዲት ሴት በጠባይ አለመግባባት ቢኖር ወይም የፍቅር አለመጣጣም ቢኖር በዝሙት ካልሆነ መፈታት አትችልም። ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ አመንዝራ መባሉ ብቻ ሳይሆን የተፈታችው ሴት እርሱ በፈታት ሌላ ሰው እንዳያገባት እቀባ ተጥሎባታል፥ የተፈታች ሴት ሌላ ወንድ ካገባት አመንዝራ ይባላል። ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፥ “የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል አላቸው” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። እና ምን ትሆናለች? ሲባል ባልዋ እስኪሞት ድረስ ምንን ማግባት አትችልም፦
ሮሜ 7፥2-3 *"ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና”፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች። ”ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች”፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም"*።

ልብ አድርጉ “ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች” ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ሌላ ወንድ ማግባት ትችላለች። በተለይ የኢሥላምን ሕግ በምዕራባውያን ሚዛን ለሚመዝኑ ክርስቲያኖች ምን ይውጣቸው ይሆን? ዛሬስ በአገራችን ይህ የአዲስ ኪዳን ሕግ ይኖር ይሆን? ፍርድ ቤቱን ያጨናነቀው የክርስቲያኑን ፍቺ ያለ ዝሙት ነው። ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ኢየሱስ ባል ሚስቱ ያለ ዝሙት ምክንያት ከፈታ አመንዝራ ነው ሲል ጳውሎስ ደግሞ በተቃራኒው ሚስት ከባልዋ መለያየት ትችላለች ግን ሌላ ወንድ ሳታገባ ትኑር በማለት ይቃረናል፦
1ኛ ቆሮንቶስ 7፥10-11 *"ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ”ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር”*።

ሲጀመር ”ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር” ማለት “ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል” ከሚለው ጋር አይጋጭም? ሲቀጥል “ሳታገባ ትኑር” ፍትሐዊ ብይን ነውን? ሢሰልስ ” ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች” መባሉስ አግባብ ነውን? ጳውሎስን፦ "ይህንን ትምህርት በአንተ የሚናገረው ጌታ ነውን ወይስ እራስክ? ስንለው "እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም" ይለናል። ቀጥለን፦ "አንተስ ብትሆን የምትናገረው ጌታ ተናገር ብሎ አዞህ ነው ወይስ በሞኝነት? ስንለው አይ "የምናገረው በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም" ይለናል፦
1 ቆሮንቶስ 7፥12 *"ሌሎችንም እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም"*።
2 ቆሮንቶስ 11፥17 እንደዚህ ታምኜ ስመካ የምናገረው በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም።

ባሏ ከሞተስ? ትሉ ይሆናል፥ ባሏ ሲሞት ደግሞ መከራዋ አላለቀም። የባሏን ወንድም ታግባ የሚል ወፍራም ትእዛዝ ይጠብቃታል፦
ዘዳግም 25፥5-10 *"ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ “”የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ””፥ ከእርስዋም ጋር ይኑር። የምዋቹ ስም ከእስራኤል ዘንድ እንዳይጠፋ ከእርስዋ የሚወለደው በኵር ልጅ በሞተው በወንድሙ ስም ይጠራ። ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳይቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔ ጋር ሊኖርም አልወደደም ትበላቸው። የከተማውም ሽማግሌዎች ጠርተው ይጠይቁት፤ እርሱም በዚያ ቆሞ፦ አገባት ዘንድ አልወድድም ቢል፥ ዋርሳይቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል ስትል ጫማውን ከእግሩ ታውጣ፥ በፊቱም እንትፍ ትበልበት። በእስራኤልም ዘንድ ስሙ የጫማ ፈቱ ቤት ተብሎ ይጠራ*።

“ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ” ስሙ የጫማ ፈቱ ቤት ተብሎ ይጠራ እንጂ በግድ አግባ አይባልም። እርሷን ግን እርሷ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ ተብሎ ታዟል እንጂ እንደ ወንዱ የፈለገችውን ማግባት አትችልም። ይህ እኩልነት ነውን? ከዚያም አልፎ ሴቶች ምንም ባልሰሩት በባሎቻቸው ወንጀል ምክንያት ለሌላ ወንዶች ይሰጡ ነበር፦
ኤርሚያስ 8:10 ሰለዚህ *"ሚሰቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ"*።
2ኛ ሳሙኤል 12፥8 የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ *"የጌታህንም ሚስቶች” በብብትህ ጣልሁልህ"*።
2ኛ ሳሙኤል12፥11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ *”ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል"*።

