ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
💚💛አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!💛❤️
ሚያዝያ 19-የፋርሱ ኤጲስቆጶስ #አባ_ስምዖን_ከ150_ሰማዕታት ጋር በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ይኸውም ቅዱስ
የአርማንያ ሰው ሲሆኑ የፋርስ ሀገር ኤጲስቆጶስ ሆነው
ካገለገሉ በኋላ ከእርሳቸው ጋር ከነበሩ 150 ሰዎች ጋር
በሰማዕትነት ያረፉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በዘመኑ ባሶር
የተባለው ከሃዲ ንጉሥ ለጣዖት ካልሰገዳችሁ በማለት
ክርስቲያኖችን እጅግ ያሠቃይ ጀመር፡፡ አባ ስምዖንም ለዚህ
ከሃዲ ንጉሥ ስለ ጣዖቱ ከንቱነት ነቀፉት፡፡ የጌታችንን
የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር በመንገር ከዚህ ክፉ ሥራው
እንዲመለስ ካለተመለሰም ክርስቲያኖችን ቢያሠቃያቸውም
ክርስቶስን በማመን እስከመጨረሻው እንደሚጸኑ በደብዳቤ
ገለጹለት፡፡
ንጉሡም የአባ ስምዖንን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ እጅግ ተቆጥቶ
አባ ስምዖንን አሥሮ አሥር ቤት ውስጥ ጣላቸው፡፡
ከእርሳቸውም በፊት 150 ክርስቲያኖችን አሥሮ ያሠቃያቸው
ነበር፡፡ አባ ስምዖንም በእሥር ቤት የታሰሩትን ክርስቲያኖች
እየመከሩና እያጽናኗቸው በመንግሥተ ሰማያት
ስለሚጠብቃቸው ክብር እየነገሯቸው ሰማዕትነታቸውን በድል
እንዲፈጽሙ መከሯቸው፡፡ ንጉሡም ሰማዕታቱን ብዙ
ካሠቃያቸው በኋላ ሚያዝያ 19 ቀን አባ ስምዖንን እና
150ዎቹን ክርስቲያኖች ወደ ፍርድ አደባባይ አውጥቶ ሁሉንም
በየተራ አንገታቸውን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕትነት
ፍጻሜያቸው ሆነ፡፡ ሁሉም የክብርን አክሊል በመንግሥተ
ሰማያት ተቀዳጁ፡፡
የአባ ስምዖንና የ150ዎቹ ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸው
ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
@ በእንተ ቅዱሳን ኅሩይን