ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ይህ የሚሆነው ሰላም ሆኖ ሁከት እስከሚጠፋ ድረስ እና ሃይማኖት ለአላህ እስከሚሆን ድረስ ነው። “እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ” እስከ መቼ? “ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ” እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ወሰን አልፎ በሚመጣው ላይ ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

መጋደል ከሌለ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም ይፈርሳሉ፦
22፥40 *ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ፡፡ አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም፤ በተፈረሱ ነበር*፡፡ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

በአላህ መንገድ ከጠላት ጋር የሚደረግ ጂሃድ ሦስት አይነት ነው፥ እርሱም በእጅ የሚደረግ፣ በምላስ የሚደረግ እና በልብ የሚደረግ ነው፦
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ *“ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”*። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ “‏من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان

ሡናውን የሚይዙ እና በትእዛዙ የሚመሩ ቀደምት ሠለፎች ጂሃድን መንሃጃቸው አርገው አልፈዋል፥ የሚያሳዝነው ዛሬ ያለነው "ከእነርሱ በኃላ የማያደርጉትን የሚናገሩ እና ያልታዘዙትን የሚያደርጉ ተተኪዎች ይመጣሉ" የተባልነው ትውልድ ነን፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 86
ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ከእኔ ሕዝብ በፊት ከነቢይ አንድንም አላከም፥ ሡናውን የሚይዙ እና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያት እና ባልደረቦች ከሕዝቡ ቢያደርግለት እንጂ። ከዚያም ከእነርሱ በኃላ የማያደርጉትን የሚናገሩ እና ያልታዘዙትን የሚያደርጉ ተተኪዎች ይመጣሉ። እነርሱን በእጁ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው፣ በምላሱ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው፣ በልቡ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። ከዚህ ውጪ የጎመንዘር ያህል ኢማን የለም"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏ "‏ مَا مِنْ نَبِيٍّ بَعَثَهُ اللَّهُ فِي أُمَّةٍ قَبْلِي إِلاَّ كَانَ لَهُ مِنْ أُمَّتِهِ حَوَارِيُّونَ وَأَصْحَابٌ يَأْخُذُونَ بِسُنَّتِهِ وَيَقْتَدُونَ بِأَمْرِهِ ثُمَّ إِنَّهَا تَخْلُفُ مِنْ بَعْدِهِمْ خُلُوفٌ يَقُولُونَ مَا لاَ يَفْعَلُونَ وَيَفْعَلُونَ مَا لاَ يُؤْمَرُونَ فَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِيَدِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِلِسَانِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِقَلْبِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَلَيْسَ وَرَاءَ ذَلِكَ مِنَ الإِيمَانِ حَبَّةُ خَرْدَلٍ ‏

በእጅ፣ በምላስ እና በልቡ ያልታገለ የጎመንዘር ያህል ኢማን የለውም። ምእምናን ማለት በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፥ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው። አላህ እኛን ውርደት ያከናነበን ከጂሃድ በመራቃችን ነው፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 47
ኢብኑ ዑመር"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሪባ በተገበያያቹህ ጊዜ፣ ከብቶችን በተከትላችሁ ጊዜ፣ እርሻኝ በወዳዳቹህ ጊዜ እና ጂሃድን በተዋቹህ ጊዜ አላህ ውርደት ያከናንባችኃል፥ ይህንንም ውርደት ወደ ዲናቹህ እስካልተመለሳቹህ ድረስ ከእናንተ አያነሳም"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ إِذَا تَبَايَعْتُمْ بِالْعِينَةِ وَأَخَذْتُمْ أَذْنَابَ الْبَقَرِ وَرَضِيتُمْ بِالزَّرْعِ وَتَرَكْتُمُ الْجِهَادَ سَلَّطَ اللَّهُ عَلَيْكُمْ ذُلاًّ لاَ يَنْزِعُهُ حَتَّى تَرْجِعُوا إِلَى دِينِكُمْ

መሣጂዶች ሲፈርሱና ሲቃጠሉ በእጃችን ካተከላከልን ወይም በምላሳችን ካልተቃወምን አሊያም በልባችን ጉዳዩን ካልጠላን የእኛ ዲነኛ መሆን ፋይዳው ምኑ ላይ ነው? አላህ በእርሱን መንገድ የሚታገሉ ሙጃሂድ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቅድስት ሥላሴ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

አምላካችን አላህ በቁርኣን ከተገለጹት ስሞቹ አንዱ "አል-ቁዱሥ" الْقُدُّوس ሲሆን ትርጉሙ "ቅዱሱ" ወይም "ከጉድለት ሁሉ የጠራው" ማለት ነው፦
59፥23 እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፣ *ቅዱሱ*፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኀያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ
62፥1 በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ *ቅዱስ*፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ለኾነው ያሞግሳል፡፡ يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ الْمَلِكِ الْقُدُّوسِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ

በባይብልም ከሄድን አንዱ አምላክ "ቅዱስ" ተብሏል፥ እንደ እርሱ ያለ ቅዱስ የለም፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥2 *“እንደ ያህዌህ ቅዱስ የለምና”፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ “ከአንተ በቀር ቅዱስ” የለም*።
ራእይ 15፥4 *“አንተ ብቻ ቅዱስ” ነህና*፥

“አንተ” የሚለው ነጠላ ተውላጠ-ስም አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ ቅዱስ እንደተባለ ፍትውና ቁልጭ አድርጎ ያስረዳል፥ ሶስት ማንነትቶች ቢሆኑ ኖሮ “እናንተ” ተብሎ ይቀመጥ ነበር። “ከእናንተ” በቀር ቅዱስ የለም” ቢል ኖሮ ለሶስት አካላት ያዋጣ ነበር፥ ቅሉ ግን "አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ" ተብሏል። እርሱ ቅዱስ የተባለው ፍጡራን በተባሉበት ስሌትና ቀመር አይደለም፥ ለምሳሌ ሰው እና መላእክት ቅዱሳን ተብለዋል፦
ዘሌዋውያን 11፥45 *እንግዲህ “እኔ ቅዱስ ነኝ እና እናንተ ቅዱሳን”* ሁኑ።
ኢዮብ 15፥15 እነሆ፥ *በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም*፤ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።

"ቅዱስ" ነጠላ ተባዕታይ መደብ ሲሆን የቅዱስ ብዙ ቁጥር "ቅዱሳን" ነው። የሥላሴ አማንያን"Trinitarian"፦ "መላእክት አንዱን አምላክ ሦስት ጊዜ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ” ማለታቸው ሦስት አካላት እንዳሉ ማሳያ ነው" የሚል ስሁት ሙግት አላቸው፦
ኢሳይያስ 6፥3 አንዱም ለአንዱ፦ *“ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥” የሠራዊት ጌታ ያህዌህ፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር*።
ራእይ 4፥8 *“ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ” የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም*።

ይህ ሙግት ውኃ የማያነሳ እና የማይቋጥር ሙግት ነው። ምክንያቱም አንድ ነገር ሦስት ጊዜ መጠቀሱ ያንን ነገር ሦስት ካደረገው ኤርሚያስ ምድርን ሦስት ጊዜ “ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ” ብሎ ጠርቷል፦
ኤርምያስ 22፥29 *“ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ”*፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ።

ምድር ሦስት ጊዜ መጠራቷ ምድር ሦስት አካላት ናት ያሰኛልን? በተጨማሪ ኤርሚያስ የእግዚአብሔርን መቅደስ ሦስት ጊዜ “የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ” ብሎ ጠርቷል፦
ኤርሚያስ 7፥4 *የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ ይህ ነው እያላችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ*።

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስት ጊዜ መጠራቱ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስት አካላት ነው ያሰኛልን? ሌላ ናሙና የይሁዳ ምድር ባድማ እንደሚያደርጋት ሦስት ጊዜ ተናግሯል፦
ሕዝቅኤል 21፥27 *ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደርጋታለሁ*።

ባድማ እንደሚያደርግ ሦስት ጊዜ መናገሩ ሦስት ጊዜ ማድረጉን ያሰኛልን? መጽሐፈ ኩፋሌ የሚባለው የኦርቶዶክስ የቀኖና መጽሐፍ ላይ ደግሞ አብርሃምን ሦስት ጊዜ አብርሃም፥ አብርሃም፥ አብርሃም” ይለዋል፦
ኩፋሌ 14፥5 “እግዚአብሔርም *አብርሃምን፥ “አብርሃም፥ አብርሃም፥ አብርሃም” ብሎ ጠራው፥ አብርሃምም “አቤት አለሁ”አለ*።

አብርሃም ሦስት ጊዜ መጠራቱ አብርሃም ሦስት አካላት ነው ያሰኛልን? መልክአ ኢየሱስ የሚባለው የኦርቶዶክስ መጽሐፍ ላይ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ “ኢየሱስ፥ ኢየሱስ፥ ኢየሱስ" ይለዋል፦
*“ኢየሱስ ኢየሱስ፥ ኢየሱስ”* ክርስቶስ ዘሰረጽከ እመቤተ ሌዊ ኮሬባዊ መለኮታዊ ቃል ሰማያዊ እም ድንግል ተወለደ።

ኢየሱስ የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ መደገሙ ከድንግል የተወለደው ኢየሱስ ሦስት አካላት ነውን? ዘፍጥረት ላይ ደግሞ አብርሃም ሁለቴ ስሙ ተደግሟል፦
ዘፍጥረት 22፥11የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና። *“አብርሃም፥ አብርሃም”* አለው።
አብርሃም ሁለት አካል ነውን? ኢየሱስን ሁለት ጊዜ “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” ይሉታል፦
ማቴዎስ 7፥21 *“ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ”* የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።

ኢየሱስ ሁለት አካል ነውን? ሙሴ ሁለት ጊዜ “ሙሴ ሙሴ፥ ሙሴ ሙሴ” ተብሏል፦
ዘጽአት 3፥4 “እግዚአብሔር ከቁጥቋጦው ውስጥ እርሱን ጠርቶ፦ *ሙሴ፥ ሙሴ ሆይ አለ*።

ሙሴ ሁለት አካል ነውን? እንዳትሰክሩ ብለን እንጂ ማስረጃ በቁና ሰፍረን መስጠት እንችላለን። አይሁዶች በሥላሴ አያምኑም፥ ታዲያ ለምን አንድ ጉዳይ ሶስት ጊዜ ተደጋገመ? ለሚለው መልሳቸው "አንድ ስም ከአንድ በላይ ጊዜ መጠራት ጉዳዩን አጽንዖትና አንክሮት ለመስጠት እንጂ ያንን ስም ብዙ አካል አያደርገውም" ይላሉ።
ሲቀጥል “ቅዱስ” ተባታይ ሲሆን “ቅድስት” አንስታይ ነው፥ ሥላሴ ልክ እንደ “አጋእዝት” ማለትም “ጌቶች” ተብለው እንደሚጠቀሙበት “ቅዱሳን” ተብሎ መጠራት ነበረባቸው እንጂ እንደ ሴት “ቅድስት” እንዴት ይባላሉ? ሥላሴ ሴት ናት እንዴ “ቅድስት” የተባለችው? "አይ አዛኝ “ስለሆኑ” ነው" ብሎ አንድ ክርስቲያን ወገን የቋንቋ፣ የሰዋስው ወይም የባይብል መረጃ የሌለው የጨበጣ መልስ ሰቶኛል። “ስለሆነ” ተብሎ የሚመለክ እንጂ “ስለሆኑ” ተብለው የሚመለኩ ሦስት ቅዱሳን የሉም።

