♥እንኩዋን ለካህኑ #ሰማዕት_ቅዱስ_አልዓዛር እና
ለቅዱሳን ቤተሰቡ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም
አደረሳችሁ ♥
#ቅዱስ_አልዓዛር_ካህን
ይህ ቅዱስ #የብሉይ_ኪዳን_ሰማዕታት ተብለው
ከሚታወቁት ዋነኛው ነው:: የነበረበት ዘመንም ቅድመ ልደተ
ክርስቶስ ሲሆን " #ዓመተ_መቃብያን / #ዘመነ_ካህናት "
ይባላል::
በወቅቱ ሰሎሜ የምትባል ደግ ሴት አግብቶ ይኖር የነበረው
ቅዱስ አልዓዛር በኢየሩሳሌም ተወዳጅ ነበር:: ሐረገ ትውልዱ
ከአሮን ወገን ነውና በክህነቱ ተግቶ ያገለግል ነበር:: በዚያ
ላይ ሊቀ ካህንነትን በመመረጡ ሕዝቡን ይሠራ: ያስተምር:
ያስተዳድር ነበር::
ቅዱስ አልዓዛር ከተባረከች ሚስቱ ሰሎሜ 7 ወንዶች ልጆችን አፍርቷል:: እነርሱንም በሥርዓት አሳድጐ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጐ ነበር:: በዚያው
ዘመን በኢየሩሳሌም አካባቢ የሚኖሩ 3 እኩያን (ክፉ) ካህናት
ነበሩ:: እነዚሁም ሕዝቡን ከማስቸገር: ፈጣሪን ከማሳዘን ቦዝነው
አያውቁም ነበር:: የክፋታቸው መጨረሻ ግን የገዛ ሃገራቸውን
ማጥፋት ሆነ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- 3ቱም ተመካክረው
የአልዓዛርን የሊቀ ካህንነት ቦታ ሊቀሙ ወስነው ወደ እርሱ
ሔዱና እንዲህ አሉት::
"ሹመት በተርታ: ሥጋ በገበታ" ሲሆን ያምራልና እኛ
በተራችን በወንበሩ ላይ እንቀመጥ::" እርሱ ግን "ሕዝቡን ጠይቃችሁ ተሾሙ" አላቸው:: እነርሱም
ሕዝቡን ጠርተው "ሹመት ይገባናል" ቢሏቸው ሕዝቡ መልሶ
"አልዓዛርን የሾመው እግዚአብሔር ነውና እናንተም ከፈጣሪ ጠይቃችሁ ተሾሙ" አሏቸው:: በዚህ ጊዜ 3ቱ እኩያን ተቆጡ:: ምክንያቱም እግዚአብሔር እንደ ማይሰጣቸው ያውቃሉና:: ወዲያው ግን 3ቱም
ከአካባቢው ጠፉ:: ከኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ጨካኙ
የግሪክ ንጉሥ አንጥያኮስ ሔዱ::
+አንጥያኮስ ማለት "ቀኝ ዐይናችሁን ገብሩልኝ" የሚል ንጉሥ ነው:: እርሱን "#ኢየሩሳሌም ባለቤት የላትምና ሒደህ ውረራት" አሉት:: "አጥሩ ጥብቅ ነው:: በምን እገባለሁ?"