እግር እራስን አያክም። በኢሥላም ያለውን የፍች እሳቤ ለመተቸት ቅድሚያ እነዚህ የባይብል አናቅጽ መልስ መስጠት ግድ ይላል እንጂ ሱሪ በአንገት ላድርግ አትበሉ። አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልጅት እናትን መደብደብ

በጥንት ጊዜ እመቤት ባሪያይቱን ትደበድባት ነበር። በመጨረሻው ዘመን ግን ልጅት እናትን መደብደብ ከሰዓቲቱ ምልክት አንዱ ነው፦
ዑመር ኢብኑ ኽጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ የመንገደኛነት ምልክት አይታይበትም ነበር፦ ወደ ነቢዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት አስጠግቶ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ስለ ሰዓቲቱ ንገረኝ" አላቸው፥ እርሳቸውም፦ "ስለ እርሷ ተጠያቂው እኮ ከጠያቂው የበለጠ ዐያውቅም" አሉ። እርሱም፦ "እሺ ስለ ምልክቶቿ ንገረኝ" አለ፥ እርሳቸውም፦ "ባሪያይቱ እመቤትዋን ስትወልድ እና ጫማ የሌላቸውን፣ የተራቆቱትን፣ ድሀና ችግረኛ እረኞችን በቤት ግንባታ ሲሽቀዳደሙህ ያየህ ጊዜ ነው"*። قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَجَاءَ رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَلْزَقَ رُكْبَتَهُ بِرُكْبَتِهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ أَخْبِرْنِي عَنْ السَّاعَةِ قَالَ مَا الْمَسْئُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ بِهَا مِنْ السَّائِلِ قَالَ فَأَخْبِرْنِي عَنْ أَمَارَاتِهَا قَالَ أَنْ تَلِدَ الْأَمَةُ رَبَّتَهَا وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبِنَاءِ

የነቢያችን"ﷺ" ትንቢት እየተፈጸመ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሴት ልጅ እናቷ ቤት ልክ እንደ እመቤት መጦሯ እና እናት ልጇን ቤት ውስጥ እየሠራች መካደሟ እሙንና ቅቡል ቢሆን በህንድ አገር አንዲት ልጅት እናቷን ደብድባ ከአልጋ ላይ ወርራታለች። ይህ እኩይ ድርጊት ያማል! አሏህ ከእንዲህ እኩይ ተግባር ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
መኪይ እና መደኒይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

24፥1 *”ይህች ያወረድናት እና የደነገግናት “ሡራህ” ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል”*፡፡ سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا

አምላካችን አላህ ቁርኣንን በሡራህ መከፋፈሉን ለማመልከት ብዙ አናቅጽ ላይ “ሡራህ” እያለ ይናገራል፦
24፥1 *”ይህች ያወረድናት እና የደነገግናት “ሡራህ” ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል”*፡፡ سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
9፥64 መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው *”ሡራህ” በእነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ*፡፡ يَحْذَرُ الْمُنَافِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيْهِمْ سُورَةٌ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِي قُلُوبِهِمْ