ሢሰልስ "ቅድስት" ለብዙ ቁጥር ወይም ለማኅበር ይውላል፥ ለዛ ነው "ሥሉስ ቅዱስ" ማለትም "ሦስት ቅዱስ" የሚሉት። "ሦስት ቅዱስ አለ" ብሎ ማመን የጤንነት ነውን? በሦስነቱ ሲቀደስ እና ሢሰለስ የሚኖር አምላክ በባይብል ሽታው የለም። ከዚህ በተቃራኒ ውዳሴ ማርያም ይወድስዋ ላይ መልአኩ ማርያምን ሦስት ቅዱስ እንዳለና ወልድ "ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው" ይለናል፦
"መልአኩም እንዲህ አላት፦ "መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል፥ *ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው*።

"ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ሉቃስ ላይ አለመኖሩ በራሱ የተጭበረበረ ሐረግ ነው። እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ ፈጣሪን «ሦስት ናቸው» አትበሉም፥ ተከልከሉ። ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ በአንድነቱ ላይ ሦስትነት የሌለበት አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ እኛንም በተውሒድ ያጽናን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ታላቁ ታምር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6:124 "ታምርም" በመጣላቸው ጊዜ፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ وَإِذَا جَآءَتْهُمْ ءَايَةٌۭ قَالُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ حَتَّىٰ نُؤْتَىٰ مِثْلَ مَآ أُوتِىَ رُسُلُ ٱللَّهِ ۘ ٱللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۥ ۗ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟ صَغَارٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعَذَابٌۭ شَدِيدٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَمْكُرُونَ ፡፡

ቁርኣን ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ከተሰጣቸው ተአምራት ውስጥ ታላቁ እና ዋነኛው ነው፣ የቁርኣን ተአምራዊነት ከቀደምት ነቢያት ተአምራት በሁለት መልኩ ይለያል፦
አንደኛ የቀደምት ነቢያት ተአምራት በአይን የሚታይ፣ በእጅ የሚዳሰስ ነው፣ ይህም ታምር ”ሒስሲይ” ይባላል፣ የቀደምት ነቢያት ተአምር ከነቢይነት ዘመናቸው ጋር ብቻ የተቆራኘ ነው፣ ከእነርሱ ሞት በኋላ ያበቃል፣ ይህም ታምር ”ወቅቲይ” ማለትም ጊዜአዊ ይሰኛል፡፡
ሁለተኛ ለነቢያችን ነቢይነት እንደ ማስረጃ የተሰጣቸው ቁርኣን ግን ህሊናን የሚያናግር፡ አእምሮን የሚቆጣጠርና ልብን የሚገዛ፣ በሚያስተላልፋቸው መልእክቱ ሰዎችን ለለውጥ የሚዳርግ ነው፣ ይህም ታምር ”መዕነዊይ” ይባላል፣ ቁርኣን ከነቢያችን ሞት በኋላ እንኳ ተአምራዊነቱ አላከተመም፣ እስከ ቂያማ ድረስ በነበረው ተአምራዊነቱ ይቀጥላል፤ በዚህም ”አበዲይ” ይሰኛል፡፡ እስቲ ይህንን ታላቅ ታምር በወረደበት ወቅት ሰዎች እንዴት እንዳስተባበሉት እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"የአላህ ታምራት"
ቁርአን በወረደ ጊዜ ሰዎች፦ "ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም" አሉ፤ አምላካችን አላህም፦ "አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው" በላቸው ብሎ መለሰ ሰጠ፦
6:37 *«ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም»* አሉ፡፡ *«አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው*፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

አላህ ቁርኣንን ታምር አድርጎ ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ እንዳወረደው ይናገራል፦
3:108 ይህች በአንተ ላይ በእዉነት የምናነባት ስትሆን የአላህ *ታምራት* آيَاتُ ናት፤
45:6 እነዚህ፣ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤ ከአላህና *ከታምራቶቹም* وَآيَاتِهِ ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
2:252 እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤
3:58 ይህ *ከታምራቶች"* الْآيَاتِ እና ጥበብን ከያዘዉ ተግሣጥ ሲሆን በአንተ ላይ እናነበዋለን።

አላህ የሚነበብ ሆኖ ቁርአን መወረዱ ታምር እንደሆነ እንደነገረን ሁሉ ነብያችንም ቁርአን ለእሳቸው ነብይነት ታምር እንደሆነ በአጽንኦትና በአንክሮት ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 66 , ሐዲስ 3:
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ነብዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ ማንኛውም ነብይ ህዝቦቹ ያምኑበት ዘንድ ታምር ተሰጠውታል፣ ነገር ግን ለእኔ የተሰጠኝ ታምር አላህ ወደ እኔ ያወረደው ወህይ ነው عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَا مِنَ الأَنْبِيَاءِ نَبِيٌّ إِلاَّ أُعْطِيَ مَا مِثْلُهُ آمَنَ عَلَيْهِ الْبَشَرُ، وَإِنَّمَا كَانَ الَّذِي أُوتِيتُ وَحْيًا أَوْحَاهُ اللَّهُ إِلَىَّ فَأَرْجُو أَنْ أَكُونَ أَكْثَرَهُمْ تَابِعًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏" ።

ነጥብ ሁለት
"ማስተባበያ"
ሰዎች ቁርአን ታምር ሆኖ በመጣላቸው ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም" ወይም "ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” ብለው ይህንን ታምር አስተባበሉ፦
6:124 *"ታምርም በመጣላቸው ጊዜ"*፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ፡፡
28:48 እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ ። ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን? አሉም “የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” ፤ አሉም “እኛ በሁለቱም ከሀዲዎች ነን”።

ለሙሳ የተሰጠው ግልጽ የሆኑን "ዘጠኝ ታምራቶች" ናቸው፦
17:101 ለሙሳም ግልጽ የሆኑን "ዘጠኝ ታምራቶች" በእርግጥ ሰጠነው፤

አላህ ታምር ብሎ "ዘጠኝ ታምራቶች" ቢያሳይም በወቅቱ ሙሳና ሃሩንን "የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” አሉ፤ ከዚህ ታምር ይልቅ "ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም" አሉ፦
2:55 ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ በአንተ በፍጹም አናምንልህም ”

በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ስለ ነብያችን፦ "ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ፤ አላህም፦ "ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን?" በማለት ያ የተባለው ታምር ተመልሶ ቢመጣ አሁን ማስተባበላቸውን እንደማይቀር ተናግሯል።
ነጥብ ሶስት
"አስጠንቃቂ"
እነዚያም የካዱት፦ "በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?" ብለው የጠየቁት ታምር የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ አይነት ታምር ነው፤ ይህንን ታምር ነብያችን በራሳቸው ማምጣት አይችሉም፤ እርሳቸው አስጠንቃቂ እንጂ በፍላጎታቸው ታምር እውራጅ አይደሉም፤ ታምር አውራጅ አላህ ነው፤ ስለሆነም ቁርአን በእርሳቸው ላይ ታምር አድርጎ አውርዷል፦
13:7 እነዚያም የካዱት፦ "በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?" ይላሉ፤ አንተ "አስጠንቃቂ" ብቻ ነህ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው።
10:20 በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ታምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡
6:37 «ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም» አሉ፡፡ «አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው፡፡

በእርግጥም አንድ መልእክተኛ ሲመጣ አላህ በፈቃዱ ከሚሰጠው ታምር በራሱ ሊያመጣ አይችል፦
13:38 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ፥ ታምር ሊያመጣ አይገባውም*፤
40:78 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ ታምርን ሊያመጣ አይገባውም*።

መደምደሚያ
በኢየሱስ ዘመንም ኢየሱስ ብዙ ታምር እያደረገ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች የሚጠይቁት ታምር ግን ከሰማይ ነው፤ ኢየሱስም እነርሱን የጠየቁትን ታምር ከመፈፀም ይልቅ "ለዚህ ትውልድ *"ምልክት አይሰጠውም"* ብሎ መለሰ፦
ማርቆስ 8፥11-12 ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት *"ከሰማይ ምልክት"* ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር። በመንፈሱም እጅግ ቃተተና፦ ይህ ትውልድ ስለ ምን *"ምልክት"* ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፥ ለዚህ ትውልድ *"ምልክት አይሰጠውም"* አለ።
ማቴዎስ 16:4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ *"ምልክት"* ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር *"ምልክት አይሰጠውም"*። *ትቶአቸውም ሄደ*።

ኢየሱስ፦ "ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም" ማለቱ ሰዎች የፈለጉት ከሰማይ ምልክት አላደርግም ማለት እንጂ ምልክት አለማድረግን አያሳይም፣ እነርሱ የፈለጉት ምልክት ከሰማይ ምልክት ነው፣ ነገር ግን ኢየሱስ እነርሱ ከጠየቁት ታምር በተቃራኒው ያደረገውን ታምር በፊታቸው ምንም ቢያደርግ በእርሱ አላመኑም፦
ዮሐንስ 12፥37-38 ነገር ግን ይህን ያህል *"ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ"* ነቢዩ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ *"በእርሱ አላመኑም"*።

በተመሳሳይም በነቢያችን ዘመን የነበሩት ሰዎች ታምር ብለው የሚሉትና አላህ ታምር የሚለው ሁለት ለየቅል ነው፣ የቁርአንን ታላቅ ታምርነት በወቅቱ የነበሩት ሰዎች እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ባይመጣም ለሰው የሚበጅ ታምር ማምጣት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፤ ከላይ የቀረበውን ነጥብ በኢየሱስ ታምር ማሳያነት በቀላሉ መረዳት ይቻላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉሏህ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

94፥4 *መወሳትህንም ለአንተ ከፍ አድርገንልሃል*፡፡ وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ

አምላካች አላህ እኛ አማንያን ነቢያችንን"ﷺ" በሸሃደተይን፣ በዒቃም፣ በአዛን፣ በተሸሁድ ጊዜ እና ስማቸው ሲጠራ ሶለዋት በማውረድ እንደናወሳቸው አድርጓል፦
94፥4 *መወሳትህንም ለአንተ ከፍ አድርገንልሃል*፡፡ وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ

