ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
💚💛ሐምሌ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅዱሳን 72ቱ አርድእት (ዛሬ ሁሉም ይታሠባሉ)
4.ቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት
5.ቅድስት መስቀል ክብራ (የቅዱስ ላሊበላ ሚስት)
6.ቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ
7.ቅዱሳት አንስት (ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና
አክስቲያና-የቅዱስ ዼጥሮስ ተከታዮች)
🌈ወርሐዊ በዓላት🌈
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
3.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
4.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)

" ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው:: "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና
ደም ይሕንን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ:: እኔም
እልሃለሁ:: አንተ #ዼጥሮስ ነህ:: በዚህችም ዓለት ላይ
ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ:: የገሃነም ደጆችም አይችሏትም:: የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች
እሰጥሃለሁ:: በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 16:17)
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌼🌼
" በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና:: የምሔድበትም ጊዜ ደርሷል:: መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖትን
ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት # የጽድቅ_አክሊል ተዘጋጅቶልኛል::
ይሕንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል::" (2ጢሞ. 4:6)
@dn yordanos abebe
🌼 ሐምሌ ፭ 🌼
እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለምቅዱሳን #ዼጥሮስ
#ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም:: ለቤተ ክርስቲያን ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ:
ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች::

"ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት"
የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው:: ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው::
¤በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ
አድጐ
¤ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን
የተቀበለው:: በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ: በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል::
ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል:: (ማቴ. 16:17, ዮሐ. 21:15)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው
ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል:: ቅዱስ ዼጥሮስ
እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል:: ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል::
በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል:: አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል:: እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል:: የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው
ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ::

ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ/ም የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው::
"እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም" አላቸው:: እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል:: በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባብ ደርሶ ነበር::
💚💛ሐምሌ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅዱሳን 72ቱ አርድእት (ዛሬ ሁሉም ይታሠባሉ)
4.ቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት
5.ቅድስት መስቀል ክብራ (የቅዱስ ላሊበላ ሚስት)
6.ቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ
7.ቅዱሳት አንስት (ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና
አክስቲያና-የቅዱስ ዼጥሮስ ተከታዮች)
🌿ወርሐዊ በዓላት🌿
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
3.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
4.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
"ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው:: "
የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይሕንን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ:: እኔም
እልሃለሁ:: አንተ #ዼጥሮስ ነህ:: በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ:: የገሃነም ደጆችም አይችሏትም:: የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ:: በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ
ይሆናል:: በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ.16:17)

"በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና:: የምሔድበትም ጊዜ ደርሷል:: መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት #የጽድቅ_አክሊል ተዘጋጅቶልኛል:: ይሕንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል:: " (2ጢሞ. 4:6)
@senkesar @senkesar
💚💛ሐምሌ ፭💛❤️
✞እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን #ዼጥሮስ #ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም:: ለቤተ ክርስቲያን ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ:
ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች::

💚💛" ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት "💛❤️
የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው:: ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው::

¤በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጐ

¤ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው:: በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ: በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል:: ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል:: (ማቴ. 16:17, ዮሐ.
21:15)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል:: ቅዱስ ዼጥሮስ
እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከ አካፍሏል:: ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል::

በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል:: አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል::
እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል:: የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ::

ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ/ የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው::."እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም"
አላቸው:: እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል:: በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባብ ደርሶ
ነበር::

#የቅዱስ_ዼጥሮስ መጠሪያዎች:-
1.ሊቀ ሐዋርያት
2.ሊቀ ኖሎት (የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ)
3.መሠረተ ቤተ ክርስቲያን
4.ኰኩሐ ሃይማኖት (የሃይማኖት ዐለት)
5.አርሳይሮስ (የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ)

💚💛#ቅዱስ_ዻውሎስ_ሐዋርያ 💛❤️
የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ ዐማርኛ እንገልጠዋለን?

¤ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው?

¤የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ?

¤ይልቁኑስ የርሱን 14ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም::

#ቅዱስ_ዻውሎስ ከነገደ ብንያም #ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር:: ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት
ምርጥ ዕቃ አደረገው:: ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር:: ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ:: ጨው ሆኖ አጣፈጠ::

ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን (የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ:: ስለ ወንጌል ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ:: በድንጋይ ተወገረ: በጦር ተወጋ:: ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ:: በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ:: ለ25 ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ::

እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ: በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል::.ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል:: ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘ ማለት ነው::

የቅዱስ ዻውሎስ መጠሪያዎች:-
1.ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ)
2.#ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ)
3.#ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ)
4.#ብርሃነ_ዓለም
5.#ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ)
6.#የአሕዛብ_መምሕር
7.#መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ)
8.#አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ)
9.#ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ)
10.#መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን)
11.#መርስ (ወደብ)
12.#ዛኅን (ጸጥታ)
13.#ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ
ያፈለቀ)
14.#ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ / ባሕር)
15.#ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . .

ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
From dn yordanos abebe

@senkesar @senkesar