ስለዚህ የቁርኣን ሡራህ ሡራህ የተባለው ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ ነው። የሡራዎችን ቅድመ-ተከተል እና ስም ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በተናገሩት መሠረት የተቀመጠ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3366
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ለዑስማን ኢብኑ ዐፋን፦ “ሡረቱል አንፋልን ከመቶ በታች የሆነችበት፣ ሡረቱል በራኣህ(ተውባህ) ከመቶ በላይ የሆነችበት፣ በመካከላቸውም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ያልተጻፈበት(ሱረቱል በራኣህ) እና ባለ ሰባት አናቅጽ(ሡረቱል ፋቲሓህ) የሆችበት ምክንያታችሁ ምንድን ነው? አልኩኝ። ዑስማን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አንዳች የቁርኣን ክፍል በሚወርድላቸው ጊዜ ከጸሐፊዎቹ አንዱን በመጥራት፦ “ይህንን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት” ይሉ ነበር። አሁንም በድጋሚ የተወሰኑ የቁርኣን አንቀጾች ሲወርድላቸው፦ “እነዚህን አንቀጾች እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት” ይሉ ነበር”*። حَدَّثَنَا ابْنُ عَبَّاسٍ، قَالَ قُلْتُ لِعُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ مَا حَمَلَكُمْ أَنْ عَمَدْتُمْ، إِلَى الأَنْفَالِ وَهِيَ مِنَ الْمَثَانِي وَإِلَى بَرَاءَةَ وَهِيَ مِنَ الْمِئِينَ فَقَرَنْتُمْ بَيْنَهُمَا وَلَمْ تَكْتُبُوا بَيْنَهُمَا سَطْرَ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ وَوَضَعْتُمُوهُمَا فِي السَّبْعِ الطُّوَلِ مَا حَمَلَكُمْ عَلَى ذَلِكَ فَقَالَ عُثْمَانُ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِمَّا يَأْتِي عَلَيْهِ الزَّمَانُ وَهُوَ تَنْزِلُ عَلَيْهِ السُّوَرُ ذَوَاتُ الْعَدَدِ فَكَانَ إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ الشَّىْءُ دَعَا بَعْضَ مَنْ كَانَ يَكْتُبُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَؤُلاَءِ الآيَاتِ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا وَكَذَا وَإِذَا نَزَلَتْ عَلَيْهِ الآيَةُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَذِهِ الآيَةَ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا

ይህ ሐዲስ የሚያሳየው የሡራው ቅድመ-ተከተል እና እከሌ የሚለው ስም በአላህ ነቢይ የታዘዘ መሆኑን ነው። ከሦስት ሡራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሡራህ ስማቸው በውስጣቸው አለ፥ እነዚህም ስማቸው በውስጣቸው ያልተጠቀሱ ሦስት ሡራዎች ሡረቱል ፋቲሓህ፣ ሡረቱል አንቢያህ እና ሡረቱል ኢኽላስ ናቸው። እንደዛም ሆኖ የሡራህ ስያሜ ሶሓባዎች ከነቢያችን"ﷺ" የተማሩት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 45
ሠህል ኢብኑ ሠዒድ እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ለአንድ ሰው፦ "ከቁርኣን ማንኛውም ነገር አገኘህን? ብለው አሉት። ያም ሰው፦ "አዎ! እንዲህና እንዲያ የሚል ሡራህ፣ እንዲህና እንዲያ የሚል ሡራህ እና የሡራህ ስያሜ" አለ"*። عَنْ سَهْلِ بْنِ سَعْدٍ، قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لِرَجُلٍ ‏ "‏ أَمَعَكَ مِنَ الْقُرْآنِ شَىْءٌ ‏"‌‏.‏ قَالَ نَعَمْ سُورَةُ كَذَا وَسُورَةُ كَذَا‏.‏ لِسُوَرٍ سَمَّاهَا‏.‏

ነቢያችን”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ሡራህ መውረድ ጀምሮ እስከ 63 ዓመታቸው ድረስ ቀስ በቀስ በሒደት 114 ሡራዎች ወርደውላቸዋል፥ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ወሕይ ተቀብለው በ 63 ዓመታቸው ሞተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 128
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ወሕይ መቀበል ጀመሩ፥ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ቆይተው በ 63 ዓመታቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ بُعِثَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَرْبَعِينَ سَنَةً، فَمَكُثَ بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ سَنَةً يُوحَى إِلَيْهِ، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ فَهَاجَرَ عَشْرَ سِنِينَ، وَمَاتَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ‏.‏
ሡራዎች ወደ ነቢያችን”ﷺ” ልብ በጨረቃ አቆጣጠር ከ 610 ድኅረ-ልደት እስከ 632 ድኅረ-ልደት ለ 23 ዓመት ቀስ በቀስ ወረዱ፥ ለ 13 ዓመት 86 ሡራዎች በመካ የወረዱ ሲሆኑ ለ 10 ዓመት ደግሞ 28 ሡራዎች የወረዱት በመዲና ነው። በዚህም በመካ የወረደች ሡራህ "መኪይ" مَكِّيّ ማለት "መካዊ" ስትባል በመካ የወረዱት 86 ሡራዎች ደግሞ "መኪዩን" مَكِّيُّون‎ ይባላሉ፥ በመዲና የወረደች ሡራህ "መደኒይ" مَدَنِيّ ማለት "መዲዊ" ስትባል በመዲና የወረዱት 28 ሡራዎች ደግሞ "መደኒዩን" مَدَنِيُّون ይባላሉ። ሡራዎች በመካ ይሁን በመዲና የት እንደወረዱ የተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦች ስለሚያውቁ መኪይ እና መደኒይ በማለት ሰይመዋቸዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 24
ዐብደሏህ አብኑ መሥዑድ"ረ.ዐ." እንደተናገረው፦ *"ወሏሂ! ከአሏህ በቀር አምላክ የለም፥ በአሏህ መጽሐፍ ምንም ሡራህ አይወርድ እኔ የት ቦታ እንደወረደች ባውቃት እንጂ"*። قَالَ قَالَ عَبْدُ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ وَاللَّهِ الَّذِي لاَ إِلَهَ غَيْرُهُ مَا أُنْزِلَتْ سُورَةٌ مِنْ كِتَابِ اللَّهِ إِلاَّ أَنَا أَعْلَمُ أَيْنَ أُنْزِلَتْ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4, ሐዲስ 65
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ከቁርኣን ሡራህ እንደሚያስተምሩን አት-ተሸሁድ ያስተምሩን ነበር"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُعَلِّمُنَا التَّشَهُّدَ كَمَا يُعَلِّمُنَا السُّورَةَ مِنَ الْقُرْآنِ ‏.‏