በተጨማሪም መወሳትን ከፍ ለማድረግ "ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉሏህ" فِدَاكَ أَبِي وَأُمِّي يَا رَسُولَ اللَّه ማለትም "አባቴ እና እናቴ ለእርሶ ቤዛ ይሁንልዎ" እንላለን። እዚህ መወሳት ላይ ሚሽነሪዎች ረብጣ በሆነ ዕውቀት እጦት ሁለት ዐበይት ጥያቄ ያነሳሉ። አንዱ "መስዋዕት ለዛውም ሰው የሆኑ አባት እና እናት መስዋዕት እንዴት ለፍጡር ይቀርባል? ሲሆን ሁለተኛው "አንድ ማንነት በሌለበት በሁለተኛ መደብ "ሆይ" በማለት ማናገር ዱዓእ አይደለምን? በማለት ይጠይቃሉ። እነዚህ ጥያቄዎች በሰላና በሰከነ አእምሮ ለመመለስ ሁለት የሙግት ነጥቦችን እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ቤዛ"
"ፊዳእ" فِدَاء የሚለው ቃል "ፈዳ" فَدَى ማለትም "ቤዘወ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቤዛ" "ዋቢ" "ዋስ" "ተያዥ" ማለት ነው። እኛ ነቢያችንን"ﷺ" "ፊዳከ አቢ ወኡሚ" የምንልበት እሳቸውን ዋቢ ለማድረግ እንጂ ለእርሳቸው መስዋዕት ማቅረባችንን በፍጹም አያሳይም። ምክንያቱም እራሳቸውን ነቢያችን"ﷺ" ባልደረባቸውን "ፊዳከ አቢ ወኡሚ" ብለውታል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 1
ዐሊይ እንደተረከው፡- "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ወላጆቹን በመሰብሰብ ለሰዕድ ኢብኑ ማሊክ እንዳሉት ለማንም ሲሉ አልሰማኋቸውም፥ እኔ የኡሑድ ዘመቻ ቀን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፡፦ "ሰዕድ ሆይ! በጠላት ላይ በትርህን ወርውር! *"አባቴ እና እናቴ ቤዛ ይሁኑልክ"*። عَنْ عَلِيٍّ، قَالَ مَا رَأَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ جَمَعَ أَبَوَيْهِ لأَحَدٍ غَيْرِ سَعْدِ بْنِ مَالِكٍ فَإِنَّهُ قَالَ لَهُ يَوْمَ أُحُدٍ ‏ "‏ ارْمِ سَعْدُ فِدَاكَ أَبِي وَأُمِّي ‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "ቤዛ" የሚለውን "መስዋዕት" በሚል ብቻ ብንረዳው ነቢያችን"ﷺ" ለሰዕድ ኢብኑ ማሊክ መስዋዕት ያቀርቡ ነበር ይባል ነበር፥ ቅሉ ግን እንደዛ አይደለም። ምክንያቱም የሰው መስዋዕት አይደለም ለሰው ለአምላክ አይቀርብም። ሲቀጥል የነቢያችን"ﷺ" አባት እና እናት በሕይወት የሉም ፥ የሌሉትን "ቤዛ ይሁኑልክ" ማለት "ዋቢ ይሁኑልክ" "ዋስ ይሁኑልክ" ማለት እንጂ "የእርድ መስዋዕት ይሁኑልክ" ማለት በፍጹም አይደለም። ይህ ፍቅርን የሚገልጹበት ዘይቤአዊ አንጋገር ነው። ሢሰልስ “መስዋዕት” የሚለው ቃል “ኑሡክ” نُسُك ሲሆን ለአላህ ብቻ የሚቀርብ "እርድ" ነው፦
22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን*፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ አዘዝናቸው፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ
6፥162 *«ስግደቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው»* በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

“ሀድይ” هَدْي ማለት “የእርድ እንስሳ” ሲሆን ጊደር፣ በግ፣ ፍየል፣ ጥጃ፣ ግመል ነው፥ ይህ ለአላህ የሚቀርበው መስዋዕት “ቁርባን” ይባላል። “ቁርባን” قُرْبَان የሚለው ቃል “ቀረበ” قَرَّبَ ማለትም “ቀረበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መቃረቢያ” “አምኃ” “እጅ መንሻ” ማለት ነው።
"ቤዛ" ማለት የግድ "መስዋዕት" ማለት ብቻ ነው ብሎ መተርጎም ክፉኛ ስህተት ነው፥ "ቤዛ" በሚለው ቃል ዙሪያ የቋንቋ ምሁራን "ዋቢ" "ዋስ" "ተያዥ" ማለት ነው ብለው አስቀምጠዋል። የተለያዩ ሙዳየ-ቃላት ይመልከቱ፦
1. አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ 1948 ድኅረ-ልደት ገጽ 266.
2. ከሣቴ ብርሃን ተሰማ 1951 ድኅረ-ልደት ገጽ 532.

ይህንን ሙግት ወደ ባይብል በማነጻጸር ስንመለከት "ቤዛ" ማለት የግድ "መስዋዕት" ማለት ከሆነ ሀብት ለሰው ነፍስ መስዋዕት ነው ማለት ነው፦
ምሳሌ13፥8 *ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው*፤ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።

ሀብት ለሰው ነፍስ ዋስትና ነው ማለት እንጂ ልክ እንደ በግ፣ በሬ፣ ፍየል ለፈጣሪ የሚቀርብ እርድ ነው ማለት እንዳልሆነ እሙን ነው፦
ምሳሌ 21፥18 *ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፥ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው*።
ኢሳይያስ 43፥3 *ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ*።

"ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፣ በደለኛ የቅን ሰው ቤዛ ነው፣ ግብጽን ለእስራኤል ቤዛ ነው" ማለት "ኀጥእ የጻድቅ መስዋዕት ነው፣ በደለኛ የቅን ሰው መስዋዕት ነው፣ ግብጽ ለእስራኤል መስዋዕት ነው" ማለት እንደልሆነ ቅቡል ነው፦
የሐዋርያት ሥራ7፥35 በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና *ቤዛ አድርጎ ላከው*።

"ሙሴ ለእስራኤል ቤዛ ነው" ማለት "ሙሴ ለእስራኤል መስዋዕት ነው" ማለት አይደለም። እኛ ነቢያችንን"ﷺ" "ፊዳከ አቢ ወኡሚ" ማለታችን በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። ይህንን የሙግት ዚቅ በስሜት ሳይሆን በስሌት፥ በሙቀት ሳይሆን በዕውቀት ለመረዳት ሞክሩ።
ነጥብ ሁለት
"ሆይ"
በሁለተኛ መደብ "ያ" يَا ማለት "ሆይ" ማለት ሲሆን "ሐርፉ አን-ኒዳእ" حَرْف النِدَاء ማለትም "ሙያዊ መስተዋድድ"vocative particle" ነው። "አንድ ማንነት ሌላውን ማንነት "ሆይ" ብሎ መጠቀሙ ዱዓእ ነው" ብሎ ማለት ስህተት ነው። ምክንያቱም አምላካችን አላህ ነቢያትን አደም ሆይ! ኢብራሂም ሆይ! ሙሳ ሆይ! ዳውድ ሆይ! እያለ ይናገራል፦
2፥33 *«አደም ሆይ!* ስሞቻቸውን ንገራቸው» አለው፡፡ قَالَ يَا آدَمُ أَنبِئْهُم بِأَسْمَائِهِمْ
37፥104 ጠራነውም፤ አልነው *«ኢብራሂም ሆይ!* وَنَادَيْنَاهُ أَن يَا إِبْرَاهِيمُ
27፥9 *«ሙሳ ሆይ!* እነሆ እኔ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ነኝ፡፡ يَا مُوسَىٰ إِنَّهُ أَنَا اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
38፥26 *ዳውድ ሆይ!* እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሃልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ፡፡ يَا دَاوُودُ إِنَّا جَعَلْنَاكَ خَلِيفَةً فِي الْأَرْضِ فَاحْكُم بَيْنَ النَّاسِ بِالْحَقِّ

በተጨማሪ ሙያዊ መስተዋድድ ተጠቅሞ "ሆይ" ማለት ወደዚያ ማንነት መጸለይን አለማሳየቱ አምላካችን አላህ ነቢያችንን"ﷺ" በሁለተኛ መደብ "አንተ ተከናናቢው ሆይ! አንተ ደራቢው ሆይ! አንተ መልክተኛ ሆይ! አንተ ነቢዩ ሆይ! በማለት መናገሩ ነው፦
73፥1 *አንተ ተከናናቢው ሆይ!* يَا أَيُّهَا الْمُزَّمِّلُ
74፥1 *አንተ ደራቢው ሆይ!* يَا أَيُّهَا الْمُدَّثِّرُ
5፥67 *አንተ መልክተኛ ሆይ!* يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ
33፥45 *አንተ ነቢዩ ሆይ!* يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ

እንግዲህ "ሆይ" ማለት አላህ እየጸለየ ነው የሚለውን እንደማያሲዝ ሁሉ እኛም ቁርኣን ባነበነብን ቁጥር አንተ ተከናናቢው ሆይ! አንተ ደራቢው ሆይ! አንተ መልክተኛ ሆይ! አንተ ነቢዩ ሆይ! በማለት እናስታውሳቸዋለን። ልክ እንደዚሁ "ያ ረሱሉሏህ" يَا رَسُولَ اللَّه እንላቸዋለን።
ይህ በፍጹም ጸሎት ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም በባይብል እራሱ የሌሉ አካላትን በሌሉበት ያዕቆብ ሆይ! ዛብሎን ሆይ! ይሳኮር ሆይ! እያለ ይናገራል፦
ዘኍልቍ 24፥5 *ያዕቆብ ሆይ*፥
ዘዳግም 33፥18 *ዛብሎን ሆይ* በመውጣትህ፥
*ይሳኮር ሆይ*፥ በድንኳንህ ውስጥ ደስ ይበላችሁ።

እሩቅ ሳንሄድ የማይሰሙ አካላትን ምንጭ ሆይ! ተራሮች ሆይ! ምድር ሆይ! በገና ሆይ! ፍርስራሾች ሆይ! ሰይፍ ሆይ! ሞት ሆይ! ሲኦል ሆይ! አጥንቶች ሆይ! እንስሶች ሆይ! ፈረሶች ሆይ! የጥድ ዛፍ ሆይ! እያለ ይናገራል፦
ዘኍልቍ 21፥17 አንተ *ምንጭ ሆይ*፥
2ኛ ሳሙኤል 1፥21 *እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ*፥
ኢዮብ 16፥18 *ምድር ሆይ*፥
መዝሙር 108፥2 *በገና ሆይ*፥
ኢሳይያስ 52፥9 እናንተ የኢየሩሳሌም *ፍርስራሾች ሆይ*፥
ኤርምያስ 47፥6 አንተ የእግዚአብሔር *ሰይፍ ሆይ*፥
ሆሴዕ 13፥14 *ሞት ሆይ*፥ ቸነፈርህ ወዴት አለ? *ሲኦል ሆይ*፥ ማጥፋትህ ወዴት አለ?
ሕዝቅኤል 37፥4 እናንተ የደረቃችሁ *አጥንቶች ሆይ*፥
ኢዮኤል 2፥22 እናንተ የምድር *እንስሶች ሆይ*፥
ኤርሚያስ 46፥9 *ፈረሶች ሆይ*፥
ዘካሪያስ 11፥2 *የጥድ ዛፍ ሆይ*፥

መቼም እነዚህን በድን እና ዐቅል የሌላቸው አካላት ሙያዊ መስተዋድድ ተጠቅሞ "ሆይ" ማለት ወደ እነዚያ አካላት መጸለይን ሳይሆን ዘይቤአዊ አነጋገር ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን ጥያቄ በዚህ ልክና መልክ ተረዱት። የእናንተን ጥያቄ እንደ ውኃ ፈሳሽ እንደ እንግዳ ደራሽ ለመመለስ መቸኮል ሳይሆን እረጋ ብለን ልጡ የተራሰ ጉድጓዱ የተማሰ መልስ መስጠት ግድ ይላል።
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉሏህ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አማኑኤል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አምላካችን አላህ የሩቅ ነገር ሁሉ ዐዋቂ ነው፥ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት የተከሰተው ክስተት ለነቢያችን"ﷺ" ይተርክላቸዋል። ከተረከላቸው የሩቅ ወሬ መካከል የዒሣ ከመርየም በድንግልና መወለድ ነው፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

በባይብል ስንሄድ ኢየሱስ በድንግልና እንደተወለደ በተመሳሳይ ይናገራል፥ ነገር ግን ዐበይት ክርስትና፦ "የተወለደው አምላክ ነው" የሚል እምነት አላቸው። እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸው "ኢየሱስ በትንቢት አማኑኤል መባሉ ነው" የሚል ሙግት ያቀርባሉ፦
ኢሳይያስ 7፥14 *ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች*።לָכֵן יִתֵּן אֲדֹנָי הוּא, לָכֶם--אוֹת: הִנֵּה הָעַלְמָה, הָרָה וְיֹלֶדֶת בֵּן, וְקָרָאת שְׁמוֹ, עִמָּנוּ אֵל.

