♥ቅድስት #ክርስቶስ_ሠምራ♥
እጅግ የከበረችና የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ክርስቶስ
ሠምራን እናመሰግናታለን:: እርሷ በሁሉ ጐዳና ፍጹምነትን
ያሳየች ኢትዮዽያዊት እናት ናት:: ገና ከልጅነት የነበራት
የትሕትናና የመታዘዝ ሕይወት እጅግ ልዩ ነበር:: እናታችን
ቅድስናን ያገኘችው ገና በትዳር ውስጥ እያለች ነው::
+ከተባረከ ትዳሯ 12 ልጆችን አፍርታ: ምጽዋትን የዕለት ተግባሯ
አድርጋ ኑራለች:: በዚህ ደግነቷም ሙት እስከ ማንሳት
ደርሳለች:: አብያተ ክርስቲያናትን አንጻ አንድ ልጇ ዳግማዊ
ቂርቆስን አዝላ ምናኔ ወጥታልች::
+በደብረ ሊባኖስ የቆየችው ቅድስት እናት ተጋድሎዋን
የፈጸመችው ግን #ጣና_ሐይቅ ውስጥ ነው:: በተለይ ለ22
ዓመታት ሐይቁ ውስጥ አካሏ አልቆ: አሣ በሰውነቷ ውስጥ
እስከሚያልፍ ድረስ ተጋድላለች:: በቀኝና በግራ 12 ጦሮችን
ተክላም ጸልያለች::
+ብዙ ኃጥአንን አማልዳ: 12 ክንፎችን አብቅላ: ከፍ ከፍ
ብላለች:: ከርሕራሔዋ ብዛት የተነሳ ሰይጣንን እንኩዋ
ለማስታረቅ ሞክራለች:: ጌታም ከሲዖል ነፍሳትን እንድታወጣ
ፈቅዶላታል:: ቅድስት #ክርስቶስ_ሠምራ ያረፈችው በዚህ ዕለት
ሲሆን አጽሟ ዛሬ በራሷ ገዳም (ጣና ዳር) ይገኛል::
እጅግ የከበረችና የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ክርስቶስ
ሠምራን እናመሰግናታለን:: እርሷ በሁሉ ጐዳና ፍጹምነትን
ያሳየች ኢትዮዽያዊት እናት ናት:: ገና ከልጅነት የነበራት
የትሕትናና የመታዘዝ ሕይወት እጅግ ልዩ ነበር:: እናታችን
ቅድስናን ያገኘችው ገና በትዳር ውስጥ እያለች ነው::
+ከተባረከ ትዳሯ 12 ልጆችን አፍርታ: ምጽዋትን የዕለት ተግባሯ
አድርጋ ኑራለች:: በዚህ ደግነቷም ሙት እስከ ማንሳት
ደርሳለች:: አብያተ ክርስቲያናትን አንጻ አንድ ልጇ ዳግማዊ
ቂርቆስን አዝላ ምናኔ ወጥታልች::
+በደብረ ሊባኖስ የቆየችው ቅድስት እናት ተጋድሎዋን
የፈጸመችው ግን #ጣና_ሐይቅ ውስጥ ነው:: በተለይ ለ22
ዓመታት ሐይቁ ውስጥ አካሏ አልቆ: አሣ በሰውነቷ ውስጥ
እስከሚያልፍ ድረስ ተጋድላለች:: በቀኝና በግራ 12 ጦሮችን
ተክላም ጸልያለች::
+ብዙ ኃጥአንን አማልዳ: 12 ክንፎችን አብቅላ: ከፍ ከፍ
ብላለች:: ከርሕራሔዋ ብዛት የተነሳ ሰይጣንን እንኩዋ
ለማስታረቅ ሞክራለች:: ጌታም ከሲዖል ነፍሳትን እንድታወጣ
ፈቅዶላታል:: ቅድስት #ክርስቶስ_ሠምራ ያረፈችው በዚህ ዕለት
ሲሆን አጽሟ ዛሬ በራሷ ገዳም (ጣና ዳር) ይገኛል::