ቢላቸው "እኛ በመላ እናስገባሃለን" አሉት:: እርሱም
240,000 ሠራዊት አስከትቶ ወረደ:: እነርሱ ቀድመው ወደ ኢየሩሳሌም ገብተው ያስወሩ ጀመር::
"እናንተ ሹመት ብትነሱንም እኛ ግን አንጥያኮስን ያህል ንጉሥ
በእሥራኤል አምላክ አሳምነን መጣን" እያሉ ይሰብኩ ገቡ::
ቅዱስ አልዓዛር "አትስሟቸው:: በዚያም ላይ አሕዛብ
የተቀደሰውን ምድር መርገጥ የለባቸውም" ብሎ ነበር::
ነገር ግን አንዳንድ ችኩሎች አይጠፉምና ፈጥነው
የከተማዋን በር ከፈቱት:: ሠራዊቱን ደብቆ ትንሽ ራሱን የቆመ
የመሰለው አንጥያኮስ በምክንያት: በክፋትና በመላ ሁሉን
ሠራዊቱን አስገባ:: የሚገርመው በጊዜው የከተማዋ ሕዝብ
12 እልፍ (120,000) ሲሆን ንጉሡ ያስገባው ሠራዊት ግን
24 እልፍ (240,000) ሆኖ ተገኘ::
ወዲያው አንጥያኮስ ሕዝቡን ሰበሰበና አልዓዛርን ለብቻው
ጠርቶ ተናገረው:: "አንተ አምላክህን እንደምትወድ
ሰምቻለሁ:: አንተ የበጉን መስዋዕት በልተህ: #ለስዕለ_
ኪሩብ ሰግደህ: ሕዝቡን ግን እሪያ (አሳማ) እንዲበላና
ለጸፀሐይ እንዲሰግድ አድርግልኝ" አለው::
ቅዱስ አልዓዛር መለሰለት:- "እግዚአብሔር የሾመኝኮ በጐ
ሃይማኖትን ላስተምር እንጂ ለክፋት አይደለም:: ለሕዝቤ
የክፋት አብነት ፈጽሞ አልሆንም" አለው:: ያን ጊዜ ንጉሡ
በቅዱሱ ላይ ተቆጣ:: "የምልህን ካላደረግህ ብዙ ግፍ
ይደርስብሃል" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "የፈለግኸውን አድርግ"
አለው:: በዚያን ጊዜ ንጉሡ የቅዱሱን ሚስትና 7 ልጆች
እንዲያመጡለት አዘዘ:: ቅዱሱ እያየ ከፊቱ ላይ 7ቱንም
ልጆቹን በሰይፍ አስመታቸውና 7ቱም ወደቁ:: ለአንድ አባት
ይህ የመጨረሻው መራራ ፈተና ነው:: #አልዓዛር ግን ምን
አንጀቱ በኀዘን ቢቃጠልም ከልጆቹ ለእግዚአብሔር አድልቷልና
ቻለው ታገሠው::
በዚህ ለውጥ እንዳልመጣ ያየው ንጉሡ ሌላ ፍርድ
ተናገረ:: ቅዱሱንና ሚስቱን ( #ሰሎሜን ) በፈትል ጠቅልለው
በሠም ነከሯቸው:: (ጧፍ እንደሚሠራበት መንገድ ማለት
ነው:: )
አሁንም ግን ከአምልኮታቸው ፈቀቅ ባለማለታቸው ትልቅ
ብረት ምጣድ ተጥዶ: 2ቱም ከነነፍሳቸው እንዲቃጠሉ
ተደረገ:: ቀጥሎም ሕዝቡን እንዲፈጁ አዋጅ ወጣ::
በከተማዋ ከነበረው ሕዝብ 40,000 ያህሉ ተገደሉ::
+40,000 ያህሉ ሲማረኩ 40,000 ያህሉን ደግሞ # ይሁዳ
የሚባል አርበኛ በር ሰብሮ ይዟቸው ሸሸ:: "እንሾማለን:
እንሸለማለን" ብለው ሕዝባቸውን ያስፈጁ እነዚያ ካህናትም
#እግዚአብሔር ፈርዶባቸው እነርሱም ተገደሉ:: ቅዱሱ
የአልዓዛር ቤተሰብ ግን የክብርን አክሊል አግኝተዋል::
#የእሥራኤል_አምላክ ቸሩ_እግዚአብሔር_እንዲህ ካለው_መከራ_በኪነ_ጥበቡ_ይሰውረን::_ከቅዱሳኑ_በረከትም_አይለየን::