"ኢማኑ-ኤል" עִמָּנוּ אֵל የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ኢማኑ" עִמָּ֥נוּ ማለት "ከእኛ ጋር" ማለት ሲሆን "ኤል" אֵֽל ማለት ደግሞ "አምላክ" ማለት ነው። በጥቅሉ "አምላክ ከእኛ ጋር" ማለት ነው፥ ልክ እንደ "እስማ-ኤል" "ሳሙ-ኤል" "መላል-ኤል" "ባቱ-ኤል" "እስራ-ኤል" ወዘተ..ነው። "አምላክ" የሚለው አጫፋሪ ስም መድረሻ ቅጥያsuffix" ሆኖ የመጣ ነው፥ "አምላክ" አጫፋሪ ስም ሆኖ በመድረሻ ቅጥያ ላይ መግባት አምላክነትን ካሳየማ "እስማ-ኤል" "ሳሙ-ኤል" "መላል-ኤል" "ባቱ-ኤል" "እስራ-ኤል" ወዘተ.. አምላክ ይሆኑ ነበር። ቅሉ ግን "ኤል" አምላካዊ ማዕረግን"theo-phoric" እንጂ አምላክነትን በፍጹም አያሳይም። ሲቀጥል ይህ ስም የወጣው በወቅቱ ለተወለደ ሕጻን ነው፦
ኢሳይያስ 8፥3 *"ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፤ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች"*።
ኢሳይያስ 8፥8 *አማኑኤል ሆይ፥ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች*።
ኢሳይያስ 8፥10 *አምላክ ከእኛ ጋር ነውና*።

"ነቢይቱ" የተባለችው ሴት ማርያም እንዳልሆነች ቅቡል ነው፥ ያ የተወለውን ሕጻን በሁለተኛ መደብ "አማኑኤል ሆይ" በማለት ያናግረዋል። በወቅቱ የተወለደውን የአማኑኤልን አገር የአሦር መንግስት ሞልቶቷም። በዚህ ጊዜ ምልክቱ አምላክ ከእነርሱ ጋር ነው፥ "አምላክ ከእኛ ጋር ነውና" ተብሎ የተቀመጠው የዕብራይስጥ ቃል "ኢማኑ-ኤል" עִמָּנוּ אֵל መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ ሕጻን አምላክ ከእስራኤላውያን ጋር ለመሆኑ ምልክት ስለሆነ ስሙ "አማኑኤል" ነው። በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ሲመጡ፥ አምላክ ከሶርያ ጋር የተባበሩትን የኤፍሬምን ነገድ በ 65 ዓመት ውስጥ እንደሚሰባብር ምልክት ይሆን ዘንድ አምላክ አካዝን እንዲጠይቅ ተጠይቆ ለዛ ምልክት ምላሽ "ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች" የሚል ነው፦
ኢሳይያስ 7፥16 *ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች*።
ኢሳይያስ 8፥4 *ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና"*።

ይህ ሕጻን አባት ስላለው “አባቱንና እናቱን” የሚል ኃይለ-ቃል እናነባለን። “ድንግል” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጡ ቃል “አልማ” הָעַלְמָ֗ה ሲሆን “ልጃገረድ” “ወጣት ሴት” “ኮረዳ” “ቆንጂት” “ድንግል” “ብላቴናይት” ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 24፥43 እነሆ፥ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፤ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም *ቆንጆ* הָֽעַלְמָה֙ ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ፡ ስላት፥
ዘጸአት 2:8 የፈርዖንም ልጅ፦ ሂጂ አለቻት፤ *ብላቴናይቱም* הָֽעַלְמָ֔ה ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች።

ስለዚህ ወጣት ሴት ወይም ድንግል ሴት አሊያም ብላቴናይት ልጅ የምትወልደው አግብታ ነው። ነቢይቱም አማኑኤልን በወቅቱ ወልዳዋለች፥ ልጇ "አማኑኤል" መባሉ አምላክ መሆኑን ወይም አምላክ መወለዱን በፍጹም አያሳያም። ስለዚህ ከመነሻው የኢሳይያስን 7፥14 ዐውደ-ንባብ በወቅቱ ለተወለደ ሕጻን ነው፥ የማቴዎስ ጸሐፊ ይህንን ትንቢት ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ማቴዎስ 1፥22-23 *በነቢይ ከጌታ ዘንድ፦ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው*።

የማቴዎስ ጸሐፊ እራሱ ማቴዎስ አይደለም። ይህ ሌላ አርስት ነው፥ ነገር ግን የማቴዎስ ጸሐፊ ከኢሳይያስ 7፥14 “የቀጥታ ጥቅስ”metaphrase quotation” ሲያስቀምጥ በትክክል አላስቀመጠም። ኢሳይያስ "ብላ ትጠራዋለች" የሚለውን አዛብቶ "ይሉታል" ብሎ አስቀምጦታል፥ "ትለዋለች" የሚለውን ለውጦ "ይሉታል" የሚለውን ከየት አምጥቶ ነው? ምን አለ ኮፒ ሲደረግ በትክክል ኮፒ ቢደረግ? ማን ነው የተሳሳተው መንፈስ ቅዱስ ወይስ ጸሐፊው? መንፈስ ቅዱስ ስለማይሳሳት ጸሐፊው ወይም ከጊዜ በኃላ እደ-ክታባትን ያዘጋጁት ተሳስተዋል። ሲቀጥል ኢሳይያስ የጠቀሳት ሴት ልጇን ስሙንም አማኑኤል ብላ እንደምትጠራው ይናገራል፥ ማርያም ግን ልጇን የምትጠራው "አማኑኤል" ብላ ሳይሆን "ኢየሱስ" ብላ ነው፦
ሉቃስ 1፥31 *"እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ*።
ሉቃስ 2፥21 *ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ*።

ስለዚህ አማኑኤል ብላ ካልጠራችው ኢሳይያስ የጠቀሳት ሴት ማርያም ሳትሆን በወቅቱ የነበረችው ነብይቱ ናት። ዋናው የመጣጥፉ ነጥብ ኢሳይያስ 7፥14 "አምላክ ይወለዳል" የሚለው የተንሸዋረረ መረዳት በፍጹም አያሳይም ነው። ፈጣሪ መውለድ እና መወለድ የሚባሉ የፍጡራን ባሕርይ የለውም፦
112፥3 *"አልወለደም አልተወለደምም"*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኃያል አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

22፥74 አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ *"አላህ በጣም ኃያል አሸናፊ ነው"*፡፡ مَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

ብዙ ዐበይት ክርስትና፦ "አምላክ ተወልዷል" ብለው ከሚጠቅሷቸው አናቅጽ መካከል ይህ ጥቅስ ነው፦
ኢሳይያስ 9፥6 *ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል*። לם רבה (לְמַרְבֵּה) הַמִּשְׂרָה וּלְשָׁלוֹם אֵין-קֵץ, עַל-כִּסֵּא דָוִד וְעַל-מַמְלַכְתּוֹ, לְהָכִין אֹתָהּ וּלְסַעֲדָהּ, בְּמִשְׁפָּט וּבִצְדָקָה; מֵעַתָּה, וְעַד-עוֹלָם, קִנְאַת יְהוָה צְבָאוֹת, תַּעֲשֶׂה-זֹּאת

"ሕጻን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። የዚህን ጥቅስ ዐውደ-ንባብ ስመለከት ይህ ሕጻን በወቅቱ የተወለደ ሕጻን ነው፦
ኢሳይያስ 7፥16 *ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች*።
ኢሳይያስ 8፥4 *ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና"*።
ኢሳይያስ 8፥3 *"ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፤ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች"*።

"ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና" የተባለው ሕጻን ነቢይቱ የወለደችው ወንድ ልጅ እንደሆነ ፍትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ይህ ሕጻን የማዕረግ ስሙ፦ "ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ" የሚል ነው፥ እነዚህ አራት ስም የሁለት ውሕደት ስም"compound Noun" ናቸው። አጉራ ዘለል መረዳት ያላቸው ሰዎች "ኃያል አምላክ" የሚለውን ለአምላክነቱ ከተጠቀሙ "የዘላለም አባት" የሚለውን ለአብነቱ መጠቀም ነበረባቸው፥ ምክንያቱም "ኤል" אֵ֣ל ማለትም "አምላክ" የሚለው እና "አብ" אֲבִ ማለትም "አባት" የሚለው በዕብራይስጡ በመነሻ ቅጥያ"prefix" አጫፋሪ ስም ሆነው የመጡ ናቸው። ልክ "ኤል-ጊቦር" אֵ֣ל גִּבּ֔וֹר ለሕጻኑ ስም እንደሆነ ሁሉ "ኤል-አብ" "ኤል-አታህ" "ኤል-ናታህ" "ኤል-ሹአ" "ኤል-ያህ" ለሰዎች ስም ሆኖ መጥቷል፥ ልክ "አብ-አድ" אֲבִיעַ֖ד ለሕጻኑ ስም እንደሆነ ሁሉ "አብ-ራሃም" "አብ-ጋኤል" "አብ-አሳፍ" "አብ-አልቦን" "አብ-ያህ" ለሰዎች ስም ሆኖ መጥቷል። እነዚህ ሰዎች "አምላክ" እና "አብ" እንዳልሆኑ ሁሉ ሕጻኑም "አምላክ" እና "አብ" አይደለም።
ቅሉ ግን "ኤል" אֵ֣ל አምላካዊ ማዕረግን"theo-phoric" እንጂ አምላክ መሆንን እንደማያሳይ ሁሉ "አብ" אֲבִ አባታዊ ማዕረግን"Patro-phoric" እንጂ አብ መሆን በፍጹም አያሳይም።
ሙግቱን አጥብበን ሕጻኑ ኢየሱስ ነው ብለን ብንቀበል እንኳን ኢየሱስ አምላክ እና አባት ነው ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም ኢየሱስ የራሱ አምላክ እና አባት አለው፦
2ቆሮንቶስ 1፥3 *"የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይባረክ*።

"ኢየሱስ አባትነቱ ለእኛ እንጂ የራሱ አባት አለው" ካላችሁ እንግዲያውስ አምላክነቱ ለእናንተ እንጂ የራሱ አምላክ አለው። ይህም አባት እና አምላክ የሁሉም አንድ አባት እና አንድ አምላክ ነው፦
ሚልኪያስ 2፥10 *ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?*
ኤፌሶን 4፥6 *ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ኢየሱስ "የእኔ አምላክ" "የእኔ አባት" የሚለው ይህንን አንድ አምላክ እና አንድ አባት ነው፦
ዮሐንስ 20፥17 *"እኔ" ወደ አባቴ እና ወደ አባታችሁ፥ ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ"* ብለሽ ንገሪአቸው፤ አላት።