"አይነ" أَيْنَ ማለትም "የት" የሚለው መጠይቅ ቦታን ያማከለ ነው፥ እንዚህ ቦታዎች መካ እና መዲና ናቸው። አንዲት ሡራህ መኪይ ወይም መደኒይ የሚያሰኛት በውስጧ የያዘችው አናቅጽ አብዛኛው መኪይ ወይም መደኒይ ስለሆነች እንጂ በመኪይ ሡራህ ውስጥ መደኒይ አንቀጽ እንዲሁ በመደኒይ ሡራህ ውስጥ መኪይ አንቀጽ ሊገኝ ይችላል። ለምሳሌ ሡረቱል አንፋል መደኒይ ሲሆን በውስጡ መኪይ አንቀጽ ይዟል፥ እንዲሁ ሡረቱል አንዓም መኪይ ሲሆን በውስጡ መደኒይ አንቀጽ ይህንን ይዟል፦
8፥64 አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ በቂህ ነው፡፡ ለተከተሉህም ምእምናን አላህ በቂያቸው ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ حَسْبُكَ اللَّهُ وَمَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ
6፥153 *"ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ" በል"*፡፡ وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

ስለ ሡረቱል መኪይ እና ስለ ሱረቱል መደኒይ በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል! “አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሸሪዓዊ መንግሥት ይመጣል!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥81 በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና» وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقً

እውነት ሲመጣ ውሸት ተወጋጅ ነው፥ በዓለም ላይ ያለው የኢሉሚናቲ እሳቤ ባጢል ነው። ሸሪዓዊ መንግሥት ሲመጣ ባጢሉ ኢሉሚናቲ እሳቤ ይወገዳል። ሸሪዓዊ መንግሥት በዓለም ላይ እንደሚመጣ ደግሞ በነቢያችን"ﷺ" ተነግሯል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 14, ሐዲስ 163
ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ነብይነት አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በነቢይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ይጀመርና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም ዘውዳዊ ንግሥና ቦታውን ይይዝና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም የአንባገነን ንግሥና ይነሳልና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በስተመጨረሻም በነቢይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ከእንደገና ይመጣል*። فَقَالَ حُذَيْفَةُ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ – صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ -: « تَكُونُ النُّبُوَّةُ فِيكُمْ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةٌ عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا عَاضًّا فَيَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا جَبْرِيَّةً فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةً عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ

ምነው ፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች፦ "ርኆቦት እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን" ሲሉ ወይም "በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከካሉ" ሲሉ ወንጀል ካልሆነ፦
ዘፍጥረት 26፥22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርስዋም አልተጣሉም፤ ስምዋንም ርኆቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።
ፊልጵስዩስ 2፥10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥

እኛም እንደ እምነታችን "ሸሪዓዊ መንግሥት ይመጣል!" ብለን ማመናችን ወንጀል አይደለም። ሁሌ አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር እሥልምናን የሚነኩት ውስጣቸው ሐቅ ስለሌለ እና በባጢል ስለተበተቡ ነው። በቴኦክራሲ ሥርዓት ውስጥ ሕገ-መንግሥቱ የአምላክ ንግግር ነው። ዲሞክራሲ ማለት ነጻነት ማለት ሳይሆን የኢሉሚናቲ መጫረቻና መጫወቻ ልቅነት ነው፥ ሥልጣኔ በምጣኔ አውንታዊ ነገር ሆኖ ሳለ የኢሉሚናቲ ዲሞክራሲ መሠልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው። ሸሪዓዊ መንግሥት ይመጣል! አትሸማቀቅ!
ደውለቱ አሽ-ሸሪዓህ ባቂያህ!

