ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ቅዱስ_ሩፋኤል_ሊቀ _መላዕክት
#ሢመት
ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከ7ቱ ሊቃነ
መላእክት በደረጃው 3ኛ ነው:: በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት
እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በ10 ከተማ
ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች::
በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ 10ሩ ነገድ አለቃ
(መሪ) ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል::
በሁዋላም "#መጋብያን " በሚባሉ በ23ቱ ነገድ ላይ
ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት::
#ቅዱስ_ሩፋኤልና_ሐዋርያት
አንድ ቀን #ጌታችን_ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ
ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት::
ጌታም 3ቱን ሊቃናት ( #ሚካኤል: #ገብርኤል እና #ሩፋኤል
) ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው::
ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው" አለው::
እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው::
በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ
የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ::
#ረዳትነት
በመጽሐፈ #ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ
መልአክ ሰው (አዛርያን) መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ:
ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዐይን
አብርቷል:: በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን
ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል::
#ቅዳሴ ቤት
ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ
ቤቱም ናት:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ #ቴዎፍሎስ
ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ
የታነጸው በአሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው:: በመልአኩ
አጋዥነትም ለ300 ዓመታት አገልግሏል::
#ቅዱስ_ሩፋኤል
¤መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
¤አቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
¤መዝገበ ጸሎት (የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
¤ሊቀ መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት
መሪ)
¤ፈታሔ ማሕጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማሕጸን
የሚፈታ)
¤መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
"ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማሕጸኖሙ አንተ" እንዲል::
💚💛ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር💛❤️
በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት
ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ #አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም::
እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ
ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም::
በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም " #ዮሐንስ_ሐጺር -
አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል:: ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ
ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም
ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::

ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ
ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ
መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል::
ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ
ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::
ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር
በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ
ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው
ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ
"አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር:: ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::

#አባ_ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ
ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ
ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::

አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ
ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ
መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል:: ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና
ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው
አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ
አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ
ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ
ወስዶ ተከለው:: ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ:: በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው
በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ
ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም:: ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው:- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው::" ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል::
መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ
ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው
ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ
ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ
አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::
#መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ
ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር::
ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን
ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::
አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ
(ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን
#ሊቃነ_መላእክት #ሚካኤል እና #ገብርኤል በግርማ በጌታ
ፊት ቆመው ተመለከተ::
"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ
እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ
ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን
ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ #ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ
ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ
#ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል::
በ825 ዓ/ም ግን በአባ #ዮሐንስ_ፓትርያርክ ዘመን ክቡር
ሥጋው ወደ #ገዳመ_አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው
ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ
ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ #ቅዱስ_መቃርስ
ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ
ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል:: ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ::
ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ
ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
አምላከ ቅዱሳን የሐጺር ቅዱስ ዮሐንስን መታዘዙን: ትሕትናውን: ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን::
በበረከቱም ይባርከን::
Dn yordanos abebe
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ገብርኤል "ሐምሌ ፲፱"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ: በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ለዓለም ወለዓለመ ዓለም: ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል: ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል: ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ: በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት #ለቂርቆስ ሕጻን፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ #ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ።
@zemarian
ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት #ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ: ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም
መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ #ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡

ዚቅ
#ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: #ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።

ወረብ
"#ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/
ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን #ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ።

ዚቅ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት።

ወረብ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/
ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን #ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ።

ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/
ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ #ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ።

ዚቅ
በጸሎቱ ለቅዱስ #ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡

ወረብ
በጸሎቱ ለቅዱስ #ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/
ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር #ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡

ዚቅ
በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: #ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡

ወረብ
በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ/፪/
ባርካ #ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/

መልክዐ ኢየሉጣ
ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: #ኢየሉጣ ቅድስት #ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: #ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ #ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡

መልክዐ ገብርኤል
ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: #ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ።
@zemarian
ዚቅ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት።

ወረብ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት #ሊቀ_መላእክት/፪/
እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/

ምልጣን
ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ።

አመላለስ
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/

ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/
ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/

እስመ ለዓለም
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ #ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡

ወረብ
ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/
እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/

አመላለስ
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/
ምንጭ:- @estifanos_areka @estifanos_areka

@senkesar @senkesar