"ወደ" የሚለው መስተዋድድ "እኔ" የሚለውን ማንነት ከአንዱ አምላክ እና ከአንዱ አባት ነጥቶ ቁጭ አርጎታል። "አምላክ" በሚለው መድረሻ ቃል ላይ "ክ" የነበረውን ሳድስ ወደ "ኬ" ኃምስ ስናመጣው "ኬ" በሚለው ቃል ውስጥ "የእኔ" የሚል በውስጠ-ታዋቂ አገናዛቢ ዘርፍ አለ፥ "አባት" በሚለው መድረሻ ቃል ላይ "ት" የነበረውን ሳድስ ወደ "ቴ" ኃምስ ስናመጣው "ቴ" በሚለው ቃል ውስጥ "የእኔ" የሚል በውስጠ-ታዋቂ አገናዛቢ ዘርፍ አለ። ስዚህ አንዱ አምላክ እና አባት አምላክነቱ እና አባትነቱ ለኢየሱስ ሙሉ "እኔነት" እንጂ ለስጋው፣ ለሰውነቱ፣ ለቁርበቱ የሚል ድራማና ቁማር አይሠራም።
ሲቀጥል ወንድ ልጅም "ተሰጥቶናል" በሚለው ኃይለ-ቃል ሕጻኑን የሰጠ ማንነት እንዳለ ያሳያል፥ ሕጻኑ ኢየሱስ ነው ከተባለ ባይብሉ አምላክ ኢየሱስን እንደሰጠ ይናገራል፦
ዮሐንስ 3፥16 *"አምላክ" Θεὸς አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና"*።
አምላክ አምላክን ከሰጠ ሁለት አምላክ ይሆናል፥ ቅሉ ግን አምላክ የሰጠው እራሱ ወይም ሌላ አምላክን ሳይሆን ልጁን ነው።
ሢሠልስ አምላክ አሊያም አብ ተጠቅልሎ ይተኛልን? ሕጻኑ ግን ተኝቷል፦
ሉቃስ 2፥12 ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ *ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም "ተኝቶ" ታገኛላችሁ*።
ሉቃስ 2፥16 ፈጥነውም መጡ ማርያምን እና ዮሴፍን *ሕፃኑንም በግርግም "ተኝቶ" አገኙ*።

አንድ አምላክ አይተኛም፥ አያንቀላፋም። አምላክ አሊያም አብ ያድጋልን? ሕጻኑ ግን አድጓል፦ የአምላክም ጸጋ በላዩ ላይ ነበረ፦
ሉቃ2:40 *"ሕፃኑም አደገ"፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የአምላክም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ*።
ሉቃስ 2፥52 *ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በአምላክ እና በሰው ፊት "ያድግ" ነበር*።

"የአምላክም ጸጋ በአምላክ ላይ ነበረ፥ አምላክ በአምላክ ፊት ያድግ ነበር" ትርጉም አይሰጥም። አምላክ አሊያም አብ እናት አለውን? ሕጻኑ ግን እናት አለው፦
ማቴዎስ 2፥13 *ሕፃኑን እና እናቱንም* ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ።
ማቴዎስ 2፥20 *ሕፃኑን እናቱንም* ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።

ሲያረብብ ሕጻኑ "ኤል-ጊቦር" אֵ֣ל גִּבּ֔וֹר ማለትም "ኃያል አምላክ" ቢባል እንኳን "ኤል-ሻዳይ" אֵ֣ל שַׁדַּ֔י ማለትም "ሁሉን የሚችል አምላክ" ነው ማለት አይደለም። ምክንያቱም ነገሥታት ""ኤል-ጊቦር" ተብለዋልና፦
ሕዝቅኤል 32፥21፤ *"ኃያላን አምላክ" በሲኦል ውስጥ ሆነው ከረዳቶቹ ጋር ይናገሩታል፤ በሰይፍም የተገደሉት ያልተገረዙ ወርደው ተኝተዋል*። יְדַבְּרוּ-לוֹ אֵלֵי גִבּוֹרִים, מִתּוֹךְ שְׁאוֹל--אֶת-עֹזְרָיו; יָרְדוּ שָׁכְבוּ הָעֲרֵלִים, חַלְלֵי-חָרֶב

በእንግሊዝኛው Young's Literal Translation የሚባለው ትርጉም ይመልከቱ። ዐማርኛው ላይ እና አንዳንድ እንግሊዝኛ ላይ በትክክል ለማስቀመጥ ቢዳዳቸውም ዕብራይስጡ ግን "ኤል-ጊቦሪም" אֵלֵ֧י גִבּוֹרִ֛ים በማለት ሳቅማማ አስቀምጦታል፥ "ጊቦሪም" גִבּוֹרִ֛ים የጊቦር ብዙ ቁጥር ሲሆን "ኃያላን" ማለት ነው። ይህ የተለመደ አገላለጽ ነው፥ "ኤል" אֵ֣ל የሚለው አጫፋሪ ስም ለቦታ ስም ሆኖ መጥቷል፦
ዘፍጥረት 35፥7 *"የዚያንም ቦታ ስም "ኤል-ቤቴል" ብሎ ጠራው"*።

"ኤል-ቤቴል" אֵ֖ל בֵּֽית אֵ֖ל ማለት "የቤቴል አምላክ" ማለት ነው። ያ ቦታ አምላክ ነውን? "አይ የቦታው ስም እንጂ ምንነቱ አምላክ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ የሕጻኑ ስም እንጂ ምንነቱ አምላክ አይደለም። ኢሳይያስ 9፥6 "ስሙም" ስለሚል "ኃያል አምላክ" ልክ እንደ "ኤል-ቤቴል" የሕጻኑ ስም እንጂ እንደ ያህዌህ በቀጥታ "ኃያል አምላክ" አልተባለም፦
ኢሳይያስ 10፥21 *"የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ*"።

መቼም በኢሳይያስ ዘመን የተወለደው የነቢይቱ ልጅ ሕጻኑን ስሙ እንጂ "ኃያል አምላክ" ነው እንደማትሉ ሁሉ ኢሳይያስ 9፥6 ላይ ለኢየሱስ ድርብ ትንቢት ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ሕጻኑ ኢየሱስ ስሙ እንጂ ምንነቱ "ኃያል አምላክ" አይደለም። ስለዚህ ብዙ ዐበይት ክርስትና፦ "አምላክ ተወልዷል" የሚለው ድምዳሜአችሁ ሥረ-መሠረት የሌለው የእምቧይ ካብ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰንበት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥124 *"ሰንበት የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው"*፡፡ ጌታህም በትንሣኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡ إِنَّمَا جُعِلَ السَّبْتُ عَلَى الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحْكُمُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

"ሠብት" سَّبْت የሚለው ቃል "ሡባት" سُبَات ማለትም "ዕረፍት" ከሚለው የስም መደብ የረባ ሲሆን "ሰንበት" ማለት ነው፦
78፥9 *እንቅልፋችሁንም "ዕረፍት" አደረግን*፡፡ وَجَعَلْنَا نَوْمَكُمْ سُبَاتًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዕረፍት" ለሚለው ቃል የገባው "ሡባት" سُبَات መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህንን ሰንበት ለማወቅ ሳምንታዊ ቀናትን እንዳስስ፦
1. "አሐድ" أحَد ማለት "አንድ" ማለት ነው፥ "እሑድ" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ “አሐደ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንድ" ማለት ነው።
2. "ኢስነይን" اِثْنَيْن‎ ማለት "ሁለት" ማለት ነው፥ "ሰኞ" ማለት "ሰነየ" ማለትም "ደገመ" ከሚል የመጣ ሲሆን "ሁለተኛ" ማለት ነው።
3. "ሱላሳእ" ثُّلَاثَاء ማለት "ሦስት" ማለት ነው፥ "ማክሰኞ" ማለት "ማግስት" ማለት ነው፤ የእሁድ ማግስት "ሦስተኛ" ቀን ነው።
4. "አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ማለት "አራት" ማለት ነው፥ "ረቡዕ" ማለት "ረበዓ" ከሚል የመጣ ሲሆን "አራተኛ" ማለት ነው።
5. "ኸሚሥ" خَمِيس ማለት "አምስት" ማለት ነው፥ "ሐሙስ" ማለት "አምሽት" "አምስት" ከሚል የመጣ ሲሆን "አምስተኛ" ማለት ነው።
6. "ጁሙዓህ" جُمُعَة ማለት "ስብስብ" ማለት ነው፥ "ዓርብ" የሚለው "ረበዐ" ማለትም "ሰበሰበ" ማለት ሲሆን "መሰብሰቢያ" ስድስተኛ ነው።
7. "ሠብት" سَّبْت ማለት "ዕረፍት" ማለት ነው፥ "ቅዳሜ" ማለት "ቀዳሚት" ማለት ሲሆን የጥንቷና የቀደመችው ሰንበት ናት። "ሰንበት" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ "እረፍት" ማለት ነው።
ስለዚህ ይህቺ ሰንበት ሰባተኛዋ ቀን ናት፥ "ሠብዓህ" سَبْعَة ማለት እራሱ "ሰባት" ማለት ነው። በዚህ በሰባተኛው ቀን እረፍት የተደረገው በእስራኤል ልጆች ብቻ ነው፦
16፥124 *"ሰንበት የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው"*፡፡ ጌታህም በትንሣኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡ إِنَّمَا جُعِلَ السَّبْتُ عَلَى الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحْكُمُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

በዚህ ቀን ሥራ መሥራት የተከለከለ ነው፥ አምላካችን አላህም፦ "በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላልፉ" ብሏቸው ነበር፦
4፥154 በቃል ኪዳናቸውም ምክንያት የጡርን ተራራ ከበላያቸው አነሳን፡፡ ለእነሱም «ደጃፉን አጎንባሾች ኾናችሁ ግቡ» አልን፡፡ *ለእነርሱም «በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላልፉ» አልን*፡፡ ከእነሱም ከባድን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَرَفَعْنَا فَوْقَهُمُ الطُّورَ بِمِيثَاقِهِمْ وَقُلْنَا لَهُمُ ادْخُلُوا الْبَابَ سُجَّدًا وَقُلْنَا لَهُمْ لَا تَعْدُوا فِي السَّبْتِ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا

"ቁልና" قُلْنَا የሚለው "ወሶይና" وَصَّيْنَا ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ሲሆን "አዘዝን" ማለት ነው። በሰንበት ቀን እንዲያርፉ እና ይህንን ትእዛዝ እንዳይተላለፉ አዟቸው ነበር። ቅሉ ግን በቀይ ባሕር ዳርቻ በምድያም እና በሲና መካከል ባለችው ከተማ በእረፍታቸው ቀን ለፈተና ዓሦቻቸው የተከማቹ ኾነው ይመጡላቸው ነበር፥ በአዘቦት ቀናት ግን አይመጡም ነበር፦
7፥163 *ከዚያችም በባሕሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በሰንበት ቀን ወሰን ባለፉ ጊዜ፥ በሰንበታቸው ቀን ዓሦቻቸው የተከማቹ ኾነው በሚመጡላቸው ጊዜ የኾነውን ጠይቃቸው፡፡ ሰንበትንም በማያከብሩበት ቀን አይመጡላቸውም፡፡ እንደዚሁ ያምጹበት በነበሩት ምክንያት እንፈትናቸዋለን*፡፡ وَاسْأَلْهُمْ عَنِ الْقَرْيَةِ الَّتِي كَانَتْ حَاضِرَةَ الْبَحْرِ إِذْ يَعْدُونَ فِي السَّبْتِ إِذْ تَأْتِيهِمْ حِيتَانُهُمْ يَوْمَ سَبْتِهِمْ شُرَّعًا وَيَوْمَ لَا يَسْبِتُونَ ۙ لَا تَأْتِيهِمْ ۚ كَذَٰلِكَ نَبْلُوهُم بِمَا كَانُوا يَفْسُقُونَ