አላህ በቴኦክራሲ የሚመራውን ሸሪዓዊ መንግሥት በማምጣት ነስሩን ያቅርብልን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነፍስ መግደል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥33 *”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው። “ቂሷስ” قِصَاص የሚለው ቃል “ቋሶ” قَاصَّ ማለትም “አመሳሰለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመሳሰል” ማለት ነው፥ በቂሷስ ነፍስ ያጠፋ ነፍሱ ይጠፋል፣ ዓይን ያጠፋ ዓይኑ ይጠፋል፣ አፍንጫም ያጠፋ አፍንጫው ይጠፋል፣ ጆሮም ያጠፋ ጆሮው ይጠፋል፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ ይሰበራል። እነዚህ ቁስሎችን በቂሷስ ይፈታሉ፦
5፥45 *”በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ «ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፥ ቁስሎችንም “ማመሳሰል” አለባቸው» ማለትን ጻፍን*፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ “ማመሳሰል” ለሚለው ቃል የገባው “ቂሷስ” قِصَاص መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። መጥፎ ለሠሩ ሠዎች መጥፎ ቅጣት መቅጣት ቂሷስ ነው፥ የአሏህ መጽሐፍ ጭብጡ ቂሷስ ነው፦
42፥40 *የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም*፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 26
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የአሏህ መጽሐፍ ቂሷስ ነው”*። أَنَّ أَنَسًا، حَدَّثَهُمْ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كِتَابُ اللَّهِ الْقِصَاصُ ‏”‌‏.‏

ከዚህ ሕግ ውጪ ነፍስን መግደል አሏህ እርም አድርጓል፥ ያለ ቂሷስ ነፍስን መግደል ሐራም እና ከዐበይት ኃጢአቶች አንዱ ነው፦
17፥33 *”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏”‌‏.‏

“እርም ያረጋት” ለሚለው የገባው ቃል “ሐረመ” حَرَّمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ሐረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተከለከለ” ማለት ነው፥ እንደውም ያለጥፋት አንድን ሰው መግደል ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው፦
5፥32 *”በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፥ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው”* ማለትን ጻፍን፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا
ከዚህ ውጪ ወሰን ታልፎባቸው ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *”ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው”*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

አንቀጹ ይቀጥልና ሲበደሉ በቂሷስ ፍትሕ የሚያስተካክሉ አካላት ከሌሉ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም ይፈርሳሉ፦
22፥40 ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ፡፡ *”አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር*”፡፡ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

ስለዚህ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና መስጊዶች ማፍረስ ወሰን ማለፍ ነው። “አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። አንደኛው በሌላኛ ፍትሕ ለማስከበር መገፍተሩ ማለትም መጋደል ከሌለ ወሰን አላፊዎች ምድሩቱን ያበላሻሉ። በቂሷስ እነዚያንም ወሰን አላፊዎች በአላህ መንገድ ተጋደሉ! ወሰንንም አትለፉ! አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

የአልረሕማንም ባሮች ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ቂሷስ ሕግ የማይገድሉ ናቸው፥ ነገር ግን ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ቂሷስ ሕግ በመግደል ይህንንም የሚሠራ ሰው ከዱንያ ፍርድ ቢያመልጥ በአኺራ ከአሏህ ቅጣትን ያገኛል፦
25፥68 *”እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል”*፡፡ وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኡሱሉ_ሰላሳ_በኡስታዝ_አቡሀይደር_ያለ_ኔት_ከአማርኛ_ትርጉም_ጋር.apk
57.5 MB
በቃሌ መሰረት #ኡሱሉ_ሱላሳ በኡስታዝ #አቡሀይደር ያለኔት
ከአማርኛ የፅሁፍ ትርጉም ጋር
ከአረብኛ የመትን ፅሁፍ ጋር ይህንን ቀስት ተጭናችሁ አውርዱ

