ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ይ:ካ: እግዚአብሔር ምስለ ኰልክሙ ቄሱ:-እግዚአብሄር በሁላችሁም
አድሮባችሁ ይኑር ይበል::
#ይ:ሕ: ምስለ መንፈስከ ህዝቡም እንደቃልህ ይደረግልን ይበሉ::
#ይ:ካ: አእኩትዎ ለአምላክነ :-ቄሱ ፈጣርያችንን አመስግኑት ይበል
#ይ:ሕ: ርቱዕ ይደሉ :- ህዝቡም ዕውነት ነው ይገባል ይበሉ
#ይ:ካ: ብነ ሃበ እግዚአብሔር አምላክነ
ህዝቡም በፈጣርያችን በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋ አለን ይበሉ::
#መጽሃፍ ከመጽሃፍ ማያያዝ ልማድ ነው: አባቷ ዳዊት ለንጉሰ ሰማይ ወምድር ምስጋና
ላቅርብ ባለ ግዜ ጐሥዐ ብሎ ተናግሮ ነበርና እሱም ለንግስተ ሰማይ ወምድር ምስጋና
ላቅርብ ባለ ግዜ ጐሥዐ አለ አንድም ለአባቷ ለዳዊት የገለጸ መንፈስቅዱስ ምሥጢር
ከምስጢር አያይዞለት ጐሥዐ አለ ወአየድዕ ይላል በልብ መደብ ቁሞ ወአነ አየድዕ ይላል
በቃለ መደብ ቁሞ ልቦናዬ በጎ ነገርን አውጥቶ ተናገረ:: አንድም ልቦናየ ስንቡል
መንፈስቅዱስን ተቀብሎ በጎ ነገርን ገሳ ሐተታ:-በሃገራቸው የተመገቡት ምግብ
ያልተስማማቸው እንደሆነ ዑድ ሰንደል የሚባል ሽቱ አለ ያንን ተመግበው በጎ በጎ ነገር
ገሣው ይላሉና ያጎሥዓኒ እንዲል ትግሬ
#ሐተታ :- ሶስት ግዜ ጐሥዐ ጐሥዐ ጐሥዐ ብሎ መላልሶ ተናገረ ስለምን ቢሉ በንጽሃ ስጋ
በንጽሃ ነፍስ በንጽሃ ልቦና መዓረግ አምሳል አንድም ወጣንያን ማዕከላውያንን ፍጹማን
የሚያመሰግኗት ስለሆነ: አንድም በዚህ አለም በገነት በመንግስሠማያት ያሉ ጻድቃን
የሚያመሰግኗት ስለሆነ: ከዚህስ አስቀድሞ መንግስተ ሰማይ የገባ የለም ብሎ ኋላ
መንግስተ ሰማያት የሚገቡ ጻድቃን የሚያመሰግኗት ሲለሆነ: አንድም ሊቃውንት
በሚስጥረ ሥላሴ መጀመር ልማዳቸው ነው: ሦስት ግዜ ደጋግሞ መናገሩ የሦስትነት: ቃሉ
አለመለወጡ የአንድነት:ምሳሌ ነው:አንድም ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ
ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ የሚል ነውና ሦስት አርዕስት ተናገረ ለሦስቱም ያመጣል::
4:-ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ለማርያም:- አባቷ ዳዊት ወአነ አየድዕ ግብርየ ለንጉሥ ብሎ
ነበርና ለዚያ ዋዌ እኔም የእመቤታችንን ምስጋና እናገራለው አለ ሐተታ:- መጀመርያ ጐሥዐ
ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ አለ በቅድስና ወበንጽህና ስርጉት
አንቲ የሚል ነውና ለዚያ አርዕስት ነው::
አኮ በአብዝኖ በማብዛት አይደለም : አላ በአውህዶ በማሳነስ ነው እንጂ ሐተታ:-
የእመቤታችን ምስጋና ከምስጋና ቢበዛ እንጂ ያንሳልን? መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን
አይደለችምን ቢሉ እውነት ነው የእመቤታችን ምስጋና ሰማይና ምድር ብራና አብህርት
ቀለም ዕጽው ብርዕ አዕባን መድመድ: መላዕክት ደቂቀ አዳም ጸሃፍት ቢሆኑ ባልተፈጸመም
ነበር:እንደቅድስናዋ እንደንጽህናዋ አይደለም ሲል እንዲህ አለ ከዚያ ሁሉ ቅዱስ ቄርሎስ
የቴዎዶስዮስን እህቶች የአርቃድያ የመሪናን ምስጋናቸውን ተናግሮ ዝውዳሴንዘተናገርነ
ይውህደ እምክብርክን እንዳለ አንድም ንባብን በማብዛት ምሥጢሩን በማሳነስ አይደለም:
ንባቡን በማሳነስ ምሥጢሩን በማብዛት ነው እንጂ::
ወአነ አይድዕ ውዳሴሃ ለድንግል:- እኔም የእመቤታችንን ምስጋና እናገራለው ሐተታ:-
ሁለተኛ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ድንግል አኮ
ስፋጣን ዘናዘዙኪ አላ መላእክተ ሰማይ ሐወጹኪ በከመ ተብህለ ካህናት ወሊቃነ ካህናት
ወደሱኪ የሚል ነውና::
አኮ በአንሆ በቃለ ዝንጋዔ:- ዝንጋዔን የሚያመጣ ዝንጋዔን የሚያስከትል ነገርን በማብዛት
አይደለም: ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ: ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ:እንዲሉ ነገር ከበዛ ዘንድ ከምን
ተነስቶ ከዚህ ደረሰ ይባላልና ነው::
አላ በአሕፅሮ:-በማሳጠር በመጠቅለል ነው እንጂ ሲሰበር ይሰንጠር ሲረዝም ይጠር
እንዲሉ:
ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ ለድንግል:- የድንልን ገናንነቷን እናገራለው ሐተታ:- ሦስተኛ ጐሥዐ
ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ማርያም ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ
ብሎ የሚያመጣ ነውና: ይህስ አይደለም አርዕስት ተቀዳደመ ለፊተኛው አርቆ ለኋለኛው
አቅርቦ አይሰጥም ብሎ መጽአ ሃቤኪ ቃል ብሎ የሚያመጣ ነውና:: ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ
: ወአነ አይድዕ ቅዳሴሃ : ወአነ አይድዕ ዕበያቲሃ ብሎ ሦስት ጊዜ መላልዞ ተናገረ::
ኦ ማርያም በእንትዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ኦ ድንግል ምልዕተ ውዳሴ: ኦ ድንግል አኮ
ዘተአምሪ ርስሃተ የሚል ነውና: አንድም አባቷ ዳዊት ቀደሰ ማህደሮ ልዕል:መሰረታቲሃ
ውስተ አድባር ቅዱሳን እስመ ሓረያ እግዚአብሄር ለጽዮን ብሎ ሦስት ግዜ መላልሶ
አመስግኗታል::