"ሰንበታቸው" ለሚለው ቃል የገባው "ሰብቲሂም" سَبْتِهِمْ ሲሆን "እረፍታቸው" ማለት ነው። "ሰንበትንም በማያከብሩበት" ለሚለው ቃል የገባው የግስ መደብ "ላ ተሥቢቱነ" لَا يَسْبِتُونَ ሲሆን "በማያርፉበት" ማለት ነው። በእረፍት ቀን ዓሣ በማጥመድ በአላህ ትእዛዝ ላይ ሲያምጹ "ወራዶች ዝንጀሮዎች ኹኑ" አላቸው ሆኑም፦
7፥166 *ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነርሱ «ወራዶች ዝንጀሮች ኹኑ አልን» ኾኑም*፡፡ فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ
2፥65 *እነዚያንም ከእናንተ ውስጥ *"በሰንበት ቀን ዓሣን በማጥመድ ወሰን ያለፉትን እና ለእነርሱ «ወራዶች ዝንጀሮዎች ኹኑ» ያልናቸውን በእርግጥ ዐወቃችሁ*፡፡ وَلَقَدْ عَلِمْتُمُ الَّذِينَ اعْتَدَوْا مِنكُمْ فِي السَّبْتِ فَقُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ

ይህ ክስተት የተከሰተው አላህ ወደ ሙሳ ተውራትን ባወረደበት ዘመን ነው፥ አላህ ወደ ሙሳ ተውራትን ሲያወርድ ነቢያችን”ﷺ” አልነበሩም። ይህንን የሙሳ ወሬ “ነቁሱ ዐለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ለነቢያችን”ﷺ” የሚተርከው እራሱ ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ያወረደው አምላክ ነው፦
28፥44 *ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ባወረድንለት ጊዜ ከተራራው በምዕራባዊው ጎን አልነበርክም* ከተጣዱትም አልነበርክም፡፡ وَمَا كُنتَ بِجَانِبِ الْغَرْبِيِّ إِذْ قَضَيْنَا إِلَىٰ مُوسَى الْأَمْرَ وَمَا كُنتَ مِنَ الشَّاهِدِينَ
20፥9 *የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶልሃል*፡፡ وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ

አምላካችን አላህ ከመልክተኞቹም ወሬዎች ለነብያችን”ﷺ” መተረኩ ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “እንተርክልሃለን"፤ በዚህችም እውነቱ ነገር "ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ" መጥቶልሃል*፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
ወደ ባይብል ስንመጣ እስራኤላውያን ስድስት ቀን ሠርተው በሰባተኛው ቀን ዕረፍት ነበሩ፣ ስድስት ወር ሠርተው በሰባተኛው ወር በ 1ኛው ቀን በ 10ኛው ቀን ዕረፍት ነበሩ፣ ስድስት ዓመት ሠርተው በሰባተኛው ዓመት ዕረፍት ነበሩ፦
ዘሌዋውያን 23፥3 *ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው*።
ዘሌዋውያን 23፥24 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ *በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ*።
ዘሌዋውያን 25፥4 *"ስድስት ዓመት እርሻህን ዝራ፥ ስድስት ዓመትም ወይንህን ቍረጥ ፍሬዋንም በሰባተኛው ዓመት ግን ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት፥ ለእግዚአብሔር ሰንበት፥ ትሁን"*

ነዶ ካመጡበት ቀን በኋላ ከሰንበት ማግስት 7×7= 49 ኛው ቀን ሲያልፍ 50 ኛው ቀን እረፍት ያርፋሉ፥ ከኒሳን ወር 7×7= 49 ኛው ዓመት ሲያልፍ 50 ኛው ዓመት ኢዮቤልዩ እረፍት ያርፋሉ፦
ዘሌዋውያን 23፥15 *የወዘወዛችሁትን ነዶ ከምታመጡበት ቀን በኋላ ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቍጠሩ፤ እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቍጠሩ"*።
ዘሌዋውያን 25፥8 *"ሰባት ጊዜ ሰባት አድርገህ የዓመታትን ሰንበት ሰባት ቍጠር፤ የሰባት ዓመታትም ሰንበት ዘመን አርባ ዘጠኝ ዓመት ትቈጥራለህ*።
ዘሌዋውያን 25፥10 *አምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእናንተ ኢዮቤልዩ ነው"*።

እስራኤላውያን አንድ ሰንበት ብቻ አልነበራቸው፥ ከላይ እንደተጠቀሰው ብዙ ሰንበታት ነበሩ። እርሱም፦ "ሰንበታቴን" ይላል፦
ሕዝቅኤል 20፥12 በእኔ እና በእነርሱ መካከል ምልክት ይሆኑ ዘንድ *ሰንበታቴን* ሰጠኋቸው።

እነዚህ ቀንን፣ ወርን፣ ዓመትን እየተጠበቁ የሚታረፉ ሰንበታት ጳውሎስ ደካማ እና የተናቀ ስለሆነ ተሽሯል እያለን ነው፦
ገላትያ 4፥9 *ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን? ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ*።
ዕብራውያን 7፥18 *ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች"*።
ኤፌሶን 2፥14 *በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ"*
ቆላስይስ 2፥16 *እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ "ሰንበት" ማንም አይፍረድባችሁ። እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው*።

ዘሌዋውያን ላይ በአዋጅ የተነገሩትን የትእዛዛትን ሕግ ሰንበታት ናቸው፥ እነዚህ ሰንበታት አካሉን የሚያመላክቱ ጥላ"Typology" ስለሆኑ ተሽረዋል እያለን ነው። ስለዚህ ሰንበታት አዲስ ኪዳን ላይ የሉም።ለእኛ ለሙሥሊሞች የሚኖረው አንድምታ አላህ ለእስራኤላውያን ያዘዘው ሰንበት ለሁሉም ሕዝቦች አለመሆኑ ማሳያ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አዲስ ዓመት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

የፈረንጆች አዲስ ዓመት ጃኑአርይ ነው። “ጃኑአርይ” ማለት “ጃኑስ” የተባለው ጣዖት የሚመለክበት ወር ነው። ይህ በዓል ጁለስ ቄሳር በ 46 ቅድመ-ልደት ስለጀመረው በዚህ ወር ዓመቱ ስለሚቀየር ጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ይባላል። ቁጥሩ ደግሞ ኢየሱስ ከተወለደበት ጀምሮ የሚቆጠር የክርስትና በዓል ያደረገው በ 1582 ድኅረ-ልደት ግሪጎሪ ወይም ጎርጎርዮስ የተባለው ጳጳስ ነው፥ በዚህም የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ይባላል። ይህ ዓመታዊ በዓል ዓረማዊ እና ክርስትናን ቀላቅሎ የያዘ በዓል ነው፥ በዚህ ጊዜ "እንኳን አደረስን" ወይም "እንኳን አደረሳችሁ" ስንል ይህንን በዓል ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ሙሥሊም ያሉት ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *”አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው”*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”በሁለቱ በዓል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና ሐዲስ ብቻ መከተል አለብን፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ ማለት ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው። ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ብቻ ዒድ ያከብራል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አልተበረዘምን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?”* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون

ብዙ ጊዜ ሚሽነሪዎች ከቁርኣን በፊት የነበሩት መጽሐፍት ላለመበረዛቸው እንደማስረጃ የሚያቀርቡት "የአላህን ንግግሮች ለዋጭ የለም" የሚለውን ይዘው ነው፥ ነገር ግን ዐውደ-ንባቡን ብንመለከት እየተናገረ ያለው ስለ መመሪያ ቃል ሳይሆን ስለ ውሳኔ ቃል ነው። ይህንን ለመረዳት ስለ አላህ ቃል ጥልልና ጥንፍፍ ያለ መረዳት ያስፈልገናል። “ከላም” كَلَٰم የሚለው ቃል “ከለመ” كَلَّمَ ማለትም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ንግግር” ማለት ነው። ይህ የአላህ ንግግር በሁለት ይከፈላል፥ እርሱም፦ አንዱ “ከላሙ አት-ተሽሪዒይ” كَلَٰم التَشْرِعِي ሲባል፥ ሁለተኛው ደግሞ “ከላሙ አት-ተክውኒይ” كَلَٰم التَكْو۟نِي ይባላል። ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
“ከላሙ አት-ተሽሪዒይ”
“ተሽሪዒይ” تَشْرِعِي የሚለው ቃል “ሸረዐ” شَرَّعَ‎ ማለትም “ደነገገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ድንጋጌ” ወይም “ሕግጋት” ማለት ነው፥ ይህ ሸሪዓህ ከአላህ ወደ ነቢያቱ የሚወርድ መመሪያ፣ መርሕ፣ ሥርዓት ነው። “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው። ተውራት፣ ዘቡር፣ ኢንጂል፣ ቁርኣን ከላሙ አት-ተሽሪዒይ ናቸው። ከመጽሐፉ ሰዎች ከቁርኣን በፊት የነበሩትን የአላህ ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው በርዘውታል፦
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?”* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون

“የሚለውጡት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዩሐረፉነሁ” يُحَرِّفُونَهُ ሲሆን “የሚበርዙት” ማለት ነው። “ዩሐረፉ” يُحَرِّفُ የሚለው አላፊ ግስ “ሐረፈ” حَرَّفَ ማለትም “በረዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። የሚበርዙት ፊደሉ “ሐርፍ” حَرْف ሲባል፥ የመበረዙ ድርጊቱ ደግሞ “ተሕሪፍ” تَحْرِيف ይባላል። የመጸሐፉ ሰዎች ከአላህ የወረደውን እዉነት በዉሸት ቀላቅለውታል፥ ሊበርዙት የቻሉት አላህ እነዚህን መጽሐፍት እንዲጠብቁ ሓላፍትና የሰጣቸው ለሰዎች ስለሆነ ነው፦
3፥71 *የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ?* “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
5፥44 ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም *ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉት* እና በእርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት ይፈርዳሉ፡፡ وَالرَّبَّانِيُّونَ وَالْأَحْبَارُ بِمَا اسْتُحْفِظُوا مِن كِتَابِ اللَّهِ وَكَانُوا عَلَيْهِ شُهَدَاءَ ۚ

