♥ቅዱስ #ቶማስ_ዘመርዓስ♥
ቅዱስ ቶማስ "መርዓስ" በምትባል ሃገር የፈለቀ
¤የንጋት ኮከብ
¤ጻድቅ
¤ገዳማዊ
¤ዻዻስ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕትና ሊቅ ነው:: የዚህን ቅዱስ ተጋድሎ እንደ እኔ ያለ
ሰው አይቻለውም:: የእርሱ ሕይወት
ክርስትና ምን እንደ ሆነ ያሳያል::
#ቅዱስ_ቶማስ:-
¤ከልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተማረ
¤ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ
¤መርዓስ በምትባል ሃገር ዽዽስና ተሹሞ በእረኝነት ያገለገለ
¤በሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ አሕዛብን ወደ ክርስትና የመለሰ
¤በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው::
+ጨካኞቹ ቅዱሱን ለ22 ዓመታት አካሉን እየቆራረጡ
ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለ ነበር 2 እግሮቹ: 2 እጆቹ: 2 ጀሮዎቹ: 2
አፍንጫዎቹ: 2 ዐይኖቹ: ሁሉ አልነበሩም:: ነገር ግን እንዲህም
ሆኖ አልሞተም ነበር::
+በመጨረሻም በዘመነ መናፍቃን አርዮስን ካወገዙት 318ቱ
ሊቃውንት እንዳንዱ ተቆጥሯል:: ቅዱስ ቶማስ ዽዽስና በተሾመ
በ40 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል:: የጻድቃንን: የሰማዕታትን:
የሐዋርያትንና ሊቃውንትን አክሊልም ተቀብሏል::
♥አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ ምልጃ ክብራቸውን ያድለን::
በረከታቸውም በዝቶ ይደርብን::♥
ቅዱስ ቶማስ "መርዓስ" በምትባል ሃገር የፈለቀ
¤የንጋት ኮከብ
¤ጻድቅ
¤ገዳማዊ
¤ዻዻስ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕትና ሊቅ ነው:: የዚህን ቅዱስ ተጋድሎ እንደ እኔ ያለ
ሰው አይቻለውም:: የእርሱ ሕይወት
ክርስትና ምን እንደ ሆነ ያሳያል::
#ቅዱስ_ቶማስ:-
¤ከልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተማረ
¤ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ
¤መርዓስ በምትባል ሃገር ዽዽስና ተሹሞ በእረኝነት ያገለገለ
¤በሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ አሕዛብን ወደ ክርስትና የመለሰ
¤በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው::
+ጨካኞቹ ቅዱሱን ለ22 ዓመታት አካሉን እየቆራረጡ
ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለ ነበር 2 እግሮቹ: 2 እጆቹ: 2 ጀሮዎቹ: 2
አፍንጫዎቹ: 2 ዐይኖቹ: ሁሉ አልነበሩም:: ነገር ግን እንዲህም
ሆኖ አልሞተም ነበር::
+በመጨረሻም በዘመነ መናፍቃን አርዮስን ካወገዙት 318ቱ
ሊቃውንት እንዳንዱ ተቆጥሯል:: ቅዱስ ቶማስ ዽዽስና በተሾመ
በ40 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል:: የጻድቃንን: የሰማዕታትን:
የሐዋርያትንና ሊቃውንትን አክሊልም ተቀብሏል::
♥አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ ምልጃ ክብራቸውን ያድለን::
በረከታቸውም በዝቶ ይደርብን::♥