በሁሉም ግሩፕ #ሼርርርርር አድርጉት
🌺🌺🌺
ለምርጥ ምርጥ አፖች
t.me/ISLAMICBOOKSANDAPPS

ወይም

t.me/hussenapp
👆የኡስታዝ አቡ ሐይደር የኡስሉ ሰላሳ ትምህርቶች በአጠቃላይ በኦዲዮ መልኩ አፕልኬሽኑ ላይ ይገኛል። ዳውንሎድ አድርጋችሁ አሰራጩት
ሃሩት እና ማሩት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥102 *”ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩት እና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በእርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ”*፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ

ሰማያውያን ፍጥረታት መላእክት እንደ ጂን እና እንደ ሰው የራሳቸው ሁለት የተለያየ ነጻ ምርጫ የላቸውም። ይህ ክፉን እና ደግ የመምረጥ ነጻ ምርጫ ስለሌላቸው በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም፦
16፥49 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ *”መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም”*፡፡ وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِن دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ *”እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም”*፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አሉ፡፡ *”አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ”*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

መላእክት አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ። እዚህ ድረስ ከተግባባን የሚቀጥለውን አንቀጽ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንይ! በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደው የሲሕር ትምህርት ሰዎችን እንዴት እንደሚጎዳ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ነው። ነገር ግን ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት ሰዎችን የሚያስተምሩት ለአሉታዊ ነገር ነበር፦
2፥102 *”ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩት እና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በእርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ”*፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሃሩትና ማሩት” እንዳመጹ የሚያሳይ ኃይለ-ቃል ወይም ፍንጭ ሽታው የለም። ምናልባት፦ “እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም” የተባለው ስለ ሃሩትና ማሩት መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኃል፦
2፥102 *”እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፥ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ”*፡፡ وَمَاوَمَا هُم بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُم
ምክንያቱም ሃሩትና ማሩት ሁለት ስለሆኑ ለእነርሱ የምንጠቀምበት ተውላጠ-ስም በሙተና “ሁማ” هُمَا ነው፥ ነገር ግን “በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም” የተባሉትን ላይ “እነርሱም” ለሚለው የገባው “ሁም” هُم ሲሆን ከሁለት በላይ ጀመዕ መሆኑ “ሸያጢን” شَّيَٰطِين የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። ሸያጢን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፥ ሰዎች ከሸያጢን የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ።
ሲጀመር እዚህ አንቀጽ ላይ “ወ” وَ የሚለው መስተጻምር ሕዝብን ሲሕር የሚያስተምሩት ሸያጢን እና ሀሩትና ማሩትን የሚያስጠነቅቁበትን ትምህርት ለመለየት የገባ መስተፃምር ነው። ከመነሻው ሸያጢን የሚያስተምሩት ድግምት እና ለሀሩትና ማሩት ተወረደ የተባለው ነገር ሁለት ለየቅል የሆኑ ሀረግ መሆናቸው ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ሃሩትና ማሩት፦ “እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ” እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፥ እነርሱ ላይ የተወረደው ስለ ሲሕር አውንታዊነት ሳይሆን አሉታዊነት የሚያስረዳ ትምህርት ነው።

ሲቀጥል “ማ” مَا የሚለው ቃል ሁለት ፍቺ ይኖረዋል፤ አንዱ “ማ” مَا “መውሱላ” ሲሆን ሁለተኛው “ማ” مَا “መስደሪያ” ነው።
1ኛ. “ማ” مَا የሚለውን “መውሱላ” ማለትም “አንፃራዊ ተውላጠ-ስም” ሆኖ ከተቀራ በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደ ነገር እንዳለ ያመለክታል፥ ያ ነገር ግን ከላይ ባየነው የሰዋስም ሙግት ከሸያጢን ሲሕር ተለይቶ በመስተፃምር ተቀምጧል።
2ኛ. “ማ” مَا የሚለው መስደሪያ ማለት “አፍራሽ-ቃል” በሚለው ከተቀራ ደግሞ በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የሸያጢን ሲሕር አልተወረደም የሚል ፍቺ ይኖረዋል። ምክንያቱም አይሁዳውያን ሚድራሽ በሚባለው መፅሐፋቸው ላይ፦ “ሲሕር በሁለቱ መላእክት በኩል ባቢሎን ላይ ከፈጣሪ የተወረደ ነው” የሚሉትን ቅጥፈት አላህ እያጋለጣቸው ነው። ምክንያቱም አይሁዳውያን አስማት የሰለሞን ጥበብ ነው የሚል እምነት አላቸው፤ ይህንን እሳቤ አንዳንድ ዐበይት ክርስትና በትውፊት ይጋሩታል። ይህንን ነጥብ ኢብኑ ዐባሥ፣ ኢብኑ ጀሪር፣ ቁርጡቢ ያነሱታል።