"እንዲጠብቁ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በየዘመናቱ ነቢያት ስለሚነሱ አዲስ ወሕይ ሲወርድ የተበረዘውን በአዲሱ ወሕይ መታረም ይችል ነበር። ነገር ግን ከነቢያችም”ﷺ” በኃላ የሚመጣ ነብይ፣ የሚላክ መልእክተኛ እና የሚወርድ ተንዚል ስለሌለ አላህ ቁርኣን እራሱ አውርዶ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት እንዳመጣበት እራሱ ይጠብቀዋል፦
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም*፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ
ነጥብ ሁለት
"ከላሙ አት-ተክውኒይ"
“ተክውኒይ” تَكْو۟نِي የሚለው ቃል “ከወነ” كَوَّنَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኹነት” ማለት ነው። አላህ በቃሉ “ኩን” كُن ማለትም “ኹን” የሚለው ይኾናል፦
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

“ቃላችን” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በቁርኣን አላህ ይሆናል ብሎ የተናገረውን ንግግር ማንም ለዋጭ የለም። አላህ የትንሳኤ ቀን "ኹን" የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን ነው፥ ይህ የውሳኔ ንግግር ከመሆኑ በፊት በቁርኣን ስለተነገረ ይህ የነገረን ቃል እውነት ነው፦
6፥73 እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ *«ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን አስታውስ፡፡ ቃሉ እውነት ነው*፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ ۖ وَيَوْمَ يَقُولُ كُن فَيَكُونُ ۚ قَوْلُهُ الْحَقُّ ۚ وَلَهُ الْمُلْكُ يَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ ۚ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ

"ቃሉ እውነት ነው" የሚለው ይሰመርበት። ይህንን የአላህ የውሳኔ ቃል ነው፥ ይህንን ንግግር ማንም መለወጥ አይችልም፦
6፥115 *የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትኾን ተፈጸመች፡፡ ለቃላቱ ለዋጭ የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡ وَتَمَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ صِدْقًا وَعَدْلًا ۚ لَّا مُبَدِّلَ لِكَلِمَاتِهِ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

"ተፈጸመች" የሚለው ተነግሮ የነበረውን ንግግር መሆኑ ይሰመርበት። ይህንን አላህ "ኹን" የሚለውን የውሳኔ ንግግር ማንም መለወጥ አይችልም፥ "ሙበደል" مُبَدِّل ማለት "ለዋጭ" ማለት ሲሆን ይህንን የውሳኔ ቃል ማደናቀፉ፣ ማስቀየሱ፣ መለወጡ ደግሞ "ተብዲል" تَبْدِيل ይባላል፦
10፥64 *ለእነርሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም*፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ لَهُمُ الْبُشْرَىٰ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ ۚ لَا تَبْدِيلَ لِكَلِمَاتِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መለወጥ" ለሚለው የገባ ቃል "ተብዲል" تَبْدِيل መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ አላህ በቅርቢቱ ሕይወት እና በመጨረሻይቱ ሕይወት የተናገረውን ብስራት ማንም አይለውጠውም። ሲቀጥል ዐውደ-ንባቡን ላይ ስለ ቀድሞዎቹ መጽሐፍት ምንም ሽታው የለም። ሢሰልስ "የአላህን ንግግሮች ለዋጭ የለም" የሚለው የመመሪያ ቃል ነው ብንል እንኳን "ጃአከ" جَاءَكَ ማለትም "መጣልክ" የሚለው ነቢያችንን"ﷺ" ስለሆነ ቁርኣንን ብቻ የሚያመለክት ነው፦
6፥34 *"የአላህንም ንግግሮች ለዋጭ የለም፡፡ ከመልክተኞቹም ወሬ በእርግጥ መጣልህ"*፡፡ وَلَا مُبَدِّلَ لِكَلِمَاتِ اللَّهِ ۚ وَلَقَدْ جَاءَكَ مِن نَّبَإِ الْمُرْسَلِينَ

በቁርኣን ውስጥ አላህ የውሳኔ ንግግር ተናግሮ ያንን ንግግር መለወጥ የሚችል ማንም የለም፦
18፥27 *"ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ለቃላቶቹ ለዋጭ የላቸውም*፡፡ ከእርሱም በቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም፡፡ وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّكَ ۖ لَا مُبَدِّلَ لِكَلِمَاتِهِ وَلَن تَجِدَ مِن دُونِهِ مُلْتَحَدًا

"ኢለይከ" إِلَيْكَ ማለትም "ወደ አንተ" የሚለው ነጠላ ማንነት ነቢያችንን"ﷺ" ብቻ ስለሚያመለክት "ለቃላቶቹ ለዋጭ የላቸውም" የሚለው ወደ እርሳቸው የተወረደውን ቁርኣንን ብቻ ያመለክታል።
ሙግቱን ስንደመድመው የመመሪያ ንግግር የመለወጡ መርሐ-ግብር “ተሕሪፍ” تَحْرِيف ሲባል፥ የውሳኔ ንግግር የመለወጡ መርሐ-ግብር "ተብዲል" تَبْدِيل ይባላል። "ተሕሪፍ" እና "ተብዲል" በይዘትም ሆነ በአይነት በመንስኤም ሆነ በውጤት ሁለት ለየቅል የሆኑ ቃላት ናቸው፥ ይህ ፍርጥም ያለ መፈናፈኛ የሚያሳጣ ሙግት ነው።
ሲቀጥል "መለወጥ" የሚለው ቃል ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ መታየት ያለበት።
ሢሠልስ የአይሁድ ሆነ የክርስትና ምሁራን ባይብል የአምላክ ንግግር እና የሰው ንግግር ቅልቅል እንደሆነ ያምናሉ፥ ይህ በግሪክ “ስይነርጎስ” ይባላል። “ስይነርጎስ” συνεργός ማለትም “ቅልቅል” ማለት ነው፥ ይህም ለመበረዙ አንዱ ማሳያ ነው። ሁለተኛ ማሳያ አላስፈላጊ ያሉትን መጽሐፍ “አፓክሪፋ” በማለት ቀንሰዋል፥ "አፓክሪፋ" የሚለው ቃል “አፓክሩፎስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ እውነትን እያወቁ በማደባበስና በማለባበስ ደብቀዋል።
ስለዚህ "የአላህን ንግግሮች ለዋጭ የለም" የሚለውን ከቁርኣን በፊት የነበሩትን ግልጠተ-መለኮት ነው ማለት በምንም አግባብ ጸጉር ስንጠቃ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወሰን አትለፉ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና፥ ወሰንን ማለፍ በበዳዮች ላይ እንጂ የለም ወሰን አትለፉባቸው፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
2፥193 *ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሉዋቸው፡፡ ቢከለክሉም ወሰንን ማለፍ በበዳዮች ላይ እንጂ የለም ወሰን አትለፉባቸው*፡፡ وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ ۖ فَإِنِ انتَهَوْا فَلَا عُدْوَانَ إِلَّا عَلَى الظَّالِمِينَ

"ወሰንንም አትለፉ" መርሕ እስከ ጥቃቅን ነፍሳት ድረስ ይሄዳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 56, ሐዲስ 228
አቢ ሁራይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አንዲት ጉንዳን ከነቢያት መካከል አንዱ ነቢይ ነከሰችው፥ እርሱም የጉንዳኖች መንደር እንዲቃጠል አዘዘ። ከዚያም አላህም ወደ እርሱ፦ "የነከሰችህ አንዲት ጉንዳን ናት፥ አንተ ግን ያቃጠልከው አላህ የሚያወድሱትን ከብዙኃት ጉንዳኖች ብዙኃኑን ነው" ብሎ ወሕይ አወረደለት"*። وَأَبِي، سَلَمَةَ أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ قَرَصَتْ نَمْلَةٌ نَبِيًّا مِنَ الأَنْبِيَاءِ، فَأَمَرَ بِقَرْيَةِ النَّمْلِ فَأُحْرِقَتْ، فَأَوْحَى اللَّهُ إِلَيْهِ أَنْ قَرَصَتْكَ نَمْلَةٌ أَحْرَقْتَ أُمَّةً مِنَ الأُمَمِ تُسَبِّحُ اللَّهِ

ነቢያችን"ﷺ" እና የእርሳቸው ፈለግ የሚከተሉ ወሰን አያልፉም፦
11፥112 *እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

አሏህ የሰውን ሐቅ ከማይነኩ ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አረጋጋጭ መጽሐፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

35፥31 ያም ከመጽሐፉ ወደ አንተ ያወረድንልህ *"ከበፊቱ ላለው አረጋጋጭ"* ሲኾን እርሱ እውነት ነው፡፡ አላህ በርግጥ በባሮቹ ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነው፡፡ وَٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ هُوَ ٱلْحَقُّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ بِعِبَادِهِۦ لَخَبِيرٌۢ بَصِيرٌۭ

ክርስቲያን ሚሽነሪዎች በተለይ የዘመናችን የኢሥላም ጥላሸት ቀቢዎች ሳም ሻሙስ፣ ዲቪድ ሁድ እና አራጋቢዎቹ በኢስላም ላይ የሚያስተምሩት ጽርፈት ዕቡይ ተግዳሮት ሆኖ እኩያንን የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል፤ እነዚህ ሚሽነሪዎች እኛ ሙስሊሞች ክርስትና ላይ ላስነሳነው ስሙር ሙግት እልህ ይዟቸው የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት ይዟቸው እንደሆነ እልሃቸው ያሳብቅባቸዋል፤ ዐሊሞቻችን፦ "መልህቅ ውኃ ውስጥ ኖረ እንጂ መቼ ዋና ተማረ" ይላሉ፤ እነዚህ ኃሳውያን እስልምናን ከመዋቅሩ እና ከትምህርት መርሃ-ግብሩ ቁጭ ብለው የተማሩት ትምህርት አይደለም፤ ስለዚህ እኛ ሙስሊሞች የታሪክ ምፀት ከዐሊሞቻችን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይለናል፤ ይህን ለማድረግ አስረግጦ እና ረግጦ መረዳትና ማስረዳት ይጠበቅብናል፤ እነዚህ ነውጠኛ፦ ቁርአን ከእኛ ጋር ያለውን ባይብል ሊያረጋግጥ ወርዷል" ይሉናል፤ እስቲ የተነሳውን ይህንን ስሁት ሙግት ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
" ኑዙል"
"ኑዙል" نُزُل የሚለው ቃል "ነዝዘለ" نَزَّلَ ማለትም "አወረደ" ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን "ግህደተ-መለኮት"Revelation" ማለት ነው፣ ቁርአን የወረደው ወደ ነብያችን"ﷺ" ነው፦
38፥29 ይህ *"ወደ አንተ ያወረድነው"* ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ አወረድነው፡፡ كِتَٰبٌ أَنزَلْنَٰهُ إِلَيْكَ مُبَٰرَكٌۭ لِّيَدَّبَّرُوٓا۟ ءَايَٰتِهِۦ وَلِيَتَذَكَّرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ

ነገር ግን አላህ በሁለተኛ መደብ "ወደ እናንተ" አወረደ በማለት ወደ እኛ እንዳወረደ ይናገራል፦
21፥10 ክብራችሁ በውስጡ ያለበትን መጽሐፍ *"ወደ እናንተ በእርግጥ አወረድን"*፡፡ አታውቁምን? لَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ كِتَٰبًۭا فِيهِ ذِكْرُكُمْ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

ቁርአን የወረደው ወደ ነብያችን"ﷺ" ሆኖ ሳለ በብዙ ተሳቢ ተውላጠ ስም "ወደ እኛ" በተወረደው አመንን! በሉ በማለት ይናገራል፦
2፥136 «በአላህ እና *"ወደ እኛ በተወረደው"* ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» *"በሉ"*፡፡ قُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَآ أُنزِلَ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَمَآ أُوتِىَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَآ أُوتِىَ ٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍۢ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

ልብ አድርግ ወደ ነብያችን"ﷺ" ወርዶ ሳለ ወደ "እኛ" ወይም "ወደ "እናንተ" ካለ በተመሳሳይም ወደ ነብያት ወርዶ እያለ አላህ አይሁዳውያንንና ክርስቲያኖችን "ወደ እናንተ" የተወረደው ሲል ከላይ በተባለበት ስሌትና ቀመር ነው፦
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ «በዚያ *"ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው"* አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» *"በሉ"*። وَلَا تُجَٰدِلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمْ وَٰحِدٌۭ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

ልብ አድርግ "ወደ እኛ በተወረደው" የሚለው ነብያችንን"ﷺ" እንደሚያመለክት ሁሉ "ወደ እናንተም በተወረደው" የሚለው ነብያትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። እውን ተውራትንና ኢንጂልን የወረደው ለማን ነው? ለሙሳና ለዒሳ እንደሆነ እሙን ነው። ይህንን ነጥብ ከያዘን አላህ "በመጽሐፍቱ እመኑ" ሲል ከራሱ የወረዱትን "ኑዙል" መሆኑ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ ነው፤ ይህ ከገባን ወደሚቀጥለው ነጥብ መሄድ እንችላለን፦
ነጥብ ሁለት
"ሙሰድዲቃን"
“ሙሰድዲቃን” مُصَدِّقًا ማለት “አረጋጋጭ” ማለት ሲሆን ቁርአን የሚያረጋግጠው ከበፊቱ ያለውን ነው፤ ከበፊቱ ያለው ደግሞ ከአላህ የወረዱት ናቸው፦
35፥31 ያም ከመጽሐፉ ወደ አንተ ያወረድንልህ *"ከበፊቱ ላለው አረጋጋጭ"* ሲኾን እርሱ እውነት ነው፡፡ አላህ በርግጥ በባሮቹ ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነው፡፡ وَٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ هُوَ ٱلْحَقُّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ بِعِبَادِهِۦ لَخَبِيرٌۢ بَصِيرٌۭ
4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው፤ በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ፤ በዚያም *"ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ"*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ ءَامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِى نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ مِن قَبْلُ

"ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ" የሚለው ይሰመርበት። ስለዚህ ቁርአን የሚያረጋግጠው ከአላህ ወደ ነብያት የተወረዱትን መጽሐፍት ብቻ ነው፤ ይህ ሆኖ ሳለ አላህ ስለ አይሁዳውያንና ክርስቲያኖች በሁለተኛ መደብ "ከእናንተ ጋር ያለውን" የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩት እመኑ ይላቸዋል፦
2፥41 *"ከእናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ"* ሆኖ ባወረድኩትም እመኑ፡፡ በእርሱም የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ፡፡ በአንቀጾቼም ጥቂትን ዋጋ አትለውጡ፡፡ እኔንም ብቻ ተጠንቀቁ። وَءَامِنُوا۟ بِمَآ أَنزَلْتُ مُصَدِّقًۭا لِّمَا مَعَكُمْ وَلَا تَكُونُوٓا۟ أَوَّلَ كَافِرٍۭ بِهِۦ ۖ وَلَا تَشْتَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِى ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا وَإِيَّٰىَ فَٱتَّقُونِ

ልብ አድርግ ከላይ በነበረን ነጥብ "ወደ እናንተ" የሚለው ነብያትን እንደሚያመለክት አይተን ነበር፤ አሁንም "ከእናንተ" የሚለው ነብያትን ያመለክታል፦
3፤81 *"አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ"* ከዚያም *«ከእናንተ ጋር ላለው የሚያረጋግጥ መልክተኛ* ቢመጣላችሁ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ አስታውስ፡፡ አረጋገጣችሁን በዚህም ላይ ኪዳኔን ያዛችሁምን» አላቸው፡፡ «አረጋገጥን» አሉ፡፡ «እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው፡፡ وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ لَمَآ ءَاتَيْتُكُم مِّن كِتَٰبٍۢ وَحِكْمَةٍۢ ثُمَّ جَآءَكُمْ رَسُولٌۭ مُّصَدِّقٌۭ لِّمَا مَعَكُمْ لَتُؤْمِنُنَّ بِهِۦ وَلَتَنصُرُنَّهُۥ ۚ قَالَ ءَأَقْرَرْتُمْ وَأَخَذْتُمْ عَلَىٰ ذَٰلِكُمْ إِصْرِى ۖ قَالُوٓا۟ أَقْرَرْنَا ۚ قَالَ فَٱشْهَدُوا۟ وَأَنَا۠ مَعَكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ

ለነቢያት የሰጣቸውን መጽሐፍ ከነብያቱ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ መልእክተኛ ነብያችን"ﷺ" ናቸው፤ ልብ አድርግ "ከእናንተ ጋር ላለው" ብሎ ያለው ከነብያትን ጋር ያለውን እንደሆነ ይህ አንቀፅ ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል፤ ታዲያ ወደ ነቢያት የተወረዱትን እና ከነብያት ጋር ያሉትን "ኑዙል" ለምን ወደ አይሁድ እና ክርስቲያን በማስጠጋት "ወደ እናንተ" "ከእናንተ ጋር" በማለት ይናገራል? የሚለውን ሙግት በአንድ ናሙና መረዳት ይቻላል፤ ለምሳሌ በሙሳ ዘመን የሙሳ ህዝቦች ሙሳን፦ "ሙሳ ሆይ! አላህን በግልጽ እስከምናይ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም» ባሉት ጊዜ መብረቅ ያዛቸው፦
2፥55 «ሙሳ ሆይ! አላህን በግልጽ እስከምናይ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም» *"ባላችሁም"* ጊዜ አስታውሱ፡፡ *"እናንተም እየተመለከታችሁ መብረቅ ያዘቻችሁ*፡፡ وَإِذْ قُلْتُمْ يَٰمُوسَىٰ لَن نُّؤْمِنَ لَكَ حَتَّىٰ نَرَى ٱللَّهَ جَهْرَةًۭ فَأَخَذَتْكُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ وَأَنتُمْ تَنظُرُونَ

ግን አላህ በነብያችን"ﷺ" ዘመን ያሉትን አይሁዳውያን፦ "ሙሳ ሆይ! አላህን በግልጽ እስከምናይ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም" ያሉት እነርሱ እንደሆነ ለማሳየት "ባላችሁም ጊዜ አስታውሱ" ይላቸዋል፤ መብረቅ የያዛቸው በሙሳ ጊዜ የነበሩት ሆነው ሳለ "እናንተም እየተመለከታችሁ መብረቅ ያዘቻችሁ" በማለት ይናገራል፤ ምን ይሄ ብቻ ደመናን ያጠለለውና መናን እና ድርጭትን ያወረደው በእነርሱ ላይ እንደሆነ እና ወይፈንን አምላክ አድርገው የያዙት እነርሱ እንደሆኑ ይናገራል፦
2፥57 *"በእናንተም ላይ"* ደመናን አጠለልን፡፡ *"በእናተም ላይ"* መናን እና ድርጭትን አወረድን፡፡ وَظَلَّلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْمَنَّ وَٱلسَّلْوَىٰ
2፥51 ሙሳንም አርባን ሌሊት በቀጠርነው ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ ከዚያም ከእርሱ መኼድ በኋላ *"እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን አምላክ አድርጋችሁ ያዛችሁ"*፡፡ وَإِذْ وَٰعَدْنَا مُوسَىٰٓ أَرْبَعِينَ لَيْلَةًۭ ثُمَّ ٱتَّخَذْتُمُ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَنتُمْ ظَٰلِمُونَ

አላህ በሙሳ ጊዜ መናን እና ድርጭትን አውርዶ ግን በነብያችን"ﷺ" ዘመን ያሉትን አይሁዳውያንን በሁለተኛ መደብ "በእናተም ላይ" መናን እና ድርጭትን አወረድን ካለ፤ በተመሳሳይ ወደ ነብያት ያወረደው በነብያችን"ﷺ" ዘመን ወደነበሩት አይሁድ እና ክርስቲያን "ወደ እናንተ አወረድን" ቢል እና ከነብያት ጋር ያለውን በነብያችን"ﷺ" ዘመን ወደነበሩት አይሁድ እና ክርስቲያን "ከእናንተ ጋር ያለውን" ቢለው ምን ያስደንቃል?
ነጥብ ሶስት
"የደይሂ"
"የደይሂ" يَدَيْهِ ማለት "ከበፊቱ" ማለት ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎሽ፦ "የድ" يَد ማለት "እጅ" ማለት ነውና "ሊማ በይነ የደይሂ" لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ ማለት "በእጆቻቸው መካከል ያለውን" ሲል "በእኛ እጆች ያሉትን የግሪክ ኮይኔ እንደ-ክታባት"manu-scripts" ነው" የሚል ስሁት ሙግት አላቸው፤ ሲጀምር "የደይሂ" ማለት "ከበፊቱ" ማለት ሲሆን "ኸልፊሂ" خَلْفِهِۦ ማለትም "ከኃላው" ለሚለው ተቃራኒ ሆኖ የሚመጣ ነው፦
41፤42 *"ከኋላውም ከፊቱም"* ውሸት አይመጣበትም፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

ታዲያ "የደይሂ" ማለት "በእጆቻቸው" ማለት ነው ብለው ከተረጎሙት "ኸልፊሂ" ምን ሊሆን ነው? ሲቀጥል "ሂ" ِِه የሚለው ተውላጠ ስም ነጠላ እንጂ ብዜት ስላልሆነ እንዳሰቡት "በእጆቹ" እንጂ "በእጆቻቸው" አይሆንም፤ ምክንያቱም "ሂ" ነጠላ ሲሆን "ሂም" هَُِمْ ብዜት ስለሆነ፤ ሢሰልስ "ሂ" የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም አውዱ ላይ ያለው ቁርአን ነው፤ ታዲያ ቁርአን "እጅ" አለውን? ሲያረብብ "የድ" يَد ማለት እና "የደይ" يَدَيْ ማለት በየትኛው ሒሳብ ነው አንድ ትርጉም ያላቸው? "የደይ" ማለት "ፊት" ማለት ሲሆን "ኃላ" ለሚል ተቃራኒ ሆኖ "ቀብል" قَبْل ማለት ነው፤ ልብ አድርግ "ከኋላቸው" ለሚለው ተቃራኒ "ከበፊታቸው" ሲሆን የመጣው ቃል "አይዲሂም" أَيْدِيهِمْ ነው፦
19፥64 (ጂብሪል አለ) «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ *"በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው"* በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም፡፡ وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُۥ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّۭا

ስለዚህ ከላይ የተነሳው ስሁት ሙግት ውኃ የሚቋጥር አይደለም። የንዑዱ የአላህ ኅሩያን እንዲህ ሳይቃጠል በቅጠል ድባቅ ያስገቡታል፥ ዐሊሞቻችን ጋር ያሉት ዒልም በስፋትና በልፋት፤ በጥልቀትና በምጥቀት ነው። ሡመ አልሓምዱ ሊሏህ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም