ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ቅድስት ኤልሳቤጥ
በወንጌላዊው የተመሰገነች እናታችን ቅድስት
ኤልሳቤጥ ትውልዷ ከነገደ #ሌዊ ነው:: ሐረገ ሙላዷም
ከቅዱስ #አሮን_ካህን ወገን ይመዘዛል:: ከአሮን በቴክታና
በጥሪቃ ወርዶ #ሔርሜላ ላይ ይደርሳል::
ይህቺ ሔርሜላ የምትባል ደግ ሴት #ማጣት ("ጣ"
ጠብቆ ይነበብ) የሚባል የተባረከ ሰው አግብታ 3
ቡሩካት ልጆችን ወለደች:: የመጀመሪያዋን 'ማርያም'
አሏት:: እርሷ ቅድስት ሰሎሜን ወለደች:: ሁለተኛዋን
'ሶፍያ' አሏት:: እርሷ ደግሞ ቅድስት ኤልሳቤጥን
ወለደች::
ሦስተኛዋ ግን የተለየች ናት:: 'ሐና' ብለው ሰየሟት::
እርሷም የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነችውን ድንግል
ማርያምን ወለደች:: በዚህም መሠረት ድንግል ማርያም:
ቅድስት ኤልሳቤጥና ቅድስት ሰሎሜ የእህትማማች
ልጆች ናቸው::
ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ጊዜ ስም አጠራሩ
የከበረ: ደግ ካህን ለሆነ: ቅዱስ #ዘካርያስ አጋቧት::
እርሷ የሊቀ ካህናቱ ሚስት ናትና ክብሯ ከፍ ያለ ነበር::
ምንም ልጅ ባይኖራትም ዘወትር በጸሎትና በጾም:
ምጽዋትንም በማዘውተር: ነዳያንንም በማሰብ የምትኖር
እናትም ነበረች::
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን
ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ
መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው
በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል
አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና
በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ"
ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ
መኖር ምን ይረቅ?
ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና
ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ
ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት
ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ
ደርሶ ነበር::
ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ
እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ነቢይን
ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን
ላከላቸው:: ቅድስቲቷ መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው
ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች::
#ድንግል_እመቤታችን ወደ እርሷ መጥታ 'ሰላም'
ባለቻት ጊዜ ምንም ያሳደገቻት ልጇ ማለት ብትሆን:
መንፈስ ቅዱስ ስለ ሞላባት እመ ብርሃንን
አመስግናታለች:: ቡርክት: ብጽእት: ከፍጥረተ ዓለሙ
የከበረች መሆኗንም መስክራለች:: በማሕጸኗ ያለ የ6 ወር ጽንስም የእመ አምላክን ድምጽ ቢሰማ በደስታ ዘሏል:: ለፈጣሪውም ስግደተ-ስባሔ
አቅርቧል:: ቅድስት ኤልሳቤጥ አክላም "ወምንትኑ አነ
ከመ ትምጽኢ ኀቤየ እሙ ለእግዚእየ-የጌታየ እናቱ ወደ
እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይገባኛል?" ስትል በትኅትና
ተናግራለች:: ከጌታ እናት ጋር ለ3 ወራት በአንድ ቤት ቆይታለች::
ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው
ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር
የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም
አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ
የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ
'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን
ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል::
አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ
ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7)
ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ
ዘካርያስና ስምዖን ወርደው
ቀበሯት:: #ኤልሳቤጥ ማለት 'እግዚአብሔር መሐላየ
ነው': አንድም 'የጌታ አገልጋይ' ማለት ነው::
#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: #ቅዱስ_ሉቃስ የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር::
እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ #መልአከ_ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ
#የአርያም_ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ #ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው
#መንፈስ_ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
የእመቤታችን ልመናዋ: ክብሯ: የልጇ የወዳጇም ቸርነት በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን:: የመጥምቁንም በረከት ያብዛልን::