ባልንጀራህን አትቀየመው ።
ወኢትትቀየም ቢጸከ ⇨ ባልንጀራህን አትቀየም ⇨ be not angry with thy
neighbour" [ሢራ. ፳፰፥፯]
. እመቤታችን ያለ ምንም ነውር ፣ ሰይጣን ግን ያለ ምንም ክብር ሆነው ይኖራሉ።
. ቅዱሳን በሚደነቅ ንጽሕና እኛም በታላቅ ስንፍና የምንመላለስ ነን።
ነገር ግን ከበጎዎች ጥቂት ድክመት ከደካሞች ጥቂት በጎነት አይታጣም ።
ለዚህ ነው መጽሐፋችን ⇨ ፍጡር ከሆነ ከ #እመቤታችን በቀር ጥቂት ጽነት የሌለበት
የለም! ከነጭ ላም ከጉያዋ ከብሻሻዋ (ከብሽሽቷ) ቢፈልጉ ጥቂት ጥቁር እንዳይጠፋ፤
⇨ ፍጡርም ሆኖ ከ #ዲያብሎስ በቀር ጥቂት ቸርነት የሌለው የለምና! ከጥቁር ላም
ከጉያዋ ከብሻሻዋ ቢፈልጉ ጥቂት ነጭ እንዳይጠፋ፤
⇝ የኃጥኡ ምግባር ለጻድቁ ክብር ያበዛለታል የጻድቁም ክፋት በኃጥኡ ፍዳ የመጣበታልና
፦
እንደነ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
እንደነ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ያለ ቢሆንሳ ቢሉ ዝክራቸውን ለዘከረ ስማቸውን
ለጠራ ክብር ሲያሰጡ ይኖራሉ ይላል ፍትሕ መንፈሳዊ።(ፍትሐ ነገሥት ምዕ ፲ ቁ ፫፻፶፭
ትርጓሜ)
✧ መቼም #እኔ_ደካማ_ነኝ ! በሀገራችን እና በቤተክርስቲያናችን ላይ በዘመናችን
የመጣው ይኼ ፈተና በእኔ ምክንያት
① ነፍሴን በማጉደሌ፣ ② አምላኬን በመበደሌ እና ③ ባልንጀራዬን በማቃለሌ መሆኑን
አምናለሁ!
☞ለነፍሴ ድርሻዬን ለመወጣት እጥራለሁ!
☞ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለኝ ለምኑልኝ (ክፍለ ሥላሴ) መቼም እርሱ እግዚአብሔር
ይቀየም ዘንድ እንደሰው አይደለምና በምሕረቱ እታመናለሁ ( ኢኮነ ከመ ዕጓለ መሕያው
ዘይትቄየም ዮዲ.፰ ፥፲፮)
☞ እናንተን ባልንጀሮቼን አልሜ ሰው ለመጉዳት አልያም ተሳስቼ ለመርዳት በጻፍኩት፣
በተናገርኩት ባደረኩትም ይቅር በሉኝ ከዚህ አልፎም ከእኔ በሚጠበቀውም መጠን
ድርሻዬን ሳልወጣ ሳልጽፍ፣ ሳልናገር እና ሳላደርግ በቀረሁትም ጭምር በእጅጉ ይቅርታ!
ሐሳቤን የበለጠ ያጠነክራል ብዬ ይኽን ከቅዱስ መጽሐፍ [የጠቢቡ ሢራክን ቃልና የሊቁን
የሕማማት ሰላምታ ክፍል] ለትምህርትና ለተማጽኖ አስቀምጬ ለ"ጥቂት" ጊዜ ልሰናበት።
“ አንተ ሰው ሆነህ እንዳንተ ያለውን ሰው ሳትቀየም እግዚአብሔርን እንዴት ይቅር
በለኝ ትለዋለህ? እንዳንተ ያለ ሰው ይቅር ሳትል ኃጢዓትህን ያስተሰርይልህ ዘንድ
እንግዲህ እንዴት ትለምነዋለህ ኃጢዓትህን አስበህ ጠብን ተዋት ሞትን አስበው
መቃብርንም አስበው ትእዛዙንም ጠብቅ፤ ሕጉን አስበህ ባልንጀራህን አትቀየም" ሢራ ፳፰፥
፪–፯
በከመ ልማድኪ በሊ ኀበ ወልድኪ ከሃሊ
.ኦ ርኅሩኅ ኢተበቃሊ
.ያጠፍኦኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፦ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ።
እንደዚህ በዪ እንደልማድሽ
. ሁሉን ወደሚችለው ልጅሽ
. የምትራራ ነህና የማትበቀል
. የእጅህን ድንቅ ሥራ ጠብቅ ፣ የቀደመውን ያንተን አምሳል
ሠዓሊ ሥዕሉን እንደምን ያጠፋል?!
‘እናታችን ድንግል’ ቂም ይዞ ከማይበቀለው ጽድቀ አሚንን ፣ ርትዓተ ልቡናን
ከሚያድለው ልጅሽ ይቅርታውን ይልክልን ዘንድ ለምኚልን!