ሢሰልስ “ሀሩትና ማሩት” ማንና ምን ናቸው? የሚለውን ነጥብ ሁለት አመለካከቶች አሉት፤ ይህንም ጤናማ የተለያየ አመለካከት ያመጣው ጤናማው የቂርኣት ውበት ነው፥ “መለከይኒ” مَلَكَيْنِ የሚለው ቃል ”መለክ” مَلَك ማለትም ”መልአክ” ለሚለው ቃል ሙተና”dual” ሲሆን “ሁለት መላእክት” የሚል ፍቺ የሚኖረው “ላምን”ل ላም ፈትሓ “ለ” لَ ተብሎ ሲቀራ ነው። ሌላው “መሊከይኒ” مَلِكَيْنِ የሚለው ቃል “መሊክ” مَلِك ማለትም “ንጉሥ” ቃል ሙተና ሲሆን “ሁለት ነገሥታት” የሚል ፍቺ “ላምን” ل ላም ከስራ “ሊ” لِ ተብሎ ሲቀራ ነው። ሁለቱም ቂርኣት ከመለኮት የተወረደ እስከሆነ ድረስ በሁለቱም መቅራት ይቻላል። ይህ ነጥብ በጀላለይን፣ በአጥ-ጠበሪ፣ በዛማኽሻሪ፣ በባጋዊ እና በራዚ ተወስቷል። የውይይታችን ዋናውና ተቀዳሚው ሙግት ሀሩትና ማሩት ማንና ምን ናቸው? ሳይሆን "መላእክት በፍጹም አምጸው አያውቁም" የሚል ነው።

ከዐቃቤ እስስልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የንጽጽር ትምህርት ያለ የኢንተርኔት ማንበብ ለምትፈልጉ ይህንን አፕ ያውርዱ፦
https://www.mediafire.com/file/pzlrw8mhc8rcgwc/Ustaz_Wahid.apk/file
የሴት ስብራት

ሴት ከጎንህ የተፈጠረች አጥንት ናት፥ በደግነት ካልያስካት ትሰበራለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 17, ሐዲስ 80″
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንም በአሏህ እና በመጨረሻ ቀን የሚያምን በምንም ነገር ሲመሰክር መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል! ሴትን በደግነት ተንከባከቡ! ሴት የተፈጠረችው ከጎን አጥንት ነውና"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَإِذَا شَهِدَ أَمْرًا فَلْيَتَكَلَّمْ بِخَيْرٍ أَوْ لِيَسْكُتْ وَاسْتَوْصُوا بِالنِّسَاءِ فَإِنَّ الْمَرْأَةَ خُلِقَتْ مِنْ ضِلَعٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 138
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"እርስ በእርሳችሁ አትጠላሉ፣ እርስ በእርሳችሁ አትነቃቀፉ፣ የአላህ ባሮች ወንድማማች ሁኑ። ሙሥሊም ወንድሙን ከሦስት ሌሊት በላይ ማኩረፍ አይፈቀድም"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَبَاغَضُوا وَلاَ تَحَاسَدُوا وَلاَ تَدَابَرُوا وَكُونُوا عِبَادَ اللَّهِ إِخْوَانًا وَلاَ يَحِلُّ لِمُسْلِمٍ أَنْ يَهْجُرَ أَخَاهُ فَوْقَ ثَلاَثِ لَيَال

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 93
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አንድ ባሪያ የሌላውን ባሪያ ነውር በዚህ ዓለም የደበቀለት አላህ የትንሳኤ ቀን ነውሩን ይደብቅለታል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ يَسْتُرُ عَبْدٌ عَبْدًا فِي الدُّنْيَا إِلاَّ سَتَرَهُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَة

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 51
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የአንድ ሰው እሥልምናው ማማሩ ምልክት የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مِنْ حُسْنِ إِسْلاَمِ الْمَرْءِ تَرْكُهُ مَا لاَ يَعْنِيهِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَسْكُتْ ‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom