ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
💚💛ሐምሌ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅዱሳን 72ቱ አርድእት (ዛሬ ሁሉም ይታሠባሉ)
4.ቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት
5.ቅድስት መስቀል ክብራ (የቅዱስ ላሊበላ ሚስት)
6.ቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ
7.ቅዱሳት አንስት (ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና
አክስቲያና-የቅዱስ ዼጥሮስ ተከታዮች)
🌿ወርሐዊ በዓላት🌿
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
3.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
4.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
"ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው:: "
የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይሕንን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ:: እኔም
እልሃለሁ:: አንተ #ዼጥሮስ ነህ:: በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ:: የገሃነም ደጆችም አይችሏትም:: የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ:: በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ
ይሆናል:: በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ.16:17)

"በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና:: የምሔድበትም ጊዜ ደርሷል:: መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት #የጽድቅ_አክሊል ተዘጋጅቶልኛል:: ይሕንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል:: " (2ጢሞ. 4:6)
@senkesar @senkesar